Dataset Viewer
Auto-converted to Parquet Duplicate
instruction
stringclasses
4 values
extractive_text
stringclasses
10 values
summary
stringclasses
10 values
Summarize the following news article into a concise headline.
ከተከሰተ ከአመት በላይ ያስጠቆረው የኮቪድ ወረርሽኝ ዛሬም በደቂቃ ዘጠኝ በየእለቱ ደግሞ በሽወች የሚቆጠሩ ሰወችን እየነጠቀ ይገኛል። በጣም ተጋላጭ የሆኑት በጉልህ ይጎዳሉ፣ አሁን ላይ ያለው አደጋ ወረርሽኙን ለመግታት ባለሁለት ፍጥነት የአለም ምላሽ መኖሩ ነው ብለዋል። የገንዘብ አቅም፣ ጊዜንና የሞት መጠንን በቀነሰ መልኩ በአጭር ጊዜ ለውጥ ማምጣት የሚቻልበትን አዋጭ የጦርነት ስልት አይነት በመጠቀም የኮሮና ወረርሽኝ በአለም ላይ እያደረሰ ያለውን ከባድ ጉዳት በአጭር ጊዜ መመከት ይገባል እንደ ጉተሬስ። ከዚህም ባለፈ አይነቱን መቀያየሩና ከአለም ህዝብ አንድ ሶስተኛውን ያልደረሱት ክትባቶች አይነቱን ቀይሮ የሚመጣውን የኮሮና ወረርሽኝ ይከላከሉ አይከላከሉ በጥናት አለመረጋገጡ፣ የወረርሽኙ ባህሪ የጤናውን ስርአት አብዝቶ የሚፈትንና ከየትኛውም አገር አቅም በላይ መሆኑ ከተከሰተ ከአመት በኋላም የአለም አጀንዳነቱን እንደያዘ ቀጥሏል። የአለም ጤና ድርጅትና ሌሎች የፈጠሩት አለም አቀፍ የክትባት ፕሮግራም ኮቫክስም፣ ክትባቱ ለአገሮች በፍትሃዊነት ተደራሽ እንድሆን አላማ አስቀምጦ ቢንቀሳቀስም፣ የኮቪድ ክትባት አቅርቦት ጉልህ እጥረት ገጥሞታል። አሁን ያለውን የኮቪድ ወረርሽኝ መከላከል እንዳለ ሆኖ፣ የሚቀጥለውን ወረርሽኝ ለመከላከል ራስን ማዘጋጀትና የአለም ጤና ስርአትን ማጠናከር ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል። አገሮች ይህ መድሃኒት ያልተገለኘትን ወረርሽኝ ለመዋጋት ከቅድመ መከላከል ጀምሮ እስከ የአስቸኳይ ጊዜ ክትባት ቢዘልቁም፣ ቫይረሱን መቋቋም አልተቻለም። ቫይረሱ በአንድ ጊዜ አንድ አገር ብቻ አጥቅቶ የማይቀር በመሆኑም፣ ተጽእኖው አለም አቀፋዊ ነው። የአለም ጤና ድርጅት አመታዊ ጉባኤን በሳምንቱ መጀመርያ የከፈቱት ጉተሬስ፣ ከሶስት ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ ሰወች በቫይረሱ ምክንያት መሞታቸውንና ግማሽ ቢሊዮን ያህል ስራወች መክሰማቸውን ተናግረዋል። ወረርሽኙን የማስቆም አቅም በቡድን ሃያ አገሮች እጅ ላይ ነው የሚለው የአለም ጤና ድርጅትም፣ አገሮቹ ወረርሽኙን ለመከላከል፣ የመመርመር አቅምን ለማጠናከር፣ ክብካቤና ክትባቱም ለሁሉም በፍትሃዊ መንገድ እንድዳረስ ለማስቻል የጀመሩትን ስራ ማጠናከር ይገባቸዋል።
አለም ከኮቪድ ጋር የገጠመው ጦርነት
Create a short title for the given news content.
የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ግንቦት ፣ ሁለት ሽህ አምስት ጧት ላይ በደህንነቶች ተይዞ መወሰዱን የማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት ሃብታሙ አያሌው ለኢሳት ገልጿል። ምሽት ሰአት ላይ ያነጋገርነው የማህበሩ ቦሌ ክፍለከተማ ምክትል ሃላፊ ወጣት ጥላየ ታረቀኝ እንደገለጸው ደግሞ ከዚህ ቀደም ታስረው በነበረበት ወቅት ሲዝትባቸው የነበረው ሳምሶን የተባለ የደህንነት ሰራተኛ ወጣት ብርሃኑን እንዳስያዘው ገልጿል። የወጣት ብርሃኑ ቤተሰቦች ቤት ሲፈተሽም በአንድ መጽሃፍ ውስጥ ራሳቸው ደህንነቶች ያስገቡትን ጽሁፍ ይሃው አገኘነው በማለት ብርሃኑን እንድፈርም እንደጠየቁትና ከጠበቃየ ጋር ሳልማከር አልፈርምም እንዳለ ወጣት ጥላየ ተናግሯል። ወጣት ሃብታሙ ከሌሎች የማህበሩ አባላት ጋር በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢሄዱም፣ እስረኛውን ሊያገኙት እንዳልቻሉ ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ የወጣት ብርሃኑ ቤት እየተፈተሸ መሆኑን መረጃ እንደደረሳቸው ገልጿል። ወጣት ብርሃኑ ሰማያዊ ፓርቲ ከጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መታሰሩን ወጣት ሃብታሙ ገልጿል። በጉዳዩ ዙሪያ የጉለሌን ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊወች ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሰካም።
የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ታሰረ
Summarize the following news article into a concise headline.
አድስ አበባ፣ መጋቢት ስምንት፣ ሁለት ሽህ ኤፍ ቢ ሲ የፌደራሉ መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ ድጋፍ እንድደርስ አስፈላጊውን ገንቢ ሚና እየተጫወተና እርዳታ እንድላክ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። ከሰባት መቶ ሽህ ህዝብ በላይ እንድፈናቀል እና ከአብአላ በኩል ወደ መቀሌ የሚደረገው የሰብአዊ አገልግሎት ጉዞ እንድቋረጥ ያደረገውም፥ በአፋር ክልል ላይ ዳግም ወረራ ያካሄደው ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን መሆኑ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል ሲል መንግስት በመግለጫው አስገብዝቧል። መግለጫው እንዳመለከተው፥ ከትናንት ጀምሮ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያደርጉ አጋር ድርጅቶች ክትባትን ጨምሮ የተለያዩ መድሃኒቶች፣ የህክምና ቁሳቁስና የምግብ አቅርቦት ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ እንደሚችሉ አረጋግጠዋል። በክልሉ ህዝብ መሰረታዊ ሰብአዊ ድጋፎች ፈጥነው እንድደርሱ ለማድረግ ከቅርብ ቀናት ጀምሮ በየእለቱ አርባ ተሽከርካሪወች ወደ ትግራይ ክልል እንድጓጓዙ የሚደረግ መሆኑንም ነው መንግስት ያስታወቀው። መንግስት የህዝቡን መብት ለማረጋገጥና በችግር ላይ ያሉትን ዜጎቹን ህይወት ለመታደግ ከማንም በላይ ሃላፊነት እንደሚሰማው ገልጾ፥ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የሚላከው ሰብአዊ ድጋፍ ለህዝቡ በቀጥታ እንድደርስ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስቧል። የኢፌደሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ መንግስት ለትግራይ ህዝብ አስፈላጊ የሆኑ የምግብና የመድሃኒት ድጋፎች በአፋር ክልል በኩል እንድደርሱ ምቹ ሁኔታወችን ከመፍጠሩ በተጨማሪ በዛሬው እለት ብቻ የምግብ አቅርቦቶችን የያዙ ሃያ የጭነት ተሸከርካሪወች እና የነዳጅ ታንከሮችን የያዙ ሶስት ተሽከርካሪወች ከሰመራ ወደ መቀሌ መጓዛቸውን አስታውቋል። አለም አቀፉ ማህበረሰብም ችግሩን በሚመጥን ደረጃ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት አመልክቷል። በዚህም መሰረት ሌሎች አጋር ድርጅቶች በጭነት አውሮፕላን ሁለት መቶ ሃምሳ ሰባት ሽህ አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ኪሎ ግራም መድሃኒቶች፥ የህክምና ቁሳቁስና የምግብ አቅርቦቶችን ከአድስ አበባ ወደ መቀሌ ማጓጓዛቸው ተገልጿል። ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃወችን ለማግኘት፡ ድረ ገጽ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን።
መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ ድጋፍ እንድደርስ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ
Provide a news headline based on the following text.
