doc_id
stringlengths
1
5
text
stringlengths
42
393k
1
በትግራይ ደቡባዊ ዞን ጫት በአሳሳቢ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው ። በትግራይ ደቡባዊ ዞን ራያና አዘቦ ወረዳ በመስኖ በሚለማ የእርሻ መሬት የጫት ተክል በአሳሳቢ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ መሆኑን የራያ ሸለቆ የተቀናጀ እርሻ ልማት እህፈት ቤትና የወረዳው ፖሊስ አስታወቁ ። የእህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ተስፋይ ኪዳኔ ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል እንደገለጹት ከ5 አመት በፊት አርሶ አደሮች በመስኖ ውሃ ሰብልና ፍራፍሬዎችን ያለሙበት የነበረው መሬት በአሁኑ ወቅት በጫት ተክል እየተሸፈነ ነው ። የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አቶ...
10
የጫት ንግድና አጠቃቀምን ህግ ሊወጣ ነው 2015 0 262 197 5 አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11 2007 ዋኢማ የጫት ንግድና አጠቃቀምን ስርአት ለማስያዝ የሚያስችል ረቂቅ ህግ እየተጠናቀቀ መሆኑን የምግብ፣መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ ። በህገወጥ የምግብ፣መድሃኒትና ጤና አገልግሎት ቁጥጥር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰሞኑን በሎግያ ከተማ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ እንዳስታወቁት ወጣቱ ትውልድ ስትራቴጂካዊ...
11
በጫት ምርት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ ሊጣል ነው 2012 0 228 170 5 አዲስ አበባ ሰኔ 292004ዋኢማ በጫት ምርት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ ለመጣል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምርት ቤት ቀርቦ ውይይት ተካሂደበት። ቀደም ሲል የምርቱ ሽያጭ ይካሔድ የነበረው መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመሆኑና አብዛኞቹ ነጋዴዎችም በቋሚነት የሚታወቁበት ስፍራ ስለሌላቸው በቀረጥ አሰባሰቡ ላይ ችግር ፈጥሯል። ሁኔታውን ለማረምም ቀደም ሲል የነበረውን የጫት ግብር በኤክሳይዝ ታክስ እንዲተካ ለማድረግ የሚያስችለው...
12
የባሕር ዳር አርሶ አደሮች ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡ ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 302011ዓም አብመድ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጎርደማ አካባቢ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ለዓመታት ሲያለሙት የነበረውን ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡ አርሶ አደሮቹ ጫት እያስከተለ ያለውን ማኅበራዊ ጉዳት በመረዳት ነው ከማሳቸው በማስወገድ በሌላ ጠቃሚ ሰብልና የጓሮ አትክልት ለመተካት እንቅስቃሴ የጀመሩት፡፡ ዛሬ በአንድ ሄክታር ማሳ ላይ ያለሙትን ጫት ማስወገድ የጀመሩት አቶ ሙስጦፋ ታደሰ የተባሉ የጎርደማ አ...
13
ጫት ጫት ወይንም በርጫ፡ በርጫ በምስራቅ አፍሪካና በየመን የተለመደ ቅጠል ነው። የጫትን ቅጠል በማኘክ ምርቃና የሚባል ቃሚዎቹ ተወዳጅ ስሜት ነው የሚሉት ላይ መድረስ ይቻላል። ይህ የሚሆነው ጫት ውስጥ ያሉት ንጥረ ነግሮች ኣንጎል ላይ በሚፈጥሩት ለውጥ ሲሆን የጫት ወይም ጅማ የስነ ፍጥረት ስሙ በእንግሊዝኛ Catha edulis ነው። ጫት የተገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ይባላል። የጫት ዝርያዎች በኤትዮጵያ ወስጥ በተለያዪ ክፍለ ሃገራት ይገኛል። እንደየአገሩም የጫት የተክሉ ዓይነት እና በወስጡ ያለው ንጥረ...
2
የባሕር ዳር ዙሪያ አርሶአደሮች ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጎርደማ አካባቢ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ለዓመታት ሲያለሙት የነበረውን ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡ አርሶ አደሮቹ ጫት እያስከተለ ያለውን ማኅበራዊ ጉዳት በመረዳት ነው ከማሳቸው በማስወገድ በሌላ ጠቃሚ ሰብልና የጓሮ አትክልት ለመተካት እንቅስቃሴ የጀመሩት፡፡ ዛሬ በአንድ ሄክታር ማሳ ላይ ያለሙትን ጫት ማስወገድ የጀመሩት አቶ ምስጦፋ ታደሰ የተባሉ የጎርደማ አካባቢ ነዋሪ ናቸው፤ ሌሎችም የእርሳቸ...
3
ጫት እንዴት ሊጠፋ ይችላል ጫት በማምረት የሚተዳደሩ እጅግ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ጫትን በማምረት ልጆቻቸዉን ያስተምራሉ፤ቤተሰባቸዉን ያስተዳድራሉ እንዲሁም ህይዎታቸዉን ይመራሉ፡፡ በተለይ በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ እጅግ ቁጥሩ ብዙ ገበሬዎች ሌሎች ሰብሎችን ከማምረት ይልቅ ጫትን በቀላሉ በማምረት ተጠቃሚ ናቸዉ፡፡በዚህ ወረዳ የሚኖሩ ወጣቶች ሀብት ንብረት አፍርተዉበታል፡፡እንደሚታወቀዉ ይሄ ወረዳ ለከተማዉ ቅርብ በመሆኑ በተለምዶ ቦታዉን በመሸጥ ወደ ተለያየ ቦታ ይፈልሳሉ፡፡ አስቡት የአበባበ ምርት ም...
4
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ብዙ በልተኸው ርቦህ ትነሳለህ። ሳይቀቀል እና ሳይጠበስ ከነቆሻሻው በታሸገ ውኃ ትቅመዋለህ፤ ከታጠበ አያመረቅንም ተብሎ ይገመታል። በዲዲቲ ምክንያት ትል ያለውን ወይም ትል የበላውን ፈልገህ ትቅማለህ፣ ምክንያቱም ትል ከሌለው መድኃኒት የተረጨበት ነው ተብሎ ይታመናል። ዋነኛ የጫት መቃሚያ ሰዓት ማለት ዋነኛ የሥራ ሰዓት ነው። ሰው ሥራ ጠግቦ ሲመለስ አንተ ብው ብለህ ለሥራ ትወጣለህ። የአንጎልህ እሽክርክሪት በብዙ እጥፍ ይጨምራል። ቩቩቩቩቩኡኡኡኡኡ ዘወትር ለእብደት ሩብ ...
5
የባሕር ዳር አርሶ አደሮች ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጎርደማ አካባቢ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ለዓመታት ሲያለሙት የነበረውን ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡ አርሶ አደሮቹ ጫት እያስከተለ ያለውን ማኅበራዊ ጉዳት በመረዳት ነው ከማሳቸው በማስወገድ በሌላ ጠቃሚ ሰብልና የጓሮ አትክልት ለመተካት እንቅስቃሴ የጀመሩት፡ ዛሬ በአንድ ሄክታር ማሳ ላይ ያለሙትን ጫት ማስወገድ የጀመሩት አቶ ሙስጦፋ ታደሰ የተባሉ የጎርደማ አካባቢ ነዋሪ ናቸው፤ ሌሎችም የእርሳቸውን አርዓ...
6
ጫት መቃም ለማቆም የሚያግዙ 5 ምክንያቶች ጫት መቃም ለአፍ ቁስለት፣ ለአፍ ካንሰርና ለጥርስ መቦርቦር ይበልጥ ያጋልጣል። 2 ጫት መቃም ለእንቅልፍ ማጣት፣ ለስሜት መሸበርና ለድካም ይዳርጋል። 3 ጫት መቃም ለተጓዳኝ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል። 4 ጫት የጸረኤችአይቪ መድሀኒቶችን ውጤታማነት ይቀንሳል። 5 ጫት መቃም የምግብ ፍላጎትን ይቀንሳል።
7
ዜጎችን ከጫት ጉዳት ለመታደግ መንግስት ፈጣን እርምጃ መውሰድ አለበት ምሁራን በዜጎችና በሃገር ላይ ጉዳት እየደረሰ ያለውን ጫት በዘላቂነት ለመከላከል መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ምሁራን አመለከቱ። በጫት ሱስ ምክንያት የሚመጡ የጤና፣የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን በነቃ የህብረተሰቡ ተሳትፎ እንከላከል በሚል መሪ ሃሳብ ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሄዷል። በዚህ ወቅት የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስነልቦና ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ታምራት ዘላ...
8
ዜጎችን ከጫት ጉዳት ለመታደግ መንግስት ፈጣን እርምጃ መውሰድ አለበት ምሁራን በዜጎችና በሃገር ላይ ጉዳት እየደረሰ ያለውን ጫት በዘላቂነት ለመከላከል መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ምሁራን አመለከቱ። በጫት ሱስ ምክንያት የሚመጡ የጤና፣የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን በነቃ የህብረተሰቡ ተሳትፎ እንከላከል በሚል መሪ ሃሳብ ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሄዷል። በዚህ ወቅት የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስነልቦና ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ታምራት ዘላ...
9
በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በጫት ምርት ላይ ከነገ ሚያዚያ 172010ዓም ጀምሮ ቀረጥ ሊጣል መሆኑ ተገለፀ፡፡ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዘውዱ ክፍሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ በጫት ምርት ላይ ከነገ ጀምሮ በተደራጁ ማህበራት አማካኝነት የቀረጥ ስራ ይጀመራል፡፡ በዋናነት ቀረጥ ማስቀመጥ ያስፈለገበትን ምክንያትም ሲገልፁ፤ በጫት ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የገዥን አቅም ማዳከምና ጫት የሚቅም ወጣትን ለመታደግ የታሰበ ነው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩልም ለከተማው ከፍተኛ የገቢ ...
