text
stringlengths
26
19k
የፎቶው ባለመብት EPA-EEE/REX/SHUTTERSTOCK-በሁቲዎች ጥቃት የሰመጠችው የመጀመሪያዋ መርከብ ሩቢይማር-የየመን ሁቲዎች አማጺያን በቀይ ባሕር በኩል በሚያቋርጡ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸም ከመጀመሩ ከወራት በኋላ የመጀመሪያዋ ግዙፍ መርከብ ሰመጠች።-በብሪታኒያ የተመዘገበችው የጭነት መርከብ ማዳበሪያ ጭና በቀይ ባሕር በኩል ለማቋረጥ ስትሞክር ነበር ከሁለት ሳምንት በፊት በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ በሁቲ ታጣቂዎች ሚሳኤል ተመትታ የቆመችው።-የየመን መንግሥት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ሪቢይማር የተባለችው መርከብ ጥቃት ከተፈጸመባት በኋላ ውሃ ወደ ውስጧ እየገባ ለቀናት በባሕሩ ላይ ስትዋልል ቆይታ ሰምጣለች።-በኢራን የሚደገፉት ሁቲ አማጺያን ካለፈው ኅዳር አንስቶ በቀይ ባሕር የሚያቋርጡ መርከቦችን ዒላማ ማድረግ ከጀመሩ ወዲህ ይህች መርከብ ጥቃት ከተፈጸመባቸው መካከል በመስመጥ የመጀመሪያዋ ሆናለች።-የሰመጠችው መርከብ ማዳበሪያ ጭና እየተጓዘች ሳለ ነው በሁቲዎች ሚሳኤል የተመታችው። የመርከቧ መስመጥ በቀይ ባሕር ላይ “የተፈጥሮ አካባቢ ጉዳትን” የሚደቅን ነው ሲሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።-ሩቢይማር የተባለችው ይህች መርከብ በኤደን ባሕረ ሰላጤ በኩል ባብ ኤል መንደብ አቅራቢያ ሳለች ነው በየመን ሁቲ አማጺያን በተተኮሱ ሁለት ሚሳኤሎች የተመታችው።-ከአስር ቀናት በፊት የብሪታኒያ መንግሥት መርከቧ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ወደ ውስጧ ውሃ እየሰረገ መሆኑን እና 24 የመርከቧ ሠራተኞችን ማትረፍ መቻሉን ገልጾ ነበር።-ከአንድ ሳምንት በፊት ቢቢሲ ያገኘው ምሥል ላይ የተወሰነ የመርከቧ ክፍል በውሃ ተውጦ ቀሪው ክፍል በውሃ ላይ እየተንሳፈፈ ያሳይ ነበር።-የመርከቧ ባለቤቶች በወቅቱ መርከቧ ተጎትታ በአቅራቢያ ወደሚገኘው የጂቡቲ ወደብ እየተወሰደች መሆኗን፣ ነገር ግን ልትሰምጥ እንደምትችል አመልክተው ነበር።-መርከቧ በብሪታኒያ ተመዝግባ በአንድ የሊባኖስ ተቋም አማካይነት ስትንቀሳቀስ የቆየች ናት። ጥቃቱ በተፈጸመባት ጊዜም አሞኒየም ናይትሬት የተባለውን ማዳበሪያ ጭና እንደነበር ተነግሯል።-በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና ያለው የየመን መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ቢን ሙባራክ፣ የመርከቧን መስመጥ “አጋጥሞ የማያውቅ የአካባቢ አደጋ ነው” ሲሉ ገልጸውታል።-በዓለም ዙሪያ ላሉ የውሃ አካላት ደኅንነት የሚከራከረው የአካባቢ ጥበቃ ተከራካሪው ግሪን ፒስ በበኩሉ የአሞኒየም ናይትሬት ማዳበሪያው ወደ ባሕሩ መግባት “ከውሃ በታች ባለው ሥነ ምኅዳር ላይ ከፍተኛ ተጽእኖን ይፈጥራል” ብሏል።-ሁቲዎች በጋዛ ውስጥ ላሉ ፍልስጤማውያን ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ካለፈው ኅዳር ጀምሮ በቀይ ባሕር እና በኤደር ባሕረ ሰላጤ በኩል በሚያቋርጡ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው ባሏቸው መርከቦች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ነው።-ለዚህም ምላሽ አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም የመን ውስጥ በሚገኙ የሁቲ ይዞታዎች ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን ፈጽመዋል።-ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ኪንግደም የባሕር ላይ ንግድ ተቋም ቅዳሜ ዕለት እንዳሳወቀው፣ ከየመኗ ወደብ ሞካህ በስተ ምዕራብ አንዲት መርከብ ላይ ጥቃት እንደተፈጸመ ሪፖርት ደርሶታል።-ጨምሮም “የመርከቧ ሠራተኞች መልህቋን እንድትጥል አድርው በወታደራዊ ባለሥልጣናት ከመርከቧ እንዲወጡ ተደርገዋል” ብሏል።-የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ “እራስን ለመከላከል በተወሰድ እርምጃ” ከየመን በኩል በሁቲዎች ሊተኮስ ተዘጋጅቶ የነበረ ከምድር ወደ አየር የሚወነጨፍ ሚሳኤልን መምታቱን አሳውቋል።-ወታደራዊ ማዘዣው ሊወነጨፍ የነበረው ሚሳኤል በአሜሪካ አውሮፕላን ላይ አሳሳቢ ስጋትን ደቅኖ እንደነበር አመልክቷል።-የአማጺያኑ ጥቃት የዓለም የባሕር ላይ ንግድ 12 በመቶው በሚዘዋወርበት በወሳኙ የቀይ ባሕር በኩል የሚያቋርጡ የግዙፍ የጭነት መርከብ ኩባንያዎች መስመራቸውን እንዲቀይሩ አስገድዷል።-ምንም እንኳን በአሜሪካ የሚመራው የባሕር ኃይል ጥምረት አገራት በሁቲ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸም ከጀመሩ አንድ ወር ቢያልፋቸውም፣ አማጺያኑ አሁንም በመርከቦች ላይ ከባድ ጥቃቶችን የመፈጸም አቅም እንዳላቸው አሳይተዋል።-ሁቲዎች በቀይ ባሕር ላይ በሚተላለፉ የምዕራባውያን መርከቦች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት የሚያቆሙት፣ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ውስጥ በሐማስ ላይ የምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ ስታቆም መሆኑን አሳውቀዋል።
የፎቶው ባለመብት EPA-ለስድስት ሳምንታት በሚደረግ የተኩስ አቁም ጋዛ ፋታ ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል-አምስት ወራት ያስቆጠረውን የእስራኤል ጋዛ ጦርነትን ጋብ ለማድረግ በሚያስችል ንግግር ላይ ለመሳተፍ የሐማስ ልዑካን ግብፅ ካይሮ መግባታቸውን ተከትሎ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ይደረሳል የሚል ተስፋ ተፈጥሯል።-ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን እስራኤል “ከሞላ ጎደል” የተኩስ አቁም ስምምነቱን መቀበሏን ገልጸዋል።-አሁን ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የስድስት ሳምንታት የተኩስ አቁም ስምምነት ተጨማሪ እስራኤላውያን ታጋቾች እና ፍልስጤማውያን አስረኞች ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።-ሁለቱ ወገኖች ተኩስ እንዲያቆሙ የሚደረገው ግፊት የተጠናከረው ባለፈው ሐሙስ ጋዛ ውስጥ እርዳታ በጫኑ ተሽከርካሪዎች ዙሪያ ከተሰበሰቡ ሰዎች መካከል ቢያንስ 112 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ ነው።-የምግብ እርዳታ ለመቀበል በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ የእስራኤል ወታደሮች ተኩስ ከፍተዋል ሲል ሐማስ ከሷል። እስራኤል ግን ይህንን ክስ በማስተባበል ወታደሮቿ ሊወሯቸው በመጡ “በርካታ ሰግለሰቦች ላይ” መተኮሳቸውን በመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ መረዳቷን እና አብዛኞቹ ሰዎች የሞቱት በግርግር ምክንያት በተፈጠረ መረጋገጥ ነው ብላለች።-ከኳታር ጋር በመሆን በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚካሄደውን ንግግር የሚመሩት የግብፅ ባለሥልጣናት የሐማስ እና የአስራኤል ተወካዮች በድርድሩ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።-በሚቀጥሉት ከ24 አስከ 48 ሰዓታት ባለው ጊዜ ውስጥ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ሊደረስ እንደሚችል ሐማስ መናገሩ ተዘግቧል። አንድ የቡድኑ ምንጭ ለግብፅ መገናኛ ብዙኃን ስምምነቱ የሚሰምረው እስራኤል የሐማስን ጥያቄዎች ከተቀበለች እንደሆነ ገልጿል።-አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለስድስት ሳምንታት በሚቆየው የተኩስ አቁም ማዕቀፍ ላይ እስራኤል “ስምምነት” ማሳየቷን ማረጋገጣቸውን ተከትሎ የተኩስ አቁሙ ዕውን እንደሚሆን ተስፋ ተጥሏል።-ባለፈው መስከረም 26 ሐማስ በደቡባዊ እስራኤል ላይ ጥቃት ፈጽሞ 1200 ሰዎችን በመግደል 253 የሚሆኑትን ደግሞ አግቶ ወደ ጋዛ ከወሰደ በኋላ እስራኤል ሐማስን ለማጥፋት መጠነ ሰፊ የምድር እና የአየር ጥቃቶችን እያካሄደች ነው።-ሐማስ የሚመራው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር እንደሚለው በእስራኤል ጥቃት አስካሁን 21000 ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ 30410 ሰዎች መገደላቸውን፣ 71700 መቁሰላቸውን እንዲሁም 7000 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።-የተኩስ አቁም እንዲደረግ ግፊቱ የበረታው የእርዳታ ድርጅቶች በሰሜናዊ ጋዛ የረሃብ አደጋ ስጋት እንዳንዣበበ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ ነው።-የኖርዌይ ስደተኞች ካውንስል ኃላፊ ያን ኤግላንድ በጋዛ ለሦስት ቀናት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው ከተመለሱ በኋላ ለቢቢሲ ዛሬ እሁድ እንደተናገሩት፣ የከፋ ነገር ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።-“ነዋሪዎች እየተራብን ነው፤ ልናልቅ ነው” በማለት እርዳታ ሲለምኑ እንዳዩ እና በሰሜን ጋዛ ረሃብ መኖሩን አመልክተዋል። አስራኤል እርዳታ እንዲገባ ስላለፍቀደች በስፍራው 300 ሺህ ሰዎች በፍርስራሾች ውስጥ በችግር ላይ ይገኛሉ ብለዋል።-ባለፈው ሐሙስ ከአንድ መቶ በላይ እርዳታ የሚጠብቁ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ፣ አሜሪካ ቅዳሜ ዕለት የመጀመሪያውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ከሦስት የጭነት አውሮፕላኖች ላይ በፓራሹት ወደ ጋዛ አውርዳለች።-እስራኤል በበኩሏ ዛሬ እሁድ ጠንካራ የአየር ድብደባዎችን በደቡባዊቷ የጋዛ ከተማ ኻን ዩኒስ ላይ መፈጸሟን ገልጸላች። ስለደረሰው ጉዳት ግን አስካሁን የታወቀ ነገር የለም።-ትናንት ቅዳሜ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን በተጠለሉበት በደቡባዊ ጋዛ የራፋህ ካምፕ ላይ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 11 ሰዎች መገደላቸውን ሐማስ አስታውቋል።-የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጥቃቱን “አስደንጋጭ” ያሉት ሲሆን፣ የእስራኤል ሠራዊት ደግሞ ጥቃቱ በእስላማዊ ጂሃድ ታጣቂዎች ላይ “ያነጣጠረ ነው” ብሏል።
የፎቶው ባለመብት Reuters-የአሜሪካ የእርዳታ አቅርቦት ከአየር ላይ ሲወርድ-አሜሪካ ለጋዛ የመጀመሪያውን ሰብአዊ እርዳታ ከ30 ሺህ በላይ ምግቦችን በሦስት ወታደራዊ አውሮፕላኖች አማካይነት በፓራሹት ከአየር ላይ ማቅረቧን አስታወቀች።-ከዮርዳኖስ አየር ኃይል ጋር በጥምረት የተካሄደው ይህ ድጋፍ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለጋዛ ይሰጣል ተብሎ ከታወጀው የመጀመሪያው ነው።-ሐሙስ ዕለት ሕዝቡ ከመኪና ላይ እርዳታ ለመቀበል ሲሞክር ቢያንስ 112 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ፕሬዝዳንቱ እርዳታውን ለማጠናከር ቃል ገብተው ነበር።-የአየር ድጋፉ ወደ ጋዛ የተላከው አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን በጋዛ ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ዕቅድ መኖሩን ከተናገሩ በኋላ ነው።-የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣን ቅዳሜ ዕለት እንደተናገሩት እስራኤል አዲሱን የተኩስ አቁም ስምምነት “ይብዛም ይነስም ተቀብላለች” ብለዋል።-“ሐማስ የተጋላጭ ታጋቾችን ማለትም የታመሙትን፣ የቆሰሉትን፣ አዛውንቶችን እና ሴቶችን ለመልቀቅ ከተስማማ ከዛሬ ጀምሮ በጋዛ ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነትተፈጻሚ ይሆናል”ሲሉ ስማቸው ያልተጠቀሰው ባለሥልጣን ተናግረዋል።-ሸምጋዮቹ ዛሬ እሁድ በካይሮ ይሰባሰባሉ። የግብፅ ባለሥልጣናት የሐማስ እና የእስራኤል ልዑካን ለድርድር ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።-አንድ ባለሥልጣን እንደተናገሩት በስምምነቱ ዙሪያ አንዳንድ ቴክኒካዊ ጉዳዮች አሁንም መፍትሄ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል።-ለምሳሌ ምን ያህል የፍልስጤም እስረኞች በሐማስ በተያዙ ታጋቾች ምትክ እስራኤል ትለቃለች የሚለው አንዱ ነው።-ቅዳሜ ዕለት ሲ-130 የተባሉ የማጓጓዣ አውሮፕላኖች በጋዛ የባሕር ዳርቻ ላይ ከ30 ሺህ በላይ ምግቦችን ከአየር ወደ መሬት መጣላቸውን የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።-“ይህ የአየር እርዳታ አቅርቦት በተሽከርካሪ የመገባውን የእርዳታ ፍሰት ማስፋትን ጨምሮ ወደ ጋዛ ተጨማሪ እርዳታ ለማስገባት የሚደረጉ ቀጣይ ጥረቶች አካል ነው” ሲል አክሏል።-የፎቶው ባለመብት Reuters-ከአንድ መቶ በላይ እርዳታ ጠባቂዎች ከተገደሉበት ጥቃት በርካቶች ቆስለው በህክምና ላይ ናቸው-ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ ግብፅ እና ዮርዳኖስን ጨምሮ ሌሎች አገራት በተመሳሳይ መንገድ እርዳታ ወደ ጋዛ ያደረሱ ሲሆን፣ ይህ ግን ለአሜሪካ የመጀመሪያዋ ነው።-የአሜሪካ አስተዳደር ባለሥልጣናት የሐሙሱ “አሳዛኝ ክስተት፣ ለአስከፊው የሰብአዊ ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት የሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲደርስ ማስፋፋት እና ማስቀጠል ያለውን ጠቀሜታ” አጉልቶ አሳይቷል ብለዋል።-የእርዳታ ድርጅቶች ከአየር ላይ ወደ መሬት የእርዳታ አቅርቦትን መጣል በችግር ላይ ላሉት የጋዛ ነዋሪዎች ከሚያስፈልገው ድጋፍ አንጻር በቂ እና አስተማማኝ አይደሉም ብለዋል።-የጋዛ ከተማ ነዋሪው ሜድሃት ታሄር ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገረው እንዲህ ዓይነቱ ዘዴ ለሚጠበቀው እርዳታ በቂ ምላሽ አይደለም።-“ይህ ለትምህርት ቤት በቂ ይሆናል? ይህ ለ10 ሺሀ ሰዎች በቂ ነው? እርዳታን በድንበር በኩል መላክ በፓራሹት ከአየር ከማውረድ የተሻለ ነው” ብሏል።-ፕሬዝዳንት ባይደን አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ “የጋዛ ነዋሪዎች የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እንዲያገኙ ብዙ የጭነት መኪናዎችን እና በርካታ መንገዶችን እንድታመቻች እስራኤልን አጥብቀን እንጠይቃለን” ብለዋል።-የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ የእስራኤል የጦር ካቢኔ አባል የሆኑትን ቤኒ ጋንትዝን ሰኞ ዕለት ዋሽንግተን ውስጥ እንደሚገናኙ አንድ የዋይት ሐውስ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።-በሐሙሱ ክስተት በጋዛ ከተማ ደቡብ ምዕራብ ጫፍ ላይ የእርዳታ መኪኖችን የከበቡ 112 ሰዎች ሲገደሉ ከ760 በላይ ቆስለዋል።-በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ በመክፈቷ የፍልስጤማውያኑ ሕይወታቸው ማለፉን ጠቅሶ ሐማስ ቢከስም ቴል አቪብ ግን የማስጠንቀቂያ ጥይት ሲተኮስ በተፈጠረ መረጋገጥ አደጋው መድረሱን ገልጻለች።-በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ (ኦቻ) የጋዛ ንዑስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጊዮርጊዮስ ፔትሮፖሎስ እርሳቸው እና ወደ አል-ሺፋ ሆስፒታል የተላከው ቡድን በጥይት የተጎዱ በርካታ ሰዎችን ማግኘታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።-ሐማስ በበኩሉ ቅዳሜ ዕለት በደቡባዊ ጋዛ በራፋህ በሚገኝ የመጠለያ ጣቢያ ላይ በእስራኤል በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት በትንሹ 11 ሰዎች መገደላቸውን ተናግሯል።-የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጥቃቱን “አስደንጋጭ” ሲሉ ጠርተውታል። የእስራኤል ጦር በበኩሉ በአካባቢው በሚገኙ እስላማዊ ጂሃድ ታጣቂዎች ላይ “ዒላማውን የጠበቀ ጥቃት” ፈጽሜያለሁ ብሏል።-የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በጣም ትንሽ እርዳታ ባገኘችው እና 300 ሺህ የሚገመቱ ሰዎች በአነስተኛ ምግብ ወይም ውሃ በሚኖሩባት ሰሜናዊ ጋዛ ውስጥ ረሃብ ሊፈጠር እንደሚችል አስጠንቅቋል።
የፎቶው ባለመብት EPA-ቅዳሜ ዕለት ተከታታይ የሪፐብሊካን ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ውድድርን ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ፣ የፓርቲው ዕጩ ለመሆን ተቃርበዋል።-ከድላቸው በኋላም ተቀናቃኛቸውን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ስደተኞች ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ መንገድ ከፍተዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል።-የቀድሞው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሚዙሪ፣ ሚቺጋን እና አይዳሆ የውክልና ድምጽ ሰጪዎችን [ካውከስ] ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በማግኘት አሸነፈዋል።-የ77 ዓመቱ ትራምፕ በቨርጂኒያ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለደጋፊዎቻቸው እንደተናገሩት “ለሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ሆነው ለመቅረብ እንደሮኬት እየተተኮስኩ ነው” ብለዋል።-በሚቀጥለው ሳምንት ዕጩ መሆናቸውን እንደሚያረጋግጡም ይጠበቃል።-በውድድሩ የቀሩት ብቸኛ ተቀናቃኛቸው የቀድሞዋ የደቡብ ካሮላይና ገዢ ኒኪ ሄሊ እስካሁን አንድም ድል አላስመዘገቡም።-የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር የሆነው ሲቢኤስ እንደዘገበው ከሆነ በሚዙሪ እና በአይዳሆ የሚገኙትን ሁሉንም ውክልናዎች እና በሚቺጋን የቀሩትን ሁሉ ትራምፕ እንደሚያሸንፉ ገምቷል።-በእነዚህ ግዛቶች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ልዑካን ትራምፕ አሳማኝ በሆነ መንገድ ካሸነፉበት የመጀመሪያ ውድድር በኋላ በዚህ ሳምንት መጀመሪያም የሚፈልጉትን ድል አግኝተዋል።-ልዑካን የሚባሉት በፓርቲያቸው ብሔራዊ ጉባኤ ላይ ክልላቸውን ወይም አካባቢያቸውን የሚወክሉ እና ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ማን እንደሚሆን የሚወስኑ ናቸው።-ትራምፕ እስካሁን 247 የሪፐብሊካን ተወካዮችን ድጋፍ ማግኘታቸውን ሲቢኤስ ዘግቧል። ሄሊ 24 ብቻ ነው ያሳኩት።-ቅዳሜ ዕለት በቨርጂኒያ ዋና ከተማ ሪችመንድ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ትራምፕ በአካቢው የስብሰባ ማዕከል ሲናገሩ ለመስማት ለብዙ ሰዓታት ተሰብስበው ቆይተዋል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-15 ግዛቶች ፕሬዝዳንታዊ ዕጯቸውን በሚመርጡበት በዕለተ ማክሰኞ “ትልቅ ድል” በማስመዝገብ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ለመሆን ከጫፍ የሚያደርሳቸውን ውጤት እንደሚያስመዘግቡ ቃል ገብተዋል።-“ዛሬ የማይታመኑ ቁጥሮችን አግኝተናል” ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።-በቨርጂኒያ እና ቀደም ሲል ደግሞ በሰሜን ካሮላይና በተካሄደው ዝግጅት ላይ ያደረጉት ንግግር በአብዛኛው ያተኮረው በዩናይትድ ስቴትስ-ሜክሲኮ ድንበር ላይ ስላለው የፍልሰተኞች ጉዳይ ነው።-ይህም የደጋፊዎቻቸው ትልቅ ትኩረት መሆኑ ታይቷል። ቅዳሜ ዕለት ሃሳባቸውን ለቢቢሲ የሰጡ ከደርዘን በላይ የሚቆጠሩ የትራምፕ ደጋፊዎች ጉዳዩ ቀዳሚ ስጋታቸው እንደሆነ ተናግረዋል።-እአአ በ2018 ልጇን ሺንን ፌንታኒል የተባለ መድኃኒትን ከመጠን በላይ በመውሰድ ያጣችው ሻሮን ሮበርትስ “ከቁጥጥር ውጭ” የሆነ ድንበር ሌሎች ቤተሰቦችም በተመሳሳይ የሚወዷቸውን እንዲያጡ ያደርጋል የሚል ስጋት ጭሮባታል።-“እኔ ድጋፌ 100 በመቶ ለትራምፕ ነው። ምክንያቱም እሱ እነዚህን ድንበሮች ይዘጋቸዋል” ስትል ተናግራለች።-ባይደን እና ትራምፕ ባለፈው ሳምንት የድንበር አካባቢዎችን ከጎበኙ በኋላ፣ ትራምፕ በቀጥታ ችግሩን ወደ ባይደን በመውሰድ እንደገና ተጠያቂ አድርገዋቸዋል።-ፕሬዝዳንት ባይደን ሆን ብለው ስደተኞችን ከሜክሲኮ ድንበር እንዲሻገሩ እያበረታቱ ነው የሚል የሴራ ሃሳብ በመሰንዘር ትራምፕ ባይደንን ከሰዋል።-“ባይደን እና ግብረ አበሮቹ የአሜሪካን ሥርዓት በማፍረስ፣ የእውነተኛ የአሜሪካ መራጮችን ፍላጎት ውድቅ በማድረግ እና ትውልድን የሚቆጣጠሩበት አዲስ የኃይል መሠረት ማቋቋም ይፈልጋሉ። በሚቀጥለው ምርጫ ድምጽ እንዲሰጡ ለማስመዝገብ እየሞከሩ ነው” ብለዋል ትራምፕ።-ለዚህም ከባይደን የምርጫ ዘመቻ ቡድን ፈጣን ምላሽ ተሰጥቶታል። የቡድኑ ቃል አቀባይ አማር ሙሳ የሁለትዮሽ የኢሚግሬሽን ሕግን በመጥቀስ “ትራምፕ በድጋሚ ለብዙ አሥርተ ዓመታት ፍትሃዊ እና ከባድ የሆነውን የድንበር ደኅንነት ሕግን ገድሏል ከሚለው እውነታ የአሜሪካን ሕዝብ ለማዘናጋት እየሞከረ ነው። ምክንያቱም ይህ ዘመቻውን ይረዳል ብለው ስለሚያምኑ ነው” ብለዋል።-ቅዳሜ ዕለት የተለቀቀው አዲስ የኒውዮርክ ታይምስ እና የሲዬና የሕዝብ አስተያየት እንዳመለከተው 48 በመቶ አሜሪካውያን መራጮች ትራምፕን እንደሚደግፉ ገልጸው፤ ለአሁኑ ፕሬዝዳንት ድጋፋቸውን የሚሰጡት 43 በመቶ ናቸው። ከሁለቱ ወገኖች መካከል በባይደን ላይ ጠንካራ ቅሬታዎችን መኖራቸው ተለይቷል።-በሪችመንድ ሰልፍ ላይ ትራምፕ ወደ ምርጫው ጣቢያ ጠቁመው ደጋፊዎቻቸው ማክሰኞ ዕለት ግልጽ “መልዕክት እንዲያስተላልፉ" አሳስበዋል። ባገኙት ድጋፍም “አከብራችኋለው” ብለዋል።-በምርጫው ግን 45 በመቶ የሚሆኑት መራጮች ሄሊን ሲመርጡ 35 በመቶዎቹ ደግሞ የወቅቱን ፕሬዝዳንት እንደሚደግፉ አሳይተዋል።-“በአጠቃላይ ምርጫ ጆ ባይደንን በሁለት አሃዝ አሸንፌአለሁ። ትራምፕ ግን ከዚህ ውጪ ናቸው” ሲሉ ሄሊ የሕዝብ አስተያየቱ ውጤት ይፋ ተደረጎ ብዙም ሳይቆይ ተናግረዋል።-ትራምፕ በሪችመንድ ባደረጉት ንግግር ሄሊን ላይ አነጠጥረው ሪፐብሊካኖች በኅዳር ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የጀርመን ወታደሮች-ጀርመን የጦር መኮንኖቿ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን ስለመስጠት እና ጥቃት ስለሚፈጸምባቸው የሩሲያ ዒላማዎች ሲወያዩ የሚሰማበት ስብሰባ የድምጽ ቅጂ በሩሲያ መጠለፉን አመነች።-በቪዲዮ የተካሄደው የወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባው የድምጽ ቅጂ በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ይፋ የተደረገው በሩሲያ መንግሥት የሚተዳደረው የቴሌቪዥን ጣቢያ አርቲ ሥራ አስኪያጅ ነው።-ሩሲያ ከዩክሬን በኃይል የነጠቀችውን ክራይሚያን ከሩሲያ ጋር የሚያገናኘውን ኬርች የተባለው ድልድይ እንዴት በሚሳኤል ሊመታ እንደሚችል የጀመርመን መኮንኖች ሲወያዩ ይሰማል።-የተጠለፈው ድምጽ ይፋ መሆንን ተከትሎ የሩሲያ ፖለቲከኞች “ደመኛ ጠላት” ያሏቸው ጥቃት እያቀዱ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።-የተጠለፈውን ድምጽ በተመለከተ የጀርመን መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ቅዳሜ ዕለት እንደተናገሩት “ክስተቱ ብርቱ ጉዳይ በመሆኑ በጣም በጥንቃቄ፣ በጥልቀት እና በፈጠነ ሁኔታ አሁን ምርመራ እየተደረገበት ነው” ብለዋል።-ዴር ስፒግል የተባለው የጀር መን መጽሔት እንደዘገበው በወታደራዊ መኮንኖቹ መካከል የተደረገው የቪዲዮ ኮንፈረንስ ደኅንነቱ በተጠበቀ የሠራዊቱ የግንኙነት መረብ ሳይሆን ዌብኤክስ በተባለ የበይነ መረብ መድረክ ላይ የተከናወነ ነው።-ባለ 38 ደቂቃው የተጠለፈ የድምጽ ቅጂ ይፋ ያደረገችው የሩሲያ መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ ኃላፊ ማርጋሪታ ሲሞንያን፣ ጀርመን ክራይሚያ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ዕያቀደች እንደነበር የሚያረጋግጥ ነው ብላለች።-በተጠለፈው የድምጽ ቅጂ ላይ የጦር መኮንኖቹ የዩክሬን ኃይሎች የጀርመን ሥሪት የሆኑትን ታውረስ የተባሉትን ሚሳኤሎች ስለሚጠቀሙበት ሁኔታ እና ስለሚኖረው ተጽእኖ ሲወያዩ ተደምጠዋል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-ታውረስ የተባለው ጀርመን ሠራሽ ሚሳኤል-የጀርመን የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የአየር ኃይል መኮንኖች ምሥጢራዊ ውይይት መጠለፉን ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል በማረጋገጥ፣ ነገር ግን ድምጹ ይፋ ከመሆኑ በፊት ማስተካከያ እንደተደረገበት ለማረጋገጥ እንደማይቻል ተናግረዋል።-የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛኻሮቫ ጀርመን በጉዳዩ ላይ “በአስቸኳይ” ማብራሪያ እንድትሰጥ ጠይቀዋል።-“ጥያቄውን ላለመመለስ የሚደረጉ ሙከራዎች [በድምጽ ቅጂው ላይ] የተባለውን ነገር እንደማመን ይቆጠራል” በማለት ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል።-የሩሲያ የደኅንነት ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፑቲን ቀኝ እጅ የሆኑት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ በቴሌግራም ላይ “የዘመናት ተቀናቃኞቻችን - ጀርመኖች - ደመኛ ጠላቶቻችን ሆነዋል” ሲሉ ጠንከር ያሉ ቃላትን ሰንዝረዋል።-“ጀርመኖች በእናት አገራችን እና በሕዝባችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ የሚያስችሉ ዒላማዎችን በጥንቃቄ እና በዝርዝር ግዛታችንን ስለማጥቃት ሲወያዩ እና ሲመርጡ ተመልከቱ” ብለዋል ከፍተኛው ባለሥልጣን።-የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ቅዳሜ ዕለት እንደተናገሩት ውይይቱ የጀመርመን ጦር ኃይሎችን “መሰሪ ዕቅድን” ያጋለጠ ዋነኛ ማስረጃ ነው ብለዋል።-ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለምታካሂደው ጦርነት 500 ኪሎ ሜትሮች ያህል በመጓዝ ጥቃት ማድረስ የሚችሉትን ታውረስ የተባሉትን ሚሳኤሎች እንድትሰጣት ትፈልጋለች።-የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ግን ሚሳኤሎቹን መስጠት ግጭቱን ሊያባብሰው ይችላል በሚል ፈቃደኛ ሳይሆኑ አስካሁን ቆይተዋል።-ፈረንሳይ እና ብሪታኒያ ግን 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያሉ ዒላማዎችን መምታት የሚችሉትን ስካልፕ ወይም ስቶርም የተባሉትን ሚሳኤሎችን ለዩክሬን አስታጥቀዋል።-የጀርመን ወግ አጥባቂ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ሮድሪክ ኪስዌተር ተጨማሪ የድምጽ ቅጂዎች ሳይጠለፉ አይቀርም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።-“በእርግጠኝነት ሌሎች በርካታ ውይይቶች በሩሲያ ተጠልፈዋል፤ በኋላ ላይ ለሩሲያ በሚጠቅም ሁኔታ ይፋ ሊደረጉ ይችላሉ” በማለት ለአንድ የጀርመን መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።-ጨምረውም የጦር መኮንኖቹ “ውይይት በዚህ ጊዜ በሩሲያ ሆን ተብሎ ይፋ የተደረገው አንዳች ዓይነት ፍላጎትን ለማሳካት” እንደሆነ የገመቱት ፖለቲከኛው፤ ይህም “ጀርመን ታውረስ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን እንዳትሰጥ ለማድረግ ነው” ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት BBC-ሊዮኒድ ዛኩተንኮ የተባለው መርዝ ሻጭ-በዩናይትድ ኪንግደም ቢያንስ 130 ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተውበታል የተባለውን መርዝ የሸጠውን ዩክሬናዊ ቢቢሲ ተከታትሎ ደርሶበታል።-ሊዮኒድ ዛኩተንኮ የተባለው ይህ ግለሰብ ራስ ማጥፋትን የሚያበረታታበት እንዲሁም አገልግሎቱን የሚያስተዋውቅበት ድረ ገጽ አለው።-ግለሰቡ ለቢቢሲም ምሥጢራዊ ዘጋቢ በየሳምንቱ አምስት እሽጎችን ወደ ዩናይትድ ኪንድም (ዩኬ) እንደሚልክ ተናግሯል።-ግለሰቡ ባለፈው ዓመት በቁጥጥር ስር ከዋለው እና በ14 የግድያዎች ወንጀል ከተከሰሰው ካናዳዊ ኬኔት ሎው ጋር ተመሳሳይ ንጥረ ነገር ሲያቀርብ ቆይቷል።-ቢቢሲ ንጥረ ነገሮቹን በተመለከተ ያቀረበለትን ጥያቄ ሊዮኒድ ውድቅ አድርጎታል።-ቢቢሲ ግለሰቡ ወደሚኖርበት ዩክሬን መዲና ኪዬቭ መኖሪያ ቤቱ ድረስ አቅንቶም ገዳይ የሆነውን ኬሚካል ስለመሸጡ ቢጠይቀውም አላመነም። ቢቢሲ የዚህን ንጥረ ነገር (ኬሚካል) ስም አይጠቅስም።-ግለሰቡ ባያምንም ነገር ግን ቢቢሲ በምርመራው ይህንን ገዳይ ንጥረ ነገር ለዓመታት ሲያቀርብ እንደቆየ አረጋግጧል።-ኬሚካሉ በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ሊሸጥ ይችላል፤ ነገር ግን ይህ የሚሆነው አሳማኝ ለሆኑ ግልጋሎቶች ብቻ ለሚጠቀሙ ኩባንያዎች ነው።-ንጥረ ነገሩን ለምን ተግባር እንደሚውል መሠረታዊ ምርመራ እና ፍተሻ ካላደረጉ በስተቀር አቅራቢዎች ለደንበኞች መሸጥ የለባቸውም።-ንጥረ ነገሩ በአነስተኛ መጠን ቢወሰድ እንኳን ለሞት ሊዳርግ ይችላል።-ሊዮኒድ ዛኩተንኮ የተባለው መርዝ ሻጭ-ባለፈው ዓመት ይህ ግለሰብ በለንደን ነዋሪ ለሆኑት መንታ እህትማማቾች ሊንዳ እና ሳራ መርዝ ከሸጠላቸው በኋላ ሕይወታቸው አልፏል።-የሁለቱ እህትማማቾች ቤተሰቦችም ስለዚህ ግለሰብ ሲያወሩ “በጭካኔ የተሞላ እና ክፉ ሰው ነው” ሲሉ ገልጸውታል።-ከእህትማማቾቹ አንዷ ሊንዳ ስለ መርዝ ሻጩ መረጃ ያገኘችው እውቅና ባለው ራስን የማጥፋት የውይይት መድረክ ላይ እንደሆነ እህቷ ሄለን ኪት ትናገራለች። እህቷ በጥቂት ፓውንድ የሞት ጽዋዋን እንደቀመሰች ተናግራለች።-ራሷን ስላጠፋችው የ54 ዓመት እህቷ ስትናገር “አሳቢ፣ አስተዋይ እና ጎበዝ ነበረች” ስትል ታስታውሳታለች።-እህቶቿም ሆነ ሌሎች በርካታ ራሳቸውን ያጠፉ ሰዎች ኬሚካሉን እንዳያገኙ ባለሥልጣናት የወሰዱት እርምጃ አለመኖሩን በመተቸት “ብሔራዊ ቅሌት” ነው ስትል ሄለን ውቀሳለች።-ግለሰቡ የሚሸጠው ኬሚካል እነ ሊንዳ በሚጠቀሙበት የበይነ መረብ መድረክ ላይ በግልጽ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን፣ አባላቶቹም እንዴት እንደሚገዙ እና እንደሚጠቀሙበት ምክር ይለዋወጣሉ።-በለንደን ኩዊን ሜሪ ዩኒቨርስቲ ሳይንቲስት የሆኑት ፕሮፌሰር አምሪታ አህሉዋሊያ በበኩላቸው ኬሚካሉ በዩናይትድ ኪንግደም ከአውሮፓውያኑ 2019 ጀምሮ ከተከሰቱት 130 ራስን ማጥፋቶች ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል።-ፕሮፌሰሯ በፖሊስ እና በላብራቶሪዎች የተላኩላቸውን ደም እና ሌሎች ናሙናዎችን በመመርመራቸው ነው እንዲህ ዓይነት ድምዳሜ ላይ የደረሱት።-ከመረመሯቸው 187 ናሙናዎች ውስጥ 71 በመቶው ገዳይ የሆነ ኬሚካል መኖሩን የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህን ቢያንስ 133 ሰዎች በዚህ ንጥረ ነገር እንደሞቱ የሚያሳይ ነው ተብሏል።-“አንድ ነገር ሊደረግ ይገባዋል” ሲሉም ፕሮፌሰሯ ያሳስባሉ።-“ለምን ጥቅም ላይ እንደሚውል ሙሉ ምርመራ ሊደረግ ይገባል። አጠቃቀሙ ለታለመለት ዓላማ ይውል ዘንድም ቁጥጥር መደረግ አለበት” ይላሉ።-የፎቶው ባለመብት Facebook-ምግብ አብሳይ የሆነው ካናዳዊው ኬኔት ሎው ባለፈው ዓመት በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በ14 የግድያ ወንጀሎች እና ራስን ማጥፋትን በማገዝ ክስ ቀርቦበታል።-ግለሰቡ ኬሚካሉን በዓለም ዙሪያ ባሉ 40 አገራት ሸጧል። ከ1 ሺህ 200 በላይ ሽያጮችን አካሂዷል የተባለው ይህ ግለሰብ፣ በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ራሳቸውን ባጠፉ 93 ሰዎች ሞት ውስጥም እጁ አለበት ተብሏል።-ቢቢሲ ባደረገውም ምርመራ ሊዮኒድ ዛኩተንኮ የተባለው ግለሰብ ከአውሮፓውያኑ 2020 ጀምሮ ተመሳሳይ ኬሚካል እየሸጠ መሆኑን አረጋግጧል።-በተጨማሪም በበይነ መረብ ላይ ራስን የማጥፋት መመሪያዎች ውስጥ የተካተቱ ሦስት የተለያዩ በህክምና ባለሙያ የሚታዘዙ መድኃኒቶችንም ያቀርባል።-ካናዳዊው ኬኔት ሎው ራስን ማጥፋት በሚያስተዋውቅበት የበይነ መረብ መድረክ ላይ ይህም ግለሰብ ለአጭር ጊዜ አገልግሎቱን ያስተዋውቅ ነበር።-ከዚያን ጊዜም ጀምሮ የመድረኩ ተጠቃሚዎች የእሱን አድራሻ በመልዕክቶች ይቀያየሩ ነበር።-ቢቢሲ ሊዮኒድ ዛኩተንኮንን ያገኘው በዩክሬን መዲና ኪዬቭ በሶቪዬት ኅብረት ዘመን በተሠራ ህንጻ ውስጥ በሚገኝ አነስተኛ የጋራ መኖሪያ ቤት ነው።-በርካታ እሽጎችንም ለመላክ በአካባቢው ፖስታ ቤት እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት ነው ቢቢሲ የተጋፈጠው።-ራሳቸውን ለማጥፋት ለሚፈልጉ ሰዎች ለምን መርዛማ ኬሚካል እንደሚልክም ተጠየቀ።-እጁን የቢቢሲ ካሜራን ለመሸፈን ከመሞከሩ በፊት “ይህ ውሸት ነው” በማለት ለማስተባበል ሞክሯል።-ቢቢሲም ዛኩተንኮንን በዚያች ቀን እሽግ እንዲልክለት መጠየቁን ተከትሎ ቢያንስ አንዱ እሽግ ኬሚካል እንደያዘ ለማረጋገጥ ችሏል።-ቤተሰቦቻቸውን በዚህ ኬሚካል ላጡ ሰዎች ምን ምላሽ አለህ? ተብሎ በቢቢሲ ሲጠየቅም “ስለምን እንደምታወሩ አልገባኝም” ሲል መልሷል።-ራሳቸውን ያጠፉት ቶም እና ጆ ኒሂል-ዴቪድ ፓርፌት የተባለ ግለሰብ የ22 ዓመት ልጁ ቶም ተመሳሳይ ኬሚካል ከኬኔት ሎው ገዝቶ ከሦስት ዓመታት በፊት ሕይወቱን አጥፍቷል።-ፓርፌት በአሁኑ ወቅት ከራስ ማጥፋት ጋር የተያያዙ የውይይት መድረኮችን ለማዘጋት እና እንደ ዛኩቴንኮ ያሉ መርዝ ሻጮችን ለማስቆምም ዘመቻ እያደረገ ይገኛል።-ሌላኛው የ23 ዓመት ጆ ኒሂል የተባለ ወጣት ሞት መንስዔን የመረመረው ባለሙያ ማስጠንቀቂያ ለብሪታንያ ባለሥልጣናት መድረሱን ተከትሎ ስለ ኬሚካሉም ሆነ በበይነ መረብ ላይ ስለሚፈጸመው የመርዝ ንግድ ከአውሮፓውያኑ መስከረም 2020 ጀምሮ እንደሚያውቁ ይፋ ሆኗል።-መርማሪው ለፖሊስ፣ ለአስከሬን መርማሪ ዋና ኃላፊ እንዲሁም ለኬሚካል አቅራቢዎች ስለ አደገኛው ንጥረ ነገር ንግድ አስጠንቅቆ ነበር።-ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በመላው ዩኬ የሚገኙ የአስከሬን መርማሪዎች ስለ ኬሚካሉ እና ራስን ስለ ማጥፋት እየተደረጉ ስላሉ የበይነ መረብ የውይይት መድረኮችን በተመለከተ አምስት ጊዜ ያህል ለተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ማስጠንቀቂያ ጽፈዋል።-ዴቪድ ፓርፌትም ባለሥልጣናቱ እሽጉን ያስቆሙት እንደሆነ ለማየት እና ሥርዓቱንም ለመፈተሽ ከዛኩተንኮ መርዛማውን ኬሚካል ገዝቷል።-እሽጉን ካዘዘ ከጥቂት ቀናት በኋላ ፖሊስ ደኅንነቱን ለመጠበቅ ጎበኝቶት ነበር። ነገር ግን ኬሚካሉ በሳምንታት ውስጥ የደረሰው ሲሆን፣ ፖሊስም እንደገና አልጎበኘውም።-“ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ እያወቅን አሁንም እንዲህ ዓይነት ነገር ይከናወናል ብሎ ማመን ከባድ ነው” ሲልም ተናግሯል።-ኬኔት ሎው በካናዳ ከታሰረ በኋላ በዩኬ ውስጥ ንጥረ ነገሩን በሚገዙ ሰዎች ላይ ተመሳሳይ የደኅንነት ማረጋገጫ ጉብኝቶች ተካሂደዋል።-የዩኬ የብሔራዊ ወንጀል ኤጀንሲ እንዳረጋገጠው ኬሚካሉን ከኬኔት ሎው ገዝተው ፖሊስ የደኅንነት ጥየቃ ካደረገ በኋላ የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጧል።-“እንዲህ አይነት ጉዳዮች የሚስተናገዱት በፖሊስ አባላት አማካይነት ፖሊሲያቸውን እና ብሔራዊ መመሪያዎችን ተከትሎ ነው” ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።-የሚወዷቸውን ሰዎች በኬሚካሉ የተነጠቁት ዴቪድ ፓርፌት እና ሄለን በእነዚህ የራስ ማጥፋት የውይይት መድረኮች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እንዲወሰድ እየጠየቁ ይገኛሉ።-የዩኬ መንግሥት በበኩሉ ባለፈው ዓመት የጸደቀው አዲሱ የበይነ መረብ ደኅንነት ሕግ እንደነዚህ ዓይነት የውይይት መድረኮችን በመገደብ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተናግሯል።
ባለፈው ሲቲ ከዩናይትድ ሲገናኙ ውሃ ሰማያዊ ለባሾቹ በልበ-ሙሉነት ነበር ግጥሚያውን የረቱት። እሑድ ኢቲሃድ የሚካሄደውን ፍልሚያስ ማን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል?-የቢቢሲ ስፖርት ተንታኝ ክሪስ ሱተን “ማንቸስተር ዩናይትድ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ድል ሲቀናው ነበር፤ ነገር ግን ሲቲ ያለበት ደረጃ ላይ አይደሉም” ይላል።-የዘንድሮውን ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች እየገመተ ያለው ሱተን፣ የማንቸስተር ደርቢን ጨምሮ ከቅዳሜ እስከ ሰኞ ያሉ ጨዋታዎች ግምቱን ጀባ ብሏል።-ቼልሲ ባለፈው ቅዳሜ በካራባዎ ዋንጫ ፍፃሜ በሊቨርፑል ተረትቷል። ይህ ጨዋታውም ቀላል ይሆንላቸዋል ብዬ አልገምትም።-ብሬንትፈርድ በበኩሉ እንደ አምናው ያለ አቋም እያሳየን አይደለም። ካለፉት ስድስት የሊጉ ጨዋታዎች በአምስቱ ተረትቷል።-እና ይህን ጨዋታ ምን ብዬ ብገምት ይሻለኛል? ለብሬንትፈርድ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ እጅግ አስፈላጊው ነው። ምክንያት ከወራጅ ቀጣና በጥቂት ነጥብ ነው ርቀው የሚገኙት።-የቼልሲው አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፓቼቲኖ በክለቡ መቀጠል ከፈለጉ የያዝነውን የውድድር ዘመን ጠንካራ ሆነው ማጠናቀቅ አለባቸው።-ይህ ጨዋታ ከአቻ የተለየ ውጤት ይኖረዋል ብዬ አላስብም።-ግምት፡ 1 - 1-ኤቨርተን ከወራት በፊት የተጣለበት የ10 ነጥብ ቅጣት ተቀንሶ 6 ሆኖለታል። ይህ ደግሞ ለዚህ ጨዋታ መነቃቃት ይሆነዋል።-ኤቨርተኖች ድል ካጣጣሙ ቆይተዋል። ቅጣቱ መስተካከሉ ይህን ጨዋታ ለማሸነፍ ቆርጠው እንዲገቡ ያደርጋቸዋል ብዬ አስባለሁ።-ከብራይተን ጋር የነበራቸውን ጨዋታ ማሸነፍ ይገባቸው ነበር።-ብራዚላዊው ሉካስ ፓኩዌታ ከጉዳት መመለሱ ለዌስት ሀም መልካም ዜና ነው።-ነገር ግን እኔ ኤቨርተን በሜዳው አደገኛ ቡድን ነው ብዬ ነው የማስበው። ለዚህ ነው ዌስት ሀም ያለምንም ነጥብ ይመለሳል የምለው።-ግምት፡ 1 - 0-ብራይተን በዎልቭስ ተሸንሮ ከኤፍ ኤ ዋንጫ ውጪ መሆኑ አስደንቆኛል። ነገር ግን ዘንድሮ ወጥ አቋም አለማሳየቱ መርሳት የለብንም።-በዚያ ላይ ካሮ ሚቶማ መጎዳቱ ሌላ ደንቃራ ይሆንባቸዋል። ሁለት ጨዋታ በተከታታይ ማሸነፍ ብዙም ያልሆነላቸው ብራይተኖች ይህ ጨዋታ እንደሚከብዳቸው እገምታለሁ።-ለዚህ ነው የዚህ ጨዋታ ውጤት ወደ ፉልሀም ያደላል የምለው። ፉልሀም ባለፈው ሳምንት ወደ ኦልድ ትራፈርድ ተጉዞ የሚገባውን 3 ነጥብ ይዞ ተመልሷል።-ግምት፡ 2 - 1-ምንም እንኳ ማቴውስ ኩንሀ ቢጎዳባበትም ዎልቭስ ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻለ መምጣቱን መመልከት ችያለሁ።-ኒውካስልም እንደ ዎልቭስ ለኤፍ ኤ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ደርሷል።-ሁሌም ኒውካስል በሜዳው ይረታል ብዬ ብገምትም በውጤቱ እያፈርኩ ነው። በሜዳው ያደረጋቸውን ያለፉትን አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።-አሠልጣኙ ኤዲ ሃው መንበራቸው ላይ መቆየት ከፈለገ ይህን መቀየር አለበት። ምንም እንኳ የመባረር ስጋት ባይኖርበትም የውድድር ዘመኑን በመልካም ውጤት ማጠንቀቅ ይገባዋል።-ዎልቭስ ለዚህ ጨዋታ ያንሳል ብዬ ባልገምት ውጤት ወደ ኒውካስል የምታደላ ይመስለኛል።-ግምት፡ 2 - 1-የሊቨርፑል ታዳጊ ተጫዋቾች ከቼልሲ ጋር በነበረው ፍፃሜ ባሳዩት ብቃት ውዳሴ እየደረሳቸው ነው። በኤፍ ኤ ዋንጫም ሳውዝአምፕተንን ረትተዋል።-ሳምንቱ ለየርገን ክሎፕ ድንቅ ነው። የመጀመሪያውን ዋንጫ ከማግኘታቸው ባለፈ ሌላ ዋንጫ የማግኘት ተስፋቸውም ለምልሟል።-ሞሐመድ ሳላህ፣ ዶሞኒክ ስፖስዝላይ እና ዋታሩ ኤንዶ ወደ መልካም አቋማቸው ቢመለሱ ደግሞ ሊቨርፑልን ማቆም ከባድ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።-ፎረስት ከመውረድ አደጋ ነፃ ቢሆኑም፣ ነጥብ ሊቀንስባቸው እንደሚችል እየተወራ ነው። ይህ ደግሞ ስጋት ላይ የሚጥል ነው።-በያዝነው ዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ድል የቀናው የኑኖ ኤስፔሪቶ ሳንቶ ቡድን ቅዳሜ ዕለት ድል ይቀናዋል የሚል ግምት የለኝም።-ግምት፡ 0 - 2-ቶተንሀም አሁንም በሚቀጥለው ዓመት በቻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን ነጥብ እያሳደደ ነው።-አሠልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ በዚህ ፍጥነት እስከ አራተኛ ለመውጣት ይፋለማሉ ብዬ አልገመትኩም ነበር። ነገር ግን ቡድኑ በያዝነው የውድድር ዘመን ምርጥ ብቃቱን እያሳየን ነው።-አዲሱ የክሪስታል ፓላስ አሠልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር፤ በርንሊን በመርታት ሥራውን በሦስት ነጥብ ጀምሯል። ነገር ግን ይህ ጨዋታ ይከብደዋል።-ምንም እንኳ ስፐርስ ባለፉት ሳምንታት ነጥብ ሲጥል ብንመለከትም ከፓላስ የተሻሉ ተጫዋቾችን ይዟል።-ግምት፡ 3 - 0-ሉተን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ባሳየው ብቃት ውዳሴ ተችሮታል። ሉተን በፕሪሚዬር ሊጉ የሚቆይ ከሆነ አሠልጣኝ ሮብ ኤድዋርድስ የውድድር ዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝ መባል አለበት ብዬ ከዚህ ቀደም ተናግሪያለሁ።-ነገር ግን ኤቨርተን የተቀነሰበትን ነጥብ መልሶ ማግኘቱ እና ሉተን ያለፉትን ተከታታይ ጨዋታዎች መሸነፉ ስጋት ላይ የሚጥል ነው።-የአስተን ቪላ ተጫዋቾች ወደ ተቃራኒ ቡድን ግብ አቅጣጫ ሲያመሩ ያስፈራሉ። ነገር ግን ይህ የራሱ ጉዳት አለው።-ሉተን ጎል ያስቆጥራል ብዬ ባምንም ቪላ ነጥቡን ያገኛል ነው ግምቴ።-ግምት፡ 1 - 3-በርንሊ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ አለበት ማለት ከጀመርኩ ሳምንታት ተቆጥረዋል። ከወራጅ ቀጣናው ለመውጣት 11 ነጥብ ያስፈልገዋል። የቀረው ደግሞ 12 ጨዋታ ነው። በውድድር ዘመኑ ሦስት ጊዜ ብቻ ነው ድል የቀናቸው።-ከኋላ ኳስ መሥርተው ለመጫወት የሚያደርጉት መኩራ ኪሳራ እያመጣባቸው ነው።-ቦርንመዝም እንዲሁ ምርጥ አቋም ላይ አይደሉም። የዶሚኒክ ሶላንኬ መጎዳት ደግሞ ሌላ ደንቃራ ነው። ቢሆንም በበርንሊ ይረታሉ ብዬ አልገምትም።-ግምት፡ 1 - 1-ዩናይትድ በኤፍ ኤ ዋንጫ ከኖቲንግሀም ሲጫወት ያሳየው ብቃት ሲቲን የሚያስጨንቅ አይደለም። ምንም እንኳ ያገኙት ድል ለአሠልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ አስፈላጊ ቢሆንም፣ የራስመስ ሆይለንድ መጎዳት ሌላ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል።-ማርከስ ራሽፈርድ የቀደመ አቋሙን ካሳየን ቆይቷል። ነገር ግን ኤሪክ ቴን ሀግ ሲቲን ለመርታት የሚሆን የተለየ ታክቲክ ሊጠቀሙ ይችላሉ።-ሲቲ ይህን ጨዋታ እንደሚረታ ምንም ጥርጥር የለኝም። ጥያቄው በምን ያህል የጎል ልዩነት የሚለው ነው።-ግምት፡ 6 - 1-አርሰናል በፕሪሚዬር ሊጉ የሚያደርገውን ጨዋታ በጎል በመንበሽበሽ እየረታ ይገኛል። ልክ እንደ ሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲ ነጥብ መጣል የሚባል ነገር አአምሯቸው ላይ ሊመጣ አይገባም።-ባለፈው ሼፊልድ ወደ ኤሜሬትስ ስታድየም አቅንቶ 5 ለምንም ተረትቶ ተመልሷል። በወቅቱ ኤዲ ኒኬታህ ሦስት ጎል አስቆጥሮ ነበር።-ሼፊልድ ከአርሰናል ጋር አንገት ለአንገት ይተናነቃል ብዬ አላስብም። ባይሆን አርሰናል ጎል እንዳያገባ ለመከላከል ቆርጠው የሚገቡ ይመስለኛል።-መድፈኞቹ ቀድመው ጎል የሚያስቆጥሩ ከሆነ ለሼፊልድ አደጋ ነው የሚሆነው።-ግምት፡ 0 - 3
የፎቶው ባለመብት ethiopian/fb-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስያ አገራት ለሚያደርጋቸው በረራዎች ይጠቀምበት በነበረው የሶማሊያ የአየር ክልል በኩል መብረር ማቆሙን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለቢቢሲ ገለጹ።-አየር መንገዱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከሶማሊያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች “አስተማማኝ የአየር ትራፊክ አገልግሎት” ባለማግኘቱ እንደሆነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ለቢቢሲ አማርኛ አርብ ከሰዓት በኋላ የተናገሩ ቢሆንም፣ ድርጅቱ ምሽት ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባሰራጨው መግለጫ የአቶ መስፍንን አስተያየት አስተባብሏል።-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ባወጣው መግለጫ “ሪፖርቱ ትክክል ያልሆነ እና የተዛባ ነው” ያለ ሲሆን፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚው “የሶማሊያ አየር ክልል ደኅንነቱ አስተማማኝ አይደለም” አለማለታቸውን በመግለጽ፣ ቢቢሲ ማስተካከያ እንዲያደርግ ጠይቋል።-ቢቢሲ ዘገባውን ከዋና ሥራ አስፈጻሚው ጋር የተደረገን ቃለ ምልልስ መሠረት አድርጎ የሠራ ሲሆን፣ እንደተባለው አቶ መስፍን ከተናገሩት ውጪ የተካተተ ወይም የተዛባ አስተያየት እንደሌለ ያረጋግጣል።-ለዚህም ከዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ እዚህ አያይዟል።-ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስያ ለሚደርጋቸው በረራዎች “ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ” ይጠቀምበት በነበረው የሶማሊያ አየር ክልል መብረር ያቆመው፤ የአየር መንገዱ አውሮፕላን ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም. በአገሪቱ የአየር ክልል ውስጥ ካጋጠመው ክስተት ጋር በተያያዘ መሆኑን አቶ መስፍን አስታውሰዋል።-ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን፤ “በዓለም አቀፍ አሠራር መሠረት እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲያጋጥም ለሚመለከታቸው የሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣናት ሪፖርት እናደርጋለን። [የቅዳሜውን ክስተት በተመለከተም] ለሶማሊያ እና ለኢትዮጵያ የሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣናት ሪፖርት ተደርጓል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁንና እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩን አክለዋል።-የቅዳሜ ዕለቱ ክስተት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሶማሊያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሚሰጠውን አገልግሎት “አስተማማኝ ሆኖ እንዳያገኘው” ማድረጉን አቶ መስፍን ገልጸዋል።-በዚህም ምክንያት ይህ ክስተት ካጋጠመበት ማግስት እሁድ የካቲት 17/2016 ዓ.ም. አንስቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሶማሊያን አየር ክልል መጠቀም ለማቆም መወሰኑን አስታውቀዋል።-ቢቢሲ ፍላይትራዳር24 እና ፍላትአዌር የተባሉ ዓለም አቀፍ የበረራ መስመሮች መከታተያ ድረ ገጾች ላይ ባደረገው ማጣራት ባለፈው ሳምንት በሶማሊያ የአየር ክልል ውስጥ በኢትዮጵያ እና በኳታር አውሮፕላኖች መካከል ያጋጠመውን ክስተት ተከትሎ የበረራ መስመር ለውጥ እንዳለ ለመረዳት ችሏል።-በዚህም አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም ወደ ባሕረ ሰላጤው አገራት የሚያደርጋቸው በረራዎች በሶማሊያ የአየር ክልል በኩል የነበሩ ሲሆን፣ ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ ግን ጉዞዎቹ በጂቡቲ በኩል እንደሆኑ ድረገጾቹ ያመለክታሉ።-የበረራ መስመር ለውጥ ያደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን የኳታር አየር መንገድም ቀደም ሲል ከኡጋንዳ ኢንተቤ ወደ ዶሃ፣ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በኩል ጉዞ ሲያደርግ የነበረ ሲሆን፣ ባለፉት ቀናት ግን በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በኩል እየበረረ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።-አቶ መስፍን፤ ከክስተቱ በኋላ ካለው ቀን አንስቶ “አማራጭ ለመጠቀም ወስነናል። ለዚህም ዋናው ምክንያት [የቅዳሜ ዕለቱ ክስተት] ነው። እዚያ በነበረው ሁኔታ፤ የአየር ክልሉ አስተማማኝ የአየር ትራፊክ አገልግሎት ስላላገኘንበት ለደኅንነት ስንል አማራጭ መንገዶች እየተጠቀምን ነው” ሲሉ የአየር መንገዱን ውሳኔ አብራርተዋል።-አየር መንገዱ ወደ እስያ ለሚያደርጋቸው በረራዎች የሚጠቀመው የሶማሊያን የአየር ክልል እንደነበር ያስታወሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ በአሁኑ ሰዓት እነዚህ በራረዎች የሚደረጉት በጂቡቲ አየር ክልል በኩል መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጂቡቲን የአየር ክልል እየተጠቀመ ያለው “ተጨማሪ ወጪ በማያመጣ መልኩ” እንደሆነም አክለዋል።-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሌለሎች አገራት ለሚደረጉ በራረዎች የሶማሊያን አየር ክልል መጠቀም ቢያቆምም ወደ ሞቃዲሾ እና ወደ የሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሀርጌሳ ከተማዎች የሚያደርጋቸውን በራረዎች “ያለ ችግር” መቀጠሉን አብራርተዋል።-ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ ሲጓዝ የነበረው የአየር መንገዱ የበረራ ቁጥር 602 አውሮፕላን፤ የኳታር ኤር ዌይስ አውሮፕላን እየቀረበው እንደሆነ መረጃ መቀበሉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቢቢሲ ገልጾ ነበር።-በሶማሊያ የአየር ክልል ውስጥ እየበረረ የነበረው የኳታሩ አውሮፕላን የነበረበትን ከፍታ በመጨመር ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የቀረበው ከሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በተሰጠው ፈቃድ መሆኑን አየር መንገዱ ጠቅሶ ነበር።-የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢሜል ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ በሁለቱ አውሮፕላኖች መካከል የነበረው ርቀት 23 ኪሎ ሜትር እንደሆነ ገልጿል።-ይህንን ክስተት አስመልክቶ መግለጫ ያወጣው የሶማሊላንድ አቪየሽን እና ኤርፖርቶች ባለሥልጣን የኢትዮጵያ እና የኳታር አውሮፕላኖች “አደገኛ በሆነ ርቀት” ላይ እንደነበሩ እና “ሊጋጩ ተቃርበው” እንደነበር መግለጹ ይታወሳል። ይህም የሆነው በሞቃዲሾ የሚገኙት የሶማሊያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በሰጡት “የተሳሳተ መረጃ” እንደሆነ በመግለጽም ከስሶ ነበር።-ይሁንና የሶማሊያ አቪዬሽን ባለሥልጣን በበኩሉ በሁለቱ አውሮፕላን መካከል የነበረው ርቀት አደጋን የሚያስከትል ስጋት ላይ አልነበረም ሲል ጉዳዩን አስተባብሏል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ማር በውስጡ የያዘው ከፍተኛ የካሎሪ መጠን በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ስለሚጨምር የምንወስደው መጠን ትንሽ መሆን እንዳለበት ይመከራል።-ንቦች ከአበባ የሚገኝን ጣፋጭ ፈሳሽ [ኔክታር] ቀስመው የሚያዘጋጁት ማር ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገራት እንደ መድኃኒት ይቆጠራል።-ከቤት ውስጥ መጥፋት ከሌለባቸው ምግቦች ውስጥም ሲጠቀስ ይሰማል።-ጥንታውያን ግሪኮች ማርን “የፈጣሪ ምግብ” ሲሉ ነው የሚገልጹት። በቻይና ደግሞ መድኃኒት ተደርጎ ነው የሚታሰበው።-በአብዛኛው ወርቃማ ቀለም ያለው ይህ ጣፋጭ የተፈጥሮ ፈሳሽ ለምግብነት እና ለመድኃኒትነት የሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ ይዟል።-እንደየ አካባቢው እና ንቦች እንደሚቀስሙት የአበባ ዓይነትም ቀለሙ የተለያየ ይሆናል።-ለመሆኑ ከስኳር የሚጣፍጠው የተፈጥሮ ማር ብቸኛው የስኳር አማራጭ ነው? ለሁሉም ሰውስ በእኩል ይጠቅማል? ሕጻናትን ለመመገብስ የዕድሜ ገደብ አለው? የምንወስደው መጠንስ ምን ያህል መሆን አለበት?-ለእነዚህ የበርካታ ሰዎች የዘውትር ጥያቄዎች የሥነ ምግብ ባለሙያ የሆኑት ጆ ልዊን ምላሽ አላቸው።-ንጹህ የተፈጥሮ ማር [ያልተቀነባበረ] በውስጡ አሚኖ አሲድ፣ አንታይኦክሲደንት፣ ቫይታሚኖች፣ ሚኒራሎች እና ስኳር ይዟል።-ማር ከፍተኛ የፍሩክቶስ ይዘት ያለው በመሆኑም ከስኳር በላይ ጣፋጭ ነው። ነገር ግን ግላይቼሚክ ኢንዴክስ (ጂአይ) ባወጣው ደረጃ መሠረት ማር ያለው ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገር (ካርቦሃይድሬት) መካከለኛ ነው።-ጂአይ እያንዳንዱ የምንመገበው ምግብ ተፈጭቶ በምን ያህል ፍጥነት በደማችን ውስጥ የሚገኝ የስኳር (ግሉኮስ) መጠን ላይ ተፅእኖ እንደሚያደርስ የሚያሳይ የመለኪያ ሥርዓት ነው።-አንድ የሾርባ ማንኪያ (20 ግራም) ማር 58 ኪሎ ካሎሪ፣ 15.3 ግራም ካርቦሃይድሬት፣ 15.4 ግራም ስኳር፣ 0.1 ግራም ፕሮቲን እና 0 ግራም ስብን ይይዛል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-የማር የጤና ጥቅሞች በሚቀነባበርበት መንገድ እና ንቦች በሚቀስሙት የአበባ ጥራት ላይ ይወሰናል።-ንጹህ የተፈጥሮ ማር በማንኛውም መንገድ ያልቀለጠ፣ ያልተቀነባበረ፣ ያልተጣራ፣ ያልተጠለለ ወይም ሌላ ግብዓት ያልተጨመረበት ነው። እንዲህ ዓይነቱ ማር በማቀነባበር ሒደት ያልተወገዱ እና ለጤና የሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ነው።-በሚይዛቸው ንጥረ ነገሮችም ማር ለበርካታ ዓመታት ረቂቅ ተህዋስያንን ለማጥፋት ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል።-መጠነኛ የሆነ ቆዳ ላይ የሚያጋጥሙ ቁስሎችን፣ የብግነትን ( አልሰር) እና የቃጠሎ ጉዳቶችን የማገገም ሒደትን ማር ያፋጥናል ተብሎም ይታመናል።-ማር በውስጡ ግሉኮስ እና ፍሩክቶስ የተባሉ የስኳር ዓይነቶችን የያዘ ሲሆን፣ እነዚህ ስኳሮች ደግሞ ፈሳሽን የመምጠጥ ባህሪ አላቸው።-በመሆኑም በውስጡ እነዚህን የስኳር ዓይነቶች የያዘው ማር በቁስል ላይ ያለን ፈሳሽ የመምጠጥ እና የማድረቅ አቅም አለው። ይህም በተጎዳው አካል ላይ ያለውን የባክቴሪያ እና የፈንገስ እድገትን ይገታል።-ጠቆር የሚለው የማር ዓይነት ደግሞ ‘ፍላቮኖይድ’ በተባለ ኬሚካላዊ ውህድ የበለጸገ ነው።-ፍላቮኖይድ ፀረ ባክቴሪያ፣ ፀረ ቫይረስ፣ እንዲሁም አለርጂ እና የሰውነት መቆጣትን የሚከላከል ንጥረ ነገር አለው። ባለው የፍላቮኖይድ ንጥረ ነገር ምክንያትም በርካቶች ስኳርን እና አንታይኦክሲደንትን ለማግኘት ማርን እንደ ጤናማ የምግብ አማራጭ ይወስዱታል።-ሆኖም ግን አወሳሰዱ ላይ ጥንቃቄን ሲያደርጉ አይስተዋልም።-የሥነ ምግብ ባለሙያ የሆኑት ጆ ልዊን እንደሚሉት ማር ከአንድ የሾርባ ማንኪያ ስኳር ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ የካርቦሃይድሬት መጠን ነው ያለው። ሆኖም በውስጡ የያዘው ከፍተኛ የካሎሪ መጠን በደም ውስጥ ያለን የስኳር መጠን ስለሚጨመር በመጠኑ እንዲወሰድ ይመክራሉ።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-ማር ከስኳር በላይ ጣፋጭ ስለሆነ የሚያስፈልገን ትንሽ ነው።-ማር ከስኳር ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ የካርቦሃይድሬት መጠን ያለው። ይህ ማለት በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን እንደ ስኳር በፍጥነት አይጨምረውም ማለት ነው። ማር ከስኳር ይበልጥ ጣፋጭ በመሆኑም መመገብ የሚያስፈልገን ትንሽ ነው።-አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ብዙ ካሎሪ ስላለው በምንወስደው መጠን ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።-ማር ምርጫችን ከሆነና መመገብ የምንችል ከሆነ ከስኳር ይልቅ ብዙ ቫይታሚኖችን፣ ኤንዛይሞችን፣ አንታይኦክሲደንቶችን እና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን በውስጡ የያዘውን ንጹህ የተፈጥሮ ማር መመገብ የጤና ጠቀሜታው የላቀ መሆኑን ባለሙያው አስረድተዋል።-በሚመከረው መጠን ልክ ከተወሰደ ማር ከስኳር ነጻ እንደሆነ ምግብ የሚቆጠር ነው። ለበርካታ አዋቂዎችም ጤና ጠቃሚ ሲሆን፣ የሚያስልጋቸውን ትክክለኛ መጠን ግን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል።-ስኳር ላለባቸው ሰዎች አሊያም በደማቸው ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለማስተካከል ጥረት እያደረጉ ያሉ ሰዎች ስኳርን በማር መተካታቸው “አልሸሹም ዞር አሉ” እንደማለት ነው። ምክንያቱም ሁለቱም በደም ውስጥ ያለን የስኳር መጠን ይጨምራሉ።-ከዚህም ባሻገር ከ12 ወር አሊያም ከአንድ ዓመት በታች ያሉ ሕጻናት ንጹህ [ያልተቀነባበረም] ሆነ የተቀነባበረ ማር መመገብ የለባቸውም። ምንያቱም የሰውነት የነርቭ ሥርዓት ላይ ጉዳት ለሚያደርስ ‘ቦቱሊዝም’ ለተባለ የምግብ መመረዝ ተጋላጭ ሊያደርጋቸው ስለሚችል ነው።-ምንም እንኳን አብዛኞቻችን ማርን በምግብ ዝርዝራችን ውስጥ ብናካትትም በሁሉም ሰው ዘንድ ተቀባይነት ላይኖረውም ይችላል።-የእንስሳት ተዋፅኦ ለማይመገቡ [ቪጋን] ለሆኑ ሰዎች ማር ተመራጭ አይደለም። ምክንያቱም ማር ምንም እንኳን ምንጩ አበባ [እፅዋት] ቢሆንም በክረምት ወራት የራሳቸውን ሕይወት ለማቆየት ሲሉ ታትረው ማር ከሚሰሩት ንቦች ጋር ስለሚያያዝ በቪጋኖች ዘንድ እንደ የእንስሳት ተዋፅኦ ይቆጠራል።
የፎቶው ባለመብት SOCIAL MEDIA-የተፈረደባቸው የአይኤስ አባላት በፍርድ ቤት-ለአይኤስ ለመዋጋት ወደ ሶማሊያ ገብተው ተይዘዋል የተባሉ ስድስት ሞሮኳውያን በሞት እንዲቀጡ ሲወሰንባቸው አንድ ኢትዮጵያዊ ደግሞ የ10 ዓመት እስር ተፈረደበት።-የተከሳሾቹን ጉዳይ የተመለከተው የሶማሊያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በአይኤስ አማካይነት በአገሪቱ ውስጥ ተሰማርተው ተገኝተዋል ብሎ ውሳኔ የሰጠባቸው ስድስት ሞሮኳውያን፣ አንድ ኢትዮጵያዊ እና ሁለት ሶማሊያውያን ናቸው።-ሞት የተፈረደባቸው የሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ ዜጎች በአንድ ወር ውስጥ ይግባኝ አቅርበው ተቀባይነት ካላገኙ በጥይት ተረሽነው ፍርዱ ተግባራዊ ይሆናል።-የወታደራዊው ፍርድ ቤት ምክትል ሊቀመንበር ኮሎኔል አሊ ኢብራሂም “ግለሰቦቹ ወደ ሶማሊያ የመጡት አይሲስ [ኤይኤስ] ደም እንዲያፈስ እና አገሪቱን እንዲያወድም ለማገዝ ነው” ማለታቸው ተዘግቧል።-ሞት የተፈረደባቸው ሞሮኳውያን አይኤስን እንዲቀላቀሉ መታለላቸውን እና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ መጠየቃቸውን የተከሳሾቹ ጠበቃ ተናግረዋል።-የግለሰቦቹ ክስ የታየባት የከፊል ራስ ገዟ የፑንትላንድ ባለሥልጣናት ወደ አይኤስ ሊቀላቀሉ ነበር የተባሉ የውጭ ዜጎችን ሲከሱ እና ቅጣት ሲበይኑ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።-ወታደራዊው ችሎት ሞት ከፈረደባቸው ስድስት ሞሮኳውያን ጋር የአንድ ኢትዮጵያዊ እና የሶማሊያዊ ጉዳይን ተመልክቶ በእያንዳንዳቸው ላይ የ10 ዓመት እስር ሲበይን፣ ሌላኛው ሶማሊያዊ ደግሞ በቂ ማስረጃ አልቀረበበትም በማለት በነጻ አሰናብቷል።-ክሱን ሲከታተሉ ከነበሩት ዓቃብያነ ህግ መካከል አንዱ ለቢቢሲ ሶማሊኛ እንደገለጹት፣ ታጣቂዎቹ የተያዙት የፑንትላንድ የንግድ ማዕከል ከሆነችው ቦሳሶ በስተምሥራቅ በሚገኝ ተራራማ ቦታ ላይ ነው።-ተራሮቹ አይኤስ ጠንካራ ይዞታ መሆናቸው የሚነገር ሲሆን፣ በስፍራውም ቡድኑ ወታደራዊ ሠፈር አለው።-በሶማሊያ የአይኤስ ቅርንጫፍ ከዘጠኝ ዓመት በፊት የተመሠረተው ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ካለው እና የአገሪቱ ዋነኛው ጂሃዲስት ቡድን ከሆነው ከአልሻባብ ተገንጥለው በወጡ ታጣቂዎች ነው።-በሶማሊያ ያለው የአይኤስ ቡድን ከነዋሪዎች ገንዘብ በማስገደድ የሚሰበስብ ሲሆን፣ አነስተኛ መጠን ያላቸው ጥቃቶችን አልፎ አልፎ የሚፈጽም መሆኑን የአሜሪካ ብሔራዊ መረጃ ጽህፈት ቤት አመልክቷል።-ነገር ግን የሞት ቅጣቶች እንዲቀሩ በርካታ የሶማሊያ እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቡድኖች ጥሪ ሲያቀርቡ ቢቆዩም፣ ከሽብርተኝነት ጋር በሚገናኝ ወንጀል በሚዙ ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት መበይን የተለመደ ነው።-የመብት ቡድኖች ባለፈው የካቲት ወር ባወጡት ሪፖርት መሠረት ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት በሶማሊያ በ55 ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት ተፈጽሟል።-ከእነዚህም ውስጥ 23 የሞት ቅጣቶች የተፈጸሙት በፑንትላንድ እና በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ውስጥ ነው።
የፎቶው ባለመብት Mayor Office/fb-በአዲስ አበባ እምብርት ፒያሳ፤ የሚኒሊክ ሀውልት እና የአራዳው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚያዋስኑት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። በቅርቡ ከታደሰው እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ከሚገኝበት ማዘጋጃ ቤት ጋር ደግሞ በድልድይ ተገናኝቷል።-እስከ ዛሬ ድረስ የራሱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሳይኖረው የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትም ቋሚ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚያገኘው በዚህ ፕሮጀክት ነው። እየተጠናቀቀ ያለው ይህ ፕሮጀክት ሁለት ሺህ ሰዎችን የሚይዝ የከተማ አዳራሽም በውስጡ ይዟል።-ከሁሉም በላይ ግን የዓድዋ ሙዚየም ፕሮጀክት ግዙፍነት የሚነሳው ሊዘክረው ካሰበው ታሪካዊ ሁነት ነው። ይህ ግዙፍ መንግሥታዊ ፕሮጀክት፤ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት በተለየ የኢትዮጵያን ነጻነት ያስጠበቀው እና በተለያዩ አገራት የፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴን ያነሳሳው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ነው።-የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ካስገነባቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች ውስጥ የሚጠቀሰው የዓድዋ ሙዚየም፤ ግንባታው የተጀመረው ሐምሌ 2011 ዓ.ም. ነበር። ሙዚየሙ የካቲት 3/2016 ዓ.ም. ተመርቆ ተከፍቷል።-የፒያሳ አዲስ ምልክት ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የዚህ ሙዚየም ዋና አርክቴክት እስክንድር ውበቱ ነው።-የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአርክቴክቸር እና የከተማ ፕላን ምሩቁ እስክንድር፤ ህንጻዎችን ሲነድፍ 28 ዓመት ገደማ አሳልፏል። ከሥራዎቹ መካከል አዲስ አበባ ሰንጋ ተራ አካባቢ የሚገኘው ባለ 37 ወለሉን የሕብረት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት “ሕብር ታወር” ተጠቃሽ ነው።-ከእስከ ዛሬ ሥራዎቹ መካከል ትልቁ ደግሞ ፒያሳ ላይ የተዘረጋው የዓድዋ ሙዚየም ነው።-እንደ እስክንድር አገላለጽ ይህ ፕሮጀክት፤ እንደ ሌሎች ሥራዎች የደንበኛን ፍላጎት በህንጻ ንድፍ የመተርጎም ሥራ ብቻ አይደለም። “ከ1.5 ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ የሚቀመጥ ነገር ህንጻ ብቻ አይደለም” የሚለው እስክንድር፤ በትምህርት፣ በሙያ እና በንባብ ያሰባሰበውን የ“ኧርባን ዲዛይን” ጽንሰ ሀሳብ በትልቅ ደረጃ ሙከራ (experiment) ያደረገበት መሆኑን ይገልጻል።-የፎቶው ባለመብት Eskinder Woubtu-አርክቴክት እስክንድር ውበቱ በዓድዋ ሙዚየም-የዓድዋ ሙዚየምን የሚገነባው ተቋራጭ “ቻይና ጂያንግሱ ኢንተርናሽናል” ከእስክንድር ጋር ሲሠራ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። እስክንድር የነደፈውን የሕብረት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንጻን የገነባው ይህ ኩባንያ ነበር።-በ2011 ዓ.ም. የዓድዋ ሙዚየምን ለመገንባት ጨረታ የወጣው ከቤተ መንግሥት ፓርኪንግ እና ከአብርሆት ቤተ መጽሐፍት ፕሮጀክቶች ጋር በአንድ ላይ እንደነበር እስክንድር ያስታውሳል። እነዚህን ፕሮጀክቶች ለመገንባት የሚጫረቱ ተቋራጮች የህንጻውን ንድፍ የሚሠራ የአርክቴክት ድርጅት አብረው ማቅረብ ነበረባቸው።-በዚህ ጨረታ ላይ የሚወዳደረው ጂያንግሱ ኢንተርናሽናል ለኢትዮጵያዊው የአርክቴክቸር ድርጅት “እስክንድር አርክቴክትስ” የእንጣመር ጥያቄ አቀረበ።-“እነዚህን ፕሮጀክቶች ሲጫረቱ ከፕሮጀክቶቹ ውስጥ ‘የትኛው ውስጥ መሳተፍ ትፈልጋለህ?’ ተብሎ ነው [ጥያቄው] የመጣው። ከነበሩት ውስጥ ይበልጥ ሊፈትነኝ የሚችል እና ሀሳቡም በጣም ቅንጭብ ሆኖ የቀረበ ስለሆነ፤ ብዙ ዲዛይን የማድረግ ዕድል ስለሚኖረኝ ዓድዋን መርጬ ከቻይና ጂያንግሱ ግሩፕ ጋር ተጣማሪ ሆነን እዚህ ውስጥ ገባን” ይላል ሥራው የመጣበትን አጋጣሚ ሲያስታውስ።-ፕሮጀክቱን ያስጀመረው በቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የሚመራው የከተማዋ አስተዳደር የሚገነባውን ህንጻ በተመለከተ ያስቀመጣቸው የመነሻ ሀሳቦች ነበሩ። ህንጻው የሚኒሊክ ሀውልት ከሚገኝበት መንገድ እኩል ሆኖ እንዲጀምር እና እጅጉን ከፍታ ያለው እንዳይሆን ማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ መነሻዎች ውስጥ አንዱ ነው።-በሙዚየሙ ህንጻ ላይ የሰንሰለታማ ተራራ እና የነጋሪት ሀሳቦችን እንዲጸባረቁ ማድረግም የከተማ አስተዳደሩ መስፈርቶች ነበሩ። እነዚህ ሀሳቦች እንዴት ይካተቱ የሚለው ደግሞ የህንጻ ነዳፊው እስክንድር ፈጠራ ነው።-“የራሴን ሀሳቦች እንድጨምር ነጻነት ነበረኝ” የሚለው አርክቴክቱ፤ “ሁልጊዜ የሚጠየቀውን ኢትዮጵያዊ ኪነ ህንጻ” ለመሥራት ሙከራ ማድረጉን ይናገራል።-የፎቶው ባለመብት Eskinder Woubtu-ከሚኒሊክ ሀውልት ፊት ለፊት በሚገኘው የዓድዋ ሙዝየም መግቢያ ያለ የድል በዓል ማክበሪያ ስፍራ-በ3.3 ሄክታር ላይ ያረፈው የዓድዋ ሙዚየም ቁመቱን ከፍ ያደረገ አንድ ወጥ ህንጻ አይደለም። በተለያዩ መንገዶች የተሳሰሩ እና የአጠቃላይ ህንጻው አካል የሆኑ የተለያዩ ስብስቦችን (ሰብ ሴቶችን) የያዘ ነው።-ወደ ዓድዋ ሙዚየም የሚያስገቡት አራት ዋነኛ መግቢያዎች፤ የሚያደርሱት የተለያየ ገጽታ እና አገልግሎት ወዳላቸው የህንጻው ክፍሎች ነው። መግቢያዎቹ ስያሜያቸው የደቡብ ጀግኖች፣ የሰሜን ጀግኖች፣ የምሥራቅ ጀግኖች እና የምዕራብ ጀግኖች የሚል ነው።-እስክንድር፤ “ታሪክ እንደሚያሳየው ከሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ [ጦርነቱ ላይ] ተሳትፎ ተደርጓል ነው። ስለዚህ ሁሉም በአቅጣጫ ተወክለዋል። የበሮቹ ስያሜ ሲሰጥ ስሜቱም፣ ተመሳሌትነቱም እርሱ ነው” ይላል ከስያሜው ጀርባ ያለውን ምክንያት ሲያስረዳ።-ከዓድዋ ጦርነት ጋር የተያያዙ ቅርሶች የሚቀመጡበት ሙዚየም የሚገኘው በሚኒሊክ ሀውልት በኩል ባለው የሰሜን ጀግኖች መግቢያ ነው። ይህ መግቢያ ሀውልቱ ከሚገኝበት መንገድ እኩል (flat) ሆኖ የሚጀምር ሲሆን ለዓድዋ ድል በዓል ማክበሪያ የሚውል ሰፊ ፕላዛን ይዟል።-ከዚህ ዓመት ጀምሮ የዓድዋ ድል በዓል በዚህ ስፍራ ላይ እንደሚከበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።-በዓድዋ ድል በዓል ማክበሪያው ስፍራ መሀል ላይ በአንድ ጎኑ ከፍ ያለ ባለመስታወት ክብ ቅርጽ ተቀምጧል። ከመስታወቱ ስር የሚገኘው፤ ምድር ቤት (basement) ውስጥ የተሠራው ባለ ሁለት ወለል ሙዚየም ነው።-መስታወቱ፤ አስፓልቱን ተሻግሮ ባለው የሚኒሊክን ሀውልት ላይ የምታርፈውን ፀሐይ ወደ ታች አውርዶ ምድር ቤት በሚገኘው ሙዚየሙ ውስጥ ተፈጥሯዊ ብርሃን ይፈነጥቃል። በክብ መስታወት (circular skylight) በኩል 20 ሜትር ቁልቁል የሚወረወረው የፀሐይ ብርሃን ማረፊያው ደግሞ በሙዚየሙ መሀል፣ ከመስታወቱ ትይዩ የተቀመጠ ነጋሪት ነው።-የፎቶው ባለመብት Eskinder Woubtu-በሙዚየሙ መሃል ላይ ከብርሃን ማስገቢያው መስታወት ትይዩ የሚገኘው ነጋሪት-እስክንድር የነጋሪቱን አቀማመጥ ሲገልጽ፤ “የሙዚየሙ መጀመሪያም፣ ማጠንጠኛም ነው” ይላል።-“ጦርነት ሲገባ፣ አዋጅ ሲነገር፣ ክተት ሲታወጅ የሚጎሰመው ነጋሪት ነው። ነጋሪቱ መሃል ላይ ሆኖ የሙዚየሙ የትኩረት ማዕከል (focal point) ነው፤ መነሻም ነው። ሙዚየም ውስጥ ስትገባ ጉብኝትህን ከአንድ ነገር ትጀምራለህ” ሲል ያብራራል።-“ሙዚየሙ ራሱ ሙሉ በሙሉ ከመሬት በታች ነው ያለውና ቀጥታ የሚመጣልህ ብርሃን ነው” የሚለው አርክቴክቱ፤ “ብርሃንን ቀርጾ ማስገባት እና በብርሃን መጫወትን” ሙከራ ያደረገበት የህንጻው ክፍል መሆኑን ያስረዳል።-እስንክድር፤ በህንጻው ንድፍ ላይ ደጋግሞ ያንጸባረቀው ሌላኛው ሀሳብ የዓድዋ ጦርነት የተካሄደበትን ምድረ ገጽ የሚወክለው ሰንሰለታማ ተራራ ነው። የህንጻው የውስጥ እና የውጭ ጎኖች፣ የደረጃ መደገፊያዎች ላይ በተቀመጡት ወጣ ገባ እያሉ አግድም በሚሄዱ መስመሮች እንዲሁም በደረጃ ፋንታ በተቀመጡት ተዳፋቶች (ramp) ላይ መንጸባረቁን እስክንድር ይናገራል።-ተራራ “በአርክቴክቸራል ቋንቋ” ከተገለጸባቸው የህንጻው ክፍሎች ውስጥ አንዱ በማዘጋጃ ቤት በኩል የሚገኘው መግቢያ ነው። በዚህ መግቢያ ላይ ከደረጃ ባሻገር የተቀመጠው ዚግ ዛግ የሚሄድ ተዳፋት (ramp) ከርቀት ሲታይ የተራራ ይመስላል።-በዚህ መግቢያ ወደ የሚዘልቁ ጎብኚዎች ደረጃውን እንደጨረሱ የሚያገኙት እቴጌ ጣይቱ በመቀለው ውጊያ የውሃ ምንጮችን በመያዝ የጣልያን ጦር እጅ እንዲሰጥ ለተጠቀሙት ስልት መታሰቢያነት የዋለ የውሃ ፋውንቴን ነው።-ተራራማ እና ድንጋያማ አካባቢን በዓድዋ ሙዚየም ላይ የማንጸባረቅ ሀሳብ፤ የህንጻው ቀለም ላይም ታይቷል። በተለይ በህንጻው የውጭ ክፍል ላይ ጎልቶ የሚታየው ቀለም “ሸክላ መሳይ” ነው።-ከህንጻው ትልቅነት አንጻር የተለያዩ ቀለማትን መጠቀም ይቻል እንደነበር የሚናገረው እስክንድር፤ ይበልጥ “ተፈጥሯዊ ነው” ብሎ ያሰበውን ይህንን ቀለም በብቸኝነት መጠቀሙን ይገልጻል። “ተራሮቹን የበለጠ የመግለጽ አቅም ያለው ቀለም ነው። ለህንጻውም የራሱ መገለጫ ሰጥቶታል” ይላል።-የፎቶው ባለመብት Mega Projects Office/fb-ከባህላዊው ልብስ 'ድንጉዛ' የተቀዳው የዓድዋ ሙዚየም የውጭ ገጽታ-እስክንድር፤ አንድ ህንጻ ሲሠራ ለአካባቢው እና ለነዋሪዎች የሚያስተላልፈው “ጥበብ” ሊኖረው ይገባል የሚል እምነት አለው።-በዓድዋ ሙዚየም ላይ “ሞክሬዋለሁ” የሚለው ዋነኛው ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ምልክቶች እና መገለጫዎችን በህንጻ ዲዛይን ውስጥ የማካተት ሀሳብን ነው።-“ሌሎች አገራት ላይ ብዙ ፓተርኖች ላይ ኤክስፐርመንት ያደርጋሉ። እኛ አሁን ማየት ያለብን ወደ ውጭ ሳይሆን ወደ ውስጥ ነው። እነዚህን ነገሮች መሞከር እፈልግ ነበር” ሲል የህንጻን ገጽታ ከአገርኛ አውድ ጋር (local context) ጋር የማስተሳሰር ሙከራው በዚህ ፕሮጀክት መጀመሩን ያስረዳል።-በኢትዮጵያ ባህል ውስጥ “ያልታዩ ጥበቦች” መኖራቸውን የሚያነሳው እስክንድር፤ “ዘመናዊ ነገር እንሥራ ማለት አይደለም። በብዙ መልኩ እኛን የሚመስል ነገር [ወደ ማስቀመጥ] ነው መሄድ ያለብን” ይላል።-በዓድዋ ሙዚየም ላይ ያካተተው አንዱ አገርኛ ምልክት በደቡባዊ ኢትዮጵያ በጋሞ እና በወላይታ አካባቢዎች የሚለበሰው “ድንጉዛ” ነው። በደማቅ ቀይ፣ ቢጫ እና ጥቁር ቀለሞች ዐይን የሚገባው ድንጉዛ፤ በጥለቱ ላይ የሚቀመጡት ወጣ ገባ ያሉ መስመሮችም መለያዎቹ ናቸው።-ይህን የድንጉዛ ጥለት የመስመር አካሄድ ከ100 ሜትር በላይ በሚሄድ የህንጻው ክፍል ላይ ተንጸባርቋል። በህንጻው የውጪ ክፍል ላይ የሚገኙት የጦር እና ጋሻ ምልክቶች የተቀረጹት በድንጉዛ የመስመር አካሄድ በተቀመጡ ቅርጾች ላይ ነው።-ከአክሱም ሀውልት እና ከላሊበላ ኪነ ህንጻ የተወሰዱ ምልክቶችም በህንጻው የደረጃ ድጋፎች እና የኮሪደር ስፍራዎች ላይ ማንጸባረቁንም አርክቴክቱ ይናገራል።-የፎቶው ባለመብት Eskinder Woubtu-የሰባ ደረጃ ተምሳሌት በዓድዋ ሙዚየም የደቡብ ጀግኖች መግቢያ-የንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት፤ አዲስ አበባ አሉኝ የምትላቸው ኪነ ህንጻዊ ውበትን የተጎናጸፉ ህንጻዎች የተገነቡበት ነው። ብሔራዊ ቲያትር፣ ማዘጋጃ ቤት እና የንግድ ባንክ የቀድሞ ዋና መሥሪያ ቤት ከእነዚህ ህንጻዎች መካከል ናቸው።-እነዚህን ህንጻዎች የተነደፉት እንደ ፈረንሳዊው ሄንሪ ሾሜት እና ጣልያናዊው አርትሮ ሜዜዲሚ ባሉ የውጭ አርክቴክቶች ነው። እስክንድር፤ “የአካባቢውን ሁኔታ አጥንተው አካባቢያዊ አውዱን (local context) ለማምጣት የሚሞክሩ አርክቴክቶች ነበሩ” ሲል ያሞካሻቸዋል።-የእነዚህ ህንጻዎች አንድ መገለጫ ከፊታቸው አጭር ሆነው ለእግረኛ መረማመጃ ስፍራ መፍጠራቸው ነው። “የአራት ኪሎ መደዳው እና ዞሮ ወደ ፒያሳ ሲመጣ [ህንጻዎች] በደረጃዎች እተገናኙ አርኬድ (ታዛ) አላቸው። እግረኛ በምቾት፣ በጥላ እንዲሄድ ነው” የሚለው አርክቴክቱ፤ የፒያሳ ህንጻዎች ከመንገዱ ጋር “በጣም የተናበቡ” መሆናቸውን ያነሳል።-“ከፒያሳ የምወስደውን የበፊት (traditional) ፕላኒንግ ልበለው። አሁን ዘመናዊ ፕላኒንግ ደግሞ አለ። እኔ ወደዚያ [ወደበፊቱ] ነው መመለስ የምፈልገው። ያ ጥሩ ፕላኒንግ ነው” የሚለው አርክቴክቱ በዓድዋ ሙዚየም ላይ እግረኛ የሚራመድባቸው ታዛዎችን መፍጠሩን ያስረዳል።-በሙዚየሙ ህንጻ ውስጥ የሚገኙት መደብሮች ደጃፋቸው እንደ ፒያሳው መብራት ኃይል ህንጻ እግረኛን የሚያስተናግዱ ናቸው።-ከአራዳ ህንጻ ጋር አዋሳኝ በሆነው አቅጣጫ የሚገኘው የዓድዋ ሙዚየም ደግሞ ሌላኛው የፒያሳ ገጽታ ምሳሌ አድርጎ የተነደፈ ነው። በሙዚየሙ ሁለት ብሎኮች መካከል ረጅም ደረጃ የተዘረጋበት ይህ የደቡብ ጀግኖች መግቢያ፤ ከፒያሳው 70 ደረጃ ጋር ተመሳሳይነት አለው።-የፎቶው ባለመብት Adanech Abiebie/fb-የዓድዋ ተራሮች በሙዚየሙ ህንጻ ንድፍ ላይ የተገለጸበት አንድ ክፍል-የዓድዋ ሙዚየም የህንፃ ንድፍ ሲሠራ ከጦርነቱ ጋር የተያያዙ 40 ገደማ ቅርጾች እንደተካተቱበት እስክንድር ይናገራል። ከእነዚህ የሚቆሙ እና በግድግዳ ላይ የሚለጠፉ ቅርጾች ውስጥ ግማሾቹ መሠራታቸውን የሚገልጸው አርክቴክቱ፤ “የተወሰኑት ወደፊት ይሰራሉ” ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅሷል።-በአሁኑ ጊዜ ተቀርጸው ከቆሙት ሀውልቶች መካከል የአጼ ሚኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ እንዲሁም 12 የጦርነቱ አዝማቾች ይገኙበታል። የአጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ሀውልት የውሃ ፋውንቴን በሚገኝበት ፕላዛ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠዋል። የጦር አዝማቾች ሀውልት ደግሞ በከተማ አዳራሽ የውጨኛ ክፍል ላይ በሚገኙት አምዶች ላይ ተቀምጠዋል።-እንደ እስክንድር ገለጻ የሀውልቶቹን አቀማመጥ በተመለከተ መጀመሪያ የሠራው ንድፍ ላይ ተጨማሪ ሀሳቦች ተካትተዋል። በንድፉ ላይ የ12ቱ የጦር አዛዦች ሀውልቶች በአንድ እልፍኝ ላይ እንዲቀመጥ ተደርጎ ነበር። የእቴጌ ጣይቱ ሀውልት ደግሞ በመቀለው ጦርነት ንግሥቲት ላመጡት የጦርነት ስልት መታሰቢያ በተሠራው የውሃ ፋውንቴን መሃል ላይ እንዲሰፍር ተነድፎ ነበር።-የእነዚህ ሀውልቶች ፎቶግራፍ በሶሻል ሚዲያ ገጾች ላይ ከተሰራጨ በኋላ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ተደምጠዋል። በቅሬታ መልክ ከተነሱት አስተያየቶች ውስጥ የሀውልቶቹን የቁመት መጠን እና ገጽታ እንዲሁም የተሰሩበት ቁስን የተመለከቱ ይገኙበታል። የሠዓሊያን እና የቀራፂያን ማኅበር በሙዚየሙ ቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች ላይ “አልተሳተፍኩም” ማለቱም ሌላኛው አስተያየት ነበር።-የሀውልት እና ሌሎች የቅርፅ ሥራዎች የሚከናወኑት ከ20 እስከ 25 አባላት ባሉት የቀራፂያን ቡድን መሆኑን የሚናገረው እስክንድር፤ “በፎቶግራፍ የተደገፉ የታሪክ መጽሐፍትን ይዘው፤ ጊዜው በቂ እንኳን ባይሆን [የሀውልቶቹን] ገጽታ ከዚያ ላይ እያጠኑ ሠርተዋል። ይህንን አይቻለሁ” ይላል።-ይሁንና የቅርጽ ሥራዎቹ ቀድመው ተጀምረው ለጥናት ሰፊ ጊዜ መሰጠት እንደነበር ይገልጻል።-የፎቶው ባለመብት Adanech Abiebie/fb-የአጼ ሚኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሀውልት በዓድዋ ሙዚየም-አርክቴክቱ እንደሚያስረዳው በዓድዋ ሙዚየም ውስጥ ከሚቀመጡት የቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች መካከል “ወሳኝ” የሆኑት ከነሐስ እንዲሠሩ በህንጻው ንድፍ ላይ ሰፍሯል። ይሁንና በአሁኑ ሰዓት ለሀውልቶቹ ግንባታ ጥቅም ላይ የዋለው ቁስ ሌላ መሆኑን አመልክቷል።-“እኛ ስናስቀምጥ ወሳኝ ሥራዎች በነሐስ እንዲሠሩ ተቀምጧል። የተያዘላቸው የሥራ ዝርዝር እንደዚያ ነው። በዚህኛው ግን አሁን ለማስመረቂያ ስለማይደርሱ፤ በመቀጠል የነሐስ ሀውልቶች እንደሚሠሩ ነው የማውቀው” ሲል በህንጻው ንድፍ ላይ በተቀመጠው መሠረት ሀውልቶቹ በድጋሚ ይሠራሉ የሚል እምነቱን ገልጿል።-ሀውልቶቹ አሁን የተሠሩበት ቁስም ቢሆን ግን ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ቅርፆችን ለመሥራት ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑን አስረድቷል።-ከቅርፅ ሥራዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱትን አስተያየቶች እንደሚጋራ የሚናገረው እስክንድር፤ “የአርት ሥራን መልሶ አሻሽሎ መሥራት፣ መለወጥ ይቻላል” ይላል። በአሁኑ ሰዓት ያልተሠሩት የቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች ሲከናወኑ “ከዚህ ልምድ ተወስዶ የሚቀጥለውን ሂደት በማሳተፍ፣ ጊዜ በመስጠት እና በጥናት ይበልጥ ቢኬድበት” የሚል ምክረ ሀሳቡን አስቀምጧል።-የሀውልቶቹን ሥራ ጨምሮ ከዋና ንድፍ ላይ ለውጥ የተደረገባቸው ነገሮች ቢኖሩም “90 በመቶ በሚባል ደረጃ” ያስቀመጠው አርክቴክቸር ወደ ተግባር መተርጎሙን እስክንድር ይናገራል። የዓድዋ ሙዚየም ግንባታ “በአስቸጋሪ” ሁኔታ ውስጥ የተከናወነ መሆኑን በመጥቀስም ጥሩ ሥራ መሠራቱን ያስረዳል።-ከሙዚየሙ ግንባታ ጋር የሜካኒካል፣ የኤሌክትሪካል እና የኦዲዮ ቪዥዋል ሥራዎችም “በጣም በከፍተኛ ሁኔታ” መከናወናቸውን በመግለጽ፣ በግንባታው ሂደት ጥቅም ላይ የዋሉት እቃዎችም ደረጃውን የጠበቁ እንደሆኑ አክሏል።-እስክንድር፤ “ለዓድዋ በሚመጥን መልኩ ያለንን ሁሉ ሰጥተን ሠርተነዋል። ለብዙ ጊዜ ሌሎች ሥራዎችን ሳንሠራ ሁልጊዜ እዚህ ጋር ነን። ማንኛውም እንደዚህ [ዓይነት] ኪነ ህንጻ ሲሠራ ፍጹም ሊሆን አይችልም፤ ብዙ ትችቶች እንደሚመጡ አውቃለሁ። ግን ባለን አቅም ሁሉ የምንችለውን ጥረት አድርገን [ሠርተነዋል]” ይላል።-እስክንድር ወደ ሦስት አስርት ዓመታት እየተጠጋ ባለው የሥራ ልምዱ ውስጥ ትልቁ ስለሆነው ፕሮጀክት ሲያነሳ፤ “በውጭም ዓለም ሙዚየምን የሚሠራ አርክቴክት ‘ዕድለኛ ነው’ ይባላል። በክፍለ ዘመን [አንዴ] የሚመጣ ዕድል ሊሆን ይችላል። እጅግ በጣም ዕድለኛ ነኝ” ሲል ስሜቱን ለቢቢሲ አጋርቷል።-የፎቶው ባለመብት Eskinder Woubtu
የፎቶው ባለመብት PA Media-ዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የምታዘዋውረው በትንንሽ ጀልባዎች ወደ ግዛቷ የሚገቡትን ለመከላከል በሚል ነው-ዩናይትድ ኪንግደም ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከግዛቷ ወደ ሩዋንዳ ለሚሰፍሩት ካላት እቅድ ለተወሰነው 370 ሚሊዮን ፓውንድ እንደምትከፍል የመንግሥት ወጪዎችን የሚከታተለው ተቋም ይፋ አደረገ።-ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በአምስት ዓመታት ውስጥ ወደ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ለሚዘዋወሩ ለእያንዳንዳቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች 150000 ፓውንድ ለሩዋንዳ መንግሥት ይከፍላል።-ሌበር ፓርቲ የኦሪት ጽህፈት ቤቱ ያወጣውን የገንዘቡን መጠን በተመለከተ “ብሔራዊ ቅሌት” ሲል የተቃወመው ሲሆን፣ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ግን “አንድ ነገር ለመሥራት ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል” ብሏል።-የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ “አሁን አንድ እርምጃ ካልወሰድን በ2026 ለጥገኝነት ጠያቂዎች መኖሪያ የሚወጣው ገንዘብ በየዓመቱ 11 ቢሊዮን ፓውንድ ይደርሳል” ሲሉ የውሳኔውን መነሻ አብራርተዋል።-የኦዲት ሪፖርቱ ይፋ የተደረገው የዩኬ ምክር ቤት አባላት ስደተኞችን ወደ ሌላ አገር የማዘዋወሩ ዕቅድን በተመለተ ከፍተኛ ግልጽነት እንዲኖር መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው።-ለአምስት ዓመታት በተደረሰው ስምምነት መሠረት፣ ዩናይትድ ኪንግደም በሕገወጥ መንገድ ወደ ግዛቷ የሚገቡ ሰዎችን ወደ ሩዋንዳ በመላክ እዚያ ጥገኝነት እንዲጠይቁ ይደረጋል።-የዚህ ፖሊሲ ዓላማም በእንግሊዝ ቦይ በኩል በባሕር የሚገቡ ሰዎችን ለማስቆም ሲሆን፣ ይህ ዕቅድም ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ከቀዳሚ ዓላማዎቻቸው መካከል አንዱ ነው።-ቢሆንም ግን ዕቅዱ የሕጋዊነት እንቅፋት ስለገጠመው በእንጥልጥል ላይ ያለ ሲሆን፣ አስካሁን አንድም ሰው ወደ ሩዋንዳ አልተዘዋወረም።-ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የተዘጋጀው ሕግ በፓርላማ አባላት የጸደቀ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ሳምንት ክርክር ይደረግበታል። ነገር ግን አሁን ይፋ የሆነው የገንዘብ መጠን ጉዳይ እንቅፋት ሊሆን ይችላል ተብሏል።-በዚህ መርሃ ግብር አማካይነት የዩኬ የአገር ውስጥ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለሩዋንዳ የምጣኔ ሃብት ድጋፍ እና ወደ አገሩ ለሚገቡት ሰዎች ሰዎች የሚውል ገንዘብ ይሰጣል።-ከአውሮፓውያኑ 2022 ጀምሮ አስካሁን ዩኬ 220 ሚሊዮን ፓውንድ ለሩዋንዳ የሰጠች ሲሆን በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታትም በየዓመቱ 50 ሚሊዮን ፓውንድ በመስጠት አጠቃላዩ 370 ሚሊዮን ፓውንድ ይሆናል።-ከ300 በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሩዋንዳ የሚላኩ ከሆነ፣ በአንድ ጊዜ 120 ሚሊዮን ፓውንድ እና ተጨማሪ በእያንዳንዳቸው ሰዎች 20 ሺህ ፓውንድ ተክፍላለች።-በተጨማሪም ወደ ሩዋንዳ ለሚዘዋወሩት ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእያንዳንዳቸው የመኖሪያ፣ የምግብ እና የትምህርት ወጪ የሚሆን 150874 ፓውንድ መድቧል።-ነገር ግን ግለሰቦቹ ከሩዋንዳ ውጪ የሚሄዱ ከሆነ ገንዘቡ የሚቆም ሲሆን ለጉዟቸው የሚሆን 10 ሺህ ፓውንድ ብቻ ይሰጣቸዋል።-የኦዲት ተቋሙ ባወጣው መረጃ መሠረት ይህ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለማዘዋወር የወጣው ዕቅድ በ370 ሚሊዮን ፓውንድ ላይ የሚቆም ሳይሆን ተጨማሪ ወጪዎች እንደሚኖሩት አሳውቋል።-ተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ በሚቀጥለው ምርጫ የሚያሸንፍ ከሆነ ወደ ሩዋንዳ ስደተኞችን ለማዘዋወር የተያዘውን እቅድ እንደሚሰርዘው አስታውቋል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላለፉት አምስት ዓመታት ያደረጉትን ጦርነት በንግግር ለመፍታት በመወሰን በዛንዚባር ንግግር የጀመሩት ከወራት በፊት ነበር።-በመጀመሪያው ዙር ድርድር ማን ምን ይፈልጋል የሚለውን የለዩበት አንደነበር የሚናገሩት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ወክለው የተሳተፉት አቶ ጅሬኛ ጉደታ ይህም ለሁለተኛ ዙር ድርድር መንገድ የጠረገ እንደነበር ይጠቅሳሉ።-ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው ንግግር በመልካም መግባባት ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ለሁለተኛ ዙር ድርድር በታንዛኒያ ዋና ከተማ ዳሬ ሰላም ተገናኝተው ነበር።-የሁለተኛው ዙር ድርድር በሁለቱም ወገን ደጋፊዎች በኩል መግባባት ላይ ተደርሶ የሰላም ንግግሩ በፊርማ ይጠናቀቃል የሚል እምነት አሳድሮ ነበር።-ለዚህም ምክንያት የሆነው ከፍተኛ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መሪዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መኮንኖች በንግግሩ ላይ መሳተፋቸው ነበር።-ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግሥትም ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮቹ በቀጥታ በውይይቱ ላይ ተሳትፈው ነበር።-በኦሮሞ ነጻነት ግንባር በኩል ዋና አዛዡ መሮ ድሪባ፣ ምክትሉ ገመቹ አቦዬ እና ሌሎችም ሲሳተፉ በኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ የነበሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንዲሁም የፍትህ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) ተሳታፊ ነበሩ።-በአደራዳሪነት ደግሞ አሜሪካ፣ ኖርዌይ እንዲሁም የኢጋድ ተወካዮች ሲሳተፉ፣ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድጋፍ መስጠቱን ቢቢሲ በወቅቱ ተሳታፊ ከነበሩ አካላት መረዳት አችሏል።-ይህ ከሳምንት በላይ በዝግ የተካሄደው ስብሰባ ባለመግባባት ተጠናቅቋል።-በወቅቱ ሁለቱ አካላት እንዳልተስማሙ ከመግለጻቸው በስተቀር ያላግባቧቸው ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ምንም ዓይነት ማብራሪያ እስከ ዛሬ ድረስ አልሰጡም።-የኦሮሞ ነጻነተ ሠራዊት አዛዥ መሮ ድሪባ ዋና አማካሪ የሆኑት እና በድርድሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩት አቶ ጅሬኛ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የዳሬሰላሙ ድርድር ለምን ሳይሳካ እንደቀረ ሲናገሩ “ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ” ጉዳዮች እንዳላግባቧቸው ተናግረዋል።-አቶ ጅሬኛ በዳሬሰላሙ ድርድር መጀመሪያ ላይ በሁለቱም ወገኖች በኩል ስምምነት ላይ ለመድረስ ቁርጠኝነት የነበረበት ነው ይላሉ።-“ለዚህ አንዱ ማሳያ ብዙ ጊዜ ተገድሏል ሲባል የነበረው መሮ ድሪባ እና ሌሎች የጦሩ አመራሮች መገኘታቸው ነው።”-አደራዳሪዎቹም ቢሆኑ እነ መሮ ይመጣሉ የሚል ሙሉ እምነት አንዳልነበራቸው የሚያስታውሱት አቶ ጅሬኛ “ሲመጣ ግን እኛንም አስደስቶናል” ሲሉ በወቅቱ የነበውን ስሜት ያስታውሳሉ።-እርሱን ከምዕራብ ኦሮሚያ ዳሬሰላም ለማምጣትም ቢሆን አደራዳሪዎቹ ከፍተኛ ኦፕሬሽን ማካሄዳቸውን ይናገራሉ።-“እንግዲህ ሁለተኛ ዙር ውይይት ላይ ብዙ ርዕሶችን አንስተን ተነጋግረናል። ግን ከእነዚህ ውስጥ ሁለት ዋና ዋና አከራካሪ ሀሳቦች አንዱ የአገሪቱ ወታደራዊ እና ደኅንነት እና የፖለቲካ ጉዳዮች" እንደነበሩ አቶ ጅሬኛ ጠቅሰዋል።-ዋና አከራካሪ የነበረው እና ያላስማማቸው ነጥብ በአገሪቱ የሚገኙ የፀጥታ አካላት አወቃቀር እና አመራርን በተመለከተ አካታች እንዲሆን የተነሳው ነጥብ ነው ይላሉ።-በዚህ ንግግር የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፌደራል እስከ ክልል ባሉ የፀጥታ አካላት አወቃቀር ላይ አካታች በሆነ መልኩ እንደገና እንዲዋቀሩ መጠየቁን አቶ ጅሬኛ ጠቅሰዋል።-“ሁሉንም ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ጨምሮ፣ አመራር ውስጥ ድርሻ ሊኖራቸው ይገባል የሚል አንስተናል። እነርሱ አልተቀበሉትም።”-ቢቢሲ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራር የአገሪቱ መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ ውስጥ እንዲካተት ስለመጠየቃቸው አቶ ጅሬኛን ጠይቆ ይኸው መከናወኑን አመልክተዋል።-“እዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር ያለባቸው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና መንግሥት ናቸው ብለን እናምናለን። በሌሎች ፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲካተቱ አንስተናል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።-በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኩል በኢትዮጵያ ከፍተኛ ችግር ነው ብሎ የሚያነሳው የፖለቲካ ጉዳይ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ጅሬኛ፣ “እርሱ መፍትሄ ስላላገኘ ነው ወደ ትጥቅ ትግል የገባነው” ይላሉ።-የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች ባሳተፈ ሁኔታ የዜጎች መብት የሚከበርበት፣ የሚዲያ ነጻነት የሚረጋገጠበት፣ ነጻ ምርጫ ቦርድ የሚኖርበት፣ የፖለቲካ ምኅዳሩ የሰፋበት ሥርዓት እንዲገነባ፣ የፍትህ አካላት ነጻነት እንዲኖራቸው በወቅቱ መጠየቁን ይገልጻሉ።-አቶ ጅሬኛ “ይህ ጉዳይ ሲነሳ መንግሥትን የወከሉ ተደራዳሪዎች አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ጥያቄ የለም። በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት ነው ሥልጣን የያዘው። ሕገ መንግሥቱን በጠበቀ መልኩ ትጥቃችሁን ፈትታችሁ ግቡ” የሚል ምላሽ መስጠቱን ያነሳሉ።-የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በበኩሉ “የሕዝብ ጥያቄ አለ፣ የአገሪቱን ወታደር እና የፖሊስ ኃይልን መንግሥት ይዞ ሕዝቡን እያፈነ እና ነጻነቱን እያሳጣ መሆኑን በመጥቀስ የራሱን ዕድል በራሱ አንዳይወስን እያደረገ መሆኑን” በመጥቀስ መከራከራቸውን ይናገራሉ።-“የአገር ጦር ሠራዊት ፖለቲካ ውስጥ መግባት የለበትም፣ ለፓርቲም ተገዢ አይሁን” ሲሉ መከራከራቸውንም አክለው ተናግረዋል።-“መንግሥት የራሱን ሥልጣን ለመከላከል የአገሪቱን ፖሊስ እና ወታደር እየተጠቀመበት ነው” የሚሉት አቶ ጅሬኛ፣ የፀጥታ ኃይሉ የተቃዋሚውም ሆነ የገዢው ፓርቲም መከታ መሆን አለበት ብለው ቢከራከሩም ከመንግሥት ወገን ይህ ተቀባይነት አለማግኘቱን አቶ ጅሬኛ ይናገራሉ።-መንግሥት የአገሪቱን ሕገ መንግሥት በተከተለ እና ባከበረ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን በመጥቀስ መከራከራሩን ጨምረው አስረድተዋል።-ሌሎች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ወሰንን በተመለከተ በወሎ፣ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ባከበረ እና ባለቤትነት በተረጋገጠ መልኩ እንዲሆን መጠየቃቸውን ገልጸዋል።-መንግሥት ይህንን ጥያቄ ሕገ መንግሥቱን በጠበቀ መንገድን እንመልሳለን የሚል መልስ መስጠቱን እና መግባባት ላይ መድረሳቸውን ያስረዳሉ።-ሌላው መግባባት ላይ የደረሱበት ኦሮምኛ የፌደራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆን የሚለው ጥያቄ መሆኑን ያነሱት አቶ ጅሬኛ፣ ይህም በሕገ መንግሥቱ መሠረት ተፈጻሚ አንደሚሆን መግባባታቸውን አመልክተዋል።-ድርድሩ ከተጠናቀቀ በኋላ በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በኩል መንግሥት መሮ ድሪባን ጨምሮ ለኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ሥልጣን ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን ተጠይቀው ይህንን አረጋግጠዋል።-“ለሺህ ሰው የሚሆን ከፌደራል እስከ ክልል የታችኛው መዋቅር ድረስ ሥልጣን የመስጠት ጥያቄ ለማቅረብ አስበው ነበር” በማለት አለመቀበላቸውን ተናግረዋል።-“እኛ እንደ ግል የጠየቅነው ሥልጣን የለም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሠራ ሥርዓት እንዲገነባ ነው የጠየቅነው። ያ ሥርዓተ ሲኖር በጦርነት እና በጉልበት ሕዝቡንም አታስቸግርም። . . . ሥልጣን የመጨረሻ ግባችን አይደለም። ጠንካራ ሥርዓትን መገንባት ነው። እነርሱ ደግሞ ሥልጣን የመጨረሻ ግባችን እንደሆነ አድርገው ነው ለግለሰቦች ሥልጣን ለመስጠት ያሰቡት።”-መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከሳምንት በላይ በዳሬ ሰላም ያደረጉት ድርድር ባለመስማማት መጠናቀቁን ተከትሎ የመንግሥት ተወካዮቸ አዳራሹን ጥለው መውጣታቸውን አቶ ጅሬኛ ይናገራሉ።-ለአቶ ጅሬኛ ሦስተኛ ዙር ድርድር ይኖራል ተብለው ተጠይቀው “የሁለተኛው ዙር ድርድር አጨራረስ ጥሩ ስላልነበረ ከአደራዳሪዎቹ ጋር ሳንነጋገር ቆይተናል” ይላሉ።-አደራዳሪዎቹ ሰሞኑን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮችን ስለ ሦስተኛ ዙር ድርድር ማነጋገራቸውን የተናገሩት አቶ ጅሬኛ “በተጨባጭ ግን መቼ እና የት ይካሄዳል የሚል ስምምነት የለም” ብለዋል።-የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ዋና አዛዥ ይገኝበታል ከሚባለው የምዕራብ ኦሮሚያ ድርድሩ ወደ ሚካሄድበት ዳሬሰላም ማን ወሰደው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል አቶ ጅሬኛ።-“ከመንግሥት ጋር አንድም ቀን መተማመን የለንም” ካሉ በኋላ፣ ነገር ግን አደራዳሪዎቹ ከመንግሥት ጋር መግባባት ላይ የደረሱበት ነገር መኖሩን ያነሳሉ።-መሮን ከነበረበት በሂሊኮፕተር አንስቶ ወደ ደምቢዶሎ ከተማ የወሰደው የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት መሆኑን ጠቅሰዋል።-ከደምቢዶሎም በአውሮፕላን ናይሮቢ፣ ከናይሮቢ ዳሬሰላም እንደሄደ አቶ ጅሬኛ ጨምረው ተናግረዋል።-ከድርድሩ በኋላስ የአማጺው ቡድን መሪ ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ለመመለስ ግን ያጋጠመ ችግር ነበር ይላሉ አቶ ጅሬኛ።-“የኢትዮጵያ መንግሥት ቃሉን አልጠበቀም። ቀይ መስቀል እና ሌሎቹ መካከላችን የነበሩ አካላት ወዳመጡበት የመመለስ ኃላፊነት ቢኖርባቸውም የኢትዮጵያ መንግሥት ባለመፍቀዱ መመለስ አንዳልቻሉ ነገሩን።”-“እኛ በራሳችን መንገድ ወደ መጡበት አንዲመለሱ አድርገናል፤ ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ” በማለት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ወደ አገር ውስጥ ገብተዋል ሲሉ ተናገረዋል።
የፎቶው ባለመብት Bahirdar Communication-በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።-በከተማዋ ሦስት ቀበሌዎች ዛሬ አርብ የካቲት 22/2016 ዓ.ም. ማለዳ 12፡00 ሰዓት ላይ ውጊያው መጀመሩን የተናገሩት አራት ነዋሪዎች፤ የከባድ መሳሪያ ድምጾችንም መስማታቸውን ተናግረዋል።-የክልሉ መንግሥት ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ በባሕር ዳር ዙሪያ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የፀጥታ ኃይል በጋራ በመሆን ሰርጎ ገብቷል ያለውን “ጽንፈኛ ቡድን በየቤቱ የማሰስ እና የማጽዳት ሥራ እየሠራ ይገኛል” ይገኛል ብሏል።-ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ቢቢሲ ያናገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በቀበሌ 14 አቡነ ሃራ እና ልደታ በሚባሉ የመኖሪያ ሰፈሮች፤ እንዲሁም ቀበሌ 11 አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራ ሰፈር እና ቀበሌ 13 በዓታ ቤተ ክርስቲያን ወይም ወራሚት አካባቢ ውጊያ መደረጉን ተናግረዋል።-አንድ የከተማዋ ነዋሪ “...ከጠዋቱ 12፡20 ጀምሮ ውጊያ ነበር። ቅርብ ለቅርብ የሚመስል የክላሽ ድምጽ ነበር። ይህም እስከ 1፡40 አካባቢ ድረስ የቀጠለ ነበር። በማስከተል ድግሞ የከባድ መሳሪያ፤ ትልልቅ መሳሪያዎች ድምጽ ይሰሙ ነበር” ብለዋል።-አባይ ማዶ በተባለው አካባቢ ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ የተኩስ ልውውጦች እንደነበሩ የተናገሩት ሌላ ነዋሪ፤ አየር ጤና በተባለው ሰፈር “ሌሊቱን ሙሉ” በመከላከያ እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እንደነበር ተናግረዋል።-በመኖሪያ ሰፈሮች አካባቢ ተደርጓል የተባለው የዛሬው ውጊያ ለአንድ ሰዓት ያህል ተጋግሎ መደረጉንና ረፋድ 3፡00 ሰዓት አካባቢ ጋብ ማለቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ከዚያም በኋላ ረፋድ ላይ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጾች ይሰሙ ነበር ብለዋል።-ትናንት ሐሙስ የካቲት 21/2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ “ውጊያ ሊኖር ይችላል ተጠንቀቁ” የሚል መረጃ እንደሰሙ የተናገሩት አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ጥዋት 12፡00 ሰዓት አካባቢ የተኩስ ድምጽ መስማታቸውን ተናግረዋል።-ግለሰቡ የተኩስ ልውውጡ በተደረገበት አንደኛው ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ ሲሆኑ፤ ይሰማ የነበረው “የተኩስ ልውውጥም በከባድ መሳሪያ የታገዘ ነበር” ብለዋል።-ውጊያ የመኖሪያ ሰፈሮች አካባቢ ላይ ቢደረግም እስካሁን ሰላማዊ ሠዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ለማወቅ እንዳልቻሉ የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ከተሰማ በኋላ በከተማዋ “ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም” ብለዋል።-“ትምህርት ቤት የሚሄዱ ልጆች ነበሩ። ምግባቸውን አዘጋጅተን ነበር [ትምህርት ቤት] ለመላክ። ነገር ግን 12፡00 ሰዓት አካባቢ ተኩሱ ሲጀመር . . . አስቀረናቸው። እኛም ሥራ አልሄድንም” ሲሉ በከተማዋን አርብ ጠዋት ላይ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።-የፋኖ ታጣቂዎች ሳይሆኑ አይቀሩም ያሏቸው “ታጣቂዎች” በሰፈራቸው በኩል ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን መመልከታቸውንም ጠቅሰው ውጊያው የረገበው “ለዚህ ይመስላል” ብለዋል።-“ከተማዋ ጸጥ ረጭ ብላለች” ያሉት ሌላ ነዋሪ፤ ከቤታቸው መውጣት ስላልቻሉ “ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልንም” ሲሉ እንቅስቃሴ እንደሌለ ተናግረዋል።-“ምንም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም። ሱቆች እና ሆቴሎች ሁሉም ተዘግተዋል። ሰው በመኖሪያ ሰፈሩ አካባቢ በር ላይ ብቻ ነው ቆሞ የሚታየው” ብለዋል።-የልጆች አባት እንደሆኑ የተናገሩ አንድ ነዋሪ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረው፤ “የንጹሃን እልቂት” ይደርሳል የሚል ፍርሃት እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር እና ከባሕር ዳር አዲስ አበባ ተይዘው የነበሩ በረራዎችን ለመሰረዝ መገደዱን ቢቢሲ አረጋግጧል።-ለዛሬ አርብ የተያዙ ስድስት የሚደርሱ በረራዎች መሰረዛቸው የታወቀ ሲሆን፤ በረራው መቼ ሊጀመር እንደሚችል “ማወቅ አይቻልም” ተብሏል።-ዛሬ ረፋድ ላይ መግለጫ ያወጣው የአማራ ክልል መንግሥት በባሕር ዳሩ ዙሪያ “ሰርጎ ገቦችን” መዋጋቱን ገልጾ፤ በውጊያ የበላይነትን መቀናጀቱን ጠቁሟል።-በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ የባሕር ዳር ከተማ እና አካባቢው “ጽንፈኛ” ሲል ከጠራው ቡድን እንደጸዳ እና በተጨማሪም የፋኖ አባላትን እያሰሰ መሆኑንም አስታውቋል።-የክልሉ መስተዳደር በመግለጫው “ሕግ ማስከበር” ላለው እርምጃ ሕዝቡ ከጎኑ በመቆም “ለሰላም ዘብ ሊሆን ይገባል” በማለት ጥሪ አቅርቧል።-በባሕር ዳር ከተማ በመንግሥት እና በፋኖ ኃይሎች መካከል ውጊያ ሲደረግ የዛሬው የመጀመሪያ አይደለም። ግጭቱ በተቀሰቀሰበት ጊዜ የፋኖ ታጣቂዎች ወደ በርካታ የክልሉ ከተሞች ገብተው የነበረ ሲሆን፣ በባሕር ዳር እና በዙሪያዋ ውጊያዎች መካሄዳቸው ይታወሳል።-በወቅቱም የመንግሥት ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች ከሕግ ውጪ ሰላማዊ ሠዎችን መግደላቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል በምርመራው ማረጋገጡን ከሰሞኑን ይፋ አድርጓል።-ይህኑ ግድያ በማስታወስ አንድ የከተማዋ ነዋሪ “ባለፈውም እንደሆነው ንጹሃን ያልቃሉ ብለን እንሰጋለን፤ የሚያሳስበን ነገር እሱ ነው” ሲል ተናግረዋል።-“...[የመንግሥት ኃይሎች] ‘እናንተ የፋኖ መደበቂያ ናችሁ፤ እናንተ ናችሁ እንደዚህ እንዲሆን የምታደርጉት’ ስለሚሉ ሠው ይፈራል። ለዚህ ይመስለኛል ሁሉም ነገር ጸጥ ያለው” በማለት ከዚህ ቀደም እንደሆነው ግድያ ይፈጸማል የሚል ስጋት እንዳለ ጠቁመዋል።-ሌላ ነዋሪም “የመንግሥት ኃይሎች “ፋኖን ትደግፋላችሁ” በሚል ሌላ አካባቢ እርምጃ ስለወሰዱ እኛ ላይም ይከሰታል የሚል ስጋት ሕዝቡ ላይ አለ” ሲሉ ስጋታቸውን ተናግረዋል።-ካለፈው ሳምንት መገባደጃ ጀምሮ በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ማገርሸቱ ታውቋል።-በተለይም በጎጃም እና በሸዋ አካባቢዎች “ከባድ ውጊያዎች” እተደረጉ መሆኑን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።-ከዚህም ጋር ተያይዞ ከደብረ ብርሃን ወደ ደሴ የሚወስደው መንገድ ከቅዳሜ፣ የካቲት 16/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱን የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት መወሰኑን ማስታወቁ ይታወሳል።-ካለፈው ዓመት አጋማሽ በኋላ የክልሉን ልዩ ኃይል ለመበተን እና ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ታጣቂዎች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።-የክልሉ መስተዳደርም ሁኔታው ከአቅሙ በላይ መሆኑን በመግለጽ የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ እንዲገባ በመጠየቁ በክልሉ እና እንዳስፈላጊነቱ በመላው አገሪቱ ተግባራዊ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጥሎ የፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት ወደ ክልሉ ተሰማርቶ ይገኛል።-ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በተካሄዱ ወታደራዊ ግጭቶች በበርካታ የክልሉ አካባቢዎች ውስጥ መደበኛ እንቅስቃሴዎች የተስተጓጎሉ መሆናቸውነ ነዋሪዎች ሲናገሩ ቆይተዋል።-በተጨማሪም በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ኃይሎች መካከል በሚካሄዱ ውጊያዎች እና በሚፈጸሙ ጥቃቶች ምክንያት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውነ እና የንብረት ውድመት ማጋጠሙ እየተዘገበ ነው።
የፎቶው ባለመብት GoFundMe-በአሜሪካ መንገድ ተሳስታ በገጠር የመኪና ጥርጊያ መንገድ ላይ መኪናዋን ያስገባችውን የ20 ዓመት ወጣት ተኩሶ የገደለው ግለሰብ በ25 ዓመት እስር ተቀጣ።-ሟቿ ኬይሊን ጊሊስ እና ጓደኞቿ ከጥቂት ወራት በፊት በኒውዮርክ ግዛት የሚሄዱበትን ድግስ (ፓርቲ) አድራሻ እየፈለጉ በነበረበት ወቅት ነው ወደ ግለሰቡ የጥርጊያ መንገድ በስህተት የገቡት።-ኬቨን ሞናሃን የተባለው ይህ ግለሰብ ጊሊስን አንገቷ ላይ በጥይት ከመታት በኋላም ሕይወቷ አልፏል።-የ66 ዓመቱ ግለሰብ በሁለተኛ ደረጃ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው በጥር ወር ሲሆን፣ ዐቃቤ ሕግ ከፍተኛው የተባለውን የ25 ዓመት እስራትም እንዲቀጣ ጠይቋል።-ዳኞቹም ግለሰቡን በግድያ ወንጀል እንዲሁም በግዴለሽነት የሰዎችን ሕይወት አደጋ ውስጥ በመክተት እና ማስረጃዎችን በማበላሸት ጥፋተኛ ሆኖ አግኝተውታል።-አርብ ዕለት ውሳኔው የተላለፈበት ሞናሃን በችሎቱ ላይ ለመናገር የተሰጠውን ዕድል ውድቅ አድርጓል።-ከፍርድ ቤቱም ሲወጣ አንድ ሰው “ፈሪ” በማለትም እንደዘለፈው የኤፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።-“በመኪና መንገድዎ ላይ ስላዞሩ ሰዎች ላይ በጥይት መተኮስ እንዲሁም መግደል እንደማይቻል ሊገነዘቡ ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ” ሲሉም ዳኛው አዳም ሚሼሊኒ መናገራቸውን የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ዘግቧል።-ጊሊስ እና ጓደኞቿ ከጥቂት ወራት በፊት ከአልባኒ በስተሰሜን ምሥራቅ 88 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኬብሮን በተሰኘች ትንሽ ከተማ ወደ ሞናሃን ረጅም እና ጠመዝማዛ የመኪና መንገድ የገቡት የድግስ አድራሻ ፍለጋ ነበሩ።-ይህች ገጠራማ ቦታም ደካማ የሞባይል አገልግሎት ያላት ናት ተብሏል።-ጊልስና ጓደኞቿን በዙሪያው ያገኘው ግለሰቡ “በወራሪዎች ተከብቤያለሁ” ብሎ እንዳሰበም ተናግሯል።-ሟቿ እና ጓደኞቿ የተሳሳተ ስፍራ ውስጥ እንደገቡ ሲያውቁ መኪናቸውን ሲያዞሩ ግለሰቡ ከቤቱ ወጥቶ ከበረንዳ ላይ ሁለት ጥይቶችን ተኩሷል።-ሁለተኛውም ጥይት መኪናውን ሲያሽከረክር ከነበረው የወንድ ጓደኛዋ አጠገብ የተቀመጠችውን ጊሊስን ያገኛት ሲሆን ሕይወቷም አልፏል።-የወንድ ጓደኛዋ ገዳዩን ሞናሃን “በፍጹም ይቅር ሊለው እንደማይችልም” ተናግሯል።-የሞናሃን ጎረቤት እንደተናገሩት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሞናሃን ተሳስተው በመንገዱ በሚያዞሩ ሰዎች በጣም እየተበሳጨ እንደነበር ተናግረዋል።-የጊሊስ ጓደኞች በመኪና መንገዱ ላይ የነበረውን የግል የሚለውን ምልክት እንዳላስተዋሉ በችሎቱ መስክረዋል።
የፎቶው ባለመብት Ethiopian Federal Police-በእሳት ከተቃጠሉ ንብረቶች አንዱ የሆነው ተሽከርካሪ-በስድስት ወራት ከደረሱት የእሳት ቃጠሎዎች 16 ያህሉ ሆን ተብለው የተፈጸሙ መሆናቸውን እና ከእነዚህም መካከል 15ቱ በአዲስ አበባ መከሰታቸውን የፌደራል ፖሊስ በፎረንሲክ ምርመራ ማረጋገጡን አስታወቀ።-በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በመላው አገሪቱ ከደረሱት የእሳት አደጋዎች መካከል 90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የደረሱት በዋና ከተማዋ ውስጥ እንደሆነ ፖሊስ ተገልጿል።-በ2016 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ በአገር አቀፍ ደረጃ 139 የእሳት ቃጠሎዎች መድረሳቸውን የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-ከእነዚህ የእሳት አደጋዎች ውስጥ 130 ያህሉ የተከሰቱት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መሆኑን ኃላፊው አመልክተው፣ ቀሪዎቹ ዘጠኝ ቃጠሎዎች የተከሰቱት በአፋር፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሐረሪ ክልሎች መሆኑንም አክለዋል።-የፌደራል ፖሊስ የእሳት ቃጠሎዎቹን መንስኤ ለማወቅ የፎረንሲክ ምርመራ ማድረጉን የሚገልጹት አቶ ጄይላን፤ በተደረገው ምርመራ ከስምንቱ ውጪ የሌሎቹ ቃጠሎዎች ምክንያት መለየቱን አስረድተዋል። ባለፉት ስድስት ወራት ለተከሰቱ የእሳት ቃጠሎዎች በቀዳሚነት የተጠቀሰው ምክንያት በኤሌክትሪክ የቴክኒክ ችግር መሆኑንም ጠቅሰዋል።-በዚህ ምክንያት የደረሱ የእሳት አደጋዎች ብዛት 76 መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ጄይላን፤ ይህ ቁጥር ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ተመሳሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ለ24 የእሳት አደጋዎች መነሻ በመሆን በሁለተኛነት የተቀመጠው ጉዳይ በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈጠር የመካኒካል ችግር እንደሆነ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አንስተዋል።-የፌደራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ እንደሚያመለክተው ሆን ብሎ የእሳት ቃጠሎ እንዲከሰት ማድረግ በስድስቱ ወራት ውስጥ ለተከሰቱት ቃጠሎዎች ሌላ ምክንያት ነው። በዚህ መልኩ በአዲስ አበባ ከተማ 15 እና በአፋር ክልል ደግሞ አንድ የእሳት ቃጠሎዎች ሆን ተብለው መከሰታቸውን አቶ ጄይላን ጠቅሰዋል።-ግለሰቦች የኢንሹራንስ ካሳ ለማግኘት፣ የራስን ጥቅም ለማስጠበቅ ወይም ሌላ ሰው ላይ ጉዳት ለማድረስ ሲሉ ሆነ ብለው የእሳት ቃጠሎ እንደሚያስነሱ እንደተሰደረበትም ገልጸዋል።-አቶ ጄይላን፤ “ኢንሹራንስ ለማግኘት ያረጀ ወይም አልሸጥ ያለ መኪና አቃጥለው ‘በእሳት አደጋ ነው’ ብለው ኢንሹራንስ [ጉዳቱን] እንዲሸፍንላቸው የሚፈልጉ አሉ” ሲሉ አንዱን ምክንያት ለቢቢሲ ጠቅሰዋል።-ይህ ዓይነቱ ቃጠሎ በብዛት በተሽከርካሪዎች ላይ እንደሚደርስ እና ቤቶችም እንደሚገኙበት አንስተዋል። ሆነ ብሎ የእሳት ቃጠሎ ከማስነሳት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች መኖራቸውን የጠቀሱት አቶ ጄይላን፤ ምን ያህል ሰዎች እንደተያዙ እና የደረሰውን አደጋ መጠን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።-የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደሚያስረዱት በስድስት ወራቱ ውስጥ በዚህ ዓይነቱ ምክንያት የደረሱት የእሳት አደጋዎች ብዛት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በስድስት ቀንሷል።-በአጠቃላይ ከደረሱት የእሳት ቃጠሎዎች መካከል 15 ያህሉ በቸልተኝነት እና በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት የተከሰቱ መሆናቸውን አቶ ጄይላን ተናግረዋል።-በስድስት ወራት ውስጥ በተከሰቱት የእሳት ቃጠሎዎች ምክንያት በሰው ላይ ስለደረሰው ጉዳት እና በንብረት ላይ የደረሰውን የውድመት መጠንን በተመለከተ የተሰጠ አሃዝ የለም።
-በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው ድሃ አገራትን ለመደጎም አዲስ በጀት ጸድቋል። ነገር ግን ለደረሰው ውድመት የላቀ ድርሻ ማዋጣት ያለበት ማን ነው? በሚለው ዙሪያ ክርክሮች አሉ።-በሌላ በኩል አዲስ በመበልጸግ ላይ የሚገኙ እንደ ቻይና እና ህንድ የመሳሰሉ አገራት ደግሞ ከምዕራባውያን ጋር እኩል ማዋጣት የለብንም የሚል ሃሳብ ያነሳሉ። ለመሆኑ በጀቱ ምንድን ነው? ለማንስ ነው የሚሰጠው?
