Dataset Viewer
Auto-converted to Parquet Duplicate
_id
stringlengths
17
17
title
stringlengths
12
80
text
stringlengths
434
4.06k
d364c0501024c192b
የታይዋን ሐኪሞች "ላብ ቀሳሚ" አራት ንቦች የሰው ልጅ አይን ውስጥ አገኙ
የ28 አመቷ ሴት ስሟ እንዲገለጥ ያልተፈለገ ሲሆን ንቦቹ አይኗ ውሰጥ ሲገቡ እርሷ አረም እያረመች ነበር ተብሏል። ዶ/ር ሆንግ ቺ ቲንግ ከታማሚዋ አይን ውስት አራት ሚሊ ሜትር ርዝመት ያላቸው ሃሊሲቲዴት ተብለው የሚጠሩት ወይም ማንኛውንም እርጥበት ስለሚወዱ በተለምዲ ላብ ቀሳሚ የሚል ስያሜ ያላቸው ንቦችን ጎትተው ሲያወጡ ክው ብለው ደንግጠው ነበር። ታማሚዋ አሁን ከሆስፒታል የወጣች ሲሆን በቤቷ ሆና እያገገመች ነው ተብሏል። ስዊት ቢ (ላብ ቀሳሚ) የሚባሉት የንብ ዝርያዎች በማንኛውም እርጥበት የሚሳቡ ሲሆ...
db39213a37c57c95c
የአረና ፓርቲ አባል ንብረት የሆኑ 13 ፍየሎች መታሰራቸው ተነገረ
ፎቶ፡ GettyImages የአረና ፓርቲ ሊቀመንብር አቶ አብርሃ ደስታ በላፈው ረቡዕ የፓርቲው አባል ንብረት የሆኑ 16 ፍየሎች በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን ወረዳ ንኡስ ወረዳ ወርቅ አንባ ቀይሕ ተኽሊ ቀበሌ ውስጥ መታሰራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። • ህወሓትና የትግራይ ወጣቶች፡ ሆድና ጀርባ? • "108ኛው" ፓርቲ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ይዞ? የፍየሎቹ ባለቤት የሆኑት አቶ ዜናዊ አስመላሽ 16 ፍየሎቻቸው ታስረውባቸው እንደነበረ ተናግረው፤ ታስረው ከነበሩት ፍየሎች ሶስቱ አምልጠው ወደ ቤት መመለሳቸውን ለቢቢ...
de4e5f3c16b84d436
ቲክ ቶክ፡ የዓለም መንግሥታት ለምን ቲክ ቶክ ላይ አደሙ?
ይህ በሚሊዮኖች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ማሕበራዊ ድር-አምባ እንዴት የአሜሪካ መንግሥት የደህንነት ስጋት ሊሆን ቻለ? ቲክ ቶክ ላይ የሚለጠፉ ምስሎች አብዛኛውን ጊዜ ፈገግ የሚያሰኙ ናቸው። አንዳንዶቹ ከጥቂት ሰከንድ በላይ ዕድሜ የላቸውም። ቢሆንም ግን ድርጅቱ ከእነዚህ ምስሎች ሚሊዮኖች ያተርፋል። መተግበሪያው የዓለም ገበያን የተቀላቀለው ታኅሣሥ 2010 ነው። ነገር ግን በፍጥነት የሚሊዮኖችን ተንቀሳቃሽ ስልክ ለማዳረስ ጊዜ አልወሰደበትም። በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደንበኞቹ ወጣቶች ናቸው። ቲክ ቶክ ልክ...
d2a04e34a13bbb6b3
የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በይፋ እንዳልተጀመረ ተገለፀ
ሚኒስትሩን ዶ/ር ስለሺ በቀለን ዋቢ አድርገው የአገር ውስጥ ሚዲያዎች እንደዘገቡት የውሃ ሙሌቱ የግድቡን ተፈጥሯዊ የግንባታ ሂደት በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ እንደሆነ ገልጸዋል። ከሰሞኑ በሕዳሴው ግድብ አካባቢ የተገኙት የሳተላይት ምስሎች በግድቡ ውስጥ ያለው የውሃ መጠን እየጨመረ መሆኑን ያመላከቱ ሲሆን፣ ይህም ምስል ትክክለኛ መሆኑንና የግድቡ ሙሌት መጀመሩን የሚያሳይ መሆኑ ሚኒስትሩ መግለፃቸው ተዘግቧል። የግድቡ ሙሌት መጀመሩን አስመልክቶ ሚኒስትሩ ለቢቢሲ በሰጡት ምላሽ ዘገባው "በስህተት የወጣ ነው፤ ...
df4d59dfd8145a5ae
የዓለማችን 'ጭንቀታም' እና 'ደስተኛ' ሃገራት ደረጃ ይፋ ሆነ
በ140 ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ 150 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት ድብርት እየተጫናቸው እንደመጣ የተናገሩ ሲሆን፤ ቢያንስ ከአምስቱ በአንዱ የሃዘን እና የብስጭት ስሜት ተመዝግቧል። ዓመታዊው ጋሉፕ ዓለም አቀፍ የውስጣዊ ስሜት ሪፖርት (Gallup Global Emotions Report) ሰዎችን አዎንታዊ እና አሉታዊ ልምዶቻቸውን ጠይቋል። • የዓለማችን ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች እነማን ናቸው? • የማትተነፍሰው ከተማ: አዲስ አበባ ከተጠየቁት ...
d2418b994996b4cb3
እንግሊዝ በኮቪድ-19 ስጋት ኢትዮጵያን ጨምሮ የ4 አገራት ተጓዦችን ልታግድ ነው
ከዚህ ቀደም 30 ያህል አገራት ላይ ተመሳሳይ እርምጃ የወሰደችው እንግሊዝ አሁን ደግሞ ከዝርዝሩ ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ኳታርን፣ ኦማንንና ሶማሊያን ማካተቷን አስታውቃለች። አገሪቱ ለዚህ እንደምክንያት ያቀረበችው እየተካሄደ ያለው የወረርሽኙ ክትባት መስጠት ዘመቻ ወሳኝ ደረጃ ላይ ባለበት ወቅት በደቡብ አፍሪካ በብራዚል የተገኙትን የመሰሉ አዲስ አይነት የኮሮናቫይረስ ዝርያዎችን ለመከላከል ነው ተብሏል። ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ በእንግሊዝ "ቀዩ ዝርዝር" ውስጥ ከተካተቱት ከኢትዮጵያና ከሦስቱ አገራት ከአርብ ...
