verse_id
stringlengths
8
8
book
stringclasses
66 values
chapter
stringclasses
151 values
verse
int64
1
176
verse_text
stringlengths
0
495
text
stringlengths
13
511
000_0008
ኦሪት ዘፍጥረት
8
17
ከአንተ ጋር ያሉትን አራዊት ሁሉ፥ ሥጋ ያላቸውን ሁሉ፥ ወፎችንና እንስሶችን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ከአንተ ጋር አውጣቸው፤ በምድር ላይ ይርመስመሱ፥ ይዋለዱ፥ በምድርም ላይ ይብዙ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 8:17] ከአንተ ጋር ያሉትን አራዊት ሁሉ፥ ሥጋ ያላቸውን ሁሉ፥ ወፎችንና እንስሶችን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ከአንተ ጋር አውጣቸው፤ በምድር ላይ ይርመስመሱ፥ ይዋለዱ፥ በምድርም ላይ ይብዙ።
000_0008
ኦሪት ዘፍጥረት
8
18
ኖኅም ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወጣ፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 8:18] ኖኅም ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወጣ፤
000_0008
ኦሪት ዘፍጥረት
8
19
አራዊት ሁሉ፥ ተንቀሳቃሾች ሁሉ፥ ወፎችም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚርመሰምሰው ሁሉ በየዘመዳቸው ከመርከብ ወጡ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 8:19] አራዊት ሁሉ፥ ተንቀሳቃሾች ሁሉ፥ ወፎችም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚርመሰምሰው ሁሉ በየዘመዳቸው ከመርከብ ወጡ።
000_0008
ኦሪት ዘፍጥረት
8
20
ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፥ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 8:20] ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፥ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።
000_0008
ኦሪት ዘፍጥረት
8
21
እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ። ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰው አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና፤ ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደ ገና አልመታም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 8:21] እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ። ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰው አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና፤ ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደ ገና አልመታም።
000_0008
ኦሪት ዘፍጥረት
8
22
በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም። a
[ኦሪት ዘፍጥረት 8:22] በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም። a
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
1
እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው እንዲህም አላቸው። ብዙ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:1] እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው እንዲህም አላቸው። ብዙ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
2
አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በምድር አራዊት፥ በሰማይም ወፎች፥ በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱትም፥ በባሕር ዓሦችም ሁሉ ላይ ይሁን፤ እነርሱም በእጃችሁ ተሰጥተዋል።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:2] አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በምድር አራዊት፥ በሰማይም ወፎች፥ በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱትም፥ በባሕር ዓሦችም ሁሉ ላይ ይሁን፤ እነርሱም በእጃችሁ ተሰጥተዋል።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
3
ሕይወት ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መብል ይሁናችሁ፤ ሁሉን እንደ ለመለመ ቡቃያ ሰጠኋችሁ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:3] ሕይወት ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መብል ይሁናችሁ፤ ሁሉን እንደ ለመለመ ቡቃያ ሰጠኋችሁ።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
4
ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:4] ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፤
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
5
ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፤ ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፤ ከሰውም እጅ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:5] ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፤ ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፤ ከሰውም እጅ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
6
የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል፤ ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:6] የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል፤ ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
7
እናንተም ብዙ፥ ተባዙ፤ በምድር ላይ ተዋለዱ፥ እርቡባትም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:7] እናንተም ብዙ፥ ተባዙ፤ በምድር ላይ ተዋለዱ፥ እርቡባትም።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
8
እግዚአብሔርም ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ተናገረ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:8] እግዚአብሔርም ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ተናገረ።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
9
እኔም እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተና በኋላ ከሚመጣው ከዘራችሁ ጋር አቆማለሁ፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:9] እኔም እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተና በኋላ ከሚመጣው ከዘራችሁ ጋር አቆማለሁ፤
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
10
ከእናንተ ጋር ላሉትም ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፥ ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት ለወፎች፥ ለእንስሳትም ለምድር አራዊትም ሁሉ፥ ለማንኛውም ለምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:10] ከእናንተ ጋር ላሉትም ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፥ ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት ለወፎች፥ ለእንስሳትም ለምድር አራዊትም ሁሉ፥ ለማንኛውም ለምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
11
ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ አቆማለሁ፤ ሥጋ ያለውም ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:11] ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ አቆማለሁ፤ ሥጋ ያለውም ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
12
እግዚአብሔርም አለ። በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘላለም የማደርገው የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:12] እግዚአብሔርም አለ። በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘላለም የማደርገው የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፤
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
13
ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:13] ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
14
በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቲቱ በደመናው ትታያለች፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:14] በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቲቱ በደመናው ትታያለች፤
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
15
በእኔና በእናንተ መካከል፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ሥጋ ሁሉ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ሥጋ ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:15] በእኔና በእናንተ መካከል፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ሥጋ ሁሉ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ሥጋ ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
16
ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:16] ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
17
እግዚአብሔርም ኖኅን። በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው ሁሉ መካከል ያቆምሁት የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው አለው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:17] እግዚአብሔርም ኖኅን። በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው ሁሉ መካከል ያቆምሁት የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው አለው።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
18
ከመርከብ የወጡት የኖኅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፥ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከነዓን አባት ነው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:18] ከመርከብ የወጡት የኖኅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፥ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከነዓን አባት ነው።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
