text
stringlengths
4
267
እነሱም በታላቅ ድምፅ “ታርዶ የነበረው በግ ኃይል፣ ብልጽግና፣ ጥበብ፣ ብርታት፣ ክብር፣ ግርማና በረከት ሊቀበል ይገባዋል” አሉ።
እንዲሁም በሰማይ፣ በምድር፣ ከምድር በታችና በባሕር ያለ ፍጡር ሁሉ፣ አዎ በውስጣቸው ያሉ ነገሮች ሁሉ “በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉ በረከት፣ ክብር፣ ግርማና ኃይል ለዘላለም ይሁን” ብለው ሲናገሩ ሰማሁ።
አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት “አሜን!” ይሉ ነበር፤ ሽማግሌዎቹም ተደፍተው ሰገዱ።
ከዚያም አየሁ፤ እነሆ፣ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሟል፤ ከእሱም ጋር የእሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው 144,000 ነበሩ።
ከሰማይ እንደ ብዙ ውኃዎችና እንደ ኃይለኛ የነጎድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ ሲወጣ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምፅ በገናቸውን እየደረደሩ የሚዘምሩ ዘማሪዎች ዓይነት ድምፅ ነው።
እነሱም በዙፋኑ ፊት እንዲሁም በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታትና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ የሚመስል መዝሙር እየዘመሩ ነበር፤ ከምድር ከተዋጁት ከ144,000ዎቹ በስተቀር ማንም ይህን መዝሙር ጠንቅቆ ሊያውቀው አልቻለም።
እነዚህ ራሳቸውን በሴቶች ያላረከሱ ናቸው፤ እንዲያውም ደናግል ናቸው። ምንጊዜም በጉ በሄደበት ሁሉ ይከተሉታል። እነዚህ ለአምላክና ለበጉ እንደ በኩራት ሆነው ከሰዎች መካከል ተዋጅተዋል፤
በአፋቸውም የማታለያ ቃል አልተገኘም፤ ምንም ዓይነት እንከን የለባቸውም።
ሌላም መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤ እሱም በምድር ላይ ለሚኖር ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ሕዝብ ሁሉ የሚያበስረው የዘላለም ምሥራች ይዞ ነበር።
እሱም በታላቅ ድምፅ “አምላክን ፍሩ፤ ክብርም ስጡት፤ ምክንያቱም የሚፈርድበት ሰዓት ደርሷል፤ በመሆኑም ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና የውኃ ምንጮችን የሠራውን አምልኩ” አለ።
ሌላ ሁለተኛ መልአክ “ወደቀች! ብሔራት ሁሉ የዝሙቷን የፍትወት ወይን ጠጅ እንዲጠጡ ያደረገችው ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች!” እያለ ተከተለው።
ሌላ ሦስተኛ መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፦ “ማንም አውሬውንና ምስሉን የሚያመልክና በግንባሩ ወይም በእጁ ላይ ምልክት የሚቀበል ከሆነ
እሱም፣ ሳይበረዝ ወደ ቁጣው ጽዋ የተቀዳውን የአምላክ የቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ እንዲሁም በቅዱሳኑ መላእክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በድኝ ይሠቃያል።
የሥቃያቸውም ጭስ ለዘላለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ደግሞም አውሬውንና ምስሉን የሚያመልኩ እንዲሁም የስሙን ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ምንም እረፍት አይኖራቸውም።
የአምላክን ትእዛዛት የሚጠብቁና የኢየሱስን እምነት አጥብቀው የሚከተሉ ቅዱሳን፣ መጽናት የሚያስፈልጋቸው እዚህ ላይ ነው።”
ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፦ “ይህን ጻፍ፦ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከጌታ ጋር ያላቸውን አንድነት ጠብቀው የሚሞቱ ደስተኞች ናቸው። መንፈስም ‘አዎ፣ ያከናወኑት ሥራ ወዲያው ስለሚከተላቸው ከድካማቸው ይረፉ’ ይላል።”
ከዚያም አየሁ፤ እነሆም፣ ነጭ ደመና ነበር፤ በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጧል፤ እሱም በራሱ ላይ የወርቅ አክሊል ደፍቷል፤ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዟል።
ሌላ መልአክ ከቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው “የአጨዳው ሰዓት ስለደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፤ ምክንያቱም የምድር መከር ደርሷል” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደ፤ ምድርም ታጨደች።
አሁንም ሌላ መልአክ በሰማይ ካለው ቤተ መቅደስ ቅዱስ ስፍራ ወጣ፤ እሱም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር።
እንደገናም ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጣ፤ እሱም በእሳቱ ላይ ሥልጣን ነበረው። በታላቅ ድምፅ ጮኾም ስለታም ማጭድ የያዘውን መልአክ “የምድሪቱ የወይን ፍሬዎች ስለበሰሉ ስለታም ማጭድህን ስደድና የምድርን የወይን ዘለላዎች ሰብስብ” አለው።
መልአኩ ማጭዱን ወደ ምድር በመስደድ የምድርን ወይን ሰበሰበ፤ ከዚያም ወደ ታላቁ የአምላክ የቁጣ ወይን መጭመቂያ ወረወረው።
ወይኑ ከከተማው ውጭ ተረገጠ፤ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስ ከፍታ ያለውና 296 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ያለው ደም ወጣ።
መልአኩም ከአምላክና ከበጉ ዙፋን ወጥቶ የሚፈሰውን እንደ ክሪስታል የጠራ የሕይወት ውኃ ወንዝ አሳየኝ፤
ወንዙም በከተማዋ አውራ ጎዳና መካከል ቁልቁል ይፈስ ነበር። በወንዙ ግራና ቀኝ በየወሩ እያፈሩ በዓመት 12 ጊዜ ፍሬ የሚሰጡ የሕይወት ዛፎች ነበሩ። የዛፎቹም ቅጠሎች ሕዝቦችን ለመፈወስ የሚያገለግሉ ነበሩ።
በዚያም ከእንግዲህ እርግማን አይኖርም። ከዚህ ይልቅ የአምላክና የበጉ ዙፋን በከተማዋ ውስጥ ይሆናል፤ ባሪያዎቹም ቅዱስ አገልግሎት ያቀርቡለታል፤
ፊቱንም ያያሉ፤ ስሙም በግንባራቸው ላይ ይሆናል።
በተጨማሪም ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ይሖዋ አምላክ በእነሱ ላይ ብርሃን ስለሚፈነጥቅ የመብራት ብርሃንም ሆነ የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ደግሞም ለዘላለም ይነግሣሉ።
መልአኩም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ቃላት አስተማማኝና እውነት ናቸው፤ አዎ፣ ነቢያት በመንፈስ መሪነት እንዲናገሩ የሚያደርገው ይሖዋ አምላክ፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ መፈጸም ያለባቸውን ነገሮች ለባሪያዎቹ ለማሳየት መልአኩን ልኳል።
እነሆ፣ እኔ ቶሎ እመጣለሁ። በዚህ ጥቅልል ውስጥ የሚገኙትን የትንቢት ቃላት የሚጠብቅ ማንኛውም ሰው ደስተኛ ነው።”
እነዚህን ነገሮች ስሰማና ስመለከት የነበርኩት እኔ ዮሐንስ ነኝ። እነዚህን ነገሮች በሰማሁና ባየሁ ጊዜ እያሳየኝ ለነበረው መልአክ ልሰግድ እግሩ ሥር ተደፋሁ።
እሱ ግን “ተጠንቀቅ! ፈጽሞ እንዳታደርገው! እኔ ከአንተም ሆነ ነቢያት ከሆኑት ወንድሞችህና በዚህ ጥቅልል ውስጥ የሰፈሩትን ቃላት ከሚጠብቁት ሁሉ ጋር አብሬ የማገለግል ባሪያ ነኝ። ለአምላክ ስገድ” አለኝ።
ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ “የተወሰነው ጊዜ ስለቀረበ በዚህ ጥቅልል ውስጥ የሰፈሩትን የትንቢት ቃላት በማኅተም አታሽጋቸው።