የፎቶው ባለመብት REUTERS-ባለፉት ሳምንታት በቀይ ባሕር በኩል በመርከቦች ጭነት ማጓጓዝ ፈታኝ ሆኗል። በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማጽያን በሰው አልባ አውሮፕላን እና በሚሳኤል መርከቦች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ነው።-ታጣቂዎቹ በተጨማሪም በጀልባ እና በሄሊኮፕተርም ጥቃት አድርሰዋል።-አብዛኛውን የመን የሚቆጣጠሩት ሁቲዎች “በጋዛ እና በዌስት ባንክ ላሉ ፍልስጤማውያን ወንድሞች” ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል።-ወደ እስራኤል የሚጓዙ የንግድ መርከቦችን ዒላማ እንዳደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።-ቢቢሲ ባጣራው መረጃ መሠረት ሁቲዎች ጥቃት የሰነዘሩት በደቡባዊ ቀይ ባሕር ነው። ይህም በየመን ባሕር ዳርቻ በባብ ኤል-ማንዳብ መተላለፊያ ላይ ነው።-ወደ ኤደን ባሕረ ሰላጤ የሚጓዙ መርከቦች ላይም ጥቃት ተሰንዝሯል።-ነገር ግን በጥቃቱ ዒላማቸውን የመቱት የተወሰኑት ብቻ ናቸው። ከእነዚህም መካከል እአአ ጥር 17 የተፈጸመው ጥቃት ይገኝበታል።-በዚህም በአሜሪካ መርከብ ላይ ነበር ጥቃቱ የተቃጣው። ነገር ግን መርከቡ በሁቲዎች ድሮን ጎኑ ላይ ቢመታም ጉዞውን ቀጥሏል።-ጥቃቱን የሚያሳይ ምሥል ያነሳው የሕንድ የባሕር ተዋጊ መርከብ ነበር። ይህም የሁቲዎችን ጥቃት ለመመከት ያለውን ትብብር ማሳያም ነው።-የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን ነው ሁቲዎች የሚጠቀሙት።-በተለይ ደግሞ ሚሳኤሎች እና ድሮኖችን ይጠቀማሉ።-ቃስፍ-1 እና ቃስፍ-2 ድሮኖች አሏቸው። እነዚህም እስከ 200 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፉ ናቸው። እስከ 1800 ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘጉ መሣሪያዎችም አሏቸው። በ800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለ መርከብን ማጥቃት ይችላሉ ማለት ነው።-ሁቲዎች ትናንሽ ጀልባዎችን በመጠቀም መርከቦች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል።-ሄሊኮፕተር በመጠቀም መርከብ ላይ ጥቃት የሰነዘሩበትም ወቅት ነበር።-በሄሊኮፕተር መርከብ ላይ የወረዱት ጥቃት አድራሾች አንድ መርከብን አግተዋል። ጋላክሲ ሊደር የተባለው መርከብ አሁንም በየመን ባሕር ዳርቻ እንደተያዘ ነው።-የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ከአገሪቱ መንግሥት የተወሰዱ መሣሪያዎች በሁቲዎች እጅ ናቸው።-የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፣ ከምሥራቅ እስያ በሲቪሎች አማካይነት የተገኙም መሣሪያዎች አሏቸው።-አብዛኞቹ ዘመናዊ ድሮኖች እና ሚሳኤሎች ግን ከኢራን እንደተገኙ በስፋት ይነገራል።-አሜሪካ እንዳለችው፣ ከየመን ወደ ኢራን በዓሣ ማስገሪያ ጀልባ ተጭኖ እየተጓዘ የነበረ የሚሳኤል እና የአየር መቃወሚያ ይዛለች።-ወታደራዊ ተንታኞች እንዳሉት ኤምቪ ቤሻድ የተባለ የኢራን መርከብ ሁቲዎች ዒላማ እንዲመቱ እያገዘ ነው።-ቀድሞ ማጓጓዣ የነበረው መርከብ አሁን የደኅንነት መቆጣጠሪያ መሆኑን ያስረዳሉ።-ቢቢሲ ከኢራን መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ቢጠይቅም ምላሽ አላገኘም።-የፎቶው ባለመብት INDIAN NAVY-በቀጠናው የደኅንነት ቡድን የመሩት ክሪስ ፋረል እንደሚሉት፣ የተለያየ ቁሳቁስ የጫኑ መርከቦች ጥበቃ የሚደረግላቸው ቢሆንም ከአየር የሚደረግ ጥቃትን መከላከል የሚያስችል መሣሪያ ግን የላቸውም።-ይህ በቀይ ባሕር በኩል የሚያቋርጡ “የንግድ መርከቦች ከረዥም ጊዜ በኋላ የገጠማቸው ከባድ ችግር ነው” ይላሉ።-ዓለም አቀፍ ምላሽ ከመጠናከሩ ጋር በተያያዘ አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም በጋራ በየመን የሁቲ አማጽያን ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጽመዋል።-በዚህም ሁለቱ አገራት የአማጽያኑን ወታደራዊ አቅም ለማዳከም ያለመ ጥቃት ነበር የሰነዘሩት።-ሆኖም ግን የየመንን ሰፊ ተራራማ አካባቢዎች ሁቲዎች ይቆጣጠራሉ።-መደበቅ የሚችሉትም በዚህ ምክንያት እንደሆነ ወታደራዊ ተንታኞች ይናገራሉ።-ባለፈው ታኅሣሥ በአሜሪካ የሚመራ ወታደራዊ ጥምረት የንግድ መርከቦችን ለመጠበቅ እንደሚሠራ ተገልጿል።-በዚህም ቀይ ባሕርን የመቆጣጠር ሥራ የሚሠሩ ሲሆን ዩናይትድ ኪንግደም ለዚህ ተግባር መርከብ እንደምታቀርብ አስታውቃለች።-ከአሜሪካ ጥምረት ውጪ እንደ ፈረንሳይ ያሉ አገራትም በቀጠናው መቆጣጠሪያ ጣቢያ አላቸው።-የአሜሪካ የባሕር ኃይል ካፕቴን ብራድሊ ማርቲን እንደሚሉት የተለያዩ ዓለም አቀፍ አጋሮችን ማስተባበር ፈታኝ ነው።-ባሕሩ ላይ የሚከናወነውን ጥበቃ የሚያካሂዱትን መርከቦቹ ነዳጅ ሞልቶ መሣሪያ ማስታጠቅም ከፍተኛ ወጪን ይጠይቃል።-ከሁቲዎች የሚተኮሱትን እንደ ሲ ቫይፐር ያሉ ሚሳኤሎችን መከላከል በሚሊዮን ዶላር የሚያስወጣ ነው።-በተቃራኒው ሁቲዎች የድሮን ጥቃት ለመፈጸም የሚያወጡት በሺዎች የሚቆጠር ዶላር ነው።-የፎቶው ባለመብት EPA-በርካታ ተቋማት መርከባቸው በቀይ ባሕር እንዳይጓዝ እያደረጉ ነው።-ይህ ማለት ደግሞ ኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ በተባለው የአፍሪካ ዳርቻ መንገድ ለመጓዝ ከፍተኛ ወጪን ያወጣሉ ማለት ነው።-ለጅሙን የውቅያኖስ ላይ ዙሪያ ጥምጥም መንገድ በማስቀረት በቀይ ባሕር ለመጓዝ የመረጡ ደኅንነታቸውን ለመጠበቅ አማራጮች እየተጠቀሙ ነው።-አንደኛው መንገድ የመርከቦችን አቅጣጫ የሚጠቁም መከታተያ ሥርዓት መዘርጋት ነው። ይህም ኤአይኤስ ትራኪንግ ይባላለል።-የመከታተያ ሥርዓቱ የሁቲ አማጽያን መርከቦቹን እንዳያገኙ የሚያግዝ ነው።-አንዳንድ መርከቦች ደግሞ “ከእስራኤል ጋር ግንኙነት የለንም” ብለው መርከባቸው ላይ ይጽፋሉ።-መርከቡ ላይ “ታጣቂዎች አሉ” ወይም “ሠራተኞቹ ቻይናውያን ብቻ ናቸው” ብለው የሚጽፉም አሉ።-አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም በቅርቡ ጥቃት ቢፈጽሙም ሁቲዎች ጉዳት የማድረስ አቅማቸው እንዳለ መሆኑን ወታደራዊ ተንታኙ ያስረዳሉ።-“ጥቃቱን መቀነስ ይቻላል። ነገር ግን ችግሩ የሚፈታው ለጋዛ ግጭት ፖለቲካዊ መፍትሄ ሲሰጥ ነው። መርከቦችን በመከላከል ብቻ ጥቃቱን ማቆም አይቻልም” ይላሉ።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጋዛ እስከ ሰኞ ድረስ የተኩስ አቁም እንደሚኖር ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ገለጹ።-አስተያየቱን የሰጡት የእስራኤል እና የሐማስ ባለስልጣናትን አሳትፏል የተባባለ ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ላይ መጠነኛ መሻሻል እንዳለ በተዘገበበት ወቅት ነው።-ይህም እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ እርዳታ እንዲገባ እና መስከረም 26 የተፈጸመውን የሐማስ ጥቃት ተከትሎ የተወሰዱ ታጋቾችን መልቀቅን ያካትታል።-እስራኤል በጉዳዩ ላይ አስተያየት ባትሰጥም የሐማስ ባለስልጣናት ግን ባይደን እንደጠቆሙት ሁለቱ ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ ጫፍ ላይ እንዳልደረሱ ጠቁመዋል።-ከግብጽ ጋር ድርድሩን በማካሄድ ላይ የምትገኘው ኳታር ይፋ ሊደረግ የሚችል ምንም አይነት ስምምነት እንደሌለ ተናግራለች።-የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጅድ አል-አንሷሪ እንዳሉት ዶሃ "የረመዳን ጾም ከመጀመሩ በፊት ጦርነቱ እንዲቆም ታበረታታለች። ሂደቱ ተስፋ ቢኖረውም ብሩህ አይደለም" ብለዋል።-በደቡብ እስራኤል የሐማስ ታጣቂዎች ወደ አንድ ሺህ 200 የሚጠጉ ሰዎችን ከገደሉ በኋላ እስራኤል በጋዛ መጠነ ሰፊ እና የማያባራ ጥቃት መጀመሯ ይታወሳል።-ጥቃት አድራሾቹ 253 ሰዎችን አግተው የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የተወሰኑት ተለቀዋል።-በጋዛ እስራኤል እያደረገችው ባለው የተቀናጀ የአየር፣ የምድር እና የውሃ ላይ ጥቃት ቢያንስ 97 ሺህ 878 ሰዎች ሲገደሉ፤ 70 ሺህ 215 መቁሰላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በሐማስ አስተዳደር ስር ባለው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር መሰረት ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 96 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።-ሮይተርስ የዜና ወኪል ለድርድሩ ቅርብ የሆኑ ስማቸውን ያልገለጸው ምንጭን ጠቅሶ እንደዘገበው ሐማስ በፈረንሣይ የተቀረፀውን ረቂቅ የድርድር ማዕቀፍ በማጥናት ላይ ይገኛል።-ማዕቀፉ ሁሉም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ለ40 ቀናት እንዲቋረጡ እና በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ፍልስጤማውያን 1 ለ 10 ስምምነት ከእስራኤላውያን ታጋቾች መለዋወጥን ያካትታል።-ፕሬዝዳንት ባይደን ሰኞ ዕለት በኒውዮርክ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ከጫፍ ደርሰናል። እስካሁን ግን አልተጠናቀቀም። ተስፋዬ እስከሚቀጥለው ሰኞ ድረስ የተኩስ አቁም እናደርጋለን የሚል ነው" ብለዋል።-በኋላም በኤንቢሲ ላይ የቀረቡት ፕሬዚዳንቱ ስምምነቱ ከተደረሰ እስራኤል በረመዳን ጥቃቷን ለማቆም ፈቃደኛ ትሆናለች ብለዋል።-የረመዳን ጾም ከአስር ቀን በኋላ ይጀመራል።-“ረመዳን እየደረሰ ነው። ታጋቾቹን በሙሉ ለማውጣት እስራኤል ጊዜ ለመስጠት በረመዳንም እንቅስቃሴ እንደማይያደርጉ ስምምነት ተደርሷል" ብለዋል ባይደን።-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር በበኩላቸው “ንግግሮች ይቀጥላሉ። ከእነዚህ መካከል የአንዳንዶቹ የመጨረሻው ለሐማስ የሚተዉ ይሆናል” ብለዋል ።-ሚለር አክለውም ስለ ድርድሩ ወይም ስለሚሳካበት ጊዜ ተጨማሪ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆኑም “በዚህ ሳምንት መጨረሻ ከሆነ እሰየው… ይህንን ስምምነት እንዲደረስ እየሞከርን ነው። የሚሳካም ይመስለናል” ብለዋል።-አንድ የሐማስ ባለስልጣን ቀደም ሲል ለቢቢሲ እንደተናገሩት “ሐማስ ቅድሚያ የሚሰጠው እስረኞችን መለዋወጥ ሳይሆን ጦርነቱን ማቆም ነው።”-"ከዚህ ሁሉ የህይወት እና የንብረት ውድመት በኋላ ወደ ሙሉ የተኩስ ማቆም፤ የተፈናቀሉትን መመለስ እና የጋዛን መልሶ ግንባታ የማያመጣ ማንኛውንም ሐሳብ መቀበል ምክንያታዊ አይደለም።"-የእስራኤል ዋና አጋር የሆነችው አሜሪካ ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲቆም የሚጠይቀውን ውሳኔ በመቃወሟ ከፍተኛ ትችት አስተናግዳለች።-"በተቻለ ፍጥነት" ጊዜያዊ የተኩስ አቁም እንዲደረስም የራሷን የውሳኔ ሃሳብ አቅርባለች። እስራኤል የደቡብ ጋዛዋ ራፋህ ከተማን "አሁን ባለው ሁኔታ" እንዳትወር አስጠንቅቃለች።-እስራኤል 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጤማውያን በተጠለሉባት ራፋህ ላይ ጥቃት እንዳትሰነዝር ከፍተኛ የሆነ ዓለም አቀፍ ጫና ገጥሟታል። አብዛኞቹ በግዛቱ ያሉ ሰዎች በስተሰሜን ያለውን ጦርነት ሸሽተው የተጠለሉ ናቸው።-ባይደን በቃለ ምልልሱ ወቅት “በጣም ብዙ ንፁሀን ሰዎች እየተገደሉ ነው። እስራኤል በራፋህ የምታደርሰው ጥቃት ቀንሷል። ራፋህን ከሐማስ ነጻ ከማድረጋቸው በፊት አብዛኛውን ነዋሪ ለማውጣት ለእኔ ቃል ገብተውልኛል” ብለዋል።-እሑድ ዕለት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ራፋህን ጨምሮ ከሌሎች አካባቢዎች ንፁሀን ዜጎችን ለማስወጣት ያለመውን የአገሪቱን ጦር ዕቅዶች ተቀብያለሁ ብሏል።-ኔታንያሁ እሑድ ዕለት ከሲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የእስራኤል ኃይሎች ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረስም በራፋህ ላይ ወረራ እንደሚጀምሩ በመግለጽ “የመጨረሻውን የሐማስ ምሽግ ሳንሰባብር መልቀቅ አንችልም” ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።-"ስምምነት ከደረሰን በተወሰነ መልኩ ይዘገያል እንጂ ይከናወናል። ስምምነት ካልተደረሰ ግን እናደርገዋለን” ሲሉም አክለዋል።-ሰኞ ዕለት ደግሞ የፍልስጤም አስተዳደር ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሽታይህ ዌስት ባንክን በከፊል ከሚመራው መንግሥታቸው ጋር ስልጣናቸውን ለቀዋል።-ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ለአዲስ መንግስት መንገድ ይከፍታል የተባለውን የጠቅላይ ሚንስትሩን ውሳኔ ተቀብለዋል።-የእስራኤል እና የሐማስ ጦርነት ካበቃ በኋላ ጋዛን ለማስተዳደር የፍልስጤም አስተዳደር ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ አሜሪካ አባስ ላይ ግፊት እያደረገች ነው።-ኔታንያሁ ባለፈው ሳምንት ለለግዛቲቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሲገልጹ ስለ አስተዳደሩ ሚና ምንም አልጠቀሱም።
የፎቶው ባለመብት AFP-በቤት ላሂያ የሚገኘው ካማል አድዋን ሆስፒታል ከምዕራባዊቷ የጋዛ ከተማ አስክሬኖችንና የተጎዱ ሰዎችን መቀበሉን ገልጿል።-በጋዛ እርዳታ ለማግኘት በተሽከርካሪዎች ዙሪያ ተሰባስበው የነበሩ ቢያንስ 112 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ፣ 760 የሚሆኑት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።-ሐሙስ ዕለት በርካቶች የተገደሉበት ክስተት ያጋጠመው በምግብ እጦት የተሰቃዩት ሰዎች በጋዛ በስተደቡብ ምዕራብ በሚገኘው የባህር ዳርቻ መንገድ ላይ በእስራኤል ታንኮች ታጅበው እየተጓዙ ከነበሩ ተሽከርካሪዎች እርዳታ ለማውረድ ሲሞክሩ ነበር።-የእስራኤል ጦር፣ታንክ የተተኮሰው ለማስጠንቀቂያ እንደሆነና የእርዳታ ተሽከርካሪዎቹን እንዳልመታ ገልጿል።-ሆኖም አንዳንድ ፍልስጤማውያን የእስራኤል ወታደሮች ቀጥታ ወደ እነሱ እንደተኮሱባቸው ተናግረዋል።-አንድ ፍልስጤማዊ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አብዛኞቹ ሰዎች የሞቱት እርዳታ የጫኑት መኪኖች አሽከርካሪዎች ወደ ፊት ለመጓዝ በሚሞክሩበት ወቅት ተገጭተው ነው።-የግብፅን እርዳታ የጫኑ 30 ተሽከርካሪዎች በሰላማዊ ሰዎች የተከበቡት የእስራኤል መከላከያ ኃይል “የእርዳታ ማስተላለፊያ ኮሪደር” ባለው ቦታ እየተጓዙ ሳለ ነበር።-ይህ ክስተት ያጋጠመው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር በእስራኤል እና ሐማስ መካከል ግጭት ከተከሰተ አንስቶ 21 ሺህ ሕጻናትና ሴቶችን ጨምሮ ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን ካስታወቀ ከሰዓታት በኋላ ነው።-ሚኒስቴሩ ሰባት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች እንደጠፉ እና 70 ሺህ 450 የሚሆኑት ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸውም አክሏል።-የፎቶው ባለመብት ISRAEL DEFENSE FORCES-የእስራኤል ጦር በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በእርዳታ ተሽከርካሪዎቹ ዙሪያ ተሰባስበው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አውጥቷል።-ከላይ ሆነው የተነሱ የእስራኤል ምስሎች በተሽከርካሪዎቹ ዙሪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰባስበው ያሳያሉ። በማኅበራዊ ሚዲያ የተጋሩ ምስሎች ደግሞ ባዶ የእርዳታ መኪናዎች እና የአህያ ጋሪዎች ላይ የተጫኑ አስክሬኖችን አሳይተዋል።-በዚህ ክስተት 112 ሰዎች መገደላቸውንና 760 መጎዳታቸውን የገለጸው በሐማስ የሚተዳደረው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር እስራኤልን “ በጅምላ ጭፍጨፋ” ከሷል።-የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤትም በዚህ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር አስቸኳይ ዝግ ስብሰባ ለማካሄድ እቅድ ይዟል።-ፈረንሳይም የእስራኤል ወታደሮች ምግብ ለማግኘት የተሰባሰቡ ሰላማዊ ሰዎች ላይ መተኮሳቸው ፍትሐዊ አይደለም ብላለች።-የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በበኩላቸው ይህ ክስተት በእስራኤል እና ሐማስ መካከል ጊዜያዊ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በአደራዳሪዎች እየተደረገ ያለውን ጥረት ያወሳስባል ብለዋል።-ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) ክስተቱን “ አሰቃቂ” ያለው ሲሆን አስቸኳይ እና ዘላቂነት ያለው የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።-የፍልስጤም ፕሬዚደንት ሞሃሙድ አባስም “አስከፊ ጭፍጨፋ” በመፈፀም የእስራኤልን ኃይሎች ከሰዋል።-የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ድርጊቱን አውግዘው አስቸኳይ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ያለቅድመ ሁኔታ የእስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ በድጋሜ ጥሪ አቅርበዋል።-ሰሜን ጋዛ እስራኤል በመጀመሪያው ምዕራፍ ባካሄደችው መጠነ ሰፊ የምድር ጥቃት ውድመት የደረሰበት ሲሆን ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ሥፍራው መድረስ ከቆመ በርካታ ወራት ተቆጥረዋል።-ባለፈው ሳምንት የዓለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎቹ በእስራኤል ፍተሻ ጣቢያ አቅራቢያ በተራቡ ሰዎች በመከበቡ ወደ አካባቢው የሚያደርሰውን እርዳታ ለማቋረጥ መገደዱን ገልጿል።-ማክሰኞ ዕለት የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ባለሥልጣን በጋዛ ሰርጥ ካለው ሕዝብ ሩብ የሚያህለው [576 ሺህ ሰዎች] አስከፊ ለሆነ የምግብ እጥረት መዳረጋቸውን እና ከሁለት ዓመት በታች ከሆኑ ስድስት ሕጻናት አንዱ በከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጡን በመግለጽ አስጠንቅቀዋል።-በቅርብ ቀናትም በሰሜን ጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል አስር ሕጻናት በምግብ እጥረት መሞታቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።-ተመድ ወደ 300 ሺህ የሚገመቱ ሰዎች በተጠለሉባትና በቂ ምግብ እና ንጹህ ውሃ በሌለባት የጋዛ ሰሜናዊ ግዛት ረሃብ እያንዣበበ እንደሆነ አስጠንቅቋል።-የእስራኤል ጦር ሐማስን ለማጥፋት በሚል በምድር እና በአየር መጠነ ሰፊ ጥቃት የከፈተው ባለፈው ጥቅምት ወር የሐማስ ታጣቂዎች የእስራኤልን ድንበር ዘልቀው በመግባት 1 ሺህ 200 የሚሆኑ ሰዎችን ከገደሉ እና 250 ሰዎችን አግተው ከወሰዱ በኋላ ነበር።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ይልቅ የባይደንን ፕሬዚዳንትነት እንደሚመርጡ ተናገሩ።-ባይደን የበለጠ ልምድ ያላቸው እና ሊገመት የሚችል ባህርይ ያላቸው ሰው ናቸው ሲሉም መናገራቸው በርካቶችን አስደንቋል።-ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ከመወዳደራቸው በፊት ፑቲን “ታላቅ እና ጎበዝ” ሲሉም በአውሮፓውያኑ 2016 አሞካሽተዋቸው ነበር።-ባይደን የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ፑቲንን ለዓመታት በሰላ ሁኔታ በመተቸት የሚታወቁ ሲሆን ከዩክሬን ወረራ በፊትም በአንድ ወቅት “ነፍሰ ገዳይ” ሲሉ ወርፈዋቸው ነበር።-ፑቲን በቅርቡ ከአሜሪካዊው ጋዜጠኛ ታከር ካልርሰን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይም አስተያየት የሰጡ ሲሆን ጥያቄዎቹ የሰሉ እና የተስተካከሉ ስላልነበሩ እንዳሳዘናቸውም ተናግረዋል።-ረቡዕ ዕለት ከሩሲያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የባይደን አመራር ለሩሲያ የተሻለ እንደሚሆን የተናገሩት ፑቲን ምክንያቱንም ሲጠቅሱ “የበለጠ ልምድ ያለው፣ ሊገመት የሚችል ባሕርይ፣ ፖለቲከኛ እና መሰረት ያለው ሰው ነው” ብለዋል።-ከባይደን ዕድሜ እና የአዕምሮ ብቃት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን ውድቅ ያደረጉት ፕሬዚዳንት ፑቲን ከሶስት ዓመታት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ሲገናኙም የተለየ ነገር አለማስተዋላቸውን ተናግረዋል።-“በዚያን ጊዜም [ከሦስት ዓመታት በፊት] ሰዎች አቅም እንደሚያንሰው ይናገሩ ነበር እኔ ግን እንዲህ አይነት ነገር አላየሁም” ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።-አክለውም “አዎ የያዘውን ወረቀት እየተመለከተ ነበር እኔም እውነቱን ለመናገር የያዝኩትን ወረቀት እያማተርኩ ነበር። ስለዚህ ምንም የተለየ ነገር አልነበረም” ሲሉም ነው ያስረዱት።-ፐቲን አገራቸው “የአሜሪካን ህዝብ አመኔታ ካገኘ” እና የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ካሸነፈ ከማንኛውም መሪ ጋር እንደምትሰራም በዚሁ ወቅት አብራርተዋል።-ባይደንን ከትራምፕ ይልቅ ቢመርጧቸውም የዩክሬንን ጦርነት ያወገዙበትን መንገድ “እጅግ ጎጂ” እና “ስህተት የተሞላው” ነው ሲሉ ፑቲን ገልጸውታል።-በአውሮፓውያኑ 2016 የአሜሪካ ምርጫ ወቅር ትራምፕ ከፑቲን ጋር “በጥሩ ሁኔታ እንደሚግባቡ ጠቁመው” ነበር።-በመጪው የአሜሪካ ምርጫ የሪፐብሊካኑ ቀዳሚ እጩ የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል አገራት የሚጠበቅባቸውን መዋጮ ባለመክፈላቸው አገራቸው ከየትኛውም ወረራ እንደማትከላከልላቸው ለአንድ መሪ መንገራቸውን አስረድተዋል።-በአወዛጋቢ ንግግሮቻቸው የሚታወቁት ትራምፕ በነዚህ አገራት ላይ ሩሲያ ጥቃት እንድትፈጽም “እንደሚያበረታቱም” አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።-የኔቶ ዋና አዛዥ ጄንስ ስቶልተንበርግ በምላሹ ትራምፕ የህብረቱን የጋራ ደህንነት ዋስትና “እንዳያዳክሙ” ጠይቀዋል።
የፎቶው ባለመብት Reuters-አውሮፓ ሙሉ በሙሉ ራሷን የመከላከል አቅም ለማዳበር አስር ዓመት እንደሚያስፈልጋት ግዙፉ የጀርመን የመከላከያ ኩባንያ የሆነው ርሄይንሜታል ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።-የአህጉሪቱ የጦር መሳሪያ ክምችት “መመናመኑንም” ነው አርሚን ፓፐርገር የተናገሩት።-ኃላፊው ይህንን አስተያየት የሰጡት የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ግዙፍ የተባለውን የጦር መሳሪያ ማምረቻ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ለመጣል ሎወር ሳክሶኒ በተባለችው ግዛት በተገኙበት ወቅት ነው።-በዚህ ዝግጅት ላይ የጀርመን የመከላከያ ሚኒስትር ቦሪስ ፒስቶሪየስ እና የሆላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬደሪክሰንም ተገኝተው ነበር።-ለዚህ ሁሉ የጦር መሳሪያ ክምችት “መመናመን” ስጋት መነሻ የሆነው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቀናት በፊት የሰጡት አስተያየት ነው።-በመጪው የአሜሪካ ምርጫ የሪፐብሊካኑ ቀዳሚ እጩ የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል አገራት የሚጠበቅባቸውን መዋጮ ባለመክፈላቸው አገራቸው ከየትኛውም ወረራ እንደማትከላከልላቸው ለአንድ መሪ መንገራቸውን አስረድተዋል።-በአወዛጋቢ ንግግሮቻቸው የሚታወቁት ትራምፕ በነዚህ አገራት ላይ ወራሪዎች የፈለጉትንም እንዲያደርጉ “እንደሚያበረታቱም” አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።-ርሄይንሜታል በአዲሱ የጦር መሳሪያ ማምረቻ ላይ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ እንደሚያፈስም አስታውቋል።-ማምረቻው በየዓመቱ 200 ሺህ የሚሆኑ የከባድ መሳሪያ ጥይቶችን እንደሚያመርትም ተነግሯል።-ሆኖም “ኔቶን መዋጋት የሚፈልግ ወራሪ ከመጣ” ለጦር ዝግጅት ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት።-“በሦስት፣ አራት ዓመታት ጥሩ እንሆናል። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ለመዘጋጀት አስር ዓመት ያስፈልገናል” ብለዋል።-“በአውሮፓ በየዓመቱ 1.5 ሚሊዮን ጥይቶች ማምረት ይጠበቅብናል” ሲሉም ነው ኃላፊው ያስረዱት።-አውሮፓ የነበራት የጦር መሳሪያ ክምችት ዩክሬንን ለማገዝ የሄደ ሲሆን “ይህም የአገሪቱን ክምችት አመንምኖታል” ብለዋል።-“ጦርነት እስከቀጠለ ድረስ ዩክሬንን ልናግዝ ይገባል፤ ነገር ግን የሚያስፈልገንን የጦር መሳሪያ ክምችት ለመሙላት ቢያንስ አምስት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ለመዘጋጀት ደግሞ አስር ዓመት ያስፈልገናል” ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።-የጀርመኑ ቻንስለር ሾልዝ የትራምፕ አስተያየት ስጋት ፈጥሮባቸው እንደሆነ ቢጠየቁም ምላሽ ለመስጠት ባይፈልጉም የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ለካናዳ፣ ለአሜሪካም ሆነ ለአውሮፓ አገራት “ፍጹም አስፈላጊ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
ዳረን ፍራንኪሽ ለ17 ዓመታት ያክል ከባድ የራስ ምታት ሲያሰቃየው ኖሯል።-ይህ ራስ ምታት ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ጭንቅላቱን ከግድግዳ እያላተመ እና እየጮኸ ነው ስቃዩን የሚወጣው።-የ53 ዓመቱ እንግሊዛዊ ራስ ምታቱ ሲነሳ አንዳች ቅቤ የጠገበ ዱላ ጭንቅላቱን የመታው ያህል ይሰማዋለ። ይህ አልበቃ ብሎ ዓይኑን በጩቤ የተወጋ ያክል ያመዋል።-በእንግሊዝኛው ክላስተር ሄድኤክ የተሰኘ ስም ያለው ይህ ራስ ምታት እጅግ በጣም ስቃዩ የበዛ ነው።-“በኮቪድ ወቅት ወደ ሆስፒታል ስሄድ ትዝ ይለኛል። አውቶቡስ ሲመታ ዘለህ ግባ ግባ ይለኛል። ራስ ማጥፋት የሚያስመኝ ራስ ምታት ነው ቢሉ አይገርምም” ሲል ለቢቢሲ ይናገራል።-የሆርቲካልቸር ኢንጂነር የሆነው ዳረን “መች እንደሚጀምረኝ ስለማላውቅት በፍርሀት ነው የምኖረው” ይላል።-“ይህ ስነ-ልቡናዊ ስቃይ ነው። በየትኛውም ሰዓት ሊጀምረኝ ይችላል። በጣም ያስፈራኛል።”-ይህ ዓይነቱ ራስ ምታት ከ15 ደቂቃ ጀምሮ እስከ 3 ሰዓታት ሊቆይ የሚችል ሲሆን በቀን ሰባት አሊያም ስምንት ጊዜ ይነሳል።-ነገር ግን ዳረን ለ12 ሰዓታት የቆየ ራስ ምታት እንዳጋጠመው ያስታውሳል።-የፎቶው ባለመብት DOUG ARMAND/ GETTY IMAGES-ራስ ምታቱ ሲጀምረው በግራ ጭንቅላቱ በኩል ከግራ ዓይኑ ከፍ ብሎ ባለው ክፍል ነው።-ግራ ዓይኑ መቅላት ሲጀምር እና ውሀ ሲሞላው እንዲሁም አፍንጫው ሲደፈን እና ጭንቅላቱ በአንዳች ስቃይ ሲሞላ ራስ ምታቱ ጀመረ ማለት ነው።-“የማደርገው ይጠፋኛል። በትራስ ታፍኜ እጮኃለሁ። ጭንቅላቴን ወስጄ ከግድግዳ አሊያም ከአንዳች ጠንካራ ነገር ጋር አላትመዋለሁ። ብርሀን ካየሁ ስለሚብስኝ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እቀመጣለሁ።”-ዳረን አንዳንድ ጊዜ ውሀ የሚሞላውን ግራ ዓይኑን ሸፍኖ የእግር ጉዞ ለማድረግ እንደሚወጣ ይናገራል።-“ራስ ምታቱ ሲመጣብኝ ከማንም ጋር መነጋገር አልችልም” ይላል።-እሱ እንደሚለው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ራስ ምታቱ በተደጋጋሚ እየጎበኘው መሆኑ ሳያንስ ከተለመደው ጊዜ በላይ እየቆየ ነው።-ባለፈው ግንቦት ሁለት ጊዜ ወደ ሕክምና መስጫ እንዲሄድ ያደረጉት ሁለት ራስ ምታቶች እያንዳንዳቸው ለ12 ሰዓታት የቆዩ ናቸው።-ክላስተር ሄድኤክ የተሰኘው የራስ ምታት ዓይነት ከ1000 ሰዎች መካከል አንድ ሰው ነው የሚያጠቃው።-ይህ ማለት በዩናይትድ ኪንግደም 65 ሺህ ሰዎች በዚህ ራስ ምታት ይሰቃያሉ ማለት ነው።-“ይህ ከራስ ምታት በላይ ነው” ይላሉ የብሬይን ሪሰርች ዩኬ የጥናት ባለሙያዋ ኬቲ ማርቲን።-“ዳረን እንደገለጠው ይህ ራስ ምታት እጅግ ከባድ ነው። መሸከም የሚችሉት አይደለም። ሰዎች በስቃይ እንዲጮሁ የሚያደርግና ከራስ ምታቱ ለመገላገል ከግድግዳ የሚያላትም ነው።”-በዚህ ራስ ምታት የሚሰቃዩ አብዛኛዎቹ ሰዎች ዕድሜያቸው ከ30 በላይ ሰዎች ናቸው።-ይህ ራስ ምታት ብዙውን ጊዜ ከሴቶች በላይ በወንዶች ላይ ይስተዋላል።-አንዳንድ ጊዜ ይህ ራስ ምታት በጥቂት ቀናት እየቆየ ይመጣል፤ በሌላው ጊዜ ደግሞ ተጠቂዎችን በቀን በተደጋጋሚ ሊጎበኝ ይችላል።-ይህ ራስ ምታት ያለባቸው ሰዎች በተደጋጋሚ ሆስፒታል ሊጎበኙ ግድ ይላቸዋል።-የሕይወት ዘይቤን የሚያመሰቃቅለው ይህ ራስ ምታት ተጠቂዎችን ሥራ አልባ ሊያደርጋቸው ይችላል።-አልፎም ይህ ራስምታት ተጠቂዎችን ድባቴ ሊጥልና የራስ ማጥፋት አዝማሚያቸውን በሶስት እጥፍ ሊጨምረው እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ።-በሽታው መድኃኒት የለውም።-ዳረን ለመጀመሪያ ጊዜ ይህ ራስ ምታት የጀመረው በ37 ዓመቱ ነው።-“ከቤተሰቦቼ ጋር ልዝናና ወደ ፕራግ አቅንቼ ነበር። በጣም ኃይለኛ ራስ ምታት ሲጀምረኝ መጀመሪያ የመሰለኝ የጭንቅላቴ ዕጢ ነበር” ይላል የሁለት ልጆች አባት የሆነው ዳረን።-ይህ ራስ ምታት ከጀመረው ወዲህ እንደ ስቴሮይድ፣ ሊቲየም፣ የልብ ሕክምና እና የሚጥል በሽታ [ኤፒለፕሲ] መድኃኒቶችን ወስዷል።-“የሚጥል በሽታ የለብኝም። ነገር ግን ምናልባት ከሠራ በሚል መድኃኒት ሰጡኝ። ነገር ግን የትኛውም መድኃኒት ሊሠራ አልቻለም። አንዳንዴ የሚሠራልኝ በመርፌ የሚሰጥ መድኃኒት ነው።”-ዳረን ሕመሙን ለማስታገስ የሚውል ኦክሲጂን የሚያመነጭ ብልቃጥ ቤቱ አይጠፋም።-ሕመሙ እንዲቀልለት በሚል የተለያዩ ምግቦች ሞክሯል፤ ከአልኮል መጠጦችና ትምባሆ ማጨስ አቁሟል። ነገር ግን ሕመሙ ሊቆም አልቻለም።-“ቀጣዩ እርምጃ ወደ ጭንቅላቴ የሚሄደውን ነርቭ የሚከላከል መድኃኒት መወጋት ነው” ይላል።-ይህ ሕክምና በሽታውን ለጥቂት ጊዜም ቢሆን የሚያስታግስ ነው። ስቴሮይዱ ለአንድ ዓመት ያክል ራስ ምታቱ የሚመጣበት ጊዜ ሊቀንስለት ይችላል።-“ትዳሬ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል። ለፍቺዬ ምክንያት ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው። ልጆቼ የኔን ጩኸት እየሰሙ ማደጋቸው ያሳዝነኛል።”-ዳረን ለጊዜው ከዚህ ራስ ምታት ጋር ከመኖር ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የአል-ናስር አጥቂው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ሜዳ ላይ ባሳየው ድርጊት ምክንያት የአንድ ጨዋታ ቅጣት ተላለፈበት።-በሳዑዲ ፕሮ ሊግ የሚጫወተው ሮናልዶ “ደጋፊዎችን በመቀስቀስ” በሚል ነው የተቀጣው።-ሮናልዶ ቡድኑ አል-ናስር ከአል-ሸባብ ጋር ሲጫወት የሸባብ ደጋፊዎችን ለማበሳጨት ባሳየው ምልክት ምክንያት አንድ ጨዋታ ያመልጠዋል።-የአል ሸባብ ደጋፊዎች “ሜሲ፤ ሜሲ” እያሉ የሮናልዶን የረዥም ጊዜ ተፎካካሪ ለማብሸቅ ሞክረዋል።-መዲናዋ ሪያድ የተደረገውን ጨዋታ አል-ናስር 3-2 አሸንፏል።-የ39 ዓመቱ የፖርቹጋል አጥቂ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ እጁን ተጠቅሞ ለደጋፊዎች ባሳየው ምልክት አሳይቷል።-በተጨማሪ የሳዑዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተጫዋቹ 30 ሺህ የሳዑዲ ሪያል እንዲከፍል ፈርዶበታል።-ገንዘቡ ወደ ፓውንድ ሲመነዘር 6300 ገደማ ይሆናል።-የፌዴሬሽኑ የዲስፕሊን እና ሥነ-ምግብር ኮሚቲ እንዳለው ሮናልዶ የተወሰነበት ውሳኔ አሜን ብሎ ከመቀበል ባለፈ ይግባኝ መጠየቅ አይችልም።-በጨዋታው ሮናልዶ የመጀመሪያዋን ጎል በማስቆጠር ቢጀምር አል-ሸባብ ሁለት ጊዜ ከመመራት ተነስተው 2 አቻ ሆነዋል። ነገር ግብ በ87ኛው ደቂቃ ታሊስካ ባስቆጠራት ጎል አል-ናስር ባለድል ሆኗል።-ሮናልዶ፤ በነፃ ዝውውር ከማንቸስተር ዩናይትድ አል-ናስርን የተቀላቀለው በአውሮፓውያኑ ታኅሣሥ 2022 ነው።-ተጫዋቹ በዓለማችን እጅግ ከፍተኛውን ደሞዝ የሚያገኝ እግር ኳስ ተጫዋች እንደሆነ ይታመናል።-በያዝነው የውድድር ዘመን በ22 የሊግ ጨዋታዎች 20 ጎሎች ለቡድኑ ያስቆጠረ ሲሆን፤ አል-ናስር በሳዑዲ ፕሮ ሊግ ከአል-ሂላል ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።-ሮናልዶ አል-ናስርን ከተቀላቀለ በኋላ በሁሉም ውድድሮች በ48 ጨዋታዎች 42 ጎሎች አስቆጥሯል።
የፎቶው ባለመብት Office of the Prime Minister-Ethiopia-የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሊያ ጋር ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን ያሉት ዛሬ ማክሰኞ ጥር 28/2016 ዓ.ም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ውሏቸው ከሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ ጋር ከአንድ ወር በፊት የተፈራረሙት የባሕር በር ለማግኘት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።-ኢትዮጵያ እራሷን እንደ ነጻ አገር ካወጀችው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ካላገኘችው ሶማሊላንድ ጋር 20 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የባሕር ጠረፍ ለማግኘት የፈረመችው የመግባቢያ ሰነድ ሶማሊያን በእጅጉ አስቆጥቶ በቀጠናው ከፍተኛ ውጥረትን ያስከተለ ሆኗል።-ይህ ከሆነ ከ36 ቀናት በኋላ ለተወካዮች ምክር ቤት ገለጻ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አገራቸው ከሶማሊያ ጋር የመዋጋት ፍላጎት እንደሌላት ተናግረው፤ በስም ያልጠቀሷቸው “ኃይሎች” ኢትዮጵያን ከሶማሊያ ጋር ለማጋጨት እየሰሩ ነው ሲሉ ከሰዋል።-“የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የመጋጨት ፍላጎት ያለው አይመስለኝም - ስገምት። ግን ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች ሶማሊያን በእጅ አዙር መጠቀም ይፈልጋሉ። ለዚያ ደሞ’ እኛ አንመችም። ምንም አይነት የከፋ ነገር ለመናገርም፣ ለማደረግም ዝግጁ አይደለንም” ብለዋል።-አክለውም “ [ይህንን] የሚመኙ ኃይሎች ለአንዳንድ ዲያስፖራ ወንድሞቻችን ሚዲያ እንደከፈቱ ሁሉ ለአንዳንድ ሶማሌ ወንድሞቻችን የተወሰነ ነገር ሊያደርጉላቸው ይችላሉ፤ ሊያዋጉን ግን አይችሉም። ቢያንስ በእኛ በኩል አንዋጋም” ብለዋል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥታቸው ለሶማሊያ ሰላም እና አንድነት በመሥራት የሚወዳደረው አካልም እንደሌለም ጠቅሰዋል።-“ለሶማሊያ አንድነት እንደዚህ መንግሥት የሠራ የለም። ሶማሊላንድ እና ሶማሊያን ለማገናኘት ጥረት አድርገናል። ነገም ሶማሊያ እና ሶማሊላንድ ቢስማሙ የመጀመሪያ ተደሳች አገር ኢትዮጵያ ነች” ብለዋል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ከማንም መቀማት አንፈልግም። የማንንም ሉዓላዊነት መንካት አንፈልግም” በማለትም የመንግሥታቸውን አቋም አንጸባርቀዋል።-ሆኖም ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና ስለመስጠት እና ስለቀጣዩ እርምጃ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጡም።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ማብራሪያ አገራቸው “ከወራሪ” ይልቅ “የሰፈር ጎረምሳ” እንዳስቸገራት አንስተው የውጪ ኃይልን ለመመከት የሚያስችል በቂ አቅም እንዳላት ተናግረዋል።-“ኢትዮጵያ ማንም ወርራ አታውቅም፣ [ሌላ አገር] ወርሯት ደግሞ አሸንፏት አያውቅም። ሦስት አይደለም አስር ቢደመር ኢትዮጵያን ማሸነፍ አይችልም። እኛ አንዋጋም። አንፈልግም። ወደዚህ ከመጣ ደግሞ አይችልም። በቂ የሆነ አቅም አለን . . . ወደማንም አንሄድም፣ ማንም ከመጣብን ግን ራሳችንን እንከላከላለን። በሱ ስጋት አይደርባችሁ” ብለዋል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶማሌላንድ ከተፈራረሙት የባሕር በር ስምምነት በተጨማሪ ጨምሮ አገሪቷን እየናጧት እያሉ ግጭቶች እንዲሁም ድርቅ እና የኑሮ ውድነት እና የአገር ሀብት ምዝበራን አስመልክቶ ምላሾችን ሰጥተዋል።-በዛሬው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሏቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ረዘም ያለ ጊዜ ወስደው ምላሽ የሰጡት በአገሪቷ እየተነሱ ባሉ ግጭቶች ላይ ሲሆን፣ እነዚህም አንዳንድ ጅምሮችን አደናቅፏል ብለዋል።-በአማራ እና በትግራይ ክልል ያለውን የግዛት ይገባኛል ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ ለመመለስ የተጀመረው ጥረት በግጭቶች ምክንያት መደናቀፉን፣ በጉዳይ ላይ ሁለቱ ክልሎች መረጃ ከተሰጣቸው በኋላ ወደ ተግባር ለመግባት የተደረገው ጥረት አለመሳካቱን ጠቅሰዋል።-“በምሁራን፣ በሃይማኖት አባቶች፣ በሽማግሌዎች፣ በወጣቶች ወይይት እያደረግን በሕዝበ ውሳኔ፣ ሕዝቡ ወደ ፈለገበት እንዲመለስ እናድርግ ይህንን ካደረግን ዘላቂ ሰላም ልናመጣለን እንችላለን” ሲሉም ተደምጠዋል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ከዚህ ውጪ ያለው አማራጭ ግን ጊዜያዊ ድል ዘላቂ ሰላም አያረጋግጥም የሚል አቋም ወስደን ለሁለቱም ክልሎች ነግረን ሥራ ልንጀምር ስንዘጋጅ ግጭቶች አጋጠሙን” ብለዋል።-በወሰን ይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ሕዝበ ውሳኔ እና ውይይት እስኪካሄድ ድረስ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደቀያቸው እንዲመለሱ፣ እንዲሁም የራሳቸውን ተወካዮች መርጠው እንዲተዳደሩም መንግሥታቸው ይሠራል ብለዋል።-በመጨረሻም በሕዝበ ውሳኔ ህዝቡ በሚፈልገው መንገድ በአንደኛው ክልል በሚጠቃለልበት ሁኔታ ላይም መንግሥታቸው እንደሚሠራ ጠቅሰዋል።-በትግራይ እና በአማራ ክልል የሚነሱ የግዛት ይገባኛል ጥያቄዎች ዘላቂ ሰላምን በሚያረጋግጥ መልኩ ሊፈታ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።-“የወሰን ጥያቄዎችን በተመለከተ የፌዴራል መንግሥት 'እከሌን ገፍተህ የኔን ጥያቄ መልስ' የሚለውን መንገድ ሳይሆን ለሁሉም ክልሎች እኩል መፍትሔ የሚሰጠውን መንገድ ይከተላል” ብለዋል።-ቀጥለውም ከሕዝበ ውሳኔ ወጪ ያሉ ሌሎች አማራጮች ካሉ መንግሥት እንደሚቀበልም አንስተዋል።-“ከጦርነት መለስ ያለ ሌላ አማራጭ ካለ የፌደራል መንግስት ተባባሪ ነው” ሲሉም ተደምጧል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ከማለታቸው አንድ ቀን ቀድም ብሎ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከአማራ ክልል ጋር በይገባኛል እያወዛገቡ ያሉትን አካባቢዎች ጉዳይ በሕዝብ ውሳኔ መፍትሄ ለመስጠት ከስምምነት ተደርሷል መባሉን አስተባብሎ ነበር።-ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለፈው ሳምንት በመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን የወጣወን መግለጫ መነሻ አድርጎ የአከራካሪ ቦታዎችን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታት “ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ከአማራ እና ከትግራይ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ ነበር” ማለቱን በመጥቀስ ነው፤ “ፍጹም የተሳሳተ [ነው]” ሲል አስተባብሏል።-ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአገሪቱ ሕግ አውጪ አካል በሰጡት ማብራሪያ ላይ ጉዳዩ ለሁለቱም ክልሎች “መነገሩን” ገልጸዋል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ክልል የተለያዩ ማኅበረሰቦች ጋር ባደረጓቸው ቀደምት ውይይቶች የወሰን ይገባኛል ጥያቄ ከሦሰቱ መሠረታዊ ጥያቄዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።-ከወሰን በተጨማሪም ሕዝቡ የሚያነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች ልማት፣ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እንደሆነ ጠቅሰው እነዚህንም ጥያቄዎች ለመመለስ መንግሥታቸው እየሠራም እንደሆነ ተናግረዋል።-መንግሥት የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚል ባለፉት አምስት ዓመታት ሥራዎችን እየሠራ እንደሆነ አመልክተው፣ ከእነዚህም ውስጥ 3200 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው፣ 53 የመንገድ ፕሮጀክቶች ሥራን በዋቢነት አንስተዋል። ከዚህም ውስጥ 1300 ኪሎ ሜትር መጠናቀቁን ጠቅሰዋል።-ሌላኛው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቀሱት በ2.4 ቢሊዮን ብር በባሕር ዳር እየተገነባ ያለውን የዓባይ ወንዝ ድልድይን በአባሪነት አንስተዋል።-ድልድዩ በኢትዮጵያ ደረጃም በጥራቱም ሆነ በወጪው ተወዳዳሪ የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም መንግሥታቸው እየሄደበት ያለውን ርቀት አመላካች ነው ብለዋል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌላው ያነሱት በቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ እመርታ አለው ያሉትን የጎርጎራ ፕሮጀክት ነው። ቀጥለውም የፋሲል ቤተ መንግሥት እድሳት ተደርጎለት በአዲስ አበባ እንዳሉ ፕሮጅክቶች ገቢ እንዲያመጣ ሥራ ለመጀመር ቢታቀደም አለመሳካቱን አንስተዋል።-በክልሉ ውስጥ ታሪካዊ የሆነውን የፋሲል ቤተ መንግሥት የፈረሰው አካል እድሳት ቢታሰብም በተለያዩ አሉባልታዎች እና ሴራዎች ሥራው መቆሙን ነው የተናገሩት።-“[የፋሲል ቤተ መንግሥት እድሳት] በተለያዩ አሉባልታዎች እና ሴራዎች ሥራው እንዳይከናወን አስቁመውታል” ካሉ በኋላ “ጦርነትም” ሌላው ምክንያት እንደሆነ አስቀምጠዋል።-ጥገናውን ለማካሄድ ያላስቻሉትን “አሉባልታዎች” ያልጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የመደመር መጽሐፍን ሽያጭ በመጠቀም ለመጠገን ታቅዶም እንደነበር አመልከተዋል።-የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለማደስ ከፈረንሳይ መንግሥት ጋር በመተባበር እየተሠሰራ መሆኑን እንደ አንድ የመንግሥታቸውን ቁርጠኝነት ማሳያነት ያወሱት ዐቢይ፣ በጦርነቱ ምክንያት መስተጓጎል እየገጠመው እንደሆነም አልደበቁም።-በተጨማሪም በቱሪዝም፣ በመንገድ፣ በግብርና እና ኢንደስትሪ ዘርፎች ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።-ዐቢይ በክልሉ ላሉ ታጣቂ ኃይሎች በድጋሚ የሰላም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ አማራ ክልልን ጨምሮ በክልሎች ድጋፍ ከተደረገለት “እገረ መንገዱን የአማራ ክልል [የሕገ መንግሥት] ጥያቄ ይመልሳል” ብለዋል።-መሠረታዊ ባሉት የሕገ መንግሥት የማሻሻያ ጥያቄም ከዚህ ቀደም ባልነበረ መልኩ መስተናገድ የሚችልበትን ማዕቀፍ በመፍጠር በሕዝቦች ውይይት እና ምክክር አገሪቷ ዘላቂ ሕገ መንግሥት እንዲኖራት የሚያስችል ሥራ የምክክር ኮሚሽኑ እየሠራ ነው ብለዋል።-“ሕገ መንግሥት ከነገሥታት ጋር የሚቀየር ሁኔታ መሆን የለበትም። በውይይት ዘላቂ ሕገ መንግሥትም ለመቅረጽ እየተሠራ ነው” ብለዋል።-በሌላ በኩል “ሕገ ማስከበር አጠናክረን እንቀጥላለን። እጃችሁን አጣጥፋችሁ ተቀመጡ የሚለንን አንስማም፣ አንቀበልም፣ አናደርግም። መንግሥት ነን አቅም በፈቀደ መጠን እንሠራለን። ሕግ ለማስከበር ሰንሠራ በእያንዳንዷ ሰከንድ ለሰላም ዝግጁ የሆነ ኃይል ካለ ለሰላም ዝግጁ ነን” ብለዋል።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥታቸው ሸኔ እያለ ከሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር በቅርቡ ለሁለተኛ ጊዜ በታንዛንያ ተደርጎ ስላልተሳካው የሰላም ድርድር ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።-ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር የተደረገው የሰላም ውይይት ግልጽነት የጎደለው ነው የሚሉ ኃይሎች እንዳሉ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ንግግር ሲጀመር ለሕዝቡ መንግሥታችው ቀድሞ ማሳወቁን ጠቅሰዋል።-ንግግሩ ከተጠናቀቀ በኋላ ይህ ነው የሚባል ፍሬ ሃሳብ ላይ ባለመደረሱ መናገር ባይቻልም የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የአገሪቱን ሕግ እና ሥርዓት ባከበረ መልኩ ውይይት አድርጎ ተጨባጭ ነገር ላይ መድረስ ከተቻለ ለሕዝቡ ይፋ ይሆናል ሲሉ የመንግሥታቸውን አቋም አስታውቀዋል።-የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ጨምሮ በርካታ ተፋላሚ ወገኖች ወደ አገሪቱ ገብተው በሰላም እንዲታገሉ መንግሥታቸው ጥሪ ማድረጉን ያስታወሱት ዐቢይ፣ ኦብነግ፣ ኦነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ኢህአፓ በአገሪቱ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ብለዋል።-እነዚህ ወገኖች በተለያዩ ደረጃዎች በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ከ“ሸኔ ጋር” ምን ዓይነት መግባባት ተደርሶ ነበር? ምንስ ቃል ተገብቶላቸው ነው የሚሉ ጥያቄዎችን አጣጥለዋል።-ኦነግን ወክለው በአመራ ደረጃ አስመራ ላይ ከመንግሥት ጋር የተደራደሩ ሰዎች አብዛኛዎቹ አዲስ አበባ መሆናቸውን የተወሰኑትም በመንግሥት ኃላፊነት ላይ ናቸው ብለዋል።-“የተለየ የሰላም ውይይት ካለ ግማሹ እዚህ ገብተው የሚሠሩበት ከፊሎቹ ደግሞ ጫካ ገብተው ሕዝብ የሚያሰቃዩበት ምንም ምክንያት አይኖርም። ለሁሉም የቀረቡት ጥሪዎች ተመሳሳይ ናቸው” ብለዋል።-ሸኔ ሲሉ የጠሩት ኃይል በአሥመራ በተደረገው ድርድር ከመንግሥት የተገባለት ቃል ሳይሳካ ከሆነ ጫካ የገባው “ሕዝብን እየገደሉ፣ እየዘረፉ፣ እታገላለሁ ማለት ተቀባይነት የለውም” ሲሉም ተደምጠዋል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ደም አፋሳሽ ጦርነት የቋጨውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደዳር በትብብር ትላልቅ ድሎችን ማስመዝገብ የቻሉበት ነው ብለዋል።-አክለውም ለእነዚህ ሥራዎች የፌዴራል መንግሥት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በጋራ መሥራታቸውን ተናግረው ጊዜያዊ አስተዳደሩን አሞካሽተዋል።-እነዚህን ውጤቶች በአየር መንገድ፣ በቴሌኮም፣ በኢንደስትሪ፣ ትምህርት እና ጤና ዘርፎች በማብራራት፤ በመቀለ፣ በሽረ እና በአክሱም አየር መንገድ ሥራ መጀመራቸው የሰላም ስምምነቱ ውጤት ነው ብለዋል።-በቴሌኮም ከ20 ሺህ በላይ የቤት ስልክ መስመሮች መጠገናቸው፤ በትግራይ 600 የባንክ ቅርንጫፎች በብሔራዊ ባንክ 10 ቢሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ መለቀቁን፣ በኢንዱስትሪ 217 ፋብሪካ ሥራ መጀመራቸው እንዲሁም በግብርና 630 ሺህ ሄክታር መሬት መታረሱ ትልቅ ውጤት ነው ሲሉ አንስተዋል።-በክልሉ ያለውን የግብርና ዘርፍ ለማገዝ እንዲሁ 500 የሚሆኑ ትራክተሮች ለክልሉ ተገዝተው ጂቡቲ ወደብ መድረሳቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ዘርፎች ድጋፍ ቢደረግም በቂ እንዳልሆነም ነው የጠቀሱት።-ሆኖም ይህ ውጤት “በቂ አይደለም። የኢትዮጵያ አቅም ውስን ስለሆነ ነው እንጂ ከዚህ በላይ መታገዝ አለባቸው” ብለዋል።-ተፈናቃዮችን በመመለስ እንዲሁም የይገባኛል የግዛት ጥያቄዎች ሊመለሱ እንደሚገባ ጠቅሰው፣ መንግሥታቸው ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሥራዎችን አብሮ ያከናውናል ብለዋል።-በርካታ የረድዔት ተቋማት ኢትዮጵያ የከፋ ረሃብ ሊያጋጥማት እንደሚችል እያስጠነቀቁ ባለበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርቁን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ መጠቀም አግባብ አይደለም ሲሉ በዛሬው ውሏቸው ተደምጠዋል፡፡-በዘንድሮው ዓመት በትግራይ፣ በአማራ አና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ድርቅ መከሰቱን ገልጸው የዚህንም ታሪካዊ ዳራ ጠቅሰዋል።-“ድርቅ መንግሥት አላመጣውም፣ ችግኝ እንተከል ሲባል ምን ያደርጋል ስንል፣ ስንዴ እናምርት ስንል ምን ያደርጋል ብለን ድርቅ መጣ ብለን ብንጮህ ትርጉም የለውም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡-“በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም” ብለውም የተከሰተው ድርቅ የሰው ሕይወት እንዳይቀጥፍ መተባበር እንደሚገባ አሳስበዋል።-አንዱ ክልል ተርቦ አንዱ በልቶ ሊያድር አይችልም ሲሉም ገልጸው ባለፉት ጥቂት ወራት በትግራይ ክልል 5 መቶ ሺህ ኩንታል እህል በመንግሥት እና በሌሎች አካላት ትብብር ወደ ክልሉ ማድረስ መቻሉን አስረድተዋል።-መንግሥታቸው አንድም ቦታ በረሃብ የሚሞት ሰው አይቶ ዝም አይልም በማለትም በመተባበር ይህንንም ጊዜ እንዲሻገር እንደሚሠሩም አስረድተዋል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የስኳር በሽታ ዕድሜ ልክ አበሮ የሚቆይ ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የሚዳርግ ከባድ ህመም ነው።-ህመሙ የሚከሰተው ሰውነት በደምስር ውስጥ ያለን ስኳር (ግሉኮስ) በሙሉ በተገቢው መጠን ማመንጨት ሲያቅተው ነው።-ይህም እንደ የልብ ድካምን፣ ስትሮክን፣ ዐይነ ስውርነትን፣ የኩላሊት ሥራ ማቆምን ሊያስከስት እና ከወገብ በታች ያለን የሰውነት ክፍል ላይ ከባድ ጉዳትን ሊያስከትል ይችላል።-በመላው ዓለም በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። እንደ የተባበሩት መንግሥታት ከሆነ ባለፉት 40 ዓመታት የታማሚዎች ቁጥር በአራት እጥፍ ጨምሮ አሁን 422 ሚሊዮን ሰዎች በበሽታው ይሰቃያሉ።-የስኳር ህመም ምንም እንኳ አደገኛ ቢሆንም፣ በሽታው ካለባቸው ሰዎች መካከል ገሚስ የሚሆኑት የጤና እክሉ እንዳለባቸው እንኳ አያውቁም።-ነገር ግን የሕይወት ዘይቤን በመቀየር ለዚህ አደገኛ ህመም የመጋለጥ ዕድልን መቀነስ እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ።-ስንመገብ ሰውነታችን ካርቦሃድሬቶችን ወደ ስኳር (ግሉኮስ) ይቀይራል። በቆሽት ውስጥ የሚመረተው ኢንሱሊን የተባለው ሆርሞን የሰውነታችን ሕዋሳት ኃይል ለማመንጨት ስኳር እንዲይዙ ትዕዛዝ ይሰጣል።-ኢንሱሊን ሳይመረት ሲቀር ወይም በአግባቡ ሳይሰራ ሲቀር እና ስኳር በደማችን ውስጥ ሲከማች የስኳር በሽታ ይከሰታል።-የተለያዩ አይነት የስኳር በሽታዎች አሉ።-ዓይነት 1 በሚባለው የስኳር በሽታ ቆሽት ኢንሱሊን ማምረት አቁሞ ግሉኮስ በደም ቧንቧ ውስጥ ይከማቻል።-ተመራማሪዎች ይህ ለምን እንደሚሆን ትክክለኛውን ምክንያት ባያውቁትም በዘር እንደሚተላለፍ ወይም በቆሽት ውስጥ ኢንሱሊን የሚያመርቱት ሴሎች በኢንፌክሽን ሲጠቁ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አላቸው።-የስኳር በሽታ ካለባቸው አጠቃላይ ሰዎች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ዓይነት 1 የሚባለው የስኳር በሽታ አለባቸው።-ዓይነት 2 የሚባለው የስኳር በሽታ ደግሞ ቆሽት በቂ የሆነ ኢንሱሊን አያመርትም ወይም ሆርሞኑ በተገቢው ሁኔታ ሥራውን ሳያከናውን ሲቀር ነው።-ኢንሱሊን በቆሽት ውስጥ የሚመረት ሆርሞን ሲሆን፣ ሰውነታችን ስኳር እንዲዋሃድ የሚስችል ነው።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ብዙ ጊዜ የሚያጠቃው በመካከለኛ የዕድሜ ክልል ውስጥ እና ዕድሜያቸው የገፉ ሰዎችን ነው። ከልክ በላይ ውፍረት እና ብዙ እንቅስቃሴ በማያደርጉ ወጣቶች ላይ እንዲሁም በደቡብ እስያ በሚገኙ የተወሰኑ ዘሮች ላይ ይከሰታል።-አንዳንድ ነፍሰጡር ሴቶችም ከእርግዝና ጋር የሚመጣ የስኳር ሕመም ሊያጋጥማቸው ይችላል። ይህ የሚሆነው ሰውነት ለእናት እና ለጽንሱ በቂ የሆነው ኢንሱሊን ማምረት ሲያቅተው የሚከሰት ነው።-የተለያዩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ከ6 አስከ 16 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ከእርግዝና ጋር የሚመጣ የስኳር ሕመም ያጋጥማቸዋል።-በሽታው ወደ ዓይነት 2 እንዳይቀየር ነፍሰጡር እናቶች የስኳር መጠናቸውን በአመጋገባቸው ማስተካከል፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ወይም ኢንሱሊን መውሰድ ሊኖርባቸው ይችላል።-ከዚህ ውጪ ሰዎች ለስኳር በሽታ ተጋላጭ መሆናቸውን በምርመራ ሊያውቁ ይችላሉ። በሰውነት ውስጥ ከፍ ያለ የጉሉኮስ መጠን ወደ ስኳር በሽታ ሊያመራ ይችላል።-ከፍተኛ የድካም ስሜት፣ የማይቋረጥ የውሃ ጥም እና ከተለመደው ውጪ በተደጋጋሚ መሽናት በስፋት የሚስተዋሉ የስኳር በሽታ ምልክቶች ናቸው።-የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ በተደጋጋሚ የሚከሰት የሰውነት ቁስለት፣ ብዥ ያለ ዕይታ እንዲሁም ቀላል የሰውነት መቁሰል እና ቶሎ አለመዳን ሌሎችም በብዙዎች ላይ የሚስተዋሉ ምልክቶች ናቸው።-እንደ የብሪቲሽ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት ከሆነ ዓይነት 1 የስኳር በሽታ ምልክቶች ገና በለጋ ዕድሜ የሚስተዋል ሲሆን ሕመሙም ከባድ ነው።-ዓይነት 2 በተባለው የስኳር በሽታ አይነት ከባድ ጉዳት ላይ ሊወድቁ የሚችሉት ዕድሜያቸው 40 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣ በሽታው ያለባቸው እናት፣ አባት፣ ወንድም ወይም እህት ያላቸው ናቸው።-በተጨማሪም ከመጠን በላይ የሰውነት ክብደት ያላቸው፣ ከደቡብ እስያ አገራት አካባቢ የሆኑ ቻይናውያን፣ አፍሮ-ካረቢያን ወይም ጥቁር አፍሪካውያን ዝርያ ያላቸው ላይ ይከሰታል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-የስኳር በሽታ መከሰት የሚመሠረተው በዘር ወይም በአካባቢያዊ ሁኔታዎች ላይ ነው።-ይሁን እንጂ ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓትን በመከተል እና አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረግ የስኳር መጠንን መቆጣጠር ይቻላል።-ስኳርን በጥራጥሬዎች እና አትክልቶች በመተካት በደም ውስጥ ያለን የስኳር መጠን መቆጣጠር ያስችላል።-በፋብሪካ የተቀነባበሩ ጥፋጭ ምግቦችን እና መጠጦችን፤ ነጭ ዳቦ እና ፓስታን ማስወገድ ጠቃሚ ነው።-ነጭ የስንዴ ዱቄት፣ ነጭ ዳቦ፣ ነጭ ሩዝ፣ ነጭ ፓስታ፣ ለስላስ መጠጦች፣ እንደ ከረሜላ ያሉ ጣፋጮች ለጤና ጠንቅ ከመሆናቸው በላይ ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑት ንጥረ ነገሮቻቸው የወጡላቸው ናቸው።-የስኳር በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር አትክልት፣ ፍራፍሬ እና ጥራጥሬዎችን መመገብ ጠቃሚ ውጤት እናዳላቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ።-አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግም የስኳር መጠንን ለመቆጣጠር ጉልህ ጥቅም አለው። የብሪታኒያ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት በፍጥነት መራመድ እና ደረጃ መውጣትን ሊጨምር የሚችል በሳምንት ለ2.5 ሰዓት አንቅስቃሴ ማድረግን ይመክራል።-በደም ሰር ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ስኳር የደም ስሮችን በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ ይችላል።-ደም በሰውነት ውስጥ እንደልብ ካልተንሸራሸረ ደም ወደሚያስፈልገው የሰውነት ክፍል ላይደርስ ይችላል። ይህ ደግሞ ነርቭን ሊጎዳት፣ ዕይታን ሊያሳጣ እና በእግር ላይ ኢንፌክሽን ሊፈጥር ይችላል።-የዓለም ጤና ድርጅት ለዐይን ስውርነት፣ ለኩላሊት ሥራ ማቆም፣ ለልብ ድካም፣ ለስትሮክ እና ለሌሎችም ከባድ ጉዳቶች ዋነኛ ምክንያት የስኳር በሽታ ሊሆን ይችላል።-በአውሮፓውያኑ 2016 ላይ ለ1.6 ሚሊዮን ሰዎች ሞት ቀጥተኛ ምክንያቱ የስኳር በሽታ ነበር።-እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ከሆነ በአውሮፓውያኑ 1980 የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 108 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን፣ በ2014 ላይ አሃዙ ወደ 422 ሚሊዮን ከፍ ብሏል።-እንደ ዓለም አቀፉ የስኳር በሽተኞች ፌዴሬሽን ከሆነ፣ የስኳር በሽታ ካለባቸው 80 በመቶ ያህሉ የሚገኙት የአመጋገብ ሥርዓት በፍጥነት እየተቀየረባቸው በሚገኙት በመካከለኛ እና አስተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ነው።-እያደጉ ባሉ አገራት ውስጠ ያሉ ሰዎች ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑት በድህነት እና ርካሽ በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን ስለሚመገቡ ነው።
የፎቶው ባለመብት WAM-በጥቃቱ የተገደሉ የኤምሬትስ መኮንኖች አስከሬን ወዲያው ወደ አገራቸው ተወስዷል-በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና የባህሬን መኮንኖችን ጨምሮ አምስት የጦር መኮንኖች መገደላቸው ተገለጸ።-ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በተፈጸመው ጥቃት ሦስት የኤምሬትስ፣ አንድ የባሕሬን እና የሶማሊያ የጦር መኮንኖችን ጨምሮ ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።-ቢቢሲ ሶማሊኛ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ካልፈቀዱ የደኅንነት እና የስለላ ባለሙያ ባገኘው መረጃ መሠረት በጥቃቱ ከተገደሉት የአረብ ኤምሬትስ የጦር መኮንኖች መካከል ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ይገኙበታል።-በሶማሊያ ውስጥ ኤምሬቶች ካላት ሚና አንጻር ወሳኝ ሚና የነበራቸው ከፍተኛው ወታደራዊ መኮንን ኮሎኔል ሞሐመድ አል ማንሱር በጥቃቱ ከተገደሉት አንዱ ናቸው በማለት ምንጩ ገልጸዋል።-ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ መንግሥት የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው “የሽብር ድርጊት” ባለው ጥቃት የተገደሉት መኮንኖች የሶማሊያ ኃይሎችን በማሠልጠን ተልዕኮ ላይ ሳሉ ነበር።-ጥቃቱን የፈጸመው ግለሰብ ወደ ወታደራዊ ሠፈሩ በመግባት አሠልጣኞችን ዒላማ በማድረግ ተኩስ ከፍቶ ነው አምስት ሰዎችን ገድሎ ሁለት ሌሎችን ማቁሰሉን አንድ ወታደራዊ መኮንን እና የሆስፒታል ሠራተኛን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።-የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ጥቃቱን “አስከፊ የሽብር ድርጊት” በማለት አውግዘው፣ ሶማሊያን ከሽብርተኝነት ነጻ በማውጣት እና ሠራዊቱን መልሶ በመገባት ሂደት መስዋዕትነት የከፈሉ ላሏቸው መኮንኖች አድናቆታቸውን ገልጸዋል።-የጥቃቱን አስመልክቶ መግለጫ ያወጣው የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ከተገደሉት መኮንኖች አሃዝ ውጪ ዝርዝር መረጃ ያልሰጠ ሲሆን፣ ጥቃቱን ለመመርመር “ከሶማሊያ መንግሥት ጋር የሚያደርገው ትብብር እንደሚቀጥል” አመልክቷል።-በአረብ ኤምሬትስ በሚመራው የጦር ሰፈር ውስጥ ተኩስ ከፍቶ መኮንኖችን የገደለው እና ጉዳት ያደረሰው አህመድ በሚል ስም ብቻ የተገለጸው አዲስ ሠልጣኝ ወታደር ጥቃቱን በፈጸመበት ጊዜ ተተኩሶበት ተገድሏል።-“ወታደሩ አሠልጣኝ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና የሶማሊያ ወታደራዊ መኮንኖች በጸሎት ላይ ሳሉ ነበር ተኩስ የከፈተው። በጥቃቱ አራት የኤምሬትስ መኮንኖች ሲቆስሉ፣ አራት የሶማሊያ ወታደሮች ተገድለዋል” ሲል አንድ መኮንን ለሮይተርስ ገልጿል።-መኮንኑ ጨምሮም ጥቃት ፈጻሚው ወታደር በሶማሊያ እና በአረብ ኤምሬት ተመልምሎ ወደ ሥልጠና ከመግባቱ በፊት ከአል ሻባብ የከዳ የቡድኑ አባል ነበር።-ከአል ቃኢዳ ጋር ትስስር ያለው አል ሻባብ ባወጣው መግለጫ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን፣ ተዋጊዎቹ 17 ወታደሮችን መግደላቸውን ገልጿል።-ከተገደሉት ወታደራዊ መኮንኖች በተጨማሪም አስር የሶማሊያ ወታደሮች ቆስለው ወደ ህክምና መወሰዳቸውን የሆስፒታል ምንጮች ለሮይተርስ ተናግረዋል።-አል ሻባብ ሰፊ የሶማሊያ ግዛትን ተቆጣጥሮ በደካማው የሶማሊያ መንግሥት ላይ ዋና ከተማዋን ጨምሮ ከአስር ዓመታት በላይ የሽምቅ ጥቃቶችን ሲፈጽም ቆይቷል።-ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በከፈቱት ተከታታይ ዘመቻ አልሻባብ ከባድ ሽንፈት ገጥሞት ከአንዳንድ ይዞታዎቹ ለመልቀቅ ተገዷል።-ቢሆንም ግን ቡድኑ አሁንም በመንግሥት ኃይሎች እና በሌሎችም ላይ ከባድ ጥቃቶችን እየፈጸመ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን ቀጥሏል።
የእንዳ አባ ገሪማ ካሕናት የበዓል ልብሰ ተክህኗቸውን ለብሰው፤ ቀሳውስቱ የሚያብረቀርቅ መጎናጸፊያ አጊጠው የዕጣን ማጠኛ ጽንሃቸውን ይዘው፤ ዲያቆናት በመጾር መስቀል በወርቅ ዣንጥላ ተንቆጥቁጠው፤ መሪጌቶች ግራ እና ቀኝ የቤተ ክርስቲያኑ ዐውደ ምህረት መወጣጫ ላይ እዚህም እዚያም እጅብ ብለው ተቀምጠዋል።-በጥንግ ድርብ ልብሳቸው ተውበው እጄታቸው ከብር የተሠሩ መቋሚያቸውን ተደግፈው ለዐውደ ዓመት የሚወጣ ጽናጽላቸውን እንደያዙ ይጠባበቃሉ።-መሬት ላይ ግዙፍ ከበሮዎች ተደግፈው የተቀመጡ ልጅ እግር ሊቃውንት እንግዶቻቸውን ጥበቃ በር በር ያያሉ።-የአንድ ቀበሌ ሙሉ ሚሊሻዎች የጠመንጃቸውን ሰደፍ በመዳፋቸው ጨብጠው አፈሙዙን ትከሻቸው ላይ እንዳስደገፉ ግራ እና ቀኝ ተሰልፈው "ቱታ" እያሉ በፉከራ ወደ ቤተክርስቲያኑ ግቢ ዘለቁ።-የትምህርት ቤታቸው መለያ ልብሳቸውን የለበሱ ተማሪዎች፤ የሚበላ ምግብና የሚጠጣ ጠላ የተሸከሙ እናቶችን ከፊት አስቀድመው እንግዶቹን አጅበው ብቅ አሉ።-የአባ ገሪማ ገዳም ሊቃውንት እንግዶቹ መድረሳቸውን አይተው ከየተቀመጡበት ተነስተው ዐውደ ምህረቱ ላይ ተሰየሙ።-እልልታው ዝማሬውና ጭብጨባው ደመቀ።-የጉዞ ዓድዋ 1 የመጀመሪያ አምስት ተጓዦች ከአዲስ አበባ በእግራቸው 43 ቀናት ተጉዘው የዓድዋ ተራሮች ታሪካዊ መካነ እምብርቱ ላይ እንዳ አባ ገሪማ ገዳም የካቲት 21 ቀን 2006 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ ደረሱ።-የዶጋሊ እና የዓድዋው ጀግና ራስ አሉላ እንግዳ (አባ ነጋ) የእረፍት መካን፤ የዓለማችን ቁጥር አንድ ጥንታዊው መጽሐፍ ቅዱስ መገኛ፤ ግርማ ሞገስ ከተላበሱ የሰማይ ምሶሶ መሳይ ተራሮች መሐል የሚገኘው የእንዳ አባ ገሪማ ገዳም የንግሥ በዓል እንጂ እግረኛ ተጓዦችን ለመቀበል የወጣ አጀብ የማይመስል ትልቅ ትዕይንት አስተናገደ።-ሊቃውንቱ በቅኔ ስለ ዓድዋ ተቀኙ፤ መዘምራኑም ለዚያች ቀን በሰላም ያደረሰን አምላክ ይመስገን ሲሉ “ንሴብሖ” በማለት በወረብ ጀምረው በቸብቸቦ አሳረጉት።-ሁሉም ነገር ውብ ነበር። በፍጹም የማይረሳ!-የመጀመሪያው ጉዞ ዓድዋ።-ከሰባት ዓመታት በኋላ በ8ኛው ጉዞ ዓድዋ 97 ተጓዦች ከአዲስ አበባ ተነስተው ለ26 ቀናት 600 ኪሎ ሜትሮችን በእግራቸው ከተጓዙ በኋላ ለ10 ቀናት አላማጣ በሚገኝ አንድ ሕንጻ ውስጥ እንደ እስረኛ ታጉረው ተቀምጠዋል።-ከዛሬ ነገ “እንሄዳለን” በማለት በጉጉት የሚጠብቁት ተጓዦች፤ ዓድዋ ሳይደርሱ ጊዜው ሊጠናቀቅ መኾኑን በማሰብ በከፍተኛ መረበሽ ስሜት ውስጥ ሆነው አመላቸው ለራሳቸው ጭምር እስኪያታክታቸው ተሰላችተዋል።-የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የጉዞው መጠናቀቂያ ቀን ነበር።-ከአላማጣ 400 የኪሎሜትር ያህል ጉዞ ይቀራል፣ የቀረው ቀን ግን የአንድ ሳምንት ጊዜ ያህል ብቻ ነው።-በአማካኝ በአንድ ቀን ውስጥ 30 ኪሎ ሜትሮችን የመጓዝ አቅም ያላቸው ተጓዦች በቀራቸው ጊዜ ዓድዋ መድረስ እንደማይቻል ቢገባቸውም፤ በቀን እስከ 50 ኪሎ ሜትሮች በመጓዝ እንደርሳለን የሚል እልህ ውስጥ ቢገቡም በአንድ ቦታ “ታስረው” መቀመጣቸው ተስፋቸውን እያመነመነው መጥቷል።-ሕንጻው የመከላከያ ሠራዊት ጊዜያዊ ካምፕ ነው። የሲቪል አገልግሎት መስጫ የነበረው ባለ አራት ፎቅ ሕንጻ እና ቅጥር ግቢው በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ወደ ጦር ካምፕነት ተቀይሯል።-ወታደሮቹ ከተጓዦች ጋር በእጅጉ ተላምደዋል። ምግብ በጋራ ሲበስል ሽንኩርት በመላጥ ጭምር እያገዙ ሰንብተዋል።-በዚህ ቆይታ መሐል መርዶው መጣ።-ሰፊ አዳራሽ ውስጥ ከመቶ ያላነሱ ተጓዦች እና አስተባባሪዎች ለምክክር ተቀምጡ።-ከጉዞ አስተባባሪዎች መሐል አንደኛው ከአካባቢው የመከላከያ አመራሮች ጋር የተደረገውን ውይይት አጠር አድርጎ በማቅረብ ከዚህ በኋላ ያለውን ጉዞ ማድረግ በፍጹም የሚቻል አለመኾኑን አረዳቸው።-ድንጋጤ እና መረበሽ አዳራሹን ወረረው።-“ኮሌኔሉ እንደነገረን ከኾነ...” አለና መናገር ቀጠለ “ከዚህ በኋላ ያሉ መንገዶች በሙሉ የተቆራረጠ ውጊያ አለ። መሬቱ ፈንጅ ይኑረው አይኑረው አይታወቅም። እናንተን ዓድዋ ይዘን መድረስ የምንችለው በግራ እና በቀኝ አጅበን ሲሆን ብቻ ነው።-“ይህ ሆነ ማለት ደግሞ የወታደራዊ ቀጠና ትኩረት ስለምትስቡ ለጥቃት ያጋልጣችኋል...ከረዥም ርቀት በመድፍ ልትመቱ ወይንም በድንገት የሽምቅ ጥቃት ሊደርስባችሁ ይችላል።-“እኛም በሚፈጠሩ ጥርጣሬዎች ሁሉ ድንገተኛ እርምጃ ብንወስድ ሰላማዊ ሰው ሊጎዳብን ይችላል... መሔዳችሁም መቅረታችሁም ኪሳራ ነው... ከሁለቱ ኪሳራ ደግሞ የሚመረጠው መቅረታችሁ ነው። ምክንያቱም በመቅረታችሁ ከሞት ትተርፋላችሁ።”-የጉዞውን መቋረጥ የሰማ ተጓዥ አዳራሹን ወደ ለቅሶ ቤት ለወጠው።-“እኔ የማለቅሰው ዓድዋ ባለመድረሴ አይደለም” አለች አንዲት የሁለት ልጆች እናት የሆነች ተጓዥ ዕንባዋን እየዘረገፈች።-“እኔ የማለቅሰው ዓድዋ ባለመድረሴ አይደለም፤ ዓድዋ መድረስ ያልቻልኩበት ምክንያት ነው የሚያስለቅሰኝ። አገሬ እንዲህ ሆና እርስ በእርሳችን ተቋስለን መተያየት የማንችልበት ዘመን ላይ በመድረሳችን ለልጆቼ የማስረክባት አገር ተስፋ አልባነት ነው የሚያስለቅሰኝ።”-ጉዞ ዓድዋ የተመሰረተው በ2006 ዓ.ም. ከዛሬ ዘጠኝ ዓመታት በፊት ነበር።-ከተጓዦች መሐል የፊልም ባለሙያ የኾነው ሙሉጌታ መገርሳ አማሩ ለጉዞው ጥንስስ መነሻ ሀሳብ አፍላቂው እሱ ነበር።-ሙሉጌታ መገርሳ በፊልም ሙያ ውስጥ አዳጋች የሆኑ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን እና የአካል አደጋ ሊከስቱ የሚችሉ ትዕይንቶችን ዋናዎቹን ተዋንያን ተክቶ በመሥራት ተዋቂነትን ያተረፈ (ስታንት) ሙያተኛ ነው።-የራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ እና የፊልም ሙያተኛ የሆነው ጋዜጠኛ ብርሐኔ ንጉሤ ጋር በአንድ ወቅት ሙሉጌታ መገርሳ እና የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በጋራ በመኾን አጭር ፊልም ይሠሩ ነበር።-ወደ ዓድዋ የእግር ጉዞ የማድረግ ፍላጎታቸውንም አስረድተውት በምን ሊተባበራቸው እንደሚችል ይጠይቁታል።-ብርሐኔ ንጉሤ በሀሳቡ በመደሰቱ በዓድዋ ድል ላይ የሚሠሩ አንዲት ባለሐብት እንደሚያውቅ እና እሳቸውን ብናገኛቸው የጉዞውን ወጪ የሚሸፍን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተስፋ በማድረግ የሚችለውን እንደሚሞክር ገለጸ።-ጋዜጠኛ ብርሐኔ የተባሉትን ባለሐብት ለማግኘት እንደ መሰላል መጠቀም የፈለጋቸው ሰው ደግሞ እውቁ ፖለቲከኛ አቶ ስብሐት ነጋ (አቦይ ስብሐት) ነበሩ።-አቦይ ስብሐትን በስልክ እንዳናገራቸው እና ድጋፍ ያደርጋሉ የተባሉት ባለሐብት በአገር ውስጥ ባለመኖራቸው ነገር ግን እሳቸው ሀሳቡን የመስማት ፍላጎት ስላደረባቸው በማግስቱ ወደ ቢሯቸው በመሄድ ምክክር እንዲያደርጉ ጋበዟቸው።-አቦይ ስብሐት በሰዓቱ በቢሯቸው ተገኝተዋል። ጋዜጠኛ ብርሐኔ ይዟቸው የገባውን የቀረጻ ባልደረቦቹን አስተዋውቆ የጉዞውን ዓላማ አጠር አድርጎ አስረዳቸው።-አቦይ ስብሐት የጋዜጠኛ ብርሃኔን ገለጻ አይናቸውን ጨፍነው ሲያደምጡ ከቆዩ በኋላ ንግግሩን ሲጨርስ ለሌሎቹ ሁለት ሰዎች በጣታቸው እየጠቆሙ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቁ።-ሰውዬውን ከዚህ ቀደም አይቷቸው ለማያውቅ ሰው በደጅ ከሚነገረው ዝናቸው አንጻር ፍርሐት የሚያሳድር ምስል ያላቸው ቢኾኑም እንኳን በጽህፈት ቤታቸው ለተቀበሏቸው እንግዶች ፍርሐታቸውን የሚያስለቅቅ አቀራረብ ነበራቸው።-ሁለቱም በየተራ የጉዞውን ዓላማ በአጭሩ አስረዱ።-አቦይ ስብሐት ሁሉም ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ለአፍታ ቆይታ ዐይናቸውን እንደጨፈኑ ጸጥ አሉ።-ረጋ ባለ ድምጽ የተመጠኑ ቃላት ብቻ እያወጡ መናገር ጀመሩ።-ለዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ንግግራቸውን ቃል በቃል ወረቀት ላይ መዝግቦ ለማስቀረት የማያግድ ረጋ ያለ አቀራረብ ስለነበራቸው ጸሃፊው አንዱንም ቃላቸውን ሳያስቀር መመዝገብ ችሎ ነበር።-የእግር ጉዞ ማድረግ እምብዛም ከባድ አለመኾኑን ሳቅ በሚያጭር ንግግር አዋዝተው ከገለጹ በኋላ፣ ሐሳቡ ግን ግዙፍ መኾኑን ተናገሩ።-“እኛ ከደደቢት ተነስተን አዲስ አበባ የደረስነው እየተዋጋን ስለነበር 17 ዓመት ፈጅቶብናል። እናንተ ግን ውጊያ ስለሌለባችሁ እንኳን እንደኛ 17 ዓመት ይቅርና እንደ አፄ ምኒልክ ሠራዊት አምስት ወር አይፈጅባችሁም” ሳቅ ካሉ በኋላ ትንሽ አፍታ ወስደው መናገር ቀጠሉ።-“እንደ አፄ ምኒልክ ሠራዊት አምስት ወር አይፈጅባችሁም ያልኩት ደግሞ በየአገሩ አቀባበል እና ድግስ ስለማይበዛባችሁ ነው” ብለው ረዘም ያለ ሳቅ ሳቁ፤ ሁሉም በፈገግታ አጀቧቸው።-የተመጠኑ ቃላቶችን ተጠቅመው ሐሳባቸውን በሚገባ ካቀረቡ በኋላ፣ ጉዞ ምን ቢመስል ጥሩ እንደሚኾን ሐሳብ ሰነዘሩ።-ተጓዦች በዛ ማለት ቢችሉ እና የየጦር አዛዦችን እየወከሉ ቢጓዙ መልካም መኾኑን ተናገሩ። የጉዞው ፍጻሜ ቀንም ምን አይነት አቀባበል ሊኖር እንደሚገባ ጭምር ሐሳብ ሰጡ።-በመሐል ደግሞ የጉዞው ሐሳብ ቢኾን መልካም ነው ብለው ያሰቡትን መሪ መፈክር አቀረቡ።-“ይከበር ይዘከር ለዘላለም” ይህ ሐሳብ የዚያን ጊዜ ተመዘገበ። ጉዞ ዓድዋ በቆየባቸው ዓመታት ሁሉ የጉዞው መፈክር በመኾን አገልግሏል።-ስለ ጉዞው ወጪ ድጋፍ ጉዳይ “ሐሳባችሁን በጽሑፍ አቅርቡልኝና ለባለሀብቷ ሲመለሱ እሰጥላችኋለሁ” በማለት ንግግራቸው ጨርሰው እንግዶቻቸውን አሰናበቱ።-ጉዞ ዓድዋ በታቀደው የጉዞ መርሐ ግብር መሰረት የመጀመሪያው ቀን እየተቃረበ መጣ። በአቶ ስብሐት በኩል ይገኛሉ የተባሉት ባለሀብት ግን ወደ አገር አልተመለሱም።-የዚህን ጊዜ ጋዜጠኛ ብርሐኔ ንጉሤ ጉዞውን ራሱም ለመጓዝ መወሰኑን በመግለጽ ኪሳችን ውስጥ ባለን ገንዘብ ጉዞውን እንጀምረው በማለት ጓዶቹን አደፋፈረ።-ጉዞውን ለመጀመር የሚያስችል በጀት ባይኖርም እንኳን አዲስ አበባን ለቆ ለመውጣት መንግሥት ፍቃድ የሰጠበትን ደብዳቤ መያዝ አስፈላጊ በመኾኑ የጉዞውን ዓላማ የሚያስረዳ ደብዳቤ በመጻፍ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የፍቃድ ደብዳቤ እንዲሰጥ ጠየቅን።-ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጥ ዝምታን መርጦ ቆየ። የቀኑን ማጠር ግምት ውስጥ በመክተት አማራጭ ሐሳብ ተፈለገ፤ በወቅቱ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት አቶ ሬድዋን ሁሴን በዚህ ጉዳይ ላይ የትብብር ደብዳቤ እንዲጽፉ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ደውሎ ጠየቃቸው።-አቶ ሬድዋን ሁሴን ሀሳቡን እንደወደዱት እና በአስቸኳይ በማግስቱ ደብዳቤውን ከጽህፈት ቤታቸው መጥቶ መውሰድ እንደሚቻል ገልጸው ደብዳቤው ተጻፈ።-ለጉዞው ድጋፍ ያደርጋሉ የተባሉት ሰው በአገር ውስጥ ስላልተገኙ፣ አቦይ ስብሐት “በተስፋ ስላስጠበቅኳችሁ በመጠኑ እንዲረዳችሁ ከግሌ ይህንን ብር እንኩ” በማለት የጉዞ ዓድዋ የመጀመሪያ መዋጮ 15000 ብር በካኪ ጠቅልለው ሰጧቸው።-ለሎጂስቲክስ ማመላለሻ የሚኾን ከአዲካ ባለቤት ከአቶ አዋድ መሐመድ በውሰት በተገኘ ፒክ አፕ መኪና እና ከአቶ ስብሐት ነጋ በተበረከተ 15000 ብር ጉዞው ሊጀመር ቀን ተቆረጠ።-ጉዞ ዓድዋ ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ ተጓዦች ደብረ ብርሐን እስኪደርሱ ድረስ በየትኛውም ሚዲያ ይህ ጉዞ ሳይዘገብ በምስጢር ተይዞ ቆየ።-ጉዞ ዓድዋ ባሳለፋቸው ስምንት የጉዞ ዓመታት ሁሉ የአፄ ምኒልክ ጉዳይ አነታራኪነቱ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ ባለመምጣቱ በጉዞው ላይ ራሱን የቻለ በርካታ ገጠመኞችን አስተናግዷል።-አፄ ምኒልክ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዳር እስከዳር በአንድነት አሰልፈው ጦሩን በብቃት መርተው ለውጤት ያበቁ በዓለም የነጻነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና የነበራቸው ሰው መኾናቸው እንኳንስ ታሪክ እያጠና ለሚጓዝ የጉዞ ዓድዋ አባል ይቅርና ለማንኛውም ሰው ግልጽ የሆነ እውነታ ነው።-የመጀመሪያው የጉዞ ፈተና ተብሎ ሊወሰድ የሚችለው በአፄ ምኒልክ ዙሪያ በጉዞው ጅማሬ ወቅት ሚዲያውን ተቆጣጥሮት የነበረው ትርክት ነው ብሎ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ያምናል።-በተለይም ከአኖሌ ሐውልት መመረቅ ጋር በተያያዘ በወቅቱ በቴሌቪዥን ቀርቦ የነበረው ዘገባ እና እሱን ተከትሎ በርካታ የወቅቱ ጋዜጦች እና መጽሔቶች፣ ከዚያም አልፎ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ለዘገባው የሰጧቸው ምላሾች የዳግማዊ አፄ ምኒልክን ስም አንስቶ ጉዞ ለሚያደርግ ሰው የደኅንነቱ ጉዳይ አሳሳቢ ነበር።-በዚህም ምክንያት ጉዞው ደብረ ብርሃንን ከማለፉ በፊት በየትኛውም ሚዲያ ሳይዘገብ በምስጢር ተይዞ ቆየ።-በጉዞ ዓድዋ 1 ፍጻሜ ወቅት የካቲት 23 ቀን 2006 ዓ.ም. በዓድዋ ከተማ በሚገኘውና “ሰልፍ ሜዳ” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የከተማው ሕዝብ ነቅሎ ወጥቶ ተጓዦችን በክብር በተቀበለበት ሥነ ሥርዓት ላይ ጋዜጠኛ ብርሐኔ ንጉሤ በመድረኩ ላይ ያቀረበው ንግግር የመጀመሪያ አረፍተ ነገር የዳግማዊ አፄ ምኒልክን እና የእቴጌ ጣይቱን ስም አክብሮ በመጥራት የሚጀምር ነበር።-በሚቀጥሉት ተከታታይ ሦስት ዓመታት በተመሳሳይ መልኩ ዓድዋ ከተማ በሚገኘው ሰልፍ ሜዳ ላይ የዓድዋ ድል በዓል ቀን በደማቅ ማክበር ተለመደ።-በዚህችም ወቅት ሕዝቡ ግልብጥ ብሎ በመውጣት አዳራቸውን የሶሎዳ ተራራ አናት ላይ አሳልፈው የሚወርዱትን ተጓዦች በክብር ተቀብሎ አደባባዩ ላይ በተዘጋጀው መድረክ በጉዞው መሪ ንግግር ይደረጋል።-በዓድዋ እና አካባቢው ያሉ ታዳጊ ተማሪዎች ተጓዦችን ለመቀበል ሰልፍ ሜዳ የሚገኘውን ሕዝብ ትተው ወደ ተራራው አናት ቧጠው በመውጣት ለተጓዦች አቀባበል ማድረግም ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ልማድ ሆነ ቆዬ።-የዚህ ጊዜ አንድ ችግር ተፈጠረ። የሶሎዳ ተራራን ሽቅብ ወጥተው ተጓዦችን የሚቀበሉ ታዳጊ ተማሪዎች ያለ መሪ እና ደጋፊ በቁጥቋጦ የተሸፈነውን እና በሚናዱ አለቶች የተሞላው ግዙፍ ተራራ የታዳጊ ተማሪዎቹን እሽቅድድም ማስተናገድ ወደማይችልበት ደረጃ ደረሰ።-አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በተከሰተ የአለት ናዳ ምክንያትም ዕድሜያቸው 11 እና 12 የሆነ ሁለት ታዳጊዎች ሕይወት አለፈ።-በዓሉ በሰልፍ ሜዳ ላይ ተከብሮ እንደተጠናቀቀ የታዳጊዎቹ ሞት ተሰማ። ተጓዦች የጉዞ ፍጻሜ ስኬታቸውን በፌሽታ የሚያሳልፉበት ቀን በቅጽበት በሐዘን ተዋጠ።-ሁሉም ተጓዥ ወደ ሟች ሕጻናቱ ቤተሰቦች እና ቤተክርስቲያን በነበረው የቀብር ሥነ ስርዓት ላይ ለመታደም ሄዶ ሁሉም ሲላቀስ ውሎ አመሸ።-ይህ አጋጣሚ በታሪካዊው የዓድዋ ድል ዕለት ከነበረው ስሜት ጋር ተመሳስሎሽ ነበረው። ኢትዮጵያውያን የጣልያንን ጦር ሙሉ ለሙሉ ደምስሰው ድል በእጃቸው ማስገባታቸው ፌሽታ ሲፈጥር፤ ከኢትዮጵያ ወገን የወደቁ እልፍ ጀግኖች ሰማዕታት ደግሞ በጎን ይለቀስላቸው ነበር።-ከጉዞ ዓድዋ አንድ አንስቶ በተከታታይ ለአራት ዓመታት ያህል ግን በኦሮሚያ ክልል ከ80 ኪ.ሜትር ያልበለጠው የጉዞ መስመር እስኪታለፍ ድረስ በይፋ ከአዲስ አበባ ሽኝት ተደርጎ አያውቅም።-ነገሩ የተቀየረው በኅዳር ወር 2010 ዓ.ም የጣና ሐይቅ በእንቦጭ አረም መወረሩን ተከትሎ በወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ እና በወቅቱ የነበሩ የኦህዴድ ባለሥልጣናት ወደ ባሕር ዳር ከክልሉ የተሰባሰቡ ወጣቶች እና የአገር ሽማግሌዎችን አስቀድመው “ጣና ኬኛ” በሚል መፈክር ባሕር ዳር ከተማ ባቀኑበት ጊዜ ነበር።-በዚህ ዓመት ተዘጋጅቶ በነበረው 5ኛው ዙር ጉዞ ዓድዋ ተሳታፊ የነበሩ 25 ተጓዦች ጥር 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ሆቴል ውስጥ በተዘጋጀ የመጀመሪያው የጉዞ ዓድዋ የሽኝት መርሐ ግብር በጥሩ መልኩ ተከናወነ። ተደብቆ የአምስት እና የስድስት ቀናትን መንገድ መጓዝ ቀረ።-ከዚያም አልፎ ከአዲስ አበባ መውጫ በር ጀምሮ ያሉ ሁሉም የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ለተጓዦች በሬ ጥለው ጭምር አቀባበል ማድረግ ጀመሩ። የነበረው ስጋት በሙሉ ተነነ።-በየመንገዱ ላይ ያጋጥሙ የነበሩ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች ተጓዦችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ሽሚያ ጀመሩ። “ድግስ ሲበዛ መንገድ ይረዝማል” የሚለው የአቶ ስብሐት ንግግር እውነት ሆኖ ተገኘ።-በአምስት ቀናት ውስጥ ይታለፉ የነበሩ መንገዶች ሰባት ቀናት እንዲወስዱ ድግስ ምክንያት ሆነ። የአፄ ምኒልክን ስም ማንሳትም ሆነ ድምጽን ከፍ አድርጎ እየዘመሩ ለመጓዝ የማያሰጋ ብቻ ሳይሆን የሚያበረታታ ጭምር አጋጣሚ ተፈጠረ።-ለጊዜው ሁሉም ነገር ሰላም መሰለ።-ጉዞ ዓድዋ ከመጀመሩ በፊት በዓድዋ ከተማ የዓድዋ ድል በዓል የሚከበረው በየአምስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ብቻ ነበር።-ጉዞ ዓድዋ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ለተጓዦች አቀባበል በሚል በየዓመቱ የዓድዋ ድል በዓልን ከማክበር አልፎ በወቅቱ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስተዳደር የሕዝቡን አንድነትን የሚያጎሉ ሥራዎች መሰራት አለባቸው ባለው መሠረት የዓድዋ ድል በዓል በፌደራል መንግሥት በድምቀት እንዲከበር ወሰነ።-በዚህ ወቅት ጉዞ ዓድዋ ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የ100000 ብር ድጋፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አገኘ። ጉዞ ዓድዋ አራት የተካሄደው 121ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሚከበርበት ወቅት ነበር።-ጉዞውን ለማካሄድ የታቀደውም በ121 ተጓዦች ነበር። ሆኖም በወቅቱ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በየአካባቢው ተፈጥረው የነበሩ ከፍተኛ ውጥረቶች ለመጓዝ ከተመዘገቡት ተጓዦች መሀል ጉዞውን ለማድረግ ፈቅደው የተገኙት ስምንት ተጓዦች ብቻ ነበሩ።-የጉዞ ዓድዋ አራት የመጨረሻ ፍጻሜ በሶሎዳ ተራራ አናት ላይ የተፈጸመ ቢሆንም ከዓመት በፊት ተፈጥሮ በነበረው የተራራ መናድ አደጋ ሳቢያ ወደ ተራራው የሚያስወጡ መንገዶች በሙሉ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ተደረገ።-በዓሉም በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበር በመሆኑ የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በዝግጅቱ ላይ ታድመዋል።-ዝግጅቱም 100ኛው የዓድዋ ድል በዓል ከተከበረ ከ21 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ተላልፏል።-ባለፉት ሦስት ዓመታት እንደተለመደው መድረኩ ላይ ደማቅ አቀባበል ከተደረገ በኋላ ተጓዦች መድረክ አግኝተው መልዕክት የሚያስተላልፉበት ዝግጅት መታጠፉን እና በእንግዶች ፊት ተራምደው ብቻ እንዲያልፉ መታዘዙን ለጉዞው አዘጋጆች ተነገራቸው።-በበዓሉ ላይ በቀረበው ተውኔት ውስጥ የዳግማዊ አፄ ምኒልክንም ይሁን የእቴጌ ጣይቱን ስም ካለማንሳት አልፎ መድረክ ላይ ይተላለፉ በነበሩ መልዕክቶች እንዲሁም በየቦታው በተሰቀሉ ግዙፍ ፖስተሮች ላይ አንድም ቦታ ላይ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ስም እንዳይገለጽ መደረጉ የጉዞውን አባላት ሁሉ ያሳዘነ ድርጊት ሆነ።-ተጓዦች ከሕዝቡ ያገኙት ደማቅ አቀባበል ቢያስደስታቸውም መድረኩን አልፈው ወደ ተዘጋጀላቸው አንድ ጥግ ተወትፈው የመድረኩን ዝግጅት መታደም ቀጠሉ።-በዚህም ወቅት የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር የወቅቱ ሚንስትር ዲኤታ የነበሩት ወ/ሮ መዓዛ ገብረ መድኅን ከተቀመጡበት የክብር እንግዶች ወንበር በመነሳት ተወሽቀው ወደ ተቀመጡት ተጓዦች አመሩ።-የእንኳን ሰላም ገባችሁ ደስታቸውን ሁሉንም ተጓዦች እያቀፉ ከገለጹ በኋላ፣ ተጓዦች ስለተከፉበት ምክንያት ሲጠይቁ መድረክ መከልከላቸውን ተናገሩ።-ወ/ሮ መዓዛ ገብረ መድኅን ንዴታቸው ፊታቸው ላይ እየተነበበ በፍጥነት ወደ መጡበት የክብር ወንበር ተመልሰው አዘጋጅ ኮሚቴዎቹ እና ከሚንስትሯ ዶ/ር ሂሩት ጋር ሲነጋገሩ ተጓዦች ከርቀት ሁኔታውን ይመለከቱ ነበር።-መድረክ ላይ ሲተላለፍ የነበረው ሙዚቃ እንደተፈጸመ መድረክ መሪው የጉዞ ዓድዋ ዋና አስተባባሪ ወደ መድረኩ በመውጣት ንግግር እንደሚያደርግ አስተዋውቆ የጉዞውን ዋና አስተባባሪ ወደ መድረክ ጠራ።-የጉዞው አስተባባሪ ንግግሩን እንዲያቀርብ ከተሰጠው 3 ደቂቃ ውስጥ ግማሹን ብቻ በመጠቀም የዳግማዊ አፄ ምኒልክን፣ የእቴጌ ጣይቱን እና የሌሎች አዝማቾችን ስም በመጥራት ጀግኖች አያቶችንን ለመዘከር በመብቃታቸው ተጓዦች ደስተኞች መሆናቸውን በመግለጽ ምስጋና አቅርቦ ወረደ።-በዚያች ዕለት ረዥም ቴአትር እና በርካታ ንግግሮች እንዲሁም ብዙ ዝግጅቶች የተደረጉ ቢሆንም የዳግማዊ አፄ ምኒልክን ስም በመድረክ የጠሩ ሁለት ሰዎች ብቻ ነበሩ። የጉዞ ዓድዋው አስተባባሪ እና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ታቦ ምቤኪ።-በቀጣዩ ዓመት እንደ ባለፈው ዓመት ሁሉ በኦሮሚያ ከተሞች የነበረው አቀባበል የተለየ እና መልካም የነበረ ቢሆንም ወቅቱ ሌላ ችግር ተከስቶ አስፈሪ ድባብ ተፈጥሮ ነበር።-ይኸውም ጉዞው በተጀመረ በ3ኛው ቀን፣ የጥምቀት ቃና ዘገሊላ በዓል ወቅት በወልዲያ ከተማ በተፈጠረ ችግር በርካታ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ተገድለው ሕዝባዊ ቁጣ ተቀስቅሶ ነበር።-ጉዞው ከተጀመረ ሶስት ቀናት እንዲሁም ወልዲያ ለመድረስ ከ20 በላይ ቀናት የሚቀሩ ቢሆንም በተጓዦች እና ቤተሰቦቻቸው ዘንድ ፍርኅት ማሳደሩ ግን አልቀረም።-የሆነው ሆኖ ጉዞው በተያዘለት መርሐ ግብር ተካሂዶ ከ20 ቀናት በኋላ ተጓዦች ወልዲያን አልፈው ቆቦ ከተማ ድረሱ።-በቆቦ ከተማ ተነስቶ በነበረው አመጽ የበርካታ ህንጻዎች መስታወት ተሰባብረው መኪኖች ተቃጥለው እና በርካታ የንግድ ተቋማት ከጥቅም ውጪ ሆነው ነበር። በዚህ አስፈሪ ኹነት መሐል ማለፍ እና እያንዳንዱን ዝርዝር ታሪክ መጻፍ በዚህ አጭር ማስታወሻ ላይ ማስፈር ከባድ ነው።-ተፈጥሮ የነበረው ሁከት የብሔር ጥላቻ ጎልቶ እንዲወጣ በከፍተኛ ደረጃ ተሠርቶበት የነበረ በመኾኑ ወደ ትግራይ ይሄዱ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ይህንን መንገድ መጠቀም አቁመው በአፋር በኩል ይሄዱ እንደነበር ይነገራል። በተጓዦች ግምት መንገድ ዝግ ይሆናል እንጂ ማለፍ እንችላለን ብለው አልገመቱም ነበር።-ጉዞው ቀጥሎ የቆቦ ከተማን በማለፍ ዋጃ ወደ ተባለችው ትንሽዬ ከተማ ተጓዦች እንደደረሱ የነበረው ሁኔታ ሁሉንም ያስደነገጠ ነበር።-የጉዞ ዓድዋ ተጓዦች መስመር ሠርተው በሰልፍ የሚራመዱ በመሆናቸው ከዋጃ በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የታጠቀ ሠራዊት እና የጦር ተሽከርካሪዎች የዋጃ ከተማ መግቢያ ላይ ካለ ድልድይ አጠገብ ባልተለመደ መልኩ ካምፕ መስርተው በተጠንቀቅ ቆመው ይጠብቃሉ።-የዋጃ ከተማ መግቢያ ድልድይ ላይ ተጓዦች ሲደርሱ የሁሉም ፍርሀት እየጨመረ የመጣ ቢኾንም ከፊት ለፊት መንገዱን አጥረው የሚታዩ ወታደሮች የተጓዦችን ማንነት መለየት በመቻላቸው ነገሩ ወደ ተረጋጋ መንፈስ ቀስ በቀስ መቀየር ጀመረ።-በወታደሮች ታጅበው ብቅ ያሉት ኮሎኔል እኹት የተባሉ የጊዜያዊ ካምፑ አዛዥ ለተጓዦች ራሳቸውን ካስተዋወቁ በኋላ፣ ሁሉም በሰልፍ እንዲከተሏቸው አዘው ከመንገዱ በስተግራ ወደሚገኝ መታጠፊያ ይዘዋቸው ገቡ። ቦታው በእጅጉ አስፈሪ ነው።-ኮሎኔሉ ከጉዞው አስተባባሪ ጋር መረጃዎችን ከተነጋገሩ በኋላ ጉዞውን ለማድረግ የተፈቀደበትን ደብዳቤ ጠይቀው ተሰጣቸው። ደብዳቤውን አንብበው ከጨረሱ በኋላ በቁጣ መናገር ጀመሩ።-“የፈቀዱላችሁ ሰዎች ምን ነክቷቸው ነው? እንደዚህ አይነት እንግዶች እየመጡ ነው እወቁት ብለው ለእኛ መናገር ነበረባቸው። እናንተ እኮ ከመመታት የተረፋችሁት በተአምር ነው...-“.... ወታደራዊ ሰልፍ ሰርታችሁ ስትመጡ የተደራጀ ጥቃት ሊሰነዝር የሚፈልግ ኃይል የመጣ ኃይል ስለመሰለን ተዘጋጅተን በግራም በቀኝም ቆርጠን ቀለበት ውስጥ ከተናችሁ ነበር። ... ለማንኛውም ተርፋችኋል። በሉ ይህንን ብሉ” አሉና ወታደሮቹ ይዘው የመጡትን የታሸጉ ብስኩቶች ዘረገፉላቸው።-ከቀናት በኋላ የካቲት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. የጉዞ ዓድዋ አምስት አባላት አጉላዕ የተባለችውን ከመቀለ በፊት የምትገኝ ትንሽ ከተማ በመጠኑ እንዳለፉ አንዲት መንገድ ዳር የምትገኝ አነስተኛ ሻይ ቤት በረንዳ ላይ ዙርያ ከበው በመቀመጥ የመጻሕፍት ንባብ ለማከናወን በጋራ ታድመዋል።-ከሻይ ቤቷ ውስጥ አንዲት አስተናጋጅ መጥታ ሽብር የሚመስል መረጃ ለተጓዦቹ አጋራች። “ኃይለማርያም ሥልጣን የመልቀቅ ጥያቄ አቀረበ” የሚል ሰበር ዜና ደጋግሞ በቴሌቪዥን እየታየ ነው ብላ ተናገረች።-ከቤቱ ርቆ ያውም በእግሩ ረዥም ርቀት መንገድ ላይ ለሚገኝ ሰው እንዲህ ያለ ዜና ከፍተኛ መረበሽ የሚፈጥር ነበር። ከደቂቃዎች በፊት መንገዱን ሰንጥቀው ያልፉ የነበሩ መኪኖች እንቅስቃሴ ምን የተለየ ነገር እንደነበረው የታዘበ ሰው አልነበረም።-ቦታው የስልክ ኔትወርክ የሌለበት በመሆኑ በቴሌቪዥኑ ከሚተላለፈው መረጃ በቀር ምን እንደተፈጠረ የሚነግር አንዳችን ፍንጭ አልነበረም።-በዚህም ሳቢያ ቀድሞ 1 ሰዓት ያህል ይፈጅ የነበረው የ6 ኪሎ ሜትር ርቀትን በግማሽ ሰዓት ውስጥ በሩጫ ጭምር ተዋክቦ ወደ ቀጣይዋ ከተማ ሁሉም ከነፈ።-በቅርብ ርቀት የሚገኝ ከተማ ባለመኖሩ የመንገዱን ዳር ተከትሎ የተሠራ አንድ የገጠር ትምህር ቤት በልመና ለማደር ፍቃድ ስለተገኘ ገና ሳይመሽ የዕለቱ ጉዞ ተጠናቆ ተጓዥ ሁሉ በጊዜ ወደ ማደሪያው ተከተተ።-እንዲህ ባለው ሁኔታ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሥልጣናቸው የመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው፤ ፓርቲያቸው ምላሽ እስኪሰጣቸው እና በምትካቸው ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት የነበሩት ቀናት ለጉዞ ዓድዋ 5 ተጓዦች ዓድዋ ከተማ እስከሚደርሱበት ቀን ድረስ የፖለቲካው ሁኔታ ያልለየለት በመሆኑ በተጓዦች ላይ ውጥረት ሰንብቶ ከርሟል።-የዚያኑ ዓመት በጉዞ ዓድዋ 5 ፍጻሜ የካቲት 23 ቀን ጉዞ ዓድዋን ለሁለት የሚከፍል አጋጣሚም ተከስቶ ነበር።-***-የቢቢሲ ማስታወሻ፡ ጉዞ አድዋ ከዚህ ቀደም ለዓመታት መከፋፈል ባጠላበት ሁኔታ ሲካሄድ ቆይቷል። "የጥቁር ነፃነት ተምሳሌት"፤ የዓለም ድሃ አገራትን የናቀና ጦር መሳሪያውን የተማመነ ኃይል የተንበረከከበት በሚል የሚዘክሩት ቢኖሩም የአድዋ ታሪክ፣ አተረጓጎም ሐሳባዊ ፍጭቶችንም ማስተናገዱን ቀጥሏል።-አፄ ምኒልክ የነበራቸው ሚና፣ የሰንደቅ አላማ ጉዳይ በታሪክ ተርጓሚዎች ዘንድ መነታረኪያ ሆኖም ቀጥሏል። ለባለፉት ሁለት ዓመታት በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተዛምቶ በመቶ ሺዎችን ሕይወት በቀጠፈው ጦርነት ምክንያት ጉዞው ተገትቶ ቆይቷል።-*ፀሐፊው ያሬድ ሹመቴ ከጉዞ አድዋ አስተባባሪነቱ በተጨማሪ፣ በተለያዩ ፊልሞች በዳይሬክተርነት፣ በፀሐፊነት እንዲሁም ሙዚቃዎችን የሚሰራ ባለሙያ ሲሆን፣ በቅርቡ በቦረና ለተከሰተው ድርቅ ድጋፍ ለማድረግ ገንዘብ በማሰባሰብና በሌሎችም የበጎ ሥራ እንቅስቃሴዎች ይታወቃል።