dc6df205ff423a3bf
'አስጸያፊ' ከመባል ኦስካር ወደማሸነፍ
የንጽህና መጠበቂያው ሞዴስ ሲሠራ ትላንት ባልተለመደ ሁኔታ ያለ አስተዋዋቂ የተካሄደው የኦስካር የሽልማት ሥነ ሥርዐት በርካታ ጥቁር ፊልም ሠሪዎች ጎልተው የወጡበት ነበር። 'ብላክ ፓንተር' በምርጥ ኦሪጅናል ስኮር፣ በፕሮዳክሽን ዲዛይንና በኮስቲውም ዲዛይን ሦስት ሽልማቶች አግኝቷል። በተጨማሪም ዛንዚባር የተወለደው የሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቀኛ ህይወትና ሥራ የሚዳስሰው ፊልም እንዲሁም፣ ለበርካታ ዓመታት ሽልማት ሳይገኝ የቆየው ስፓይክ ሊ ተሸልሟል። ሌላው ተሸላሚ የጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ላይ የሚያተኩረው ዘጋቢ ...
de20caba2a4cdf6e4
ፓኪስታን በተጭበረበረ 'መንጃ ፈቃድ' አውሮፕላን ያበረሩ ፓይለቶቿን እያደነች ነው
የፓኪስታን አቪየሽን ሚኒስትር ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ይፋ እንዳደረጉት አብዛኛዎቹ የንግድ አውሮፕላን የሚያበሩ የአውሮፕላን 'ሾፌሮች' የማብረሪያ ፈቃዳቸው የተጭበረበረ ነው፡፡ ይህ የማጥራት ዘመቻን የቀሰቀሰው ባለፈው ወር በፓኪስታን 97 ሰዎችን ጭኖ ይበር የነበረ አውሮፕላን ለማረፍ ሲቃረብ በካራቺ መከስከሱን ተከትሎ ነው፡፡ በዚህ አደጋ ከ2 ተሳፋሪዎች ውጭ በሙሉ አልቀዋል፡፡ የመከስከሱ ምክንያት ሲፈተሸም የአብራሪው ብቃት ማነስ እንደሆነ ተደርሶበታል፡፡ የአቪየሽን ሚኒስትሩ ለፓኪስታን ፓርላማ ሲናገሩ የ...
d3bd262c6eda85283
ጀርመን የፑቲን ተቃዋሚው መመረዙን አረጋገጥኩ አለች
የላብራቶሪው ምርመራ ውጤት ናቪቾክ ስለመመረዙ ማረጋገጫ ነው ሲሉ የአሌክሴ ናቪቾክ ደጋፊዎች ተናግረዋል። የጀርመን መንግሥት አሌክሴ ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልጾ፤ ሩሲያ በአስቸኳይ ማብራሪያ እንድትሰጥ ጀርመን ጠይቃለች። መራሂተ መንግሥት አንጌላ መርክል በጉዳዩ ላይ ከካቢኔ አባላቶቻቸው ጋር አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጣቸውም ተነግሯል። የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንን በድፍረት በመተቸትና በማብጠልጠል የሚታወቀው አሌክሴ ናቫልኒ ድንገተኛ ህመም ካጋጠመው በኋላ ለህክምና ወደ ጀርመን ...
d95669987406a0b6a
ተሰንጥቋል የተባለው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ከበረራ ታገደ
ቦይንግ፤ የ737 ኤንጂ አውሮፕላኖች ክንፋቸው ሊሰነጠቅ እንደሚችል ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፤ በርካታ አየር መንገዶች አውሮፕላናቸውን እየፈተሹ ነው። • ቦይንግ ትርፋማነቴ ቀንሷል አለ • ቦይንግ 737 ወንዝ ውስጥ ገባ • ቦይንግ የ737 ማክስ ሶፍትዌርን አሻሽያለሁ አለ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው፤ በመላው ዓለም ወደ 50 የሚጠጉ አውሮፕላኖች ከበረራ ታግደዋል። ካንታስ አውሮፕላኑ ላይ የተገኘው ስንጥቅ አሁን ላይ ለአደጋ ባያጋልጥም፤ ደህንነታቸው አስተማማኝ ያልሆነ አውሮፕላኖችን ማብረር እንደማያስፈል...
d6a7ad97f07b434b8
ለ10 ዓመታት እጆቹን ያልታጠበው የቴሌቪዥን አቅራቢ
እጆቼን አለመታጠቤ ክትባት እንደመወጋት ያህል ነው -ፒት ሄግሴት በሚያቀርበው ፕሮግራም ፒት አነዚህ ጥቃቅን ፍጥረታት (ጀርሞች) በዓይን ስለማይታዩ የሉም ብሎ ማመኑን ተናግሯል። "እራሴን ነው የምከትበው" በማለት የሃርቫርድና የፕሪንስተን ምሩቁ ተናግሯል። ደስታን አጥብቀን ስለፈለግን ለምን አናገኘውም? መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች ይህንም ኑዛዜ ያስከተለው ኤድ ሄንሪ እና ጄደዳያ ቢላ የተሰኙት ባልደረቦቹ ያደረ ፒዛ እበላለሁ ሲላቸው ይህም ይግረማችሁ ብሎ ነበር። "በ2019 ለእራሴ ቃል የገባ...
d5faa61ee5e762af2
የምርጫ ቦርድ ማሻሻያና የብርቱካን ሚደቅሳ ሹመት ምንና ምን ናቸው?
