text
stringlengths
4
267
በጥቅሉ ሲታይ ትሑት ሰው፣ ልኩን የሚያውቅ ማለትም ስለ ችሎታውና ስላከናወነው ነገር ሚዛናዊ አመለካከት ያለው ሰው ነው፤ እንዲህ ዓይነቱ ግለሰብ ስህተቱን አምኖ መቀበልም ሆነ የሌሎችን ሐሳብ ማስተናገድ አይከብደውም።
ትሕትና ይሖዋን በጣም ያስደስተዋል።
ልክን ማወቅ የሚለውም አገላለጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሠራበት ስለ ራስ ሚዛናዊ አመለካከት መያዝን እንዲሁም አቅምን ማወቅን ለማመልከት ነው።
አንድ ሰው አቅሙን ማወቁ በሚያሳየው ባሕርይ ላይ ለውጥ ያመጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ በተጻፈበት ቋንቋ ይህ አገላለጽ በዋነኝነት የሚያመለክተው ይህን ሳይሆን አይቀርም።
አንድ ሰው ሳይታወቀው፣ በአስተሳሰቡም ሆነ በድርጊቱ ልኩን የማወቅ ችግር እንዳለበት የሚጠቁሙ ነገሮችን ማድረግ ሊጀምር ይችላል፤ ይህ የሚሆነው እንዴት ነው?
ይህን የሚጠቁሙ አንዳንድ ምልክቶችን እስቲ እንመልከት።
ለራሳችንም ሆነ ላገኘናቸው መብቶች ከልክ ያለፈ ቦታ እንሰጥ ይሆናል።
ምናልባትም ወደ ራሳችን ተገቢ ያልሆነ ትኩረት መሳብ ጀምረን ሊሆን ይችላል።
አሊያም ደግሞ ያለንን ቦታ፣ ኃላፊነት ካላቸው ሰዎች ጋር ያለንን ቅርርብ ወይም የግል አመለካከታችንን መሠረት በማድረግ ሌሎች የእኛን አቋም እንዲቀበሉ ለመጫን እንፈተን ይሆናል፤ እንዲህ ስናደርግ ልካችንን ማወቅ ተስኖን እብሪተኛ ወደ መሆን እየሄድን እንደሆነ እንኳ ላይታወቀን ይችላል።
የጤና ችግርን ጨምሮ ከቁጥጥራችን ውጭ የሆኑ ሌሎች ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ይሖዋ እንደሚያስብልን በመተማመን የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ በእሱ ላይ መጣል ይኖርብናል።
በተጨማሪም ከክርስቲያናዊ ስብሰባዎችና ከሌሎች መንፈሳዊ ዝግጅቶች ጥቅም ለማግኘት አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ እናድርግ።
ከእውነት ቤት የወጡ ልጆች ስላሏቸው ታማኝ ወላጆችስ ምን ማለት ይቻላል?
አረጋዊው ሳሙኤል ትላልቅ የሆኑ ልጆቹ እሱ ያስተማራቸውን የጽድቅ መሥፈርቶች እንዲጠብቁ ማስገደድ አይችልም ነበር።
ሳሙኤል ጉዳዩን ለይሖዋ ከመተው በቀር ምንም አማራጭ አልነበረውም።
ሆኖም ንጹሕ አቋሙን ይዞ በመቀጠል የሰማይ አባቱን ማስደሰት ይችላል።
በዛሬው ጊዜም እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ክርስቲያን ወላጆች አሉ።
ይሖዋ ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞች ወደ እሱ የሚመለሱበትን ጊዜ በጉጉት እንደሚጠባበቅ ይተማመናሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ የእነሱ ታማኝነት ልጃቸው ወደ ይሖዋ እንዲመለስ እንደሚረዳው በመተማመን ምንጊዜም ለይሖዋ ታማኝ ለመሆን ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።
ለምትቀርበው ሰው ስሜትህን አውጥተህ መናገርህ ጭንቀትህን ለማቅለል ይረዳሃል።
ለትዳር ጓደኛህ፣ ለቅርብ ወዳጅህ አሊያም ለጉባኤህ ሽማግሌ ስሜትህን መናገርህ ስላለህበት ሁኔታ ሚዛናዊ አመለካከት እንዲኖርህ ሊረዳህ ይችላል።
ስሜትህን በግልጽና በሐቀኝነት መናገርህ ያለህበትን ሁኔታ ለመረዳትና መፍትሔ ለመፈለግ በእጅጉ ይረዳሃል።
መጽሐፍ ቅዱስ መመካከር ከሌለ የታቀደው ነገር ሳይሳካ ይቀራል፤ በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል ይላል።
ይሖዋ፣ በየሳምንቱ በሚደረጉት ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች አማካኝነትም አገልጋዮቹ ጭንቀትን መቋቋም እንዲችሉ ይረዳቸዋል።
በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ፣ ስለ አንተ ከሚያስቡና ሊያበረታቱህ ከሚፈልጉ የእምነት ባልንጀሮችህ ጋር መገናኘት ትችላለህ።
በዚህ መንገድ እርስ በርስ መበረታታታችሁ በመንፈሳዊ የሚያጠነክርህ ከመሆኑም በላይ ያለብህን ማንኛውንም ጭንቀት መቋቋም ቀላል እንዲሆንልህ ያደርጋል።
ጳውሎስ እንደ ሥጋ ፈቃድ መኖር የሚያስከትለውን አደጋ ለቅቡዓን ክርስቲያኖች መጥቀስ ያስፈለገው ለምንድን ነው?