የፎቶው ባለመብት fana tv-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ-የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከዚህ ቀደም ከመንግሥት ጋር በነበረው ድርድር የተዘጋጀውን “የመጨረሻ ሰነድ” የሚቀበል ከሆነ ሦስተኛ ዙር ድርድር ሊኖር እንደሚችል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሰው እና መንግሥት ‘ሸኔ’ ከሚለው ታጣቂ ቡድን ጋር የሚደረግ ሦስተኛ ድርድር “ወደ ሰላም ለመምጣት ወይም እስከ መጨረሻው ላለመነገጋር” የሚወሰንበት የመጨረሻ ንግግር ሊሆን እንደሚችልም አመልክተዋል።-የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የፌደራል መንግስት ድርድር ያለ ስምምነት ከተጠናቀቀ ወዲህ በጉዳዩ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት የሰጡት ሰኞ ታኅሣሥ 1/2016 ዓ.ም. ለመንግስት ቅርበት ባለው ፋና ቴሌቪዥን በተላለፈ ቃለ መጠይቅ ላይ ነው።-የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ታንዛኒያ ዛንዚባር ውስጥ እንዲሁም በዚህ ዓመት ኅዳር ወር መጀመሪያ ላይ ያደረጓቸው ሁለት ዙር ንግግሮች ያለውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል።-ኢታማዦር ሹሙ ለቴሌቪዥን ጣቢያው በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ ካለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ እስከ ኅዳር 11 ድረስ በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም የተደረገው ሁለተኛው ዙር ድርድር ላለመሳካቱ ምክንያት ያሏቸውን ጉዳዮች አብራርተዋል።-የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ ኩምሳ ድሪባን እና ሌሎች የጦሩ አዛዦች ለመጀመሪያ ጊዜ ከፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ፊት ለፊት የተገናኙበት ሁለተኛው ዙር ድርድር “በስምምነት ይቋጫል” የሚል ተስፋ በብዙዎች ዘንድ ፈጥሮ ነበር።-ድርድሩ ከተጀመረ ከቀናት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዴዎን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ንግግሩን መቀላቀላቸውም በጥሩ ምልክትነት ተወስዶ ነበር።-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑም ድርድሩ “በጥሩ ሁኔታ” እየተካሄደ እንደነበር የተናገሩ ሲሆን፣ በሁለቱ አካላት መካከል አለመስማማትን የፈጠሩ ጉዳዮች የተነሱት መጨረሻ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።-“የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና አንድነትን መቀበል ላይ፣ የኢትዮጵያን አገረ መንግሥት፣ በምርጫ የመጣ ቅቡልነት ያለው መንግሥት መሆኑ ላይ መግባባት ተደረሰ። ከዚያ [ግን] በዝርዝሩ ነው እነዚህን መግባባቶች የሚሸረሽር ነገር የመጣው” ሲሉ መጀመሪያ ላይ ሁለቱ አካላት የተግባቡባቸውን ጉዳዮች ጠቅሰዋል። በዚህ ድርድር ላይ “አደራዳሪዎች እንኳ ያመኑበት የመጨረሻ ሰነድ” ተዘጋጅቶም እንደነበር አስታውሰዋል።-ኢታማዦር ሹሙ አለመግባባት አምጥተዋል ካሏቸው “ዝርዝር ጉዳዮች” መካከል በቀዳሚነት የጠቀሱት “ሥልጣን አካፍሉኝ” በሚል ቀርቧል ያሉትን ጥያቄ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ይህንን ጥያቄ ያቀረበው የራሱን “ፕሮፖዛል” አዘጋጅቶ መሆኑን ያነሱት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ “መሠረታዊ ልዩነት የፈጠረውን” ይህንን ጥያቄ መንግሥት እንዳልተቀበለው ተናግረዋል።-“መንግሥት ሥልጣን ላካፍል ቢልም ሥልጣን ማካፈል አይችልም። ሥልጣን የማካፈል መብት የለውም። ማድረግ የሚችለው ማሳተፍ ነው። ማሳተፍ ይችላል፤ ማካፈል ግን አይችልም። መጀመሪያውኑ ለምን ወደ ምርጫ ተሄደ?” ሲሉ የኢትዮጵያ መንግሥት በምርጫ ሥልጣን ላይ የተቀመጠ መሆኑ የታጣቂ ቡድኑ ጥያቄ ውድቅ እንዲሆን ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።-የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ፤ በሁለተኛነት የጠቀሱት ሁለቱን አካላት ያላግባባ ጉዳይ ትጥቅ መፍታትን የሚመለከት ነው።-ከመንግሥት ጋር ድርድር የሚቀመጥ አካል ጥያቄዎቹን ማንሳት ያለበት “ወደ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ለመመለስ፣ በሰላም ለመታገል፣ ፓርቲ አቋቁሞ ለመታገል፣ ለሕዝብ ምርጫ ለመቅረብ፣ የገጠር ትጥቅ ትግል ትቶ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሕዝብ ለመመለስ“ ተስማምቶ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።-የታጣቂ ቡድኑ አባላትም ትጥቅ መፍታት፣ መበተን እና ወደ ሕብረተሰቡ መዋሃድ እንዳለባቸው የተናገሩት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ዘንድ ግን ይህንን ጉዳይ “ለመቀበል የመቸገር ነገር ተከስቷል” ሲሉ ወቅሰዋል።-“ይሄንን ካልተቀበልክ ድርድር ብሎ ነገር የለም። ይሄንን ያለቀመበል ችግር አለ። ስለዚህ [ድርድሩ] ጥሩ ሄዶ ሄዶ የቆመው በእነዚህ ሁለት ምክንያቶች ነው” ብለዋል።-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ሁለቱን ነጥቦች “በተሳሳተ መንገድ እንዲወስዱ” በማድረግ ረገድ “ሌሎች ኃይሎች እጃቸው” እንዳለበት በቃለ መጠይቁ ላይ ተናግረዋል።-ኢታማዦር ሹሙ፤ “በዚህ ኃይል [ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት] ላይ ታዝለው የሚሄዱ ኃይሎች አሉ። በዚህ ኃይል ተሸካሚነት የሚሄዱ ኃይሎች አሉ። አገር ውስጥም ከአገር ውጪም፤ ባዕዳንም፣ ዜጎችም። እነዚህ ኃይሎች፤ ይሄ ኃይል ነገሮችን በሰከነ መንገድ አይቶ ስምምነት እንዳይቀበል አድርገውታል” ሲሉ ለድርድሩ አለመሳካት በስም ያልጠቀሷቸውን ኃይሎች ተጠያቂ አድርገዋል።-አክለውም፤ “ችግር ውስጥ ያሉት እነሱ [ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት] ናቸው፤ [በድርድሩ ላይ] ራሳቸው መወሰን ነበረባቸው። ሌላው ኃይል ጣልቃ ስለገባ በዓለም ልምድ ታይቶ የማይታወቅ ቅድመ ሁኔታ በማቅረብ መንግሥትን አስቸግረዋል” ብለዋል።-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ይህንን ቢሉም ከድርድሩ መጠናቀቅ በኋላ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ባወጣው መግለጫ ለድርድሩ አለመሳካት ተጠያቂ ያደረገው መንግሥትን ነበር።-ታጣቂ ቡድኑ በድርድሩ ከስምምነት ላይ መድረስ ያልተቻለው የኢትዮጵያ መንግሥት “የአገሪቱን ደኅንነት እና ፖለቲካን ፈተና ውስጥ ለከተቱ መሠረታዊ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ፍላጎት ባለማሳየቱ” ነው ብሎ ነበር።-ከድርድሩ መጠናቀቅ በኋላ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም ሆነ መንግሥት በተናጠል ባወጧቸው መግለጫዎች ላይ ሦስተኛ ዙር ድርድር ማድረግን በሚመለከት የተጠቀሰ ነገር አልነበረም።-የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ግን ሰኞ ዕለት በቀረበው ቃለ መጠይቅ ላይ ሦስተኛ ዙር ድርድር ሊደረግ ይችላል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።-“ሦስተኛ ዕድል ይኖራል ወይ? የሚለው ሊኖር ይችላል። ምናልባት ሰከን ብለው አስበው። የመጨረሻ ሰነድ እኮ ተዘጋጅቷል፤ እነዚህ አደራዳሪዎች እንኳ የሚያምኑበት። እሱን ወደ መቀበል ደረጃ ከተደረሰ ሦስተኛ ዙር ውይይትም ሊኖር ይችላል” ሲሉ መንግሥት በሦስተኛውም ዙር ድርድር ከዚህ ቀደም የተዘጋጀው ሰነድ ላይ እንደሚመሠረት ጠቁመዋል።-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ በመንግሥት እና በታጣቂ ቡድኑ መካከል ሊደረግ የሚችለው ቀጣይ ድርድር እንደ ሁለተኛው ዙር ድርድር “ሰፊ ውይይት” የማደረግበት ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል።-“እስካሁን የተደከመበት ውይይት እና ሰነድ አለ። እሱን መቀበል ላይ ከተደረሰ ሦስተኛ [ዙር ድርድር] ሊኖር ይችላል። ሦስተኛው ውይይትም የመጨረሻ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። ወደ ሰላም ለመምጣት ወይም እስከ መጨረሻው ላለመነገጋር የመጨረሻ ሊሆን ይችላል” ሲሉ ቀጣዩ ድርድር የሁለቱን አካላት ወደፊት ግንኙት ለመበየን ወሳኝ መሆኑነ በአጽንኦት ተናግረዋል።-ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተነጥሎ በበርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች የትጥቅ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከሁለት ዓመት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብር ቡድንነት መፈረጁ ይታወቃል።-የታጣቂ ቡድኑ እንቅስቃሴ በተለይ በምዕራባዊው የአገሪቱ ክፍል ውስጥ የጎላ ሲሆን፣ ከመንግሥት ኃይሎች ጋር በሚካሄዱ ግጭቶች እና በሚፈጸሙ ጥቃቶች የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ላላፉት አምስት ዓመታት ከባድ የሕይወት እና የንብረት ጉዳት መድረሱ ሲዘገብ ቆይቷል።-ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎችም ግጭቶች እና ጥቃቶችን በመሸሽ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
የፎቶው ባለመብት Merawi Communications-መርዓዊ ከተማ በከፊል-በአማራ ክልል በአዲሱ ሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ሰኞ፣ ጥር 20/2016 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቤተሰቦች፣ ነዋሪዎች አና የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።-ከክልሉ ዋና ከተማ ከባሕር ዳር በ35 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው መርዓዊ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተደረገ ውጊያን ተከትሎ በነዋሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት፣ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።-የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባሕር ዳር ቢሮ በመርዓዊ ከተማ በንጹሃን ላይ ጥቃት እንደደረሰ ከተለያዩ ምንጮች መረጃው እንደደረሰው፣ ክትትል እና ምርመራም እያከናወነ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።-ክስተቱን ተከትሎ ባለፉት ቀናት የሆስፒታል ምንጭን ጨምሮ አምስት ሰዎችን ቢቢሲ ያነጋገረ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ነዋሪዎች ግድያው የተፈጸመው በቤታቸው እና በመንገድ ላይ በተገኙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።-ሰኞ ጥር 20/2016 ዓ.ም. ከጥቃቱ ቀደም ብሎ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ኃይሎች መካከል “ከባድ ውጊያ” እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ያንን ተከትሎ ከ50 እስከ 100 የሚደርሱ ሰዎች “ተረሽነዋል” ብለዋል።-ይህ ጥቃት የተፈጸመው ረፋድ አምስት ሰዓት አካባቢ የፋኖ ኃይሎች ከተማዋን ለቅቀው መውጣታቸውን ተከትሎ “መከላከያ ሠራዊት ቤት ለቤት በመዞር እና መንገድ ላይ ያገኛቸውን ሰዎች መረሸኑን” የተናገሩት የዐይን እማኞች፤ ጥቃቱ እስከ ምሽት አንድ ሰዓት የዘለቀ ነበር ብለዋል።-በቀን ሥራ ይተዳደር የነበረ የአራት ልጆች አባት የሆነ ወንድማቸው እንደተገደለባቸው የሚናገሩ ነዋሪ “መጀመሪያ እኔ ቤት መጥተው ሲፈትሹ ‘የቤተ-ክርስትያን ሰው ነኝ’ ስላቸው ወጥተው ሄዱ። ቀጥለው ወንድሜ ቤት ገብተው ይዘውት ሄዱ።”-ወንድማቸው ለጥያቄ ተወስዶ ይመለሳል ብለው እየጠበቁ የነበሩት ነዋሪ፣ ከሌሎች ጋር በሰደፍ እና በቆመጥ እየተደበደቡ ሲወሰዱ እና ሲገድሏቸው መመልከታቸውን ገልጸዋል።-“አንዱን ልጅ በአምስት ጥይት እዚያው ሰፈራችን ኮብሉ ላይ ገድለው ጣሉት። እነሱን [ወንድማቸውንና ሌሎች ሰዎችን] ደግሞ ሰብስበው አንድ ላይ 13 ሰዎች ወደ አስፓልት ይዘው ወጥተው ገደሏቸው። …ፊታችን ስለገደሏቸው ነው ያመንነው” ብለዋል።-ይህንኑ ክስተት በተመለከተ አንድ የህክምና ባለሙያ 13ቱ ሰዎች ከአስፓልት ዳር መገደላቸውን እንደሚያውቁ ለቢቢሲ አረጋግጠው፣ በአጠቃላይ በከተማዋ ውስጥ በዚያ ዕለት 85 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።-ሌላ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ እና ታናሽ ወንድማቸው እንደተገደለባቸው የሚናገሩት የመንግሥት ሠራተኛ ወንድማቸው ከልጁ እቅፍ ተነጥሎ ተወስዶ “በጭካኔ ተረሽኖብኛል” ብለዋል።-“ወንድሜን ልጁን ይዞ ከተቀመጠበት ቤቱ ተወስዶ ነው የተገደለው። ባለቤቱ ‘ህጻኑን ተቀበይ ተብዬ ተገደድኩ፤ ህጻኑን ተቀበልኩት።…ዐይኔ እያየ ነው ግንባሩ ብለው መንገድ ላይ የገደሉት። አብሮት የነበረውንም ጓደኛውን ገድለውታል’ ብላ ነግራኛለች።”-ከወንድማቸው ባሻገርም በዕለቱ መንገድ ላይ 50 የሚሆኑ ሰዎችን አስከሬን መመልከታቸውን ተናግረዋል። ሆኖም “በየመንገዱ እና በየጥሻው” በርካታ ሰው ሳይገደሉ እንዳልቀረ ገምተዋል።-ሌላ የዐይን እማኝ ደግሞ በበርካታ ቀብሮች ላይ መገኘታቸውን ጠቅሰው የሟቾችን ቁጥር ከ100 በላይ አድርገዋል።-ጥቃቱ በተፈጸመ ማግስት ጥር 21/2016 ዓ.ም. ጠዋት ላይ 48 አስከሬን መቆጠራቸውን የሚናገሩ የመርዓዊ ከተማ ነዋሪ፤ “ከማርዘነብ ሆቴል እስከ በረድ ወንዝ ድረስ ግራ እና ቀኝ አስከሬን ብቻ ነበር” ብለዋል።-የሟቾችን ቁጥር 115 ገደማ የሚያደርሱ አንድ የዐይን እማኝ መከላከያ ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ስታዲየም እና ጤና ጣቢያ በተባሉ ሰፈሮች “ከስድስት ዓመት ህጻን እስከ 75 ዓመት አዛውንት” ድረስ ግድያ ተፈጽሟል ይላሉ።-የሆስፒታል ሠራተኛ የሆኑት የዐይን እማኝ በከተማዋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የስድስት ወር ነፍሰ ጡርን ጨምሮ 25 ሰዎች ቆስለው መጥተው “የተረፈ የለም” ይላሉ።-“24ቱ ሆስፒታል የመጡት ሞተው ነው። አንዲት የስድስት ወር ነፍሰ ጡር ሴት ከነ ነፍሷ መጥታ ሆስፒታል እንደደረሰች አርፋለች። አጠቃላይ 25 ነበር የመጡት” ብለዋል።-መከላከያ ሠራዊት ከቤት ለቤት አሰሳው ባሻገር የአብነት ተማሪዎችን ጨምሮ መንገድ ላይ የተገኙ ሰዎችን እና የቀን ሠራተኞችን “በበቀል አንበርክኮ” ረሸኗል ሲሉ ነዋሪዎች፣ ቤተሰቦች እና የዐይን እማኞች ተናግረዋል።-በከተማዋ ውስጥ በሁለት ስፍራ ላይ ሰፍሮ ከሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል በከተማዋ አስተዳደር ህንጻ ውስጥ በነበሩት ላይ የፋኖ ታጣቂዎች ሰኞ ጠዋት ለፈጸሙት ድንገተኛ ጥቃት ምላሽ የተወሰደ “የበቀል እርምጃ” ለበርካታ ሰዎች ግድያ ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።-“ፋኖን አሳድራችኋል፤ ያስጠቃችሁን እናንተ ናችሁ፤ ፋኖን ትቀልባላችሁ” እያሉ “እየዛቱ” ነበር ያሉ አንድ ቤታቸው የተፈተሸ ነዋሪ፤ “ከመሞት መሰንበት” ብለን ዝም አልን ሲሉ ጥቃቱ የበቀል ነበር ብለዋል።-በርካታ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች ላይ ተገድለው ተጥለው በመቆየታቸው ዘግናኝ ሁኔታ መመልከታቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸው “የተገደሉ ሰዎች አስከሬንን ለመለየት እንኳ አስቸጋሪ ነበር” ይላሉ።-“አብዛኛው ሰው በአለባበሱ፣ በሰውነት ቅርጹ ነበር የሚለየው። አስከሬኖች በጥይት ክፉኛ ከመበሳሳታቸው በተጨማሪ፣ ማንሳት አይቻልም ተብሎ አንድ ቀን አሳድረዋቸዋል” ያሉ አንድ እማኝ መለየት አስቸጋሪ በመሆኑ በጅምላ ቀብር እንደተፈጸመ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-“እንደ ባህሉ እና ሥርዓቱ ለተገደሉት ሰዎች ተገቢው ቀብር አልተፈጸመም” ያሉት ነዋሪዎች፤ ሐዘን መቀመጥ እና ለቅሶ መድረስ አይታሰብም በማለት “የተፈጸመው ከግፍም በላይ ግፍ” ሲሉ ጥቃቱን ገልጸውታል።-በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደው ውግያ በአካባቢው ሁለት አብያተ ክርስቲያናት “በከባድ መሳሪያ ጉዳት ደርሶባቸዋል” የተባለ ሲሆን፣ የግል ንብረቶች እና 15 የሚሆኑ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) ሆን ተብለው እንዲቃጠሉ መደረጋቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።-ይህ በርካታ ሰዎች በተገደሉበት ጥቃት በከተማዋ በደማቅ ሁኔታ በየዓመቱ ጥር 21 የሚከበረው የማርያም ንግስ በዓል ዋዜማ በመከሰቱ ምክንያት ከተማዋ በሐዘን ተውጣ በዓሉ እንዳልተከበረም ነዋሪዎቹ አክለው ተናግረዋል።-ጥቃቱ ከተፈጸመ አምስት ቀን ያለፈው ቢሆንም አሁንም ከተማዋ በእጅጉ መቀዝቀዟን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ባንኮች እና የንግድ ተቋማት ዝግ በመሆናቸው “እንቅስቃሴ የለም” ብለዋል።-ከክልሉ እና ከዞኑ መስተዳደር እንዲሁም ከአካባቢው ኮማንድ ፖስት ስለክስተቱ ማብራሪያ እና ምላሽ ለማግኘት ቢቢሲ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።-በአማራ ክልል የተለያዩ አካበቢዎች ካለፈው ዓመት ጀምሮ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል።-የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም. ባወጣው ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖች ውስጥ በተለያየ ደረጃ እና ጊዜ የትጥቅ ግጭት መካሄዱን ገልጾ በዚህም ሳቢያ በርካታ ሲቪሎች እንደተገደሉ እና የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቶ ነበር።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኢትዮጵያውያንን በሕገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር የተጠረጠሩ አራት የኬንያ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ።-መርማሪዎች በሕገ ወጥ መንገድ የተዘዋወሩ 37 ኢትዮጵያውያንን ከኬንያ መዲና ናይሮቢ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ በአንድ ቤት ውስጥ አግኝተዋቸዋል ተብሏል።-አራቱ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋሉትም ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲፈፀም በመርዳት ተጠርጥረው ነው ።-ኢትዮጵያውያኑ የተሻለ ሕይወትን ፍለጋ ወደ ደቡብ አፍሪካ እያቀኑ መሆናቸውን ለኬንያ ባለስልጣናት መናገራቸውን የግል ጋዜጣ የሆነው ዘ ስታር ዘግቧል።-የቤቱን ባለቤት እንዲሁም በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳትፈዋል የተባሉ ሌሎች አባላትን ለመያዝም ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑ ተነግሯል።-ኬንያ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ለሚሞክሩ ኢትዮጵያውያን ተመራጭ የመሸጋገሪያ መንገድ እንደሆነች የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ አይኦኤም አስታውቋል።-ስደተኞቹ በአብዛኛው ከኦሮሚያ፣ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የመጡ ወንዶች ሲሆኑ በሞያሌ ድንበር በኩል ወደ ኬንያ በመግባት ወደ ታንዛንያ እና በመጨረሻም ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያቀኑ ኤጀንሲው ገልጿል።-ከጥቂት ወራት በፊት በኬንያ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው ኢትዮጵያዊ 31 ዓመታትን በእስር እንዲያሳልፍ በናይሮቢ የሚገኝ ፍርድ ቤት መበየኑ ይታወሳል።-ይበቃል ጌታቸው የተባለው ግለሰብ ከሁለት ዓመታት በፊት በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በመኖሪያ ቤቱ እጃቸው በሰንሰለት የታሰሩ 12 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ነበር።-ከጥቂት ወራት በፊት በኬንያ መዲና ናይሮቢ ኢስሊ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ፖሊስ 30 ሰነድ አልባ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ስለማዋሉ ሪፖርት ተደርጓል።-20 ወንዶች እና 10 ሴቶች መዳረሻቸው እስካሁን ወዳልተገለጸ ቦታ ሊዘዋወሩ ሲሉ እንደተያዙ የኬንያን ፖሊስ ዋቢ አድርጎ ስታንዳርድ የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል።-ከጥቂት ወራት በፊት ደግሞ በማቻኮስ ግዛት አቲ ሪቨር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሕገ-ወጥ መልኩ ኬንያ የገቡ ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ጥቃቱ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት አላደረሰም-በየመን የሑቲ አማጺያን በአሜሪካ መርከብ ላይ የሚሳኤል ጥቃት ሰነዘሩ። ጥቃቱን ያደረሱት ‘ጂብራልተር ኤግል’ በተሰኘው አቃ ጫኝ ግዙፍ መርከብ ላይ ነው።-የመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ማዘዣ ማዕከል ጥቃቱ በየመን ጠረፍ አካባቢ መፈጸሙን አምኖ ነገር ግን የከፋ ጉዳት እንዳልደረሰ አብራርቷል።-የማርሻል አይላንድ አርማን የያዘው ይህ መርከብ ጉዞውን በኤደን ባሕረ ሰላጤ ቀጥሏል።-በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት ሑቲዎች በቀይ ባሕር አካባቢ የባሕር ጉዞን ማስተጓጎል የጀመሩት እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ያለውን ጥቃት በመቃወም ነው።-‘ኤግል በልክ’ የተሰኘው የመርከብ ድርጅት እንዳለው መርከብ ብረት ጭኖ ከኤደን ጠረፍ 160 ኪሜ ምትር ርቀት ላይ እየተጓዘ ነው ጥቃቱ የደረሰበት።-ጥቃቱ ያደረሰው ጉዳት መጠነኛ ስለነበረ መርከቡ ጉዞውን ቀጥሏል ብሏል ኩባንያው።-አሜሪካ እንዳለችው ከዚህ የሚሳኤል ጥቃት አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ ሌላ ሚሳኤል በሑቲዎች የተተኮሰ ቢሆንም በአሜሪካ ተዋጊ ጄቶች አየር ላይ እንዲመክን ሆኗል።-ይህ ሚሳኤል ዒላማ አድርጎ የነበረው በቀይ ባሕር የአሜሪካ ባሕር ኃይልን ነበር።-ሑቲዎች የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን እንደሚቀጥሉ ዝተዋል።-ሆኖም ጥቃቶቹ በሁሉም የንግድ መርከቦች ሳይሆን ከእስራኤል ጥቅም ጋር የተሳሰሩ ላይ ብቻ እንደሚሆን ተናግረዋል።-ሑቲዎች ጥቃቶቹ የሚቀጥሉት እስራኤል በጋዛ በሐማስና በንጹሐን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እስከቀጠለች ድረስ ነው።-የዩኬ ባሕር ኃይል ይህ ጂብራልተር ኤግል መርከብ ከእስራኤል ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው አረጋግጫለሁ ብሏል።-ሑቲዎች በሰጡት ምላሽ ደግሞ የአሜሪካ ማንኛውም ጥቅም ላይ ጥቃት እንሰነዝራለን ብለዋል።-ናሲር አል ዲን የተባሉ የሑቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን ‘’የአሜሪካ የሆነ መርከብ ሁሉ ጥቃት ሊሰነዘርበት ይገባል’’ ብለዋል።-በቀይ ባሕር ሑቲዎች ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ በርካታ ግዙፍ የመርከብ ኩባንያዎች ጉዟቸውን በሌላ አቅጣጫ ለማድረግ ተገደዋል። ይህ ደግሞ በዓለም የንግድ መርከብ ሰንሰለት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው።-የትናንቱን የሑቲዎች ጥቃት ተከትሎ የአሜሪካ የትራንስፖርት ሚኒስትር የአሜሪካ ባንዲራ ያላቸው እና የአሜሪካ ንብረት የሆኑ መርከቦች በቀይ ባሕር የተወሰኑ አካባቢዎች እንዳይጠጉ መክሯል።-ሰኞ ዕለት በዓለም ሁለተኛው ግዙፍ የነዳጅ ኩባንያ የሆነው ኳታር-ኢነርጂ መርከቦች በቀይ ባሕር በኩል እንዳያልፉ ውሳኔ አስተላልፏል።-ባለፈው ሳምንት አሜሪካና ዩኬ በሑቲ ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ከባድ ጥቃት መሰንዘራቸው አይዘነጋም። ጥቃቶቹ የሑቲዎችን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሽመደምደው ይጠበቃል።-ጥቃቶቹ በአየርና ከባሕር የተነሱና በአሜሪካ አጋሮች የጋራ ጥምረት የተሰነዘሩ ሲሆን የሑቲ ሚሳኤሎች እና የአየር መቃወሚያዎች የሚገኙበትን የየመን የጦር ሰፈር ዒላማ ያደረገ ነበር።-ጥቃቱን ተከትሎ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ 13 የሑቲ የአየር ጥቃት መነሻ ነበሩ የተባሉ የጦር ሥፍራዎች እንዳልነበሩ ሆነው ወድመዋል ብለዋል።-የአሜሪካ ደኅንነት በበኩሉ ከአጋሮች ጋር ባለፈው ሳምንት የመን ላይ የተሰነዘረው ጥቃት አንድ ሦስተኛውን የሑቲዎች የጦር መሣሪያን አውድሟል።-ዋሺንግተን ኢራንን ከሑቲ የሚሳኤል ጥቃት ጀርባ አለች ስትል ትከሳለች፤ ኢራን ታስተባብላለች።-የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሑሴን አሚር አብዱላሒ ትናንት ሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ምዕራባዊያን በየመን ላይ የሚሰነዝሩትን ጥቃት ማቆም አለባቸው ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት Reuters-እስራኤል መስከረም 26 ጥቃት ከተፈጸመባት በኋላ በጋዛ እየፈጸመች ባለችው ወታደራዊ ዘመቻ ቢያንስ ግማሽ የሚሆነው የጋዛ ሕንጻዎችን ማውደሟን የቢቢሲ ምርመራ አመለከተ።-ከጦርነቱ በፊት የተነሱ ምስሎች አሁን ካለው ጋር ሲነጻጸሩ በደቡባዊ እና መካከለኛው ጋዛ የደረሰውን ከፍተኛ ውድመት ያሳያሉ።-የጋዛ ነዋሪዎች የመኖሪያ መንደሮች ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል። ብዙዎች የሚገበያዩባቸው ቦታዎች እንዳልነበሩ ሆነዋል። የዩኒቨርሲቲ ሕንጻዎች ሙሉ በሙሉ ወድመው ጋዛ ከላስቲክ በተሰሩ መጠለያዎች ተሸፍናለች።-በዚህ ጦርነት አብዛኛዎቹ ሕጻናት እና ሴቶች የሆኑ ከ26ሺህ ያላነሱ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከአጠቃላይ የጋዛ ነዋሪ 80 በመቶ የሚሆነው 1.7 ሚሊዮን ሕዝብ ከመኖሪያው ተፈናቅሏል።-በዚህ ሁሉ ውድመት ውስጥ ግን የእስራኤል ጦር እያደረገ ባለው ጥቃት ዒላማ እያደረገ ያለው ሐማስን እና የሐማስ መሠረተ ልማቶችን ብቻ መሆኑን ይገልጻል።-ቢቢሲ የሳተላይት ምስሎችን ተመልክቶ በሰራው ትንተና ከ114ሺህ እስከ 175ሺህ የሚሆኑ የተለያየ መጠን ያላቸው ሕንጻዎች በእስራኤል የቦምብ ድብደባ ወደ ፍርስራሽነት ተቀይተረዋል።-ይህ አሃዝ ታዲያ ከ50-61 በመቶ የሚሆነው የጋዛ ሕንጻ መውደሙን ያመለክታል።-በቅርብ ወራት ደግሞ በደቡባ ጋዛ የምትገኘው ኻን ዩኒስ ከፍተኛ ውድመት ካጋጠማቸው አካባቢዎች አንዷ ነች። ከ38ሺህ በላይ ሕንጻዎች ውድመት አጋጥሟቸዋል። በኻን ዮኒስ ባለ 16 ፎቁ ረዥሙ ሕንጻ አል-ፋራ ታዎር አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ በቦታው የለም።-በጋዛ ተዋቂ የነበረው ሳናበል ሸዋርማ ምግብ ቤት ሕንጻ አሁን እንዳልነበር ሆኗል።-“የእስራኤል ወታደሮች በኻን ዩኒስ መሃል ከተማ መኖሪያ ሕንጻዎችን ዒላማ ሲያደርጉ ነበር” በማለት ከመኖሪያዋ ተፈናቅላ የምትገኘው የ20 ዓመቷ የጋዛ ነዋሪው ራዋን ቃዳህ ለቢቢሲ ተናግረዋለቸ።-የእስራኤል ጦር በተደጋጋሚ የሐማስ ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች መገኛ ቦታዎች እራሳቸውን እየሸሸጉ ነው ከማለቱ በተጨማሪ ሐማስ መሠረተ ልማቶቹን የገነባው እንደ ሆስፒታል እና ትምህርት ቤት ሥር ባሉ ዋሸዎች ውስጥ ነው ሲል ቆይቷል።-በእስራኤል ጦር ውድመት ያጋጠማቸው ግንባታዎች ብቻ ሳይሆኑ የእርሻ መሬቶችንም ወድመዋል፤ አስፓልት መንገዶችም ተቆፍረዋል።-ለቢቢሲ አረብኛ ቃላቸውን የሰጡ ሰዒድ የተባሉ አርሶ አደር እንደ ሎሚ እና ብርቱኳን ያሉ ምርቶችን የሚምርቱበት የእርሻ መሬታቸው በእስራኤል ጦር ሙሉ በሙሉ እንዲወድም በመደረጉ ከመላ ቤተሰባቸው ጋር ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ መገደዳቸውን ገልጸዋል።-ቢቢሲ ከገለልተኛ ወገን ባያረጋግጥም የእስራኤል ጦር ሆነ ብሎ በቡልዶዘር የእርሻ መሬቶችን እና መንገዶችን ቆፍሯል።-ይህ ክስ እውነት ሊሆን የሚያመላክት የሚችል ቃል መጠይቅ በእስራኤል ጦር ከሁለት ወራት በፊት ተለቆ ነበር።-በዛ ቪዲዮ ላይ የእስራኤል ጦር ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኮለኔል ዮጌቭ ባር-ሼሽተ ቃለ መጠይቅ ሲሰጡ፤ “ወዲህ የሚመለስ ካለ፤ የተቆፈረ መሬት ነው የሚያገኘው። መኖሪያ ቤት የሌለበት፣ የእርሻ መሬት የሌለበት፣ ምንም የሌለበት ነው የሚያገኙት። በዚህም ምንም ሕይወት አይኖራቸውም” ሲሉ ተደምጠዋል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ባለው የማያባራ ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ከ30 ሺህ በላይ መድረሱን በሃማስ አስተዳደር ስር ያለው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።-ከተገደሉት መካከል አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውንም ከጤና ሚኒስትሩ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።-ከመስከረም መጨረሻ በኋላ የተገደሉት ፍልስጤማውያን ቁጥር ጋዛ ካላት 2.3 ሚሊዮን ያህል ህዝብ 1.3 በመቶው ነው ተብሏል።-የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ጦርነቱ ምን ያህል አስከፊ መሆኑንም አመላካች ነው ተብሏል።-የተገደሉት ሰዎች አኃዝ ምን ያህሉ ሰላማዊ ዜጎች ምን ያህሉ ታጋዮች እንደሆኑ አይገልጽም።-ሚኒስቴሩ በባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 81 ሰዎች መገደላቸውን ገልጾ በአጠቃላይም የተገደሉ ሰዎችን ቁጥርም 30 ሺህ 35 እንደደረሰ በዛሬው ዕለት አስታውቋል።-አጋዙ ሆስፒታል ሳይደርሱ ህይወታቸው ያለፉ ፍልስጤማውያንን ያላካተተ በመሆኑም የተገደሉ ሰዎች ቁጥር እጅግ ከዚህ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል። ከነዚህም ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩት እስራኤል በአየር ጥቃቶቿ ወደ ፍርስራሽነት በቀየረቻቸው ህንጻዎች ስር ተቀብረው ይገኛሉ።-በጥቃቱ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች መጎዳታቸውንም የጋዛ የጤና ሚኒስቴር መዝግቧል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት መረጃዎችን የሚያገኙት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ነው።-የዓለም ጤና ድርጅት ከጋዛ አስተዳዳሪ ጋር “የረጅም ጊዜ ትብብር” እንዳለው እንዲሁም “በመረጃ አሰባሰብ ወይም ትንተና የዳበረ አቅም” እንዳለው ተናግሯል። አስተዳደሩ ቀደም ሲል ሲያቀርበው የነበሩ ሪፖርቶች በተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ተዓማኒነት ያለው እና በደንብ የተጠናከረ ነው ተብሎም ይታሰባል።-የዓለም ጤና ድርጅት በባለፉት የጋዛ ጦርነቶች ውስጥ የተገደሉ ፍልስጤማውያንን መረጃ ሲያወዳድርም በአሁኑ የህጻናት እና ሴቶች ሞት ከፍተኛ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ በጦርነቱ የተገደሉ የሰላማዊ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንም ያሳያል ብሏል።-በጋዛ ስለተገደሉ ሰላማዊ ዜጎች እና ታጋዮች የተጠየቀው የእስራኤል ጦር በበኩሉ “10 ሺህ ያህል ገደማ አሸባሪዎች ተገድለዋል” ሲል ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል።-የፍልስጤማውያን ሞት በጋዛ የሚመዘገበው አስከሬን ወይም የአስከሬን አካል በህክምና ባለሙያዎች/ በሆስፒታል ሰራተኞች ሲታይ ነው።-በእያንዳንዱ ቀን መጨረሻ ላይ ሆስፒታሎች የሁሉንም ሟቾች ዝርዝሮችን የሚታወቁ ከሆነ ከስማቸው ጋር፣ የመታወቂያ ቁጥር፣ ጥቃት የደረሰባቸው ወይም የሞቱበት ቀን፣ እና የጉዳታቸውንም ሁኔታ ለጤና ሚኒስቴሩ ይልካሉ። የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ለነዚህም መረጃዎች የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል።
የፎቶው ባለመብት AFP-ኬንያ ወደ ግዛቷ ለሚገቡ ተጓዦች ቪዛ መጠየቋን ካቆመች በኋላ ከጀመረችው አዲስ የጉዞ ፈቃድ ማረጋገጫ ጥያቄ እና ክፍያ ኢትዮጵያውያን ነጻ እንዲሆኑ መወሰኗን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አስታወቁ።-አምባሳደር ባጫ ደበሌ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ኢትዮጵያውያን ከአዲሱ አሠራር ነጻ ሆነው ቀደም ሲል እንደነበረው ወደ ኬንያ መግባት እንዲችሉ በመንግሥት የቀረበውን ጥያቄ የኬንያ መንግሥት ተቀብሎታል።-ኬንያ ካለንበት የአውሮፓውያን ዓመት መጀመሪያ አንስቶ የመላው ዓለም ተጓዦች ያለ ቪዛ በበይነ መረብ አማካይነት የጉዞ ፈቃድ ለማግኘት በማመልከት እና ክፍያ በመፈጸም ብቻ ወደ አገሯ እንዲገቡ አዲስ አሠራር መጀመሯ ይታወቃል።-ነገር ግን ለበርካታ ዘመናት ወደ ኬንያ ያለ ቪዛ እና ክፍያ ሲገቡ በነበሩት ኢትዮጵያውያን ላይ ይህ አሠራር ወጪን እና በውስብስብ የጉዞ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በማድረግ ቅሬታ እና ጥያቄን ሲፈጥር ቆይቷል።-ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን ከኬንያ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገርበት አሳውቆ የነበረ ሲሆን፣ አሁን የኬንያ መንግሥት ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል እንደነበረው ወደ አገሩ ያለ ምንም ክፍያ እንዲገቡ መፍቀዱን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ አስታውቀዋል።-አምባሳደር ባጫ በኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ገጻቸው ላይ የኬንያ መንግሥት ኢትዮጵያውያንን ከአዲሱ የጉዞ ማረጋገጫ የክፍያ ሥርዓት ውጪ እንዲሆኑ የቀረበለትን ጥያቄ በአፋጣኝ ተቀብሎ በመወሰኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።-አምባሳደሩ አክለውም ወደ ኬንያ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ እና ተያያዥ ክፍያ እንደማያስፈልጋቸው ገልጸው፣ ነገር ግን በበይነ መረብ በኩል የሚሞላውን ፎርም ቀድመው መሙላት እንደሚጠበቅባቸው አሳውቀዋል።-ኬንያ ከየትኛውም የዓለም ክፍል ለሚመጡ ተጓዦች ቪዛን በማስቀረት አዲሱን የማመልከቻ እና የክፍያ ሥርዓት የጀመረችው ጎብኚዎች እንደልብ እንዲንቀሳቀሱ ለማስቻል በሯን ክፍት ለማድረግ በያዘችው ዕቅድ መሠረት ነው።-ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ቀድሞውኑም ቪዛም ሆነ ሌላ ማመልከቻ ሳያስፈልጋቸው ወደ ኬንያ በመግባት አስከ ሦስት ወራት የመቆየት ፈቃድ ነበራቸው። የአዲሱን አሠራር መተዋወቅ ተከትሎ ይህ የኢትዮጵያውያን ነጻ እንቅስቃሴ ለተወሰነ ጊዜ ተስተጓጉሎ ነበር።-የኬንያ መንግሥት የጉዞ ማረጋገጫ እና የክፍያ ሥርዓትን ተግባራዊ ካደረገ ከሁለት ወራት ገደማ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄን ተቀብሎ ኢትዮጵያውያን ያለክፍያ ወደ ኬንያ መግባት የሚችሉበት መንገድ መከፈቱን አምባሳደር ባጫ ለቢቢሲ ገልጸዋል።-ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለረጅም ዘመናት ዜጎቻቸው ወደ አንዳቸው ግዛት ሲጓዙ ያለቪዛ ለመግባት የሚያስችል ስምምነት ሰላላቸው የሁለቱ አገር ዜጎች ያለቪዛ እና ክፍያ ያለችግር ሲዘዋወሩ ቆይተዋል።-አዲሱ አሠራር ከተጀመረ በኋላ ኢትዮጵያ አባል ካልሆነችበት የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ አባል አገራት ዜጎች ውጪ ያሉ የአፍሪካ አገራት በሙሉ ኤሌክትሮኒክ የጉዞ ፍቃድ (ኤሌክትሮኒክ ትራቭል ኦተራይዜሽኝ - ኢቲኤ) የሚባለውን እንዲፈጽሙ ይጠበቅባቸዋል።-በዚህ ሂደትም ተጓዦች ከጉዟቸው ሦስት ቀናት ቀድመው ከኬንያ መንግሥት ባለሥልጣናት በበይነ መረብ የሚሞሉት ፎርም ተቀባይነት ማግኘት እና እስከ 30 ዶላር የ ሚደርስ ክፍያ እንዲፈጽሙ ይጠበቅባቸዋል።
አንድ “ግዙፍ ሚዲያ” ለመፍጠር በሚል ዋልታ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት እንዲሁም ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን፤ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ስር ሊጠቃለሉ ነው። በፋና እና በዋልታ ውስጥ የ25 በመቶ ድርሻ ያለው የትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) በጉዳዩ ላይ አለመሳተፉን ለቢቢሲ ገልጿል።-ከገዢው ፓርቲ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው እነዚህ ተቋማት ከሌሎች በተለየ መንግሥታዊ ዜና እና መረጃዎችን በቀዳሚነት በማግኘት እና በማቅረብ የሚታወቁ ናቸው።-ቀደሞ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) አሁን ደግሞ ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ፋና እና ዋልታ፤ እንዲዋሃዱ ለማድረግ ሥራው ካለፈው ታኅሣሥ ወር ጀምሮ በሂደት ላይ እንደሆነ የሁለቱ መገናኛ ብዙኃን ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል።-ለተቋማቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚያስረዱት ሁለቱ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እና የኹነት አዘጋጁ ድርጅት ዋፋ እንዲዋዱ እየተደረገ ያለው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ሀሳብ አመንጪነት” ነው።-በኢህአዴግ የትጥቅ ትግል ጊዜ የተቋቋመው ፋና፤ በአዲስ መልክ የመጀመሪያው “የግል” ሬዲዮ ጣቢያ ሆኖ የተቋቋመው ከ29 ዓመታት በፊት በ1987 ዓ.ም ነበር። ፋና ራዲዮን የመሠረቱት ከአራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ጋር “ግንኙነት አላቸው” የሚባሉት የትግራዩ ኤፈርት፣ የአማራው ንጋት ኮርፖሬት (የቀድሞው ጥረት)፣ የኦሮሚያው ቱምሳ ዲቨሎፕመንት ግሩፕ (የቀድሞው ዲንሾ) እንዲሁም የ“ደቡብ” ክልሉ ወንዶ ናቸው።-ፋና ሬዲዮ በ2003 ዓ.ም. ወደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያደገ ሲሆን፣ ከስድስት ዓመት በፊት በ2010 ዓ.ም. ደግሞ የቴሌቪዥን ጣቢያ መክፈቱ ይታወሳል። ፋና ሬዲዮ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በተለያዩ ክልሎች በሰባት ቋንቋዎች ፕሮግራሞችን የሚያስተላልፉ 12 የማሰራጫ ጣቢያዎች አሉት።-ከፋና ተመሳሳይነት ባለው መልኩ በአራቱ የልማት ድርጅቶች ባለቤትነት የተቋቋመው ዋልታም ምሥረታው ከኢህአዴግ ጋር ግንኙነት ያለው ነው። “የኢህአዴግ ኢንፎርሜሽን ማዕከል” በሚል ስያሜ የዜና ተቋም ሆኖ የተመሠረተው ዋልታ፤ የተቋቋመው በ1986 ዓ.ም ነው።-ዋልታ ካለፈው ዓመት መጨረሻ አንስቶ “አዲስ ዋልታ” ተብሎ የሚጠራውን የቴሌቪዥን ጣቢያ በ2010 ዓ.ም. ያቋቋመ ሲሆን፣ በቅርቡም በውጭ ቋንቋዎች ፕሮግራሞችን የሚያስተላልፍ “አፍሮ ኒውስ” የተባለ የቴሌቪዝን ጣቢያ ከፍቶ በሙከራ ሥርጭት ላይ ነው። ከዚህም ባሻገር የቀድሞውን “አፍሮ ኤፍኤም” በመግዛት እና “አዲስ ዋልታ ኤፍኤም” ወደሚል መጠሪያ በመቀየር የሬዲዮ ጣቢያ ባለቤት ሆኗል።-ሁለቱ ግዙም የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ፋና እና ዋልታ፤ በ2000 ዓ.ም በኹነት ዝግጅት (event organizing) ሥራ ላይ የተሰማራውን ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን አቋቁመዋል። ከሁለቱ ተቋማት ስም የመጀመሪያዎቹን ፊደላት በመውሰድ የተመሠረተው ዋፋ መንግሥታዊ ኹነቶችን በማዘጋጀት በይበልጥ ይታወቃል።-ቢቢሲ የተመለከተው ተቋማቱን ለማዋሃድ የተዘጋጀው ባለ 28 ገጽ የመነሻ ዕቅድ ሰነድ እንደሚያስረዳው፤ ዋልታ፣ ፋና እና ዋፋ እንዲቀላቀሉ የተፈለገበት “ዋናው” ምክንያት “በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ውስጥ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት” የመገናኛ ብዙኃን ተቋም ለመፍጠር ነው።-ሰነዱ “አገራችን ለማሳካት እየሠራችበት ያለውን ብሔራዊ ገዥ ትርክት ዋና አጀንዳው በማድረግ የአገራችንን የብልጽግና ጉዞ ለማፋጠን የሚያስችል ዋነኛ የሚዲያ እና የኮሙዩኒኬሽን አቅም ይሆናል” ሲል በተቋማቱ ውህደት የሚፈጠረው “ግዙፍ ሚዲያ” ምን ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ አስፍሯል።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ ከአራት ወራት በፊት ጥቅምት ላይ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ሥልጠና በሰጡበት ወቅት ስለ ገዢ ትርክት የመፍጠር አስፈላጊነት ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል።-የመነሻ ዕቅድ ሰነዱ እንደሚያስረዳው ከውህደቱ በኋላ የሚፈጠረው መገናኛ ብዙኃን “ለብሔራዊ ጥቅም ዘብ” ሆኖ የሚቆም ሲሆን፣ የመንግሥትን ፖሊሲ እና የተቋማትን አፈጻጸምም “እየተቸ የሚደግፍ ሚዲያ” ይሆናል።-የመገናኛ ብዙኃኑ “ብሔራዊ ገዥ ትርክትን የኢትዮጵያውያን አቋም እና እምነት እንዲሆን” እንደሚሠራ የሚገልጸው ሰነዱ፤ ይህንን ማስረጽ በሚያግዙ “የሚዲያ ሥራዎች” ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግም ይገልጻል።-“የብሔራዊነትን ትርክት በልዩ ልዩ መንገድ ማስረጽ ዓላማቸው የሆኑ የፊቸር ፊልም፣ የዶክመንትሪ ፊልም፣ የሙዚቃ ዝግጅት እና የኅትመት፣ የቴአትር፣ የልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ መድረኮች ሥራዎች” በሚዲያው አማካኝነት እንደሚከወኑም ተጠቅሷል።-የተቋማቱ መዋሃድ ጥቅም ሆኖ በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው ሌላኛው ጉዳይ “ውድድርን ማሸነፍ የሚችል” መገናኛ ብዙኃን የመፍጠር ጉዳይ ነው።-ሰነዱ ይህንን ሀሳብ ሲያብራራ፤ “የሁለቱን ሚዲያዎች አቅም በማቀናጀት የሚፈጠረው ሚዲያ ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር በሰው ሃብት፣ በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስ፣ በቁሳቁስ እና በሌሎችም አቅሞች ተወዳዳሪ ብሎም በልዩ የትኩረት አጀንዳዎቹ መሪ ሚዲያ ለመሆን ይችላል” ይላል።-ተቋማቱ ተዋህደው ይህንን ሥራ የሚያከናውነው የመገናኛ ብዙኃን ሲመሠረት “ፋና” የሚለውን “የነባሩን ሚዲያ ስያሜ” እንደያዘ መቀጠሉ “ተመራጭ” እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል።-ሰነዱ “በሚዲያ ዘርፍ በተለይም በሬዲዮ ሚዲያ ዘርፍ ሰፊ ተቀባይነት ያለው፤ በቴሌቪዥን ዘርፍ ደግሞ ከኢቢሲ የሚወዳደር፣ አንዳንድ ጊዜም ከኢቢሲ የሚበልጥ ሚዲያ በመሆኑ፤ ከዋልታ ስም አንጻር የፋና ስም ገናና ነው” ሲል ፋና የተመረጠበትን ምክንያት ያስረዳል።-ፋና የተመረጠው “በአድማጭ ተመልካቹ ዘንድ የተገነባውን መልካም ስም ለይዘት ለተዓማኒነት ያለውን ፋይዳ ግምት” በማስገባት የተቀመጠ መሆኑን የሚጠቅሰው ሰነዱ፤ ተቋሙ “በገበያ ውስጥ ያለውን የቆየ ስም ማስቀጠልም” ሌላኛው ምክንያት ሆኖ ተጠቅሷል።-ተቋማቱ ሲዋሃዱም አሁን ያለው “ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት” የሚል ስያሜ “ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን” ተብሎ እንደሚቀየር ይጠቁማል።-የፎቶው ባለመብት fana-የመነሻ ዕቅድ ሰነዱ፤ የሦስቱ ተቋማት ውህድ የሆነው “ግዙፍ” የመገናኛ ብዙኃን ሲደራጅ “የቲቪ ዘርፍ፣ የሬዲዮ ዘርፍ፣ የኪነ ጥበብ ዘርፍ፣ እና የኤቨንት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎች” እንዲኖሩት በምክረ ሀሳብነት አስቀምጧል። ተቋሙ ከውህደቱ በኋላ ሦስት የቴሌቪዥን እና ሁለት የራዲዮ ጣቢያዎች እንደሚኖሩትም አስፍሯል።-የመጀመሪያው የቴሌቪዥን ጣቢያ “በዜና፣ በወቅታዊ እና በመዝናኛ” ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ ነባሩ ፋና ቲቪ ለዚህ ተመርጧል። ፋና ቴሌቪዥን ካሉት ጣቢያዎች ውስጥ “ለዜና እና ለወቅታዊ ጉዳዮች አማራጭ” መሆኑ እንዲሁም፤ የጣቢያው የመዝናኛ ፕሮግራሞች “ተመልካች ያላቸው” መሆን ለዚህ ምርጫ በምክንያትነት ተጠቅሷል።-የመዝናኛ ፕሮግራሞች በዚህ ጣቢያ ላይ የሚተላለፍ ቢሆንም ለመዝናኛ እና ለሲኒማ “ራሱን የቻለ ተጨማሪ” የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሚያስፈልግ ሰነዱ አመልክቷል።-ሁለተኛው የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘጋቢ ፊልሞች ላይ የሚያተኩር እንደሚሆነ በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። ዘጋቢ ፊልሞችን ለማስተላለፍ የታቀደው በ“አዲስ ዋልታ” ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲሆን፣ ጣቢያው እንደ አዲስ ስያሜ ሲያገኝ “የዋልታን ስያሜ ፈጠራ በተሞላበት አግባብ መጠቀም” በአማራጭነት ተቀምጧል።-በዋልታ ስር የሚገኘው “አፍሮ ኒውስ” የቴሌቪዥን ጣቢያ ደግሞ በአገር ውስጥ እና በውጭ ቋንቋዎች የሚዘጋጁ ይዘቶችን የሚያስተናግድ እንዲሆን ታጭቷል። ይህ ጣቢያ ይዘቶቹን ሲያቀርብ “ሁለቱም ሚዲያዎች እስካሁን ሲሠሩባቸው የቆዩትን እና አዳዲስ የአገር ውስጥ ቋንቋዎችን” እንደሚጠቀም ሰፍሯል።-ዋልታ ያስጀመረው “አዲስ ዋልታ ኤፍ ኤም” የራዲዮ ጣቢያ “በውጭ ቋንቋ የኢትዮጵያን መልክ እና ጉዞ ለ24 ሰዓት የሚያሰራጭ” እንደሚሆን ሰነዱ ይጠቅሳል። ፋና ሬዲዮ ደግሞ አሠራሩ ላይ “ሪፎርም” አድርጎ ቀድሞም የነበረውን የአገር አቀፍ እና የክልል ሥርጭቶች ይቀጥላል።-በሁለቱ ተቋማት የተመሠረተው የኹነት አዘጋጁ ተቋም ዋፋ በአንጻሩ፤ “ለግዙፉ ተቋም የኹነት ዝግጅት አቅም በመሆን የይዘት ልህቀትን እና የገቢ አቅምን የሚያሳድግ አንድ ዘርፍ” ሆኖ እንደሚቀጥል በሰነዱ ላይ ተቀምጧል። ዋፋ “ሚዲያው ለሚያከናውናቸው የመዝናኛ፣ የፓናል እና ሌሎች የኹነት ሥራዎች አንድ ጠንካራ ክንፍ እንዲሆን ማድረግ” እንደሚቻል ሰነዱ ላይ ተመላክቷል።-ዋፋ “በአገሪቱ ቁጥር አንድ የኤቨንት አዘጋጅ” እንዲሆንም የታቀደ ሲሆን፣ “ደረጃውን የጠበቀ የድምጽ ማቀነባበሪያ እና መቅረጫ ስቱዲዮ እንዲኖረው” እንደሚደረግም ሰነዱ ያመለክታል። “በኪነ ጥበቡ ዘርፍ በአገሪቱ የመጀመሪያ የሚሆነውን የፊልም መንደር በመገንባት” የሚመሠረተው መገናኛ ብዙኃን ለራሱ ፊልሞች እንዲጠቀም እና ለሌሎች ፊልም ሠሪዎች እንዲያከራይ ማድረግም ከዕቅዶቹ መካከል ነው።-ባለ 28 ገጹ የውህደት ሰነድ እንደሚያስረዳው የመገናኛ ብዙሃኑ የውህደት ሂደት በበላይነት የሚመራው ከሁለቱም ተቋማት የሚወጣጡ አባላት ባሉት ዐቢይ ኮሚቴ ነው። የዐቢይ ኮሚቴው አባላት የሚመረጡት በጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሆነ ሰነዱ ላይ ሰፍሯል። ከዐቢይ ኮሚቴው ስር ስድስት የቴክኒክ ኮሚቴዎች እንደሚኖሩም ተጠቅሷል።-ቢቢሲ ያነጋገራቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚያስረዱ ኮሚቴዎቹ ተቋቁመው ሥራ ከጀመሩ ሁለት ወር ገደማ ሆኗቸዋል። ኮሚቴዎቹ የሚመሩት የውህደት ሥራ እስከ ቀጣዩ መጋቢት ወር ድረስ እንደሚጠናቀቅ እና ለተቋሙ አዲስ ሥራ አስፈጻሚ ይመረጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የቢቢሲ ምንጮች ገልጸዋል።-ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከፋና እና ዋልታ አመራሮች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረጋቸው ጥረቶች አልተሳኩም።-የዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፋንታዬ ጌታነህ በበኩላቸው ውህደትን በተመለከተ “በግላቸው” የደረሳቸው ነገር እንደሌለ እና ከአገር ውጭ እንደነበሩ በመግለጽ ስለ ውህደቱ ማረጋገጫ ከመስጠት ተቆጥበዋል።-ይሁንና ሥራ አስፈጻሚዋ “ገና ነው” ሲሉ ሂደቱ መረጃ መስጠት በሚያስችል ደረጃ አለመሆኑን ጠቅሰዋል። ወ/ሮ ፋንታዬ አክለውም፤ “[ውህደት] ለጥሩ ነገር የሚደረግ ነገር እንደሆነ ነው ማሰብ የሚቻለው። ለብቻ ከመሮጥ፤ መተባበር መተዘጋገዝ ክንድ ነው። ተጋግዞ መሥራት፣ ተጋግዞ መሄድ የበለጠ አቅም ይፈጥራል” ብለዋል።-የዋልታ እና ፋና ውህደትን አስመልከቶ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በሂደቱ ላይ “ሊያጋጥሙ የሚችሉ” ተብለው ከተጠቀሱ ተግዳሮቶች መካከል በተቋማቱ ውስጥ ድርሻ ያለው የትግራዩ ኤፈርት ጉዳይ ይገኝበታል።-ከኤፈርት በኩል “ከባለቤትነት ጋር የተያያዘ ፈተና” ሊያጋጥም እንደሚችል የጠቀሰው ሰነዱ፤ “ህወሓት እንደ ድርጅት በሁለቱም ተቋማት ውስጥ በኢንዶውመንቱ በኩል የነበረው የባለቤትነት ጉዳይ እልባት ማግኘቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል” ሲል የመፍትሔ ሀሳብ አስቀምጧል።-በስሩ 34 ድርጅቶችን የያዘው ኤፈርት ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተይይዞ እስካለፈው ዓመት መጨረሻ ድረስ ተቋማቱን እንዳያስተዳድር በፍርድ ቤት እግድ ተጥሎበት ነበር።-በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ ድርጅቶቹን ሲያስተዳድር የነበረው የኮሜርሻል ኖሚኒስ እንደነበር የኤፈርት የኢንቨስትመንት እና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎይቶም ይብራህ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-ይሁንና ኤፈርት ድርጅቶቹን ከኮሜርሻል ኖሚኒስ ከተቀበለ በኋላ ከነሐሴ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተደጋጋሚ ደብዳቤዎችን ቢጽፍም በዋልታ እና በፋና የአመራር ቦርዶች ውስጥ ሊኖረውን የሚገባውን ውክልና እስካሁን ድረስ አለማግኘቱን ገልጸዋል።-በዚህም ምክንያት የተቋማቱን ውህደት በተመለከተ በኤፈርት በኩል የተደረገ ተሳትፎ አለመኖሩን የሚናገሩት አቶ ጎይቶም፤ ይሁንና “በመረጃ ደረጃ” ስለ ጉዳዩ መስማታቸውን ገልጸዋል።-“እንደ ባለድርሻ በብዙኃን ድምጽ (majority) የማይወሰን ነገር አይኖርም ብዬ አላስብም። ግን የባለድርሻ ሀሳቡ መደመጥ አለበት። ሀሳቡ ከተደመጠም በኋላ የራሱን ውሳኔ ሊወስን ይችላል” ሲሉ በመገናኛ ብዙኃን ተቋማቱ ውስጥ 25 በመቶ ድርሻ ያለው የኤፈርት ሀሳብ ሊካተት እንደሚገባ ተናግረዋል።-በሁለቱ ተቋማት ውስጥ ሌላኛው ባለድርሻ የሆነው ንጋት ኮርፖሬት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ስለማሳለፉ ከቢቢሲ ጥያቄ የቀረበላቸው የኮርፖሬቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ስዩም መኮንን፤ “በቅርብ ስላልነበርኩ አላወቅሁም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።-ከቱምሳ ዲቨሎፕመንት ግሩፕ ተመሳሳይ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ ያቀረበው ጥያቄ ይህ ዘገባ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ምላሽ አላገኘም።
የፎቶው ባለመብት COSMEDACARE-ዶ/ር ኦጉን ኤርሰን ይባላል። ቱርካዊ የሰውነት ክብደት ቅነሳ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ነው።-“ክብደት መቀነሻ” መንገዶች የሚላቸውን በመሸጥ ይታወቃል።-ቢቢሲ ስለ ዶክተሩ የበለጠ ለማወቅ ምርመራ አድርጓል። ጋዜጠኛ መሆኗን ሳትጠቅስ ዶክተሩን ያናገረችው የቢቢሲ ጋዜጠኛ፣ ይህ ዶክተር “ክብደት ጨምሪ” እንዳላት ትናገራለች።-የሰውነት ክብደትና ቁመት መመጣጠን በሚለካበት ቢኤምአይ መሠረት 24.4 ናት። ሆኖም ግን “ምግብ በመብላት” ሰውነቷን እንድትጨምር በዶክተሩ ተነግሯታል።-“ተመገቢ፣ ተመገቢ፣ ተመገቢ። የሰውነት ክብደትሽን ከአጠቃላይ ቁመናሽ አንጻር ከፍ አድርጊው” ብሏታል።-የሰውነት ክብደት መቀነሻ የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱን ለማግኘት መወፈር እንዳለባት ነበር ለጋዜጠኛዋ የነገራት።-ጋዜጠኛዋ ወደ ዶክተሩ ቢሮ ሄዳ ትክክል ያልሆነ የሰውነት ክብደት መጠን አስመዘበች። ምርመራ ያደረገላት አልነበረም።-ዶ/ር ኦጉን ከሦስት ወር በኋላ ለቀዶ ሕክምና ቀጠራት።-እስከዚያው ክብደት እንድትጨምር ነገራት።-አንድ የጤና ባለሙያ ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ ታካሚዎች ክብደት እንዲጨምሩ ማበረታታት ከሙያዊ ሥነ ምግባር ውጭ ነው።-ቀዶ ሕክምና ካላስፈለገ መከናወን እንደሌለበት እና ከሆነ በኋላ መቀልበስ ለማይቻል ለጉዳቶች እንደሚዳርግ ያስረዳሉ።-በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ክብደት የመቀነስ ቀዶ ሕክምና እስከ 15 ሺህ ፓውንድ ያስወጣል። በቱርክ ግን በ2000 ፓውንድ ይሠራል።-ከሙያዊ ሥነ ምግባር ውጭ ሕክምናውን የሚሰጡ ተቋማት እንዳሉ የቢቢሲ ምርመራ ይጠቁማል።-በቱርክ ካሉ ብዙ ሐኪም ቤቶች አንዱ ኢኮል ነው።-ዩኬን ጨምሮ በተለያዩ አገራት ደንበኞች ለማግኘት ማስታወቂያ ይሠራል።-ከልክ ያለፈ ውፍረት የሚገጥማቸው ሰዎች የሚደረግላቸው ቀዶ ሕክምና (bariatric surgery) ባልተገባ ሁኔታ የሚሰጥ ተቋም እንደሆነ ታይቷል።-ለምሳሌ የሰውነት ክብደታቸው ከቁመተቻው አንጻር (ቢኤምአይ) ሲነጻጸር ለዚህ ቀዶ ሕክምና በቂ ያልሆነ ሰዎችን ለሕክምናው ይመዘግባል።-የቢቢሲ ጋዜጠኛ በድብቅ ያነሳው የዶክተሩ ፎቶ-ከ40 በታች ቢኤምአይ ያላቸው እና ከልክ ካለፈ የሰውነት ክብደት ጋር በተያያዘ ሕመም የሌለባቸው ሰዎች ይህንን ቀዶ ሕክምና እንዲያደርጉ አይመከርም።-ይህ ቀዶ ሕክምና ከልክ ያለፈ ውፍረት አስጊ የጤና ሁኔታ ውስጥ ላስገባቸው ሕሙማን የሚከናወን የመጨረሻ የሕክምና አማራጭ ነው።-ይህ ማለትም ከ40 አልያም ከ35 የዘለለ አይቢኤም ያላቸው እና ከልክ ካለፈ ውፍረት ጋር በተያያዘ የጤና እክል የገጠማቸው ታካሚዎች እንደ አማራጭ የሚሰጣቸው ቀዶ ሕክምና ነው።-የሰውነት ክብደት ለመቀነስ ሞክረው ያልተሳካላቸው ታካሚዎች መሆንም አለባቸው።-ሁለት ታዋቂ የሰውነት ቅነሳ ቀዶ ሕክምናዎች አሉ። አንደኛው የሆድ ክፍል ወጥቶ ምግብ የሚብላላበትን መንገድ ለመለወጥ የሚደረገው (Sleeve gastrectomy or gastric bypass) ነው።-ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ የሆድን መጠን በመቀነስ ሰዎች የሚመገቡትን መጠን መቀነስ (Gastric band) ነው።-ሁለት የቢቢሲ ጋዜጠኞች ወደ ቱርኩ ሆስፒታል አቅንተው ነበር።-የአንደኛዋ ቢኤምአይ 29 የሌላዋ 33 ነበር። በሕክምና አሠራር መሠረት ሁለቱም ቀዶ ሕክምናው አያስፈልጋቸውም።-አንደኛዋ ጋዜጠኛ የድባቴ ችግር እንደገጠማት ተናግራለች። ይህም ለቀዶ ሕክምናው ዝግጁ እንዳልሆነች ጠቋሚ መሆን ነበረበት።-ሆኖም ግን ሆስፒታሉ ጋዜጠኛው የምትመገበውን መጠን ጨምራ እና ወፍራ ለቀዶ ሕክምና እንድንትሄድ ተነገራት።-የሆስፒታሉ የሽያጭ ባለሙያ “የምበላውን በማስተካከል ለመቀነስ 30 ዓመት ሞክሬያለሁ። ይሄ ባህላዊ መንገድ ይሻላል? ለጥቂት ወራት ከፍተኛ ስብና ካሎሪ መብላት እና መመለስ አይሻልም” ብላታለች።-ሆስፒታሉ ግን ከዓለም አቀፍ መርኅ በተጻራሪው ቀዶ ሕክምናው ለማያስፈልጋቸው እንደማይሰጥ ነው የሚያስተዋውቀው።-ዶ/ር ኦጉን አስተያየቱን ሲጠየቅ ታካሚዎች ከልክ ያለፈ እንዲወፍሩ መንገሩን አስተባብሏል።-የሽያጭ ባለሙያዋ ደግሞ “የጤና ሥርዓቱ መቋቋም ከሚችለው በላይ ከልክ ያለፈ ውፍረት ተፈጥሯል። ሕክምናው የበለጠ ተደራሽ መሆን ነበረበት” ብላለች።-የሰውነት ቅነሳ ቀዶ ሕክምና አማካሪው ኦማር ካሀን እንደሚሉት፣ ታካሚዎች እንዲወፍሩ መገፋፋት ተቀባይነት የለውም።-“በጣም ያሰጋኛል። ታካሚዎቹ ውፍረታቸውን ጨምረው ቀዶ ሕክምና ማድረግ የግድ የሚሆንበት ነጥብ ላይ እንዲደርሱ ነው የሚገፋፋው። ይሄ ከሙያው ሥነ ምግባር ያፈነገጠ ነው” ብለዋል።-የጎንዮሽ ጉዳት የማያስከትል ቀዶ ሕክምና እንደሌለ፣ ነገር ግን እነዚህን ውስን ለማድረግ እንደሚሞከር የሚናገሩት ባለሙያው፣ “ቀጭን ሰው ይህንን ቀዶ ሕክምና ማድረግ የለበትም። ምንም ሳይጠቀሙ ለጎንዮሽ ጉዳት ብቻ ይጋለጣሉ” በማለት ችግሩን ያስረዳሉ።-ለውበት የሚደረግ ቀዶ ሕክምና ተቋም ያላቸው ባለሙያ ጊል ባይርድ፣ ለሰውነት ቅነሳ ቀዶ ሕክምና የሚሄዱ ሰዎችን እንደማይቀበሉ ይናገራሉ።-“አንዳንዶች ከባድ ነገር ኪሳቸው ውስጥ ከተው የሰውነት ክብደታቸው ከፍተኛ ስለሆነ ቀዶ ሕክምና እንደሚፈልጉ ሊያሳምኑን ይሞክራሉ። እኛ የምንመዝነው ግን ፈትሸን ነው” ይላሉ።-“ይህን ሲያደርጉ የሚደርስባቸውን ጉዳት አያስቡትም” ሲሉ ባለሙያዋ ያብራራሉ።-ቀዶ ሕክምናውን ማግኘት ያልቻሉ ሰዎች ወደ ሌሎች አገራት እየሄዱ ሕክምናውን እንደሚወስዱም ባለሙያዋ አክለዋል።-“አንድ ቀዶ ሕክምናውን አናደርግልሽም ያልናት ሴት ሌላ አገር ሄዳ ቀዶ ሕክምናውን አደረገች። በጣም ያሳዝናል። ከሳምንታት በኋላ መሞቷን ሰማን። ይህ ቀዶ ሕክምና ቀላል ነገር አይደለም” ሲሉም ተናግረዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ-የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከአማራ ክልል ጋር በይገባኛል እያወዛገቡ ያሉትን አካባቢዎች ጉዳይ በሕዝብ ውሳኔ መፍትሄ ለመስጠት ከስምምነት ተደርሷል መባሉን አስተባበለ።-ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለፈው ሳምንት በመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን በኩል የአከራካሪ ቦታዎችን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታት “ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ከአማራ እና ከትግራይ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ ነበር” ማለቱን በመጥቀስ ነው፤ “ፍጹም የተሳሳተ [ነው]” ሲል አስተባብሏል።-የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዛሬ ሰኞ ጥር 27/2016 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ ሕዝበ ውሳኔውን እና ሌሎች ጉዳዮችን በማንሳት ምላሽ ሰጥቷል።-የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጥር 23/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ በፌደራል መንግሥት በኩል ለትግራይ ክልል ተደረገ ያለውን የበጀት እና ሌሎች ድጋፎችን በዝርዝር አስፍሯል።-የተፈናቃዮች እና የይገባኛል ጥያቄ ስለሚነሳባቸው አካባቢዎች የጠቀሰው የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ “የአከራካሪ ቦታዎችን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታትም በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ጉዳዩ በዋናነት ከሚመለከታቸው ከአማራ እና ከትግራይ ክልሎች ጋር መግባባት ተደርሶ ነበር” ሲል አትቷል።-በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ ጉዳዩን “ፍጹም የተሳሳተ” ሲል በዛሬው መግለጫ አስተባብሎ፣ ጉዳዩን “ተቀባይነት የሌለው” ሲል ውድቅ አድርጎታል።-ጉዳዩን በሕዝብ ውሳኔ ለመፍታት ስምምነት ተደርሷል መባሉ፤ “ጊዜያዊ አስተዳደሩም ሆነ ፌደራል መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማድረግ ጉዳዩን ለመፍታት ከደረሱበት ስምምነትም ሆነ ካላቸው ሥልጣን ውጪ የሆነ ተግባር” መሆኑን አስተዳደሩ አብራርቷል።-ከዚህ በተጨማሪም ከተፈናቃዮች ጋር በተያያዘ በመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን በኩል የወጣውን መግለጫም እንደማይቀበለው ይፋ አድርጓል።-የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎቱ በመግለጫው ተፈናቃዮችን በተመለከተ የፌደራል መንግሥቱ ያከናወነውን ሥራ ጠቅሷል።-መግለጫው “በአንዳንድ አካባቢዎችም ትክክለኛ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ አድርጓል” ሲልም አክሏል።-የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ይህን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ “እጅግ አደገኛ” ሲል በመግለጽ፣ “‘ትክክለኛ ተፈናቃይ’ [እና] ‘ትክክለኛ ያልሆነ ተፈናቃይ’ በሚል መፈታት የነበረበትን ችግር የበለጠ የሚያባብስ አደገኛ ትንታኔ ስለሆነ አንቀበለውም” ሲል መግለጫውን ውድቅ አድርጎታል።-የአቶ ጌታቸው ረዳ አስተዳደር አክሎም፤ “እንደዚህ ዓይነት መግለጫ መውጣቱ የፌደራል መንግሥቱ የመፍትሄው አካል መሆን ሲገባው የችግሩ አካል ለመሆን የወሰነ የሚያስመስለው ስለሆነ በፍጹም ተቀባይነት የለውም” ብሏል።-የፌደራል መንግሥቱ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወዲህ ለትግራይ ክልል ያደረገውን የበጀት እና መሰል ድጋፎች በተመለከተ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት እንደሚቀርብ የጊዜያዊ አስተዳደሩ በዛሬው መግለጫው በመጥቀስ ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቷል።-በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎች ለሁለቱም ክልሎች እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ሲሆን፣ ሁለቱንም ክልሎች የሚያስማማ መፍትሄ ሳይገኛ በእንጥልጥል ያለ ነገር ነው።-ይህ የአወዛጋቢዎቹ አካባቢ ጉዳይ ዘላቂ እና አስማሚ መፍትሄ ያልተገኘለት ከመሆኑ ባሻገር በፌደራል መንግሥቱ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል ዋነኛ የራስ ምታት ሆኖ ዘልቋል።
የፎቶው ባለመብት NATASHA KERR-በቀዶ ሕክምና ሰበብ ከሞቱት ሴቶች መካከል የ31 ዓመቷ ሜሊሳ ኬር አንዷ ናት-የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለውበት ሲባል በቱርክ በሚደረግ የቀዶ ሕክምና የሚሞቱ ሴቶች ቁጥር በመጨመሩ ከቱርክ መንግሥት ጋር ሊነጋገር ነው።-ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ዜጎች የመቀመጫ መጠን ከፍ ለማስደረግ በቱርክ ቀዶ ሕክምና ካደረጉ በኋላ ሕይወታቸው አልፏል።-ይህን ተከትሎ የዩኬ ባለሥልጣናት የሕክምና እና የኮስሞቲክስ (ውበት) ቀዶ ሕክምና ቱሪዝም መመሪያዎች እና ደንቦችን በተመለከተ ከቱርክ አቻዎቻቸው ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልጿል።-የ31 ዓመቷ ሜሊሳ ኬር እአአ 2019 ኢስታንቡል ከተማ በሚገኝ ሜዲካና ሃዝኔዳር በተባለ የግል ሆስፒታል የመቀመጫ መጠንን ከፍ ለማስደረግ ቀዶ ሕክምና ካደረገች በኋላ ሕይወቷ አልፏል።-የሜሊሳ ኬር ሞትን የመረመረው የዩኬ መንግሥት አካል የ31 ዓመቷ ሴት ወደ ቱርክ አቅንታ የውበት ቀዶ ሕክማናውን ከማድረጓ በፊት ቀዶ ሕክምናው ሊያስከትለው ስለሚችለው ጉዳት በቂ መረጃ አልተሰጣም ብሏል።-የዩኬ የጤና ሚኒስትር ማሪያ ካውልፊልድ መንግሥት ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል።-ካውልፊልድ የጤና ሚኒስቴር እና ማኅበራዊ አገልግሎት ባለሥልጣናት በጉዳዩ ላይ ከቱርክ አቻዎቻቸው ጋር ለመምክር በቅርቡ ወደ ቱርክ ያመራሉ ብለዋል።-የሜሊሳ ኬር ሞትን የመረመረው አካል ለውበት ተብለው ከሚደረጉ ቀዶ ሕክምናዎች በሙሉ የመቀመጫ መጠንን ከፍ ለማድረግ የሚደረገው አደገኛ ነው ያለ ሲሆን፤ ለወጣቷ ሞት ምክንያትም በቀዶ ሕክምና ወቅት የረጋ ደም ወደ ሳምባዋ በመግባቱ ነው ብሏል።-የዩኬ መንግሥት ዜጎቹ በቂ መረጃ ሳይኖራቸው ለውበት ሲባል የሚደረግ የቀዶ ሕክምና ለማድረግ ከአገር ውጭ መጓዛቸውን ቀጥለዋል ይላል።-እአአ 2020 ላይ የሦስት ልጆች እናት የነበረች ሴት ስብ ከሰውነቷ ለማስመጠጥ ባመራችበት ቱርክ ሕይወቷ አልፏል። ከዚህ በተጨማሪም ክብደት ለመቀነስ ቀዶ ሕክምና ያደረጉ 7 እንግሊዛውያን በቱርክ ሕይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቦ ነበር።-ሚኒስትሯ የአንዳንድ አገራት የጤና አሰጣጥ መመሪያ እና ደንብ ከዩናትድ ኪንግደም ደረጃ ጋር እንደማይስተካከል መንግሥት ያውቃል ያሉ ሲሆን፣ ወደፊት የታካሚዎችን ለአደጋ የመጋለጥ ዕድል ለመቀነስ “ግልጽነት ያለው አሰራር እና ደረጃ ማውጣት ያስፈልጋል” ብለዋል።-ሴቶች የመቀመጫቸውን መጠን ከፍ ለማድረግ ቀዶ ሕክምና ለማድረግ ከመወሰናቸው በፊት ሕክምናው ሊያስከትለው የሚችለው የጎንዮሽ ጉዳት በተመለከተ ሙሉ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።-በተለይ ለውበት ተብለው ከሚደረጉ ቀዶ ሕክምናዎች መካከል የመቀመጫ መጠንን ከፍ ለማድረግ ተብሎ የሚከናወነው ቀዶ ሕክምና 10 እጥፍ የሞት አደጋን ይደቅናል ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሶማሊያ የባሕር ጠረፍ ዘራፊዎች እንደ አዲስ መርከቦችን ዒላማ ማድረግ ጀምረዋል።-ይህ ክስተት ከአስርት ዓመታት በፊት የነበረውን ትዝታ አየመለሰ ነው።-በወቅቱ የታጠቁ የሶማሊያ ፓይሬቶች የባሕር ጠረፉን ተቆጣጥረው መርከቦችን በማገት ሚሊዮን ዶላሮች ክፍያ ይጠይቁ ነበር።-ይህ ዓለምን አስጨንቆ የነበረ ዝርፊያ ሀገራት ተደራጅተው የሥፍራውን ደኅንነት ለመጠበቅ ባደረጉት ሙከራ ቀዝቅዞ ነበር።-ነገር ግን ከሰሞኑ ታጣቂዎች መርከቦችን እያገቱ ክፍያ መጠየቅ መጀመራቸው አቅማቸውን አደራጅተው እንደ አዲስ ተነስተው ይሆን ወይ የሚለውን ጥያቄ ጭሯል።-በምስራቅ አፍሪካ የባሕር ጠረፍ ደኅንነት የሚቆጣጠረው የአውሮፓ ኅብረቱ ኢዩናቫፎር አታላንታ መረጃ እያሰባሰበ ነው።-ድርጅቱ እንደሚለው ካለፈው ኅዳር ጀምሮ 14 መርከቦች በሶማሊያ የባሕር ጠረፍ ፓይሬቶች ታግተዋል።-በዚያው ወር የኢራን ባንዲራ የሰቀለች ዓሳ አጥማጅ መርከብ ጥቃት ደረሰበት። ከሁለት ቀናት በኋላ ደግሞ የላይቤሪያ ባንዲራ ያነገበች መርከብ የፓይሬቶቹ ዒላማ ሆነች።-በሁለቱም መርከቦች ውስጥ የነበሩ ሠራተኞች አልተጎዱም።-ሴንትራል ፓርክ የተሰኘውን የላይቤሪያ መርከብ ያዳኑት የአሜሪካ ወታደሮች ሲሆኑ ታጣቂዎች የሶማሊያ ፓይሬቶች ሳይሆኑ አይቀሩም ይላሉ።-ባለፈው ታኅሣሥ ደግሞ የማልታ ባንዲራ የሰቀለችው ኤምቪ ሩዌን ታገተች።-መርከቧ አሁንም በታጣቂዎቹ ቁጥጥር ሥር ያለች ሲሆን 17 የመርከቧ ሠራተኞችም ታግተው ይገኛሉ።-ዓለም አቀፉ ማሪታይም ቢሮ እንደሚለው ይህች መርከብ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሶማሊያ የባሕር ጠረፍ ዘራፊዎች ቁጥጥር ሥር የዋለች የመጀመሪያዋ መርከብ ናት።-ባለፈው የጥር ወርም እንዲሁ ተመሳሳይ ጥቃቶች የደረሱ ሲሆን የሕንድ ባሕር ኃይል ባሳፍነው ሳምንት ብቻ ሶስት መርከቦችን አድኗል።-ባለፈው አርብ የሕንድ ባሕር ኃይል 11 ኢራናዊያን እና 8 ፓኪስታናዊያን የያዘች መርከብ ማዳኑን ተናግሯል።-የሶማሊያ ፓይሬቶች በአዲስ መልክ ሥራ የጀመሩት ያለውን የደኀንነት ክፍተት አይተው ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ።-ትሮልስ በርሻል ሄኒንግሰን የሮያል ዳኒሽ ዲፌንስ ኮሌጅ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው።-በአውሮፓውያኑ 2005 እና 2012 በሥፍራው የባሕር ጠረፍ ዘራፊዎች መንሰራፋት ሲጀምሩ የዓለም ሀገራት ተደራጅተው ቦታውን መጠበቅ ጀምሩ።-ነገር ግን በቅርቡ በቀይ ባሕር ጠረፍ የየመን ሁቲ ታጣቂዎች የሚያደርሱትን ጥቃት ለመግታት በማለት እኒህ ኃይሎች አድራሻቸውን ቀይረዋል ይላሉ።-“በወታደራዊ ቋንቋ ስናወራ የየመን ሁቲዎችን ሚሳዔል እና ድሮን ጥቃት መመከት ትልቅ ሥራ ነው። ስለዚህ ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ማድረግ ከባድ ነው” ይላሉ ምሑሩ።-የኢንዲያን ኦሽን ኮሚሽን እንደ ሲሼልስ እና ኮሞሮስ ያሉ ሀገራት ያሉበት ቀጣናዊ ድርጅት ነው።-ኮሚሽኑ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ የባሕር ጠረፍ ዘራፊዎች እንደ አዲስ ያገረሹበት ሌላም ምክንያት አለ ይላል።-የሶማሊያ ፓይሬቶች ከፍተኛ ጥቃት አድርሰው የነበረው ከ10 ዓመታት በፊት ነበር።-አሁን አሁን አንዳንድ ዓሳ አጥማጆች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ዓሳ የሚያጠምዱ የውጭ ድርጅቶች ኑሮ የሚገፉበትን መንገድ ሲቀሟቸው ወደ ባሕር ጠረፍ ዘራፊነት ገብተዋል ይላል ኮሚሽኑ።-ኢስላማዊው ታጣቂ ቡድን አል-ሸባብ የባሕር ጠረፍ ዘራፊዎች ከዘረፉት ገንዘብ ኮሚሽን የሚያገኙ ከሆነ ለዘራፊዎች የጦር መሣሪያ እንደሚሰጡ የሚጠቁሙ ዘገባዎች መውጣት ጀምረዋል።-የፎቶው ባለመብት INDIAN NAVY-የህንድ ባሕር ኃይል የባሕር ጠረፍ ዘራፊዎች በቁጥጥር ሥር ካዋለ በኋላ የለጠፈው ፎቶ-በአውሮፓውያኑ 2005 እና 2012 በአፍሪካ ቀንድ ያሉ የባሕር ጠረፍ ዘራፊዎች ከ339 እስከ 413 ሚሊዮን ዶላር ዘርፈዋል ይላል የዓለም ባንክ ዘገባ።-ይህ የሚያደርጉት መርከቦችን በቁጥጥር ሥር በማዋልና ሠራተኞችን አግቶ ክፍያ በመጠየቅ ነው።-የናይጄሪያው ፌዴራል ዩኒቨርሲቲ መምሕር የሆኑት ሳሙዔል ኦየዌሌ በቅርብ ጊዜ እየታዩ ያሉት እገታዎች ዋና ዓላማቸው ገንዘብ ነው ይላሉ።-የምስራቅ አፍሪካን የባሕር ጠረፍ የሚያጠኑት ምሑሩ ሌላም ምክንያት ሊኖር እንደሚችል ቡገምቱም ማወቅ ቀላል አይሆንም ይላሉ።-“ከዚህ ቀደም በሥፍራው የነበሩትን እገታዎች ዓለም አቀፍ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች መግታት ችለው ነበር።”-“አሁን ግን ምክንያታቸው ምን እንደሆነ ማወቅ ከባድ ነው” ሲሉ ያስረዳሉ።-ኢንዲያን ኦሽን ኮሚሽን በቅርቡ የታዩት እገታዎች “አሳሳቢ ናቸው” ብሎ የተባበሩት መንግሥት ፀረ-ፓይሬትስ ተቋም አስቸኳይ ስብሰባ ማድረግ አለበት ሲል ይመክራል።-ሌሎች መሰል ተቋማት በሶማሊያ ባሕር ጠረፍ ላይ እየታዩ ያሉትን እገታዎች “እጅግ አሳሳቢ ናቸው” የሚሉ መግለጫዎች እያወጡ ነው።-ቢሆንም ይህ የዓለም አቀፍ ንግድ መተላለፊያ የሆነ ቦታ ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት “በሌላ ክስተት ተውጧል” ይላሉ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ።-“በቀይ ባሕር ላይ እየሆነ ያለው ነገር በእርግጥም ከዚህ የበለጠ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፤ አደገኛም ነው” ሲሉ የየመን ታጣቂዎች ጥቃት የሶማሊያውን እንደሸፈነው ይናገራሉ።-ኢንዲያን ኦሽን ኮሚሽን እንደሚለው በቅርቡ ከተከሰቱት እገታዎች 6 ያክሉ የባሕር ጠረፍ ዘረፋ ባሕሪ አላቸው።-ኢንተርናሽናል ማሪታይም ቢሮም እንዲሁ “እገታዎች የባሕር ጠረፍ ዘረፋ [ፓይሬሲ] ናቸው” ሲል ለቢቢሲ ይናገራል።-መገናኛ ብዙኃን ዘራፊዎቹ መርከቦችና ሠራተኞቻቸውን ካገቱ በኋላ ማስለቀቂያ ገንዘብ እየጠየቁ ነው ሲሉ ዘግበዋል።-የቼስተር ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ቀንድ ምሑር የሆኑት ዶ/ር ጄስ ሲሞንድስ ከሰሞኑ የተከሱት እገታዎችን በዝግታ ማጥናት ያስፈልጋል የሚል አስተያየት ይሰጣሉ።-የተባበሩት መንግሥታትን ትንታኔ ጠቅሰው እንደሚሉት የባሕር ጠረፍ ዘረፋ ከአንድ ሀገር የውሃ ክልል ውጭም ሊከሰት ይችላል።-ዶ/ር ሄኒንግሰን እና ዶ/ር ኦየዌሌ ሥፍራውን ሲቆጣጠሩ የነበሩት ዓለም አቀፍ የባሕር ኃይሎች በየመን ጠረፍ አቅራቢያ ያለውን ጥቃት ለመመከት ወደ ሥፍራው ቢያቀኑም የሶማሊያውን ዘረፋ ለመመከት የሚያስችል አቅም አሁንም አላቸው ይላሉ።-ኢዩናቭፎር እና ሌሎች እንደ ሕንድ፣ እና ዩናይትድ ስቴትስ ያሉ የባሕር ኃይሎች ከሰሞኑ በርካታ ጥቃቶችን ማክሸፍ ችለዋል።-ነገር ግን ኢንዲያን ኦሽን ኮሚሽን እንደሚለው ከሕንድ ባሕር ኃይል በቀር ሌሎቹ አቅማቸውን ቀንሰው ነው በሥፍራው እየተንቀሳቀሱ ያሉት።-ዶ/ር ኦየዌሌ እንደሚሉት በሥፍራው ያለው ፖለቲካዊ ውጥንቅጥ አሁን ለተከሰተው የባሕር ጠረፍ ዝርፊያ አስተዋፅዖ አድርጓል።-የሁቲ አማፂያን እስራኤል በጋዛ የምታደርሰውን ወታደራዊ እርምጃ የምታቆም ከሆነ መርከቦች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት ለማቆም ቃል ገብተዋል።-ሶማሊያ ደግሞ ነፃነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር አለመግባባት ላይ ናት።-ሶማሊላንድ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ጋር የገባቸውን ስምምነት ተከትሎ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት ውጥረት ዘንቦበታል።
የፎቶው ባለመብት Abdulkadir Mohamed Nur-የሶማሊያ እና የቱርክ የመከላከያ ሚኒስትሮች (አብዲካዲር ሞሐመድ ኑር እና ያሳር ጉለር)-የሶማሊያ እና የቱርክ መንግሥታት በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች ትብብር ለማድረግ ስምምነት መፈራረማቸውን ይፋ አደረጉ።-ይዘቱ በዝርዝር ያልተገለጸው የሁለቱ አገራት ስምምነት የመከላከያ ሚኒስትሮቻቸው በተገኙት መፈረሙን የሶማሊያ የዜና ወኪል እና የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጸዋል።-የሶማሊያ ዜና ወኪል (ሶና) ታሪካዊ ሲል የገለጸው ስምምነት የተፈረመው ሞቃዲሹ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በደረሰችው የባሕር ጠረፍ የማግኘት ስምምነት ከአዲስ አበባ ጋር ውጥረት ውስጥ በገባችበት ወቅት ነው።-ስምምነቱ በቱርክ መዲና አንካራ በሚገኘው የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ሲፈረም የቱርክ የመከላከያ ሚኒስትር ያሳር ጉለር “ሶማሊያ በአፍሪካ የቱርክ ወሳኝ አጋር ነች” ብለዋል።-ሚኒስትሩ ከሶማሊያው አቻቸው ጋር ውጤታማ የሆነው ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸው፣ በበውይይታቸው ላይ “የሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት አስፈላጊነት ላይ ተነጋግረናል” ስለማለታቸው የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።-የሶማሊያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ስምምነቱ የሶማሊያን እና የቀጠናውን ደኅንነት የማጠናከር ዓላማ ያለው ነው ብሏል።-የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብዲካዲር ሞሐመድ ኑር “ለሶማሊያ ሕዝብ እና መንግሥት የቱርክ መንግሥት ለሚያደርገው የማይቋረጥ ወንድማዊ ድጋፍ” ምስጋና ማቅረባቸውን የዜና ወኪሉ ዘግቧል።-ሁለቱ የመከላከያ ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የመከላከያ እና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን እንዲሁም የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ከስምምነቱ መፈረም በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።-የሶማሊያው መከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃዲር ሙሐመድ ኑር በአንካራ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል የቱርክ አቻቸውን አመስግነው፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን እአአ 2011 ላይ ሶማሊያን ከጎበኙ በኋላ ይበልጥ መጠናከር ጀምሯል ብለዋል።-የሶማሊያው መከላከያ ሚኒስትር በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው ስምምነት ተከትሎ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስምምነቱ “ሽብርን ለመዋጋት እና ወታደራዊ የፋይናንስ” ትብብርን እንደሚጨርም አመልክተዋል።-ቱርክ አሁን ከሶማሊያ ጋር ውዝግብ ከገባቸው ኢትዮጵያ ጋር ከሁለት ዓመት በፊት ወታዳራዊን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ስምምነቶችን መፈራረሟ ይታወሳል።-ከአንድ ወር በፊት እራሷን ነጻ አገር አድርጋ ያወጀችው ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ የባሕር መተላለፊያ ለመስጠት እና ከኢትዮጵያ የአገርነት እውቅናን ለማግኘት የተፈራረመችው ስምምነት የሶማሊያ መንግሥትን አስቆጥቷል።-በዚህም ሳቢያ ሶማሊያ ኢትዮጵያ ከግዛት አካሌ ጋር ስምምነት በማድረግ ሉዓላዊነቴን ተጋፍታለች ስትል በመውቀስ ጉዳዩን ወደ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የወሰደች ሲሆን፣ ቱርክን ጨምሮ የተለያዩ አገራትም የሶማሊያ ሉዓላዊነት እንዲከበር ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያን ወደ ጂቡቲ የሚያደርጉት የበረሃ ጉዞን ለመመልከት አደገኛ የተባለውን የጂቡቲ-ኦቦክ የጉዞ መስመር ላይ ደርሰናል።-ኦቦክ ትንሽ የባሕር ዳርቻ ከተማ ናት።-በባሕር ዳርቻዋ ላይ ወዲያ ወዲህ ሲሉ የሚታዩት ከነዋሪዎቿ ይልቅ ስደተኞች ናቸው።-ከአገሪቱ ይፋዊ የሥራ ቋንቋ ፈረንሳይኛ እና አረብኛ ይልቅ የባሕር ዳርቻው መግባቢያ ኦሮምኛ ይመስላል።-በከተማዋ የሚገኙ ቤቶች ካስጠለሏቸው ባልተናነሰ የባሕር ዳርቻዎቹ ላይ አሸዋ ተንተርሰው፣ ካርቶን ለብሰው የሚያድሩ ስደተኞች ቁጥር ቀላል አይደለም።-እነዚህ በኦቦክ የቀይ ባሕር ዳርቻ የሚውሉ ስደተኞች የሚበሉት ባለመኖሩ ከትንሿ ከተማ ነዋሪዎች ደጃፍ እየቆረቆሩ ምጽዋት ይጠይቃሉ።-በዚህችም ከተማ ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 20ዎቹ አጋማሽ የሚቆጠሩ ከአማራ እና ከኦሮሚያ ክልሎች የተለያዩ ከተሞች የመጡ ወጣቶችን አግኝተናል።-ይህ ግን የስደት መንገድ እስኪመቻች የሚቆይበት ከተማ እንጂ ዘላቂ መሸሸጊያ አይደለም።-የስደት ጉዞ ሲሟላ፣ ደላላ አሁን በረሃውን መሻገር ይቻላል ሲል፣ በአንድ መኪና ተጭኖ ወደ ጌሄሬ መሄድ ያስፈልጋል።-አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ቢፈልጉም ለመመለስ የሚያስችላቸው ነገር የላቸውም።-ጌሄሬ ከኦቦክ አንድ ሰዓት ተኩል ያህል ትርቃለች።-ይህች ስፍራ ደላሎች ወደ የመን መሻገር የወሰኑ ስደተኞችን የሚያሰባስቡባት በረሃ ናት።-በእርግጥ ደላሎቹ ስደተኞቹን የሚያሰባስቡባቸው ሦስት ስፍራዎች እንዳሉ ሰምተናል።-ከኦቦክ አንድ ሰዓት ተኩል በመኪና ተጉዘን፣ 40 ኪሎ ሜትር ርቃ ወደ ምትገኘው ጌሄሬ በመኪና ስንፈጥን መንገዳችን ላይ የወደቀ ሸበጥ ተመለከትን።-መንገድ ያዛለው ስደተኛ፣ ጫማው የከበደው መንገደኛ የጣለው ሸበጥ ብዙ ይናገራል።-ጫማው ላይ ‘ትግራይ ዓደይ’ [ትግራይ አገሬ] የሚል ጽሑፍ ሰፍሯል።-የዚህ በመንገድ የዛለ ስደተኛ መነሻ ትግራይ ሳይሆን አይቀርም። መድረሻውን ግን ማንም አያውቅም።-በዚህ አሸዋው በሚፋጅበት በረሃ፣ ሀሩሩ በሚያነድ የስደተኞች መንገድ ላይ ሁለት እግር ጫማውን ጥሎ ወዴት ሄዶ ይሆን?-ከጂቡቲ የድንበር ጠባቂዎች ዕይታ እየተሹለከለኩ በባዶ እግር ጉዞ ምን ያህል ርቀትስ ያስጉዛል?-ይህ አጋጣሚ ለኦቦክ አስተዳዳሪ ሙሳ አደን አዲስ አይደለም። በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተጫሙት ጫማ አብሯቸው በረሃውን መዝለቅ አቅቶት ባዶ እግራቸውን በጋለ አሸዋ ላይ ሲጓዙ ተመልክተዋል።-በዚህም ዳፋ የተነሳ እግራቸው አብጦ በየበረሃው የቀሩ፣ የቻሉም ወደ ከተማዋ የሕክምና ተቋም መጥተው መታከማቸውን ያስታውሳሉ።-የቢቢሲ ጋዘጠኞችን የያዘው መኪና፣ ወደ ጌሄሬ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መኪናን በቅርብ ርቀት ተከትሎ ይከንፋል።-መኪናችን የተነሳው ከትንሿ የጂቡቲ ከተማ ኦቦክ ነው።-ኦቦክ ጂቡቲያውያን ከተማዋን የሚጠሩበት ስያሜ ቢሆንም ኢትዮጵያውያኑ ግን ሀዩ ማለትን ይመርጣሉ። ለምን አንደሆን እነርሱም አያውቁም።-ከኢትዮጵያ ድንበር ታጁራ፣ ከታጁራ ሀዩ ምቹ በሆነ አስፓልት ላይ ነው ስደተኞቹ የሚጓዙት።-ደላሎች ተራራውን አልያም የበረሃውን መንገድ ካልመረጡ በስተቀር የኢትዮጵያውያን ስደተኞች የየመን ጉዟቸውን የሚመርጡት በዚህ ቅቤ በሆነ አስፓልት ላይ በሚከንፍ የአይሱዚ ጀርባ ላይ ተጭነው ነው።-አይሱዚው ሠላሳም፣ አርባም ሰው በአንድ ጊዜ ያሳፍራል።-ሁሉም ለእግራቸው መጫሚያ ነጠላ ጫማ፣ አልያም ኮንጎ ከማድረጋቸው ውጪ በረሃውን የሚረዳቸው አለባበስ አይታይባቸውም።-ሁሉም ከኢትዮጵያ የገጠር መንደር እንደወጡ በአፋር በኩል አድርገው ወደ ጂቡቲ ማቋረጣቸውን ይናገራሉ።-የዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) የመስክ ቅኝት ቡድን ከባሕር ዳርቻው አካባቢ ወደ የመን ለመሻገር ከተሰባሰቡ ስደተኞች መካከል የተወሰኑት መታመማቸው መረጃ ስለደረሰው ነው ወደዚያው የሚያቀናው።-የድርጅቱ የሕክምና ባለሙያ ዶ/ር የሱፍ ሙሳ እንዲህ ዓይነት የቅኝት ጉዞ በተደጋጋሚ እንደሚያደርጉ በጉዟችን መነሻ ላይ ነግረውናል።-ደላሎች ስደተኞችን በዚህ የጂቡቲ በረሃ የተለያየ ስፍራዎች በማሰባሰብ ወደ የመን ያሸጋግራሉ።-የአይኦኤም የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን ጌሄሬ ሲደርስ ቁጥራቸው ወደ 70 የሚጠጋ ስደተኞች በየዛፉ ጥላ ስር እዚህም እዚያም ተኝተዋል።-በአንድ የዛፍ ጥላ ስር የታመመ ወጣትን ከብበው የሚታዩ በርካታ ወንዶች ወዳሉበት ተጠጋን።-ከቡታጅራ፣ ከስልጤ፣ ከቆቦ፣ ከትግራይ፣ ከኦሮምያ የመጡ ስደተኞችን በዚህ ከተራራ ስር ተዘርግቶ በሚገኝ ሜዳ አገኘናቸው።-ከተራራው ስር አነስተኛ ቤት እና የአይኦኤም ውሃ ታንከር ይታያል።-ስደተኞች በተኙበት አቅራቢያ አገልግሎት የሰጠ ብረት ድስት ወድቋል።-ከዚያ ውጪ ዓይን እስከ ቻለው ቢያማትሩ ጭው ያለ በረሃ ነው።-በየዛፉ ጥላ ስር የተሰባሰቡት ስደተኞች ከየአካባቢያቸው ልጆች ጋር መሆኑን ይመርጣሉ።-ከወጣት ሴቶች እና ወንዶቹ መካከል ታዳጊ ልጆችም አሉ።-ዕድሜያቸው 15 እና 16 የሆናቸው ከስልጤ እና አድዋ-ትግራይ የመጡ ታዳጊዎችን የቢቢሲ የጋዜጠኞች ቡድን ተመልክቷል።-ጌሄሬ ስንደርስ ታምመው ያገኘናቸው ስደተኞች ቁጥር አራት ነበሩ።-ስደተኞቹ ምግብ የቀመሱት ከኦቦክ ከመነሳታቸው በፊት መሆኑን ይናገራሉ።-ከተኙበት አጠገብ ፌስታል ቢታይም የሚቀመስ ምግብም ሆነ ጉሮሯቸውን የሚያርስ ውሃ አልያዙም።-ከራያ ቆቦ የመጣው እና እስከ ሰባተኛ ክፍል ድረስ እንደተማረ የሚናገረው ወጣት ከባጃጅ ሹፌርነት ይልቅ ሳዑዲ ሄጄ ሠርቼ ያልፍልኛል ብሎ ለእናት አባቱ ደጃፍ ጀርባውን ሰጥቶ ነው እዚያ የደረሰው።-ስለዚህ የስደት መስመር ማን ነገረህ ሲባል “ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ብዙ ስደተኛ ሞልቶ የለም እንዴ? በስደት የቀናቸው በደህና አሉ፤ በዚያው የቀሩም አሉ። እነርሱን እነርሱን ስናይ እኛም እንሞክረው ብለን ወጥተናል” ይላል።-እንደ እርሱ ከዋጃ አካባቢ የመጣው ሌላው ቢቢሲ ያነጋገረው ወጣትም፣ ከቤተሰቦቻቸው ጎጆ ከወጡ ሁለት ሳምንት እንዳለፋቸው ይናገራል።-ለሁለት ሳምንት ያህል ጎናቸው የረባ መኝታ፣ በቂ ምግብ እና ውሃ ሳያገኙ ጌሄሬ ደርሰዋል።-“እዚህ በየዛፉ ጥላ ስር ተረፍርፎ የምታየው ሁሉ ያደከመው ረሃብ እና ውሃ ጥም ነው” ሲል ያክላል።-በአንድ መኪና እስከ 50 የሚደርሱ ሰዎች ተጭነው መምጣታቸውን እና ከአንድ በላይ መኪና ሌሊቱን ስደተኞችን አምጥቶ እዚህ ማድረሱን ይገልጻሉ።-ምንም እንኳ ሌሊቱን ተጉዘው እዚህ መድረሳቸውን ቢናገሩም፣ እኛ በስፍራው ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ እስክንደርስ ድረስ ምግብም ሆነ ውሃ አልቀመሱም።-ይህ እስከ መቼ አንደሚቀጥል እነርሱም አያውቁም።-“ትናንት የበላን ነን። ለሊቱን ስንጓዝ አደርን። እስካሁን ምንም እህል በአፋችን አልዞረም፤ እንደምታየው አብዛኛውን በየዛፉ ስር አስተኝቶት የሚታየው ረሃብ ነው” ይላል ከዋጃ እንደመጣ የተናገረው ወጣት።-ከራያ ቆቦ የመጡት እና ከሁለት ሳምንት በፊት መነሳታቸውን የሚናገረው ወጣት ከኢትዮጵያ ሳይወጡ ሃራ እና ሎጊያ ላይ ተይዘው የቀሩ ጓደኞች አሏቸው።-ከቆቦ አካባቢ የመጡ እና ቁጥራቸው ከ13 በላይ የሆኑት ወጣቶች፣ አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው።-ከቀያቸው ከመነሳታቸው በፊት ድንበር ለመሻገር፣ ባሕር ለማቋረጥ መመካከራቸውን ይናገራሉ።-ከትግራይ አድዋ እንደመጡ የሚናገሩት እና አነስተኛ ዛፍ ጥላ ስር ተሰባበስበው ያገኘናቸው ሌሎች ወጣቶች ከአድዋ ከመውጣታቸው በፊት እንዲሁ መመካከራቸውን ነግረውናል።-ከእነዚህ ወጣቶች መካከል የተወሰኑት ሴቶቹ ፀጉራቸውን እርስ በእርስ ሲጎናጎኑ፣ ወንዶቹ ደግሞ የወደቀ ግንድ ተደግፈው ያንጎላጅጃሉ።-የእኛን መምጣት የተረዳች አንዲት ታዳጊ የራስ ምታት ኪኒን ይዘን እንደሆን ስትጠይቅ፣ ሌላኛዋ ደግሞ የሚበላ በእጃችን መኖሩን እና አለመኖሩን አረጋገጠች።-ከእነዚህ ሦስት ወንድ እና ስድስት ሴቶች መካከል፣ ሁለቱ ሴቶች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን ቢቢሲ ጠይቆ መረዳት ችሏል።-በአካባቢው ላይ ተበትነው የሚታዩት ሁሉም ስደተኞች በረሃብ እና በውሃ ጥም እንዲሁም ያለ በቂ መኝታ ሁለት ሳምንት ማሳለፋቸውን ይናገራሉ።-እነዚህ ወጣቶች ቤተሰቦቻቸውን ለመጨረሻ ጊዜ ካወሩ 10 ቀን አልፏቸዋል።-የኢትዮጵያን ድንበር ካለፉ በኋላ ስልክ ስለሌላቸው መደወል አልቻሉም።-በየዛፉ ጥላ ስር የተኙት ፍልሰተኞች ሁሉ የተገናኙት ኦቦክ ነው።-በአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን በርካታ ሰዎች በሕገወጥ መንገድ የሚሻገሩባቸው መስመሮች-ከኢትዮጵያ ሲነሱ በስልክ ያነጋገሩት ደላላ ድንበር አይሻገርም። ድንበር ተሻግረው ለሚገኙ ሌሎች በስልክ አሳልፎ ይሰጣቸዋል።-ኦቦክን አልፈው ጭው ባለው ጌሄሬ በረሃ ላይ ሲደርሱም ደላላው በአቅራቢያቸው የለም።-በራባችሁ ሰዓት ምግብ ካላቀረበ፣ ውሃ ካላቀበላችሁ፣ ለታሙት መድኃኒት ካልሰጠ ታድያ የደላላው እርዳታ ምንድን ነው? የእኛ ጥያቄ ነበር።-አንዱ ከቆቦ የመጣ ወጣት ቀልጠፍ ብሎ “ማረፊያ ቦታ ምግብ ያመጡልናል። ባሕር ላይ በማሻገር ይተባበሩናል። ርቀት ያለውን መንገድ ደግሞ በመኪና ይጭኑናል” ሲል ደላሎቹ የሚያደርጉትን ያስረዳል።-ሁሉም መዳረሻቸው ሳዑዲ አረቢያ እንደሆነ ይናገራሉ። ከደላሎች ጋር የሚገናኙት በስልክ አማካይነት ነው።-ኦቦክ ላይ ሁለት ቀን ያህል አድረዋል። እንደእነርሱ አባባል በየመንገዱ አንድም ሁለትም ቀን ማደር የተለመደ ነው።-የጂቡቲን ድንበር መቼ ነው የምታሻገሩት ሲባሉ “አላወቅንም እርሱን፤ ከእዚህ ሊያሳድሩንም ሊያውሉንም ይችላሉ” የሁሉም ምላሽ ነው።-“መቼ እንደምንሻገር አልነገሩንም፤ እግዚአብሔርን አምነን ቁጭ ብለናል” ያለችው ደግሞ ከአድዋ የመጣችው ወጣት ናት።-ቢቢሲ በስፍራው ያገኛቸውን ስደተኞች ጠይቆ መረዳት አንደቻለው የጂቡቲን ድንበር ተሻግሮ የመን ለመግባት እስከ 50 ሺህ ብር ለመክፈል የተስማሙ አሉ።-40 እና 50ሺህ ብር ብዙ አይደለም? ማን ይከፍለዋል?-ገንዘቡ የወላጆቻቸው በሬዎች ተሽጠው፣ አልያም ባሕር ማዶ እህት ወይም ወንድም ያለው እነርሱ እንዲከፍሉ በማድረግ እንደሚከፍል ያስረዳሉ።-ከትግራይ የመጡት ወጣቶች እስካሁን ድረስ ለትራንስፖርት እስከ 10 ሺህ ብር መክፈላቸውን፣ ድንበር ከተሻገሩ በኋላ ደግሞ ቀሪውን እንደሚከፍሉ ተናግረዋል።-ሴቶች የሚጠየቁት ብዙ ብር መሆኑን እና ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ አብዛኛውን ጊዜ በእግራቸው ለመጓዝ ስለሚከብዳቸው በመኪና ስለሚሻገሩ መሆኑን እና ወንዶች ግን የተወሰነውን መንገድ በእግር በመሄድ ወጪያቸውን ለመቀነስ እንደሚሞክሩ ያስረዳሉ።-በጌሄሬ የአይኦኤም የሕክምና ቡድንን የመሩት ዶ/ር የሱፍ እኤአ ከሐምሌ እስከ መስከረም 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 54 ስደተኞች ጂቡቲ ውስጥ መሞታቸውን ይናገራሉ-በየዓመቱ ወደ የመን እና ሳዑዲ አረቢያ መሻገር የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የጅቡቲ ኦቦክ መንገድን ይመርጡታል።-ይህች የባሕር ዳርቻ ከተማ የሆነችው ኦቦክ ስደተኞች አደገኛ የሆነውን የባሕር ላይ ጉዞ ለመጀመር ለአጭር ጊዜ የሚቆዩባት ከተማ ነች።-በ2022 (እአአ) ብቻ ወደ ጅቡቲ የገቡ ስደተኞች ቁጥር ከቀዳሚው ዓመት በእጥፍ የጨመረ እንደነበረ መረጃዎች ያሳያሉ።-በዚሁ ዓመት ብቻ በሚጓጓዙበት ትራስፖርት ላይ በሕመም እንዲሁም በአስከፊ የአየር ጠባይ፣ ባሕር ላይ በመስመጥ እና በግጭት የተነሳ 89 ስደተኞች መሞታቸው አልያም መጥፋታቸው ተመዝግቧል።-ከዚህ የሚልቀው ሞት እና መሰወር ደግሞ ሳይመዘገብ እንደቀረ ይታመናል።-በጌሄሬ የአይኦኤም የሕክምና ቡድንን የመሩት ዶ/ር የሱፍ እኤአ ከሐምሌ እስከ መስከረም 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 54 ስደተኞች ጅቡቲ ውስጥ መሞታቸውን መመዝገባቸውን ነግረውናል።-23 የሚሆኑት ደግሞ የገቡበት ሊታወቅ አልቻለም።-በዚሁ ጊዜ ብቻ የዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት ለ2930 ፍልሰተኞች የምግብ እና የመጠጥ ውሃ ድጋፍ ሲያደርግ፣ ለ267 ደግሞ በመንገዳቸው ላይ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት የሕክምና ድጋፍ አድርጓል።-ከታኅሣሥ እስከ ሐምሌ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ የጂቡቲ ጤና ሚኒስቴር በአገሪቱ 241 ስደተኞች መሞታቸውን፣ 258 ደግሞ በአሊ ሳቤህ፣ በአርታ፣ በዲኪል፣ ኦቦክ እና ታጁራ የሕክምና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረጉንም መረጃዎች ያሳያሉ።-የቢቢሲ የጋዜጠኞች ቡድን ጌሄሬ በደረሰበት ወቅት የዓለም አቀፉ የስደተኞች ቡድን አራት በጠና የታመሙ ስደተኞችን ሕክምና እርዳታ ሲሰጥ ተመልክቷል።-ሦስቱ የተሻለ ሕክምና ስለሚያስፈልጋቸው ወደ ኦቦክ ለመሄድ ተስማምተዋል “ዕድለኞች ነን ወደ ኦቦክ ለመሄድ መስማማታቸው” ይላሉ ዶ/ር የሱፍ ሙሳ።-አብዛኛውን ጊዜ ድንበር ላይ የደረሱ ስደተኞች ወደ ኋላ ለመመለስ ፈቃደኛ አይሆኑም።-ደላሎቹ ከጂቡቲ ወደ የመን የሚያሻግሯቸውን ብቻ ሳይሆን ከየመን ወደ ጂቡቲ የሚመለሱትንም በእዚሁ ጌሄሬ ላይ ነው የሚያስቀምጧቸው።-በቅርብ የምትገኘው ደግሞ ኦቦክ ናት - በአገር ልጅ አጠራር ሀዩ።-ችግሩ ኦቦክ ቅርብ መሆኗን ብቻ ደላሎቹ ይናገራሉ እንጂ ተመላሾቹን ከተማዋ ድረስ ይዘው አይመጡም።-ስለዚህ በበረሃ ጉዞ የደከሙ ስደተኞች በእግራቸው የጂቡቲን ደረቅ በረሃ ማቋረጥ ይጠበቅባቸዋል።-በዚያ በረሃ ያለ አንዳች መንገድ አመላካች ለሚባዝኑ ስደተኞች አቅጣጫ ለመጠቆም የሚያግዝ መፍትሄ ድርጅቱ አዘጋጅቷል።-አይኦኤም ይህንን የስደተኞች ጉዞ ለማገዝ የውሃ ታንከሮች በየመንገዱ ላይ ሰቅሏል።-እነዚህ የውሃ ታንከሮችም ለተጠማ ጉሮሮ የሚያርስ ውሃ ብቻ ሳይሆን፣ ኦቦክ በየት አቅጣጫ እንደሆነች እና ምን ያህል ኪሎሜትር እንደሚቀራቸው የሚጠቁም መረጃን ያሳያል።-“ከአገሪቱ ነዋሪ ጋር እኩል ሊሆኑ ምንም አይቀራቸውም. . . በኦቦክ ከነዋሪው በላይ የሚሆኑት ስደተኞች ናቸው”-የኦቦክ ከተማ አስተዳደሪ የሆኑት ሙሳ አደን ሚጌኔ፣ ወደዚህች ከተማ ከመምጣታቸው በፊት በአሊሳቤህ በአስተዳዳሪነት ቆይተዋል።-በእነዚህ የጅቡቲ ከተሞች በአስተዳዳሪነትም ሆነ በነዋሪነት በቆዩባቸው ዓመታት ሁሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየበረሃው በውሃ ጥም እና በረሃብ ሲሞቱ መመልከታቸውን ይናገራሉ።-ኦቦክ ከ23ሺህ ብዙም የማይዘል ነዋሪ እንዳላት አስተዳዳሪው ጠቅሰዋል።-በየወሩ ወደ ከተማዋ ድንበር አቋርጦ ለመሻገር በማሰብ የሚመጣው ስደተኛ ቁጥር ግን ከ10ሺህ በላይ እንደሚደርስ ያላቸውን ግምት ይናገራሉ።-“ከአገሪቱ ነዋሪ ጋር እኩል ሊሆኑ ምንም አልቀራቸውም. . . በኦቦክ ከነዋሪው በላይ የሚሆኑት ስደተኞች ናቸው” የሚሉት ዋና አስተዳዳሪው፣ በየቤቱ በልመና ከመሰማራታቸው ባሻገር አንዳንድ ጊዜ ግጭት ስለሚከሰት የከተማዋ ፀጥታ እና ደኅንነት አስከመታወክ ደርሷል ይላሉ።-ይህ ግን የአስተዳዳሪው ብቻ ሳይሆን የነዋሪዎቹም ስሞታ ሆኖ አግኝተነዋል።-ስደተኞች ለመንገድ ምቹ የሆነ ጫማ ስለማያደርጉ በየበረሃው ጫማቸውን ጥለው ባዶ እግራቸውን ሲጓዙ እግራቸው አብጦ፣ በውሃ ጥም ደክመው፣ በተለያዩ በሽታዎች ተጠቅተው በየቦታው ይገኛሉ።-ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ በሽታዎች የሚታመሙ ፍልሰተኞችን ወደ ከተማዋ ሕክምና ተቋም በማስገባት እንደሚያክሙም ያስረዳሉ።-ቢቢሲ በኦቦክ እንዲሁም በጌሄሬ በተዘዋወረበት ወቅት ፍልሰተኞች በኮሌራ ታመው የሕክምና ድጋፍ ሲያገኙ ተመልክቷል።-በከተማዋ ወደ የመን ለመሻገር የሚመጡ ስደተኞች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የሚናገሩት አስተዳዳሪው፣ ከየመን የሚመለሱ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም መኖራቸውን ያነሳሉ።-በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዲያስፖራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ግዛቸው ቡሹ በ2015 ዓ.ም. ብቻ 1700 የሚሆኑ ስደተኞችን ከአይኦኤም ጋር በመተባበር ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ነግረውናል።-ቢቢሲ የኦቦክ ቆይታውን አጠናቅቆ ስደተኞቹን ባሉበት ትቶ ወደ ታጁራ መንቀሳቀስ ጀምሯል።-በመንገዳችን ላይ በመኪና ተጭነው ወደ ኦቦክ የሚጓዙ ስደተኞችን በአንድ በኩል በሌላ አቅጣጫ ደግሞ ወደ ታጁራ በእግራቸው የሚጓዙ ስደተኞችን ተመልክተናል።-ወደ ታጁራ የሚሄዱ እና የተጎሳቆሉ ውሃ የሚለምኑ ስድስት ወጣቶችን ስናይ መኪናችን አቆምን።-አደም መሐመድ እና ጓደኞቹ የጂቡቲን ድንበር አቋርጠው ወደ የመን ተሻግረው ነበር።-ሳዑዲ ለመሻገር መሞከራቸውን እና ተይዘው እስር ቤት ስለሞላ በሚል ወደ የመን እንደተላኩ ይናገራሉ።-“ድንበር ላይ በርካታ ሬሳ ተራምደን ተሻግረናል” ይላል አወል ሰዒድ አህመድ፣ እርሱም እጁን በፍንጣሪ እንደተመታ በማሳየት።-የመን ላይ በልመና ስድስት ወር የቆዩት እነዚህ ወጣቶች፣ ቤተሰቦቻቸው ከብቶቻቸውን እና መሬታቸውን ሸጠው በባሕር ለመሻገር የሚያስችል ገንዘብ ስለላኩላቸው ጂቡቲ ድንበር ላይ መድረሳቸውን ይናገራሉ።-አደም እና አወል የመን ላይ በርካታ ሰዎች መመለሻ አጥተው መቀመጣቸውን ይናገራሉ።-የየመን ታጣቂዎችን አልፎ ሳዑዲ መግባት አስቸጋሪ መሆኑን የሚገልጹት ስደተኞች፣ ከየመን ለመውጣት በርካቶች ቢፈልጉም በተለያየ ምክንያት አልቻሉም ይላሉ።-የጂቡቲ መንገድ ስደተኛ መቀበል እና መሸኘት ልማዱ ነው። የቀይ ባሕር ዳርቻም ስደተኛ ማሻገር አልያም በሰፊ ሆዱ ውጦ ማስቀረት አይታክተውም።-የኦቦክ ባሕር ዳርቻዎችም ከለላ ያጣን ስደተኛ ለማሳደር ፊታቸውን አያጠቁሩም።-በርካቶች ወደ አገራቸው የሚመልሳቸው እንዳጡ በሚናገሩባት ኦቦክ፣ ሌሎች በርካቶች ደግሞ እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል በሚል ጂቡቲ ድንበር ሆነው የመንን ይናፍቃሉ።-ከየመን ለመውጣት ቀዳዳ የጠፋባቸውን በርካታ ስደተኛ የተመለከቱት እነ አደም ደግሞ፣ ወደ ኦቦክ ለአዲስ ስደት የሚተመውን ወጣት እየተመለከቱ ለእኛ ግን ከዚህ ሁሉ አገር ቤት ገብቶ የሚሆነውን መጠበቅ ይሻለናል ሲሉ የእግር ጉዟቸውን ወደ ኢትዮጵያ ቀጥለዋል።-ማን ያውቃል ከስደት የተመለሱባት ምድር በአዲስ ሲሳይ ትቀበላቸው፣ አልያም ደላላ ለዳግም ስደት ልባቸውን አሸፍቶት ወደ በረሃ ይወጡ ይሆናል።
