text
stringlengths
26
19k
የፎቶው ባለመብት SM/ Biniam Hirut-መስቀል አደባባይ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ቦታ ካላቸው ስፍራዎች መካከል አንዱ ነው።-ከአራት ኪሎ ለመውጣትም ወደ አራት ኪሎ ለመግባትም መስቀል አደባባይ ቅርብ ነው።-የመስቀል አደባባይ የፖለቲካ ንዝረት አራት ኪሎ ጮኽ ብሎ ይሰማል። ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የአገሪቱን የፖለቲካ ትኩሳት መለኪያ ቦታው መስቀል አደባባይ ነው።-መስቀል አደባባይ የባለጸጋ አጸድ ሳይመስል በፊት የአገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት መለኪያ፣ የብሶት ማስተንፈሻ ...
የፎቶው ባለመብት US CENTRAL COMMAND-የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከብ በጋዛ ጊዜያዊ ወደብ ለመገንባት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ጉዞ መጀመሯን የአገሪቱ ጦር አስታወቀ።-ለወደብ ግንባት ግብዓቶችን የጫነችው ጀነራል ፍራንስ ኤስ ቤሰን የተባለችው መርከብ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ከአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ተነስታለች።-የመርከቧ ጉዞ የተሰማው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካ ለጋዛ ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ተንሳፋፊ የሆነ ጊዜያዊ ወደብ እንደምትገነባ ካስታወቁ በኋላ ነው።-የተባበሩት መንግሥታት በእስራኤል...
የፎቶው ባለመብት Reuters-አሜሪካ በወሮበላ ቡድኖች አመጽ እየታመሰች ካለችው ሄይቲ መሠረታዊ ያልሆኑ የኤምባሲ ሠራተኞችን ከአገሪቱ በአየር ማስወጣቷን ገለጸች።-አሜሪካ በሄይቲ ዋና ከተማ ፖርት-አው -ፕሪንስ በሚገኘው ሚሽኗ የጸጥታ ጥበቃንም አጠናክራለች።-በዚህ ሳምንት በአውሮፕላን ማረፊያ፣ በፖሊስ ጣቢያዎች እና በማረሚያ ቤቶች ላይ ጥቃት ያደረሱት ወሮበሎች የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪዬል ሄንሪ ከስልጣን እንዲወርዱ ግፊት እያደረጉ ነው።-ለሦስት ቀናት ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአንድ ወ...
የፎቶው ባለመብት @AUC_PAPS-የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮች ባሉበት የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊዎች በፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጸም መዘግየት ዙሪያ ውይይት ጀመሩ።-ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጥሯል።-ምንም እንኳ ከስምምነቱ መፈረም በኋላ የተኩስ አቁም ተደርጎ ጦርነቱ ቢቆምም የስምምነቱ አካል የሆኑ ሌሎች ጉዳዮች ተፈጻሚነት መዘግየቶች ገጥመውታል።-በተለይ በስምምነቱ የተካ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በኢንዶኔዢያ በረራ ላይ ሳሉ ለ28 ደቂቃዎች ተኝተው በነበሩ ዋና አብራሪ እና ምክትል አብራሪ ላይ ምርመራ መከፈቱ ተገለጸ።-የአገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር የባቲክ አየር መንገድ አብራሪዎች ከሥራ ታግደው ምርመራው እየተካሄደባቸው እንደሆነ አስታውቋል።-ሁለቱ አብራሪዎች በረራ ላይ ሳሉ እንቅልፍ የጣላቸው ከ7 ሳምንታት በፊት በነበረ ወደ መዲናዋ ጃካርታ ሲደረግ በነበረ የአገር ውስጥ በረራ ላይ ነበር።-አብራሪዎቹ ምንም እንኳ ለበርካታ ደቂቃዎች ተኝተው የነበረ ቢሆንም ...
የፎቶው ባለመብት PRINCE OF WALES-የዌልሷ ንግሥት ለእናቶች ቀን የለቀቀችው ፎቶ በዜና ወኪሎች ውድቅ መደረጉን ተከትሎ “ለተፈጠረ ግራ መጋባት” ይቅርታ ጠይቃለች።-ካትሪን በኬኒስንግተን ቤተ-መንግሥት የማሕበራዊ ገፅ በኩል በወጣ መግለጫ ነው ይቅርታ የጠየቀችው።-“እንደ ማንኛውም ጀማሪ ፎቶ አንሺ አንዳንድ ጊዜ እኔም ፎቶዎችን ለመሟሸት እሞክራለሁ” ብላለች።-የዌልሷ ንግሥት ኬት ሚድልተን ባለፈው ጥር ቀዶ ጥገና ካደረገች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የዌልሱ ንጉሥ ባነሱት ፎቶ ላይ የታየችው።-ፒኤ፣ ጌ...
የፎቶው ባለመብት EPA-EFE/REX/SHUTTERSTOCK-ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ምርጫ አሸንፈው ፕሬዝደንት ከሆኑ ለዩክሬን ምንም ድጋፍ አይሰጡም ሲሉ የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክተር ኦርባን ተናገሩ።-ወግ አጥባቂው ጠቅላይ ሚኒስትር በአሜሪካዋ ፍሎሪዳ ግዛት ከትራምፕ ጋር ከተወያዩ በኋላ “ለዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት አምስት ሳንቲም እርዳታ አያደርጉም። ለዚህ ነው ጦርነቱ ያበቃል የምንለው” ብለዋል።-የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ከተመረጡ ጦርነቱን “በ24 ሰዓታት” እንደሚቋጩት ቢናገሩም እንዴ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ለእስልምና እና ለክርስትና እመነት ተከታዮች ዋነኞቹ የፆም ወቅት የሆኑት ረመዳን እና ዓቢይ ፆሞች ተጀምረዋል። የሁለቱም እምነቶች ምዕመናን የፆሙን ጊዜ በየራሳቸው ሥርዓት እና ደንብ መሠረት የሚከውኑት ሲሆን፣ በየዕለቱ ለረጅም ሰዓታት ከምግብ እና ከውሃ ርቀው ይቆያሉ።-የየእምነቶቹ ተከታዮች በፆም ወቅት ከእህል ውሃ ከመቆጠባቸው በተጨማሪ በልገሳ እና መልካም ነገሮችን እያደረጉ በጸሎት እና በምሥጋና ወደ ፈጣሪያቸው የበለጠ የሚቀርቡበበት ነው።-ምዕመናን በዋናነት በፆም...
