text
stringlengths
4
267
ኤልተቄ፣ ጊበቶን፣ ባዓላት፣
የሁድ፣ ብኔበራቅ፣ ጋትሪሞን፣
መሃይያርቆን፣ ራቆን እና ከኢዮጴ ትይዩ ያለው ድንበር ነበር።
የዳን ዘሮች ርስታቸው በጣም ጠቧቸው ነበር። በመሆኑም ወጥተው ለሸምን ወጉ፤ ከተማዋንም በመቆጣጠር በሰይፍ መቷት። ከዚያም ከተማዋን ርስት አድርገው በመያዝ በዚያ መኖር ጀመሩ፤ ለሸምንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት።
የዳን ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር። ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ።
በዚህ መንገድ ምድሪቱን በየክልሉ በርስትነት አከፋፍለው ጨረሱ። ከዚያም እስራኤላውያን ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት።
እነሱም የጠየቀውን ከተማ ማለትም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ቲምናትሰራን በይሖዋ ትእዛዝ መሠረት ሰጡት፤ እሱም ከተማዋን ገንብቶ በዚያ ተቀመጠ።
ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገዶች የአባቶች ቤት መሪዎች በሴሎ በይሖዋ ፊት በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ርስት አድርገው በዕጣ ያከፋፈሉት ድርሻ ይህ ነበር። በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን አከፋፍለው ጨረሱ።
የሃጾር ንጉሥ ያቢን ይህን ሲሰማ ወደ ማዶን ንጉሥ ወደ ዮባብ፣ ወደ ሺምሮን ንጉሥ፣ ወደ አክሻፍ ንጉሥ
እንዲሁም በስተ ሰሜን በሚገኘው ተራራማ አካባቢ፣ በደቡብ ኪኔሬት ባሉት ሜዳዎችና በሸፌላ ወደሚገኙት እንዲሁም በስተ ምዕራብ በዶር ሸንተረሮች ወዳሉት ነገሥታት፣
በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ወዳሉት ከነአናውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ሂታውያን፣ ወደ ፈሪዛውያን፣ በተራራማው አካባቢ ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሳውያን እንዲሁም በምጽጳ ምድር በሄርሞን ግርጌ ወደሚገኙት ወደ ሂዋውያን መልእክት ላከ።
እነሱም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ ከሆነው ሠራዊታቸው ሁሉ ጋር ወጡ፤ እጅግ ብዙ ፈረሶችና የጦር ሠረገሎችም ነበሯቸው።
እነዚህም ነገሥታት በሙሉ አንድ ላይ ለመገናኘት ተስማሙ፤ ከዚያም እስራኤልን ለመውጋት መጥተው በመሮም ውኃ አጠገብ አንድ ላይ ሰፈሩ።
በዚህ ጊዜ ይሖዋ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ሰዓት ገደማ ሁሉንም ለእስራኤላውያን አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍሯቸው፤ እናንተም ትፈጇቸዋላችሁ። የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ቁረጡ፣ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።”
ከዚያም ኢያሱና አብረውት የነበሩት ተዋጊዎች በሙሉ በመሮም ውኃ አጠገብ ድንገተኛ ጥቃት ሰነዘሩባቸው።
ይሖዋም ለእስራኤላውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነሱም ድል አደረጓቸው፤ እስከ ታላቋ ሲዶና፣ እስከ ሚስረፎትማይምና በስተ ምሥራቅ እስካለው እስከ ምጽጳ ሸለቆ ድረስም አሳደዷቸው፤ አንድም ሰው በሕይወት ሳያስቀሩ መቷቸው።
ከዚያም ኢያሱ ልክ ይሖዋ እንደነገረው አደረገባቸው፤ የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ቆረጠ፤ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።
ከዚህም በተጨማሪ ኢያሱ ተመልሶ ሃጾርን ተቆጣጠረ፤ ንጉሥዋንም በሰይፍ መትቶ ገደለው፤ ምክንያቱም ሃጾር ቀደም ሲል የእነዚህ መንግሥታት ሁሉ የበላይ ነበረች።
እነሱም በውስጧ ያለውን ሰው ሁሉ በሰይፍ በመምታት ፈጽመው አጠፉ። እስትንፋስ ያለው አንድም ነገር አላስቀሩም። ከዚያም ሃጾርን በእሳት አቃጠላት።
ኢያሱ የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች በሙሉ በቁጥጥር ሥር አዋለ፤ ነገሥታታቸውንም ሁሉ በሰይፍ ድል አደረገ። የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ባዘዘውም መሠረት ፈጽሞ አጠፋቸው።