14
በምስራቅ ሀረርጌ 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ግሪሳ ወፍ ተከሰተ የአይሮፕላን ድጋፍ አስፈልጓል ። በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሶስት ወረዳዎች 7 ነጥብ 4 ሚሊየን የግሪሳ ወፍ መንጋ መከሰቱን የዞኑ ግብርና ልማት መምሪያ አስታወቀ ፤ 30 ኪሎ ሜትር በመብረር ጉዳት እንደሚያደርስም ገለጸ ። በመምሪያው አዝርእት ትበቃ ቡድን መሪ አቶ ሞገስ ሂርመጂ ዛሬ ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል እንዳስታወቁት የግሪሳ ወፍ መንጋው የተከሰተው ካለፈው መስከረም አጋማሽ ጀምሮ ነው ። ወፉ በባቢሌ ፣ ፈዲስ እና ጉርሱም ወረዳዎች በሚገኙ ...
15
7 ነጥብ 4 ሚሊየን ግሪሳ ለመከላከል በአይሮፕላን ኬሚካል መርጨት ተጀመረ ። በምስራቅ እትዮጵያ የተከሰተውን 7 ነጥብ 4 ሚሊየን የግሪሳ ወፍ መንጋን ለመከላከል በአይሮፕላን ትናንት የኬሚካል ርጭት መጀመሩን የሀረር አዝርእት ትበቃ ክሊኒክ አስታወቀ ። የክሊኒኩ ሃላፊ አቶ ሰይፉ ወልደኪዳን ዛሬ ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል እንዳስታወቁት ርጭቱ የተጀመረው ከክልል ፣ ከዞንና ከወረዳ ግብርና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ለአንድ ወር ያህል በተካሄደው አሰሳ በተገኙት የተለያዩ 64 ሄክታር የወፎቹ መራቢያና ማደ...
16
9 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚገመት የግሪሳ ወፍ ተወገደ ። በምስራቅ እትዮጵያ ባለፈው መስከረም መጨረሻ የተከሰተውን 9ነጥብ6ሚሊየን የሚገመት የግሪሳ ወፍ መንጋ ለማስወገድ መቻሉን የሀረር አዝርእት ትበቃ ክሊኒክ አስታወቀ ። በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ባቢሌ ፣ ፈዲስና ጉርሱም ወረዳዎች ፤ በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ዞንና በሀረሪ ክልል የተከሰተውን ግሪሳ ወፍ ለመከላከል የተቻለው ባለፉት 12 ቀናት በአውሮፕላን በተካሄደው የመድሃኒት ርጭት መሆኑን የክሊኒኩ ሃላፊ አቶ ሰይፉ ወልደኪዳን ገልጸዋል ። በዚሁ ...
17
በዝዋይ ግብርና ልማት ማእከል ፤ማረሚያ ቤቶችና በአካባቢዉ በሚገኙ ገበሬዎች ማሳ ላይ ተከስቶ የነበረዉ የግሪሳ ወፍ መንጋ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ለመቆጣጠር መቻሉ ተገለጠ ። የዝዋይ ሰብል ጥበቃ ክሊኒክ ኤክስፐርት አቶ ዘብዲዎስ ሰላቶ እንደገለጡት ከፍተኛ ቁጥር ያለዉን የግሪሳ ወፍ መንጋ ለመቆጣጠር የተቻለዉ በአካባቢዉ በአዉሮፕላን የኬሚካል ርጭትና በባህላዊ ዘዴ የተጠናከረ የመከላከል ስራ በመካሄዱ ነዉ ። የግሪሳ ወፎች የደረሰዉን የበቆሎ ፍሬ በመብላትና ሽፋኑን በመላጥ ለዝናብ እንዲጋለጥ በማድረግ ...
18
በቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ በየጊዜው የሚከሰተውን የግሪሳ ወፍ መንጋ ለመከላከል በአምስት ሚሊዮን ብር የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የወረዳው አስተዳደር ገለጸ፡፡ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ታዲ ዋቆ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት የፌዴራሉ መንግስት በመደበው በጀት ግንባታው በመከናወን ላይ ያለው ጣቢያ 100 ሜትር ስፋትና ሁለት ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ የጣቢያው ግንባታ ሲጠናቀቅ መንጋው በሰብል ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል እንደሚረዳና ከዚህ ቀደም ከጎረቤት ...
19
በምስራቅ ሽዋ ዞን ስምጥ ሸለቆ አከባቢ በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች ተከስቶ የነበረውን ከ3ነጥብ8 ሚሊዮን በላይ የግሪሳ ወፍ በሰብል ላይ ጥፋት ሳያደርስ ለማስወገድ መቻሉን የባቱ እፅዋት ክሊኒክ ፅሀፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የፅሀፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ተሾመ ቡርቃ ለኢትዮጰያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት በስመጥ ሸለቆ በሚገኙት የአዳሚ ቱሉ ጅዶ፣ ዱግዳ ቦራና ዝዋይ ወረዳዎች ተከስቶ የነበረውን የግሪሳ ወፍ ማስወገድ የተቻለው በአውሮፕላን በመታገዝ በተካሄደ የኬሚካል ርጭት ነው፡፡ በዚሁ ዘመቻ ወፎቹ የሚያርፉበትና የሚ...
20
የግሪሳ ወፍ በማሽላ ሰብላችን ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው – የሰሜን ሸዋ ዞን አርሶ አደሮች ደብረ ብርሃን ጥቅምት 82011 በማሽላ ሰብላችን ላይ የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ በባህላዊ መንገድ ለመከላከል ጥረት ብናደርግም ከአቅማችን በላይ በመሆኑ ተቸግረናል ሲሉ በአማራ ክልል የሰሜን ሽዋ ዞን አርሶ አደሮች ገለፁ። ከ280 ሺህ በላይ የሚገመተውን ሰብል አውዳሚ የግሪሳ ወፍ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአውሮፕላን በታገዘ መንገድ ርጭት ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል። በቀወት ወረዳ የ...
21
ሰሜን ሸዋ ውስጥ በማሽላ ሰብል ላይ የተከሰተው የግሪሳ ወፍ መከላከል ተቻለ 1285 Share ደብረ ብርሀን ጥቅምት 202011 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት እና ኤፍራታ ግድም ወረዳዎች በማሽላ ሰብል ላይ ተከስቶ የነበረ ከሁለት ሚሊዮን 500ሺህ በላይ የግሪሳ ወፍ በማስወገድ መከላከል ተቻለ፡፡ የዞኑ ግብርና መምሪያ እንዳስታወቀው በወረዳዎቹ የለን እና ነጌሶ በተባሉት ቀበሌዎች በለማ የማሽላ ሰብል ከሁለት ሳምንታት በፊት ተከስቶ የነበረውን የግሪሳ ወፉን መከላከል የተቻለው በአውሮፕላን በተካሄደ የኬ...
22
የግሪሳ ወፍ በኅዳር ወር 2006 ዓም የግሪሳ ወፍ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች Eና ሕዝቦች በኮንሶ Eና Aማሮ ልዩ ወረዳዎች፤ ከOሮሚያ በዝዋይ ዱግዳ፣ ተለተሌ፣ Aዳሚ ቱሉ Eና ሊበን Eንዲሁም ከAማራ ክልል በቀወት፣ ኤፍራታ፣ ጂሌ ጥሙጋ፣ ዳዋ ጨፌ Eና ቃሉ ወረዳዎች የተከሰተ ሲሆን ወፎቹ ወደ Eህል ማሳ ሳይዛመቱ በተካሄደዉ ተገቢ Eና Aፋጣኝ የኬሚካል ርጭት Eርምጃ በቁጥጥር ሥር ሊዉል Eንደቻለ በግብርና ሚኒስቴር ከAዝርEት ጥበቃ ክፍል የተገኘዉ መረጃ ይጠቁማል። የአዕዋፍ ዝርያዎች ማሽላን የሚያጠቁ ቢሆን...
23
ባሳለፍነው ነሐሴ ወር የተዛማች ፀረ ሰብል ተባዮች የበረሐ አንበጣ፣ ተምችና ግሪሳ ወፍ ክስተት በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ አለመኖሩን ከክትትል መረጃዎች ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የግሳ ወፎች በነሐሴ ወር የግሪሳ ወፍ ክስተት በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያልነበረ ቢሆንም ባለንበት መስከረም ወር በመካከለኛ፣ ስምጥ ሸለቆና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ክስተቱ ሊኖር ስለሚችል በየአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮችና የልማት ሠራተኞች አስፈላጊውን አሰሳ በማድረግ ወረርሽኙ ከተከሰተ ለሚመለከተው ክፍል በፍጥነት ሪፖርት...
24
‹‹በአማራው ላይ የተሰራው የህዝብ ቆጠራ ስህተት እንዳይደገም ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡›› የክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ባሕር ዳር፡ የካቲት 262011 ዓምአብመድ የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ የአሰልጣኞች ስልጠና በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች እየተሰጠ ነዉ። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽን ፀሀፊ አቶ ተስፋ ተገኝ እንደተናገሩት በስልጠናው ከሰሜን፣ ከማዕከላዊ፣ ከምዕራብ እና ከደቡብ ጎንደር ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች እና ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የአይሲቲ ባለሙያዎች ...