ጻድቅ ያልሆነ፣ በዓመፅ ጎዳናው ይቀጥል፤ ርኩስ የሆነውም በርኩሰቱ ይቀጥል፤ ጻድቅ የሆነው ግን በጽድቅ ጎዳና መመላለሱን ይቀጥል፤ ቅዱስ የሆነውም በቅድስና ይቀጥል።
“‘እነሆ፣ እኔ ቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምከፍለው ብድራት ከእኔ ጋር ነው።
እኔ አልፋና ኦሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፣ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ።
ከሕይወት ዛፎች ፍሬ የመብላት መብት እንዲያገኙና በበሮቿ በኩል ወደ ከተማዋ መግባት እንዲፈቀድላቸው ልብሳቸውን የሚያጥቡ ደስተኞች ናቸው።
ውሾች፣ መናፍስታዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ ሴሰኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎች እንዲሁም ውሸትን የሚወዱና የሚዋሹ ሁሉ ከከተማዋ ውጭ አሉ።’
“‘እኔ ኢየሱስ ለጉባኤዎቹ ጥቅም ስል ስለ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ለመመሥከር መልአኬን ልኬአለሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር እንዲሁም ደማቅ አጥቢያ ኮከብ ነኝ።’”
መንፈሱና ሙሽራይቱም “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም ሁሉ “ና!” ይበል፤ የተጠማም ሁሉ ይምጣ፤ የሚፈልግ ሁሉ የሕይወትን ውኃ በነፃ ይውሰድ።
“በዚህ ጥቅልል ላይ የሰፈሩትን የትንቢት ቃላት ለሚሰማ ሁሉ እመሠክራለሁ፦ ማንም በእነዚህ ነገሮች ላይ አንዲት ነገር ቢጨምር አምላክ በዚህ ጥቅልል ውስጥ የተጻፉትን መቅሰፍቶች ይጨምርበታል፤
ማንም በዚህ የትንቢት መጽሐፍ ጥቅልል ላይ ከሰፈሩት ቃላት አንዲት ነገር ቢያጎድል አምላክ በዚህ ጥቅልል ላይ ከተጠቀሱት የሕይወት ዛፎችና ከቅድስቲቱ ከተማ ዕጣ ፋንታውን ይወስድበታል።
“ስለ እነዚህ ነገሮች የሚመሠክረው ‘አዎ፣ ቶሎ እመጣለሁ’ ይላል።” “አሜን! ጌታ ኢየሱስ፣ ና።”
የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከቅዱሳኑ ጋር ይሁን።
እኔም ሌላ ታላቅና አስደናቂ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ ሰባት መቅሰፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ነበሩ። የአምላክ ቁጣ የሚደመደመው በእነዚህ ስለሆነ እነዚህ መቅሰፍቶች የመጨረሻዎቹ ናቸው።
እኔም ከእሳት ጋር የተቀላቀለ የብርጭቆ ባሕር የሚመስል ነገር አየሁ፤ እንዲሁም አውሬውን፣ ምስሉንና የስሙን ቁጥር ድል የነሱት የአምላክን በገናዎች ይዘው በብርጭቆው ባሕር አጠገብ ቆመው ነበር።
የአምላክን ባሪያ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፦ “ሁሉን ቻይ የሆንከው ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ሥራዎችህ ታላቅና አስደናቂ ናቸው። የዘላለም ንጉሥ ሆይ፣ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው።
ይሖዋ ሆይ፣ ለመሆኑ አንተን የማይፈራና ስምህን ከፍ ከፍ የማያደርግ ማን ነው? አንተ ብቻ ታማኝ ነህና! የጽድቅ ድንጋጌዎችህ ስለተገለጡ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”
ከዚህ በኋላ አየሁ፤ የምሥክሩ ድንኳን ቅዱስ ስፍራ በሰማይ ተከፍቶ ነበር፤
ሰባቱን መቅሰፍቶች የያዙት ሰባቱ መላእክትም ንጹሕና የሚያንጸባርቅ በፍታ ለብሰው እንዲሁም ደረታቸውን በወርቅ መታጠቂያ ታጥቀው ከቅዱሱ ስፍራ ወጡ።
ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት አንዱ ለዘላለም በሚኖረው አምላክ ቁጣ የተሞሉ ሰባት የወርቅ ሳህኖችን ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።
ቅዱሱ ስፍራም ከአምላክ ክብርና ከኃይሉ የተነሳ በጭስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባት መቅሰፍቶች እስኪፈጸሙ ድረስም ወደ ቅዱሱ ስፍራ ማንም መግባት አልቻለም።
ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም፣ በሰማይ የተከፈተ በር ነበር፤ በመጀመሪያ ሲያናግረኝ የሰማሁት ድምፅ እንደ መለከት ድምፅ ያለ ነበር፤ እንዲህም አለኝ፦ “ና ወደዚህ ውጣ፤ መፈጸም ያለባቸውን ነገሮች አሳይሃለሁ።”
ከዚያም ወዲያውኑ የአምላክ መንፈስ ወረደብኝ፦ እነሆም፣ በሰማይ አንድ ዙፋን ተቀምጦ ነበር፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠ ነበር።
በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው የኢያስጲድ ድንጋይና የሰርድዮን ድንጋይ ዓይነት መልክ ነበረው፤ በዙፋኑም ዙሪያ መረግድ የሚመስል ቀስተ ደመና ነበር።
በዙፋኑ ዙሪያ 24 ዙፋኖች ነበሩ፤ በእነዚህም ዙፋኖች ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ 24 ሽማግሌዎች ተቀምጠው አየሁ።
ከዙፋኑ መብረቅ፣ ድምፅና ነጎድጓድ ይወጣ ነበር፤ በዙፋኑም ፊት የሚነድዱ ሰባት የእሳት መብራቶች ነበሩ፤ እነዚህም ሰባቱን የአምላክ መናፍስት ያመለክታሉ።
በዙፋኑ ፊት የክሪስታል መልክ ያለው እንደ ብርጭቆ ያለ ባሕር የሚመስል ነገር ነበር። በዙፋኑ መካከል እና በዙፋኑ ዙሪያ ከፊትም ሆነ ከኋላ በዓይኖች የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጥረታት ነበሩ።
የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ይመስላል፤ ሁለተኛው ሕያው ፍጡር ወይፈን ይመስላል፤ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር የሰው ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛው ሕያው ፍጡር ደግሞ የሚበር ንስር ይመስላል።
እነዚህ አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች አሏቸው፤ ክንፎቹ በዙሪያቸውና በውስጥ በኩል በዓይኖች የተሞሉ ናቸው። ያለማቋረጥም ቀንና ሌሊት “የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው፣ ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ አምላክ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው” ይላሉ።
ሕያዋን ፍጥረታቱ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውንና ለዘላለም የሚኖረውን ከፍ ከፍ ባደረጉ ቁጥር እንዲሁም እሱን ባከበሩና ባመሰገኑ ቁጥር
ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት ተደፍተው ለዘላለም ለሚኖረው አምልኮ ያቀርባሉ፤ እንዲሁም አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት ጥለው እንዲህ ይላሉ፦
“ይሖዋ አምላካችን፣ ሁሉንም ነገሮች ስለፈጠርክ እንዲሁም ወደ ሕልውና የመጡትም ሆነ የተፈጠሩት በአንተ ፈቃድ ስለሆነ ግርማ፣ ክብርና ኃይል ልትቀበል ይገባሃል።”
እኔም የጥልቁን ቁልፍና ታላቅ ሰንሰለት በእጁ የያዘ አንድ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ።
እሱም ዘንዶውን ያዘውና ለ1,000 ዓመት አሰረው፤ ይህም ዘንዶ ዲያብሎስና ሰይጣን የሆነው የጥንቱ እባብ ነው።