ሆኖም እስራኤላውያን ኢያሱ ካቃጠላት ከሃጾር በስተቀር በኮረብቶቻቸው ላይ ካሉት ከተሞች አንዱንም አላቃጠሉም ነበር።
እስራኤላውያን ከእነዚህ ከተሞች ያገኙትን ምርኮና የቤት እንስሳ ሁሉ ለራሳቸው ወሰዱ። ሰዎቹን ግን አንድ በአንድ በሰይፍ መተው ሁሉንም አጠፏቸው። እስትንፋስ ያለው አንድም ሰው አላስቀሩም።
ይሖዋ አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ ሙሴም ኢያሱን አዞት ነበር፤ ኢያሱም እንደተባለው አደረገ። ኢያሱ፣ ይሖዋ ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ሳይፈጽም የቀረው አንድም ነገር አልነበረም።
ኢያሱ ይህን ምድር በሙሉ ይኸውም ተራራማውን አካባቢ፣ ኔጌብን በሙሉ፣ የጎሸንን ምድር ሁሉ፣ ሸፌላን፣ አረባን፣ የእስራኤልን ተራራማና ቆላማ አካባቢዎች በሙሉ ድል አደረገ፤
ወደ ሴይር ሽቅብ ከሚወጣው ከሃላቅ ተራራ አንስቶ በሄርሞን ተራራ ግርጌ በሊባኖስ ሸለቆ እስከሚገኘው እስከ በዓልጋድ ድረስ ያለውን አካባቢ በሙሉ ድል አደረገ፤ ነገሥታታቸውን ሁሉ በቁጥጥር ሥር አዋለ፤ ድል አደረጋቸው፤ ገደላቸውም።
ኢያሱ ከእነዚህ ሁሉ ነገሥታት ጋር ለተወሰነ ጊዜ ተዋጋ።
በገባኦን ከሚኖሩት ሂዋውያን በስተቀር ከእስራኤላውያን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት የፈጠረ አንድም ከተማ አልነበረም። ሌሎቹን ሁሉ በጦርነት ድል አደረጓቸው።
በእስራኤል ላይ ጦርነት እንዲከፍቱና ምንም ሳይራራላቸው ፈጽሞ ያጠፋቸው ዘንድ ልባቸው እንዲደነድን የፈቀደው ይሖዋ ነው። ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሙሉ በሙሉ መጥፋት ነበረባቸው።
በዚያን ጊዜ ኢያሱ ከተራራማው አካባቢ ከኬብሮን፣ ከደቢር፣ ከአናብ እንዲሁም ከይሁዳ ተራራማ አካባቢዎች ሁሉና ከእስራኤል ተራራማ አካባቢዎች ሁሉ ኤናቃውያንን ጠራርጎ አጠፋ። ኢያሱ እነሱንም ሆነ ከተሞቻቸውን ሙሉ በሙሉ አጠፋቸው።
በእስራኤላውያን ምድር የተረፈ አንድም ኤናቃዊ አልነበረም፤ ኤናቃውያን የነበሩት በጋዛ፣ በጌት እና በአሽዶድ ብቻ ነበር።
ስለዚህ ኢያሱ ይሖዋ ለሙሴ በገባው ቃል መሠረት ምድሩን ሁሉ ተቆጣጠረ፤ ከዚያም ኢያሱ ለእስራኤላውያን በየነገዳቸው ድርሻቸውን ርስት አድርጎ ሰጣቸው። ምድሪቱም ከጦርነት አረፈች።
የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ ይሖዋ የሙሴ አገልጋይ የነበረውን የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ አለው፦
“አገልጋዬ ሙሴ ሞቷል። እንግዲህ አንተም ሆንክ ይህ ሕዝብ ተነስታችሁ ዮርዳኖስን በመሻገር ለእስራኤላውያን ወደምሰጣቸው ምድር ግቡ።
ለሙሴ በገባሁት ቃል መሠረት እግራችሁ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ እሰጣችኋለሁ።
ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስና እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ይኸውም መላው የሂታውያን ምድር እንዲሁም በስተ ምዕራብ እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል።
በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም። ከሙሴ ጋር እንደነበርኩ ሁሉ ከአንተም ጋር እሆናለሁ። አልጥልህም ወይም አልተውህም።
ይህን ሕዝብ ለአባቶቻቸው ልሰጣቸው ወደማልኩላቸው ምድር የምታስገባው አንተ ስለሆንክ ደፋርና ብርቱ ሁን።
“ብቻ አንተ ደፋርና ብርቱ ሁን፤ አገልጋዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም። በምትሄድበት በየትኛውም ቦታ ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን እንድትችል ከዚህ ሕግ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል።
ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ በውስጡ የተጻፈውንም በጥንቃቄ መፈጸም እንድትችል ቀንም ሆነ ሌሊት በለሆሳስ አንብበው፤ እንዲህ ካደረግክ መንገድህ ይቃናልሃል፤ እንዲሁም ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን ትችላለህ።