የፎቶው ባለመብት social Media-በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በሚካሄደው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ በታንዛንያ የሚገኘው የጦሩ ዋና አዛዥ ኩምሳ ድሪባ “ፖለቲካ አያውቅም” የተባለው ሠራዊታቸው ኃያላን ባሉበት ለድርድር መቀመጡን ተናገረ።-መንግሥት 'ሸኔ' የሚለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ የሆነው ኩምሳ ድሪባ ይህንን የተናገረው ቅዳሜ ኅዳር 08/ 2016 ዓ.ም. በዙም አማካኝነት ከደጋፊዎቹ ጋር ባደረገው ወይይት ላይ ነው።-“ፖለቲካ አያውቁም፤ ልጆች ናቸው፤ አላማ የላቸውም። እርስ በርስ አይስማሙም ተብለን ስንናቅ የነበረው [የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት] ዛሬ ኃያላን ባሉበት እየተደራደርን እንገኛለን” በማለትም ተናግሯል።-ለዓመታት የዘለቀውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት እየተደረገ ያለው ሁለተኛ ዙር ንግግር በታንዛንያ የቀጠለ ሲሆን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ዋና አዛዥ ጃል መሮ ከአገር ሲወጣም ሆነ ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው።-ከአስር ቀናት በላይ የተካሄደው ውይይት መቼ እንደሚጠናቀቅም ሆነ ስለተደረሰበት ደረጃ እስካሁን ቢቢሲ በቂ መረጃ አላገኘም።።-ለመጀመሪያ ጊዜ በዳሬሰላም የሰላም ድርድሩ ላይ ተሳታፊ የሆነው ድሪባ ኩምሳ በመካሄድ ላይ ስላለው የሰላም ድርድር ማብራሪያ ባይሰጥም በዙም ባደረገው አጭር ቆይታ “ሻይ ሰዓት ላይ ነው እየተናገርኩ ያለሁት” ሲል አስታውቋል።-“አሁን እየተካሄደ ስላለው ድርድር ይህ ነው፣ ያ ነው ማለት አልፈልግም። ነገር ግን ትልቅ ፈተና እንዳለብን ማወቅ አለባችሁ” ሲልም መልዕክቱን አስተላልፏል።-“በሥራችን ገምግሙን እንጂ በወሬ ብቻ አትመሥረቱ። እኛ ሥራ ላይ ነን” ሲልም ተደምጧል።-“የኦሮሞ ሕዝብ መወዳደር ያለበት በወሬ ሳይሆን በተግባር ነው። አንገታችሁን ደፍታችሁ በርትታችሁ ሥሩ። ታይታ ጥቅም የለውም” ብሏል።-የኦሮሞ ነጻነት እንቅስቃሴን በገንዝብ እየደገፉ ላሉ የዲያስፖራው ማኅበረሰብ አባላት ባደረገው ንግግር “በገንዘብ ለምታደርጉት ድጋፍ እናመሰግናችኋለን። እኔ በበኩሌ ገንዘቡም ይቅር እያልኩ ነው። ሁሉም ሰው ባለው ሙያ እና ችሎታ እንዲደራጅ እፈልጋለሁ” ሲልም አስረድቷል።-“በሁሉም ነገር ባንስማማም እንዳልተስማማን አምነን በሰላም መኖር ራሱ እንደ አንድ ትግል ነው የማየው” ሲልም ተደምጧል።-አክሎም “እኛ መገንባት የምንፈልገው ሥርዓትን ነው። ለሚመጣው ትውልድ ምን ዓይነት ሥርዓት እና አገር እናስረክባለን የሚለው ነው የሚያሳስበን” አክሎም “እኛ እናልፋለን ነገር ግን ለመጪው ትውልድ ምን ዓይነት አሻራ ጥለን ነው የምናልፈው የሚለው ነው የሚያሳስበኝ” ብሏል የጦር አዛዡ።-የጦር አዛዡ ስለ ገንዘብ ጉዳይ ለምን እንዳነሳ ግልጽ ባይሆንም አንዳንድ መጭበርበሮች እንዳሉ ግን ጠቁሟል።-“ኦሮሞ ሌላ ፓርቲ መመሥረት” እንደሚችል የተናገረው ድሪባ ኩምሳ “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብቻ አይደለም። የራሳችሁ ፓርቲ መሥርቱ። ለዚህ ሰፊ ሕዝብ ብዙ ፓርቲዎች ቢኖሩት እኔ ተቃውሞ የለኝም። ነገር ግን በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ስም ግን መነገድ ይቁም” ሲልም ለደጋፊዎቹ ተናግሯል።-የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በዋና አዛዡ ኩምሳ ድሪባ እና በምክትሉ ገመቹ አቦዬ በሚመራ ልዑካን የታንዛንያው የሰላም ውይይት ተሳታፊ መሆኑንም ኅዳር 3/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።-ከሁለት ዓመት በፊት በሽብርተኛ ቡድንነት በመንግሥት የተፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ውስጥ የትጥቅ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ሲሆን፣ በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።-በመጀመሪያው ዙር ውይይት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካይ የነበሩት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዴዎን ጢሞቴዎስ ታንዛንያ ይገኛሉ።-ሁለቱ ልዑካን በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተዛምቶ ለበርካቶች እልቂት ለሆነው ጦርነት እልባት ለማግኘት የፌደራሉን መንግሥት ወክለው በፕሪቶሪያ ከህወሓት ጋር የተደራደሩት ልዑካን አባል መሆናቸው ይታወሳል።-በኢትዮጵያ በኩል ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና ባለሥልጣናትን ጨምሮ ሰባት ልዑካን በውይይቱ ላይ ተሳታፊ መሆናቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።-ከፌደራሉ መንግሥት ልዑካን በተጨማሪ የኦሮሚያ ክልል ሁለት ተወካዮች በውይይቱ ላይ መገኘታቸውን ቢቢሲ ሰምቷል።-የኢትዮጵያ መንግሥትን እና የትግራይ ኃይሎችን በማሸማገል ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በታንዛንያ እንደሚገኙም ተነግሯል።-በመጀመሪያው ዙር ንግግር ኬንያ እና ኖርዌይ የአሸማጋይነት ስፍራ የነበራቸው ሲሆን የአሜሪካ ዲፕሎማቶችም ድጋፍ እየሰጡ እንደነበር ቢቢሲ ለውይይቱ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ሰምቶ ነበር። በአሁኑ ውይይት አሜሪካ፣ ኬንያ፥ ኖርዌይ እና ኢጋድ የማሸማገሉን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።-የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በአምስት ከፍተኛ የጦር አዛዞዦች እና በሁለት የዲፕሎማሲ ተወካዮች በአጠቃላይ በሰባት ልዑካን ተወክሏል።-ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የጸጥታ ችግሮች እየተባባሱ ይገኘሉ።-በአሁኑ ወቅት ሁለቱ አካላት ለግጭቱ ሰላማዊ እልባት ለመስጠት እየተወያዩ ባለበት ወቅትም ጦርነት በተለያዩ ወረዳዎች ተጠናክሮ መቀጠሉን ቢቢሲ ከነዋሪዎች ሰምቷል።-በምዕራብ ሸዋ በሚገኙን ዲሬ ኢንጪኒ በተባለው አካባቢ እና በሆሮ ጉድሩ ጀማ ገናቲ በተባለ ስፍራ በባለፉት ሁለት ቀናት ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መደረጉንም ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።-የሰላም ድርድር እየተካሄደ ባለበት ወቅት ግጭቱ ለምን እንደተባባሰ ግልጽ ባይሆንም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከስድስት ወር በፊት በታንዛኒያ ራስ ገዝ አስተዳደር በሆነችው ዛንዚባር እየተደረገ በነበረው የመጀመሪያ ዙር ድርድርም ተመሳሳይ ሁኔታ ተከስቷል።-የኢትዮጵያ መንግሥት ውይይቱ ከተጀመረ ከአንድ ሳምንት በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በኩል ንግግሩ እየተካሄደ ስለመሆኑ ቢያረጋግጥም ዝርዝሩ አልተገለጸም።-የጋራ መተማመን እና መግባባት ለመፍጠር በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በመንግሥት መካከል ውይይት እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ድርድር በሁለቱ ወገኖች መካከል መግባባት ተፈጥሮ እንደነበርም መገለጹ ይታወሳል።
የፎቶው ባለመብት HoPR/FB-ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ-የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) ወክለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ።-የምክር ቤት አባሉን ረቡዕ ጥር 22/2016 ዓ.ም. በቁጥጥር ስር ያዋሏቸው አራት የታጠቁ የፀጥታ አካላት መሆናቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት የቤተሰብ አባል ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከአራቱ መካከልም ሁለቱ የፌደራል ፖሊስን የደንብ ልብስ መልበሳቸውንም አክለዋል።-የዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ቤተሰብ አባል የሆኑት ግለሰብ ረቡዕ አመሻሽ የነበረውን ክስተት ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ የፀጥታ ኃይል አባላቱ የምክር ቤት አባሉን የያዟቸው ቴዎድሮስ አደባባይ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነው።-“በር በተደጋጋሚ ተንኳኳ፤ ማንነታቸውን እንዲገልጹ ስንጠይቅ ፈቃደኛ አልነበሩም፤ በሩ ሲከፈት ደሳለኝን ወደ ሕግ ትፈለጋለህ ብለው ወሰዱት” ሲሉ አስረድተዋል።-ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ረቡዕ ማታ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ዛሬ አርብ ረፋድ ላይ በቤታቸው ውስጥ ለሁለት ሰዓታት ገደማ የቆየ ፍትሻ መካሄዱን እኒሁ የቤተሰብ አባል ገልጸዋል። ፍተሻውን ያካሄዱት ስድስት የፌደራል ፖሊስ አባላት ወረቀት፣ ፍላሽ፣ ስልክ እና ታብሌት መውሰዳቸውንም አክለዋል።-የምክር ቤት አባሉ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል የሚገኙ መሆናቸውን የገለጹት የቤተሰብ አባሉ፣ ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ግን እስካሁን የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገልጸዋል።-ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግስት ላይ ጠንካራ ትችት እና አስተያየቶችን በመስጠት ይታወቃሉ። ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በተካሄዱ የፓርላማ ስብሰባዎች ላይ ዶ/ር ደሳለኝ አልተገኙም ነበር።-የምክር ቤት አባሉ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ በነበረ የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ለጊዜያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ መጠየቃቸው ይታወሳል። ዶ/ር ደሳለኝ በዚሁ ስብሰባ ላይ የተወካዮች ምክር ቤት አባላትም ፓርላማውን እንዲበትኑ እና “ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ” ጠይቀው ነበር።-የሕዝብ እንደራሴው በዚሁ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ ተስተውሏል ላሉት “ሁለንተናዊ ምስቅልቅል፣ ቀውስ፣ ውድመት እና አገራዊ መክሸፍ” የመንግሥትን እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን “የወደቀ” አመራር ተጠያቂ አድርገዋል።-እንደ ዶ/ር ደሳለኝ ሁሉ ሌላኛው የአብን ተመራጭ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለም ከስድስት ወራት በፊት በተመሳሳይ በፀጥታ አካላት ተይዘው በእስር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።-ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የአመራር አባል የሆኑበት ፓርቲያቸው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ስለመታሰራቸው አስካሁን ያለው ነገር የለም።-የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ክርስቲያን በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለፈው ዓመት በአማራ ክልል ከተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጀ ጋር በተያያዘ መሆኑ ተገልጿል።-አቶ ክርስቲያንም በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሥልጣን እንዲለቁ በምክር ቤቱ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ጠይቀዋል።-ሁለቱም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሕገ መንግሥቱ ያለ መከሰስ መብት የተሰጣቸው ሲሆን፣ በቁጥጥር ስር መዋል ካለባቸውም ምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸውን ማንሳት ይኖርበታል።-የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን የሚመለከተው የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ፤ “ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም በወንጀልም አይከሰስም” ይላል።
በደብረ ብርሃን ከተማ ረቡዕ ከንጋት እስከ ቀኑ አጋማሽ የቆየ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን የከተማዋ ከንቲባ እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።-በከተማዋ እንቅስቃሴ መቆሙን ነዋሪዎች የተናገሩ ሲሆን በደብረ ብርሃን በሚገኙ የባለ ሶስት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች ላይም ለሁለት ቀናት የሚቆይ እገዳ ተጥሏል።-ከአዲስ አበባ ከተማ 130 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው ደብረ ብርሃን ከተማ ረቡዕ ታህሳስ 24፤ 2016 ዓ.ም “በተለያዩ አቅጣጫዎች” የተኩስ ልውውጥ መሰማት የጀመረው ከጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ ጀምሮ መሆኑን ሶስት የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል።-የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በከተማዋ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን ለቢቢሲ ያረጋገጡ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ግን ከመስጠት ተቆጥበዋል።-በከተማዋ ውስጥ የተኩስ ልውውጥ የነበረው “አልፎ አልፎ” እንደነበር የሚናገሩት ተቀዳሚ ከንቲባው፤ በአሁኑ ሰዓት ይህ ተኩስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።-አቶ በድሉ የተኩስ ልውውጡ በማን መካከል እንደተደረገ ባይገልጹም ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች የተኩስ ልውውጥ የተካሄደው በክልሉ በሚንቀሳቀሱት የፋኖ እና በአማራ ክልል የአድማ ብተና ኃይሎች መካከል እንደሆነ ተናግረዋል።-አንድ ነዋሪ በበኩላቸው ከረፋዱ አራት ሰዓት ገደማ በኋላ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማዋ መግባቱን ጠቅሰዋል።-በከተማዋ በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ህይወት ማለፉን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት ነዋሪዎች ገልጸዋል።-አንድ የከተማዋ ነዋሪ “በተለይ ኡራኤል አካባቢ እና በአንኮበር መስመር ላይ የተኩስ ልውውጦች ነበሩ። በእሱም በተባባሪ ጥይት የተወሰኑ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል” ሲሉ የደረሰውን ጉዳት ገልጸዋል።-ሌላ ነዋሪ በበኩላቸው “ሁለት ወይም ሶስት” ሰዎች ስለመሞታቸው “መረጃው እንዳላቸው” ተናግረዋል።-ይሁንና ቢቢሲ የሰዎች ህይወት ስለማለፉ ከሌላ አካል አላረጋገጠም። ቢቢሲ የሰው ህይወት ስለማለፉ ከከተማዋ ተቀዳሚ ከንቲባ እንዲሁም ከደብረ ብርሃን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።-የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎቹ እንደሚያስረዱት የተኩስ ልውውጡ የተካሄደው በተለያዩ የከተማዋ መግቢያ አካባቢዎች ላይ ነው።-በሶስት አቅጣጫዎች ተኩስ እንደነበር የሚናገሩ አንድ የከተማዋ ነዋሪ “[የተኩስ ልውውጥ የተካሄደባቸው] በከተማዋ መግቢያ የሚገኙ አካባቢዎች ናቸው። በማረሚያ ቤት በኩል ያለው አካባቢ ወደ ደሴ መውጫ ነው። [ሌላኛው ተኩስ የተሰማበት] አንሳስ ማርያም ወደ አንኮበር መውጫ ነው። ሶስተኛው ደግሞ ወደ መራቢቴ መውጫ ነው። በእነዚህ አቅጣጫዎች ተኩስ ነበር” ብለዋል።-“ማረሚያ ቤት” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆኑት እኚህ ግለሰብ፤ በዚህ አካባቢ ከረፋዱ አራት ሰዓት ጀምሮ በከባድ መሳሪያ የታገዘ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን ገልጸዋል።-ሌላ የከተማይቱ ነዋሪ በበኩላቸው ተኩስ የነበረው “ዙሪያውን” እንደሆነ በመጥቀስ ተመሳሳይ ሐሳብ አንስተዋል።-እንደ ነዋሪው ገለጻ ኡራኤል፣ አንኮበር መውጫ እንዲሁም 02፣ 03 እና 08 አካባቢዎች የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል።-ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሶሰት ነዋሪዎች እንደሚገልጹት የተኩስ ልውውጡ ከጠዋት ጀምሮ የተሰማ ቢሆንም ተኩሱ በየመሃሉ ጋብ የሚልባቸው ጊዜያት ነበሩ።-አንድ ነዋሪ፤ “[ተኩሱ] በየጊዜው የሚነሳ አይነት ነው። ግን ሲጀምር ደግሞ ምልልስ ያለው አይነት ነው። የተፋዘዘ ነገር ሳይሆን ቆየት ብሎ ይነሳል ግን በጣም 'አክቲቭ' የሆነ ድባብ አለው” ሲሉ የተኩስ ልውውጡ በተደጋጋሚ ሲነሳ መቆየቱን ጠቁመዋል።-በደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ የተሰማው ይህ የተኩስ ልውውጥ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ገደማ ጀምሮ መቆሙን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል። በከተማዋ ያለው እንቅስቃሴ ግን እስካሁን ድረስ መቆሙን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።-በከተማዋ የሚገኙ ባንኮች፣ መደብሮች እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ መሆናቸውን ሶስቱም ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።-የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የከተማዋ ኮማንድ ፖስት በባለ ሶሰት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን አስታውቋል።-ይህ የእንቅስቃሴ ገደብ እስከ ነገ ሐሙስ ታህሳስ 25፤ 2016 ድረስ የሚቆይ መሆኑን የገለጸው የከተማ አስተዳደሩ፤ “የባጃጅ አሽከርካሪዎች በተጠቀሱት ቀናቶች ከማሽከርከር ወይም ከእንቅስቃሴ እንድትቆጠቡ እንገልጻለን” ሲል አሳስቧል።
የፎቶው ባለመብት EPA-በስፔን የተገደለው አንድ ግለሰብ ሩሲያን ከድቶ ወደ ዩክሬን ኮብልሏል የተባለው ሩሲያዊ ፓይለት መሆኑ ተገለጸ።-ማስኪም ኩዝሚኖቭ ባለፈው ዓመት ነበር የጦር ሄሊኮፕተሩን እያበረረ ወደ ዩክሬን ግዛት ዘልቆ በመግባት እጁን የሰጠው።-የስፔን ፖሊስ ባለፈው ሳምንት በአሊካንቴ ግዛት አቅራቢያ ስለተገደለው ሰው ማንነት በይፋ አልገለጸም።-ሆኖም የዩክሬን ደኅንነት የተገደለው ግለሰብ ሩሲያዊው ፓይለት ኩዝሚኖቭ መሆኑን ሰኞ እለት አረጋግጧል።-የደኅንነት ቃለ አቀባይ ለዩክሬን ጋዜጣ ዩክሬይንስካ ፕራቭዳ እንደተናገሩት” [ፓይለቱ] መሞቱን አረጋግጠናል… በዩክሬን ከመቆየት ይልቅ በስፔን ለመኖር ወስኖ ሄደ” ብለዋል።-“እኛ የምናውቀው ነገር ቢኖር የቀድሞ የትዳር አጋሩን አብራው እንድትኖር ከጠራት በኋላ በጥይት ተመትቶ መገኘቱን ነው” ብለዋል።-የስፔን ባለስልጣናት በበኩላቸው ሟቹ በሐሰተኛ የማንነት ሽፋን ሳይኖር እንዳልቀረ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-የኩዝሚኖቭ አስክሬን በስፔን ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ በምትገኘው በቪላጆዮካ ከተማ በሚገኝ የመኖሪያ ስፍራ የተገኘ ሲሆን አብሮት የተገኘውም የማንነት ሰነድ ትክክለኛ ዜግነቱን ቢያረጋግጥም የሰፈረው ስም ሌላ እንደሆነ የስፔን የዜና ወኪል ኢፌ ዘግቧል።-ገዳዮቹ የተጠቀሙበት መኪና ወንጀሉ ከተፈጸመበት ስፍራ አጠገብ ተቃጥሎ መገኘቱንም የስፔን የስለላ ድርጅት ለዜና ወኪሉ ኢፌ መግለጹም ተዘግቧል።-ኩዝሚኖቭ አገሩን ሩሲያን ከድቶ ከመኮብለሉ በፊት ስለ ውሳኔው የዩክሬን የስለላ አገልግሎትን አነጋግሮ ነበር።-“ዘመቻ ሲኒቲሺያ” በሚል ስያሜ የተሰጠው የማስኮብለል ተግባርም ፓይለቱ ኤምአይ-8 የተሰኘችውን ሄሊኮፕተር ከድንበር አካባቢ እያበረረ በምስራቅ ዩክሬን በኩል ዘልቃ እንድትገባም ያለመ ነበር።-ይህም ባለፈው ዓመት ነሐሴ ተሳክቷል።-በሄሊኮፕተሯ ተሳፍረው የነበሩ እና የፓይለቱን እቅድ ያላወቁ ሌሎች ሁለት ሰዎች ሄሊኮፕተሯ ካረፈች በኋላ ወደ ድንበሩ መሮጥ ሲጀምሩ በጥይት ተገድለዋል። በወቅቱ እግሩ ላይ የተመታው ኩዝሚኖቭም ለግለሰቦቹ ግድያ ተጠያቂው የሩሲያ ጦር መሆኑን ተናግሮ ነበር።-ኩዝሚኖቭ ለዚህ ውሳኔ ያደረስው ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጦርነት በመቃወም አጋርነቱን ለመቀየር ምክንያት እንደሆነም ከጥቂት ወራት በፊት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግሯል።-በተጨማሪም ዩክሬን 500 ሺህ ዶላር፣ አዳዲስስ የማንነት እና የጉዞ ሰነዶች እና ለቤተሰቡ ጥበቃ ለማድረግ ቃል እንደገባችለትም ተናግረዋል።-በተጨማሪም የዩክሬን ባለስልጣናት ፓይለቱ በዩክሬን እንዲኖርም እድል እንደሰጡት ተናግረዋል።-“በእርግጠኝነት እዚህ [ዩክሬን] ቢኖር ጥበቃ ይደረግለት ነበር። በስፔን ውስጥ እንዳደረጉት አሳፋሪ ተግባር እዚህ ያደርጋሉ ብዬ አላምንም” ሲሉም የዩክሬን ብሔራዊ ደኅንነት እና መከላከያ ምክር ቤት ጸሐፊ ኦሌክሲ ዳኒሎቭ ተናግረዋል።-ከሩሲያ ባለስልጣናት ስለ ፓይለቱ ግድያ ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ ባይሰጥም፤ ነገር ግን ማክሰኞ ዕለት የሩሲያ የውጭ የስለላ አገልግሎት ዳይሬክተር ሰርጌይ ናሪሽኪን "ያ ከዳተኛ እና ወንጀለኛ ሞራል የሌለው አስከሬን ነበር" ሲሉም ወርፈውታል።
የፎቶው ባለመብት Reuters-ሰሜናዊ ምዕራብ አፍሪካ እና የደቡብ አውሮፓ ግዛቶች በከፋ የሙቀት ማዕበል ተመቱ።-በመጪዎቹ ቀናትም በታሪክ ከፍተኛው የተባለው የሙቀት መጠንም ሊመዘገብ እንደሚችል ተጠብቋል።-በአንዳንድ የስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ክሮሺያ እና ቱርክ የሙቀት መጠኑ ከ40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ከፍ እንደሚልም ተተንብይዋል።-በጣሊያን የሙቀት መጠኑ እስከ 48.8 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደሚደርስ ሲጠበቅ ፍሎረንስ እና ሮምን ጨምሮ በአስር የጣሊያን ከተሞች ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።-ማክሰኞ ዕለት በሰሜን ጣሊያን ነዋሪ የነበረ በ40ዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ግለሰብ በሙቀት ምክንያት ራሱን ስቶ ህይወቱ አልፏል።-የ44 ዓመቱ ግለሰብ በሚላን አቅራቢያ በምትገኘው ሎዲ ከተማ መንገድ ቀለም እየቀባም እያለ ነው በሙቀት ምክንያት ተዝለፍልፎ የወደቀው። ግለሰቡን ከወደቀበት አፋፍሰው ወደ ሆስፒታል ቢወስዱትም ህይወቱ ሊተርፍ አልቻለም።-“ልንቆጣጠረው የማንችለው የሙቀት ማዕበል ገጥሞናል” በማለት ጣሊያናዊው ፖለቲከኛ ኒኮላ ፍራቶያኒ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።-“ከፍተኛ ሙቀት በሚያጋጥሙ ሰዓታት ውስጥ ጠቃሚ የሚባሉ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ዛሬ በሎዲ ውስጥ እንደተፈጸመው አሳዛኝ ሁኔታን ለመከላከል ሊረዳ ይችላል” ሲሉም አክለዋል።-በርካታ አገሪቷን እየጎበኙ ያሉ ቱሪስቶች በሙቀት ማዕበሉ ምክንያት ተዝለፍልፈው ወድቀዋል።-የጣሊያን ሜትሮሎጂ ማህበር ጣሊያናዊው ጸሃፊ ዳንቴ አሊጌሪ ኢንፌርኖ በተሰኘው ግጥም ውስጥ ሶስት ጭንቅላት ያለው ጭራቅ- ሴርቤሩስ ሲሉም የሙቀት ማዕበሉን ሰይመውታል።-የሙቀት ማዕበሉ በሚቀጥሉት ቀናትም በጣም የከፉ ሁኔታዎችን ሊያስከትል እንደሚችልም ይጠበቃል።-የሜትሮሎጂ ጽህፈት ቤት አርብ ላይ የሙቀት መጠኑ ከፍተኛ እንደሚሆን ሲተነብይ የቢቢሲ የአየር ጸባይ ትንበያ በኩሉ ደቡባዊ የአውሮፓ ግዛቶች ዝቅተኛው የተባለው እስከ 40ዎቹ አጋማሽ እንዲሁም ከፍ ያለ ሙቀት ያጋጥማል ብሏል።
ዓለም ከተማ የመርሐቤቴ ወረዳ ዋና ከተማ ነች-በአማራ ክልል መርሐቤቴ ወረዳ ከአንድ ትምህርት ቤት አቅራቢያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ቢያንስ አራት ሰዎች እንደቆሰሉ ነዋሪዎች እና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ለቢቢሲ ገለጹ።-በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በምትገኘው መርሐቤቴ ወረዳ ዓለም ከተማ የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት አርብ ጥር 3/2016 ዓ.ም. መሆኑን ሦስት ነዋሪዎች እና የትምህርት ቤቱ አስረድተዋል።-ከቀኑ ሰባት ሰዓት ገደማ የተፈጸመው ጥቃት ያረፈው አርበኞች አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መግቢያ አካባቢ መሆኑ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አሻግሬ አበበ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በተፈጸመው በዚህ የድሮን ጥቃት የተደናገጡት የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ባደረባቸው ስጋት ምክንያት በዛሬው ዕለት ሰኞ ወደ ትምህርት ቤት አለመመለሳቸውን ርዕሰ መምህሩ ጨምረው አረጋግጠዋል።-ከዘጠኝ እስከ 12ተኛ ክፍል የሚያስተምረው ትምህርት ቤቱ በዚህ ዓመት ከ2600 በላይ ተማሪዎችን እንደተቀበለ ርዕሰ መምህሩ ገልጸዋል።-ርዕሰ መምህሩ እና ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚያስረዱት በትምህርት ቤቱ አቅራቢያ ጥቃቱ የተፈጸመው በአካባቢው በሚገኘው “ካርል” የተባለ መናፈሻ ውስጥ የፋኖ ታጣቂዎች ይገኛሉ በሚል ነው።-ከትምህርት ቤቱ በ20 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ መናፈሻ የፋኖ ኃይሎች “ለሬሽን እና ሎጂስቲክስ አቅርቦት የሚጠቀሙበት” መሆኑን አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር ለቢቢሲ ገልጸዋል። መምህሩ፤ “[በትምህርት ቤቱ እና መናፈሻው] መሃል ያለው አንድ አገር አቋራጭ መንገድ ነው። [ጥቃት የተፈጸመው] እነሱ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ በሚል እሳቤ ነው። እርምጃው ወደ ተማሪውም ጭምር ያነጣጠረ ነው” ብለዋል።-እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ በዚህ የድሮን ጥቃት ሁለት የፋኖ አባላት የተገደሉ ሲሆን፣ በመንገድ ላይ የነበሩ ቢያንስ አራት ንጹሃንም ጉዳት ደርሶባቸዋል። ጥቃቱ በተፈጸመበት ሰዓት የሁለተኛ ፈረቃ ተማሪዎች በትምህርት ላይ እንደነበሩ የገለጹት ርዕሰ መምህሩ አቶ አሻግሬ፤ ተማሪዎች ላይ የተፈጠረው ድንጋጤ “ከልክ በላይ” የሚባል አይነት መሆኑን ገልጸዋል።-ርዕሰ መምህሩ፤ “አንዳንድ ተማሪዎች በአጥር ዘለው ሊወጡ ሲሉ እጃቸውን ቆርቆሮ የቆረጣቸው አሉ። [ጥቃቱ] የነበረው በፊት ለፊት በኩል ስለነበር [እና ጥቃቱ] ይደገማል ተብሎ ስለታሰበ በየአጥሩ እንዲወጡ ነው የተደረገው” ሲሉ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ ቅጥር እንዲወጡ የተደረገበትን መንገድ አስረድተዋል።-አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር በበኩላቸው፤ “የድሮን ጥቃቱ ሲፈጸም አካባቢው በጭስ እና በፍንጥርጣሪ በመታፈኑ ተማሪዎች በተፈጸመባቸው ረብሻ የተወሰኑ ተማሪዎች መስታወት በመስበር በመስኮት ለመውጣት [ሲሞክሩ] መጠነኛ የመቁሰል፣ የመውደቅ፣ የመሰበር አደጋ ደርሶባቸዋል” ሲሉ ተመሳሳይ ሃሳብ አንስተዋል።-በሳምንቱ የመጨረሻ የትምህርት ቀን የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት ተከትሎ የተቋረጠው ትምህርት በዛሬው ዕለት አለመጀመሩን ርዕሰ መምህሩ እና ሌላ መምህር አስረድተዋል። ርዕሰ መምህሩ አቶ አሻግሬ፤ “ዛሬ [ወደ ትምህርት ቤት] ገብቼ ነበር። ነገር ግን አንድም ተማሪ ሳይመጣ ቀረ። እኔም ወጣሁ” በማለት ተማሪዎች ላይ ስጋት መፈጠሩን አመልክዋል።-“ትምህርት ቤት አካባቢ እንደዚህ ጥቃት መፈጸሙ ትምህርት እንዲቋረጥ የሚያደርግ ነው። አሁን የትኛው ተማሪ መጥቶልን እንደምናስተምር አናውቅም” ያሉት አቶ አሻግሬ፤ ጥቃቱ የመማር ማስተማር ሥራው ላይ ተጽእኖ ያደርሳል የሚል ስጋታቸውን ገልጸዋል።-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ቢሮ በኅዳር ወር ላይ ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል ፋኖ ታታቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች የሚያደርጉትን ውጊያ ተከትሎ በሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን እየተገደሉ መሆኑን አስታውቆ ነበር።-በክልሉ በሰሜን ሸዋ ዋደራ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህር ቤት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሦስት መምህራንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች እንደተገደሉ በመግለጫው ላይ ተጠቅሶ ነበር።-የፋኖ ታጣቂዎች በሚንቀሳቀሱበት በመርሐቤቴ ወረዳ ዓለም ከተማም የድሮን ጥቃት ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በኅዳር ወር መጨረሻ ላይ “ገምሹ” በሚባል ካምፕ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሁለት ሰዎች እንደተገደሉ አንድ የከተማዋ ነዋሪ አስታውሰዋል። በዚህ ጥቃት “በርካታ ሰዎች” ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚናገሩት ነዋሪው፤ በወቅቱ ጉዳት የደሰረባቸው “ንጹሃን” እንደነበሩ ጠቅሰዋል።-ቢቢሲ አርብ ዕለት በዓለም ከተማ ስለተፈጸመው ጥቃት ከመከላከያ ሠራዊት እና ከክልሉ ባለሥልጣናት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ይሁንና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ታኅሣሥ ወር ላይ ለመንግሥት ቅርበት ባለው ፋና ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ መጠይቅ በእነዚህ ጥቃቶች ንጹሃን እየተገደሉ ነው መባሉን አስተባብለዋል።-የመከላከያ ሠራዊት የድሮን ጥቃት የሚፈጽመው የፋኖ ታጣቂዎች “ስብስብ ዒላማ” ላይ መሆኑን የተናገሩት ኤታማዦር ሹም ብርሃኑ፤ “ሕዝብ ላይ ድሮን አይጣልም፤ አይተኮስም። መንደር ላይ እንኳ አይተኮስም። የጠላት ስብስብ ሲገኝ ግን ይተኮሳል” ብለው ነበር።-በክልሉ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተለያዩ አካባቢዎች ለወራት እየተካሄደ ባለው ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸው እና ያለ ፍርድ ግድያን ጨምሮ ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና ሌሎችም ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወቃል።-መንግሥት የክልል ልዩ ኃይልን በማፍረስ መልሶ ለማደራጀት እና ሌሎች ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት መወሰኑን ተከትሎ ካለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ጀምሮ በአማራ ክልል የተከሰተው ውጥረት ተባብሶ ሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ ወደለየለት ግጭት መግባቱ ይታወሳል።-በተለያዩ ጊዜያት መንግሥት የክልሉ አካባቢዎች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሱ መሆናቸውን ቢገልጽም፣ አሁንም በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ውጊያ እንዳለ ይሰማል።-የተለያዩ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ እና በውይይት ችግራቸውን እንዲፈቱ ጥሪ እያቀረቡ ቢሆንም፣ እስካሁን የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸው የሚጠቁሙ መረጃዎች የሉም።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ የአሸናፊነት ግምት የተሰጣቸው አገራት ብዙ ትኩረት ባልተሰጣቸው አገራት መሸነፋቸውን ቀጥለዋል።-ትልቅ የዋንጫ ግምት የተሰጣት ሞሮኮ በደቡብ አፍሪካ 2 ለ 0 ተሸንፋ ከውድድሩ ተሰናብታለች።-በትናንት ምሽቱ ጨዋታ ባፋና ባፋናዎች በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው 2 ጎሎችን ሞሮኮን አሸንፈው ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።-ከዚህ ጨዋታ በፊት ቀድሞ በተካሄደው ጨዋታ ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ ተገኝተው የነበረ ሲሆን ማሊ ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።-በመጀመሪያው አጋማሽ የቡርኪና ፋሶው ተከላካይ በራሱ ግብ ላይ ጎል አስቆጥሮ ማሊ 1ለ0 እየመራች እረፍት ወጥተዋል።-ከመልበሻ ክፍል መልስ አጥቅታ ስትጫወት የነበረችው ማሊ በሲናዮኮ አማካይነት ሁለተኛ ግብ ማስቆጠር ችላለች።-በማሊ የግብ ክልል ውስጥ ኳስ በእጅ በመነካቱ ቡርኪና ፋሶ ፍፁም ቅጣት ምት አግኝታ ትራኦሬ ወደ ጎል ቀይሮት ቡርኪና ፋሶ ወደ ጨዋታው ተመልሳ ነበር። ይሁን እንጂ ተጨማሪ ጎል ማስቆጠር ባለመቻላቸው ጨዋታው 2ለ1 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።-ማሊ በሩብ ፍፃሜው የፊታችን ቅዳሜ ከአስተናጋጇ አይቮሪ ኮስት ጋር ትገናኛለች።-ሳይጠበቅ ሞሮኮን 2 ለ 0 ያሸነፈችው ደቡብ አፍሪካ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ ከኬፕ ቨርድ ጋር የምትገናኝ ይሆናል።-ትናንት በነበረው ጨዋታ ሁሉም ቡድኖች ከእረፍት በፊት ግብ ማስቆጠር አልቻሉም ነበር።-አጥቂው ማክጎፓ በ57 ደቂቃ ደቡብ አፍሪካን ቀዳሚ ማድረግ ችሎ ነበር። ጨዋታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩ ሞሮኮ ወደ ጨዋታው ልትመለስ የምትችልበትን ወርቃማ ዕድል ሳትጠቀምበት ቀርታለች።-ኳስ በእጅ መነካቱን ተከትሎ ሞሮኮ ፍጹም ቅጣት ምት ብታገኝም ተከላካዩ አሽራፍ ሃኪሚ ኳሷን ከግቡ አግዳሚ ጋር አጋጭቶ ዕድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።-90ኛው ዲቀቃ የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቹ አምራባት በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ደግሞ የሞሮኮን ፈተና የበለጠ ያወሳሰበ ሆኖ ነበር።-በጨዋታ ማብቂያው ላይ ቶቦሆ ሞኮኤና ከቅጣት ምት ድንቅ ጎል አስቆጥሮ የደቡብ አፍሪካን ድል አረጋግጧል።-በቀሪዎቹ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ናይጄሪያ ከአንጎላ ዓርብ ምሽት የሚገናኙ ሲሆን፤ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደግሞ ከጊኒ ጋር በተመሳሳይ ዓርብ ምሽት የሚጫወቱ ይሆናል።
የፎቶው ባለመብት AFP-የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከወራት በፊት አገራቸው የአፍሪካ አገራት ዜጎች ቪዛ ሳያስፈልጋቸው ኬንያን መጎብኘት ይችላሉ በማለት ይፋ ካደረጉ በኋላ ብዙዎች አወድሰዋቸው ነበር።-የፕሬዝዳንቱ ‘ቪዛ አያስፈልግም’ አዋጅ ግን ‘ለቪዛ ክፍያ አንጠይቅም’ ማለት እንዳልሆነ አፍሪካውያን ተጓዦች የገባቸው ዘግይቶ ነው።-ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ የአፍሪካ አገራት ዜጎች ኬንያ ሲደርሱ ፓስፖርታቸው ላይ ምልክት ተደርጎላቸው ያለ ምንም ክፍያ እና ቪዛ በአገሪቱ እስከ ሦስት ወራት መቆየት ይችሉ ነበር።-በዚህ አሠራር ሲጠቀሙ የቆዩት ኢትዮጵያውያን እና ሌሎችም መጉላለት ሳይገጥማቸው ለሥራ ወይም ለጉብኝት ወደ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ሲገቡ እና ሲወጡ ቆይተዋል።-ፕሬዝዳንት ሩቶ ኬንያ ‘ከቪዛ ነጻ’ ትሆናለች ብለው ይፋ ያደረጉት አዋጅ ተፈጻሚ መሆን ሲጀምር ግን በርካቶች ለወጪ እና ለእንግልት እየተዳረጉ ነው።-በዚህ አዋጅ ቪዛ ቀርቷል ቢባልም ተጓዦች ኤሌክትሮኒክ የጉዞ ፍቃድ (ኤሌክትሮኒክ ትራቭል ኦተራዜሽኝ - ኢቲኤ) ከጉዟቸው ሦስት ቀናት ቀድመው ከኬንያ መንግሥት ባለሥልጣናት ማግኘት ይኖርባቸዋል።-ይህ አዲሱ አሰራር ቀድሞ ያልነበረ አዲስ ክፍያ ከመጠየቁም በላይ ተጓዦች ፎርም እንዲሞሉ ይገደዳሉ።-በተለይ ደግሞ የጉዞ ፍቃዱን ለማግኘት የሚጠየቀውን 30 ዶላር ለመክፍል ዓለም አቀፍ ክፍያ መፈጸሚያ ካርድ ማግኘት ከባድ በሆነባቸው እንደ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ያሉ አገራት ዜጎች ደግሞ ፍቃዱን የማግኘት የበለጠ ውስብስብ ያደርገዋል።-አዲኦ የተባለ በጀርመን ነዋሪ የሆነ የዚምባብዌ ዜጋ ወደ ኬንያ ለመብረር ሻንጣው ሸክፎ ከአየር ማረፊያ ሲደርስ መጉላላት ሊገጥመው እንደሚችል ፈጽሞ አልጠረጠረም።-አውሮፕላን ከመሳፈሩ በፊት ሻንጣ መላኪያ መስኮት ጋር ሲደርስ ከዚህ በፊት ባልገጠመው ሁኔታ ኬንያ ለመግባት ፍቃድ እንዳለው ጥያቄ ቀረበለት።-“ለጉዞ ፍቃድ አያስፈልገኝም ብዬ ተከራክሬ ነበር” ሲል የ33 ዓመቱ ተጓዥ ይናገራል።-እርሱ እንዳለው ከጥቂት ሳምንታት በፊት ዚምባብዌን ጨምሮ የ40 የአፍሪካ አገራት ዜጎች ቪዛ ሳያስፈልጋቸው ኬንያ መግባት ይችሉ ነበር።-ካልንበት የአውሮፓውያኑ 2024 ጀምሮ ኬንያ ከቪዛ ነጻ ትሆናለች ሲባል፣ የተረዳሁት ወደ አገሪቷ የሚደረገው ጉዞ ቀላል እንደሚሆን ነበር የዚምባብዌ ዜጋው አዲኦ።-“የጉዞ ፍቃዱን ዝርዝር ስመለከት ከቪዛ ነጻ የተባለው ከክፍያ ነጻ ማለት እንዳልሆነ ተረዳሁ” ይላል።-አዲኦ በጉዞ ወኪሎች ድጋፍ 160 ዶላር ወጪ አውጥቶ የሚጠበቅበትን ለሟሟላት ቢጥርም የጉዞ ፍቃዱ እስኪደርሰው ሰዓታት በማለፋቸው በረራው አምልጦታል።-በኬንያ አዲሱ የጉዞ ሕግ መሠረት ተጓዦች ወደ ኬንያ ከመጓዛቸው በፊት ኢቲኤ ማግኘት ይኖርባቸዋል።-ኢቲኤ 30 ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን አንድ ተጓዥ በኬንያ ለ90 ቀናት እንዲቆይ ይፈቅዳል።-ይህንን ፈቃድ ለማግኘት ተጓዦች የጉዞ ትኬት ዝርዝር እና በኬንያ የሚቆይበት አድራሻን ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል።-“ለእንደ እኔ ዓይነት ሰዎች አዲሱ ሕግ ነገሮችን ቀላል አያደርግም። ከዚህ ቀደም ወደ ኬንያ ለመምጣት ምንም ነገር አይጠበቅብንም ነበር” ይላል አዲኦ።-ኬንያዊው የኢሚግሬሽን ጠበቃ የሆኑት ዴቪስ ኛጋህ የኬንያ መንግሥት ያስተዋወቀው ኢቲኤ “በስም እንጂ ከቪዛ በምንም አይለየም” ይላሉ።-“ከሕግ አንጻር በኢቲኤ እና በቪዛ መካከል ምንም ልዩነት የለም። ልዩነቱ በፓስፖርት ላይ የሚለጠፈው የቪዛ ፈቃድ መቅረቱ ብቻ ነው” ይላሉ።-ምናልባት የኬንያ መንግሥት ይህን አዲስ ሕግ ያስተዋወቀው ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት ሊሆን ይችላል።-አሁን ላይ የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ከሚባሉት ዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ ውጪ ያለ የየትኛው አገር ጎብኚ ወደ አገሪቱ በገባ ቁጥር 30 ዶላር ይከፍላል።-ከዚህ ቀደም የነበረው አሠራር የተወሰኑ አገራት ዜጎች 50 ዶላር ከፍለው ለበርካታ ጊዜያት እንዲገቡ እና እንዲወጡ የሚያስችል ፍቃድ ያስገኝላቸዋል።-የኬንያ መንግሥት ገቢ ለመጨመር ያረቀቀው ሕግ ግን ጎብኚዎችን በማሸሽ ዋጋ ሊያስከፍለው እንደሚችል ተንታኞች ስጋታቸውን ይገልጻሉ።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-ለምሳሌ ሩዋንዳ ሁሉም የአፍሪካ አገራት ዜጎች ያለ ምንም ክፍያ ካለ ቪዛ ወደ አገሯ እንዲገቡ ማድረጓ የጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምርላት ማድረጉን አስታውቃ ነበር።-በሩዋንዳ ለአፍሪካውያን ካለ ቪዛ ወደ አገሯ እንዲገቡ ከተፈቀደ በኋላ የአፍሪካውያን ጎብኚዎች ቁጥር በ14 በመቶ መጨመሩን ትገልጻለች።-የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አንቶኒ ማብያንጌ “ጎብኚዎችን እና ንግድን ለማበረታታት የተቀላጠፈ የጉዞ አማራጭ እጅግ ወሳኝ ናቸው” ይላሉ።-ባለሙያው ተጓዦች የጉዞ ፍቃድ እንዲያገኙ መጠየቃቸው የኬንያን ምጣኔ ሃብት በአጭር እና በመካከለኛ ጊዜ ውስጥ ሊጎዳው እንደሚችል ይገምታሉ።-ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ ከፍተኛ የኬንያ መንግሥት ባለሥልጣን ለጉዞ ፍቃዱ ክፍያ የሚጠየቀው የአገሪቱን ደኅንነት ለማረጋገጥ ከሚወሰዱ እርምጃዎች መካከል አንዱ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-የኬንያ መንግሥት ፕሬስ ሴክሬታሪ የሆኑት ሳሊም ሳዋሌህ “ሽብርተኛነት በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ስጋት ነው። ስለዚህ ወደ ኬንያ የሚመጣው በሙሉ ለአገሪቱ ደኅንነት ስጋት አለመሆኑን የምናረጋግጥበት መንገድ ያስፈልጋል” ብለዋል።-ኃላፊ ጨምረውም አዲሱ ሕግ እየተለመደ ሲመጣ ለተጓዦች ቀላል እንደሚሆን እና በረዥም ጊዜ የጎብኚዎች ቁጥርን ከፍ እንደሚያደርግ የኬንያ መንግሥት ትንበያዎች ማሳየታቸውን ገልጸዋል።-የኬንያ መንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት አይዛክ ማኢጉአ በበኩላቸው ምንም እንኳ ኢቲኤ “ጊዜያዊ የሆኑ ችግሮች” ቢያጋጥሙት በሂደት ነገሮች የተቀላጠፉ ይሆናሉ ይላሉ።-ባለፉት 30 ቀናት ከ60 ሺህ በላይ የጉዞ ፍቃዶች መሰጠታቸውን የገለጹት ቃል አቀባዩ፤ የኬንያ መንግሥት የዘረጋው ሥርዓት በቀን የ5000 ሰዎች ጥያቄን የማስተናገድ አቅም እንዳለው ተናግረዋል።-በአፍሪካውያን አገራት የሚተገበሩ ጠንካራ የቪዛ መስፈርቶች አፍሪካውያን የአፍሪካ አገራትን እንዳይጎበኙ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው።-ሊቢያ፣ ሱዳን፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ግብፅ ጥብቅ የቪዛ መስፈርቶች ያሏቸው አገራት ናቸው።
የፎቶው ባለመብት AFP-አንድ የ46 ዓመት ጎልማሳ ያለ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት አውሮፕላን ተሳፍሮ ከዴንማርክ ተነስቶ በአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ ከተማ ከደረሰ በኋላ በቁጥጥር ሥር ዋለ።-ሰረጌይ ኦቺጋቫ የተባለው ግለሰብ ያለ ፍቃድ እና በቂ የጉዞ ሰነድ ሳይዝ ድንበር በመሻገሩ በአሜሪካ በቁጥጥር ሥር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል።-ግለሰቡ በሎስ አንጀለስ በቁጥጥር ሥር ሲውል የሩሲያ እና የእስራኤል መታወቂያዎች ይዞ የተገኘ ሲሆን እስካሁን ግን ዜግነቱን መለየት አልታቻለም።-ወንጀል መርማሪዎች ግለሰቡ ከዴንማር እስከ ሎስ አንጀለስ 12 ሰዓታት በሚወስደው ጉዞ ላይ እራሱን ለመደበቅ ምንም ዓይነት ጥረት አለማድረጉን ይለቁንም ከሌሎች ተሳፋሪዎች ጋር ለማውራት ጥረት ሲያደርግ ነበር ብለዋል።-ኦቺጋቫ ጥቅምት 24/2016 ዓ.ም. ሎስ አንጀለስ ከተማ ደርሶ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ፓስፖርቱን አውሮፕላን ውስጥ መርሳቱን ለመርማሪዎቹ ተናግሮ ነበር። ይሁን እንጂ ምንም ዓይነት የጉዞ ሰነድ ተሳፍሮበት በነበረው አውሮፕላን ላይ አልተገኘም።-ከዚህ በተጨማሪም መርማሪዎች ወደ አሜሪካ ለሚደረግ ጉዞ ግለሰቡ ምንም ዓይነት የአየር ትኬት አለመቁረጡን እንዲሁም ከየትኛው አገር ሆኖ የአሜሪካ ቪዛ አለመጠየቁን አረጋግጠዋል።-ኦቺጋቫ ለመርማሪዎች በሰጠው ቃል “የአውሮፕላን ቲኬት ሳይኖረኝ አይቀርም . . . እርግጠኛ ግን አይደለሁም” ስለማለቱ የከተፈተበት የወንጀል ክስ ሰነድ ያሳያል።-ግለሰቡ ለቀረበበት ክስ ጥፋተኛ አይደለሁም ያለ ሲሆን ከሁለት ሳምንታት በኋላ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።-መርማሪዎች ግሰለቡ ምንም ዓይነት የጉዞ ሰነድ ሳይዝ እንዴት አውሮፕላን መሳፈር ቻለ የሚለውን ለመመለስ እየመረመሩ ይገኛሉ።-ኦቺጋቫ ግን ከዴንማርክ ተስቶ ወደ አሜሪካ እየበረረ በነበረው ስካንዲኔቪያን አየር መንገድ በረራ ላይ እንዴት እንደተሳፈረ እንደማያስታውስ ተናግሮ። ''ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንቅልፍ አልተኛሁም፣ በዴንማርክ አየር ማረፊያ የደኅንነት መቆጣጠሪያዎችን እንዴት እንዳለፍኩም አላስታውስም'' ብሏል።-ይህ የሩሲያ እና የእስራኤል መታወቂያዎች ይዞ የተገኘው ግለሰብ ቀድሞውኑ እንዴት ዴንማርክ ሊገባ እንደቻለ ምርመራ እየተደረገ ነው።-ኦቺጋቫ ለአሜሪካ መርማሪዎች በሰጠው ቃል “ከረዥም ዓመታት በፊት” በሩሲያ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ሆኜ ሠርቻለሁ ብሏል።-ስካንዲኔቪያን አየር መንገድ ሠራተኞች ያልተመዘገበ ትርፍ ተጓዥ ይዘው መብረራቸውን ያወቁት ከመርማሪዎች ጥያቄዎች ሲቀርቡላቸው ነበር። የበረራ አስተናጋቾች ኦቺጋቫ በበረራው ወቅት በተደጋጋሚ ወንበር እየቀየር ሲቀመጥ እንደነበረ ተናግረዋል።-የበረራ አስተናጋቾች ለተጓዦች ምግብ ሲያቀርቡም ኦቺጋቫ ተጨማሪ ምግብ እየጠየቀ ሲመገብ እንደነበረ የተናገሩ ሲሆን አንድ የበረራ አስተናጋጅ ኦቺጋቫ ሌሎች ተሳፋሪዎችን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም ተሳፋሪዎች ግን መልስ አልሰጡት ስትል ተናግራለች።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ቲቢ ጆሽዋ-ዩቲዩብ፤ የጥላቻ ንግግር ደንብ ጥሷል በማለት በቅርቡ ፈጽሞታል በተባለው ከባድ በደል ክስ የቀረበበትን የሟቹ ናይጄሪያዊ ሰባኪ የቲቢ ጆሽዋ ቴሌቪዥን ታዋቂ የዩቲዩብ ቻናልን ዘጋ።-ይህ የዩቲዩብ ውሳኔ ይፋ የሆነው ቢቢሲ እና ኦፕንዴሞክራሲ ሟቹ ሰባኪ ቲቢ ጆሽዋ መጠነ ሰፊ የወሲብ ጥቃቶችን እና አካላዊ ሰቆቃዎችን መፈጸሙን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ያየዘ የምርመራ ዘገባ ካቀረቡ ከሳምንታት በኋላ ነው።-ቲቢ ጆሽዋ ከአካባቢ ፓስተርነት ወደ ዓለም አቀፍ ታዋቂነት እንዲሸጋገር ‘ኢማኑኤል ቲቪ’ የተባለው የራሱ የቴሌቪዥን ስርጭት ቁልፍ ሚና መጫወቱ ይነገራል።-ታዋቂው ናጄሪያዊ ሰባኪ ከሦስት ዓመት በፊት የሞተ ሲሆን፣ ሲናጎግ ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽንስ የተባለው ቤተክርስቲያኑ በአሁኑ ጊዜ በባለቤቱ ኤቭሊን ጆሽዋ እየተመራ ይገኛል።-ቤተክርስቲያኑ እስካሁን የዩቲዩብ ቻናሉ ስለመዘጋቱ የሰጠው አስተያየት የለም፣ በተጨማሪም ከዚህ በፊት በቲቢ ጆሽዋ ላይ የቀረቡት ክሶች “መሰረተቢስ” ናቸው ማለቱ ይታወቃል።-አሁን እንዲዘጋ የተወሰነበት የኢማኑኤል ቲቪ ዩቲዩብ ቻናል ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተከታዮች እና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዕይታን ያገኘ ነው።-ይህ ቻናል የዩቲዩብን የማኅበረሰብ መመሪያዎችን ጥሷል በሚል የአሁኑን ጨምሮ ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሁለተኛ ጊዜ ነው ዕግድ የተጣለበት።-ከቢቢሲ ጋር በመሆን ኦፕንዴሞክራሲ ባካሄደው ምርመራ ኢማኑኤል ቲቪ በበይነ መረብ በኩል ያሉትን ይዘቶች የፈተሸ ሲሆን፣ ዩቲዩብ ላይ ቢያንስ 50 “አዋራጅ/ስቃይ” የሚታይባቸው ቪዲዮዎችን አግኝተዋል።-የምርመራ ቡድኑ እነዚህን ቪዲዮዎች በተመለከተ ለዩቲዩብ በማሳወቃቸው ቻናሉ ከሰኞ ጥር 20/2016 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲታገድ ተደርጓል።-በጉግል ባለቤትነት ስር የሚገኘው የቪዲዮ ማጋሪያ መድረክ የሆነው ዩቲዩብ ለቢቢሲ በሰጠው አስተያየት፣ ኢማኑኤል ቲቪ “የጥላቻ ንግግር ደንቦችን . . . በመጣሱ እንዲዘጋ ተደርጓል” ብሏል።-ቲቢ ጆሽዋ “በፈውስ” አገልግሎቱ ዝናን ያገኘ ሲሆን፣ የአካል ጉዳት ያለባቸው እና በጽኑ የታመሙ ሰዎች ተፈወሱባቸዋል የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፈውስ አገልግሎቶች በፊልም ተቀርጸዋል። ነገር ግን በርካታ የቀድሞ የቤተክርስቲያኗ አባላት ሐሰት መሆናቸውን አጋልጠዋል።-በኦፕንዴሞክራሲ በኩል የቀረበ ዘገባ በኢማኑኤል ቲቪ ምስሎች አማካይነት የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በሰንሰለት ታስረው፣ የሕክምና መረጃዎችን ማዛባት እና በቲቢ ጆሽዋ ወሲባዊ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው በተናገሩ ሴቶች ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደሚካሄድ ተገልጿል።-ቲቢ ጆሽዋ ፈጽሞታል የተባለው በደል ይፋ ከሆነ በኋላ ዲኤስቲቪ እና ጎቲቪ የተባሉ ተወዳጅ ቻናሎችን የሚያቀርበው ታዋቂው የደቡብ አፍሪካ የሳተላይት ቴሌቪዥን አግልግሎት ሰጪ ኢማኑኤል ቲቪን ከሚያሰራጫቸው ቴሊቪዥን ጣቢያዎች ዝርዝር ውስጥ አስወጥቶታል።-ኢማኑኤል ቲቪ ቻናል በመላው ዓለም በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች በመታየት ለበርካታ ዓመታት ስኬታማ የክርስቲያን ቴሌቪዥን ጣቢያ በመሆን ቆይቷል።-ቢቢሲ በቲቢ ጆሽዋ ላይ ለሁለት ዓመታት ያካሄደውን የምርመራ ዘገባ ይፋ ማድጉን ተከትሎ፣ በዘገባው ላይ ስለሚያውቁት ነገር ምስክርነት በሰጡ ግለሰቦች ላይ ከቤተክርስቲያኗ እና ከኢማኑኤል ቲቪ ጋር ግንኙነት ባላቸው አካውንቶች አማካይነት ዛቻ እና ማስፈራሪያ ተሰንዝሮባቸዋል።-ይህም በኦፕንዴሞክራሲ አማካይነት ለዩቲዩብ ሪፖርት ቢደረግም እስካሁን እንዲነሱ አልተደረገም።-ዩቲዩብ እና ሌሎችም የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ከሚከተሉት የደኅንነት ፖሊሲዎች አንጻር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጠንካራ ክትትል እና ትችት እየተሰነዘረባቸው ነው።
የፎቶው ባለመብት AFP-በአውሮፓውያኑ 2035 ከግማሽ በላይ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ ‘ወፍራም’ ወይም ‘ከልክ ያለፈ ክብደት’ ያለው ተብሎ ሊመደብ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጠ።-የዓለም ኦቢሲቲ ፌዴሬሽን አፋጣኝ እርምጃዎች ካልተወሰዱ ከአንድ አስርት ዓመታት በኋላ አራት ቢሊዮን ሕዝብ ለጤና አስጊ የሆነ ክብደት ይኖረዋል ብሏል።-አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የአፍሪካ እና ኢሲያ አገራት ደግሞ ከልክ ያለፈ ክብደት ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ ጭማሪ የሚታይባቸው አገራት ሊሆኑ እንደሚችሉ ፌዴሬሽኑ ያወጣው ሪፖርት ያመላክታል።-በብዛት ከመጠን ያለፈ ክብደት የሚኖራቸው ሕጻናት እና አፍላ ወጣቶች እንደሚሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ከልክ ካለፈ ውፍረት ጋር ተያይዞ የዓለም ዓመታዊ ወጪ 4 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚሆን ተገልጿል።-የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሉዊስ ቦር የሪፖርቱ ግኝቶች አገራት በአስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ ካልሆነ ደግሞ ወደፊት ለሚመጣው አደጋ እንዲዘጋጁ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ነው ብለዋል።-ከልክ ያለፈ ውፍረት አነስተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ላይ የሚኖረው ተጽእኖ በሪፖርቱ የተመላከተ ሲሆን፤ በመላው ዓለም ከሚገኙ አገራት በዜጎች ውፍረት ምክንያት ከፍተኛ ችግር ከሚገጥማቸው ቀዳሚ 10 አገራት መካከል 9ኙ በአፍሪካ እና በኢሲያ የሚገኙ አስተኛ ገቢ ያላቸው አገራት ናቸው።-የሰዎች ክብደት ከልክ እንዲያልፍ ምክንያት ናቸው ከተባሉት መካከል በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን መመገብ ማዝወተር፣ የአካል እንቅስቃሴ ያለማድረግ ባህሪ መጨመር፣ የምግብ አቅርቦት እና ገበያ ፖሊስ ቁጥጥር ደካማ መሆን እንዲሁም ክብደትን ስለመቆጣጠር እንዲሁም የጤና ትምህርት ትኩረት አለማግኘት ተጠቃሽ ናቸው።-ሪፖርቱ በመላው ዓለም ከልክ ያለፈ ውፍረት የሚኖራቸው ሰዎች ቁጥር መጨመሩ በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል ብሏል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ቢቢሲ በሳዑዲ አረቢያ በስደት የሚኖረውን ያህያን ሲያነጋግረው በእግሩ ላይ ከደረሰበት ጉዳት ገና እያገገመ ነበር።-ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለስደት ከወጣ አምስት ወራቶች ያስቆጠረው ያህያ፣ እግሩን በጥይት የተመታው የሳዑዲን ድንበር ለማቋረጥ ሲሞክር እንደሆነ ይናገራል።-ያህያ ሳዑዲ ከመድረሱ አስቀድሞ ወደ የመን ነው የተሰደደው።-በየመን ደላሎች ይዘው ካቆዩት በኋላ ድንበር ተሻግሮ ወደ ሳዑዲ የሚገባበት ቀን ሲደርስ ከሌሎች ስደተኞች ጋር በመሆን በተከፋይ መንገድ መሪዎች አማካይነት ጉዞ ጀመሩ።-እጅግ አስቸጋሪውን የበረሃ ጉዞ በረሃብ እና በጥማት ተጎድተው ከተጓዙ በኋላ ያጋጣማቸው ነገር ከሞት ጋር የሚያጋፍጥ ከባድ ፈተና ነበር።-ከሳዑዲ ድንበር በተወሰነ ርቀት ላይ የአገሪቱ ድንበር ጠባቂ ወታደሮች ከክላሽ እስከ ዲሽቃና ሞርታር ታጥቀው ከፊት ለፊታቸው በከባድ ጥበቃ ላይ ነበሩ።-“የአንድ ሰዓት መንገድ ሲቀረን ከርቀት ነበር ያዩን። እኔ አንድ በመንገድ የደከመች እህታችንን ተሸክሜ ለመሻገር ነበር ያሰብኩት። እሷን ተሸክሜ ከኋላ ቀርቼ ስለነበርኩ ሲተኮስብን ተመታሁ።”-ያህያ በጥይት ፍንጣሪ መመታቱ እና መቁሰሉ ወደ ሳዑዲ ድንበር ከመገስገስ አላስቆመውም።-ከኢትዮጵያ ሲነሱ ጀምሮ በየመንገዱ በደላሎች፣ በሽፍቶች እና በታጣቂዎች ስቃይ እየደረሰባቸው፣ ገንዘብ እየተጠየቁ ሳዑዲ ድንበር ላይ የሞት ፅዋ እንደጠብቃቸው የሚናገረው ያህያ “በየበረሀው ስንት ወጣት ረግፎ ቀርቷል። በየመንገዱ እንደ እንስሳ ወድቆ የቀረው ቁጥር የለውም።-“በብዛት ዲሸቃ ነው የሚተኩሱት። ቁጥራቸው በርከት ያሉ ስደተኞች ለመሻገር ሲሞክሩ ግን ከባድ መሳርያ ሳይቀር ይተኩሳሉ” በማለት ያስረዳል።-ያህያ ከሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች እንደተተኮሰ በሚገልፀው መሳርያ እግሩ ቢመታም፣ ድንበሩን እንደምንም ተሻግሮ ወደ አገሪቱ መግባት ችሏል።-ከደረሰበት ጉዳት ለማገገምም ከአንድ ወር በላይ ሕክምና ማግኘት ነበረበት። በተደረገለት ሕክምና ዛሬ ላይ መራመድ ቢችልም ግን ትንሽ ከፍታ ቦታ መውጣት ግን ያስቸግረዋል።-ተስፋይ [ስሙን የተቀየረ ስደተኛ] ልክ እንደ ያህያ በዚህ መንገድ ያለፈ ስደተኛ ነው። ለሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ ከቆየችው ትግራይ ተነስቶ ሳዑዲ አረቢያ ከገባ ጥቂት ወራት ብቻ እንዳስቆጠረ ይናገራል።-የመን እንደገባ ወደ ሳዑዲ ለሚያሻግሩት ደላሎች እና መንገድ መሪዎች የሚሰጥ ገንዘብ ቢጠየቅም የመክፈል አቅም ግን አልነበረው። ከዚያም ክፍያውን መፈፀም የሚችልበት አቅም እስኪያገኝ እዚያው ለመቆየት ተገደደ።-እነዚህ ለክፍያ የሚሆን ገንዘብ የሚጠየቁ ስደተኞች ብሩን እስኪያገኙ ደላሎቹ በሚቆጣጠሯቸው እጅግ አስከፊ በሆኑ ማቆያ ቦታዎች እንዲቆዩ የሚደረግ ሲሆን፣ ክፍያው ከተፈፀመ በኋላ መንገድ የሚመሩ ሰዎች ተመድበውላቸው ወደ ሳዑዲ ድንበር ጉዞ ይጀምራሉ።-በዚህ መልኩ ከየመን ወደ ሳዑዲ ድንበር እንደተሻገረ የሚናገረው ተስፋይ፣ ክፍያው ሲፈጸም በመንገድ መሪዎች ድጋፍ ጉዞ ተጀምሮ ወደ ሳዑዲ ድንበር ሲደርሱ መሪዎቹ “ከዚህ በላይ እንድንመራችሁ የሚያስችል ክፍያ አልተፈፀመላችሁም” ብለው በረሃ ላይ ጥለዋቸው እንደሚመለሱ ያስረዳል።-በዚህ ሁኔታ በድንበር አቅራቢያ የተተዉ ስደተኞች በማያውቁት ተራራማ እና በረሃማ ቦታ ወደ ተለያየ አቅጣጫ ለመጓዝ ሲሞክሩ ችግር ይገጥማቸዋል።-“የተወሰኑ ዕድል የቀናቸው ሳዑዲ ሲገቡ፣ አብዛኞቹ ግን መንገድ ስተው አድፍጠው ያለማስጠንቀቂያ አነጣጥረው ወደ ሚተኩሱ ወታደሮች አቅጣጫ በመሄድ የጥይት እራት ሆነው በየበረሃው ይቀራሉ” የሚለው ተስፋይ፣ እሱም ከሌሎች 14 ስደተኞች ጋር የብዙ ሰዎች አስከሬኖች እያየ ድንበሩን እንደተሻገረ ይናገራል።-ተስፋይን ጨምሮ በቡድን ሆነው ሲጓዙ ከነበሩ 15 ስደተኞች መካከል እሱ እና ሌላ ሁለተኛ ሰው ብቻ ናቸው ከሚተኮስባቸው ተኩስ ተርፈው ድንበር ተሻግረው ወደ ሳዑዲ መግባት የቻሉት።-ተስፋይ እንደሚለው ከሆነ ድንበር ለመሻገር በሚሞክሩት ላይ የሚተኮሰው ከሳዑዲ አረቢያ በኩል ሲሆን፣ ድንበር ጠባቂ ወታደሮቹ እንደየ ሁኔታው ከክላሽ እስከ ከባድ መሳርያ ነው የሚተኩሱት። በድንበሮቹ አካባቢም ምሽጎች አሏቸው።-ሌላኛው ቢቢሲ ያነጋገረው ከኦሮሚያ ክልል በ2011 ዓ.ም በድርቅ እና ግጭት ምክንያት ወደ ስደት የወጣ ሞሐመድ ሙሲም ሙሜ ይባላል። አሁን ላይ በየመን የስደተኞች ማቆያ ውስጥ ይገኛል።-“በሳዑዲ በድንበር ላይ ስደተኞች በአየር እና በመሬት ይገደላሉ። ወገኖቻችን በየቦታው እየተገደሉ ነው፤ በድንበር ጠባቂዎች ብቻ ሳይሆን በሰው አዘዋዋሪዎች ጭምር ይገደላሉ። ሰዎች በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ ናቸው” በማለት ስለሁኔታው ይናገራል።-አክሎም ኢትዮጵያውያን የጥቃት ዒላማ መሆናቸውን ሲያስረዳ “እየተገደለን እና እየተደፈርን ነው። ወንዶች እንኳን ይደፈራሉ” ብሏል።-ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች በሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች እየተታለሉ ድንበር ተሻግረው አደንዛዥ እጽ እንዲያጓጉዙ እየተደረገ መሆኑን በመግለፅም “ይህም በሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች የሚገደሉ ወገኖቻችን ቁጥራቸው እንዲጨምር አድርጓል” ሲል ያስረዳል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-ያህያ በላያቸው ላይ እየተተኮሰባቸው ድንበሩን ሲሻገሩ የተሸከማት ኢትዮጵያዊት ስደተኛ በሕይወት ተርፋ ዛሬ ሪያድ ውስጥ ትገኛለች። ሌሎች ሴቶች እና ወንዶች ግን ተመትተው ሲወድቁና ሲሞቱ ተመልክቷል። ከእነሱ በፊት ለመሻገር ሲሞክሩ በጥይት ተመትተው በረሀው ላይ የቀሩ በርካታ አስከሬኖች ማየቱንም ይናገራል።-“አስከሬን ሞልቷል። ከጭነት መኪና የተራገፈ ድንጋይ ነው የሚመስለው። የሞተውን አልፈን ነው የምንሄደው። አንዳንዶቹ ሸክማቸውን እንደያዙ፣ ሌሎቹም እንዲሁ በአንድ ላይ ተደራርበው ወድቀው አስከሬናቸውን የበረሃው ፀሐይ እያነደደው አይተናል። ብዙ ናቸው።”-በበረሀው ከወደቁ አስከሬኖች መካከል አብዛኞቹ የሴቶች እንደነበሩ የሚናገረው ያህያ፣ ከእሱ ጋር ተመትተው ቆስለው ድንበሩን መሻገር የቻሉ አራት ሰዎች እንዳሉም ለቢቢሲ ተናግሯል።-ከድንበር ጠባቂ ወታደሮች በማይተናነስ መልኩ ደላሎቹ በስደተኞቹ ላይ የሚያደርሱት ስቃይ እና እንግልት ከባድ እንደሆነ የሚናገረው ተስፋይ በበኩሉ፣ ዕድሜያቸው እስከ 12 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችም የዚህ ሰለባ መሆናቸውን ሲሆኑ ማየቱን ይገልፃል።-ደላሎቹ ካለምንም ርህራሄ በዕድሜ ያልደረሱትን ጭምር ከአገራቸው እንዲወጡ በማድረግ የመን ውስጥ እያጎሯቸው መሆኑን በመጥቀስ፣ ከየመን ወደ ሳዑዲ ለመሻገር ሲሞክሩ የጥይት እራት ሆነው እየቀሩ ናቸው ይላል።-አክሎም “እኔ ድንበሩን ስሻገር በቁጥር መግለፅ የማልችለው የአካባቢዬ ሰዎች አስከሬን ሳይቀር ነው ያየሁት። ቀድመውን ለመሻገር ከሞከሩት ስደተኞች እንዲሁም ከእኛ ጋር ከነበሩ በርካቶች ተመትተው ሞተው እያየን ነብሳችንን ለማዳን ስንሮጥ ነበር” ሲል ያጋጠመውን ያስታውሳል።-ሕይወቱን በሞት ቁማር አስይዞ አስከሬኖችን ተሻግሮ የሳዑዲ አረቢያን ድንበር እንደተሻገረ የሚናገረው ተስፋይ፣ ያን ሁሉ ሰቆቃ አልፎ በአሁኑ ጊዜ በሐዘን እና ቁጭት ውስጥ ይገኛል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያነሳው ወደ ስደት ከመነሳቱ በፊት ሲሰማ እና ሲያስብ የነበረውን ሁኔታን ሊያገኝ አለመቻሉ ነው።-“እዚህ ያለው ሁኔታ እንደጠበቅኩት አይደለም። ሥራ የለም። በፀሐይ እየነደድን ነው። አስቸጋሪ ሁኔታ ነው ያለው። በየት በኩል ይገኝ ይሆን እንጂ የምመለስበት ዕድል ባገኝ በፍፁም አላመነታም ነበር። ቁጭቱ ሊወጣልኝ አልቻለም” ሲል ስላለበት ሁኔታ ይናገራል።-ዛሬ በስደት አገኘዋለሁ ብሎ የጠበቀውን እና ሲሰማው የነበረውን ማግኘት አልቻለም። ይልቁንም በረሃ ላይ ምግብ እና ውሃ እንዲሁም መጠለያ በሚገባ ሳያገኝ፣ ዕድሉ ሲገኝ የቴምር ዛፍ የመንከባከብ ሥራ እየሰራ ይገኛል።-ከአገር ቤት ሲነሳ የነበረው መረጃና ተስፋ አሁን በመሬት ላይ ከጠበቀው ጋር ፈፅሞ ሊጣጣምለት እንዳልቻለ የሚናገው ያህያም፣ ልክ እንደ ተስፋይ ካለበት ለመድረስ የከፈለውን ዋጋ ያህልም ባይሆን አሁን ያለበት ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን ይናገራል።-እሱ እና ተስፋይ እንደሚሉት መንግሥት ዜጎቹ በሳዑዲ አረቢያ ስላሉበት እጅግ አስከፊ ሁኔታ መረጃ ሳይኖረው ቀርቶ ሳይሆን “ለጉዳዩ ትኩረት ካለመስጠት እና ለዜጎቹ ካለ መቆርቆር” ሺዎች በበረሀ ወድቀው እየቀሩ ነው ይላሉ።-ይቅርና በበረሀ ለሚወድቁት በሳዑዲ እስርቤቶች ስላለው አሰቃቂ የኢትዮጵያውያን ሁኔታ እንኳ አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ባለመቻሉ መንግሥታቸውን ይወቅሳሉ።-ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት አስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ያሉ ዜጎችን ሲመልስ እንደነበር ይታወቃል።-የተሻለ ሕይወት ፍለጋ በሕገወጥ መንገድ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን እንደመሸጋገሪያ በሚጠቀሙበት የየመን እና የሳዑዲ አረቢያ ድንበር ላይ በርካታ ስደተኞች በሳዑዲ የፀጥታ ኃይሎች ሆን ተብሎ እየተገደሉ መሆኑን ‘ሚድል ኢስት አይ’ የተባለው የዜና ድረ-ገፅ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።-‘ሚክስድ ማይግሬሽን ሴንተር’ (MMC)] የተባለው ዓለም አቀፍ የፍልሰት ጥናት እና ትንተና መረብ ሐምሌ 5/2023 እ.ኤ.አ ያወጣውን አዲስ ጥናት መሠረት በማድረግ ድረ-ገጹ ባጠናቀረው ዘገባ ላይ “ሥራ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በስናይፐር እና በሞርታር ኢላማ ሆነዋል” ብሏል።-የግድያው ሰለባ የሆኑት ስደተኞች በኢኮኖሚ ችግር እና በጦርነት ሳቢያ ከአገራቸው በመፈናቀል ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ፣ ከዚያም በአደገኛ ሁኔታ በባሕር ወደ የመን፣ በመጨረሻም ወደ ሳዑዲ አረቢያ በየብስ ለመሻገር ሲሞክሩ በድንበር በጠባቂዎች እየተገደሉ መሆናቸውን የ‘ሚክስድ ማይግሬሽን ሰንተር’ መረጃ ያመለክታል።-የሳዑዲ-የመን ድንበር በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አደገኛ እየሆነ መምጣቱ የሚነገር ሲሆን፣ ከጥር 1 እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2022 በነበረው ጊዜ ብቻ ወደ 430 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸው እና 650 መቁሰላቸው ‘ሚድል ኢስት አይ’ ገልጿል።-ይህ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ተፈፀመ የተባለው ግድያ እና ጥቃት በየመን የሁቲ ታጣቂዎች በሚቆጣጠሩት አል-ጃውፍ በሚባል መስመር ሲሆን፣ ተመሳሳይ ጥቃቶችም በሳዑዲ አረቢያ ጂዛን ግዛት መፈጸማቸውን ዘገባው ጠቅሷል።-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ቀደም ሲል በጉዳዩ ላይ ስጋቱን የገለፀ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2022 “በስደተኞች ላይ ስለሚፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች” በርካታ ልዩ ዘገባዎች አውጥቶ ነበር።-ድርጅቱ እንደገለጸውም ከተጎጂዎች መካከል 30 በመቶ ሴቶች እና 7 በመቶ ህጻናት ናቸው።-በአካባቢው ጉዳት ለሚደርስባቸው ሰዎች እርዳታ ለማድረግ አስቸጋሪ በመሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች የተጎዱትን መርዳት አልቻሉም።-በስተደኞች ላይ በሚከፈተው ተኩስ ጉዳት የሚደርስባቸው ሰዎች ሕክምና ለማግኘት የቻሉትን ሁሉ የሚጥሩ ቢሆንም፣ ራቅ ባለ አካባቢ የሚገኝ አንድ ሆስፒታልም አቅሙ የተገደበ ነው ይላል ዘገባው።-እንደ ‘ሚክስድ ማይግሬሽን ሰንተር’ የተባለው ዓለም አቀፍ የፍልሰት ጥናት እና ትንተና መረብ ገለጻ እስካሁን ድረስ በግድያው እና በመብት ጥሰቶቹ ላይ ምንም አይነት ውጤታማ ምርመራ አለመካሄዱን አስታውቋል።-በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት እንዲሁም በሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልክ እና በኢሜይል በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።-ከዚህ በተጨማሪም ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በኩል ስለቀረቡት ክሶች ምላሽ እና ማብራሪያ ለመጠየቅ ባለፈው ሳምንት ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢሜይል ጥያቄ ብናቀርብም፣ ይህ ዘገባ እስከ ታተመበት ቀን ድረስ ምላሽ አላገኘንም።
የፎቶው ባለመብት TPLFOFFICIAL/FB-ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር እና ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር)-ከተመሠረተ ግማሽ ምዕተ ዓመት ሊሞላው የተቃረበው ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከአማጺ ቡድንነት ተነስቶ በአገር መሪነት ጉልህ ሚና ይዞ ከቆየ በኋላ፣ ከማዕከላዊ መንግሥት ተገፍቶ ተመልሶ ወደ ትግራይ ክልል ከተመለሰ በኋላ ለሁለት ዓመታት በተካሄደው ጦርነት ወደ ሽምቅ ተዋጊነት ለመመለስ ተገዶ ነበር።-ደም አፋሳሹ የእርስ በርስ ጦርነት ያስቆመውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተከትሎ በትግራይ ክልል የበላይ ገዢ በመሆን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ዳግም ቦታ ለማግኘት ጥረት እያደረገ መሆኑን አንዳንዶች ቢናገሩም፣ የህወሓት መሪዎች ግን ዋና ትኩረታቸው ትግራይ መሆኗን ይናገረሉ።-በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን እና ከፍተኛ መጠን ላለው የሃብት እና ንብረት ውድመት ምክንያት ከሆነው ከትግራይ ጦርነት እና ከአፈታቱ ጋር በተያያዘ እየተተቸ የሚገኘው ህወሓት፣ የስትራቴጂካዊ አመራር ችግር እየገጠመው መሆኑን የፓርቲው የቁጥጥር ኮሚሽን በተደጋጋሚ ሲያሳውቅ ተደምጧል።-ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት በሚልም በሥራ ላይ ያሉ አምስት ሥራ አስፈፃሚ አባላት፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የትግራይ ሠራዊት አዛዦችን እና ከፓርቲው የተሰናበቱ የቀድሞ አመራሮችን በመያዝ በሩን ለስብሰባ ዘግቶ ከሁለት ወር በላይ ቆይቷል።-ህወሓት ተመሳሳይ ችግር ሲያጋጥመው ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ከአመራር ጋር የተያያዙ በርካታ ፈተናዎችን እና ውጣ ውረዶችን ገጥመውታል።-የህወሓት የመጀመርያው ፈተና ተብሎ የሚጠቀሰው ክስተት ፓርቲው በተመሠረተበት አንደኛ ዓመቱ ያጋጠመ ሲሆን “ሕንፍሽፍሽ” (ክፍፍል/ትርምስ) በመባል የሚታወቅ እና በአመራሮቹ ውስጥ ያጋጠመ መከፋፈል ነው።-በወቅቱ ልዩነቶቹ የተፈቱበት መንገድ ኢ-ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እና በቡድኑ ላይ ጠባሳ ትቶ ያለፈ እንደነበር ብዙዎች ይናገራሉ።-በ1977 ዓ.ም. ያጋጠመ የፖለቲካ ልዩነት ደግሞ የፓርቲው መሥራቾች እና ከፍተኛ አመራሮች የነበሩትን አቶ አረጋዊ በርሄ እንዲሁም አቶ ግደይ ዘርዓጽዮንን ለስደት ዳርጓል።-ቀጣዩ መከፋፈል በ1993 ዓ.ም. የተከሰተ ሲሆን፣ በፓርቲው የፖለቲካ መዋቅር እና በተለይም በትግራይ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አስከትሏል ተብሎ ይታመናል።-በቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የሚመራው ቡድን በወቅቱ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩትን አቶ ገብሩ አስራትን እና የቀድሞ የሥራ አስፈፃሚ አባላትን አቶ ስዬ አብርሃ እንዲሁም ወይዘሮ አረጋሽ አዳነን ከሥልጣን በማባረር የፓርቲ እና የመንግሥት ሥልጣንን በመያዝ ቀጠለ።-ማባረሩ በፖለቲከኞች ላይ ብቻ አላቆመም። ከልዩነቱ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ እና የአየር ኃይል አዛዥ ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖትንም ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።-በወቅቱ “አንጃ” ተብሎ የተባረረውን ቡድን ይደግፋሉ የተባሉ በርካታ ሰዎችም ከመንግሥት ኃላፊነታቸው ተሰናብተዋል።-ከዚህ ባሻገር በፓርቲው ታሪክ የቅርብ ጊዜ ፈተና ተብሎ የሚጠቀሰው በ2010 ዓ.ም. የተደረገው የአመራር ለውጥ ነው።-በወቅቱ አስር ቀናት በወሰደው ግምገማ የፓርቲው አመራርን “በፀረ-ዴሞክራሲያዊነት እና ቡድንተኝነት” በመገምገም ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ የፓርቲውን አመራርነት በመረከብ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ አባይ ወልዱን ከሥራ አስፈፃሚነት በማንሳት ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አውርዷል።-የሥራ አስፈፃሚ አባል የነበሩትን ወይዘሮ አዜብ መስፍንንም ከኃላፊነት በማንሳት ከፓርቲው አባልነት አግዷል።-አቶ በየነ መክሩንም ከፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዝቅ አድርጓል።-ይህን ተከትሎ ፓርቲው ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤልን የድርጅቱ ሊቀመንበር እና የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት፣ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄርን ምክትል አድርጎ ሾመ።-በእነዚህ ሁለት ሰዎች የሚመራው ህወሓት የፌደራል መንግሥት ሕገወጥ ብሎ የፈረጀውን ምርጫ አካሄደ። በፓርቲው እና በፌዴራል መንግሥት መካከል የነበረው የፖለቲካ ውጥረት ተባብሶም በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም. ላይ ጦርነት ተቀሰቀሰ።-የጦርነቱን መቀስቀስ ተከትሎም በርካታ የህወሓት መሪዎች እና ነባር ታጋዮች የወጣትነት ዘመናቸውን ወደ አሳለፉበት የትግራይ በረሃ ለመመለስ ተገደዱ።-በተለያየ የፖለቲካ አቋም የሚታወቁት የክልሉ ተወላጆች የትግራይ መከላከያ ሠራዊት በመባል የሚታወቀውን ጦር መሥርተው ከስምንት ወራት ትግል በኋላ ዋና ከተማዋን መቀሌን ጨምሮ አብዛኛውን የትግራይ ክፍል ተቆጣጠሩ።-ህወሓትም “ሕዝብ የመረጠው መንግሥት ወደ ቦታው ተመልሷል” ብሎ ነበር።-ጦርነቱን ለማቆም የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በህወሓት የበላይነት የተያዘ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቋመ።-ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በአቶ ጌታቸው ረዳ በሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር እና በህወሓት አመራሮች መካከል ልዩነቶች እንደተፈጠሩ የሚገልጹ መረጃዎች በስፋት ሲደመጡ ቆይተዋል።-የፓርቲው የቁጥጥር ኮሚሽንም ፓርቲው “ብቃት ያለው አመራር በማጣቱ እየፈራረሰ መሆኑን” በተደጋጋሚ አስታውቆ ነበር።-ህወሓት ይህንን የአመራር ችግር ለመፍታት በሚል ከሁለት ወራት በላይ በዝግ ስብሰባ ሲያካሂድ ቆይቶ፣ ስብሰባውን ትናንት ረቡዕ ጥር 22/2016 ዓ.ም. ማጠናቀቁን ቢገልጽም የሚጠበቀውን የአመራር ለውጥ ግን አላደረገም።-በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ስትራቴጂክ ጥናት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ገብረመድኅን ገብረሚካኤል፣ የህወሓት የአመራር ቀውስ ለብዙ ዓመታት የቀጠለ መሆኑን በመጥቀስ፣ የፓርቲው እውነተኛ እምነት ይህ ነው ወይ የሚል ጥያቄ ያነሳሉ።-“ህወሓት አሁን ብቻ ሳይሆን የቆየ የአመራር ቀውስ ገጥሞታል። በዚህ መልኩ ራሱን ከገመገመ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል። ታድያ እንደዚህ ከሆነ የችግሩ ምንጭ የሆነው አመራር በተለይም ስትራቴጂካዊ እየተባለ በሚጠራው አመራር ላይ ለውጥ ይመጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።-“ሆኖም ግን ይህ እየታየ አይደለም። ምክንያቱም አንደኛ 'ችግሩ አለብኝ' ብሎ እያመነ ያለው ከውጭ ጫና ስላለበት እና ተደጋጋሚ ትችት ስለሚደርስበት እሱን ለማረጋጋት እንጂ ‘በእርግጥ እምነቱ ነው ወይ? በዚህ መሰረት ራሱን ለመፈተሽ እና ለመታገል ቁርጠኛ ነው ወይ?' የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ብልሹ መሪዎችን እና ድክመቶቹን ለመለወጥ ቅን የሆነ እውነተኛ የውስጥ ትግል ስለሌለው ይመስለኛል” በማለት ያስረዳሉ።-ከመሪዎቹ መካከል በአቅም ጎላ ብሎ መታየት የሚችል ተደማጭነት ያለው ሰው አለመኖሩንም እንደ ሁለተኛ ምክንያት አቶ ገብረ መድኅን ይጠቅሳሉ።-“ሁሉም በተመሳሳይ የብልሽት ደረጃ ላይ ናቸው። ውድቀቱ የአንድ ወይም የሁለት አይደለም። ድርጅታዊ፣ ስትራቴጂያዊ እና የአመራር ነው። የተሻለ ሆኖ የሚታይ ግለሰብ ወይም መሪ የለም። ማን ከማን ይበልጣል? ማን ነው ሊወጣ የሚችለው? ማን ይለወጣል? የሚል ጥያቄ አለ። እኔም እንደዛ ነው የማምነው” ብለዋል።-ቀደም ሲል በፖለቲካው ተሳትፎ የነበራቸው በአሁኑ ወቅት ግን የትግራይን ፖለቲካን በመከታተል የሚተነትኑ በአዲግራት የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አብርሃ ተክሉም ከዚህ ጋር የሚስማማ ሐሳብ አላቸው።-“ህወሓቶች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እስካለፉበት ድረስ በአንፃራዊ ሁኔታ ያጋጠሙ ነገሮችን በተገቢው ማዕቀፍ ውስጥ አስገብተው የማየት ብቃቱ ነበራቸው። ‘ምንድን ነው ያጋጠመን? ለምን ተከሰተ?’ ይላሉ። ዓለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ ሁኔታን እንዲሁም ራሳቸውን ይመለከቱ ነበር።-“አሁን ያለው አመራር ግን ከዚህ ሂደት የተለየ ነው። የሐሳብ ለውጥ እንዳያመጣ በሐሳብ ደረጃ አይደሉም እየተሟገቱ ያሉት። የአመራር ለውጥ ያላመጡበት ምክንያት ደግሞ እርስ በርስ እየተጨቃጨቁ እና እየተባሉ ስላሉ ነው፤ ይህ ደግሞ ወደ ከፍተኛ አለመተማመን እና ጥርጣሬ ወስዷቸዋል” ብለዋል።-መምህር አብርሃ ተክሉ የውጭ ጣልቃ ገብነትም ሌላ ችግር ሊሆን እንደሚችል “ፓርቲው በተነጻጻሪ ዝግ በሆነ ሂደት ችግሮቹን የመፍታት ልምድ ነው ያለው። ዛሬ ላይ ግን ምስጢሮችን መደበቅ አይችልም። መረጃዎች በየጊዜው ነው የሚለቀቁት። በዚህ መጠንም ከውጪ ሆኖ ሁኔታውን ሊያባብሰው የሚሻ አካል በሚፈልገው ሰው በኩል የማተራመስ እንዲሁም መረጋጋት እንዳይኖር የማድረግ ዕድሉ ሰፊ ነው” በማለት ያስረዳሉ።-ህወሓት ችግሮቹን በስብሰባ እና በግምገማ የመፍታት ልምዱን የሚያደንቁ በርካታ ሰዎች ቢኖሩም፣ በፓርቲው ውስጥ የተለመደ የቡድንተኝነት አካሄድ ግን ፓርቲው እውነተኛ ለውጥ እንዳያመጣ እንቅፋት ሆኗል ይላሉ። በአሁኑ ጊዜም ፓርቲው በተመሳሳይ ሁኔታ በቡድንተኝነት ተከፋፍሎ ከሐሳብ ትግል ወጥቶ በመወነጃጀል እና በመካሰስ ላይ እንደሚገኝ የሚያመለክቱ መረጃዎች ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ሳይቀር እየተደመጡ ነው።-የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በአንድ ሕዝባዊ መድረክ ላይ ሲናገሩ፣ ፓርቲው ለሁለት ወራት ባካሄደው ስብሰባ በሕዝብ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ አለመወያየቱን እና በግምገማው ወቅት ወደ አካባቢያዊነት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ለማስተሳሰር የሞከሩ መሪዎች እንዳሉ በግልጽ አመልክተዋል።-ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የህወሓት የቀድሞ አመራር አባል የሆኑት አቶ ስብሃት ነጋ በቅርቡ ትግራይ ሚድያ ሀውስ ለተባለው ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለ-መጠይቅ በስም ያልጠቀሷቸው የተወሰኑ የክልሉ ሠራዊት አመራር እና የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባላትን “የሲአይኤ ወኪሎች” በማለት ፓርቲውን ለማፍረስ እያሴሩ ነው ሲሉ ከስሰዋል።-የመቀለ ዩኒቨርሲቲው መምህር ገብረመድኅን እንደሚሉት በፓርቲው አመራሮች መካከል ያለው መቧደን በጥቅም ላይ የተመሠረተ ነው።-“እኔ ከጥቅም አልፈው በሃሳብ እና በሕዝብ ጉዳዮች ላይ የተመሠረቱ አይመስለኝም። አንደኛው በሥልጣን ላይ ለመቆየት ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ወደ ሥልጣን ለመምጣት ነው የሚጥሩት” በማለት ያስቀምጣሉ።-መምህር አብርሃም ተክሉም ተመሳሳይ መረጃ እና ግንዛቤ ነው ያላቸው።-“ጥቅም ነው። መቧደኑ ለውጥን በሚፈልጉ እና ለውጡን በማይቀበሉት የሚገለጽ አይደለም። ‘አሮጌው አዲስ አመራሮች ወደፊት እንዳይመጡ እየተከለከለ ነው’ የሚለው አባባልም ከእውነታው የራቀ ነው” ይላሉ።-ህወሓት ረቡዕ ጥር 22/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ለ41 ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ እና ግምገማ እንዳጠናቀቀ፤ “የስትራቴጂክ አመራር ድክመት ቁልፍ ችግሩ መሆኑን ለይቶ ማወቅ እንደቻለ” በመግለጽ በቀጣይ የአመራር ለውጥ እንደሚያደርግ አመልክቷል።-የፓርቲው የመንፈስ አባት ናቸው የሚባሉት አቶ ስብሃት ነጋ ከቴሌቪዥን ጣቢያው ጋር በነበራቸው ቆይታ “ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች ከህወሓት ጋር ሊወዳደር የሚችል ፓርቲ የለም” ሲሉ አስረግጠው ሲናገሩ ተደምጠዋል።-ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለቱ የትግራይ ምሁራን እንደሚገመግሙት ግን ፓርቲው መሠረታዊ ለውጥ ካላመጣ ህልውናውን በቅርቡ የሚያከትም ይሆናል።-በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ምሑሩ አቶ ገብረመድኅን ገብረሚካኤል “ህወሓት ተጠናክሮ ይወጣል ብዬ አልጠብቅም። ለተወሰነ ጊዜ መቆየቱ አይቀርም። ምክንያቱም ሌላ የተዘጋጀ ኃይል እና አማራጭ የለም። እንደ ፓርቲ ግን በተለይም ሥልጣን ላይ ሆኖ ራሱን አስተካክሎ ወደ ተሻለ ደረጃ ይሸጋገራል ብዬ አላምንም” ሲሉ ደምድመዋል።-የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህሩ አብርሃም ተክሉ በበኩላቸው “የተጠላ እና የተናቀ ፓርቲ” ያሉት ህወሓት መሠረታዊ ለውጥ ካመጣ መዳን ይችላል የሚል ግምት አላቸው።-“ለሕዝብ ሲሉ የግል ፍላጎታቸውን ትተው ራሳቸውን ለመስዋዕትነት ዝግጁ እስከማድረግ ከመጡ መትረፍ ይችላሉ” በማለት ሐሳባቸውን ቋጭተዋል።
የፎቶው ባለመብት SM-በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወይም 57 ሚሊዮን ሕዝብ አሊያም ከአጠቃላይ ሕዝቡ 51 በመቶ የሚሆነው ምንም አይነት የኤሌክትሪክ አቅርቦት የለውም ይላል - የዓለም ባንክ መረጃ።-በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ባለፉት አስርት ዓመታት ከፍ እያለ ቢሄድም አገሪቱ ከሰሀራ በታች የኤሌክትሪክ እጥረት ካለባቸው አገራት በሦስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።-በአሁኑ ወቅት የሕዳሴ ግድብ ሁለት ዩኒቶችን ጨምሮ ኢትዮጵያ ካላት የኃይል ማመንጫዎች 5250 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ እንደምታመርት የኢትዮጵያ ኤሌክሪክ ኃይል ይገልጻል።-ይህንን ቁጥር በማሳደግ የኤሌክትሪክ ሽፋንን ለመጨመር በኢትዮጵያ አምስት የኃይል ማመንጫዎች እየተገነቡ ይገኛሉ።-ኮይሻ በግንባታ ላይ ካሉ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው።-ከአዲስ አበባ በ540 ኪሎ ሜትር ርቆ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ኮይሻ ወረዳ ግንባታው እየተከናወነ ያለው የኮይሻ ግድብ የኦሞ ወንዝን መሠረት አድርጓል። ይህ ግድብ ጊቤ ሦስት ከተገነባበት ስፍራ በ120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።-ኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ከባሕር ጠለል በላይ 783 ሜትር ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ 201 ሜትር ከፍታ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሞገስ ለቢቢሲ ገልጸዋል።-በየካቲት ወር 2008 ዓ.ም. ግንባታው የተጀመረው ኮይሻ 1800 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አለው።-ግድቡ ይጠናቀቃል ተብሎ ከተያዘለት ጊዜ ባሻገር አሁንም ግንባታ ላይ ነው። ግንባታው እየሄደበት ያለው ፍጥነትም አዝጋሚ ነው።-“ከብድር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ፕሮጀክቱን በሚፈለገው መጠን እና ፍጥነት አላስኬዱትም” ይላሉ አቶ ሞገስ።-ስድስት ዩኒቶች የሚኖሩት የኮይሻ ግድብ 100 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን እና 6.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዝ የሚችል ማጠራቀሚያ (reservoir) ይኖረዋል።-እንደ አቶ ሞገስ ገለጻ፣ ይህ ግድብ አነስተኛ የውሃ ማጠራቀሚያ ያለው ቢሆንም ባለው ከፍታ ምክንያት ከፍተኛ ኃይል ማመንጨት የሚችል ነው።-ግድቡ ቀደም ሲል 2100 ሜጋዋት እንደሚያመነጭ ተገልጾ ነበር። ይህም ኮይሻን ከሕዳሴ ግድብ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛው ከፍተኛ የኃይል ማመንጫ እንደሚያደርገው ተጠብቆ ነበር።-ሆኖም ግን ግድቡ የሚያመነጨው ኃይል ቀድሞ ከታቀደው በ300 መቶ ሜጋዋት ቀንሷል። ይህም 1870 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ካለው የጊቤ ሦስት ግድብ ጋር የተቀራረበ የኃይል ምርት እንዲኖረው ያደርገዋል።-ለመሆኑ የግድቡ የማመንጨት አቅም ለምን እንዲቀንስ ተደረገ?-“የሚያዋጣውን መምረጥ የተቋሙ [የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል] ድርሻ ነው የሚሆነው” የሚሉት አቶ ሞገስ፣ ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን እና ከፍታ ላይ “ምንም አይነት ለውጥ” ሳይደረግ ዩኒቶቹን መቀነስ ግድቡን “ውጤታማ እንዲሆን ያደርገዋል” ሲሉ ያብራራሉ።-“ስለዚህ ተቋሙ በስድስትም በስምንትም ዩኒቶች ተመሳሳይ ዓመታዊ ኃይልን በአማካኝ የሚያገኝበት ሳይንሳዊ ምክንያት ካለው አስር ዩኒት መትከል አስፈላጊ አይደለም ማለት ነው” ሲሉም አክለዋል።-አቶ ሞገስ ለቢቢሲ እንዳጋሩት መረጃ የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አሁን ላይ 61 በመቶ ደርሷል።-ግንባታው እዚህ ደረጃ ሲደርስ ሁለት የፋይናንስ ምንጮች አሉት።-የኮይሻ ጅማሮ ላይ ሳቼ የተባለ የጣልያን ባንክ ለግንባታው ብድር አቅርቧል።-ሆኖም ባንኩ “ለፕሮጀክቱ ግንባታ የሚያስፈልገውን ብድር እንደሚያቀርብ ከተስማማ በኋላ አንድ ጊዜ ብቻ ብድር ሰጥቶ ሌላውን በስምምነቱ መሠረት ማቅረብ አልቻለም” ሲሉ አቶ ሞገስ ገልጸዋል።-በዚህም ሳቢያ ግንባታው ተስተጓጉሎ የነበረ ሲሆን፣ ግድቡ ከዘገየባቸው ምክንያቶች ቀዳሚው ተደርጎ ይጠቀሳል።-“በወቅቱ ሌላም አበዳሪ ሊገኝ ስላልቻለ መንግሥት በውጭ ምንዛሬ መከፈል የነበረበትን በመሸፈን ፕሮጀክቱ እንዲቀጥል አድርጓል” የሚሉት ኃላፊው ግንባታው ከመነሻው የገንዘብ ምንጩ ብድር የነበረ ሲሆን፣ አሁን ወደ መንግሥት ካዝና መዞሩን ጠቅሰዋል።-ግድቡ ሲጀመር 2.4 ቢሊዮን ዩሮ እንደሚፈጅ ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ወጪው ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ይታመናል።-ወጪውን ሊጨምሩ ከሚችሉ ምክንያቶች አንዱ ግንባታው በተስተጓጎለበት ወቅት ተቋራጩ ያለሥራ የቆየበትን ካሳ በመጠየቁ ነው።-ግድቡ አሁን ባለው የፋይናንስ አቅርቦት ከቀጠለ ለመጠናቀቅ እስከ አራት ዓመታት እንደሚፈጅ የሚናገሩት አቶ ሞገስ፣ ሌላ የተሻለ የፋይናንስ መንገድ ከተገኘ ግን “ከዚህም ባጠረ ጊዜ” ሊጠናቀቅ ይችላል።-አቶ ሞገስ የኮይሻ ግድብን ጥቅም የተቀራረበ ኃይል የማመንጨት አቅም ካለው ጊቤ ሦስት ጋር አነጻጽረው ይናገራሉ።-እንደ እሳቸው ገለጻ 2800 ሜጋዋት የማመንጨት አቅም ያለው ጊቤ ሦስት ከፍተኛ የኃይል ተጠቃሚ በሚኖርበት ሰዓት እስከ 40 በመቶ የአገሪቱን የኃይል ፍጆታ ይሸፍናል። ከዚህ ውጪ ባለው ሰዓት ደግሞ እስከ 60 በመቶ ሊደርስ ይችላል።-ይህ ማለት ኮይሻ ከጊቤ ሦስት ጋር ተቀራራቢ የሆነ ኃይል ለአገሪቱ ማመንጨት ይችላል ማለት ነው የሚሉት አቶ ሞገስ፣ ግድቡ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ሽፋን በማሳደግ ከፍተኛ የሆነውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አመልክተዋል።-ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ኮይሻ በድምሩ 6950 ሜጋዋት ማመንጨት ይችላሉ። ይህ ቁጥር አሁን በአገሪቱ ያለውን የማምረት አቅም የሚበልጥ ነው።-ለንጽጽር ያህል የሁለቱን ግድብ ልዩነት እንመልከት፡-ከ12 ዓመታት በፊት የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውሃ ማጠራቀሚያ (reservoir) 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዝ የሚችል ነው።-ከዚህ ግድብ ግንባታ 5 ዓመታትን በኋላ የተጀመረው ኮይሻ ደግሞ ከሕዳሴው ግድብ 67.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ያነሰ ውሃ ይይዛል። የኮይሻ ውሃ ማጠራቀሚያ 6.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃን ያቁራል።-ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጅማሮው ላይ 3.6 ቢሊዮን ዩሮ እንደሚችል ይፋ ሆኖ ነበር። የኮይሻ ግድብ ደግሞ ሲጀመር 2.4 ቢሊዮን ዩሮ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል።-የሕዳሴ ግድብ 16 ተርባይኖች እንደሚኖሩት ተገልጾ የነበረ ሲሆን፣ በቅርቡ ወደ 13 ዝቅ መደረጋቸው ተነሯል። የሚያመነጨው ኃይልም እንዲሁ መጀመሪያ ከታቀደው 6450 ሜጋ ዋት ወደ 5150 ዝቅ ብሏል።-በተመሳሳይ የኮይሻ ግድብ የሚያመነጨው ኃይል ከመጀመሪያው ዕቅድ በ300 መቶ ሜጋዋት ዝቅ ብሏል። ተርባይኖቹም ከ8 ወደ 6 ዝቅ እንዲሉ ተደርገዋል።-በኢትዮጵያ አምስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ሲሆን፣ የውኃ ኃይል ማመንጫዎች (ሃይድሮ ፓወር) ሰፊውን ቦታ ሲይዝ ከንፋስ እና ጂኦተርማል (እንፋሎት) ኃይል የሚያመነጩ ፕሮጀክቶችም ግንባታ ላይ ናቸው።-ከፕሮጀክቶቹ ቀዳሚው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሲሆን 5150 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚችል ግዙፉ ግድብ ነው።-ሌላኛው ከሰባት ዓመታት በፊት የተጀመረው ኮይሻ ነው። ኮይሻ 1800 ሜጋ ዋት ኃይል እንደሚያመነጭ ይጠበቃል።-በሌላ በኩል በድምሩ ሁለት 220 ሜጋ ዋት የሚያመነጩ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።-የመጀመሪያው በሶማሊ ክልል አይሻ ወረዳ እየተገነባ ያለው፣ የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ነው። አይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ሲጠናቀቅ 120 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል።-በኦሮሚያ ክልል አሰላ ውስጥ የሚገኘው የንፋስ ኃይል ማመንጫ 35 በመቶ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም 100 ሜጋ ዋት ኃይልን ያመነጫል።-ሌላኛው የአሉቶ ጂኦቶርማል ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እየተከናወነ ሲሆን በሁለት ዙር የሚገነባ እና 72 ሜጋ ዋት ኃይልን የሚያመነጭ ነው። በመጀመሪያ ዙር ግንባታውም 98 በመቶ ደርሷል።
