headline
stringlengths
2
1.42k
⌀
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
6
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
1
36.2k
link
stringlengths
28
740
የኦሊምፒክ ማጣሪያ ተሳታፊዎች የሚለዩበት ቻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል
ስፖርት
January 14, 2021
2
ብርሃን ፈይሳየኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የክለቦች ቻምፒዮና በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተሻለ ብቃት ያሳዩ ቦክሰኞች ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ታውቋል።በቦክስ ስፖርት ከሚካሄዱት ዓመታዊ ቻምፒዮናዎች መካከል አንዱ በክለቦች መካከል የሚካሄደው ነው፤ የዚህ ውድድር የመጀመሪያው ዙር በአዲስ አበባ ከተማ ተጀምሯል። የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ከአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ቻምፒዮና፤ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ...
https://www.press.et/Ama/?p=39481
አዲስ ዘመን ድሮ
መዝናኛ
December 28, 2020
4
 የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ቀደምት ዘገባዎች በእጅጉ ተነባቢ ዛሬም ላገኛቸው በእጅጉ ተነባቢ ናቸው።እኛም ከእነዚህ ዘገባዎች ጋዜጣው በ1950ቹ ያስነበባቸውን ወጣ ያሉ ዘገባዎች ለዛሬ ይዘንላችሁ ቀርበናል። በዛሬው የአዲስ ዘመን ዱሮ አምዳችን አዲስ ዘመን ጋዜጣ በ1950ዎቹ ይዟቸው ከወጣ ዘገባዎች በአዘጋገባቸውና በይዘታቸው ተነባቢ ናቸው ያልናቸውን እና ሌሎች አስደናቂ ዘገባዎችን ይዘን ቀርበናል። ማገጃ ምልክት ይሰጠውማንኛውም የሥራ ድርጅት በብዙ ድካም ከተቋቋመ በኋላ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገለት የተሠራው...
https://www.press.et/Ama/?p=38334
የአረንጓዴ ጎርፍ በጎ አድራጎት አምባሳደሮች ተሰየሙ
ስፖርት
January 6, 2021
6
ቦጋለ አበበየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ የአትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር‹‹የገና በዓልን ከአንጋፋ አትሌቶች ጋር እናሳልፍ›› በሚል ትናንት በኢትዮጵያ ሆቴል በተዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መድረክ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ሁለት አምባሳደሮች ተሰይመዋል፡፡ በዚህም ከሴት ፈር ቀዳጇ የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር የቀድሞ ኮከብ አትሌት ኮማንደር ቁጥሬ ዱለቻ የተሰየመች ሲሆን በወንድ ፋና ወጊው የኦሊምፒክ የሦስት ሺ ሜትር መሰናክል የነሐሴ ሜዳሊያ...
https://www.press.et/Ama/?p=39010
የሊጉ በቢዝነስ ሞዴል መመራት አበረታች ጅምር መሆኑ ተገለጸ
ስፖርት
January 6, 2021
5
ብርሃን ፈይሳአዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሼር ካምፓኒ እንዲተዳደር መደረጉና የቴሌቪዥን ሽፋን ማግኘቱ ለሌሎች ስፖርቶችም አበረታች ጅምር መሆኑ ተገለጸ። በብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት የ2013ዓም የስፖርት ዘርፍ አፈጻጸም ሰነድ ላይ እንደተመለከተው፤የሃገሪቷ ስፖርት በቢዝነስ ሞዴል እንዲመራ በማድረግ ረገድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሪሚየር ሊጉን (ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ) በሼር ካምፓኒ እንዲመራ ማድረጉ መልካም ጅማሬ ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ የተደራጀው ካምፓኒው ውድድሩን የ...
https://www.press.et/Ama/?p=39011
የኦሊምፒክ ሥራ አስፈፃሚው እስከ ቶኪዮ ኦሊምፒክ ማግስት ይቀጥላል
ስፖርት
January 6, 2021
12
ቦጋለ አበበ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አርባ አምስተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ባለፈው እሁድ በሐዋሳ ከተማ ሲያካሂድ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡፡ ባለፉት አራት ዓመታት ሲያገለግል ቆይቶ ዘንድሮ ይጠናቀቅ የነበረው የኮሚቴው የስራ አስፈፃሚና የፕሬዚዳንት የስልጣን ዘመን በመጪው ክረምት እስከሚካሄደው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ማግስት ድረስ እንዲቀጥል ጉባዔው ወስኗል፡፡ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረ ቢሆንም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለአስራ ስድስት ወራት ተራዝሞ በመጪው ክረ...
https://www.press.et/Ama/?p=39012
‹‹ሃገራዊ ችግሮችን ለማረምና አብሮነትን ለማጠናከር ስፖርት ወሳኝ ነው››- አቶ ደመቀ መኮንን የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ
ስፖርት
December 30, 2020
10
 ብርሃን ፈይሳ አዲስ አበባ፡- እንደ ሃገር እየታዩ ያሉትን ስብራቶችና ችግሮች ለማረምና የአብሮነትን ጉዞ ለማጠናከር ስፖርት ወሳኝ ሚና አለው ሲሉ የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ። ለስፖርቱ ዘርፍ ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቆመ። የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ደመቀ መኮንን ትናንት የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት የመጀመሪያ መደበኛ ጉባኤ በተካሄደበት ...
https://www.press.et/Ama/?p=38512
በውድድር ወቅት በወረርሽኙ መከላከያ መመሪያዎች አተገባበር ላይ ስጋት እንዳለው ሚኒስቴሩ ጠቆመ
ስፖርት
December 30, 2020
3
ብርሃን ፈይሳ አዲስ አበባ፡- ስፖርታዊ እንቅስቃሴና ውድድሮች በሚከናወኑበት ወቅት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎች አተገባበር ላይ ስጋት እንዳለው የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ትናንት በተካሄደው በብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በጤና ሚኒስትር እንዲሁም በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር የወጡ የኮቪድ 19 መከላከያ መመሪያዎችን ታሳቢ አድርጎ ውድድሮችንና እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መ...
https://www.press.et/Ama/?p=38515
ስፖርትን ከፖለቲካ የመለየት ፈተናዎች
ስፖርት
December 31, 2020
11
ቦጋለ አበበ‹‹ስፖርትና ፖለቲካ አንድ ናቸው ወይም ጠንካራ ግንኙነት አላቸው›› ብለው የሚያምኑ በርካቶች የመሆናቸውን ያህል ‹‹ስፖርት ከፖለቲካ ነፃና ገለልተኛ ነው ወይም መሆን አለበት›› ብለው በምክንያት የሚሞግቱ ጥቂት አይደሉም።ከዚህ በተለየ መልኩ በዘመናዊው ዓለም ስፖርት የፖለቲካ መጠቀሚያ ዋነኛ መሳሪያ እየሆነ በመምጣቱ ነፃ ሊወጣ እንደሚገባ የሚሞግቱ አልጠፉም።እነዚህ ሞጋቾች ግን ስፖርትን ከፖለቲካ ሙሉ በሙሉ ነፃ ለማውጣት ወይም የመሰንጠቅ ፈተናዎች እንዳሉባቸው በርካታ ማሳያዎችን በመደርደር የሚ...
https://www.press.et/Ama/?p=38578
የዓለም አትሌቲክስና 2020 የውድድር ዓመት
ስፖርት
January 1, 2021
10
ቦጋለ አበበ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የዓለም ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ገፅታ ዝብርቅርቁ በወጣበት የፈረንጆች 2020 ዓመት የዓለም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችም ቀላል የማይባል አሉታዊ ተፅዕኖ አርፎባቸዋል። ኦሊምፒክን ጨምሮ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊና የአገር ውስጥ ስፖርታዊ ውድድሮች በተሰረዙበትና በተራዘሙበት የውድድር ዓመት የአትሌቲክስ ስፖርት በርካታ ፈተናዎችን ማሳለፉ ይታወቃል። በዓለም ሕዝብ ዘንድ ጥሩ ትውስታን ጥሎ ያላለፈው 2020 ተሸኝቶ ዛሬ በ2021 የውድድር ዓመት አንድ ብሎ የሚጀምር...
https://www.press.et/Ama/?p=38650
ለራስ ሲባል ሌላውን …
መዝናኛ
April 27, 2020
24
ኧሯ! እንዴት ሆኖ እንዴት ሆኖ እኛንማ አይደፍርም! ብለን ነበር ደፈረን። በሩቅ ሆኖ የሰማነው ዜና ገስግሶ መጥቶ አጠገባችን ከደረሰ የወራት እድሜን አስቆጠረ። በሰው ሀገር ሲነገር፤ ሲወራ እኛ ዘንድ የማይደርስ መስሎን ተዘናግተንማል። እኛ ሀገር አይገባም ፤ ጥቁሮችን አይነካም በማለት እራሳችንን በማይሆን ተስፋ እያታለልን ቆይተናል። ቁርጡ ቀን ደርሶ በሀገራችን የቫይረሱን መገኘት እውነታ ሲነገር ሰምተን ላለማመን ያመነታነው ስንቶቻችን እንሆን? ታዲያ አስፈሪ ዝናውን አስቀድሞ በርካቶቻችንን ኮርኩሮ ሃሳ...
https://www.press.et/Ama/?p=31198
የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት ቀጥሏል
ስፖርት
December 22, 2020
8
 ቦጋለ አበበ ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ኮትዲቯር የ2023 አፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ የምታደርገው ዝግጅት በሚፈለገው ደረጃ ቀጥሏል።የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባለፈው ዓመት ከተከሰተ ወዲህ በርካታ የዓለማችን አገራት ስፖርታዊ ውድድሮችን ከማቆም ባለፈ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የሚያደርጉት ዝግጅት ተስተጓጉሏል።የ2023 አፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ዕድሉ የተሰጣት ኮትዲቯር ግን ወረርሽኙ ሳያግዳት ዝግጅቷን በተገቢው መንገድ እንደቀጠለች ኢንሳይድ ዘጌምስ አስነብቧል። የአፍሪካ እግር ኳ...
https://www.press.et/Ama/?p=37905
የባለሀብቶች ተሳትፎ ያልታከለበት የማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ
ስፖርት
December 24, 2020
7
ብርሃን ፈይሳወቅቱ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ የሰፋበት መሆኑን ጥናቶች ያመላክታሉ። የማዘውተሪያዎች ዘመናዊነትና ጥራት የሰለጠኑ ከተሞች አንዱ መለያ እየሆነ ከመምጣቱም ባሻገር ኦሊምፒክ፣ ዓለም ዋንጫ እና የተለያዩ ስፖርት ቻምፒዮናዎችን ለማሰናዳት ዋነኛው መስፈርትም ነው። ሀገሮች ዜጎቻቸው በአእምሮና በአካል የተዋጣላቸውና ብቁ እንዲሆኑም በማዘውተሪያ ስፍራዎች አስፈላጊነትም እምነት ጥለዋል። በመሆኑም የከተሞቻቸውን ዲዛይን ሲያዘጋጁም ሆነ ግንባታውን ሲያከናውኑ ነዋሪዎ...
https://www.press.et/Ama/?p=38041
ቡናን ያለዛፍ ጥላ – በቀርጫንሼ ደበቃ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 18, 2021
32
አስቴር ኤልያስስፍራው ሞቃታማ ቢሆንም ቅጥር ጊቢው ግን በቡና ችግኞችና በተለያዩ የፍራፍሬ ዛፎች በመሙላቱ ለአይን አርንጓዴነቱ ደምቆ፤ ለአፍንጫ ደግሞ መልካም መዓዛው ዘልቆ ስለሚመጣ ለጎብኚው ማየትም መማግም ግዴታ ሳይሆን በውዴታ የሚያጣጥመው ነገር ነው። ወዲህ ለቡና ተክሉ የተስተካከለ ውሃ ይደርሰው ዘንድ አዲስ የሆነና የውሃው ልክ በኮምፒውተር የሚታዘዝበት ቴክኖሎጂ ያለበት አንድ ክፍል ይታያል፤ ወዲያ ደግሞ ወደ 750 ሜትር ኪዩብ ውሃ የሚይዝ የውሃው ሪዘርቫይር ይስተዋላል ፤ ቦታው በምዕራብ ጉጂ ዞን ...
