text
stringlengths
26
19k
የፎቶው ባለመብት EPA-EEE/REX/SHUTTERSTOCK-በሁቲዎች ጥቃት የሰመጠችው የመጀመሪያዋ መርከብ ሩቢይማር-የየመን ሁቲዎች አማጺያን በቀይ ባሕር በኩል በሚያቋርጡ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸም ከመጀመሩ ከወራት በኋላ የመጀመሪያዋ ግዙፍ መርከብ ሰመጠች።-በብሪታኒያ የተመዘገበችው የጭነት መርከብ ማዳበሪያ ጭና በቀይ ባሕር በኩል ለማቋረጥ ስትሞክር ነበር ከሁለት ሳምንት በፊት በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ በሁቲ ታጣቂዎች ሚሳኤል ተመትታ የቆመችው።-የየመን መንግሥት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ሪቢይማር የተባ...
የፎቶው ባለመብት EPA-ለስድስት ሳምንታት በሚደረግ የተኩስ አቁም ጋዛ ፋታ ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል-አምስት ወራት ያስቆጠረውን የእስራኤል ጋዛ ጦርነትን ጋብ ለማድረግ በሚያስችል ንግግር ላይ ለመሳተፍ የሐማስ ልዑካን ግብፅ ካይሮ መግባታቸውን ተከትሎ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ይደረሳል የሚል ተስፋ ተፈጥሯል።-ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን እስራኤል “ከሞላ ጎደል” የተኩስ አቁም ስምምነቱን መቀበሏን ገልጸዋል።-አሁን ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የስድስት ሳምንታት የተኩስ አቁም ስምምነት ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የአሜሪካ የእርዳታ አቅርቦት ከአየር ላይ ሲወርድ-አሜሪካ ለጋዛ የመጀመሪያውን ሰብአዊ እርዳታ ከ30 ሺህ በላይ ምግቦችን በሦስት ወታደራዊ አውሮፕላኖች አማካይነት በፓራሹት ከአየር ላይ ማቅረቧን አስታወቀች።-ከዮርዳኖስ አየር ኃይል ጋር በጥምረት የተካሄደው ይህ ድጋፍ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለጋዛ ይሰጣል ተብሎ ከታወጀው የመጀመሪያው ነው።-ሐሙስ ዕለት ሕዝቡ ከመኪና ላይ እርዳታ ለመቀበል ሲሞክር ቢያንስ 112 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ፕሬዝዳንቱ እርዳታውን ለማጠናከር ቃል ገብተው...
የፎቶው ባለመብት EPA-ቅዳሜ ዕለት ተከታታይ የሪፐብሊካን ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ውድድርን ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ፣ የፓርቲው ዕጩ ለመሆን ተቃርበዋል።-ከድላቸው በኋላም ተቀናቃኛቸውን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ስደተኞች ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ መንገድ ከፍተዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል።-የቀድሞው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሚዙሪ፣ ሚቺጋን እና አይዳሆ የውክልና ድምጽ ሰጪዎችን [ካውከስ] ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በማግኘት አሸነፈዋል።-የ77 ዓመቱ ትራምፕ በቨርጂኒያ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለደጋፊዎቻቸው እንደተናገሩ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የጀርመን ወታደሮች-ጀርመን የጦር መኮንኖቿ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን ስለመስጠት እና ጥቃት ስለሚፈጸምባቸው የሩሲያ ዒላማዎች ሲወያዩ የሚሰማበት ስብሰባ የድምጽ ቅጂ በሩሲያ መጠለፉን አመነች።-በቪዲዮ የተካሄደው የወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባው የድምጽ ቅጂ በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ይፋ የተደረገው በሩሲያ መንግሥት የሚተዳደረው የቴሌቪዥን ጣቢያ አርቲ ሥራ አስኪያጅ ነው።-ሩሲያ ከዩክሬን በኃይል የነጠቀችውን ክራይሚያን ከሩሲያ ጋር የሚያገናኘውን ኬርች የተባ...