በዚህ ምክር ቤት ስር ደግሞ ምርጫ ቦርድና የምርጫ ህግን ማሻሻል፤ በተጨማሪ እንደ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ እንባ ጠባቂ ተቋምና ፌደሬሽን ምክር ቤት ያሉትን ተቋማዊ ይዘታቸውን መፈተሽ ላይ የሚሠራ የዲሞክራሲያዊ ተቋማት የተሰኘ ቡድን ተቋቁሟል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት የቡድኑ አስተባባሪ ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ የምርጫ ህጉና ምርጫ ቦርድን የማሻሻሉ ነገር ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ተብሎ ቡድኑ እዚህ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ እንደሆነ ይናገራሉ። ቡድኑ እንደ ሃሳብ እየተወያየባ...
d93c6f3422c468c2a
በሩዋንዳ ዘር ጭፍጨፋ የሚፈለጉት ተጠርጣሪ ፈረንሳይው ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ካቡጋ ፈረንሳይ ውስጥ አዝኒዬር ሱር ሴን በተሰኘ ሥፍራ ማንታቸውን ቀይረው እየኖሩ ነበር ተብሏል። ዓለም አቀፉ የሩዋንዳ ወንጀል ችሎት የ84 ዓመቱን ግለሰብ በዘር ማጥፋት ወንጀል እና የሰው ልጅ ላይ ሰቆቃን በመፈፀም ወንጀል ይፈልጋቸዋል። በፈረንጆቹ 1994 የሁቱ አክራሪዎች 800 ሺህ ያክል ሰዎችን ሲጨፍጭፉ ሰውዬው አክራሪዎቹን በገንዘብ ደግፈዋል ይባላል። የሁቱ አማፅያን በወቅቱ የአናሳዎቹን ቱትሲዎችና የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ዒላማ አድርገው ነበር ጥፋት የፈፀሙት። ዩናይትድ ስቴትስ፤ ካቡጋ ያለበትን ...
d052031b74dda5608
ትግራይ ፡ እነ አቶ ስብሐት ነጋ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አቶ አባይ ወልዱ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አብረሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ ሰለሞን ኪዳነ (ዶ/ር) እና አቶ ስብሐት ነጋ አቶ ስብሃት ነጋና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ከሰባት ቀናት በፊት በጠየቀው ቀጠሮ መሰረት የደረሰበትን የምርመራ ሂደት ለችሎቱ አብራርቷል። ተጠርጣሪዎቹ በሃገር ክህደት ወንጀል፣ በክልሉ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በማድረስና፣ በመሳሪያ በታገዘ አመፅና ሁከት በማነሳሳት በሚሉ ወንጀሎች ነው ፍር...
dfcc94d7c4e89e215
የናይጄሪያ ዩኒቨርስቲ በቢቢሲ ዘገባ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅም የታየውን መምህሩን አገደ
ቦኒፌስ ኢግቤንጉ (ዶ/ር) ከመምህርነቱ በተጨማሪም ፓስተር ሲሆን ዘጋቢ ፊልሙ ከታየ በኋላ ከሚያገለግልበት ቤተ ዕምነትም ታግዷል። የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ የተሰራው በምዕራብ አፍሪካ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሲሆን፣ መምህራኖች የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ወሲብን እንደመደራደሪያነት እንደሚያቀርቡ ያሳያል። ይህ የምርመራ ዘገባ በትናንትናው ዕለት ከተላለፈ በኋላ በምዕራብ አፍሪካና በሌሎች ሀገራትም በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እነርሱ በሚማሩበት ተቋምም ተመሳሳይ ነገር እንደሚፈፀም እየጠቀሱ ፅፈዋል። •...
d461c4770762604c4
አማድ ዲያሎ - ቀጣዩ ሳሙኤል ኤቶ?
አማዱ ዲያሎ፤ ከጣልያኑ ክለብ አትላንታ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ኃያሉ ዩናይትድ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ነው የመጣው። ዲያሎ ከኤቶ አልፎ በጣሊያን ሴሪ-አ ለሮማ፣ ለፓርማ ከተጫወተው ሌላኛው አይቮሪ ኮስታዊ ዠርቪንሆ ጋር እየተነፃፀረ ነው። ለዩዲኒዜና ቬሮና ለአስር ዓመታት ያክል የተጫወተው ኢማኑኤል ባዱ "ዲያሎ የአፍሪካ ከዋክብትን ብቃት አጣምሮ የያዘ ነው" ሲል ለቢቢሲ አፍሪካ ስፖርት ይናገራል። "ኳስ ይዞ በመጫወት ረገድ የሳሙኤል ኤቶን ብቃት ይዟል። ኳስ መያዝ እንዴት እንዳለበት ያውቃል። ደግ...
d3204a0858f13c9cb
የአሜሪካና ቻይና የንግድ ጦርነት፡ ዓለምን አደኽይቶ አደጋ ላይ ይጥላል
አይኤምኤፍ የዘንድሮ እና የቀጣዩ ዓመት ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ይቀንሳል ሲል ትንበያ ሰጥቷል። ከቻይና ጋር የተጧጧፈው የንግድ ጦርነት ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊያስከትል ይችላልም ብሏል። •አሜሪካ የቻይና እቃዎች ላይ አዲስ ታሪፍ ጣለች "የሃገራት የንግድ ፖሊሲ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን የሚያንፀባርቅ ነው። በርካታ ሃገራት ደግሞ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ናቸው፤ ይህም ሌላ አደጋ ሊያስከትል ይችላል" ሲሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ሞሪስ ኦብስፌልድ ይናገራሉ። በቅርቡ ቻይና የ60 ቢሊየን ዶላር አዲስ የንግድ ታሪፍ በአ...
dc8a3dbaf4106fd12
የሶሪያ ጦርነት፡ በአሜሪካ የሚደገፈው ጦር ራቃን ተቆጣጠርኩ አለ
ራቃ ከአይ አስ ነጻ መውጣቷን የሚያረጋግጥ ይፋዊ እወጃ እየተጠበቀ ነው የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች አይ ኤስ የሞት ቅጣትን በይፋ ሲያስፈጽምበት የነበረውን የአል-ናይም አደባባይም ተቆጣጥረናል ብለዋል። ድላቸውም በቅርብ ሰዓታት በይፋ እስኪታወጅ እየተጠባበቁ ነው። ከ3000 በላይ የሚሆኑ ንጹኃንም ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ከአይ ኤስ ነጻ ሆነዋል። ጦሩ ለወራት ከተማዋን ከቦ የአይ ኤስ ታጣቂዎች እስኪወጡ እየተጠባበቀ ነበር ራቃ አይ ኤስ ከአውሮፓውያኑ 2014 ጀምሮ ከተቆጣጣራቸው ትልልቅ ከተሞች አንዷ ነበ...
