text stringlengths 4 267 |
|---|
እነዚህ ወጣቶች በአምላክ ኃይል ላይ እምነት ስለነበራቸው የአንበሶችን አፍ ዘግተዋል እንዲሁም የእሳትን ኃይል አጥፍተዋል ሊባልላቸው ችሏል። |
እንደ ሚካያህ እና ኤርምያስ ያሉት ነቢያት መዘባበቻ በመሆንና ወህኒ ቤት በመጣል ፈተና ቢደርስባቸውም እምነት ስለነበራቸው ተቋቁመውታል። |
እንደ ኤልያስ ያሉ ሌሎች ደግሞ በየበረሃው፣ በየተራራው፣ በየዋሻውና በምድር ውስጥ ባሉ ጉድጓዶች ተቅበዝብዘዋል። |
ሁሉም መጽናት የቻሉት ተስፋ የተደረጉትን ነገሮች በእርግጠኝነት ይጠብቁ ስለነበር ነው። |
የውጭ አገር ሰዎች ወደ መንግሥት አዳራሻችን መጀመሪያ ሲመጡ ሞቅ አድርገን በመቀበል ደግነት ልናሳያቸው እንችላለን። |
እኛ ወደምንኖርበት አገር በቅርቡ የመጡ የሌላ አገር ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ዓይናፋርነት እንደሚታይባቸውና ከሌሎች ጋር መቀላቀል እንደሚከብዳቸው አስተውለን ይሆናል። |
በአስተዳደጋቸው ወይም በማኅበረሰቡ ውስጥ ባላቸው ቦታ የተነሳ ሌላ ዘር ወይም ዜግነት ካላቸው ሰዎች እንደሚያንሱ ሊሰማቸው ይችላል። |
በመሆኑም ቅድሚያውን ወስደን ሞቅ አድርገን ልንቀበላቸውና ልባዊ አሳቢነት ልናሳያቸው ይገባል። |
JW Language ጄ ደብልዩ ላንግዌጅ የተባለው አፕሊኬሽን በቋንቋህ የሚገኝ ከሆነ ከሌላ አገር ለመጡ ሰዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሰላምታ ለመስጠት ይረዳሃል። |
ከአንተ የተለየ ባሕል ካላቸው ሰዎች ጋር መጨዋወት ይከብድህ ይሆናል። |
እንዲህ ያለውን ስሜት ለማሸነፍ ስለ ራስህ አንዳንድ ነገሮች ልትነግራቸው ትችላለህ። |
ይህን ስታደርግ ከልዩነቶቻችሁ ይልቅ የሚያመሳስሏችሁ ነገሮች እንደሚበዙ ትገነዘብ ይሆናል፤ በተጨማሪም እያንዳንዱ ባሕል የራሱ የሆነ ጥሩም ሆነ መጥፎ ጎን እንዳለው ትረዳለህ። |
ይሖዋ፣ ታማኝ አገልጋዮቹ አንዳንድ መብቶችን እስኪያገኙ አሊያም ደግሞ ያሉበት ሁኔታ እስኪስተካከልላቸው ድረስ የተወሰነ ጊዜ እንዲያልፍ ሊፈቅድ ቢችልም ምንጊዜም እነሱን ከመደገፍ ወደኋላ አይልም። |
ይሖዋ፣ ለአብርሃም ወንድ ልጅ እንደሚሰጠው ቃል ቢገባለትም ይህ የአምላክ አገልጋይ በእምነትና በትዕግሥት መጠበቅ አስፈልጎታል። |
ይስሐቅ እስኪወለድ ድረስ ዓመታት ቢያልፉም አብርሃም ተስፋ አልቆረጠም፤ ይሖዋም አላሳፈረውም። |
እርግጥ ነው፣ በትዕግሥት መጠበቅ ቀላል አይደለም። |
የጠበቅነው ነገር አለመሳካቱን እያሰብን የምንብሰለሰል ከሆነ ተስፋ ልንቆርጥ እንችላለን። |
ከዚህ ይልቅ ጊዜያችንን መንፈሳዊ ብቃቶችን ለማዳበር ብንጠቀምበት ጥበብ ይሆናል። |
የአምላክን ቃል በማንበብና ባነበብነው ላይ በማሰላሰል ጥበብን፣ ጥልቅ ማስተዋልን፣ እውቀትን፣ የማመዛዘን ችሎታንና ጤናማ አስተሳሰብን ማዳበር እንችላለን። |
መዝናኛን፣ አለባበስንና አጋጌጥን፣ የገንዘብ አያያዝን እንዲሁም ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነት በተመለከተ ውሳኔ የሚጠይቁ ነገሮች በየዕለቱ ያጋጥሙናል። |
ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማርነውን ነገር በተግባር በማዋል ይሖዋን የሚያስደስቱ ውሳኔዎችን ማድረግ እንችላለን። |
አምላክ፣ በሚቆጣበት ጊዜም እንኳ ብዙ ሰዎች እንደሚያደርጉት ያልታሰበበት ውሳኔ አያደርግም። |
ይሖዋ የነነዌ ሰዎች ንስሐ እንደገቡና እንደተለወጡ ሲያይ ውሳኔውን ቀይሯል። |
ይህን በማድረግ ምክንያታዊ፣ ትሑትና ሩኅሩኅ አምላክ መሆኑን አሳይቷል። |
እኛም አንዳንድ ጊዜ፣ ያደረግነውን ውሳኔ መለስ ብለን ማጤናችን ጥሩ ይሆናል። |
እንዲህ ለማድረግ የሚያነሳሳን ሁኔታዎቹ መቀየራቸው ሊሆን ይችላል። |
ይሖዋም ቢሆን ሁኔታዎች በመለወጣቸው የተነሳ ውሳኔዎቹን የቀየረባቸው ጊዜያት አሉ። |
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ውሳኔያችንን እንድንቀይር የሚያደርግ አዲስ መረጃ እናገኝ ይሆናል። |
ንጉሥ ዳዊት የሳኦል የልጅ ልጅ የሆነውን ሜፊቦስቴን በተመለከተ የተሳሳተ ወሬ ተነግሮት ነበር። |
ከጊዜ በኋላ ዳዊት ስለ ሁኔታው ትክክለኛ መረጃ ሲያገኝ ውሳኔውን አስተካክሏል። |
የአምላክ ቃል፣ በሕዝቡ ላይ የተሾሙትን ሰዎች ይመራቸው የነበረው እንዴት ነው? |
ንጉሥ ኢዮስያስን እንደ ምሳሌ እንውሰድ። |
የሙሴ ሕግ መጽሐፍ ከተገኘ በኋላ የኢዮስያስ ጸሐፊ ሕጉን አነበበለት። |
ኢዮስያስ በአምላክ ቃል በመመራት የጣዖት አምልኮን ለማጥፋት ከፍተኛ ዘመቻ አካሄደ፤ እንዲሁም የፋሲካን በዓል ከዚያ በፊት ታይቶ በማያውቅ መልኩ አከበረ። |
ኢዮስያስና ሌሎች ታማኝ መሪዎች፣ በአምላክ ቃል ይመሩ ስለነበር ለሕዝቡ የሚሰጡትን መመሪያ ለማስተካከል ፈቃደኞች ሆነዋል። |
እነዚህ ለውጦች የጥንቱ የአምላክ ሕዝብ ከእሱ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ እንዲመላለስ አስተዋጽኦ አድርገዋል። |
ይሁን እንጂ የጥንቶቹን የአምላክ ሕዝቦች ይገዙ ከነበሩት ነገሥታት አንዳንዶቹ የአምላክን መመሪያዎች አልታዘዙም። |
ይሖዋ ለእነዚህ መሪዎች ተግሣጽ የሰጠባቸው ወይም በሌላ መሪ እንዲተኩ ያደረገባቸው ጊዜያት ነበሩ። |
እሱ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ ደግሞ ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው ከነበሩት መሪዎች ሁሉ የላቀ መሪ ሾመ። |
በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች የመምረጥ ነፃነታቸውን አላግባብ ሲጠቀሙበት አልፎ ተርፎም ሌሎችን የሚጎዳ ነገር ሲያደርጉበት ይታያሉ። |
በእርግጥም መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ እንደተናገረው በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የማያመሰግኑ ሆነዋል። |
እኛም ይሖዋ የሰጠንን ይህን ውድ ስጦታ አላግባብ እንዳንጠቀምበት እንዲሁም ለዚህ ስጦታ አድናቆት እንዳናጣ እንጠንቀቅ። |
ይሁንና የመምረጥ ነፃነታችንን አላግባብ እንዳንጠቀምበት ምን ሊረዳን ይችላል? |
ሁላችንም ከጓደኛ፣ ከአለባበስ፣ ከአጋጌጥ እንዲሁም ከመዝናኛ ምርጫ ጋር በተያያዘ የግላችንን ውሳኔ የማድረግ ነፃነት አለን። |