ደፋርና ብርቱ ሁን ብዬ አዝዤህ አልነበረም? አምላክህ ይሖዋ በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር ስለሆነ አትሸበር፤ አትፍራ።”
ከዚያም ኢያሱ የሕዝቡን አለቆች እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦
“በሰፈሩ ውስጥ በመዘዋወር ሕዝቡን እንዲህ በማለት እዘዙ፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ ለመውረስ በሦስት ቀን ውስጥ ዮርዳኖስን ስለምትሻገሩ ስንቃችሁን አዘጋጁ።’”
ኢያሱም ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ እንዲህ አላቸው፦
“የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ እንዲህ በማለት ያዘዛችሁን ቃል አስታውሱ፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ እረፍት ሰጥቷችኋል፤ ይህን ምድር አውርሷችኋል።
ሚስቶቻችሁ፣ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ በሰጣችሁ ከዮርዳኖስ ወዲህ ባለው ምድር ላይ ይቀመጣሉ፤ ሆኖም ብርቱ የሆናችሁት ተዋጊዎች በሙሉ የጦርነት አሰላለፍ በመከተል ወንድሞቻችሁን ቀድማችሁ ትሻገራላችሁ። እነሱን መርዳት ይገባችኋል፤
ይሖዋ ለእናንተ እንዳደረገው ሁሉ ለወንድሞቻችሁም እረፍት እስከሚሰጣቸውና አምላካችሁ ይሖዋ የሚሰጣቸውን ምድር እስከሚወርሱ ድረስ ይህን ማድረግ ይኖርባችኋል። ከዚያም እንድትይዟትና እንድትወርሷት ወደተሰጠቻችሁ ይኸውም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ወደሰጣችሁ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ወደምትገኘው ምድር ትመለሳላችሁ።’”
እነሱም ለኢያሱ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “የምታዘንን ሁሉ እንፈጽማለን፤ ወደምትልከንም ሁሉ እንሄዳለን።
ሙሴ የሚለንን ማንኛውንም ነገር እንሰማ እንደነበር ሁሉ አንተንም እንሰማለን። ብቻ አምላክህ ይሖዋ ከሙሴ ጋር እንደነበረ ሁሉ ከአንተም ጋር ይሁን።
መመሪያህን አልታዘዝም የሚልና የምትሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ የማይሰማ ማንኛውም ሰው ይገደል። ብቻ አንተ ደፋርና ብርቱ ሁን።”
ይሁን እንጂ ከይሁዳ ነገድ የሆነው የዛራ ልጅ፣ የዛብዲ ልጅ፣ የካርሚ ልጅ አካን ለጥፋት ከተለየው ነገር ላይ በመውሰዱ እስራኤላውያን ለጥፋት ከተለየው ነገር ጋር በተያያዘ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጸሙ። በዚህም የተነሳ የይሖዋ ቁጣ በእስራኤላውያን ላይ ነደደ።
ከዚያም ኢያሱ “ወጥታችሁ ምድሪቱን ሰልሉ” በማለት ከቤቴል በስተ ምሥራቅ በቤትአዌን አቅራቢያ ወደምትገኘው ወደ ጋይ ሰዎችን ላከ። በመሆኑም ሰዎቹ ወጥተው ጋይን ሰለሉ።
ሰዎቹም ወደ ኢያሱ ተመልሰው እንዲህ አሉት፦ “ሕዝቡ ሁሉ መውጣት አያስፈልገውም። ጋይን ድል ለማድረግ ሁለት ሺህ ወይም ሦስት ሺህ ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ብቻ ይበቃሉ። ነዋሪዎቿ ጥቂት ስለሆኑ መላው ሕዝብ እንዲሄድ በማድረግ ሕዝቡን አታድክም።”
በመሆኑም 3,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ወደዚያ ወጡ፤ ይሁን እንጂ ከጋይ ሰዎች ፊት ለመሸሽ ተገደዱ።
የጋይ ሰዎችም 36 ሰዎችን ገደሉ፤ ከከተማዋ በር አንስቶ እስከ ሸባሪም ድረስ በማሳደድ ቁልቁለቱ ላይ መቷቸው። በዚህም የተነሳ የሕዝቡ ልብ ቀለጠ፤ እንደ ውኃም ፈሰሰ።
በዚህ ጊዜ ኢያሱ ልብሱን ቀደደ፤ እስከ ምሽትም ድረስ በይሖዋ ታቦት ፊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እሱም ሆነ የእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲሁ አደረጉ፤ በራሳቸውም ላይ አቧራ ይበትኑ ነበር።
ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ወዮ! ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ይህን ሁሉ ሕዝብ ዮርዳኖስን አሻግረህ እዚህ ድረስ ያመጣኸው ለአሞራውያን አሳልፈህ በመስጠት እንድንጠፋ ለማድረግ ነው? እዚያው በዮርዳኖስ ማዶ አርፈን ብንቀመጥ ይሻለን ነበር!