25
የህዝብና ቤት ቆጠራው እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳብ መቅረቡ ተገቢ አይደለምየትግራይ ክልላዊ መንግስት ኢፕድ የክልሉ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብርሀም ተከስተ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት የቆጠራ ስራው በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። የቆጠራ ስራው እንዲራዘም ያጋጠመ የተለየ ችግር የለም ያሉት ኃላፊው አስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቶ እንዲራዘም የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ የመንግስትን የአመራር ግልጽነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው ብለዋል። ውሳኔው ከህገመንግ...
26
የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2011 ባካሄደው ስብሰባ አራተኛዉን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማካሄድ የተደረገዉን ዝግጅት በመገምገም የዉሳኔ ሃሳቦች ኣሳልፏል በዚህም መሠረት • የሕዝብና ቤት ቆጠራው እንዲቀጥል በቴክኒክ ደረጃ በቂ ዝጅግት የተደረገ መሆኑንና ኮሚሽኑና ማእከላዊ እስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሰፊ ስራ የሰሩ መሆኑን፤ • የካርታ እና ተያያዥ ስራዎች እየተገባደዱ መሆኑን፤ • ሌሎች ዝግጅቶችም እየተደረጉ መሆኑን ግንዛቤ ወስዶ የቆጠራውን አላማና ግብ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስች...
27
‹‹የሕዝብና ቤት ቆጠራው ከመንግሥት በላይ ለሃይማኖት ተቋማት አስፈላጊ በመሆኑ ከስህተት የጸዳ ቆጠራ እንዲካሄድ እየሠራን ነው፡፡›› የሃይማኖት አባቶች ባሕር ዳር፡ የካቲት 272011 ዓምአብመድ ከ12 ዓመታት በኋላ የሚካሄደው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ መጋቢት 29 ቀን 2011ዓም ሊጀመር ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡ ዓመታትን አስቆጥሮ የመጣውን ይህን የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ በውጤት እንዲጠናቀቅ የሃይማኖት አባቶች ድርሻቸው ከፍተኛ እንደሆነ የሃይማኖት አባቶች ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ...
28
ቆጠራው ህልውናን የሚፈታተን በመሆኑ በቀጣዩ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አብን አሳሰበ። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄአብን በደብረታቦር ከተማ ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር ተወያይቷል። ወቅታዊ ጉዳዮችንና የሕዝብና ቤቶች ቆጠራን አስመልክቶ ነው ውይይቱን ያዘጋጀው። ለውይይት መነሻም ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል። በፅሁፉም የአንድን ሃገር የሕዝብ ቁጥር ያላገናዘበ ምንም ዓይነት ልማት እንደማይሰራ ተብራርቷል። የሥራ አጥ ቁጥርን፣ የኑሮ ሁኔታን፣ የህብረተሠቡን የፍልሰት ሁኔታ፣ የግብር ከፋይ ቁጥርን እና...
29
እኛ አማራዎች የህዝብና ቤት ቆጠራው እንዲራዘም የምንፈልግበት ምክንያቶች፦ 1የፖለቲካ መተማመን ስለሌለ 2በሀገሪቱ አብዛኛው አካባቢ የፀጥታ ስጋት ስላለ ለቆጣሪዎች 3ዜጎች ራሳቸውን በማንነታቸው ቢገልፁ ብሄራቸውን Identify ቢያደርጉ የጥቃት ሰለባ ሊሆኑ ስለሚችሉ በነገራችን ላይ አሜሪካም በትራምፕ አስተዳደር ጥቃት ይደርስብናል ያሉ ጥቁሮች ቅሬታ ስላቀረቡ ህዝብና ቤት ቆጠራው እያወዛገበ ነው 4የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማከናወን ብቁ እና ተዓማኒ ተቋም፣ ባለሙያና ቴክኖሎች ባለመኖሩ 5የህዝብና ቤት ቆጠራው ...
30
‹‹ያጣነውን ታማኝነት በአራተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጣራ መመለስ አለብን፡፡›› ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን ባሕር ዳር፡ መጋቢት 022011ዓም አብመድ በአራተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ከዚህ በፊት በአማራ ክልል ሕዝብ የተሰሩት ስህተቶች እንዳይደገሙ ሁሉም የክልሉ ሕዝብ በጥንቃቄ መሥራት እንዳለበት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡ መጋቢት 29 ቀን 2011ዓም ለሚደረገው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ እስካሁን ክልሉ የሄደበት ደረጃ እና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ የክልሉ ...
31
በመጋቢት ወር መጨረሻ 4ኛውን ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራን ለማካሄድ ዝግጅቶች እየተደረገ መሆኑን፣ ቆጠራውን የሚያካሂደው ማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል። የዚህ ቆጠራ ሂደት ዋነኛው ፈተና ብሄርን ከማስመዝገብ ጋር የተያያዘ ነው። በቆጠራ ቅጹ ላይ ዜጎች ማንነታቸውን እንዲገልጹ የሚገደዱት በብሄራቸው እንጅ በዜግነታቸው ወይም በኢትዮጵያዊነታቸው አለመሆኑን የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማሃኝ አስረስ ይናገራሉ። በቅጹ ላይ ኢትዮጵያዊነት እንደ አንድ መስፈርት አለመቀመጡ፣ ...
32
የህዝብና ቤቶች ቆጠራውን ማስተላለፍ ለስኬታማ ውጤት የተሻለ አማራጭ ነው አበራ ውሂብ ዶር እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በ 1984 በተደረገው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤቶች ቆጠራ ላይ የማከላዊ እስታቲስቲክስ ጽቤት ሰራተኛ ሆኜ ገና ከኮሌጅ በወጣሁ በሁለት አመት የተሳተፍኩበትና ለሃገሪቱም የመጀመሪያው ስለነበር በብዛት ትዝ የሚለኝና የማረሳው ግዜ ነበር። ወቅቱ የደርግ ጊዜ ነበርና በሲዳሞ ክፍለ ሃገር በያቤሎ አውራጃ የቴክኒክ ሃላፊ ሆኜ ለሶስት ወራት ያህል በመስክ ላይ ስለነበርኩ በመሬት ላይ የነበረውን ሁኔታ በደን...
33
በዚህ ዓመት በአማራ ክልል የሚከናወነው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ የጠፉ ዜጎችን የማፈላለግ ጉዳይ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ባለፉት 12 ዓመታት ከ2 ነጥብ 5 እስከ 3 ሚሊዮን የሚደርሱ የአማራ ክልል ነዋሪዎች መጥፋታቸውንና የጠፉት ነዋሪዎች ከአንድ ትልቅ ዞን ሕዝብ ቁጥር በላይ ይሆናሉ እንደሚሆኑ የአማራ ክልል ፕላን ኮሚሽን ባለሙያ ተናገሩ፡፡ ባሕር ዳር፡ የካቲት 262011 ዓምአብመድ ኢትዮጵያ ከአሁን በፊት ለሦስት ጊዜ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ሥራዎችን አካሂዳለች፡፡ ከአከናወነቻቸው የሕዝብና ቤት ቆጠራዎች በ19...
34
የህዝብና ቤት ቆጠራ የለም። ☆☆☆☆☆ የህዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት በቀጣይ አመታት በሀገሪቷ ላይ ለሚደረጉ ማንኛውም የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ዉሳኔዎች መሰረት ነዉ። የኢትዮጵያ መንግስት መጋቢት 292011 ዓም ሊያካሄድ ያሰበዉ የህዝብና ቤት ቆጠራ ሀ በአገሪቷ ወቅታዊ የፀጥታ ችግር ለ የአማራ ህዝብ የማንነትና የወሰን ጥያቄዎች እልባት ሳያገኙ ሐ የአማራ ህዝብ በየአቅጣጫው እየተፈናቀለ ባለበት ሁኔታ መ በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ዙሪያ የአብይ አህመድ ፓርቲ ኦዴፓ በለማ መገርሳና ታከለ ኡማ አስፈ...
35
‹‹ሦስት ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያለ በጀት እየኖረ ነው፡፡ ስለዚህም 4ኛው ዙር የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ለአማራ ሕዝብ ልዩ ጥቅም አለው፡፡›› ፕላን ኮሚሽን ባሕር ዳር፡ መጋቢት 062011ዓም አብመድ አራተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ መካሄዱ ለአማራ ክልል ሕዝብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በአማራ ፕላን ኮሚሽን የሥነ ሕዝብ ባለሙያ አቶ ታደለ አሳቤ ተናግረዋል፡፡ አቶ ታደለ እንደሚሉት በሀገራችን በ1976፣ 87 እና 99 ዓመተ ምሕረቶች ለሦስት ጊዜያት ቆጠራዎች ተካሂደዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ቆጠራዎች ...
36
የሕዝብና ቤት ቆጠራው ወቅታዊ ሁኔታ ሀ የደቡብ ክልል አሁን ባለው ሁኔታ ለማስቆጠር አቅም የለኝም ብሏል። አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ማጓጓዝም ሆነ ቆጣሪዎቹን ማሰልጠን አልቻልኩም ማለቱም ተሰምቷል። ለ የሶማሊ ክልል አክቲቪስቶች ሕዝብና ቤት ቆጠራ መካሄድ የለበትም የሚል አቋም ይዘው ሕዝቡን እያስተባበሩ ነው። ባለፈው የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወሳል። ሐ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። ስብሰባው የተጠራበት ዋና ምክኒያት ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎቹ አካባቢዎች ቆጠራውን በታቀደለት...