https://www.press.et/Ama/?p=39687
ኮቭድ-19- ዳግም የቶኪዮ ኦሊምፒክ ሥጋት
ስፖርት
December 25, 2020
7
ቦጋለ አበበ ጃፓን ከሰባት ዓመታት በላይ ብዙ የለፋችበት የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ካለፈው ዓመት ጀምሮ የዓለም ሕዝብ የጤና ጠንቅ በሆነው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለአስራ ስድስት ወራት ተራዝሞ ዘንድሮ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል። ኦሊምፒኩ በተራዘመው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚካሄድም እርግጠኛ ሆነው የውድድሩ አዘጋጆች መናገር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የተለያዩ አገራትም በአዘጋጆቹ ተማምነው የስፖርት ልዑካን ቡድኖቻቸውን እያዘጋጁ ይገኛሉ።የዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጨምሮ የውድድሩ አዘጋጆች ...
https://www.press.et/Ama/?p=38136
ምክር ቤቱ አቅጣጫና ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል
ስፖርት
December 28, 2020
9
ብርሃን ፈይሳ አዲስ አበባ፡- ብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤት ነገ የመጀመሪያ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያከናውን ተገለጸ። በጉባኤው ላይም አቅጣጫዎችን እንደሚሰጥና ውሳኔዎችንም እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤቱ ባለፈው ዓመት ህዳር 4 ቀን 2012 ዓ.ም መስራች ጉባኤውን ማካሄዱ ይታወሳል፤ ይሁን እንጂ ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን በተያዘለት ወቅት ማካሄድ አልተቻለም። በመሆኑም ነገ የመ...
https://www.press.et/Ama/?p=38365
የከተማ አቀፍ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ተመልሷል
ስፖርት
December 29, 2020
7
ቦጋለ አበበ ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ አዲሱ ለሚ ኮራ ክፍለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ በይፋ ተጀምሯል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ‹‹ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ፤ ለመከላከያ ሰራዊት ቅድሚያ እሰጣለሁ›› በሚል መሪ ቃል በየካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አደባባይ ከትናንት በስቲያ የተካሄደ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም ተሳታፊ ሆነዋል ። በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባ...
https://www.press.et/Ama/?p=38442
አዳዲስ የአትሌቲክስ ማዘውተሪያዎች ግንባታ ይከናወናል
ስፖርት
December 24, 2020
10
ብርሃን ፈይሳአዲስ አበባ፡- ለአትሌቲክስ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ የሚሆኑ ቦታዎች ምልከታ ተደረገ። ማዘውተሪያዎቹ በአዲስ አበባ አቅራቢያ በሚገኙ አራት ከተሞች ላይ የሚገኙ መሆኑም ታውቋል። በቅርቡ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የተመረቀውን የአትሌቲክስ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ተከትሎ ሌሎች ግንባታዎችም እንደሚከናወኑ ተጠቁሞ ነበር። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፤ ከለገዳዲ ለገጣፎ ባሻገር በተለያዩ ከተሞች በአጭር ጊዜ ቦታ ...
https://www.press.et/Ama/?p=38042
የአገር አቋራጭ ሩጫና የፆታ እኩልነት ሙግቶች
ስፖርት
December 26, 2020
9
በታሪክ አጋጣሚ ቀደም ባሉት ዓመታት በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ወንድና ሴት አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች በተመሳሳይ ውድድር ላይ ሲሮጡ መመልከት የተለመደ ነው። ‹‹ወንዶች የሚሮጡትን ርቀት ሴቶች መሮጥ አይችሉም›› የሚል አስተሳሰብ በነበረበት ዘመን በተመሳሳይ ውድድር ላይ ሴቶች ከወንዶች ያነሰ ርቀት ለመሮጥ ይገደዱ ነበር። እንዲያውም በአንዳንድ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ላይ ወንዶች በሚሮጡበት ርቀት ሴቶች እንደማይወዳደሩ ከታሪክ መረዳት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል በታላቁ የዓለማችን የስፖርት መድረ...
https://www.press.et/Ama/?p=38194
የዓለም አትሌቲክስ በዶፒንግ ጉዳይ ጥርስ አውጥቷል
ስፖርት
December 28, 2020
10
ቦጋለ አበበ ኢትዮጵያ አበረታች ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም በስፖርቱ ዓለም በተለይም በአትሌቲክስ ትልቅ ስጋት ካንዣበበባቸው የዓለማችን አምስት አገራት አንዷ እንደሆነች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ሲያሳስቡ ቆይተዋል። በተቃራኒው ኢትዮጵያ ይህን ስጋት ለመቀነስ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በብሔራዊ ደረጃ የፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ፅሕፈት ቤት አቋቁማ አበረታች ለውጥ ማምጣቷንም የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ኤጀንሲ መስክሮላታል። ይሁን እንጂ ስጋት አለባቸው ከተባሉት አምስት አገራት ተ...
https://www.press.et/Ama/?p=38366
በቻን ውድድር ስቴዲየሞች በከፊል ለተመልካች ክፍት ይሆናሉ
ስፖርት
December 29, 2020
10
ቦጋለ አበበ በአገር ውስጥ ሊጎች ብቻ የሚሳተፉ ተጫዋቾች የሚሳተፉበት የአፍሪካ ሁለተኛው ትልቁ የእግር ኳስ ውድድር(ቻን) ላይ ደጋፊዎች ስቴድየም ገብተው ጨዋታዎችን እንደሚመለከቱ ተገለፀ። ከመጪው ጥር አጋማሽ ጀምሮ በካሜሩን በሚካሄደው ውድድር የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ በማድረግ ተመልካቾች ስቴድየም እንዲገቡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) ማሳወቁን ኢንሳይድ ዘ ጌምስ ዘግቧል። ባለፈው ሚያዝያ ወር ሊካሄድ የነበረው የቻን ውድድር በኮቪድ- 19 ስጋት ወደ ዘንድሮው...
https://www.press.et/Ama/?p=38441
ከተራ – የጎንደር ልዩ ውበት
ሀገር አቀፍ ዜና
January 19, 2021
7
ክፍለዮሐንስ አንበርብርጎንደር አሸብርቃለች:: ተፈጥሮም ሰውም አጅቧታል:: ከተራ ለጎንደር፤ ጎንደርም ለከተራ ውበት ናቸው:: ቆነጃጅት ሽሩባቸውን በባህላዊ አሠራር አስውበው፣ በሐበሻ አለባበስ አምረውና ደምቀው ወደ ማደሪያው የሚሸኙትን ታቦታት ይከተላሉ:: ወጣት ወንዶች በሀገርኛ አለባበስ አምረውና ደምቀው፣ ሽመል ይዘው በሆታ እያደመቁ፤ በእግራቸው መሬት ረግጠው  እየነቀነቁ አቧራው ወደ ላይ ቡን! ቡን! ብሎ በሰዎች መሐል ወደ ላይ ቦለል ሲል እንደ ሰኔ ደመና እየተቆራረጥ ወደ ላይ ሲወጣ አንዳች የተለየ ...
https://www.press.et/Ama/?p=39749
” የሱዳን ሃይል በተጠናከረ ሁኔታ ወደ ውስጥ እየተስፋፋ መሄዱ የግድቡን ግንባታ ለማስተጓጎል ነው‘ – ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ንጋቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 17, 2021
48
ዘላለም ግዛው  አዲስ አበባ:- የሱዳን ሃይል በተጠናከረ ሁኔታ ወደ ውስጥ እየተስፋፋ መሄዱ የግድቡን ግንባታ ለማስተጓጎል የተደረገ መሆኑን ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ንጋቱ አስታወቁ። ትዕግስቱ ከበቂ በላይ በመሆኑ የሃይል አጸፋ እንደሚያስፈልግ አመለከቱ። የቀድሞ መከላከያ ሰራዊት ባልደረባ ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፤ የሱዳን አሁናዊ የመሬት ወረራ ዋናው ግብ በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ የሚገኘውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስቆም፣ ወደ ሃይል ማመንጨት ሂደቱ ከ...
https://www.press.et/Ama/?p=39619
የአትሌቶችን ጥያቄ የሚመልስ ማዘውተሪያ
ስፖርት
December 13, 2020
12
 ብርሃን ፈይሳበኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኦሮሚያ ክልል ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነባው የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ የአሸዋ ትራክ ተመረቀ። በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎችም ተመሳሳይ ማዘውተሪያዎች እንደሚገነቡ ታውቋል።በኦሮሚያ ክልል ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነባው የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ ስፍራ ትናንት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል። ግንባታው ለረጅም ርቀትና አጭር ርቀት አትሌቲክስ ስፖርት መለማመጃ የሚውለው የአሸዋ ትራክ እንዲሁም የአትሌቶች ልብስ መቀየሪያ፣ የማረፊያና የንጽህና መጠበቂያ ስፍራን ያጠቃል...
https://www.press.et/Ama/?p=37292
ከቅጣት ያመለጠው ታሪካዊ ጥፋት
ስፖርት
December 13, 2020
13
ቦጋለ አበበእግር ኳስን በመሳሰሉ ተወዳጅና ንክኪ በሚበዛባቸው ስፖርቶች ተጫዋቾች በእንቅስቃሴ ውስጥ እያሉ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች ላይ ጥፋት(ፋውል) ይሰራሉ። እነዚህ ጥፋቶች ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉና ያስከተሉበት አጋጣሚም በርካታ እንደነበር መመልከት ይቻላል። በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ወቅት ስፖርተኞች መሰል ጥፋት ሲሰሩ ውድድሩን በሚመሩ ዳኞች ከቢጫ የማስጠንቀቂያ ካርድ አስከ በርካታ ጨዋታዎች መታገድ ሊያደርሱ የሚችሉ ቅጣቶች ይከተሏቸዋል። ዳኞች አ...
https://www.press.et/Ama/?p=37293
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሰበሩ ከሚገኙ የዓለም ክብረወሰኖች ጀርባ
ስፖርት
December 14, 2020
7
ቦጋለ አበበበኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ለበርካታ ወራት ተቋርጠው የቆዩ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ካለፈው ሐምሌ መጨረሻ ጀምሮ በሂደት ወደ መደበኛ መርሃግብራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ውድድሮች በተመለሱበት ጥቂት ወራትም በተለይም የረጅም ርቀት የዓለም ክብረወሰኖች ለማመን በሚቸግር መልኩ ሲሰበሩ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡ ይህም የስፖርቱን አፍቃሪዎች ከማነጋገሩ ባሻገር ተንታኞች ጭምር ግራ እንዲጋቡ ያደረገ ክስተት ሆኗል፡፡ በተለይም የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን ከወረርሽኙ በፊትም ቢሆን ...
https://www.press.et/Ama/?p=37367
ታላቁ ሩጫን በጥንቃቄ
ስፖርት
December 14, 2020
9
 ቦጋለ አበበ የ20ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጥር 2 ቀን ይካሄዳል። የውድድሩ ምዝገባ ባለፈው ታህሳስ 2 ቀን የጀመረ ሲሆን ፣ተሳታፊዎች በያሉበት የአሞሌን መተግበሪያ በመጠቀም ምዝገባውን እንዲያካሂዱ ተደርጓል ። የመጀመሪያዎቹ 200 ተሳታፊ ተመዝጋቢዎች ለውድድሩ መዘጋጃ የሚሆን የመለማመጃ ቲ-ሸርት በነጻ እንደሚሰጣቸውም የውድድሩ አዘጋጆች ከላኩት መግለጫ ታውቋል። 20ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዘንድሮ ውድድሩ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ 12ሺ500 ተሳታፊዎች ብቻ ይኖሩታል። በተጨማሪም የአ...