አዋድ ኦማር በሞምባሳ ኦልድ ታውን ገበያ አነስተኛ ሱቅ ዘርግቷል። ከሳዑዲ አረቢያ የሚመጣ ጣፋጭ ቴምር እና ከየመን እና ከጀርመን የሚገባ ማር ይሸጣል።-የአዋድ ትልቁ የገበያ ወቅት አሁን ነው። የረመዳን ወር። ለፆመ ረመዳን ብዙ ሲዘጋጅ ቢከርምም ቀይ ባሕር ላይ ያለው ነገር አሳስቦታል።-ለዚህ ነው ከሌላው ጊዜ ቀደም ብሎ ከውጭ አገር ምርቶች ለሚያመጡለት ደንበኞቹ ትዕዛዝ የሰጠው።-ነገር ግን በዚህ ምክንያት የኬንያ መንግሥት ለረመዳን ያስቀመጠው ከታሪፍ ነፃ ምርት የማስገባት ዕድል አምልጦታል።-የኬንያ መን...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የህንድ መንግሥት ጸረ ሙስሊም ተብሎ የተተቸውን አወዛጋቢ የዜግነት ማሻሻያ ህግ ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ።-የዜግነት ማሻሻያ ህግ (ሲኤኤ) የተባለው ህግ ከፓኪስታን፣ ከባንግላዴሽ እና ከአፍጋኒስታን የሚመጡ ሙስሊም ያልሆኑ የሌላ አናሳ ሃይማኖቶች ዜግነት እንዲጠይቁ የሚያስችል ነው።-ባለስልጣናቱ ለግዞት የተዳረጉ ሰዎችን እንደሚረዳ ተናግረዋል።-ህጉ በአውሮፓውያኑ 2019 ሲጸድቅም በርካታ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈበት እና የታሰሩበት ህዝባዊ ተቃውሞም አስነስቶ ነ...
የፎቶው ባለመብት JOHN BARNETT-ቦይንግ የተሰኘው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ የቀድሞ ሠራተኛ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል።-የቀድሞው ሠራተኛው የድርጅቱን ምስጢር በማጋለጥ ይታወቅ ነበር።-ጆን ባርኔት ለቦይንግ ፋብሪካ ለ32 ዓመታት የሠራ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2017 ነበር ጡረታ የወጣው።-ከመሞቱ በፊት ባሉት ቀናት ቦይንግ በተመሠረተበት ክስ ላይ ምስጢር አሾላኪ ሆኖ ቀርቦ ምስክርነቱን እየሰጠ ነበር።-ቦይንግ በቀድሞው ሠራተኛው ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጧል።-የቻርልስተን ክፍለ-ግዛት ባለሥል...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ለሳምንታት የዘለቀውን ከፍተኛ ጫና እና በአገሪቱ እየጨመረ ያለውን ከባድ ነው ተከትሎ የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪየል ሄንሪ ከስልጣን ለመልቀቅ መስማማታቸውን የካሪቢያን አገራት ቡድን ሊቀ መንበር አስታወቁ።-የቀጣናው መሪዎች በሄይቲ የፖለቲካ ሽግግር ላይ ለመምከር ሰኞ ዕለት በጃማይካ መገናኘታቸውንም ተከትሎ ነው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ለመልቀቅ መስማማታቸው የተነገረው።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሁኑ ወቅት በታጠቁ ቡድኖች ወደ አገራቸው እንዳይመለሱ በመከልከላቸው በፖ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ ዩክሬን “ነጭ ባንዲራ የማንሳት ድፍረት ሊኖራት ይገባል” ማለታቸውን ተከትሎ ኪዬቭ የቫቲካን ተወካይዋን ጠርታለች።-የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ሊቀ-ጳጳሱ በሰጡት አስተያየት ኪዬቭ “መከፋቷን” ለተወካዩ ኑንሲዮ ቮሎድሚር ኩልቦካስ ነግረናቸዋል ብሏል።-በተያያዘ ዜና ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ዩክሬን ከሰሞኑ ከገጠማት ሽንፈት “አገግማ አሁን መረጋጋት ላይ ትገኛለች” ብለዋል።-ነገር ግን የዩክሬን አጋሮች ለሀገሪቱ የሚያደርጉት ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላት አከባባርን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ አዋጅ ኃይማኖታዊ እና ብሔራዊ የህዝብ በዓላት ላይ የሚታዩ ሰንደቅ ዓላማዎችን ዓይነት በግልጽ እንዲያስቀምጥ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ተጠየቀ።-ጥያቄው የተነሳው የህዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባባር ለመወሰን ወጣው ረቂቅ አዋጅ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 3፤ 2016 ዓ.ም. ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበበት ወቅት ነው።-ረቂቁ በምክር ቤቱ የቀረበው ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-አወዛጋቢው ተጽእኖ ፈጣሪ አንድሩ ቴት እና ታናሽ ወንድሙ ትሪስታን ቴት በዩናይትድ ኪንግደም የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው በኋላ ሩሜኒያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ።-ሁለቱ ወንድማማቾች በዩኬ የእስር ማዘዣ የወጣባቸው ብሪታኒያ ውስጥ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ፈጽመዋል የሚል ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ነው።-የ37 ዓመቱ አንድሩ ቴት እና የ35 ዓመቱ ወንድሙ የቀረቡባቸውን ክሶች “ሙሉ በሙሉ ውድቅ” እንደሚያደርጉ ተወካያቸው ገልጸዋል።-ሁለቱ ግለሰቦች በሩሜኒያ ፖሊስ ከተያዙ በኋላ ማክ...