የፎቶው ባለመብት SOPA IMAGES VIA GETTY IMAGES-በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያሉት የዓለማችን ዋነኛው ተጽእኖ ፈጣሪ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ፌስ ቡክ፣ ከተጀመረ 20 ዓመት ሆነው።-ይህ ሲጀመር “ዘ ፌስቡክ” የሚል ስያሜ የነበረው ማኅበራዊ ሚዲያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በምድራችን ላይ በተከሰቱ የተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የራሱ ሚና ነበረው።-ማርክ ዛከርበርግ እና የኮሌጅ ጓደኞቹ ዶርማቸው ውስጥ ሆነው ፌስቡክን ሲፈጥሩት የነበረው ገፅታ ከታች በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ነበር።-በሂደትም የትየለሌ ጊዜ ቅርፁን ቀያይሯል። ከፍተኛ ሃብትንም ለማፍራት በመቻል ስሙ ይጠቀሳል።-ነገር ግን ሲጀመር የነበረውን ዓላማ አሁንም አንግቧል - ሰዎችን በበይነ መረብ አማካይነት መስተሳሰር።-እንደው ከተቻለ ደግሞ ከማስታወቂያ ሚሊዮንም፣ ቢሊዮንም ዶላሮች መሰብሰብ።-እነሆ ፌስቡክ 20 ዓመት ደፈነ።-ለመሆኑ ፌስቡክ ዓለማችንን የቀየረባቸው አራት መንገዶች የትኞቹ ናቸው?-የፎቶው ባለመብት Niall Kennedy-ከፌስቡክ ቀደሞ እንደ ማይስፔስ ዓይነት ሌሎች ማኅበራዊ ሚድያዎች ነበሩ።-ነገር ግን የማርክ ዛከርበርግ የፌስቡክ መድረክ በአውሮፓውያኑ 2004 ሲመሠረት ከመመንጠቅ ያገደው አልነበረም።-ፌስቡክ ገና በአንድ ዓመቱ እየዳኸ ሳለ ነው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ያፈራው።-በአራት ዓመት ውስጥ ደግሞ ማይስፔስን ሰልቅጦ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማቅረብ ጀመረ።-ከጓደኞቻችሁ ጋር ማታ ወጥታችሁ ፍላሽ ያለው ካሜራ ይዛችሁ ፎቶ ካነሳችሁ በኋላ ፎቶ ለጥፎ “ታግ ማድረግ” የታዳጊነት ዘመን ትዝታ እየሆኑ መጥተዋል።-በርካታ ሰዎች በፌስቡክ ሱስ የተጠመዱት ድረ-ገፁ ያለማቋረጥ አዳዲስ ይዘት ይዞ ብቅ በማለቱ ነው።-በአውሮፓውያኑ 2012 ፌስቡክ ለመጀመሪያ ጊዜ የወርሃዊ ተጠቃሚዎቹ ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን በላይ ሆነ።-በ2021 በየቀኑ ፌስቡክን የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ዝቅ ብሎ 1.92 ቢሊዮን ከመግባቱ በቀር ቁጥሩ እየጨመረ እንጂ እየቀነሳ አልመጣም።-ብዙም ተጠቃሚ ወደሌለባቸው አገራት በመዛመትም እንዲሁም ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎት በመስጠት ጭምር ኩባንያው የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከፍ ማድረግ ችሏል።-በ2023 መጨረሻ ፌስቡክ በቀን ከ2 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ይፋ አድርጓል።-እርግጥ ነው በታዳጊዎች ዘንድ የፌስቡክ ተወዳጅነት እየቀነሰ መጥቷል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ከዓለማችን ማኅበራዊ ሚድያዎች እጅግ ተወዳጅ ከመሆን አላገደውም።-አንዳንዶች ፌስቡክ እና ተቀናቃኝ ማኅበራዊ ሚድያዎች በሰዎች መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጨምር አድርጓል ይላሉ።-ሌሎች ደግሞ ሱስ የሚያስዙ አጥፊ ቴክኖሎጂዎች አድርገው ይቆጥሯቸዋል።-የፎቶው ባለመብት Facebook-ላይክ እና ዲስላይክ ሲመነዘር ረብጣ ዶላር እንደሚወጣው ቀድሞ የገባው ፌስቡክ ነው።-የፌስቡክ እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ [ጉግልን ሳንረሳ] በማኅበራዊ ሚዲያው መድረክ ከሁሉ የላቀበት የሙያ መስክ ነው።-ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 2023 በሦስተኛው ገሚስ ብቻ ሜታ ከማስታወቂያ 34 ቢሊዮን ዶላር አፍሷል። 11.5 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ነው።-ሜታ ማስታወቂያዎቹን የሚቸበችበው የተጠቃሚዎችን ግላዊ [የግል ማለት ቢከብድም] መረጃችንን ተጠቅሞ ነው።-ነገር ግን ፌስቡክ የመረጃ ስብሰባ የሚውለው “ለበጎ” ተግባር ብቻ አይደለም የተጠቀመበት።-ሜታ በተደጋጋሚ ግላዊ መረጃን በዝብዟል ተብሎ ቅጣት ተከናንቧል።-የኬምብሪጅ አናሊቲካ ታሪክ የሚረሳ አይደለም። ይህ የሆነው በ2014 (እአአ) ነው። ፌስቡክ በዚህ ክስ ምክንያት 725 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት እንዲከፍል ግድ ሆኖበታል።-በ2022 ደግሞ ግላዊ መረጃ ከቋቱ አውጥቶ ሸጧል በሚል በአውሮፓ የ265 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ተጥሎበታል።-ባለፈው ዓመት ደግሞ የአይሪሽ መረጃ ጥበቃ ኮሚሽን እስከ ዛሬ ተሰምቶ የማያውቅ 1.2 ቢሊዮን ዩሮ እንዲከፍል ፌስቡክ አዟል።-የዙከርበርግ ኩባንያ ይህ ቅጣት የተላለፈበት የአውሮፓውያንን መረጃ ከአህጉሪቱ ባሻገር አሳልፎ ሰጥቷል ተብሎ ነው።-ፌስቡክ ይግባኝ ጠይቆ ምላሹን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።-የፎቶው ባለመብት Reuters-ፌስቡክ ማስታወቂያ ሲያቀርብልዎ ለእርስዎ የሆነውን መርጦ ነው። ለዚህ ነው ምርጫ ሲደርስ ተመራጨነቱ እየጨመረ የሚመጣው።-የአሜሪካ ምርጫ 2020 ሊካሄድ አምስት ወራት ሲቀሩት የተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን 40 ሚሊዮን ዶላር መድቦ በፌስቡክ ማስታወቂያ አስነግሮ ነበር።-ርዕዮተ-ዓለማቸውን ለነባር እና ለአዳዲስ ተከታዮቻቸው ማሰራጨት የፈለጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፌስቡክን ተመራጭ እና አማራጭ መንገድ አድርገውታል።-በበርካታ አረብ አገራት ተቀስቅሶ የመንግሥታት ለውጥ እና በአንዳንዶ ቹ ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነትን ከቀሰቀሰው “የአረብ ስፕሪንግ” ወቅት ተቃውሞ ለማስተባበር፣ እንዲሁም ወቅታዊ ዜና ለማሰራጨት ፌስቡክ እና ትዊተር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።-ነገር ግን ፌስቡክን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀም ከትችት አልተረፈም።-በ2018 የተባበሩት መንግሥታት ያወጣው ዘገባ፤ ሰዎች ፌስቡክን ተጠቅመው በምያንማር “ግጭት ቀስቅሰዋል” ሲል ይወቅሳል። ፌስቡክም በዚህ ይስማማል።-የፎቶው ባለመብት Reuters-ፌስቡክ ስኬትን ያጎናፀፈው ማርክ ዛከርበርግ ሜታ የተሰኘ ግዙፍ የማኅበራዊ ሚድያ እና የቴክኖሎጂ ማዕከል አቋቁሟል።-ይህ ኩባንያ በዓለማችን አሉ ከሚባሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ተርታ የሚመደብ ነው።-ፌስቡክ ስሙን ወደ ሜታ የቀየረው በአውሮፓውያኑ መጋቢት 2022 ነው።-ቢሆንም ፌስቡክ እነ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና ኦኩለስን የጠቀለለው ከሜታ መወለድ ቀድሞ ነው።-ሜታ እንደሚለው በየቀኑ 3 ቢሊዮን ሰዎች ቢያንስ አንዱን ምርቱን ይጠቀማሉ።-ግዙፉ ሜታ ተቀነቃኝ መተግበሪያዎችን መግዛት ሲያቅተው በተመሳሳይ ምርት ተጠቃሚዎችን እያታለለ ነው እያሉ የሚወቅሱት ብዙ ናቸው።-ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ላይ ታይተው የሚጠፉት “ስቶሪዎች” ከስናፕቻት የተቀዱ ናቸው፤ የኢንስታግራም “ሪል” ደግሞ ከቲክቶክ የተኮረጀ ነው።-አዲሱ የሜታ ምርት የሆነው ትሬድስ ደግሞ የትዊተር መልክ አለው፤ የሚሉ ወቀሳዎች ይሰማሉ።-ውድድሩ ጨምሯል፤ ቁጥጥሩም እንደዚያው። ይህን ለማለፍ ሜታ የሚጠቀማቸው መንገዶች አሉ።-የፌስቡክ አቅም እየጨመረ መምጣት እና ያለው ተፅዕኖ ማርክ ዛከርበርግ ምን ያህል ቴክኖሎጂውን ጠንቅቆ እንደያዘው ምስክር ነው።-ነገር ግን በሚቀጥሉት 20 ዓመታት እጅግ ተወዳጁ ማኅበራዊ ሚድያ ሆኖ ይቆያል ወይ? የሚለው ጥያቄ መልሱ ከባድ ሊሆን ይችላል።-ሜታ አሁን ሜታቨርስ እያለ ወደሚጠራው ፅንሰ-ሐሳብ እያቀና ነው። ይህን የሚያደርገው አፕልን ለመገዳደር ነው።-ሜታ ሌላኛው ሐሳቡ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ላይ ነው።-ኩባንያው ከተጠነሰሰበት ሰዎች የማገናኘት ሐሳብ እየሸሸ ሲመጣ ምን ሊገጥመው ይችላል? የሚለውን አብረን የምናየው ይሆናል።
የፎቶው ባለመብት UN-በፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ሲያካሂድ (ፎቶ ፋይል)-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ ማምሻውን በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ጉዳይ ላይ ሊመክር መሆኑ ተሰምቷል።-ይህ በሁለቱ አገራት መካከል ውዝግብን በፈጠረው ጉዳይ ላይ የሚካሄደው ውይይት በዝግ የሚከናወን ሲሆን ስብሰባ “የአፍሪካ ሠላም እና ፀጥታ” በሚል ርዕስ እንደሚካሄድ ታውቋል።-በዚህ ስብሰባ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ሀና ስርዌ ቴተ ቀርበው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።-አንድ ወር ሊሞላው የተቃረበው ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው ስምምነት የድርጅቱን ቻርተር ጥሷል በሚል ምክር ቤቱ ስብሰባ እንዲቀመጥ ሶማሊያ ባለፈው ሳምንት ጥያቄ አቀርባ ነበር።-የወሩ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ፈረንሳይ የዛሬውን ስብሰባውን መጥራቷ ታውቋል።-ፈረንሳይ ‘ኤ ፕላስ ዋን’ ከሚባለው እና አልጄሪያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሴራ ሊዮን እና ጉያናን ካቀፈው ቡድን ጋር በጉዳዩ ዙሪያ በተደጋጋሚ ውይይት አድርጋለች።-እነዚህ አገራት ከሶማሊያ እና ከኢትዮጵያ ጋር በተናጠል ውይይት ማድረጋቸውም ታውቋል።-ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ታኅሣሥ 22/2016 ዓ.ም. በመሪዎቻቸው መካከል በተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ መሠረት፣ ኢትዮጵያ ነጻ አገር መሆኗን ላወጀችው ሶማሊላንድ ዕውቅናን ለመስጠት፣ ሶማሊላንድ በበኩሏ ደግሞ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ለመፍቀድ ስምምነት ደርሰዋል።-ይህም ሶማሊላንድን የግዛቱ አንድ አካል እንደሆነች የሚገልጸው የሶማሊያ መንግሥት ስምምነቱን አጥብቆ በመቃወም፣ የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚጥስ ድርጊት ነው በማለቱ በአካባቢው ውጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ በአዲስ አበባ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት በቀጣናው ላይ ውጥረት ከፈጠረ ሳምንታት ተቆጥረዋል።-በአንድ ወር ውስጥ ይፈጸማል በተባለው በዚህ ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ ለወታደራዊ እና ንግድ አገልግሎት የሚውል የባሕር በር ታገኛለች።-ኢትዮጵያ በምላሹ ሶማሊላንድን እንደ አገር የሚያስቆጥራትን እውቅና ለመስጠት መስማማቷን የሃርጌሳ ባለሥልጠናት ተናግረዋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ስምምነት የፈጸመው ጉዳዩን በጥልቀት አጢኖ አቋም ለመያዝ መሆኑን አስታውቋል። ከዚህ ባሻገር ግን ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ እንደሚኖራት የኢትዮጵያ መንግሥት መግለጹ ይታወሳል።-ሞቃዲሾ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጻፈችው ደብዳቤ ስምምነቱ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት “የሚጥስ ነው” ብላለች።-“ያለ ሶማሊያ ፌደራላዊ መንግሥት ፍቃድ ወይም ዕውቅና የተደረሰው ስምምነት የአገሪቱን ሕገ-መንግሥት የሚጥስ ነው” ከማለት ባለፈ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሠላምን እና ደኅንነትን በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ምክር ቤቱ “የኢትዮጵያን ግልጽ ጥሰቶች በፍጥነት እንዲያወግዝ” እና የዓለም አቀፍ ሕግን እንዲያስከበር ጠይቃለች።-ኢትዮጵያ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ እንዳይሰበሰብና ችግሩን በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በፃፈችው ደብዳቤ አሳውቃ ነበር።-ኢትዮጵያ የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራመችው ከዓለም አቀፍ ደንቦች ጋር በተጣጣመ መልኩ መሆኑን እና ባሕር በር ለማግኘት መንገድ እንደሚከፍትላት አስታውቃለች።-በሁለቱ አገራት መካከል ንግግር እንዲያመቻቹ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በተሾሙት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በኩል ለመነጋገር መዘጋጀቷን በመጥቀስም የፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እንዳይመከር ጠይቃለች።-በስብሰባው ለምክር ቤቱ አባላት በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ ሀሳብ እንዲለዋወጡ እና ቀጠናዊ ሠላምን፣ መረጋጋትን እና ደኅንነት በሚጠበቅበት መንገድ ላይ ውይይት እንዲያደርጉ ዕድል ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።-በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት በተመለከተ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) እና የአረብ ሊግ በተናጠል ስብሰባ ማድረጋቸው ይታወቃል።-ኢትዮጵያ ያልተሳታፈችበት የኢጋድ ስብሰባ አገራቱ ውጥረቱን በማርገብ ንግግር እንዲያደርጉ ጥሪ ሲያቀርብ፣ የአረብ ሊግ ደግሞ ኢትዮጵያን በማውገዝ ለሶማሊያ ድጋፉን ገልጿል።-የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ ኢትዮጵያ እና የሰሜን ሶማሊያ ግዛት (ሶማሊላንድ) የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በአዲስ አበባ እና በሞቃዲሾ መካከል የተፈጠረው ውጥረት እንዳሳሰበው አስታውቋል።-ምክር ቤቱ ከውይይቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያን ጨምሮ የሁሉም የኅብረቱ አባል አገራት “ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እና ነጻነት” እንዲጠበቅ “ጠንካራ ቁርጠኝነት እና ድጋፍ” እንዳለው አስታውቋል።-የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ተወካዮች በተገኙበት ውይይቱን ያካሄደው ምክር ቤቱ፤ ሁለቱ አገራት የተፈጠረው ውጥረት ግንኙነታቸውን ሊያበላሽ ከሚችሉ ተጨማሪ ድርጊቶችን ከመፈጸም እና እርምጃዎችን ይፋ ከማድረግ እንዲቆጠቡ ጠይቋል።-ቻይና፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካን እና የአውሮፓ ህብረት ጨምሮ በርካታ አገራት በሁለቱ ወገኖች መካከል እየጨመረ ያለው ውጥረት እንዳሳስባቸው ገልጸዋል። የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የማክበርን አስፈላጊነትንም አስምረውበታል።-በተባበሩት መንግሥታት በሚካሄደው ስብሰባ ላይ በርካታ አባላት በቀጠናው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱን እንደሚያሳስባቸው እና ሁለቱም ወገኖች ጉዳዩን በውይይት እና በመተባበር እንዲፈቱት ያሰምሩበታል ተብሎ ይጠበቃል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ልክ የዛሬ 10 ዓመት፣ በዕለተ ሐሙስ እኤአ ጥቅምት 03 ቀን 2013፣ 368 ኤርትራውያን ስደተኞች በላምፔዱዛ የባሕር ዳርቻ በጀልባ አደጋ ሞቱ።-ሟቾቹ ከቀናት በፊት ጉዞ መጀመራቸውን በስልክ የነገሯቸው ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው “በሰላም ገብተናል” የሚል ምሥራች እየጠበቁ ሳለ ነበር በመላው ዓለም የመገናኛ ብዙኃን ይህ አስደንጋጭ ዜና ተሰማው።-ከላምፔዱዛ የባሕር ዳርቻ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የደረሰው አደጋ፣ በካሜራ እና በሕዝቡ ዐይን በመታየቱ ቢቢሲን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በአስከፊ አደጋ ማለቃቸውን ዘገቡ።-ከአደጋው በሕይወት መትረፍ የቻሉትን ኤርትራውያን አድሃኖም ፍትዊ፣ እስክንድር ገብሪት እና አብርሃለይ አማረ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሱታል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-ሦስቱም ስደተኞች ጣልያን ላምፔዱዛ የምታደርሳቸውን ጀልባ ከመሳፈራቸው በፊት አገራቸውን ጥለው፣ ቤተሰቦቻቸውን ተሰናብተው መጀመሪያ የተሰባሰቡት ሱዳን ነበር።-አሰባሳቢዎቻቸው ደግሞ ከእያንዳንዳቸው ጠቀም ያለ ገንዘብ የተቀበሉ ሕገ ወጥ ደላሎች ናቸው።-በሰሃራ በረሃ ላይ ካደረጉት አስቸጋሪ ጉዞ በኋላ፣ ከ500 በላይ ስደተኞችን ባሳፈረው ጀልባ የሜዲትራንያንን ባሕር አቋርጠው፣ ሰላምና ፀጥታ በሰፈነባቸው የአውሮፓ አገራት ሕይወታቸውን ለመለወጥ አቅደው ነበር።-ምንም እንኳን ሁሉም ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ምክንያቶች ቢኖራቸውም፣ እያንዳንዱ ደግሞ የራሱ የሆነ ልዩ ታሪክ አለው።-በእርግጥ ከሊቢያ የባሕር ዳርቻ ላምፔዱዛ ለመድረስ የሁለት ቀን የባሕር ላይ መንገድ ሲሆን፣ ፀሎት እና ዕድል ካልታከለበት ባሕሩ ውጦ የሚያስቀር ሰፊ መቃብር ነው።-እነ አድሃኖም ወደ ላምፔዱዛ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት፣ ዋዜማው ላይ በርካቶች በተስፋ እና በጭንቀት ተሞልተው እንደነበር ያስታውሳሉ።-ጣልያን ባሕር ዳርቻ የምታደርሳቸው ጀልባ እስክትሞላ ድረስ “መዝርዓ” እየተባሉ በሚጠሩ የባሕር ዳርቻ መንደሮች ላይ ተሰባስበው ነበር።-በርከት ያለ ተሳፋሪ ከተሰባሰበ በኋላ ያቺ ተለቅ ያለች ጀልባ ወደ ባሕር ዳርቻው እየተጠጋች መጣች።-የሊቢያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች እንዳያገኙዋቸው፤ በቶዮታ መኪና እያስጠጉ ነበር የሚያሳፍሩዋቸው።-እነ አድሐኖም ወደ ጣልያን የምታደርሳቸውን የአሳ አጥማጆች ጀልባ ከመሳፈራቸው በፊት ወደ ፈጣርያቸው ፀሎት ማድረሳቸውን ያስታውሳሉ።-በሜድትራኒያን ባሕር ሞት በሽ ነው። ስደተኞች በሰላም አውሮፓ ተሻገሩ ብቻ ሳይሆን ጀልባው ተገልብጦ ሰጥመው ሞቱ የሚል ወሬ በሁሉም አፍ ላይ ቤቱን ሰርቷል።-ይህንን የሚያውቀው አብርሃለይ ፍርሃት አድሮበት እንደነበር ያስታውሳል። ፍርሃቱ ግን ተስፋ ያረገዘ ነው።-“ጉዞ የምትጀምርበት ዋዜማ ላይ ተስፋ እና ፍርሃት ይፈራረቅብሃል። በሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ብዙ ጊዜ አደጋዎች እንደሚኖሩ እናውቃለን፤ ስለዚህ በአንድ በኩል ፈርተንም ቢሆን በሰላም እንድንገባ እንመኛለን” ይላል አብርሃለይ በወቅቱ የነበረውን እያስታወሰ።-አብርሃለይ ሁሉንም ነገር ለፈጣሪ ሰጥቷል። አምላኩን ደጋግሞ እየጠራ በሰላም ደረቅ መሬት ላይ እንዲደርሱ ይጸልይ ነበር።-አብርሃለይ 500 ያህል ስደተኞችን እንደያዘች በተገመተችው ጀልባ ላይ የተሳፈረው በዚህ ስሜት ነው።-እስክንድር በበኩሉ “በፈጣሪ ኃይል ሁሉንም ነገር እንወጣዋለን” ብሎ ያምን እንደነበር ያስታውሳል።-ጀልባዋ ከአፍ እስከ ገደፏ በርካታ ሰዎች ጭና ትንሽ ከተንቀሳቀሰች በኋላ ካፕቴኑ ደላሎችን ጠርቶ ጀልባዋ ሚዛን ስለሳተች የተወሰኑትን እንዲቀንሱ ጠየቃቸው።-ደላሎቹም ባልተወለደ አንጀታቸው በዱላ እየቀጠቀጡ እና እየገረፉ 26 ሰዎችን አውርደው በትናንሽ ጀልባዎች ወደ ባሕር ዳርቻው መለሷቸው።-ወደ ላምፔዱዛ የተሳፈሩትን 518 ተጓዦችን የሚያመሳስላቸው በሰላም ጣልያን ገብተው ለመማር፣ ቤተሰብ ለማፍራት እና ሕይወታቸውን ለመለወጥ ማለማቸው ነው።-ሁሉም በየፊናው ወደ አምላኩ መፀለዩም፣ በአሳ አጥማጆች ጀልባ ላይ ተሳፍረው የሚጓዙ ስደተኞችን የሚያመሳስላቸው ሌላው ነጥብ ነው።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-እስክንድር “አውሮፓ ልግባ እንጂ ተምሬ እና ሰርቼ ሕይወቴን እቀይራለሁ” የሚለው ሕልሙ ሩቅ እንዳልሆነ ሲሰማው ተደሰተ።-ከፊት ለፊቱ የነበረው እና ጩራ የተባለ ወጣት በቀጥታ ወደ እሱ መጥቶ “እስክንድር፣ አንተ ተወዳጅ ሰው ነህ” ሲለው “ይሄ ልጅ ምን ሆነ?” ሲል ራሱን ጠየቀ።-ብዙም ሳይቆይ ሌላ ስደተኛ ከኋላው መጥቶ፣ “እስክንድር ሲጋራ ካለህ ለሁሉም ስጥ፣ ዶላር ካለህም ጣለው፤ አይጠቅምህም” ሲለው “ሰዉ ምን ሆኗል?” ብሎ መገረሙን ያስታውሳል።-ሕገ ወጥ የሰዎች አሸጋጋሪዎች 518 መንገደኞችን ከእንጨት በተሰራች ጀልባ በመጫን፣ ስደተኞቹን እየደበደቡ እና እያንገላቱ ጉዞው ተጀመረ።-ሌሊቱን በሙሉ ሰላማዊ ጉዞ ነበር፤ ለፈጣሪያቸው ምስጋና እያቀረቡ ሳለ ከርቀት የሚፍለቀለቅ ብርሃን በመመልከታቸው ላምፔዱዛ መድረሳቸው፣ ወደ ደረቅ መሬት መቅረባቸው ተነገራቸው።-ስደተኞቹም የከተማዋን መብራት አይተው “ገባን!” አሉ።-አንዳንዶቹ በደስታ እየጮኹ ዘመሩ።-ሌሎች ደግሞ ጣሊያን ውስጥ አሻራ ትተው ቀጣዩ ጉዟቸው እንዳይሰናከል፣ በተከታይነት ማድረግ ስላለባቸው ነገር ያስቡ ነበር።-“የላምፔዱዛን ከተማ መብራቶች ስናይ ‘ገባን’ አልን። በጉዞው ደክመን ነበር፤ ብዙዎቻችን ደግሞ በነበርንበት ተኝተን ነበር” ይላል አድሃኖም።-የደስታቸው ሰበብ ላምፔዱዛ በአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ላይ መሆኗ ብቻ አይደለም።-በርካቶቹ እዚህ ለመድረስ የራሳቸውን ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቻቸውን ጥሪት አሟጠዋል።-ከሊቢያ ብቻ ወደ ጣልያን ለመሻገር እያንዳንዳቸው 1600 ዶላር ከፍለዋል።-ከሰላሳ ስድስት ሰዓታት የማያቋርጥ አደገኛ የባሕር ላይ ጉዞ እና የጋዝ ሽታ በኋላ በርቀት የአውሮፓ መሬትን ሲመለከቱ በተወሰነ መልኩ የቅዠታቸው መጨረሻም መስሏቸው ለመውረድ ዝግጅት የጀመሩም ነበሩ።-ካፕቴኑ የጀልባዋ ሞተሩን አጥፍቶ የጣልያን ባህር ጥበቃዎች ገፍተው እንዲያስገቧቸው እየተጠባበቁ ነበር።-በጀልባዋ በላይኛው ክፍል ላይ የነበሩት ብርድ ልብሳቸውን ለብሰው ተቀምጠው የነበረ ሲሆን፣ የተወሰነም ንፋስ ነበረው።-የታችኛው የጀልባው ክፍል ተጨናንቋል፤ የባሕሩ ሽታ እያጥወለወላቸው በርካቶችም ታጉረዋል። በዚህም ወቅት ነው የባሕሩ ውሃ ወደ ጀልባዋ መግባት የጀመረው።-በወቅቱ የነበሩ የዐይን እማኞችም እንደሚናገሩት ካፕቴኑ ከላይኛው የጀልባው ክፍል ወደ ታችኛው ወርዶ ሞተሩን ሊያስነሳ ቢሞክርም እምቢ አለው።-የተጨነቀው ካፕቴን ጋዝ ብርድ ልብስ ላይ አርከፍክፎ ባሕር ዳርቻው ላይ በማሳየትም ትኩረት ለመሳብ እና እርዳታ ለማግኘት ሞከረ።-ሆኖም ያ ከመሆኑ በፊት እሳቱ እጁን ስላቃጠለው ጣለው። እሳት ጀልባው ላይ መንደድ ጀመረ። ተኝተው የነበሩ ስደተኞች በጩኸት እና በእሳቱ በድንጋጤ ተነሱ። በስደተኞች የታጨቀችው ጀልባም በረብሻ፣ በጩኸት እና በዋይታ ተሞላች።-በርካቶች ከእሳቱ ለማምለጥም ሲሞክሩ እና ሲረጋገጡ ጀልባዋም እያጋደለች መስመጥ ጀመረች። በታችኛው የጀልባዋ ክፍል የነበሩትም የመትረፍ ዕድል አልነበራቸውም።-ከላይ የነበሩት ደግሞ ወደ ባሕሩ ተወረወሩ፤ የተወሰኑት በደመ ነፍስ ጀልባዋን የሙጥኝ ብለው ለመትረፍ ሞከሩ።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-አብርሃለይ እሳቱ እና ጩኸቱ ሲባባስ እንቅልፍ ላይ ስለነበረ ህልም መስሎ ተሰማው።-ሰዎች ከእሳት ለማምለጥ ወደ ባሕሩ ዘለው ሲገቡ፣ ዋኝቶ የማያውቀው አብርሃለይ ደነገጠ፤ ፈራ።-“አምላኬ ሆይ ራስህ አድነኝ!” ብሎ ጀልባው ውስጥ ለረጅም ጊዜ መቆየቱን እና ዘግይቶ ወደ ባሕሩ መግባቱን ያስታውሳል።-“ከዚያ ጩኸት ብቻ ሆነ፤ ምንም የማደርገው ነገር ስላልነበረ ዝም ብዬ እጮኻለሁ። ሁሉም ሰው ይጮሃል። አንዳንዶቹ እንዳይደክምህ ዝም በል ይሉኛል። . . . በመጨረሻ ግን ባሕር ላይ መሆኔን ረስቼ ቤተሰቦቼ ይታዩኝ ጀመር። በማዕበሉ እየተገፋሁ ሀሳብ ውስጥ ሰመጥኩ። በመጨረሻም በእግዚአብሔር ቸርነት ተረፍኩ።”-አድሃኖም በበኩሉ ሁኔታውን ሲያስታውስ “ደክሞኝ ነበር፣ ሰው ሁሉ ወደ ባሕር ሲገባ ልክ ወራጅ ውሃ ውስጥ እንደተሰበሰቡ ጊንጦች ሆንን። በጣም ደክሞኝ ስለነበር የተወረወረልኝን የነብስ ማዳኛ ጎማ እንኳን መያዝ አልቻልኩም። ነገር ግን በተዓምር ከዳኑት መካከል እንድሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር” ይላል።-እስክንድርም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚያስታውሰው።-“እግዚአብሔር ቀንህን ካልቆረጠው አትሞትም የሚለው አባባል እውነት መሆኑን ያመንኩት ያኔ ነው። ውሃ ውስጥ ገብተው የማያውቁ ሰዎች ይድኑ ነበር፣ ነገር ግን የቀድሞ የባሕር ኃይል አባላት እና ዋናተኞች ግን አልተረፉም” ሲል በሕይወት መትረፉን ከፈጣሪ ፈቃድ ጋር ያስተሳስረዋል።-የፎቶው ባለመብት YOSEPH AND ADHANOM-የላምፔዱዛን እልቂት በመገናኛ ብዙኃን ሲዘገብ የተጎጂ ቤተሰቦች እና የዓለም ማኅበረሰብ አሰቃቂውን አደጋ በጥልቅ ሐዘን ነበር ተከታተለው።-የተጎጂ ቤተሰቦች የወንድሞቻቸውን፣ የእህቶቻቸውን እና የልጆቻቸውን ሞት መርዶ ሰሙ።-ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሞክሩ የነበሩ ሰዎች ምስሎች፣ የአስከሬኖች ምስሎች፣ በእሳት የተቃጠለው ጀልባ ሲሰምጥ የሚያሳዩ ምስሎች በስፋት በመገናኛ ብዙኃን ታዩ።-“ትናንት አብረውን የበሉና የጠጡትን፣ ለወራት አብረውን የተጓዙትን፣ ብዙ ተስፋ እና ህልም ያላቸው፣ አንዳንዶቹ ቦርቀው ያልጠገቡ ህጻናት ድንገት ባሕር ላይ ቀርተው አስክሬናቸው ሲወጣ ማየት ከባድ ነበር” ይላል አድሃኖም።-ከጥቂት ቀናት በኋላ ከአደጋው በሕይወት መትረፍ የቻሉት ሰዎች ምን እንደተፈጠረ ለዘመዶቻቸው መንገር ጀመሩ።-እስክንድር ከስድስት ቀናት በኋላ ደቡብ ሱዳን ጁባ ወደ ሚገኘው ታላቅ ወንድሙ ስልክ ደውሎ በሕይወት መትረፉን ተናገረ።-“በሰላም ገብቻለሁ፤ ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በመጎዳታቸው መጥፎ ሁኔታ ላይ ነኝ” ብሎ ስልኩን ዘጋ።-አድሃኖም ግን ብዙ የቤተሰቡ አባላት ስለተጎዱ ሐዘኑ ከባድ ነበር። ቤተሰቦቹ የአድሃኖምን በሕይወት መትረፍ ከጓደኛው ነበር የሰሙት።-አብርሃለይ ደግሞ አዲስ አበባ ይኖር ወደ ነበረው ታላቅ ወንድሙ እና አሥመራ ወደ ምትገኘው እናቱ ደውሎ ከአደጋው መትረፉ ነገራቸው።-ዛሬ ከአስር ዓመታት በኋላ ክስተቱን ሲያስታውሱ ሁሉም አሰቃቂው አደጋ ትናንት የተከሰተ ያህል ነው የሚሰማቸው።-“የ369 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፎ እንዴት በሰላም ትኖራለህ?” ሲል አድሃኖም ያለበትን ሁኔታ ይናገራል።-ከሁሉም በላይ ተጎጂዎቹ የተለመደው የቀብር ሥነ ሥርዓት ሳይፈጸምላቸው በየቦታው መቀበራቸው እረፍት ይነሳዋል።-“የሟች ቤተሰቦች ልጆቻቸውን አልቀበሩም። ብዙ እናቶች የተከሰተውን ነገር አልተቀበሉትም፤ ልጄ የሆነ ቦታ ላይ ሆኖ ነው እንጂ ይኖራል እንደሚሉ እንዳሉ ስለምታውቅ እንዴት ተብሎ እረፍት ይገኛል?” ይላል።-አድሃኖም በአሁኑ ወቅት የሁለት፤ እስክንድር ደግሞ የሦስት ልጆች አባት ሆነዋል።-አብርሃለይ በቅርቡ ትዳር ለመመሥረት ሂደት ላይ ነው።
ጥንታዊቷ የስቶን ታውን ከተማ-በዛንዚባሯ ደሴት መዲና ታሪካዊቷ ስቶን ታውን ኮፍያቸውን ያጠለቁ ሙስሊም ሽማግሌዎች የሚያፈሉት ቡና መዓዛ በሩቅ ይጣራል።-ቡናቸውን በቀረፋ፣ ቅርንፉድ እና ዝንጅብል ቅመሞች በመቀመምም ካፈሉ በኋላ ከባልዲያቸው ሲኒ እያወጡ ቡናውን በአገሬው አጠራር 'ካሃዋ' ያድላሉ።-ሲኒዎቹ በሚያስገርም ሁኔታ ከኢትዮጵያ ጋርም ተመሳሳይ ናቸው። ሲኒው ብቻ ሳይሆን ዛንዚባራውያን “ሰውን ሰው ያደረገው ዕቁብ ነው” ይላሉ።-በስቶን ታውን ‘ጆስ ኮርነር’ በምትገኘው ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሙስሊም ወንዶች፣ ሼሆች ቡናቸውን ያጣጥማሉ።-የአረብ ሱልጣኖች መናገሻ፣ የፋርስ፣ የሕንድ፣ የአውሮፓ እና የአፍሪካ ሥልጣኔዎችን ባዋሃደችው የባሕር ዳርቻዋ የዛንዚባር የድንጋይዋ ከተማ የእንግድነት ስሜት የለም። አላፊ አግዳሚው ሰው ለመሆንዎ እውቅና በመስጠት ፈገግ ብሎ ይቀበልዎታል።-ይዘይርዎታል። ከየት እንደመጡ ታሪክዎትን ይጠይቃል።-በታሪካዊቷ የድንጋይ ከተማ (ስቶን ታውን) በእግራችን ስንረማመድም አንድ ጠና ያሉ ሼህ “እንኳን ከአቢሲኒያ በሰላም መጣችሁ አሉን?”-ቆም ብለውም በፈግታ “አቢሲኒያ እንዴት ናት?” ብለው ጠየቁን።-ስለ ሰሜኑ ጦርነት ጠቀሱልን፤ “ጊዜ ይቀየራል፤ አቢሲኒያ ታላቅ ናት” አሉን።-በውጭ አገራት የታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ አቢሲኒያ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ ከጥንቷ ዛንዚባር ጋር ግንኙነት ይኖራት ይሆን?-ለዘጠኝ ቀናት ባደረግነው የዛንዚባር ቆይታችንም በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን አቢሲኒያ እያሉ ሲጠሯትም ሰምተናል። ንጉሥ የሚባለው የአቢሲኒያ ስያሜ በዛንዚባር እንደሚታወቅና ነጃሺ እንደሚባሉ ሌላ መንገደኛም አጫወቱን።-በየመን ቢልቂስ በመባል የምትታወቀው ንግሥት ሳባም የአቢሲኒያ መሠረት እንዳላት የስቶን ታውን ነዋሪ ነግረውናል። የጥንቷ አቢሲኒያ ግዛት እስከ ዛንዚባር እና ሕንድ ውቅያኖስ እንደሚደርስ በአፈታሪክ ሲነገርም በተደጋጋሚ ቢሰማም ይህ ነው የሚባል የታሪክ ማጣቀሻ አላገኘንም።-በስቶን ታውን ‘ጆስ ኮርነር’ ቡና እየጠጡ ያሉ የእድሜ ባለጸጋ-አቢሲኒያ እንዴት ናት ወዳሉን እንመለስና ከኬንያ ናይሮቢ ለዘገባ እንደመጣን ነገርናቸው።-የቢቢሲ ጋዜጠኞች ከናይሮቢ ወደ ዛንዚባር የመጣነውም የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ታሪካዊ ንግግርን ለመዘገብ ነበር።-ተደራዳሪዎቹ ከኢትዮጵያ የ3 ሰዓት 42 ደቂቃ የአየር መንገድ ርቀት ያላትን በተፈጥሮ እና በታሪክ የታደለችውን ዛንዚባር ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተቀምጠው ግጭታቸውን በሰላም ለመቋጨት ለውይይት የመረጧት።-ከመንግሥትም ሆነ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኩል ታንዛንያ የትኛዋ ከተማ እንደሚካሄድ መረጃ ባይሰጥም ራስ ገዝ አስተዳደር በሆነችው ዛንዚባር ላይ ንግግሩ እንደሚካሄድ ሰምተን ሚያዝያ 18/2015 አቀናን።-ዛንዚባር ለመድረስ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚያጋጥማቸውን የቪዛ ጥያቄ እና የጉዞ መስተጓጎል በዚህ ጽሁፍ ላይ ወደ ኋላ መለስ ብለን የምናየው ይሆናል።-እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ በከፍተኛ ምስጢርነት የተያዘው ይህ ውይይትም በዛንዚባር የት እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ ቀናትን ፈጅቶብናል።-የፎቶው ባለመብት EMERALD-የድርድሩ ስፍራ - ኤመራልድ-በኬንያ እና በኖርዌይ አቀራራቢነት እየተካሄደ የነበረው ውይይት በሰሜናዊ ምሥራቅ ዛንዚባር በምትገኘው ሙዩኒ የባሕር ዳርቻ ላይ በሚገኘው ኤምራልድ ሪዞርት እና ስፓ እንደሆነ ሰማን።-ኤምራልድ በምሥራቅ አፍሪካ እና በሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ ያሉ የቅንጦት እና የመዝናኛ ሆቴሎች ስብሰብ ውስጥ ከሆነው አንዱ ሲሆን፣ በመስተንግዶ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ40 ዓመታት በላይ ልምድ ባለው በጣሊያኑ ስካራፒቺያ ቤተሰብ ነው የሚተዳደረው።-ኤመራልድ በዛንዚባር አስደናቂ ከሆነው የሙዩኒ የባሕር ዳርቻ በአንዱ አጠገብ ተንጣሎ ይታያል።-በርካታ ቱሪስቶች በጀልባ የሕንድ ውቅያኖስ አካል የሆነውን ደሴት ለማቋረጥ፣ ደሴቱን የሚከፍለውን ነጭ አሸዋ ለመመልከት፣ በጥልቀት ለመዋኘት እና ብርቅዬ የሆኑትን ሰማያዊ አሳዎችም ለማየት ይጎርፋሉ።-በውይይቱ ለመሳተፍም ሆነ ተሳታፊዎችን ለማግኘት ዕድሉ አልነበረም። ከመዲናዋ ስቶን ታውን በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይም ከሚገኘው ኤመራልድ ሪዞርት ኤንድ ስፓ ከሚገኝበት ሙዩኒ አጠገብም ሌላ ምኔባ የምትባል ደሴት ትገኛለች።-በስቶን ታውን የቢቢሲ ዘጋቢዎች ያገኙት በባሕር ዳርቻዎች ላይ የእግር ኳስ ውድድር (ቢች ፉት ቦል) የሚያዘጋጀው ላጢፍ ምኔባ “ይህ የማን ደሴት እንደሆነ ታውቂያለሽ?” ሲል ጠየቀኝ። በጥያቄ ዐይን ስመለከተውም “በዓለም ቱጃር የሆነው የቢል ጌትስ ደሴት ነው” አለኝ።-በዛንዚባር ቢል ጌትስ የራሱ ደሴት አለው?-ምኔባ የተሰኘችው ደሴት የግል ስትሆን ኤንድ ቢዮንድ የተሰኘ ቅንጡ ሪዞርት ይገኛል።-ወደ ደሴቲቱ እንደፈለጉ ዘሎ መግባት አይቻልም፤ የሪዞርቱ እንግዶች ወይንም በአስጎብኝዎች ከመጡ ብቻ ነው።-ቢል ጌትስም ሆነ ሌሎች ታዋቂ ቱጃሮች ደሴቶቹን በሊዝ እንደተከራዩዋቸው ቢነገርም ቢቢሲ ማረጋገጥ አልቻለም። በዛንዚባር ቆይታችን ምኔባ የተሰኘችው ደሴትን ቢል ጌትስ በሊዝ መከራየቱን ከበርካቶች ሰምተናል።-ምኔባ በርካቶች ከዶልፊን ጋር የሚዋኙበት እንዲሁም በጥልቀት ለመዋኘት የሚያስችለውን የመተንፈሻ መሳሪያ ገጥመው በሕንድ ውቅያኖስ ላይ የሚዋኙበት ነው።-የፎቶው ባለመብት and beyond Mnemba Island-ቢል ጌትስ በሊዝ ተከራይቷታል የምትባለው ምኔባ አይላንድ-ዛንዚባር ቱምባቱ፣ ኑንግዊ እና ኬንድዋ የሚባሉ ደሴቶች እና ምድራዊ ገነት የሚመስሉ የባሕር ዳርቻዎች አሏት።-እነዚህ ደሴቶች በአሁኑ ወቅት በየዓመቱ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ቱሪስቶችን የሳቡ ቢሆንም፣ በርካቶቹ የምሥራቅ አፍሪካ ባሪያዎችን ለማስቀመጥ፣ ለማሰር እና በሕንድ ውቅያኖስንም አሻግሮ ለመሸጥ እና ለመለወጥ ዋነኛ ማዕከላት ነበሩ።-በእነዚህ ደሴቶች ባሪያዎችን በማጋዝ የሚታወቁት ፖርቹጋልን በማሸነፍ ዛንዚባርን የተቆጣጠሩት የኦማን አረቦች ናቸው። የኦማን አረቦች መናገሻ እና መዲናቸውም ጥንታዊቷ የድንጋይ ከተማ - ስቶን ታውን ናት።-ጥንታዊቷ የስቶን ታውን ከተማ-በአረብኛ ማዲናት ዛንጂባር አል ሃራያ፣ በስዋሂሊ ምጂ ኮንግዌ ይሏታል - የዛንዚባሯን መዲና ስቶን ታውንን።-የድንጋይዋ ከተማ፣ የባሕር ዳርቻዋ መናገሻ የአረብ፣ የፋርስ፣ የሕንድ፣ የአውሮፓ፣ የአፍሪካ የኪነ ህንጻ አሻራዎች ይታዩባታል።-ኮራል በተሰኘው ድንቅ ድንጋይ የተገነባችው ስቶን ታውን ያለፈችባቸውን የምዕተ ዓመታት ታሪክን ግልጽ አድርጋ ታሳያለች።-በአምስት መቶ ዓመታት የተሰሩት ጥንታዊ የሱልጣኖች መናፈሻዎች፣ ቤተ መንግሥቶች፣ የባርያ መሸጫዎች እና ማሰቃያዎች፣ የጦር ምሽጎች መነካትም ሆነ ማፍረስ ጥብቅ ትዕዛዝ በመውጣቱ ጊዜ የቆመ ይመስላል።-ትልልቅ የጣውላ በሮቿ በብር እና በመዳብ አሁንም እንዳጌጡ ነው። በበሮቹ ላይ የሕንድ እና የአረብን ኪነ ጥበብ መራቀቅ የሚያሳዩ የቁርዓን ጥቅሶች እና አበባዎች ተቀርጸዋል። እንዲሁም በበሮቹ ላይ ከነሐስ የተሰሩ ጉጥ መሳይ የተገጠመላቸው ሲሆን ይህም ዝሆንን ለመከላከል እንደሆነም የአካባቢው አስጎብኚዎች ይናገራሉ።-በኪነ ህንጻዋ ብቻ ሳይሆን ነዋሪዎቿም የአረብ፣ የሕንድ፣ የፋርስ፣ የአውሮፓ እና የአፍሪካ ውህድ ማንነት ይዘዋል።-መኪና በማያሳልፉ ጠባብ መንገዶች ሲረመማዱ በታሪክ ወደ ኋላ የተመለሱ ይመስላል። በየሰዓቱም ከየመስጊዱ የሚወጡት በመወረዋ ድምጽ የሚወጡት አዛኖች ልብን ያማልላሉ።-ስቶን ታውን ያላት ኪነ ህንፃም ሆነ የታሪክ አሻራ የሚያስደምም ቢሆን በጨለማም ታሪክ የተሞላ ነው። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ባሪያዎችም ተገብረውባታል።-ስቶን ታውን በዓለም አቀፍ ደረጃም የመጨረሻዋ ክፍት የባሪያ ገበያዎች አንዷ ነበረች። ብሪታንያን ጨምሮ አውሮፓውያኑ ባሪያን እንደ እቃ መሸጥ እና መለወጥ ካቆሙ በኋላም ቢሆን እስከ አውሮፓውያኑ 1873 ድረስ ክፍት ነበር።-ባሪያዎቹ ሜይን ላንድ (ዋና ምድር) ተብሎ ከሚጠራው ከታንዛንያ እና ከሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ታጭቀው ይመጣሉ። በጉዞም ላይ የሚታመሙ እና ሰምጠው ውሃ የሚባላቸው በርካቶች ነበሩ።-በአሁኑ ወቅት የእንግዶች ማረፊያ በሆነው ሴንት ሞኒካም በርካታ ሴቶች እና ህጻናት ምንም አየር እንዲሁም መጸዳጃ በሌለበት ሁኔታም ታጉረው ይጋዙ ነበር።-ስቶን ታውንን ያስጎበኘን ኦማር እንደነገረን ባሪያዎቹ ወደ ውጭ ወጥተው በአካል መጠናቸው እንዲሰለፉ ይደረጋሉ። ጥንካሬያቸውንም ለመፈተሽም ከዛፍ ላይ ታስረው ደም በደም እስኪሆኑ ይገረፋሉ።-ያላለቀሱ ወይንም ራሳቸውን ስተው ያልወደቁ ዋጋቸው ከፍ ባለ ሁኔታ ለሽያጭ ይቀርባሉ።-የባሮች ክፍት ገበያ በነበረው ስፍራ የአንግሊካን ካቴድራል የክርስቶስ ቤተክርስቲያን-በአሁኑ ወቅት ይህ የባሮች ክፍት ገበያ በነበረው ስፍራ የአንግሊካን ካቴድራል የክርስቶስ ቤተክርስቲያን (ክራይስት ቸርች) ቆሟል። የመግረፊያው ቦታም መሰዊያ በሚመስለው የቤተ ክርስቲያኑ በኩል የባሪያዎቹን ደም ለማመልከት ቀይ ቀለም ተቀብቶ በነጭ እምነበረድ ተከቧል።-በአፍሪካ ውስጥ በሚሲዮን መልዕክተኛነቱ የሚጠቀሰውን የስኮትላንዱ ዴቪድ ሊቪንግስተንንም ይህ ስፍራ ይዘክረዋል። ሕይወቱ በዛምቢያ ካለፈ በኋላ አስከሬኑ ወደ ትውልድ መንደሩ ቢላክም ልቡ በአንድ መንደር ተቀበረ።-ልቡ በተቀበረበትም ስፍራ በበቀለ ዛፍ የተሰራ መስቀልም በቤተ ክርስቲያኑ እንደተሰቀለ አስጎብኚያችን ኦማር ነገረን።-በርካታ ቱሪስቶች ከሚጎበኙት ይህ ስፍራ ውጪም የባሪያዎችን ስቃይ የሚያሳይ በካቴና እና በሰንሰለት የተጠፈሩ ሃውልቶች ይታያሉ።-የባሮች ክፍት ገበያ የባሪያዎችን ስቃይ የሚያሳይ በካቴና እና በሰንሰለት የተጠፈሩ ሃውልቶች-በስቶን ታውን ሌላኛዎቹ ታሪካዎቹ ስፍራዎች የሱልጣኖች ቤተ መንግሥት የነበረው ‘ፓላስ ሙዝየም’፣ እንደ የጦር ሰፈር ወይም ሱልጣኖች ምሽግነት የሚጠቀሙበት ኦልድ ፎርት እንዲሁም በዛንዚባር የመጀመሪያው ኤሌክትሪክ የገባለትና በምስራቅ አፍሪካ አሳንሰር የተገጠመለት ሃውስ ኦፍ ዋንደርስ ቤተ መንግሥት ተጠቃሽ ናቸው።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-እንደ የጦር ሰፈር ወይም ሱልጣኖች ምሽግነት የሚጠቀሙበት ኦልድ ፎርት-ስለ ስቶን ታውን ስናወራ በሕንድ ውቅያኖስ ስለተከበበችው ፎሮዳኒ ፓርክ ወይም የአትክልት ስፍራ አለመጥቀስ አይቻልም።-ዛንዚባር የደረስነው በአምስተኛዋ የኢድ በዓል ዕለት ነበር።-ምንም እንኳን 55 ሚሊዮን የሚሆነው የታንዛንያ አብዛኛው ሕዝብ ክርስቲያን ቢሆንም፣ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉት የዛንዚባር ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ሙስሊሞች ናቸው።-እንደ ዕድል ሆኖ በዓመቱ ትልቅ ክብረ በዓል በሆነው እና የዛንዚባር ሕዝብ በፈንጠዝያ በሚሞላበት የኢድ አል ፈጥር በዓል አካባቢ ነው የደረስነው። በዛንዚባር የኢድ በዓል ለአምስት ተከታታይ ቀናት ነው የሚከበረው።-በታንዛንያ የሚገኙት የቢቢሲ ጋዜጠኞችም ወደዚህች ስፍራ ዕራት እንድንበላ እና እንድናይ ጋበዙን።-በኢድ በመጀመሪያው ቀን ህጻናት ከቤት ቤት እየዞሩ በር እያንኳኩ ገንዘብ ይጠይቃሉ፤ ምናልባትም ከቡሄ ወይም ከአሸንዳ ባህል ጋር ተመሳሳይ ይመስላል።-ህፃናቱ ነጭ ካንዙ የተሰኘ ቀሚስ ለብሰው ኮፍያቸውንም አጥልቀው ይዞራሉ። የኢድ ገንዘብም ይበረከትላቸዋል። ሁሉም ቤተሰቦች ለህፃናቱ ገንዘብ መስጠት የባህሉ አካል እንደሆነ ላጢፍ ነገረን።-በስቶን ታውን ፎሮዳኒ አካባቢ የሚገኙ ሆቴሎች-ከተማዋ በርችት ትደምቃለች። የከተማው ሁሉ ሰው ውጭ ያለ በሚመስል ሁኔታ በጠባቦቹ የስቶን ታውን መንገዶች አዳዲስ መኪኖች ጥሩምባቸውን እየነፉ፣ በፒክ አፕ መኪኖች የተጫኑ ሙስሊሞች በሳቅ እና በደስታ መንገዱን አጥለቅልቀውታል።-ህጸናት እጅ ለእጅ ተያይዘው ምግብ ያማርጣሉ። በርካታ እህት እና ወንድማቾች ሰብሰብ ብለው ታዋቂ ከሆነው እና ቱሪስቶች ከሚበዙት ኬፕታውን ፊሽ ማርኬት የሚወጣውን ሙዚቃ እየሰሙ፣ በህንድ ውቅያኖስ በተከከበበችው፣ በጀልባዎች እና በመርከቦች በታጀበችው ፎሮታኒ ፓርክ በዓሉን ያከብራሉ።-ትልቅ ስፍራን በሚሸፍነው ፎሮታኒ ፓርክ ከሚበስለው ምግብ የሚወጣው ጭስ ምራቅ ያስውጣል። የሚጠበስ አክቶፐስ ከካሳቫ ጋር፣ በዝንጅብል የታጠበ የሥጋ ጥብስ፣ ታዋቂው እና የእንቁላል ኦምሌት የሚመስለው የዛንዚባር ፒዛ፣ ዋሊ ና ማሃራጌ (ባቄላ ሩዝ ከኮናት ጋር ተቀላቅሎ)፣ ሺሽ ክበብ የሚመስለው በቅመም ያበደው ሚሽካኪ፣ ጣፋጭ ከፈለጉ ደግሞ ዶናት መሳዩ ቪቱምባ ተሞልቷል።-ትንሽ በፓርኩ ውስጥ ተረማምደን ከምግብ ምግብ እያማረጥን ቺክን ሺዋርማ ወስደን እንዲሁም የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ከሚንት ጋር የተቀላቀለ የሚጠጣ ይዘን በባሕር ዳሩ ቁጭ አልን። የእነዚህ ትንንሽ የጎዳና ላይ ሬስቶራንቶች ምግብ ቸርቻሪዎች ገንዘብ አይጠይቁም፤ በእምነት ዝም ብለውን ነው የሚሰጡት።-የቢቢሲው የታንዛንያ ባልደረባችን ምግቡን አጣጥማችሁ ከበላችሁ በኋላ ተዝናንታችሁ ስትጨርሱ መጥታችሁ እንደምትከፍሉ ያውቃሉ አለን።-ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎቹም ዛንዚባራውያን በፎሮታኒ ያሉ ክፍት ሬስቶራንቶች ገንዘብ መጀመሪያ አይጠይቁም። እየተገረምን በአካባቢው እየዘለሉ በሕንድ ውቅያኖስ የሚዋኙ ወጣቶችን እየተመለከትን በባሕሩ ድምጽ፣ በኢድ መንፈስ እና በዛንዚባራውያን የሚጋባ ደስታ እና በመርከቦች እና ጀልባዎች ድምጽ ታጅበን ምግባችንን አጣጣምን።-ዛንዚባራውያን አላፊ እና አግዳሚውን ሰላም እንዳሉ ነው። እንዲሁ መንገድ ላይ የሚያዋራችሁ ሰውም አታጡም። ትህትናቸውም ለየት ያለ ነው።-የቢቢሲው ባልደረባችንም ቀልድና ቁም ነገር በታጀበ መልኩ ፖሊሶች ወንጀለኛን በቁጥጥር ስር ሲያውሉ “እባክህ እጅህን በካቴና እንሰረው?” ብለው ጠይቀው ነው አለን። ባልደረባችን ቀልድ እንዳልሆነ ነገረን። እንግዲህ ይሁን አልን።-ለትህትናቸው፣ ቀለል ማለታቸው፣ ሁሉን ነገር ረጋ ባለ ሁኔታ ስለማከናወናቸው ለሰላምተኝነታቸው ብዙም ርቀን መሄድ አላስፈለገንም፤ ለሰውነታችሁ እውቅና የሚሰጣችሁ ሕዝብ እና ስፍራ ነው ዛንዚባር።-ፎሮዳኒ-ቱሪስቶች እንደሚጎበኟቸው ሌሎች የባሕር ዳርቻዎች የወሲብ ንግድ በዛንዚባር በከፍተኛ ሁኔታ የተዛመተ ነው።-በተለይም ቱሪስቶች በሚያዘወትሯቸው ደሴቶች እንዲሁም በስቶን ታውን ታዳጊ ወንዶችን ከነጭ ሴቶች ጋር ማየት የተለመደ ነው። ቢች ቦይስ (የባሕር ዳርቻ ታዳጊ ወንዶች) የሚል ስያሜ የተሰጣቸው እነዚህ ታዳጊዎች በዕድሜያቸው የሚበልጧቸውን ሴቶችን ከተማዋን ያስጎበኟቸዋል፣ አብረው ቀንም ሆነ ምሽት ይዝናናሉ።-ከነጮቹ ሴቶች ገንዘብ እንዲሁም በተለያዩ ስፍራዎች ያሉ መዝናኛቸውን ይከፍሉላቸዋል። አንዳንዶቹም ወደ ውጭ አገራት እንደሚወስዷቸው ነገረን።-በስቶን ታውን ታዋቂ በሆኑት ሬስቶራንቶችና የምሽት ክበቦች ፓታሙ (ታቱ)፣ ሲክስ ዲግሪስ ሳውዝ፣ አፍሪካ ሃውስ እና ቢች ሃውስ ከቀኑ ለየት ባለ መልኩ ታዳጊ ወንዶች ከትልልቅ ነጭ ሴቶች ጋር ሲሳሙም ይታያል።-በበርካቶቹ የምሽት ክበቦች ኮኬይንን የመሳሰሉ አደንዛዥ ዕጾችም የተለመዱ ናቸው። በግልጽም መግዛት ይፈልጉ እንደሆነ ሲጠይቁ ይሰማል። መጠጥ ነውር በሆነባት ዛንዚባር በተለየ መልኩ መጠጥ ይንቆረቆራል። በአንዳንድ ሬስቶራንቶች ታዳጊ ሴቶችን በዕድሜ ጠገብ ካሉ ፈረንጅ ወንዶች ጋር ማየትም የተለመደ ነው።-የምሽት ህይወት በስቶን ታውን-የዛንዚባር የምሽት ሕይወት ደመቅ ያለ ነው። ስቶን ታውን ሌቱ አይነጋባትም። የዛንዚባር ታራብ እና ቦንጎ ፍሌቫ፣ አፍሪካን ያጥለቀለቃትን የደቡብ አፍሪካው አማፒያኖ፣ የናይጄሪያው አፍሮ ቢትስ እና የጃይማካው ሬጌ ዳንስ ሆል የምሽቱን ታዳሚ ያወዛውዙታል። የዛንዚባርን ሙዚቃ በዓለም የሙዚቃ መድረክ እንዲታወቅ ያደረገችውን ቢ ኪዱዴን እንዴት ዛንዚባራውያን እንደሚኮሩባት ይናገራሉ።-በየዓመቱ አገሪቷን የሚጎበኙት ኦማኖች ወደነዚህ መጠጥ ቤቶች ባይሄዱም በርካታ ሺሻ ቤቶችን ያዘወትራሉ። ስቶን ታውን በእነዚህ ሁሉ ቱሪስቶች ትጨናነቃለች።-ዛንዚባርን በጎበኘንበት ወቅት የቱሪስቶች ቁጥር አነስተኛ በሆነበት ወቅት ነበር። ሆኖም አንዳንድ ያልተለመዱ ነገሮችን ተመልክተናል።-ባረፍንበት ታሪካዊው እና መቶ ዓመታትን ባስቆጠረው ዳው ፓላስ ሆቴል በነጻ ቁርስ የምትበላ እና ቤት አልባ የሆነች ፈረንጅ ሴት አጋጥማናለች።-የሆቴሉ ምክትል አስተዳደር ቤት የሌላቸው ፈረንጆች ወደ ሆቴሉ እንደሚመጡና አንዳንዴም በሆቴሉ የመጨረሻ ፎቅ ባለው ክፍት ቦታ ላይ ሲያድሩ እንደያዟቸው ነገረን። ይህ ብቻ ሳይሆን በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ፈረንጅ ሴቶችም አሉ አለን።-የዛንዚባርን ሙዚቃ በዓለም የሙዚቃ መድረክ እንዲታወቅ ያደረገችውን ቢ ኪዱዴን-በአፍሪካ ቁንጮ የቱሪስት መዳረሻ የሚል ስያሜ የተሰጣት እና በውብ ደሴቶቿ የምትታወቀው ዛንዚባር ባለፈው ዓመት 600 ሺህ የሚሆኑ ቱሪስቶችን ተቀብላ ነበር።-ሕዝቧ ሙሉ በሙሉ ሙስሊም በሆነባት ዛንዚባር መሸፋፈን አስገዳጅ ባይሆንም፣ በበርካታ አካባቢዎች ባህሉን እና አገሪቷን ባከበረ መልኩ እንዲለብሱ የሚያስታውሱ ጽሁፎች እዚህም እዚያም ተለጥፈዋል።-በሪዞርቶች እና በሆቴሎች አካባቢ የመዋኛ ልብሶችን መልበስ ቢቻልም እንደ ስቶን ታውን ባሉ አካቢዎች ግን እነዚህ አለባበሶች አይበረታቱም። ከሁለት ዓመታት በፊት የዛንዚባር ቱሪዝም ሚኒስትር በአደባባዮች እርቃን የወጣ ሰው 2 ሺህ ዶላር አስጎብኚዎችን እንደሚቀጣ አስጠንቅቋል።-ይህም በርካቶች ምንም አይነት እራፊ ጨርቅ ሳይጥሉ እርቃናቸው በመታየታቸው ነበር።-በተጨማሪም አልኮል በሕዝብ አደባባዮች ላይ መጠጣት እንዲሁም መሳሳም ሆነ የትኛውንም የተቃራኒ ጾታ ፍቅር ማሳየት ነዋሪዎችን ሊያስቆጣ ስለሚችልም አገሪቷን የሚጎበኙ ቱሪስቶች ከዚህ እንዲቆጠቡ ይመከራሉ።-የፎቶው ባለመብት SM-በዛንዚባር የተካሄደውን የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ውይይት ለመዘገብ ከናይሮቢ ስንነሳ አስበን የነበረው ቪዛ በምንደርስበት ወቅት እንደምናገኝ ነበር። ነገር ግን ለኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲደርሱ እንደማይቻል እና የታንዛንያም ኢሚግሬሽን ቪዛ ካላገኙ እንዳታሳፍሯቸው የሚል ትዕዛዝ እንደተሰጣቸውም ከናይሮቢ ተነገረን።-ቢቢሲ ለኬንያም ሆነ ለታንዛንያ ኢሚግሬሽን የጻፋቸው የትብብር ደብዳቤዎች ትርጉም ስላልነበራቸው ያቀድነው በረራ አመለጠን። በዚያኑ ቀን ቪዛ አግኘተን ወደ ዛንዚባር ብናቀናም ቪዛ ማግኘት ለኢትዮጵያውያን እንዲህ የጠበቀበትን ምክንያት መጠየቃችን አልቀረም።-በታንዛንያ የሚዲያ ምናብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሲባል ጎልቶ የሚሰማው ስደተኞች ብቻ ናቸው የሚለው ነው። ይህንንም ለማየት ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግም። ኢትዮጵያውያን በታንዛንያ ብሎ ጉግል ላይ ቢፈልግ በርካታ አሰቃቂ ዜናዎች ይወጣሉ።-በጭነት መኪና ታፍነው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ በተጨናነቀ አውራ ጎዳና ላይ አስከሬናቸው ተጥሎ መገኘት፣ መውጪያ ያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ በሕገወጥ መንገድ ሲገቡ የተገኙ ኢትዮጵያውያን እስር፣ ፍርድ ቤት መቅረብ፣ ወደ አገር መጋዝ፣ አፈና፣ ሕገወጥ የሰው ዝውውር እና ሌላም ሌላም ሞልቶታል።-አንዳንዶች ኢትዮጵያውያንም አስደንጋጭ ታሪክ ሲናገሩም ይሰማል። በዛንዚባር ያገኘናት ኢትዮጵያዊት በአንድ ወቅት በሕገወጥ መንገድ ገቡ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሲያዙ የዘጠኝ ዓመት ልጅ አግተው አንለቅም ማለታቸው ተሰምቷል።-ምናልባት በርካታ ስደተኞች ታንዛንያን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ መሻገሪያ አድርገው መጠቀማቸው የኢሚግሬሽን እና የቪዛ ፖሊሲው ላይ ተጽእኖ አሳርፏል ማለትም ይቻላል። ሆኖም በመጨረሻ አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከበረረን በኋላ አቤይድ አማኒ ካሩሜ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደረስን።-የፎቶው ባለመብት Airport Technology-አቤይድ አማኒ ካሩሜ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ-አየር ማረፊያው የተሰየመው ለ500 ዓመታት ያህል በአረቦች በበላይነት እና ሚሊዮኖች እንደ እቃ የተለወጡባት እና የተሸጡባትን የባርያ ንግድ እንዲከትም ያደረገውን አብዮት ተከትሎ አገሪቷን በመጀመሪያ ፕሬዚዳንትነት የመሩት አቤይድ አማኒ ካሩሜ ስም ነው።-የዛንዚባር የመጨረሻው ሱልጣን ሰር ጃምሺድ ቢንን የገረሰሰው አብዮትም በዛንዚባር ውስጥ ስር ነቀል ለውጥ ላመጡት አቤይድ አማኒ ካሩሜ በር ከፈተ።-በአውሮፓውያኑ ጥር 1964 አብዮቱ ከተቀሰቀሰ ከሦስት ወራት በኋላ የተባበሩት የታንዛንያ ሪፐብሊክ ተመሠረተች። የኅብረቱም መሪ ሶሻሊዝምን በአፍሪካዊ መንገድ የቃኙት እና ተራማጅ የሚባሉት የታንጋኒካው መሪ ጁሊየስ ኔሬሬ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሆኑ። ካሩሜ ኅብረቱን መቃወምም ሆነ መንካት እንደ ክህደት በሚታይባት ታንዛንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆኑ።-ካሩሜ በፓርቲያቸው አፍሮ ሽራዚ ዋና መሥሪያ ቤት ባኦ የተሰኘውን የሙዚቃ መሳሪያ ሲጫወቱ አራት ታጣቂዎች ተኩሰው ገደሏቸው።-ካሩሜ በሥልጣን ዘመናቸው የአረቦች እና የሕንዶችን መሬት ወደ አገሪቱ ብሔራዊ ሃብት በማስገባት ለበርካታ መሬት አልባ ዛንዚባራውያን አከፋፋለዋል።-ሌላኛው ከመቃብር በላይ የነገሰው ስማቸው እና ጥለውት ያለፉት አሻራቸው ቀለም እና ዘር ሳይለዩ ነጻ የትምህርት እና የጤና አገልግሎት ሥርዓት መዘርጋታቸው ነው።-ለዛንዚባር ትልቅ ራዕይ ነበራቸው የሚባሉት አብዮተኛው መሪ፣ በተለይም ንጋምቦ በተሰኘችው በቀድሞ ባሮች በተቆረቆረችው ከተማ ምቼንዚ በሚባለው ሰፈር በሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም የተቃኙ ቤቶችን መገንባታቸው ነው።-የፎቶው ባለመብት WIKI-ዛንዚባርን በመጀመሪያ ፕሬዚዳንትነት የመሩት አቤይድ አማኒ ካሩሜ-ካሩሜ አብዮተኛ ብቻ ሳይሆኑ አወዛጋቢም ነበር። በ1970 የ64 ዓመቱ ካሩሜ አራት የፋርስ ታዳጊዎች ሊያገቡት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በተለያዩ ባህሎች እና ዘሮች እንዳይጋቡ እንቅፋት ሆነዋል ያላቸውን አስር ወንድ ዘመዶቻቸው እንዲታሰሩ አድርገዋል።-እነዚህን እና ሌሎች ኢታንሼሪ የተሰኙትን የፋርስ ማኅበረሰቦችን ከአገር አስወጣችኋለሁ በሚልም አስፈራሩ። ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ ባደረጉት ተጽእኖ ክሱን ቢተዉትም ከወራት በኋላ አራት ሌላ የፋርስ ሴት ታዳጊዎች የአብዮታዊ ምክር ቤት አባላቱን እንዲያገቡ ተገደዱ። የእነዚህ ታዳጊዎች 11 ዘመዶችም እንዲታሰሩ እና እንዲገረፉ ተወሰነ።-ካሩሜ ስለዚህም ተጠይቀው ሲናገሩ “በቅኝ ግዛት ዘመን አረቦች አፍሪካዊ ዕቁባቶቻቸውን ዝም ብለው ይወስዳሉ፤ አያገቧቸውም ነበር። አሁን እኛ ነን ሥልጣን ላይ ያለነው። ሁኔታው ተቀይሯል” ማለታቸውን ታሪክ ያስታውሳል።-አዲሷ ወይም አብዮታዊቷ ዛንዚባር ኮሚኒስቶች እና የአፍሪካ አብዮተኞች እንዲሁም የታሪክ ታላላቆችን ለትምህር ቤቶቿ መጠሪያ፣ ለስታዲየሟ፣ ለሆስፒታሏ በመሰየም ትዘክራቸዋለች።-* ከእነዚህም ውስጥ ኮንጎ ከቤልጂየም ቅኝ ግዛት ቀንበር ከተላቀቀች በኋላ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት ፓትሪስ ሉምሙባ የተሰየመ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት-* ሶቭየት ኅብረትን የመሠረተው እና የመጀመሪያው መሪ አብዮተኛው እና ፖለቲከኛው በቭላድሚር ሌኒን የተሰየመ የማስታወሻ ሆስፒታል-* የኢትዮጵያ የሰለሞናዊው ስርወ መንግሥት የመጨረሻው ንጉሥ አጼ ኃይለ ሥላሴን ለማስታወስ የተቋቋመ የሕዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት-* ከነጻነት በኋላ የአልጀሪያ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት፣ የሶሻሊስት ወታደር እና አብዮተኛው በአህመድ ቤን ቤላም ስም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አቋቁማለች-* የቻይናን ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የመሠረቱት እና የቻይና ኮሚዩኒስት አብዮተኛው ማኦ ዜዶንግ ‘ሊቀ መንበር ማኦ’ ስምም ስታዲየምም ገንብታለች-ዛንዚባር ትልቋ የምሥራቅ አፍሪካ የባሪያ መሸጫ፣ መለወጫ ማዕከል ትባላለች። በምዕተ ዓመታት ውስጥም በሚሊዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ሕንድ ውቅያኖስን አቋርጠው ወደ አረብ ባሕረ ሰላጤ ግዛቶች ተልከዋል።-ከዛንዚባር ስቶን ታውን በስተሰሜን 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ማንጋፕዋኒ ዋሻ ጥልቅ ዋሻ አንዱ ነው። የተፈጥሮ ዋሻው ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ ያለው ሲሆን መጎብኘት የቻልነውም ባትሪ ይዘን ነበር።-በርካታ ባሪያዎችን ያከማች የነበረው ይህ ዋሻ በጥልቀት ሲገቡበት ለመተንፈስም ያስቸግራል። አስጎብኚችንም የልብ ህመም ወይም የመተንፈስ ችግር ያለባቸው ሰዎች ይህንን የባሪያዎች ማከማቻ ዋሻ እንዳይጎበኙ ይመከራል አለን።-ትንፋሻችን ለራሳችን እየተቆራረጠ ስለተሰማንም ከሰላሳ ደቂቃ በላይ በዋሻው መቆየት ፈታኝ ነበር። የዋሻው መውጫ ተራራ የሚመስል ቋጥኝ ሲሆን፣ ላብ በላብም ሆነን ነው የወጣነው።-ታላቋ ብሪታንያ በአውሮፓውያኑ 1890 የዛንዚባር ሱልጣን በእኔ ቁጥጥር ስር ነው አለች። ከስድስት ዓመት በኋላ ገዢው ሱልጣን ሲሞት ካሊድ ኢብን ባርጋሽ ራሱን የዛንዚባር ሱልጣን አድርጎ ሰየመ።-ብሪታንያ ሱልጣኑን ከሥልጣን እንዲለቅ ብትጠይቀውም ፈቃደኛ ባለመሆኑ፣ እንግሊዞች ቤተ መንግሥቱን በማጥቃት ወደ አንግሎ ዛንዚባር ጦርነት አመሩ።-በታሪክ አጭር ጦርነት ተብሎ የሚጠራው ይህ ጦርነት፣ ከአንድ ሰዓት ባነሰ ለአርባ ደቂቃ ብቻ ነበር የተካሄደው።-እንግሊዞች ኻሊድን ካሸነፉ በኋላ ለእነሱ ታዛዥ የሆነውን ሱልጣን በመሾም የእጅ አዙር ቅኝ ግዛታቸውን ቀጠሉ።-በአውሮፓውያኑ 1963 ዛንዚባር የኮመንዌልዝ አባል በመሆን ገዢው ሱልጣን ነጻነት ቢሰጠውም፣ በቀጣዩ ዓመት በዛንዚባር በተነሳው አብዮት ተገለበጠ።ዛንዚባርም ነጻነቷን አወጀች።
ባለፉት አስርተ ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጸምበት ስለነበረው ማዕከላዊ እስር ቤት ብዙ ሰምተናል።-‘ጄል ኦጋዴን’ ተብሎ ከሚጠራው የጂግጅጋ ከተማ ማረሚያ ቤት የወጡ የሰቆቃ ድምጾችንም እንዲሁ።-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚፈራረቅባት ኢትዮጵያ በርካቶች ስለሚታሰሩበት የአዋሽ ወታደራዊ ካምፕ ግን ብዙ የተባለለት ነገር የለም።-አዋሽ አርባ ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በተለይ በሕዝባዊ ተቃውሞ እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት እስረኞችን በጅምላ ለመቅጣት ሁነኛ ምርጫ ሲሆን ተስተውሏል።-ቢቢሲ ያነጋገራቸው እና በአህአዴግ እንዲሁም በብልጽግና አስተዳደር ታስረው የወጡ ግለሰቦች በተፈጸሙባቸው የመብት ጥሰቶች ምክንያት ሥፍራውን “የምድር ሲኦል” ሲሉ ይገልጹታል።-ለመሆኑ አዋሽ አርባ ያለው ምንድን ነው? ወታደራዊ ካምፑ ሲመሰረትስ ለእስረኛ ማቆያ የተዘጋጁ ቦታዎች ነበሩት? ተጠርጣሪዎችስ ወደ አዋሽ የሚጋዙት ለምንድን ነው?-ቢቢሲ ወታደራዊ ካምፑ ሲመሠረት በወቅቱ በአመራርነት ላይ የነበሩ የጦር መኮንኖችን እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን በማነጋገር እንዲሁም ካምፑን የተመለከቱ ሰነዶችን መሠረት በማድረግ ታሪካዊ ዳራውን ለመዳሰስ ሞክሯል።-የአጼ ኃይለ ሥላሴ ንጉሣዊ ሥርዓት ተገርስሶ ጊዜያዊው ወታደራዊ አስተዳደር - ደርግ የሥልጣን መንበሩን ከተቆጣጠረ በኋላ አልጋ በአልጋ የሆነ ነገር አልገጠመውም።-ለውጡን ተከትሎ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ የገባችው ኢትዮጵያ፣ በፖለቲካ ኃይሎች መካከል ደም አፋሳሽ ግጭቶችን አስተናግዳለች። በዚህም አያሌ ምሁራንን እና ወጣቶችን ቀርጥፎ የበላው የቀይ ሽብር ጭፍጨፋ ተጠቃሹ ነው።-በወቅቱ ወታደራዊው መንግሥት በምሥራቅ እና በደቡብ በሶማሊያ ወረራ፣ በሰሜን ደግሞ በኤርትራ ሽምቅ ተዋጊዎች፣ በመሃል አገር ደግሞ በኢህአፓ እና በመኢሶን ውስጣዊ ትግል ተወጥሮ የተያዘበት ፈታኝ ጊዜ ነበር።-በዚህ ወቅት ነበር አዋሽ አርባ ለደርግ ፈጥኖ የደረሰለት።-አዋሽ አርባ ከመዲናዋ አዲስ አበባ በ220 ኪሎ ሜትሮች ገደማ ርቀት ላይ በአፋር ክልል ውስጥ የሚገኝ ቦታ ነው።-አየሩ ሞቃታማ፣ መሬቱም አሸዋማ።-ወታደሮችን ለማሠልጠን የመሬት አቀማመጡ እና የአየር ጠባዩ የተመረጠ እንደሆነ ይነገርለታል። በዚያ ላይ የሶማሊያን ወረራ እና የሰሜን ሸማቂዎችን ለመመከት የሚያመች ሁነኛ ቦታ።-ሆኖም ካምፑ ሲመሠረት ለዚሁ ዓላማ ተብሎ የተመረጠ እንዳልነበረ የካምፑን የአመሠራረት ታሪክ ለቢቢሲ ያጋሩ እና ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የቀድሞ የጦር መኮንንኖች ይናገራሉ።-እነርሱ እንደሚሉት ቦታው መጀመሪያ ላይ በመንገድ ግንባታ ላይ የተሰማራ ተቋም ካምፕ ነበር።-ካምፑ የአዲስ አበባ - አሰብ መንገድን ለመሥራት መቀመጫውን እዚያ አድርጎ በነበረው ‘ትራምፕ’ በሚባል የመንገድ ተቋራጭ ኩባንያ ነው የተቆረቆረው።-ትራምፕ የጀርመን ኩባንያ ነበር። ኩባንያው መንገዱን ሰርቶ ሲጨርስ አካባቢውን ለቆ ወጣ።-ይህ ነበር በወቅቱ የበጀት እጥረት ለገጠመው የደርግ ሥርዓት ጥሩ አጋጣሚ የፈጠረለት።-ካምፑ በብሎኬት የተሰሩ አጫጭር ቤቶች ነበሩት። ጥሩ መዋኛ ገንዳ እና ምግብ ቤቶች፤ ከሞላ ጎደል መሠረተ ልማቱም የተሟላለት ነበር።-አካባቢው ግን ትምህርት ቤት፣ ሐኪም ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ የእምነት ተቋማት የሌሉበት ምድረ በዳ ነበር።-አርባ የተባለው መንደርም ለመንገድ ግንባታው ሠራተኞቹ ሻይ እና ምግብ ለማቅረብ በአካባቢው በከተሙ ሰዎች ቀስ በቀስ ነበር የተቆረቆረው።-በጥድፊያ ላይ የነበረው የደርግ መንግሥት ታዲያ ትራምፕ ኩባንያ ጥሎት የወጣውን ካምፕ በመጠቀም የተወሰነ ጦር በአስቸኳይ ወደ ካምፑ እንዲገባ አድርጎ የመጀመሪያውን አንድ ሻለቃ ጦር (500 ወታደር) አሰለጠነ።-በጦር ግንባሮች ያሉ የወታደሮች ቁጥር መሳሳት ሲጀምሩ እና ተጨማሪ ሠራዊት ለማሰልጠን ከያኔዋ ሶቪየት ኅብረት ግብዓቶችን በማስመጣት አስር ብሎክ የጣውላ ቤቶችን አሰራ።-የጦር አመራሮቹ እንደሚሉት እነዚህ መኖሪያ ቤቶች ሁሉም ነገር የተሟላላቸው የነበሩ ሲሆን፣ ለመኮንኖች እና ለአማካሪዎች የተሠሩ ነበሩ።-ቀስ እያለ የውትድርና ሠልጣኞች ቁጥር እየተበራከተ መጣ። በአፋጣኝ ግድግዳውም ጣሪያውም ቆርቆሮ የሆነ አንድ ብሎክ ቤት ተሠራ። ከዚህ በኋላ ነበር የበታች ሹም አካዳሚ ተብሎ በይፋ የተመሠረተው።-ትዕዛዙን የሰጡትም አሁን በስደት ዚምባብዌ የሚገኙት የአብዮታዊ ጦር ጠቅላይ አዛዥ እና የደርግ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማሪያም ነበሩ። ጊዜው ደግሞ 1970 ዓ.ም.።-በዚህ ካምፕ የሚሰለጥኑት የበታች ሹማምንት ነበሩ። የበታች ሹማምንት የእግረኛ ጦር መሪዎች ማለት ናቸው። በአንድ ውጊያ ውስጥ ያላቸው ሚና ከፍ ያለ ነው። የጦር መኮንኖች ቢጎዱ አሊያም ቢሞቱ እነርሱን ተክተው የሚያዋጉ ማዕረጋቸው ትንሽ፣ ሚናቸው ግን ትልቅ የጦር መሪዎች ናቸው።-ያኔ ሌተናንት ኮሎኔል አሊ ሐጂ አብዱላሂ የትምህርት ቤቱ አዛዥ ነበሩ።-እየቆየ ሲሄድ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የማሠልጠኛ ካምፖችን ለማስተዳደር እና ለድርጅታዊ ሥራዎች ችግር በመፈጠሩ የካቲት 1971 ዓ.ም. አርባ የተባለው የጦር ሰፈር ተገነባ።-በወቅቱ በውጊያ የቆሰሉ የጦር መኮንኖችን በመያዝም በአራት ካምፖች ውስጥ ታንከኞች እና ሜካናይዝድ ጦሮችን አስገብተው ማሠልጠን ጀመሩ።-ከዚያ በኋላ የበታች ሹም አካዳሚ መሆኑ ቀርቶ ‘የውጊያ እና የቴክኒክ አገልግሎት ትምህርት ቤት’ ተብሎ አድማሱን አሰፋ።-ደብረዘይት የነበረው የአየር መቃወሚያ፣ ናዝሬት የነበረው ሜካናይዝድ ጦር ማሠልጠኛ፣ እዚያው አዋሽ የነበረው ታንከኛ እና መድፈኛ አንድ ላይ ተሰባስበው በ1972 ዓ.ም. የተሟላ የውጊያ ትምህርት ቤት ለመሆን በቃ።-አዋሽ አርባ የወታደሮችን አቅም የሚፈትሽ ለሥልጠናው ምቹ ቦታ እንደሆነ የጦር አመራሮቹ ይናገራሉ።-ይህ ወታደራዊ ካምፕ ከአገር ውስጥ ባሻገር ከፍተኛ የውጭ ጄኔራሎች ጭምር እንደፈሩበት ‘የውጊያ ትምህርት ቤት አርባ’ በሚል ርዕስ የታተመ አንድ የምረቃ መጽሔት ላይ በአጭሩ ሰፍሯል።-አሁን ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያ የሚገኙባት የዚምባብዌ የነጻነት ታጋዮች ሥልጠና እና ትጥቃቸውን አሟልተው የሄዱት ከዚሁ ካምፕ ነበር።-“እነዚህ ወታደሮች መንግሥቱን እንደሚጠይቁትና አሁን ላይ ትላልቅ ጄኔራሎች እንደሆኑ ሰምቻለሁ” ብለዋል ቢቢሲ ያነጋገራቸው የዚያን ጊዜው የጦር አመራር።-በተጨማሪም ከደቡብ አፍሪካ እና ከደቡብ ሱዳን መጥተው በተመሳሳይ ሥልጠናቸውን እና ትጥቃቸውን አሟልተው የሄዱ የነጻነት ታጋዮችም ጥቂት አልነበሩም።-ሥልጠናውን የሚሰጡት የጦር አዛዦችም በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት እና በኩባ ተምረው የመጡ ነበሩ።-በግቢው ውስጥ ሩሲያኛ፣ ስፓኒሽ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች ይነገርበት ነበር።-በካምፑ የሠለጠኑት የሌሎች አገራት የነጻነት ታጋዮች ከነጻነት በኋላ በአገራቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚደርሱ እሙን ነው የሚሉት ምንጮቻችን፣ ብዙዎች ጥሩ ደረጃ ደርሰው እንደሚሆንም ይገምታሉ።-ቢቢሲ በተመለከተው መጽሔት ላይ እንደሰፈረው ጄኔራል አሊ ሐጂ አብደላህ የመጀመሪያው አዛዥ ነበሩ። ከዚያም ኮሎኔል ኃይለ ተስፋሚካኤል፣ ጄኔራል ተስፋዬ ትርፌ፣ ጄኔራል ሞገስ በቀለ፣ ኮሎኔል እጅጉ ላቀው፣ ብርጋዲየር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ፣ ጄኔራል ኃየሎም አርአያ የትምህርት ቤቱ አዛዥ ሆነው አገልግለዋል።-የዚህ ጽሑፍ ዋናው ትኩረት አዋሽ አርባ ቢሆንም ስለአዋሽ ሰባትም በዚሁ ጠቆም አድርገን እንለፍ። በደርግ ዘመን የአዋሽ ሰባት ካምፕ የአዲስ አበባ - አሰብ እንዲሁም የሚሌ መንገድን የሚቆጣጠር መቶኛ ብርጌድ ካምፕ እንደነበር የጦር አመራሮቹ ያስታውሳሉ።-እነርሱ እንደሚሉት የዚህ ብርጌድ ዋነኛ ሥራው መንገድ ጥበቃ ብቻ ነበር። የመንገድ ጥበቃው ዋና መሥሪያ ቤትም ነበር።-ከደርግ መውደቅ በኋላ ኢህአዴግ ሥልጣን በያዘበት ጊዜ በስፍራው ላይ አዲስ ካምፕ ተሰርቶ የጦር መኮንኖች ማሠልጠኛ ሳይሆን እንደማይቀርም አመራሮቹ ጠቁመዋል።-ኢህአዴግ የአገሪቱን መሪነት መንበረ ሥልጣኑን ከተረከበ በኋላ በቀደመው ዘመን የተኩስ ልምምድ በሚደረግበት አካባቢ ዘመናዊ ቤቶች የተሠሩ ሲሆን፣ ለአሠልጣኞች እና ለቤተሰባቸው መኖሪያ ይሆን ዘንድም ባለሁለት ፎቅ ቤቶች ተገንብተዋል።-ከወራት በፊት ካምፑን ጎብኝተውት እንደነበር የሚናገሩት የቀድሞው የጦር አመራር “ቀድሞ ከነበረው አድጎ እና ተሻሽሎ ነበር ያገኘሁት” ብለዋል።-ሆኖም ለአውራ ጎዳናው ካምፕ ተብለው የተሰሩት አጫጭር ቤቶች የእስረኛ ማቆያ መደረጋቸውን ታዝበዋል።-እርሳቸው እንደሚሉት በካምፑ ውስጥ ሰዎችን ማሰር የተጀመረው በኢህአዴግ የሥልጣን ዘመን ነው።-ኢህአዴግ በተለይ በ1993 ዓ.ም. እና በ1997 ዓ.ም. በገጠመው ተቃውሞ ወቅት አዋሽ አርባን ጨምሮ በዴዴሳ፣ በጦላይ እና በሌሎች ወታደራዊ ካምፖች ውስጥ በሚገኙ ጊዜያዊ ማቆያ ቦታዎች ሰዎችን ያስሩ እንደነበርም የቅርብ ጊዜ ትውስታቸው እንደሆነ ይናገራሉ።-“አሁን አገሪቷን እያስተዳደሩ ያሉትም ከእነርሱ ተምረው ድሮ የነበሩትን አሮጌ ቤቶች ለማሰር ይጠቀሙባቸዋል” ብለዋል።-በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ ከተደነገጉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ጋር በተያያዘ በጅምላ የተያዙ ግለሰቦች በእነዚህን ቤቶች እንደሚታሰሩ እና የመብት ጥሰቶች እንደሚፈፀምባቸው የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች በሚያወጧቸው ሪፖርቶች ሲገልጹ ቆይተዋል።-በዚህ የታሳሪዎች ማቆያ ስፍራ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ሰቆቃዎች ተፈጽመውብናል የሚሉ ሰዎች፣ ቦታውን አሜሪካ የአል ቃኢዳ ተጠርጣሪዎችን ያለፍርድ ይዛ ካቆየችበት “ጓንታናሞ ቤይ” ጋር ያመሳስሉታል።-“በደርግ አስተዳደር ዘመን እንደዚህ ዓይነት እስር አልነበረም” የሚሉት ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጦር መኮንን፣ ደርግ ለእስር ይጠቀም የነበረው ፖሊስ ጣቢያዎችን እና ወህኒ ቤቶችን እንደነበር ያስታውሳሉ።-በእርግጥ ነጻ የመገናኛ ብዙኃን፣ የአገር ውስጥ የሰብዓዊ መበት ተቋማት እና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሌሉበት በዚያ ዘመን በካምፑ ስለተፈጸሙ ነገሮች በትክክል የሚታወቅ ነገር የለም።-የሕግ ባለሙያው እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ያሬድ ኃይለማሪያም ግን “በደርግ ጊዜም ቢሆን እነዚህ የጦር ካምፖች ለእንደዚህ ዓይነት አገልግሎት መዋላቸው ምንም ጥያቄ የለውም” ይላሉ።-ተሟጋቹ ወታደራዊ ካምፖች ዜጎችን ለማሰቃየት ይውሉ እንደነበር እንደ ማሳያነት የሚጠቅሱት የቀይ ሽብር የክስ ሂደቶችን ነው።-አቶ ያሬድ የሕግ ባለሙያ ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተርም ናቸው። በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ዋና መርማሪ ሆነው ለስምንት ዓመታት ሰርተዋል።በዚህ ወታደራዊ ካምፖች የተፈፀሙ አንዳንድ ጉዳዮችንም መርምረዋል።-በኢህአዴግ ጊዜ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች የሰፈሩበት ሕገ መንግሥት፣ ሚዲያዎች እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ቢኖሩም፤ሥልጣን በያዘ ማግሥት የኢሠፓ አባላትን ለተሃድሶ በሚል ወስዶ ያሰራቸው በወታደራዊ ካምፖች እንደነበር ያሬድ ያስታውሳሉ።-ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚነሱ አመጾችም ይሁኑ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተያያዙ ግጭቶች ሲኖሩ በጥርጣሬ ‘የሚታፈሱ’ ሰዎች የሚወሰዱት ወደ ወታደራዊ ካምፖች ሆኗል።-“እስካሁንም ከዚህ አዙሪት አልወጣንም” ይላሉ አቶ ያሬድ።-በአገሪቷ ከተከሰቱ ተቃውሞዎች በኋላ ከአምስት ዓመታት በፊት ወደ ሥልጣን የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “አጣርተን እናስራለን እንጂ አስረን አናጣራም” በማለት በመጀመሪያዎቹ የሥልጣናቸው ወራት በቀደመው አስተዳደር የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞችን እንዲለቀቁ በማድረጋቸው ውዳሴን አትርፈው ነበር።-በወቅቱም በመላው አገሪቱ በሚገኙ እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች የተለቀቁ ሲሆን፣ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተመራማሪ የነበሩት አቶ ፍስሐ ተክሌም ነጻ የወጡት ሰዎች አሃዝ 45 ሺህ እንደሚደርስ ተናግረው ነበር።-ሆኖም ይህ የቆየው ለአጭር ጊዜ ነበር።-ከዚያ በኋላም የጅምላ እስር እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳዮች የአገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የዘወትር ሪፖርት ሆኗል።-ያሬድ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የሕዝብ ቅቡልነት ለማግኘት ከተደረገ የምርጫ ዘመቻ ንግግር የተለየ ባህርይም የለውም” ይላሉ።-ለዚህም የሚያቀርቡት ምክንያት በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ምሎ ሥልጣን የያዘ አካል ማንኛውም ሰው ያለማስረጃ እንዳይታሰር፣ ሳይጣራ እንዳይታሰር፣ ፍትሕ እንዳያጣ እና ዋስትና እንዳይከለከል ማድረግ ችሮታ ሳይሆን ግዴታው ነው የሚል ነው።-ሆኖም አሁን ላይ በአገሪቷ ተባብሶ የሚታየው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከቁርጠኝነት የመነጨ እንዳልሆነ እንደሚያሳይ ይናገራሉ።-ባለፉት አስርተ ዓመታት በተለይ በተደጋጋሚ በታወጁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ወቅት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እስረኞችን ከከተማ ርቀው ወደሚገኙ ወታዳራዊ ካምፖች ሲወስዱ ይስተዋላል።-ይህም በጅምላ ለማስቀመጥ የሚመች ቦታ ስለሆነ እና ጥብቅ ወታደራዊ ጥበቃ ስላለ እንደሆነ ይነገራል።-በሌላ በኩል አካባቢዎቹ በተፈጥሮ ፈታኝ በሆኑ ቦታዎች ላይ የተመሠረቱ በመሆናቸው ታሳሪዎች ላይ ሥነ ልቦናዊ ጫና ለመፍጠር፣ ያለጠያቂ ለማስቀረት፣ ከመገናኛ ብዙኃን እና ከሌሎች የመብት ተሟጋቾች ዕይታ ለመሰወር ነው የሚሉ ክሶችም ይቀርባሉ።-ኢሰመኮ በአዋሽ አርባ ታስረው የሚገኙ የምክር ቤት አባላትን እና ሌሎች ታሳሪዎችን ከጎበኘ በኋላ ባወጣው ሪፖርት በአዲስ አበባ ያለው የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ በመጣበቡ እስረኞቹን ወደ ጊዜያዊ ማቆያው ማምጣት እንዳስፈለገ በፖሊስ ገለጻ እንደተደረገለት አመልክቷል።-የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ያሬድ እንደሚሉትም በአገሪቷ ውስጥ አለመረጋጋት ሲከሰት በሚደነገጉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች የጅምላ እስሮች ስለሚኖሩ መደበኛ እስር ቤቶች እነርሱን ለማስተናገድ በቂ አይሆኑም። በመሆኑም ወታደራዊ ካምፖችን ጨምሮ መጋዘኖች፣ ትምህርት ቤቶች ሳይቀሩ ለዚህ አገልግሎት ይውላሉ።-ነገሩ ግን ከዚህም ያለፈ ነው ይላሉ የመብት ተሟጋቹ።-አዋሽ አርባ ለወታደር ማሠልጠኛ እንጂ ለሲቪሎች ምቹ የሆነ ስፍራ አይደለም። በአካባቢው ከፍተኛ ሙቀት አለ። ቢጫ ወባን ጨምሮ የወባ ወረርሽኝ የሚያጠቃው አካባቢ ነው።-ለሥራ ጉዳይ ወደ አካባቢው የሚሄድ ሰው ጥንቃቄ የሚያደርግበት ቦታ ነው። ራሳቸውን ይጠብቁ ዘንድም ‘የበረሃ አበል’ የሚከፈልበት አካባቢ ነው።-ሆኖም በቂ ምግብ፣ ውሃ እና መታጠቢያ በሌለበት እስረኞችን ማቆየት ተፈጥሮን እንደ ማሰቃያ መጠቀም እንደሆነ አቶ ያሬድ ይናገራሉ።-ሲቪል ሰዎችን በወታደራዊ ካምፖች ማሰር ምንም ዓይነት ሕጋዊ መሠረት የለውም የሚሉት ተሟጋቹ፣ ወታደራዊ ሥልጠናዎች እንደቅጣት የዋሉባቸው አጋጣሚዎችም በሪፖርቶች እንደተሰነዱ አመልክተዋል።-ይህም ከዚያ በሚወጡ ታሪኮች ምክንያት ጋዜጠኞች ዝም እንዲሉ፣ ሕዝቡም በፍርሃት ተሸብቦ እንዲኖር እንደ መቀጣጫም ጭምር ነው ጥቅም ላይ የሚውሉት ይላሉ።-አቶ ያሬድ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ምርመራ በሚያደርጉበት ጊዜ በትግራዩ ጦርነት ወቅት በአዋሽ አርባ የወታደር ካምፕ የታሰሩ ጋዜጠኞች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ ጥሰት እንደተፈፀመ ለመረዳት ችለዋል።-“እስካሁንም የአዕምሮ ቁስለት (ትራውማ) አለቀቃቸውም” ብለዋል።-በአዋሽ አርባ የእስረኞች ማቆያ ማዕከል ውስጥ ይፈጸማሉ ስለሚባሉት የመብት ጥሰቶች እና በደሎችን በተመለከተ ቀደም ሲል የነበረውም ሆነ የአሁኑ የአገሪቱ አስተዳዳር በይፋ ያሉት ነገር የለም።-[በቀደመውና በአሁኑ አስተደዳር በአዋሽ ሰባት እና አዋሽ አርባ በሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች ውስጥ በሚገኙ ጊዜያዊ ማቆያዎች ታስረው የተለቀቁ ግለሰቦች ያጋሩንን ታሪክ በቀጣይ ዘገባዎቻችን ይዘን እንመለሳለን።]
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ጥቅምት 2016 ዓ.ም፤ የላስታዋ ላሊበላ ውጥረት ላይ ነበረች።-ወጣቶቿ “ፋኖን ትደግፋላችሁ” በሚል በገፍ ተይዘው በኮምቦልቻ እየታሰሩ ነው። የከተማውን ጥግ ጥግ የከበበ ታጣቂ ኃይል አለ። በሌላ ጎን ደግሞ ከባድ መሳሪያ ተክሎ ጆሮውን ከፍቶ መከላከያ ሰራዊት በተጠንቀቅ ይጠባበቃል።-ከቅዳሜ ጥቅምት 24 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ወሎዋ ላሊበላ ዙሪያ በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ ተደርጓል።-በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል ግጭቱ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ሲጀመር በትሩ ከበረታባችው አካባቢዎች ውስጥ ላሊበላ አንዷ ናት። ከተማዋ በሐምሌ ወር መጨረሻ ለቀናት በፋኖ ቁጥጥር ስርም ነበረች።-ነገር ግን ጥቅምት 28 እና 29 2016 ዓ.ም ለታሪካዊቷ ላሊበላ ጥቁር ቀናት ሆኑ። በሁለቱ ኃይሎች መካከል ውጊያው ለቀናት ዘልቆ ረቡዕ ጥቅምት 28 2016 ዓ.ም ፋኖ ከተማዋን ቢቆጣጠርም በማግስቱ ጥሎ ወጥቷል።-በሁለቱ ቀናት በከተማዋ የተፈጠረውን ሁነት የአይን እማኞች “በደል፣ ግፍ፣ እልቂት” ሲሉ ይገልጹታል።-ከተማዋን ጥቅምት 28 2016 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ የተቆጣጠረው ፋኖ ‘በአሰሳ’ ያገኛቸውን 15 የሚሆኑ የፖሊስና ሚሊሻ አባላትን መግደሉን የአይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል።-በውጊያው ከፊት ሆነው ተሰልፈው ነበር የተባሉት የፖሊስና ሚሊሻ አባላቱ ፋኖ ከተማዋን መቆጣጠሩን ተከትሎ ከላሊበላ 11 ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱ በሆነው ቤተ አባ ሊባኖስ እና በሰዎች ቤት ተጠልለው እንደነበር እማኞቹ ገልጸዋል።-“ተኩሱ ከተጀመረ በኋላ [የፋኖ ታጣቂዎች] ሰርገው ወደ መሀል ከተማ ስለገቡ፤ ጦርነቱም እየከፋ ሲመጣ በመጨረሻ ከከተማ ለመውጣት ሳይሆን ቤተ ክርስቲያኗን ለመጠጋት ወደ ቤተ ክርስትያን ገቡ። ሴቶቹ የአካባቢው ኅብረተሰብ የተለያየ ልብስ በመስጠት ከሞት ታደጋቸው። እነዛኞቹ ከነ ልብሳቸው [የደንብ ልብስ] ስለተገኙ ቢያንስ ስምንት ዘጠኝ ይሆኑ ነበር ይዘዋቸው [ፖሊስ ጣቢያ] ሄዱ። እዛው ፖሊስ ጣቢያ በታሰሩበት ነው [የገደሏቸው]” ሲሉ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአይን እማኝ ተናግረዋል።-ሌላ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የላሊበላ ነዋሪ ከቤተ ክርስትያን ከተወሰዱት 10 የአካባቢው የፖሊስና ሚሊሻ አባላት ውስጥ የላስታ ወረዳ ፖሊስ አዛዥን ጨምሮ ዘጠኙ ተገድለዋል ብለዋል።-አባላቱ ከቤተ ክርስትያን ከተጠለሉበት ተወስደው መገደላቸውን የኃይማኖት አባቶችና ማህበረሰቡ እንዳወገዙትም ተናግረዋል።-“መጥተው በመስቀል ምለው ከወሰዱ በኋላ በመረሸናቸው የአካባቢውን ሰው እጅግ አስቆጥቷል” ቢሉም ታጣቂው “ሽፍታ” በመሆኑና “ስልጠና ባለመውሰዱ የሚያስወቅሰው ነገር ያለ አይመስለኝም” ብለዋል።-የፋኖ ታጣቂዎች በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ ለፖሊስና ሚሊሻዎች “እርስ በእርሳችን አንጠፋፋ” በሚል ማስጠንቀቂያ ማድረሳቸውን ነዋሪዎች ጠቅሰዋል።-ለጸጥታ አባላቱ ከፋኖ ተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ይደርሳቸው ነበር የሚሉት ሌላ እማኝ፣ ጥቅምት 28 2016 ዓ.ም የተገደሉ የጸጥታ ኃይሎች ቁጥር 15 ሳይደርስ አይቀርም ብለዋል።-ከዚህ ቀደም ቢቢሲ ያናገራቸው የፋኖ አመራሮች የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ግድያን በተመለከተ የማስጠንቀቂያ መልዕክት እንደሚያደርሱ ገልጸው “በቀጥታ የጦርነቱ አካል እስከሆኑ ድረስ መሳሪያ ከያዘው ወታደር አንለያቸውም” ብለው ነበር።-የፖሊስ አባላቱ ቤት ለቤትና ከቤተ ክርስትያን “ተለቃቅመው” በከተማዋ አደባባይ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መገደላቸውን ተናግረዋል።-ሐሙስ ለጥቅምት 29 2016 ዓ.ም አጥቢያ፣ የፋኖ ታጣቂዎች ከተማዋን ለቅቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ዳግም ላሊበላን የተቆጣጠረው መከላከያ ሰራዊትም “በበቀል ተነሳስቶ” ንጹሃን ላይ ግድያ ፈጽሟል በሚል በነዋሪዎች ይከሰሳል።-የሟች ቤተሰቦችና የአይን እማኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት መከላከያ ጥቅምት 29 2016 ዓ.ም ከተማዋን ዳግም ከያዘ በኋላ ከዝርፊያ ጀምሮ፤ በጦርነቱ ተሳትፎ በሌላቸው ንጹሃን ላይ እስር፣ ድብደባና ግድያ መፈጸሙን ተናግረዋል።-ባለቤታቸውና ልጃቸው በመከላከያ ሰራዊት “ተረሽነውብኛል” ያሉ እናት፣ ሌላ የቤተሰብ አባላቸው ላይ ተመሳሳይ እጣ እንዳይደርሳቸው በመስጋት ለመገናኛ ብዙኀን ከመናገር ተቆጥበዋል።-በእንባ ታጅበው “ምን ሊፈይድልኝ” ሲሉ አለመናገርን የመረጡት እናት፣ ለሚዲያ ተናገራችሁ ተብለው የተገደሉ ሁለት ሰዎችን በመጥቀስ በስጋት አለመናገርን መርጠዋል።-በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩት አቶ አበበ [ስማቸው የተቀየረ] በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በላሊበላ ከተገደሉት መካከል ናቸው።-ለደህንነታቸው በመስጋት ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአቶ አበበ ባለቤት የሁለት ልጆች እናት ናቸው።-የአራት ዓመት ልጃቸውን ለማምጣት የወጡት ባለቤታቸው፣ በራቸው ላይ በመከላከያ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ እንደተረሸኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-ከጎረቤታቸው ጋር በመከላከያ ሰራዊት “ቁጥጥር ስር የዋሉት” ሟች፣ ሀሙስ ጥቅምት 29 2016 ዓ.ም በሰራዊቱ ከተወሰዱ በኋላ ቤተሰባቸው ያሉበትን ቦታ ለማወቅ ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ገልጸዋል።-“ከቤት ልጅቷ ወጥታበት ሊያመጣ ሲል ነው [የተያዘው]። ይዘውት ሲወጡ የአራት ዓመት ልጄ እያለቀሰች ነበር። ጎረቤታችንንም ይዘውት ሄዱ። ሁለቱም የቀን ሰራተኛ ናቸው። ሁለቱንም ይዘዋቸው ሄዱ። እኛ እየተከተልን እሪ [እያልን] ምን ፈልጋችሁ ነው ብንላቸው ሊሰሙን አልቻሉም። ተከትለናቸው ብንሄድም መፍትሄ አጣን። አርብ ምሳ ይዘን ያሉበትን አሳዩን ብለን ቻይና ካምፕ [የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ] ብንሄድ ‘አናውቅም እንደዚህ አይነት ሰው፤ እስረኛም የለም’ አሉን” ይላሉ።-አቶ አበበና ጎረቤታቸው “ተረሽነው” ጥልቀት በሌለው መቃብር ካምፕ ውስጥ መቀበራቸውን በሰው እንደተረዱም ተናግረዋል። በቁጥጥር በዋሉበት ቀን እጃቸውን ወደ ኋላ ታስረው (የፍጥኝ) ተገድለዋል የተባሉት ሁለቱ ግለሰቦች “በውለታ” አስከሬናቸው ከተቀበሩበት ተቆፍሮ ቅዳሜ (ህዳር አንድ) ለቤተሰብ መሰጠቱ ታውቋል።-ቀብራቸውም በዚሁ ቀን በድጋሚ ተፈጽሟል።-“አገር የእነሱን ስራ ስለሚያውቅ ሁሉም ህዝብ ነው ያለቀሰው። ወይ የፋኖ ምንነት የላቸው፤ ወይ ምን አላሉ፤ በቃ ቀናቸው ነው ብለን ነው። እጃቸው ቢኖርበት [እንደሚገደሉ] እንጠረጥር ነበር። ጠይቀው ይመልሷቸዋል እንጂ እንደዚህ ያደርጓቸዋል ብለን አላሰብንም። ሙሉ ከተማው ነው ያለቀሰው። ምክንያቱም ‘ወይ ታጥቀው በሞቱ፤ ወይ ፋኖ ሆነው በሞቱ፤ ያለስራቸው’ እየተባለ ነበር” ብለዋል።-በባለቤታቸው ስራ እንደሚተዳደሩ የሚናገሩት የአቶ አበበ ባለቤት ቀጣይ የቤተሰባቸውን ህይወት ለፈጣሪ ከመስጠት ውጭ ሌላ መንገድ አይታያቸውም።-“እንደዚህ ያደረገን ፈጣሪ፤ እሱ ያውቅልናል” ይላሉ በቁጭት።-ከአባቷ እቅፍ የተነጠለችው የአራት ዓመት ልጃቸው የአባቷን የመመለሻ ቀን እየጠየቀች ነው።-“ከሁሉም በላይ የእሷ ነው የከበደኝ። በነጋ ቁጥር ትጠይቃለች። ‘ምናለ የወሰዱት ሰዎች ቢያመጡት’ ትላለች። ምንም አልመልስላትም፤ ስራ ሄዷል ስላት እንኳ አታምነኝም። ሁልጊዜ ትጠይቃለች፤ የልጅን ጥያቄ መመለስ ከባድ ነው” ይላሉ።-ሌላ የከተማዋ ነዋሪ ሁለት የቅርብ ዘመዶቻቸውን ጨምሮ እርሳቸው የሚያውቋቸው አራት ሰዎች በመከላከያ ሰራዊት እንደተገደሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-“ፋኖ ናችሁ፤ ፋኖን ትደግፋላችሁ በሚል ከቤታቸው እየተጎተቱ የተገደሉ፤ የተረሸኑ ንጹሃን አሉ። እኔ እንኳ በትክክል የማውቃቸው አራት ንጹሃን የሆኑ ልጆች ናቸው። አንደኛው ወንድሙ ፖሊስ የነበረ ‘የት ነው ያለኸው እያለ፤ ተረፍክ ወይ’ እያለ እየተደዋወለ [እያለ] ስልኩን ቀምተው ካምፓቸው እስከ ጓደኛው ወስደው ደብድበው ገደሏቸው። ሁለቱ ደግሞ የኔ ቅርብ ቤተሰብ ናቸው። ከቤታቸው ጎትተው [ወንድማማቾችን] ነው የረሸኗቸው” ብለዋል።-ሌሎች ሦስት የቤተሰባቸው አባላትም ተይዘው ሊገደሉ ሲሉ የሚያውቃቸው ሰው በመገኘቱ መትረፋቸውንም የአይን እማኙ ተናግረዋል።-በመከላከያ ሰራዊት ከ10 እስከ 15 የሚደርሱ ንጹሃን ሳይገደሉ አይቀርም የሚሉት ሌላው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የላሊበላ ነዋሪ፤ በጦርነቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች “የእሳት እራት” መሆናቸውን አመልክተዋል።-“ስልክ የሚያወራ ከተገኘ መረጃ እየሰጠ ነው በሚል ይገደላል” ያሉት አንድ ነዋሪ ያረጋገጧቸው አራት ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።-ቢቢሲ ይህን ዘገባ ለማዘጋጀት በርካታ የአይን እማኞችና የተጎጂ ቤተሰቦችን ቢያናግርም “ስልካችን ይጠለፋል፣ መረጃ ሰጣችሁ ተብለን ችግር ይገጥመናል፣ ያሰጋናል” በሚል ፍራቻ በላሊበላ የተፈጸመውን በፈቃደኛነት ከመናገር ወደ ኋላ ብለዋል።-የፋኖ ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው በወጡ በሰዓታት ውስጥ ከተማዋን የያዘው መከላከያ ሰራዊት ዝርፊያ፣ ድብደባና ግድያ በመፈጸም ነዋሪዎች ክስ አቅርበውበታል።-“ወንድ የተባለን ከቤት እያስወጡ፤ ሽማግሌ የለ፣ ወጣት፣ ከአስራ ምናምን በላይ እድሜ ያለውን አውጥተው ኮብል ስቶን ላይ አምበርክከው ገርፈው፤ እዛው እንዳትንቀሳቀሱ ብለዋቸው ጥለዋቸው ሄዱ። ጸሐይ ሲቆላቸው ውሎ ወደ ማታ አካባቢ ነው ወደ ቤታቸው ገባን ያሉትና፤ እዚህ ቅዱስ ቦታ ላይ እንደዚህ ከሆነ ሌላ ቦታ ላይ ምን አይነት ግፍ ይፈጸማል የሚለውን ለመገመት የሚያዳግት አይደለም” ብለዋል።-“. . . ያገኙትን [ፋኖን] ትደግፋላችሁ በሚል በቀል ነው። በድንገት ያገኟቸውን ነው ከቤት አውጥተው የገደሏቸው” በማለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቂም በቀል ተነሳስቶ ንጹሃንን ገድሏል ሲሉ አንድ ነዋሪ በወቅቱ የተፈጸመውን ገልጸዋል።-“ብስጭት ይታይባቸው ነበር” ያሉ ሌላ የአይን እማኝ፤ ይህን ብስጭታቸውንም ህዝቡ ላይ ይወጣሉ ሲሉ አሁንም እርምጃዎች መቀጠሉን ያስረዳሉ።-“ይሄ ቄስ ነው ትናንት ያስገደለን” በሚል ከቤተ ክርስትያን ተወስደው በፋኖ ለተገደሉ ፖሊሶች በቀል በአንድ የኃይማኖት አባትና ሁለት ጥበቃዎች ላይ ከባድ ድብደባ መፈጸሙን ደግሞ ሌላ እማኝ ገልጸዋል።-“ቄሰ ገበዙን አንገታቸው ላይ ቆመው ደብደቧቸው። ጥበቃዎቹ ቄሱን ሲደበድቡ እየተተኮሰባቸው አመለጡ። ቄሱ ጆሯቸውን ታመው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከጆሯቸው ደም ይፈሳል።”-በከተማዋ የተወሰኑ የንግድ ተቋማት መዘረፋቸውንም ነዋሪዎች ተናግረዋል።-“መኪና አስጠግተው ነው የተወሰኑ ሱቆችን የዘረፏቸው፤ ወርቅ ቤት፣ ሱፐር ማርኬት፣ ቡቲክ ጭነው ዘረፉባቸው። እርስ በእርሳቸው አንዴ ሚሊሻ ነው፤ አንዴ ፖሊስ ነው፤ አንዴ መከላከያ ነው ይባባላሉ፤ መልስ የሚሰጥ ጠፋ። ዞሮ ዞሮ የመንግሥት ኃይል ነው የዘረፈው” በማለትም አክለዋል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-“ያለምክንያትና ያለስራቸው” በመከላከያ ሰራዊት ተገድለዋል የተባሉት የእነ አቶ አበበ [ስማቸው የተቀየረ] ቤተሰቦች ስለ ድርጊቱ መንግሥት እንዲያውቅ እንፈልጋለን ይላሉ።-የላሊበላ ነዋሪዎችም በከተማዋ ስለተፈጸሙ ግፎች ፍትህና ተጠያቂነትን ይሻሉ።-“ተጠያቂነት ያስፈልጋል። አንድ መንግሥት ነን ከሚል አካል የማይጠበቅ [ነው]። ጥፋት ያጠፉ ሰዎች በገለልተኛ አካል ተጣርቶ የተበደሉት ፍትህ ቢያገኙ ደስ ይለኛል” ሲሉ አንድ ነዋሪ ተናግረዋል።-“መንግሥት እንዲህ ሽፍታ ሆኖ፤ ይህን ያህል መአት ሲያወርድብን ሌላ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሚሏቸው ገብተው ተጣርቶ፤ በዚህ እጃቸው ያለበት፤ የተሳተፉ ኃይሎች ተጠያቂ እንዲሆኑልን እንፈልጋለን። ጊዜ ሊወስድ ይችላል፤ [ግን] ተጠያቂነት ወደ ፊት አይቀርም” ሲሉ አንድ ነዋሪ ፍትህ ማግኘት የጊዜ ጉዳይ ነው ይላሉ።-ቢቢሲ ላሊበላ ላይ ስለተፈጸሙ ግድያዎችና ጥሰቶች የጠየቀው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጉዳዩን “እየተከታተለና እየመረመረ” መሆኑን ተናግሯል።-“ኢሰመኮ ጉዳዩን በትኩረት እየተመለከተው ነው። ምርመራዎችን እያደረገና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር አዳዲስ ሁነቶችን በቅርበት እየተከታተለ ነው” ሲል አስተያየት ሰጥቷል።-ቢቢሲ ላሊበላ ላይ ተፈጸሙ ስለተባሉ ግድያዎች ከመንግስት አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።-የፎቶው ባለመብት AFP-በየዓመቱ ታሕሳስ 29 የሚከበረው የገና በዓል በላሊበላ እጅጉን ይደምቃል።-ከተማዋ በዚህ ወቅት እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጅቷን የምታገባድድበት ወቅት ነበር።-አሁን ግን ላሊበላ ጥቁር ልብሷን መግፈፍ እንዳልቻለች ነዋሪዎቿ ይናገራሉ።-ላሊበላ ተወልደው ያደጉ አንድ የሀይማኖት አባት በከተማዋ ጥቅምት 28 እና 29 2016 ዓ.ም የተፈጸመውን ድርጊት “ዘግናኝ ነው” ይሉታል።-“ሙሉ ሕዝቡ እኮ ጥቁር ነው የለበሰው። ያሳደጉን፣ አብረውን የነበሩ ሰዎች፣ አብረውን ያደጉ ወንድሞቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ በእድሜ የሚበልጡን፣ የምንበልጣቸው ሲለዩን ለመኖር ተስፋ አለመኖሩን ነው ያየነው። ሰው በልቶ ጠጥቶ ከቤተሰቡ ጋር ተወያይቶ መኖር ይችል ነበር። ልጆቻቸውን ፈሰስ አድርገው ነው የሄዱት” በማለት የነበረውን ሁኔታ ይገልጹታል።-የከተማዋ ሀዘን መንግሥትን ትደግፋላችሁ እና ፋኖን ትደግፋላችሁ በሚል የሞቱት ሰዎች የአካባቢው ተወላጆች በመሆናቸው መበርታቱን ሌላ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ ተናግረዋል።-“ሀዘን በሀዘን ነው የነበረው። ፖሊስም ብትይው ፋኖም ብትይው የአንድ አካባቢ ልጆች ናቸው። አባት ሚሊሻ ነው፤ ልጁ ፋኖ ሆኖ የሞተ አለ። እና ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው። ከዛም የሞተው ከዚህም የሞተው አንድ አይነት ነው። ባለፈውም 15 ኪ.ሜ አካባቢ መንግሥት በድሮን የመታቸው አሉ፤ የሞቱትም የላሊበላ ልጆች ናቸው። በጣም አስቸጋሪ ነው። አሁንም [ላሊበላ] ሀዘን ላይ እንዳለች ነው የሚሰማኝ” ብለዋል።-“ግፉ ብዙ ነው። እግዚአብሔር ምህረቱን ካላከልን በምንም ሚዛን ጉዳቱ ይሄ ነው ብለሽ በዚህ ደረጃ ልትይው አትችይም። ግፉ ብዙ ነው። ክፋቱም ብዙ ነው” ሲሉ ሌላ ነዋሪ ተናግረዋል።-“. . .የከተማው ሰው ጥቁር ልብስ ለብሶ ነው የሚታይው። ‘ታሞ ሞተብህ ወይስ በዘመኑ በሽታ [ጦርነት] ሞተብህ?’ እስከመባል እየደረሰ ነው” በማለት የማኅበረሰቡን ሀዘን ይገልጻሉ።-የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች ሀዘን ለገና በዓል የሚደረገው ዝግጅት ላይ ጥላውን ማጥላቱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ።-“ዳቦ የሚሸጠው፣ ቆሎ የሚሸጠው፣ ሆቴል የሚያከራየው፣ ጋይድ የሚያደርገው [የሚያስጎበኘው] በተስፋ ዓመቱን የሚንቀሳቀስበት ነው፤ የሚዘጋጅበት ሰዓት ነበር። የዘንድሮው ግን በዚህ ከቀጠለ እንግዳ መምጣት አለመምጣቱ አስጊ ነው የሚሆነው” ሲሉ መንገዶች መዘጋታቸው ጠቅሰው ሁኔታው “አሳዛኝ” እንደሆነ ተናግረዋል።-“እንደ ራሴ በዓሉን አከብራለሁ ብዬ አላስብም። ውስጤ ጥሩ አይደለም። በከተማዋ በዓሉ ይከበራል የሚል የለኝም። ሆቴሎችም እንደተዘጋጉ ነው። ቱሪስትም ምንም የለም። ስለዚህ በዓሉ ይከበራል የሚል [እምነት] የለኝም። አንደኛ ከተማው የጦርነት አውድማ እስከሚመስል ድረስ አሁንም መከላከያ ከከተማው አናት ላይ ምሽግ መሽጎ ባለበት፤ ከከተማው መግቢያ ላይ ምሽግ መሽጎ ባለበት በዓል ማክበር እንደራሴ በጣም የቀዘቀዘ ስሜት ነው ያለኝ። ህዝቡም እንደዛ ይመስለኛል” ብለዋል።-ላሊበላ ምንም እንኳ “ሀይማኖታዊ ቅዱስ ስፍራ” ብትሆንም ለገና በዓል ግን በተለየ ሁኔታ ጎብኝዎችና አማኞች የሚጎርፉባት ከተማ ናት።-የከተማዋ ምጣኔ ሀብትም ቱሪዝም ነው።-“የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ስለሆነ፤ በለቅሶም ሆነን ቢሆን የግድ እናከብረዋለን” የሚሉት አንድ ለቤተ ክርስትያን ቀረብ ያሉ ነዋሪ፤ በከተማዋ ገናን ለማክበር ከሞላ ጎደል ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።-የላሊበላ ከተማ አስተዳደር በዓሉን “በድምቀት ለማክበር” እየተዘጋጀሁ ነው ያለ ሲሆን፤ ለታዳሚዎችም “በዓሉን አብረን እናክብር” ሲል ጥሪ አቅርቧል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በአገራቸው የተሠራ ቅንጡ መኪና በስጦታ ማበርከታቸውን ደቡብ ኮሪያ ተቃወመች።-የሰሜን ኮሪያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት የፑቲን ስጦታ የሆነው ሊሞዚን፣ ፒዮንግ ያንግ ውስጥ ለፕሬዝዳንቱ ከፍተኛ ረዳቶች የተሰጠው እሁድ ዕለት ነው።-የፑቲን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ስጦታው መበርከቱን አረጋግጠው፣ አውረስ ከተባለ ቭላድሚር ፑቲን ከሚጠቀሙት ጋር ተመሳሳይ ቅንጡ መኪና መሆኑን ተናግረዋል።-ከምዕራባውያን ጋር ሆድ እና ጀርባ የሆኑት ሁለቱ አገራት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከፈጸመች በኋላ ግንኙነታቸውን አጠናክረዋል።-በሁለቱ አገራት ላይ ማዕቀብ የተጣለባቸው ቢሆንም፣ ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ መድፍ፣ ሮኬት እና ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን እያስታጠቀች ነው ቢባልም፣ አገራቱ ግን ያስተባብላሉ።-ባለፈው መስከረም ወር ኪም ሩሲያን በጎበኙበት ጊዜ በፑቲን መኪና በተጓዙበት ወቅት በቅርበት ተመልከተውት ነበር። የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ለመኪኖች የተለየ ፍቅር ያላቸው ሲሆን፣ ቅንጡ የውጭ አገራት መኮንኖችን የመሰብሰብ ልምድ አላቸው።-የኪም እህት ዮ ጆንግ “ስጦታው በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል ያለውን ልዩ ግንኙነት የሚያሳይ ነው” ማለታቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።-ነገር ግን የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስጦታው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅንጡ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ሌሎችንም ወደ ሰሜን ኮሪያ እንዳይገቡ የተጣለውን ዕቀባ የሚጥስ ነው ብሏል።-ሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ ፑቲን በቅርቡ ፒዮንግያንግን እንደሚጎበኙ አመልክተዋል።-ሰሜን ኮሪያ በምታካሂደው የኑክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ እና በተወንጫፊ ሚሳኤሎች ያልተቋረጠ ሙከራ ምክንያት ከጎረቤቶቿ እና ከምዕራባውያን ጋር ሆድ እና ጀርባ ስትሆን፤ ሩሲያ ደግሞ ሁለት ዓመት ሊሞላው በተቃረበው የዩክሬን ወረራ ምክንያት ከምዕራባውያኑ ጋር ተፋጣለች።