https://www.press.et/Ama/?p=37370
የባዶ እግር ትሩፋቶች
ስፖርት
December 15, 2020
16
ብርሃን ፈይሳየበጋማው ወቅት ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ጎዳናውን ቢያግለውም፣ ባዶ እግሩን ሮጦ ከማሸነፍ አላገደውም። ጦር ያዘመተችባት ሃገር ሽንፈትን በተከናነበችበት ማግስት ብቻውን ዘምቶ እንደ አንድ ባታሊዮን ጦር አሸንፎ የኢትዮጵያዊያንን አንጀት አራሰ እንጂ፡፡ በእርሱ እግር የተተካውም፤ በቀናት ልዩነት በመም የተካፈለበትን ርቀት ከመጤፍ ሳይቆጥር በማራቶንም ዳግም ሃገሩን በክብር አስጠርቷል፡፡ሌላኛው ደግሞ እስርና ሌላ ኦሊምፒክን ማሳለፍ ተስፋ ሳያስቆርጠው በአንድ ኦሊምፒክ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማጥ...
https://www.press.et/Ama/?p=37432
የቀጣዩ አራት ዓመት የአትሌቲክስ መሪዎች
ስፖርት
December 16, 2020
8
ቦጋለ አበበየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከትናት በስቲያ ባደረገው 24ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በቀጣይ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን የሚመሩ ሰዎችን ለይቷል።ከአራት ዓመት በፊት ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት የተመረጠው ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ሁለት ዓመት አገልግሎ በራሱ ፍቃድ ስልጣኑን ከለቀቀ በኋላ ሌላኛዋ ጀግና አትሌት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ፌዴሬሽኑን ስትመራ ቆይታለች።ከትናንት በስቲያ ማታ በካፒታል ሆቴል በተደረገው ምርጫም ደራርቱ ለቀጣዩ አራት ዓመት ፌዴሬ...
https://www.press.et/Ama/?p=37493
ቡድኑ ዝግጅቱን አስቀድሞ መጀመሩ ለውጤታማነት ያግዘዋል
ስፖርት
December 17, 2020
13
ብርሃን ፈይሳ የቶኪዮ 2021 ኦሊምፒክ ከመካሄዱ ወራትን አስቀድሞ ዝግጅት መጀመሩ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የሚያደርግ መሆኑ ተገለጸ። በኦሊምፒክ መድረክ ሃገራቸውን ለወከሉ አትሌቶች የተካሄደው የምስጋና መርሃ ግብር፤ ለመጪው ኦሊምፒክ ተሳታፊዎች መነሳሳትን እንደሚፈጥርም ተጠቆመ፣ ከዚህ ቀደም ይደረግ ከነበረው በተለየ ሁኔታ ከወራት በፊት ካምፕ በመግባት የረጅም ጊዜ ዝግጅት ማድረግ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የተሻለ ውጤት እንዲያመዘገብ ያስችላል ተብሏል። በ5ሺ ሜትር ሃገሩ...
https://www.press.et/Ama/?p=37572
ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባለድርሻ አካላትን አመሰገነ
ስፖርት
December 19, 2020
10
ቦጋለ አበበ ባለፈው ህዳር 27/2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሁለት አህጉራዊ ስኬቶችን በስፖርቱ ዘርፍ አስመዝግቧል። በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ጠቅላላ ጉባዔን ማስተናገድ የመጀመሪያው ስኬት ነው። ከጉባዔው ጎን ለጎን ለመሪዎች የሚበረከተውን የአኖካ የስፖርት የክብር ኒሻን ሽልማት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በማሸነፋቸው የሽልማት ሥነሥርዓቱን ማስተናገድ ሌላው ስኬት ነው። ሁለቱን ታላላቅ የስፖርት ኩነቶች ኢትዮጵያ በአንድ ቀን በስ...
https://www.press.et/Ama/?p=37676
በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም ምክንያታዊ ትውልድ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 17, 2021
10
መርድ ክፍሉአዲስ አበባ፡- በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለዘለቄታው ለማስቆም በምክንያት የሚያምን ትውልድ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። በአገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች በአገር ጉዳይ ምክንያታዊ የሆነ አስተሳሰብን መፍጠር የሚስችላቸው የሙግትና የንግግር መድረክ በአዲስ አበባ ተጀመረ። የብልጽግና ወጣት ሊግ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽህፈት ቤት ኃላፊ ወጣት አክሊሉ ታደሰ ትናንት መድረኩን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንዳስታወቁት ፤ በአገሪቱ በእምነት እና በፖለቲካ ልዩነት እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ወደ ግጭት እየ...
https://www.press.et/Ama/?p=39630
በጎንደር የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በደማቅ ሥነ- ሥርዓት ለማክበር የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 17, 2021
22
 መሃመድ ሁሴን አዲስ አበባ:- በጎንደር ከተማ የሚከበረውን የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት ለማክበር የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ። በከተማዋ በሚደረገው ክብረ በዓልም የተለያዩ አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀቱን መምሪያው ገልጿል። በጎንደር ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ኃላፊ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የዘንድሮውን የጥም...
https://www.press.et/Ama/?p=39628
የሃገር ፍቅር ያጀገነው ወታደሩ ኦሊምፒያን
ስፖርት
December 20, 2020
23
ብርሃን ፈይሳየኢትዮጵያ አትሌቲክስንና ድልን ያወዳጃቸው ጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ ይሁን እንጂ፤ የድሉን ቀጣይነት ያወጀው ሌላኛው ወርቃማ አትሌት ሻምበል ማሞ ወልዴ ነው። ማሞ የአበበን ፈለግ ተከትሎ ሃገሩ የለመደችው እንዳይጎድልባት በላቡ ክብሯን አድምቋል፤ ኢትዮጵያዊያን በቀላሉ የማይደፈሩ ጀግኖች መሆናቸውንም ለዓለም አረጋግጧል፡፡ የአሸናፊነት ወኔው ሳይሸረሸር ውጣ ውረዶችን ተሻግሮ የሃገሩን ክብር እንዳስጠበቀ ያለፈ፤ ገድሉም ከኢትዮጵያ የጀግኖች መዛግብት በወርቅ ቀለም የሰፈረ ነው፡፡ ይሁን ...
https://www.press.et/Ama/?p=37748
አካል ጉዳተኞችን ተደራሽ ያላደረገው ስፖርት
ስፖርት
December 21, 2020
10
 ስፖርት እድሜ ጾታና የሰውነት አቋም የማይለይ አካላዊ እንቅስቃሴና የሰው ልጆች መብት ምት ጭምር ነው፡፡ ይህም ማለት አካል ጉዳተኞችንም አካቶ የአካላዊና አእምሯዊ ጤናን ለመጠበቅ የሚያስችል ሚዛን ነው፡፡ ይሁን እንጂ በብዙ ሃገራት አካል ጉዳተኞችን በስፖርት ማሳተፍ አልተለመደም፡፡ በእርግጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ አካል ጉደተኞችን በስፖርታዊ እንቅስቃሴና ውድድር ማካፈል እየተለመደ የመጣው ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ እንቅስቃሴ እንደሚጠበቀው ጎልቶ ባለመታየቱ አካል ጉዳተኞችን ለማሰ...
https://www.press.et/Ama/?p=37833
በሲሚንቶ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ አሁንም ችግሮች እንደሚታዩ ሚኒስቴሩ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 17, 2021
42
አስናቀ ፀጋዬ አዲስ አበባ፡- በሲሚንቶ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ አሁንም ችግሮች እንደሚታዩ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሀገሪቱ የሚታየውን የሲሚንቶ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም አመለከተ። በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የብረታ ብረትና ኬሚካል ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ዱጋሳ ዶንሳ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት ፣ሚኒስቴሩ ከስድስት ወር በፊት በምርትና በአቅርቦት በኩል የተፈጠረውን የሲሚንቶ እጥረት መንስኤ ለማጥናት በሀገር አቀፍ ደረጃ ኮሚቴ አቋቁሞ ሲሰ...
https://www.press.et/Ama/?p=39629
“የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ በሁለትዮሽ ስምምነቶች እና በጋራ የድንበር መድረኮች አማካኝነት መፈታት አለበት” – ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር
ሀገር አቀፍ ዜና
January 16, 2021
8
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለው የድንበር ጉዳይ ባሉ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እና የጋራ የድንበር መድረኮች አማካኝነት በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ አሳሰቡ። ከሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የብሔራዊ ድንበር ኮሚሽን ተቀማጭነታቸው በሱዳን ለሆኑ ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች፣ ቆንስላዎች እና የዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ገለጻ አድርጓል። በዚህም ወቅት፣ አምባሳ...
https://www.press.et/Ama/?p=39551
የጎዳና ላይ ሩጫ በቢሾፍቱ
ስፖርት
December 7, 2020
5
ቢሸፍቱ ፦የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከወራት መቋረጥ በኋላ የመጀመሪያውን አገር አቀፍ የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አካሂዷል፡፡ ለ7ኛ ጊዜ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው በዚህ ውድድር ላይም በአጠቃላይ ነጥብ በሴቶች ኦሮሚያ ፖሊስ በሴቶች ደግሞ መከላከያ ስፖርት ክለብ ቀዳሚ በመሆን አጠናቀዋል፡፡ የመከላከያዋ አትሌት ገበያነሽ አየለ በሴቶች ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ፤ የገባችበት ሰዓት ደግሞ 1:47.03 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የግል ተወዳዳሪዎቹ ብርሃን ምህረቱ እና ንግስት ሙሉነህ ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ በ...
https://www.press.et/Ama/?p=36908
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የቫሌንሺያን የግማሽ ማራቶን አሸነፈች
ስፖርት
December 7, 2020
9
አዲስ አበባ፡- አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በስፔን በቫሌንሺያ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸነፈች። በመካከለኛ እና የአጭር ርቀት ሩጫ የምትታወቀው አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ግማሽ ማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ ተወዳድራ አሸናፊ መሆን ችላለች። ጀግናዋ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ18 ሴኮንድ ፈጅቶባታል።የገባችበት ሰዓት የቦታው አዲስ ክብረወሰን በመሆንም ተመዝግቧል። ውድድሩን በሁለተኛነት ያጠናቀቀችው ኬንያዊቷ ሼይላ ቼፕኪሩይ ስትሆን፤ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ሰንበሬ ተፈሪ ደግ...
https://www.press.et/Ama/?p=36915
ከተፋቀርን አባይ ይገደባል ፤ እኛም እንጠግባለን
መዝናኛ
March 9, 2020
44
ተሰልፈን ቆመናል አምባሳደር አካባቢ ታክሲ ተራ።ታክሲዎች ተሳፋሪውን ተራ በተራ እየጫኑ ወደ መድረሻቸው ይጓዛሉ።ተሳፋሪው ሌላ ታክሲ እስኪመጣ ይጠብቃል።አንድ ከፍ የለ ድምፅ በሰልፍ የቆመውን ተሳፋሪ ትኩረት ስቧል።ሁሉም ወደ ተሰማው ድምፅ አማተረ።አንድ ወጣት አንዲት ህፃን ልጅ አቅፎ ተሳፋሪውን ቀረበና በእጁ የያዘውን በፕላስቲክ ማሸጊያ የተለበጠ ወረቀት ላይ የተፃፈ ጽሁፍ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያነባል፡፡የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚሰማ ምልዕክት አይነት የመሰለው አይንና ጆሮው መለሰ። ልጁ ቀጥሏል...
https://www.press.et/Ama/?p=28753
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔን አካሄደ
ስፖርት
December 7, 2020
8
አዲስ አበባ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ትናንት አካሂዷል፡፡ ያለፈው ዓመት ባጋጠሙ በርካታ ውጣ ውረዶች ስፖርቱ አሉታዊ ተጽእኖ ቢደርስበትም የተሻለ አፈጻጸም የተመዘገበበት መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውን የካፍ አካዳሚን በማስጠገን ለአገልግሎት መብቃቱ፤ ፌዴሬሽኑ ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ ታድጓል። የአህጉርና ዓለም አቀፍ ግንኙነትን በማጠናከር ረገድም ጠንካራ ሥራ በመከናወኑ ኢትዮጵያ በሴካፋ የመሪነት ቦታ ማግኘቷም ...