ይሁንና ለራሳችን ምኞት ባሪያ ከሆንን ወይም በዓለም ውስጥ ያለውን ቅጥ ያጣ ፋሽን መከተል ከጀመርን የመምረጥ ነፃነታችንን የክፋት መሸፈኛ እያደረግነው ነው ሊባል ይችላል። |
ነፃነታችንን የሥጋን ፍላጎት ለማርካት መጠቀም አንፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ የምናደርጋቸው ምርጫዎች ሁሉንም ነገር ለአምላክ ክብር አድርጉ የሚለውን ምክር ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱን መሆን ይኖርባቸዋል። |
ኖኅ ይኖር የነበረው በዓመፅና በሥነ ምግባር ብልግና በተሞላ ዓለም ውስጥ ነበር። |
ኖኅ የይሖዋን የማስጠንቀቂያ መልእክት በታማኝነት የሰበከ ቢሆንም በዙሪያው ያሉት ክፉ ሰዎች መልእክቱን እንዲቀበሉ ማስገደድም ሆነ የጥፋት ውኃው የሚመጣበትን ጊዜ ማፋጠን አይችልም። |
ኖኅ፣ ይሖዋ ክፋትን ለማጥፋት የገባውን ቃል በትክክለኛው ጊዜ ላይ እንደሚፈጽም መተማመን ያስፈልገው ነበር። |
እኛም የምንኖረው በክፋት በተሞላ ዓለም ውስጥ ሲሆን ይሖዋ ይህን ክፉ ዓለም ለማጥፋት ቃል እንደገባ እናውቃለን። |
ያም ቢሆን ሰዎች የመንግሥቱን ምሥራች እንዲቀበሉ ማስገደድ አንችልም። |
ታላቁ መከራ የሚጀምርበትን ጊዜ ማፋጠን እንደማንችልም የታወቀ ነው። |
ልክ እንደ ኖኅ፣ እኛም ይሖዋ በቅርቡ እርምጃ እንደሚወስድ በመተማመን ጠንካራ እምነት እንዳለን ልናሳይ ይገባል። |
ይሖዋ፣ ይህን ክፉ ሥርዓት የሚያጠፋበትን ጊዜ ወስኗል፤ ይህ ጊዜ በአንድ ቀንም እንኳ እንዲራዘም እንደማይፈቅድ እርግጠኞች ነን። |
የጽድቅ ሰባኪ የነበረው ኖኅ፣ አምላክ የማስጠንቀቂያ መልእክት እንዲያውጅ የሰጠውን ሥራ በታማኝነት አከናውኗል። |
ኖኅ እንዲህ ማድረጉ እምነቱን ለማጠናከር እንደረዳው ግልጽ ነው። |
ከስብከት ሥራው በተጨማሪ ጉልበቱንና የማሰብ ችሎታውን ተጠቅሞ አምላክ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት መርከብ ሠርቷል። |
ልክ እንደ ኖኅ፣ እኛም የጌታ ሥራ የበዛልን ለመሆን ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን። |
ይህ ሥራ፣ የአምልኮ ቦታዎችን መገንባትንና መጠገንን፣ በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ በፈቃደኝነት ማገልገልን እንዲሁም በቅርንጫፍ ቢሮ ወይም በርቀት የትርጉም ቢሮዎች ውስጥ ማገልገልን ይጨምራል። |
ከሁሉም በላይ ግን ምንጊዜም በስብከቱ ሥራ መጠመድ ይኖርብናል፤ ይህም ተስፋችን ይበልጥ ብሩህ እንዲሆንልን ያደርጋል። |
በእርግጥም በስብከቱ ሥራ መካፈላችን ለሕይወት በምናደርገው ሩጫ ተስፋ እንዳንቆርጥ ይረዳናል። |
እንደ አባቱ እንደ አሳ ሁሉ ኢዮሳፍጥም አስፈሪ የሆነ የጠላት ሠራዊት በመጣበት ጊዜም እንኳ ሙሉ በሙሉ ለአምላክ ያደረ መሆኑን አሳይቷል። |
ኢዮሳፍጥ ፈርቶ ስለነበር ይሖዋን ለመፈለግ ቆርጦ ተነሳ። |
እሱም ሆነ ሕዝቡ ይህን ታላቅ ሠራዊት ለመቋቋም የሚያስችል ኃይል እንደሌላቸው በመግለጽ ትሕትና የተሞላበት ጸሎት አቅርቧል፤ አክሎም ምን ማድረግ እንዳለብንም አናውቅም ሲል ተናግሯል። |
በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ መናገሩም በይሖዋ ሙሉ በሙሉ እንደሚታመን ያሳያል። |
ልክ እንደ ኢዮሳፍጥ ሁሉ እኛም አንዳንድ ጊዜ፣ ችግር ሲያጋጥመን ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ እንጋባ ምናልባትም በፍርሃት እንዋጥ ይሆናል። |
በዚህ ጊዜ፣ ኢዮሳፍጥ ምን እንዳደረገ ማስታወሳችን ጠቃሚ ነው፤ እሱም ሆነ የይሁዳ ሰዎች ጠላቶቻቸውን የመቋቋም አቅም እንደሌላቸው በሕዝቡ ፊት ባቀረበው ጸሎት ላይ ገልጿል። |
የቤተሰብ ራሶች ችግር በሚያጋጥማቸው ጊዜ ይሖዋ አስፈላጊውን መመሪያና ሁኔታውን ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት እንዲሰጣቸው በመለመን የኢዮሳፍጥን ምሳሌ መከተል ይችላሉ። |
በቤተሰብህ ፊት እንዲህ ዓይነት ልመና ማቅረብ ሊያሳፍርህ አይገባም። |
የቤተሰብህ አባላት እንዲህ ያለ ጸሎት ስታቀርብ መስማታቸው በይሖዋ እንደምትታመን እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል። |
አምላክ ኢዮሳፍጥን እንደረዳው ሁሉ አንተንም ይረዳሃል። |
ኢየሱስ አገልግሎቱን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በቅዱሳን መጻሕፍት ይመራ ነበር። |
ከመሞቱ በፊት የተናገረው የመጨረሻ ሐሳብ እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ መሲሑ የተነገሩ ትንቢቶችን የያዘ ነበር። |
በተቃራኒው በወቅቱ የነበሩት የሃይማኖት መሪዎች፣ የአምላክ ቃል ከራሳቸው ወግ ጋር በሚጋጭበት ጊዜ ቃሉን ችላ ይሉት ነበር። |
ኢየሱስ ስለ እነዚህ ሰዎች ሲናገር ይሖዋ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ያስነገረውን ትንቢት በመጥቀስ እንዲህ ብሏል፦ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው። |
የሚያስተምሩት የሰውን ሥርዓት ስለሆነ እኔን የሚያመልኩት በከንቱ ነው። |
ኢየሱስ የሚያስተምረውም ትምህርት ቢሆን በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ ነበር። |
ኢየሱስ የሃይማኖት መሪዎቹ ጥያቄ በሚያነሱበት ጊዜ መልስ ይሰጥ የነበረው የራሱን ጥበብ ወይም ተሞክሮ በመጠቀም አይደለም። |
ከዚህ ይልቅ ቅዱሳን መጻሕፍትን እንደ መጨረሻ ባለሥልጣን አድርጎ ይጠቅስ ነበር። |
ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በፊት በነበሩት አሥርተ ዓመታት ቻርልስ ቴዝ ራስልና ተባባሪዎቹ፣ የሕዝበ ክርስትና ድርጅቶች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንደማያስተምሩ ተገንዝበው ነበር። |
በመሆኑም ከሐሰት ሃይማኖት ለመራቅ ወሰኑ። |