የፎቶው ባለመብት X-የሱዳን ጦር በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ለወራት በቁጥጥር ስር ሆኖ የቆየውን የብሔራዊ ቴሌቪዥን ማሰራጫ ዋና መስሪያ ቤትን መልሶ ተቆጣጠረ።-ጦሩ በኦምዱርማን ከተማ የሚገኘውን ጣቢያ መልሶ መያዙ ለ11 ወራት በዘለቀው የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ትልቅ ድል ተደርጎ ተመዝግቦለታል።-በጀነራል ሐምዳን ዳጋሎ (ሔሜቲ) የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የብሔራዊ ቴሌቪዥን ማሰራጫ ዋና መስሪያቤቱን የእርስ በእርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ ነበር የተቆጣጠረው።-ማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተዘዋወሩ ያሉ ተንቀሳቃ...
“በረመዳን ወቅት እኛ እየፆምን ነው፤ እነሱ [በጋዛ ያሉ ፍልስጤማውያን] ግን እየተራቡ፣ እየሞቱ ነው” ነው ይላል ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የሚገኘው ካሊድ።-በአየርላንድ፣ ቤልፋስት የተወለደው እና ባለቤቱ እና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት በጋዛ የተገደሉበት ፍልስጤማዊ በሙስሊሞች ዘንድ ቅዱስ ተብሎ የሚጠራውን የረመዳንን ወር እንደ ከዚህ ቀደሙ ማክበር እንደሚቸገር ይገልጻል።-ካሊድ ኤል ኤስታል በኅዳር ወር ጋዛን ለቀው ከሸሹት ሁለት ልጆቹ ጋር መገናኘት ችሏል።-ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት በጋዛ ሰርጥ ለቀሩት አባ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ምርጫ ለመፎካከር የሚያስችላቸውን ድምፅ አገኙ።-የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ከ8 ወራት በኋላ ኅዳር 2017 ዓ.ም. ይካሄዳል።-አራት ግዛቶች፣ አንድ የአሜሪካ ክፍል እና በመላው ዓለም የሚኖሩ ዴሞክራቶች ማክሰኞ ዕለት ዕጯቸውን መርጠዋል።-ይህ ማለት በአውሮፓውያኑ 2020 የተመለከትነው የባይደን እና ትራምፕ ፍጥጫ በ8 ወራት ውስጥ ይደገማል።-ሁለቱ ቁንጮ ፓርቲዎች በቅርቡ በየፊናቸው በ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ትናንት ማክሰኞ ምሽት በተከናወኑ የቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፈ ጨዋታዎች አርሰናል እና ባርሴሎና ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ።-ከሦስት ሳምንት በፊት በነበረው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ፖርቶ በሜዳው ባለቀ ሰዓት ጎል አስቆጥሮ አርሰናልን 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል።-ትናንት በተደረገው የመልስ ጨዋታ መድፈኞቹ በደጋፊዎቻቸው ፊት በዘጠና ደቂቃ 1 - 0 ማሸነፍ ችለዋል።-ማርቲን ኦዴጋርድ በድንቅ ሁኔታ ያሻገራትን ኳስ ሊያንድሮ ትሮሳርድ ከመረብ አገናኝቷል...
ትሪስታን ቴት (ግራ) እና አንድሩ ቴት-አወዛጋቢው ተጽዕኖ ፈጣሪ አንድሩ ቴት እና ታናሽ ወንድሙ ትሪስታን ቴት ለዩናይትድ ኪንግደም ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ ሲል የሮሜኒያ ፍርድ ቤት ወሰነ።-ፍርድ ቤት ይህን ያለው ሁለቱ ወንድማማቾች በዩናይትድ ኪንግድም የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ ነው።-ትናንት የዋለው ፍርድ ቤት አንድሩ እና ትሪስታን ቴት በሮሜኒያ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የቀረበባቸውን የክስ ሂደት ካጠናቀቁ በኋላ ለዩኬ ተላልፈው እንደሚሰጡ ነው የወሰነው።-ከፍርድ ቤቱ ው...
የፎቶው ባለመብት Coptic Orthodox Church/Faceboo-ሦስቱ የኦርቶክስ መነኮሳት በስለት ተወግተው ስለመገደላቸው ምልክት ማግኘቱን ፖሊስ አስታውቋል።-ሦስት የግብፅ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነኮሳት በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ ገዳም ውስጥ “ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ” መገደላቸው ተገለጸ።-አባ ታክላ ሙሳ፣ አባ ሚናህ አቫ ማርከስ እና አባ ዮስቶስ አቫ ማርከስ ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም. መገደላቸውን የግብፅ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያ የደቡብ አፍሪካ አገረ ስብከት ባወጣው መግለጫ አስታ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ዩናይትድ ኪንግደም በአገሯ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችን እስከ 3 ሺህ ፓውንድ በመክፈል ወደ ሩዋንዳ ልትልክ መሆኑን አስታወቀች።-ለመጀመሪያ ጊዜ በዘ ታይምስ ይፋ የሆነው ይህ አዲስ የስደተኞች ዕቅድ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ያልተሳካላቸው ስደተኞች በበጎ ፈቃደኝነት ወደ አገራቸው እንዲመለሱና ለዚህም የሚሆን ገንዘብ ይሰጣቸዋል።-የጥገኝነት ጥያቄያቸው በዩናይትድ ኪንግደም ውድቅ ለተደረገባቸው ለማንኛውም ስደተኞች ክፍት ይሆናል ተብሏል።-ይህ ዕቅድ በ...
የፎቶው ባለመብት አቶ ክርስቲያን ታደለ-የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሐሙስ መጋቢት 5፤ 2016 ዓ.ም በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ የሆኑትን የአቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው።-አቶ ክርስቲያን ታደለ ፓርላማ የገቡት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ምርጫ ክልል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)ን ወክለው ተወዳድረው ነው። አቶ ክርስቲያን ፓርላማ ከገቡ በኋላ በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ...
የፎቶው ባለመብት Sani Maikatanga-በናይጄሪያ ሰሜናዊ ግዛት በምትገኘው ካኖ የሚገኘው እስላማዊ ፖሊስ ሰኞ ዕለት በጀመረው የረመዳን ጾም ወቅት ምግብ ሲበሉ የታዩ 11 ሙስሊሞችን በቁጥጥር ስር አዋለ።-ካኖ የተሰኘችው ግዛት አብዛኛው ማህበረሰቧ ሙስሊም ሲሆን የእስላማዊ ህግ ስርዓት (ሻሪያ) ከዓለማዊ ህግ ጋር በአንድ ላይ ይሰራበታል።-ሂስባህ በመባል የሚታወቁት እስላማዊ ፖሊሶች በየዓመቱ በረመዳን ጾም በምግብ ቤቶች እና የገበያ ስፍራዎች ላይ ፍተሻዎችን ያካሂዳሉ።-በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት 10...