አቤቱ ይሖዋ ሆይ ይቅር በለኝ፣ እንግዲህ እስራኤል ከጠላቶቹ ፊት እንዲህ የሚሸሽ ከሆነ ምን ማለት እችላለሁ?
ከነአናውያንና የምድሪቱ ነዋሪዎች በሙሉ ይህን ሲሰሙ መጥተው ይከቡንና ስማችንን ከምድር ገጽ ያጠፉታል፤ ታዲያ አንተ ለታላቁ ስምህ ስትል ምን ታደርግ ይሆን?”
ይሖዋም ለኢያሱ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ተነስ! በግንባርህ የተደፋኸው ለምንድን ነው?
እስራኤላውያን ኃጢአት ሠርተዋል። እንዲጠብቁት ያዘዝኳቸውን ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል። ለጥፋት ከተለየው ነገር ላይም ሰርቀው ወስደዋል፤ ከራሳቸው ዕቃዎችም ጋር በመቀላቀል ደብቀው አስቀምጠውታል።
ስለዚህ እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን መቋቋም አይችሉም። ዞረውም ከጠላቶቻቸው ፊት ይሸሻሉ፤ ምክንያቱም እነሱ ራሳቸው ለጥፋት የተለዩ ሆነዋል። ለጥፋት የተለየውን ነገር ከመካከላችሁ ካላስወገዳችሁ በስተቀር ከእንግዲህ እኔ ከእናንተ ጋር አልሆንም።
ተነስና ሕዝቡን ቀድስ! እንዲህም በላቸው፦ ‘ነገ ራሳችሁን ቀድሱ፤ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “እስራኤል ሆይ፣ በመካከልህ ለጥፋት የተለየ ነገር አለ። ለጥፋት የተለየውን ነገር ከመካከልህ ካላስወገድክ ጠላቶችህን መቋቋም አትችልም።
ማለዳ ላይ በነገድ በነገድ ሆናችሁ ትቀርባላችሁ፤ ይሖዋ የሚመርጠውም ነገድ ወደ ፊት ይቀርባል፤ ከዚያም በወገን በወገኑ ሆኖ ይቀርባል፤ ይሖዋ የሚመርጠውም ወገን ወደ ፊት ይቀርባል፤ ከዚያም በቤተሰብ በቤተሰብ ሆኖ ይቀርባል፤ ይሖዋ የሚመርጠውም ቤተሰብ ወደ ፊት ይቀርባል፤ ከዚያም በግለሰብ በግለሰብ ሆኖ ይቀርባል።
ለጥፋት የተለየውን ነገር ወስዶ የተገኘውም ሰው በእሳት ይቃጠላል፤ እሱም ሆነ የእሱ የሆነው ሁሉ ይቃጠላሉ፤ ምክንያቱም ይህ ሰው የይሖዋን ቃል ኪዳን አፍርሷል፤ እንዲሁም በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪ ተግባር ፈጽሟል።”’”
ስለሆነም ኢያሱ በሚቀጥለው ቀን በማለዳ ተነስቶ እስራኤላውያን በነገድ በነገድ ሆነው ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ የይሁዳም ነገድ ተመረጠ።
የይሁዳ ወገኖች ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከመካከላቸውም የዛራውያን ወገን ተመረጠ፤ ከዚያም ከዛራውያን ወገን የሆኑት ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከዚያም ዛብዲ ተመረጠ።
በመጨረሻም የዛብዲ ቤተሰብ በግለሰብ በግለሰብ ሆኖ ወደ ፊት እንዲቀርብ አደረገ፤ ከዚያም ከይሁዳ ነገድ የዛራ ልጅ፣ የዛብዲ ልጅ፣ የካርሚ ልጅ አካን ተመረጠ።
ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ፣ እባክህ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን አክብር፤ ለእሱም ተናዘዝ። እባክህ ያደረግከውን ንገረኝ። አትደብቀኝ።”