d3b0e9fd931696679
ኮሮናቫይረስ፡ በዩኬ የኮሮና ፅኑ ህሙማን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ተባለ
ነርስ ሆስፒታል ውስጥ በዚህ ምክንያትም ባለፈው ዓመት ቫይረሱ ካደረሰው ሰብዓዊ ጉዳት በላይ አሁን እያስተናገደች ነው። የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩትም የታማሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ነው። ለአብነት በኮሮና ተኅዋሲ ለሚጠቁ ጽኑ ህሙማን እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የትንፋሽ መስጫ መሳሪያ (ቬንትሌተር) የሚያስፈልጋቸው የኮሮናቫይረስ ህሙማን ቁጥር በአንድ ወር ያህል በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመሪያ ጊዜ በሜካኒካል ቬንትሌተ...
dff5213aeb59b5ec2
የላሙ ፕሮጀክት ቦርድ አባላት በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
አምባሳደር መለስ አለም እና የላሙ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ጄኔራል ሲልቪስተር ካሱኩ በፕሮጀክቱ ዳይሬክተር ጄኔራል ሲልቪስተር ካሱኩ የሚመራው ይህ የልዑክ ቡድን፤ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ በሚያደርገው ቆይታ ከተለያዩ የመንግሥት አካላት ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ጉብኝት ላይ 30 የሚሆኑ አባላት የላሙ ኮርደር ልማት የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ከኢትዮጵያ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የሚወያይ ሲሆን በተጨማሪ በኬንያ በኩል የደረሰበትን ደረጃ ማብራሪያ እንደ...
dbf076eee1e9ebad5
ኢራን ለአሜሪካ ሲሰልል ነበር ያለችውን ዜጋ በቁጥጥር ሥር አዋለች
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢራን የአሜሪካ ጥምር ዜግነት ያላቸውን በርካታ ዜጎች ለጠላት አገር አሜሪካ ይሰልላሉ በሚል ምክንያት ዘብጥያ ስታወርድ ሰንብታለች። ግለሰቡ በስም ባይጠቀስም ከዚህ ቀደም ተከሶ በዋስ የወጣና ክሱን ከውጭ ሆኖ እየተከታተለ የነበረ ሰው ነው ብላለች። ሆኖም የክስ ሂደቱን ከውጭ ሆኖ እየተከታተለ ሳለ ተደብቆ ምዕራባዊ ድንበር አቋርጦ ሊያመልጥ ሲል ነው በቁጥጥር አዋልኩት ያለችው። የኢራን መገናኛ ብዙሃን ባለፈው ሳምንት አንድ አሜሪካዊ ኢራናዊ ጥምር ዜግነት ያለው ነጋዴ ነኘ የሚል ኢማድ ሻር...
d205ebcc8169d2060
በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ዓለማችን 1.3 ቢሊየን ቶን የፕላስቲክ ቆሻሻ መሸከም ትችል ይሆን?
ይህ መረጃ ይፋ የሆነው በሚቀጥሉት 20 ዓመታት አጠቃላይ የዓለም የፕላስቲክ አጠቃቀም ችግርና መጠን ምን እንደሚመስል በተደረገ ጥናት ላይ ነው። ከሊድስ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ዶክተር ኮስታስ ቬሊስ እንደሚሉት ቁጥሩ እጅግ አስፈሪ ቢሆንም ችግሩን ለመቅረፍ የሰው ልጅ የደረሰበት የቴክኖሎጂ ምጥቀትና ስልጣኔ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊኖረው ይችላል። '' በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሊኖር ስለሚችለው ጉዳት ጠቅለል ያለ ጥናት ሲሰራ ይሄ የመጀመሪያው ሲሆን የፕላስቲክ ክምሩ ምን ያክል መጠን እንደሚኖረው ማሰብ ከባድ ነው። ም...
de2ddd2fcd7c65ced
ኮሮናቫይረስ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የሚጠቁም መላ ሊፈጠር ነው
መሣሪያው አንድ ሰው በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የቅርብ ግንኙነት ካደረገ ለግለሰቡ መረጃ የሚሰጥ ነው። መሣሪያው በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለማሰስ ጥቅም ላይ ለሚውሉ መተግበሪያዎች የመረጃ ግብዓት እንደሚሰጥ ተገልጿል። መሣሪያውን መጠቀም የሚፈልጉ ሰዎች ማንነታቸውን ሳያሳውቁ መመዝገብ ይችላሉ። ቫይረሱ ከያዛቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ማድረግ አለማድረጋቸው የሚጣራውም የስልካቸውን ብሉቱዝ በመጠቀም ነው። መሣሪያውን የሚጠቀም ሰው ካገኛቸው ሰዎች መካከል ኮቪድ-19 የተገኘባቸው ግለሰቦች...
de4f71ff063586f55
"የአደገኛ ግለሰቦች" የፌስቡክ ገጽ መዘጋት ጀመረ
የማህበራዊ ሚዲያው የሴራ (ኮንስፓይረሲ) ድረ ገጽ የሆነውን 'ኢንፎዋርስ' አቅራቢ አሌክስ ጆንስ፣ የእንግሊዙ ድርገጽ አርታኢ ፖል ጆሴፍ እና የቀድሞው 'የበሬይትባርት' አርታኢ ሚሎ ይአኖፓውሎስን በጥላቻ ንግግር ከሷቸዋል። የጸረ አይሁድ መልዕክቶችን ያስተላለፈውና 'የኔሽን ኦፍ ኢስላም' መሪ የሆነው ሉዊስ ፋራካሃንም ከታገዱት መካከል ነው። • ፌስቡክ የጽንፈኛ አመለካከት አራማጆችን ሊያግድ ነው • እነ ፌስቡክ ግላዊ መረጃዎትን ያለአግባብ እንደሚጠቀሙበት ያውቃሉ? በእንግሊዝ እንደሚገኘው ብሪቴይን ፈርስት ...