የፎቶው ባለመብት YT-ከደቡብ ኢትዮጵያ ለጉልበት ሥራ ወደ ሕዳሴ ግድብ ሲያመሩ በአማራ ክልል ውስጥ በታጣቂዎች የታገቱ ወጣቶች ቤተሰቦች ስለ ልጆቻቸው ጉዳይ መፍትሄ የሚሰጠን አጥተን ጭንቀት ላይ እንደሚገኙ ተናገሩ።-ከጥቂት ሳምንታት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለደን ምንጣሮ ወደ ሕዳሴ ግድብ ሲያመሩ አማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ አካባቢ በፋኖ ታጣቂዎች ስለመታገታቸው መገለጹ ይታወሳል።-እገታውን ፈጽሟል ለተባለው የፋኖ ታጣቂ ቡድን ቅርበት ያላቸው ማኅበራዊ ሚዲያዎች ግን ወ...
የፎቶው ባለመብት John Barnett-የቦይንግን ምስጢር በማጋለጥ የሚታወቀው ጆን ባርኔት-የአሜሪካው ግዙፉ የዘመናዊ አውሮፕላኖች አምራች ኩባንያ ድሪምላይነር አውሮፕላኖች የነበረባቸውን ጉድለቶች በተመለከተ ምሥጢር በማጋለጥ የሚታወቀው ጆን ባርኔት ከሰሞኑ መኪናው ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል።-የቀድሞ የቦይንግ ሠራተኛ የነበረው ጆን በዓለም ላይ ግዙፍ የሆነውን የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ሳይፈራ በመጋፈጡ ይፋ ባደረገው መረጃ “ደፋር፣ ታማኝ እና ለመርሁ ሟች ነው” ሲሉ ጠበቆቹ አሟካሽተውታል።-ባለሥልጣናት ባርኔት...
የፎቶው ባለመብት REUTERS AND YOUTUBE-ጋይ ፊሊፕ፣ ባርቢኪው፣ ኢዞ-ጠመንጃውን እየነቀነቀ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት የሚወደው የቀድሞው የፖሊስ መኮንን፣ በሜሪካ ውስጥ ታስሮ የቀየው ታራሚ እና የራፕ ሙዚቃ ክሊፖች ላይ የሚታየው ወጣቱ ወንበዴ ሄይቲ ውስጥ ለሥልጣን ፉክክር ላይ ናቸው።-እነዚህ በሄይቲ ዋና ከተማ ፖርት-አው-ፕሪንስ ለተነሳው ነውጥ ተጠያቂ ናቸው የሚባሉትን ዋነኞቹ ሁለት የወሮበላ ቡድኖችን የሚመሩ ናቸው።-ለወራት በወሮበሎች ጥቃት ሥር የቆየችው ሄይቲ፣ ባለፉት ሳምንታት ነውጡ ተባብሶ ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የእስራኤል ኃይል በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ራፋህ የሚገኘው የዕርዳታ ማዕከሉ ላይ ጥቃት እንዳደረሰበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።-በዚህም ጥቃት አንድ የማዕከሉ ሰራተኛ መገደሉን እንዲሁም 22 ሰዎች መቁሰላቸውን የተመድ የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ አክሎ አስታውቋል።-በተመድ ተቋማት ላይ የሚደርሰው ጥቃት “ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ህግጋትን ግልጽ በሆነ መንገድ በጣሰ መልኩ” ተደጋጋሚ እየሆነ እንደመጣ የኤጀንሲው ኃላፊ ፊሊፕ ላዛራኒ ገልጸዋል።-በሐማስ አስተዳደር ስር ያለ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ዴንማርክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴቶችን ለብሔራዊ ውትድርና መመልመል መጀመሯን ገለጸች።-አውሮፓዊቷ ሀገር ከዚህ አልፎ ቀድሞ የነበረውን ብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ጊዜን ማራዘሟን አስታውቃለች።-ዴንማርክ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የመከላከያ በጀቷን 6 ቢሊዮን ዶላር በማድረስ የኔቶን ግብ ለመምታት ማቀዷንም ይፋ አድርጋለች።-“ይህን የምናደርገው ጦርነት ፈልገን አይደለም። ይህን የምናደርገው ጦርነትን ማስወገድ ስለምንፈልግ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴር ፍሬድሪክሰን።-...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ቲክቶክን በመላ ሀገሪቱ ለማገድ የሚያስችል ረቂቅ ይፋ አደረጉ።-ይህ ማለት የቻይናው ግዙፉ ኩባንያ ባይትዳንስ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ያለውን የአክሲዮን ድርሻ መሸጥ አለበት፤ አሊያም መተግበሪያው አሜሪካ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል ይደረጋል።-ምንም እንኳ ረቂቅ አዋጁ በአብላጫ ድምፅ በእንደራሴዎቹ ድጋፍ ቢያገኝም ሕግ ለመሆን ሴኔቱ ይሁንታ ሰጥቶ ፕሬዝደንቱ ሊፈርሙበት ይገባል።-ሕግ አውጭዎቹ ቻይና ቲክቶክን ተጠቅማ ጫና...
የፎቶው ባለመብት EPA-EFE/REX/Shutterstock-ፓርቲያቸው ባለፈው ዓመት ኔዘርላንድስ በተደረገው ምርጫ በከፍተኛ ድምጽ ያሸነፈው ጸረ እስላም ፖለቲከኛ ጌርት ዋይልደርስ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት እጩነት ራሳቸውን አገለሉ።-“ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የምችለው በጥምረቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም ፓርቲዎች የሚደግፉት ከሆነ ብቻ ነው። ይህ ሊሆን አይችልም” ሲሉም ፖለቲከኛው በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።-ፍሪደም (ፒቪቪ) የተሰኘው ፓርቲያቸው ባለፈው ዓመት በአገሪቱ በተደረገው ምርጫ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፍ ችሏል።-...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር-ደቡብ አፍሪካ በጋዛ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ውስጥ ከእስራኤል ጦር ሠራዊት ጉን ተሰልፈው የሚዋጉ ዜጎቿ እስር እንደሚጠብቃቸው አስጠነቀቀች።-የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ከእስራኤል የመከላከያ ኃይሎች ጋር በመሆን እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተሳተፉ የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ወደ አገራቸው በሚመለሱ ጊዜ በቁጥጥር ስር ይውላሉ ማለታቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ (ኤፒ) ዘግቧል።-“የደቡብ አፍሪካ ዜጋ ሆነው በጦርነ...
አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ)፡ ፎቶ ከፋይል-የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።-ከስድስት ዓመት በፊት ነሐሴ 21/2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለው አስካሁን በእስር ላይ የቆዩት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ከእስር የተለቀቁት ዐቃቤ ሕግ ክሱን በማንሳቱ መሆኑን ጠበቃቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።-ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው እስክንድር ገዛኸኝ እንደተናገሩት የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተ...
የፎቶው ባለመብት SM-የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው መዝገብ ቀርበው የነበሩ ክሶች ለሕዝብ ጥቅም ሲባል እንዲቋረጡ መወሰኑን አስታወቀ።-በተመሳሳይ በቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) መዝገብ የነበሩ ክሶች ለሕዝብ ጥቅም ሲባል እንዲቋረጡ መደረጋቸው ይፋ ተደርጎ ነበር።-በቀድሞ ርዕሰ መስተዳደር ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ መቋረጡ ከተገለጸ በኋላ ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።-በአቶ አብዲ ሞሃመድ ኡመር የክስ መዝገ...
አፍሪካ ውስጥ አሉ ከሚባሉ የብስክሌት ውድድሮች ቁንጮ ነው የሚባለው ቱር ደ ሩዋንዳ በቅርቡ ተጠናቋል።-በዚህ ውድድር በዓለማችን አሉ የሚባሉ እንደ እስራኤል ፕሪሚዬር እና ዩኤኢ ያሉ ክለቦችን ጨምሮ በርካታ ብሔራዊ ቡድኖች ተሳትፈዋል።-በውድድሩ ከተሳተፉ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል አንዱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የብስክሌት ቡድን ነው።-ከየካቲት 10 አስከ 17 በዋና መዲናዋ ኪጋሊ እና በተወሰኑ የአገሪቱ ክፍሎች የተካሄደው ውድድ 740 ኪሎ ሜትሮችን ሸፍኗል።-አብዛኞቹ በውድድሩ የተሳተፉ ክለቦች እና ብሔራዊ ቡድኖች...
የሐማስን ጥቃት ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ሠራዊታቸው ጋዛ ውስጥ የሚያካሂደው ዘመቻ ዓላማ “የሐማስን አስተዳደራዊ እና ወታደራዊ አቅም በማንኮታኮት” መደምሰስ ነው በማለት በተደጋጋሚ ተናግረዋል።-መስከረም ወር መጨረሻ ላይ የተጀመረው የጋዛ ጦርነት አምስት ወራት ሞላው። ከ30 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን፣ እስራኤል ደግሞ “ሙሉ ድል ለመቀዳጀት” ወሳን እርምጃ ላይ መሆኗን አሳውቃለች።-ነገር ግን ሐማስ እንዲሁ በቀላሉ የ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ከሰሜን እስከ ደቡብ በሚገኙ በርካታ የአፍሪካ አገራት የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ተገለጸ።-አገልግሎቱ ከተቋረጠባቸው አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ላይቤሪያ፣ ጋና እና ቡርኪና ፋሶ ይገኙበታል።-በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ መረጃ የሚሰጠው ክላውድፍሌር ራዳር የተሰኘ ተቋም ከሰሜን እስከ ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አገራት በተመሳሳይ ሰዓት የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟቸዋል ብሏል።-የሳይበር ደኅንነት እና የኢንተርኔት ግንኙነትን የሚከታ...
የፎቶው ባለመብት SOS Méditerranée-በፕላስቲክ በተሰራ አነስተኛ ጀልባ ተጭነው በሜዲትሪኒያን ባሕር ላይ ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች መካከል ቢያንስ 60 ያህሉ መሞታቸውን በሕይወት የተረፉ ተሳፋሪዎች ተናገሩ።-በጀልባው ላይ ከነበሩት ስደተኞች ውስጥ 25ቱ ሊተርፉ የቻሉት ኤስ.ኦ.ኤስ ሜዲትራኒያን የተባለው የሰብዓዊ ቡድን የሚያንቀሳቅሳት “ኦሽን ቫይኪንግ” ወደ ተሰኘች መርከብ በመዘዋወራቸው ነው።-ስደተኞቹ ዛዊያ ከተባለው የሊቢያ የባሕር ዳርቻ ከተነሱ ቀናት መቆጠራቸውን ለሰብዓዊ ቡድኑ ተናግረዋል።-ጀል...