የፎቶው ባለመብት BBC-ሊዮኒድ ዛኩተንኮ የተባለው መርዝ ሻጭ-በዩናይትድ ኪንግደም ቢያንስ 130 ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተውበታል የተባለውን መርዝ የሸጠውን ዩክሬናዊ ቢቢሲ ተከታትሎ ደርሶበታል።-ሊዮኒድ ዛኩተንኮ የተባለው ይህ ግለሰብ ራስ ማጥፋትን የሚያበረታታበት እንዲሁም አገልግሎቱን የሚያስተዋውቅበት ድረ ገጽ አለው።-ግለሰቡ ለቢቢሲም ምሥጢራዊ ዘጋቢ በየሳምንቱ አምስት እሽጎችን ወደ ዩናይትድ ኪንድም (ዩኬ) እንደሚልክ ተናግሯል።-ግለሰቡ ባለፈው ዓመት በቁጥጥር ስር ከዋለው እና በ14 የግድያዎች ወንጀል ...
ባለፈው ሲቲ ከዩናይትድ ሲገናኙ ውሃ ሰማያዊ ለባሾቹ በልበ-ሙሉነት ነበር ግጥሚያውን የረቱት። እሑድ ኢቲሃድ የሚካሄደውን ፍልሚያስ ማን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል?-የቢቢሲ ስፖርት ተንታኝ ክሪስ ሱተን “ማንቸስተር ዩናይትድ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ድል ሲቀናው ነበር፤ ነገር ግን ሲቲ ያለበት ደረጃ ላይ አይደሉም” ይላል።-የዘንድሮውን ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች እየገመተ ያለው ሱተን፣ የማንቸስተር ደርቢን ጨምሮ ከቅዳሜ እስከ ሰኞ ያሉ ጨዋታዎች ግምቱን ጀባ ብሏል።-ቼልሲ ባለፈው ቅዳሜ በካራባዎ ዋንጫ ፍፃሜ በሊቨርፑል...
የፎቶው ባለመብት ethiopian/fb-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስያ አገራት ለሚያደርጋቸው በረራዎች ይጠቀምበት በነበረው የሶማሊያ የአየር ክልል በኩል መብረር ማቆሙን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለቢቢሲ ገለጹ።-አየር መንገዱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከሶማሊያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች “አስተማማኝ የአየር ትራፊክ አገልግሎት” ባለማግኘቱ እንደሆነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ለቢቢሲ አማርኛ አርብ ከሰዓት በኋላ የተናገሩ ቢሆንም፣ ድርጅቱ ምሽት ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባሰራጨው መግለጫ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ማር በውስጡ የያዘው ከፍተኛ የካሎሪ መጠን በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ስለሚጨምር የምንወስደው መጠን ትንሽ መሆን እንዳለበት ይመከራል።-ንቦች ከአበባ የሚገኝን ጣፋጭ ፈሳሽ [ኔክታር] ቀስመው የሚያዘጋጁት ማር ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገራት እንደ መድኃኒት ይቆጠራል።-ከቤት ውስጥ መጥፋት ከሌለባቸው ምግቦች ውስጥም ሲጠቀስ ይሰማል።-ጥንታውያን ግሪኮች ማርን “የፈጣሪ ምግብ” ሲሉ ነው የሚገልጹት። በቻይና ደግሞ መድኃኒት ተደርጎ ነው የሚታሰበው።-በአብዛኛው ወ...
