text
stringlengths
26
19k
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ-የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግንኙነት ከፕሪቶርያ ስምምነት በኋላ እንደ ቀድሞው አለመሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም ወደ አሥመራ በተጓዙበት ወቅት “ፕሬዝደንት ኢሳያስ. . . ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ክብርና ፍቅር አለው” ካሉ በኋላ፣ “ለኢትዮጵያ ልማትና ሰላም የሚጨነቅ፣ በሁለቱም አገራት ግንኙነት ብቻ ሳይሆ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ሐመር ዲመካ ገበያ-በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎት ውስጥ በተከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ በሶማሌ እና በደቡብ ክልል በሚገኙ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች እርዳታ እንደሚያስፍልጋቸው ባለሥልጣናት ተናገሩ።-በአሁኑ ወቅት በምሥራቅ አፍሪካ በሚገኙ አገራት ለተከታታይ ዓመታት ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመዝነቡ በተከሰተ ድርቅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለከፋ የረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል።-በኢትዮጵያም በድርቁ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የኢትዮጵያ መንግሥት ዛምቢያ ውስጥ መንገድ ዳር ተገኙ ስለተባሉት የኢትዮጵያውያን አስከሬኖች ጉዳይ ከአገሪቱ መንግሥት ጋር በመተባበር እንደሚያጣራ አስታወቀ።-ኢትዮጵያውያን ናቸው የተባሉት 27 አስከሬኖች እሁድ ዕለት ከዛምቢያ ዋና ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ መንገድ ዳር መገኘታቸውን በተመለከተ የወጣውን ዘገባ ተከትሎ ነው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምርመራ እንደሚያደረግ የገለጸው።-ለዚህም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይህንን በሕገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት እንዲቋቋም በተወሰነበት በፕሪቶሪያው ስምምነት ወቅት ዋነኛ ተደራዳሪ ነበሩ። አሁን ደግሞ ጊዜያዊ አስተዳደሩን እንዲመሩ በህወሓት ተመርጠዋል።-በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማስቆም በተደረሰው ስምምነት መሠረት በምርጫ ተካሂዶ መደበኛ አስተዳደር እስኪመሠረት የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት በሚያካሂዱት ፖለቲካዊ ውይይት ጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚቋ...
የፎቶው ባለመብት PM Office/Twitter-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሁለተኛውን ተርባይን ሥራ ሲያስጀምሩ-የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሥራ ወደ 83.3 በመቶ መድረሱን የግድቡ ግንባታ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ተናገሩ።-ሥራ አስኪያጁ ይህንን ያሉት የግድቡ ሁለተኛው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይን ኃይል የማመንጨት ሥራን ለማስጀመር በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው።-ግንባታው ከተጀመረ አስር ዓመታትን ያስቆጠረው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ አብዛኛው የግንባታ ሥራው ወደመጠናቀቁ የተቃረበ ሲሆ...
የፎቶው ባለመብት TIGRAY TV/FACEBOOK-ባለፉት ዓመታት በተካሄደው እና በቅርቡ በሰላም ስምምነት መቋጫ ባገኘው ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው የትግራይ ተዋጊዎች ያሉበት ሁኔታ እንዲስተካከል በመጠየቅ መቀለ ውስጥ አደባባይ መውጣታቸው ተዘገበ።-ከመቀለ ከተማው ዳርቻ ተነስተው ወደ መሃል ከተማዋ ያመሩት ሰልፈኞች ከክልሉ ባለሥልጣናት ጋር የተነጋገሩ ሲሆን የፀጥታ ኃይሎች ሰልፈኞች ለማስቆም አስለቃሽ ጋዝ መጠቀማቸውም ተዘግቧል።-የጦር ጉዳተኞቹ እንዲቆዩ በተደረገበት ማዕከል ውስጥ አስፈላጊውን የሕክምና ድጋ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የአፍሪካ ኅብረት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ንግግር እንዲያስጀምሩ ጠየቀ።-የኅብረቱ የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ረቡዕ ጥር 08/2016 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ነው ይህን ምክረ ሐሳብ ያቀረበው።-ከሁለት ሳምንት በፊት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የግዛቴ አካል ናት የምትላት ሶማሊላንድ የባሕር በር ለመስጠት እና በምላሹ እንደ አገር ዕውቅና ለማግኘት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ-የማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው የሊጉ መሪ የሆነውን አርሰናልን አሳማኝ በሆነ ጨዋታ እና ውጤት ካሸነፈ በኋላ አሁን ዋንጫው በእጃችን ነው አሉ።-ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው “ከማሸነፍ ውጪ ሌላ አማራጭ በማይኖርበት ወቅት" ማሸነፍ የሚችል ቡድን መሆኑን አረጋግጧል ብለዋል።-አርሰናል አሁንም የሊጉ መሪ ቢሆንም ሲቲ ሁለት ቀሪ ጨዋታ እያለው ከአርሰናል ያለው የነጥብ ልዩነት 2 ብቻ ነው።-ሲቲ ሁለቱን ቀሪ ጨዋታዎቹን ሲያሸንፍ ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆነው ለሌላ አገር ብሔራዊ ቡድን የሚጫወቱ እግር ኳስ ተጨዋቾች ብዙ አይደሉም።-አሊ አሕመድ ከኢትዮጵያ ቤተሰቦች ነው የተገኘው የ22 ዓመት ወጣት ሲሆን፣ በዜግነት ካናዳዊ ነው። ምናልባትም ለካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ ለመጫወት የመጀመሪያው ትውልደ ኢትዮጵያ ሊሆን ይችላል።-አሊ ለአራት ዓመታት ለቫንኩቨር ዋይት ካፕስ ቡድን የተጫወተ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት የካናዳ ተስፋ ያለው ምርጥ ወጣት ተጫዋች በሚል ተሸልሟል። ክለቡም ዋንጫ አንስቷል።-የአምስት ል...
የፎቶው ባለመብት eotc-የቤተክርስቲያኗ ሲኖዶስ አባላት በከፊል-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሪዎች ከሰሞኑ በተከሰተው ችግር ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር እንደተወያዩ ቤተክርስቲያኗ አስታወቀች።-ቤተክርስቲያኗ በዛሬው ዕለት የካቲት 03/2015 ዓ.ም ባወጣችው መግለጫ ከመንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ጥሪ ማቅረቧን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የእንወያይ ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጻለች።-ሲኖዶሱ ሐሙስ የካቲት 02/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የቤተክርስቲያኗን ሥርዓት...
የፎቶው ባለመብት EOTC-በኢትዮጵያ ነፍጥ አንስተው እየተዋጉ ያሉ በሙሉ የጦር መሳሪያቸውን አውርደው ለሰላም እና ዕርቅ ቅድሚያ እንዲሰጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጥሪ አቀረቡ።-ፓትርያርኩ የሰላም ጥሪውን ያቀረቡት በአማራ ክልል በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እየተካሄደ ባለበት ወቅት ዛሬ አርብ ነሐሴ 12/2015 ዓ.ም. ባስተላለፉት መልዕክት ነው።-“በአራቱም ማዕዘናት ነፍጥ ያነሳችሁ በሙሉ ያነገባችሁትን ገዳይ መሣርያ አውርዳችሁ ለሰላ...
የፎቶው ባለመብት REUTERS-ኪም ጆንግ ኡን-የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሩሲያን ድንበር አልፈው ገቡ።-ኪም ወደ ሩሲያ ያቀኑት ፑቲንን ለማግኘት ነው።-ሁለቱ መሪዎች በተለይ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ለከፈተችው ጦርነት የጦር መሣሪያ ከሰሜን ኮሪያ የምታገኝበትን መንገድ ይመክራሉ ተብሏል።-የሰሜን ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ማክሰኞ እንዳረጋገጠው ኪም የተሳፈሩበት የጦር ባቡር የሩሲያን ድንበር አልፎ ገብቷል።-ኪም አሁን የሩሲያን ድንበር አልፈው ወደ ወደብ ከተማዋ ቪላዲስቮስቶክ በማቅናት ላይ ናቸው።...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ወረርሽኝ አንገብጋቢ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አወጀ።-በድርጅቱ ምደባ መሠረት ይህ ውሳኔ ከወረርሽኞች አሳሳቢነት አንጻር ከፍተኛው ደረጃ ሲሆን፣ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በዓለም ዙሪያ እየጨመረ በመሄዱ ነው የሕዝብ ጤና ስጋት ተብሎ እንዲፈረጅ የተወሰነው።-ውሳኔው የተላላፈው የዓለም ጤና ድርጅት ከቀናት በፊት በቫይረሱ ዙሪያ ለሁለተኛ ጊዜ ማካሄድ በጀመረው የበሽታው የአስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴ ስብሰባ ማብቂያ ላይ ...
የፎቶው ባለመብት PRESS SERVICE OF "CONCORD"-የቫግነር ቅጥረኛ ቡድን ወታደራዊ አመፅ 24 ሰዓት እንኳ ሳይሞላው ተቀጭቷል። ነገር ግን ይህ አመፅ ለዓመታት በቅናት፣ በተቀናቃኝነት እና በዓላማ ሲብላላ የቆየ ነው።-የዚህ ድራማ መሪ ተዋንያን አንዱ የቅጥረኛው ቡድን ቫግነር አድራጊ ፈጣሪ የቭገኒ ፕሪጎዢን ነው።-የተቀሩት ደግሞ የግዙፉ የሩሲያ ጦር መሪ የሆኑት ሰርጌ ሾይጉ እና ቫለሪ ጌራሲሞቭ ናቸው።-ፕሪጎዢን በ1980ዎቹ በተደራጀ የወንጀል ድርጊት ተከሶ ዓመታትን ዘብጥያ አሳልፏል። ላካበተው ...
