Dataset Viewer
Auto-converted to Parquet Duplicate
instruction
stringclasses
2 values
extractive_text
stringclasses
3 values
summary
stringclasses
3 values
Summarize the following news article into a concise headline.
ከተከሰተ ከአመት በላይ ያስጠቆረው የኮቪድ ወረርሽኝ ዛሬም በደቂቃ ዘጠኝ በየእለቱ ደግሞ በሽወች የሚቆጠሩ ሰወችን እየነጠቀ ይገኛል። በጣም ተጋላጭ የሆኑት በጉልህ ይጎዳሉ፣ አሁን ላይ ያለው አደጋ ወረርሽኙን ለመግታት ባለሁለት ፍጥነት የአለም ምላሽ መኖሩ ነው ብለዋል። የገንዘብ አቅም፣ ጊዜንና የሞት መጠንን በቀነሰ መልኩ በአጭር ጊዜ ለውጥ ማምጣት የሚቻልበትን አዋጭ የጦርነት ስልት አይነት በመጠቀም የኮሮና ወረርሽኝ በአለም ላይ እያደረሰ ያለውን ከባድ ጉዳት በአጭር ጊዜ መመከት ይገባል እንደ ጉተሬስ። ከዚህም ባለፈ አይነቱን መቀያየሩና ከአለም ህዝብ አንድ ሶስተኛውን ያልደረሱት ክትባቶች አይነቱን ቀይሮ የሚመጣውን የኮሮና ወረርሽኝ ይከላከሉ አይከላከሉ በጥናት አለመረጋገጡ፣ የወረርሽኙ ባህሪ የጤናውን ስርአት አብዝቶ የሚፈትንና ከየትኛውም አገር አቅም በላይ መሆኑ ከተከሰተ ከአመት በኋላም የአለም አጀንዳነቱን እንደያዘ ቀጥሏል። የአለም ጤና ድርጅትና ሌሎች የፈጠሩት አለም አቀፍ የክትባት ፕሮግራም ኮቫክስም፣ ክትባቱ ለአገሮች በፍትሃዊነት ተደራሽ እንድሆን አላማ አስቀምጦ ቢንቀሳቀስም፣ የኮቪድ ክትባት አቅርቦት ጉልህ እጥረት ገጥሞታል። አሁን ያለውን የኮቪድ ወረርሽኝ መከላከል እንዳለ ሆኖ፣ የሚቀጥለውን ወረርሽኝ ለመከላከል ራስን ማዘጋጀትና የአለም ጤና ስርአትን ማጠናከር ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል። አገሮች ይህ መድሃኒት ያልተገለኘትን ወረርሽኝ ለመዋጋት ከቅድመ መከላከል ጀምሮ እስከ የአስቸኳይ ጊዜ ክትባት ቢዘልቁም፣ ቫይረሱን መቋቋም አልተቻለም። ቫይረሱ በአንድ ጊዜ አንድ አገር ብቻ አጥቅቶ የማይቀር በመሆኑም፣ ተጽእኖው አለም አቀፋዊ ነው። የአለም ጤና ድርጅት አመታዊ ጉባኤን በሳምንቱ መጀመርያ የከፈቱት ጉተሬስ፣ ከሶስት ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ ሰወች በቫይረሱ ምክንያት መሞታቸውንና ግማሽ ቢሊዮን ያህል ስራወች መክሰማቸውን ተናግረዋል። ወረርሽኙን የማስቆም አቅም በቡድን ሃያ አገሮች እጅ ላይ ነው የሚለው የአለም ጤና ድርጅትም፣ አገሮቹ ወረርሽኙን ለመከላከል፣ የመመርመር አቅምን ለማጠናከር፣ ክብካቤና ክትባቱም ለሁሉም በፍትሃዊ መንገድ እንድዳረስ ለማስቻል የጀመሩትን ስራ ማጠናከር ይገባቸዋል።
አለም ከኮቪድ ጋር የገጠመው ጦርነት
Create a short title for the given news content.
የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ግንቦት ፣ ሁለት ሽህ አምስት ጧት ላይ በደህንነቶች ተይዞ መወሰዱን የማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት ሃብታሙ አያሌው ለኢሳት ገልጿል። ምሽት ሰአት ላይ ያነጋገርነው የማህበሩ ቦሌ ክፍለከተማ ምክትል ሃላፊ ወጣት ጥላየ ታረቀኝ እንደገለጸው ደግሞ ከዚህ ቀደም ታስረው በነበረበት ወቅት ሲዝትባቸው የነበረው ሳምሶን የተባለ የደህንነት ሰራተኛ ወጣት ብርሃኑን እንዳስያዘው ገልጿል። የወጣት ብርሃኑ ቤተሰቦች ቤት ሲፈተሽም በአንድ መጽሃፍ ውስጥ ራሳቸው ደህንነቶች ያስገቡትን ጽሁፍ ይሃው አገኘነው በማለት ብርሃኑን እንድፈርም እንደጠየቁትና ከጠበቃየ ጋር ሳልማከር አልፈርምም እንዳለ ወጣት ጥላየ ተናግሯል። ወጣት ሃብታሙ ከሌሎች የማህበሩ አባላት ጋር በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢሄዱም፣ እስረኛውን ሊያገኙት እንዳልቻሉ ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ የወጣት ብርሃኑ ቤት እየተፈተሸ መሆኑን መረጃ እንደደረሳቸው ገልጿል። ወጣት ብርሃኑ ሰማያዊ ፓርቲ ከጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መታሰሩን ወጣት ሃብታሙ ገልጿል። በጉዳዩ ዙሪያ የጉለሌን ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊወች ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሰካም።
የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ታሰረ
Summarize the following news article into a concise headline.
አድስ አበባ፣ መጋቢት ስምንት፣ ሁለት ሽህ ኤፍ ቢ ሲ የፌደራሉ መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ ድጋፍ እንድደርስ አስፈላጊውን ገንቢ ሚና እየተጫወተና እርዳታ እንድላክ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። ከሰባት መቶ ሽህ ህዝብ በላይ እንድፈናቀል እና ከአብአላ በኩል ወደ መቀሌ የሚደረገው የሰብአዊ አገልግሎት ጉዞ እንድቋረጥ ያደረገውም፥ በአፋር ክልል ላይ ዳግም ወረራ ያካሄደው ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን መሆኑ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል ሲል መንግስት በመግለጫው አስገብዝቧል። መግለጫው እንዳመለከተው፥ ከትናንት ጀምሮ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያደርጉ አጋር ድርጅቶች ክትባትን ጨምሮ የተለያዩ መድሃኒቶች፣ የህክምና ቁሳቁስና የምግብ አቅርቦት ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ እንደሚችሉ አረጋግጠዋል። በክልሉ ህዝብ መሰረታዊ ሰብአዊ ድጋፎች ፈጥነው እንድደርሱ ለማድረግ ከቅርብ ቀናት ጀምሮ በየእለቱ አርባ ተሽከርካሪወች ወደ ትግራይ ክልል እንድጓጓዙ የሚደረግ መሆኑንም ነው መንግስት ያስታወቀው። መንግስት የህዝቡን መብት ለማረጋገጥና በችግር ላይ ያሉትን ዜጎቹን ህይወት ለመታደግ ከማንም በላይ ሃላፊነት እንደሚሰማው ገልጾ፥ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የሚላከው ሰብአዊ ድጋፍ ለህዝቡ በቀጥታ እንድደርስ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስቧል። የኢፌደሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ መንግስት ለትግራይ ህዝብ አስፈላጊ የሆኑ የምግብና የመድሃኒት ድጋፎች በአፋር ክልል በኩል እንድደርሱ ምቹ ሁኔታወችን ከመፍጠሩ በተጨማሪ በዛሬው እለት ብቻ የምግብ አቅርቦቶችን የያዙ ሃያ የጭነት ተሸከርካሪወች እና የነዳጅ ታንከሮችን የያዙ ሶስት ተሽከርካሪወች ከሰመራ ወደ መቀሌ መጓዛቸውን አስታውቋል። አለም አቀፉ ማህበረሰብም ችግሩን በሚመጥን ደረጃ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት አመልክቷል። በዚህም መሰረት ሌሎች አጋር ድርጅቶች በጭነት አውሮፕላን ሁለት መቶ ሃምሳ ሰባት ሽህ አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ኪሎ ግራም መድሃኒቶች፥ የህክምና ቁሳቁስና የምግብ አቅርቦቶችን ከአድስ አበባ ወደ መቀሌ ማጓጓዛቸው ተገልጿል። ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃወችን ለማግኘት፡ ድረ ገጽ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን።
መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ ድጋፍ እንድደርስ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ
README.md exists but content is empty.
Downloads last month
4