አምላክ እንደ ወዳጆቹ አድርጎ የተቀበላቸውና እንደ ጻድቃን የሚቆጥራቸው በዛሬው ጊዜ የሚኖሩ ክርስቲያኖችስ ተመሳሳይ አደጋ ሊያጋጥማቸው ይችላል?
የሚያሳዝን ቢሆንም የትኛውም ክርስቲያን በኃጢአተኛ ሥጋው ምኞት መመራት ሊጀምር ይችላል።
ለምሳሌ፣ ጳውሎስ በሮም ከነበሩት ወንድሞች መካከል አንዳንዶቹ ለራሳቸው ፍላጎት ባሪያዎች እንደነበሩ ጽፏል፤ ይህም የፆታ ፍላጎትን አሊያም የምግብ፣ የመጠጥ ወይም ሌላ ዓይነት ፍላጎትን ሊጨምር ይችላል።
አንዳንዶቹ የየዋሆችን ልብ እያታለሉ ነበር።
በቆሮንቶስ ጉባኤ፣ ለተወሰነ ጊዜ ያህል ከአባቱ ሚስት ጋር የሚኖር ወንድም እንደነበረም እናስታውስ።
እንግዲያው አምላክ፣ ክርስቲያኖች በሥጋዊ ነገሮች ላይ ማተኮር እንደሌለባቸው በጳውሎስ በኩል ማሳሰቢያ መስጠቱ የሚያስገርም አይደለም።
ይህ ማስጠንቀቂያ ዛሬም ቢሆን ይሠራል።
ሌሎችም የራሳቸውን ውሳኔ የማድረግ ነፃነት እንዳላቸው አምነን መቀበል አለብን።
ለምን?
እያንዳንዱ ክርስቲያን የመምረጥ ነፃነት ስለተሰጠው፣ ሁለት ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ፍጹም አንድ ዓይነት ውሳኔ ያደርጋሉ ብሎ መጠበቅ አይቻልም።
ይህ ደግሞ በምናሳየው ምግባርና በምናቀርበው አምልኮ ላይም እንኳ ሊንጸባረቅ ይችላል።
እያንዳንዱ ክርስቲያን የራሱን የኃላፊነት ሸክም መሸከም እንዳለበት ከተገነዘብን ሌሎች ሰዎች ያን ያህል ትልቅ ቦታ በማይሰጣቸው ጉዳዮችም ረገድ የመምረጥ ነፃነታቸውን ተጠቅመው የራሳቸውን ውሳኔ የማድረግ መብት እንዳላቸው አምነን እንቀበላለን።
ይሖዋ የመምረጥ ነፃነት ሰጥቶናል፤ ይህም እውነተኛ ነፃነት ያስገኝልናል።
የመምረጥ ነፃነታችን ይሖዋን ምን ያህል እንደምንወደው የሚያሳዩ ውሳኔዎችን ለማድረግ ስለሚያስችለን ለዚህ ስጦታ ከፍተኛ አድናቆት አለን።
ይህን ውድ ስጦታ ለአምላክ ክብር በሚያመጣና ሌሎች ያላቸውን የመምረጥ ነፃነት እንደምናከብር በሚያሳይ መንገድ በመጠቀም ስጦታውን ከፍ አድርገን መመልከታችንን እንቀጥል።
በሥነ ምግባር ልቅ በሆነው በዚህ ዓለም ውስጥ ኃጢአት አስነዋሪ ነገር መሆኑ እየቀረ ነው፤ በመሆኑም ብዙዎች ለኃጢአታቸው ቤዛ እንደሚያስፈልጋቸው አይገነዘቡም።
ብዙዎች ኃጢአት ምን እንደሆነ፣ በእኛ ላይ ምን ተጽዕኖ እንደሚያሳድር እንዲሁም ከኃጢአት ባርነት ነፃ ለመውጣት ምን ማድረግ እንዳለብን አያውቁም።
ልበ ቅን የሆኑ ሰዎች ኃጢአት ምን እንደሆነ ሲገነዘቡ እንዲሁም ይሖዋ በታላቅ ፍቅሩና በጸጋው ተነሳስቶ ልጁን ወደ ምድር በመላክ ከኃጢአትና የኃጢአት ውጤት ከሆነው ከሞት እንደዋጀን ሲያውቁ በጣም ይደሰታሉ።
የክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት፣ አምላክ ለእኛ ያለውን ፍቅር የገለጸበት ከሁሉ የላቀ ስጦታ ከመሆኑም ሌላ የይሖዋ ጸጋ የተትረፈረፈ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።
አቢሳ ወደ ሳኦል የጦር ሰፈር በገባበት ወቅት ታማኝነት ያሳየው ለተገቢው አካል አልነበረም።
አቢሳ ለዳዊት ያለው ታማኝነት ንጉሥ ሳኦልን ለመግደል እንዲነሳሳ አድርጎት ነበር፤ ዳዊት ግን ይሖዋ በቀባው ላይ እጅ ማንሳት ተገቢ እንዳልሆነ ስለተገነዘበ ይህን እንዳያደርግ አቢሳን ከልክሎታል።