የፎቶው ባለመብት PA Media-አንድ ታዳጊ ወሲባዊ ይዘት ያለው ፎቶግራፍ እንዲልኩ ገንዘብ ከፍሏል በሚል ከሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ የነበረው ጋዜጠኛ ማንነት ይፋ ሆኗል።-በዚህ የተወነጀለው ለአራት አስርት ዓመታት በቢሲ በጋዜጠኝነትና አቅራቢነት እያገለገለ ያለው ሂው ኤድዋርድስ መሆኑን የተናገረችው ባለቤቱ ናት።-ባለቤቱ ጋዜጠኛው ሂው ኤድዋርድስ “በከባድ የአዕምሮ ጤና ጉዳዮች” ምክንያት ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኝ በተናገረችበት መግለጫዋ ነው ከዚህ ውዝግብ ጀርባ ያለው ባለቤቷ መሆኑን የጠቀሰችው።-ዘ ሰን የተባለው ጋዜጣ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ወሲባዊ ይዘቶች ያላቸው ፎቶዎችን እንዲልኩ ለማድረግ ለአንድ ታዳጊ ስለመክፈሉ ዘገባ ማውጣቱን ተከትሎም ከሰሞኑ የጋዜጠኛው ማንነት አነጋጋሪ ሆኖ ነበር።-ቢቢሲ የግል የመረጃ መብታቸው ጋር ይጣረሳል በሚል የአቅራቢውን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥቦ ነበር።-ባለቤቱ ቪኪ ፍሊንድ ጋዜጠኛውን በመወከልም ይህንን መግለጫ እንድትሰጥ ምክንያት የሆናት “በዋነኛነት ለእምሮ ጤንነቱ እና ልጆቻችንን ለመጠበቅ በማሰብ ነው” ብላለች።-የቢቢሲ የቴሌቪዥን መርሃ ግብር አቅራቢ አንድ ታዳጊ ወሲባዊ ይዘት ያለው ፎቶግራፍ እንዲልኩ መክፈላቸውን በመጀመሪያ የዘገበው ዘ ሰን ጋዜጣ ነው።-ማንነታቸው እንዲሁም ፆታቸው ያልተገለጸው ጋዜጠኛ ማንነታቸው እንዲሁም ፆታቸው ያልተገለጸ ታዳጊን ከ17 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ልቅ ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ፎቶዎች እንዲልኩ በአስር ሺህ ፓውንዶች የሚቆጠር ገንዘብ መክፈላቸውን የጋዜጣው ሪፖርት ይጠቁማል።-ፖሊስ በበኩሉ ወንጀል እንዳልተፈጸመና የ61 ዓመቱ ጋዜጠኛ ምንም ዓይነት የወንጀል ምርመራ እንደማይከፈትበት አረጋግጧል።-ጋዜጠኛው ጤናው ሲስተካከል ለቀረበበት ክስ ማብራሪያ እንደሚሰጥም የቤተሰቡ መግለጫ አክሏል።-“የቢቢሲ ጋዜጠኛን በተመለከተ በቅርብ የወጡ ዘገባዎችን መሰረት በማድረግም ነው ባለቤቴን ሂው ኤድዋርድስን ወክየ ነው መግለጫ የምሰጠው። ዜናው ከወጣ በኋላ የተከተሉት አምስት ቀናት ለቤተሰባችን እጅግ ፈታኝ እለታት ሆነዋል። ይህንን መግለጫ የምሰጠው በዋነኝነት ለአምሯዊ ደህንነቱ እንዲሁም ልጆቻችንን ለመጠበቅ ነው” ብላለች።-“ሂው በከባድ የአዕምሮ ጤና እክሎች እየተሰቃየ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከከፋ የድባቴ ህመም ጋር በተያያዘ ህክምና እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል” ብላለች።-“ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የተከሰቱ ሁኔታዎች የአዕምሮ ጤና እክሉን በእጅጉ አባብሰውታል።በአሁኑ ወቅትም የከፋ የጤና እጅል ገጥሞትም በሆስፒታል ውስጥ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል” ስትል አስፍራለች።-ለአራት አስርት ዓመታት በቢቢሲ ጋዜጠኝነት የሰራው ሂው ኤድዋርድስ በተቋሙ ውስጥ ከፍተኛ ደመወዝ ከሚከፈላቸውም አንዱ ነው። በአውሮፓውያኑ 2022፣ 435 ሺህ ፓውንድ እንዲሁም በ2023፣ 439 ሺህ 999 እንደተከፈለው መረጃዎች ያሳያሉ። ጋዜጠኛው ከባለቤቱና ከአምስት ልጆቹ ጋር በለንደን ይኖራል።
ከትናንት በስትያ ታኅሣሥ 24/ 2016 ዓ. ም. በአማራ ክልል፣ ደብረ ብርሃን ከተማ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ አምስት ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ እና የሆስፒታል ባልደረባን ጨምሮ አራት ሰዎች እንደቆሰሉ የደብረ ብርሃን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምንጭ ለቢቢሲ ተናገሩ።-ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው ከትናንት በስትያ ከሰዓት እና ትናንት ቢያንስ የሰባት ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት መከናወኑን ገልጸዋል።-በደብረ ብርሃን ከተማ ባሳለፍነው ረቡዕ እስከ ቀኑ አጋማሽ የቆየ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን የከተማዋ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸው ነበር።-እንደ ነዋሪዎች ገለጻ፣ የፋኖ ታጣቂዎች እና የፀጥታ ኃይሎች ከትናንት በስትያ ጠዋት አንስቶ የተኩስ ልውውጥ ያካሄዱት “በተለያዩ የከተማዋ አቅጣጫዎች” ነው።-የረቡዕ ዕለቱን ሁነት አስመልክቶ ትናንት ታኅሣሥ 23/ 2016 ዓ. ም. መግለጫ ያወጣው የደብረ ብርሃን ከተማ እና አካባቢው ኮማንድ ፖስት “ጽንፈኛ” ሲል የጠራው ኃይል “ጉዳት ለማድረስ በማሰብ” ወደ ከተማዋ “በአቋራጭ” ገብቶ እንደነበር አስታውቋል።-ይህንን ተከትሎም የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም የአማራ ክልል አድማ ብተና እና የከተማዋ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች በወሰዱት “የተቀናጀ ኦፕሬሽን በአጭር ጊዜ ከተማው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው” መመለሱንም ኮማንድ ፖስቱ ገልጿል።-ኮማንድ ፖስቱ “የፀጥታ ችግር” ሲል በጠራው የትናንት በስትያው ክስተት “በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት” መድረሱን በመግለጫው አስታውቋል።-ይሁንና መግለጫው በምን ያህል ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ በቁጥር አልጠቀሰም።-ቢቢሲ ያነጋገራቸው የደብረ ብርሃን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምንጭ አራት ሰዎች ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ወደ ሆስፒታሉ እንደተወሰዱና አንድ ግለሰብ ደግሞ ተጎድቶ ሄዶ ሕይወቱ ማለፉን ተናግረዋል።-ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ የተወሰዱት አራት ግለሰቦች “በአጀብ” ወደ ሆስፒታሉ መግባታቸውን የሚገልጹት የቢቢሲ ምንጭ፤ በዚህም ምክንያት የፀጥታ ኃይል አባላት ናቸው የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።-ወደ ሆስፒታሉ ከገባ በኋላ ሕይወቱ ያለፈው ተጎጂ በአንጻሩ ሲቪል ግለሰብ መሆኑን አመልክተዋል።-ይህንን ግለሰብ ጨምሮ ተጎድተው ወደ ሆስፒታሉ የተወሰዱ ንጹሃን ዜጎች ቁጥር አራት መሆኑን የሚናገሩት የቢቢሲ ምንጭ፤ ከእነዚህ ውስጥም “አስጊ” በሚባል ደረጃ የተጎዳው ታካሚ የሆስፒታሉ ባልደረባ መሆኑን አብራርተዋል።-የቢቢሲ የሆስፒታል ምንጭ እንደሚያስረዱት፣ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የሆስፒታሉ ባልደረባ ለተሻለ ሕክምና አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የቃጠሎ፣ የአደጋና ድንገተኛ ሆስፒታል (አቤት) ተዛውሯል።-ይህ ግለሰብ እና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ቀሪዎቹ ንጹሃን ዜጎች የቆሰሉት “በተባራሪ ጥይት” መሆኑንም አክለዋል።-ቢቢሲ በከተማዋ ከሚገኙ ሌሎች የጤና ተቋማት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።-ይሁንና ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱ ግለሰቦች ባሻገር ሌሎችም ሰዎች በረቡዕ ዕለቱ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ሕይወታቸው እንዳለፈ ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።-አንድ የከተማዋ ነዋሪ፤ “በተባባሪ ጥይት” ተመትተው ሕይወታቸው ያለፈ ንጹሃን ዜጎች ትናንት የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መከናወኑን ገልጸዋል።-ሌላ የከተማዋ ነዋሪ በበኩላቸው፤ “ከትናንት በስትያ ከሰዓትም የተቀበሩ አሉ። እኔ የማውቃቸው ልጆች መሞታቸውን ሰምቻለሁም፤ አውቄያለሁም። [...] ፖሊስ፣ አድማ በታኝ፣ ጥበቃዎችን ጨምሮ [ቀብራቸው የተፈጸመው] ቢያንስ ከአስር በላይ ሰዎች ይሆናሉ” ሲሉ ከፍ ያለ ቁጥር ጠቅሰዋል።-ቢቢሲ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰዎች አጠቃላይ የአሐዝ መረጃ ለማግኘት ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ያደረገው የስልክ ጥሪ አልተሳካም።-ረቡዕ ዕለት የተካሄደውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በከተማዋ ቆሞ የነበረው እንቅስቃሴ በተወሰነ ደረጃ ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን ሦስት የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።-የደብረ ብርሃን ከተማ እና አካባቢው ኮማድ ፖስትም ትናንት ባወጣው መግለጫ “የመንግሥት ተቋማት፣ ሱቆች፣ ባንኮች፣ ሆቴሎች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት” ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው መመለሳቸውን አስታውቋል።
የፎቶው ባለመብት EPA-የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፓል ካጋሜ የአፍሪካ አገራት ዜጎች ወደ ሩዋንዳ ያለ ቪዛ እንዲገቡ የሚፈቅድ አሠራር ይፋ አደረጉ።-ያለ ቪዛ አፍሪካውያን ወደ ግዛቷ እንዲገቡ በመፍቀድ ሩዋንዳ አራተኛዋ አፍሪካዊ አገር ናት።-“ማንኛውም አፍሪካዊ አውሮፕላን ተሳፍሮ ወደ ሩዋንዳ መምጣት እንደሚችል ለመግለጽ እወዳለሁ። አንዳችም ገንዘብ መክፈል አይጠበቅበትም” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።-ፕሬዝዳንቱ ይህ ውሳኔ የተላለፈው በአህጉሪቱ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ እያደገ ካለው የአፍሪካ ቱሪዝም አገራቸውን ተጠቃሚ ለማድረግ መሆኑን አክለዋል።-ሩዋንዳ የቱሪዝም ዘርፏን ለማሳደግ ንቅናቄ እያደረገች ነው።-አገሪቱ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እንደ አርሰናል እና ባየር ሙኒክ ካሉ የእግር ኳስ ክለቦች ጋር ጥምረት ስታደርግ ቆይታለች።-ኬንያ የቪዛ ገደቦችን በማንሳት ሁሉም አፍሪካውያን ቪዛ ሳያስፈልጋቸው ወደ ግዛቷ መግባት እንዲችሉ በሯን ለመክፈት መዘጋጀቷን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከቀናት በፊት መግለጻቸው ይታወሳል።-እስካሁን አፍሪካውያን ያለ ቪዛ መግባት እንዲችሉ የፈቀዱ አገራት ሲሸልስ፣ ጋምቢያ እና ቤኒን ናቸው።-ብዙ የአፍሪካ አገራት ያለ ቪዛ እንቅስቃሴ እንዲደረግ የሁለትዮሽ ስምምነት እየተፈራረሙ ይገኛሉ።-ከእነዚህም መካከል ጋና እና ደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ኡጋንዳ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮምጎ ይገኙበታል።-በአህጉሪቱ አገራት መካከል ከቪዛ ነጻ ጉዞ እንዲኖር ማድረግ ከአፍሪካ ኅብረት ያለፉት ዓመታት ግቦች አንዱ ነበር።-በአገራት እና በአገራት መካከል በሚደረጉ ስምምነቶች መሠረት ከቪዛ ነጻ እንቅስቃሴን የፈቀዱ ቢኖሩም የኅብረቱ ግብ ተግባራዊነት ግን አሁንም አዝጋሚ ነው።-አፍሪካ ኅብረት በ2016 ነበር የአፍሪካን ፓስፖርት ይፋ ያደረገው። ዓላማው ሁሉም አፍሪካውያን በአህጉሪቱ ውስጥ ያለምንም ቪዛ በቀላሉ እንዲዘዋወሩ ለማድረግ ቢሆንም በስፋት አልተሰራጨም።-ለዚህ ማነቆ ከሆኑት መካከል ደኅንነት፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የሥራ ዕድል ጫና ይገኙባቸዋል።-የቪዛ ጥያቄን ማስቀረት ባይቻል እንኳን የቪዛ ዋጋን በመቀነስ፤ በደረሱበት አገር ቪዛ በመስጠት እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የኢ-ቪዛ ሥራ ላይ በማዋል ማሻሻል እንደሚቻል ቪዛ ኦፕነስ ኢንዴክስ ያወጣው ሪፖርት ያሳያል።
የፎቶው ባለመብት ANADOLU-"ስለቤተሰቡ ሲጠይቀኝ መልስ መስጠት አልችልም። በረዥሙ እተነፍስና ርዕሰ ጉዳዩን በመቀየር ጥያቄውን ለማረሳሳት እሞክራለሁ።”-የአራት ዓመቱ ኦማር በሕይወት የተረፈው ብቸኛ ዘመዱ የሆነው አጎቱ ሞኢን አቡ ሬዝክ ነው። ኦማርም ቢሆን በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ በዲር አል-ባላ በሚገኘው አል-አቅሳ ሆስፒታል ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ላይ ነው።-ኦማር ግራ እጁን መቆረጥ ነበረበት። በቀኝ እግሩ ላይ ትልቅ ቁስል አለ። ደረቱ እና ፊቱ ላይ ትናንሽ ቁስሎች አሉት። መንጋጋውም ጉዳት ደርሶበታል። እንደ ሞኢን ገለጻ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት የኦማር እናት፣ አባት እና አያቱን ጨምሮ 35 የቤተሰቡ አባላት ተገድለዋል።-ሞኢን እስካሁንም ለኦማር ስቤተሰቦቹ አሟሟት ላለመናገር ወስኗል። ዜናው ጤናውን ሊያቃውሰው ይችላል በሚል ስጋት ነው። ይህ ደግሞ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መንግሥት እና በቀይ ጨረቃ አማካይነት ከጋዛ በግብፅ በኩል ለሕክምና ለመውጣት ያለውን ዕድል ያሰናክለዋል።-ሞኢን ለቢቢሲ አረብኛ ሲናገርም “እንዳይደነግጥ ወይም ወደማይችለው ሁኔታ እንዳይገባ ዜናው በጥንቃቄ ሊነገረው ይገባል” ብሏል።-“ሁሉንም እንዳላያቸው ያውቃል። ‘እናቴ የት አለች? አያቴስ የት ነው ያለችው? ወደ የት ሄዱ?” ብሎ መጠየቅ እንደሚያስፈልግ ይሰማዋል” ብሏል።-ማዕከላዊ ጋዛ በሚባለው አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ እና የቦምብ ጥቃት ስለሚፈጸም ኦማርን በአምቡላንስ ወደ ግብፅ ድንበር ማጓጓዝ ዋስትና ያለው አይደለም።-የፎቶው ባለመብት EPA-የእስራኤል የምድር ጦር ከሐማስ ጋር ባደረገው ጦርነት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ጋዛ ከተማን ሙሉ በሙሉ በመክበብ ጋዛን ለሁለት ከፍሏታል።-የአገሪቱ ታንኮች እና ወታደሮች ወደ ደቡባዊቷ ኻን ዩኒስ ከተማ እየገፉ ነው። ከዲር አል-በላህ ጋር የሚያገናኘው ዋናው አውራ ጎዳና “የጦር አውድማ” ተብሎ ተፈርጇል። ይህም በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ለመሸሽ ያላቸው ብቸኛ ደኅንነቱ የተጠበቀ መንገድ የሜዲትራኒያን ባሕር እንዲሆን አድርጓል።-በጋዛ ሰሜናዊ ክፍል የሚኖሩ በርካታ ፍልስጤማውያን ከሁለት ወራት በፊት ቤታቸውን ለቀው ከዋዲ ጋዛ ወንዝ በስተደቡብ እንዲሄዱ የእስራኤል ጦር ካዘዛቸው በኋላ ወደ ማዕከላዊ ጋዛ አቅንተው ተጠልለዋል።-ጦሩ ትዕዛዙን የሰጠው መስከረም 26 የሐማስ ታጣቂዎች ድንበር ተሻግረው በፈጸሙት ጥቃት አንድ ሺህ 200 ሰዎችን ገድለው 240 ገደማ ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውን ተከትሎ መሰንዘር ከጀመረው ጥቃት በኋላ ነው።-እስራኤል እያካሄደችው ባለው ጥቃት ከ18 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ ሚመራው የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። እስካሁን ጉዳት ከደረሰባቸው ከ49 ሺህ በላይ ሰዎች መካከል አንዱ ኦማር ነው።-የእስራኤል ጦር አሸባሪዎችን ለማጥፋት፣ መሣሪያ እና የሽብር መሠረተ ልማቶችን ለማውደም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል። ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ ከ22 ሺህ በላይ ዒላማዎች ተመተዋል ሲልም አክሏል።-ሞኢን ለቢቢሲ አረብኛ እንደተናገረው ኦማር እና ቤተሰቦቹ ከዲር አል ባላህ በስተሰሜን በሚገኘው ኑሴይራት መጠለያ ጣቢያ የሚገኙትን አያቱን ሲጎበኙ ነበር የእስራኤል ጦር ምንም ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የቦምብ ጥቃት ያደረሰባቸው።-“እንዲህ አይነት ሚሳኤሎች ከዚያ በፊት አይተን አናውቅም። ሚሳኤሉ ሲወድቅ በዙሪያው ያለውን የመኖሪያ አካባቢ በሙሉ አወደመ” ሲል አስታውሷል።-“እንደ ዕድል ሆኖ ቤቱ በነበረው ቀዳዳ ኦማር ወደቀ። የግራ እጁ በጣም በመጎዳቱ ወዲያውኑ መቆረጥ ነበረበት።”-“[ቅዳሜ ዕለት] ወደ 1 ነጥበ 5 ሊትር የሚጠጋ ደም ፈሰሰው። የሂሞግሎቢን መጠኑም ከ 9.5 ወደ 7.4 ዝቅ አለ። ስለዚህ የደም ዝውውር እንዲደረግለት ወደ ቀዶ ሕክምና ክፍል መዘዋወር ነበረበት።”-ሆስፒታሉ በጣም በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ በመሆኑ ጉዳቱ ከባድ ቢሆንም ሐኪሞች አልጋ ማግኘት ባለመቻላቸው፤ ዶክተሮች እና ነርሶች በቻሉት መጠን ኮሪደር ላይ ሕክምናውን እንዲያከናውኑለት አስገድዷቸዋል ሲል ሞኢን ገልጿል።-“የሁሉም የሕክምና መሳሪያዎች ቁጥር በጣም አነስተኛ በመሆናቸው የተነሳ ከተለመደው መንገድ ውጪ ማስተናገድ ነበረብን።”-“የሕመም ማስታገሻዎች ስለሌሉ እሱን ለማረጋጋት እየቀለድን ልናስቀረው ሞክረናል።”-ይህ ዘዴ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ እንደሚሠራ የገለጸው ሞኢን ነገር ግን “ሌላ አማራጭ የለንም” ብሏል።-ኦማር ሐሙስ ዕለት በግብፅ ድንበር ወደሚገኘው የራፋህ ድንበር ማሻገሪያ ተወስዶ በመቀጠልም ለተሻለ ሕክምና ወደ ትልቅ ሆስፒታል እንደሚወሰድ ተስፋ አለው።-የፎቶው ባለመብት NURPHOTO-ሊና ሻኮራ፣ ባለቤቷ እና ሦስት ልጆቿ ከእስራኤል የቦምብ ጥቃት እስካሁን በሕይወት ተርፈዋል። አሁንም ግን “በቅዠት ውስጥ” እየኖሩ መሆናቸውን ተናግራለች።-በጋዛ ከተማ ሼክ ራድዋን አውራጃ ከሚገኘው ቤታቸውን ሸሽተው በመውጣት ከዲር አል ባላህ ወጣ ብሎ በሚገኝ የእርሻ ቦታ ከዘመዶቻቸው ጋር ተጠልለዋል።-“በየቀኑ ከእንቅልፌ የምነቃው ሰዎች እየተራቡ እና በጦርነት ላይ መሆናችንን እያስታወስኩ ነው። ከቤት መፈናቀል እና ምግብ ሳያገኙ መኖር ከባድ ነው” ስትል ሊና ለቢቢሲ አረብኛ ተናግራለች።-“እኔ እና ቤተሰቤ በአንድ ክፍል ውስጥ ከ40 ግለሰቦች ጋር ተጠልለናል። በቦምብ ፍንዳታ ምክንያት ሁሉም መስኮቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል። በመሠረቱ ከቤት ውጪ ተጠልለናል ማለት ይቀላል ... በጣም ቀዝቃዛ ከመሆኑም ባለፈ ውርደትም ነው።”-ወንድ ልጆቿ ውሃ በማመላለስ ምክንያት የወገብ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በነዳጅ እጥረት ምክንያት ውሃ ማጣሪያው እና ፓምፑ ስለማይሠራ ውሃውም ንጹህ አይደለም።-ሱቆቹ ባዶ ስለሆኑ እና ምንም ዓይነት እርዳታ ባለማግኘታቸው የተበላሸ ምግብ ለመብላት መገደዳቸውን ተናግራለች።-“ትልቁ ተስፋችን ለመጋገር እንድንችል ዱቄት ማግኘት ነው። ዱቄቱ ቢገኝም መጋገር የምንችለው በማገዶ እንጨት ነው።”-“ሰዎች ያገኙትን እንጨት እየዞሩ ይሰበስባሉ። እንጨቱ የሚሰበሰበው በቦምብ ጥቃት ከደረሰበት አካባቢ በመሆኑ ዳቦው ሲጋገር ይበክለዋል” ትላለች።-የተባበሩት መንግሥታት እሑድ ዕለት እንዳስታወቀው በግብፅ ድንበር ላይ ከምትገኘው ራፋህ ከተማ ውጪ እርዳታ ማሰራጨት ያልቻለው በሚካሄደው ጦርነት እና የእንቅስቃሴ ገደቦች በመጣሉ ነው።
ፓስተር ቲቢ ጆሽዋ-የዓለማችን ትልቅ ቤተ እምነቶች መካከል አንዱ የሆነው ቤተ-ክርስቲያን መሥራች እና መሪ ፓስተር ቲቢ ጆሽዋ ምዕመናን አስገድዶ መድፈሩን እና ማሰቃየቱን የቢቢሲ ምርመራ አጋለጠ።-የሲኖግ ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽን የቀድሞ አባላት የሆኑ አምስት እንግሊዛውያን በናይጄሪያዊው ፓስተር ቲቢ ጆሽዋ አስገድዶ መድፈር እና በግዳጅ ጽንስ ማቋረጥን የሚጨምር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል።-መስል ጥቃቶቹ ምሥጢራዊ ተብሎ በተለየና በሌጎስ ከተማ በሚገኝ አንድ ግቢ ውስጥ ለ20 ዓመታት ሲፈጸም ቆይቷል።-እአአ 2021 ዓ/ም ላይ ሕይወቱ ያለፈው ፓስተር ቲቢ ጆሹዋ ስመ ገናና እና ስኬታማ ሰባኪ የነበረ ሲሆን በመላው ዓለም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተከታዮች ማፍራት ችሎ ነበር።-ቢቢሲ ለሁለት ዓመታት ባደረገው የምርመራ ዘገባ ሰዎችን በሰንሰለት ማሰር እና መግረፍን የሚጨምር አካላዊ ጥቃት መፈጸሙን ከበርካታ የዓይን ምስክሮች ሰምቷል።-በርካታ ሴቶች ሌጎስ ከተማ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት በተደጋጋሚ ሲደፈሩ ቆይተዋል።-በጆሹዋ አስገድዶ መድፈር ምክንያት የተረገዘ ጽንስ በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ በግዳጅ እንደሚወጣ ተጎጂዎች ገልጸዋል።-በተጨማሪም ጆሽዋ “ተዓምራዊ የሆኑ ፈውሶችን” ለሚሊዮኖች በሚሰራጭ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ በማታለል እንደሚያስተላልፍ ተናግረዋል።-በጆሹዋ ጥቃት ከተፈጸመባቸው ሴቶች መካከል ሪያ የተባለች እንግሊዛዊት ሴት ትገኝበታለች። ሪያ ለጆሽዋ ቤተ-ክርስቲያን ስትመለመል ገና የ21 ዓመት ወጣት ነበረች።-ሪያ እአአ 2002 ላይ ቤተ-ክርስቲያኑን ከተቀላቀለች በኋላ በኮንክሪት ግንብ በታጠረው የሌጎሱ ጊቢ ውስጥ ከጆሹዋ “ደቀ መዛሙርት” መካከል አንዷ ሆና ለ12 ዓመታት ኖራለች።-“ሁላችንም ገነት እንደገባ ነበር የምናስበው፤ የነበርነው ግን ሲኦል ውስጥ ነበር። እጅግ አስከፊ ነገሮች ተከስተዋለ” በማለት ለቢቢሲ ተናግራለች።-ሪያ በቲቢ ጆሾዋ ጾታዊ ጥቃት እንደተፈጸመባት እና ለሁለት ዓመታት ለብቻዋ በአንድ ክፍል ውስጥ እንድትቆይ መደረጓን ትገልጻለች።-የሚደርስባት ጥቃት እጅግ አስከፊ ከመሆኑ የተነሳ እራሷን ለማጥፋት ብዙ ሙከራ ማድረጓን ሪያ ትናገራለች።-ዘ ሲኖግ ቸርች ኦፍ አል ኔሽንስ የተባለው ቤተ-ክርስቲያን በመላው ዓለም እጅግ በርካታ ያላቸው ተከታዮች ያሉት ሲሆን ኤማኑኤል የተባለው የቤተ-ክርስቲያኑ የቴሉቪዥን ጣቢያ እና ማኅብራዊ ሚዲያዎቹ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾች አሉት።-እአአ በ1990ዎቹ እና በ2000ዎቹ መጀመሪያ ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ፣ ከደቡብ ምሥራቅ እሲያ እና ከአፍሪካ በቤተ-ክርስቲያኑ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ እና የቲቢ ጆሹዋን “አስደናቂ ፈውስ” ለመመልከት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ሌጎስ ሲተሙ ቆይተዋል።-ምሥጢራዊ ነው በሚባለው በሌጎሱ ግቢ ውስጥ 150 የሚሆኑ ጎብኚዎች ‘ደቀ መዛሙርት’ ተብለው ከጆሹዋ ጋር አብረው ኖረዋል።-አንዳንዶቹ ታዲያ በግቢው የኖሩት ለዐሥርተ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ነው።-ሪያ-ከ25 በላይ የሆኑ የቀድሞው የጆሽዋ ‘ደቀ መዛሙርት’ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ግማሾቹ ከዩኬ፣ ከናይጄሪያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ከናሚቢያና ጀመርን ናቸው።-በጆሽዋ ቸርች ውስጥ ስለተፈጸመባቸው ግፍ፣ ጾታዊ ትንኮሳ፣ መደፈር እማኝነታቸውን ለቢቢሲ አጋርተዋል።-ብዙዎቹ የጥቃት ሰለባዎች በጆሽዋን ቸርች ማምለክ ሲጀምሩ በዐሥራዎቹ ዕድሜ ላይ ነበሩ።-አንዳንዶቹ የዩኬ አማኞች ወደ ሌጎስ የአውሮፕላን ወጪያቸውን ተችለው ነው የሄዱት። ይህም የሆነው የጆሽዋ ቸርች እንግሊዝ ካሉ ቤተ-ክርስቲያነት ጋር በመቀናጀት ነው።-ሪያ እና ሎሎች ቃላቸውን የሰጡ የጆሽዋ ‘ደቀ መዛሙርት’ የነበሩ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የነበራቸውን ቆይታ ከባዕድ አምልኮ ጋር ያቀራርቡታል።-ጄሲካ ከናሚቢያ ናት። በጆሽዋ ቤተ ክርስቲያን ያሳለፈችው ፍዳና ስቃይ ለአምስት ዓመታት የዘለቀ ነው። ፓስተር ጆሽዋ መጀመርያ አስገድዶ ሲደፍራት ገና 17 ዓመቴ ነበር ትላለች። ከዚያ በተከታታይ አብራው ለመተኛት ተገዳለች።-በዚህም የተነሳ አምስት ጊዜ ጽንስ ለማቋረጥ ተገዳለች።-“እነዚህ ውርጃዎች ሕገ ወጥ የሆኑ ናቸው። መድኃኒቶቹ አደገኛ ናቸው። ምናልባትም ልሞት እችል ነበር” ትላለች።-ሌሎች የጆሽዋ ‘ደቀ መዛሙርት’ የሆኑ ሴቶች ከርሱ ጋር አልተኛም በማለታቸው በተደጋጋሚ በኤሌክትሪክ ሽቦ ይገረፉ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግረዋል።-ፓስተር ጆሽዋ በፈረንጆቹ 2021 ሰኔ ወር ላይ ሕይወቱ ሲያልፍ በአፍሪካ ታሪክ ታላቁ ተጽእኖ ፈጣሪና ነቢይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ በሚል ስሙ ናኝቶ እንደነበር ይታወሳል። እርሱ የገነባው የእምነት ‘ሥርወ መንግሥት’ ታላላቅ ፖለቲከኞችን፣ ሥመ ጥር ሰዎችን፣ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ያካተተ ነበር።-በ2014 ደግሞ የርሱ እንግዳ መቀበያ አዳራሽ ተንዶ 116 ሰዎች ሕይወታቸው በመጥፋቱ ዜና መሆን ችሎ ነበር።-ቢቢሲ ከኦፕን ዲሞክራሲ ጋር በመተባበር የዚህን ፓስተር ተጠቂዎች ሲያጋልጥ የመጀመርያ ጊዜ ነው።-የርሱ ‘ደቀ መዛሙርት’ ወደ ሚዲያ ወጥተው ለመናገር ሲደፍሩም የመጀመርያ ነው። ከዚህ ቀደም ይህን ለማድረግ የሞከሩ እርሱ በዘረጋው ሰፊ መረብ አፋቸውን እንዲዘጉ ይደረጉ ነበር።-በርካታ ናይጄሪያ የሚገኙ ቃላቸውን ለቢቢሲ የሰጡ ሰዎች ስለ ጆሽዋ እናጋልጣለን በማለታቸው መደብደባቸውን ተናግረዋል። አንድ ሰው ደግሞ በጥይት ተመቶ ቆስሏል። በጥይት የቆሰለው ግለሰብ በዩትዩብ ጆሽዋን ለማጋለጥ በመሞከሩ ነው።-በመጋቢት 2022 የቢቢሲ ጋዜጠኞች ቡድን በሌጎስ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ቀረጻ ለማድረግ በሞከረ ጊዜ የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂዎች ተኩስ ተከፍቶባቸዋል። የተወሰኑትም ለሰዓታት ታስረው ነበር።-ቢቢሲ በጉደዩ ዙርያ ቤተክርስቲያኑን ለማነጋግረ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ይሁንና በፓስተራችን ዙርያ የሚወራው ሐሰት ነው ሲል አስተባብሏል።-“መሠረተ ቢስ ክስ በነቢይ ቲቢ ጆሽዋ ላይ መፈብረኩ አዲስ አይደለም። አንዱም ክስ ተጨባጭነት የለውም። ” ሲል በጽሑፍ ምላሸ ሰጥቷል።-አራት የእንግሊዝ ዜጎች በቤተ ክርስቲያኑ ስለሚፈጸመው በደል ለዩኬ ባለሥልጣናት አቤት ቢሉም የተወሰደ እርምጃ እንዳልነበረ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-አንድ እንግሊዛዊና ባለቤቱ የደረሰባቸውን ስቃይ በቪዲዮ ጭምር ለቢቢሲ አሳይተዋል። ፖሊስ ነን በሚሉ የጆሽዋ ሰዎች ሽጉጥ ተገደግኖባቸው መረጃውን በናይጄሪያ ለእንግሊዝ ኤምባሲ እአአ 2010 ላይ ሰጥተው ነበር።-ይህ እንግሊዛዊ እንደሚለው ሚስቱ በፓስተር ጆሽዋ በተደጋጋሚ መደፈሯን እና ሌሎች እንግሊዛዊያንም በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ እንደሚገኙ ለኤምባሲው አስታውቆ ነበር።-ይሁንና በናይጄሪያ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ የወሰደው እርምጃ የለም።-አኔካ-የዩኬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጉዳዩ ዙርያ ከቢቢሲ ተጠይቆ የሰጠው ምላሽ የለም። ይሁንና በእንግሊዛዊያን ላይ የትም አገር የሚደርስ የመደፈርና ጾታዊ ጥቃቶችን በዋዛ እንደማይመለከት ገልጿል።-የጆሽዋ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ድረስ ከፈተኛ ተከታዮች አሉት። አሁን ቤተ ክርስቲያኑን የምታስተዳድረው የጆሽዋ ባለቤት የነበረቸው ኤቨሊን ናት። ባለፈው ሐምሌ ምዕመናንን ይዛ ወደ ስፔን ተጉዛ ነበር።-አኔካ ከደርቢ ዩኬ ወደ ጆሽዋ ቤተክርስቲያን ስትሄድ 17 ዓመቷ ነበር። ለቢቢሲ እንደተናገረችው በጆሽዋ ግፍ የተፈጸመባቸው ነገር ግን ወደ አደባባይ ያልወጡ እጅግ በርካታ ሰዎች አሉ።-“ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ውስጣቸው ሊፈተሽ ይገባል። ይህ ሰው ለዚህን ያህል ዘመን እንዴት ግፍ እየፈጸመ ምንም ሳይባል ቀረ የሚለው ከርሱ ጋር የሚሰሩ አብያተ ክርስቲያናትንም ሊያስጠይቅ ይገባል” ትላለች።
በአየር ንብረት ለውጥ እና በግጭት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለችግር በመጋለጣቸው እርዳታን እንደሚሹ እየተነገረ ነው።-በዚህም ሳቢያ በአገሪቱ ውስጥ ከ20 ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) ገልጿል።-የአገር ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ እና የግለሰቦች ስብስብም ለችግር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለመርዳት የተለያዩ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ። ካጋጠመው ችግር አንጻር አሃዞች ምን ያሳያሉ?
የፎቶው ባለመብት THIS IS LEBANON/FB PAGE-መጋቢት 02/2015 ሥልጠና ተጀምሯል። ሥልጠናው የሚሰጠው በነጻ ነው። የዕድሜ ገደብም አልተቀመጠለትም።-ለዚህም የሚሆኑ ከ70 በላይ የሥልጠና ማዕከላት ተዘጋጅተዋል።-ቅድሚያ የሚሰጠው ከዚህ በፊት ወደ ተለያዩ አረብ አገራት ደርሰው ለተመለሱት ነው።-ይህ በውጭ አገራት የሥራ ዕድል ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ሥልጠና ነው።-ማንኛውም ሠርቶ መለወጥ የሚፈልግ ሰው ሥልጠናውን ወስዶ ወደ ውጭ አገር ሄዶ መሥራትም ይችላል ተብሏል።-ሥልጠናው ቋንቋን ጨምሮ በመዳረሻ አገራት ያለውን ባህል፣ ሃይማኖት እና የሥራ ሁኔታን የሚያጠቃልል ነው።-ከሥልጠናው በኋላ ምዘና የሚኖር ሲሆን ብቁ ለሆኑትም የምስክር ወረቀት ይሰጣል።-በመጀመሪያው ዙር 67 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ሥልጠናውን አጠናቀዋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ 68 ሺህ የሚጠጉት እየተሳተፉ ነው።-ይህ እየተከናወነ ያለው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በተለይም ወደ ሳዑዲ አረቢያ 500 ሺህ ቤት ሠራተኞችን ለመላክ ስምምነት በመኖሩ መሆኑን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ደጋግመው ዘግበዋል።-የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አበበ አለሙ ግን በተቋሙ በኩል ከሳዑዲ አረቢያ የቀረበ ቁርጥ ያለ ቁጥር አለመኖሩን ለቢቢሲ ተናግረዋል።-“500 ሺህ በሚል በማኅበራዊ ሚድያ የሚዘዋወረው ምንጩ የሚታወቅ አይደለም” ሲሉም ያሰምሩበታል።-መሥሪያ ቤቱ በተያዘው በጀት ዓመት 3.7 ሚሊዮን የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዷል። “ከዚህ ውስጥ 100 ሺህ ብቻ ነው በውጭ አገር ተጠቃሚ እናደርጋለን ብለን ያቀድነው” ሲሉም የመንግሥትን ዕቅድ ያብራራሉ።-በኮቪድ ወረርሽኝ ተቋረጠ እንጂ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር የነበረው ስምምነት እስከ አውሮፓውያኑ 2018 የተደረሰ ነበር።-“የሠራተኞች መሠረታዊ መብት እንዲጠበቅ በሚል ነው አሁን እንደ አዲስ እየተነሳ ያለው” ብለዋል ኃላፊው።-ለሥራ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን የሥራ ቆይታቸው በሚፈጽሙት ስምምነት መሠረት ከሁለት እስከ ሦስት ዓመት ሊቆይ የሚችል ነው።-ይህ ስምምነት በቅርቡ ከሳዑዲ የተመለሱትን አይመለከትም። ለዚህም ሕጋዊ አይደላችሁም በሚል በመመለሳቸው ምክንያት መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው “ወደ ሌላ አገር መሄድ ግን ይችላሉ” ሲሉ ገልጸዋል።-ለጊዜው ሳዑዲ አረቢያ ያቀረበችው ፍላጎት የቤት ሠራተኞችን ለመውሰድ ነው።-እንደ አቶ አበበ ገለጻ “ከረዥም ጊዜ አኳያ ግን የሠለጠኑ እና በከፊል የሠለጠኑትን ወደ ውጭ ለመላክ ቅድመ-ዝግጅት አለ። የተጀመረው ሥልጠናም የዚያ አካል ነው።”-“ስምምነቱ አሠሪዎችን ይቆጣጠራል”-ከዚህ ቀደም በመንግሥት፣ በሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ወይም በግል በሚደረግ ጥረት የሥራ ዕድሉ ይገኝ ነበር። በዚህ ውስጥ የመንግሥት ተሳትፎ ‘ብዙ’ አልነበረም። አሁን ግን በመንግሥት ዕውቅና የሚሄዱበት ዕድል ነው የተመቻቸው።-የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ከሰሞኑ እንደተናገሩት ከዚህ በፊት ከኳታር፣ ከዮርዳኖስ፣ ከሳዑዲ አረቢያ እና ከዩናይትድ አረብ ኢሚሬቶች ጋር ሕጋዊ ስምምነት እንዳለ ጠቁመው፤ ወደ አፍሪካ እና የአውሮፓ አገራትም ወደፊት እንደሚኖር አስታውቀዋል።-ኢትዮጵያ ለዜጎቿ የተሻለ ክፍያ፣ መብት እና ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ ከተለያዩ አገራት ጋር መስማማቷን የጠቀሱት ሚኒስትሯ፣ መንግሥትም በውጭ አገራት የሚሠሩ የዜጎቹ መብት እና ጥቅም እንዲከበር ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል።-“[የተደረሰው ስምምነት] አሠሪዎችን ይቆጣጠራል። አንድ ቀንም ደመወዛቸው ሳይከፈላቸው ማደር የለበትም። ደኅንነታቸው እና ጤንነታቸው እንዲጠበቅ ይደረጋል” ሲሉ አቶ አበበ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-መንግሥት ሕገወጥ የተባሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ መልሷል-ባንቺ ይመር የእኛ ለእኛ በስደት ማኅበር መሥራች ናት። ባንቺ አሁን የምትገኘው ካናዳ ቢሆንም በሊባኖስ ለሰባት ዓመት ያህል በሰው ቤት ሠርታለች።-ማኅበሩ ትኩረቱን በሊባኖስ በሚኖሩ የቤት ሠራተኛ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ ቢያደርግም፣ በሌሎች አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞችንም ያግዛል።-የእነዚህን ዜጎች የሰብዓዊ መብት ማስከበር እና የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ መሠማራቱን ትገልጻለች።-መንግሥት በተለይም ወደ ሳዑዲ አረቢያ ቤት ሠራተኞችን ለመላክ መዘጋጀቱን ተገቢ አይደለም ስትል ትሞግታለች።-ሳዑዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ከአሠሪዎቻቸው በተጨማሪ በመንግሥት ደረጃ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ታነሳለች።-“ከአስር ዓመታት በላይ የዘለቀ የጉልበት ብዝበዛ፣ እስር ቤት ውስጥ ማሰቃየት፣ ንብረታቸውን ነጥቆ ከአገር ማባረርን ጨምሮ ብዙ ዓይነት ጥሰቶች እየተፈጸመባቸው ነው። [የሳዑዲ መንግሥት] በሚያሠማራቸው የፀጥታ ኃይሎች፣ በእስር ቤት ጥበቃዎች ነው ዜጎቻችን የሚዘረፉት እና የመብት ጥሰት የሚፈጸምባቸው” በማለት ይህ መጀመሪያ መፈታት ያለበት መሆኑን አጽንኦት ሰጥታ ትጠቅሳለች።-ሌላው የምታነሳው ስጋት ካፋላ የተሰኘውን ሠራተኞችን ወደ አገር ለማስገባት እና ለመቅጠር የሚያገለግል ሥርዓት ነው። ከሠራተኞች ቅጥር ጋር በተያያዘ የዋስትና ወይም “የስፖንሰርነት ሥርዓት” ነው።-በዚህ አሠራር አንድ አሰሪ ከሌላ አገር የሚቀጥራትን የቤት ሠራተኛ በተመለከተ በርካታ መብቶች እንዲኖረው ያደርጋል።-አንዲት ሠራተኛ ባስመጣት ቀጣሪ ቁጥጥር ስር ብቻ ሆና ነው ባለችበት አገር ውስጥ መሥራት የምትችለው። ነገር ግን ከአሰሪዎቿ ቤት ወይም የሥራ ቦታ ከወጣች ሕገ ወጥ ስደተኛ መሆንን ያስከትልባታል ይህ የካፋላ ሥርዓት።-ይህ ቁጥጥር ደግሞ ሠራተኛዋ በቀጣሪዎቿ በደል እና ጥቃት ቢደርስባት እንኳን ሌላ አማራጭ እንዲኖራት የማያደርግ አስገዳጅ እና የማይቀየር ነው።-ይህ የካፋላ ሥርዓት በሊባኖስ፣ ዮርዳኖስ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ በኩዌት፣ በባህሬይን፣ በኦማን፣ በሳዑዲ አረቢያ እና በሌሎችም የባሕረ ሰላጤው አገራት ይተገበራል።-በዚህ ሕግ አማካኝነት ሠራተኞቹ መደራጀት አይችሉም። በአጠቃላይ ሕይወታቸው በአሠሪያቸው ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ በማድረጉ ለጥቃት እንዲጋለጡ ማድረጉን የሚያሳዩ በርካታ ጥናቶች አሉ።-ስደተኛ ሠራተኞች ከመደበኛው የአገራቱ የአሰሪ እና ሠራተኛ ሕግ የተገለሉ ናቸው። ይህ በልማድ ሳይሆን በሕግ የተደነገገ ነው።-“በዚህ የካፋላ ሥርዓት ዜጎቻችን ሳዑዲ የሚገቡት በስፖንሰሮቻቸው ስም ነው። እየታዩ ያሉትም እንደባርያ በመሆኑ፣ ዘመናዊ ባርነት ነው” ትላለች ባንቺ።-ኤጀንሲዎች ወይም ቀጣሪዎቻቸው “[ሠራተኞቹ] ከኤርፖርት እንደወጡ ነው መታወቂያቸውን፣ ፓስፖርታቸውን እና ያላቸውን ሰነድ ፈትሽው የሚቀበሉት። ይህንን እንዳያደርጉ የአገሪቱ መንግሥት ቢከለክልም ማንም አያከብረውም” ስትል ስጋቷን ታስቀምጣለች።-አቶ አበበ አለሙ እንደሚሉት አሁን ተግባራዊ እየተደረገው አሰራር “ዜጎቻችን በአግባቡ ሄደው በሚያጋጥማቸው ሁኔታ ባይስማሙ እንኳን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የሚደረገበት ሁኔታ ተዘጋጅቷል” ይላሉ።-“ለሳዑዲ ብቻ ብለን ያዘጋጀነው ነገር የለም። መካከለኛ ምሥራቅ በሚል ነው እየተሠራ ያለው። በዚህም ሕገ ወጥ አሠራርን ለመከላከል እና አገርም ከዚህ እንድትጠቀም ማድረግ መቻል ነው” ብለዋል አቶ አበበ አለሙ።-ወደ ውጭ አገራት በመሄድ ከሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በተያያዘ ሌላው የሚነሳው ጥያቄ፣ የሚያገኙት ደመወዝ ከሌሎች አገራት አቻ ሠራተኞች አንጻር ዝቅተኛ መሆኑ ነው።-በሳዑዲ አረቢያ በነበራቸው ቆይታ ከፍተኛ የሠራተኛ ፍላጎት መኖሩን ማረጋገጣቸውን የጠቀሱት ወይዘሮ ሙፈሪያት በበኩላቸው፤ ሠራተኞች ትርጉም ያለው የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግ፣ መብትና ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ ተነጋግረናል ብለዋል።-ስምምነቱን ከዚህ በፊት ሠራተኞች በሕገወጥ መንገድ ሲኖሩ ሕጋዊ ከለላ እንዳይኖራቸው ይደረጉ የነበሩትን ችግሮች እንደሚቀርፍ አብራርተዋል።-የዜጎች ስምሪት እንደ ከዚህ ቀደሙ በግለሰቦች መልካም ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን፤ መንግሥት ለመንግሥት በሚደረግ ጠንካራ የድጋፍ አና የክትትል ሥርዓት ላይ የተመሠረተ ይሆናል ብለዋል።-በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በሕገወጥነት በተለያዩ አስርቤቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ የመብት ድርጅቶች በተደጋጋሚ ያወጧቸው ሪፖርቶች ያመለክታሉ።-ባንቺ እንደምተለውም በተለያዩ አገራት ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ያሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ እጅግ የከፋ መሆኑን በመጥቀስ፣ “የነበረው ችግር ሳይፈታ ግማሽ ሚሊዮን ዜጎችን በድጋሚ መላኩ ተገቢ አይደለም” ትላልች።-“የኢትዮጵያም ሆነ የሳዑዲ መንግሥታት መብታችሁን እጠብቃለሁ ቢሉም፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሠራተኞች ያሉበትን ሁኔታ እና ችግራቸውን ለማወቅ የሚስችል አቅም የላቸውም።”-ባንቺ ጨምራም ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ስምምነት የፈጸሙ አገራት ቢኖሩም የዜጎቻችው ሕይወት ምንም ዓይነት መሻሻል እንዳላሳየ ትናገራለች።-“አንድ ሰው ቤት ውስጥ በር ተቆልፎበት ከቤት የማይወጣ ከሆነ፤ ስልክ የሚከለከል ከሆነ ምን እንደገጠመው ማወቅ አይቻልም። ስለዚህም የዜጋችን መብት እና ጥቅም ለመጠበቅ አስቸጋሪ ይሆናል” ትላለች።-ከዚያ ይልቅ ከዚህ ቀደም በመብት ድርጅቶች ብዙ የተባለለት እና “የሠራተኞችን መብት ይገፋል” በሚል አገራቱ እንዲያስወግዱት ሲጠየቁ የቆየው “የካፋላ ሥርዓት መነሳት ወሳን ነው” ትላለች ባንቺ።-“የካፋላ ሥርዓቱ ከተነሳ ማንኛውም ሠራተኛ ቤት ተከራይተው ሥራቸውን ሰርተው ወደ ቤታቸው የሚመለስበት፤ ቀጣሪዎቹ ጋር ሆኖ መሥራት ከፈለገም በራሳቸው የሚወስኑበት ዕድልን ይፈጥራል።”-በዚህም የመኖሪያ እና የሥራ ፈቃዳቸው እንዲሁም ሁሉም ሕጋዊ ሰነዶቻቸው በእጃቸው ላይ ስለሚሆኑ ለጥቃት እና ለበደል የመጋለጥ ዕድላቸው በእጅጉ የቀነሰ ይሆናል የምትለው ባንቺ፣ እነዚህ ነገሮች በቅድሚያ መስተካከል እንዳለባቸው ታሳስባለች።-በዚህ ረገድ በመዳረሻ አገራት የሚገኙ ኤምባሲዎች ሠራተኞች ያሉበትን ሁኔታ ቁጥጥር እና ክትትል ማድረግ የሚያስችላቸው ሥርዓት መዘርጋቱን ደግሞ ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ተናግረዋል።
የፎቶው ባለመብት Reuters-የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል-አምስት አስርት ዓመታት ለሚሆን ጊዜ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ ጉልህ ሚና የነበረው ህወሓት ለሁለት ዓመታት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ጦርነት ውስጥ ቆይቷል። ጦርነቱ በአጠቃላይ በአገሪቱ ላይ በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል ላይ ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመትን አስከትሏል።-በጦርነቱ ወቅት በትግራይ በኩል ዋነኛ ተዋናይ የነበረው ህወሓት በሽብር ቡድንነት ተፈርጆ ሕገወጥ ሆኖ ቢቆይም፣ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በተደረሰው የሰላም ስምምነት አማካይነት ይህ ፍረጃው ተነስቶለታል። ቢሆንም ግን አሁንም የተገፈፈውን ሕጋዊ ዕውቅና አላገኘም።-ለበርካታ አስርት ዓመታት ትግራይ ክልልን በብቸኝነት ሲያስተዳደር የቆየው ህወሓት፣ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት በፌደራል መንግሥቱ ሥር ሌሎችንም በማካተት ጊዜያዊ አስዳደር ሲያቋቁም፣ የቀድሞው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቦታቸውን ለቀዋል።-የትግራይ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳደር እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ስለፓርቲያቸው እና በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ዋና ዋና ነጥቦቹን እነሆ፡-ቢቢሲ፡ የፕሪቶሪያ ስምምነትን ተከትሎ ጊዜያዊ መንግሥት ለመመሥረት 5 ወራት ወስዷል።ይህ የሆነው ደግሞ በህወሓት አባላት መካከል ስምምነት ባለመኖሩ ነው ተብሏል። ይህ ከነበረ ችግሩ ለምን እርስዎ ሥልጣንዎን አልለቀቁም?-ዶ/ር ደብረጽዮን፡ የእኔ ጉዳይ ለብቻው በራሱ ተነጥሎ የሚታይ ጉዳይ አይደለም።ማነው [በእኔ መነሳት ጉዳይ] የሚወስነው የሚለው ነው ዋናው ነጥብ። የሚወስነው ፓርቲው ነው። አመራር ነው የሚወስነው።-የእኔ የግለሰብ ፍላጎት ከሆነ ያ ሌላ ጉዳይ ነው። የድርጅታችን አሰራርም አይደለም። በእኛ አሰራር ሥልጣን የግል ፍላጎት ስላልሆነ። ማን ይቀጥል ማን አይቀጥል የሚለውን የሚወስነው ህወሓት እንጂ በግለሰብ ፍቃድ የሚመለስ ጥያቄ አይደለም።-ቢቢሲ፡ እርስዎ የሥልጣን ፍላጎት ስላልዎ እኔ ካልሆንኩ ብለው ከማስቸገርዎም በላይ፣ ድምጽ ተሰጥቶኛል ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘንድ መሄድዎ ነው የሚነገረው። ጠቅላይ ሚኒስትሩም “እርስዎ አይሆኑም፤ ሥልጣን ለወጣቶች ይስጡ” ብለው እንደመለስዎ ነው የተሰማው።-ዶ/ር ደብረጽዮን፡ ተናገርኩ እኮ። ውሳኔው የእኔ ሳይሆን የፓርቲው ነው። እኔ ካልሆንኩ የሚባል ነገር የለም። ምርጫ እኮ ተካሄደ። 38 ይቀጥል አለ፤ 3 ተቃውሞ ነበር።በድምጽ ብልጫ ነው የሚጸድቀው። በአሰራሩ መሠረት ነው የሄድነው። ዐቢይ ይህን ነበር ያልተቀበለው።-በኋላ ላይ ሌሎች ምሁራን፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ቢመሩ የሚል ነገር መጣ። ይህን ማዕከላዊ ኮሚቴ ነው ያጸደቀው አልን። ከዚያ በኋላ ነው ህወሓት እና ፌዴራል መንግሥት ውይይት ያደረገው። ተመካክረን ብንሰራ ይሻላል ብለን ወጣት ቢሆኑ ተቃውሞ ስላልነበረን በሐሳቡ ተስማማን። ነገሩን በቀና ልብ ወስደን ምርጫ አድርገን በመጨረሻ ጌታቸው ተመረጠ።-ቢቢሲ፡ ከዚያ ሁሉ እልቂት በኋላ ህወሓት ለምንድነው ከሥልጣን ያልወረደው? ለዚህ ሁሉ ለደረሰው እልቂት ማነው ኃላፊነት የሚወስደው?-ዶ/ር ደብረጽዮን፡ አሁንም እራሳችን በመከላከል ላይ ነው ያለነው። የትግራይ ሕዝብ አሁንም በወራሪዎች ሥር ነው የሚገኘው። ምን ጎደለ?፣ ምንድነው ያጠፋነው? ብለን እንገመግማለን።ይህ የራሱ ጊዜ አለው።-ወደ ሥልጣን የሚያወጣንም፣ ከሥልጣን የሚያወርደንም ሕዝብ ነው። ማንም ሰው መጥቶ 'ውረድ' ስላለ ወይ ደግሞ ማንም ሰው መጥቶ 'በቃ ተው' ስላለ ሥልጣን አይለቀቅም።-ህወሓትን ሕዝብ እኮ ነው የመረጠው። በትግራይ ሕዝብ ትግራይ ውስጥ ነው የተመረጠው፣ ስለዚህ ሕዝቡ ነው የሚያወርደው።-የፕሪቶሪያ ስምምነት ሌላ ነው። ለሰላም ሲባል የተከፈለ ዋጋ ነው። ከዚህ ሌላ ግን ለምን ከሥልጣን አልወረዳችሁም የሚባለው ወዴት ነው ከሥልጣን የምንወርደው? ኃላፊነት የሰጠን እኮ ሕዝቡ ነው።-ቢቢሲ፡ ሕዝብ መርጦናል ካላችሁ ሕዝቡ ድምጽ የሰጣችሁ ከአደጋ እንድትጠብቁት ነበር ። ሆኖም ብዙ ሕዝብ ህወሓት ከዚህ አደጋ ሊጠብቀን አልቻለም ይላል፤ ይህ እርስዎ ከሚሉት ነገር ጋር አይጋጭም?-ዶ/ር ደብረጽዮን፡ አይጋጭም። ደጋግሜ እንደገለጽኩት ሁሉንም ነገር ገና ለግምገማ አላቀረብንም። ምን ጎደለ? ማን አጠፋ? የሚለው ወደፊት በግምገማ የሚታይ ነው።-አላዳናችሁንም የሚባለው ነገር ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ ግንባሩን ነው የሰጠው። ሳይሰስት ነው የመከተው። ከቀድሞ አመራሮች ጀምሮ መስዋዕት ሆነዋል። የሚችለውን እና የሚገባውን ሁሉ አድርጓል። እንዲያም ሆኖ ግን አጉድሏል ከተባለ በግምገማ የሚታይ ነው የሚሆነው።-ቢቢሲ፡ ህወሓት ሕጋዊነቱን ለመመለስ ከምርጫ ቦርድ ጋር ስምምነት ላይ አልደረሰም። ይህ ጉዳይ እንዴት ነው የሚፈታው?-ዶ/ር ደብረጽዮን፡ በአዲስ መልክ ተመዝገቡ ነው የሚሉት። በአዲስ መልክ ልንመዘገብ አንችልም። 50 ዓመት የደፈነ ፓርቲ አዲስ ሕጻን ልጅ ሆኖ እንደ አዲስ ፓርቲ ሊመዘገብ አይችልም። ይህ ተቀባይነት የለውም።-በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት እኛን ፌዴራል መንግሥት እውቅና ሰጥቶናል። እውቅና ሰጥቶም ነው ሊፈራረም የቻለው። አሸባሪ ነው የፈረመው ቢሉም፣ አሸባሪም ብለው እውቅና ሰጥተውን ተፈራርመናል። አሸባሪነቱን በኋላ እናየዋለን፣ መፈረም ነው የሚበጀን ብለን ተፈራርመናል።-ይህ ቀድሞውንም በስምምነት ያለቀ ጉዳይ ነው። በኋላ የተወካዮች ምክር ቤት ከአሸባሪነት ስሙን ፍቆታል። የህወሓት አመራሮች እስር ቤት ያሉትም ክሳቸው ተነስቷል። ምርጫ ቦርድ ፍርድ ቤት አቤት እንድንል ነው የሚፈልገው። የፓርቲያችን ማዕከላዊ ኮሚቴ የወሰነው ደግሞ ፍርድ ቤት አንሄድም መፍትሔው ፖለቲካዊ ነው ብሎ ወስኗል። እንደ አዲስ የመመዝገብ ነገረ የማይታሰብ ነው።-ቢቢሲ፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህወሓት ሃብት ተወርሶ ዕዳው እንዲከፈል እና የተረፈ ካለ ደግሞ ለሥነ ዜጋ ትምህርት እንዲውል መወሰኑ ይታወሳል። ይህ የታገደው ገንዘብ መጠኑ ስንት ነው?-ዶ/ር ደብረጽዮን፡ በባንክ የነበረው ገንዘብ 70 ሚሊዮን ይሆናል።-ቢቢሲ፡ 70 ሚሊዮን ብር ነው ወይስ ዶላር?-ዶ/ር ደብረጽዮን፡ እንዴ! በኢትዮጵያ ባንክ እኮ ነው ያለው። ውጭ አገር አይደለም እኮ። ብር ነው እንጂ።-ቢቢሲ፡ በእርስዎ የመሪነት ዘመን ከግማሽ ሚልዮን በላይ የትግራይ ተወላጆች ሕይወታቸው እንዳለፈ ይነገራል፤ የትግራይ ሕዝብ እርስዎን በምን የሚያስታውስዎት ይመስለዎታል? እርስዎስ ምን ዓይነት መሪ ነኝ ብለው ያስባሉ?-ዶ/ር ደብረጽዮን፡ ስለዚህ ጉዳይ የምገልጽበት ጊዜ ነው ብዬ አላስብም።-የፎቶው ባለመብት tplf/fb-የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል-የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች ጉዳዮችም ላይ ከቢቢሲ ትግርኛ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ነበር።-የፕሪቶሪያው ስምምነት-ዶ/ር ደብረጽዮን ስምምነቱ አገሪቱን ከከባድ ጦርነት ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ምዕራፍ ያሸጋገራት መሆኑን በመግለጽ፣ አንዳንድ ተግባራዊ የተደረጉ እና አሁንም በሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።-“ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሆኗል ማለት አይቻልም፤ ነገር ግን ሰላሙን ለማጠናከር በፌዴራል መንግሥት እና በትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት የተወሰዱ ጥሩ እርምጃዎች አሉ” ብለዋል።-ነገር ግን በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የትግራይ ኃይሎች ትጥቅ ከፈቱ በኋላ የፌደራል መንግሥት የኤርትራ ጦርን እና የአማራ ኃይልን ከትግራይ የማስወጣት ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም፣ እስካሁን ተፈጻሚ ባለመሆኑ የተፈናቀሉ ሰዎች ስቃይ ውስጥ እንደሚገኙ አመልክተዋል።-የተፈናቀለው ሕዝብ-በደም አፋሳሹ ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ላለፉት ሦስት ዓመታት በተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ በአስከፊ ሁኔታ እየኖሩ መሆኑን የሚገልጹት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ “ወራሪዎች” ብለው በገለጿቸው የአማራ እና የኤርትራ ኃይሎች ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸውና ወደ ንብረታቸው ሊመለሱ አልቻሉም ብለዋል።-“መሬት ላይ የተለወጡ ነገሮች አሉ፤ አዲሶቹ ሰፋሪዎች ሊወጡ ይገባል” በማለት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ እንዲችሉ የትግራይ አስተዳደር ፖሊስ እና የፀጥታ ኃይሎች ወደ አካባቢው ገብተው በወረራ ሥር ከቆየው ሕዝብ እና የአገር ሽማግሌዎች ጋር መመካከር እና መግባባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።-“[ከጦርነቱ በኋላ] የገቡ ሰፋሪዎች ሳይለቁ [እነሱን] መደረብ አይቻልም። ሰፋሪዎች መጀመሪያ አካባቢውን መልቀቅ አለባቸው። አስፈላጊው ሎጅስቲክስ ተዘጋጅቶለት ሕዝቡም ተደራጅቶ መግባት አለበት” በማለት ያሉትን የአፈጻጸም ዝርዝር ጠቁመዋል።-የምዕራብ እና የደቡብ ትግራይ ዕጣ ፈንታ?-ዶ/ር ደብረጽዮን የምዕራብ እና የተወሰነ የደቡብ ትግራይ አካባቢን ተቆጣጥረው የሚገኙት የአማራ ኃይሎች እና የክልሉ አስተዳደር አዳዲስ ሰፈራዎች እያቋቋሙ እና መታወቂያ እየሰጡ እንዳሉ መረጃ እንዳላቸው በመግለጽ፣ ተቃውሟቸውን ለፌደራል መንግሥት እንደገለጹና “ጊዜ ስጡን እንፈታዋለን” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ይገልጻሉ።-በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልኡካን ቡድን በቅርቡ ባሕር ዳርን በጎበኘበት ወቅት መሬት ላይ መፈጸም ስላለበት ነገር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየቱንም ተናግረዋል። ግንኙነቱ በፌዴራል መንግሥት ሸምጋይነት እንደሚካሄድ እና የፕሪቶሪያን ስምምነት እንደሚያጠናክርም አስረድተዋል።-የኤርትራ ጦር ትግራይ ውስጥ ስለመኖሩ-ዶ/ር ደብረጽዮን እንደገለጹት የኤርትራ ጦር በምሥራቃዊ እና በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ ይገኛል።-“የኤርትራ ጦር በአልጀርስ ስምምነት ተወስኖልኛል በሚላቸው አካባቢዎች ብቻ ሳይሆን በትግራይ መሬት ውስጥ በእገላ፣ በዓዲ አርባዕተ እና በሰሜን ምዕራብ ድንበሮች አለ” ብለዋል።-በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተካሄደው የድንበር ጦርነት ማዕከል የነበረችው ባድመ በአሁኑ ጊዜ በኤርትራ ጦር ይዞታ ሥር የምትገኝ ሲሆን፣ ዶ/ር ደብረጽዮን የኤርትራ ሠራዊት ከባድመም እንዲወጣ ይፈልጉ እንደሆነ እና የአልጀርስ ስምምነትን ጉዳይ ተጠይቀው ነበር።-“የድንበር ጉዳይ የኤርትራ እና የትግራይ ጉዳይ አይደለም። የድንበር ጉዳይ የፌደራል መንግሥቱ ጉዳይ ነው። ነገር ግን የትግራይ መሬት ላይ ስላሉ ከትግራይ መውጣት አለባቸው። በምንም መልኩ የድንበር ጥያቄ በጉልበት የሚፈታበት ሁኔታ መኖር የለበትም፤ የፌደራል መንግሥትም በዚህ ነው የሚያምነው።-ስለዚህ በድንበር ጉዳይ የሚደራደረው የፌደራል መንግሥት ነው፤ አሁን ድንበር የማጥራት ጉዳይም አይደለም።በኃይል የተወረረ አካባቢ መልቀቅ አለበት! የአልጀርስ፣ የባድመ የሚባል ነገር አሁን ሊመጣ አይችልም። በጉልበት ሳይሆን በሕግ እና በሥርዓት ተግባብተን ነው መፈጸም ያለበት። አቋማችን በኃይል የተያዘ ቦታ መኖር የለበትም ነው” ካሉ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች ለቀው የሚወጡበት የጊዜ ገደብ እንዳላስቀመጠ ተናግረዋል።-ከኤርትራ ፕሬዝዳንት ስለመታረቅ-ወታደራዊውን መንግሥት ለመጣል አጋር የነበሩት ህወሓት እና የኤርትራ ነጻ አውጪ በድንበር ይገባኛል ምክንያት ደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ከገቡ በኋላ በጠላትነት ፍጥጫ ውስጥ ቆይተዋል።-በሁለት ዓመቱ ጦርነት ወቅትም የኤርትራ ሠራዊት ከፌደራሉ መንግሥት ኃይሎች ጎን ተሰልፎ መዋጋቱ ይታወቃል። ቢሆንም ህወሓት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ሰላም ሲያወርድ የኤርትራ መንግሥት ተሳታፊ አልነበረም። ህወሓት ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር ለመታረቅ ይፈልግ ይሆን?-"የትግራይ መሪዎች ወደ ጦርነቱ ከመግባታችን በፊትም ጉዳዮቻችንን በሰላማዊ፣ በሕጋዊ እና በሥርዓት መፍታት አለብን ብለን ከሁሉም አካላት ጋር እየሰራን ነበር” በማለት እንደ ሕዝብ እና ፓርቲ ከኤርትራ ጋር ሁሉም ነገር በሰላም እንዲፈታ ፍላጎት እንደነበራቸው ዶ/ር ደብረጽዮን አስረድተዋል።-ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ከኤርትራ ጋር ለመታረቅ የተወሰደ ምንም ዓይነት እርምጃ ባይኖርም፣ አገራዊ ግንኙነቱ በፌዴራል መንግሥት በኩል እንደሚተገበር በመጠቆም “የኤርትራ ጦር አሁንም ድረስ በትግራይ ግፍ እየፈጸመ ስለሆነ የሰላም ዝግጁነቱ እንዲጠናከር ሠራዊቱ ከትግራይ መውጣት አለበት” ብለዋል።-የተሰረቀ ሰብአዊ እርዳታ-ባለፈው ግንቦት ወር የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ለተረጂዎች የላኩት የእርዳታ አቅርቦት ተሰርቆ ላልተገባ አላማ መዋሉ እና ለገበያ መቅረቡን ገልጸው ነበር።-ከዚህ ጋር ተያይዞ ማጭበርበር ያጋጥም እንደነበር እና ይህንንም ለማስተካከል በየጊዜው እርምጃዎች ይወሰዱ እንደነበር ዶ/ር ደብረጽዮን ተናግረዋል።-በእርሳቸው የአመራር ወቅት የተፈፀመውን የእርዳታ ምግብ ስርቆት በተመለከተም በእርዳታው ሥርጭት ወቅት ማጭበርበር እና የሕዝብ ቅሬታዎች እንደነበሩ፣ አስፈላጊው ማጣራት እየተደረገ ተገቢ የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ እንደነበርም ተናግረዋል።-በዚህ ጦርነት የተከፈለው የሰው ሕይወት-በትግራይ በኩል በጦርነቱ በአጠቃላይ ስንት ሰው እንደሞተ የተጠየቁት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ “በጊዜው ይገለጻል” በማለት ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።-ጊዜያዊ አስተዳደሩ የትግራይ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ለማሳወቅ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነም ተናግረዋል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኢትዮጵያ አራተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ ሙሌትን አከናውኛለሁ ማለቷን ተከትሎ ግብጽ ከናይል ወንዝ የማገኘው የውሃ መጠን አቅርቦት ላይ አደጋ የጋረጠ ነው ስትል ከሳለች።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቀናት በፊት የታላቁ የህዳሴ ግድብ አራተኛ እና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።-በግድቡ የውሃ ሙሌት እና ከግድቡ በሚለቀቀው የውሃ መጠን ላይ ህጋዊ እና አስገዳጅ ሶስትዮሽ ስምምነት ካልተፈረመ ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌቱን ማከናወን እንደሌለባትም ግብጽ ስትወተውት መቆየቷ ይታወሳል።-ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የናይል ወንዝ 85 በመቶ የሚሆነውን የውሃ መጠን ድርሻ በሚገብረው አባይ ወንዝ ላይ የተገነባ ነው።-የአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ከሱዳን ጋር ከሚዋሰነው ድንበር በስተደቡብ 30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።-ከ1.6 ኪሎሜትር በላይ እርዝማኔ እና 145 ሜትር ከፍታ አለው።-ሙሉ በሙሉ ግንባታው ያልተጠናቀቀው የህዳሴ ግድብ 12 ዓመታትን ያህል ፈጅቷል።-4.2 ቢሊዮን ዶላር ያህል የአገሪቷ እና የህዝቧ አንጡራ ሃብት የፈሰሰበት ግድብ የታላቋን ለንደን የሚያህል ስፋት አለው።-ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን እየገነባች ያለችው በጨለማ ውስጥ ያለው 60 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽፋን እንዲያገኝ ነው።-ከዚያም አልፎ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም በእጥፍ በማሳደግ ለተቋማት የማያቋርጥ የኃይል አቅርቦት ለማቅረብ እና ልማቱን በማሳደግ ተስፋ ተጥሎበታል።-ለጎረቤት አገራቱ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ኤርትራን የመሳሰሉ አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙበት እንደሆነም ተነግሯል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-ወደ 107 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ግብጽ ለውሃ እቅርቦትም ሆነ ለህልውናዋ መሰረት የናይል ወንዝ ነው ትላለች።-ብዙ ውሃ የሚያስፈልገውን ጥጥ ለማምረት ጨምሮ ለተለያዩ እርሻዎችም ሆነም ለመኖሪያ ቤቶች የሚጠጣ ውሃ የምታገኘው ከናይል ወንዝ ነው።-ይህ ብቻ አይደለም ግብጽ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት የገነባችውን አስዋን ግድብንም ሙሌት የሚካሄድበትን የናስር ሃይቅንም ለመሙላት የምትጠቀመው ናይልን ነው።-48 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሱዳንም በናይል ወንዝ ላይ ጥገኛ ናት።-ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ ግብጽ እና ሱዳን እያነሱ ያሉት ስጋት አገራቱ የሚያገኙትን የውሃ መጠን አቅርቦት ኢትዮጵያ እንድትቆጣጠር ያስችላታል የሚል ነው።-ሌላኛው ግብጽ የምታነሳው ቅሬታ ዝናብ በሚቀንስበት ወቅት ወይም ድርቅ ቢያጋጥም ኢትዮጵያ ለታችኛው ተፋሰስ አገራት በቂ ውሃ እንደሚፈስ ዋስትና ትስጥ የሚለውን ነው። በተጨማሪም በነዚህ ወቅቶች ኢትዮጵያ ግድቡን ኃይል ለማመመንጫነት ሙሉ አቅሙን ትጠቀማለች የሚለውም ላይ ያላትን ስጋት ታነሳለች።-“የኢትዮጵያ የተናጠል እርምጃዎች የታችኛውን ተፋሰሰስ አገራት ጥቅምና መብት እንዲሁም የውሃ ደህንነታቸውን ችላ ያለ ነው” ሲልም ነው የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሙሌቱ በኋላ በመግለጫው ያስታወቀው።-ግብጽ ከናይል የማገኘው የውሃ መጠን አቅርቦት 2 በመቶ ከቀነሰ በመስኖ የለማ 200 ሺህ ሄክታር መሬትን የሚያወድም ነው ስትልም ትከራከራለች። በወንዙም ላይ ዝቅተኛ የውሃ መጠንም በናይል ላይ ያለውን ትራንስፖርት ሊጎዳ ይችላል ትላለች።-ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ሙሌት በሶስት ዓመት አጠናቅቄ ጨርሻለሁ በማለት ያስታወቀች ሲሆን ግብጽ ከዚህ ቀደም የግድቡ ሙሌት ከ12 እስከ 21 ዓመታት መውሰድ እንዳለበት ስትከራከር ቆይታለች።-ሱዳን በናይል ወንዝ የውሃ መጠን ላይ የግብጽን ያህል የጎዳት ባይመስልም ለግድቡ የምትሰጠው ምላሽ ግን አገሪቱን እየናጣት ባለው ጦርነት ምክንያት ቀንሷል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታው ከተጀመረበት ከአውሮፓውያኑ 2011 ጀምሮ በሶስቱ አገራት መካከል የውዝግብ መንስኤ ሆኗል።-ኢትዮጵያ ባልነበረችበት የተፈረሙትና በተደጋጋሚ የቅኝ ግዛት ስምምነቶች ብላ የምትጠራቸው የአውሮፓውያኑ 1929 እና የ1959 በናይል ላይ የተደረሱት ስምምነቶች ሱዳንና ግብጽን በወንዙ ድርሻ ላይ የበላይነት መብት የሰጠ ነው።-እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የላይኛው ተፋስስ አገራት በወንዙ ላይ ፕሮጀክቶችን ካሰቡም ከውሃ ድርሻቸው የመንፈግ መብትም የሰጠ ነው።-85 በመቶ በላይ የአባይን ውሃ የምትገብረውን ኢትዮጵያ ያለ ውሃ የሚያስቀር አግላይና ኢፍትሃዊ ነው በማለትም በነዚህ ስምምነቶች መተዳደር የለብኝም በማለትም ግድቡን መገንባት ጀመረች።-ወቅቱም ግብጽ በአረብ አብዮት በምትናወጥበት ወቅት ነው።-ሶስቱ አገራት በአውሮፓውያኑ 2015 የህዳሴ ግድብ የትብብር መግለጫ ስምምነት ቢፈራረሙም ከህዳሴ ግድብ ሙሌት እና አስተዳደር ጋር የተያያዙ የሶስትዮሽ ድርድሮች ፍሬ ማፍራት አልቻሉም።-ግጭቶችን ለመከላከል የሚሰራው አለም አቀፉ የክራይሲስ ቡድን በአገራቱ መካከከል የትጥቅ ግጭት ሊኖር እንደሚችልም ነው ያስጠነቀቀው።-በአውሮፓውያኑ 2019 የህዳሴ ግድብን የማደራደር እና ግብጽ እና ኢትዮጵያንም የማሸማገል ሚናን አሜሪካ ብትወስድም ፍሬ ሳያፈራ ቀርቷል።-ለሁለት ዓመት ተቋርጦ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድርም ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላቷን ማጠናቀቋን ከማሳወቋ ከሶስት ሳምንታት በፊት ተጀምሯል።
የፎቶው ባለመብት Reuters-የቀድሞው የፌስቡክ የይዘት ተቆጣጣሪ (content moderator) ሥራው የአእምሮ ጤንነቱ ላይ ስላመጣው ጫና ለቢቢሲ ይናገራል።-ሰዎችን ራሳቸውን ሲያጠፉ ከሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ጀምሮ በጣም አሰቃቂ የሚባሉ ይዘቶችን ይቆጣጠራ። እኒህ ይዘቶች የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ጋር እንዳይደርሱ ይጥራል።-ግለሰቡ ኬንያ መዲና ናይሮቢ መቀመጫውን ባደረገ አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ውስጥ የሚሠራ ነው።-ፌስቡክ አፍሪካ ውስጥ በጣም አስከፊ እና አሰቃቂ የሚባሉ ይዘቶችን እየተቆጣጠረ አይደለም የሚል ወቀሳ በተደጋጋሚ እያስተደናገደ ይገኛል።-እሱ “ማሽን መሰል” ሲል በሚጠራው የናይሮቢ ቢሮ ካለው ኮምፒውተር ፊት ቁጭ ብሎ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች አሰቃቂ ይዘት እንዳይመለከቱ ይቆጣጠራል።-ነገር ግን እነዚህ ይዘቶች እሱ ላይ ከሚያደርሱት ተፅዕኖ የሚጠብቀው የለም።-“ስለ ወሲብ ያለኝ ግንዛቤ አሁን ትርጉም አልባ ሆኗል” ይላል።-“ሰዎች ከእንስሳት፣ ከሕፃናት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ወሲብ ሲፈፅሙ እናያለን። ይህም በጣም ብዙ ጊዜ ይገጥመናል። ሁሉም የምር የሆኑ ናቸው” ሲል ለቢቢሲ ይናገራል።-ነገር ግን ከሁሉ በላይ የአእምሮ ጤናውን የጎዳው ሰዎች ራሳቸውን ሲያጠፉ አሊያም የገዛ አካላቸውን ሲጎዱ የሚያሳዩ ምስሎችን ሲመለከት ነው።-“ዓይኖቼን ስጨፍን ቲኬቱን አየዋለሁ” ይላል።-ቲኬት ማለት የይዘት ተቆጣጣሪዎች ለአንድ የፌስቡክ ልጥፍ የሚሰጡት ስያሜ ነው።-ኬንያ የሚገኙ የፌስቡክ ይዘት ተቆጣጣሪዎች አብዛኞቹ ወጣት ሴት እና ወንዶች ከኢትዮጵያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከሩዋንዳ፣ ከደቡብ አፍሪካ እና ሌሎች የአህጉሪቱ አገራት የመጡ ናቸው።-የይዘት ተቆጣጣሪዎቹ በአስር ቋንቋዎች ፌስቡክ ላይ የሚለጠፉ አሰቃቂ እና አስከፊ የሚባሉ ይዘቶችን ይቆጣጠራሉ።-የሚያሰራቸው ተቋም ሳማ ይባላል። መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ አድርጎ በኬንያ ቀጣናዊ ቢሮ ያለው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።-ራሱን በፈረንጆቹ ጥቅምት 2021 ሜታ ሲል የሰየመው ፌስቡክ አፍሪካ ውስጥ ላለው የይዘት ቁጥጥር ይህን ድርጅት ቢቀጥርም እርምጃው ገንዘብ ከመቆጠብ አንፃር ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-አንዲት ሠራተኛ ከተቀጠረች በኋላ ሥልጠና ሲሰጣት ካየቻቸው መካከል በማኅበራዊ ሚዲያው መድረክ ላይ ከኢትዮጵያ የተለጠፈን አንድ ይዘትን አትዘነጋውም።-“አስታውሳለሁ ሁሉም የሚጀምረው ከሥልጠና ነው። ሥልጠናው ላይ ሰዎች ራሳቸውን ሲያጠፉ እንድንመለከት እንደረጋለን። እነዚህን ሰዎች አልረሳቸውም። መቼም ቢሆን የምረሳው አይመስለኝም” ስትል ለቢቢሲ ትናገራለች።-“ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ደግሞ በጣም ብዙ አሰቃቂ ምስሎች እናያለን። ሰዎች በሕይወት እያሉ ሲቃጠሉ፣ የጅምላ ግድያ እና የተለያዩ ጥቃቶች እናያለን።”-“አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ሲቀሰቀሱ እና ሲጋጋሉ እናያለን። ሁሉም ነገር ተመዝግቦ ይቀመጣል። እዚህ ቁጭ ብለን ጦርነቱን ያየን ያህል ነው። ምንም የሚያመልጠን ነገር የለም” ትላለች።-ቢቢሲ ያናገራቸው የድርጅቱ ሠራተኞች ምሬት እና የደቡብ አፍሪካ ዜጋ የሆነው የድርጅቱን ምስጢር ያሾለከው ዳንዔል ሞታውንግ ያቀረበው ክስ ተመሳሳይነት አላቸው።-ደቡብ አፍሪካዊው ዳንዔል ሳማ የተሰኘውን ድርጅት ኬንያ ውስጥ ፍርድ ቤት አቁሞታል።-“መጀመሪያ ለሳማ መሥራት ስጀምር እኔ እና የሥራ አጋሮቼ ሰዎች ሲታረዱ፣ ሕፃናት ሲደፈሩ፣ ሲገደሉ አሊያም ጥቃት ሲደርስባቸው የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ቪድዮዎችን እናያለን ብዬ አልጠበቅኩም ነበር” ይላል ዳንዔል።-“ፎቶዎቹ አስከፊ መሆናቸው ሳያንስ ሰዎች ሲቀሉ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ተመልክቻለሁ” ሲል ለችሎቱ እንደተናገረ የፍርድ ቤት መዛግብት ያሳያሉ።-ዳንዔል “ያለአግባብ ከሥራ ተባርሪያለሁ” ከሚል ክስ አንስቶ እሱ እና የሥራ ባልደረቦቹ “የሕይወት ዘመን የአእምሮ ጉዳት ደርሶብናል” የሚል ክስ ነው ያቀረበው።-እሱ እንደሚለው በሥራው አማካይ የጭንቀት ተጠቂ እንደሆነ አልፎም ፒቲኤስዲ የተሰኘው የአእምሮ በሽታ እንዳጋጠመው ተናግሮ ሕይወቴ ተበላሽቷል ይላል።-“እንዴት አድርጌ ወደ ተሻለ ሕይወት መመለስ እንዳለብኝ አላውቅም።”-የሜታ እና የሳማ ጠበቃዎች የዳንዔል ክስ ውድቅ እንዲሆን ጥያቄ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ በዳንዔል ክስ ላይ ውሳኔ እስካሁን አልሰጠም።-በፈረንጆቹ 2020 አሜሪካዊያን የይዘት ተቆጣጣሪዎች ፌስቡክ ለአእምሮ ጤና መረበሽ ዳርጎናል ሲሉ ከሰው ድርጅቱ 52 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍል መወሰኑ አይዘነጋም።-ኬንያ የሚገኘው የፌስቡክ አጋር የሆነው ሳማ ሠራተኛ ለቢቢሲ እንደምትናገረው ድርጅቱ “የአእምሮ ጤና ጥበቃ” የሚል ፕሮግራም ቢኖረውም ከሚደርስባቸው ጫና አንፃር በቂ አይደለም።-“በየቀኑ ነው መሰል ይዘት የምናየው። ቤት ስንገባ የምንረሳው ጉዳይ አይደለም። ትዝ ይለናል። በሕልማችን ይመጣል። ስለዓለም ያለን አተያይ ይቀየራል። ምክንያቱም ሥራ ላይ ቀኑን ሙሉ የምናየው መጥፎ ነገር ነው” ትላለች።-ቢቢሲ ይህን ቅሬታ በተለመከተ ከሜታ አስተያየት ቢጠይቅም “በሳሙዔል ክስ ምክንያት” አስተያየት መስጠት አንችልም የሚል ምላሽ ነው ያገኘው።-ሳማ በበኩሉ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።-የፎቶው ባለመብት Reuters-ነገር ግን ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መባቻ ታይም የተሰኘው የአሜሪካ መጽሔት ተመሳሳይ ቅሬታ ያላቸውን ሠራተኞች አስመልክቶ ለሠራው ዘገባ “ሐሰት እና አሳሳች” የሚል ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል።-በወቅቱ ሳማ አክሎም “ለሠራተኞቼ የአእምሮ ጤና በጥልቀት አስባለሁ” የሚል ዘገባ ምላሽ አስነብቦ ነበር።-“በመጀመሪያ ሠራተኞች በሳምንት ከ37.4 ሰዓት በላይ እንዲሠሩ አንፈቅድም። በተጨማሪ ሠራተኞቻችን የአእምሮ ጤናቸው እንዲጠበቅ በማሰብ በቀን የአንድ ሰዓት ተኩል የጤና እና የምግብ እረፍት እንዲወስዱ እናደርጋለን። በሦስተኛ ደረጃ ሳምንቱን ሙሉ ቀንና ሌሊት ሠራተኞች በፈለጉ ጊዜ የምክር አገልግሎት እንሰጣለን” ሲል ሳማ በድረ-ገፁ ላይ ባወጣው ማስተባበያ አስታውቋል።-ዳንዔል በፍርድ ቤት መዝገቡ ላይ ምንም እንኳ የይዘት ቁጥጥር ለሜታ አስፈላጊ ቢሆንም ሥራውን ለሌላ ድርጅት አኮናትሯል ሲል ይከሳል።-ይህን ያደረገውም “በርካሽ ዋጋ የሰው ኃይል ለመሸመትና የሥነ አእምሮ ድጋፍ ዋጋን ለማስቀረት ነው” በማለት ይወቅሳል።-የዳንዔል ጠበቃዎች ኬንያ ካለው ቢሮ ተቀጥረው የሚሠሩ 240 ባለሙያዎች በደቡብ እና ምሥራቅ አፍሪካ ያለውን የይዘት ቁጥጥር ሥራ ለመሥራት በቂ አይደሉም ይላሉ።-አልፎም በኬንያ ብቻ 10 ሚሊዮን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እንዳሉ ያሰምራሉ።-“ገበያው ላይ ያሉትን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ደኅንነት እና የይዘት ተቆጣጣሪዎችን ጤና ለመጠበቅ ተጨማሪ ሠራተኞች መቀጠር አለባቸው” ይላሉ ጠበቃዎቹ።-ቢቢሲ ካናገራቸው የድርጅቱ ሠራተኞች መካከል አንዱ “የጤና ጥበቃ ፕሮግራም” ተብሎ የሚሰጠው መርሐ ግብር ምስጢር የማይጠበቅበት ነው ሲል ይኮንናል።-“ስላየኸው የፌስቡክ መልዕክት እና ስለተሰማህ ነገር ይጠይቁሃል። ለአማካሪህ የነገርከውን ነገር ከሥል ባልደረባህ መልሰህ ትሰመዋለህ” ይላል።-ቢቢሲ ያናገራቸው የሳማ ሠራተኞች የሚከፈላቸው ክፍያ እጅግ አነስተኛ እንደሆነም ጨምረው ይናገራሉ።-“ሥራው አካላዊ ድካም እና አእምሯዊ ተፅዕኖ አለው። የሚከፈለን ክፍያ በፍፁም ከሥራው ጋር የሚመጣጠን አይደለም። ሁሉም ሰው በልቶ ስለማደር ይጨነቃል።”-ሳማ በድረ-ገፁ በሰጠው ምላሽ ሠራተኞቹ ተገቢውን ክፍያ እያገኙ አይደለም የሚባለው ሐሰት ነው ሲል ያስተባብላል።-“የይዘት ቁጥጥር ከበድ ያለ ሥራ ከመሆኑ አንፃር ከዝቅተኛው ክፍያ ሦስት እጥፍ፤ ከኬንያ አማካይ ክፍያ ሁለት እጥፍ የሆነ ገንዘብ እንከፍላለን” ይላል።-ሳማ የተሰኘው ድርጅት ከሜታ ጋር ያለው የሥራ ኮንትራክት በቅርቡ እንደሚያበቃ ታውቋል።-በምትኩ ማጆሬል የተሰኘ ድርጅት የይዘት ቁጥጥር ሥራውን እንደሚረከብ የተሰማ ሲሆን፣ ድርጅቱ ከሳማ በግማሽ ያነሰ ክፍያ የሚከፍል ነው።-የኬንያ ፍርድ ቤት በዳንዔል ሞታውንግ ጉዳይ ቀጣይ ቀጠሮ ለጥር 29/2015 ዓ.ም. ሰጥቷል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኢትዮ-ሶማሊ ጦርነት-ከሰሞኑ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን በአንድ በተመሳሳይ አጀንዳ ተይዘዋል።-መገናኛ ብዙሃኑ ኢትዮጵያን እንደ ታሪካዊ ጠላት አድርጎ የሚገልጸውን እና ጦርነት የሚጎስመውን ሙዚቃ ደጋግመው እያጫወቱ ይገኛሉ።-አንዳንዶች በሶማሊያ መንግሥታዊ ሚዲያዎች እየተከፈተ ያለው ይህ የሶማሊያ ፖሊስ ባንድ ሙዚቃ “ስሜት ቀስቃሽ” ነው ይሉታል።-ከሳምንታት በፊት ኢትዮጵያ እና ነጻ አገርነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ የባሕር ጠረፍ ያስገኛል የተባለውን የመግባቢያ ሠነድ መፈራረማቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በሞቃዲሾ መካከል ውጥረት ሰፍኗል።-ይህ የመግባቢያ ሠነድ ተፈጻሚ ሲሆን ኢትዮጵያ ለምትቀበለው የባሕር ጠረፍ በምላሹም ሶማሊያ እንደ አንድ ግዛቷ ለምትመለከታት ሶማሊላንድ የአገርነት ዕውቅናን ትሰጣለች ተብሏል።-ይህ በእጅጉ ያስቆጣቸው የሶማሊያ ባለስልጣናት ስምምነቱ በአገራችን ሉዓላዊነት ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው ሲሉ የቆዩ ሲሆን በተለያዩ መድረኮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ውስጥ ለመገባት ዝግጁ ነን ሲሉ ተደምጠዋል።-የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዛ አብዲ ባሬ ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ውስጥ ለመግባት ዝግጁ ነን ብለው ነበር።-“ካልተዋችሁን፤ እንድትተዉን የሚያደርግ ነገር እናሳያችኋለን። . . .ወደ ሶማሊያ ግዛት አንድ ኢንች ለመግባት ቢሞከሩ፤ አስክሬኖችን ይዘው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ” ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ሐምዛ አብዲ ባሬ።-ከዚህ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ቀደም ብሎ ደግሞ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ኢትዮጵያን የሶማሊያ “ጠላት” ሲሉ ገልጸዋት ነበር።-የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃንም ሁለቱ አገራት ከ50 ዓመታት ገደማ በፊት ያደረጉትን ጦርነት የሚያስታውስ ሙዚቃ እያጫወቱ ይገኛሉ።-“ሰላም ካልፈለጋችሁ፤ በ1977 (እአአ) ያደረግናችሁን እንድታስታውሱ ዕድል እንሰጣቹሃለን” ይላል ይህ ሙዚቃ።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሶማሊያ ጦር አባላት-የኢትዮ-ሶማሊ ጦርነት ወይም የኦጋዴን ጦርነት ከእአአ 1977 እስከ 1978 ድረስ የተካሄደ ሲሆን የሲዓድ ባሬ ሠራዊት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ገብቶ በርካታ አካባቢዎች ይዞ ነበር።-ይሁን እንጂ የኮሎኔል መንግሥት ኃይለ ማርያም ጦር የጠላትን ኃይል ከኢትዮጵያ ክልል አስወጥቷል።-ይህን ጦርነት ሁለቱም አገራት አሸንፈናል ይላሉ።-ከዚህ ‘ሪመምበር ዋት ዊ ዲድ ቱ ዩ ኢን 1977’ (በ1977 ያደረግናችሁን አስታውሱ) ተብሎ ከሚጠራው ሙዚቃ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዙ ሌሎች ሁለት ሙዚቃዎች በሶማሊያ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተሰራጩ ነው።