የፎቶው ባለመብት ASHRAF AMRA/ANADOLU AGENCY VIA GETTY IMAGES-የፍልስጥኤሙ ታጣቂ ቡድን ሐማስ ታይቶ የማይታወቅ የተባለለትን የተቀናጀ ጥቃት እስራኤል ላይ ሰንዝሯል። ተዋጊዎቹም በጋዛ ሰርጥ አቅራቢያ የሚገኙ ነዋሪዎችን ገድለዋል፣ አግተዋል።-ስለተሳታፊዎቹ እና ስለጥቃቱ ቦታዎች ማወቅ ያለብዎት ነገር ወሳኝ መረጃዎችን እንደሚከተለው አጠናቅረናል።-ሃማስ የጋዛን ሰርጥ የሚያስተዳድር የፍልስጥኤም እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ነው።-ሃማስ እስራኤልን ለማጥፋት ቃል የገባ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 20...
የፎቶው ባለመብት Juan Martinez-የአቤ/አብሄ ሐይቅ ደረቱን ለሰማይ ሰጥቶ፤ በኢትዮጵያ እና በጂቡቲ ድንበር መካከል ይገኛል።-ክችች ያለ መሬት እንጂ ለም ነገር በሥፍራው አይታይም፤ ልክ አልባው በረሃ ዐይን ማየት ከሚችለው ርቀት በላይ ተዘርግቷል።-የአቤ ሐይቅ [የአካባቢው ሰዎች አብሄ ይሉታል] ከዓለማችን ድንቅ ተፈጥሮዎች አንዱ ነው።-19 ኪሎ ሜትር ስፋት ይዞ፤ 17 ኪሎ ሜትር ረዝሞ የተዘረጋው ይህ ሐይቅ እጅግ ጨዋማ ስለሆነ ውሃው መርዛማ ነው።-በመቶዎች የሚቆጠሩ የላይምስቶን ክምሮች ዙሪያውን ተ...
የፎቶው ባለመብት GETTY IMAGES-በዌስት ባንክ ሰፋሪ የሆነ ታጣቂ እስራኤላዊ።-እስራኤል በኃይል በተያዘችው ዌስት ባንክ በፍልስጤማውያን ላይ ሁከት የሚፈጥሩ ጽንፈኛ እስራኤላውያን ላይ የቪዛ ማዕቀብ መጣሏን አሜሪካ አስታወቀች።-የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በፍልስጤማውያን ላይ ጥቃት በሚያደርሱ የእስራኤል ሰፋሪዎች ላይ ያነጣጠረ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል።-እገዳው በአመጽ በተከሰሱ ፍልስጤማውያን ላይም ተግባራዊ ይሆናል ሲሉ አክለዋል።-በጋዛ ሰርጥ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በዌስ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-በጎንደር በሚገኝ ካምፕ ውስጥ ምግብ እርዳታ ለማግኘት የተሰለፉ ኢትዮጵያዊያን-የመንግሥታቱ ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ እጅግ ድሃ በሆኑ አገራት የሚገኙ ነፍሰ ጡሮች ዘንድ ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መስተዋሉን ገለጸ።-ድርጅት እንዳለው በእነዚህ ድሃ አገራት ነፍሰ ጡር ሆነው በተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ያሉ ሴቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ ታይቷል።-ይህ ሪፖርት እንደሚያትተው ከድሃ አገሮች መካከል ለእናቶች ያለው ሁኔታ የከፋ የሆነው በአፍጋኒስታን፣...
የፎቶው ባለመብት UN-በማላዊ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ በርካታ የሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እንዳሉበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።-ድዛሌካ በተሰኘው የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ በወንዶች፣ በሴቶች እና በህፃናት ላይ መጠነ ሰፊ ብዝበዛ እንደሚደርስ ይፋ የተደረገው በተባበሩት መንግሥታት የመድኃኒት እና የወንጀል ፅህፈት ቤት (ዩኤንኦዲሲ) እና የማላዊ ፖሊስ ባደረጉት የጥምረት ክትትል ነው።-ተቋሙ ከ90 በላይ ሰለባዎችን መታደጉን ገልጾ፣ አብዛኛዎቹ ከ18-30 የ...
በትግራይ ክልል የሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ-በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ፤ በተለይ በትግራይ ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ የነበረው የባንክ አገልግሎት መጀመሩ ይታወሳል።-ሆኖም ሥራ ጀምረው የነበሩት ባንኮች በጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ሙሉ አግልገሎት እየሰጡ እንዳልሆነ የክልሉ ነዋሪዎች እና የባንክ ሠራተኞች ይገልጻሉ።-በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር በተያያዘ የፀጥታ ችግር ባለበት የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ-አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው በታላቁ የሕዳሴ ግግድብ ዙሪያ ለግብፅ የሚወግን አስተያየት አለመሰንዘራቸው የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ።-የሶማሊያ መንግሥት ይህን ያለው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ከግብፁ አቻቸው አብዱለ ፋታህ አል ሲሲ ጋር ካይሮ ውስጥ በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው ግድብ ዙሪያ ተነጋግረዋል መባሉን ተከትሎ ነው።-የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ...
የፎቶው ባለመብት SM-የአካባቢ ጥበቃና የሥነ ህይወት ሳይንቲስቱ ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሄር በ83 ዓመታቸው ትናንት መጋቢት11/2015 ዓ.ም ሌሊት ላይ ማረፋቸውን ከልጃቸው እንደሰማ በሳይንቲስቱ ህይወት ዙሪያ መጽሐፍ የጻፈው ዘነበ ወላ ለቢቢሲ ተናግሯል።-ህልፈታቸውን ከልጃቸው ሮማን ተወልደ ብርሃን እንደሰማ የተናገረው ደራሲው ዶክተር ተወልደ ብርሃን ለረጅም ጊዜ የቆየ ህመም እንደነበረባቸው ገልጿል።-የመንግሥታቱ ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ድረ ገጽ ያወጣው ግለ ታሪክ ዶ/ር ተወልደ ብርሃን የካ...
የፎቶው ባለመብት FDRE DEFENSE FORCE-ሱ-30 ጀት-የአገሪቱን ሠራዊት የውጊያ አቅም ይጨምራሉ የተባሉ ተዋጊ የጦር ጄት እና ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የኢትዮጵያ አየር ኃይል መረከቡን ይፋ ተደርጓል።-አየር ኃይሉ ማክሰኞ ጥር 7/2016 ዓ.ም. የተረከበው ሩሲያ ሰራሹ ሱሆይ ሱ-30 ጦር ጀት እና ቱርክ ሰራሹን ባይራክታር አኪንቺ የተባለ ዘመናዊ ሰው አልባ አውሮፕላን ነው።-በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጦር አውሮፕላኖቹ ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ እንዲሁም የምርቶቹ አቅራቢያዎች እነማን እንደሆ...
የፎቶው ባለመብት Tom Gardner-የ6 ዓመቱ ታዳጊ ከለገ ደንቢ ማዕድን ማውጫ አቅራቢያ ሲወለድ የቀኝ እርግ መዳፉ እና የግራ እግሩ ሦስት ጣቶቹ አጥንት የላቸውም።-በነዋሪዎች ላይ ከባድ የጤና ጉዳት እያስከተለ ነው ያለው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ማዕድን ማውጫ ስፍራ በአስቸኳይ እንዲዘጋ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂማን ራይትስ ዋች ጠየቀ።-ሚድሮክ በለገ ደንቢ የማዕድን ማውጫ ሰፍራ አካባቢ በሚኖሩ ሰዎች ላይ የማዕድን ማውጣት ሥራው ከፍተኛ የጤና ጉዳት ቢያደርስም፣ ኩባንያው ለዓመታት ምንም አይነት ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ማንቸስተር ሲቲ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ድል ለዘመናት ሲታወስ የሚከርም ነው።-ሲቲ ላለፉት ዓመታት ሲጠማቸው የነበረውን ዋንጫ በስተመጨረሻ አንስተዋል። ሶስት ዋንጫ በማፈስም ታሪክ ፅፈዋል።-ይህን ድል ያጣጣሙት የቡድኑ አባላትና አሠልጣኙ ሁሌም ሲዘከሩ ይኖራሉ።-የማንቸስተር ሲቲ ባላንጣ የሆኑት ማንቸስተር ዩናይትድ ተመሳሳይ ታሪክ በፈረንጆቹ 1998-99 የውድድር ዘመን አሳክተዋል።-ይህ ሲሆን በወቅቱ ሲቲ በእንግሊዝ እግር ኳስ ሶስተኛ ደረጃ ውድድር ላይ ተሳታፊ ነበሩ...
የፎቶው ባለመብት EOTC Broadcasting Service Agency--በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሰሞኑ ከተከሰተው ችግር ጋር ተያያይዞ ለየካቲት 05/2015 ዓ.ም. የተጠራው ሰልፍ ፍቃድ እንደሌለው የፀጥታ እና ደኅነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕገወጥ ነው ካለችው የጵጵስና ሹመት እና አዲስ ሲኖዶስ መመስረት ጋር ተያይዞ መንግሥት ጣልቃ በመግባት እንዲሁም ድጋፍ በመስጠት ወረራዎች፣ እስሮች፣ ማዋከቦች እና ግድያዎች ተፈጽመዋል በሚል ...
በሽረ የስደተኞች መጠለያ-በትግራይ እርዳታ ላልተገባ ዓላማ መዋሉን ተከትሎ እርዳታ በመቋረጡ ቢያንስ 1 ሺህ 400 ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን አንድ ባለሥልጣን ተናገሩ።-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዲሁም የአሜሪካ መንግሥት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ለትግራይ የሚያደርጉትን የምግብ እርዳታ ከአራት ወራት በፊት አቋርጠዋል።-የትግራይ ባለሥልጣናት ባደረጉት ምርመራ ወደ 500 የሚጠጉ ሰዎች በስርቆቱ ተሳትፈው መገኘታቸውን አንድ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል።...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የጁቬንቱስ አማካይ ፖል ፖግባ አበረታች መድኃኒት በመውሰድ ተጠርጥሮ ለጊዜው ከእግር ኳስ መታገዱ ተሰምቷል።-የጣሊያን ፀረ-አበረታች መድኃኒት ችሎት በአውሮፓውያኑ ነሐሴ 20 ጁቬንቱስ ዩዲኒዜን 3-0 ሲረታ ፖግባ ‘ቴስቴስትሮን’ ከፍ የሚያደርግ መድኃኒት ወስዷል ብሏል።-ፈረንሳዊው የ30 ዓመት አማካይ በዚህ ጨዋታ ባይሰለፍም ከግጥሚያው በኋኃ በነብስ ወከፍ ተመርጠው ከተመረመሩ ተጫዋቾች መካከል ነበር።-ፖግባ አበረታች መድኃኒት መውሰዱ ከተረጋገጠ ከሁለት እስከ አራት ዓመ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በአሜሪካ ውስጥ በሕጻናት ላይ የመጀመሪያ የሆኑ ሁለት በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ልጆች መገኘታቸውን የጤና ባለሥልጣናት አሰታወቁ።-በሽታው በአገሪቱ ውስጥ እየተስፋፋ ነው እየተባለ ባለበት በአሁኑ ወቅት በበሽታው የተያዙት ሁለቱ ሕጻናት የተገኙት ካሊፎርኒያ ውስጥ ነዋሪ በሆነ እና በሌላ በዋሽንግተን በኩል ሊያልፍ የነበረ የአገሪቱ ዜጋ ባልሆነ ልጅ ላይ ነው።-የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) እንዳለው ሁለቱ ሕጻናት በአሁኑ ጊዜ “በመልካም ጤንነት ላይ ናቸ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የቫግነር ቡድን መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን ከሩሲያ ሲወጡ-በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ላይ አመጽ አስነስተው ወደ ሞስኮ ሲገሰግሱ የነበሩት የቅጥረኛው ቫግነር ቡድን መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን የጦር እንቅስቃሴያቸውን ለማቆም ተስማምተው ከአገር ወጡ።-የቫግነር መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን ወደ ጎረቤት አገር ቤላሩስ ማቅናታቸው ነው የተገለጸው።-የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ የቫግነር መሪን እና ፑቲንን ካነጋገሩ በኋላ የቅጠረኛ ቡድን መሪው እና ወታደሮቻቸው ላይ ክስ እንደ...
የፎቶው ባለመብት PA MEDIA-አሜሪካ የአውሮፕላን ተሸካሚዎችን፣ የጦር መርከቦችን እና ጄቶች ወደ ምሥራቃዊ ሜዲትራኒያን ባህር እያስጠጋች መሆኑን ገለጠች።-ለእስራኤል ተጨማሪ መሳሪያዎችን እና ጥይቶችን እንደምትሰጥም አስታውቃለች።-አሜሪካ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ሐማስ በደቡብ እስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ሲሆን ፕሬዝዳንት ባይደን ጥቃቱን “ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅና አሰቃቂ” ሲሉ ጠርተውታል።-አሜሪካ ዜጎቿ ስለመገደላቸው እና በምርኮ ከተወሰዱት መካከል ስለመኖራቸውን ለማረጋገጥ እየሠራች...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ዶ/ር ጥሩሰው አሰፋ እና ዶ/ር ፍቃዱ ሞረዳ ይባላሉ። ሁለቱም ከፍተኛ የውሃ ሃብት ኢንጂነሮች ናቸው። ተቀማጭነታቸው በአሜሪካ ነው። ዶ/ር ጥሩሰው ከፍሎሪዳ፣ ዶ/ር ፍቃዱ ደግሞ ከኖርዝ ካሮላይና።-በአዲስ አበባ የውሃ እጥረት ዙርያ ጠለቅ ያለ ጥናት ሠሩ። የጥናታቸው ግኝት መልሶ ራሳቸውን አስደነገጣቸው።-ከተማዋ ክፉኛ እንደተጠማች ደረሱበት። እሱ አይደለም ይበልጥ ያሳሰባቸው።-አንድ መፍትሄ ካልተበጀ አዲስ አበባን እንኳንስ ዲፕሎማቱ፣ ነዋሪዎቿም የሚሸሿት ከተማ እንደምት...
የፎቶው ባለመብት SM-በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን፣ ወገል ጤና ከተማ አምቡላንስ ላይ በተፈፀመ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት አሽከርካሪውን እና አንድ የጤና ባለሙያን ጨምሮ በአቅራቢያው የነበሩ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ።-ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት አምቡላንሱ ከደሴ ከተማ መድኃኒት ጭኖ እየተመለሰ ሳለ ነበር ጥቃቱ የተፈፀመበት።-በዚህ ጥቃት አሽከርካሪው እና አንድ የመድኃኒት ባለሙያ (ፋርማሲስት) ሲገደሉ፣ የሆስፒታ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በርስ ጦርነት አንዴ ጋብ ሲል ሌላ ጊዜ ደግሞ የተፋፋመ ጦርነት እያስተናገደ ሁለት ዓመት ሊደፍን የጥቂት ቀናት ዕድሜ ነው የቀረው።-‘አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ’ ተብሎ በዙር የተከፋፈለው ጦርነት ለበርካቶች ሕይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል። እንደ ጦር ወንጀልና እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ መጠነ ሰፊ ጥሰቶች ተፈጽመውበታል።-መሰረተ ልማቶችን አውድሟል። የአገሪቱን መዋዕለ ንዋይ አሟጧል እንዲሁም የምጣኔ ኃብት ቀውስ አስከትሏል።-ምናልባት...
የፎቶው ባለመብት PROF JASON ARDAY-ያሰን አርዴ ልጅ ሳለ ኦቲስቲክ [የአእምሮ እድገት ውስንነት] እንዳለበት በሐኪም ተነግሮት ነበር።-እስከ 11 ዓመቱ መናገር አይችልም ነበር። 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ ደግሞ ማንበብም ሆነ መፃፍ አይችልም።-እነሆ አሁን በ37 ዓመቱ በዩናይትድ ኪንግደም ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ በዕድሜ ትንሹ ጥቁር ፕሮፌሰር ተብሏል።-ምንም እንኳ ልጅ እያለ መናገር ባይችልም ጥያቄ ከመጠየቅ አላገደውም።-“ለምንድነው ሰዎች ቤት አልባ የሚሆኑት? ጦርነት ለምን ይነሳል?” እያለ ይጠይቅ...
ከሦስት ዓመት በፊት በምሥራቅ ሸዋ አድአ ወረዳ ደንካካ ገበሬ ማኅበር የሚገኙ አርሶ አደሮች ማሳቸው ላይ አቮካዶ ተክለው የውጪ ምንዛሬ እንደሚያገኙ ሲናገራቸው ሁሉም በአንድ ልብ አልተቀበሉትም ነበር።-በማሳቸው ላይ ጤፍ እና ስንዴ የሚያበቅሉት ገበሬዎች እንደ አቮካዶ ያለ ቋሚ ተክል ተክሎ የውጪ ምንዛሬ ማለምን ፈጽሞ አስበውት አያውቁም።-ከዚህ ባሻገር ደግሞ አቮካዶ አምርተው ወደ ውጪ ለመላክ ብቻ ሳይሆን ለምግብነት እንኳ ተጠቅመውት አያውቁም።-የመንግሥት ተወካዮች ወደ ቀበሌያቸው መጥተው የአቮካዶ ችግኝ እ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሰሜን ኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት በዘላቂነት ለማስቆም የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት ከስምምነት ከደረሱ ከወራት በኋላም የኤርትራ ሠራዊት አባላት በመድፈር ወንጀል ክስ እየቀረበባቸው ነው።-የእርዳታ ድርጅት ሠራተኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎች የኤርትራ ጦር አባላት በጾታዊ ትንኮሳ ተግባራቸው ቀጥለዋል ብለዋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት እና የህወሓት ተወካዮች በፈገግታ ተሞልተው የሰላም ስምምነቱን በተፈራረሙበት ዕለት ምሽት፤ ለታይ በተሸሸገችበት ድልድይ ላይ ለሊቱን በሙ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ-የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ታይዋን ቢያቀኑ መዘዙ ከባድ ነው ስትል ቻይና አስጠነቀቀች።-አፈ ጉባኤዋ ታይዋንን ሊጉበኙ ነው የሚል መረጃ መውጣቱ ቻይናን እጅጉን አበሳጭቷል ተብሏል።-ለአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ መንበር ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ፔሎሲ፤ የራስ ገዝ ግዛት ወደሆነችው ታይዋን ጉዞ ቢያደርጉ ከእአአ 1997 ወዲህ ታይዋንን የጎበኙ ከፍተኛ ባለስልጣን ያደ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-አሜሪካ የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን እየፈጸሙት ያለውን “የጦር ወንጀል” እንዲያቆሙ የቻይናው ፕሬዚዳንት በቭላድሚር ፑቲን ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጠየቀች።-አሜሪካ ይህንን ያለችው የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ከጦርነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሞስኮ ማቅናታቸውን ተከትሎ ነው።-ፕሬዚዳንት ፑቲን እና አቻቸው ዢ ጂንፒንግ ዛሬ መጋቢት 12፣ 2015 ዓ.ም እንደገና ተገናኝተው ይወያያሉ።-የዋይት ሃውስ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃለ አቀባይ ለቻይናው ፕሬዚዳንት ባስተላለፉት ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ባይራክታር ቲቢ2 (Bayraktar TB2)-እንደ ዛሬው የአውሮፓ አገራት ዩክሬንን በከባድ የጦር መሣሪያ መደገፍ ከመጀመራቸው በፊት፣ ዩክሬን ራሷን ከሩሲያ ወረራ ለመከላከል በስፋት ትጠቀም የነበረው አንድ መሣሪያ ነበር።-ባይራክታር ቲቢ2 (Bayraktar TB2) ይባላል። ቱርክ ሠራሽ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ነው።-ይህ መሣሪያ የጠቀመው ዩክሬንን ብቻ አይደለም።-ከሁለት ዓመት በፊት አዘርባጃን የአርሜንያን ኃይሎች ድል ነስታ ግዛቷን ያስመለሰችው በዚህ ሰው አል...
ወ/ሮ መሠረት አዲስ-የወ/ሮ መሠረት አዲስ ድምጽ በጣም የደከመና የሚንቀጠቀጥ ነው። የ83 ዓመታቸው ሲሆን አብዛኛውን ጊዜያቸውን አልጋ ላይ ነው የሚያሳልፉት።-በአፍንጫቸው በኩል በገባላቸው ለመተንፈስ በሚረዳቸው ቱቦ በኩል ነው አየር ወደ ሰውነታቸው የሚያስገቡት።-“መሰቃየት አልፈለግም፤ መራብ አልፍለግም፤ እንዲበርደኝም አልፈልግም” ይላሉ ወ/ሮ መሠረት።-አዲስ አበባ ውስጥ በምትገኝ ትንሽዬ ቤታቸው ውስጥ ከሦስት የልጃቸው ልጆች ጋር ነው የሚኖሩት። ባሏ የሞተባለት ሴት ልጃቸው ልጆቿን ወ/ሮ መሠረት ላይ ጥ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ሰኞ ግንቦት 8/2023 (እአአ) ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ካሳደጉት እና ካሳደጋቸው ቤታቸው ለቀው ከወጡ አሥር ዓመት የደፈነበት ቀን።-እሳቸው ከኦልድ ትራፈርድ መለቀቃቸውን በይፋ ከማወጃቸው አንድ ቀድሞ ዜናው ወጣ።-ማንቸስተር ዩናይትድ የፈርጊን መልቀቅ ዜና በድብቅ ለመያዝ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም፤ ነገር ግን አልተሳካለትም።-እነሆ ክለቡ ከዝነኛው አሠልጣኝ ከተለያዩ አሥር ዓመት ቢሆነውም ከሕመሙ አላገገመም።-ስኮትላንዳዊው አሠልጣኝ አሁን በእንግሊዝ እግር ኳስ ታ...
የፎቶው ባለመብት MAHBERE KIDUSAN-ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አውግዛ የለየቻቸው ወገኖች በአብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እንዳይደርሱ እንዲሁም ንብረቶቿን እንዳይጠቀሙ የእግድ አቤቱታ ማቅረባቸውን ጠበቆቿ ለቢቢሲ ገለጹ።-ቤተክርስቲያኒቱን ከወከሉ ጠበቆች አንዱ የሆኑት አንዷለም በዕውቀቱ ገዳ እንደተናገሩት እግዱ የተጠየቀው ኤጲስ ቆጶሳቱን በሾሙት ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ጠበቃቸው እና ቃለ አቀባያቸው ኃይለሚካኤል ታደሰ ላይም ጭምር ነው።-ጠበቃው...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-“የደብረ ጽዮን ፎቶ ያለበትን መጽሄት አቃጠልን፣ የትግራይ ሰንደቅ አላማን አቃጠልን።”-“ድሮኖች 'ትራክ' እያደረጉ መኪኖችን እያጠቁ ነው ስለተባልን፤ የግል መኪኖች በተለይም ነጭ ቀለም ያላቸውን በጭቃ፣ በቀለም፣ በአፈር፣ ካርታሜ (የአስፓልት መስሪያ ሬንጅ) ቀብተን ከዕይታ ለመደበቅ ሞከርን።”-እነዚህ ንግግሮች የተሰሙት ከሁለት ዓመት በፊት መቀለ ከነበሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ነው።-የትግራይ ክልል መዲና መቀለ በፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ከመዋሏ በፊት።-ልክ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኤልዶሬት በተባለችው የኬንያ ግዛት 15 የተቀቀለ እንቁላል የዋጠው የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ መጨረሻ ሆስፒታል ሆኗል።-ማንቸስተር ዩናይትድ ያሸንፋል ብሎ የአርሰናል ደጋፊ ከሆኑ ጓደኞቹ ጋር ውርርድ የገባው ቶማስ ኪፑታኒ ኬምቦይ ዩናይትድ ከተሸነፈ 30 የተቀቀለ እንቁላል ለመብላት መወራረዱን የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ፅፈዋል።-ባለፈው እሑድ አርሰናል በኤሜሬትስ ስታድየም ማንቸስተር ዩናይትድ ሲያስተናግድ ነው ይህ የሆነው።-ዩናይትድ በጨዋታው 3-1 መረታቱን ተከትሎ አን...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ዋይት ሀውስ የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመቆጣጠር በሺዎች የሚቆጠሩ ክትባቶች በአሜሪካ ግዛቶች እንደሚያከፋፍል አስታወቀ።-ምርመራ የሚያካሂዱና ክትባቱን የሚወስዱ ሰዎች ቁጥር እንደሚጨምርም ተገልጿል።-ከዚህ ቀደም አፍሪካ ውስጥ በመሰራጨት የሚታወቀው ቫይረሱ በአሜሪካ እና በአውሮፓ በፍጥነት እየተሰራጨ ይገኛል።-በአሜሪካ እስካሁን 306 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የሞተ ሰው ግን የለም።-የአገሪቱ የጤና ባለሥልጣኖች እንዳሉት፣ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በይፋ ከተነገረውም በ...
የፎቶው ባለመብት Ephrem-ኤፍሬም ዩሴፍ እና ወንድሙ ፍፁም ዩሴፍ-በአሜሪካ የሚኖሩት ኤፍሬም እና ወንድሙ ፍፁም ዩሴፍ ተወልደው ያደጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።-እነዚህ ወንድማማቾች የኮሌጅ ትምህርታቸውን ኢኮኖሚክስ አጥንተው ሲያጠናቅቁ እና ቤተሰቦቻቸው ምግብ ቤት ሲከፍቱ ተገጣጠመ።-እነ ኤፍሬም በክብ እንጀራ ዙሪያ፣ ክብ ሰርቶ ተሰባስቦ ማዕድ መቋደስን ያደጉበት ነው።-ሠፌዱም፣ ምጣዱም፣ መሶቡም ክብ የሆነን እንጀራ ግን የወደፊት መተዳደሪያቸው ይሆናል ብለው አላሰቡም።-አዲስ ተመራቂዎቹ ወንድማማቾች በአሜሪ...
የፎቶው ባለመብት EPA-በሞስኮ ውጥረት ነግሷል። ከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊት እንቅስቃሴ ከዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ እየታየ ነው።-በአንጻሩ የቫግነር ቅጥር ገዳይ ቡድን በደቡብ ሮስቶቭ የመከላከያ ዋና መሥሪያ ቤትን ተቆጣጥሯል።-ፍጹም ያልተጠበቀ ነው የተባለው ይህ የቫግነር ከሩሲያ መከላከያ እዝ አፈንግጦ ማመጽ ብዙ እያነጋገረ ነው።-የቫግነር መሪ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትርና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ሩሲያን ክደዋል ሲል ይከሳል።-ይህን ውጥረት ተከትሎ ቪላድሚር ፑቲን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ለሕዝባቸው ንግግር አ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በአሜሪካዋ ግዛት አሪዞና ስር በሚገኝ አንድ አከባቢ የውሃ አገልግሎት መቋረጡን ተከትሎ ነዋሪዎች ጥቅም ላይ የዋለ የሻወር ውሃ እና መጸዳጃ ቤቶች የሚለቀቅ ውሃን በዝናብ ውሃ ለመተካት መገደዳቸው ተሰምቷል።-በአሜሪካዋ አሪዞና ግዛት ስር የምትገኘውና የስኮትዴል አጓራባች የሆነችው ሪዮ ቬርድ ከፈረንጆቹ ጥር 1 ጀምሮ የውሃ አቅርቦት ተቋርጦባታል።-ይህ አወዘጋቢ ውሳኔ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከውሃ አቅርቦት ውጪ ያደረገ ሲሆን ነዋሪዎች የውሃ አቅርቦትን መልሶ ለማግኘት...
የፎቶው ባለመብት BAHIR DAR COMMUNICATION-የአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር በከፊል-በአማራ ክልል ለወራት በቀጠለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም. ባወጣው ዝርዝር መግለጫ ይፋ አደረገ።-ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭቶች እየተካሄዱ ሲሆን፣ በክልሉ ውስጥ የአስቸ...
የፎቶው ባለመብት AFP-በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር ተስተካካይ የሆኑ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ተፈጽመዋል የሚሉ ሪፖርቶች ቀደም ብለው ሲወጡ ነበር።-ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተሳተፉት በሙሉ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ፈጽመዋል አለ።-አምነስቲ ትናንት በኬንያ መዲና ናይሮቢ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መከላከያ፣ የትግራይ ኃይሎች፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ ሚሊሻ ከባድ የመብ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ሳምንታት በቀረው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላማዊ ዜጎች ላይ መደፈር፣ ወሲባዊ ጥቃቶች፣ የዘፈቀደ ግድያ እና ረሃብ እንደ ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ መዋላቸውን አዲሱ የተመድ ሰብአዊ መብት ሪፖርት ይፋ አደረገ ።-19 ገጾች ያሉትና የመጀመሪያ ግኝት የሆነው ይህ ሪፖርት ይፋ የተደረገው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት፣ በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት የተፈጸሙ ጥሰቶች በሚያጣራው የሰብዓዊ መብቶች የባለሙያዎች ቡድን ነው።...
የፎቶው ባለመብት South Radio and Television Agency/ FB-የኦንጎታን ቋንቋ የሚናግሩት አምስቱ ሰዎች: ጉያኦ ቆራዮ፣ ጌዳ ቃውላና ኢዳ ቆራዮ [ከላይ - ከግራ ወደቀኝ] ጎምቦ ቃውላና ጎምቦ ቃሮ [ከታች ከግራ ወደቀኝ]-ወይጦ ወንዝ የብራይሌ ብሔረሰብ የኑሮ መሠረት ነው።-ብራይሌዎች ከወንዙ የሚያገኟቸው ዓሳዎች እና በዳርቻዎቹ የሚበቀሉት ፍሬዎች እና ስራስሮች ዋነኛ የምግብ ምንጫቸው “ነበር”።-ዛሬ አከባቢው ክፉኛ በድርቅ ተጎድቷል። ወይጦም ለመድረቅ ተቀርቧል። ምግብ ብርቅ ሆኗል።-ከብት ...
የፎቶው ባለመብት SRTV-ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ከሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ጋር-የሶማሊያው እስላማዊ ታጣቂ ቡድን አልሻባብ በሶማሌ ክልል ውስጥ የከፈተው ጥቃት የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች መክተው መመለሳቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ለቢቢሲ ተናገሩ።-አቶ ሙስጠፌ አልሻባብ በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመው ጥቃት አሁን ካለው ቀጠናዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ዝግጅቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ያሳየ ነው ሲሉ ተናግረዋል።-ርዕሰ መስተዳደሩ ከቢቢሲ ጋር የስልክ ቃለ ምልልስ ባደረጉበት ዛሬ ማክሰ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን-የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የእስር ትዕዛዝ አወጣ።-ፕሬዝዳንቱ ህጻናትን በሕገወጥ መንገድ ከዩክሬን ወደ ሩሲያ ማፈናቀልን ጨምሮ በጦር ወንጀሎች ተጠያቂ ናቸው ሲል ነው የእስር ትዕዛዙን ያወጣባቸው።-እነዚህ ወንጀሎች የተፈጸሙት ሩሲያ በዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ ከከፈተችበት ካለፈው ዓመት የካቲት አጋማሽ ጀምሮ መሆኑንም አሳውቋል።-ሩሲያ ግን በወረራው ወቅት ተፈጽመዋል የተባሉን የጦር ወን...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በሄግ ተቀማጭነቱን ያደረገው ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የእስር ትዕዛዝ አውጥቷል።-ሆኖም ይህ ገና ጅማሮ እንደሆነ እና በጣም የረዘመ ሂደትም እንደሚኖረው ተነግሯል።-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሩሲያ መሪን በዩክሬን ወረራ ምክንያት የጦር ወንጀል ለመክሰስ በቂ ማስረጃ እንዳለው በግልፅ ያምናል።-ይሁን እንጂ የዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት አንድ ፕሬዝዳንትን ፍርድ ቤት ለማቆም ፈታኝ ሥራ ነው የሚሆንበት።-በአሁኑ ጊዜ ፕሬዝዳ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል እና የወሊድ ምጣኔ መቀነስ ለበርካታ አገራት አሳሳቢ ሆኗል።-አዲስ የሚተካ ትውልድ ቁጥር እየተመናመነ ነው። በአንዳንድ አገራት አረጋውያን ጧሪ አጥተው ፊታቸውን ወደ ሮቦቶች እስከ መዘርጋት ደርሰዋል።-ትኩስ የሠራተኛ ኃይል እጥረትም አጋጥሟቸዋል።-ይህም በምጣኔ ሃብታቸው ላይ ተፅዕኖ እያደረሰ እንደሆነ ጥናቶች እያመለከቱ ነው።-ይህንን ስጋት ለመቀልበስ ታዲያ “እባካችሁ ውለዱ!” የሚል ተማፅኖን ጨምሮ ሌሎች የማበረታቻ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ማንቸስተር ሲቲዎች መድፈኞቹን ከሊጉ አናት አውርደው የዘንድሮው ፕሪሚዬር ሊግ የዋንጫ ባለድል ሆነዋል።-አብዛኛውን የውድድር ዘመን ከሚኬል አርቴታ ቡድን ኋላ ሆነው የከረሙት ሲቲዎች በመጨረሻው ወር ዋንጫውን ማንሳት ችለዋል።-በርካታ ክስተቶች በታዩበት የዘንድሮው ፕሪሚዬር ሊግ የዋንጫውን ዕጣ ፈንታ የወሰኑ 10 ክስተቶችን እንመልከት።-አሁን ስናስበው ከዘመናት በፊት የሆነ ይመስላል። የውድድር ዘመኑ ሊጀምር አካባቢ በኮሚዩኒቲ ሺልድ ግጥሚያ ኧርሊንግ ሃላንድ ጎል ማግባት...
የፎቶው ባለመብት EOTC-የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አባ ጴጥሮስ-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእምነት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብበሳ አድርጎ ባወጣው መግለጫ አመለከተ።-በዚህም የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በወሰዷቸው እርምጃዎች በቤተክርስቲያኗ አባላት ላይ የሕይወት እና የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።-ቅዱስ ሲኖዶሱ በመግለጫው በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የቤተክርስቲያኒቱን...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ትግራይ ሰላም ከራቃት ድፍን ሁለት ዓመታት ተቆጠሩ።-ለሁለት ዓመት በዘለቀው ደም አፋሳሽ ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደ ቅጠል ረግፈዋል፣ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል፣ ለህሊና የሚከብዱ ፣ ለሰሚው የሚሰቀጥጡ ጭካኔዎች ተፈጽመዋል።-በፌዴራሉ መንግሥት እና በትግራይ ሃይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ክልሏን ጨለማ ውስጥ ከቷታል።-ትግራይ ከመሰረታዊ አገልግሎቶች ጋር ተቆራርጣለች።-በክልሉ ሰላም ብቻ ሳይሆን ለዕለተ’ለት ኑሮ ወሳኝ የሆኑ አገልግሎቶች የሉም።-ትምህር...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የ2023/24 የቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ድልድል ይፋ የሆነ ሲሆን ጨዋታውም ከሁለት ሳምንታት ገደማ በኋላ ይጀምራል።-በእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰፍራ ስለሚሰጠው ውድድር ምን ያህል ያውቃሉ?-በእነዚህ ጥያቄዎች እራስዎን ይፈትኑ።
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው የተገኘ ሲሆን፣ አገሪቱ ከሞሮኮ በመቀጠል በአፍሪካ ወረርሽኙ የተገኘባት አገር ሆናለች።-በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከዚህ በፊት በሽታው መከሰቱን በተመለተ ሪፖርት አልተደረገም።-የአገሪቱ የተላላፊ በሽታዎች መቆጣጠሪያ ተቋም በጉተንግ አውረጃ የሚኖር የሰላሳ ዓመት ሰው ላይ በሽታው መገኘቱን ገልጿል።-ሰውዬው ከሌሎች ሰዎች ጋር የነበረው ንክኪ እየተጠና ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ሌሎች አገራት አለመጋዙም ተረጋግጧ...
የፎቶው ባለመብት nebe/fb-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ-ለሁለት ዓመት የተደረገውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ተከትሎ በፕሪቶሪያ ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት ተፈርሟል። በዚህም ስምምነት መሠረት ትግራይ ለብቻዋ አድርጋው የነበረው ምርጫ ፉርሽ እንዲሆን እና የተመሠረተው መንግሥትም እንዲፈርስ ሆኗል።-በአሁኑ ወቅት ክልሉ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ እና የተለያዩ ፖርቲዎች ጥምረት የሆነው ጊዜያዊ መንግሥት እያስተዳደረው ይገኛል።-የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለሚቋቋመው ጊ...
የፎቶው ባለመብት AFP-ምክትል ፕሬዝዳንቱ ቴዎዶሮ ኦቢያንፍ ንጉዌማ-የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ልጅ የሆኑት ሩልሳን ኦቢያንግ ኑሴ የመንግሥት አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ሸጠዋል ተብለው በመከሰሳቸው ታሰሩ።-እንዲታሰሩ ትዕዛዙን የሰጡት የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የታሰሩት ግለሰብ ወንድም ናቸው።-የታሰሩት የምክትል ፕሬዝዳንቱ ወንድም እንዲሁም ምክትል ፕሬዝዳንቱም የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ንጉዌማ ኦቢያንግ ማንጉዬ ልጆች ናቸው።-የታሰሩት የፕሬዝዳንቱ ልጅ የቀድሞው የሴቢያ ዓለም አ...