37
4ተኛው ዙር የህዝብ ቤት ቆጠራ ባሕር ዳር፡ጥር 232011 ዓምአብመድ 1 የህዝብ ቤት ቆጠራ ትርጉም የህዝብ ቤት ቆጠራ በተወሰነ ወቅት እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወይም በሀገር ውስጥ በተወሰነ የአስተዳደር ክልል ስለአለው የህዝብ ብዛት እና የስነ ህዝብ ባህሪያት፣ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ወይም በተወሰነ የአስተዳደር ክልል ስለሚገኙ ቤቶች ብዛት ፣ስለ ቤቶች ሁኔታ የሚገልፁ ስታስቲካዊ ሁኔታ መረጃዎችን የመሰብሰብ ፣የማጠናቀር፣የመተንተን፣ትክክለኛነቱንም በመገምገም የትንተና ...
38
የሕዝብ እና የቤት ቆጠራን አስመልክቶ፣ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄአብን የተሰጠ የአቋም መግለጫ በ19989 ዓም የተደረገውን የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ተከትሎ፣ መንግሥት ባወጣው ይፋዊ የቆጠራ ውጤት፣ 25 ሚሊየን የሆነ የአማራ ሕዝብ ጠፍቷል ተብሎ ለአገራችን ፓርላማ ሪፖርት መደረጉ ይታወቃል፡፡ በመንግሥት የታመነው እና ጠፋ የተባለው የአማራ ሕዝብ ብዛት 25 ሚሊየን ቢሆንም፣ እኤአ የ1984፣ የ1994 እና የ2007ን የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ያጠኑ ምሁራን፣ የታዳጊ አገሮችን የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ፣ የሌሎች ...
39
4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማከናወን መምህራንን ጨምሮ 180 ሺህ ሰራተኞች ይሰማራሉ ተባለ On Feb 6 2019 1235 አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2011 ኤፍቢሲ አራተኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማከናወን መምህራን፣ የግብርናና የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 180 ሺህ የመንግስት ሰራተኞች እንደሚሰማሩ ተገለጸ። የማዕከላዊ ስታቲስትክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ቆጠራው ከስህተት የጸዳ ለማድረግ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይልና በአሰራር ስርዓት ልዩ ...
40
በህዝብና ቤት ቆጠራ ላይ የመረጃ ደህንነትና የሳይበር ጥቃት እንዳይኖር ዝግጅት ተደርጓል አዲስ አበባ ጥር 232011 በአራተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ የመረጃ ደህንነትና የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል ዝግጅት መደረጉን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ቆጠራው ተዓማኒ የሆነ ውጤት እንዲኖረው ለማስቻል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር መዘርጋቱም ተጠቁሟል። ኤጀንሲው የቆጠራውን ቀንና የዝግጅት ስራዎችን ዛሬ ይፋ ሲያደርግ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቢራቱ ይገዙ እንደተናገሩት ፤ የዘንድሮውን የህዝብና ቤ...
41
አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ በቴክኖሎጂ ታግዞ እንደሚከናወን ተገለጸ Wed Feb 20 2019በአድማሱ አራጋውአካሉ ጰጥሮስ የሀገር ዉስጥ ዜና በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ከፖለቲካና ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ በቴክኖሎጂ ታግዞ እንደሚሰራ የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ገልጿል፡፡ በዘንድሮ የህዝብና ቤት ቆጠራ በተለያዩ ምክንያቶች ከአከባቢያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችንም መቁጠር የሚያስችል ቴክኒክ መዘጋጀቱን የኮሚሽኑ ፀሓፊ አቶ ቢራቱ ገዙ ለዋልታ ቴሌቭዥ...
42
የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ መጋቢት 29 ሊካሄድ ነው፡፡ ፡፡ ባሕር ዳር፡ጥር 232011 ዓምአብመድ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ እና የኢትዮጵያ ፕላን ኮሚሽን ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ 4ኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ በሚቀጥለው መጋቢት 292011 ዓም ይካሄዳል፡፡ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ በ1979፣1987 እና 1990 ዓም ላይ ለሶስት ጊዜ ሲካሄድ በርካታ ቅሬታዎች ይነሱበት ነበር፡፡በተለይም በአማራ ...
43
4ኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ተራዘመ፡፡ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 092011ዓም አብመድ መጋቢት 29 ቀን 2011ዓም እንደሚካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው 4ኛው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በድጋሜ ተራዘመ፡፡ ከዓመት በፊት ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በተወሰኑ ክልሎች በነበረ የፀጥታ ችግር መራዘሙ የሚታወስ ነው፡፡ የፀጥታ ችግሮች ተቀርፈው በዚህ ዓመት እንደሚካሄድ ተጠብቆ የነበረና ሰፊ ቅድመ ዝግጅት የተደረገ ቢሆንም ዋልታ እንደዘገበው የሕዝብና ቤት ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፡፡ አብ...
44
የሕዝብ አለመቆጠር ክልሉን ጥቅም እንደሚያሳጣው ፟፟መገንዘብ እንደሚገባ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አሰማኸኝ አሳሰቡ ባሕር ዳር፡ ጥር 292011 ዓም አብመድ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ እንደሚከናወን አቶ አሰማኸኝ አስረስ ተናገሩ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በየ10 ዓመቱ የሚደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ መጋቢት 29 ይጀመራል፡፡ ለአራተኛ ጊዜ ነው ቆጠራው የሚከናወነው፡፡ ለህዝብ እና ቤት ቆጠራው የሚያግዙ 180 ሺህ የሚጠጉ ታብሌት ኮምፒውተሮች ተገዝተ...
45
ግጭት ያለባቸውን አካባቢዎችና የተፈናቀሉ ዜጎችን ያማከለ ቆጠራ ለማካሄድ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ መጋቢት 29 በሚጀመረው የህዝብና ቤት ቆጠራ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችና የተፈናቀሉ ዜጎችን ያማከለ ቆጠራ እንደሚካሄድ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችንና የተፈናቀሉ ዜጎችን ጉዳይ በተመለከተ እያንዳንዱ ክልል ከለውጡ በኋላ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ ከሁለት ወራት በፊት ስብሰባ ተደርጎ መገምገሙን በኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነትና መረጃ አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዲ ገል...
46
‹‹ባለፈው የሕዝብና ቤት ቆጠራ የአማራ ክልል ሕዝብ ቅሬታ ነበረው፤ አሁን ይህን ቅሬታ ለመፍታት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል፡፡›› የአማራ ክልል ፕላን ኮሚሽን ባሕር ዳር፡ የካቲት 262011 ዓምአብመድ በአማራ ክልል ባለፉት ጊዜያት የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ሲካሄድ የተሠሩ ስህተቶች ከዕውቀት ማነስ የመነጩ እንደነበሩና ስህተቶችን ለማረም መንግሥት በስፋት ሊያስተምር እንደሚገባ አብመድ ያነጋገራቸው አስተያዬት ሰጭዎች ተናገሩ፡፡ አራተኛውን የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ በተመለከተ ለአብመድ አስተያዬት የሰጡት በአማራ ክ...
47
ስለሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ግንዛቤው እንደሌላቸው አብመድ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ገለጹ ባሕር ዳር፡ የካቲት 302011 ዓምአብመድ አርሶ አደሮች ስለሕዝብ እና ቤት ቆጠራው ዕውቅና እንዲኖራቸው እየሠራ መሆኑን ደግሞ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄደው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓም ይጀመራል፡፡ ለሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ከወዲሁ ሰፊ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረገ መሆኑንም በመንግሥት በኩል እየተገለጸ ነው፡፡ ከዝግጅቶች መካከል ኅ...
48
የ3ኛው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት እንዲሰረዝ አብን ጠየቀ። ባሕር ዳር፡ መጋቢት 102011ዓም አብመድ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን በ1999 ዓም የተካሄደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት እንዲሰረዝ ጠይቋል። ንቅናቄው ዛሬ በሰጠው መግለጫ በቆጠራው የተሳተፉ ባለሙያዎችና ባለስልጣናት ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸውም አቋሙን አሳውቋል። በቆጠራው ለተፈጠረው ስህተትም መንግስት ካሳ መክፈል እንዳለበት ነው አብን የጠየቀው። በአዲስ አበባ እና አካባቢው ስለታማ ነገሮችን በመያዝ ከህግ አግባብ ውጭ እተንቀሳቀሱ እና...
49
የሕዝብና ቤት ቆጠራ መራዘም ጉዳይ የፌደራል መንግሥት ከኦሮሞ ኤሊቶችና ኦነግ ውጭ በሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ለአንዳቸውም መልስ ሲሰጡ አይታይም፤ ይህ አንድም ንቀት አሊያም ምን ታመጣላችሁ ነው፡፡ በንቀት እየተሔደበት ያለው አንደኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራው ነው፡፡ አጀንዳ በአጀንዳ ላይ እየደራረቡ የሕዝብና ቤት ቆጠራው የሚጀመርበት ቀን ላይ መድረስን ነው እንደመፍትሔ ያደረጉት፡፡ ይህ አካሔድ አደገኛ እንደሆነ እንዲረዱን እንፈልጋለን፡፡ ምናልባትም በጅምር የቀረው አቢዮት መጨረሻ ሊሆን ይችላል፡፡ በትንሹ ሊቆ...