19
የኖኅ ልጆች እነዚህ ሦስቱ ናቸው፤ ከእነርሱም ምድር ሁሉ ተሞላች።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:19] የኖኅ ልጆች እነዚህ ሦስቱ ናቸው፤ ከእነርሱም ምድር ሁሉ ተሞላች።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
20
ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:20] ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
21
ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ዕራቁቱን ሆነ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:21] ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ዕራቁቱን ሆነ።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
22
የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:22] የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
23
ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:23] ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
24
ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:24] ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
25
እንዲህም አለ። ከነዓን ርጉም ይሁን፤ ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:25] እንዲህም አለ። ከነዓን ርጉም ይሁን፤ ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
26
እንዲህም አለ። የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:26] እንዲህም አለ። የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
27
እግዚአብሔርም ያፌትን ያስፋ፥ በሴምም ድንኳን ይደር፤ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:27] እግዚአብሔርም ያፌትን ያስፋ፥ በሴምም ድንኳን ይደር፤ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
28
ኖኅም ከጥፋት ውኃ በኋላ ሦስት መቶ አምሳ ዓመት ኖረ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:28] ኖኅም ከጥፋት ውኃ በኋላ ሦስት መቶ አምሳ ዓመት ኖረ።
000_0009
ኦሪት ዘፍጥረት
9
29
ኖኅም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 9:29] ኖኅም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
1
የኖኅ ልጆች የሴም የካም የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ ከጥፋት ውኃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:1] የኖኅ ልጆች የሴም የካም የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ ከጥፋት ውኃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
2
የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:2] የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
3
የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:3] የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
4
የያዋንም ልጆች ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:4] የያዋንም ልጆች ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
5
ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:5] ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
6
የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:6] የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
7
የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው። የራዕማ ልጆችም ሳባ፥ ድዳን ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:7] የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው። የራዕማ ልጆችም ሳባ፥ ድዳን ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
8
ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:8] ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
9
እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም። በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:9] እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም። በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
10
የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:10] የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
11
አሦርም ከዚያች አገር ወጣ፤ ነነዌን፥ የረሆቦትን ከተማ፥ ካለህን፥
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:11] አሦርም ከዚያች አገር ወጣ፤ ነነዌን፥ የረሆቦትን ከተማ፥ ካለህን፥
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
12
በነነዌና በካለህ መካከልም ሬሴንን ሠራ፤ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:12] በነነዌና በካለህ መካከልም ሬሴንን ሠራ፤ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
13
ምጽራይምም ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥ ነፍታሌምን፥ ፈትሩሲምን፥
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:13] ምጽራይምም ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥ ነፍታሌምን፥ ፈትሩሲምን፥
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
14
ከእነርሱ የፍልስጥኤም ሰዎች የወጡባቸውን ከስሉሂምን፥ ቀፍቶሪምንም ወለደ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:14] ከእነርሱ የፍልስጥኤም ሰዎች የወጡባቸውን ከስሉሂምን፥ ቀፍቶሪምንም ወለደ።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
15
ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጢያውያንንም፥
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:15] ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጢያውያንንም፥
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
16
ኢያቡሳውያንንም፥ አሞራውያንንም፥
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:16] ኢያቡሳውያንንም፥ አሞራውያንንም፥
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
17
ጌርጌሳውያንንም፥ ኤዊያውያንንም፥
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:17] ጌርጌሳውያንንም፥ ኤዊያውያንንም፥
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
18
ዐሩኬዎንንም፥ ሲኒንም፥ አራዴዎንንም፥ ሰማሪዎንንም፥ አማቲንም ወለደ። ከዚህም በኋላ የከነዓናውያን ነገድ ተበተኑ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:18] ዐሩኬዎንንም፥ ሲኒንም፥ አራዴዎንንም፥ ሰማሪዎንንም፥ አማቲንም ወለደ። ከዚህም በኋላ የከነዓናውያን ነገድ ተበተኑ።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
19
የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን አንሥቶ ወደ ጌራራ በኩል ሲል እስከ ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሰቦይም በኩልም ሲል እስከ ላሣ ድረስ ነው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:19] የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን አንሥቶ ወደ ጌራራ በኩል ሲል እስከ ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሰቦይም በኩልም ሲል እስከ ላሣ ድረስ ነው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
20
የካም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራችውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:20] የካም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራችውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
21
ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የያፌት ታላቅ ወንድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆነ ነው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:21] ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የያፌት ታላቅ ወንድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆነ ነው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
22
የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:22] የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
23
የአራምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሶሕ ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:23] የአራምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሶሕ ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
24
አርፋክስድም ቃይንምን ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን፥ ሳላም ዔቦርን ወለደ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:24] አርፋክስድም ቃይንምን ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን፥ ሳላም ዔቦርን ወለደ።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
25
ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፥ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:25] ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፥ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
26
ዮቅጣንም ኤልሞዳድን፥ ሣሌፍንም፥ ሐስረሞትንም፥
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:26] ዮቅጣንም ኤልሞዳድን፥ ሣሌፍንም፥ ሐስረሞትንም፥
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
27
ያራሕንም፥ ሀዶራምንም፥ አውዛልንም፥
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:27] ያራሕንም፥ ሀዶራምንም፥ አውዛልንም፥
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
28
ደቅላንም፥ ዖባልንም፥ አቢማኤልንም፥