d71a6dcc0dab3027b
ኮሮናቫይረስ ፡ ትራምፕ የዋይት ሐውስ አባላት የኮቪድ-19 ክትባት ቀድመው ይወስዳሉ መባሉን ተቃወሙ
ቀደም ብሎ ባለሥልጣናት የትራምፕ አስተዳደር ከፍተኛ ባለሙያዎች የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት ከሚሰጣቸው ሰዎች መካካል እንደሚሆኑ ተናግረው ነበር። ይሁን እንጂ ትራምፕ በእቅዶቹ ላይ ማስተካካያ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። አሜሪካ ክትባቱን ለድንገተኛ/ አስቸኳይ ጊዜ ለመጠቀም የፈቀደች ሲሆን ሥርጭቱ ዛሬ እንደሚጀምር ተገልጿል። ይህ ክትባት ኮቪድ -19ን 95 በመቶ የመከላከል አቅም አለው ተብሏል። የመጀመሪያው ሦስት ሚሊየን ክትባትም በመላው አሜሪካ በ50 ግዛቶች በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰራጭቷ...
dffba0eef7b46adbe
ሬፓን የሸርኮሌው ስደተኛ፡ የድንቅ ሥራዎች ፈጣሪ
ሬፓን ከገነባው ቤት ፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ሬፓን የኢትዮጵያን መሬት የረገጠው ገና በአንድ ዓመቱ ነበር። ሱዳን በጦርነት ስትታመስ ነው ቤተሰቡ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ ሸርኮሌ የስደተኞች መጠለያ የገባው። ያኔ ጨቅላ ነበር፥ ከሚነግሩት ውጪ ሁኔታዎች እንዴት እንደነበሩ አያስታውስም፤ ሁኔታዎች ተረጋግተዋል ተብሎ ወደ ትውልድ ስፈራው ከተመለሰ በኋላ ግን ያሰበው ሁሉ እንዳልነበር በመሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ ስደተኛ ሆኖ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ግድ ሆኖበት ከዓመታት በኋላ ተመልሷል። የዛሬ 14 ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ...
d498c3e3108ac47ea
ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች
"መንገድ ላይ ከጓደኞቼ ጋር የእግር ጉዞ እያደረገን እያለ ነው ያየኋት። እንዳየኋት ወደድኳት" ይላል ወንድሙ ሁለት አስርት ዓመታት የተሻገረውን የአብሮነት ጥንስስ ሲተርክ። መተያየት ወደትውውቅ፥ እርሱም ወደ ፍቅር ግንኙነት ሲያድግ ጊዜ አልፈጀበትም። ለጥቆም ትዳር መጣ። ልጆች ተከታተሉ። ሶፍያ የእስልምና እምነቷን እንደያዘች፥ ወንድሙም ከክርስትና የኃይማኖት ጎዳና ፈቀቅ ሳይል። "መጀመሪያ ስንገናኝ የኃይማኖታችን መለያየት ብዙም ችግር ሆኖ አልታየኝም" ትላለች ሶፍያ። "ልጅነትም ስለነበረ ስለዚህ ጉዳይ አ...
d218823e6048d95ae
የፕላስቲክ ብክለትን እንደሚያስቆም ተስፋ የተደረገበት ስምምነት
በአካባቢ ደህንነት ላይ ትልቅ ችግር የሚያስከትሉት የፕላስቲክ ቁሳቁሶች የአካባቢ ጥበቃ ስምምነቶች ትኩረት መሆናቸውን ኤክስፐርቶች ይናገራሉ። ስለዚህም ተስፋ በተጣለበት ስብሰባ ፕላስቲኮች የሚያስከትሉትን የአካባቢ ቀውስ የሚያስቆም ጠንካራ ስምምነት እንዲደረግ በኬንያ ናይሮቢ የከተሙት ልዑካን ዝግጅት እያደረጉ ነው። ስምምነቶቹ በጠንካራ እርምጃ የሚታገዙ እንደሚሆኑም ይታመናል። ልዑካኑ ፕላስቲኮችና ጥቃቅን ፕላስቲክ ነክ ቆሻሾች የሚያስከትሉትን ችግር ለመቅረፍ የሚረዱ አማራጮችንም እየተመለከቱ ነው። አሜሪካ ...
dfe9f68cb8763528b
ቦይንግ በ737 አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው ከ144 ሺህ ዶላር በላይ ሊከፍል ነው
በኢንዶኔዢያው ላየን ኤርና በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ላይ በደረሰው አደጋ ለሞቱት 346 ሰዎች ከቦይንግ የገንዘብ ድጋፍ ፈንድ ወጪ ተደርጎ ለአደጋዎቹ ሰለባ ቤተስቦች እንዲከፈል 50 ሚሊዮን ዶላር ተመድቧል። በሐምሌ ወር ቦይንግ ይፋ ያደረገው ቀሪ የ100 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ደግሞ ለትምህርትና ለልማት ፕሮግራሞች ይውላል ተብሏል። • "ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት • "ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም" አቶ ተወልደ ገብረማርያም ገንዘቡን የሚከፍለው አካል...
df250dd89f7041106
ሩሲያ የአሜሪካን እርምጃ ተከትሎ 60 ዲፕሎማቶችን ከሀገሯ እንዲወጡ አደረገች
በሴይንት ፒትስበርግ የሚገኘው የአሜሪካ ቆንፅላ ሊዘጋ ነው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳሉት ሩሲያዊያንን ከሀገራቸው ያስወጡ ሀገራት ሁሉ "ተመጣጣኝ" የሆነ ምላሽ ይጠብቃቸዋል። ይህ እርምጃ የመጣው በደቡባዊ እንግሊዝ ይኖር የነበረ የሩሲያ የቀድሞ ሰላይ እና ልጁ ነርቭን በሚጎዳ መርዝ መመረዛቸውን ተከትሎ ነው። ዋይት ሀውስ ይህ የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ከሀገሯ የማስወጣት ድርጊት "ያልተጠበቀ አይደለም" ሲል ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። መግለጫው አክሎም "በአሜሪካና በሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ...