ከአድስ አበባ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውና በሃይቅ በተከበበችው ቢሾፍቱ ከተማ በቢሾፍቱ ሃይቅ ዳርቻ ይገኛል አሻም አፍሪካ ሆቴልና ሪዞርት። ከስያሜ ባለፈ አንድ ኬኒያዊ እንግዳ በናይጀሪያ ስም የተሰየመ መኝታ ቤት ሲገባ ስለ ናይጀሪያ የተለያዩ መረጃወችን ያገኛል ያሉት የ አመቱ አቶ ሳህሉ በየአገራቱ ስም መሰየሙና የየአገሩ ስእል በየመኝታ ቤቱ መሰቀሉ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ያብራራሉ። እንደ ሪዞርቱ ባለቤት አቶ ሳህሉ ሃይሉ ገለፃ ይህን ቦታ አጽድቶ እዚህ ለማድረስ መኪና ቆሻሻ ማንሳት ነበረባቸው። ስሩ አምስት ሜትር ድረስ ወደ መሬት ይጠልቃል የተባለው ይሄው ሳር አፈር በውሃና በንፋስ እንዳይሸረሸር በማድረግ ረገድ ወደር የለሽ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ከሆለታ ግብርና ምርምር አምጥተው እንደተከሉትም የ አሻም አፍሪካ ጠቅላላ አገልግሎት ኦፊሰርና የእለቱ አስጐብኝ አቶ ዳንኤል ግርማ ገልጸውልናል። አሻም አፍሪካ ሆቴልና ሪዞርት በቢሾፍቱ ሃይቅ ዙሪያ ከተገነቡት አምሳያወቹ በብዙ ነገሮች ይለያል። በአጠቃላይ ከአካባቢና ከተፈጥሮ ጋር ህብር የፈጠረ ሆቴልና ሪዞርት ነው ማለት ይቻላል። እኔ ባለሃብት አይደለሁም ሪዞርቱን የገነባሁት ከላይ እንደገለጽኩት አፍሪካን አንድ የሚያደርግና የሚያቀራርብ እንድሆን ነው ያሉት አቶ ሳህሉ አብዛኛውን ወጭ ከባንክ በተገኘ ብድር መሸፈናቸውንና ብር ሲያገኙ ሲቀጥሉ ብር ሲያጥራቸው ሲያቋርጡ ለግንባታው ወደ አምስት አመት ገደማ መውሰዱንም ተናግረዋል። አሻም አፍሪካን ለየት ከሚያደርጉት ገጽታወች መካከል ከመታጠቢያ ክፍሎች ከወጥ ቤትና ከሌሎች ክፍሎች የሚወጡ ፍሳሾችን በማጣራትና ሪሳይክል በማድረግ በድጋሚ ጥቅም ላይ ማዋሉ ሲሆን ከዚህም ባሻገር ለባዮ ጋዝነት በማዋል በባዮ ጋዝ ምግብ እንደሚያበስል ለማወቅ ችለናል። በአሜሪካ አገር ስሩ ሽቶና እጣን የሚሰራበት የሳር አይነት ከሪዞርቱ ግርጌ መጨረሻ ላይ ተተክሏል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ መድና እንደመሆኗ የአፍሪካ ባህል ገጽታ እና አጠቃላይ ሁኔታ በመጠኑም ቢሆን በአንድ ቦታ የሚገኝበት አሻም አፍሪካን በመገንባቴ ደስተኛ ነኝ ብለዋል አቶ ሳህሉ ሃይሉ።
አመድ ሰፈርን ያስዋበው አሻም አፍሪካ
Write a brief headline summarizing the article below.