አካንም ለኢያሱ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “በእርግጥም በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ላይ ኃጢአት የሠራሁት እኔ ነኝ፤ እንግዲህ ያደረግኩት ይህ ነው፦
ከምርኮው መካከል ከሰናኦር የመጣ የሚያምር የክብር ልብስ፣ 200 ሰቅል ብርና 50 ሰቅል የሚመዝን ጥፍጥፍ ወርቅ አይቼ ስለተመኘሁ ወሰድኳቸው። አሁንም ገንዘቡ ከታች ሆኖ ድንኳኔ ውስጥ መሬት ውስጥ ተቀብረው ይገኛሉ።”
ኢያሱም ወዲያውኑ መልእክተኞች ላከ፤ እነሱም ወደ ድንኳኑ እየሮጡ ሄዱ፤ ልብሱንም ድንኳኑ ውስጥ ተደብቆ አገኙት፤ ገንዘቡም ከልብሱ ሥር ነበር።
ከዚያም ከድንኳኑ አውጥተው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤላውያን ሁሉ አመጧቸው፤ በይሖዋም ፊት አስቀመጧቸው።
በኋላም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ የዛራን ልጅ አካንን፣ ብሩን፣ የክብር ልብሱን፣ ጥፍጥፍ ወርቁን፣ ወንዶች ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹን፣ በሬውን፣ አህያውን፣ መንጋውን፣ ድንኳኑንና የእሱ የሆነውን ሁሉ ወደ አኮር ሸለቆ አመጡ።
ኢያሱም አካንን “መዓት ያመጣህብን ለምንድን ነው? ይሖዋም በዛሬው ዕለት መዓት ያመጣብሃል” አለው። ከዚያም እስራኤላውያን በሙሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሏቸው። በዚህ መንገድ ሁሉንም በድንጋይ ወግረው ገደሏቸው።
በእሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታየውን የድንጋይ ቁልል ከመሩበት። በዚህ ጊዜ የይሖዋ ታላቅ ቁጣ በረደ። የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ የሚባለው በዚህ የተነሳ ነው።
ኢያሱም ዕድሜው ገፍቶና አርጅቶ ነበር። በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ ዕድሜህ ገፍቷል፤ አርጅተሃል፤ ሆኖም መወረስ ያለበት ገና ሰፊ ምድር ይቀራል።
የሚቀረውም ምድር ይህ ነው፦ የፍልስጤማውያንና የገሹራውያን ምድር በሙሉ
(ከግብፅ ፊት ለፊት ከሚገኘው ከአባይ ወንዝ ቅርንጫፍ አንስቶ በሰሜን እስከ ኤቅሮን ወሰን ድረስ ያለው ክልል የከነአናውያን ግዛት እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠር ነበር) እንዲሁም በጋዛ፣ በአሽዶድ፣ በአስቀሎን፣ በጌት እና በኤቅሮን የሚኖሩትን የአምስቱን የፍልስጤም ገዢዎች ምድር የሚጨምር ሲሆን የአዊም ሰዎችንም ምድር ያካትታል፤
እነሱም በደቡብ በኩል ይኖሩ ነበር፤ መላው የከነአናውያን ምድር፤ የሲዶናውያን ይዞታ የሆነችው መአራ፣ እንዲሁም በአሞራውያን ወሰን ላይ እስከሚገኘው እስከ አፌቅ ድረስ ያለው አካባቢ፤
የጌባላውያን ምድር፣ በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ያለው መላው ሊባኖስ ይኸውም በሄርሞን ተራራ ግርጌ ከሚገኘው ከበዓልጋድ አንስቶ እስከ ሌቦሃማት ድረስ ያለው አካባቢ፤
በተራራማው አካባቢ፣ ከሊባኖስ እስከ ሚስረፎትማይም ባለው ምድር የሚኖሩት ነዋሪዎች በሙሉ እንዲሁም ሲዶናውያን በሙሉ ናቸው። እነሱንም ከእስራኤላውያን ፊት አባርራቸዋለሁ። አንተም ባዘዝኩህ መሠረት ምድሩን ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ ስጥ።