d80b6ce0a459326cd
የቄለም ወለጋ ዞን ባለስልጣን የተገደሉት ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል
የቄለም ወለጋ ዞን የጸጥታና ህዝብ ደህንነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ ታምሩ በበኩላቸው አምስት ሰዎች በመከላከያ ኃይል መገደላቸውን አረጋግጠዋል። ነገር ግን እሳቸው እንደሚሉት የተገደሉት ሰዎች ንጹሃን ሳይሆኑ የታጠቁ ሃይሎች ናቸው ብለዋል። "የመከላከያ ሰራዊት እርምጃ የወሰደው በንጹሃን ዜጎች ላይ ሳይሆን በታጠቁ እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ሽፍቶች ላይ ነው" ብለዋል። •በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ •«ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ...
dcf279ffac481d502
በማኅበረሰቦች መካከል ሰላም ለመፍጠር የቴሌቪዥን ጣቢያ የከፈተችው አዲሷ ሚኒስትር
ፊልሰን አብዱላሂ አህመድ መጋቢት 3/2012 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ በዕጩነት ቀርበው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሹመታቸው ከጸደቀው ሚኒስትሮች መካከል ለእንዲህ አይነቱ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነት ከበቁት መካከል አዲሷ የሆነችው ወ/ሮ ፊልሰን በማኅበረሰቦች መካከል መግባባትን ለመፍጠር የሚሰራ የቴሌቪዥን ጣቢያን መስርታ ስትሰራ ቆይታለች። የ29 ዓመቷ ወ/ሮ ፊልሰን እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚኒስትርነት የኃላፊነት ቦታ ላይ ካገለገሉ ወጣት ተሿሚዎች መካከልም የምትጠቀስ እንደሆነም ይነገራል። ከጥቂት ...
d1faa0c4cbd2dca03
በሕንድ በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የተያዙ ስድስት ግለሰቦች ተገኙ
ስድስቱ ሰዎች ከዩናይትድ ኪንግደም በቅርብ የተመለሱ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ቫይረሱ ከተገኘባቸው በኋላ ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ መደረጉ ተነግሯል። ሕንድ ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጣ ምንም አይነት የአየር ትራንስፖርትን ያገደችው ባለፈው ሳምንት ነበር። ባለሙያዎች አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በፍጥነት የሚዛመት መሆኑን ገልፀው ነገር ግን አደገኛነቱ እምብዛም ነው ብለዋል። ሕንድ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያረጋገጠቻቸው ዜጎቿ ቁጥር 10 ሚሊዮን ያለፈ ሲሆን ይህም በተህዋሲው ከተጠቁ የዓለም አገራት መካ...
d7c6a8920658c9dac
ባለጊዜው የግመል ወተት
የአውስትራሊያ የግመል ወተት ንግድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎመራ መጥቷል። በአገሪቱና በዓለም አቀፍ ደረጃም የግመል ወተት ፍላጎት እየጨመረ ነው። ላውረንና ቤተሰቦቿ በግመል ወተት ንግድ የተሰማሩት ትርፋማ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፤ ሥራውን ስለሚወዱት ጭምርም ነው። ግመሎቹን ከቤተሰቡ አባላት ለይተው እንደማያዩዋቸው ትናገራለች። • የዱቄት ወተት እና የእናት ጡት ወተት ምንና ምን ናቸው? "እንደ ሰው የተለያየ ባህሪ አላቸው። አጠገባቸው ሆነሽ ስለ ምንም ጉዳይ ብታወሪ ይረዱሻል" ትላለች። ብዙ የአውስታራሊያ አርሶ አ...
dbc7317421186ee17
በአንበጣ መንጋ ስጋት ሶማሊያ ብሔራዊ አደጋ አዋጅ አወጀች
የሶማሊያ የግብርና ሚንስቴር በከፍተኛ ሁኔታ አዝርእትን ሊያወድም የሚችለው አንበጣ "በሶማሊያውያን የምግብ ደህንነት ላይ አደጋ ደቅኗል" ብሏል። ምርት ከሚሰበሰብበት ሚያዚያ ወር በፊት የአንበጣ መንጋውን በሶማሊያ መቆጣጠር እንደማይቻል ተነግሯል። የተባበሩት መንግሥታት በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ የተከሰተው መንጋ በአገራቱ 25 ዓመታት ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ብሏል። የምግብ እና ግብርና ድርጅት (ፋኦ) እንደሚለው ጎረቤት አገር ኬንያ ደግሞ ይህን መሰል የአንበጣ መንጋ ሲገጥማት ከ70 ዓመታት በኋላ ለመጀ...
d4695c41de581ee46
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በእንግሊዝ የክብር ማስታወሻ ምልክቶች ተቀመጠላቸው
ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በእንግሊዝ ቆይታቸው ወቅት የጣልያን ጦር ኢትዮጵያን በተቆጣጠረበት ወቅት ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ እ.አ.አ. ከ1936 እስከ 1940 ድረስ በስደት ኑሯቸውን በእንግሊዟ ባዝ አድርገው እንደነበር ይታወሳል። • ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ • ችግኝን በዘመቻ መትከል መቼ ተጀመረ? በእንግሊዝ ቆይታቸውም ዌስቶን ሱፐር ሜር ወደ ሚባል ቦታ በመሄድ በውሃ ዋና ይዝናኑ እንደነበር ይነገራል። 'ብሉ ፕሌክ' በመባል የሚታወቀው ይህ የክብር ማስታወሻ እንግሊዝ ውስጥ የማይረሳ ሥራ የሠሩ ...