የፎቶው ባለመብት SOCIAL MEDIA-የተፈረደባቸው የአይኤስ አባላት በፍርድ ቤት-ለአይኤስ ለመዋጋት ወደ ሶማሊያ ገብተው ተይዘዋል የተባሉ ስድስት ሞሮኳውያን በሞት እንዲቀጡ ሲወሰንባቸው አንድ ኢትዮጵያዊ ደግሞ የ10 ዓመት እስር ተፈረደበት።-የተከሳሾቹን ጉዳይ የተመለከተው የሶማሊያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በአይኤስ አማካይነት በአገሪቱ ውስጥ ተሰማርተው ተገኝተዋል ብሎ ውሳኔ የሰጠባቸው ስድስት ሞሮኳውያን፣ አንድ ኢትዮጵያዊ እና ሁለት ሶማሊያውያን ናቸው።-ሞት የተፈረደባቸው የሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ ዜ...
የፎቶው ባለመብት Mayor Office/fb-በአዲስ አበባ እምብርት ፒያሳ፤ የሚኒሊክ ሀውልት እና የአራዳው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚያዋስኑት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። በቅርቡ ከታደሰው እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ከሚገኝበት ማዘጋጃ ቤት ጋር ደግሞ በድልድይ ተገናኝቷል።-እስከ ዛሬ ድረስ የራሱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሳይኖረው የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትም ቋሚ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚያገኘው በዚህ ፕሮጀክት ነው። እየተጠናቀቀ ያለው ይህ ፕሮጀክት ሁለት ሺህ ሰዎችን የሚይዝ የከ...
የፎቶው ባለመብት PA Media-ዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የምታዘዋውረው በትንንሽ ጀልባዎች ወደ ግዛቷ የሚገቡትን ለመከላከል በሚል ነው-ዩናይትድ ኪንግደም ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከግዛቷ ወደ ሩዋንዳ ለሚሰፍሩት ካላት እቅድ ለተወሰነው 370 ሚሊዮን ፓውንድ እንደምትከፍል የመንግሥት ወጪዎችን የሚከታተለው ተቋም ይፋ አደረገ።-ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በአምስት ዓመታት ውስጥ ወደ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ለሚዘዋወሩ ለእያንዳንዳቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች 150000 ፓውንድ ለሩዋንዳ መንግሥት ይከፍላል።-ሌበር ፓ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላለፉት አምስት ዓመታት ያደረጉትን ጦርነት በንግግር ለመፍታት በመወሰን በዛንዚባር ንግግር የጀመሩት ከወራት በፊት ነበር።-በመጀመሪያው ዙር ድርድር ማን ምን ይፈልጋል የሚለውን የለዩበት አንደነበር የሚናገሩት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ወክለው የተሳተፉት አቶ ጅሬኛ ጉደታ ይህም ለሁለተኛ ዙር ድርድር መንገድ የጠረገ እንደነበር ይጠቅሳሉ።-ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው ንግግር በመልካም መግባባት ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ለሁለተ...
የፎቶው ባለመብት Bahirdar Communication-በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።-በከተማዋ ሦስት ቀበሌዎች ዛሬ አርብ የካቲት 22/2016 ዓ.ም. ማለዳ 12፡00 ሰዓት ላይ ውጊያው መጀመሩን የተናገሩት አራት ነዋሪዎች፤ የከባድ መሳሪያ ድምጾችንም መስማታቸውን ተናግረዋል።-የክልሉ መንግሥት ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ በባሕር ዳር ዙሪያ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የፀጥታ ኃይል በጋራ በመሆን ሰር...
የፎቶው ባለመብት GoFundMe-በአሜሪካ መንገድ ተሳስታ በገጠር የመኪና ጥርጊያ መንገድ ላይ መኪናዋን ያስገባችውን የ20 ዓመት ወጣት ተኩሶ የገደለው ግለሰብ በ25 ዓመት እስር ተቀጣ።-ሟቿ ኬይሊን ጊሊስ እና ጓደኞቿ ከጥቂት ወራት በፊት በኒውዮርክ ግዛት የሚሄዱበትን ድግስ (ፓርቲ) አድራሻ እየፈለጉ በነበረበት ወቅት ነው ወደ ግለሰቡ የጥርጊያ መንገድ በስህተት የገቡት።-ኬቨን ