text stringlengths 4 267 |
|---|
ከዚያም ሙሴ በትሮቹን በሙሉ ከይሖዋ ፊት አውጥቶ ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ አመጣቸው። እነሱም በትሮቹን አዩ፤ እያንዳንዱም ሰው የራሱን በትር ወሰደ። |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለዓመፀኞቹ ልጆች ምልክት ሆኖ እንዲያገለግል የአሮንን በትር መልሰህ ምሥክሩ ፊት አስቀምጠው፤ ይህም የሚሆነው በእኔ ላይ ማጉረምረማቸውን እንዲተዉና እንዳይሞቱ ነው።” |
ሙሴም ወዲያውኑ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ። ልክ እንደተባለውም አደረገ። |
ከዚያም እስራኤላውያን ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ መሞታችን ነው፤ በቃ ማለቃችን ነው፤ ሁላችንም ማለቃችን ነው! |
ወደ ይሖዋ የማደሪያ ድንኳን የሚቀርብ ማንኛውም ሰው ይሞታል! በቃ በዚህ መንገድ ሁላችንም መሞታችን ነው?” |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“ለእስራኤላውያን ምድያማውያንን ተበቀልላቸው። ከዚያ በኋላ ወደ ወገኖችህ ትሰበሰባለህ።” |
በመሆኑም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ በምድያም ላይ የሚወስደውን የበቀል እርምጃ ለማስፈጸም ከምድያም ጋር ለሚደረገው ጦርነት ከመካከላችሁ ወንዶችን አስታጥቁ። |
ከሁሉም የእስራኤል ነገድ ከእያንዳንዱ 1,000 ወንዶችን ወደ ጦርነቱ ላኩ።” |
ስለዚህ በሺዎች ከሚቆጠሩት እስራኤላውያን መካከል ከአንድ ነገድ 1,000 ወንዶች ተመርጠው በአጠቃላይ 12,000 ወንዶች ለጦርነቱ ታጠቁ። |
ከዚያም ሙሴ ከየነገዱ የተውጣጡትን አንድ አንድ ሺህ ወንዶች ወደ ጦርነቱ ላካቸው፤ ከእነሱም ጋር የሠራዊቱ ካህን የሆነውን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሃስን ላከው፤ ቅዱስ የሆኑት ዕቃዎችና በጦርነት ጊዜ የሚነፉት መለከቶች በእሱ እጅ ነበሩ። |
እነሱም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት በምድያም ላይ ጦርነት ከፈቱ፤ ወንዶቹንም ሁሉ ገደሉ። |
ከተገደሉትም መካከል ኤዊ፣ ራቄም፣ ጹር፣ ሁር እና ረባ የተባሉት አምስቱ የምድያም ነገሥታት ይገኙበታል። እንዲሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉ። |
ሆኖም እስራኤላውያን የምድያምን ሴቶችና ትናንሽ ልጆች ማርከው ወሰዱ። በተጨማሪም የቤት እንስሶቻቸውን፣ ከብቶቻቸውን እንዲሁም ንብረታቸውን በሙሉ ዘረፉ። |
ይኖሩባቸው የነበሩትን ከተሞችና ሰፈሮቻቸውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። |
ሰውም ሆነ እንስሳ የማረኩትንና የዘረፉትን በሙሉ ወሰዱ። |
ከዚያም የማረኳቸውን ሰዎችና የዘረፉትን ንብረት በኢያሪኮ፣ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ ወደሚገኘው ሰፈር ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛርና ወደ እስራኤል ማኅበረሰብ አመጡ። |
ከዚያም ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛርና የማኅበረሰቡ አለቆች በሙሉ ከእነሱ ጋር ለመገናኘት ከሰፈሩ ውጭ ወጡ። |
ሆኖም ሙሴ ከጦርነቱ በተመለሱት የሠራዊቱ አዛዦች ይኸውም በሺህ አለቆቹና በመቶ አለቆቹ ላይ ተቆጣ። |
እንዲህም አላቸው፦ “ሴቶቹን በሙሉ እንዴት ሳትገድሉ ተዋችኋቸው? |
የበለዓምን ቃል ሰምተው እስራኤላውያን በፌጎር በተከሰተው ነገር የተነሳ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት እንዲፈጽሙ ያሳቷቸውና በዚህም ምክንያት በይሖዋ ማኅበረሰብ ላይ መቅሰፍት እንዲመጣ ያደረጉት እነሱ አይደሉም? |
በሉ አሁን ከልጆች መካከል ወንዶቹን በሙሉ እንዲሁም ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት የፈጸሙ ሴቶችን በሙሉ ግደሉ። |
ሆኖም ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁትን ወጣት ሴቶች ሁሉ በሕይወት እንዲተርፉ ልታደርጉ ትችላላችሁ። |
እናንተም ለሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጭ ቆዩ። ከመካከላችሁ ሰው የገደለም ሆነ የሞተ ሰው የነካ ማንኛውም ሰው በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፤ እናንተም ሆናችሁ የማረካችኋቸው ሰዎች ራሳችሁን አንጹ። |
ማንኛውንም ልብስ፣ ማንኛውንም ከቆዳ የተሠራ ነገር፣ ማንኛውንም ከፍየል ፀጉር የተሠራ ነገር እንዲሁም ማንኛውንም ከእንጨት የተሠራ ነገር ከኃጢአት አንጹ።” |
ከዚያም ካህኑ አልዓዛር ወደ ጦርነቱ ሄደው የነበሩትን ወንዶች እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ ሙሴን ያዘዘው የሕጉ ደንብ ይህ ነው፦ |
‘ወርቁን፣ ብሩን፣ መዳቡን፣ ብረቱን፣ ቆርቆሮውንና እርሳሱን ብቻ |
ይኸውም እሳትን መቋቋም የሚችለውን ማንኛውንም ነገር በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አድርጉ፤ እሱም ንጹሕ ይሆናል። ያም ሆኖ ለማንጻት በሚያገለግለው ውኃ መንጻት አለበት። እሳትን መቋቋም የማይችሉ ነገሮችን በሙሉ በውኃ ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ አለባችሁ። |
በሰባተኛውም ቀን ልብሶቻችሁን እጠቡ፤ ንጹሕም ሁኑ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ትችላላችሁ።’” |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“የምርኮውን ብዛት ቁጠር፤ ሰዎችም ሆኑ እንስሳት የተማረኩትን ሁሉ ቁጠር፤ ይህንም ከካህኑ ከአልዓዛርና ከማኅበረሰቡ የአባቶች ቤት መሪዎች ጋር አድርግ። |
ምርኮውንም በጦርነቱ ለተካፈሉት ተዋጊዎችና ለቀረው ማኅበረሰብ ሁሉ እንዲከፋፈል ለሁለት ክፈለው። |
ለይሖዋም ግብር እንዲሆን በጦርነቱ ከተካፈሉት ተዋጊዎች ላይ ከሰውም ሆነ ከከብት፣ ከአህያም ሆነ ከመንጋ ከ500 አንድ ነፍስ ውሰድ። |
ለእነሱ ተከፍሎ ከተሰጣቸው ድርሻ ላይ ወስዳችሁ ለካህኑ ለአልዓዛር የይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ስጡት። |
ለእስራኤላውያን ተከፍሎ ከተሰጣቸው ድርሻ ላይ ደግሞ ከሰውም ሆነ ከከብት፣ ከአህያም ሆነ ከመንጋ እንዲሁም ከማንኛውም እንስሳ ከ50 አንድ ወስደህ ከይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ጋር በተያያዘ ያለባቸውን ኃላፊነት ለሚወጡት ለሌዋውያኑ ስጥ።” |
በመሆኑም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። |
በውጊያው የተካፈሉት ሰዎች ማርከው ካመጡት ምርኮ ውስጥ የቀሩት 675,000 በጎች፣ |
72,000 ከብቶች |
እንዲሁም 61,000 አህዮች ነበሩ። |
ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁት ሴቶች በአጠቃላይ 32,000 ነበሩ። |
በውጊያው ለተሳተፉት ተከፍሎ የተሰጣቸው ድርሻ በአጠቃላይ 337,500 በግ ነበር። |
ከበጎቹ መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 675 ነበሩ። |
ከብቶቹ ደግሞ 36,000 ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 72 ነበሩ። |
አህዮቹ 30,500 ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 61 ነበሩ። |
ሰዎቹ ደግሞ 16,000 ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 32 ሰዎች ነበሩ። |
ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ግብሩን ለይሖዋ መዋጮ እንዲሆን ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው። |
ሙሴም በጦርነቱ የተካፈሉት ሰዎች ካመጡት ላይ ከፍሎ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ድርሻ ይህ ነው፦ |
ሙሴ ከፍሎ የሰጣቸው ድርሻ 337,500 በግ፣ |
36,000 ከብት፣ |
30,500 አህያ |
እንዲሁም 16,000 ሰው ነበር። |
ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን ተከፍሎ ከተሰጣቸው ድርሻ ላይ ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ከ50 አንድ ወስዶ በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለሚወጡት ሌዋውያን ሰጠ። |
ከዚያም በሠራዊቱ ክፍሎች ውስጥ የተሾሙት አዛዦች ይኸውም የሺህ አለቆቹና የመቶ አለቆቹ ወደ ሙሴ ቀርበው |
እንዲህ አሉት፦ “እኛ አገልጋዮችህ በሥራችን ያሉትን ተዋጊዎች ቆጥረናል፤ ከመካከላችን አንድም የጎደለ የለም። |
ስለዚህ እያንዳንዳችን በይሖዋ ፊት ለራሳችን ማስተሰረያ እንዲሆኑልን፣ ያገኘናቸውን ነገሮች ይኸውም የወርቅ ጌጣጌጦችን፣ የእግር አልቦዎችን፣ የእጅ አምባሮችን፣ የማኅተም ቀለበቶችን፣ የጆሮ ጉትቻዎችንና ሌሎች ጌጣጌጦችን ለይሖዋ መባ አድርገን ማቅረብ እንፈልጋለን።” |
በመሆኑም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁን ይኸውም ጌጣጌጡን ሁሉ ተቀበሏቸው። |
ከሺህ አለቆቹና ከመቶ አለቆቹ ተቀብለው ለይሖዋ መዋጮ እንዲሆን የሰጡት ወርቅ በጠቅላላ 16,750 ሰቅል ሆነ። |
በሠራዊቱ ውስጥ ያሉት ወንዶች እያንዳንዳቸው ከምርኮው ላይ ድርሻቸውን ወስደው ነበር። |
ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁን ከሺህ አለቆቹና ከመቶ አለቆቹ ተቀብለው በይሖዋ ፊት ለእስራኤል ሕዝብ ማስታወሻ እንዲሆን ወደ መገናኛ ድንኳኑ አስገቡት። |
ይሖዋ ሙሴንና አሮንን በድጋሚ እንዲህ አላቸው፦ |
“ይሖዋ ያዘዘው የሕጉ ደንብ ይህ ነው፦ ‘እንከን የሌለባትና ቀንበር ተጭኖባት የማታውቅ በጥሩ ሁኔታ ላይ የምትገኝ አንዲት ቀይ ላም እንዲያመጡልህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። |
ለካህኑ ለአልዓዛርም ስጡት፤ እሱም ከሰፈሩ ውጭ ይወስዳትና በፊቱ ትታረዳለች። |
ከዚያም ካህኑ አልዓዛር ከደሙ ላይ በጣቱ ወስዶ ደሙን በቀጥታ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። |
ከዚያም ላሟ ዓይኑ እያየ ትቃጠላለች። ቆዳዋ፣ ሥጋዋና ደሟ ከፈርሷ ጋር አብሮ ይቃጠላል። |
ካህኑም የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ሂሶጵና ደማቅ ቀይ ማግ ወስዶ ላሟ የምትቃጠልበት እሳት ውስጥ ይጨምራል። |
ከዚያም ካህኑ ልብሶቹን በውኃ ያጥባል፤ ገላውንም ይታጠባል፤ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል፤ ሆኖም ካህኑ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። |
“‘ላሟን ያቃጠለውም ሰው ልብሶቹን በውኃ ያጥባል፤ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። |
“‘ንጹሕ የሆነ ሰው የላሟን አመድ አፍሶ ከሰፈሩ ውጭ ባለ ንጹሕ ቦታ ያጠራቅመዋል፤ የእስራኤል ማኅበረሰብም ለማንጻት የሚያገለግለውን ውኃ ለማዘጋጀት እንዲውል አመዱን ያስቀምጠው። ይህ የኃጢአት መባ ነው። |
የላሟን አመድ የሚያፍሰው ሰው ልብሶቹን ያጥባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። “‘ይህም ለእስራኤላውያንና በመካከላቸው ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል። |
የሞተ ሰው የነካ ማንኛውም ሰው ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። |
ይህ ሰው በሦስተኛው ቀን ራሱን በውኃው ያንጻ፤ በሰባተኛውም ቀን ንጹሕ ይሆናል። በሦስተኛው ቀን ራሱን ካላነጻ ግን በሰባተኛው ቀን ንጹሕ አይሆንም። |
የሞተ ሰው የነካና ራሱን ያላነጻ ሰው ሁሉ የይሖዋን የማደሪያ ድንኳን አርክሷል፤ ይህ ሰው ከእስራኤል መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። የሚያነጻው ውኃ ስላልተረጨበት ርኩስ ነው። አሁንም ከርኩሰቱ አልነጻም። |
“‘አንድ ሰው በድንኳን ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፦ ወደ ድንኳኑ የሚገባም ሆነ ቀድሞውኑም በድንኳኑ ውስጥ የነበረ ሰው ሁሉ ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። |
መክደኛው ላዩ ላይ ያልታሰረ ክፍት ዕቃ ሁሉ ርኩስ ነው። |
በሰይፍ የተገደለን ወይም በድንን ወይም አፅምን ወይም መቃብርን የነካ በሜዳ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። |
ለረከሰውም ሰው ከተቃጠለው የኃጢአት መባ አመድ ላይ ወስደው በዕቃ በማድረግ ከወራጅ ውኃ የተቀዳ ውኃ ይጨምሩበት። |
ከዚያም ንጹሕ የሆነ ሰው ሂሶጵ ወስዶ ውኃው ውስጥ ከነከረ በኋላ በድንኳኑ፣ በዕቃዎቹ ሁሉ፣ እዚያ በነበረው ሰው ሁሉና አፅሙን ወይም የተገደለውን ሰው አሊያም በድኑን ወይም መቃብሩን በነካው ሰው ላይ ይረጨዋል። |
ንጹሕ የሆነውም ሰው ውኃውን በረከሰው ሰው ላይ በሦስተኛው ቀንና በሰባተኛው ቀን ላይ ይረጨዋል፤ በሰባተኛውም ቀን ከኃጢአት ያነጻዋል፤ ከዚያም ሰውየው ልብሶቹን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ ማታም ላይ ንጹሕ ይሆናል። |
“‘ሆኖም የረከሰውና ራሱን ያላነጻው ሰው የይሖዋን መቅደስ ስላረከሰ ይህ ሰው ከጉባኤው መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። የሚያነጻው ውኃ ስላልተረጨበት ሰውየው ርኩስ ነው። |
“‘ይህ ለእነሱ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል፦ የሚያነጻውን ውኃ የሚረጨው ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ የሚያነጻውን ውኃ የሚነካውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። |
የረከሰው ሰው የሚነካው ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል፤ ይህን የነካ ሰውም እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።’” |
የእስራኤል ሕዝብ በሙሴና በአሮን መሪነት በየምድቡ በመሆን ከግብፅ ምድር በወጣ ጊዜ የተጓዘው በዚህ መልክ ነበር። |
ሙሴም በጉዟቸው ላይ ሳሉ ያረፉባቸውን ቦታዎች ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይመዘግብ ነበር፤ ከአንዱ ስፍራ ተነስተው ወደ ሌላው የተጓዙት በሚከተለው ሁኔታ ነበር፦ |
በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ15ኛው ቀን ከራምሴስ ተነሱ። ልክ በፋሲካ በዓል ማግስት እስራኤላውያን ግብፃውያን ሁሉ እያዩአቸው በልበ ሙሉነት ወጡ። |
በዚህ ጊዜ ግብፃውያን ይሖዋ በመቅሰፍት የመታቸውን በኩሮቻቸውን ሁሉ እየቀበሩ ነበር፤ ምክንያቱም ይሖዋ በአማልክታቸው ላይ የቅጣት እርምጃ ወስዶ ነበር። |
በመሆኑም እስራኤላውያን ከራምሴስ ተነስተው በሱኮት ሰፈሩ። |
ከዚያም ከሱኮት ተነስተው በምድረ በዳው ዳርቻ ላይ በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ። |
በመቀጠልም ከኤታም ተነስተው በበዓልጸፎን ትይዩ ወደምትገኘው ወደ ፊሃሂሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ። |
ከዚያም ከፊሃሂሮት ተነስተው ባሕሩን በማቋረጥ ወደ ምድረ በዳው ሄዱ፤ በኤታም ምድረ በዳ የሦስት ቀን መንገድ ከተጓዙ በኋላ በማራ ሰፈሩ። |
ከዚያም ከማራ ተነስተው ወደ ኤሊም መጡ። በኤሊም 12 የውኃ ምንጮችና 70 የዘንባባ ዛፎች ነበሩ፤ በመሆኑም በዚያ ሰፈሩ። |
በመቀጠል ደግሞ ከኤሊም ተነስተው በቀይ ባሕር አጠገብ ሰፈሩ። |
ከዚያ በኋላ ከቀይ ባሕር ተነስተው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ። |
ከሲን ምድረ በዳ ተነስተው ደግሞ በዶፍቃ ሰፈሩ። |
በኋላም ከዶፍቃ ተነስተው በአሉሽ ሰፈሩ። |
በመቀጠልም ከአሉሽ ተነስተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጣው ውኃ አልነበረም። |
ከዚያ በኋላ ከረፊዲም ተነስተው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። |
ከሲና ምድረ በዳም ተነስተው በቂብሮትሃታባ ሰፈሩ። |
ከዚያም ከቂብሮትሃታባ ተነስተው በሃጼሮት ሰፈሩ። |
በኋላም ከሃጼሮት ተነስተው በሪትማ ሰፈሩ። |
በመቀጠል ደግሞ ከሪትማ ተነስተው በሪሞንጰሬጽ ሰፈሩ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.