በአለም ላይ ከሁለት መቶ ሃምሳ በላይ ጋዜጠኞች ታስረዋል በመገባደድ ላይ በሚገኘው የፈረንጆች ሁለት ሽህ ብቻ በመላው አለም ከሁለት መቶ ሃምሳ በላይ ጋዜጠኞች መታሰራቸውንና ላለፉት አመታት ከአለማችን አገራት መካከል በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ቀዳሚነቱን ይዛ የዘለቀችው ቻይና፤ ዘንድሮም በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ ተነግሯል። በአመቱ አርባ ሰባት ጋዜጠኞችን በማሰር በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ቱርክ መሆኗን የጠቆመው የሲፒጀ ሪፖርት፤ ያም ሆኖ ግን በአገሪቱ የታሰሩት ጋዜጠኞች ቁጥር አምና ከነበረው በስልሳ ስምንት መቀነሳቸውን አመልክቷል። በአመቱ በመላው አለም ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞች ቁጥር አምና ከነበረው ሁለት መቶ ሃምሳ አምስት፣ በአምስት ብቻ የቀነሰ ሲሆን በመላው አለም ለእስር ከተዳረጉት ሁለት መቶ ሃምሳ ጋዜጠኞች መካከል ሃያወቹ ሴቶች መሆናቸውንና የሴት ጋዜጠኞች ድርሻ ከአምናው በ በመቶ መቀነሱን ሪፖርቱ አስረድቷል። ተቀማጭነቱ በኒው ዮርክ የሆነው አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጀ ባለፈው ረቡእ ይፋ ባደረገው አመታዊ ሪፖርቱ እንዳለው፤ ባለፉት ወራት ጊዜ ውስጥ አርባ ስምንት ያህል ጋዜጠኞችን ያሰረችው ቻይና፣ ብዛት ያላቸው ጋዜጠኞች በማሰር ከአለማችን አገራት ቀዳሚነቱን ይዛለች። በአለማቀፍ ደረጃ ሃሰተኛ ዜናወችን አሰራጭተዋል በሚል በመንግስታት ለእስር የሚዳረጉ ጋዜጠኞች ቁጥር ባለፉት አራት ተከታታይ አመታት እያደገ መምጣቱን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ በአመቱ በዚህ ሰበብ ስላሳ ጋዜጠኞች ለእስር መዳረጋቸውንም አመልክቷል። ሳኡድ አረቢያና ግብጽ እያንዳንዳቸው በተመሳሳይ ሃያ ስድስት ጋዜጠኞችን በማሰር በሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፣ ኤርትራ እንድሁም ቬትናም ጋዜጠኞችን በማሰር የአራተኛና የአምስተኛ ደረጃን መያዛቸውንም ሪፖርቱ ይጠቁማል። ሲፒጀ በየአመቱ ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞችን ዝርዝር በማጥናት ሪፖርት ማውጣት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች የታሰሩበት አመት ሁለት ሽህ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፣ በአመቱ ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ጋዜጠኞች መታሰራቸውንም ሪፖርቱ አስታውሷል።
ቻይና ጋዜጠኞችን በማሰር ዘንድሮም አለምን ትመራለች
Create a short title for the given news content.