የፎቶው ባለመብት DEBREMARKOS CITY COM.-ደብረ ማርቆስ-በአማራ ክልል፣ ደብረ ማርቆስ ከተማ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በተከሰተ ግጭት ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ።-በአማራ ክልል ካሉ ትላልቅ ከተሞች አንዷ በሆነችው የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረ ማርቆስ ሐሙስ ጥቅምት 08/2016 ዓ.ም. በተከሰተው የተኩስ ልውውጥ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።-በከተማዋ ነዋሪ የሆኑት እነዚህ ግለሰቦች ለቢቢሲ እንደተናገሩት በመከላከያ ኃይል እና በፋኖ ታጣ...
በጋምቤላ ክልል የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 185 ሺህ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።-የክልሉ መዲናን ጨምሮ 12 ወረዳዎች ላይ ከሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ ባለው ወቅት ከባድ ዝናብ መዝነቡን የተመድ ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) አስታውቋል።-በዚህም 185 ሺህ 200 ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ያስተወቀው ተቋሙ በፈታኝ ሁኔታም ውስጥ ይገኛሉ ብሏል።-በአሁኑ ወቅት በተጨናነቀ ሁኔታ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት ላይ ተጠልለው እንዲሁም...
የፎቶው ባለመብት Reuters-በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጠበቃ ነኝ በማለት በርካታ ክሶችን ተከራክሮ የረታው ግለሰብ በባለሥልጣናት በቁጥጥር ስር ዋለ።-ግለሰቡን በተመለከተ የሚወጡ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት “ጠበቃው” ከመታሰሩ በፊት ከከፍተኛው ፍርድ ቤት ጀምሮ አስከ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ድረስ 26 ጉዳዮችን ይዞ በመከራከር ለመርታት ችሏል።-ግለሰቡ ሊያዝ የቻለው ለኬንያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ተገቢው ትምህርት እና ብቃት ሳይኖረው በማስመሰል በዘርፉ በመሰማራቱ ከተለያ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images/Kaari/ Michigan University/UN-የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ያቋቋመው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ፈቃድ አገኘ።-የፈረንሳዩ ዜና ወኪል (ኤኤፍፒ) እንደ ዘገበው ኮሚሽኑ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ከኢትዮጵያ መንግሥት ፈቃድ አግኝቷል።-የኮሚሽኑ መርማሪዎች ወደ ክልሎች መንቀሳቀስ እንዲችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ፈቃድ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን የዜና ወኪሉ ዘገባ ያመለክታል።...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች [ድሮኖች] የዩክሬን ሰማይ ላይ ይከንፋሉ።-እነዚህ ድሮኖች የተለያየ ተልዕኮ አላቸው።-አንዳንዶቹ የጠላትን መገኛ እና ይዞታዎችን ይለያሉ። ወታደራዊ ግብዓቶችን ከሚጓጉዙት በተጨማሪ በጠላት ኃይል ላይ ሚሳኤል ለመተኮስ ጥቅም ላይ የሚውሉም አሉ።-በዚህ ጦርነት ተሳታፊ የሆኑት ሁለቱም ወገኖች፤ ለወታደራዊ ዓላማ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እየተጠቀሙ ነው።-የዩክሬን ጦር በዋነኛነት የታጠቀው ቱርክ ሠራሹን ባይ...
ጠ/ሚ ዐቢይ፣ ፕ/ት ኢሳያስ፣ ፕ/ት ኪር፣ ጄ/ል አል ቡርሓን፣ ፕ/ት ሐሰን እና ፕ/ት ጊሌ-ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያን ያካተተው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በአህጉሪቱ ውስጥ እንዲሁም በዓለም ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ ወሳኝ ሚና ያለው ስፍራ ነው።-የአፍሪካ ቀንድ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከባሕረ ሰላጤው አገራት ነዳጅ እና ከእስያ ደግሞ ወሳኝ የኢንዱስትሪ ምርቶች ሰፊ ተጠቃሚ ወዳለባቸው የአውሮፓ እንዲሁም የአሜሪካ አህጉር የሚተላለፍበት ቁልፉ የቀይ ባሕር መ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በሩሲያ አቻቸው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላወጣው የእስር ማዘዣ ድጋፋቸውን ሰጡ።-ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ፑቲንን በዩክሬን የጦር ወንጀል በመፈጸም የከሰሳቸው ሲሆን ፕሬዚዳንት ባይደንም የሩሲያው መሪ “በግልጽ” ፈጽመውታል ብለዋል።-ሩሲያ በዩክሬን ወረራ ከፈጸመች በኋላ ሕጻናትን ከዩክሬን ወደ ሩሲያ በህገወጥ መንገድ አፈናቅላለች የሚልም ክስ ቀርቦባታል።-ሞስኮ ይህንን ውንጀላ ውድቅ አድርጋ የእስር ት...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ሼኽ ጃሲም ቢን ሃማድ አል ታኒ የእንግሊዙን ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ ለመግዛት የተሻሻለ ገንዘብ አቅርበዋል።-ምንጮች ለቢቢሲ ስፖርት እንደገለጡት የካታሩ ቱጃር ማክሰኞ ዕለት ሬይን ግሩፕ ለተሰኘው ድርጅት አዲስ ጨረታ አቅርበዋል።-የኦልድ ትራፈርዱን ክለብ ለመግዛት የካታሩ ባንከር እና ኢኔዎስ ግሩፕ የተሰኘው ድርጅት ባለቤት የሆኑት ጌታ ጂም ራትክሊፍ እየተፎካከሩ ይገኛሉ።-ሁለቱም ባለሃብቶች ባለፈው የፈረንጆቹ ወር መጨረሻ ለሦስተኛ ጊዜ የጨረታ ዋጋቸውን አሻሽለው ቀ...
የፎቶው ባለመብት atakhelti dejene-መቀለ በምሽት--መሠረት ሓድሽ ከቀናት በፊት ሞባይሏ መልዕክት እንደደረሳት የሚጠቁም ድምጽ አሰማት - አንድ አርቲስት ባልደረባዋ ነበር።-“ትናንት እኔም እንደአንቺ ተመሳሳይ ነገር ደረሰብኝ፤ ልዩ ኃይል ነን ያሉ ታጣቂዎች ጨለም ወዳለ ቦታ ወስደው ያለኝን ነገር በመዝረፍ ቀጥቅጠው አሰናበቱን” የሚል መልዕክት እንደላከላት ታስታውሳለች።-ይህም የራሷን አጋጣሚ አስታወሳት።-ሰኞ ጥር 22/2015 ዓ.ም. ከሥራ ወጥታ ወደ ቤቷ እየተመለሰች ሳለ መቀለ ሐውዜን አደባባይ ...
የኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ህይወትን የቀጠፈ ሲሆን ሌሎች ሚሊዮኖች ደግሞ ለችግርና ለረሃብ ተጋልጠዋል።-በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ሲሆን የአቅርቦት እጥረት የጤና ስርዓቱን ለውድቀት ዳርገውታል።-የትግራይ ክልል ለሁለት ዓመት ያህል ከአለም ተቆራርጣ የምትገኝ ሲሆን በከበባም ውስጥ ነው ያለችው።-የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እገዳ ጥለዋል የሚለውን የማይቀበሉት ሲሆን ህወሃትንም ሲከሱ ይሰማሉ።-ይህየምርመራ ዘገባ እንደሚያሳየው በትግራይ ያለው ከበባ...
የፎቶው ባለመብት AFP-ለ23 ወራት ያህል የርስ በርስ ጦርነት ማዕከል በሆነችውና እገዳ ላይ ባለችው ትግራይ መሰረታዊ የመድኃኒት እጥረት ህሙማንን እየገደለ ነው።-ሁለቱም ወገኖች ደቡብ አፍሪካ ሊደረግ ታቅዶ ለነበረው የሰላም ውይይት ተስማምተናል ባሉበት በዚህ ወቅት አንድ ዶክተር ሰብዓዊ ቀውሱ እልባት እንዲሰጠው እየተማጸኑ ነው።-ዶክተር ፋሲካ አምደስላሴ የሚናገሩት ጉዳይ መሬት ላይ ያሉትን ተጨባጭ እውነታዎች ቢሆንም ሁኔታውን ሲናገሩ በጣም አሳዛኝ ነው።-“የሰመመን መስጫ መድኃኒት፣ በደም ስር የሚሰጡ ፈ...
ጦርነት ከመጀመሩ በፊት እና ከተጀመረ በኋላ የመቀለ ከተማ የምሽት ገጽታ።-በምሽት ከሕዋ ላይ የተነሱ አዳዲስ ምሥሎች በጦርነት ቀጠና ያለችው የትግራይ ክልል ሕዝብ፣ በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉ ሰብአዊ ቀውሶች አስከፊውን እየተጋፈጠ መሆኑን አሳይተዋል።-በክልሉ የመብራት አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ከተሞች በ20 ወራት ውስጥ እየደበዘዙና እየጨለሙ እንደመጡም የናሳ ሳተላይት ምሥሎች ማሳያ ናቸው።-የናሳ ሳተላይት ምሥሎች ለቢቢሲ የተጋሩት ከጎረቤት ኤርትራ ሠራዊት ጋር በመሆን ከትግራይ ጦር ጋር እየተዋጋ ያለው የኢ...
የፎቶው ባለመብት SAMUEL GIZAW-ሳሙኤል ግዛው በሙያ አስተዋጽዖ ለማበርከት ያለውን ፍላጎት ለማሟላት አንድ የሥራ ሃሳብ መጣለት።-አርሱም ቦምብ ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ጎማ ተራ እና ሚሊተሪ ተራ የመሳሰሉትን መርካቶ መሃል ያሉ የገበያ ቦታ ስያሜ ላይ በመመርኮዝ የመገበያያ መተግበሪያውን 'ልክተራ'ን የመጀመር።-ሳሙኤል ልክተራን የጀመረው ወላጆች ለልጆቻቸው የሚፈልጓቸውን ትምህርታዊ መጽሐፍት በቀላሉ እንዲያገኙ ለማድረግ በማሰብ ነው።-የበይነ መረብ አገልግሎት በኢትዮጵያ አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳን የጀመረው ሥራ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ታዋቂዎቹ የዌልስ የሴት እና የወንድ ብሔራዊ ቡድን አባላት (ጄስ ፊሽሎክ፣ አሮን ራምሴይ፣ ሶፊ ኢንግል እና ብሬናን ጆንሰን)-የዌልስ የወንድ እና የሴት ዋና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች አገራቸውን ወክለው በሚጫወቱበት ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመሳሳይ ክፍያ ሊሰጣቸው ነው።-የዌልስ የእግር ኳስ ማኅበር በክፍያው ላይ ከስምምነት መድረሱን እና ለሁለቱም ጾታዎች የአገሪቱ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አባላት ክፍያው ወዲያው ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል።-የሴቶቹ ተጫዋቾች ክፍያ ከወንዶ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ደገም፣ ኩዩ፣ ያያ ጉለሌ፣ ሂደቡ አቦቴ፣ ወረ ጃርሶ እና ደራ ወረዳዎች ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱባቸው ሲሆኑ በተለያየ ጊዜ ሰዎች እየታገቱ ገንዘብ አንዲከፍሉ ይጠየቃሉ።-ይህ ጉዳይ በእነዚህ ወረዳዎች በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለ እና ከሁለት ዓመት በላይ ያስቆጠረ ነዋሪዎችን ያሳሰበ ጉዳይ ነው።-አቶ ደቻሳ*፣ ስማቸው ለደኅነንታቸው ሲባል የተቀየረ፣ አንድ ሌሊት ከቤታቸው በታጣቂዎች ተወስደው መታገታቸውን ይናገራሉ።-በታጣቂዎች ታግተው በቆዩባቸው አ...
የፎቶው ባለመብት Gambella Press Secretariat Office-በጋምቤላ ከተማ ታጣቂ ቡድኖች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን በክልሉ የተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ።-የክልሉ መስተዳደር የኦነግ-ሸኔ እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች ናቸው ያላቸው ኃይሎች ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም. ማለዳ ላይ በዋና ከተማዋ ውስጥ ጥቃት ከፍተው ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር መካሄዱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።-ስማቸው እንዲጠ...
የፎቶው ባለመብት GETTY IMAGES-የአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የነበሩት ቦብ ሜኔንዴዝ በግብፅ ወኪልነት አዲስ ክስ ቀረበባቸው።-አንጋፋው የምክር ቤት አባል ቦብ ሜኔንዴዝ ከዚህ ቀደም የግብፅ መንግሥትን ለመደገፍ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዶላር ጉቦ ተቀብለዋል በሚል የሙስና ክስ ተከፍቶባቸዋል።-ሜኔንዴዝ እና ባለቤታቸው ናዲን የግብፅ መንግሥትን የረዱ “የአሜሪካ መንግሥት ምሥጢራራዊ መረጃ” አሳልፎ በመስጠት ነው ክስ የተመሠረተባቸው።-ጥንዶቹ ከሳምንታት በፊት በ...
(ከላይ ከግራ ወደ ቀኝ) መርዋ ኢሳ፣ ሞሐመድ ዳይፍ፣ አብዱላህ ባርጉቲ፣ (ከታች ከግራ ወደ ቀኝ ) ያህያ ሲንዋር፣ ኢስማኤል ሃኒያህ እና ማህሙድ ዛሃር-ሐማስ “የአል-አቅሳ ጎርፍ” ብሎ በሰየመው ዘመቻ ድንገተኛውን እና ታይቶ የማይታወቀውን የተቀናጀ ጥቃት ቅዳሜ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ ከፈጸመ ለኋላ በርካቶች የቡድኑ መሪዎች እነማን ናቸው? የሚል ጥያቄን እያነሱ ነው።-ጋዛን የሚያስተዳድረው የሐማስ አብዛኞቹ መሪዎች በመገናኛ ብዙኃን ሲቀርቡ ፊታቸውን በጭንብል ሸፍነው ሲሆን፣ ኑሯቸውን...
የፎቶው ባለመብት DR HABTAMU GEBEYEHU-ትውልድ እና እድገቱ ሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር ከተማ ነው።-ኦሮምኛ ሲናገር ለሰማው ግን ዕድገቱ በኦሮሞ ማኅብረሰብ ውስጥ ሊመስለው ይችላል።-የ30 ዓመቱ ዶ/ር ሃብታሙ ገበየሁ ኦሮምኛ ቋንቋ አንድ ብሎ መማር የጀመረው ግን ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር።-አሁን ላይ ቋንቋውን አቀላጥፎ ከመናገሩ ባሻገር ቋንቋውን ለመማር የሚያግዝ የኦሮምኛ ቋንቋ ሰዋሰው መጽሐፍ ማዘጋጀት ችሏል።-በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ የጤና ተቋም ውስጥ በጤና ባለሙያነት እያገለገለ የሚገኘው ...
የፎቶው ባለመብት city addis ababa-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በከተማዋ ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ኦሮምኛ ቋንቋ ከአማርኛ ጋር እንደ ሁለተኛ ቋንቋ እንዲሰጥ ውሳኔ አሳለፈ።-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከብዝሃ ቋንቋ ሥርዓተ ትምህርት ጋር በተያያዘ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማርኛ ለሆኑ ተማሪዎች፣ ኦሮምኛ እንደ ተጨማሪ ሁለተኛ ቋንቋ እንዲሰጥ ሲል ውሳኔ አሳለፏል።-የከተማ አስተዳደሩ ዛሬ ሐሙስ ጥር 04/2015 ዓ.ም. ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት፣ በከተ...
የአፍሪካ ቀንድ መሪዎች በአንድ ቀን የተለያዩ ጉብኝቶችን አድርዋል። ሰኞ መጋቢት 04/2015 ዓ.ም. ዋነኞቹ የአፍሪካ ቀንድ አገራት መሪዎች በተለያዩ ከተሞች ተገናኝተው መክረዋል።-የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ደቡብ ሱዳን አምርተው ከፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና ከምክትላቸው ሬክ ማቻር ጋር ተወያይተዋል።-የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደግሞ በተመሳሳይ ዕለት የሱዳን ሽግግር ምክር ቤት ም/ፕሬዝዳንት ሌ/ጄኔራል ሃምዳን ዳጋሎን እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድን በአሥመራ...
የፎቶው ባለመብት AFP-በአንድ አገር ቀውስ ሲያጋጥም ስደተኞችን ወይም የሕዝብ ቁጥራቸው አናሳ የሆኑ ማኅበረሰቦችን ተጠያቂ ማድረግ የተለመደ ነው።-ይሄ በተለይም በልወደድ ባይ ፖለቲከኞች ወይም በምርጫ ለማሸነፍ በሚሞክሩ አምባገነን መንግሥታትም ተግባራዊ ሲደረግም ይታያል።-የቱኒዝያው ፕሬዝዳንት ካይስ ሰኢድ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት የመጡ ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ ንግግር ማድረጋቸውም ከዚህ ጋር የተያያዘ ይመስላል።-ፕሬዝዳንቱ በዋነኝነት አረብ እና ሙስሊም የሆነችውን የሰሜን አፍሪካዋን አገራቸውን...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመጪው 30 ዓመታት የዓለምን ግማሽ የሕዝብ ቁጥር ይይዛሉ ያላቸውን ስምንት አገራት ይፋ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኮንጎ፣ ናይጄሪያ እና ታንዛኒያ ከአፍሪካ አገራት በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል።-እንዲሁም በሚቀጥለው ዓመት ቻይናን በመብለጥ በዓለም ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት አገር የምትሆነው ሕንድ እንዲሁም ፓኪስታን ከስምንቱ አገራት መካከል ናቸው።-ሕንድ 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ በመያዝ ነው በሕዝብ ብዛቷ ለዓመታት የዓለም ቁንጮ ሆና የቆየችው...
የፎቶው ባለመብት HTTPS://HR.USEMBASSY.GOV/-የአውሮፓውያኑ 2023 የዲቪ ሎተሪ ደርሷቸው ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት የጉዞ ሂደት የዘገየባቸው ኢትዮጵያውያን ዕድለኞች ስጋት ላይ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገለፁ።-ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር 2700 ኢትዮጵያውያን የ2023 የዲቪ ሎተሪ ዕድለኞች ሆነው መመረጣቸው ተነግሯቸው ነበር።-የዚሁ የዲቪ ሎተሪ ዕድለኞች የሆኑ ሰዎችም በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በኩል የተለያዩ መስፈርቶችን ካሟሉ በኋላ ቪዛ በማግኘት ወደ አሜሪካ ያቀናሉ።-ይህንን የዲቪ...
የፎቶው ባለመብት DT-አቶ ማቴዎስ ገብረሕይወት በመቀለ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበረ ሲሆን፣ በሚያገኘው ደመወዝ ቤተሰቡን ይደግፍ ነበር።-ሆኖም ላለፉት 19 ወራት ምንም ዓይነት ገቢ አልነበረውም። “በጓደኞቻችን እና በወንድሞቻችን እርዳታ ይህን ክፉ ጊዜ አሳልፈናል” ሲል ስላለበት ሁኔታ ለቢቢሲ ተናግሯል።-ለሁለት ዓመታት የቆየው አውዳሚው ጦርነት እና እሱን ተከትሎ በፌዴራል መንግሥት በተጣለው እገዳ ምክንያት በክልሉ ሁሉም መሠረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጦ ቆይቷል።-ጦርነቱን በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት በኢትዮጵያ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በተለምዶ ቀበሌ 16 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የመቀለ ከተማ ደላሎች መናኸሪያ ሆኗል።-በአንድ ወቅት መቀለ ውስጥ ጭር ያለ የመኖሪያ አካባቢ የነበረው ይህ ቦታ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በበርካታ መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ተሞልቷል።-እዚህ አካባቢ በጣም አስፈላጊ መረጃ የፈለገ ሰው፣ እስከ ገዛ ገረላሰ ምግብ ቤት የሚወስደውን መስመር ተከትሎ መሄድ ይበቃዋል።-እዚህ አካበቢ ተቀምጠው የዕለት እንጀራቸውን የሚጋግሩ ደላሎች፣ የመቀለን ሸማች ሕዝብ ዕጣ ፈንታ ይወስና...
የፎቶው ባለመብት MAXAR TECHNOLOGIES-የመገናኛ ዘዴዎች በተቋረጡበት፣ ጋዜጠኞች በአካባቢው ለመዘገብ ፈቃድ በተከለከሉበት እና በዓለም ስውር ጦርነቶች አንዱ በሆነው በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ትግራይ ክልል ውስጥ የሚካሄደውን ጦርነት በተመለከተ የሳተላይት ምስሎች ለየት ያለ ዕይታን ሰጥተዋል።-በባለፉት ሳምንታት ከሳተላይት የተነሱት ምስሎች ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የጦር ሠራዊት ክምችት እና መሳሪያዎች የተጠመዱባቸውን ቦታዎች አሳይተዋል።-የኤርትራ ጦር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሰዎች አስክሬን በጅብ መበላቱ፣ ከተሞች ላይ የአየር ድብደባ መፈጸሙ፣ አረጋውያን እና ታዳጊ ሴቶች ለውትድርና መመልመላቸው በትግራይ ጦርነት ሳቢያ ከተሰሙ አሰቃቂ ታሪኮች መካከል ናቸው።-በጦርነቱ ሳቢያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው ይገመታል።-ከጦርነቱ በፊት ትግራይ የጎብኚዎች መዳረሻ ነበረች። ከዓለት ድንጋይ የተፈለፈሉ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ ጥንታዊ መስጊዶች፣ ዕድሜ ጠገብ በግዕዝ የተጻፉ መዛግብትም የሚገኙባት ናት።-ዛሬ ላይ ግን ትግራይ የጦርነት አ...
የፎቶው ባለመብት TPLF-ህወሓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈበትን የፓርቲው ሕጋዊ ሰውነት ስረዛ እንዲነሳለት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።-ምርጫ ቦርድ ህወሓት ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በተደነገገው አዋጅ መሠረት በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ሕጉን መሠረት አድርጎ ሲፈቅድ መሆኑንም ዛሬ ግንቦት 5/ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።-ህወሓት ለምርጫ ቦርድ የሕጋዊ ሰውነት ስረዛና የፓርቲው ንብረት እገዳ ይነሳልኝ ጥያቄ ያቀረበው...
በፈረንሳይዋ ማርሴ ከተማ ‘ኮብል ስቶን’ መንገድ ዳር ኳስ እየለጋ ያደገው ዚዙ አገሩ ፈረንሳይ ከዓለም ዋንጫ ስተሰናበት ገና የ10 ዓመት ነበር።-ሕልሙ ብስክሌት እንዲገዛለት ከተቻለም የቆዳ ኳስ እንዲመረቅለት እንጂ የወርቅ ኳስ ሽልምት (ባሉን ዶር) አልነበረም።-እኛ ዚነዲን ዚዳን እንለዋለን፤ ሲያሻን ደግሞ ዚዙ ብለን እናቆላምጠዋለን። አብሮ አደጎቹ ግን ያዝ ይሉታል።-ዚዳን አደገ። ተመነደገ። አገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ እንድታነሳም አደረገ። በዘር የተከፋፈለችውን ፈረንሳይ በኳስ አዋሃደ።-ግን ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በርካታ ቁጥር ያላቸው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደአ በርጋ ወረዳ በታጣቂው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቡድን አባላት መታገታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገለጹ።-ቢቢሲ ከነዋሪዎች እና ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች እንዳረጋገጠው ከ30 ያላሱ የሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች ትናንት ረቡዕ ኅዳር 21/2015 ዓ.ም. ንጋት ላይ በታጣቂ ቡድኑ አባላት ታግተዋል።-የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሁለት ኃላፊዎችም በሠራተኞቻቸው ላይ ያጋጠመውን ችግር ...
በምዕራብ ኦሮሚያ ደምቢዶሎ ውስጥ በመንግሥት ኃይሎች እና በሸኔ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።-መንግሥት በሽብርተኝነት የሰየመውና ኦነግ-ሸኔ የሚለው፣ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሲል የሚጠራው ኃይል የሕዝብ ግንኙነት ኦዳ ተርቢ በትዊተር ገጻቸው ላይ በደምቢዶሎ እና በጊምቢ ወታደራዊ ዘመቻ እያደረገ መሆኑን አስፍረዋል።-ቢቢሲ ያነጋገራቸው የደምቢዶሎ ነዋሪዎች በከተማዋ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።-ስማቸው እንዳይገ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ-የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እያንዳንዱ የሐማስ አባል በሞት ጥላ ሥር መሆኑን ተናገሩ።-ኔታንያሁ ይህን ያሉት በአገሪቷ ከተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ መንግሥት የመጀመሪያ ስብሰባ በኋላ ነው።-ከእርሳቸው በተጨማሪም የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ቤኒ ጋንትዝ አሁን የጦርነት ጊዜ ነው ብለዋል።-ሆኖም የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከኔታንያሁ ጋር መነጋገራቸውን ገልጸው፣ እስራኤል ዘመቻዋን በጦርነት ሕግ መሠረት ማድረግ እንዳለባት አሳስ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በመካከለኛው ምሥራቅ ፍልስጥኤም ለሁለት ተከፍላ የአረብ እና የአይሁዳውያን አገራት እንዲመሠረቱ ከተወሰነ በኋላ ፍጥጫ እና ጦርነት በተለያየ መጠን ሞቅ፣ ቀዝቀዝ እያለ ሲካሄድ ዘመናት ተቆጥረዋል።-በእስራኤል እና በፍልስጥኤማውያን ኃይሎች መካከል የሚካሄደው ጥቃት እና ጦርነት እየተደጋገመ የቀጠለ ቢሆንም፣ ባለፈው ቅዳሜ የተከሰተው ግን ከሌሎች ጊዜያት የተለየ በመሆኑ አሳሳቢ ሆኗል።-የፍልስጥኤሙ እስላማዊ ታጣቂ ቡድን የፈጸመው ድንገተኛ፣ የተቀናጀ እና መጠነ ሰፊ ጥቃት ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ሐኪሞች ድብታ የሚመጣው ከኬሚካሎች ሚዛን መዛባት ነው ሲሉ ኖረዋል።-በአጭሩ ለማስቀመጥ፣ በአእምሮ ውስጥ ‘የደስታ ሆርሞን’ አለ። ሴሮቶኒን ይባላል።-የዚህ ኬሚካል መጠኑ አነስተኛ ሲሆን ከባድ ድባቴ ውስጥ እንዘፈቃለን።-ስለዚህ መጠኑን ለማስተካከል መድኃኒት እንወስዳለን።-በቅርብ ግን አዲስ ጥናት ወጣ። እንዲህ ብሎ ነገር የለም የሚል ነው የጥናቱ ድምዳሜ።-ይህ ነገር አሁን በስፋት እያነጋገረ ነው።-እርግጥ ነው ይህ ጥናት የድብታ መድኃኒቶች ጨርሶውኑ ውሸት ስለመሆናቸው...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሰው አዘዋዋሪዎች አሉ። አባብለው ዜጎችን ለስደት የሚዳርጉ።-ከደቡብ ክልል እስከ ደቡብ አፍሪካ፤ ከአፋር እስከ ሊቢያ።-የቀንድ ከብት አዘዋዋሪዎችም አሉ፤ ፍየል አባብለው ከአገር የሚያስወጡ። ከአፋር በጂቡቱ እስከ ሳዑዲ አረቢያ፥ ከሶማሌ ክልል፣ በሶማሊያ እስከ ኤምሬትስ።-አንዳንዴ ደግሞ ደላሎቹ ከብቶቹን ግጦሽ ፍለጋ አስመስለው ይነዷቸዋል፤ ከድንበር ያደርሷቸዋል።-ከዚያ አብረው ድንበሩን ይሻገሩታል። ከድንበር ማዶ አሰፍስፎ የሚጠብቅ ተቀባይ አለ።-ለፍየል በዶላር የሚ...