db7a6a073ad1cef94
አርሜንያ እና አዘርባጃን በአወዛጋቢው ክልል ተጋጩ
የአርሜንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን እንዳስታወቁት የአዘርባጃን ወታደሮች በአየር እና በዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች በመታገዝ ጥቃት ሰንዝረዋል። አክለውም የአርሜንያ ወታደሮች በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ ሁለት የአዘርባጃን ሄሊኮፕተሮችን እና ሶስት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ተኩሰው መጣላቸውን አስታውቀዋል። አዘርባጃን በበኩሏ አርሜንያ በአወዛጋቢው ክልል መስመር ላይ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን በመጠቀም ዘመቻ መክፈቷን ገልጻለች። ናጎርኖ- ካራባክ የተባለውን ክልል ተከትሎ ለረዥም ዓመታት የቆየው ይህ የሁለቱ አገ...
d3e7e1cd523446059
አብን አቶ ክርስቲያንን ጨምሮ ከአምስት መቶ በላይ አባላቶቹ እንደታሰሩ ገለፀ
በቁጥጥር ስር የዋሉት ዛሬ ረፋድ ላይ ስለታሰሩ የአብን አባላት ሁኔታና አያያዝ ሁኔታ ጋር ለመወያየት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባመሩበት ወቅት እንደሆነ የአብን ሊቀ መንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በወቅቱ ቦታው ላይ የነበሩት ዶ/ር ደሳለኝ እንዲሚያስረዱት ውይይታቸውን ጨርሰው በር ላይ እንደደረሱ የደህንነት ሰዎች ነን የሚሉ ግለሰቦች ለምርመራ እንደሚፈለጉ ገልፀው አቶ ክርስቲያን መውጣት እንደማይችሉ ነግረዋቸዋል። •አብን ከ100 በላይ አባላቶቼ ታስረዋል አለ •"ብ/ጄኔራል አሳምነውን ...
df4cb624f6130892c
የ 'ኮፒ ፔስት' ፈጣሪ ሞተ
ላሪ ተስለር ከት፣ ኮፒ እና ፔስት የሚሉትን ሦስት የኮምፒውተር ትዕዛዝ አይነቶች የፈጠረው ግለሰብ ላሪ ተስለር ይባላል። የኮምፒውተር ልሂቁ ላሪ በ74 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ላሪ በግዙፉ የቴክኖሎጂ ማዕከል ሲልከን ቫሊ መሥራት የጀመረው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1960ዎቹ መባቻ ነበር። ያኔ ኮምፒውተር ያላቸው ሰዎች እምብዛም አልነበሩም። • የሰዎችን ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ እያከራከረ ነው • ሞና ሊሳ "ነፍስ ዘራች" ላሪ የፈጠራቸው ኮፒ፣ ፔስት እና ከት የኮምፒውተር አጠቃቀምን አቅልለዋል፤ ...
dbb51e7065dd18d8d
'በእርግማን' የተፈጠረው የኮንሶው 'ኒው ዮርክ'
ከሕብረተሰቡ መመሪያ አፈንግጦ ስህተት የሠራው ይህ ልዑል፤ 'የጎሣ መሪ የሆነ ንጉሥ ሁለት ሚስት ማግባት አይችልም' የሚለውን የኮንሶዎች ሕግ ተላልፎ ሁለት ትዳር መሠረተ። የልዑሉ ድርጊት የሌሎች ጎሣ መሪዎችን ልብ አሳዘነ፤ አስቆጣቸውም። በዚህ ብቻ አላበቁም፤ 'ቅጣትም ይከትልሃል' ሲሉ በየኑ። •የጠቅላይ ሚኒስትሩ 200 ሚሊዮን ችግኞች •"እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ •ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው ብይኑ ደግሞ እንዲህ ይላል፤ 'ከዚህ በኋላ ንጉ...
d784c7c0a69b47480
በሞያሌ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ በህይወት እና በአካል ላይ ጉዳት ደረሰ
የከተማዋ ነዋሪዎች እንደነገሩን ከሆነ በሞያሌ ከተማ መናሃሪያ አካባቢ በኦሮሞ እና በሶማሌ ተወላጆች መካከል ግጭት ከተከሰ በኋላ የእጅ ቦንብ ተወርውሮ ቢያንስ ሁለት ግለሰቦች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ ለጉዳት ተዳርገዋል። የሞያሌ ወረዳ ጤና ጣቢያ ጽ/ቤት ምክት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሁሩካ ጎዳና ለቢቢሲ እንደተናገሩት በፍንዳታው ሁለት ሰዎች መገደላቸውን እና ወደ 63 የሚጠጉ ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ከዞኑ የኮምዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለተው የሟቾቹ ቁጥር አራት የደረ...
d18451040f510c12f
የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት አምቦ ውስጥ ተፈጸመ
ይሁን እንጂ አሁንም ድምጻዊው መቀበር ያለበት በአዲስ አበባ ነው በሚል ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ በርካቶች ናቸው። ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በመገኘት ሽኝት አድርገዋል። በስታዲየሙ የተገኘው ሰው ቁጥር አነስተኛ እንዲሆን የተደረገው በደኅንነት ስጋት መሆኑ ተነግሯል። • ከሃጫሉ ግድያ በኋላ ቢያንስ የ67 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ተገለጸ • የሰኔ 15ቱ አይነት ግድያን ለመድገም ታቅዶ እንደነበር የፌደራል ፖሊስ ገለፀ • በአምቦ የሃጫሉ አጎትን ጨምሮ አምስት ሰዎ...
d04074dbc250a12bd
ትግራይ፡ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) ሠራተኞች ትግራይ ውስጥ 'ሰዎች ሲገደሉ ማየታቸውን' ተናገሩ
ግብረሰናይ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ሠራተኞቹ ከክልሉ ዋና ከተማ መቀለ ወደ አዲግራት በሚወስደው መንገድ ላይ እየተጓዙ ሳለ በወታደሮች የተፈጸመውን ግድያ መመልከታቸውን ገልጿል። "ወታደሮቹ በሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ሲጓዙ የነበሩ ሰዎችን አስገድደው እንዲወርዱ ካደረጉ በኋላ ሴቶቹን ከወንዶቹ ለይተው እንዲሄዱ ፈቀዱላቸው። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወንዶቹ በጥይት ተመተው ተገደሉ" ሲል መግለጫው ሁኔታውን ያብራራል። "ይህ የተከሰተው የታጠቀ ቡድን በኢትዮጵያ ሠራዊት ተሽከርካሪዎች ላይ የደፈጣ ጥቃት ...