እንግዲህ ይህን ምድር ለዘጠኙ ነገዶችና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገህ አከፋፍል።”
የተቀረው የምናሴ ነገድ እኩሌታና ሮቤላውያን እንዲሁም ጋዳውያን የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ በሰጣቸው መሠረት ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ርስታቸውን ወስደዋል፤
ይህም በአርኖን ሸለቆ መካከል የምትገኘውን ከተማና የመደባን አምባ በሙሉ ጨምሮ በሸለቆው ዳርቻ ላይ ከምትገኘው ከአሮዔር አንስቶ እስከ ዲቦን ድረስ ያለውን አካባቢ፣
በሃሽቦን ሆኖ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንን ከተሞች በሙሉ እስከ አሞናውያን ወሰን ድረስ፣
ጊልያድን፣ የገሹራውያንንና የማአካታውያንን ግዛት፣ የሄርሞንን ተራራ በሙሉ፣ ባሳንን በሙሉ እስከ ሳልካ ድረስ
እንዲሁም በአስታሮት እና በኤድራይ ሆኖ ይገዛ የነበረውን በባሳን ያለውን የኦግን ንጉሣዊ ግዛት በሙሉ ያጠቃልላል። (እሱም በሕይወት ከተረፉት የመጨረሻዎቹ የረፋይም ዘሮች አንዱ ነበር።) ሙሴም ድል አድርጎ አባረራቸው።
ሆኖም እስራኤላውያን ገሹራውያንንና ማአካታውያንን ከምድራቸው አላስለቀቋቸውም፤ ምክንያቱም ገሹራውያንና ማአካታውያን እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤል መካከል አሉ።
ውርስ ያልሰጠው ለሌዋውያን ነገድ ብቻ ነበር። የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ቃል በገባላቸው መሠረት ለእሱ በእሳት የሚቀርቡት መባዎች የእነሱ ውርሻ ናቸው።
ከዚያም ሙሴ ለሮቤላውያን ነገድ በየቤተሰባቸው ርስት ሰጣቸው፤
ግዛታቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ላይ ከምትገኘው ከአሮዔር አንስቶ ያለው ሲሆን በሸለቆው መካከል የምትገኘውን ከተማ፣ የመደባን አምባ በሙሉ፣
ሃሽቦንንና በአምባው ላይ ያሉትን ከተሞቿን በሙሉ፣ ዲቦንን፣ ባሞትበዓልን፣ ቤትበዓልመዖንን፣
ያሃጽን፣ ቀደሞትን፣ መፋአትን፣
ቂርያታይምን፣ ሲብማን፣ በሸለቆው አጠገብ ባለው ኮረብታ ላይ የምትገኘውን ጸሬትሻሃርን፣
ቤትጰኦርን፣ የጲስጋን ሸንተረሮች፣ ቤትየሺሞትን፣
በአምባው ላይ የሚገኙትን ከተሞች ሁሉ እንዲሁም በሃሽቦን ሆኖ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንን ንጉሣዊ ግዛት በሙሉ ያጠቃልላል። ሙሴም ይህን ንጉሥና በምድሪቱ ይኖሩ የነበሩትን የምድያም አለቆች፣ ኤዊን፣ ራቄምን፣ ጹርን፣ ሁርን እና ረባን እንዲሁም የሲሖንን መሳፍንት ድል አድርጓቸው ነበር።
እስራኤላውያን በሰይፍ ከገደሏቸው መካከል ሟርተኛው የቢዖር ልጅ በለዓም ይገኝበታል።
የሮቤላውያን ወሰን ዮርዳኖስ ነበር፤ ከተሞቹንና መንደሮቹን ጨምሮ ይህ ግዛት ሮቤላውያን በየቤተሰባቸው የያዙት ርስት ነው።
በተጨማሪም ሙሴ ለጋድ ነገድ ይኸውም ለጋዳውያን በየቤተሰባቸው ርስት ሰጣቸው፤
ግዛታቸውም ያዜርን፣ የጊልያድን ከተሞች በሙሉ፣ ከራባ ፊት ለፊት እስከምትገኘው እስከ አሮዔር የሚደርሰውን የአሞናውያንን ምድር እኩሌታ፣