የፎቶው ባለመብት Belay Manaye FB-አምነስቲ ኢንተርናሽናል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሚጻፍ ደብዳቤ ከአራት ወራት በፊት የታሰረው ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ከእስር እንዲፈታ የሚጠይቅ ዘመቻ ጀመረ።-“የኢትዮ ኒውስ” የዩትዩብ መገናኛ ብዙኃን መሥራች የሆነው በላይ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋለው ከአራት ወራት በፊት ኅዳር 3/2016 ዓ.ም. ነበር።-በላይ ማናዬ በቁጥጥር ሥራ ከዋለ ወራት ቢቆጠሩም ፍርድ ቤት አልቀረበም እንዲሁም ስለታሰረበት ምክንያት ያልተገለጸ ሲሆን ምርመራ አልተደረገበትም...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ቅዳሜ እና እሁድ የፕሪሚየር ሊግ እና ተጠባቂ የኤፍኤ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በኤፍኤ ዋንጫ ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል እንዲሁም ሲቲ ከ ኒውካስል ግጥሚያ ያደርጋሉ።-የቢቢሲ የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የጨዋታዎቹን ግምት እንደሚከለው አስቀምጧል።-ይህን ጨዋታ ቮልቭስ ያሸንፋል ብዬ እገምታለሁ። በሜዳቸው እንደመጫወታቸው በተሻለ የኳስ ቁጥጥር የበለይነት እንደሚይዙ ግምቴ ነው።-ግምት፡ ዎልቭስ 2 - 1 ኮንተሪ-ከዚህ ቀደም በሰጠኋቸው ግምቶች በርንሊ በሜዳ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ሆቴሉ ከአራት ዓመት በፊትም በአልሻባብ ጥቃት ተፈጽሞበት ነበር (ፎቶ፡ ፋይል)-የአል ሻባብ ታጣቂዎች በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ቤተ መንግሥት አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የደኅንነት ምንጮች እና የዐይን እማኞች ተናገሩ።-አልሻባብ በሆቴሉ ላይ በፈጸመው ጥቃት ከባድ ፍንዳታ እና የተኩስ ልውውጥ የተሰማ ሲሆን፣ በመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዳልቀረ ተዘግቧል።-እስላማዊው ታጣቂ ቡድን ሳይል በተባለው እና በሶማሊ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-አራት ተማሪዎችን በሚቺጋን ትምህርት ቤት ተኩሶ የገደለው አሜሪካዊ ታዳጊ አባት በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ።-አባትየው ጄምስ ክሩምብሌይ ለ15 ዓመት ታዳጊ ልጁ ተኩሶ የገደለበትን ሽጉጥ በመግዛት እንዲሁም የአዕምሮ ጤናውንም ችላ በማለት ነው የተከሰሰው።-ታዳጊው በአውሮፓውያኑ 2021 ጥቃቱን አድርሶ ተማሪዎቹን የገደለው።-ዳኞች ብያኔ ላይ ከመድረሳቸው በፊት ለአንድ ቀን ያህል ተወያይተዋል።-የታዳጊው እናት ጄኔፈር ክሩምብሌይ በተመሳሳይ ክስ ጥፋተኛ ሆና የተገኘች ሲሆ...
የፎቶው ባለመብት Ethiopian Sugar Industry group-ለሁለት ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ አምስት የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን የፋብሪካውን አንድ ኃላፊ ለቢቢሲ ገለጹ።-ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁት የስኳር ፋብሪካው ኃላፊ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል።-አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው።-ከተገደሉት መካከለ ሦስቱ ሠራተኞች ከወንጂ አካባቢ ሲሆኑ፣ የቀብር ሥነ ሥር...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በአርባዎቹ አጋማሽ ላይ የምትገኘው ሔለን ተስፋይ* ትዳር ከመሠረተች ሁለት ዓመት ገደማ ሆኗታል። ነገር ግን እሷ እና ባለቤቷ ልጅ የመውለድ ፍላጎት ቢኖራቸውም ሳይሳካላቸው ቆይቷል።-“ቤተሰብ ጋር ስንሄድ ‘ለምንድነው የማትወልጂው?’ ይላሉ። ይህ ደግሞ ያስጨንቃል፣ ያሳስባል። ልጅ ስለሌለኝ አሁን ላይ በጣም ይሰማኛል። እህቶቼ በሙሉ ወልደዋል። ባለመውለዴ በጣም ነው የሚሰማኝ” ስትል ትዳር ከመሠረተች በኋላ ልጅ አለመውለዷ የፈጠረባትን ተጽዕኖ የመቀለዋ ነዋሪ ትናገራለች።...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ሁለት ዓመት ባለፈው የዩክሬን እና የሩሲያ ጦርነት በርካታ ሕንዳውያን በሥራ ወኪሎች ተታልለው ለሩሲያ እየተዋጉ መሆኑን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች እየወጡ ነው።-በዩክሬን ለሩሲያ እየተዋጉ ካሉት ሕንዳውያን መካከል አንዱ በሚሳኤል ጥቃት መገደሉም ተነግሯል።-በሕንዷ ጉጅራት ግዛት የተወለደው ሄማል አሽዊንባሃይ ከሁለት ሳምንት በፊት በሚሳኤል ጥቃት መገደሉን የሂንዱ ጋዜጣ አስነብቧል።-የሄማል አባትን ቢቢሲ ከሁለት ሳምንት በፊት ባናገረበትም ወቅት ልጃቸውን ከሦስት ቀናት በፊት...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ሰላሳ የሚደርሱ ሰዎች ከሞቱበት አደጋ በኋላም ስደተኞች ከፈረንሳይ ወደ ዩኬ ማቋረጣቸውን ቀጥለዋል-ከፈረንሳይ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም በባሕር በኩል ሲያቋርጥ የሞተ አንድ የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ በፈረንሳይ መንግሥት ላይ ክስ መሠረተ።-ከሁለት ዓመት በፊት ባሕር ላይ ጀልባቸው ተገልብጣ ከሰመጡ 27 ስደተኞች መካከል አንዱ ለሆነው ለኢትዮጵያዊው ፍቅሩ ሽፈራው ሞት በፈረንሳይ መንግሥት ላይ የቀረበው ክስ ከአደጋው ጋር በተያያዘ የቀረበ የመጀመሪያው አቤቱታ ነው ተብሏል።-በዩና...
ቶም ፔሪዬሎ በሱዳን የአሜሪካ መልዕክተኛ-በሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የጽንፈኛ እስላማዊ እንቅስቃሴ ወደ አካባቢው የሚመለስበትን ሁኔታን ሊያባብስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አዲሱ በሱዳን የአሜሪካ መልዕክተኛ ቶም ፔሪዬሎ ለቢቢሲ ተናገሩ።-መልዕክተኛው ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት በመጓዝ በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት የሚያበቃበትን እና አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ የሚቀርብበትን መንገድ ለመፈለግ በጉብኝት ላይ ናቸው።-ከተጀመረ አንድ ዓመት ሊሞላው ...