50
ባለፋት ሶስት ጊዚያት በኢትዮጵያ በተካሄዱት የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራዎች የተሰሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን አሳሰበ፡፡ ባሕር ዳር፡ የካቲት 082011 ዓምአብመድ ባለፋት ሶስት ጊዚያት የተካሄዱትን የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራዎች መነሻ በማድረግ ቀጣይ በሚካሔደው ቆጠራ ስጋቶች እና መደረግ በሚገባቸው ጥንቃቄዎች ላይ በአዲስ አበባ ውይይት እያካሄደ ነው። ባለፋት የቆጠራ ጊዚያት የተሠሩት ስህተቶች መጋቢት 29 2011 ዓም በሚካሄደው 4ኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ...
51
የቆጠራ ካርታ ባልተዘጋጀላቸው አካባቢዎች የህዝብ እና ቤት ቆጠራው በልዩ ሁኔታ ይካሄዳል On Feb 25 2019 810 አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2011 ኤፍ ቢ ሲ የቆጠራ ካርታ ባልተዘጋጀላቸው የተወሰኑ አካባቢዎች የህዝብ እና ቤት ቆጠራው በልዩ ሁኔታ እንደሚካሄድ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ባለፈው አመት መካሄድ የነበረበት 4ኛው ብሄራዊ የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ መጋቢት 29 ቀን ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ነው። ለቆጠራው የሚያስፈልጉ የግብዓት ስርጭት እና የቆ...
52
አዲስ አበባ መጋቢት 62011 በተያዘው ወር መጨረሻ የሚጀመረው 4ኛው ዙር አገር አቀፍ ሕዝብና ቤት ቆጠራ ዝግጅት መጠናቀቁን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት አበራሽ ታሪኩ ከሌሎች የኤጀንሲው የስራ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓም በይፋ የሚጀመረው 4ኛው ዙር የሕዝብና ቤት ቆጠራ የካርታ ስራ፣ የመረጃ ቋት ማሳደግ፣ የሰው ኃይል ማሟላት፣ ሎጂስቲክስና ስልጠና ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። ”ለ...
53
4ኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ የብሄራዊ ፕላንና ልማት ኮሚሽን አራተኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 ጀምሮ እንደሚካሄድ አስታወቀ። የህዝብና ቤት ቆጠራውን አስመልክቶ በዛሬው እለት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ መግለጫ ተሰጥተዋል። ኮሚሽነሯ በመግለጫቸውም መጋቢት 29 ቀን 2011 የሚጀመረውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ግልጽና ተዓማኒ በሆነ መልኩ ለማካሄድ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል። እንዲሁም ከዚህ ቀደም የነበሩ ቅሬታዎች እንዳይ...
54
አዲስ አበባ መጋቢት 102011 በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወገኖች ወደ ነበሩበት ቀዬ የመመለሱ ስራ በበቂ ሁኔታ ባለመሰራቱ 4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ እንዲራዘም የዉሳኔ ሀሳብ ቀረበ። የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ባካሄደው ስብሰባ አራተኛዉን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማካሄድ የተደረገዉን ዝግጅት በመገምገም የውሳኔ ሃሳቦች አሳልፏል። በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች ትርጉም ባለው ደረጃ ወደ ነበሩበት ቦታ እስኪመለሱ ድረስ ቆጠራውን ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ እንዲ...
55
አዲስ አበባ ሰኔ 32011 የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የሕዝብና ቤት ቆጠራ መራዘምን አስመልክቶ በቀረቡ የተለያዩ ሃሳቦች ላይ ሰፊ ክርክር በማድረግ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ወስነዋል። የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ዛሬ ባደረጉት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ ልዩ የጋራ ስብሰባ የ2011 ዓም የሕዝብና ቤት ቆጠራ ይራዘም እና አይራዘም በሚሉት ሃሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። የምክር ቤቶቹ አባላት ቆጠራው ይራዘም፣ አይራዘም፣ የሚራዘምበት የጊዜ ገደብ ላልተወሰነ ጊዜ ይባልና ለ...
56
የ4ኛው ህዝብና ቤት ቆጠራ ተሳታፊዎች ስልጠና በባህር ዳር ከተማ ተጀመረ የአራተኛው ህዝብና ቤት ቆጠራ ተሳታፊዎች ስልጠና በባህር ዳር ከተማ ተጀመረ ፡፡ በአማራ ክልል አመራር ኢንስቲትዩት ማዕከል የምዕራብ አማራና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአራተኛው ህዝብና ቤት ቆጠራ ተሳታፊዎች ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል፡፡ በዚህ የሥልጠና መርሃ ግብር የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ሰልጣኞቹ በቆጠራው ችግሮች እንዳይከሰቱና የታሪክ ተወ...
57
ቤት የሌላቸው እና የተፈናቀሉ ዜጎች የሚቆጠሩበት ስልት እንደተዘረጋ የማዕከላዊ ስታቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 032011ዓም አብመድ መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓም በመላው ሀገሪቱ የሚደረገው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ከመቸውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው እየተነገረ ነው። ለዚህም በሕዝቡ በኩል ‹‹ሁሉም እንዴት እና በምን መልኩ ልንቆጠር ወይም ሊቆጠሩ ይችላሉ›› የሚሉት ጥያቄዎች እየተነሱ ነው፡፡ የተፈናቀሉ፣ ቤት የሌላቸው እና ቤታቸው የተቃጠለባቸው ዜጎች እንዴት እንደሚቆጠሩ የ...
58
ሴት ልጃችሁ ስለ ወር አበባ በቅድሚያ አውቃ እንድትዘጋጅ መርዳት ልጃገረዶች ለአቅመ ሔዋን የሚደርሱበት ዕድሜ ብዙ ለውጦች የሚካሄዱበት ጊዜ ነው። ልጃገረዶች በዚህ የእድገት ወቅት ከሚያጋጥሟቸው ለውጦች መካከል ጉልህ ሥፍራ የሚሰጠው የወር አበባ መጀመር ነው። ልጃገረዶች የወር አበባቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመጣ ሊጨነቁ እንዲሁም የተዘበራረቀ ስሜት ሊኖራቸው ይችላል። ለአቅመ ሔዋን ከመድረስ ጋር ተያይዘው እንደሚከሰቱት ሌሎች ለውጦች ሁሉ የወር አበባ መጀመርም ግራ የሚያጋባ ሊሆን ይችላል። ብዙ ጊዜ እንደሚታየው...
59
ወር አበባ ሴት ልጅ የ ወር አበባ በምታይባቸው ቀናቶች ፈፅሞ ልታደርጋቸው የማይገቡ ካረገቻቸው ትልቅ የ ጤና ቀውስ የሚያስከትሉ 4 ነገሮች እነሆ ከ አስደናቂ እውነታ …። 1ኛ ቀዝቃዛ ውሀ ፣ በረዶ ቤት የገባ ማንኛውም መጠጥ ፣ ማንኛውንም አይነት የ ለስላሳ መጠጥ እና coconut መጠቀም በጣም አይመከርም ምክንያቱም በረዶ የ ወር አበባ ደምን በመሀፀን ግድግዳ ላይ ተጣብቆ እንዲቀር ያደርጋል ይህ ደግሞ ከባድ ለሆነው የ UTERUS CANCER ያጋልጣል። 2ኛ ሻምፖ መጠቀም የጤና ባለሙያዎች አጥብቀው ይከለ...
60
የወር አበባ ችግር መደበኛ የወር አበባ መደበኛ የወር አበባ by አንድሪያ ቺሾልም MD በቦርዱ በተረጋገጠ ሐኪም በመገምገም የወር አበባ አጠቃላይ ሁኔታ ብዙ ጥንታዊ ሚስቶች ታሪኮች እና ባህላዊ ወይም ሃይማኖታዊ አመለካከቶች ጠንካራ የህክምና እውቀትን ይሸፍናሉ ስለዚህ የወር አበባ ምን እንደሆነ እንዴት እንደሚሰራ እና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው በወር አበባ ጊዜ የማሕጸን አጥንት እይታ የወር አበባ ምንድን ነው የወር አበባዎ እኩይ ተግባር እስከሚቆሙበት የመጀመሪያ ጊዜ ድረስ ...
61
ስለ ወር አበባ የተሳሳቱ አፈ ታሪኮች የወር አበባ ወደ ጉብታ ከወጣት አንስቶ እስከ ማረጥ ድረስ ይህ የሴቲቱ የሕይወት ጊዜ የመራባት ህዝባዊ ተብሎ ይጠራል የወር አበባ መኖሩ ስለ ሕልውናው በየወሩ ያስታውሰናል ስለእሷ ሁሉንም ነገር ታውቃለህ ብለው ያስባሉ እስቲ እንፈትሽ አፈታሪክ ቁጥር 1 ብዙ ደም ከተፈሰሰባቸው በኋላ የደም ማነስ ሊያድግ ይችላል በእርግጥ ባለ ብዙ ደም መፍሰስ ከብዙ አሥር አባቶች ጋር በሚሆንበት ቀን ይህ ነው ብዙ ብረት ሊያጡ ይችላሉ እንዲሁም ሰውነታችን ይህን ጠቃሚ እና ጠቃሚ የ...
62
የወር አበባ መቆም በደም ሥር ጤና ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል – ጥናት ByTeshoPublished on February 13 2020 SHARE TWEET COMMENT የወር አበባ ማየት ማቆም በሴቶች የደም ሥር ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው አዲስ ጥናት አመላከተ፡፡ በተፈጥሮ ሴቶች የወር አበባ ማየት የሚያቆሙት በ45 እና 50 ዓመት መካከል ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆኑ ይታወቃል። ሰሞኑን ይፋ የሆነው አዲስ ጥናትም የዕድሜ መግፋትን ተከትሎ የሚከሰተው የወር አበባ መቆም የሴቶችን የደም ስር ጤና የሚያውክ...