እነዚህ ወንድሞች የወሰዱትን ቅዱስ ጽሑፋዊ አቋም በተመለከተ የኅዳር 1879 የጽዮን መጠበቂያ ግንብ የሚከተለውን ግልጽ ሐሳብ ይዞ ነበር፦ የክርስቶስ ሚስት የሆነች ንጽሕት ድንግል መሆኗን የምትናገር ሆኖም ከዓለም ከአውሬው ጋር አንድነት ያላትና የዓለምን ድጋፍ የምታገኝ ማንኛዋም ቤተ ክርስቲያን በቅዱሳን መጻሕፍት መሠረት አመንዝራ ቤተ ክርስቲያን ታላቂቱ ባቢሎን በመሆኗ ልናወግዛት ይገባል። |
በወቅቱ የነበሩ ፈሪሃ አምላክ ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቁ ነበር። |
የሐሰት ሃይማኖት ድርጅቶችን እየደገፉ የአምላክን ሞገስ ማግኘት እንደማይችሉ ተገንዝበዋል። |
በመሆኑም በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የነበሩበትን ቤተ ክርስቲያን መልቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ አዘጋጁ። |
ይሖዋ በድርጅቱ ምድራዊ ክፍል ውስጥ የሚገኙ አገልጋዮቹን በታማኝና ልባም ባሪያ አማካኝነት ይመራቸዋል እንዲሁም ይመግባቸዋል፤ ይህን ባሪያ የሚመራው ደግሞ የጉባኤው ራስ ክርስቶስ ነው። |
በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበረው የበላይ አካል ሁሉ ታማኝና ልባም ባሪያም መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈስ መሪነት እንደተጻፈ የአምላክ ቃል ወይም መልእክት አድርጎ የሚቀበለው ከመሆኑም ሌላ ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዘውትረን በስብሰባዎች ላይ እንድንገኝ ያዘናል። |
እንዲሁም ትምህርታችን አንድ እንዲሆን አጥብቆ ያሳስበናል። |
የይሖዋ ቃል፣ ከምንም ነገር በላይ የአምላክን መንግሥት እንድናስቀድም ይመክረናል። |
በተጨማሪም ቅዱሳን መጻሕፍት፣ ምሥራቹን ከቤት ወደ ቤት፣ በአደባባይና መደበኛ ባልሆነ መንገድ የመስበክ ኃላፊነትና መብት እንደተሰጠን ጎላ አድርገው ይገልጻሉ። |
የአምላክ ቃል፣ ክርስቲያን ሽማግሌዎች የድርጅቱን ንጽሕና መጠበቅ እንዳለባቸው ይናገራል። |
ይሖዋ በድርጅቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ ንጽሕናቸውን መጠበቅ እንዳለባቸውም ተናግሯል። |
ኢየሱስ ፈጽሞ አትጨነቁ ሲል ምን ማለቱ ነበር? |
አንድ የአምላክ አገልጋይ በሕይወቱ ውስጥ የሚያስጨንቅ ነገር ጨርሶ እንደማይገጥመው መናገሩ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። |
ኢየሱስ ይህን ሲል፣ አላስፈላጊ ወይም ከልክ ያለፈ ጭንቀት ችግሮችን ለመፍታት እንደማይረዳ ለደቀ መዛሙርቱ ማስተማሩ ነበር። |
እያንዳንዱ ቀን የራሱ ተፈታታኝ ሁኔታዎች አሉት፤ በመሆኑም ክርስቲያኖች አሁን ያላቸው ጭንቀት እንዳይበቃቸው፣ ስላለፈው ወይም ስለ ወደፊቱ ጊዜ እያሰቡ መጨነቅ አያስፈልጋቸውም። |
አንድ ክርስቲያን ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን እያሰበ የሚብሰለሰል ከሆነ ሳያስፈልግ ሊጨነቅ ይችላል። |
ይሁን እንጂ ስለማታውቀው ሁኔታ እያሰብክ በጭንቀት ወይም በስጋት መዋጥ ምንም ፋይዳ የለውም። |
እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.