የፎቶው ባለመብት Office of prime cabinet secretary/Facebook-የኬንያ መንግሥት የገቢዎች ባለሥልጣን አዳዲስ ሠራተኞችን ለመቅጠር የእርግዝና እና የኤችአይቪ/ኤድስ ምርመራ አድርጎ አመልካቾችን ውድቅ ማድረጉ ጥያቄ አስነሳበት።-የኬንያ የፓርላማ አባላት እነዚህ ምርመራ አድርገው አይቀጠሩም የተባሉት አመልካቾችን ጉዳይ በተመለከተ ምርመራ እንዲከፈትም አዘዋል።-ተቋሙ በበኩሉ ባለፈው ዓመት ምርመራውን ካደረገ በኋላ 133 አመልካቾችን ከውድድሩ መሰረዙን አስታውቋል።-እነዚህ በግብር ሰብሳቢ ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የላታም 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን-ላታም የተባለው አየር መንገድ ንብረት በሆነ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን ላይ ያለ ቁልፍ በድንገት በመነካቱ በመንገደኞች ላይ ቀላል ጉዳት ካጋጠመ በኋላ ምርመራ ተጀመረ።-በዚህ ክስተት ምክንያትም የምርመራው ውጤት አስኪታወቅ ድረስ አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ የ787 ድሪምላይነር አውሮፕላን አብራሪዎች በአውሮፕላኑ ውስጥ ያለውን የመቀመጫቸውን ሁኔታ እንዲፈትሹ አሳስቧል።-ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው የአውሮፕላኑ የበ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-ለሶስት ቀናት በሚደረገው የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ኮሮጆዎችን ያበላሹ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩስያ ባለስልጣናት ተናገሩ።-ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በምርጫው የመጀመሪያ ቀን ዓርብ መሆኑም ተገልጿል።-የድምጽ መስጫ ኮሮጆዎች ውስጥ አረንጓዴ ቀለም ማፍሰስ፣ ኮሮጆዎቹን በእሳት መለኮስ እንዲሁም በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ ርችቶች መተኮስ ያጋጠሙ ክስተቶች መሆናቸውን የመንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል።-የዘንድሮው የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም የቭላድ...
የፎቶው ባለመብት Joseph Okpako/WireImage-በዓለም ላይ ስማቸው ከገነነ ሙዚቀኞች መካከል አንዷ ናት - አያ ናካሙራ።-አያ በፈረንሳይኛ በመዝፈን ከቋንቋው ተናጋሪዎች ባሻገር በዓለማችን ተደማጭ ከሆኑ ጥቂት ሙዚቀኞች መካከል አንዷ ናት።-ጃጃ (Djada) የሚለው ሙዚቃዋ በዩቲዩብ 954 ሚሊዮን ተመልካቾችን አግኝቷል።-ከዚህም ጋር ተያይዞ ነው በሐምሌ ወር በሚከፈተው የፓሪስ ኦሊምፒክስ ላይ የ28 ዓመቷ አያ እንድትዘፍን በአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የተጋበዘችው።-አያ በኦሊምፒክስ መክፈቻ...
የፎቶው ባለመብት Kabana-የካባና ዲዛይን መሥራች ሰምሃል ጉዕሽ-ካባና ዲዛይን ከመደበኛ ሥራ ውጪ በትርፍ ጊዜ ከሚሠራ የጊዜ ማሳለፊያ ‘ሆቢ’ የተወለደ እና ጥቂት ለማይባሉ ሰዎችም ሥራ እና ተስፋን ያስገኘ የሥራ ፈጠራ ሙከራ ነው።-የሰመሃል ጉዕሽ የትርፍ ጊዜ ሥራ የነበረው ካባና ዲዛይን አሁን ከ100 በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን፣ ተፈላጊ የቆዳ ውጤቶችን በማምረት ለውጭ ገበያ ከማቅረቡ በተጨማሪ፣ ጥቂት ለማይባሉ ሴት ባለሙያዎች ዕድልን የፈጠረ ነው።-አዲስ አበባ ያደገችው ሰምሃል ካባና ሌዘርን ከሰባት ...
የፎቶው ባለመብት CBS-በአሜሪካዋ ኦሬገን ግዛት አንድ የዩናይትድ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ አውሮፕላን የአውሮፕላን አካል ጠፍቶ ሳለ ያለምንም ጉዳት ማረፉ ተሰምቷል።-የበረራ ቁጥሩ 433 የሆነው አውሮፕላን ከሳን ፍራንሲስኮ ተነስቶ ሮግ ቫሊ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሥፍራው ሰዓት አቆጣጠር 5፡30 አርፏል።-25 ዓመት የሞላው ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን 139 መንገደኞች እና 6 የበረራ ሠራተኞችን ጭኖ ነበር።-የአውሮፕላኑ አካል እንደጠፋ ሳይታወቅ አውሮፕላኑ ቢያርፍም ምንም ዓይነት ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወንበዴ ቡድኖች እየታመሰች ካለችው ሄይቲ ዜጎችን በልዩ በረራ እንደሚያስወጣ አስታወቀ።-የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ መውጫ አጥተው በሄይቲ ለሚገኙ አሜሪካውያን ከመዲናዋ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቃ ከምትገኘው ካፕ-ሄይሺየን ከተማ በረራ እንደሚደረግ ለዜጎቹ መልዕክት አስተላልፏል።-ሚኒስቴሩ በመልዕክቱ በረራው የሚደረገው በካፕ-ሄይሺየን ያለው የጸጥታ ሁኔታ የተረጋጋ ከሆነ ብቻ መሆኑን እና አውሮፕላኑን መሳፈር የሚችሉት የአሜሪካ ዜጎ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ወደ ስምንት የሀገሪቱ ክፍሎች የተቃጡ በርካታ የድሮን ጥቃቶችን ማክሸፉን አስታወቀ።-ከተሰነዘሩት ጥቃቶች ትልቁ የሚባለው በሩሲያዋ ክራስኖዳር የተከሰተው ሲሆን በሥፍራው የነበረ የነዳጅ ማጣሪያ ጉዳት ደርሶበታል።-ስላቭያንስክ-ኦን-ኩባን በተባለው የነዳጅ ማጣሪያ ላይ በተሰነዘረው ጥቃት የሞተ ሰው እንደሌለ የተዘገበ ሲሆን በጥቃቱ ምክንያት የተነሳው እሣትም በቁጥጥር ሥር ውሏል።-ሩሲያ ጠቅላላ ምርጫ እያካሄደች ሲሆን ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ከጥቁር ዛምቢያዊት እናት እና ከነጭ የዌልስ አባት የተወለዱት ቮውን ገተን የመጀመሪያው ጥቁር የዌልስ መሪ ሊሆኑ ነው።-ቮውን ገተን በዌልስ ሠራተኞች ፓርቲ የአመራር ምርጫ 51.7 በመቶ ድምጽ በማግኘት ተቀናቃኛቸውን በጠባብ ድምጽ አሸንፈዋል።-የገተን ተፎካካሪ የነበሩት ጄሬሚ ማይልስ 48.3 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል።-ቮውን ገተን በአሁኑ ወቅት የዌልስ ተቀዳሚ ሚኒስትር የሆኑትን ማርክ ደሬክፎርድን በመተካት የፊታችን ማክሰኞ ስልጣን ይረከባሉ።-ገተን የፓርቲያቸውን የአመ...