64
የወር አበባ ለምን በአንዳንድ ሴቶች ላይ ህመም ያስከትላል 7 ጁን 2018 ይህንን ለሰው አጋራ Facebook ይህንን ለሰው አጋራ Messenger ይህንን ለሰው አጋራ Twitter ይህንን ለሰው አጋራ ኢሜይል ያጋሩ የወር አበባ ዑደት የወር አበባ ተፈጥሯዊ ጸጋ ነው። የመተንፈስ ወይም የመመገብ ያህል ከተፈጥሮ ሂደቶች አንዱ ነው። የምድርን እኩሌታ የያዙት ሴቶች ወርሀዊ ዑደትም ነው። ሆኖም ስለ ወር አበባ ማውራት እንደ ሀጢያት ይቆጠራል። ከወር አበባ ጋር የተያያዙ የተዛቡ አመለካከቶችም የትለሌ ናቸው። ከደ...
65
ብዙዎቻችሁ በጠየቃችሁን መሰረት ስለ ወር አበባ ኡደትን በመከተል እርግዝናን መከላከል ተጨማሪ ማብራሪያ ይዘን ቀርበናል። የወር አበባ ኡደትን በመከተል እርግዝናን ለመከላከል የሚመከሩ ነገሮች፡፡ የወር አበባ ዑደትን በመከተል እርግዝናን ለመከላከል የወር አበባዎ ሳይዛባ በትክክል የሚመጣ መሆን መቻል አለበት፡፡ · በመጀመሪያ ለ6 እስከ 12 ወራት የወር አበባ ዑደትዎን መመዝገብ · በመቀጠል ለአጭር ጊዜ የቆየዉንትንሹን የወር አበባ ዑደት መለየት፡ ከትንሹ የወር አበባ ዑደትዎ ላይ 18ን መቀነስ፡፡ የሚመጣዉ ...
66
ስለ የወር አበባ ምን ያህል ያውቃሉ RSA ቤተሰብ September 27 2018 1 Minute ሴቶች ስለ ወር አበባቸው ኡደት በደንብ ማወቃቸው ለራሳቸው ኖርማል የሆነውን፣ ለእርግዝና ምቹ የሆኑትን ቀናት፣ የወር አበባቸው ሳይመጣ ሲቀርና እንዲሁም ሲዘበራረቅ ለመለየት ይጠቅማቸዋል፡፡ የወር አበባ ኡደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡ በየወሩ ኦቫሪ የእንቁላል አቃፊ ከተባለው የሰውነት ክፍል ኦቩሌሽን ውጻት ...
67
የወር አበባ ስለ የወር አበባ ምን ያህል ያውቃሉ ሴቶች ስለ ወር አበባቸው ኡደት በደንብ ማወቃቸው ለራሳቸው ኖርማል የሆነውን፣ ለእርግዝና ምቹ የሆኑትን ቀናት፣ የወር አበባቸው ሳይመጣ ሲቀርና እንዲሁም ሲዘበራረቅ ለመለየት ይጠቅማቸዋል፡፡ የወር አበባ ኡደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡ በየወሩ ኦቫሪ የእንቁላል አቃፊ ከተባለው የሰውነት ክፍል ኦቩሌሽን ውጻት በተባለ ስርአት አንድ እንቁላል ይወጣል፡፡ … ...
68
የወር አበባ መቋረጥ ስለ የወር አበባ ምን ያህል ያውቃሉ ሴቶች ስለ ወር አበባቸው ኡደት በደንብ ማወቃቸው ለራሳቸው ኖርማል የሆነውን፣ ለእርግዝና ምቹ የሆኑትን ቀናት፣ የወር አበባቸው ሳይመጣ ሲቀርና እንዲሁም ሲዘበራረቅ ለመለየት ይጠቅማቸዋል፡፡ የወር አበባ ኡደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡ በየወሩ ኦቫሪ የእንቁላል አቃፊ ከተባለው የሰውነት ክፍል ኦቩሌሽን ውጻት በተባለ ስርአት አንድ እንቁላል ይወጣል...
69
የወር አበባ ኡደት ስለ የወር አበባ ምን ያህል ያውቃሉ ሴቶች ስለ ወር አበባቸው ኡደት በደንብ ማወቃቸው ለራሳቸው ኖርማል የሆነውን፣ ለእርግዝና ምቹ የሆኑትን ቀናት፣ የወር አበባቸው ሳይመጣ ሲቀርና እንዲሁም ሲዘበራረቅ ለመለየት ይጠቅማቸዋል፡፡ የወር አበባ ኡደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡ በየወሩ ኦቫሪ የእንቁላል አቃፊ ከተባለው የሰውነት ክፍል ኦቩሌሽን ውጻት በተባለ ስርአት አንድ እንቁላል ይወጣል፡...
71
በእርግዝና ወቅት የወር አበባ Written by ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ font size decrease font size increase font size Print Email Rate this item1 2 3 4 5 26 votes በዚህ እትም ለንባብ ያቀረብነው በእርግዝና ወቅት የወር አበባ ይታያልን የሚለውንና የወር አበባ ሳይታይ መኖር ይቻላልን በሚል ከሁለት ተሳታፊዎች የደረሱንን ጥያቄ ዎች መሰረት በማድረግ የተጻፈ ነው፡፡ የመጀመሪያው ጥያቄ እንዲህ ይላል፡፡ የተከበራችሁ የላንቺና ላንተ ፕሮግራም አቅራቢዎች እ...
72
ሰሙነ ሕማማት ምን ማለት ነው ሰሙነ ሕማማት ለምን ይታሰባል ቅድስት ቤተክርስቲያን ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙና ሕማማት የሕማማት ሳምንት በማለት ትዘክረዋለች፡፡ ሕማማት የሚለው ቃል ‹ሐመ፤ ታመመ› ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን፤ 1የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማሙና ሞቱ የሚዘከርት ነው፡፡ 2 በሌላም በኩል ይህ ሳምንት ከአዳምእስከ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነበሩ ነፍሳት በሲኦል የቆዩበት የአምስት ሺ አምስ መቶ የመከራ፤ የፍዳና የኵነኔ ዘመን መታሰቢያ ስለሆ...
73
ሰሙነ ሕማማት እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰኝ ያድርሳችሁ አሜን አላይን ቅዱስ ገብረኤል ህማሙን በስግደት አያከበሩ ነው፡፡ እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጠን፡፡ በረከታቹህ ይድረሰን ስንቶቻችን ህማሙን በቤታችን ሆነን እያሰብን ነው
74
ሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት ዘጠኝ ሰዓት፣ በሰርክ በዐስራ አንድ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ። በዚህ ሳምንት በተለይ ካ...
75
የሰሙነ ሕማማት ረቡዕ ምክረ አይሁድ ይባላል፡ ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተዓምራቱን የሚያደንቁ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆርቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶ...
76
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። «ሰሙነ ሕማማት» ሰሙነ ሕማማት የሁለት ቃላት ጥምር ውጤት ነው፡፡ “ሰሙን” የሚለው ቃል “ሰመነ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ስምንት ቀኖች ወይም ሳምንት ማለት ነው፡፡ ሕማማት የሚለው ቃልም እንደዚሁ “ሐመመ” ወይም “ሐመ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን መከራዎች ማለት ነው፡፡ «ሕማማት» የምንለው ለብዙ ሲሆን ነው፡፡ ለአንድ ወይም ለነጠላ ሲሆን ደግሞ ‹‹ሕማም›› እንላለን፡፡ እንግዲህ ሁለቱን ቃላት በማናበብ «ሰሙነ ሕማማት» ስንል ...
77
ሰሙነ ህማማት ዘሐሙስ ጸሎተ ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ ማቴ 26፣ 3646 ዮሐ17 ሕፅበተ ሐሙስ ይባላል፡ ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን...
78
ሰሞነ ህማማት እና ሳምንታቱ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የታላቁ ሁዳዴ ፆም መገባደጃ ሳምንት ሰሞነ ህማማት ይባላል፡፡ግሪካውያን ክርስቲያኖች ደግሞ ታላቁ ሳምንት the super week ይሉታል፡፡ ጌታ ከተስፋዋ ምድር እስራኤል ከቤተ ፋጌ ወደ እየሩሳሌም አደባባይ ትህትናንበተግባር በማስተማር በአህያ መጥቷል፡፡ ደቅመዛሙርቱም በዘንባባ ተቀብለውታል፡፡ ዘንባባ የተስፋ እና የጌታ ዘላለማዊ ስልጣን እንደማሳያ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ከፋሲካ በፊት ያለው እሁድ ሆሳዕና ይባላል፡፡ በአርማይክ በእብራይሰ...
79
ሰሙነ ሕማማት ከዕለተ ሰኑይ እስከ ቀዳሚት ሰንበት – በመምህር ቸርነት አበበ By Getu Temesgen April 3 20183105 0 Share on Facebook Tweet on Twitter መጋቢት ፳፬ ቀን ፳፻፲ ዓም መግቢያ ከአባታችን አዳም በደል ወይም ስሕተት በኋላ በሕማማት፣ በደዌያት፣ በመቅሠፍታት፣ ወዘተ በብዙ መከራ የሰው ልጅ ሊኖርባቸው ግድ የኾነባቸው ዘመናት ጥቂቶች አልነበሩም፡፡ የሰው ልጅ ቢያጠፋ፣ ቢበድል፣ ከሕገ እግዚአብሔር ቢወጣ እንኳን የዋህ፣ ታጋሽ፣ ቸር፣ አዛኝ የኾነው አምላክ የ...