ደግሞም ይህ 1,000 ዓመት እስኪያበቃ ድረስ ከእንግዲህ ሕዝቦችን እንዳያሳስት ወደ ጥልቁ ወረወረውና ዘጋበት፤ በማኅተምም አሸገው። ከዚያ በኋላ ለጥቂት ጊዜ ሊፈታ ይገባዋል።
ዙፋኖችንም አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው። ስለ ኢየሱስ በመመሥከራቸውና ስለ አምላክ በመናገራቸው የተነሳ የተገደሉትን ሰዎች ነፍሳት እንዲሁም አውሬውን ወይም ምስሉን ያላመለኩትንና ምልክቱን በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያልተቀበሉትን ሰዎች አየሁ። እነሱም ሕያው ሆነው ከክርስቶስ ጋር ለ1,000 ዓመት ነገሡ።
(የቀሩት ሙታን ይህ 1,000 ዓመት እስኪያበቃ ድረስ ሕያው አልሆኑም።) ይህ የመጀመሪያው ትንሣኤ ነው።
በመጀመሪያው ትንሣኤ ተካፋይ የሆኑ ሁሉ ደስተኞችና ቅዱሳን ናቸው፤ ሁለተኛው ሞት በእነዚህ ላይ ሥልጣን የለውም፤ ከዚህ ይልቅ የአምላክና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእሱም ጋር ለ1,000 ዓመት ይነግሣሉ።
ይህ 1,000 ዓመት እንዳበቃም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤
እሱም በአራቱም የምድር ማዕዘናት ያሉትን ብሔራት፣ ጎግንና ማጎግን ለማሳሳትና ለጦርነቱ አንድ ላይ ለመሰብሰብ ይወጣል። የእነዚህም ቁጥር በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነው።
እነሱም በምድር ሁሉ ተሰራጩ፤ እንዲሁም የቅዱሳኑን ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ። ሆኖም እሳት ከሰማይ ወርዶ በላቸው።
ሲያሳስታቸው የነበረው ዲያብሎስም፣ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ድኙ ሐይቅ ተወረወረ፤ እነሱም ለዘላለም ቀንና ሌሊት ይሠቃያሉ።
እኔም አንድ ትልቅ ነጭ ዙፋንና በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን አየሁ። ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።
ከዚያም ሙታንን፣ ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ የመጽሐፍ ጥቅልሎችም ተከፈቱ። ሌላም ጥቅልል ተከፈተ፤ ይህም የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ነው። ሙታን በጥቅልሎቹ ውስጥ በተጻፉት ነገሮች መሠረት እንደየሥራቸው ፍርድ ተሰጣቸው።
ባሕርም በውስጡ ያሉትን ሙታን ሰጠ፤ ሞትና መቃብርም በውስጣቸው ያሉትን ሙታን ሰጡ፤ እነሱም እያንዳንዳቸው እንደየሥራቸው ፍርድ ተሰጣቸው።
ሞትና መቃብርም ወደ እሳቱ ሐይቅ ተወረወሩ። ይህም የእሳት ሐይቅ ሁለተኛውን ሞት ያመለክታል።
በተጨማሪም በሕይወት መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳቱ ሐይቅ ተወረወረ።
ከዚያም በሰማይ ታላቅ ምልክት ታየ፦ አንዲት ሴት ፀሐይን ተጎናጽፋ ነበር፤ ጨረቃም ከእግሯ ሥር ነበረች፤ በራሷም ላይ 12 ከዋክብት ያሉት አክሊል ነበር፤
እሷም ነፍሰ ጡር ነበረች። ልትወልድ ስትል ምጥ ይዟት በጭንቅ ትጮኽ ነበር።
ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ። እነሆ፣ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉት፣ በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች የደፋ፣ ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ታላቅ ዘንዶ ታየ፤
ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት አንድ ሦስተኛ ጎትቶ ወደ ምድር ወረወረ። ዘንዶውም በምትወልድበት ጊዜ ልጇን ለመዋጥ ፈልጎ ልትወልድ በተቃረበችው ሴት ፊት ቆሞ ይጠብቅ ነበር።