ከዚህ ዘገባ የምናገኘው አንድ ጠቃሚ ትምህርት አለ፦ ለተለያዩ አካላት ታማኝ መሆናችን ተገቢ ቢሆንም በዋነኝነት ታማኝ መሆን የሚገባን ለማን እንደሆነ ለመወሰን በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች መመራት ይኖርብናል።
ታማኝነት የሚመነጨው ከልብ ነው፤ የሰው ልብ ግን ከዳተኛ ነው።
በመሆኑም ለአምላክ ታማኝ የሆነ አንድ ሰው፣ የቅርብ ጓደኛው ወይም ዘመዱ መጥፎ ድርጊት እየፈጸመ ቢሆንም ለእሱ ታማኝ መሆን እንዳለበት ሊሰማው ይችላል።
ይሁንና እውነትን የተወው በጣም የምንቀርበው ሰው ቢሆንም እንኳ ከማንም በላይ ታማኝ መሆን ያለብን ለይሖዋ እንደሆነ ማስታወስ ይኖርብናል።
በሮም የሚገኙ ክርስቲያኖች ቀድሞውኑ የተቀበሉትን ነገር ማረጋገጥ ያስፈለጋቸው ለምንድን ነው?
አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ እንመልከት።
ጢሞቴዎስ ቅዱሳን መጻሕፍትን ጠንቅቆ ያውቅ ነበር።
እናቱና አያቱ ከጨቅላነት ዕድሜው አንስቶ አስተምረውታል።
ያም ቢሆን ጳውሎስ በተማርካቸውና አምነህ በተቀበልካቸው ነገሮች ጸንተህ ኑር በማለት አሳስቦት ነበር።
አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንደገለጸው መቀበል ተብሎ የተተረጎመው ቃል በበኩረ ጽሑፉ አንድ ነገር እውነት መሆኑን ማመንና እርግጠኛ መሆን የሚል ሐሳብ ያስተላልፋል።
ጢሞቴዎስ እውነትን የራሱ አድርጓል።
እንዲህ ያደረገው እናቱና አያቱ ስላስገደዱት ሳይሆን በተማረው ነገር ላይ በሚገባ ካሰበበት በኋላ አምኖ ስለተቀበለው ነው።
በተመሳሳይ አንተም ትጋት የተሞላበት የግል ጥናት ማድረግህ ለሚቀርቡልህ ጥያቄዎች መልስ እንድትሰጥ፣ ማንኛውንም ጥርጣሬ እንድታስወግድ እንዲሁም እምነትህን እንድታጠናክር ሊረዳህ ይችላል።
የሰዎችን ልብ መማረክ የምንችለው ጉራ በመንዛት ወይም አላስፈላጊ ትኩረት ወደ ራሳችን በመሳብ ሳይሆን የሰከነና ገር መንፈስ በማሳየት እንደሆነ እንገነዘባለን።
በልባችን ውስጥ የኩራት ስሜት ካለ ውሎ አድሮ በድርጊታችን መታየቱ አይቀርም።
ለምሳሌ ያህል፣ ልዩ መብት እንዳለን፣ አንዳንድ ሚስጥሮችን እንደምናውቅ ወይም ኃላፊነት ካላቸው ወንድሞች ጋር የተለየ ቅርርብ እንዳለን ጠቆም እናደርግ ይሆናል።
አሊያም ደግሞ የሌሎች አስተዋጽኦ ያለበት አንድ ሐሳብ ወይም ድርጊት የእኛ ብቻ እንደሆነ በሚያስመስል መልኩ ልናወራ እንችላለን።
በዚህ ረገድ ኢየሱስ ግሩም ምሳሌ ይሆነናል።
ኢየሱስ የተናገረው አብዛኛው ነገር በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ከዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የተወሰደ ነበር።
ኢየሱስ በንግግሩ ልኩን እንደሚያውቅ አሳይቷል፤ ይህን ያደረገው አድማጮቹ የሚናገረው ነገር በራሱ እውቀትና ጥበብ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ከይሖዋ የመጣ እንደሆነ እንዲያውቁ ይፈልግ ስለነበር ነው።
ወላጆች እንደ ኢየሱስ ልብ ማንበብ የማትችሉ ቢሆንም በአምላክ እርዳታ፣ በልጆቻችሁ ልብ ውስጥ ያለውን ነገር ማስተዋል ትችላላችሁ።
አስተዋይ በመሆን በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙት ልጆቻችሁ ያላቸውን መልካም ጎን ለመመልከት ትጥራላችሁ?
ማንም ቢሆን ችግር ፈጣሪ የሚል ስም እንዲሰጠው አይፈልግም።
እናንተም ስለ ልጃችሁ ያላችሁ አመለካከትና የምትናገሩት ነገር ልጁን እንደ ዓመፀኛ ወይም አስቸጋሪ አድርጋችሁ እንደምትመለከቱት የሚያሳይ እንዳይሆን ተጠንቀቁ።
ልጃችሁ ጥፋት ቢሠራም እንኳ ያሉትን መልካም ባሕርያት እንደምታውቁና ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ከልቡ የሚፈልግ መሆኑን እንደምትገነዘቡ ንገሩት።
ለውጥና መሻሻል እያደረገ እንዳለ የሚጠቁም ነገር ስትመለከቱ አመስግኑት።
የሚቻል ከሆነ ተጨማሪ ኃላፊነት በመስጠት ያሉትን መልካም ባሕርያት እንዲያዳብር እርዱት።
ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በተያያዘ እንዲህ አድርጓል።
ኢየሱስ ከናትናኤል ጋር ከተገናኘ ከአንድ ዓመት ተኩል ገደማ በኋላ ናትናኤልን ሐዋርያ አድርጎ የመረጠው ሲሆን እሱም ቀናተኛ ክርስቲያን መሆኑን አስመሥክሯል።
ልጃችሁን ማመስገናችሁና ማበረታታታችሁ ልጁ የሚጠበቅበትን የማያሟላ ሰው እንዳልሆነ እንዲገነዘብ ከዚህ ይልቅ ይሖዋ ሊጠቀምበት የሚችል ብቁ ክርስቲያን እንደሆነ እንዲሰማው ያደርጋል።
የመጨረሻዎቹ ቀናት በ1914 ሲጀምሩ በዓለም ዙሪያ የነበሩት የይሖዋ አገልጋዮች በጥቂት ሺዎች የሚቆጠሩ ነበሩ።
አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቅቡዓን ቀሪዎች ለባልንጀሮቻቸው ባላቸው ፍቅር ተነሳስተውና በአምላክ መንፈስ እየተመሩ የመንግሥቱን ስብከት ሥራ በጽናት አከናውነዋል።
በመሆኑም ምድራዊ ተስፋ ያለው እጅግ ብዙ ሕዝብ እየተሰበሰበ ነው።
በአሁኑ ጊዜ በመላው ምድር ከ115,400 በላይ በሚሆኑ ጉባኤዎች ውስጥ የታቀፉ ከ8,000,000 በላይ የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ሲሆን ቁጥራችንም መጨመሩን ቀጥሏል።
ለምሳሌ በ2014 የአገልግሎት ዓመት ከ275,500 የሚበልጡ ሰዎች ተጠምቀው የይሖዋ ምሥክሮች ሆነዋል፤ ይህም በአማካይ በየሳምንቱ 5,300 የሚያህሉ ሰዎች ይጠመቃሉ ማለት ነው።
በዛሬው ጊዜ የምናየው አስደናቂ እድገት የተገኘው በአምላክ ላይ እምነት ስላለን እንዲሁም ይሖዋ በመንፈሱ መሪነት በተአምር ያስጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ ስለምንቀበል ነው።
የዚህ ሥርዓት አምላክ የሆነው ሰይጣን የይሖዋን ሕዝብ የሚጠላና የሚቃወም ቢሆንም እንኳ መንፈሳዊ ብልጽግና ማግኘታችን አስገራሚ ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን በሺዎች የሚቆጠሩ የቅዱሳን መጻሕፍት ቁርጥራጮችን፣ በእጅ የተገለበጡ ጥንታዊ ቅጂዎችንና ትርጉሞችን አነጻጽረዋል፤ እንዲሁም በከፍተኛ ጥንቃቄ አጥንተዋል።
ያከናወኑት ጥናት ከጥቂቶች በቀር ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ትክክለኛ መሆናቸውን አረጋግጧል።