80
ሰሙነ ሕማማት በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ሰሙነ ሕማማት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከትንሣኤ በፊት ያለው አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት የሕማማት ሳምንት በማለት ትዘክረዋለች። ሕማማት የሚለው ቃል ሐመ፣ ታመመ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማሙና ሞቱ የሚዘከርበት ሳምንት ነው።ሰሙነ ሕማማት በላቲን Hebdomas Sancta or Hebdomas Maior፣ በግሪክ ደግሞ Ἁγία καὶ Μεγάλη Ἑβδομάς Hagia kai Megale Hebdom...
81
ሰሙነ ሕማማት April 9 2012 at 503 AM በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት እጅግ ከሚወደዱ እና ከሚናፈቁ ወቅቶች አንዱ ሰሙነ ሕማማት ነው፡፡ በዕለተ ሆሳዕና ጀምሮ በዕለተ ትንሣኤ የሚጠናቀቀው እጅግ ላቅ ያለ መንፈሳዊ ሕይወት የሚታ ይበት ጊዜ ነው፡፡ በላቲን Hebdomas Sancta or Hebdomas Maior፣ በግሪክ ደግሞ Ἁγία καὶ Μεγάλη Ἑβδομάς Hagia kai Megale Hebdomas ታላቁ ሳምንት ተብሎ ይጠራል፡፡ በኛ ደግሞ ሰሙነ ሕማማት፡፡ የሕማማትን ወቅት ከመጀመርያ...
82
ሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ረቡዕ በመር ኃይለ ማርያም ላቀው ሚያዝያ ፫ ቀን ፳፻፱ ዓም ሰሙነ ሕማማት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር ስለ ተገለጠበት፣ የመሥዋዕትነት ሥራ ስለ የተሠራበት፣ የሰው ልጆች ድኅነት ስለ ተፈጸመበት፣ መድኃኔ ዓለም በመስቀል ተሰቅሎ ለእኛ ቤዛ መኾኑ በስፋት ስለሚነገርበት ‹ቅዱስ ሳምንት› ይባላል፡፡ በተጨማሪም ‹የመጨረሻ ሳምንት› ተብሎ ይጠራል፡፡ ይኸውም ጌታችን አምላችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በመዋዕለ ሥጋዌው ለፈጸማቸው የቤዛነትና የአርአያነት ተግ...
83
ሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ መጋቢት፳፻፪ ዓም ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት ፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት ፤ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት ዘጠኝ ሰዓት ፣ በሰርክ በዐስራ አንድ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግ...
84
ሰሙነ ሕማማት በመምህር ጌቱ መንክር ሰሙነ ሕማማት የሚለው የጊዜ ስያሜ ሰሙን እና ሕማማት የሚሉ የሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን ሰሙን ስምንት፣ ሳምንት ፤ ሕማም ወይም በብዙ ሕማማት ማለት ደግሞ በቁሙ ሕመም ሕመሞች ፣ መከራ፣ እንግልት ማለት ነው። በጥቅሉ ሰሙነ ሕማማት ማለት የሕማም የመከራ ሳምንት ማለት ነው። ሳምንቱ በዚህ ስያሜ የተጠራው ጌታ መዋዕለ ስብከቱን ሲፈጽም በለበሰው ሥጋ ብዙ ጸዋትወ መከራ የተቀበለበት ሳምንት በመሆኑ ነው። መከራ የተቀበለው በርግጥ ከኀሙስ ሌሊት ጀምሮ ቢሆንም በመጋቢት ፳፪ ...
85
ሰሙነ ሕማማት በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት እጅግ ከሚወደዱ እና ከሚናፈቁ ወቅቶች አንዱ ሰሙነ ሕማማት ነው፡፡ በዕለተ ሆሳዕና ጀምሮ በዕለተ ትንሣኤ የሚጠናቀቀው እጅግ ላቅ ያለ መንፈሳዊ ሕይወት የሚታይበት ጊዜ ነው፡፡ በላቲን Hebdomas Sancta or Hebdomas Maior፣ በግሪክ ደግሞ Ἁγία καὶ Μεγάλη Ἑβδομάς Hagia kai Megale Hebdomas ታላቁ ሳምንት ተብሎ ይጠራል፡፡ በኛ ደግሞ ሰሙነ ሕማማት፡፡ የሕማማትን ወቅት ከመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ክርስቲያኖች ...
100
የእምዬ ምኒልክ ውለታ ክብርና ሞገስ የጥቁር ህዝብ ተምሳሌት ለሆኑ ታላላቅ አያቶቻችን ዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2009 ዓም ስመ ገናናው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ከዚህ አለም በስጋ ካለፉ 103 ዓመት ሲሆናቸው አባ መላ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ደግሞ ዘጠና አመት ሆናቸው። ዳግማዊ አጤ ምኒልክና አባ መላ በስጋ ካለፉ ወደ አንድ ክፍለ ዘመን የሚጠጋ ዘመን ቢቆጠርም ስለታላቅነታቸውና ስለአሻራቸው ግን ዛሬም ገና አውርተን አልጠገብንም።  አባ መላ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ በንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ...
101
አወዛጋቢው Isho Birhan ስለ አድዋ ይናገራል ። አደዋ የሚኒልክ እጅ ስራ ሚኒሊክ ልትጠላዉ ትችላለህ ፤ ደግሞም ልትወደዉ ትችላለህ ። ነገር ግን ሚኒሊክ ተራ ስብዕና እንዳልነበረ ለመረዳት አይከብድም ። ሚኒሊክ ዉስብስብ ሰዉ ነዉ ። ረቂቅ ነዉ ። ደግሞ አድማጭ ነዉ ። ሚኒሊክ እንደ ገሞራ እሳት የሚፋጅ ነዉ ። ደግሞ እንደ ምንጭ ዉሃ ገር ነዉ ። ሚኒሊክ ሀገር መመስረት ፣ ግዛት ማስተዳደር ያዉቃል ። ተራ የታሪክ ሰዉ አይደለም ። ጉልህ ነዉ ። የሚኒሊክን ነገር ለማጉላት ብዬ ከሌሎች ማወዳደር ...
102
በአጤ ምኒልክ ዘመን የነበሩ አስደናቂ ታሪኮች፡፡ ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 032012ዓም አብመድ በዳግማዊ አጤ ምኒልክ ዘመን ጊዜ አስደናቂ ነገሮች ታይተዋል፡፡ ታላቁ የጥብብ ሰው ጳውሎስ ኞኞ አጤ ምኒልክ በሚለው መጽሐፋቸው ከአሰፈሯቸው በርካታ አስደናቂ ክስተቶችን ጥቂቶችን እነሆ፡፡ የሸዋ ንጉሥ መሆናቸውን አጤ ዮሐንስ አጽድቀው አጤ ምኒልክና አጤ ዮሐንስ እርቀ ሠላም ካወረዱ በኋላ ወሎ ውስጥ በደስታ ቆዩ፡፡ መጋቢት 25 1870ዓም ሁለቱም ተሰነባብተው አጤ ዮሐንስ ወደ ደራ ሔዱ፡፡ አጤ ዮሐንስ ወደ ደራ በሄዱ...
103
ስለ እምዬ ምንሊክ ያቀርብከው እዉነታ በታሪክ ተመዝግቦ የሚገኝ ሃቅ ነው። ልጨምርልህ። ስለ እምዬ ምንልክ ባይገርምህ የሚገራርሙ ታሪኮች ከእኛ በላይ በፈረንጆች ቤተ መጽሃፍትና በፈረንጆች ጸህፍት ዉስጥ ደምቆ ይነበባል። አንድ ለመንገድ ልጨምርልህና ወደ ጉዳዬ እመለሳለሁ። ምን አለ መሰልህ አቻም ችይናዎች የቻይናዎች አባት ወይም አባታችን የሚሉት ታላቁ መሪያቸው ማኦ ሴቱንግ፤ የአጼ ምንሊክ አድናቂና ተከታይ እንደነበር ስገልፅልህ በኩራት ነው ። VIVA ለታሪክ VIVA ለምንልክ ። ስለ ማኦ ሴቱንግ የተፃፈ...
104
‹‹ዓፄ ምኒልክ የጎሳ አመለካከት አልነበራቸውም፤ አንድነትን ያራምዱ እንደነበር ታሪክ ምስክር ነው፡፡›› የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት አምባሳደር አለማየው አበበ ባሕር ዳር፡ የካቲት 232011 ዓምአብመድ ‹‹የአውሮፓ ትምክተኞች በርሊን ላይ የአፍሪካን ካርታ ዘርግተው ተቀራመቷት፤ ይህም ሀገራቱ የሀገራቱን የተፈጥሮ ሀብት ለመቀራመት ያለመ ነው፡፡ ጣልያንም ይህን መሠረት አድርጎ ጊዜ ጠብቆ ለመውረር ሞከረ›› ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር፡፡ አልበርቶኒ ጣልያ...
105
ነሐሴ 12 ታሪካዊ ቀን ናት፤ በዚች ቀን በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ስፍራ ያላቸው ግለሰቦች ተወልደዋልና፡፡ በተለያዩ ዓመታት ቢሆንም ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡል እና ፊታውራሪ ገበየሁ የተወለዱት ነሐሴ 12 ቀን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ ይዘው የሚገኙት ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ነሐሴ 12 ቀን 1836 ዓም ሸዋ አንጎለላ ውስጥ ተወለዱ፡፡ አባታቸው ንጉሥ ኃይለመለኮት ሳህለሥላሴ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ ይባላሉ፡፡ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ...