https://www.press.et/Ama/?p=36914
የብስክሌት ኮርቻ ቀበኛው
መዝናኛ
March 10, 2020
203
ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል እንዲሉ አመለኛ ሌባ ያገኘውን ከመስረቅ ወደኋላ አይልም። ታዲያ ሌብነት ሁሌም አይቀናምና አንድም በሰዎች መደብደብን ባስ ሲልም በፖሊስ መያዝና ለአስር መዳረግን ያስከትላል። ሌባ ከትንንሽ እቃዎች አንስቶ አስከ ከፍተኛ ውድ እቃዎች ድረስ ፤ ከትንሽ አስከ ከፍተኛ ገንዘብ ድረስ ይሰርቃል። አንዳንድ ሌባዎች የሚሰርቋቸው እቃዎች ግን እንግዳና ያልተለመዱ ሆነው ‹‹ምን ሊያደርግላቸው ነው?›› የሰረቁት ያሰኛሉ። ከሰሞኑ ኦዲቲ ሴንትራል ይዞት የወጣው መረጃም ይህንኑ ያመለክታል። ነገሩ እን...
https://www.press.et/Ama/?p=28828
ትራምብ
መዝናኛ
March 5, 2020
25
የአድዋን ድል ለማክበር የትውልዱ ተረኛ ወጣት በነቂስ ወጥቷል:: ያስገመግማል:: ያጉተመትማል:: ሆ በል ይላል:: በባህላዊ አልባሳትና በጥንት አባቶች የጦር ሜዳ አለባበስ ተውቦ ደምቋል:: አባት አርበኞች ጋሻና ጦር ጎራዴ ይዘው ቁጭ ብድግ እያሉ በወኔ ተሞልተው ይሸልላሉ:: ያቅራራሉ:: ይፎክራሉ:: ‹‹በለው ሲል ገዳይ…ያንን ጥልያን ከተረተሩ ከጉድባው ላይ›› እያሉ:: እናቶች ወጣት ሴቶችና ወንዶች የአባቶችን ወኔና ጀግንነት በማወደስ እልልታውን ያቀልጡታል:: እልልል እንደገና:: እልልል እንደገና:: እን...
https://www.press.et/Ama/?p=28551
የእብድ ገላጋይ ያቀብላል ድንጋይ
መዝናኛ
March 10, 2020
55
 በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተፈተነች ትገኛለች፡፡ በቫይረሱም ምክንያት ሰው እንደ ቅጠል በእያንዳንዱ ሰከንድ ይረግፋል። በሽታው በትንፋሽና በንክኪ በቀላሉ የሚዛመት መሆኑ ደግሞ ስርጭቱን በቀላሉ ለመቆጣጠር አዳጋች አድርጎታል፡፡ ታዲያ በዚህ የዓለማችን ስጋት በሆነው በሽታ ስጋት የገባው አባወራ ራሱንና ልጆቹን ለማዳን ያደረገው ድርጊት የሰሞኑ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆኖ ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው ግለሰቡ የሊትዌንያ ነዋሪ ሲሆን በኮኖራ ቫይረስ ተይዛለች በሚል ስጋት...
https://www.press.et/Ama/?p=28831
ለአዳኞች እጅ የሰጠው ግዙፉ ተኩላ
መዝናኛ
March 24, 2020
36
በሩሲያ በረዷማ አካባቢዎች ላይ በሚገኙ ደኖች ውስጥ ተኩላዎች በብዛት ይኖራሉ። እነዚህ ተኩላዎች ታዲያ በጫካ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች እንስሳትን ይመገባሉ እንጂ ለአካባቢው ነዋሪዎች ብዙም ስጋት አይሆኑም። በሩሲያ አንዲት አነስተኛ መንደር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ግን በአንድ ግዙፍ ተኩላ ስጋት ገብቷቸው ሲቸገሩ ቆይተው ሰሞኑን እፎይ ብለዋል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ፅፏል። ነገሩ እንዲህ ነው፤ በሩሲያ አሌክሳንደሮቭካ በተሰኘች አንዲት አነስተኛ መንደር ውስጥ የሚኖሩት እነዚህ ሰዎች በተደጋጋሚ ሲያስጭንቃቸው የቆየው ...
https://www.press.et/Ama/?p=29010
ባይሆን ጥሩ ነበር፤ ግን ሆነ
መዝናኛ
March 23, 2020
33
ሳንፈልግ የሚያስፈግጉን፤ ሳንወድ የሚያስቁን ብዙ ሁነቶች በሰሞኑ በውዝግብ ውስጥ አሳልፈናል። እርግጥ ነው እንደ ማህበረሰብ ለጉዳዮች ያለን ግንዛቤ እጅግ ያነሰ ነው። የኛ ያልሆኑ ነገሮች ደግሞ አዳዲስ ለሚፈጠሩ ጉዳዮች ማለቴ ነው። እንጂማ ስለኛ ከኛ በላይ የሚያውቅ እንደሌለ ዘንግቼው አይደለም። እናም ከሳምንት በፊት ወደ ሀገራች ገባ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ብዙዎቻችንን በሀሳብ ኮርኩሮናል። እጅግ ደጋጎችን አይተን “እናንተማ በርክቱልን፤ ስለኛ ህይወት ጣዕም ቅመሞች ናችሁና ጤናችሁ ይብዛልን” እንዳልነ...
https://www.press.et/Ama/?p=28957
ስዕልን በሁለት እጅ
መዝናኛ
March 24, 2020
70
አለማችን ከሊዮናርዶ ዳቪንቺ እስከ ፓብሎ ፒካሶ ድንቅ ሰአሊያንን አፍርታለች። አሁንም በየሃገራቱ በተለያዩ የስነ ስዕል ዘርፎች የስዕል ጥበባቸውን ለዓለም የሚያሳዩ ዝነኛ አርቲስቶች አልጠፉም። ሃገራችንም ብትሆን ሰዓሊና ባለቅኔ ገብረ ክርስቶስ ደስታን ጨምሮ በርካታ አንጋፋና ወጣት የስነ ስዕል ጥበበኞችን አፍርታለች። ሰዓሊያን በተለያየ የስነ ስዕል ዘርፍ የየራሳቸውን የአሳሳል ዘይቤ በመከተል የስዕል ስራቸውን የሚሰሩ ቢሆንም፣ አብዛኞቹ ቀለም ነክረው በዘረጉት ሸራ ላይ የሚቀቡት በአንድ እጃቸው ብቻ ነ...
https://www.press.et/Ama/?p=29017
ለአፍሪካ አገራትም ተምሳሌት የሆነው የኢትዮጵያ ስፖርት
ስፖርት
December 8, 2020
9
ብርሃን ፈይሳየአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) የዘንድሮ መዳረሻውን ኢትዮጵያን ማድረጉ ይታወቃል፡፡ በኮሚቴው ምስረታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በነበራትና የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ከትናንት በስቲያ ጠቅላላ ጉባኤውን ከማካሄዱም ባሻገር ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በአህጉሩ ከፍተኛ የሆነውን የስፖርት የክብር ሽልማት አበርክቷል፡፡ ኮሚቴውና አባላቱ አጠቃላይ የነበራቸውን ቆይታ በተመለከተም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ለአዲስ ዘመን አብራ...
https://www.press.et/Ama/?p=36968
እግራችንን እንሰብስብ፤ ቤታችን እንዝጋ!
መዝናኛ
March 29, 2020
39
 የአለም አቀፍ ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ለሚደረገው ጥንቃቄ እያሳየነው ያለነው ዝግጁነት እንደ ጣሊያን ዋጋ እንዳያስከፍለን እሰጋለሁ። ብዙዎችም ሊመጣ የሚችለውን ችግር ቀድመው በመተንበይ እያስጠነቀቁን ነው። ነገር ግን አፍንጫው ላይ ነጭ ሽንኩርት፣ ሎሚና ጤናዳምን እስከነቅጠሉ አስሮ ከመሳለቅ በዘለለ ንክኪን ለማቆም የደፈረ የለም። ብዙዎቻችን ኮሮና ኢትዮጵያ አይገባም፤ ቢገባም አይጎዳንም የሚል ፌዝ ይዘን እራሳችን እያታለልን ነው። ማታለል ብቻም ሳይሆን ለሚመጣው ሰደድ እሳት ብዙዎችን አሳ...
https://www.press.et/Ama/?p=29384
ዶክተር ካትሪን ሀምሊን
መዝናኛ
March 29, 2020
61
   • “የኢትዮጵያ እናቶች እናት” በመባል የሚታወቁና የረጅም አመት የማህጸን ሀኪም በመሆን ያገለገሉ ናቸው። •እ.አ.አ በ1924 ሲድኒ አውስትራሊያ ውስጥ ተወለዱ።•እ.አ.አ በ1959 ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ እቅዳቸው ሦስት ሳምንት የመቆየት ብቻ ቢሆንም በርካታ ሴቶች ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው በመገንዘብ ከመሄድ ይልቅ መቆየትን መረጡ።•እ.አ.አ በ1974 አዲስ አበባ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነውን የፌስቱላ ሆስፒታል አሰሩ።•ይህ ሆስፒታል ከ45 ሺ በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ከህመም ፈውሶ መደበኛ ህይወ...
https://www.press.et/Ama/?p=29379
አንዳንድ እውነታዎች ስለ ታላቁ ህዳሴ ግድብ
መዝናኛ
March 29, 2020
54
 የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በ2003 ዓ.ም ተጀመረ።• ግድቡ ሲጠናቀቅ ከ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በላይ ቦታ ይይዛል።• የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመሙላት የሚወስድባት ጊዜ እስከ ሰባት አመት ነው።• በሚመጣው ክረምት የውሃ ሙሌት ይጀ መራል። •ታህሳስ 2013 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ። እያንዳንዳቸው የኃይል ማመንጫ ተርባይን 375 ሜጋዋት በጠቅላላው 750 ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨ ይችላሉ።• በእያንዳንዱ ኢትዮጵያውያን የገንዘብ መዋጮ የሚገነባና የሁ...
https://www.press.et/Ama/?p=29376
የብሔራዊ ስታዲየም ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ተጀመረ
ስፖርት
July 31, 2020
20
 አዲስ አበባ ቀደምት ከሚባሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ተርታ ብትመደበም፣ መጠሪያዋን ስያሜው ያደረገ ብሔራዊ ስታዲየም ሳይኖራት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ዘመናዊ ስታዲየምም መመልከት ብርቅ ሆኖባት ዘመናት አልፈዋል:: አንድ ለእናቱ የሆነው የአዲስ አበባ ስታዲየም የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ለዚህ ወቅት የሚመጥን አይደለም በሚል ማንኛውንም አኅጉራዊም ይሁን ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን እንዳያስተናግድ ክልከላ ጥሎበታል:: በ2008 ዓ.ም. ታህሣሥ ወር ላይ «ሀ»ብሎ የግንባታውን መሠረት የተጣለለት የአደይ ...
https://www.press.et/Ama/?p=36398
መልስ ያላገኘው የአፍሪካውያን የአገር አቋራጭ ሩጫ ጥያቄ
ስፖርት
July 30, 2020
18
አትሌቲክስን ፈታኝ ስፖርት ከሚያደርጉት ውድድሮች አንዱና ዋነኛው የአገር አቋራጭ ሩጫ ነው። የአገር አቋራጭ ውድድር አትሌቲክስን ፈታኝ ብቻም ሳይሆን ተወዳጅና ቀልብ ሳቢ ካደረጉት ምክኒያቶች አንዱ ነው ቢባል ስህተት አይሆንም። በገባ ወጣ መልክዓምድር፤ ኮረብታና ቁልቁለት እንዲሁም በጭቃና አልፎ አልፎም በበረዶ ክምር መሰናክሎች የታጀበው ይህ ውድድር አትሌቶች ከመምና ከጎዳና ላይ ውድድሮች ወጥተው ራሳቸውን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚፈትኑበት ነው።የአገር አቋራጭ ሩጫ የምስራቅ አፍሪካውያን የበላይነት እየገ...
