Dataset Viewer
Auto-converted to Parquet Duplicate
text
stringlengths
2
1.26k
ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 6፡00 በድንጋይ በመወራወር የተጀመረው ግጭት ለሰዎች ሕይወት መጥፋትና ለበርካታ ቤቶችና ንብረት መውደም ምክንያት ሆኗል፤ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢም ትምህርት ተቋርጧል።
ብሔርና ሀይማኖት ግለስቦችና ቡድኖችን በሥመ እየጠቀስ ቢጽፍ ፒፕሉ ከሀሳቡ ይልቅ በሥም የተጠቀሱትን በመደገፍና በመቃውም፣ በትችና ሕፅጽ በመፈለግ ይጠመድና ከቁም ነገሩ ይልቅ ሀሜቱ ይናኛል።
ኤዶም ሰው አክባሪ ብዙም የማያወራ ቤተሰቦቹን አክባሪ ከቃላቸው የማይወጣ ትሁት ፣ ከስራ መልስ ወደቤት ፣ከቤት ወደስራ ከማለት በስተቀር ምንም አይነት አመል የሌለበት ነው።
ኃላፊው እንደገለፁት የዩኒቱ ውሃ መውጫ በደለል ስለተሞላና የተርባይን ሻፍት ዝንፈት በማጋጠሙ ዩኒቱ ከስምንት ዓመታት በላይ ሥራ አቁሞ ነበር።
ግንቦት 12 2012 በኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ ሊካሄድ መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ማንንም የማታዪ የማትሰሚበት ቦታ ሄደሽ ከራስሽ ጋር ብቻ ጊዜ እያሳለፍሽ ራስሽን መፈለግ ትፈልጊያለሽ?
እንዲሁም በቶክዮ ኦሎምፒክ አገራቸውን ወክለው ለሚሳተፉ የትግራይ አትሌቶችን ለማነጋገር ወደ ትግራይ በመምጣታቸው በትግራይ ክልል መንግስት ስም አመስግነዋል።
ሲዳማ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከተደራጁ 19 ማህበራት ለተውጣጡ እና 6 የክልል ባለሙያዎች ናቸው።
በዚህም ተጨዋቹ ለክለባችን የግራ ክንፍ ሚና ትክክለኛው ሰው ነው ተብሎ መታመኑን የጣሊያን ሚድያዎች በመዘገብ ላይ ይገኛሉ።
እስከዚያ ጥግ ድረስ በመግፋት ወሰናቸው ድረስ ለመድረስ አይሞክሩ!
ዲጂታላይዜሽን በነበረው ቴክኖሎጂ ላይ አዳዲስ አሰራሮችን እና እሴት ጨምሮ ስራዎችን አውቶሜትድ ማድረግ ሲቻል ነው።
እያንዳንዱ የእናንተ እንቅስቃሴ፣ እያንዳንዱ ውብ ጨዋታችሁ ሜዳ ላይ የምታሳዩት ጥበብ፣ እንዲሁም የእናንተ የማሸነፍ መንፈስ እኛን ደጋፊዎችን ሁልጊዜም በኩራት እንድንታይ ያደርገናል።
ትውስታ ኢትዮ ቴሌኮም ከአዋሽ ባንክ ጋር በአጋርነት ጥላ የተሰኘ ያለዋስትና የዲጂታል ፋይናንስ እና የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎቶችን በቴሌብር በይፋ አስጀመረ!
5 ሰዎች ደግሞ በአደጋው ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ነቢል ሃሚድ ለአሐዱ ተናግረዋል።
በተጨማሪም አዋሽ ባንክ እና ግሎባል ባንክን የመሳሰሉ ግንባር ቀደም የግል ባንኮች በገበያው ላይ የኢኩዊቲ ኢንቨስትመንት አድርገዋል።
የሴቶች ማራቶን በአሁን ሰዓት በመካሄድ ላይ ሲገኝ ውድድሩ ከተጀመረ ሀያ ደቂቃ ሆኖታል።
ማክሮን ፤ ጠሚ ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢትዮጵያ ለስራ ጉብኝት ሲመጡ በ6 ዓመታት ይህ ሁለተኛቸው ነው።
ምን እና ማን እንደሆነ በጥፊ ስታቃጥሉት ይነግራችኋል ያልኳቸው የአካባቢው ወጣቶች ለህግ ይተላለፍ በማለት ለህግ አስረክበውት ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲህ ተጭኖ ሄዷል።
ባንተ ህይወት ካንተ በላይ ትልቅ ልዩነት የሚፈጥር አካል የለም።
ይሁንና ወረራው ከተፈጸመ 20 ዓመት በኋላ የአሜሪካ ጦር ወደ ኢራቅ መግባቱ ስህተት ነው የሚሉ አሜሪካዊያን ቁጥር 61 በመቶ መድረሱን ይሄው ተቋም ያስጠናው ጥናት ያስረዳል።
ከዚያ በኋላ የነበሩት በረራዎች የተቋረጡት፤ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ አንድ የጦር አውሮፕላን ግጀት በተባለ አካባቢ በአየር ላይ ተመትቷል መባሉን ተከትሎ መሆኑን እኚሁ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ያብራራሉ።