106
ዳግማዊ አጤ ምኒልክ – ጥቁሩ የነጭ ጌታ ምኒልክን የሚያወግዙ የዘር ፖለቲከኞች ማገናዘብ የማይፈልጓቸው 10 ነጥቦች አቻምየለህ ታምሩ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ —ጥቁሩ የነጭ ጌታ የማንነት ቀውስ ዋግ እንደመታው አገዳ ያኮሰሳቸው የዘመናችን የጥላቻ ብሔርተኞች የበታችነት ስነልቦናቸው ታሪክ በማርከስና ጀግኖችን በመዝለፍ የሚሽርላቸው እየመሰላቸው በዘመናቸው በድቅድቅ የባርነት ጨለማ ውስጥ አሳራቸውን እያዩ፤ በላያቸው ላይ የተጫነውን አገዛዝ የጭቆና ቀንበር ለመስበር ብርቱ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ያለዘመናቸው ወደኋ...
107
እቴጌ ጣይቱ ብጡል ማን ነበሩ 2221089tayitu21 ከትወልድ እስከ ሞት አጭር ትረካ ሶረኔ ከፍራንክ ፈርት በኢትዮዽያ ቀደምት ታሪክ የማይነትብ አሻራ ጥለው ካለፉት ተወዳጅ የነገስታት ሚስቶች መካከል እቴጌ ጣይቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ናቸው። እቴጌ ጣይቱ በኢትዮዽያ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ወታደራዊ፣ ሐይማኖታዊና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛና ቀዳሚ ሚና ነበራቸው። በዚሁ ተሳትፎአቸውም ዋና፣ ዋና በሆኑ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች አይነተኛ ሚና ተጫውተዋል። እቴጌ ጣይቱ በባህሪያቸው ቆ...
108
የመላው ጥቁር ህዝብ የድል ሃውልት፤ የአሸናፊነታችን ምልክት ፤ የነፃነታችን አርማ የእምዬ ምኒልክ፤ የእቴጌ ጣይቱ እና የፊታውራሪ ገበየሁ 175ኛ የልደት በዓል። እንኳን ለታላቁ ንጉስ ወ ንጉሱ ነገስት ዘኢትዮጵያ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ 175ኛ የልደት በዐል አደረሳቹህ ……… ምኒልክ በጥበብ ህዝቡን ሲያስተዳድር ህዝቡ በፍቅር እንዲከተለው እንጂ በፍርሀት አንዲገዛለት አይፈልግም። በዚህም ምክንያት በማስተዳደሩ በኩል የተዋጣለት ጥሩ መሪ ነው ግሊከን …… በምኒልክ ዘመን የሀገሪቱ ክብር አደገ። የዘመናዊ አስተዳ...
109
የአርበኛ እናቶቻችንና አባቶቻችን የአድዋ ድል ቁልፍ ሚስጥር ውስጣዊ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው በህብረትና በአንድነት ተደምረው ለአንድ ሀገር መቆማቸው ነው ጠሚ ዶር አብይ አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2011 ኤፍ ቢ ሲ የአርበኛ እናቶቻችና አባቶቻችን በአድዋ ድል የመቀዳጀታቸው እና የማሸነፋቸው ቁልፍ ሚስጥር ውስጣዊ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው በህብረትና በአንድነት ተደምረው ለአንድ ሀገር በመቆማቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 123ኛው የአድ...
110
ዳግማዊ ዐጤ ምኒልክ — ጥቁሩ የነጭ ጌታ የማንነት ቀውስ ዋግ እንደመታው አገዳ ያኮሰሳቸው ኦነጋውያንና ፋሽስት ወያኔዎች የበታችነት ስነልቦናቸው ታሪክ በማርከስና የአለም ጀግኖችን በመዝለፍ የሚሽርላቸው እየመሰላቸው የዳግማዊ ምኒልክን ድልድይ ሰብረው ሕዝባችን የሚሉትን በዘመናቸው በድቅድቅ የባርነት ጨለማ ውስጥ ከተውትና እንዳይተነፍስ ነጻነቱን አፍነው አሳሩን እንዲያይ እያደረጉ ይህንን የጫኑበትን ቀንበር ለመስበር ብርቱ ጥረት እንዳያደርግ ያለዘመናቸው ወደኋላ ተጉዘው ስላልኖሩበት ዘመን ፖለቲካ የወለደውን ...
112
ዐጤ ምኒልክና ኢጣሊያኖች 28 Feb 2013 Page 1 አጤ ምኒልክና ኢጣሊያኖች “The Study of history is the best medicine for a sick mind” Livy የታሪክ ጥናት ለሕሙም አእምሮ ፍቱን መድኃኒት ነው። በእደ ማርያም እጅጉ ረታ ኢትዮጵያ ጥንታውያን ከሚባሉት ሀገሮች አንዷ ስትሆን፣ ከአምስት ሺህ ዓመት ያላነሰ ታሪክ አላት። በእነዚህ ዘመናት፣ ቀደምት አባቶቻችን ሠርተው፣ ትተውልን ካለፉት ሥራዎች መካከል የአክሱም ሐውልት፣የላሊበላ ቤተ መቅደስ ሕንፃዎች፣ የጎንደር ቤተ መን...
113
ሚኒልክ፣ ጎበና እና ኦሮሞ ለመጀመሪያ ግዜ በዚህ በማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ ዘመኔ እንደ ማህበረሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ እና ቁጣን ያስተናገድኩት ከኦሮሞው ማህበረሰብ ጋር ነበር አንድ አራት ወይም አምስት አመት ሆነው መሰለኝያኔ የኦሮሞ ፖለቲካ በጦፈበት ሰሞን እኔ የማውቀው ኦሮሞ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የሚሰጠውን ክብር ጠቅሼ በመከራከሬ ነበር ብዙ ውግዘት የደረሰብኝ በርካታ ኦሮሞ ጓደኞቼ በውስጥ መስመርም በአደባባይም ቀልል ሲል ምክር ከፍ ባስ ሲል ደግሞ ስድብ እና ማስፈራሪያ በ...
114
ክብርና ዝና ለጀግናው አፄ ሚኒሊክና ለአድዋ አርበኞች አድዋና የካቲትት 23 ቀን 1888 ዓም ‘የነፃነትን ጥቅም የሚያውቅ ነፃ የሆነ ህዝብ ብቻ ነው’ ነፃነት ምሴ ነውና ኢትዮጵያዊነቴ የአድዋ ድል ባለቤት አድርጎኛል ወይ አድዋ ‘አድዋ በሁለት ገፅታዋ ማለትም በመከራዋ ጊዜ አንድም ኢትዮጵያውያን ጀግኖችን በማስጠለል ሌላም ወራሪን፣ ባንዳና ሹምባሽ በመፈልፈልና በማብቀልና ትታወቃለች።’ ‘የነፃነትን ጥቅም የሚያውቅ ነፃ የሆነ ህዝብ ብቻ ነው’ ነፃነት ምሴ ነውና ኢትዮጵያዊነቴ የአድዋ ድል ባለቤት አድርጎኛል ...
115
እምዬ ምኒልክን ለመሳደብ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች። ★★★ • ደግሞ SHARE አድርጉትና አሰድቡኝ አሏችሁ። ETHIOPIA የወዳጅ ምክር ነው። ጫ ብለህ ስማኝ። ምክሬንም ተጠቀምበት። ••• አንዳንድ ሰሞንቴ የሆኑ የአክራሪው የወሐቢያ ርዝራዦችና ፀረ ምኒሊክ ኃይሎች ምንም ይባል ምንም ዘለው ምኒልክን ለመርገም መንጠራራታቸውን ባየሁ ጊዜ ምኒልክን ለመስደብ ሟሟላት ያለባቸውን ነገር ልነግራቸው በመውደዴ ይህችን ቀበርቾ የመሰለች ጦማር ጣፍኩላቸው። ተጠቀሙበት በሉልኝ። ••• ወዳጄ ምኒልክን ለመርገም፣...
116
“የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ” ምኒልክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ ግብሩ እንቁላል ነበር ይኸን ጊዜ አበሻ፡፡ በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡ ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡ መድፋን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ የዘራውን እህል አጭዶና ወቅቶ ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ፡፡ እንዳቀና ብሎ ለምኖ መሬት ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አትክልት እየመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግሥት ለጓዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት ተጠማኝ ሰንብ...
117
የአጤ ምኒልክን ስም እንዳትጠራ ይቅርብህ አጤ ምኒልክ ከ100 አመት በፊት ስለ ልዩ ሀገር የሰራ ታላቅ ሰው ነው፣ ዛሬ ከመቶ አመት በኋላ የአህጉር ከተማ ላይ አንተ ስለ ግልህ ልዩ ጥቅም ትሰራለህ አጤ ምኒልክ ተቀናቃኝ ንጉሶችን በጦርነት አሸንፎ ወዳጆቹ የሚያደርግ የድሮ ዘመን እጅግ ዘመናዊ ሰው ነው። አጤ ምኒልክ ሊገድሉት ፈልገው ቆስለው የተያዙ ተቀናቃኞቹን እንደ ልጆቹ ቁስላቸውን አጥቦ ያዳነ ሩህሩህ ሰው ነው፣ ዘመናዊ ሰው ነው። በአንተ ዘመን በቀደም ከተደረገው ጋር አታወዳድረውም። ሰሞኑን ጠቅላይ ሚ...