የአካባቢ ጥበቃን መሰረት ያደረገ የስራ እድል የመፍጠር ዝንባሌ ያላቸውን ወጣት የስራ ፈጣሪወችን መደገፍ አላማው ያደረገ ፕሮጀክት ስራ ጀመረ። ካታላይዚንግ ግሪን ቢዝነስ ኢን ኢትዮጵያ በሚል ስያሜ ወደ ስራ የገባው ይህ ፕሮጀክት አላማው፣ ሰፊ ቁጥር የሚሸፍነውን የሃብረተሰብ ክፍል በተለይም ወጣቱ አካባቢን የማይጎዳ ይዘት ያለው ስራ እንደት መፍጠር ይችላል የሚለው ላይ አተኩሮ የሚሰራ እንደሆነ አስረድተዋል። የሪች ፎር ቸንጅ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሶፊያ ብራይትሆልትዝ በበኩላቸው፣ ድርጅታቸው በዋናነት ወጣት የስራ ፈጣሪወችን ማእከል ያደረገ ስራ ለማከናወን ሲያቅድ እንደ ዋነኛ ምክንያት የወሰደው ወጣት የስራ ፈጣሪወች ከማንኛውም የሃብተረተሰብ ክፍል ይልቅ፣ በዙሪያቸው ያለውን ችግር በመረዳት መፍትሄ ለማምጣት የሚስችል አቅም ባለቤት መሆናቸውን በማመን እንደሆነ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ ሁለት አበይት ጉዳዮችን ለማሳካት ያቀደ ሲሆን፣ አንደኛው በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች እንደት የአካባቢ ጥበቃ አረንጓደ ስራ እድል ፈጠራ ባለቤት መሆን ይችላሉ የሚለውን የሚደግፍ መሆኑ ተልክቷል። አይኪያ ፋውንደሽን የተሰኘው የስዊድን ግብረሰናይ ድርጅት የአንድ ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግለት ይህ ፕሮጀክት፣ ሪች ፎር ቸንጅ በተባለ ድርጅት ለ ወራት ያህል አካባቢ ጥበቃን መሰረት ያደረገ የንግድ ፈጠራ ስራ የሚያቀርቡ ወጣቶችን የሚደግፍ እንደሆነ ተገልጿል። መጋቢት ስድስት ቀን ሁለት ሽህ አመተ ምህረት በሸራተን አድስ ሆቴል ይፋ በተደረገው የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ወቅት የተገኙት የሪች ፎር ቸንጅ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ለምለም ስንቅነህ እንደተናገሩት፣ ሪች ፎር ቸንጅ በኢትዮጵያ የሚተገብረውን የአረንጓደ ስራ ፈጣሪነት ፕሮጀከት ለመደገፍና ለማዳበር አይኪያ ፋውንደሽን የአንድ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጎላቸዋል። ከላይ በተጠቀሱት የትምህርት ተቋማት የሚገኙና ተመርቀው ለመውጣት በዝግጅት ላይ የሚገኙ ተማሪወችን በባለሙያወች በማሰልጠን የሚጀምረው ይህ ፕሮጀክት፣ የሚሰጣቸውን ስልጠና ተከትሎ ጥሩ የሆኑና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተገናኙ የስራ ፈጠራወችን የሚያቀርቡ ስልሳ ተማሪወችን በገንዘብ ይደግፋል ተብሏል። ስራ ፈጣሪወች ሃሳባቸውን ወደ ተግባር በመቀየር ሂደት ውስጥ የተለያዩ ችግሮች እንደሚገጥማቸው ያስታወቁት ስራ አስፈፃሚዋ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚስተዋለው የኢንቨስትመንት ካፒታል እጥረት አንስቶ የአቅም ግንባታና የስራ ላይ ትስስር እንደሚያስፈልጋቸው አስረድተዋል። በሙከራ ደረጃ ለ ወራት በሚተገበረው ፕሮጀክት ውስጥ ለሚሳተፉ ፈቃደኛ ወጣቶች ጥሪ የሚቀርብ ሲሆን፣ ከዚያ በማስከተል ለተመረጡ ተማሪወች የአቅም ግንባታና የፋይናንስ ድጋፎች ድርጅቱ እንድያገኙ እንደሚያደርግ ፕሮጀክቱ ይፋ በተደረገበት መድረክ ተገልጿል። ላለፉት ሰባት አመታት ከሁለት መቶ ስላሳ በላይ የስራ ፈጣሪወች ሲደገፉ እንደነበር የተናገሩት ወይዘሮ ለምለም፣ በዚህ ፕሮጀክት በመጨረሻ ተመርጠው የሚቀሩትም ሆኑ ጥሪ ቀርቦላቸው ወደ ስልጠና የሚገቡት ተማሪወች የሚያገኙት ስልጠና በራሳቸው አቅም መስራት እንድችሉ የሚረዳና ግንዛቤ የሚጨብጡበት ይሆናል ብለዋል።
የአካባቢ ጥበቃን መሰረት ያደረገ የፈጠራ ስራን የሚደግፍ ፕሮጀክት ስራ ጀመረ
Provide a news headline based on the following text.
