text
stringlengths 4
267
|
|---|
ምክንያቱም መጀመሪያ እውቅና የሰጣቸው ሰዎች የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወስኗል፤ ይኸውም ልጁ ከብዙ ወንድሞች መካከል በኩር እንዲሆን ነው።
|
ከዚህም በተጨማሪ አስቀድሞ የወሰናቸውን እነዚህን ጠራቸው፤ የጠራቸውን እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው። በመጨረሻም ያጸደቃቸውን እነዚህን አከበራቸው።
|
እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንበል? አምላክ ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?
|
ለገዛ ልጁ እንኳ ያልሳሳው፣ ከዚህ ይልቅ ለእኛ ለሁላችን አሳልፎ የሰጠው አምላክ፣ ከእሱ ጋር አብሮ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ እንዴት በደግነት አይሰጠንም?
|
አምላክ የመረጣቸውን ማን ሊከሳቸው ይችላል? ምክንያቱም የሚያጸድቃቸው አምላክ ራሱ ነው።
|
እነሱን የሚኮንን ማን ነው? ምክንያቱም የሞተው ብሎም ከሞት የተነሳውና በአምላክ ቀኝ የተቀመጠው እንዲሁም ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
|
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ወይስ ጭንቀት ወይስ ስደት ወይስ ረሃብ ወይስ ራቁትነት ወይስ አደጋ ወይስ ሰይፍ?
|
ይህም “ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ሞትን እንጋፈጣለን፤ እንደ እርድ በጎችም ተቆጠርን” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
|
ከዚህ ይልቅ በወደደን በእሱ አማካኝነት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ሙሉ በሙሉ በድል አድራጊነት እንወጣለን።
|
ምክንያቱም ሞትም ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፣ መላእክትም ቢሆኑ፣ መንግሥታትም ቢሆኑ፣ አሁን ያሉት ነገሮችም ቢሆኑ፣ ወደፊት የሚመጡት ነገሮችም ቢሆኑ፣ ማንኛውም ኃይል ቢሆን፣
|
ከፍታም ቢሆን፣ ዝቅታም ቢሆን፣ ሌላ ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ከተገለጸው የአምላክ ፍቅር ሊለየን እንደማይችል ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነኝ።
|
እኔ የክርስቶስን አርዓያ እንደምከተል እናንተም የእኔን አርዓያ ተከተሉ።
|
በሁሉም ነገር ስለምታስቡኝና ለእናንተ ያስተላለፍኳቸውን ወጎች አጥብቃችሁ ስለያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።
|
ይሁንና የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፣ የሴትም ራስ ወንድ፣ የክርስቶስ ራስ ደግሞ አምላክ እንደሆነ እንድታውቁ እወዳለሁ።
|
ራሱን ሸፍኖ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ ሁሉ የእሱን ራስ ያዋርዳል፤
|
ራሷን ሳትሸፍን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ደግሞ የእሷን ራስ ታዋርዳለች፤ እንዲህ የምታደርግ ሴት ራሷን እንደተላጨች ሴት ትቆጠራለች።
|
አንዲት ሴት ራሷን የማትሸፍን ከሆነ ፀጉሯን ትቆረጥ፤ ፀጉሯን መቆረጧ ወይም መላጨቷ የሚያሳፍራት ከሆነ ግን ትሸፈን።
|
ወንድ የአምላክ አምሳልና ክብር ስለሆነ ራሱን መሸፈን የለበትም፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት።
|
ሴት ከወንድ ተገኘች እንጂ ወንድ ከሴት አልተገኘምና።
|
ከዚህም በተጨማሪ ሴት ለወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ለሴት አልተፈጠረም።
|
ከዚህ የተነሳም ሆነ ለመላእክት ሲባል ሴት በሥልጣን ሥር መሆኗን የሚያሳይ ምልክት በራሷ ላይ ታድርግ።
|
ይሁንና በጌታ ተከታዮች ዘንድ ሴት ያለወንድ አትኖርም፤ ወንድም ያለሴት አይኖርም።
|
ሴት ከወንድ እንደተገኘች ሁሉ ወንድም የተገኘው በሴት አማካኝነት ነውና፤ ሆኖም ሁሉም ነገሮች የተገኙት ከአምላክ ነው።
|
እስቲ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ፦ ሴት ሳትሸፈን ወደ አምላክ ብትጸልይ ተገቢ ይሆናል?
|
ወንድ ፀጉሩን ቢያስረዝም ውርደት እንደሚሆንበት ተፈጥሮ ራሱ እንኳ አያስተምራችሁም?
|
ሴት ግን ፀጉሯን ብታስረዝም ለእሷ ክብር አይደለም? ፀጉሯ የተሰጣት በመሸፈኛ ምትክ ነውና።
|
ይሁን እንጂ ማንም ሰው ሌላ ልማድ መከተል አለብን በሚል ለመከራከር ቢፈልግ እኛም ሆን የአምላክ ጉባኤ ከዚህ የተለየ ልማድ የለንም።
|
ሆኖም ስብሰባችሁ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እነዚህን መመሪያዎች ስሰጣችሁ ላመሰግናችሁ አልፈልግም።
|
በመጀመሪያ ደረጃ፣ በጉባኤ በምትሰበሰቡበት ጊዜ በመካከላችሁ ክፍፍል እንዳለ እሰማለሁ፤ ደግሞም ይህ በተወሰነ መጠን እውነትነት እንዳለው አምናለሁ።
|
በዚህ ሁኔታ በእናንተ መካከል ኑፋቄዎች ብቅ ማለታቸው አይቀርም፤ ይህም መሆኑ ከእናንተ መካከል ተቀባይነት የሚያገኙት ሰዎች ተለይተው እንዲታወቁ ያስችላል።
|
አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ የሚኖረው ሁኔታ የጌታ ራትን በአግባቡ ለማክበር የሚያስችል አይደለም።
|
የጌታ ራትን በምትበሉበት ጊዜ አንዳንዶች አስቀድመው የራሳቸውን ራት ስለሚበሉ አንዱ ይራባል ሌላው ደግሞ ይሰክራል።
|
የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁም? ወይስ የአምላክን ጉባኤ በመናቅ ምንም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁ? እንግዲህ ምን ልበላችሁ? ላመስግናችሁ? በዚህ ነገርስ አላመሰግናችሁም።
|
እኔ ከጌታ የተቀበልኩትን ለእናንተ አስተላልፌአለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት ሌሊት ቂጣ አንስቶ
|
ካመሰገነ በኋላ ቆርሶ “ይህ ስለ እናንተ የሚሰጠውን ሥጋዬን ያመለክታል። ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።
|
በተጨማሪም ራት ከበሉ በኋላ ጽዋውን አንስቶ ልክ እንደዚሁ አደረገ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ጽዋ በደሜ አማካኝነት የሚመሠረተውን አዲሱን ቃል ኪዳን ያመለክታል። ከዚህ ጽዋ በጠጣችሁ ቁጥር ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት።”
|
ይህን ቂጣ በበላችሁና ከዚህ ጽዋ በጠጣችሁ ቁጥር ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ሞቱን ታውጃላችሁ።
|
እንግዲህ የማይገባው ሆኖ ሳለ ከቂጣው የሚበላ ወይም ከጌታ ጽዋ የሚጠጣ ከጌታ አካልና ደም ጋር በተያያዘ ተጠያቂ ይሆናል።
|
አንድ ሰው የሚገባው እንደሆነ ለማወቅ በቅድሚያ ራሱን ይመርምር፤ ቂጣውን መብላትና ጽዋውን መጠጣት የሚችለው ይህን ካደረገ ብቻ ነው።
|
ምክንያቱም አካሉ ምን ትርጉም እንዳለው ሳይገነዘብ የሚበላና የሚጠጣ በራሱ ላይ ፍርድ የሚያመጣበትን ነገር መብላትና መጠጣት ይሆንበታል።
|
ከእናንተ መካከል ብዙዎቹ የተዳከሙትና ታማሚ የሆኑት እንዲሁም ጥቂት የማይባሉት በሞት ያንቀላፉት በዚህ ምክንያት ነው።
|
ሆኖም ራሳችንን መርምረን ብናውቅ ኖሮ ባልተፈረደብን ነበር።
|
ይሁን እንጂ በሚፈረድብን ጊዜ፣ ከዓለም ጋር አብረን እንዳንኮነን ሲል ይሖዋ ይገሥጸናል።
|
ስለዚህ ወንድሞቼ፣ ይህን ራት ለመብላት በምትሰበሰቡበት ጊዜ እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ።
|
የምትሰበሰቡት ለፍርድ እንዳይሆን የራበው ሰው ካለ እዚያው ቤቱ ይብላ። የቀሩትን ጉዳዮች ግን ስመጣ አስተካክላለሁ።
|
በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ እንዲሆን ከተጠራው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከሶስቴንስ፣
|
በቆሮንቶስ ለሚገኘው የአምላክ ጉባኤ ይኸውም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባላችሁ አንድነት ለተቀደሳችሁ፣ እንዲሁም የእነሱም ሆነ የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ሆነው ከሚጠሩ ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠራችሁ፦
|
ከአባታችን ከአምላክና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
|
በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ በሰጠው ጸጋ የተነሳ አምላኬን ሁልጊዜ ስለ እናንተ አመሰግናለሁ፤
|
ምክንያቱም በሁሉም ነገር ይኸውም በመናገር ችሎታ ሁሉና በእውቀት ሁሉ በክርስቶስ በልጽጋችኋል፤
|
ደግሞም ስለ ክርስቶስ የተሰጠው ምሥክርነት በእናንተ መካከል በሚገባ ሥር ሰዷል፤
|
ስለዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጉጉት ስትጠባበቁ ማንኛውም ስጦታ ፈጽሞ አይጎድልባችሁም።
|
በተጨማሪም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ከማንኛውም ክስ ነፃ መሆን እንድትችሉ እስከ መጨረሻው ያጸናችኋል።
|
ከልጁ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ የጠራችሁ አምላክ ታማኝ ነው።
|
እንግዲህ ወንድሞች፣ ሁላችሁም ንግግራችሁ አንድ እንዲሆንና በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳይኖር፣ ከዚህ ይልቅ በአስተሳሰብም ሆነ በዓላማ ፍጹም አንድነት እንዲኖራችሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አጥብቄ አሳስባችኋለሁ።
|
ወንድሞቼ ሆይ፣ የቀሎኤ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አንዳንዶች በመካከላችሁ አለመግባባት እንዳለ ነግረውኛል።
|
ይኸውም እያንዳንዳችሁ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፣” “እኔ ግን የአጵሎስ ነኝ፣” “እኔ ደግሞ የኬፋ ነኝ፣” “እኔ የክርስቶስ ነኝ” ትላላችሁ።
|
ታዲያ የክርስቶስ ጉባኤ ተከፋፍሏል ማለት ነው? ጳውሎስ ለእናንተ ሲል በእንጨት ላይ ተሰቅሏል እንዴ? ወይስ የተጠመቃችሁት በጳውሎስ ስም ነው?
|
ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በስተቀር ከእናንተ አንዳችሁንም ባለማጥመቄ አምላክን አመሰግናለሁ፤
|
በመሆኑም ከእናንተ መካከል በእኔ ስም እንደተጠመቀ ሊናገር የሚችል ማንም የለም።
|
እርግጥ የእስጢፋናስን ቤተሰብም አጥምቄአለሁ። ከእነዚህ ሌላ ግን ያጠመቅኩት ሰው መኖሩን አላስታውስም።
|
ክርስቶስ የላከኝ እንዳጠምቅ ሳይሆን ምሥራቹን እንዳውጅ ነው፤ ደግሞም የክርስቶስ የመከራ እንጨት ከንቱ እንዳይሆን ምሥራቹን የማውጀው በንግግር ጥበብ አይደለም።
|
ስለ መከራው እንጨት የሚነገረው መልእክት ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ሞኝነት፣ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ላለነው ለእኛ ግን የአምላክ ኃይል መገለጫ ነው።
|
“የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የሊቃውንትንም ማስተዋል ወዲያ እጥላለሁ” ተብሎ ተጽፏልና።
|
የዚህ ሥርዓት ጥበበኞች የት አሉ? ጸሐፍትስ የት አሉ? ተሟጋቾችስ የት አሉ? አምላክ የዓለምን ጥበብ ሞኝነት አላደረገም?
|
ዓለም በራሱ ጥበብ አምላክን ሊያውቀው ስላልቻለ አምላክ በጥበቡ፣ እንደ ሞኝነት በሚቆጠረውና እየተሰበከ ባለው መልእክት አማካኝነት የሚያምኑትን ሰዎች ለማዳን መርጧል።
|
አይሁዳውያን ተአምራዊ ምልክቶች ማየት ይፈልጋሉ፤ ግሪካውያን ደግሞ ጥበብን ይሻሉ፤
|
እኛ ግን በእንጨት ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁዳውያን መሰናክል ለአሕዛብ ደግሞ ሞኝነት ነው።
|
ይሁን እንጂ ክርስቶስ ለተጠሩት፣ ለአይሁዳውያንም ሆነ ለግሪካውያን የአምላክ ኃይልና የአምላክ ጥበብ ነው።
|
ምክንያቱም የአምላክ ሞኝነት እንደሆነ ተደርጎ የሚታሰበው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይበልጣል፤ የአምላክ ድክመት እንደሆነ ተደርጎ የሚታሰበው ነገር ደግሞ ከሰዎች ብርታት ይበልጣል።
|
ወንድሞች፣ ከራሳችሁ ሁኔታ መረዳት እንደምትችሉት በሰብዓዊ አመለካከት ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፣ ኃያላን የሆኑ ብዙዎች እንዲሁም ከትልቅ ቤተሰብ የተወለዱ ብዙዎች አልተጠሩም፤
|
ከዚህ ይልቅ አምላክ ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱውንም ነገር ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤
|
አምላክ በሰዎች ዘንድ ትልቅ ግምት የሚሰጠውን ነገር ከንቱ ያደርግ ዘንድ በዚህ ዓለም ዝቅ ተደርጎ የሚታየውንና የተናቀውን ነገር ይኸውም ከንቱ መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ፤
|
ይህን ያደረገው ማንም ሰው በአምላክ ፊት እንዳይኩራራ ነው።
|
ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ሊኖራችሁ የቻለው በእሱ ምክንያት ነው፤ ክርስቶስ ደግሞ ለእኛ ከአምላክ የመጣ ጥበብ፣ ጽድቅና ቅድስና ሆኖልናል፤ እንዲሁም በቤዛው ነፃ አውጥቶናል፤
|
ይህም “የሚኩራራ በይሖዋ ይኩራራ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
|
በደብዳቤያችሁ ላይ ያነሳችኋቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ፣ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ባይነካ ይሻላል፤
|
ይሁንና የፆታ ብልግና ስለተስፋፋ እያንዳንዱ ወንድ የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዷም ሴት የራሷ ባል ይኑራት።
|
ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ ሚስትም ብትሆን ለባሏ እንደዚሁ ታድርግለት።
|
ሚስት በራሷ አካል ላይ ሥልጣን የላትም፤ ሥልጣን ያለው ባሏ ነው፤ በተመሳሳይም ባል በራሱ አካል ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሥልጣን ያላት ሚስቱ ናት።
|
አንዳችሁ ለሌላው የሚገባውን አትከልክሉ፤ እንዲህ ማድረግ የምትችሉት በጋራ ስምምነት የተወሰነ ጊዜ ለጸሎት ለማዋል ካሰባችሁ ብቻ ነው፤ ደግሞም ራሳችሁን መግዛት አቅቷችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ።
|
ይሁን እንጂ ይህን ያልኩት እንዲህ ማድረግ እንደሚቻል ለመግለጽ ነው እንጂ ለማዘዝ አይደለም።
|
ይሁንና ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን ደስ ባለኝ ነበር። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ከአምላክ ያገኘው የራሱ ስጦታ አለው፤ አንዱ አንድ ዓይነት ስጦታ ሲኖረው ሌላው ደግሞ ሌላ ዓይነት ስጦታ አለው።
|
ሆኖም ላላገቡና መበለት ለሆኑ እንደ እኔ ሆነው ቢኖሩ የተሻለ ነው እላለሁ።
|
ራሳቸውን መግዛት ካቃታቸው ግን ያግቡ፤ በፍትወት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና።
|
ላገቡት ሰዎች ይህን መመሪያ እሰጣለሁ፤ ይህ መመሪያ የጌታ እንጂ የእኔ አይደለም፤ ሚስት ከባሏ አትለያይ።
|
ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባሏ ጋር ትታረቅ፤ ባልም ሚስቱን መተው የለበትም።
|
ለሌሎች ደግሞ እንዲህ እላለሁ፤ ይህን የምለው እኔ እንጂ ጌታ አይደለም፦ አንድ ወንድም አማኝ ያልሆነች ሚስት ካለችውና አብራው ለመኖር ከተስማማች አይተዋት፤
|
እንዲሁም አንዲት ሴት አማኝ ያልሆነ ባል ካላትና ባሏ አብሯት ለመኖር ከተስማማ አትተወው።
|
አማኝ ያልሆነ ባል ከሚስቱ ጋር ባለው ዝምድና የተነሳ ተቀድሷልና፤ አማኝ ያልሆነች ሚስትም ከወንድም ጋር ባላት ዝምድና የተነሳ ተቀድሳለች፤ እንዲህ ባይሆን ኖሮ ልጆቻችሁ ርኩሳን በሆኑ ነበር፤ አሁን ግን ቅዱሳን ናቸው።
|
ይሁንና አማኝ ያልሆነው ወገን ለመለየት ከመረጠ ይለይ፤ እንዲህ ያለ ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ አንድ ወንድም ወይም አንዲት እህት ምንም ዓይነት ግዴታ የለባቸውም፤ አምላክ የጠራችሁ ለሰላም ነውና።
|
አንቺ ሚስት፣ ባልሽን ታድኚው እንደሆነ ምን ታውቂያለሽ? ወይስ አንተ ባል፣ ሚስትህን ታድን እንደሆነ ምን ታውቃለህ?
|
ያም ሆነ ይህ እያንዳንዱ ሰው ይሖዋ በሰጠው ድርሻና አምላክ ሲጠራው በነበረበት ሁኔታ ይመላለስ። ለጉባኤዎችም ሁሉ ይህን መመሪያ እሰጣለሁ።
|
አንድ ሰው የተጠራው ተገርዞ እያለ ነው? እንዳልተገረዘ ሰው አይሁን። አንድ ሰው የተጠራው ሳይገረዝ ነው? ከሆነ አይገረዝ።
|
መገረዝ ምንም ማለት አይደለም፤ አለመገረዝም ቢሆን ምንም ማለት አይደለም፤ ዋናው ነገር የአምላክን ትእዛዛት መጠበቅ ነው።
|
እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ጊዜ የነበረበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በዚያው ይቀጥል።
|
የተጠራኸው ባሪያ እያለህ ነው? ይሄ አያስጨንቅህ፤ ሆኖም ነፃ መውጣት የምትችል ከሆነ አጋጣሚውን ተጠቀምበት።
|
ባሪያ እያለ የተጠራ ማንኛውም የጌታ ደቀ መዝሙር ነፃ የወጣ የጌታ ሰው ነውና፤ በተመሳሳይም ነፃ እያለ የተጠራ ሰው የክርስቶስ ባሪያ ነው።
|
በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያ መሆናችሁ ይብቃ።
|
ወንድሞች፣ እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ጊዜ የነበረበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በአምላክ ፊት በዚያው ሁኔታ ይቀጥል።
|
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.