https://www.press.et/Ama/?p=36334
የግመሎቹን ቅስም እስከ ወዲያኛው የሰበረው የዓለም ዋንጫ ክስተት
ስፖርት
August 2, 2020
26
የ1982 የዓለም ዋንጫ ለኤሽያዊቷ አገር ኩዌት የእግር ኳሷ ወርቃማ ዘመን ሆኖ ይታወሳል። የዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር ግን ይህ የኩዌት ወርቃማ የእግር ኳስ ዘመን ሲታወስ አይታይም። እግር ኳስ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እየረቀቀ ሲመጣ፤ በይነ መረብ ዓለምን ሲያቀራርብና ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭቶች እንደ ልብ እየሆኑ ሲመጡ እኤአ ከ199oዎቹ ጀምሮ በዓለም ዋንጫ የታዩ ወርቃማ ብሔራዊ ቡድኖች፤ በርካታ ከዋክብቶችና አይረሴ አጋጣሚዎች አሁንም ድረስ በእግር ኳስ አፍቃሪው ዘንድ ይታወሳሉ። ያም ሆኖ ከ1978 የዓለም...
https://www.press.et/Ama/?p=36497
የስፖርት ማህበራትን ለመከለስ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው
ስፖርት
August 1, 2020
9
ዘመናዊ ስፖርት ወደ ኢትዮጵያ ከገባ አንድ ምዕተ ዓመት ሊያስቆጥር መቃረቡን ሰነዶች ያሳያሉ። ይሁን እንጂ ስፖርት በኢትዮጵያ በዕድሜው ልክ እንዲሁም ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ አንጻር መድረስ ካለበት ስፍራ እንዳልደረሰ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። ስፖርት የአንድ ሀገር እድገት መለኪያ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ቢሆንም፤ በኢትዮጵያ የህዝቡን ጥቅምና ፍላጎት አስጠብቋል ለማለት አያስደፍርም። ለስፖርቱ እድገትም ሆነ መዳከም ድርሻ ያላቸው የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ስፖርቱን የሚመሩ አካላት ጥንካሬና ብቃት ግን ወሳኝ...
https://www.press.et/Ama/?p=36457
አይጦችን ከአገልግሎት ክፍያ ለማምለጫ
መዝናኛ
February 18, 2020
21
 በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ሆቴሎች እንደ የደረጃቸው ለደምበኞቻቸው አገልግሎቶችን ያቀርባሉ።ለአገልግሎቶቻቸውም ደምበኞቻቸውን ያስከፍላሉ።ደምበኞችም በሆቴሎቹ ቆይታቸው ከያዙት አልጋ ጀምሮ እስከተጠቀሟቸው ምግቦችና መጠጦች ድረስ ክፍያ መፈፀም ይጠበቅባቸዋል። ይሁን እንጂ አንዳንዴ ደንበኞች በሆቴሎች ውስጥ ያሻቸውን ተጠቅመው ሲያበቁ ሂሳብ ሲጠየቁ ድንጋጤ ውስጥ የሚገቡ፤ ለመክፈልም የሚያንገራግሩ አይጠፉም።ለተጠቀሙበት አልጋ፣ ምግብ፣ መጠጥና ሌላም የአገልግሎት ክፍያ ሳይፈፅሙ እንዲሁ በነፃ ከሆቴሉ ውልቅ ብለው...
https://www.press.et/Ama/?p=27458
ባድሚንተን-ትኩረት የተነፈገ ተወዳጅ ስፖርት
ስፖርት
August 3, 2020
10
 በስፖርቱ ዓለም ጥሩ የአካል ብቃት፣ሰውነትን እንደ ልብ የማዘዝ ችሎታ፣ፅናት፣ጥንካሬና ፍጥነትን ከሚሹ ጨዋታዎች መካከል ባድሚንተን ዋነኛው ነው። ከሜዳ ቴኒስ ወይንም ከጠረጴዛ ቴኒስ ጋር ተመሳሳይ አጨዋወትን የሚጋራው የባድሚንተን ስፖርት በብሪታኒያና ህንድ እንደጎለበተ የሚነገር ቢሆንም በአውሮፓዊቷ አገር ዴንማርክ ትልቅ ዝና አለው። ይህ ስፖርት ተወዳጅነቱን እያሰፋ በኤሽያ አገራት በስፋት መዘውተሩን ተከትሎም ባለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት የቻይና የበላይነት የሚንፀባረቅበት ሆኗል። እኤአ 1992 በባርሴ...
https://www.press.et/Ama/?p=36543
የሚወዱት -ሲወደድ” ደስ ይላል!
መዝናኛ
February 24, 2020
27
እነ ኒያላና ጓደኞቹ በመወደዳቸው፤ ዋልያና ቤተሰቦቹ አልቀመስ በማለታቸው አኮረፉ አሉ። ሰው የሚወደው ነገር ሲወደድ ደስ ሊለው ነው የሚገባው፤ አይደል? ምን ነካቸው? ሰሞኑን በፀደቀው አዋጅ ምክንያት አኩራፊዎች በዝተዋል ሲሉ ተገረምኩ። የእነ ሀበሻ አድናቂዎች የእነ ግስላ ቲፎዞዎች እንዲያው ምን ነካችሁ? ሰው ወዳጁ ወደላይ ከፍ እንዲልለት በብርቱ ሲመኝ እንዴት የወደዳችሁት ነገር መወደዱን ጠላችሁት ግን? አኮረፉ ‘ለምን? አሉ’ ሲሉኝ እኔ አላመንኩም ነበር። ግን አመንኩ፤ በቢራ መወደድ ማዘናችሁ፤ በሲጃራ...
https://www.press.et/Ama/?p=27764
የሚወዱት -ሲወደድ” ደስ ይላል!
መዝናኛ
February 23, 2020
26
እነ ኒያላና ጓደኞቹ በመወደዳቸው፤ ዋልያና ቤተሰቦቹ አልቀመስ በማለታቸው አኮረፉ አሉ። ሰው የሚወደው ነገር ሲወደድ ደስ ሊለው ነው የሚገባው፤ አይደል? ምን ነካቸው? ሰሞኑን በፀደቀው አዋጅ ምክንያት አኩራፊዎች በዝተዋል ሲሉ ተገረምኩ። የእነ ሀበሻ አድናቂዎች የእነ ግስላ ቲፎዞዎች እንዲያው ምን ነካችሁ? ሰው ወዳጁ ወደላይ ከፍ እንዲልለት በብርቱ ሲመኝ እንዴት የወደዳችሁት ነገር መወደዱን ጠላችሁት ግን? አኮረፉ ‘ለምን? አሉ’ ሲሉኝ እኔ አላመንኩም ነበር። ግን አመንኩ፤ በቢራ መወደድ ማዘናችሁ፤ በሲጃራ...
https://www.press.et/Ama/?p=27729
ሹል ሹል !
መዝናኛ
February 27, 2020
30
ሱራ ሽቅብ ሽቅብ ያቃስታል። ግዝፈቱ ያስጨንቀዋል። ልብስ አይበቃውም። የጫማው ቁጥር 48 ነው። የትከሻው ስፋት የሰውነቱ ግዝፈት የቁመቱ ርዝመት የሰማይ ስባሪ አስመስለውታል። አባ ግድየለሽ ሱራ ወግ ጨዋታ ይወዳል። ሰው አያስቀይምም። ውፍረቱ አስፈሪ አስደንጋጭ ነው።የሰፈሩ ሰው ልጆች ሲያለቅሱና ሲረብሹ ዋ ሱራን ነው የምንጠራው ሲባሉ ያውቁታልና በፍርሀት ርደው ጭጭ ነው የሚሉት። ሲደሰትም ሲከፋም ሱራ የአላህ ልጅ፤ የአላህ ወዳጅ የሚለው ነገር አለው። ለወላጆች ምነው ምነው ሕጻናቱ እንዲጠሉኝ እንዲፈሩኝ ባ...
https://www.press.et/Ama/?p=27990
የአርባ ሰባት ዓመታት ትዝታ የቀሰቀሰው ቀለበት
መዝናኛ
February 25, 2020
68
 ብዙ ጊዜ ጌጣጌጦች ጠፉ ሲባል ቢሰማም ፈልጎ የማግኘቱ ጉዳይ እንደ መግዛቱ ቀላል አይሆንም። በተለይ የወርቅ ጌጣ ጌጥ ጠፍቶ የመገኘት እድሉ ጠባብ ነው።ወርቅ ውድና ተፈላጊ እንደመሆኑ ያገኘውም ሰው ቢሆን የጠፋበትን ባለቤቱን አፈላልጎ ይሰጣል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።ሊገኝ የሚችልበት እድል አንድና አንድ ብቻ ነው። ሰው እጅ ያልገባ ከሆነ ብቻ።ይህ ሲሆን ከእለታት አንድ ቀን ሊገኝ ይችል ይሆናል። የጌጣጌጦች መጠን አነስተኛ መሆን ከሚጠፉበት ቦታ ውስብስብነት ጋር ተዳምሮ የመገኘት እድላቸውንም በእጅጉ ያ...
https://www.press.et/Ama/?p=27863
ኮሮና ቫይረስን በአሻንጉሊት
መዝናኛ
February 25, 2020
49
የኮሮና ቫይረስ በተለያዩ የአለም ክፍሎች እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሉ ህዝቦች በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል። አለም አቀፍ የሰዎች እንቅስቃሴም እንደወትሮው ሊሆን አልቻለም። በተለይ ደግሞ የቫይረሱ መገኛ በሆነችው ቻይና ሰዎች ቫይረሱ እንዳይዛቸው በተቻላቸው አቅም ሁሉ ራሳቸውን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ከሰሞኑ በሀገሪቱ ደቡብ ምእራብ ሲሽዋን ግዛት በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ህሙማንን ለመጎብኘት የመጣችና ስሟ ያልተጠቀሰ አንዲት ወይዘሮ ራሷን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ያደረገችው ጥረት ግን ብዙዎ...
https://www.press.et/Ama/?p=27860
ዝም ስንል
መዝናኛ
February 24, 2020
26
አቶ አንድአርጋቸው የ75 አመት እድሜ ባለፀጋ ነበሩ። እኝህ አዛውንት ደስተኛ ሆነው የሚኖሩና በጣም የሚያስቀና ቤተሰብ ያላቸው ሰው ነበሩ። ከብዙ አመታት በኋላ ልጆቻቸው አድገው የራሳቸውን ኑሮ በመመስረት ወደ ተለያየ አካባቢ ሄዱ። ባለቤታቸው እና የልጆቹ እናት ከብዙ አመታት በፊት በሞት ስለተለየቻቸው በመንደሩ ውስጥ በብቸኝነት እና በሀዘን ብዙ ጊዜያቸውን ያሳልፉ ጀመር። አቶ አንዳርጋቸው አብዛኛውን ጊዜያቸውን በብቸኝነት ቢያሳልፉም፤ የልጅ ልጆቻቸው በአመት በአል እና በእረፍት ጊዜያቸው አያታቸውን ሊጠይ...
https://www.press.et/Ama/?p=27792
አማራጭ ሃሳብ አምጡ!