የፎቶው ባለመብት Reuters-ምንም እንኳን የአሜሪካ መንግሥት ባይፋ ባይገልጸውም ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዜጋዋ አብረሃም ተክሉ ለማ የመከላከያ እና የደኅንነት ምስጢራዊ መረጃዎችን ወደ ኢትዮጵያ ያስተላልፍ ነበር መባሉ መነጋገሪያ ሆኗል።-ከዚህ ቀደም የአሜሪካ መንግሥትን የስደነገጡ ምስጢራዊ መረጃዎች ሾልከው ሲወጡ የነበሩት ወደ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ወደ ተቀናቃኞቿ ኃያላን አገራት መሆኑ የአሁኑን ክስተት የተለየ አድርጎታል።-በተለያዩ ጊዜያት ከአሜሪካ የመከላከያ፣ የደኅንነት፣ የቴክኖሎጂ ምስጢራዊ መረጃዎች መሹለካቸው ወይም ለማሹለክ የተደረጉ ሙከራዎች መኖራቸው ሲዘገብ ቆይቷል።-ከዚህ አንጻርም የአሜሪካ ተቀናቃኞች ሩሲያ እና ቻይና በዋናነት በተደጋጋሚ ስማቸው የሚነሳ ሲሆን፣ የአውሮፓ ወዳጆቿም በዚህ ድርጊት ውስጥ እጃቸው እንዳለበት ሲጠቀስ ነበር።-ለዚህም ነው ከአብረሃም ተክሉ በቁጥጥር ስር መዋል ጋር ተያይዞ የአሜሪካ የመገናኛ ብዙኃን ምስጢራዊ መረጃዎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲተላለፉ ነበር ማለታቸው አነጋጋሪ የሆነው።-የአሜሪካ መንግሥት በተጠርጣሪው ላይ ባቀረበው ባለ 16 ገጽ ዝርዝር ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ አብረሃም ከታኅሣሥ 2014 እስከ ነሐሴ 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ የደኅንነት መረጃዎችን ኮፒ በማድረግ፣ የሰነዶቹን ምስጢራዊነትን የሚያመለክቱ መለያዎችን ሠርዟል ተብሏል።-የክስ መዝገቡ ተከሳሹ ሰነዶቹን ለየትኛው አገር እንዳስተላለፈ ያላመለከተ ሲሆን፣ ነገር ግን አንድ አገር እና አንድ አካባቢ ላይ ያተኮሩ መሆናቸው እንዲሁም ምስጢራዊ የመከላከያ መረጃዎችን ለሌላ አገር የደኅንነት ተቋም ባለሥልጣን አሳልፎ መስጠቱ ተገልጿል።-በአብረሃም ተክሉ ላይ የቀረቡበት የተለያዩ ክሶች ከተደረጋገጡ በሞት ወይም ከ10 ዓመት አስከ ዕድሜ ልክ እስራት ሊያስቀጡ የሚችሉ መሆናቸው ተነግሯል።-አብረሃም ተክሉ ለማ ትውልዱ ኢትዮጵያ ሲሆን የአሜሪካ ዜጋ ነው። የ50 ዓመቱ ጎልማሳ አብረሃም ነዋሪነቱ ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ ሲሆን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ ነው።-አብረሃም ከአውሮፓውያኑ 2013 አስከ 2016 ድረስ እዚያው አሜሪካ ውስጥ ባልቲሞር በተባለው ዩኒቨርስቲ ውስጥ የኢንፎርሜሽን ሲስተምስ እና ቴክኖሎጂ ትምህርትን ተከታትሏል።-ይህ ሙያው ነው እንግዲህ በተለያዩ የአሜሪካ መንግሥት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ምስጢራዊ መረጃዎችን እንዲያገኝ እና እንዲመለከት ቅርበትን የፈጠረለት።-ለአብረሃም እነዚህ አጋጣሚዎች የተፈጠሩለት በመጀመሪያ ከአምስት ዓመት በፊት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የመረጃ እና የጥናት ክፍል ውስጥ በቴክኒሻንነት ተመድቦ ሲሠራ ነው። ከዚያም ተከትሎ በዚያው መሥሪያ ቤት ስር የዋሽንግተን ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር ሠራተኛ ሆነ።-በሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም. ደግሞ በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ ከምስጢራዊ መረጃዎች ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችለውን ፈቃድ አገኘ።-በግንቦት 2014 ዓ.ም. ደግሞ ወደ አሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ተዘዋውሮ መሥራት ጀመረ። በዚያው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ወደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ተመልሶ ለፍትሕ መሥሪያ ቤቱም መሥራቱን ቀጠለ።-በዚህ አጋጣሚም በታኅሣሥ 10/2015 እና በነሐሴ 01/2015 ዓ.ም. መካከል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ቢያንስ 85 የደኅንነት መረጃዎችን በተለያየ መልኩ በመገልበጥ ወስዷል ተብሎ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።-አብረሃም የተጠረጠረባቸውን ድርጊቶች ፈጽሟል በተባለባቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ ትውልድ አገሩ ኢትዮጵያ ተጉዞ እንደነበርም ተገልጿል።-እዚያም በክሱ ላይ የተጠቀሱ ጉዳዮችን መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም የግለሰቡ የመረጃ ልውውጥ ግንኙነት ከኢትዮጵያ ጋር ሳይሆን እንደማይቀር አመልክቷል።-አብረሃም ተክሉ በየካቲት 02/2014 ዓ.ም. እንዲሁም ባለፈው ዓመት ከፋሲካ በዓል በፊት ሚያዚያ 04/2015 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ እንደነበር ተነግሯል።-ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም. በኤፍቢአይ ወኪሎች በቁጥጥር ስር የዋለው አብረሃም፣ የብሔራዊ መከላከያ መረጃን ሌላ አገርን ለመደገፍ ለማስተላለፍ በማሴር እንዲሁም ሆን ብሎ የመከላከያ መረጃን በግል መያዝ የሚሉ ክሶች ተመስርተውበታል።-ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ግለሰቡ ላይ በይፋ ክስ የተመሠረተበት ሲሆን፣ ፈጸማቸው የተባሉ የስለላ ድርጊቶች በዝርዝር ቀርበዋል። ግለሰቡ ምስጢራዊ መረጃዎችን አሳልፎ መስጠቱ እንዲሁም ከውጭ አገር ባለሥልጣን ጋር መረጃ መለዋወጡ እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ ገንዘብ ማግኘቱም ተገልጿል።-ነገር ግን ቀደም ብሎም ሆነ አሁን ክሱ ይፋ ሲደረግ አብረሃም ተክሉ ለማ ከአሜሪካ መንግሥት የመረጃ ቋት በሥራው አጋጣሚ ያገኛቸውን ምስጢራዊ መረጃዎችን ለየትኛው አገር አሳልፎ እንደሰጠ ይፋ አልሆነም።-ነገር ግን የአሜሪካ የመገናኛ ብዙኃን ተጠርጣሪው መረጃዎችን ሲያስተላልፍ እና ግንኙነት ሲያደርግ የነበረው ወደ ኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ባለሥልጣን ጋር እንደሆነ አመልክተዋል።-በክስ ሰነዱ ላይም አብረሃም ተክሉ ለማ ወደ ትውልድ አገሩ በተደጋጋሚ መጓዙን እና እዚያም ከባለሥልጣን ጋር መገናኘቱ ተገልጿል።-ይህም ቢሆን አስካሁን ስለተጠርጣሪው እና ግንኙነት ያደርጋል ስለተባለው አገር የአሜሪካ መንግሥት ዝርዝር መረጃ ያልሰጠ ሲሆን፣ በመገናኛ ብዙኃን ስሟ የተነሳው ኢትዮጵያም በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት የሰጠችው ምላሽ የለም።-የፎቶው ባለመብት Reuters-የአሜሪካ መንግሥት ባቀረበው ዝርዝር ክስ ላይ በተለያዩ የአገሪቱ ተቋማት “ምስጢር” ተብለው የተለዩ ሰነዶችን፣ ፎቶግራፎችን፣ ማስታወሻዎችን፣ ካርታዎችን፣ የሳተላይት ምስሎችን እና ሌሎች “ከሚመለከተው አገር እና ከጎረቤት አገሮች ጋር የተያያዙ” የመከላከያ መረጃዎችን በተለያዩ ቀናት አሳልፎ መስጠቱ ተገልጿል።-አብረሃም ተክሉ በመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ አማካይነት መረጃውን ያጋራል ከተባለው አገር ባለሥልጣን ጋር፣ በአገሪቱ ውስጥ መንግሥትን የሚቃወሙ የአማጺያን ወታደራዊ እንቅስቃሴን በተመለከተ ውይይት ማድረጉ ተመልክቷል።-በአንድ ግንኙነት ወቅትም በተባለው አገር ውስጥ ያለ ክስተትን አስመልክቶ ባለሥልጣኑን “ቡድንህ ይህንን በመተንተን አንዳች ነገር ይውሰድ” በማለት መምከሩም ተገልጿል።-በሌላ የመልዕክት ልውውጥ ላይ ደግሞ ባለሥልጣኑ “ይህንን በመቀልበስ በኩል . . . በድጋሚ እንዳይከሰት . . . ጉልህ ለውጥ አግኝተናል. . . በጥቂት ቀናት ውስጥ ወሳኝ ደረጃ ላይ እንደርሳለን። . . . አጣርተህ ምን ማድረግ እንደምንችል ብታሳወቀኝ ጥሩ ይሆናል” እንዳለው በክሱ ላይ ሰፍሯል።-በተመሳሳይም ባለሥልጣኑን “ወደፊት የተሰማራ የዕዝ እና የአቅርቦት ማዕከልን ማወቅ ጠቃሚ ነው” በማለት ጥያቄ ያቀረበለት ሲሆን፣ ለማም በተጠቃሹ አገር ውስጥ ያሉ ቦታዎችን በተመለከተ ውይይት አድርጓል።-በሌላ ውይይት ላይ ባለሥልጣኑ የአማጺያንን የአቅርቦት ማዕከላትን በመሳሰሉ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ከለማ መረጃን እንደሚፈልግ እንደገለጸለት እና በምላሹም “አዎ፣ ይህንን ሳምንት በሙሉ በእዚያ ላይ አተኩሬ ነው የቆየሁት. . .” ማለቱ ተጠቅሷል።-ክሱ ጨምሮም አብረሃም “የወታደራዊ ሰፈር” ፎቶዎችን ለባለሥልጣኑ መላኩን፣ ባለፈው ዓመት መስከረም ወር አካባቢ ደግሞ ባለሥልጣኑ “ድጋፍህን የምትቀጥልበት ጊዜ ነው” በማለት መልዕክት እንደላከለት ገልጿል።-አብረሃምም በምላሹ “ተቀብያለሁ!” ማለቱ የተጠቀሰ ሲሆን፣ በሌላ ውይይታቸውም ባለሥልጣኑ “ይህች ውብ አገር ሁሌም አኩሪ ታሪኳን ለመጠበቅ ሕይወታቸውን የሚሰዉ ልዩ ሰዎች አሏት። ውጤቱ ምንም ሆነ ምን፣ ሁሌም ትታወሳለህ” በማለት አድናቆቱን እንደገለጸለት በክስ መዝገቡ ላይ ሰፍሯል።-የአሜሪካ መንግሥት በተጠርጣሪው ላይ ባቀረበው ባለ 16 ገጽ ዝርዝር ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ አብረሃም ከታኅሣሥ 2014 እስከ ነሐሴ 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ የደኅንነት ሪፖርቶችን ኮፒ በማድረግ፣ የሰነዶቹን ምስጢራዊነትን የሚያመለክቱ መለያዎችን ሰርዟል ተብሏል።-የክስ መዝገቡ ተከሳሹ ሰነዶቹን ለየትኛው አገር እንዳስተላለፈ ያላመለከተ ሲሆን፣ ነገር ግን አንድ አገር እና አንድ አካባቢ ላይ ያተኮሩ መሆናቸው እና ምስጢራዊ የመከላከያ መረጃዎችን ለሌላ አገር የደኅንነት ተቋም ባለሥልጣን አሳልፎ መስጠቱ ተገልጿል።-ተጠርጣሪውን የሚመለከቱ የባንክ ሰነዶችን የሰበሰቡት መርማሪዎች እንደሚሉት፣ አብረሃም ምስጢራዊ ሰነዶቹን ከአሜሪካ መንግሥት የመረጃ ቋት ካወጣ እና ወደ ኢትዮጵያ ደርሶ ከተመለሰ በኋላ በተለያዩ ባንኮች ውስጥ የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ አስገብቷል።-በአብረሃም ተክሉ ላይ የቀረቡበት የተለያዩ ክሶች ከተደረጋገጡ በሞት ወይም ከ10 ዓመት አስከ ዕድሜ ልክ እስራት ሊያስቀጡ የሚችሉ መሆናቸው ተነግሯል።-የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ግለሰቡ ምስጢራዊ መረጃዎችን ወደ ሌላ አገር እያሾለከ መሆኑን የደረሰበት፣ ተለይተው የተቀመጡ ብርቱ ወይም በጥንቃቄ መያዝ ያለባቸው ሰነዶች አያያዝን በተመለከተ ለሁለት ወራት ባደረገው አጠቃላይ ምርመራ አማካይነት መሆኑን የመሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ማት ሚለር ገልጸዋል።-ይህ አጠቃላይ ምርመራ እንዲካሄድ ምክንያት የሆነው ጃክ ቴሼራ የተባለው የ21 ዓመት የአሜሪካ አየር ኃይል አባል ምስጢራዊ የመረጃ እና የመከላከያ ሰነዶችን አሾልኮ አውጥቷል ተብሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ነው።-የፎቶው ባለመብት EPA/GETTY IMAGES-የዊኪሊክስ መሥራች ጁሊያን አሳንጅ-በአሜሪካ የምስጢራዊ መረጃዎች ሾልኮ የመውጣት ታሪክ ውስጥ ዋነኛ የሚባሉት አምስቱን የሚከተሉት ናቸው።-የዩክሬን ጦርነት ምስጢሮች-ከአሜሪካ የመከላከያ እና የደኅንነት ተቋማት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ምስጢራዊ መረጃዎች ሾልከው ሲወጡ ቆይተዋል። ከሳምንታት በፊትም ከአገሪቱ የመከላከያ መሥሪያ ቤት ፔንታጎን ያፈተለኩ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ምስጢራዊ ሰነዶች ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።-ሰነዶቹ በዩክሬን ውስጥ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ የኔቶ ወታደራዊ መረጃዎች ሲሆኑ፣ ይህንንም ተከትሎ ምዕራባውያን የመከላከያ ባለሥልጣናት ምስጢሮቹን አሽሉኮ ያወጣውን ወገን ለማወቅ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም።-ሰነዱ አሜሪካ እና ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚሰጡትን ወታደራዊ ድጋፍ የሚዘረዝር ሲሆን፣ በተጨማሪም አሜሪካ በሩሲያ እና በዩክሬን መሪዎች ላይ ስለላ እንደምታካሂድ። እንዲሁም አሜሪካ የሩሲያ ወታደራዊ እንቅስቃሴን በሳተላይት እንዴት እንደመትከታተል ይፋ ማድረጉ ተዘግቧል።-የኤድዋርድ ስኖውደን መረጃዎች-የደኅንነት ሠራተኛ የነበረው ኤድዋርድ ስኖውደን ይፋ ያወጣቸው ምስጢራዊ መረጃዎች በአሜሪካ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ አስለከትሎ ነበር።-የአሜሪካ ብሔራዊ የመረጃ ተቋም ሠራተና የነበረው ስኖውደን ባሾለካቸው ሰነዶች ላይ የአሜሪካ መንግሥት በተራ ዜጎቹ ላይ ከሕግ ውጪ የሚካሂደውን ክትትል፣ የአውሮፓ ኅብረትን ጨምሮ በአገራት እና በኤምባሲዎች ላይ ስለምታካሂደው ስለላ አጋልጧል።-ስኖውደን ምስጢሩን ይፋ ካደረገ በኋላ ከአሜሪካ ወደ ሆንግ ኮንግ የሸሸ ሲሆን ቀጥሎም የአሜሪካ ባላንጣ ወደሆነችው ሩሲያ ገብቷል። አሜሪካም መንግሥታዊ ንብረት የሆኑ መረጃዎችን በመዝረፍ እና በሌሎች ጥፋቶች ክስ ተመስርቶበታል።-የፎቶው ባለመብት AFP-የአሜሪካ መንግሥት በዜጎቹ ላይ የሚያደርገውን ስለላ በማጋለጡ ስኖውደን ድጋፍን አግኝቶ ነበር-የፔንታጎን ሰነዶች-አሜሪካንን ከባድ ፈተና ውስጥ ከትቷት የነበረውን የቬትናም ጦርነትን በተመለከተ የተደረገ ወታደራዊ ጥናት ብርቱ ምስጢር ከ50 ዓመታት በፊት ለኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ሾልኮ እንዲወጣ ተደርጎ ነበር። ይህም በአሜሪካ መንግሥት ላይ ከባድ ተቃውሞ እና ትችትን አስከትሎ ነበር።-እንዲሁም ይህ የመከላከያ ምስጢር በጋዜጣ ለሕዝብ ይፋ ከመደረጉ ቀደም ብሎ የአሜሪካ መንግሥት በፍርድ ቤት እንዲታገድ ቢያደርግም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዕግዱ ተነስቶ ታትሟል። ይህም በመንግሥት እና በአገሪቱ ጋዜጦች መካከል ከባድ ፍጥጫ እና ግጭትን ፈጥሮ ነበር።-የኢራቅ ጦርነት ሰነዶች-በጁሊያን አሳንጅ የሚመራው ዊኪሊክስ የአሜሪካ እና የአጋሮቿ ሠራዊት ኢራቅ ውስጥ ስለፈጸሟቸው ድርጊቶች የሚዘረዝሩ በምስጢር የተያዙ ወታደራዊ ሰነዶችን ይፋ አደረገ። መረጃዎቹ በኢራቅ ውስጥ ስለተፈጸሙ ግፎች እና የመብት ጥሰቶች ያጋለጡ ናቸው።-ሾልከው የወጡት ሰነዶች 400 ሺህ የሚደርሱ ወታደራዊ ሪፖርቶች ሲሆን፣ ከ60 ሺህ በላይ ሰላማዊ ኢራቃውያን በአሜሪካ በሚመሩት ጥምር ኃይሎች መገደላቸውን እና በእስር ቤቶች ውስጥ የሚፈጸሙ ግፎችን ጨምሮ በርካታ ምስጢራዊ መረጃዎችን ይፋ አድርገዋል።-ይህ መረጃም አሜሪካ በኢራቅ ውስጥ ባካሄደችው ጦርነት ዙሪያ የነበረው እየቀነሰ የመጣውን የሕዝብ ድጋፍ የበለጠ እንዲኣሽቆለቁል አድርጎታል። ኦባማ ጦራቸውን ለማስወጣት እንዳሰቡ ባሳወቁበት ጊዜ ከፍተኛ ድጋፍን አግኝተዋል።-የሮበርት ሃንሰን ስለላ-በአሜሪካ የአገር ውስጥ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ኤፍቢአይ ለ25 ዓመታት የሠራው ሮበርት ሃንሰን ለሶቪየት ኅብረት እና ለሩሲያ የመረጃ መሥሪያ ቤቶች አሜሪካንን ሲሰልል እንደነበረ መታወቁ ሌላኛው አነጋጋሪ ክስተት ነበር።-ግለሰቡ አስኪታወቅበት ድረስ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ሠራዊት ምስጢራዊ ዕቅዶችን እና የጦር መሣሪያ ቴክኖሎጂዎችን ለሶቪየቶች እና ለሩሲያ የስለላ ተቋማት አሳልፎ ሰጥቷል።-ሃንሰን ምስጢራዊ የደኅንነት እና ወታደራዊ መረጃዎችን አሳልፎ በመስጠት 1.4 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ መጠን ያለው ሃብትን በገንዘብ እና በአልማዝ ማግኘቱ ተደርሶበታል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኤርትራ ውስጥ የተቃውሞ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እና ሠላማዊ ሰልፎች እምብዛም ናቸው።-በተለያዩ አገራት የሚኖሩ በርካታ ኤርትራውያን ደግሞ የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አገዛዝን በመቃወም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እና ሰላማዊ ሰልፎች ሲያካሂዱ ቆይተዋል።-በአገሪቱ የተረቀቀው ሕገ መንግሥት ተግባራዊ እንዲደረግ፣ ምርጫ እንዲካሄድ፣ የፖለቲካው ምህዳር እንዲሰፋ፣ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት የታሰሩ እንዲፈቱ እና ለብዙ ወጣቶች ፍልሰት ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለት ገደብ የለሽ ወታደራዊ አገልግሎት እንዲቆምና መሰል ጥሪዎች ተደጋግመው ተሰምተዋል።-ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በተለይም ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ግን በስርዓቱ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ሁከቶች ሲቀሰቀሱ እና ከፍተኛ ጉዳቶች ሲደርሱ ታይተዋል።-የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች በወርሀ ሐምሌ በጀርመን የጊሰን ዓመታዊ ፌስቲቫልን አዘጋጅተው ነበር። በአዘጋጆቹና ፌስቲቫሉን ለመበተን በተንቀሳቀሱ ወጣቶች መካከል ሁከት ተቀስቅሶ 26 ፖሊሶችን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። በርካቶችም ታሰረው ክስ ተመሰርቶባቸዋል።-እአአ ነሐሴ 3 2023 ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ከመላው አውሮፓ የተሰባሰቡ ተቃዋሚዎች በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች የተዘጋጀውን ዓመታዊ ፌስቲቫል ሰብረው በመግባት ጥቃት ፈጸሙ። በሁከቱ ከ50 በላይ ሰዎች ጉዳት ደረሰባቸው። ከ 100 የሚበልጡት ደግሞ መታሰራቸውን ፖሊስ ገልጾ ነበር።-በተመሳሳይ ባለፈው ወር በቶሮንቶ ካናዳ ለሦስት ቀናት ሊካሄድ የነበረ ፌስቲቫል በደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች በተቀሰቀሰ ሁከት ተቋረጠ። ሁከት ሊነሳ ይችላል ብለው በሰጉ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ባሉ አገራት ደግሞ ፌስቲቫሉ እንዳይካሄድ ከልክለዋል።-ከሁሉም የከፋው ሁከት በእስራኤል ቴል አቪቭ የተፈጸመው ነው።-ባለፈው ቅዳሜ ነሐሴ 27 2015 በእስራኤል በሚኖሩ በኤርትራውያን መካከል የተፈጠረው ሁከት ከፍተኛ ጉዳትና ውድመት አስከትሏል። የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል። እስራኤልንም አስቆጥቷል።-ሁከቱ የተፈጠረው በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች የተዘጋጀ ነው የተባለውን ዝግጅት ለማወክ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎች፣ ፌስቲቫሉ ወደሚዘጋጅበት ቦታ በኃይል ከገቡ በኋላ ነው።-ሁከቱን ለመቆጣጠር የእስራኤል ፖሊስ ጥይት፣ አስለቃሽ ጭስ እና የፕላስቲክ ጥይቶችን ለመተኮስ ተገድዷል።-ግጭቱ ተስፋፍቶ ስደተኞቹ ድንጋይ፣ እንጨት እና ብረቶችን በመጠቀም በሚዘገንን ሁኔታ እርስ በእርስ ሲደባደቡ ታይተዋል። ከዚህ ባለፈም መኪኖች እና መስኮቶችን ሰባብረዋል።-የቴል አቪቭ ጎዳናዎች ለሰዓታት የጦር ሜዳ መስለው ነበር። የአደጋ ጊዜ ድምጽ መሰማቱን እና ሂሊኮፕተር ሲያንዣብብ መመልከታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።-ከ170 በላይ ስደተኞች እና ከ50 በላይ ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።-ግጭቱን ተከትሎ “ቀይ መስመር መጣሱን” የገለጹት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ በግጭቱ የተሳተፉ ኤርትራውያን እና ሌሎች በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ አፍሪካውያንን እንደሚያባርሩ ዝተዋል።-የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት በሁከቱ የተሳተፉ ኤርትራውያንን ወደ ትውልድ አገራቸው ለመመለስ ሚንስትሮችን በአባልነት የሚያቅፍ ግብረ ኃይል ይቋቋማል ብሎ ነበር።-“ባቋቋምነው ካቢኔ አንድ ሺህ የሚሆኑ በግጭቱ የተሳተፉ የስርዓቱ ደጋፊዎችን ማባረርን የሚያጠቃልል እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀናል። ስደተኞች ነን ማለትም አይችሉም። የስርዓቱ ደጋፊዎች ናቸው። የሚደግፉት ከሆነ ወደ አገራቸው መመለስ ይችላሉ” ሲሉ ኔታንያሁ ተናግረዋል።-አንድ ኤርትራዊ እስራኤላዊ ባለ ሱቅ ሁኔታውን “መዓት” ሲል ገልጾታል።-“ሁኔታው አስደንግጦናል። ኃፍረት እና ሐዘን ተሰምቶናል። ደህንነት አይሰማንም። ወዴትስ መሄድ እንችላለን? አገራችን ውስጥ ከነበረው ስቃይ ብንሸሽም፣ አምባገነኑ ስርዓት ግን አፋችን ለመዝጋት እያሳደደን ነው“ ብሏል።-ሌላ ኤርትራዊ ደግሞ “ብዙ የተጎዱ ሰዎች አይቼ አዝኛለሁ። ምክንያቱ ሁለቱም ከኔ ወገን ናቸው “ ብሏል።--ቀደም ሲል በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥርያ ቤት ያገልገሉት እና በእንግሊዝ ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በዲያስፖራ ፖለቲካ እየተከታተሉ የሚገኙት ዘርዓ ሥላሴ ረዳኢ ሸከር፤ በስደተኞች ላይ እየበረታ የመጣው ቁጣ ‘የብዙ ችግሮች ድምር ነው’ ሲሉ ይገልጹታል።-“ከነጻነት በኋላ ለረዥም ዓመታት፣ በተለይም እአአ ከ1998 ጀምሮ፣ ስርዓቱ በዜጎች ላይ ሲፈጽም የቆየው በደል፣ ሕዝብን ያገለለ እና የከፋፈለ የስርዓቱ አካሄድ ያስከተለው ውጤት ነው” ይላሉ።-ጂ-15 በመባል የሚታወቁት በኤርትራ የለውጥ እና ዲሞክራሲ ጥያቄ ያቀረቡ የሠራዊት አመራሮች እና ሚኒስትሮች እአአ መስከረም 2001 በመንግሥት ከታሠሩ በኋላ የገቡበት አይታወቅም።-ከፖለቲካ እና ሃይማኖት ነጻነት ጋር ተያይዞ አገሪቱ ዜጎቿ ላይ የመብት ጥሰት ትፈጽማለች የሚል በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ትከሰሳለች።-ገደብ ያልተበጀለት ወታደራዊ አገልግሎትም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች አገራችው ጥለው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል።-ኤርትራ ግን ተቋማቱ የምዕራባውያን የፕሮፖጋንዳ መሣሪያ እንደሆኑ በመግለጽ ለፍልሰቱም የአገራቱን ፖሊሲ ተጠያቂ ታደርጋለች።-በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዌስት ለንደን መምህር እና ሳይኮቴራፒስት የሆኑት ሠላም ኪዳነ በበኩላቸው የኤርትራ መንግሥት የዲያስፖራውን ማኅበረሰብ ለመቆጣጠር የሚያደርጋቸው ጥረቶች ለተቃውሞ እና ለሁከት ምክንያት መሆናቸውን ይገልጻሉ።-አውሮፓና ሰሜን አሜሪካን ጨምሮ ኤርትራውያን በተሰደዱበት አገር ማኅበረሰቡ “የራሳችሁን በተለይም የጥላቻ እና የጦርነት ፕሮፖጋንዳ እንድታካሂዱ አንፈቅድም” ሲል መቆየቱን ገልጸዋል።-ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተቃዋሚዎች እና በመንግሥት ደጋፊዎች መካከል በተለያዩ አገራት እየተባባሰ የመጣው ሁከት “መጥፎ አጋጣሚ” እና “ሁሉንም ኤርትራዊ የሚያከስር፤ መሆን የማይገባው” በማለት የዲያስፖራ ፖለቲካ አጥኚው ዘርዓ ሥላሴ ያስረዳሉ።-ሠላማዊ እንቅስቃሴዎች ፍሬ ባለማፍራታቸው የተፈጠረ መሆኑንም ያነሳሉ።-“ስርዓቱ ወደ ቀልቡ እንዲመለስ፣ ችግሮች በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ እና ስልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክብ በጽሑፍም በመግለጫም ጥሪ ቀርቧል። በአገር ውስጥም በውጭም እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። ስርዓቱ ግን ጆሮ ዳባ ልበስ አለ። ብዝበዛው በመቀጠሉ እና ተቃዋሚው በመብዛቱ የተቃውሞ ዕድገት መኖሩ ተፈጥሯዊ ነው” ብለዋል።-ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በተለይ ውጭ በሚኖሩ ወጣት ስደተኞች እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎች፣ ብዙ ሰዎች እየተሳተፉባቸው ያሉ ቢሆኑም፤ ያልተደራጁ እና አስተባባሪዎቹ የማይታወቁ እንደሆኑ ይገለጻል።-የዳያስፖራ ፖለቲካ አጥኚው ግን በዚህ አይስማሙም።-“ማህበራዊ እንቅስቃሴ በባህሪው ሁሉን አቀፍ ነው። እንቅስቃሴው ሁሉንም የስርዓቱን ተቃዋሚዎች ያቀፈ ነው። የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ቲንክታንኮች፣ አንቂዎች፣ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ያሉት በየአካባቢው የተደራጀ ነው“ ይላሉ።-“የተለያዩ ቦታ የተለያዩ መሪዎች አሉ” የሚሉት ሠላም ለምሳሌ በለንደን ተቃውሞ ለማዘጋጀት “ብዙ ወጣቶች እና እናቶች ነበሩ የሚታዩት” ብለዋል።-“ለዛች ሰዓት በሚል የሚደረግ ዝግጅት ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙ ሥራ ይሠራል። ብዙ ሃሳብ እና ሀብት የመሰብሰብ አቅምም ተፈጥሯል። አንድ አስተባባሪ ያለው ነው ማለት ግን አይቻልም” ሲሉ ገልጸዋል።-በእስራኤል ያለውም ተመሳሳይ መሆኑን ተናግረዋል።-በእስራኤል ያሉ ኤርትራውያን ዘንድ መንግሥትን የሚደግፍ ሊኖር አይገባም የሚሉት ሠላም፣ ምክንያት ሲባሉ “ከዚህ መንግሥት አስከፊ ጥቃት ሸሽተን የመጣን ነን የሚሉ ናቸው። ሌሎች አገሮች ከስርዓቱ በፊት የመጡ እና የተወለዱ አሉ። በእስራኤል ግን ሁሉም ሸሽተው የመጡ ናቸው። ደጋፊ ሊኖር አይገባም” ብለዋል።-መንግሥት ‘ትንንሽ ልዩነቶችን ተጠቅሞ ትልልቅ ጥላቻ እንዲኖር እና የራሱን ፕሮፖጋንዳ ለማካሄድ ስለሞከረ’ ግጭቱ መፈጠሩን ለቢቢሲ ተናግረዋል።-ለተከታታይ ቀናት “መንግሥት እና ደጋፊዎቹ ‘እየተዘጋጀን ነው እናሳያቸዋለን ሲሉ ነበር። 4ጂ የሚባል ቡድን አለን በሚገባ ይጠብቃችኋል።’ ‘ሃደ ልቢ’ የሚባልም ቡድንንም ሲያሰለጥኗቸው እና ሲያዘጋጇቸው የሚያሳይ ቪዲዮ፣ ፎቶ እና ጽሑፍ ሲሰራጭ ነበር” ብለዋል።-የኤርትራ መንግሥትን የሚቃወሙት ደግሞ ራሳቸውን “ብርጌድ ንሐመዱ” ብለው ይጠራሉ። “አገሬን፣ መሬቴን፣ ሕዝቤን ነጻ አወጣለሁ” የሚል ትርጉም እንዳለው ዘርዓ ሥላሴ ይገልጻል።-ኤርትራውያኑ የመንግሥት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ጎራ ለይተው በቴል አቪቭ ያገጠመው ሁከት ከአሁን በፊት ታይቶ የማይታወቅ እንደሆነ ምንጮች ይገልጻሉ። ሆኖም ግን የመጀሪያው አይደለም።-እአአ በ2019 በደቡብ ቴል አቪቭ አጋጥሞ በነበረ ተመሳሳይ ሁከት፤ አንድ ጥገኝነት ጠያቂ የኤርትራ መንግሥት ደጋፊ በስለት ተወግቶ ሕይወቱ አልፏል።-በእስራኤል 18 ሺህ በላይ ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራውያን እንደሚኖሩ ይገመታል። አብዛኛዎቹም ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የገቡ ናቸው።-ቀደም ሲል የኢኮኖሚ ስደተኞች ናቸው በሚል ቴል አቪቭ ከአገር ልታስወጣቸው ጥረት አድርጋለች። የፍርድ ቤት ክልከላ ግን ጥረቱ እንዳይሳካ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።-እስራኤል ውስጥ ስደተኞችን የማይፈልጉ ቀኝ ዘመም ፓርቲዎች አጋጣሚውን ስለሚጠቀሙበት (ግጭቱ) ተጽዕኖ እንደሚኖረው ሠላም ያምናሉ።-“በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ጥገኝነት የጠየቀን አካል ወደመጣባት ቦታ አትመለስውም” ብለዋል።-ወንጀል የፈጸሙ አሉ ከተባለ “መጠበቅ አለብን። መንግሥታችንን ነው የምንደግፈው ብለው ከኤርትራ ኤምባሲ ጋር ሲሠሩ እና ወገኖቻቸውን ሊያጠቁ ሲዘጋጁ የነበሩት በሚደርስባቸው ነገር ምንም ቅሬታ የለኝም” ሲሉ ገልጸዋል።-ኤርትራውያኑን ወደ ሦስተኛ አገር እንዲሄዱ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግን ጠቁመዋል።-“በእስራኤል መንግሥት የተሳሳተ ሰለባ ላለመሆን የኤርትራን የተሳሳተ መንገድ ዝም አትልም። ይህንን ከግምት አስገብተው የወሰኑት ነው” ሲሉ ተቃውሞውን ስለተቀላቀሉት ተቃዋሚዎች ተናግረዋል።-“ውጤቱ ጎጂ ነው። አገራቸው ጥሩ ስላልሆነላቸው ነው የተሰደዱት፤ ደልቷቸው አልወጡም” የሚሉት የቀድሞው የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባልደረባው ዘርዓ ሥላሴ “የእስራኤል የጥገኝነት ሕግ ከለላ የሚሰጥ አይደለም። [ስደተኞቹን ለማባረር ] ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ሚዲያ ላይም እስራኤል እንደዚህ አይነት ነገር አጋጥሟት አያውቅም የሚል ተረክ እየተጠቀሙ ነው” ሲሉ አክለዋል።--ስርዓቱ የአገሪቱን የጸጥታና ወታደራዊ ኃይል ተጠቅሞ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ ጥያቄዎችን ለሚያነሳ “የአገር ጠላት አድርጎ የማጥቃት ባህርይ ስላለው ነው [ፖለቲካዊ እንቅስቀሴውን] በውጭ አገር የምናየው” ይላሉ።-የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ተቃውሞው ወደ አገር ውስጥም መዛመቱ አይቀርም ሲሉም ግምተቸውን ያስቀምጣሉ።-“በውጭ አገር ያለው መንግሥትን ከተቃወመ በውስጥ ያለውም ስርዓቱን ይቃወመዋል። መች ይገናኛል የሚለው ግን የጊዜ ጉዳይ ነው” ብለዋል።-ከአገር ውጭ በርካታ ተቃውሞች መደረጋቸውን የሚገልጹት ሠላም ‘ተጽዕኖ የነበራቸው እና ያልነበራቸው’ እንደነበሩ ጠቁመዋል።-የእስራኤሉ ሁከት በመላው ዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ የራሱ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ግምታቸውን አስቀምጠዋል።-“ለምሳሌ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰውን ነገር እንደ መቀለጃና መጫወቻ፤ ሞታቸውን እንደ ድል እየተቆጠረ የሚደረገው ነገር ሁላችንም ልንቃወመው የሚገባን ነገር ነው። ታዳጊ ወጣቶችን መሳሪያ የሚመሰል መጫወቻ በመስጠት ወታደራዊ ልብስ በማስለበስ ለፕሮፖጋንዳ መጠቀም፤ የኤርትራ መንግሥትን የማይደግፉትን እንደማይረቡና እንደ እንስሳ በማድረግ ለማቅረብ የሚደረግ ፌስቲቫል ለማንም አይጠቅምም” ብለዋል።-ይህን መሠሉን ዝግጅት ቀደም ሲል በሠላማዊ መንገድ ለመቃወም መሞከሩን ጠቅሰው፣ አሁን አልፎ አልፎ ወደ ሁከት ማምራቱን አስታውቀዋል።-ተመሳሳይ ዝግጅት እንደ እንግሊዝ ባሉ አገራት መቅረቱን አንስተው ይህንንም “መልካም ውጤት” ብለውታል።-የኤርትራ መንግሥት ልሳን በሆነው ሻባይት ጋዜጣ መስከረም 5 2023 የወጣው አጭር ጽሑፍ አንዳንድ አገሮች ባህላዊ ፌስቲቫሉን ለማወክ፤ የተፈጠረው ሁከት “ሲያበረታቱ ታይተዋል” ሲል ከስሷል።-የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድንም ወቅሷል።-“የማይበገረው የኤርትራ ሕዝብ የመከላከል አቅም ያስደነገጣቸው ትልልቅ የስለላ ተቋማት (ሞሳድን ጨምሮ) የኤርትራ ሕዝብን አንድነት ለማወክ ጥቂት ባንዳዎች የወጠኑት ከንቱ ተንኮል” በማለት በቀጣይ ዝርዝር መግለጫ አንደሚሰጥ አስታውቋል።
የፎቶው ባለመብት EOTC-ባለፈው ሳምንት የቤተክርስቲያኗ ምዕመናን በአብያተ ክርስቲያናት በመገኘት የጸሎት ሥነ ሥርዓቶች ተካሂደዋል--ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ክስተት ጋር በተያያዘ የእምነቱ ተከታዮች መታሰራቸውን እና አብዛኞቹም ወደ አዋሽ ሰባት የጦር ካምፕ መወሰዳቸውን የቤተ ክርስቲያኗ ጠበቆች ለቢቢሲ ገለጹ።-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አያሌው ቢታኔ እስካሁን ባላቸው መረጃ ከ200 በላይ ምዕመናን መታሰራቸውን ተናግረዋል።-ሆኖም በተጨባጭ ደረጃ ቁጥሩ በትክክል እንደማይታወቅ እና በሚቀጥሉት ቀናትም ለዚህ ተግባር የተዋቀረው የመረጃ አካልም ዝርዝሩን ያቀርባል ብለዋል።-እስሩ በአብዛኛው የተከናወነው በአዲስ አበባ እና በአጎራባች አካባቢዎች ሲሆን ወደ አዋሽ ሰባት የተወሰዱ ምዕመናን ቁጥርም በርካታ ስለመሆናቸው መረጃ አለን ብለዋል።-አዋሽ ሰባት ውስጥ ምን ያህል ግለሰቦች እንደታሰሩ በትክክል ባያውቁም ከ100 አስከ 200 የሚሆኑ የዕምነቱ ተከታዮች ወደ ስፍራው መወሰዳቸውን ገልጸዋል።-በአዲስ አበባ ውስጥ ከታሰሩት መካከል የተወሰኑት ሰኞ የካቲት 06/2015 ዓ.ም. ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ‘በሽብር ተግባር እና ሕገ መንግሥቱን ለመናድ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ፈጥረው ሲንቀሳቀሱ’ ተጠርጥረው መያዛቸው ተገልጿል።-ከእነዚህም ውስጥ በእነመምህር ምህረተ አብ አሰፋ እና ኪሩቤል አሰፋ መዝገብ እንዲሁም በእነ ፌቨን ዘሪሁን እና ብሩክታዊት ነብዩ መዝገብ አስራ ሁለት ሰዎች ሰኞ ከዋለው ችሎት መቅረባቸውን የሕግ ባለሙያው አስረድተዋል።-ከመካከላቸውም ሰባት ተጠርጣሪዎች በዋስ ቢለቀቁም ሌሎቹ የስምንት ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶ ጉዳያቸው የካቲት 14/2015 ዓ.ም. እንደሚታይ ተገልጿል።-በሽብር ወንጀል ከተጠረጠሩት መካከል የቤተክርስያኗ የወጣቶች እና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት ሰብሳቢ ፌቨን ዘሪሁን፣ የኅብረቱ ዋና ጸሐፊ ብሩክታዊት ነብዩ እንዲሁም መሳይ ተፈራ፣ ተካልኝ ኢቲቻ፣ ወንደሰን ንጉሴ፣ ረ/ሳጅን ሠራዊት ፀጋ እና ፋሲል አግደው እንደሚገኙበት ማኅበረ ቅዱሳን ገልጿል።-በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያኗ በሰባኪ ወንጌልነት የሚያገለግለው መምህር ምህረተአብ አሰፋን ጨምሮ አማኑኤል አያሌው፣ ኪሩቤል አሰፋ፣ ሰይፉ አለማየሁ እና እጅጋየሁ ዳርጌ እንደተካተቱበት ተገልጿል።-ግለሰቦቹ የራሳቸውን ዓላማና የፖለቲካ ፍላጎት ለማሳካት፣ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት በመፍጠር፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት፣ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን በመናድ መጠርጠራቸውም ሰፍሯል።-ግለሰቦቹ ቤት ለቤት በተደረገ አሰሳ እንደታሰሩ የተናገሩት አቶ አያሌው፣ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ካሉት እንደ ለገጣፎ፣ ሰበታ፣ አሸዋ ሜዳ በነበሩ እስሮች ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሄዱ የነበሩ የታሰሩ ካህናት መኖራቸውን አመልክተዋል።-ባለፉት ሳምንታት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕገወጥ ነው ካለችው የጵጵስና ሹመት እና የሲኖዶስ ምሥረታ ጋር በተያያዘ እስሮቹ መፈጸማቸውን የተናገሩት የሕግ ባለሙያው፣ በተለይም የሃይማኖት አባቶች ከመንግሥት ጋር ከተወያዩ በኋላ እስሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አመራሮች ባለፈው ሳምንት አርብ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ስለተፈጠረው ክስተት መወያየታቸውን እና የቤተ ክርስቲያኗንም ጥያቄ ሙሉ በሙሉ መንግሥት መቀበሉን ማሳወቋ ይታወሳል።-ሆኖም ጠበቃው እንደሚሉት ቤተ ክርስቲያኗ በራሷ ሃይማኖታዊ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ያለ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ጉዳዩን እልባት እንድትሰጥ መንግሥት ከተስማማ በኋላ እስሮች እና ውክቢያዎች መፋፋማቸውን መረጃዎች ያሳያል ብለዋል።-ቤተ ክርስቲያኗ በሽማግሌዎች እንዲሁም በሃይማኖት አባቶች በሚመራ ኮሚቴ ጥያቄውን ለመንግሥት ያቀረበች ሲሆን፣ በልዩ ሁኔታም ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል።-ከፌደራል ፖሊስ እንዲሁም ለዚህ ተግባር ከተቋቋመው የአዲስ አባበ ኮማንድ ፖስት ጋር ቤተ ክርስቲያኗ ውይይት እያደረገች እንደሆነና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ለመስጠትም ጥረት እየተደረገም እንደሆነ ተገልጿል።-እስሮቹን በተመለከተ ቢቢሲ የአዲስ አበባ ፖሊስን ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም ስለ እስሮቹ የጠየቀ ሲሆን፣ ክትትል እያደረጉ እንደሆነ እና ምርመራም ሲጠናቀቅ እንደሚያሳዉቁ ለቢቢሲ ገልጸዋል።-በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከተከሰተው ችግር ጋር በተያያዘ ግድያዎች፣ እስሮች፣ መዋከቦች እና እንግልቶች መፈጸማቸውን ኢሰመኮ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።-አዲስ ሲኖዶስ አቋቁመናል ያሉ ጳጳሳት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን መያዛቸውን የተቃወሙ ምዕመናን ላይ የመንግሥት የፀጥታ አባላት እና ተባባሪዎቻቸው ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል መጠቀማቸው ተገልጿል።-በዚህም በጥይት እና በድብደባ ስምንት ሰዎች ሻሸመኔ ውስጥ መግደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያስታወቀ ሲሆን፣ ቤተ ክርስቲያኗ በበኩሏ ቁጥሩ ከዚህ ከፍ ያለ ነው ብላለች።-በተለያዩ ቦታዎችም አዲሱን “ቤተ ክህነት” አቋቁመናል ያሉትን ጳጳሳት በተቃወሙ ምዕመናን እና የሃይማኖት መሪዎች ላይ ድብደባ፣ ማዋከብ፣ ከቤተ ክርስቲያናት ማባረር፣ የመንቀሳቀስ መብትን በኃይል መገደብ እና ከሕግ ውጪ እስራት ተፈጽሟል ብሏል።-ከዚህም በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያኗ ለጥበቃ የወሰደችውን የጦር መሳሪያ እንድታስረክብም መጠየቋን አቶ አያሌው ይናገራሉ።-የተደራጁ ኃይሎች ከ20 በላይ በሚበልጡ አብያተ ክርስቲያናት በመዘዋወር የጥበቃ የጦር መሳሪያዎችን እንዲያስረክቡ የተጠየቁ ሲሆን፣ አምስት ወይም ስድስት ከሚሆኑ የአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት የጥበቃ የጦር መሳሪያዎች ተወስዷል ብለዋል።-ይህም “ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ” በሚል እንደተነገራቸው የገለጹት የሕግ ባለሙያው፣ ከማን ነው የሚለው ግን ግልጽ አይደለም ብለዋል።-ከፓርትርያርኩም ሆነ ከቅዱስ ሲኖዶሱ እውቅ እና ውጪ 26 ጳጳሳት መሾማቸውን ተከትሎ የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓት እና ቀኖና የሚጥስ ነው በማለት የጵጵስና ማዕረጉን የሰጡትን እንዲሁም የተሾሙትን የማውገዝና ሹመታቸውም ተሽሮ እንዲለዩ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል።-የቤተ ክርስቲያኗ አካሄድ አካታች እንዳልነበረ እና ምዕመናን በቋንቋቸው መገልገል እንዳልቻሉ በመግለጽ አዲስ ሲኖዶስ መቋቋሙን የገለጹት ጳጳሳት ውሳኔውን በማውገዝ በእርምጃቸው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።
የፎቶው ባለመብት Gettyimage-በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት ከሦስት ወራት በላይ ሆኖታል።-ክልሉ ካለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያን በተለያዩ ጊዜያት እያስተናገደ ይገኛል።-በዚህም ምክንያት በበርካታ የክልሉ አካባቢዎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ተስተጓጉለዋል። በዚህም ሳቢያ ነዋሪዎች ከመደበኛ የሥራ እንቅስቃሴ ውጪ ሆነው ሕይወታቸውን ለመምራት ተቸግረዋል።-ከክልሉ ወደ አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ወደ ክልሉ የተለያዩ ከተሞች የሚደረጉ ጉዞዎች የተገደቡ በመሆናቸው መሠረታዊ የፍጆታ እቃዎች፣ መድኃኒቶች እና ነዳጅ በበቂ ሁኔታ ማግኘት ፈተና ሆኗል ይላሉ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች።-በክልሉ በተለይ በግብርና እና በቱሪዝም ዘርፎች የተሻለ ምርት እና ገቢ የነበረ ቢሆንም የተፈጠረው አለመረጋጋት ሰብል ከሚዘራበት አስከሚሰበሰብበት ወቅት ድረስ የቀጠለ በመሆኑ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የክልሉ አርሶ አደሮች ላይ ጉዳት አድርሷል፣ ተጨማሪ ስጋትም ተደቅኗል።-በሌላ በኩል በአገሪቱ ካሉ የጎብኚዎች መዳረሻዎች መካከል በርከት ያሉት የሚገኙበት የአማራ ክልል የቱሪዝም እንቅስቃሴ ክፉኛ በመደናቀፉ ኑሯቸው በዘርፉ ላይ የተመሠረተ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በችግር ላይ እንዳሉ ይናገራሉ።-የአማራ ክልል ከፍተኛ የሰብል ምርት ከሚሰበሰብባቸው የአገሪቱ ክፍሎች አንዱ ቢሆንም፣ በክልሉ የተከሰተው አለመረጋገት በግብርናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።-በተለይ በመንግሥት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተጀመረው ግጭት ማሳ በሰብል በሚሸፈንበት እና የማዳበሪያ ግብዓት በሚሰራጭበት ወቅት ስለነበረ ተጽዕኖው የከፋ መሆኑን ቢቢሲ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ከዚህ ቀደም መግለጻቸው ይታወሳል።-በክልሉ ትርፍ አምራች ከሆኑ አካባቢዎች መካከል ምዕራብ ጎጃም ዞን አንዱ ነው። በዞኑ ጃቢ ጠህናን ወረዳ የሚኖሩት አርሶ አደር መስፍን ቻላቸው በጦርነቱ ምክንያት በመቶ ሺዎች ብር የሚገመት ንብረት ሊያጡ እንደሚችሉ ይናገራሉ።-አቶ መስፍን በዘንድሮው የምርት ዘመን ከመደበኛ ሰብሎች በተጨማሪ አንድ ሄክታር ተኩል ማሳ ላይ ሸንኮራ አገዳ አልምተዋል። ሸንኮራ አገዳው አሁን ለመሰብሰብ የደረሰ ቢሆንም ባለው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ነጋዴዎች ስጋት ስላደረባቸው ሸንኮራ አገዳውን የሚገዛ ጠፍቷል። በመሆኑም አቶ መስፍን ሌላ አማራጭ እስካላገኙ ድረስ የለፉበትን የሸንኮራ አገዳ ቆርጠው ለመጣል እንደሚገደዱ ይናገራሉ።-ሰላም ሰፍኖ መደበኛ እንቅስቃሴ ቢጀመር ኖሮ ያለሙት የሸንኮራ አገዳ ልማት ከ600 ሺህ ብር በላይ ሊያወጣላቸው እንደሚችል ይገምታሉ።-አቶ መስፍን ከዚህም በተጨማሪ እርሳቸው እና ሌሎች ጎርቤት አርሶ አደሮች የብርቱካን እና የአቮካዶ ፍራፍሬዎችን አልምተዋል። ነገር ግን የሰላሙ ሁኔታ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የፍራፍሬ ምርቱ ጉዳይም ገበያ የማያገኝ በመሆኑ አሳሳቢ ሆኖባቸዋል።-የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በክልሉ ያለው ግጭት በአርሶ አደሩ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።-ምንም እንኳ በባለሙያ የተጠና መረጃ ባይኖርም ለአርሶ አደሩ ድጋፍ ሰጪ የሆኑ ሙያተኞች ወደ ሥራ የሚሰማሩበት ሁኔታ ባለመፈጠሩ፣ አርሶ አደሮች በግጭት ምክንያት ሥራ በማቆማቸው እና ተያያዥ ምክንያቶች ከፍተኛ ጫና እንደሚያሳድር ኃላፊው ገልጸዋል።-በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸመ ዘረፋ ምክንያት ለአርሶ አደሮች መድረስ የነበረበት የግብርና ግብዓት ሳይደርስ መቅረቱንም ዶ/ር ድረስ ተናግረዋል። “እስካሁን ከ30 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ተዘርፏል” ያሉት የቢሮ ኃላፊው፣ “በወቅቱም በጦርነቱ ምክንያት ዘግይቶ የደረሰውን ግብዓት ማሰራጨት አልቻልንም” ብለዋል።-በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች አሁንም ግጭቱ እንደቀጠለ ነው። አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ተሰብስቦ በተከመረ ሰብል ላይ የሚጣል ከባድ መሣሪያ ቃጠሎ ያስነሳል የሚል ስጋት መኖሩን አርሶ አደሮች ይናገራሉ።-በሌላ በኩል በግጭቱ ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች አርሶ አደሮች ሰብል በፍጥነት መሰብሰብ ባለመቻላቸው ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል።-ሌሎች ደግሞ ያመረቱትን ሰብል ወደ ቤታቸውም ሆነ ወደ ገበያ ቦታ ለማጓጓዝ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አልፈቀደላቸውም።-ከዚህም በተጨማሪም አርሶ አደሮቹ ባለፈው ዓመት ያጋጠማቸው የማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት ዘንድሮም ተባብሶ ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።-የቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ድረስ ግን ማዳበሪያውን ቀድሞ መግዛት መቻሉን ተናግረዋል። ያም ሆኖ ግን ለሚቀጥለው ዓመት የሚሆነውን ማዳበሪያ ለማሰራጨት አሁንም የፀጥታው ሁኔታ አስተማማኝ ባለመሆኑ ስጋቱ መኖሩን ገልጸዋል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-ደሴ ከተማ-በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሏል።-ከጎንደር፣ ባሕር ዳር እና ከሌሎች የምዕራብ አማራ ከተሞች የሚነሱ ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ እና ደርሶ መልስ የሚያደርጉትን ጉዞ ካቋረጡ ወራት መቆጠራቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ።-በተለይ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ በእነዚህ አካባቢዎች እንቅስቃሴ አቁመዋል። በዚህም ምክንያት የሰዎች እና የንግድ እንቅስቃሴ ክፉኛ በመስተጓጎሉ አሽከርካሪዎችን ጨምሮ ነዋሪዎች ለከባድ ችግር መጋለጣቸውን ያነሳሉ።-መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ በማሽከርከር ሕይወቱን የሚመራው አቶ ዮሴፍ አበበ፣ ነዋሪነቱ በምዕራብ ጎጃም ፍኖተ ሰላም ከተማ ነው።-ዮሴፍ እንደሚለው ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ጉዞ ከመቆሙም በላይ በክልሉ ውስጥ ለመንቀሳቀስም ያለው የፀጥታ ችግር እና የነዳጅ አቅርቦት አለመኖር ከፍተኛ ጫና አሳድሮባቸዋል።-“ከፍተኛ የሆነ መጉላላት እና የታሪፍ ጭማሪ ተደርጓል። ከነበረው ክፍያ ጋር ሲነጻጸር ታሪፉ በእጥፍ ጨምሯል” የሚለው ዮሴፍ፣ ይህ የሆነውም የነዳጅ አቅርቦት ባለመኖሩ እና ሌሎች የንግድ እንቅስቃሴዎች በመቆማቸው ምክንያት ነው።-የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ እርሱ በሚኖርበት ፍኖተ ሰላም ከተማ እስከ 150 ብር ድረስ እንደሚሸጥ በመጥቀስ፣ ይህም ሆኖ ነዳጅ በማደያዎች ሳይሆን በደላሎች እየተፈለገ በጥቁር ገበያ እንደሚሸጥ አመልክቷል።-በክልሉ ውስጥ ጦርነቱ እዚህም እዚያም ቢቀሰቀስም ተሽከርካሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ሆነው ለመንቀሳቀስ ይሞክራሉ። ነገር ግን ጉዟቸው በሰቀቀን የተሞላ መሆኑን ዮሴፍ ይናገራል።-“አንድ ኬላ ላይ መከላከያ ይፈትሻል። ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ ፋኖ ኬላ ዘርግቶ ይጠብቀነናል” የሚለው አቶ ዮሴፍ፣ በሰላሙ ጊዜ በቀን ውስጥ ከፍኖተ ሰላም ባሕር ዳር እስከ 3 ጊዜ ደርሶ መልስ ይሰራ የነበረ ተሽከርካሪ በአሁኑ ወቅት አንድ ጊዜ ደርሶ ለመመለስ እንኳን በጣም አስቸጋሪ ነው ይላል።-“በስጋት ነው የምንጓዘው፣ አንድን ከተማ ሰላም ቢታለፍ ሌላኛው ከተማ ላይ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል” በማለት ያለው ሁኔታ ለሥራ ብቻ ሳይሆን ለሕይወትም አስጊ መሆኑን ያብራራል።-ከጦርነቱ በፊት ከፍኖተ ሰላም ባሕር ዳር ለመጓዝ 3 ሰዓት ይፈጅ የነበረው ጉዞ፣ አሁን ግን በየመንገዱ በሚደረገው ፍተሻ እና የሰላም መደፍረስ ምክንያት እስከ 6 ሰዓት ይወስዳል። በዚህ ምክንያትም አሽከርካሪዎች ያለውን የነዳጅ ዋጋ መናር እና የጉዞ መጉላላት ለማካካስ ዋጋውን በእጥፍ ጨምረውታል።-ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ከሚደረገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ በአንድ ከተማ ውስጥም ሕሙማንን እና በምጥ የተያዙ ወላዶችን ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ የተሽከርካሪ እጥረት በጣም አሳሳቢ መሆኑንም ገልጿል።-የመንግሥት ተሽከርካሪዎችን እና አምቡላንሶችን ሙሉ በሙሉ የሚጠቀምባቸው መከላከያ ሠራዊት በመሆኑ ከተቋማት የተሽከርካሪ እገዛ መጠየቅም አስቸጋሪ መሆኑን ይናገራል።-ከዚህ በተጨማሪም በከተሞች የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የተፈቀደው እስከ ምሽቱ 12፡00 በመሆኑ ከዚያ በኋላ የሚያጋጥምን ድንገተኛ ሕመም ለመታከም ተሽከርካሪ መጠቀም የማይቻል በመሆኑ ነዋሪው ላይ ከፍተኛ ችግር እየተፈጠረ መሆኑን አቶ ይሴፍ ተናግሯል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-አማራ ክልል በርካታ የጎብኝዎች መዳረሻ የሚገኝበት ክልል ነው።-በኢትዮጵያ የውጭ አገር ጎብኚዎችን በመሳብ ከሚታወቁ መዳረሻዎች አብዛኛዎቹ የሚገኙት በአማራ ክልል ነው።-የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደር የፋሲል ቤተ መንግሥት፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እና የጭስ አባይ ፏፏቴ በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው።-ነገር ግን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋት እና የሰሜኑ ጦርነት መቀስቀሱ የቱሪስት ፍሰቱን በእጅጉ ጎድቶት ቆይቶ ነበር። ከሦስት ወራት በፊት በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ደግሞ ሁኔታውን አባብሶታል።-አቶ አሰግድ ተስፋዬ በአስጎብኚነት ሙያ ለ15 ዓመታት ሠርቷል። በአብዛኛው የማስጎብኘት ሥራውን የሚያከናውነው በጎንደር እና በሰሜን ብሔራዊ ፓርክ ነው።-አሰግድ እንደሚለው በኢትዮጵያ የቱሪስት ፍሰት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርሰው ከሰኔ እስከ ጥር ባሉት ወራት ነው። ነገር ግን በእነዚህ ወራት በተለይ በአማራ ክልል ግጭት በመቀስቀሱ የቱሪዝም እንቅስቃሴው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መቆሙን ይናገራል።-የየብስ ትራንስፖርት በመቆሙ ከውጭ ጎብኚዎች በተጨማሪ የአገር ውስጥ ጎብኚዎችም እንደ መስቀል እና ጥምቀትን የመሳሰሉ የአደባባይ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ያደርጉት የነበረው ጉዞ መቋረጡንም ይገልጻል።-የዓመቱ 60 በመቶ የሚሆነው ጎብኚ ከሰኔ እስከ ጥር ባሉት ወራት የሚገባ ነው የሚለው አቶ አሰግድ፣ በጎንደር ብቻ በሰላሙ ጊዜ በዓመት 150 ሺህ የአገር ውስጥ እና 30 ሺህ የውጭ አገር ጎብኝዎችን ይቀበሉ እንደነበር ያስታውሳል።-አሁን ባለው ሁኔታ ግን የአገር ውስጥ እንግዳ ወደ ጎንደር የሚሄደው በወር በአማካይ ከ50 እስከ 60 የሚደርስ ብቻ መሆኑን በመግለጽ፣ ከአገር ውጭ ደግሞ በቀን በአማካይ አንድ ጎብኚ ብቻ እንደሚመጣ ተናግሯል።-ችግሮቹ ከመደራረባቸው በፊት ለጥምቀት ብቻ ወደ ጎንደር ከ3000 እስከ 5000 የውጭ ቱሪስቶች ይመጡ ነበር። አሰግድ እንደሚለው ይህ ቁጥር አሁን በእጅጉ ቀንሷል። ለአብነት ባለፈው ዓመት ለጥምቀት በዓል ጎንደር የተገኙት የውጭ አገር ጎብኚዎች 15 ብቻ ናቸው ይላል።-በሰሜን ፓርክ እና በጎንደር ከተማ ብቻ 200 የአካባቢ አስጎብኚዎች እና 25 አስጎብኚ ድርጅቶች አሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ ሆቴሎች፣ በቅሎ አከራዮች፣ ስካውቶች፣ ምግብ አብሳዮች፣ መንገድ መሪዎች እና ድንኳን የሚተክሉ ግለሰቦች በቀጥታ ሕይወታቸው ከጎብኚዎች ጋር የተያያዘ ነው።-በክልሉ ውስጥ የሚካሄደው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ግን ጎብኚዎቹን በማስቀረቱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሕይወት ላይ የከፋ ጫና አሳድሯል።-የሁለት ልጆች አባት የሆነው አሰግድ አሁን ሥራ በመቆሙ በሰላሙ ጊዜ ሰርቶ በቆጠበው ገንዘብ ሕይወቱን እየመራ ነው።-ለጎብኚዎች የሚሸጡ በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉ ሦስት መጻሕፍትን አዘጋጅቷል። ነገር ግን ማሳተሚያ ገንዘብ ባለመኖሩ፣ ቢታተምም መጽሐፍቱን የሚገዙት ቱሪስቶች እየመጡ ባለመሆናቸው ምክንያት “መደርደሪያ ላይ ተቀምጠዋል” ይላል።-በሌላ በኩል ደግሞ በርካታ አስጎብኚ ወጣቶች ከባንክ ተበድረው የቱሪስት ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ገዝተዋል። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ገቢያቸው ሙሉ በሙሉ በመቆሙ ብዙ ጓደኞቹ ያንን ዕዳ መልሶ ለመክፈል መቸገራቸውን ይገልጻል።-በመሆኑም “መንግሥት ቢያንስ ታኅሣሥ እና ጥር ወራትን ተኩስ አቁም ማድረግ አለበት” የሚል ሃሳብ ሰንዝሯል። ምክንያቱም በሁለቱ ወራት ቢያንስ እንግዶችን በመቀበል የተወሰነ ሥራ መሥራት ይቻላል ሚል ተስፋ አለው።-በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ የክልል ልዩ ኃይሎችን በማፍረስ መልሶ ለማደራጀት እንዲሁም ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በአማራ ክልል ተቃውሞ ገጥሞታል።-በዚህም ምክንያት በክልሉ ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ተደጋጋሚ ግጭት አካሂደው በርካታ ትላልቅ ከተሞችን መቆጣጠር ችለው ነበር።-ይህም ሁኔታ ከክልሉ አቅም በላይ መሆኑን በመግለጽ የክልሉ መስተዳደር የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ እንዲገባ በጠየቀው መሠረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ የመከላከያ ሠራዊት ተሰማርቶ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ለወራት የዘለቀ ግጭት እየተካሄደ ነው።
የፎቶው ባለመብት KOREA SUMMIT PRESS POOL-የኪም መርሰዲስ ልዩ መጸዳጃ ቤት ተገጥሞለታል-የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ወደ ሩሲያዋ ቭላዲቮስቶክ የወደብ ከተማ ፑቲንን ለማግኘት እየተጓዙ ነው።-እርሳቸው የተሳፈሩበት ‘የጦር ባቡር’ ከ20 በላይ ጥይት የማይበሳቸው መኪናዎች ተጭነውበት ጉዞው አዝጋሚ ሆኗል።-ይህ ኪም የተሳፈሩበት ባቡር ራሱ ጥይት አይበሳውም። ልዩ ልዩ ዘመናዊ የቅኝት መሣሪያዎችም ተገጥመውለታል።-የሰሜን ኮሪያ መሪዎች ለጉዞ ለምን ባቡር እንደሚመርጡ ግልጽ አይደለም። ምናልባት ከደኅንነት አንጻር ሊሆን እንደሚችል ግን ይገመታል።-አሁን ኪም ጆንግ ኡንን ያሳፈረው ባቡር ከፒዯንጊያንግ ሩሲያ ለመግባት 20 ሰዓታት ይወስድበታል። ይህ ዘገባ ሲጠናቀር ጉዞውን አጋምሰውታል።-ጠቅላላ ርቀቱ 1180 ኪሎ ሜትር ነው። ባቡሩ ደግሞ ቀሰስተኛ ነው።-በሰዓት 50 ኪሎ ሜትር ነው የሚጓዘው።-ይህ ከለንደን ፈጣን ባቡር ሲነጻጸር በጣም ቀርፋፋ ነው።-የለንደን ባቡር በሰዓት 200 ኪሎ ሜትር ይበራል። የጃፓን ሺንካንሰን ማግኔቲክ ባቡር ደግሞ በሰዓት 320 ኪሎ ሜትር ይከንፋል።-የኪም ባቡር ቀሰስተኛ ይሁን እንጂ ራሱን የቻለ ተንቀሳቃሽ ቤተ መንግሥት ነው ቢባል ይቀላል።-ውድ የፈረንሳይ ወይን መጠጦች፣ ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች፣ ሬስቶራንቶች፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ ባር ወዘተ አሉት።-ይህ ልዩ የጦር ባቡር ስሙ ታይያንጎ ነው። በኮሪያ ቋንቋ ‘ፀሐዩ’ እንደማለት ነው። የኮሪያን አባት ኪም ኢል ሱንግን ለማስታወስ ነው ፀሐዩ የተባለው። የኪምን አያት ማለት ነው።-የፎቶው ባለመብት GETTY IMAGES-ኪን ጆንግ ኡን እንደ አባታቸው ባቡር ይወዳሉ-የኪም አያት ኢል ሱንግም እንዲሁ በባቡር ረዥም ርቀት ይሄዱ ነበር።-እርሳቸው እንዲያውም ቅርብ ሩሲያ ብቻ ሳይሆን እስከ ቬትናም አንዳንዴም እስከ ምሥራቅ አውሮፓ በባቡራቸው ነበር የሚጓዙት።-የሚጓዙባቸው ባቡሮች በከፍተኛ ሁኔታ በደኅንነት ሰዎች ጥብቅና ጥልቅ ፍተሻ ይደረግላቸዋል።-በጉዞው ላይ ተቀጣጣይ ፈንጂ እንዳይኖር ቀድሞ ሐዲድ መስመሩ ላይ ጽዳት ይደረግ ነበር።-የኪም ጁንግ ኡን አባት ኪም ጆንግ ኢል ሰሜን ኮሪያን እንደ አውሮፓዊያኑ ከ1994 እስከሞቱበት 2011 ድረስ መርተዋታል።-በዚህ ሁሉ ዘመን ግን አንድም ቀን በአውሮፕላን ሄደው አያውቁም።-ይህን ሁሉ ዘመን በመኪናና በባቡር ተጉዞው ነው የሞቱት።-ኪም ጆንግ ኢል በ2001 ዓ/ም ረዥም ጉዞ ማለትም 10 ቀናትን በባቡር ተጉዘው ፑቲንን አግኝተው ያውቃሉ።-በዚያ ዘመን ኪም ጆንግ ኢልን በጉዞው አጅበዋቸው የነበሩት የሩሲያ ኮማንደር ፑሊኮቭስኪ ማስታወሻ መጽሐፍ ጽፈዋል።-ትዝታቸውን ሲያወጉ ‘በዚያ ባቡር ውስጥ ማንኛውንም ምግብ ማዘዝ ይቻላል። ለምሳሌ የሩሲያ፣ የቻይና፣ የኮሪያ የጃፓን የፈረንሳይ ምግቦች ተሟልተው ይገኙ ነበር።’ ብለዋል።-ከፓሪስ ልዩ ልዩ ወይኖች እንዲሁም ትኩስ ሎብስተር በባቡሩ ውስጥ ለእንግዶች ይቀርባል።-እኚህ ኮማንደር፣ ‘እንዲህ ዓይነት ምቾት በፑቲን የግል ባቡር ውስጥ እንኳ አይገኝም’ ሲሉ ጽፈዋል።-ሌላው የሩሲያ ዲፕሎማት ጂዯርጂ ቶሎራያ በ2019 ይህን የኪምን አባት የ10 ቀናት ረዥም የባቡር ጉዞ ሲያስታዉሱ፣ ‘ጣፋጭ የአህያ ስጋ ይቀርብ እንደነበረ ትዝ የለኛል’ ብለዋል።-የሚገርመው ኪም ጆንግ ኢል የሞቱት በሚወዱት ባቡር እየተጓዙ በልብ ድካም ነው።-ይህ የነ ኪም ልዩ ወታደራዊ ባቡር 90 የሚሆኑ ፎርጉዎች አሉት። የስብሰባ ማዕከል፣ ምቹ መኝታ ክፍሎች፣ ሳተላይት ቴሌቪዥን መመልከቻዎችም ተገጥመውለታል።-ኪም ጆንግ ኡንን ለጊዜው አንተ እንበለውና እንደ አባቱ በአውሮፕላን መብረር የሚፈራ ሰው አይደለም።-ሩሲያ ሰራሽ በሆነው የግል ጄቱ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በሯል። ሆኖም እንደ አያቱና አባቱ ባቡርን ይመርጣል።-አሁን ወደ ሩሲያ እያቀናበት ያለው የኪም ጆንግ ኡን ልዩ የጦር ባቡር ፒንክ የሌዘር ሶፋዎች ያሉት ሲሆን 21 ፉርጎዎች ይከተሉታል።-ኪም ጆንግ ኡን የተማረው በስዊዘርላንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ነው።በአውሮፕላን በተደጋጋሚ ተጉዟል። ከሥልጣን በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በአውሮፕላን የተጓዘው ደግሞ ወደ ቻይና ነበር።-በመጋቢት 2018 ቻይና ቤጂንግ ተጉዞ ነበር በባቡር። ሆኖም ከባቡር ሲወርድ የተቀበሉት ዝነኛዎቹ መርሰዲስ ኤስ ተሽከርካሪዎች ናቸው።-እነዚህ መኪናዎች ኪም በየትኛው አገር ሲጓዙ ተጭነው ይወሰዳሉ።-እያንዳንዳቸው 1.8 ሚሊዯን ዶላር የሚያወጡ ቅንጡ መኪናዎች ናቸው።-ኪም እነዚህ መኪናዎች ውስጥ ሲሳፈር አጃቢዎቹ በሶምሶማ ግራና ቀኝ ሆነው ይሮጣሉ።አሯሯጣቸው ደግሞ ዜማ አለው። አይዛነፍም።-እነዚህ የኪም ብቻ የሆኑት መርሰዲስ ኤስ ተሽከርካሪዎች ቅንጡ መጸዳጃ ቤቶች የተገጠሙላቸው ናቸው።-ኪም ዛሬ ወይም ነገ 20 ሰዓታትን ከፈጀ የባቡር ጉዞ በኋላ ፑቲንን አግኝቶ በጦር መሣሪያ ዙርያ ያወጋል።-ምዕራቡ ዓለም የፑቲንን የኪምን ግንኙነት ትንፋሹን ውጡ እየተከታተለ ነው።-ሩሲያ ኪም ለሚያርብላት የጦር መሣሪያ ከገንዘብ ባሻገር የኑክሊየር እውቀት ሽግግር ለማድረግ እንዳትስማማ ነው ፍርሃቱ።
የፎቶው ባለመብት DOREEN MORAA MORACHA-የፀረ ኤችአይቪ ሕክምና መድኃኒቶች የበሽታውን መስፋፋት በመግታት በኩል ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አላቸው-አዲስ የወጣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት እንደሚለው መሠረታዊ የጤና ፕሮግራሞችን በገንዘብ መደገፍ ከተቻለ ኤድስን በአውሮፓውያኑ 2030 ከዓለም ማጥፋት ይቻላል።-በዓለማችን ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ከሚገኝ ጠቅላላ ሕዝብ 65 በመቶ የሚሆኑት ባሉባቸው ከሰሃራ በታች አገራት እንኳ ይህንን ዕቅድ የማሳካት ዕድላቸው ሰፊ ነው ብሏል።-እንደ የተባበሩት መንግሥታት የኤችአይቪ/ኤድስ የተቀናጀ ዓለም አቀፍ እርምጃ (ዩኤንኤድስ) ከሆነ ቦትሰዋና፣ ኢስዋቲኒ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ዚምባብዌ 95-95-95 ተብሎ የሚጠራውን ዕቅድ ማሳካት ችለዋል።-95-95-95 ማለት ቫይረሱ ካለባቸው አጠቃላይ ሰዎች ውስጥ 95 በመቶ ስላሉበት የበሽታው ደረጃ ያውቃሉ፣ ቫይረሱ በደማቸው መኖሩን ከሚያውቁት መካከል 95 በመቶው የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት እየወሰዱ ነው፣ ሕክምናውን እየወሰዱ ካሉት መካከል ቫይረሱን ወደ ሌሎች በማያስተላልፉበት ደረጃ የሚገኙት 95 በመቶ ደርሰዋል ማለት ነው።-ከላይ ከተጠቀሱት አምስት የአፍሪካ አገራት በተጨማሪ ሌሎች ተጨማሪ 16 አገራት፤ ስምንቱ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገራት ናቸው፤ እንዲሁ ይህን 95-95-95 የተባለውን ዕቅድ ለማሳካት ተቃርበዋል።-የዩኤንኤድስ ዋና ዳይሬክተር ዊኒ ብያኚማ፣ ኤድስን ማስቆም አሁን ላይ ያሉ መሪዎች ሊታወሱ የሚችሉበት ትልቅ ቅርስ ይሆናቸዋል ይላሉ።-“የሚሊዮኖችን ሕይወት ከመታደጋቸውም በተጨማሪ የበርካቶችን ጤና ይጠብቃሉ። አመራርነት ምን ማለት እንደሆነ ማሳየትም ይችላሉ።”-ይሁን እንጂ ተመድ እያደጉ ባሉ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ለሚያደርገው የፀረ ኤድስ እንቅስቃሴው እስከ 2025 ድረስ ለሚያከናውናቸው ሥራዎቹ የ8.5 ቢሊዮን ዶላር እጥረት አለበት።-እአአ 2022 ላይ በየደቂቃው በኤድስ ምክንያት አንድ ሰው እየሞተ ሳለ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚደረገው ጥረት እንደሚፈለገው ውጤታማ ላይሆን ይችላል።-“በዚህ ሪፖርቶች የተገለጹት እውነታዎች እና አሃዞች እንደ ዓለም በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን ማለት አይደለም፤ ግን አሃዞቹ የሚያሳዩት ትክክለኛው መንገድ ላይ [ኤድስን ለማጥፋት] መሆን እንችላለን የሚለውን ነው” ይላሉ የዩኤንኤድስ ዋና ዳይሬክተር ዊኒ ብያኚማ።-የመንግሥታቱ ድርጅት የኤድስ ስርጭትን በጥቂት ዓመታት ውስጥ መቆጣጠር ይቻላል ቢልም፣ አሁንም ግን ከቫይረሱ ሥርጭት ጋር በተያያዘ በርካታ ፈታኝ ጉዳዮች መኖራቸውን ይገልጻል።-በየሳምንቱ በጉርምስ እና ዕድሜ ውስጥ (ከ10 እስከ 19) እና በወጣትን ዕድሜ ውስጥ ያሉ 4 ሺህ ሴቶች በኤችአይቪ ይያዛሉ።-ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት ምንም እንኳ አዎንታዊ ለውጦች ይመዝገቡ እንጂ፣ እአአ 2022 ላይ በመላው ዓለም በቫይረሱ ከተያዙ አጠቃላይ ሰዎች መካከል 63 በመቶ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የሚገኙ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ናቸው።-በደቡባዊ አፍሪካ በምትገኘው ቦትስዋና ለምሳሌ በዕድሜ የገፉ ወንዶች፣ ተጋላጭ የሆኑ ወጣት ሴቶችን ለቫይረሱ ያጋልጣሉ።-በአሁኑ ወቅት የ32 ዓመት ወጣት የሆነችው ጋኦኔ ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለች ነበር ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆነችው።-“አንድ በጣም የቅርብ ዘመዴ ብዙ ይረዳኝ ነበር። በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ነበር። በዚያን ጊዜ በዕድሜ በእጥፍ ይበልጠኝ ነበር። አምነው ነበር። ልጅነቴን መጠቀሚያ አድርጎ ከእኔ ጋር ወሲብ ይፈጽም ነበር” ትላለች።-የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ጋኦኔ ከእአአ 2012 ጀምሮ የፀረ ኤችአይቪ ሕክምና ስትወስድ ቆይታለች። ሁለቱ ልጆቿ ከኤችአይቪ ነጻ ሲሆኑ ፣ እሷም በፀረ ኤችአይቪ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊ ነች።-እርሷ እንደምትለው አሁን ድረስ የምትኖርበት ማኅብረሰብ ስለ ‘መደፈር’ እና ‘ጾታዊ ጥቃቶች’ በግልጽ ለማውራት ዝግጁ አይደለም።-“አንዳንድ ጊዜ እስከ አምስት የሆኑ ሴቶች ዘመዶቻቸው የሆኑ እና በዕድሜ የሚበልጧቸው ሰዎች ኤችአይቪ እንዳስያዟቸው መልዕክት ይልኩልኛል። ወንዶቹ ከዚህ ተግባራቸው ካልተቆጠቡ ምን ማድረግ ይቻላል” ስትል ትጠይቃለች።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-አሃዞች እንደሚያሳዩት ቫይረሱ ካለባቸው ሴቶች በላይ ወንዶቹ የሕክምና ድጋፍ ለማግኘት ብዙ ያንገራግራሉ።-ቦትስዋና ይህንን የወንዶችን አመለካከት ለመቀየር እና የኤችአይቪ ሥርጭትን ለመቀነስ ፊቷን ወደ ሃይማኖት መሪዎች አዙራለች።-“በቦትስዋና 95 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ኤችአይቪ ይኑርበት ወይም አይኑርበት ያውቃል። ኤችአይቪ ያልተመረመሩት አብዛኛው ወንዶች ናቸው” ይላሉ የሃይማኖት መሪው ቄስ ማቻክግ ሞሩክጎሞ።-ሰዎች የሃይማኖት መሪዎችን ስለሚያከብሩ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ወንዶች ምርመራ እንዲያደርጉ እና ቫይረሱ ካለባቸው የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ጥረት እያደረጉ መሆኑን የሃይማኖት መሪው ይናገራሉ።-የክርስትና ሃይማኖት መሪው ቄስ የእስልምና፣ የሂንዱ፣ የበሃኢ እንዲሁም የባህል ሃኪሞችን ያካተተ ቡድን በዚህ ጥረት ተሳታፊ መሆኑን ይገልጻሉ።-የቦትስዋና ብሔራዊ የኤድስ እና ጤና ተቋም ኃላፊ ኦንቲሬትስ ሌትለሃሬ አገራቸው ኤድስን በ2030 (እአአ) ለማጥፋት ትክክለኛው መንገድ ላይ ነች ካሉ በኋላ፣ የሃይማኖት መሪዎችም ለዚህ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ይላሉ።-እንደ ኃላፊው ከሆነ መሠረታዊ የሆነው ቁልፍ ጉዳይ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ላይ መገለል እንዳይደርስ እና ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች የሕክምና አገልግሎት ከማግኘት እራሳቸውን እንዳይቆጥቡ ማድረግ ነው።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-ከዚህ ቀደም በየትም ቦታ ያልተሞከረው የኤችአይቪ ክትባት በኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ደቡብ አፍሪካ እየተከናወነ ይገኛል።-በቀጣይ ዓመታት ኤችአይቪን ለማጥፋት በተያዘው ዕቅድ በእስያ እና ፓስፊክ አገራት የመሳካቱ ዕድል ከተቀረው ዓለም ጋር ሲነጻጸር አናሳ ነው።-በምሥራቅ አውሮፓ፣ በመካከለኛው እስያ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሰሜን አፍሪካ አሁንም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።-የተባበሩት መንግሥታት በእነዚህ አካባቢዎች የቫይረሱ ስርጭት እንዳይቀንስ ምክንያት የሆኑት ሁለት ዋነኛ ነገሮች ናቸው።-እነዚህም የተገፉ የሕብረሰብ ክፍሎች የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኙ እና እንዲገለሉ መደረጋቸው እንዲሁም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በሕግ ወንጀል ሆኖ መደንገጉ ነው።-ይሁን እንጂ ሰዎችን በኤችአይቪ የመያዝ ዕድላቸውን የሚቀንሱ እና ቀድመው የሚወሰዱ ፕሪ-ኤክስፖዘር፣ ፕሮፊላክሲስ (ፕሬፕ) የተባሉ እንክብል መድሃኒቶች ለሰዎች ተስፋን እየሰጡ ነው።-በምሥራቅ እስያዋ አገር ካምቦዲያ ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ በወሲብ ንግድ ላይ ለተሰማሩ እና ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች እነዚህ እንክብሎች በነጻ ይታደላሉ።-እነዚህ የመከላከያ እንክብሎችን ቫይረሱ የሌለባቸው ሰዎች በየዕለቱ የሚወስዷቸው ከሆነ በቫይረሱ የመያዝ ዕድላቸውን ይቀንሳሉ።-“ይህን መድኃኒት ለሦስት ተከታታይ ወር ወስጃለሁ። በመጀመሪያዎች ቀናት ራስ ምታት ነበረብኝ፣ ከዚያ በኋላ ግን ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት አላጋጠመኝም። በቀን አንድ ክኒን እወስዳለሁ” ትላለች ጾታዋን ከወንድ ወደ ሴት የቀየረችው የ32 ዓመቷ ኩይ ፖቭ።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-“ፕሬፕ የምወስደው ከብዙ ሰዎች ጋር ወሲብ ስለምፈጽም ነው። ለቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ እንደሆንኩ አውቃለሁ” የምትለው ኩይ፣ የወሲብ አጋሮቿ ሁልጊዜ ኮንዶም እንዲጠቀሙ ብትጠይቅም ሁሉም ፍቃደኛ ላይሆኑ እንደሚችሉ ታስረዳለች።-ካምቦዲያ ቫይረሱ በደማቸው ያለ በግምት 76ሺህ ሕዝብ ይኖርባታል። ከአጠቃላይ ሕዝቧ 86 በመቶው ቫይረሱ በደማቸው ይኑር ወይም አይኑር በምርመራ አውቀዋል።-እአአ 1996 ከነበረው አሃዝ ጋር ሲነጻጸር በካምቦዲያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ91 በመቶ ቀንሷል። አሁን ላይ በቀን 4 ሰዎች ብቻ በቫይረሱ እንደሚያዙ መረጃዎች ያሳያሉ። ይህም ለካምቦዲያ ትልቅ ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።-“ከዚህ በፊት ሰዎች ኮንዶም እንዲጠቀሙ ነበር የሚበረታቱት፣ ነገር ግን ለመጠቀም ፍቃደኛ ያልሆኑ አሉ። ስለዚህ ፕሬፕ መድኃኒቶች በሕብረተሰቡ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ሌላኛው አማራጭ ሆኗል” ይላሉ መንግሥታዊ ድርጅት ላልሆነ ተቋም የሚሰሩት የጤና ባለሙያው ዳኖኡ ቻይ።-እነዚህ እንክብሎች አበረታች የሆነ ውጤት እያመጡ መሆኑን የሚገልጹት የጤና ባለሙያው፣ በመርፌ መልክም ሌላ አማራጭ ይዞ የመቅረብ ዕቅድ እንዳለ ይናገራሉ።-ይህ አዲሱ አማራጭ ለኩይ እራሷን እንድትጠብቅ ዕድል ሰጥቷል።-በቅርቡ ባደረገችው የኤችአይቪ ምርመራ ቫይረሱ እንደሌለባት ማወቋም እረፍ ሆኗታል።
የፎቶው ባለመብት PA Media-ወሲባዊ ይዘት ላላቸው ፎቶዎች ለታዳጊ ከፍለዋል በሚል በታገዱት የቢቢሲ ጋዜጠኛ ዙሪያ የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር ጥያቄ ሊቀርብላቸው እንደሚችል ተጠቆመ።-ዋና ዳይሬክተሩ ቲም ዴቪ ዛሬ ሐምሌ 4፣ 2015 ዓ.ም የቢቢሲ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘዋል።-ዋና ዳይሬክተሩ ከጋዜጠኞች ጋር በሚኖራቸውም ቆይታ አብዛኛዎቹ ጥያቄዎች ከሰሞኑ መወዛገቢያ የሆነው የቢቢሲ አቅራቢ ቅሌት ዙሪያ ሊሆን እንደሚችልም ተገምቷል።-ቢቢሲ የግል የመረጃ መብታቸው ጋር ይጣረሳል በሚል የአቅራቢውን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥቧል።-ጉዳዩ እስኪጣራም ድረስ የታገዱት ጋዜጠኛ ማንነት በዚህ መግለጫ ወቅት ዋነኛ ጥያቄም ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።-የቢቢሲ የቴሌቪዥን መርሃ ግብር አቅራቢ አንድ ታዳጊ ወሲባዊ ይዘት ያለው ፎቶግራፍ እንዲልኩ መክፈላቸውን በመጀመሪያ የዘገበው ዘ ሰን ጋዜጣ ነው።-ማንነታቸው እንዲሁም ፆታቸው ያልተገለጸው ጋዜጠኛ ማንነታቸው እንዲሁም ፆታቸው ያልተገለጸ ታዳጊን ከ17 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ልቅ ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ፎቶዎች እንዲልኩ በአስር ሺህ ፓውንዶች የሚቆጠር ገንዘብ መክፈላቸውን የጋዜጣው ሪፖርት ይጠቁማል።-የታዳጊው እናት ለጋዜጣው እንደተናገሩት፣ ልጃቸው ከ17 እስከ 20 ዓመት በዚህ ሂደት አልፈው፣ ከጋዜጠኛው የተከፈለን ገንዘብ ኮኬይን መግዣ ሆኗል።-ታዳጊውን እወክላለሁ ያሉ ጠበቃ በበኩላቸው ዘ ሰን ላይ የወጣውን ዘገባ በማጣጣል የወላጆቻቸውን ቅሬታ “እርባና ቢስ” ብለውታል።-ዘ ሰን ባለፈው ሳምንት ይህንን ጽሑፍ ከማተሙ በፊት በእናታቸው ስለቀረበው ክስ ታዳጊው ሐሰት ነው በማለት ምላሽ መስጠታቸውንም እኚሁ ጠበቃ ተናግረዋል።-ዘ ሰን በበኩሉ የእናትየውን ቅሬታ የሚደግፉ ማስረጃዎችን አግኝቻለሁ ብሏል።-ጠበቃው በበኩላቸው ታዳጊው ለጋዜጣው ቅሬታው ምንም ዐይነት እውነት እንደሌለው ጠቅሰው መልዕክታቸውን ቢልኩም ጋዜጣው ይህንኑ “ያልተገባ ጽሑፍ” በማተም ገፍተውበታል ብለዋል።-በተጨማሪም እናትየውና ታዳጊው ጸብ ላይ እንደሆኑና ምንም ዓይነት ንግግር የላቸውም ሲሉም ጠቅሰዋል።-“የቢቢሲ ጋዜጠኛ ባህርይና የልጃቸው ደህንነት ጉዳይ ስላሳሰባቸው ሁለት ወላጆች ታሪክ ዘግበናል” በማለት ዘ ሰን ምላሽ ሰጥቷል።-“ቅሬታቸውን ለቢቢሲ ቢያቀርቡም ችላ ተብለዋል። ስጋቶቻቸውን የሚደግፉ ማስረጃዎች አይተናል። ማጣራትና መመርመር የቢቢሲ ሥራ ነው” ሲል ዘ ዘሰን አክሏል።-ዘ ሰን እንደዘገበው የታዳጊ ቤተሰቦች ለቢቢሲ ቅሬታቸውን ግንቦት ላይ አስገብተዋል።-ተቋሙ ጉዳዩ “በፍጥነት እንደሚመረመር” መግለጹም ተዘግቧል።-የቢቢሲ ቃል አቀባይ “ማንኛውንም ክስ በቁም ነገር ነው የምንወስደው። ይህንን የሚመለከት አሠራርም አለን” ሲሉ ተናግረዋል።
የፎቶው ባለመብት AFP-ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ አጥብቃ ከመቃወሟ በተጨማሪ በአገሪቱ ፍልስጤማውያንን የሚደግፉ በርካታ ሰልፎች ተካሂደዋል-እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄድ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ላይ ጠንካራ ተቃውሞዋን እያሰማች ባለችው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አምባሳደሯን መጥራቷን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።-እስራኤል የየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አምባሳደሩ የተጠሩት “ለምክክር ነው” ብሏል።-የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ሊዮር ሃይታ በኤክስ ገጻቸው ላይ አምባሳደሩ ወደ ቴል አቪቭ የሚመለሱት “የደቡብ አፍሪካን የቅርብ ጊዜ መግለጫ ተከትሎ ነው” በማለት ዝርዝር ሳይሰጡ አስተያየታቸውን አስፍረዋል።-ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ እያከናወነች ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ አጥበቀው ከሚተቹ ቀዳሚ አገራት መካከል አንዷ ነች።-ደቡብ አፍሪካ ትናንት ሰኞ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣ መጠየቋ ይታወቃል።-ከሁምቡዝዶ ናትሻቨሄኒ የተባሉ የደቡብ አፍሪካ ሚኒስትር ፍርድ ቤቱ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ኔታኒያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ የማይቆረጥ ከሆነ “ዓለም አቀፋዊ የአስተዳደር ውድቀት መኖሩን ያመላክታል” ብለዋል።-የእስራኤል አምባሳደር ኤሊአቭ ቤሎትሴርኮቫስኪ ወደ ቴል አቪቭ የመጠራቻቸው ዜና የተሰማው ደቡብ አፍሪካ ቻይና፣ ሩሲያ እና ኢትዮጵያን ጨምር በአባልነት የያዘው የብሪክስ አገራት በእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ዙሪያ ስብሰባ ለማስናዳት በዝግጅት ላይ እያለች ነው።-የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የሚመሩት ስብሰባ ውጤት አባል አገራት በእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ ያለመ ነው።-ከዚህ በተጨማሪም የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ዛሬ ማክሰኞ በሚኖረው ስብሰባ እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ እስክትስማማ ድረስ የእስራኤል ኤምባሲን ስለመዝጋት እና ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በማቋረጥ ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።-እስራኤል መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በሐማስ የተፈጸመባትን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ በጋዛ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯ ይታወሳል።-በዚህ ሁለት ወር ሊደፍነው እየተቃረበው ጦርነት በእስራኤል በኩል 1200 ሰዎች ተገድለው 240 ሰዎች የታገቱ ሲሆን፣ በጋዛ ደግሞ በሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚንስቴር በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ13ሺህ በላይ መሆኑን አስታውቋል።-የተባበሩት መንግሥታት እና ተቋማቱ ጋዛ ውስጥ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ እንዲቻላቸው ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ ፋታ እንዲደረግ ሲወተውቱ ቆይተዋል።-ለፍልስጤማውያን ያላትን ድጋፍ ጠንከር ባሉ አቋማ ስታንጸባርቅ የቆየችው ደቡብ አፍሪካ የእስራኤልን የጋዛ ዘመቻ “የጅምላ ቅጣት” ስትል ትተቻለች።-እስራኤል በበኩሏ ይህን ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደች ያለችው እራሷን የመከላከል መብቷን በመጠቀም መሆኑን እና የዘመቻው ዓላማም ሐማስን በመደምሰስ ተመሳሳይ ጥቃት በእስራኤል ምድር ዳግም እንዳይፈጸም ነው ትላለች።-ከጥቂት ቀናት በፊት ደቡብ አፍሪካ፣ ባንግላዴሽ፣ ቦሊቪያ፣ ኮሞሮስ እና ጂቡቲ እስራኤል ጋዛ ውስጥ የምትፈጽመውን እርምጃ የጦር ወንጀለ እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ስለመሆኑ ምርመራ እንዲደረግበት ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ወስደውታል።-በተጨማሪም ደቡብ አፍሪካ ዲፕሎማቶቿን ከእስራኤል የጠራች ሲሆን፣ ደቡብ አፍሪካዊቷ አገር በእስራኤል ለአምስት ዓመታት ያክል አምባሳደር ኖሯት አያውቅም።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-አንቶኒ ብሊንከን-ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጠብ ከሚያጭሩ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ጥሪ አቀረቡ።-ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት ሲካሄድ የነበረውን የእርስ በርስ ጦርነት ያስቆመው ስምምነት አንደኛ ዓመትን በማስመልከት ባወጡት መግለጫ ላይ ሁለቱ አገራት “ጠብ ከሚያጭሩ ድርጊቶች በመቆጠብ የአካባቢውን አገራት ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማክበር አለባቸው” ብለዋል።-የውጭ ጉዳይ ኃላፊው ይህንን ያሉት ፕሪቶሪያ ላይ የተፈረመው ግጭትን በዘላቂነት የማስወገድ ስምምነት ጉልህ እርምጃዎች መወሰዳቸው ካመለከቱ በኋላ በተጨማሪ ሊወሰዱ ይገባሉ ካሏቸው ተግባራት መካከል የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ሙሉ ለሙሉ መውጣትን ጠቅሰዋል።-በሁለቱ ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን ተሰልፋ የትግራይ ኃይሎችን ስትወጋ የነበረችው ኤርትራ ሠራዊት አሁን ድረስ በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል።-ባለፉት ጥቂት ወራት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ያላትን የባሕር በር የማግኘት ፍላጎቷን ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ጥያቄ ሲነሳ መቆየቱ ይታወሳል።-የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም እንዲሁ በደፈናው አገራቱ የሁሉንም የአካባቢውን አገራት ሉዓላዊነት በማክበር ከግጭት እንዲቆጠቡ መጠየቃቸው፣ የኤርትራ ኃይሎች በትግራይ ውስጥ መቆየት እና ከኢትዮጵያ በኩል የባሕር በር ጥያቄ መነሳቱን ለማመልከት ሊሆን ይችላል።-ከዚህ ጋር በተያያዘ ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ አበባ ውስጥ ባደረጉት ንግግር የባሕር በርን በተመለከተ “ኢትዮጵያ ውይይት ያስፈልጋታል ስትል ወራራ ሊካሄድ ይችላል የሚል ስጋት ይደመጣል” በማለት፣ አገራቸው “በኃይል እና በወረራ ማሳካት የምትፈልገው አንዳች ነገር የለም” ማለታቸው ይታወሳል።-በአፍሪካ ኅብረት፣ በአሜሪካ እና በኢጋድ አማካይነት በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር መመሥረቱን ጨምሮ የተወሰዱ ጉልህ እርምጃዎችን አሜሪካ እንደምትደግፍ ብሊንከን ባወጡት መግለጫ ላይ አመልክተዋል።-ጨምረውም “ህወሓት ኃይሎቹ ከባድ መሳሪያቸውን ፈትተው ተዋጊዎቻቸውን ማሰናበት በተጀመረበት ጊዜ በትግራይ ውስጥ ዘላቂ ሰላም ለማስፍን ተጨማሪ እርምጃዎች መውሰድ ያስፈልጋል” በማለት ለዚህም የኤርትራ ኃይሎች ሙሉ ለሙሉ መውጣት አለባቸው ብለዋል።-ከዚህ ባሻገርም “በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉት ግጭቶች ያሳስቡናል” ያሉት አንቶኒ ብሊንከን፣ ይህም በቀላሉ ሊታወክ የሚችለውን የኢትዮጵያን ሰላም አደጋ ላይ እንደጣለው አመልክተዋል።-እንዲሁም በአገሪቱ በተለያዩ ወገኖች የቀጠለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና ጥቃት፣ “የመርዛማ ንግግሮች” መስፋፋ በጦርነቱ ምክንያት የሳሳውን ማኅበራዊ ትስስር የበለጠ እየሸረሸረው ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።-ለዚህም አስተማማኝ የሽግግር ፍትሕ፣ ሐቀኛ እና አካታች ብሔራዊ ምክክር በመላዋ አገሪቱ ተግባራዊ እንዲሆን እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚካሄዱትን ግጭቶች ለመፍታት ውይይት እንዲደረግ በአስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።-በተያያዘ ዜና ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዋች በበኩሉ የሰላም ስምምነቱ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ቢያስቆምም በአገሪቱ ግን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደቀጠሉ ናቸው ብሏል።-ቡድኑ የፕሪቶሪያው ስምምነት የተፈረመበትን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ከፕሪቶሪያው ስምምነት አንድ ዓመት በኋላ ግጭት እና ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሰሜን ኢትዮጵያ እንደቀጠለ ነው ብሏል።-የኤርትራ እና አማራ ኃይሎች በትግራይ ክልል አሁንም የመብት ጥሰቶችን እየፈጸሙ ነው ያለው ሂዩማን ራይትስ ዋች፤ በአማራ ክልልም እንዲሁ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች መካከል በሚደረገው ውጊያ ምክንያት የመብት ጥሰቶች እየተመዘገቡ ነው ብሏል።-ህወሓት እና የፌደራል መንግሥት የተፈራረሙት የሰላም ስምምነት ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ፣ መሠረታዊ አግልግሎቶችን ለማስጀመር፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መስጠት እና ተፈናቃዮች ወደ ቀደመ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚያስችሉ አሰራሮችን ቢዘረጋም፤ ስምምነቱ ግን በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ ወንጀሎች የሚመረመሩበት እና አጥፊዎች የሚጠየቁበትን ሁኔታ በዝርዝር አለመያዙ ፍትሕን ከማስፈን አንጻር ትልቅ ከፍተት ፈጥሯል ብሏል።-ለሁለት ዓመታት ሲካሄድ ቆይቶ የዛሬ ዓመት ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም. ደቡብ አፍሪካ ላይ በተደረሰው ስምምነት የተቋጨው ጦርነት ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ እንደነበር ይታወሳል።-በዚህ ጦርነት ከ600 ሺህ አስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች መሞታቸውን የሚያመለክቱ አሃዞች ከተለያዩ ወገኖች ሲወጡ ቆይተዋል። በተጨማሪም ከፍተኛ የንብረት እና የመሠረተ ልማት ውድመቶች አስከትሎ ነው ጦርነቱ የተቋጨው።
የፎቶው ባለመብት Reuters-ከፍርስራሾች መካከል ዳቦ የምትጋግር ፍልስጤማዊት-ጋዛ ላይ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ ያለው የእስራኤል ጦር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፊቱን ወደ ደቡብ ጋዛ በማዞር ኻን ዩኒስ የተሰኘችውን ከተማ ዒላማ ማድረግ ጀምሯል።-2.3 ሚሊዮን ፍልስጤማዊያን ሰሜናዊ ጋዛ ጥቃት ሲደርስበት ወደ ደቡባ አቅጣጫ ነው ያመሩት። መዳረሻቸው ደግሞ ኻን ዩኒስ።-ከተማዋ በአዲስ መጥ ተፈናቃዮች ተጨናንቃለች። ምግብ፣ ውሃ እና መጠለያ ማግኘት ከባድ ሆኗል።-ከሰርጡ ቢያንስ 1.9 ሚሊዮን ያክል ሰዎች እንደተፈናቀሉ መረጃዎች ይገልጣሉ።-በእስራኤል እርምጃ ምክንያት አንድ ተፈናቃይ ወዳጅ ቤተሰቡን ይዞ እንደተሰደደ ለቢቢሲ ይናገራል።-“የእስራኤል ባለሥልጣናት በሄሊኮፕተር የማስጠንቀቂያ ወረቀት ሲበትኑልን ነበር። ሲበትኑ የነበሩት ኻን ዩኒስ ላይ ነበር። ወደ ደቡባዊው የጋዛ ሰርጥ ክፍል እንድንሄድ ነው የሚሹት። ከሰሜን ተፈናቅለን ወደ ደቡብ መጥተናል። የት እንድንሄድ ነው የሚፈልጉት? እንዲህ ሆነን የት እንሂድላቸው? ከሰሜን ስንፈናቀል ይዘነው የወጣነው ገንዘብ አልቋል። ከዚህ በኋላ የትም ልንሄድን አንችልም።”-ኻን ዩኒስ ወደ ግብፅ ከሚያሻግረው ራፋህ 9.5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። ደቡባዊ ጋዛ ከሚገኙ ከተሞች መካከልም ግዙፏ ናት። ከጦርነቱ በፊት የሕዝብ ቁጥሯ 400 ሺህ ነበር።-የሥፍራዋ ደማቅ የንግድ ከተማ ናት። ወደ ግብፅ የሚወስደው ጥንታዊ የንግድ መስመር መዳረሻም ሆና አገልግላለች።-በከተማዋ ምዕራባዊ አቅጣጫ የስደተኞች መጠለያ ይገኛል። የከተማዋን ስም ይዟል። ይህ መጠለያ ከሜዲትራኒያን ባሕር ዳርቻ እና ከራፋህ 2 ኪሎ ሜትር ብቻ ርቆ የተተከለ ነው።-እስራኤል በአውሮፓውያኑ 1948 በተቋቋመችበት ጊዜ ነው በርካታ ፍልስጤማዊያን ተፈናቅለው መጥተው እዚህ መጠለያ ሥፍራ ሕይወት የመሠረቱት።-የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤማዊያ ስደተኞች ድርጅት በዚህ መጠለያ ጣቢያ 90 ሺህ ተፈናቃዮች ተመዝግበው ይኖራሉ ይላል።-የትምህርት ሚኒስቴር አንደሚለው ደግሞ በኻን ዩኒስ ከተማ 60 ትምህርት ቤቶች እና 100 መዋዕለ ሕፃናት አሉ።-ከተማዋ ስድስት ገደማ ሆስፒታሎች አሏት። ዶክተሮች እንደሚሉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተጎድተው ሕክምና በማግኘት ላይ ይገኛሉ።-የዓለም ጤና ድርጅት፤ በደቡባዊ ጋዛ በተለይ ደግሞ በኻን ዩኒስ ከተማ የሚደረግ የምድር ጦር ዘመቻ ማለት በርካታ ሰዎች የጤና እርዳታ አያገኙም ማለት ነው ይላል።-ድርጅቱ በተለይ ደግሞ የናስር ሕክምና ማዕከል ጋዛ እና ዩሮፒያን ተሰኙት ዋና ሆስፒታሎች በሕክምና እርዳታ ፈላጊዎች ሊጨናነቁ እንደሚችሉ ይገምታል።-በቅርቡ የናስር ሜዳካል ኮምፕሌክስን የጎበኙት የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች በሆስፒታሉ ያለው ሁኔታ “አሳሳቢ ነው” ብለዋል።-የሆስፒታሉ ክፍሎች በበርካታ ሕክምና ፈላጊዎች ተጨናንቀዋል፤ ሌሎች ደግሞ መጠለያ በማጣታቸው ሆስፒታል ውስጥ አርፈዋል።-የድርጅቱ ቡድን እንደገለጠው ታካሚዎች ሆስፒታሉን ከመሙላታቸው ባለፈ የጤና ሠራተኞች ከአቅማቸው በላይ እየሠሩ ይገኛሉ።-የዓለም ጤና ድርጅት አባላት አክለው እንደሚሉት በአሁኑ ወቅት ከ1000 በላይ ታካሚዎች በሆስፒታሉ ሲገኙ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ማዕከሉን እንደመጠለያ እየተጠቀሙበት ነው።-ሆስፒታሉ 350 አልጋዎች ነው ያሉት። ጋዛ ዩሮፒያን ሆስፒታልም እንዲሁ 370 አልጋዎች ቢኖሩትም 1000 ሰዎች ሕክምና ያሻቸዋል፤ 70 ሺህ ገደማ ደግሞ ተጠልለውበታል።-ሁለቱ ሆስፒታሎች ከአቅማቸው ሦስት እጥፍ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ነው እያስተናገዱ የሚገኙት።-በአንድ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ ጥቃት የተጎዱ ሕጻናት በናስር ሆስፒታል ውስጥ-በከተማዋ ያሉ ነዋሪዎች ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ እንዲህ ያለ የአየር ጥቃት አጋጥሞን አያውቅም ይላሉ።-የእስራኤል ባለሥልጣናት በከተማዋ በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ የሚያስጠነቅቁ ወረቀቶችን በትነዋል።-በከተማዋ መሐል እና በሌሎችም አካባቢዎች የተበተኑ ወረቀቶች እንደሚጠቀሙት እስራኤል በቅርቡ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ በኻን ዩኒስ ላይ ለማካሄድ አቅዳለች።-በሥፍራው በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት የተቋቋመው የቢቢሲው ጋዛ ቱደይ ሬዲዮ ያናገረው አንድ ግለሰብ “ዛሬ ጠዋት ስንነሳ የእስራኤል ጦር በዙሪያችን ከባድ ዘመቻ መጀመሩን ስንሰማ ደንግጠናል” ይላል።-“እየወረደ ያለው ቦምብ ኃይለኛ መሆኑን ስንሰማ በጣም ደንግጠናል። ሕፃናት ፈርተዋል። ሴቶች እና የተጎዱ ሰዎች ደግሞ ተዳክመዋል። በድምፅ ማጉያ ወደ ደቡባዊ አቅጣጫ ሄደን እንድንሸሸግ ማስጠንቀቂያ ተነግሮናል። ሰላም ናቸው ወደተባሉት ሥፍራዎች ለመድረስ እጅግ አዳጋች ነው። ወደዚያ መጓዝ ለማይችሉ ሰዎች ትራንስፖርት የለም።”-አንድ ሕፃን “ይበቃል ማለት ይበቃል ነው። ያየነው ነገር ይበቃል። በጣም ፈርተናል። ከሆስፒታሉ አጠገብ ያለን አንድ ቤት አፈንድተውታል። በጣም ብዙ የተጎዱ ሰዎች አሉ” ሲል ለሬዲዮው ተናግሯል።-አንዲት ሴት ደግሞ ቀይ መስቀል እሷን እና ሌሎች የተጎዱ ሰዎችን ሰሜናዊ ጋዛ ከሚገኘው ኢንዶኔዢያን ሆስፒታል እንዳጓጓዛት ትናገራለች።-“እዚህ የመጣነው ሰላም ይኖራል ብለን ነው። ነገር ግን ከዛሬ ጠዋት [ሰኞ] ጀምሮ ቦምብ መውረዱን አላቆመም። የተጎዱ ሰዎች እጅግ በጣም ፍራቻ ውስጥ ናቸው” ትላለች።-“ቀይ መስቀልን እዚህ ባለንበት እንዲጠብቀን፤ የምንሄድበተ እንደሌለን ነግረናቸዋል። እዚህ ያለንበት ትምህርት ቤት እንኳ ቢተኩሱብን አንቀሳቀስም። በአምቡላንስ አሊያም በባስ አንድ ላይ መንቀሳቀስ ብቻ ነው የምንችለው።”-ኻን ዩኒስ ከሚገኘው ከዩሮፒያን ሆስፒታል አጠገብ የሚገኘው ዋነኛው መጠለያ ቀይ መስቀል እንዲደርስለት ጥሪ እያቀረበ ይገኛል።-“እዚህ መጠለያ የሚገኙ ሁሉ ሰላማዊ ዜጎችና የተጎዱ ናቸው። ሞት አምልጠው ነው እዚህ የመጡት። አንድ ሰው ምግብ እየበላ ሳለ በፍንጣሪ ተመትቷል። ቀይ መስቀል የተጎዱ ሰዎችን እንዲጠብቅ ጥሪ እናቀርባለን።”-ቢሆንም ግን የእስራኤል ጦር እና ሐማስ ተኩስ ለማቆም ስምምነት እስካልደረሱ ድረስ ቀይ መስቀል ይህን ሥፍራ የመጠበቅ አቅም የለውም።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሶማሊላንድ መዲና ሐርጌሳ-ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት እንደ ሀገር የሚያስቆጥራትን እውቅና ለማግኘት ስትባዝን የቆየችው ራስ ገዟ ሶማሊላንድ፤ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ሠነድ የመጀመሪያውን እውቅና እንደሚያስገኝላት ይፋ አድርጋለች።-በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የአዲስ አበባ እና ሐርጌሳ መንግሥታት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ የባሕር በር ሰጥተው በምላሹ ከአዲስ አበባ እውቅና ለመቀበል መስማማታቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ የእውቅናን ጉዳይ በተመለከተ እስካሁን ግልጽ ምላሽ አልሰጠችም።-ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር እና የባሕር ላይ ንግድ አገልግሎት የሚሰጥ የባሕር ጠረፍ በሊዝ ለማግኘት የሚያስችላትን የሊዝ ስምምነት መፈጸሙን የገለጸው የአዲስ አበባው መንግሥት፤ በምላሹ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ እንደሚኖራት አስታውቋል።-ለሶማሊላንድ እውቅና የመስጠት ጉዳይን በተመለከተ ግን በስምምነቱ ላይ የተቀመጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን “በጥልቀት አጢኖ አቋም እንደሚወስድ” መሆኑን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ከትላንት በስቲያ ረቡዕ 24፤ 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት እውቅና የመስጠቱን ጉዳይ በግልጽ ባያሳውቅም ጉዳዩ ሶማሊላንድን እንደ አንድ የግዛቷ አካል በምትቆጥረው ሶማሊያ ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል። ግብጽ እና የአረብ ሊግ ከሶማሊያ ጎን እንደሚቆሙ ባወጧቸው መግለጫዎች አንጸባርቀዋል። የአውሮፓ ኅብረትም የሶማሊያ ሉዐላዊነት እና የግዛት አንድነት እንዲከበር ጠይቋል።-የአፍሪካ ኅብረት እና ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢጋድ ደግሞ በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ አቅርበዋል።-በሰኞ ዕለቱ የመግባቢያ ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ 20 ኪሎ ሜትር የባሕር ጠረፍ ለ50 ዓመታት በሚቆይ ሊዝ እንደምታገኝ ተገልጿል። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሳ ካዪድ የመግባቢያ ስምምነቱ የባሕር በር ጉዳይን ጨምሮ ኢኮኖሚ፣ ደኅንነት፣ ትምህርት፥ ጤና እና ወታደራዊ ትብብሮችን የተመለከቱ ጉዳዮች እንደተካተቱበት ተናግረዋል።-እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጻ የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ ሶማሊላንድ ከአዲስ አበባ እውቅና ከማገኘቷ ጋር ትስስር ያለው ነው። ኢሳ፤ “ይሄ የመግባቢያ ስምምነት ነው። ይህንን ተከትሎ የተለያዩ ስምምነቶች ይመጣሉ። ፕሬዝዳንታችን ሲናገሩ እንደተደመጡት እውቅና ማግኘት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። [እውቅና መስጠት] የባሕር በሩን ማግኘት የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።-ኢትዮጵያ፤ ሶማሊላንድ “ነጻ ሀገር” ስለመሆኗ እውቅና እንደምትሰጥ ማወጅ እንዳለባት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለዋል።-የሶማሊያ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዳውድ አዊስ ግን ሀገራቸው የሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያን ፊርማ የምትመለከተው “የሶማሊ ሕዝብን ፍላጎት እና ፈቃድ የማይወክል ሕገ ወጥ የመግባቢያ ስምምነት” አድርጋ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።-ይህንን አይነቱን ስምምነት የመፈራረም ስልጣን ያለው የሞቃዲሾው የፌደራል መንግሥት መሆኑን አስረግጠው የሚናገሩት ዳውድ፤ “ክልላዊ መንግሥት ዓለማ አቀፋዊ ስምምነት መፈራረሙ የሕግ ጥሰት እና በሶማሊያ ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው” ብለዋል።-“የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክን ሉዓላዊነት፣ ነጻነት እና አንድነት ለመጣስ የሚደረግን የትኛውንም ሙከራ በተመለከተ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥትን አጥብቀን እናስጠነቅቃለን” ሲሉም ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ ተናግረዋል።-ኢትዮጵያ በዚህ “ሕጋዊ ያልሆነ ድርጊት” እንደማትቀጥል ለማረጋገጥ ሲባልም ሶማሊያ መንግሥት “በዓለም አቀፉ መድረክ የሚገኝ ማንኛውንም ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ” መሆኑን አስታውቀዋል።-“ይህ የማይደረግ ከሆነ ግዛታችንን ለመከላከል ዝግጁ ነን። ሁሉም [አማራጭ] ጠረጴዛው ላይ ነው” ያሉት የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ፤ ይሁንና ሶማሊያ ከጎረቤቶቿ ጋር “የትኛውም አይነት ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ለመግባት” ዝግጁ እንዳልሆነች ገልጸዋል። የሶማሊያ መንግሥት ጥሪ እያቀረበ ያለው ጉዳዩ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ መሆኑም አክለዋል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሳ ግን ራስ ገዟ “ከቀሪው ሶማሊያ የተነጠለች” መሆኗን በመጥቀስ የሞቃዲሾ እንቅስቃሴ “ምንም አይነት ተጽእኖ እንደማይኖረው” ተናግረዋል።-“[ሶማሊያ] በእኛ አቋም ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል ምንም አይነት ሕጋዊም ሆነ ሌላ መሠረት የላትም። የሀገሪቱ ጠቅላይ፣ የውጭ ጉዳይ ወይም የሀገር ውስጥ ሚኒስትሮች የሚናገሩት ማንኛውም ነገር በእኛ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ የለም” ሲሉም የመንግሥታቸውን አቋም አስረድተዋል።-ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና ልትሰጥ ተስማምታለች የሚለው ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማው የመግባቢያ ሠነዱ በተፈረመበት ዕለት በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ነበር።-የሀገሪቱ ካቢኔ ከትላንት በስቲያ ካደረገው ስብሰባ በኋላም ባወጣው መግለጫ ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ “ለሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ሉዐላዊነት በመስጠት የመጀመሪያዋ ሀገር” መሆኗን በመጥቀስ ምስጋውን አቅርቧል።-ሶማሊላንድ ባለፉት 33 ዓመታት እውቅና ለማግኘት ስትጥር እንደነበረ የሚያስታውሱት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሳ፤ የኢትዮጵያ እውቅና መስጠት ሀርጌሳ ስታደርግ የነበረው ጥረት ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እስካሁን ድረስ በነበረው ጥረት ብዙ ሀገራት ለሶማሊላንድ እውቅና በመስጠት የመጀመሪያ ሲያፈገፍጉ እንደነበርም ጠቁመዋል።-የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ “ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ እስካሁን ጥያቄ ስናቀርብላቸው የነበሩ ሁሉም ሀገራት [ለሶማሊላንድ እውቅና በመስጠት] የመጀመሪያ ሀገር እንደማይሆኑ፤ [ነገር ግን] ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ሀገር እንደሚሆኑ ነግረውናል። ስለዚህ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሀገር ናት” ሲሉ ሌሎች ሀገራት ይህንን ፈለግ ሊከተሉ እንደሚችሉ አመልክተዋል።-ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድም ሆነ ለአፍሪካ እና ለተቀረው ዓለም “በጣም ወሳኝ ሀገር” መሆኗን የሚናገሩት ኢሳ፤ “ብዙ ለውጥ ያመጣል። ምክንያቱም [እውቅና ለማግኘት] በአፍሪካ ኅብረት፣ አረብ ሊግ እና የአውሮፓ ኅብረት [በምናደርገው ጥረት] ኢትዮጵያ ከእኛ ጋር ሆና ዘመቻ ታደርጋለች” ብለዋል።-የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካን በመተንተን የሚታወቁት አሌክስ ደ ዋል ግን የኢትዮጵያ እውቅና መስጠት ሌሎች ሀገራትም እንዲከተሉ ማድረጉ ላይ ብዙም እምነት እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠትን በተመለከተ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች “ምናልባት ቀጣይ እርምጃ የምትወስድ ሀገር” ልትሆን እንደምትችል አሌክስ አስረድተዋል። “ነገር ግን ይሄ ሌሎች እንዲከተሉ የሚስችል አሻራ ያስቀምጣል ብሎ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። ይልቁንስ በቀጠናው ላይ ጠላትነትን ሊያፋፍም ይችላል” ሲሉ ጉዳዩ ስጋት የሚጭር መሆኑን ገልጸዋል።-በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ እና በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ዙሪያ ጥናቶችን ያደረጉት አቶ ነገራ ጉደት፤ የመግባቢያ ስምምነቱ ለሶማሊላንድ ትልቅ ጥቅም ይዞ ይመጣል ይላሉ። “ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ሠነድ ከዲፕሎማሲ አንጻር ካየነው እንደ ሀገር እውቅና እንዲያገኙ ያስችላዋለች። ይህ ትልቅ ትርጉም አለው” የሚሉት አቶ ነገራ፤ ኢትዮጵያም ለጂቡቲ ወደብ የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ እንደሚቀንስላት ያስረዳሉ።-ከዚህም ባሻገር ከሶማሊላንድ በሚገኘው 20 ኪሎ ሜትር የባሕር ጠረፍ ላይ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል መገንባት የምትችል መሆኑን በእድልነት ያነሱታል። “አንድ አገር ሙሉ የሆነ ጠንካራ ሠራዊት ገንብቷል የሚባለው በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአየር፣ የምድር እና የባሕር ኃይሎች ሲኖረው ነው” ሲሉም የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር መገንባት ያለውን ጥቅም ይጠቅሳሉ።-ይሁንና አቶ ነገራ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሊላንድ ጋር የደረሰው ስምምነት “ምርቃትም፤ እርግማንም ይዞ ይመጣል” ባይ ናቸው። የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያው ኢትዮጵያ በኤደን ባሕረ ሰላጤ ወይም በቀይ ባሕር ላይ የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር የምትገነባ ከሆነ ሂደቱ በቀጠናው ላሉ አገራት እረፍት የሚነሳ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።-ይህ ስምምነት ተፈጻሚ የሚሆን ከሆነ ጠላት የሆኑት የሶማሊያ መንግሥት እና ጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን አል-ሸባብ አንድ ሆነው ኢትዮጵያ ላይ ብረት ሊያነሱ ይችላሉ ሲሉም ይገምታሉ። አቶ ነገራ እንደሚሉት ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ጋር ያላትን ግንኙነት ሊያበላሽ ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋል።-የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተንታኙ አሌክስ ደ ዋል በበኩሉ ከስምምነቱ ወዲህ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል እየታየ ያለው መካረር “በአጭር ጊዜ” ውስጥ ወደ ወታደራዊ እርምጃ የመቀየር እድሉ ዝቅተኛ መሆኑን ይናገራል።-“የዲፕሎማሲው አካሄድ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ ወይም ኤርትራ ጋር ላላት ግንኙነት ምን አይነት ትርጉም ይሰጣል የሚለው ወደፊት የሚታይ ነው የሚሆነው። ጉዳዩ ብዙ ስጋት እየፈጠረ ያለው እዚህ ላይ ነው” ሲል በአሁኑ ሰዓት በጉዳዩ ላይ በእርግጠኝነት መናገር እንደማይቻል ይጠቁማል።-ይሁንና በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት “እጅጉን ወታደራዊ” እና “ራሱን እያስታጠቀ” መሆኑ እንዲሁም የመንግሥት እንቅስቃሴ “ወጥ ያልሆነ” መሆኑ ስጋት መሆኑን ያነሳል። “ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግሥት ሀገሪቱ ውስጥም ሆነ በድንበር አካባቢዎች የሚገኝ የትኛውንም ጦርነት የሚያጠናክር ከሆነ ስፋት ያለው ቀጠናዊ ጦርነት ሊፈጠር ይችላል” ሲል ስጋቱን ገልጿል።-በሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ ስምምነት ውስጥ የአረብ ኤምሬቶች “አሻራ ይታያል” የሚለው የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተንታኙ አሌክስ ደ ዋል፤ አቡ ዳቢ “በሶማሌ ላንድ እና ወደቧ ላይ በጣም ፍላጎት” እንዳላት ያስረዳል።-“ሳውዲ አረቢያ፣ ኳታር እና ሌሎች ሀገራት የተባበሩት ኤምሬቶች በአፍሪካ ቀንድ፣ ቀይ ባሕር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ የምታደርገው እንቅስቃሴ እየተከታተሉት ያለው በከፍተኛ ስጋት ነው” ሲልም ከዚህ ስምምነት ቀጥሎ በአቡ ዳቢ የሚወሰድ እርምጃ “በቀጠናው ላይ ጠላትነትን ሊያፋፍም” እንደሚችል ይናገራል።-