ምሁራኑ እርግጠኛ ያልሆኑባቸው ጥቂት ጥቅሶች ቢኖሩም እነዚህ ጥቅሶች አጠቃላዩን የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት አይለውጡትም።
በጥንታዊ የቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂዎች ላይ የተደረጉት ጥናቶች፣ ዛሬ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ በመንፈሱ መሪነት መጀመሪያ ያሰፈረውን ሐሳብ የያዘ መሆኑን ቅን ልብ ያላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች እንዲያምኑ አድርገዋቸዋል።
ጠላቶች የአምላክን ቃል ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፤ ያም ቢሆን ይሖዋ፣ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ በስፋት በመተርጎም ረገድ የአምላክ ቃል ተወዳዳሪ የሌለው መጽሐፍ እንዲሆን አድርጓል።
ብዙዎች በአምላክ በማያምኑበት ዘመን እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ በብዛት ከተሸጡ መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ የመጀመሪያውን ቦታ ይዟል፤ እንዲሁም በከፊልም ሆነ በሙሉ ከ2,800 በሚበልጡ ቋንቋዎች ይገኛል።
እርግጥ ነው፣ ግልጽ ወይም እምነት የሚጣልበት በመሆን ረገድ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የሚጎድላቸው ነገር ቢኖርም ተስፋ የሚሰጠውንና ስለ መዳን የሚገልጸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና መልእክት የትኛውንም ትርጉም በማንበብ መረዳት ይቻላል።
ቃላት ሰዎችን የመጉዳት አሊያም የመፈወስ ኃይል አላቸው።
በሰይጣን ዓለም ውስጥ በቃላት ተጠቅሞ ሌሎችን መጉዳት የተለመደ ነው።
የመዝናኛው ዓለም፣ ሰዎች ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ እንዲስሉ እንዲሁም መርዘኛ ቃላቸውን እንደ ቀስት እንዲያነጣጥሩ ያበረታታል።
አንድ ክርስቲያን እንዲህ ካለው ጎጂ ልማድ መራቅ ይኖርበታል።
መርዘኛ ቃላት ተብለው ሊፈረጁ ከሚችሉት አነጋገሮች አንዱ ሽሙጥ ነው፤ ሽሙጥ ሌሎችን ለማቃለል ወይም ለመዝለፍ ተብሎ የሚሰነዘር ስሜትን የሚጎዳ አነጋገር ነው።
ብዙውን ጊዜ ለቀልድ ተብሎ የሚነገር ቢሆንም ሳይታሰብ መልኩን ሊቀይርና ሌሎችን የሚያንኳስስ ወይም ስድብ አዘል መልእክት የሚያስተላልፍ ሊሆን ይችላል።
መርዘኛ የሆነ ሽሙጥ፣ ስድብ በመሆኑ ክርስቲያኖች ሊያስወግዱት ይገባል።
ቀልድ ጨዋታን ሊያጣፍጥ ቢችልም ሌሎችን በነገር በመውጋትና ስሜታቸውን የሚጎዳ ወይም እነሱን የሚያንቋሽሽ አሽሙር በመናገር ለማሳቅ ከመሞከር መቆጠብ አለብን።
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይመክረናል፦ እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎቹን ሊጠቅም የሚችል መልካም ቃል ብቻ እንጂ የበሰበሰ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።