መዝናኛ
March 1, 2020
27
ከብዙ ጊዜያት በፊት በአንድ አገር ውስጥ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ነበሩ። እነርሱንም የሚያስተዳድር አንድ ንጉሥም ነበር። ይህ ንጉሥ የሚያስተዳድራቸውን ነዋሪዎች በደስታ ያኖራቸው ነበር። በእሱ የአገዛዝ ዘመን ሁሉም ነዋሪዎች በነፃነት ተገቢውን ነገር በማድረግ በሰላም ኑሯቸውን ይመራሉ። ንጉሣቸው እርሱ በመሆኑም በጣም ደስተኞች ነበሩ። በአንድ ወቅት ንጉሡ በአገሪቷ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን፣ የአምልኮ ስርዓት የሚፈፀምባቸው ቤተክርስቲያናትን እንዲሁም እርሱ በአገዛዙ ወቅት ያልተመለከታቸውን እና በርቀት ያሉ...
https://www.press.et/Ama/?p=28167
ደንበኞች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያልተጠቀምንበትን የታሪፍ ክፍያ እያስከፈላቸው መሆኑን አመለከቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 13, 2021
12
– አገልግሎቱ በደንበኞች የሚቀርቡ ማናቸውንም ቅሬታዎች ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ በጋዜጣው ሪፖርተሮች አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያልተጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ አገልግሎት እያስከፈላቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አመለከቱ። አገልግሎቱ በበኩሉ በደንበኞች የሚቀ ርቡ ማናቸውንም ቅሬታዎች ለመፍታት ዝግጁ መሆ ኑን አስታወቀ። የጋዜጣው ሪፖርተር በሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ቁጥር ሁለት አገልግሎት መስጫ ማዕከል ያነጋገራቸው የአገልግሎቱ ደንበኛ ምንተስኖት ፍሬው፣ “ቤቴ የንግድ አይ...
https://www.press.et/Ama/?p=39377
በአማራ ክልል ከ328 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚሸፍን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 13, 2021
7
ሰላማዊት ውቤ አርማጮሆ፦ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዘንድሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በሚገኝ ከ328 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን የአማራ ቤሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በሥራው 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች እንደሚሳተፉ ገለጸ። በቢሮው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር ተወካይ እስመለዓለም ምህረት ለጋዜጣው ሪፖርተር እንዳስታወቁት ከትላንት ጀምሮ እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ከ20 እስከ 30 ለሚደርሱ ቀናት ...
https://www.press.et/Ama/?p=39389
የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች መያዝ የህግ የበላይነትን በተግባር ያረጋገጠ መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 13, 2021
28
ሞገስ ተስፋ አዲስ አበባ፡- የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች መያዝ የህግ የበላይነትን በተግባር ያረጋገጠ እንደሆነ አዲስ ዘመን ያነጋገራቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።ለተንኮል ሸራቢ አካላትም ትልቅ ትምህርት የሰጠ መሆኑን አመለከቱ፡፡ አዲስ ዘመን ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጌትነት ደምሌ እንደገለጹት፣ በቁጥጥር ስር የዋሉ የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች ለ27 ዓመታት ሀገርን እመራለሁ በሚል አምባገነናዊ የአገዛዝ ቀንበራቸውን በህዝብ ጫንቃ ላይ በግድ በመጫን ህዝብን በዘር፣ ኃ...
https://www.press.et/Ama/?p=39385
የኮሮና ቫይረስን በቃሪያና በርበሬ?
መዝናኛ
February 6, 2020
460
ዓለም ሰሞኑን ከቻይና ተነሳ በተባለው ኮሮና ቫይረስ መታመስ ይዛለች። ዓለም አቀፉ ሚዲያ በስፋት እየዳሰሰውም ይገኛል። ኮሮና ቫይረስ የዓለማችን ቁጥር አንድ አሸባሪ ቫይረስ ሆኖ ተከስቷል። እንደ አልቃይዳ፤ አልሻባብ፤ ዓለምን ማሸበሩን ቀጥሏል።‹‹የጨነቀ ነገር መላው የጠፋ፤ ደሞ ምን ጉድ አመጡብን?›› አሉ አዛውንቷ እማማ አለሚቱ። ‹‹ከዚህ ከሚወራው መአት አምላክ ይጠብቀን እንጂ ምን ሊባል ይችላል›› አሉ በፍርሀት ጎብጠው። ‹‹ደሞ በትንፋሽ፣ በንክኪ ይተላለፋል የሚሉት ነው እኮ የበለጠ የሚያሸብረው። እ...
https://www.press.et/Ama/?p=26779
ልጃገረድነትን ማስመሰል የቻለው የ40 ዓመት ጎልማሳ
መዝናኛ
February 4, 2020
33
ስለ አንድ ነገር አይቶ መናገር ይቻላል፤ ሰምቶም እንዲሁ። አንዳንዴ ግን ያዩትንም የሰሙትንም ማመን ይከብዳል። ኦዲቲ ሴንትራል በቅርቡ ይዞት የወጣ መረጃ እንዳመለከተው፤ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የጃፓን ልጃገረድ የሚመስል ሰው፣ በመካከለኛ እድሜ ላይ የሚገኝ አባወራ ነው። በዊኪፒዲያ ላይ እንደተጠቀሰው፤ ታኩማ ታኒ የተባለው ይህ ጃፓናዊ ድምጻዊ የተወለደው እኤአ በ1977 ነው። ይህ መረጃ ግን ይህን ሰው በፍጹም አይገልጸውም። ሁሉም የግለሰቡ ምስሎች ተማሪ ልጃረገድ ነው የሚመስሉት። ታኩማ ከወጣትነቱ አን...
https://www.press.et/Ama/?p=26632
ኮሚሽኑ ስኬታማ ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ
ስፖርት
July 20, 2020
11
የኮሮና ወረርሽኝ (ኮቪድ 19) በየዘርፉ የተለያዩ ተጽእኖዎችን ማድረሱ ግልጽ ነው። ከእነዚህ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው ስፖርት ሲሆን፤ ጠቅላላ እንቅስቃሴው ተገቶ እንዳልነበር ለመሆን ተገዷል።በርካታ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ ስልጠናዎች፣ ጉባኤዎችና ሌሎች ክንዋኔዎች በቫይረሱ ስጋት ምክንያት ሲሰረዙና ሲራዘሙ መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን የተለያዩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት ለተቋረጡት ስፖርታዊ ኩነቶች አማራጮችን በመፈለግ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል።እንደ መፍትሄ ባስቀመጧቸው ሃሳቦች...
https://www.press.et/Ama/?p=35740
ቶማስ ባኽ ተጨማሪ ዓመታት የመቆየት ፍላጎት አላቸው
ስፖርት
July 20, 2020
14
ዘጠነኛው የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው የኮሚቴው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ። ላለፉት ስምንት ዓመታት ኮሚቴውን የመሩት የ66 ዓመቱ ባኽ በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነም ለቀጣይ አራት ዓመታት በፕሬዚዳንትነታቸው የሚቆዩ ይሆናል። በህግ ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸውና በስፖርቱ ዓለምም የተዋጣላቸው ቶማስ ባኽ ኮሚቴውን መምራት የጀመሩን እአአ በ2013 ነበር።በምዕራብ ጀርመን የተወለዱት ቶማስ ባኽ በትምህርት ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ቢሆ...
https://www.press.et/Ama/?p=35754
“ከፍተኛ የክብር ኒሻን ሽልማቱ ከጀነራል ብርሃኑ ጁላ አልፎ ለአገርም ትልቅ ትርጉም ያለው ነው” – ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ የጀግና ሜዳይ ተሸላሚ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 13, 2021
16
 እፀገነት አክሊሉአዲስ አበባ፦ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ከጅቡቲ መንግሥት የአገሪቱን የመጨረሻ ደረጃ ከፍተኛ ኒሻን መሸለማቸው ከግለሰቡ አልፎ ለአገርም ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ የጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ገለጹ።ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ ሽልማት ማለት አንድ ሰው ለሠራው ሥራ ላበረከተው አስተዋጽዖ እውቅና መስጠት ነው፤ በተለይም እንደዚህ አይነት የእውቅና...
https://www.press.et/Ama/?p=39376
ከሌሊሶ ሜዳ እስከ ማልታ ደሴት
ስፖርት
July 21, 2020
11
በደቡብ ክልል ከምባታ ጠምባሮ ዞን ዋና ከተማ ዱራሜ ነው የተወለደችው። ሰባት ልጆች ላፈሩት እናት እና አባቷ አምስተኛ ልጅ ስትሆን፤ ከልጅነቷ ጀምሮ ነበር በኳስ ፍቅር የወደቀች። የእግር ኳስ መሰረቷን የጣለችው ተወልዳ ባደገበችበት ዱራሜ ከተማ በሰፈር ውስጥ ነው። ከሰፈር የተነሳው የኳስ ህይወት ከሀዋሳ ከተማ አንስቶ በደደቢት እና ብሔራዊ ቡድን በግብ አስቆጣሪነት ስሟ እስከመነሳት የደረሰም ነበር፤ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድንና በማልታ ቢርኪርካራ እግር ኳስ ቡድን አጥቂ ሎዛ አበራ። የሎዛ የእግር ኳስ...
https://www.press.et/Ama/?p=35843
ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከአቶስ ጋር ውሉን አራዘመ
ስፖርት
July 23, 2020
5
 ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከግዙፉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኩባንያ አቶስ ጋር ያለውን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ማራዘሙን ገለፀ። አዲሱ ውል እስከ 2024 እንደሚዘልቅም ሁለቱ ተቋማት ባለፈው ሳምንት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል። ኮሚቴውና ኩባንያው እኤአ ከ1989 ጀምሮ አብረው እየሰሩ እዚህ ደርሰዋል። የፈረንሳዩ አቶስ ኩባንያ የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ግንባር ቀደም ስፖንሰር በመሆን 2014 ላይ ለስድስት ዓመታት የሚዘልቅ ውል ማሰሩ የሚታወስ ነው። የሁለቱ አካላት አዲስ ስምምነት ለ2022 የቤ...
https://www.press.et/Ama/?p=35901
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና እና ተስፋው
ሀገር አቀፍ ዜና
January 11, 2021
17
ጽጌረዳ ጫንያለው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ለአፍሪካውያን ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ይናገራሉ::የአፍሪካ ነፃ ንግድ ሰነዱም ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው::በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህሩ ዶክተር ዳዊት ሀዬሶ እንደሚናገሩት፤ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና አስፈላጊ የሚሆንበት ዋናው ምክንያት እንደ አህጉር የእርስ በእርስ ንግድ ትስስሩ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ እና ይህንን ወደ ከፍታ ለመመለስ ነው::ከዚያም ባሻገር ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር፣ ሰፊ የገበያ አማራጭ ለመፍጠር፣ ጥ...
https://www.press.et/Ama/?p=39249
የጁንታው መያዝ መንግስት እየወሰደ ላለው የሕግ ማስከበር ትልቅ ስኬት እንደሆነ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 11, 2021
33
ሞገስ ተስፋ አዲስ አበባ፡- የጁንታው ቁንጮ አቦይ ስብሃት መያዝ መንግስት እየወሰደ ላለው የሕግ ማስከበር ትልቅ ስኬት እንደሆነ አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።ኢትዮጵያ በሴራ እና ተንኮል እንደማትፈርስ በተግባር ያረጋገጠ እንደሆነም አመለከቱ ።አዲስ ዘመን ያነጋገራቸው አቶ ውብሸት ጌታሁን እንዳሉት፣የጁንታው ቁንጮ የሆኑት አቶ አቦይ ስብሃት ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው እያሉ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር ሲሰብኩ የነበሩ ናቸው::ነገር ግን በሴራ እና በተንኮል ኢትዮጵያ እንደማትፈርስ አይተዋ...
https://www.press.et/Ama/?p=39248
በግማሽ የበጀት ዓመቱ ለግድቡ ግንባታ በአዲስ አበባ ከተማ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 11, 2021
11
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በግማሽ በጀት ዓመቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ከ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ እንደገለጹት÷ በስድስት ወራት በከተማው በቦንድ ግዢ ሽያጭ እና በስጦታ የተሰበሰበው ገንዘብ ባለፉት 8 ዓመታት በድምሩ ከተሰበሰበው የሚበልጥ ነው::ከ2003 ዓ.ም ሐምሌ ወር እስከ 2012 ዓ.ም ሐምሌ ወር ባሉ ...
https://www.press.et/Ama/?p=39247
ስፖርቱ የማገገሚያ ድጎማ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ስፖርት
July 22, 2020
7
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የዓለም ወቅታዊው ሁኔታ፤ የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ፣ አስተሳሰብና ልማድ እንዲቀየር ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህ መንስኤነትም አካላዊና አእምሯዊ ጤናን ከመጠበቅና ከማዝናናት ባለፈ ከፍተኛ ገንዘብ የሚዘዋወርበት ስፖርትም በቀድሞ ቁመናው ላይ እንዳይገኝ ሆኗል፡፡ በዘርፉ በዓለም ደረጃ እአአ በ2011 ከተገኘው ገቢ በ45 በመቶ የላቀ ትርፍ ከሁለት ዓመታት በፊት መገኘቱን ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ያመላክታል፡፡ ይህ እአአ በ2018 የተገኘው 471ቢሊዮን ዶላር በዚህ ዓመት በእጅጉ ሊያ...