የፎቶው ባለመብት HRW-ስደተኞች በተጨናነቀ የሳዑዲ እስር ቤት ውስጥ-በሳዑዲ አረቢያ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ናቸው የተባሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ስደተኞች በተጨናነቁ እስር ቤቶች በሰቆቃ ውስጥ እንደሚገኙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።-ዓለም አቀፉ ሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ ያሉበትን ሁኔታ እና እየገጠማቸው ያለውን አሳሳቢ ሁኔታን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ቁጥራቸው ከ30 ሺህ እንደሚልቅ አመልክቷል።-ጨምሮም የሳዑዲ ባለሥልጣናት “በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ኢሰብአዊ እና ጭካኔ በተሞላበት አያያዝ ላልተገደበ ጊዜ በእስር ከቆዩ በኋላ በግድ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ይደረጋል” ብሏል።-ኢትዮጵያውያኑ ለዚህ ስቃይ የሚዳረጉት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ስለሌላቸው ሲሆን፣ ይህም ሁኔታ ሳዑዲ ባላትና “ጨቋኝ” ነው በሚባለው ‘ካፋላ’ የሠራተኞች ቅጥር ሥርዓት ምክንያት የተባባሰ መሆኑን አመልክቷል።-አምነስቲ ኢንትርናሽናል የኢትዮጵያውያኑን ሁኔታ ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ ላይ እንዳለው፣ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች የሚገኙባቸው ስደተኞቹ በዘፈቀደ ተይዘው በእጅጉ የተጨናነቁ ናቸው ባላቸው አል-ኻራጅ እና አል-ሹማይሲ በተባሉ እስር ቤቶች ይገኛሉ።-የመብት ተቆርቋሪ ድርጅቱ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የሰሜን አፍሪካ አካባቢ ኃላፊ የሆኑት ሄባ ሞራዬፍ እንደተናገሩት ባለፉት አምስት ዓመታት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ አረቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ በማለፋቸው “በርካቶች ለከባድ እና ለዘላቂ አካላዊ እና አእምሯዊ ችግሮች ተዳርገዋል።”-“በአሁኑ ወቅትም ከ30000 በላይ ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ ሁኔታ ተይዘው ተመሳሳይ ዕጣ እየተጋፈጡ ነው። አንድ ሰው ሕጋዊ ሰነድ የለውም ማለት ሰብአዊ መብቱ ይገፈፋል ማለት አይደለም” ብለዋል ሄባ።-በኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በተመለከተ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የሳዑዲ ባለሥልጣናት ባለፉት ሁለት ዓመታት በእስር ቤቶች በስደተኞቹ ላይ የተፈጸሙ ማሰቃየቶችን እንዲሁም ቢያንስ 10 ሞቶች ላይ ምርመራ እንዲያካሂዱ ጠይቋል።-ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ የሳዑዲ ባለሥልጣናት የመኖሪያ ሰነድ ሳይኖራቸው በአገሪቱ ውስጥ ይገኛሉ ያሏቸውን ስደተኛ ሠራተኞችን በአሰሳ በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የማድረግ ዘመቻ ሲያካሂዱ ቆይተዋል።-“ሳዑዲ ባላት ካፋላ በተባለው ጨቋኝ ሥርዓት” ሰነድ የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች የሆኑ ሠራተኞች ሕጋዊ እንዲሆኑ የሚያስችል ዕድል አይሰጥም። በተጨማሪም ሕጋዊ ሰነድ ይዘው ስቃይ ከሚፈጽሙባቸው አሰሪዎች ያመለጡ ሠራተኞች ከሆኑም ሕጋዊነታቸውን ያጣሉ።-በሳዑዲ አረቢያ በአሁኑ ወቅት 10 ሚሊዮን የሚገመቱ ስደተኛ ሠራተኞች የሚገኙ መሆናቸውን ያመለከተው አምነስቲ፣ በተለይ ለስቃይ የተጋለጡ ናቸው ባላቸው ኢትዮጵያውያን ላይ ማተኮሩን ገልጿል።-የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ መንግሥታት እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮፓውያን ዓመት ቢያንስ 100 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ዕቅድ መያዛቸውንም መግለጫው አመልክቷል።-በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሻለ ሥራ እና ሕይወት ፍለጋ በአደገኛ መንገድ ከሚሰደዱባቸው የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት መካከል ሳዑዲ አረቢያ አንዷ ስትሆን፣ ስደተኞቹ በመንገዳቸው ላይ ከሚገጥሟቸው አደጋዎች ባሻገር በመድረሻቸውም ከባድ ሰቆቃ ይገጥማቸዋል።-ኢትዮጵያውያኑ በአደጋኛ ባሕር እና በረሃ አቆራርጠው በሕገወጥ መንገድ በሚጓዙበት ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩት ባሕር ውስጥ የመስመጥ፣ በአዘዋዋሪዎች እና ድንበር ጠባቂዎች የመገደልና በረሃብና በውሃ ጥም መንገድ ላይ መሞታቸው ሲዘገብ ቆይቷል።-በሳዑዲ አረቢያ በመቶ ሺዎች ኢትዮጵያውን ስደተኞች የሚገኙ ሲሆን፣ ባለሥልጣናት ሕገ ወጥ ናቸው ባሏቸው ስደተኞች ላይ እርምጃ በሚወስዱበት ኢላማ ከሚሆኑት መካከል አንዱ ናቸው።-በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የሳዑዲ እስር ቤቶች ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ከዚህ ቀደም ቢቢሲ በድምጽና በምስል ያገኛቸው መረጃዎችን መሠረት አድርጎ በተደጋጋሚ መዘገቡ አይዘነጋም።
የፎቶው ባለመብት tigray tv/fb-በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በትግራይ ፖለቲካ ውስጥ ጎልተው ከሚታዩ ፖለቲከኞች አንዱ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉን አስፈጻሚ አካል በማዋቀር የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መሾማቸው ተገልጿል።-በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል ውስጥ በኃላፊነት በቆዩባቸው ዓመታት በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ላይ በመቅረብ ሃሳባቸውን በመግለጽ እና በመከራከር በተደጋጋሚ ከሚታወቁ ጥቂት ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ናቸው።-በአገሪቱ ውስጥ ፖለቲካዊ ለውጥ ከመጣ በኋላ በነበሩት ባለፉት አምስት ዓመታት በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ እና በግንባሩ ዋና መሥራች ህወሓት መካከል የነበረውን አለመግባባት ተከትሎ በተፈጠረው የፖለቲካ ትርምስ ውስጥ ጎልተው ወጥተዋል።-በተለይ ለሁለት ዓመት በዘለቀው ጦርነት ወቅት በትግራይ አመራሮች በኩል የሚነሱ ሃሳቦችን በክልሉ ባሉ መገናኛ ብዙኃን ላይ በመደበኛነት እየቀረቡ፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ላይም በተደጋጋሚ ብቅ እያሉ የህወሓት አንደበት ሆነው ቆይተዋል።-ደም አፋሳሹን ጦርነት ያስቆመው በመንግሥት እና በህወሓት መካከል በተካሄደው ድርድር ወቅት ግንባር ቀደም ተደራዳሪ የነበሩት እና በስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ማን ናቸው?-አቶ ጌታቸው ረዳ አላማጣ ውስጥ ሰኔ 1967 ዓ.ም. ነው የተወለዱት። የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዚያው በትውልድ ከተማቸው የተማሩ ሲሆን ለታናሽ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው አርአያ መሆናቸው ይነገራል።-አቶ ጌታቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ የመማር እና የማንበብ ልዩ ፍቅር ስለነበራቸው፣ ከእኩዮቻቸው እና ከዘመዶቻቸው ጋር ለመማር እና ለመጫወት ጊዜ የነበራቸው ቢሆንም፣ የማንበብ ፍቅራቸው ከፍተኛ ስለነበረ ሰፊውን ጊዜያቸውን ያጠፉ የነበረው ከመጽሐፍት ጋር እንደነበረ ታናሽ ወንድማቸው ይናገራሉ።-በተለይም ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲገቡ ከትምህርታዊ መጻሕፍት ባሻገር በእንግሊዝኛ የተፃፉ አዳዲስ እና ቆየት ያሉ መጻሕፍትን በማንበብ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ያጠፉ ነበር።-ከእነዚህም መጻሕፍት መካከል የኒቼ፣ የካርል ማርክስ፣ የሌኒን እና ሌሎችም ረጅም ዘመናት ያስቆጠሩ ሥራዎች የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ ካነበቧቸው መካከል ይጠቀሳሉ።-ከሁለተኛ ደረጃ ተማሪነት ጀምሮ በእንግሊዝኛ የተፃፉ መጻሕፍትን የሚያነቡት አቶ ጌታቸው አሁንም ከመጽሐፍት ጋር እንደሚውሉ ቤተሰቦቻቸው እና በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ።-የፎቶው ባለመብት Reuters-አቶ ጌታቸው የሚያነቧቸው መጻሕፍትን ባይመርጡም በዋናነት ግን በፍልስፍና፣ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ እንዲሁም በዓለም ታሪክ ላይ የሚያተኩሩትን መጻሕፍት ያዘወትራሉ።-አቶ ጌታቸው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸውን ያዳበሩት ከሚያነቧቸው መጻሕፍት እንደሆነ የሚገልጹት ታናሽ ወንድማቸው ዶ/ር ሞላ ረዳ “ የተዋሰውን መጽሐፍ ነገ መልስ ከተባለ ሌሊቱን ሙሉ ተቀምጦ ሲያነብ አየው ነበር” ይላሉ።-የቅርብ ጓደኛቸው እና በመቀለ ዩኒቨርስቲ ባልደረባቸው የነበሩት ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም በጻፈው አንድ ጽሑፍ ስለ አቶ ጌታቸው እና ለንባብ ስላላቸው ፍቅር አስተያየታቸውን አስፍሮ ነበር።-“ጌታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቀ በኋላ አብሮን በትግራይ የቀድሞው ቢዝነስ ኮሌጅ ነበር የተቀጠረው። እንግዳ በሆነበት በዚያ ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ ከእኛ ጋር ሲገናኝ አንድ ካፌ ውስጥ ጥግ ይዞ መጽሐፍ እያነበበ ነበር” ይላሉ።-“አዲስ ተመራቂ ከሙያው ጋር ካልሆነ በስተቀር ፍልስፍናን የሚነካ መጽሐፍ ሲያነብ አያጋጥመኝም” የሚሉት አቶ ሙሉወርቅ፣ ጌታቸው ግን ካሉበት የሙያ ዘርፍ ባሻገር በተለያዩ መስኮች የተዘጋጁ መጽሐፍትን እንደሚያነቡ እንዲሁም በመጽሐፍት እና በተለያዩ ሐሳቦች ላይ እንደሚወያዩ ገልጸዋል።-አቶ ጌታቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ታዳጊዋ ኢትዮጵያ በመባል በሚታወቀው ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን፣ በ1985 ዓ.ም. ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት በመግባት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሕግ አግኝተዋል።-አቶ ጌታቸው ረዳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከተመረቁ በኋላ መቀለ ዩኒቨርሲቲን በመምህርነት ተቀላቅላቅለው በሕግ ትምህርት ክፍል አገልግለዋል።-ከዚያም በኋላ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ በአሜሪካ አላባማ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ሁለተኛ ዲግሪ ለማግኘት ችለዋል።-ከዚህ በኋላ ወደ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተመልሰው ማስተማር የቀጠሉ ቢሆንም፣ ብዙም ሳይቆዩ በ1997 በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ በኃላፊነት ተመድበው ወደ አዲስ አበባ አቀኑ።-ከምርጫ 1997 ዓ.ም. በኋላ በተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ ኢህአዴግ ከባድ ፈተና ገጥሞት የነበረ ሲሆን፣ አቶ ጌታቸው ፓርቲያቸው እንደጠላት ሲመለከታቸው በነበሩ የግል ጋዜጦች ላይ የፓርቲያቸውን ሃሳብ የሚገልጹ ጽሑፎችን ያወጡ ነበር።-በተለይም በኢህአዴግ ዘመን ከታዩ የፕሬስ ውጤቶች መካከል ከፍተኛ ተነባቢነት በነበራት “አዲስ ነገር” ጋዜጣ ላይ በፓርቲያቸው ላይ የሚቀርቡ ትችቶችን በመከላከል እና አቋሙን በመግለጽ ያቀርቡ በነበረው ጽሑፍ ይታወሳሉ።-አቶ ጌታቸው ከመምህርነት ሙያ ወጥተው ወደ ፖለቲካ እና የመንግሥት የኃላፊነት ቦታን ከያዙ በኋላ፣ በተለይ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩባቸው ጊዜያት በሁለቱም ከፍተኛ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ በኃላፊነት ሠርተዋል።-በዚህም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር እና ዋና ዳይሬክተር፣ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር እና የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ልዩ አማካሪ ነበሩ። በተጨማሪም በአላማጣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው ተመርጠው ነበር።-አቶ ጌታቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች እንደሚሉት ምንም እንኳን በከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን ላይ የነበሩ ቢሆንም ቀለል ያለ ሕይወትን የሚመሩ እና ወደ ፈለጉት ቦታ ያለ አጃቢ በራሳቸው መሄድና መቆየትን የሚመርጡ ናቸው።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕህመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ጉልህ ለውጥ እና ሽግሽግ ሲካሄድ፣በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ውስጥ ትልቅ ለውጦች መታየት ጀመሩ።-በዚህ ምክንያት ግንባሩን ከመሠረቱት አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ዋነኛው የሆነው ህወሓት በብዙ መልኩ ከአዲሱ መንግሥት እና ከሚወስዳቸው እርምጃዎች ጋር መጣጣም ባለመቻሉ ከኢህአዴግ ራሱን አገለለ።-ይህንንም ተከትሎ አቶ ጌታቸው ረዳ ከሌሎች የትግራይ ከፍተኛ ፖለቲከኞች እና ባለሥልጣናት ጋር ወደ ትግራይ ተመልሰው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አማካሪ፣ እንዲሁም የህወሓት እና የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ ሆነው ሠርተዋል።-አቶ ጌታቸው በፖለቲካው እና በሕዝብ ግንኙነቱ ዘርፍ የህወሓት ቁልፍ ሰው መሆናቸውን በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት አስመስክረዋል። በመንግሥት እና በህወሓት መካከል በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ በተደረጉት ድርድሮች ወቅት ከፊት መስመር ላይ እንደነበሩ በግልጽ ታይቷል።-ሰላም ያመጣውን ስምምነት ህወሓትን በመወከል የፈረሙት አቶ ጌታቸው ከፌደራል መንግሥቱ፣ ከአህጉራዊ፣ ከዓለም አቀፋዊ እና ከምዕራባውያን አገራት ጋር በትግራይ በኩል በነበሩ ግንኙነቶች ውስጥ ሁሉ ጉልህ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል።-ለወራት ምሥረታው የዘገየውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተደደርን እንዲመሩ በህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰየሙት አቶ ጌታቸው፣ ይህንን ተከትሎ አሁን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር እንዲሆኑ ተሹመዋል።-በፖለቲካው መስክ የጎላ ሚና ሲጫወቱ የነበሩት አቶ ጌታቸው በጦርነት የደቀቀውን ክልል መልሶ በማዋቀር እና በመገንባት በኩል ደግሞ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ወደፊት የሚታይ ይሆናል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኢትዮጵያ አራተኛው እና የመጨረሻው ዙር የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሙሌት መጠናቀቁን ገለፀች-ኢትዮጵያ የመጨረሻውን የሕዳሴ ግድብ ሙሌት “በተሰካ ሁኔታ” ማካሄዷን ገለፀች።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በይፋዊ የኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ “አራተኛውንን እና የመጨረሻውን ሙሌት በተሳካ ሁኔታ” ማካሄዷን ይፋ አድርገዋል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድቡን ለመገደብ በገንዘብ በዕውቀት፣ በጉልበት እና በጸሎት የተሳተፉትን ሁሉ በዚሁ መልዕክታቸው ላይ አመስግነዋል።-ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ግንባታን ከጀመረች አስራ ሁለት ዓመታት ያህል አስቆጥራለች።-ግብፅ እና ሱዳን ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው ግዙፍ ግድብን በውሃ መሙላት ከመጀመሯ በፊት አስገዳጅ ስምምነት ላይ መደረስ አለበት በማለት ሲወተውቱ ቢቆዩም፣ ኢትዮጵያ ሳትቀበለው ለአራት ዙር ግድቡ ውሃ እንዲይዝ አድርጋለች።-ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በግድቡ ዙሪያ እየተጀመረ ሲቋረጥ የቆየ ድርድር ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን፣ ሱዳን እና ግብፅ የግድቡን የውሃ ሙሌት እና ቀጣይ ሥራን በተመለከተ አስገዳጅ ስምምነት እንዲፈረም ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል።-በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብፅ መካከል ሲደረግ የነበረው እና ለሁለት ዓመት ያህል ተቋርጦ የቆየው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ድርድር በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ በካይሮ ተካሂዶ ያለውጤት ተበትኗል።-ይህ ውይይት በመስከረም በኢትዮጵያ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ ተደርሷል።-የግድቡ ግንባታ 11ኛ ዓመት ላይ፣ባለፈው ዓመት የካቲት 13፣ 2014 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።-ግድቡ 145 ሜትር ከፍታና ወደ ጎን ደግሞ 1 ሺህ 780 ሜትር ርዝመት አለው።-ግድቡ የሚይዘውን 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ሙሉ በሙሉ ሲይዝም ውሃው የሚተኛበት ስፍራ ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር እነደሚደርስ ባለሙያዎች ይናገራሉ።-ግብፃውያን ግድቡ አገራቸው ከአባይ ወንዝ የምታገኘውን የውሃ መጠንን በመቀነስ ጉዳት ያስከትልባታል የሚል መከራከርያ ያቀርባሉ።-ኢትዮጵያ ግን የአባይ ውሃን የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብት እንዳለት በመግለጽ፣ ግድቡ የታችኛው ተፋሰስ አገራትን የውሃ አቅርቦት በማይጎዳ ሁኔታ የኤሌክትሪክ ኃይልን ለማመንጨት እንደምታውለው ትገልጻለች።-ግንባታው ከተጀመረ ከአስር ዓመት በላይ የሆነው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፣ 90 በመቶው መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን፣ ከአምስት ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለጎረቤት አገራት ኃይል ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።-ላለፉት ሦስት ዓመታት በተከታታይ የውሃ ሙሌቱ ሲካሄድ የነበረው ግድብ ባለፈው ዓመት በተወሰነ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወቃል።-ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ መጀመሯን ይፋ ማድረጓን ተከትሎ ከግብፅ እና ከሱዳን በኩል ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማት ሲሆን፣ የግድቡ ጉዳይም ከአፍሪካ ኅብረት ባሻገር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥም መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።-ሦስቱ አገራት በግድቡ ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት በአፍሪካ ኅብረት እና በአሜሪካ አደራዳሪነት ንግግር ቢያደርጉም ሁሉንም ከሚያግባባ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ቆይተዋል።-ተጠናቆ ሥራውን ሲጀምር በአፍሪካ ግዙፉ እንደሆነ የሚነገርለት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አገሪቱ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ ከራሷ በማውጣት እያከናወነች ነው።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ከጥቂት ወራት በፊት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የተቀረጸና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተሰራጨ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል በርካቶችን አስደንግጧል።-ምስሉ ላይ አንድ በሕይወት ያለ ግለሰብ በዙሪያው ሰዎች በተሰበሰቡበት ከሚነድ እሳት ውስጥ ሲጨመርና ይህንን የሚያበራታቱ ንግግሮች ተሰምተዋል።-ይህ ቪዲዮ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በስፋት ከተዘዋወረ በኋላ በርካቶች ድርጊቱን ሲያወግዙና መንግሥት በፈጻሚዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ሲጠይቁ ነበር።-ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ጥቃቱ በእኔ ወገን ላይ ነው የተፈጸመው የሚሉ ሰዎች ደግሞ ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በግልጽ ለበቀል እርምጃ ጥሪ ሲያቀርቡ፣ ሌሎች ደግሞ ድርጊቱን በማደናነቅ "ጠላት" በሚሉት ወገን ላይ ተመሳሳዩ እንዲፈጸም ሲያበረታቱ ታይተዋል።-እንዲህ አይነቶቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ይዘቶችና መልዕክቶች ጥቃትንና ጥላቻን በማስፋፋት የማኅበረሰቦችን ደኅንነት ከማናጋት ባሻገር ሥነ ልቦናዊ ጫናቸውም የከፋ ነው።-ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መሰል አሰቃቂ ምስሎችን በፌስቡክና መሰል ማኅበራዊ ሚድያዎች መመልከት የየዕለት አጋጣሚ ሆኗል።-የአዲስ አበባው ነዋሪው ወንድሜነህ እንግዳ "ፌስቡክ መጠቀም ካቆምኩ ሁለት ወር አለፈኝ" ሲል ለቢቢሲ ይናገራል።-"በቃ ስገባ የሚታየው ምስልና ጽሁፍ ስለግድያ እና ሞት ነው። በተጨማሪም በጥቃት ሰለባዎች ላይ የሚያላግጡ መልዕክቶችም በስፋት ይነበባል። ታዲያ ይሄ አእምሮዬን ይረብሸው ጀመር" ሲል ከማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ራሱን ያራቀበትን ምክንያት ያስታውሳል።-ስለዚህም "ተመልሼ ፌስቡክ የምጠቀም አይመስለኝም" ይላል።-ቢቢሲ በፌስቡክና ትዊተር እንዲሁም ቴሌግራም በተሰኘው የመልዕክት ማስተላለፊያ መድረክ ላይ የተመለከታቸው ቪድዮዎችና ምስሎች አሰቃቂ መሆናቸውን መታዘብ ችሏል።-እኚህ ምስሎች አንዳንድ ጊዜ በጥቃት አድራሾቹ አሊያም በወቅቱ በአካባቢው የነበሩ ነዋሪዎች የተቀረጹ መሆናቸውን መናገር ይቻላል።-ፌስቡክ፣ትዊተርና ዩቲዩብ የራሳቸው መተዳደሪያ መርኅ ያላቸውና ቢሊዮኖች የሚጠቀሟቸው ማኅበራዊ ሚድያዎች ናቸው።-ታድያ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራጩ መሰል ቪድዮዎች፣ ሐሰተኛ መረጃዎችና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን መቆጣጠር ለምን ተሳናቸው?-ይህ ጥያቄ በርካቶችን ሐሳብ ውስጥ የከተተ ይመስላል።--የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ባላቸው ሰፊ ተደራሽነትና ተሳትፎ ሳብያ በጎምሆኑ አሉታዊ መልዕክቶች በቀላሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩና በዓለም ዙሪያ ላሉ ሰዎች ለማዳረስ ያስችላሉ።-ይህም በሰዎች ላይ ጉዳትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ይዘቶች በቁጥጥር አድራጊ አካላት ዕይታ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት በርካቶች ዘንድ ስለሚደርሱ አሉታዊ ውጤታቸው በአጭር ጊዜው ውስጥ ሊታይ ይችላል።-በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በሚንጣቸው አገራት ውስጥ ማኅበራዊ ሚዲያን ለአሉታዊ ዓላማ የሚጠቀሙ ግለሰቦችና ቡድኖች እጅግ በርካታ ናቸው።-በዚህም በግለሰቦች፣ በማኅበረሰቦች እና በፖለቲካ ቡድኖች መካከል ያለውን ግንኙነት በማበላሸት ለግጭትና ለጥቃት መሳሪያ ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል ሰፊ ነው።-በቅርቡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የተፈጸሙ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ተከትሎ፣ መረጋጋትና ከአደገኛ ድርጊቶች ሁሉም እንዲቆጠብ ከሚጠይቁት በላይ ግጭቶችን የሚያባብሱ ግለሰቦች በተለያዩ መድረኮች ላይ ተስተውለዋል።-አሰቃቂ ድርጊቶቹን በተመለከተ በተለያዩ ጎራዎች የተሰለፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጥቃቶችን ሲያበረታቱ አሊያም ለበቀል እርምጃ ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል።-ይህ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፖለቲከኞችን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን እያሳሰበ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።-ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ እሥር ቤት የቆዩት ታዋቂው ፖለቲከኛ፣ ጃዋር መሐመድ፣ ይህ ሁኔታ ካሳሰባቸው ዜጎች መካከል አንዱ ናቸው።-ፖለቲከኛው በአውሮፓና በአሜሪካ ከደጋፊዎቻቸው ጋር እያደረጓቸው ባሉት ውይይቶች ላይ ኢትዮጵያውያን በማኅበራዊ ሚድያ ገፆቻቸው መገዳደልን ከመስበክ እንዲቆጠቡ ሲጠይቁ ተደምጠዋል።-አቶ ጃዋር አክለው “ኦሮሞ እየሞተ ከሆነ፤ አማራ እየሞተ ከሆነ፤ ትግሬው እየሞተ ከሆነ፤ ጉሙዝ እየሞተ ከሆነ፤ ማነው እየገደለ ያለው? እየተገዳደልን ነው ማለት ነው” ይላሉ።-ፖለቲከኛው "እያለቁ ያሉት ምንም የማያውቁ ሕፃናትና እናቶች ናቸው" በማለትም በውጭ አገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን በዩቲዩብ በኩል ለሚያገኙት ሳንቲም ሲሉ ሕዝቡን ለጥቃት ከማነሳሳት እንዲቆጠቡ መክረዋል።-የፎቶው ባለመብት Getty Images-የኢትዮጵያሕዝብ ቁጥር 120 ሚሊዮን ገደማ እንደሆነ ይገመታል።-ከአጠቃላይየሕዝብ ብዛት 24 በመቶ ያክሉ ከ13 እስካ 24 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ነው።-ዳታሪፖርታልየተሰኘው ድረ ገጽ ባወጣው መረጃ መሠረት 30 ሚሊዮን ገደማአገር ቤት ያሉ ኢትዮጵያውያን የበይነ መረብ ተጠቃሚዎች ናቸው።-ይህቁጥር በየዓመቱ በፍጥነት እየተመነደገ ነው።-ድረ-ገጹ አክሎም በፈረንጆቹ 2022 የኢትዮጵያ በይነ መረብ መስፋፋት 25 በመቶ እንደሆነ ይገልጣል።-እንደሮይተርስ ያሉ የዜና ወኪሎችን ጨምሮ የበይነ መረብ ተጠቃሚዎችን ቁጥር በጥናት አስደግፈው ይፋ የሚያደርጉ ገፆች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያለው ማኅበራዊ ሚድያ ፌስቡክ እንደሆነ ይፅፋሉ።-ባለፈውየፈረንጆቹ ዓመት የወጡ ዘገባዎች በኢትዮጵያ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር 7 ሚሊዮን አካባቢ እንደሆነ ይጠቅሳሉ።-ፌስቡክኢትዮጵያ ውስጥ ግጭትን የሚያበረታቱ መልዕክቶችን መቆጣጠር አልቻለም የሚል ከባድ ወቀሳ ይደርስበታል።-የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባሉ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገራት የፌስቡክ ሠራተኞች ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን ተመልክተው ለበላዮቻቸው ቢያሳውቁም ድርጅቱ እርምጃ አልወሰደም የሚል ይፋዊ ክስ ቀርቦበታል።-ፌስቡክ፤ኢትዮጵያን የግጭት አደጋ ካንዣበባቸው የዓለማችን አገራት መካከል ቢመድባትም የድርጅቱ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶች መቆጣጠሪያ ክንፍ የድርሻውን አልተወጣም በሚል ተደጋጋሚ ትችት ይሰነዘርበታል።-ዎልስትሪት ጆርናል ጋዜጣ መስከረም 2014 ባስነበበው ጽሑፍመመ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች ጭካኔ የተሞላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ያለከልካይ ፌስቡክ ላይ ሲለጥፉ ነበር ብሏል።-ሜታ ለተሰኘው የፌስቡክ ባለቤት ኩባንያ ይሠሩ የነበሩት ፍራንሲስ ሃውግን ፌስቡክ እንደ ኢትዮጵያና ምያንማር ያሉ አገራትን እያፈራረሰ ነው ሲሉ መረጃ ማሾለካቸው ይታወሳል።-ለማርክዙከርበርግ ድርጅት ይሠሩት የነበሩት መረጃ አጋላጯ በአሜሪካ ሴኔት ፊት ቀርበው ነው ይህን ያሉት።-ይህ ዜና በበርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ከተዘገበ በኋላ ፌስቡክ እርምጃ መውሰድ ጀምርያለሁ ብሎነበር።-ለምሳሌ ድርጅቱ በወርሃ ኅዳር በለቀቀው ዘገባ ከ92 ሺህ በላይ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ የፌስቡክ እና የኢንስታግራም ይዘቶች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል።-አልፎም ባለፈው ሚያዚያ “መቀመጫቸውን ግብፅ አድርገው 'ኢትዮጵያ ላይ አነጣጥረዋል'” ያላቸውን ገፆች መዝጋቱን ገልጦ ነበር።-ነገር ግን የፌስቡክ እርምጃ በቂ አይደለም፤ አሁንም በርካታ ተጠቃሚዎች ግጭት ቀስቃሽ መልዕክት ያለከልካይ እያስተላለፉ ነው የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ።-ሜታ እንደ ፌስቡክና ኢንስታግራም ባሉ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ተጠቃሚዎች ጎጂ መልዕክት እንዳያስተላልፉ እንደሚሠራ ይገልጣል።-ድርጅቱ ይህን ሥራ ራሱ በቀጠራቸው ሠራተኞች ጨምሮ በአጋር ድርጅቶች አማካኝነት ያከናውናል።-መቀመጫውን በኬንያ መዲና ናይሮቢ ያደረገ ሳማ ሶርስ የተባለ ድርጅት በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በትግርኛ ቋንቋዎች የይዘት ቁጥጥር [content moderation] ያደርጋል።-ለዚህ ድርጅት የሚሠሩ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሠራተኛ በተለይ ከትግራይ ጦርነት በኋላ በፌስቡክ የሚሠራጩ የጥላቻ ንግግሮች ጨምረዋል ይላሉ።-"ቁጥጥር ከምናደርግበትይዘት 80 በመቶ የሚሆነው ግጭት ቀስቃሽ መልዕክትና የጥላቻ ንግግር ያዘለ መልዕክት ነው" ይላሉ።-ፌስቡክ በተለያዩ ክፍለ ዓለማት ይዘት ቁጥጥር የሚያደርጉለት ድርጅቶች ቢኖሩትም በሦስቱ ቋንቋዎች የሚሠራው ሳማ ይዘትን የመቆጣጠር አቅም እንደሌለው ይናገራሉ።-ፌስቡክ የይዘት ቁጥጥር የሚያደርገው ተጠቃሚዎች ‘ሪፖርት’ ሲያደርጉ እንደሆነ ይገልጣል።-በሌላ በኩል ተጠቃሚዎች ግጭት ቀስቃሽ መልዕክት እንዲለቁ ይፈቅዳል ተብሎ የሚወቀሰው በጉግል የሚተዳደረው ዩቲዩብ የተሰኘው የተንቀሳቃሽ ምስል ማጋርያ ድር ነው።-በርካታ ተጠቃሚዎች በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን በዩቲዩብ ገፆች ሲያስተላልፉ ቢቢሲ መታዘብ ችሏል።-ዩቲዩብ ለዚህ ወቀሳ ምላሽ እንዲሰጥ ቢቢሲ ናይሮቢ ለሚገኘው የጉግል ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ቢደውልም መልስ ማግኘት አልቻለም።-የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ለዚህጥያቄ ምላሽ አላቸው።-ዳይሬክተሩ፤ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ዲጂታል ማኅበረሰብ አባል እንደመሆንዋ በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ከሚሠራጩ የተሳሳቱ መረጃዎችና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶች ማምለጥ አትችልም ይላሉ።-የኢንሳ ዳይሬክተር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚከሰቱ ግጭቶችና ለሚያደርሱት መፈናቀል እንዲሁም ለሰው ነፍስ መጥፋት የማኅበራዊ ሚድያው ሚና ቀላል አይደለም ሲሉ ይናገራሉ።-"ይህ ኢትዮጵያን ያሰጋታል" የሚሉት ዳይሬክተሩ ይህንን ‘አደጋ’ ለመግታት መሥሪያ ቤታቸው እንቅስቃሴ እንደ ጀመረ ይገልጣሉ።-ምንም እንኳ መንግሥት በነፃነት ሐሳባቸውን የሚያቀርቡ ሰዎችን ድምጽ እያፈነ ነው ተብሎ ቢወቀስም፤ ኃላፊው መሥሪያ ቤታቸው ከዚህ በፊት ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ያሠራጩ ሰዎችን ለሕግ ማቅረቡን ያወሳሉ።-“ሐሰተኛ አካውንቶች ስለሚበዙ ማኅበራዊ ሚድያዎች በሚገዙበት መርኅ መሠረት እንዲዘጉ አሊያም እንዲታገዱ ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች [ፌስቡክና ጉግል] ጋር እንሠራለን" ይላሉ።-"ማኅበራዊ ሚድያውየሚከፍላቸው አሉ [ለምሳሌ ዩቲዩብ]። እነዚህ ሰዎች ስለትግሬ መራብ፣ ስለኦሮሞ መጎሳቆል፣ ስለ አማራ ሞት አይገዳቸውም። ሕዝቡን አጋጭተው ስለሚያገኙት ገንዘብ ነው የሚጨነቁት። ሕብረተሰቡ ይህን እንዲያውቅና በጥንቃቄ እንዲጠቀም እንመክራለን።"-ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ማኅበራዊ የትስስር ድረ ገጾችን ለሐሰተኛ መረጃና ለጥላቻ ንግግር ማስተላለፊያነት የሚጠቀሙ ሰዎችን ተጠያቂ የሚያደርግ ሕግ ማውጣቷ የሚዘነጋ አይደለም።-በአዋጁ ከተካተቱ ሕግጋት መካከል የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ ወይንም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎችን በመጠቀም ያስተላለፈ እስከ 2 ዓመት በሚደርስ እስራትና በ100 ሺህ ብር ይቀጣል የሚል ይገኝበታል።-በተላለፈው የጥላቻ ንግግር ምክንያት በግለሰብ አሊያም በቡድን ላይ ጥቃት ከደረሰ አልፎም መረጃው ከ5 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት ገጽ ከተላለፈ ቅጣቱ እስከ 5 ዓመት ሊደርስ እንደሚችል አዋጁ ያትታል።-ብዙዎች ይህ ሕግ፣ መንግሥት የማኅበረሰብ አንቂዎችን ያለጥፋታቸው ወደ እሥር ቤት እንዲልክ ሊያደርግ ይችላል ሲሉ ይሰጋሉ።-መንግሥት በቅርቡ በአማራ ክልል በወሰደው “የሕግ ማስከበር ዘመቻ” በርካታ ጋዜጠኞች እና የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር ይታወሳል።-አቶ ሹመቴ በአዲሱ አዋጅ መሠረት ግጭት ቀስቃሽና የተሳሳቱ መረጃዎችን በፌስቡክ፣ በትዊተርና በዩቲዩብ የሚያሠራጩ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ይላሉ።-በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተማረችው ነገር ግን በሕግ ሙያ ላይ የተሰማራችው ወ/ሮ ነጻነት ወልደገብርኤል፣ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩ መልዕክቶችና ምስሎች ከሚያሳስቧቸው መካከል ናት።-ለዚህም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ አደረጃጀትና ያለው የተካረረ ፖለቲካዊ አመለካከት ሰፊ ድርሻ እንዳለው በማንሳት "ፖለቲከኞች እንዲህ ያሉትን ጥላቻና ጥቃትን የሚያበረታቱ መልዕክቶች በይፋበመቃወምና በማውገዝ ሚና አላቸው" ትላለች።-አንዳንዶች መንግሥት ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግ ሲከፋም እንዲዘጋ የሚጠይቁ ቢኖሩም ወ/ሮ ነጻነት ግን፣ ከዚህ ይልቅ መድረኩን ለበጎ ተግባራት የሚጠቀሙትን በማበረታታት "ለክፋት የሚያውሉትን ማዳከም ይቻላል" በማለት ታስባለች።-ከራሷተሞክሮ በመነሳትም "ለአእምሯዊ ጤናዬ ስል ጥላቻንና ጥቃትን የሚያበረታቱ ገጾችንና ግለሰቦች አልከተልም፤ በእግረ መንገድ የሚያጋጥሙኝን ይዘቶችንም አልመለከትም" ብላለች።
የፎቶው ባለመብት @TheVillaSomalia-የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ማህሙድ-ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት እስካላነሳች እና ለሶማሊያ የግዛት አንድነት ማረጋገጫ እስካልሰጠች ድረስ ከአዲስ አበባ ጋር ለሚደረግ ሽምግልና “ቦታ እንደሌላት” ሶማሊያ አስታወቀች።-ሶማሊያ ይህንን አቋሟን ያሳወቀችው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ትላንት ረቡዕ ካደረገው ስብሰባ በኋላ ሁለቱ አገራት “ትርጉም ያለው ንግግር” በማድረግ ችግራቸውን እንዲፈቱ መጠየቁን ተከትሎ ዛሬ ሐሙስ ጥር 9/2016 ዓ.ም. ባወጣችው መግለጫ ነው።-ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ታኅሣሥ 22/2016 ዓ.ም. በመሪዎቻቸው መካከል በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት ኢትዮጵያ ነጻ አገር መሆኗን ላወጀችው ሶማሊላንድ ዕውቅናን ለመስጠት፣ ሶማሊላንድ በበኩሏ ደግሞ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ለመፍቀድ ስምምነት ደርሰዋል።-ይህም ሶማሊላንድን የግዛቱ አንድ አንድ አካል እንደሆነች የሚገልጸው የሶማሊያ መንግሥት ስምምነቱን አጥብቆ በመቃወም፣ የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚጥስ ድርጊት ነው በማለት በአካባቢው ውጥረት እንዲፈጠር አድርጓል።-የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤቱ በውይይቱ ኢትዮጵያ እና የሰሜን ሶማሊያ ግዛት (ሶማሊላንድ) የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በአዲስ አበባ እና በሞቃዲሾ መካከል የተፈጠረው ውጥረት እንዳሳሰበው አስታውቋል።-ምክር ቤቱ ከውይይቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያን ጨምሮ የሁሉም የኅብረቱ አባል አገራት “ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እና ነጻነት” እንዲጠበቅ “ጠንካራ ቁርጠኝነት እና ድጋፍ” እንዳለው አስታውቋል።-የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ተወካዮች በተገኙበት ውይይቱን ያካሄደው ምክር ቤቱ፤ ሁለቱ አገራት የተፈጠረው ውጥረት ግንኙነታቸውን ሊያበላሽ ከሚችሉ ተጨማሪ ድርጊቶችን ከመፈጸም እና እርምጃዎችን ይፋ ከማድረግ እንዲቆጠቡ ጠይቋል።-ምክር ቤቱ በመግለጫው፤ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለጉዳዩ ሰላማዊ መፍትሄ ለመስጠት ሲባል ትርጉም ያለው ንግግር እንዲያደርጉም ጠይቋል።-የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በሁለቱ አገራት መካከል ንግግር እንዲያመቻቹ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሾማቸውን ኮሚሽኑ እንደሚቀበለውም በመግለጫው ላይ ሰፍሯል።-የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ውይይትን አስመልክታ ዛሬ መግለጫ ያወጣችው የሶማሊያ ምክር ቤቱ ኅብረቱ ለሁሉም አባል አገራት “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት” ማረጋገጫ መስጠቱን እንደሚቀበለው ገልጿል።-“ይህንን መርኅ ከመደገፍ አኳያ፤ ኢትዮጵያ ከሰሜን ሶማሊያ ግዛት (ሶማሊላንድ) ጋር ሕገወጡን የመግባቢያ ስምምነት ስትፈራረም የሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ተጥሷል” ስትል ኅብረቱ የሚደግፈው መርኅ መጣሱን ገልጻለች። “በተቃራኒው ሶማሊያ እነዚህን የተከበሩ መርሆዎች አልጣሰችም” ስትል ጥፋት የተፈጸመው በኢትዮጵያ ነው የሚል አቋሟን አንጸባርቃለች።-ሶማሊያ በመግለጫዋ፤ “በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ የፈረመችውን የመግባቢያ ስምምነት እስካላነሳች እና የሶማሊያን የግዛት አንድነት እስካላረጋገጠች ድረስ ለሽምግልና የሚሆን ቦታ የለም” ስትል የኅብረቱ የፀጥታ ምክር ቤት ሁለቱ አገራት እንዲያደርጉ ለጠየቀው ንግግር ቅድመ ሁኔታን አስቀምጣለች።-ስምምነቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ በየትኛውም ወገን ላይ ጉዳት የማያደርስ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።-ሶማሊያ የዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት በማድረግ ሁሉንም ወገን በሚጠቅም መልኩ “የኢኮኖሚ እድገት እና የጋራ ብልጽግና” የሚያመጣ ግንኙነት ከሁሉም የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ኅብረት እና የኢጋድ አባል አገራት ጋር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በመግለጫው አስታውቃለች።-የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ያደረገው ውይይት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን የተሰጠ መግለጫም ሆነ አስተያየት የለም።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ በአዲስ አበባ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት በቀጣናው ላይ ውጥረት ከፈጠረ ከሁለት ሳምንት በላይ ሆኗታል። በአንድ ወር ውስጥ ይፈጸማል በተባለው በዚህ ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ ለወታደራዊ እና ንግድ አገልግሎት የሚውል የባሕር በር ታገኛለች።-ኢትዮጵያ በምላሹ ሶማሊላንድን እንደ አገር የሚያስቆጥራትን እውቅና ለመስጠት መስማማቷን የሃርጌሳ ባለሥልጠናት ተናግረዋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ስምምነት የፈጸመው ጉዳዩን በጥልቀት አጢኖ አቋም ለመያዝ መሆኑን አስታውቋል። ከዚህ ባሻገር ግን ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ እንደሚኖራት የኢትዮጵያ መንግሥት መግለጹ ይታወሳል።
የፎቶው ባለመብት FACEBOOK-ምሥጢራዊ ሰነዶችን ይፋ በማድረግ የተከሰሰው ጃክ ቴሼራ አሁንም የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ነው ሲል የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ተናገረ።-ከ100 በላይ ገጾች ያሉትን ምሥጢራዊ ሰነዶች አደባባይ ያወጣው ወጣት አሁንም ቁልፍ የሚባሉ ሰነዶች በእጁ ሊኖሩ ይችላሉ ሲል ዐቃቤ ሕግ ስጋቱን ገልጿል።-በአሜሪካ አየር ኃይል ብሔራዊ ዘብ የዝቅተኛ እርከን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆነው የ21 ዓመት ወጣት ከሳምንታት በፊት ምሥጢራዊ ሰነዶችን በማውጣቱ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወሳል።-ቴሼራ ይፋ ባደረጋቸው ሰነዶች በዩክሬን እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ምሥጢራዊ ጉዳዮችን ይፋ ከማድረጉም በላይ አሜሪካ በአጋሮቿ ላይ ስለላ ስለማድረጓ አጋልጧል።-ሰነዶቹ የምዕራባውያን አገራት ልዩ ኃይሎች በዩክሬን ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ስለመሆናቸው አሳይቷል።-ከዚህ በተጨማሪም ሰነዶቹ የተባባሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጌቴሬዝ የሩሲያን ፍላጎት ለሟሟላት ፍላጎት አላቸው ብላ አሜሪካ እንደምታምን ሰነዶቹ አጋልጠዋል።-ዐቃቤ ሕግ የ21 ዓመቱ ወጣት ከእስር ቤት ከወጣት ከተጠያቂነን ለማምለጥ ሊሸሽ ስለሚችል ጉዳዩን በእስር ቤት ሆኖ መከታተል አለበት ብለዋል።-መርማሪዎች እስካሁን ድረስ ከፍተኛ አገራዊ ምሥጢሮች እንዴት ቴሼራ እጅ ገቡ የሚለውን ለመለየት እየሠሩ ነው።-የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ጃክ ቴሼራ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ በመኖሪያ ቤቱ እንዲወድሙ የተደረጉ እና ቆሻሻ መጣያ ውስጥ የተጣሉ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር፣ ታብሌት እና ኤክስ ቦክስ ጌም መጫወቻ ተገኝቷል ብሏል።-የአሜሪካ ባለሥልጣናት ወጣቱ ምሥጢራዊ ሰነዶቹን ሆነ ብሎ አደባባይ ማውጣቱን ቢናሩም፤ ጃክ ቴሼራ ሰነዶችን አሾልኮ ለማውጣት ምን እንዳነሳሳው ያሉት ነገር የለም።-ክስተቱን ተከትሎ በወጣትነት ዕድሜ እና በታችኛው እርከን ባለ ሠራተኛ እጅ እንዲህ አይነት አገራዊ የምሥጢር ሰነድ እንዴት ሊገባ ቻለ የሚሉ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል።-የአሜሪካ አየር ኃይል ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የጃክ ቴሼራ ምድብ ውስጥ የበላይ አለቆች የሆኑ ሁለት ኮማንደሮች ከሥራ ታግደውም ምርመራ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።-ቴሼራ ምሥጢራዊ ሰነዶቹን በማውጣቱ እስከ 15 ዓመታት በእስር እንዲያሳልፍ ሊፈረድበት ይችላል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በጀርመኗ ጊሰን ከተማ በኤርትራውያን የባሕል ፌስቲቫል ላይ በተከሰተ ግጭት 26 የጀርመን ፖሊስ አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።-የአገሪቱ ፖሊስ በጊሰን ከተማ የተዘጋጀውን የባሕል ፌስቲቫል ለማወክ የወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያንን ለመበተን ዱላ እና ዐይን የሚያቃጥል ፈሳሽ ረጭቷል፤ ሄሊኮተፕር ጭምር በአካባቢው አሰማርቶ ነበር።-ፖሊስ በግጭቱ ተሳታፊ ናቸው ያላቸውን ከ100 የማያንሱ ኤርትራውያንን እና ትውልደ ኤርትራውያንን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ጨምሮ ገልጿል።-ሁከቱ የተፈጠረው በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች የተዘጋጀ ነው የተባለውን ዝግጅት ለማወክ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎች ፌስቲቫሉ ወደሚዘጋጅበት ቦታ በኃይል ለመግባት ጥረት ማድረጋቸውን ተከትሎ ስለመሆኑ የጀርመን መገናኛ ብዙኃን በስፋት ዘግበዋል።-የባሕል ፌስቲቫሉ መዘጋጀቱን በመቃወም አደባባይ የወጡ፤ ፌስቲቫሉ ለኤርትራ መንግሥት ፕሮፖጋንዳ የተዘጋጀ ነው ይላሉ።-የጀርመን ፖሊስ ትናንት ቅዳሜ ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም. የተከሰተው ግጭት ለሰዓታት መቆየቱን እና 26 የፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል።-አሶሺዬትድ ፕሬስ የጀርመን ፖሊስን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ሁከቱን ለመቆጣጠር 1 ሺህ የፖሊስ አባላት፣ ሄሊኮፕተር እና ውሃ በከፍተኛ ኃይል የሚረጭ አድማ በታኝ መኪና ተሰማርቶ ነበር።-የከተማዋ አስተዳዳሪዎች በሁከቱ ወቅት የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ መሐል የከተማ ክፍል ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።-በጀርመኗ ከተማ የተከሰተውን ግጭት የሚያሳዩ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተጋሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች፣ በአብዛኛው ወጣት የሆኑ ኤርትራውያን ድንጋይ ወደ ፖሊስ ሲወረውሩ እና በከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ ፖሊስ ሲያባርራቸው ታይተዋል።-ፖሊስም ተቃዋሚዎቹ በሕግ አስከባሪ ኃይል አባላት ላይ ጠርሙስ፣ ድንጋይ እና የጭስ ቦምብ መወርወራቸውን፣ ተሸከርካሪዎችን ማውደማቸውን እና ፌስቲቫሉ የሚካሄድበትን ስፍራ የመከለያ አጥር ማፍረሳቸውን አስታውቋል።-ፖሊስ ጨምሮ እንደገለጸው ተቃዋሚዎቹ ወደ ፌስቲቫሉ ስፍራ ተሳታፊዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ አውቶብስ ላይ ድንጋይ ወርውረዋል።-የጀርመን ዜና አገልግሎት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከንጋት 11፡30 ጀምሮ ፌስቲቫሉ ወደሚካሄድበት ቦታ በኃይል ለመግባት ጥረት ሲያደርጉ ከነበሩ ከ100 በላይ ሰዎች መከልከላቸውን ዘግቧል።-ከአንድ ዓመት በፊት በተመሳሳይ ከዚህ ፌስቲቫሉ መካሄድ ጋር በተያያዘ ሁከት ተፈጥሮ በርካታ ሰዎች ተጎድተው ነበር።-የጀርመን ዜና ወኪል ዲፒኤ ከአንድ ዓመት በፊት በነበረው ሁከት 100 የፌስቲቫል አዘጋጆች እና ጎብኚዎች ላይ ጉዳት ደርሶ እንደነበር ዘግቧል።-ይህን ተከትሎ ሊከሰት ይችላል የተባለን ተመሳሳይ ሁከት ለመከላከል ፌስቲቫሉ ዘንድሮ እንዳይካሄድ የከተማዋ ባለሥልጣናት እና ፖሊስ ከልክለው የነበረ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤት ግን ፌስቲቫሉ መከልከል የለበትም በሚል ተካሂዶ ዳግም ግጭት ተከስቷል።-በሁከቱ ምንክንያት ከፍንራንክፈርት በስተሰሜን በምትገኘው እና የ84 ሺህ ሕዝብ መኖሪያ በሆነችው ጊሰን ከተማ የትራፊክ እንቀስቃሴ ተገድቦ ቆይቷል።-ፌስቲቫሉ ከአርብ ሰኔ 30 እስከ እሁድ ሐምሌ 2/2015 ዓ.ም. ድረስ እንዲካሄድ የተዘጋጀው የኤርትራውያን ማዕከላዊ ምክር ቤት በተባለ እና ለኤርትራ መንግሥት ቅርብ ነው በተባለ አካል ነው።-በቅርብ ዓመታት ጀርመን ከፍተኛ ቁጥር ላለቸው ኤርትራውያን ስደተኞች ጥገኝነት የሰጠች ሲሆን፣ ይህም በአውሮፓ ኅብረት ካሉ አፍሪካውያን ማኅብረሰቦች ኤርትራውያኑን ከቀዳሚዎቹ ተርታ አስልፏቸዋል።-በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የኤርትራ መንግሥት በዜጎቹ ላይ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚፈጽም ይገልጻሉ።-በዚህም ምክንያት በኤርትራ ያለውን የፖለቲካ እና የእምነት ነጻነት ጭቆና እንዲሁም የጊዜ ገደብ የሌለውን አስገዳጅ የብሔራዊ አገልግሎት በመሸሽ በርካቶች ኤርትራውያን አገር ጥለው ይሰደዳሉ።
የፎቶው ባለመብት EOTC-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሪዎች ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት የቤተክርስቲያኗ አቋም ተቀባይነት በማግኘቱ ለእሁድ ታቅዶ የነበረው ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገለጸ።-በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ ውጥረት በነገሰበት ጊዜ በቤተክርስቲያኗ እና በመንግሥት መሪዎች መካከል አርብ ከሰዓት በኋላ በተደረገው ውይይት፣ መንግሥት ቤተክርስቲያኗ ያቀረበችውን ቅድመ ሁኔታ መቀበሉ ተገልጿል።-ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 04/2015 ዓ.ም. የውይይቱን ውጤት በተመለከተ የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በውይይቱ በዋነኛነት ከቤተ ክርስቲያኗ ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሕግ ውጪ ምንም አይነት ድርድር እንዳልተደረገ ተገልጿል።-በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት በአማርኛ እና በኦሮምኛ በቀረበው መግለጫ ላይ “መንግሥት የቤተ ክርስቲያንን አቋም በመቀበል ወደፊትም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት እና ሉዓላዊነትን በጠበቀ መንገድ እንደሚሠራ አረጋግጧል” ተብሏል።-በውይይቱ ላይ በፓትርያርክ አቡነ ማቲዮስ የተመሩ አሥራ ሁለት ጳጳሳት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች መገኘታቸው ተገልጿል።-በቤተክርስቲያኗ አባቶች መካከል ከሦስት ሳምንት በፊት ጀምሮ የተከሰተውን ችግር ተከትሎ በቤተክርስቲያኗ አባላት ላይ የሕይወት እና የአካል ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ጉዳይ በውይይቱ ላይ ተነስቶ መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንደሚያደርግ ተገልጿል።-በተጨማሪም አሁን ላይ እስር፣ እንግልት እየተፈጸመባቸው ያሉት አባቶች እና የቤተክርስቲያኗ አባላት ላይ የሚደርሰው ችግር በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ እና አገልግልታቸውን በሰላም እና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል።-የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ በመሆኑ ይህንን ለማስፈጸም ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት 05/2015 ዓ.ም. ሊካሄድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉ ተገልጿል።-በቤተክርስቲያን በኩልም በሕግ የተያዙት ጉዳዮች የሕግ ሂደታቸውን ተከትለው የሚቀጥሉ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ መንግሥትም የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ተቀብሎ ለውይይት ፈቃደኛ መሆኑን የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማክበር በውሳኔው መሠረት የሚፈጸም መሆኑን በማረጋገጡ ምስጋና አቅርበዋል።--ጥር 14/2015 ዓ.ም. ሦስት ጳጳሳት ቤተክርስቲያኗ ሁሉን አሳታፊ አይደለችም እንዲሁም በቀሪው የአገሪቱ ክፍል ያሉ ምእመናንን በቋንቋቸው እያገለገለች አይደለም በሚል ለ26 ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ከሰጡ በኋላ ነበር ቀውሱ የተጀመረው።-የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ደግሞ ሹመቱ ከቤተክርስቲያኗ ቀኖና፣ ዶግማ እና አስተዳደራዊ ሂደት የተቃረነ በመሆኑ ሿሚዎቹ እና ተሿሚዎቹ በይቅርታ እስኪመለሱ ድረስ ተወግዘው እንዲለዩ ወስኗል።-ይህንንም ተከትሎ በቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካቢኔ ስብሰባ ላይ በሰጡት አስተያየትም በመንግሥት እና በቤተክርስቲያኗ መካከል መካረር ተፈጥሮ ቆይቷል።-መንግሥት ቢያስተባብልም ቤተክርስቲያኗ በተደጋጋሚ በሰጠችው መግለጫ መንግሥት ወገንተኛ ሆኗል ሕግንም እያስከበረ አይደለም በማለት የቤተክርስቲያኗ ተከታዮች እሁድ የካቲት 05/2015 ዓ.ም. አደባባይ ወጥተው ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ ቀርቦ ነበር።-ነገር ግን መንግሥት የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ በወሰደው እርምጃ ከቤተክርስቲያኗ መሪዎች ጋር በመወያየት ከስምምነት በመድረሱ ሰልፉ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ እና የቤተክርስቲያኗ ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ መወሰኑን ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ ላይ አሳውቃለች።-ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄድበታል በተባለው እለት ምዕመናን ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው በመሄድ እንዲጸልዩ እና ትምህርት እንዲማሩ ቤተክርስቲያኗ የገለጸች ሲሆን ምዕመናን ቤተ ክርስቲያኒቱን መጠበቃቸውን እንዲቀጥሉም አሳስባለች።-እስካሁን ስለውይይቱም ሆነ ተደርሷል ስለተባለው ስምምነት ከመንግሥት በኩል የተባለ ነገር የለም።
የፎቶው ባለመብት Debremarkos City Communication-በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት ምክንያት በትራንስፖርት እና በመድኃኒት እጥረት ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸውን ተናገሩ።-በላሊባላ ደብረ ማርቆስ እና ሸዋሮቢት የሚገኙ ነዋሪዎች በቀጠለው ግጭት ምክንያት የትራንስፖርት ችግር፣ የመድኃኒት እጥረት እና መሰረታዊ ፍጆታዎች እጥረት እንዲሁም ዋጋቸውም መናሩን ለቢቢሲ አስረድተዋል።-በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎችም በመድኃኒት እጥረት ህሙማን ለከፋ አደጋ መጋለጣቸውንም ነው ነዋረዎች የሚናገሩት።-ከሰሞኑ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር የሚገኘው የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በክልሉ ባለው ግጭት ምክንያት ሥራ አቋርጦ እንደነበር ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል።-ቢቢሲ ከሆስፒታሉ ሠራተኞች እና ከዩኒቨርስቲው ኃላፊ ለማረጋገጥ እንደቻለው ሆስፒታሉ የተለመደ መደበኛ ሥራውንም እየሰራ አልነበረም።-የአማራ ክልል መንግሥት ሰላም እየሰፈነ እና የአካባቢዎቹም የንግድ እንቅስቃሴ ወደቀደመ ሁኔታ እየተመለሰ ነው ይላል።-ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የላሊበላ ነዋሪ በአካባቢያቸው ውጊያዎች እየተካሄደ እንደሆነ ገልጸዋል።-ብልባላ፣ አይና ቡግና፣ ኩል መስክ እና ጋሸና የተሰኙት አካባቢዎች ከቀናት በፊት ውጊያዎች ማስተናገዳቸውን ይናገራሉ።-እንቅስቃሴም በመገደቡ ከከተማ ውጭ ሰዎች መንቀሳቀስ የማይችሉበት ሁኔታም ተፈጥሯል።-በተለይም በላሊበላ ዙሪያ ያሉ አርሶ አደሮች ወደከተማዋ መግባት እና መውጣት በመከልከላቸው የግብርና ምርቶች በሶስት እና አራት እጥፍ ማሻቀባቸውንም እኚሁ ነዋሪ ይናገራሉ።-እሳቸው እንደሚሉት ውጊያዎች እየተካሄደባቸው ካሉ ስፍራዎች የሚመጡ አርሶአደሮች ወደ ከተማ ገብተው ምርቶቻቸውን መሸጥ በአሁኑ ወቅት አልቻሉም።-“ለፋኖ ድጋፍ ይሰጣሉ እንዲሁም ታጣቂዎቹ ከእነዚህ አርሶ አደሮች ጋር ተቀላቅለው ይገባሉ” በሚል ስጋትም ወደ ከተማዋ መግባት ተከልክለዋል።-አርሶ አደሮቹ ወደ ከተማዋ ከመጡም ድብደባና እንግልት እንደሚደርስባቸውም እኚሁ ነዋሪ ያስረዳሉ።-በዚህም ምክንያት ምርቶቹ በከፍተኛ ሁኔታ ዋጋቸው መናሩን እንዲሁም እጥረት በማጋጠሙ የአካባቢው ነዋሪ ተቸግሯል ይላሉ።-አካባቢዎቹ ለሳምንታት እና ወራት እንቅስቃሴ በመገደቡም የገቢ ምንጭ መቀዝቀዙን እና የአካባቢውም ምጣኔ ኃብት እያሽቆለቆለም እንደሆነ ነው ነዋሪዎች የሚናገሩት።-በደብረ ማርቆስ አካባቢም ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪ “በሰላም ገብተን መውጣታችንንም አናውቅም” ይላሉ።-ከተማዋን ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚያገናኙ አገር አቋራጭ ትራንስፖርቶች ከተቋረጡ መሰነባበታቸውን ቢቢሲ ከነዋሪዎች ሰምቷል።-ከእንቅስቃሴዎች ገደብ እና ከትራንስፖርት መቋረጥ ጋር ተያይዞም ከፍተኛ የመድኃኒት እጥረት ገጥሟል ይላሉ።-“ከመድኃኒት እጦት ጀምሮ ይሄ ነው ተብሎ መግለጽ አይቻልም፤ ቃላት ያጥራል። በመድኃኒት እጦት ምክንያት እናቶች ህይወታቸው አልፏል። ህክምና ባለማግኘታቸው ሰዎች እየሞቱ ነው” ይላሉ።-በአካባቢው በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በከፊል ስራ ቢኖርም ውስን እንደሆነ ቢቢሲ ያናገራቸው የሸዋሮቢት ነዋሪ ገልጸዋል።-ኑሯቸው በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደገባ የሚናገሩት እኚህ ነዋሪ በከተማዋ ውጊያ ባይኖርም አካባቢው በግጭት እና በደህንነት እጦት ምክንያት እየተፈተነ እንደሆነ ይናገራሉ።-በአካባቢው የትጥቅ ትግል እየተካሄደ በመሆኑም እንቅስቃሴ ተገድቧል፤ መኪኖች በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻሉም ይላሉ።-ነዋሪዎች በግጭት ምክንያት የአካባቢው ምጣኔ ኃብት ተቀዛቅዟል፣በኑሮ ውድነት እና በጸጥታ እጦት እየተፈተንን ነው ቢሉም የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንገሻ ፈንታው ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ በክልሉ የሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ሰላማቸው እየተመለሰ ነው ብለዋል።-በጸጥታ ችግር ተገድበው የነበሩ የንግድ እንቅስቃሴዎችም አሁን በተሻለ ሁኔታ ይገኛሉ ሲሉ ተደምጠዋል።-ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት በክልሉ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ መታወጁ ይታወቃል።-እስካሁንም ድረስ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ግጭቶች መቀጠላቸው ተዘግቧል። በዚህም ሳቢያ መደበኛ እንቅስቃሴዎች በመተስጓጓላቸው በጤና እና በአግልግሎት አቅራቢ ተቋማት ላይ ጫና መፈጠሩን ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ አውሮፕላናቸው የቴክኒክ ብልሽት ገጥሞት ያለዕቅዳቸው ሕንድ ለመቆየት ተገደዋል።-የካናዳ ጦር ሠራዊት ትሩዶን በፍጥነት ወደ ቤታቸው ሊያመጣቸው እየተሯሯጠ ቢሆንም ከማክሰኞ ከሰዓት በፊት ካናዳ እንደማይገቡ ቢሯቸው ገልጧል።-በቡድን 20 ሃገራት ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ ሕንድ ያቀኑት ትሩዶ ከሕንዱ አቻቸው ናሬንድራ ሞዲ ጋር ጠጠር ያለ ውይይት ካደረጉ በኋላ ዕለተ ሰንበት ነበር ሊመለሱ ያቀዱት።-ቢሯቸው እንደገለጠው በረራቸው “ይህ ነው የሚባል ጊዜ አልተቆረጠለትም።”-የካናዳ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት ለቢቢሲ በላከው መግለጫ “የካናዳ ሮያል አየር ኃይል ሲሲ-150 ፖላሪስ የተሰኘችው አውሮፕላን «የቴክኒክ ብልሽት» ገጥሟታል” ብሏል።-መግለጫው አክሎ “የተሳፋሪዎቻችንን ደኅንነት መጠበቅ የኛ ኃላፊነት ነው፤ ለዚህም ነው ከበረራ በፊት ሁሌም የቴክኒክ ምርመራ የምናካሂደው” ብሏል።-ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶን ይዛ ከሕንድ የምትመለስ ምትክ አውሮፕላን ማክሰኞ ከዩናይትድ ኪንግደም ተነስታ እንደምትሄድ ተሰምቷል።-ነገር ግን የካናዳ መከላካይ ሠራዊት ምትክ አውሮፕላን መዘጋጀቱን ከመጥቀስ ውጭ የአውሮፕላኗ መነሻ ከየት? መቸስ ይመለሳሉ? የሚሉ ጥያቄዎችን ከመመለስ ተቆጥቧል።-ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ በተራዘመ በረራ ሲንገላቱ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም።-በአውሮፓውያኑ 2019 ጋዜጠኞችን አሳፍራ የነበረች አውሮፕላን እሳቸውን ይዛ ልትበር ከቆመች ሌላ አውሮፕላን ክንፍ ጋር መጋጨቷ የሚታወስ ነው።-በካናዳዋ ብሪቲሽ ኮለምቢያ ባለፈው ሰኔ የሲክ ብሔር መገንጠልን የሚያቀነቅነው ሲንግ ኒጃር መገደሉ ይታወሳል።-የሲክ መገንጠልን የሚያቀነቅኑ ሰዎች በቶሮንቶ አውራ ጎዳና የሕንድ መንግሥትን በይፋ ተቃውመዋል። ለግለሰቡ መገደሉም ኃላፊነት ሊወስድ ይገባል ብለዋል።-ሞዲ ከትሩዶ በነበራቸው ውይይት “ፀረ-ሕንድ አክቲቪስቶች በካናዳ እየበረከቱ በመሆናቸው” የተሰማቸውን ስጋት ገልጠዋል።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ከአውሮፓውያኑ ከ1980ዎቹ ጀምሮ በደሙ ውስጥ ኤችአይቪ ቫይረስ የነበረበት ግለሰብ ከበሽታው ነጻ መሆኑን ዶክተሮች ገለጹ።-በዚህም እስካሁን ከኤችአይቪ ቫይረስ ነጻ መሆናቸው ከተነገረላቸው ሰዎች አራተኛው ሆኗል።-ግለሰቡ የነበረበትን የደም ካንሰር ለማከም በተፈጥሮ ቫይረሱን ለመቋቋም ከሚችል አንድ ግለሰብ የአጥንት መቅኔ ዝውውር ሕክምና ተደርጎለታል።-ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ የተነገረለት ግለሰብ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የ66 ዓመት ሰው ሲሆን፣ አሁን የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት መውሰድ ማቆሙ ተነግሯል።-ቫይረሱ በደሙ ውስጥ እንደሌለ ባወቀበት ጊዜ ግለሰቡ በሰጠው አስተያየት ከቫይረሱ መፈወሱን “ከአድናቆት በላይ ነው” ሲል ገልጾታል።-ግለሰቡ በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት፣ ዱዋርቴ ውስጥ በሚገኘው ‘ሲቲ ኦፍ ሆፕ’ ሆስፒታል ውስጥ ሕክምናውን ሲከታተል የቆ ሲሆን ማንነቱ እንዲገለጽ ስላልፈለገ መጠሪያው በሆስፒታሉ ስም እንዲሆን ጠይቋል።-እንደ ግለሰቡ በቫይረሱ ተይዘው የነበሩ አብዛኞቹ ጓደኞቹ የፀረ ኤችአይቪ ሕክምና ከመምጣቱ በፊት ለሞት ተዳርገዋል።-እነዚህ መድኃኒቶች በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ በደማቸው ያለ ሰዎች ከጤናማነት ጋር የተቀራረበ ሕይወትን እየመሩ ነው።-ቫይረሱ የሰውን ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከያ ሥርዓት በመጉዳት ወደ ኤድስ በሽታ የሚያመራ ሲሆን በሽታውን ለመቋቋም ጥረት ያደርጋል።-ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ የተገለጸው ግለሰብ እንዳለው “ከ35 ዓመት በፊት ቫይረሱ እንዳለብኝ በምርመራ ሲረጋገጥ፣ እንደሌሎቹ ሁሉ ሞት የተፈረደብኝ ያህል ነበር ያሰብኩት። ፈጽሞ ከቫይረሱ ነጻ የምሆንበት ቀን ይመጣል ብዬ አስቤ አላውቅም” ብሏል።-ግለሰቡ በ63 ዓመቱ የደም ካንሰር ስለተገኘበት በካንሰር የተጠቁትን ህዋሳቱን ለመተካት የአጥንት መቅኔ ዝውውር ሕክምና ተደርጎለታል።-በዚህ ወቅትም የአጥንት መቅኔውን የለገሰው ግለሰብ ኤችኤይቪ የሚቋቋም ተፈጥሮ ስለነበረው ለግለሰቡ መፈወስ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።-የኤችአይቪ ቫይረስ በሽታን ተከላካይ ነጭ የደም ህዋሳትን በማጥቃት ወደ ኤድስ የሚሸጋገር ሲሆን፣ አንዳንድ ሰዎች ግን ይህንን የሚከላከል ተፈጥሯዊ ባህሪ እንዳላቸው ተደርሶበታል።-ከኤችአይቪ ነጻ የሆነው ሕመምተኛ የመቅኔ ሽግግር ከተደረገለት በኋላ በሐኪሞች ክትትል ሥር ቆይቶ ቫይረሱ በደሙ ውስጥ ከማይለይበት ደረጃ ላይ መድረሱን አረጋግጠዋል።-በዚህም ከ30 ዓመት በላይ ሲወስደው የነበረው የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒትን እንዲያቆም በሐኪሞቹ ተነግሮታል።-ከ10 ዓመት በፊት ራይ ብራውን የተባለው ግለሰብ ከኤችአይቪ ነጻ መሆኑ የተገለጸ የመጀመሪያ ሰው ሲሆን፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ሌሎች ሦስት ሰዎችም ከበሽታው መፈወሳቸው ተዘግቧል።-አሁን አሜሪካ ውስጥ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ የተነገረው ግለሰብ በዕድሜ የገፋ ቫይረሱ በደሙ የነበረበት እና የመጀመሪያው ሰው ሲሆን፣ የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት ለረዥም ጊዜ የወሰደ እንደሆነም ተነግሯል።
የፎቶው ባለመብት Reuters-የቭጌኒ ፕሪጎዢን የሩሲያዋን ከተማ ሮስቶቭን ለቆ ሲወጣ-ከሁለት ሳምንት በፊት የቫግነር ቅጥረኛ ቡድን ከአመጹ በኋላ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቡድኑ መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን ጋር ተገናኝተው እንደነበር ክሬሚሊን አስታወቀች።-የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንዳሉት የቫግነር ቅጥረኛ ቡድንን የሚመራው ፕሪጎዢን፣ በሞስኮ በተካሄደው ስብስባ ላይ እንዲገኙ ከተጋበዙ 35 ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበር።-ከአስራ አንድ ቀናት በፊት በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ወቅትም ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬንን ኃይል እና አመጹን መገምገማቸውን ቃል አቀባዩ ጨምረው ተናግረዋል።-በቫግነር ቅጥረኛ ቡድኑ መሪ ፕሪጎዢን የተመራው የትጥቅ አመጽ የተቀሰቀሰው እንደ አውሮፓውያኑ ሰኔ 23 ሲሆን የቆየው ለ24 ሰዓታት ብቻ ነበር።-አመጹ እና ፍጥጫው በቤላሩሱ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ አማካይነት በተደረሰው ስምምነት መሠረት የቆመ ሲሆን፣ ፕሪጎዢን ላይ የቀረበው የአገር ክህደት ክስ ተነስቶ ወደ ቤላሩስ እንዲሄድ ተፈቅዶለትም ነበር።-በቅጥረኛ ቡድኑ ቫግነር እና በሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መካከል አለመግባባቶች የነበሩ ሲሆን ፕሪጎዢን ለቡድኔ ጥይት አልቀረበለትም ሲል ሚኒስቴሩን በተደጋጋሚ ከሷል።-ይሁን እንጂ አመጹ ከከሸፈ ከአምስት ቀናት በኋላ በክሬሚሊን በተደረገው ስብሰባ ላይ ከተጋበዙ ወታደራዊ አዛዦች መካከል አንዱ እንደነበር ፔስኮቭ ተናግረዋል።-የሩሲያ መንግሥት የዜና ወኪል ኢንተርፋክስ የሩሲያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭን ጠቅሶ እንደዘገበው “ፕሬዚደንት ፑቲን በጦር ግንባር ላይ ቅጥረኛ ቡድኑ የፈፀመውን ድርጊት ገምግመዋል።”-ከዚህም በተጨማሪም በሰኔ 24 የተፈጠረውን ክስተት የገመገሙ ሲሆን፣ ፑቲን የጦር አዛዦቹ የሰጡትን ገለጻ አድምጠዋል።-ስለየወደፊቱ ቅጥር እና ወደፊት በጦርነት ውስጥ ስለሚጠቀሙባቸው የተለዩ አቅጣጫዎችም አስተያየት ሰጥተዋል ብለዋል።-እንደ ቃል አቀባዩ ከሆነ ፕሪጎዢን ቅጥረኛው ቡድን ቫግነር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በታማኝነት እንደረዷቸው ለፑቲን ነግረዋቸዋል።-የቫግነር ቡድን የግል ቅጥረኛ ወታደሮች ያሉት ሠራዊት ሲሆን፣ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያካሄደችው ባለው ጦርነት ውስጥ ከአገሪቱ መደበኛ ሠራዊት ጎን ተሰልፎ ሲዋጋ ቆይቷል።-የቫግነር ቡድን አመጽን ተከትሎ የተፈጠረውን ወታደራዊ ፍጥጫ ለማብቃት የቤላሩሱ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ባደረጉት የሽምግልና ጥረት አመጹ መቋረጡ ይታወሳል።-በተደረሰው ስምምነት መሠረት ፕሪጎዢን ላይ የቀረበው የአገር ክህደት ክስ ተነስቶ ወደ ቤላሩስ እንዲሄድ እንደተፈቀደለት ተነግሮ ነበር።-ይህንንም ተከትሎ የቤላሩሱ ፕሬዝዳንት የቭጌኒ ፕሪጎዢን ከሩሲያ ወጥቶ ወደ አገራቸው መግባቱን ተናግረው ነበር።-ነገር ግን ፕሪጎዢን ያለበት ስፍራ ሳይታወቅ ከቆየ በኋላ የቤላሩሱ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ዛሬ ባለፈው ሳምንት ለጋዜጠኞች ፕሪጎዢን በአገራቸው ግዛት ውስጥ ሳይሆን እዚያው ሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ እንደሚገኝ ተናግረው ነበር።-ፕሪጎዢን የቡድኑን ተዋጊዎች በመጠቀም በሩሲያ ላይ አመጽ ባካሄደበት ወቅት፣ ዩክሬን ውስጥ የነበሩ ተዋጊዎቹን በማንቀሳቀስ በደቡባዊ ሩሲያ በምትገኝ ከተማ ውስጥ ያሉ አንዳንድ የደኅንነት ማዘዣ ማዕከላትን ተቆጣጥሮ ነበር።-ከዚያም በኋላ አማጺያኑ ወደ ዋና ከተማዋ ሞስኮ ማምራት በመጀመራቸው፣ የሩሲያ መንግሥት ሞስኮን ጨምሮ በበርካታ የአገሪቱ ግዛቶች ውስጥ የደኅንነት ጥበቃውን አጠናክሮ ነበር።-ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንም በወቅቱ ቡድኑን በአገር ክህደት የከሰሱት ቢሆንም፣ አመጹን ለማስቆም በተደረሰው ስምምነት ለቡድኑ መሪ ፕሪጎዢን የደኅንነት ዋስትና በመስጠት በቫግነር ቡድን ላይ የቀረበውን የወንጀል ክስ ውድቅ ተደርጓል።-የቡድኑ ተዋጊዎችም የሩሲያ ጦርን ለመቀላቀል ኮንትራት እንዲፈርሙ፣ ካልፈለጉ ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ወይም ወደ ቤላሩስ እንዲሄዱ አማራጭ ቀርቦላቸዋል።
የፎቶው ባለመብት Reuters-የአፍሪካ መሪዎች የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሐማስ በሰነዘረው ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት የተቀሰቀሰውን ግጭት እንዲያቆሙ ሁሉንም ተፋላሚ ወገኖች ጠይቀዋል።-የአገራቱ አቋም ግን ሙሉ ለሙሉ ተመሳሳይ አልነበረም።-ዛምቢያ፣ ኬንያ እና ጋና ሐማስን በግልጽ አውግዘዋል። እስራኤልን እንደሚደግፉም አስታውቀዋል። ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ደቡብ አፍሪካ ለፍልስጥኤማውያን ያላቸውን ድጋፍ በይፋ ገልጸዋል።-እስራኤል ባለፉት አስር ዓመታት በአህጉሪቱ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ አሳድጋለች። በርካታ የአፍሪካ አገራትም ኤምባሲዎቻቸውን ከቴል አቪቭ ወደ እየሩሳሌም ለማዛወር አቅደዋል። ይህ ግን እስራኤል በዚህ ግጭት ከአፍሪካ የምትጠብቀውን ድጋፍ ሙሉ በሙሉ አላስገኘላትም።-የአፍሪካ ህብረት በፈረንሳይኛ እና በእንግሊዘኛ መግለጫ አውጥቷል። የግጭቶቹ መነሻ "የፍልስጥኤም ህዝብ በተለይም ነፃ እና ሉዓላዊ መንግስት የመመስረት መሠረታዊ መብቶች መነፈግ" መሆኑን ገልጿል።-“ሊቀመንበሩ ሁለቱ ወገኖች ወታደራዊ ግጭቶችን እንዲያቆሙ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ድርድር ጠረጴዛው እንዲመለሱ ጠይቀዋል። የፍልስጥኤምን ህዝብ እና የእስራኤላውያንን ጥቅም ለማስጠበቅ የሁለት መንግስታትን መርህ ተግባራዊ እንዲደረግም በአስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል” ሲሉ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ አክለዋል።-እስራኤል ቀደም ሲል በአፍሪካ ህብረት ስብሰባዎች ላይ በታዛቢነት ለመሳተፍ የነበራት ፍላጎት በአንዳንድ አገራት ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል።-የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ተፋላሚ ወገኖች ወደ "ሁለት አገራት መፍትሔ" እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። በተከሰተው ግጭት ማዘናቸውን በመግለጫቸውም አስታውቀዋል።-የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሻሻል በሚደረገው ጥረትም ሙሴቬኒ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በአውሮፓውያኑ 2016 እና 2020 አቀባበል አድርገውላቸዋል። የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት እአአ በ2020 በእስራኤል እና በሱዳን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ሠርተዋል።-ድጋሚ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ግን የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፍልስጥኤማውያን ድጋፍ ሰጥተዋል።-"በአሁኑ ጊዜ በፍልስጥኤምእየተከሰተ ያለውን አደገኛ እና አሳሳቢ ሁኔታ ሱዳን በቅርበት እየተከታተለችው ነው። የፍልስጥኤም ህዝቦች ነፃ አገር እና ህጋዊ መብት እንዲኖራቸው ሱዳን ድጋፏን በድጋሚ ትገልጻለች። ዓለም አቀፍ የግጭት አፈታቶች እንዲተገበሩ እና ንፁሃን ዜጎችን ከጥቃት እንዲጠብቁ ትጠይቃለች" ሲል በመንግስታዊው የዜና ወኪል ሱና በፌስቡክ ገጹ መግለጫውን አስነብቧል።-ደቡብ አፍሪካ "አፋጣኝ የተኩስ አቁም" እንዲደረስ ጥሪ አቅርባለች።-የአገሪቱ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ቢሮ "ቀጠናው በተባበሩት መንግስታት የሁለት መንግሥታት መፍትሔ እና በእስራኤል እና በፍልስጥኤም መካከል ፍትሐዊ እና ሁሉን አቀፍ ሠላም እንዲሰፍን ቀደም ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች የሚተገብር የሠላም ሂደት ይፈልጋል" ሲል አስታውቋል።-ናይጄሪያ በበኩሏ “አሁን ያለው የተባባሰው የብጥብጥ እና የበቀል አዙሪት በህዝብ ላይ የማያቋርጥ የስቃይ አዙሪት እንዲኖር ያደርጋል” በማለት አስጠንቅቃለች።-የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ “የጉዳቱ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ተፋላሚዎቹ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።-"ኬንያ ለዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ከፍተኛ ስጋት ለሆነ ሽብርተኝነት ምንም አይነት ምክንያት ሊኖር እንደማይገባ አጥብቃ ታምናለች። ወንጀለኛው ማንም ይሁን ማን፤ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ሁሉም የሽብርተኝነት፣ የአመጽና የጽንፈኝነት ድርጊቶች አስጸያፊ፣ ህገወጥ እና ኢፍትሐዊ ነው" ሲሉ ኤክስ ላይ ጽፈዋል።-የዛምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስታንሊ ካኩቦ የሐማስን ጥቃት በማውገዝ እስራኤልን ደግፈዋል።-"በሚያሳዝን ሁኔታ ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት በሆነው እና በእስራኤል ላይ በቅርቡ የተፈጸመውን ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን። ሁሉንም ጥቃት እና የጥቃት ድርጊቶች በማያሻማ ሁኔታ እናወግዛለን። ዓለም አቀፍ ግጭቶችን ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን መከተል አስፈላጊ መሆኑንም አበክረን እናሳውቃለን" ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት pm office-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ-የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አገራቸው በኃይል እና በወረራ ማሳካት የምትፈልገው ነገር እንደሌለ በመግለጽ በአጎራባች አገራት ላይ ወረራ የመፈጸም ፍላጎት እንደሌላት ተናገሩ።-ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያ የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት ለአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ያደረጉት ንግግር በአካባቢው ውጥረትን እና ግጭትን ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሮ ቆይቷል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ116ኛው የኢትዮጵያ ሠራዊት ቀን ዛሬ ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶች በተከበረበት ጊዜ ነው ኢትዮጵያ በኃይል እና በወረራ ፍላጎቷን ማሳካት እንደማትሻ የተናገሩት።-የአገሪቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ ውይይት ያስፈልጋታል ስትል ወራራ ሊካሄድ ይችላል የሚል ስጋት ይደመጣል” በማለት አገራቸው የውይይት እንጂ የግጭት ፍላጎት እንደሌላት በሥነ ሥርኣቱ ላይ ተናግረዋል።-ጨምረውም “ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ለአገር መከላከያ ሠራዊት ማረጋገጥ የሚፈልገው፣ ኢትዮጵያ በኃይል እና በወረራ ማሳካት የምትፈልገው አንዳች ነገር የለም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።-ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር ለጋራ ጥቅም፣ ለጋራ ዕድገት፣ ለጋራ ብልፅግና፣ ሁሉም አሸናፊ በሚሆንበት መንገድ የጋራ ጥቅማችንን ለማስከበር እንደምትሠራ በመግለጽ፣ “በወንድሞቻችን ላይ ቃታ የማንስብ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ” ብለዋል።-የፎቶው ባለመብት BBC/Amensisa Ifa-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ባደረጉበት በ116ኛው የኢትዮጵያ ሠራዊት ቀን ላይ ከቀረቡት ወታደራዊ ትርኢቶች መካከል-ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲነሳ የነበረው የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጉዳይን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ እና በብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈ ስብሰባ የኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ጉዳይ ውይይት የሚያስፈልገው የሕልውና ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።-ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቋ ግን የባሕር በር የሌላት አገር የሆነችው ከ30 ዓመት በፊት ኤርትራ ነጻ መውጣቷን ተከትሎ ነው።-ከዚያ በኋላ አገሪቱ ለገቢ እና ለወጪ ንግዷ የትንሿን ጎረቤት አገር ጂቡቲን ወደብ በመጠቀም ላይ ትገኛለች።-“ቀይ ባሕር እና አባይ ኢትዮጵያን የሚበይኑ፣ ከኢትዮጵያ የተቆራኙ ለኢትዮጵያ ዕድገት እና ጥፋት መሠረት ናቸው” በማለት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ መሸሽ እንደማያስፈልግ ተናግረው ነበር።-ከቅርብ ወራት በፊት ለኢትዮጵያ የባሕር በር ስለማስገኘት በይፋ ሲባል ባይሰማም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣትን ተከትሎ አገሪቱ የፈረሰውን የባሕር ኃይሏን መልሳ ማቋቋሟ ይታወቃል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላነሱት የባሕር በር ጥያቄ ኤርትራ፣ ጂቡቲ እና ሶማሌላንድ አማራጮች ሊሆኑ እንደሚችሉ በመዘርዘር፣ ይህ የኢትዮጵያ ፍላጎት ሊሳካባቸው የሚችሉባቸው ያሏቸውን ከግጭት ውጪ ያሉ አማራጮችን አስረድተዋል።-ባለፉት ሳምንታት ዋነና መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግርን ተከትሎ ኤርትራ፣ ጂቡቲ እና ሶማሊያ በወደብ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ በኩል ስለተነሳውን ሃሳብ እንደማያውቁ መግለጻቸው ይታወቃል።-ይህ ለኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳብ ከረጅም ጊዜ ጠላትንት በኋላ ከኤርትራ ጋር የተሻሻለውን ግንኙነት ሊያበላሸው እንደሚችል እንዲሁም ከጂቡቲ እና ከሶማሊያ ጋርም ውጥረትን ያስከትል ይሆንል የሚል ስጋት ፈጥሮ ነበር።-የፎቶው ባለመብት BBC/Amensisa Ifa
የፎቶው ባለመብት GETTY IMAGES-መስከረም 26/2016 ዓ.ም ሐማስ እስራኤል ላይ ሊያደርስ ያቀደውን ጥቃት የአክስዮን ድርሻ ነጋዴዎች ቀድመው ያውቁ ነበር መባሉን በተመለከተ እስራኤል ምርመራ እንደምታካሂድ አስታውቃለች።-አንድ አካዳሚያዊ ጥናት የአክስዮን ድርሻ ነጋዴዎች በጥቃቱ ምክንያት የእስራኤል ኢኮኖሚ ሊያጋጥመው የሚችለው ሁኔታ ላይ “በመቆመር” ትልቅ ትርፍ አግኝተዋል ሲል አመልክቷል።-አጥኚዎቹ በጥቃቱ ጊዜ የአክስዮን ድርሻ ነጋዴዎች ‘ፈጣን ሽያጮችን’ ሲያከናውኑ እንደነበር ጠቅሰዋል።-‘ፈጣን ሽያጭ’ ነጋዴዎች ኪሳራ እንደሚያጋጥማቸው ቀድመው ከተረዱት የአክስዮን ድርሻቸውን፣ ቦንድ ወይም ሌላ የፋይናንስ አማራጭን ለገበያ በማቅርብ ገንዘብ ለማግኘት የሚሞክሩበት ዘዴ ነው።-ይህንንም የሚያደርጉት በዝቅተኛ ዋጋ ሲሆን፣ የገበያው ዋጋ መልሶ ከመረጋጋቱ በፊት መልሰው በርካሽ ዋጋ እንደሚገዙት ተስፋ በማድረግ ያከናውኑታል።-በኮሎምቢያ እና በኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙት አጥኚዎቹ “ጥቃቱ ከመፈጸሙ አንድ ቀን ቀድመው፣ የሚመጣውን ነገር አስቀድመው በመገመት የአክሲዮን ድርሻ ሽያጭ ሲከናወን ነበር” ብለዋል።-ጨምረውም ‘ፈጣን ሽያጩ’ ከዚህ ቀደም ከነበረው የፋይናንስ ቀውስ፣ በአውሮፓውያኑ 2014 ከነበረው የእስራኤል ጋዛ ጦርነት እና ከኮቪዲ 19 ወረርሽኝ ወቅቶች በላቀ ሁኔታ ሲከናወን ነበር ብለዋል።-በቴላ አቪቭ ‘የስቶክ ገበያ’ በአስገራሚ ሁኔታ የእስራኤል ተቋማት የድርሻ ሽያጭ ጨምሮ ታይቷል።-በሌላ በኩል አጥኚዎቹ የእስራኤል የገበያ ድርሻ ሽያጭን የሚከታተል አንድ ተቋም ያልተለመደ ከፍተኛ የሽያጭ እንቅስቃሴ መመልከቱን ገልጸዋል።-ጥናቱ የእስራኤል የአክስዮን ድርሻ ገበያ ጥቃቱ ከመፈጸሙ አምስት ቀናት አስቀድሞ “በድንገት እና በከፍተኛ መጠን መጨመሩን” የአሜሪካ የፋይናንስ ተቆጣጣሪ መረጃን ዋቢ አደርጎ ጠቅሷል።-“ጥቃቱ ከመጀመሩ ጥቂት ቀደም ብሎ በቴል አቪቭ የአክስዮን ገበያ የእስራኤል የአክስዮን ድርሻ ፈጣን ሽያጭ በአስገራሚ ሁኔታ ጨምሮ ነበር” ሲል ባለ 66 ገጹ ሪፖርት ጠቁሟል።-ይህንን ሪፖርት ተከትሎ የእስራኤል የአክስዮን ድርሻ ገበያ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በሰጠው መግለጫ ጉዳዩ እንደሚታወቅ ገልጾ የሚመለከታቸው አካላት ላይ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ጠቁሟል።-ጥናቱ ከፈረንጆቹ መስከረም 14 ጀምሮ ጥቃቱ ሊፈጸም ሁለት ቀን እስኪቀረው ድረስ የእስራኤል ትልቁ ባንክ 4.43 ሚሊዮን አዳዲስ ድርሻዎቹን ‘በፈጣኑ መሸጣቸውን’ አመልክቷል።-“የጥናታችን ግኝት የአክስዮን ድርሻ ነጋዴዎች ቀጥሎ ስለሚመጣው ጥቃት ቀድመው ተረድተው ከዚህ አሰቃቂ ሁነት አትርፈዋል” ካሉ፣ በዚህ አይነት ሁኔታ የአሜሪካ እና ኣለም አቀፍ ድርጅቶች ያላቸው የመረጃ ልውውጥ መቀነሱን ያሳያል ብለዋል።-መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሐማስ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ላለፉት ሁለት ወራት ጋዛ ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን፥ ይህም በእስራኤል እና በአካባቢው አገራት ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴ ላይ የራሱ የሆነ ተጽእኖ እንዳለው ይታመናል።