የፎቶው ባለመብት @hawelti-ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ፕሬዝዳንት ሐሰንን አሥመራ ውስጥ ሲቀበሉ-የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በሁለት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ለሥራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አሥመራ መግባታቸው ተገለጸ።-የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በኤክስ ገጻቸው ላይ እንደገለጹት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ዛሬ እሁድ መጋቢት 8/2016 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ አሥመራ ገብተዋል።-የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ጉብኝት በኤርትራው ፕሬዝዳን...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የዩናይትድ ስቴትስ ፖለቲከኞች አዲስ ረቂቅ ሕግ አውጥተው ቲክቶክ መታገድ አለበት አሊያ ደግሞ ባለቤቱ የቻይናው ኩባንያ ሊሸጠው ይገባል የሚል ክርክር ገጥመዋል።-የቪዲዮ ማጋሪያ የሆነው መተግበሪያ በመላው ዓለም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አሉት።-ነገር ግን የደንበኞቹ የመረጃ ደኅንነትን እየጠበቀ አይደለም፤ ከቻይና መንግሥት ጋር ግንኙነት አለው የሚሉ ክሶች ይቀርቡበታል።-ከሁለቱም የአሜሪካ አውራ ፓርቲ የተውጣጡ ፖለቲከኞች አዲስ ያረቀቁት ሕግ የቲክቶክ ባለቤት የሆ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን-ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሩሲያ ጠቅላላ ምርጫ አገሪቱን ለአምስተኛ ዙር መምራት የሚያስችላቸውን ድምጽ ማግኘታቸውን ይፋ አደረጉ።-ከአጠቃላይ ከተሰጠው ድምጽ 87 በመቶ የሚሆኑት መራጮች ለፑቲን ድምጽ መስጠታቸውን ምርጫ አስፈጻሚው ማሳወቁን ተከትሎ ፑቲን ምርጫው ከበርካታ ምዕራባውያን አገራት ዴሞክራሲ በላይ ግልጽነት የታየበት ምርጫ ነበር ብለዋል።-ፕሬዝዳንቱ ይህን ይበሉ እንጂ በዚህ ምርጫ ተዓማኒ የሆነ ትክክለኛ ተፎካካሪ የምርጫው ተሳታፊ...
የፎቶው ባለመብት Amhara Health Bureau-መድኃኒት እና ክትባቶችን ማግኘት አዳጋች መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ-ካለፈው ዓመት አጋማሽ ወዲህ በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት ተባብሶ ወደ ለየለት የትጥቅ ግጭት ካመራ ወራት ተቆጥረዋል። በበርካታ የክልሉ አካባቢዎች የሚካሄደው ግጭት በሕዝቡ የዕለት ከዕለት ሕይወት ላይ ከባድ ጫናን እያሳረፈ ነው።-በዚህም ሳቢያ የሕዝቡ መደበኛ እንቅስቃሴዎች የተስተጓጎሉ ሲሆን፣ የመንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች፣ የትራንስፖርት፣ የንግድ፣ የትምህርት እና የጤና አገልግሎ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የእስራኤል ኃይሎች በጋዛ በሚገኘው አል ሺፋ ሆስፒታል ላይ በሌሊት በከፈቱት ጥቃት በሆስፒታሉ ውስጥ በታንክ የታገዘ ከባድ ተኩስ እንደነበር ተዘገበ።-የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ፣ መከለካያ ኃይሉ በሆስፒታሉ የተወሰኑ አካባቢዎች “ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት” ዘመቻ እያካሄደ እንደሆነ ተናግረዋል።-መከላከያ ኃይሉ፣ ከፍተኛ የሐማስ አሸባሪዎች በሆስፒታሉ ውስጥ ራሳቸውን እንደገና አደራጅተው ጥቃት ለመክፈት ሆስፒታሉን እየተጠቀሙበት ነው ብሏል።-የዐይን እማኞች በ...
የፎቶው ባለመብት EPA-ትላንት ዕሁድ በቱርክ ሱፐር ሊግ ትራብዞንስፖር እና ፌኔነርባቼ ካደረጉት ጨዋታ በኋላ የፌነርባቼ ተጨዋቾች ወደ ሜዳ በገቡ የትራብዞንስፖር ተጨዋቾች ጥቃት ደርሶባቸዋል።-በፓፓራ ፓርክ የተደረገውን ጨዋታ ፌንርባቼ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ረትቷል። ይህንን ድል ተከትሎ ደስታቸውን እየገለጹ በነበረበት ወቅት ከተቃራኒ ብድን ደጋፊዎች ጥቃት ተሰንዝሮባቸዋል።-የፌንርባቼ ተጨዋች የሆኑት ዕውቆቹ ናይጀሪያዊ ኦሴይ ሳሙኤል እና ሚኪ እንዲሁም የቤልጄየም ዜግነት ያለው ባትዉዋይ ከተቃራኒ ቡድን ደጋ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያጋጠመውን “የሲስተም ችግር” ተከትሎ በባንክ ሂሳባቸው በቂ ገንዘብ ሳይኖራቸው በርከት ያለ የገንዘብ ዝውውር ፈጽመዋል የተባሉት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሆናቸው ተሰምቷል።-በጅማ ዩኒቨርሲቲ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ 5ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ወጣት አርብ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. ለሊት ላይ በርካታ ተማሪዎች በሂሳባቸው በቂ ገንዘብ ሳይኖራቸው ከገንዘብ መክፈያ ማሽኖች (ኤቲኤም) ጥሬ ገንዝበ ወጪ ማድረጋቸውን ...