https://www.press.et/Ama/?p=35809
የጎደለን…
መዝናኛ
January 19, 2020
35
በአንድ ነገር አምናለሁ። ግራ በገባው ዓለም ላይ አብዛኞቻችን የጎደለን ‹‹ትእግስት›› ነው። ይሄ እኔ የማምንበት ሀቅ ነው። ትእግስት በቀጥታ ከእምነታችን ጋር እንደሚያያዝም አውቃለሁ። ይህ ጉዳይ አንድ ነገር ያስታውሰኛል። አሁን በሕይወት የሌለው አያቴን። ምድር ላይ ያሉ እንቅፋቶችንና መሰናክሎችን በሙሉ አይኔ ማየት እንዲችል አይኔን የገለጠልኝ መሪዬ። የሕይወት መመሪያ ቁልፉን ያቀበለኝ ይህ ታላቅ ሰው በአንድ የተባረከ ቀን የእምነት እና የትግስት ሃያል ቁርኝትን ሊያሳየኝ ቻለ። እምነት ‹‹የማይታየውን ...
https://www.press.et/Ama/?p=25859
የገዳ ስርዓት – የኦሮሞ ሕዝብ የትልቅነቱ ምልክትም ሀብትም
ሀገር አቀፍ ዜና
January 11, 2021
15
አስቴር ኤልያስ ስፍራው በተለያዩ የሴቶችና የወንዶች አልባሳት ደምቋል::በአልባሳቱ ላይ ገኖ የሚታየው ነጭ ቀለም በመሆኑም አስተውሎ ለተመለከተው ዙሪያ ገባውን የፈካ ማሽላ አስመስሎታል::በተለያዩ ድንኳኖች ውስጥ ደግሞ የጉጂ የባህል ምግቦች እንዲሁም የተለያዩ ጌጣጌጦችና አልባሳት ለእይታ ቀርበዋል::በዚሁ ስፍራ አምስት የጎጆ ቤቶች በመደዳ ተሰድረው ይታያሉ::ስፍራው በምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ የጉጂ ኦሮሞ የባህል ስርዓት የሚካሄድበት ቦሌ ሀገላ ነው ::በዕለቱ የገዳ ስርዓቱን ደረጃ የሚያሳይ ትርዒት...
https://www.press.et/Ama/?p=39254
ጥምቀትና ሎሚ
መዝናኛ
January 21, 2020
36
ጥምቀት በህብረ ቀለማት ያሸበረቀና በልዩ ልዩ ክንዋኔዎች የተሞላ፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚሳተፍበት፤ እንደሌሎቹ በዓላት በቤት ውስጥ የተገደበ ሳይሆን በአደባባይ የሚከበር ብዙዎች በጋራ የሚታደሙበት ክብረ በዓል ነው። ከሃይማኖታዊ ሥርዓቱ ባሻገር ባህላዊ ወግና ሥርዓቶችን አጣምሮ ያቀፈ፤ ከከተራ አንስቶ እስከ ጥምቀት ዕለቱ የተለያዩ ትዕይንቶች የሚስተናገዱበት ታላቅ በዓል ነው። በተለያዩ የተዋቡ አልባሳት የደመቁ ካህናትና ዲያቆናት በዓሉን ያደምቁታል። «ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ» እንደተባለው ሁሉ፤ ...
https://www.press.et/Ama/?p=25918
ከድጡ ወደ ማጡ
መዝናኛ
January 21, 2020
14
ሰዎችን ከሱስ ለማላቀቅ የማይፈነቀል ድንጋይ የለም። ምክር፣ ህክምና፣ ለደግ ሲባል ማግለል እና የመሳሰሉት ሁሉ ይሞከራሉ። በተለይ ቤተሰብ ቤቱን ቆሌ ያራቀውን ይህን ችግር ለመፍታት ብዙ ይጥራል። ይህ ጥረት ጥቂቶችን ሲታደግ ቢስተዋልም፣ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይተውም እንዲሉ ይህን ሁሉ አሸንፈው እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ሱሰኛ የሚሆኑ ሰዎች ግን በርካታ ናቸው። ሜክሲኮዊቷ የባሏ መሸተኛነት መሆን በእጅጉ ያስመርራታል። መከረች ዘከረች አልሆን አላት። ቢራ መጨለጡን ሊተው ባለመቻሉ ከዚህ ችግር ሊገላግላት ...
https://www.press.et/Ama/?p=25947
193 አትሌቶች ከዓለም አትሌቲክስ የገንዘብ ድጋፍ ተጠቃሚ ይሆናሉ
ስፖርት
June 25, 2020
9
የዓለም አትሌቲክስ ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት ከውድድር በመራቃቸው የገንዘብ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል ለተባሉ አትሌቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ባለፈው ሚያዝያ መጨረሻ ማሳወቁ ይታወሳል። የዓለም አትሌቲክስ ለዚሁ ድጋፍ እንዲውል አምስት መቶ ሺህ ዶላር ማዘጋጀቱ የሚታወቅ ሲሆን ይህን ድጋፍ ለአትሌቶች ለማድረስ የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንቱ ሴባስቲያን ኮ በሊቀመንበርነት የሚመሩት የባለሙያዎች ቡድን ተቋቋሞ በስድስት ዞኖች በተከፋፈለው የዓለም አትሌቲክስ...
https://www.press.et/Ama/?p=35069
ከቤሌር ሜዳ እስከ ቤልጂየም የዘለቀው ኮከብ
ስፖርት
June 28, 2020
16
በኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪ ልብ ውስጥ በብዙ የሚታወስ ነው። እግር ኳስን ከልጅነት እስከ እውቀቱ ተጫውቷል። አሁንም ቢሆን ከክቧ ኳስ አልራቀም። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የቡድን መሪ ሆኖ አገልግሏል። ባዩ ሙሉ። የመጀመሪያውን የምሥራቅ አፍሪካ የታዳጊዎች ቻምፒዮና ለኢትዮጵያ ዋንጫ ይዘው ከመጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን በጊዜው የእርሱ ድርሻ ጉልህ ነበር። ከዚህም ሌላ ኬንያ ባዘጋጀችው «የሴካፋ ቻምፒዮና» ላይ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ለመመረጥም በቅቷል። በምሥራቅ አፍሪካ ውድድር ኢትዮጵያ ለመጀ...
https://www.press.et/Ama/?p=35264
የኦሊምፒክ ቀን በወርቃማ ኦሊምፒያኖች
ስፖርት
June 25, 2020
11
የዓለም ኦሊምፒክ ቀን እ.ኤ.አ ከ1948 ጀምሮ በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ አገራት ይከበራል። ይህም የኦሊምፒክ አባት በሆኑት ፒየር ዲ ኩበርቲን አማካኝነት በአዲስ መንፈስ የተመሠረተውን የኦሊምፒክ ጨዋታ ለማሰብ ይሁን እንጂ በዓሉ ሲከበር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማከናወን ተፈጥሮዊ መብት በመሆኑ ሁሉም ሰው ዕድሜ ፣ ፆታ ፣ ዘር እና ሃይማኖት ሳይገድበው በሁሉም ቦታ በግል እና በጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ በመቀስቀስ እና በማስተማር ጭምር ነው ።የዓለም ኦሊምፒክ ቀን ‹‹ኦሊምፒክ ለሰው ልጆ...
https://www.press.et/Ama/?p=35067
ስፖርት – ሰብዓዊነትን ጋሻ ያደረገ ማኅበራዊ ክዋኔ
ስፖርት
June 26, 2020
17
ስፖርት የሰላም፣ ፍቅር፣ የአብ ሮነትና የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የወንድማማችነት ልዩ መገለጫ ነው። ስፖርት ዘር፣ ሃይማኖት፣ ፆታና ቀለምን አይለይም። በየት ኛውም ሁኔታ ውስጥ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ አስኳል ሃሳብ ወዳጅነትና መተሳሰብ መሆኑ ይታወቃል። በታሪክ ገጾች እንደሰፈረውም በሰው ልጅ ታሪክ ባጋጠሙ በጎም ሆኑ መጥፎ ክስተቶች ስፖርት በአጋርነት ተሳትፏል። ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ሰላምንና አንድነትን የሚሰብኩ እንደመሆናቸው በማህበራዊ፣ ፖለቲ ካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በመግባት ሚናቸውን ሲወጡም ኖረዋል። ...
https://www.press.et/Ama/?p=35130
የአትሌቲክሱ ዓለም ከወራት በኋላ የሚጠብቀው የዓለም ክብረወሰን
ስፖርት
June 27, 2020
13
የዓለም ታላላቅ ስፖርት መድረኮች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ምክንያት ለበርካታ ወራት ከቆሙበት ለመቀጠል ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ለመመልከት ተችሏል። የእግር ኳሱ ዓለም ታላላቅ ሊጎች በዝግ ስቴድየምም ቢሆን ጨዋታዎችን እያስቀጠሉ ካንቀላፉበት እየነቁ ይገኛሉ። በዚሁ ወረርሽኝ ሳቢያ ክፉኛ የተጎዳው የዓለም አትሌቲክስ እንቅስቃሴም ከጥቂት ወራት በኋላ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለመመለስ ከወዲሁ እንቅስቃሴ መጀመሩ ለዓለማችን አትሌቶች መልካም ዜና ሆኗል። በተለይም ...
https://www.press.et/Ama/?p=35203
የካፍ አካዳሚ ወደ አገልግሎት የመመለስ ተስፋ
ስፖርት
June 29, 2020
16
 የኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ለመቀጨጩ በርካታ ምክንያቶች ሊዘረዘሩ ይችላሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱና ትልቁ ምክንያት ሆኖ በተደጋጋሚ የሚነሳው ታዳጊዎችን ለማሰልጠን የሚያበቃ አካዳሚ አለመኖሩ ነው። በእርግጥ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በአገር አቀፍ ደረጃ በተገነቡ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላትና አካዳሚዎች የተለያዩ ስልጠናዎች ደረጃቸውን ጠብቀው በተገነቡ የማሰልጠኛ ማዕከላት መሰጠት ጀምረዋል። ይሁን እንጂ በተገነቡት ዘመናዊ የማሰልጠኛ ማዕከላት እግር ኳሱን ከቁልቁለት ጉዞ ታድጎ አንድ ርምጃ ወደ ፊት የሚያ...
https://www.press.et/Ama/?p=35323
«የስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር መዋል ትልቅ የፖለቲካ ድል ነው» – አቶ መስፍን ደሳለኝ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር
ሀገር አቀፍ ዜና
January 10, 2021
46
እፀገነት አክሊሉአዲስ አበባ፦ ለዚህ ሁሉ መሰሪነትና ለጥፋት ስትራቴጂው ህወሓት ጁንታው አገር እንዲያተራምስ በማድረግ የትግራይ ክልልም አሁን ለገባበት ምስቅልቅል የአቶ ስብሃት ነጋ መሰሪነት ትልቁን ቦታ የሚይዝ በመሆኑ የእርሳቸው በቁጥጥር ስር መዋል ትልቅ ፖለቲካዊ ድል መሆኑን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ። የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ መስፍን ደሳለኝ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት ፣አቶ ስብሃት ነጋ በውሸትና በወንጀል እንዲሁም ለራሳቸው ከሚገባው በላይ ዋጋ ሰ...