ኢሳት ሰኔ አንድ ፥ ሁለት ሽህ ዘጠኝ የኬንያ ፖሊስ ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ አርባ ኢትዮጵያውያን ሃሙስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ። ኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ በአንድ ወኪል አማካኝነት ሰኞ ከኢትዮጵያ ተነስተው ወደ ደቡብ አፍሪካ የማቅናት እቅድ እንደነበራቸው በአስተርጓሚ በኩል ቃል እንደሰጡ የንጅሩ አስተዳደር ሃላፊ አስረድተዋል። ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት ላይ ያሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ኬንያን ጨምሮ በተለያዩ የምእራብ አፍሪካ ሃገራት ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው ለእስር ተዳርገው ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት በቃየሌ ከተማ በሚገኝ አንድ እስር ቤት በእስር ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውን በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የኒጅሩ አስተዳደር ኮማንደር ፓርቲክ ምዋምባ ኢትዮጵያውያኑ በአስተዳደሩ ስር በምትገኘው የቃየሌ ከተማ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ እንዳሉ በነዋሪወች በተደረገ ጥቆማ ሊያዙ መቻላቸውን እንደገለጹ ዘስታር የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧልል። የኬንያ ፖሊስ ምንም የጉዞ ሰነድ አልያዙም በተባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ ምርመራ መጀመሩን በመግለጽ ወኪል የተባለውን አካል ለመያዝ ፍለጋ እያካሄደ እንደሚገኝ ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። በህገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ገብተዋል የተባሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከአስር እስከ ሃያ አምስት አመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ መሆናቸው ታውቋል። ከሃገሪቱ በመሰደድ ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ወደ ተለያዩ ሃገራት የመሰደድ እቅድ እንዳላቸው ታውቋል። የኬንያ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ወደ ሃገሪቱ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውን ቁጥር መጨመርን ተከትሎ በድንበር አካባቢ አዳድስ የቁጥጥር ኬላወችን ቢያቋቁሙም የስደተኞችን ፍልሰት ሊቀንስ እንደሚችል ተገልጿል። የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ የገንዘብ ድጋፍ እያሳሰበ መሆኑን ይገልፃሉ።
በኬንያ ህወገጥ የተባሉ አርባ ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
Write a brief headline summarizing the article below.
የካቲት ዘጠኝ ቀንአመተ ምህረትኢሳትዜና በስልጣን ላይ ያለውን የህወሃት ኢህአደግ መንግስት በሃይል ለመጣል የሚንቀሳቀሱት ሶስቱ የአፋር ድርጅቶች ማለትም አርዱፍ ጋድሌና የአፍደራ ታጋዮች የካቲት ቀን አም የጋራ ግንባር ፈጥረዋል። አድሱ ግንባር ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ለመታገል ፍላጎት እንዳለውም አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል። የአርዱፍ ሊቀመንበር አቶ ኢብራሂም ሙሳ ለኢሳት እንደገለጹት ሶስቱም የአፋር ድርጅቶች በተናጠል ሆነው መዋጋታቸው ለስርአቱ እድሜ መርዘም አስተዋጽኦ በማድረጉ በቅድሚያ ድርጅቶቹ የጋራ ግንባር ፈጥረው በጋራ ለመዋጋት አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ በመድረሳቸው በአንድ ወታደራዊ እዝ ስር ሆነው ለመታገል ወስነዋል። ድርድሩ የተካሄደው በአፋር ህዝብ ፓርቲ በኩል መሆኑንም ለማወቅ ተችሎአል። ከአቶ ኢብራሂም ሙሳ ጋር የተደረገው ቃለምልልስ ከዜናው በኋላ ይቀርባል።
በትጥቅ ትግል የሚያምኑ ሶስት የአፋር ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ
Create a short title for the given news content.
በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢወች በሚገኙ ደረቅ ወደቦች ንብረት እንድጭኑ ለተከማቹ ኮንቴይነሮች የመያዣ ኪራይ ድመሬጅ እና የመጋዘን ኪራይ መንግስት በየአመቱ እስከ አስር ሚሊዮን ዶላር እንድከፍል መገደዱን የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ገለጸ። ይህንን ለማድረግ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የገቢወችና ጉምሩክ ባለስልጣን የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎትና አስመጭወች በጋራ መክረው የሚያመነጩትን የመፍትሄ ሃሳብ ደግሞ መንግስት ተቀብሎ ሊደግፍ እንደሚገባ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን አበራ በሰጡት ምላሽ በደረቅ ወደቦች ሳይነሱ የተከማቹ ንብረት የጫኑ ኮንቴይነሮች በመቶ የሚሆኑት የሌሎች አገሮች የመርከብ ኩባንያወች ንብረት መሆናቸውን ገልጸዋል። ቋሚ ኮሚቴው የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የስራ አፈፃጸሙን ለመገምገም ባካሄደው ውይይት ላይ የተቋሙ ተቆጣጣሪ የመንግስት አካላት እንድገኙ ያደረገ በመሆኑ የተቆጣጣሪ ተቋማቱ አመራሮች የተገለጸው የኮንቴይነሮች ክምችት አሳሳቢና አገራዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል። ከ ቀናት በኋላ በደረቅ ወደቦች የቆዩ ንብረት የጫነ ኮንቴይነሮችና ተሽከርካሪወች በኢትዮጵያ ገቢወችና ጉምሩክ ባለስልጣን ተወርሰው በሽያጭ መወገድ እንደሚገባቸው በህግ ቢደነገግም ኮንቴይነሮች በደረቅ ወደቦች በከፍተኛ መጠን መከማቸታቸው መቀጠሉ ለምን እንደሆነ ቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ ጠይቋል። ኮንቴይነሮቹ የተጫነባቸው ንብረት ተራግፎ ለሌላ ጭነት መዘጋጀት ሲኖርባቸው ወይም ለባለቤቶቹ መመለስ ሲገባቸው በደረቅ ወደቦች ውስጥ እንደ እቃ መጋዘንነት እያገለገሉ መሆኑን ጠቁመዋል። አስመጭወች ንብረታቸውን ማንሳት አለመቻላቸው ዋናው የችግሩ መንስኤ መሆኑን ጠቁመው በአስመጭወቹ በኩል የሚነሳው ችግር ንብረትን ለማንሳት የሚያስፈልገውን የቀረጥ ክፍያ ለመክፈል የገንዘብ እጥረት እንዳለባቸው በሌላ በኩል ደግሞ ንብረቱን ካስመጡ በኋላ ገበያ የማጣት ችግር እንዳለባቸውም የሚያወሱ መሆናቸውን ዘርዝረዋል። ኮንቴይነሮቹ ባለመመለሳቸው የኮንቴይነር መያዣና የደመሬጅ ክፍያ ያላግባብ እየወጣ መሆኑን እንደ አገርም በየአመቱ ከ ሚሊዮን ዶላር እስከ አስር ሚሊዮን ዶላር እንደሚወጣ አስረድተዋል። ለአጭር ጊዜ መፍትሄ ግን መንግስት ከአለም ባንክ ካገኘው ሚሊዮን ዶላር በደረቅ ወደቦች መጋዘኖች በመገንባት ኮንቴይነሮችን በማራገፍ ክምችት ለማስቀረት ፕሮጀክት ተቀርጾ በትግበራ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ቋሚ ኮሚቴውም ይህንኑ በማንሳት የሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅትና የተቋሙ ተቆጣጣሪ የሆነው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ክልሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የመጨረሻ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባው አሳስቧል።
በደረቅ ወደቦች እቃ ጭነው ለተከማቹ ኮንቴይነሮች ኪራይ መንግስት በየአመቱ እስከ አስር ሚሊዮን ዶላር ይከፍላል ተባለ
Provide a news headline based on the following text.
አድስ አበባ፣ ታህሳስ አንድ፣ ሁለት ሽህ ኤፍ ቢ ሲ በካናዳ የኢፌደሪ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከካናዳ የጠቅላይ ሚኒስትር የውጭና የመከላከያ ፖሊሲ አማካሪ ደቪድ ሞሪሰን ጋር ተወያዩ። ቡድኑን ለማስወገድ የተወሰደ የህግ ማስከበር ዘመቻ ንጹሃን ዜጎች ሳይጎዱ በጥንቃቄ መካሄዱን እና መጠናቀቁን አስረድተዋል። በስፍራው ማህበራዊ ድጋፍ የማቅረብና የመልሶ ማቋቋም ስራ እየተካሄደ ስለ መሆኑም ገልጸዋል። የጁንታው ቡድን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የሚካሄደውን አጠቃላይ ሃገራዊ ሪፎርም ለማበላሸት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። ወንጀለኛ ቡድኖችን በማደን ወደ ህግ ለማቅረብ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነውም ብለዋል። ደቪድ ሞሪሰን በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው ሃገራቸው ለውጡን ደግፋ የምታግዝ መሆኗን አሳውቀዋል። የተጎዱ መሰረተልማቶችን በፍጥነት ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። አምባሳደሯ የህወሃት ጁንታ የሃገሪቷን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር መመዝበሩን አንስተዋል። በቪድዮ ኮንፍረንስ በተካሄደው ውይይት አምባሳደር ናሲሴ ስለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃወችን ለማግኘት፡ የፋና ድረ ገጽ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃወችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን።
አምባሳደር ናሲሴ ከካናዳ የጠቅላይ ሚኒስትር የውጭና የመከላከያ ፖሊሲ አማካሪ ደቪድ ሞሪሰን ጋር ተወያዩ
README.md exists but content is empty.
Downloads last month
5