d640b072a395c454e
ግብጽ ቲክ-ቶክ 'ቀብጣችኋል' ብላ ያሰረቻቸውን ሴቶች እንድትፈታ ተጠየቀ
ማዋዳ ቲክ-ቶክ በተሰኘው የማኅበራዊ ድራምባ መተግበሪያ ‹‹ቀብጣችኋል›› ያለቻቸውን ሴት የቲክቶክ ዝነኞችን በማሰሯ ነው በግብጽ ላይ ጫናው የበረታው፡፡ ሴት ልጆቹ በቲክ-ቶክ በኩል ፖለቲካዊ ተቃውሞ በማሰማታቸው አይደለም የተሳረቱት፡፡ ‹‹የግብጽን ቤተሰባዊ እሴት የሚንድ…›› ተግባር ፈጽማችኋል ተብለው ነው፡፡ ሴቶቹ በቲክ-ቶክ በቄንጠኛ ልብሶች አጊጠው ሲደንሱ ነው የሚታዩት፡፡ ከነሱ ውስጥ አምስቱ እያንዳንዳቸው ሁለት ዓመት ተፈርዶባቸዋል፡፡ ‹‹ደንግጠናል፣ እህቴ ምንም መጥፎ ነገር አልሰራችም፡፡ ወንጀለኛ...
d8b3b5b74b4146760
የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት አል በሺር በሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው
ፕሬዝዳንት አል በሽር ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ ነበር ከረዥም ጊዜ ሕዝባዊ ተቃውሞ በኋላ በከፍተኛ የሃገሪቱ ጦር ሠራዊት ባለስልጣናት ከመንበራቸው እንዲወርዱ የተደረጉት። ሐሙስ እለት የወታደራዊ ኃይሉ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት የተካሄደው ተቃውሞ እንዲያበቃ ትዕዛዝ ሲሰጥ ስህተት ተከስቷል ብለዋል። ለረዥም ጊዜ የተካሄደው ተቃውሞ በወታደራዊ ኃይሉ እንዲቆም መደረጉን ተከትሎ 61 ሰላማዊ ሰልፈኞች መሞታቸውን ባለስልጣናት ቢናገሩም ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት ያለው የሐኪሞች ቡድ...
d9182b469dc7c33d0
ስንፍናን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?
ወረርሽኙ የበርካቶችን የሕይወት አቅጣጫ ለውጧል። ጊዜ ለማሳለፍ ሲሉ ቋንቋ መማር፣ ቤት ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መሥራት ወይም ምግብ ማብሰል መለማመድ የጀመሩ አሉ። አዳዲስ ነገር የመሞከር ተነሳሽነት ሁሌም አብሮን ይዘልቃል ማለት ግን አይደለም። አንዳንዴ በከባድ ስንፍና ሳቢያ ትንሽ ነገር እንኳ መፈጸም ይሳነናል። በዚህ ወቅት ራሳችንን ዳግመኛ ማነሳሳት የምንችልባቸውን ጥቂት መንገዶች እንመልከት። አዲስ ነገር መሞከር ተነሳሽነት ለራስ የሚጠቅም ተግባር ማከናወን እንዲሁም ለሌሎች መትረፍንም ያካትታል...
d1f96ee2c686eec9f
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ በቁጥጥር ሥር ዋለ
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመገደሉ ከአንድ ሳምንት በፊት በኦኤምኤን በተላለፈው ቃለ መጠይቅ ላይ ድምጻዊውን ቃለመጠይቅ ያደረገው ጉዮ መሆኑ ይታወሳል። ቢቢሲ ከቤተሰቡ አባላት እንደሰማው ዛሬ እኩለ ቀን ላይ "የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ዩኒፎርም የለበሱ" ጉዮን ከመኖሪያ ቤቱ ይዘውት ሄደዋል። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የአዲስ አበባ ቢሮ የተዘጋው የሃጫሉ መገደልን ተከትሎ በተፈጠረው ግርግር ሰኔ 24 ማክሰኞ ዕለት ነበር። ለቢቢሲ በቁጥጥር ስር መዋሉን የተናገሩት አንድ የቤተሰቡ አባል እንዳሉት ከሆነ፤ የጸጥ...
d35906584791b5daa
ተመድ ቻይና ''ሙስሊሞችን በጅምላ መያዟ » አሳስቦኛል አለ
የተመድ ቻይና በዩጉሁረስ ጎሳ አባላት ላይ መድሎ ትፈፅማለች ሲል ከሷል። ቻይና ቁጥራቸው 1 ሚሊየን የሚሆኑ፣ በምዕራብ ዣንግጂያንግ ክልል የሚኖሩ ሙስሊም የዩጉሁረስ ጎሳ አባላትን በ «መልሶ ማስተማር» ጣቢያዎች ውስጥ ማጎሯን የሚያሳይ 'ሪፖርት' መውጣቱን ተከትሎ ነው ተመድ ድምፁን ያሰማው። ቤጂንግ አቤቱታውን ብትቃወምም የተወሰኑ የሃይማኖት አክራሪዎች ለ«መልሶ ማስተማር» ዓላማ እንደያዘች አምናለች። • በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያዊያን ንብረት ተዘረፈ • ሳሙኤል ኤቶ ለቀድሞው የብሄራዊ ቡድን አምበል ቤት ...
End of preview. Expand in Data Studio

XL-Sum (MTEB retrieval format)

Multilingual news summary-to-article retrieval task across 45 languages. Each language is a monolingual subset with <lang>-corpus, <lang>-queries, and <lang>-qrels configs. Given a summary, retrieve the relevant news article. Built from the test split, capped at 1000 per language.

Reformatted into MTEB retrieval format from csebuetnlp/xlsum.

License: CC BY-NC-SA 4.0.

Downloads last month
281

Collection including bowang0911/xlsum-retrieval