https://www.press.et/Ama/?p=39214
‹‹ለሱዳን ትንኮሳ ቸኩለን ምላሽ መስጠት አይገባንም›› -ዶ/ር ኢንጅነር ጥላሁን ኤርዱኖ የታሪክና የጂኦግራፊ መምህር የነበሩና በአሁኑ ጊዜ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የካርታ ምህንድስና መምህር
ሀገር አቀፍ ዜና
January 9, 2021
41
ማህሌት አብዱል አዲስ አበባ፡- ሱዳን በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ላደረገችው የመሬት ወረራ ትንኮሳ ፈጥኖ የኃይል ምላሽ መሥጠት እንደማይገባ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር ኢንጅነር ጥላሁን ኤርዱኖ አስታወቁ፡፡ዶ/ር ኢንጅነር ጥላሁን ኤርዱኖ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ለፈፀመው የመሬት ወረራ ቸኩሎ የኃይል ምላሽ መሥጠት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። በተለይም ውስጣዊውን ችግር በተሟላ ሁኔታ መፍታት ባልተቻለበት በዚህ ወቅት ወደ ኃይል ምላሹ መግባት አ...
https://www.press.et/Ama/?p=39157
ከግልባብ ፍሬ
መዝናኛ
December 30, 2019
15
አንድ ገበሬ ናቸው። በዘመናቸው ሮጠው ያሻቸውን አድረገዋል፤ አንሰተው ጥለው እንዳላለፉ ሁሉ ዕድሜ ገሰገሰና ጉልበታቸው ከዳቸው። ጊዜ ሲገፋ አቅማቸው ሲደክም እጅ ሰጡ። በወጣትነታቸው ሌላውን የጦሩት ያህል ተረኛ መሆን ግድ አላቸው። ግን ደግሞ እድለኛ አልነበሩምና ‹‹ጧሪዬ ይሆናል›› ብለው ተስፋ የጣሉበት አንድያ ልጃቸው እስር ቤት ይገባል። ለዚያው ለገበሬ ወሳኝ በሆነው የአዝመራ ወቅት። ይህ ወቅት ገበሬው አቅሙን አሟጦ የሚጠቀምበት ነውና ሽማግሌው መሬታቸው ጦሙ ማደሩን ሲረዱ ሀሳብ ገባቸው። እናም ለልጃ...
https://www.press.et/Ama/?p=24906
በድምጽ መስጫ ሳጥን የገባው ቀለበት
መዝናኛ
December 31, 2019
38
በሀገሮች መሪዎችን ለመምረጥ ምርጫ እንደሚካሄድ ይታወቃል። ለእዚህም ዜጎች ድምጻቸውን ይሰጣሉ ፤ ድምጽ በሚሰጥበት ስፍራ ምንም አይነት ሁከት ሊፈጠር አይገባም። በእዚህ አካባቢ ድምጽ በሚሰጡበት ወቅት ወርቅ፣ ገንዘብ ፣ወዘተ ቢጠፋ ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ መጮህ አይቻልም፤ ሊያስጠይቅ ይችላል። ወርቅን ያህል ጠፍቶ ታዲያ እንዴት ዝም ይባላል ትሉ ይሆናል። ያሎት አማራጭ ተረጋግቶ በሰከነ መንፈስ ችግሩን ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቆ ድምፁ እስኪጠናቀቅ በትእግስት መጠበቅ ነው።በፈረንጆቹ ባለፈው ታኅሳስ መባቻ በእን...
https://www.press.et/Ama/?p=24956
የአሰፋ ሳይንቲስት ውብ ወጎች
መዝናኛ
January 2, 2020
50
 ክፍል ሁለትባለፈው ሳምንት ክፍል አንድ ዝግጅታችን አሰፋ ሳይንቲስትን አስመልክቶ ጥቂት ወጎች ነበሩን። በጨለማው ዘመን የበሩት ፕሮፌሰር አሰፋ በፈረንሳይ ሀገር ኬሚስትሪ ያጠኑ ተመራማሪ ኢትዮጵያዊ ምሁር ነበሩ። እውቀቱ ገፋ ገፋ፤ ከመር ከመር ያደርጋቸው ነበር። ግን እኮ የቤተክህነቱንም ትምህርት ከግእዝ እስከ አራራይ የአማርኛውን ሰምና ወርቅ ጭምር ፈትለው ይገምዱት ነበር። ይሄ ምርምር የሚጠላውን ለማወቅ ጉጉት የሌለውን ደግሞ ‹‹ደናቁርት፤ ደነዝ፤ የሰው አጋሰስ፤ ሰው ነኝ›› ብሎ እኔ አሰፋ ሳንቲስት ...
https://www.press.et/Ama/?p=25046
የመጸዳጃ ቤት ቆይታን ለማሳጠር
መዝናኛ
December 31, 2019
31
ዘመናዊ መጸዳጃ በሀገራችን ብዙም አልተስፋፋም ቢባል ዋሾ አያሰኝም፤ ይህን እጥረት መንግሥትም በሚገባ ያውቀዋል። ከዚህ አኳያም የመጸዳጃ ቤት አገልግሎትን በከተማ ለማስፋፋት እየተሰራ ይገኛል። በከተሞች የህዝብ፣ የመንግሥትና የሆቴል መፀዳጃ ቤቶች በስፋት የሚስተዋሉ ሲሆን፣ የመኖሪያ ቤቶች መጸዳጃ ቤቶች በስፋት እየዘመኑ ናቸው። በገጠርም በዚሁ ላይ ግንዛቤ በማስጨበጥ ሰዎች ጤናቸውን ለመጠበቅ በመጸዳጃ ቤት እንዲገለገሉ ለማድረግ በተለይ በጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በኩል እየተሰራ ነው። በከተሞች በተለይ በ...
https://www.press.et/Ama/?p=24949
ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲባረሩ የአሜሪካ ሕገመንግሥት 25ኛው ማሻሻያ እየተጠቀሰ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
January 9, 2021
10
በኃይሉ አበራከትናንት ወዲያ የዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች የመንግሥት መቀመጫና የሁለቱ ምክር ቤቶች አዳራሾች የሚገኙበትን ግዙፉን የካፒቶል ሒል ህንጻን ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የሴኔት ምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲባረሩ እየጠየቁ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧልበዘገባው መሰረት የአሜሪካ ሕገመንግሥት 25ኛው አሜንድመንት ወይም ማሻሻያ እየተጠቀሰ ሲሆን፤ ይህ ማሻሻያ አንድ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት አካላዊ ወይም አእምሯዊ ጤና ከራቀው ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦታውን በተጠባባቂነት ተረክቦ አገሪቱን...
https://www.press.et/Ama/?p=39204
ወራጅ
መዝናኛ
January 6, 2020
16
ረዳትና ሹፌር የታክሲ የአውቶቡስ ወይም የሌላ መጓጓዣ መሪ ጠምዛዥና መላሽ የበር በረኛ አሳላፊ ናቸው። መገኛቸው እርግጥ እዚህ ፅሁፍ ላይ የወከሉት የወሬያችን ማጣፈጫ የጉዛችን ትዝብት መነሻና ፈጣሪዎች ናቸው። አብዝተው እኛነታችንን ያሳዩናል፤ አግዝፈው ማንነታችንን በእነርሱ ውስጥ ያጎሉልናል። እርግጥ ረዳትና ሹፌር መነሻቸው ማህበረሰብ መድረሻውም ህዝብ ስለሆነ እኛን በደንብ ያውቁናል። እኛም እነርሱ የሚያውቁንን ያህል ባናውቃቸውም በምልከታና በውሏችን በግምትና በሚናገሩት የሆነ ቦታ ላይ መመደቢያ እውቀት ...
https://www.press.et/Ama/?p=25216
እንዲህ ቢባል ምን ችግር አለው?
መዝናኛ
January 5, 2020
37
በአውሮፓውቷ አገር ኖርዌይ ለትምህርት ከአንድ ዓመት በላይ ቆይቶ የመጣ አንድ ጓደኛዬ የነገረኝ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ በነገራችን ላይ ውጭ አገር ቆይቶ የመጣ ሰው ሳገኝ ቀድሜ የምጠይቀው የህዝቡን ሥነ ልቦና ነው፡፡ እንዲያው ይሄ ርዕስ በርዕስ መነቋቆር የሰለጠኑት አገሮችም አለ ይሆን የሚለውን ለማወቅ ስለምፈልግ፡፡ እናም ይሄ ጓደኛዬ የነገረኝ ነገር በሀገረ ኖርዌይ ያስተዋለው ህዝቡ ሐሜትና መነቋቆር ጉዳዩ እንዳልሆነ ነው፡፡ አለ ከተባለም አድናቆት ነው፡፡ ከከንቲባው ጀምሮ በከተማዋ ውስጥ ያለ የትኛውም ባለ...
https://www.press.et/Ama/?p=25183
ኢትዮጵያ በአፍሪካ መድረክ ተሳታፊ ክለብ የሌላት ብቸኛ አገር ሆናለች
ስፖርት
June 18, 2020
20
የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ እንደሌሎቹ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኩነቶች ሁሉ የዓለምን ስፖርት ውጥንቅጡን አውጥቶታል፡፡ ታላላቅ የዓለማችን ሊጎች የሚይዙትን የሚጨብጡትን አጥተው ከርመዋል፡፡ ከሳምንት በፊት አንስቶ ግን የዓለማችን ታላላቅ ሊጎች ወደ ውድድር እየተመለሱ ስፖርቱም እያገገመ ይመስላል፡፡ ወትሮውንም ችግር የማያጣት አፍሪካ የዚህ ችግር ገፈት ቀማሽ መሆኗ ነገሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚያደርግባት ቀድሞም የተገመተ ቢሆንም የአንዳንድ አገራት የእግር ኳስ መሪዎች አስቸጋ...
https://www.press.et/Ama/?p=34598
የለንደን ማራቶን ሊሰረዝ ይችላል
ስፖርት
June 18, 2020
17
በቀጣዩ መስከረም ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት ‹‹የግሬት ኖርዝ ረን›› ግማሽ ማራቶን ውድድር መሰረዙን ተከትሎ ጥቅምት ላይ እንደሚካሄድ የተነገረው የለንደን ማራቶንም ሊሰረዝ እንደሚችል ጥርጣሬ ፈጥሯል:: በእንግሊዝ አገር ከሚካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች መካከል ትልቁን ስፍራ የሚይዙት ሁለቱ የማራቶንና ግማሽ ማራቶን ውድድሮች ከኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ስጋት ጋር በተያያዘ ቀደም ብሎ ከሚካሄዱበት ወቅት እንዲራዘሙ ተደርጎ በቀጣዩ መስከረምና ጥቅምት ወር ሊካሄዱ ቀጠሮ ተይዞ ነበር፡፡ ዘንድሮ አርባ...
https://www.press.et/Ama/?p=34601
በ «አረንጓዴ አሻራ» መርሃ ግብሩ የስፖርት ቤተሰቡ አሻራ
ስፖርት
June 19, 2020
26
በኢትዮጵያ የደን ልማት ለማጎልበት የሚያስችለው የዘንድሮ «አረንጓዴ አሻራ» መርሃ ግብር ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መርሃ ግብሩን ሲያስጀምሩ፤ በዘንድሮ ዓመት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አምስት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ መያዙን ተናግረዋል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ችግኞችን እንዲተክል «አሻራችንን በማኖር ለኢትዮጵያ አረንጓዴ ምንጣፍ እንዘርጋ» ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን አስጀምረዋ...
https://www.press.et/Ama/?p=34666
ላሚን ዲያክ የአራት ዓመት እስር እንዲፈረድባቸው ተጠየቀ
ስፖርት
June 20, 2020
18
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፓሪስ ውስጥ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዚዳንት ላሚን ዲያክ አራት ዓመት የእስር ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ተጠየቀ፡፡ የሰማንያ ሰባት ዓመቱ አዛውንት ላይ ክስ የመሰረቱት የፈረንሳይ አቃቤ የላሚን ዲያክ ልጅ በሆኑት ፓፓ ማሳታ ዲያክ እንዲሁም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የቀድሞ የማርኬቲንግ አማካሪ ላይ የአምስት ዓመት እስርና የአምስት መቶ ሺ ፓውንድ ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ለፍርድ ቤት ጥያቄ እንዳቀረቡ ሮይ...
https://www.press.et/Ama/?p=34738