እሷም ብሔራትን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛውን ልጅ አዎ፣ ወንድ ልጅ ወለደች። ልጇም ወደ አምላክና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።
ሴቲቱም 1,260 ቀን በዚያ እንዲመግቧት አምላክ ወዳዘጋጀላት ስፍራ ወደ ምድረ በዳ ሸሸች።
በሰማይም ጦርነት ተነሳ፦ ሚካኤልና መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ ዘንዶውና መላእክቱም ተዋጓቸው፤
ነገር ግን አልቻሏቸውም፤ ከዚያ በኋላም በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።
ስለሆነም ታላቁ ዘንዶ ይኸውም መላውን ዓለም እያሳሳተ ያለው ዲያብሎስና ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የጥንቱ እባብ ወደ ታች ተወረወረ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእሱ ጋር ተወረወሩ።
በሰማይ እንዲህ የሚል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፦ “አሁን የአምላካችን ማዳን፣ ኃይልና መንግሥት እንዲሁም የእሱ መሲሕ ሥልጣን ሆኗል፤ ምክንያቱም ቀንና ሌሊት በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ወደ ታች ተወርውሯል!
እነሱም ከበጉ ደም የተነሳና ከምሥክርነታቸው ቃል የተነሳ ድል ነሱት፤ እስከ ሞት ድረስ እንኳ ለነፍሳቸው አልሳሱም።
ስለዚህ እናንተ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ምድርና ባሕር ግን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ዲያብሎስ ጥቂት ጊዜ እንደቀረው ስላወቀ በታላቅ ቁጣ ተሞልቶ ወደ እናንተ ወርዷል።”
ዘንዶውም ወደ ምድር እንደተወረወረ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ በወለደችው ሴት ላይ ስደት አደረሰባት።
ሆኖም ሴቲቱ ከእባቡ ፊት ርቃ ለአንድ ዘመን፣ ለዘመናትና ለግማሽ ዘመን ወደምትመገብበት በምድረ በዳ ወደተዘጋጀላት ስፍራ በርራ መሄድ እንድትችል የታላቅ ንስር ሁለት ክንፎች ተሰጧት።
እባቡም ሴቲቱ በወንዝ ውስጥ እንድትሰምጥ ከአፉ የወጣ እንደ ወንዝ ያለ ውኃ ከኋላዋ ለቀቀባት።
ይሁን እንጂ ምድሪቱ ለሴቲቱ ደረሰችላት፤ ምድሪቱም አፏን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ የለቀቀውን ወንዝ ዋጠች።
ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ እጅግ ተቆጥቶ የአምላክን ትእዛዛት የሚጠብቁትንና ስለ ኢየሱስ የመመሥከር ሥራ የተሰጣቸውን ከዘሯ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ።
ከዚህ በኋላ ከፍተኛ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሳ ምድር በብርሃን ደመቀች።
እሱም በኃይለኛ ድምፅ እንዲህ ሲል ጮኸ፦ “ወደቀች! ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩስ መንፈስ ሁሉ እንዲሁም የርኩሳንና የተጠሉ ወፎች ሁሉ መሰወሪያ ሆነች!
ብሔራት ሁሉ የዝሙቷ የፍትወት ወይን ጠጅ ሰለባ ሆነዋል፤ የምድር ነገሥታትም ከእሷ ጋር አመንዝረዋል፤ የምድር ነጋዴዎችም ያላንዳች ኀፍረት ባከማቸቻቸው ውድ ነገሮች በልጽገዋል።”
ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “ሕዝቤ ሆይ፣ የኃጢአቷ ተባባሪ መሆን የማትፈልጉና የሚደርስባት መቅሰፍት ተካፋይ መሆን የማትፈልጉ ከሆነ ከእሷ ውጡ።
ኃጢአቷ እስከ ሰማይ ድረስ ተቆልሏልና፤ አምላክም የፈጸመቻቸውን ኢፍትሐዊ ድርጊቶች አስቧል።