ጥቅምት 24 አሸባሪው ህወሓት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላትን የገደለበት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንም የገለደለበት ቀን ነው።
ሶስተኛው ምርታማነት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርናም በኢንዱስትሪም ምርታማነታችን ውስን ነበር።
ቆንጂት እቺ ግጥም የምትለቀው ቲክቶክ ላይባክህ አላወቅኳትምታውቃታለህ ባክህ ቆይ ላሳይህ አንድ የሷን ቪዲዮውይ ውይ0 ቆንጂት ከምትል ፈንዲሻዋ አትልም?
ኩባንያው የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት የሆነውን ኤም ፔሳን ሳይጨምር ሁሉም ዋና ዋና ዘርፎች በስድስት ወራት ውስጥ አዎንታዊ ዕድገት ማስመዝገባቸውን ገልጿል።
መልበሻ ክፍሉን እነ ማጉ እንዲህ አድምቀውታል።
ይሄ ክብር0 የህዝቡ ትክክለኛ የሀገር ፍቅር ስሜት የወለደው ነው።
ካርድ በመሙላት ብቻ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም በነፃ ያለገደብ ቀኑን ሙሉ ወይም ሳምንቱን ሙሉ ማውራት እንችላለን።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የተደረገው ሙከራ የሊቢያን የፖለቲካ ውጥረት እንዳያባብሰው ተስግቷል።
የመገናኛ መሣሪያዎችን በተመለከተ ከኢንሳ ጋር እየተነጋገርን ነው።
ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ታጣቂዎቹ አራት ህፃናትን ከአካባቢው ይዘው ተሰውረዋል፡፡የሟቾቹ አስከሬን ትላንት ተነስቶ ስርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙንም ተሰምቷል።
5 ደቂቃ ይቀራል ዝግጁ ከሆናችሁ ዝግጁ ነን በሉ!
በተሳሳተ መንገድ ህዝብን ማሰቃየት ይበቃል ይህን የሰላም አማራጭ ተጠቀሙበት የሚል መልዕክትም ለፅንፈኛው አባላት አስተላልፈዋል ዘጋቢ አበበ ካሳሁን ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ህገ መንግስቱ ላይ የአማራ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ኩርፊያ አለው።
ግጭቱ በመሬት ይገባኛል ሰበብ በሐውሳ እና በበርታ ጎሳዎች መካከል ባለፈው ወር ቢቀሰቀስም ያለፈው ሣምንት ረቡዕ እና ሐሙስ እጅግ አይሎ እንደነበር አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ኢንሰቲትዩቱ ከፈጠራ ባለሙያዎች ጋር ውይይት እያደረገ ሲሆን በውይይቱ ሀገራዊ በሆኑ ዋና ዋና ችግሮች ላይ ትኩረት ይደረጋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በምስራቅ ወለጋ ዞን ፣ ኪራሙ ወረዳ የሚገኙ ሲቪል ሰዎች ለደህንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል።
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ ብሬግዚት፤ ያልተቋጨው ውልከቅዳሜው የብሪታንያ ፓርላማ ውሳኔ በኋላ የብሬግዚት እጣ ፈንታ እንደገና ማነጋገር ይዟል።
01 ስናይፐር ተመርኳል ከ18 በላይ የነብስ ወከፍ መሳሪያዎች ተማርኳል ከ20 በላይ የሚሊሻ አባላት የተማረኩ ሲሆን በርካቶች ደግሞ እግር አውጭኝ ብለው ፈርጥጠዋል።
ኩባንያዎቹ ይህንን ሥራ ካሳኩ በኋላ በርከት ያሉ ሳይንሳዊትርፎችን ያገኛሉ።
ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን በቱርክ ለሁለተኛ ዙር የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በማሸነፍ በድጋሚ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ከህገመንግስት አንፃር ስናየው እነዚህ ኃይሎች ህጋዊ አይደሉም ህገመንግስቱ እውቅና አይሰጣቸውም።
ሲቪሊያን ሰዎች የሚኖሩበት አካባቢ ላይ ግጭት መተንኮስ አግባብ አይደለም።
የሕይወት ታሪካቸውን የሚዘክር ዐቢይ ትንሹ ዋርካ የተሰኘ ዶክመንተሪ በመርሃግብሩ ለዕይታ ቀርቧል።
ወረርሽኙ በሚያስከትለው ሕመም ሳቢያ 114 ሺሕ በላይ ሰዎች በአፍሪካ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ አንጻር ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት እንድትመለስ ለማድረግ የተሻለ ሁኔታ መኖር አለመኖሩን በቅርበት እያጤነ ነው ሲሉ ፊ ገልጸዋል።
በእርግጥ ገና ጅምር ላይ ነው፤ ነገር ግን ሊቲየም ባትሪዎች በማምረት፤በመጨረሻም ለኤሌክትሪክ መኪና የሚሆኑ ባትሪዎች ማምረት እንፈልጋለንሲሉ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ቋሚ ፀሃፊ ፋኑኤል ታግዊራ ተናግረዋል።
ባለፈው ወር ትራምፕ በቻይና ለሚገኘው ባይትዳንስ0 የቲክቶክን የአሜሪካ ንብረቶች ለመሸጥ የተሰጠውን የጊዜ ገደብ እስከ መስከረም 10 አራዝመዋል።
አንድ ወንድማችን ሸሂድ ሆኗል!
የቦይንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቭ ካልሁን ለሰራተኞቹ እንደተናገሩት የኩባንያው ትኩረት መሆን አለበት ብለዋል።
የአዲስ አበባ ሕዝብ ሂትለሩን እቅፍ እያሳደገ መሆኑን መች ጠርጥሮ?
ነገር ግን መኪናው ውስጥ አስገብቷት0 እርዳታ ሊያደርጉላት የሚፈልጉት ሰዎች ቤተሰቡ መሆናቸውን እና ይህንን ድጋፍ የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው በመተማመን ሲያወራ ግራ መጋባት ውስጥ ከተታት።
ክሱ በፍሎሪዳ በሚገኝ የፌዴራል ፍርድ ቤት ቀርቧል።
ከጥቂት ወራት በፊት እስራኤል በሶሪያ የሚገኘውን የኢራንን ቆንስላ በቦምብ ካጋየች በኋላ ቴህራን በመቶዎች የሚቆጠሩ ድሮኖችን እና ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል መተኮሷ ይታወሳል።
ግብፅ በ ዙሪያ የሦስቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም የሚያሟላ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረቷን ብትቀጥልም አልተሳካም።
1 የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!
ጥሩ ግምት ነው ከረፈደም ቢሆን ለምን እኔስ ይቅርብኝ ፣ በስም እንኳ ልተካከል ብለው የገመትከውን ስም ሰጥተውኛል።
ያንብቡ የሩስያ እና የዩክሬን ቁርሾ ምንድነው?
የተሳለ ሾተል፣ሰሚ ያጣ ጩኸትየማያባራ ግፍ፣የማይሰክን እልቂት።
ክትባቱ ውዝግብ አስነስቷል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የሶርያ ሕገ መንግሥታዊ ኮሚቴ መቋቋሙን ይፋ አደረጉ።
የ ቶተንሀም አዲሱ አሰልጣኝ ለመሆን የተቃረቡት ጣልያናዊው አንቶኒዮ ኮንቴ ከ ደቂቃዎች በኋላ አስራ ስምንት ወራት በ ሰሜን ለንደን የሚያቆያቸውን ኮንትራት እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል።
የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሌሊቱን በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት ተፈጸመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥተው ነበር።
ራይስተር ዛሬ ማክሰኞ ከፊልም ኢንደስትሪ ሰዎች ጋር እና ከአርቲስቶች ጋር በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙርያ ዉይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው ነበር።
በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ሁኔታ ህፃናት ለድህነት እና ለረሃብ እንደሚጋለጡ የአፍሪካ ቻይልድ ፖሊሲ ፎረም የፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር አቶ የኋላእሸት መኮንን ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋቲኖ ከብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ጎን እንደሚቆሙ እና ለዘረኝነት ቦታ እንደሌለ አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 672 ሺህ 637 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ባሰረው ውል 67 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ተስማምቷል።
አሚኮ እለታዊ የምንዛሬ መረጃ ጥር 162017 ዓ ም የጤና ባለሙያዎች በችግርም ውስጥ ኾነው ለማኅበረሰቡ የጤና አገልግሎት እየሰጡ ነው።
ጥቃቱ የተፈጠረው በአካባቢው ከፍተኛ መዘናጋት ስለነበር አስታውሰው፣ ከአንድ ወር በፊት በዚሁ አስተዳደር ፃታ በተባለ አካባቢ የተፈጠረውን ጥቃት እንደ ማነፃፀሪያ አቅርበዋል።
ጀነራል ሞሃመድ ካይሮ ላይ ከፕሬዚደንት አብደል ፈታህ አልሲሲ ጋር ተገናኝተዉ መምከራቸዉ ነዉ የተገለፀዉ።
ተመራቂዎች የሥራ እድል እንዲያገኙ ለማስቻል በተዘጋጀው በዚህ መርኃ ግብር ተመራቂዎች የሠሯቸውን ሥራዎች ለአውደ ርዕዩ ተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፤ አየር ኃይል የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ የገባውን አውሮፕላን መቶ መጣሉን እንደሚደግፍ ገልጿል።
በሰር አሌክስ ፈርጉሰን የአሰልጣኝነት ወቅት የትኛውም ተጨዋች በዚህ ልክ ቢያጠፋ ዳግም በክለቡ መጫወት አይችልም ነበር።
ትናንት በድንገት ሕይወታቸው ያለፈው የቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ!
ባንተ ቃል ሁሉ ይድናልካንተ በላይ ሀይል የለም።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በንጹሃን ላይ በተፈፀመው ቃጠሎ በወንጀሉ ተሳትፎ አላቸው ተብለው በተጠረጠሩ የጸጥታ አካላት ላይ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
በዚህም ምክኒያት ሞሮኮ ወደ 16 ውስጥ ለማለፍ የመጨረሻወን ጫወታ ትጠብቃለች።
የደሃዉ ልጅ አንሶ አልታይም፣ የደሃ ልጅ መባል አልፈልግም ከማለቱ የተነሳ ያለውን ገንዘብ መጠቀም ይጀመራል።
በዚህም የአብላጫ ድምፅ እና የተመጣጣኝ ውክልና በምን ያህል መቶኛ ይሁን የሚለውም የፓርቲዎቹ የልዩነት ሀሳብ ነው።
ይህ የ 18 ዓመት ወጣት አጥቂ በተሰጠው እድል ድንቅ ብቃቱን በማሳየት በጨዋታው መሃልም ትኩርትን የሳቡ እንቅስቃሴዎችን ማሳየት ችሏል።
በክረምቱ ቡድኑን እንደገና እየገነባን ነው ብለው የሚያስቡት ግሌዘርስ አሁንም ለደጋፊዎች ያላቸውን ንቀት በግልፅ እያሳዩ ነው።
ፈተናው የሚሰጠው ለመማር ባመለከታችሁበት ኢንስቲትዩት ወይም ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት መሆኑ ተገልጿል።
ተከሳሾቹ ክሱ ከደረሳቸው በኋላ ድርጊቱን ክደው በመከራከራቸው ዐቃቤ ሕግ የሰው ምስክሮችን፣ አስረጂና ገላጭ የሰነድ ማስረጃዎችን ለችሎቱ አቅርቧል።
ከሰኔ 24 2015 እስከ መስከረም 2016 ዓም ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ጊዜአዊ የህፃናትን ትምህርት ሁኔታ የሚያሳይ ሪፖርት አውጥቷል።
ዛሬ ሳይሆን ነገ ፤ አሁን ሳይሆን በኋላ።
ደሀው አባትና ሀብታሙ አባት ስለገንዘብ የሚሰጡት አስገራሚ ትምህርት በማራኪ ሁኔታ የቀረበበት፣ ሚሊዮኖች ስለገንዘብ ያላቸውን አስተሳሰብ የቀየረ መጽሐፍ!
የሰው ልጅ በውስጡ ያለው ይህንን ሀይል የማወቅ ፍላጎት በፍልስፍናው ሜታፊዚክስን ፈጠረ።
ኮሚቴው በወሳኝ አገራዊና የፓርቲ ሥራዎች ላይ ተወያይቶ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ማስቀመጡን ፓርቲው ለኢፕድ በላከው መረጃ አስታውቋል።
በቢሮው የሰብል ልማት ዳይሬክተር አቶ አሕመድ መሐመድ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በአፋር ክልል አጠቃላይ በምርት ዘመኑ 100 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ በስፋት እየተሰራ ይገኛል።
ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞግሰው።
በዚህም ተማሪዎች በአንድ ዓመት ሁለት የክፍል ደረጃዎችን እንዲያጠናቅቁ የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል።
የቴሌቪዥን ጣቢያዉ በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋ ስርጭቱን ሲያደርግ ባለፉት አምስት አመታት በሱፐር ስፖርት በኮሜንትሪ እና በትንታኔ ጨዋታዎችን ሲያስተላለፉ የነበሩ ጋዜጠኞች በዚህኛዉ ጣቢያ እንደሚቀጥሉ ታዉቋል።
የአምባሳደር ሱሌማን ደብዳቤ ሙሉ ደብዳቤ ተገኘቷል።
በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን መርዳት፣ የወደቁትን ማንሳት፣ የታመሙትን መደገፍ፣ ከቤታቸው የተፈናቀሉትን ማሰብ አንዘንጋ።
በስፔን የግብር ህግ መሰረት ሀምሳ በመቶ ያህል የሚሆነው ለስፔን መንግሥት ገቢ እንደሚሆን ተዘግቧል።
ከተለያዩ የታሪክ ማህደሮች አጠናቅሬ ያቀረብኩላችሁ አብዱረህማን ነበርኩ መልካም ምሽት።
ከ2012 ዓ ም ጀምሮ የጤፍ ሰብል ማልማት ተግባርን በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች ለማስፋት ሙከራ እየተደረገ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ጀምሩ ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።
60 ቀን ነበራቸው ስህተት ሰርተዋል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
ታጣቂው ለምን ወደ ኤምባሲው ተኩስ እንደከፈተና ፖለቲካዊ ዓላማ ይኑረው አይኑረው ግን የተባለ ነገር የለም።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባልስቲክ ሚሳኤል እና የኒውክሌር መሳሪያዎችን እንዳይሞክር መከልከሉ ግን አይዘነጋም።
End of preview. Expand in Data Studio

Amharic_Sentences_Corpus_banner_02

Amharic Sentences Corpus V1.0

Source: Telegram

This 1.6 million Amharic sentences corpus reflects current Amharic usage as of December 20, 2025, and is designed for anyone interested in:

  • Training Amharic-based LLMs
  • Fine-tuning NLP models
  • Building search, summarization, or generative systems in Amharic

The dataset is heavily cleaned and normalized, but like any serious LLM dataset, it still needs proper tokenization for pre-training.

I recommend using an Amharic-specific tokenizer such as: https://pypi.org/project/amharic-tokenizer/0.2.6

Another useful Amharic Sentences corpus by @rasyosef & @Addis AI

How did I create this text corpus?

This project is fully open-source & community-driven. If you’re building in NLP, AI research, or language technology, this is for you.

Use it. Improve it. Build on top of it.

Downloads last month
110