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:28] ደቅላንም፥ ዖባልንም፥ አቢማኤልንም፥
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
29
ሳባንም፥ ኦፊርንም፥ ኤውላጥንም፥ ዩባብንም ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:29] ሳባንም፥ ኦፊርንም፥ ኤውላጥንም፥ ዩባብንም ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
30
ስፍራቸውም ከማሴ አንሥቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥራቅ ተራራ ድረስ ነው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:30] ስፍራቸውም ከማሴ አንሥቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥራቅ ተራራ ድረስ ነው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
31
የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:31] የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።
000_0010
ኦሪት ዘፍጥረት
10
32
የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። አሕዛብም ከጥፋት ውኃ በኋላ በምድር ላይ ከእነዚህ ተከፋፈሉ። a
[ኦሪት ዘፍጥረት 10:32] የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። አሕዛብም ከጥፋት ውኃ በኋላ በምድር ላይ ከእነዚህ ተከፋፈሉ። a
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
1
ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:1] ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
2
ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:2] ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
3
እርስ በርሳቸውም። ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፋት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:3] እርስ በርሳቸውም። ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፋት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
4
እንዲህም። ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:4] እንዲህም። ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
5
እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:5] እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
6
እግዚአብሔርም አለ። እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:6] እግዚአብሔርም አለ። እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
7
ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:7] ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
8
እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:8] እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
9
ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:9] ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
10
የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም የመቶ ዓመት ሰው ነበረ፥ አርፋክስድንም ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ወለደ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:10] የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም የመቶ ዓመት ሰው ነበረ፥ አርፋክስድንም ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ወለደ።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
11
ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:11] ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
12
አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ቃይንምንም ወለደ፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:12] አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ቃይንምንም ወለደ፤
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
13
አርፋክስድም ቃይንምን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ሳላንም ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን ከወለደ በኋላ ሶስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:13] አርፋክስድም ቃይንምን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ሳላንም ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን ከወለደ በኋላ ሶስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
14
ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:14] ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ፤
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
15
ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:15] ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
16
ዔቦርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥ ፋሌቅንም ወለደ፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:16] ዔቦርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥ ፋሌቅንም ወለደ፤
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
17
ዔቦርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:17] ዔቦርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
18
ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ራግውንም ወለደ፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:18] ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ራግውንም ወለደ፤
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
19
ራግውንም ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:19] ራግውንም ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
20
ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሴሮሕንም ወለደ፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:20] ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሴሮሕንም ወለደ፤
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
21
ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:21] ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
22
ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ናኮርንም ወለደ፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:22] ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ናኮርንም ወለደ፤
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
23
ናኮርንም ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:23] ናኮርንም ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
24
ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ታራንም ወለደ፤
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:24] ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ታራንም ወለደ፤
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
25
ታራንም ከወለደ በኋላ ናኮር መቶ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:25] ታራንም ከወለደ በኋላ ናኮር መቶ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
26
ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:26] ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
27
የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፤ ሐራንም ሎጥን ወለደ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:27] የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፤ ሐራንም ሎጥን ወለደ።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
28
ሐራንም በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:28] ሐራንም በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
29
አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፤ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነው።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:29] አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፤ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነው።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
30
ሦራም መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:30] ሦራም መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
31
ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥን የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፤ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:31] ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥን የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፤ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።
000_0011
ኦሪት ዘፍጥረት
11
32
የታራም ዕድሜ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ሆነ፤ ታራም በካራን ሞተ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 11:32] የታራም ዕድሜ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ሆነ፤ ታራም በካራን ሞተ።
000_0012
ኦሪት ዘፍጥረት
12
1
እግዚአብሔርም አብራምን አለው። ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።
[ኦሪት ዘፍጥረት 12:1] እግዚአብሔርም አብራምን አለው። ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።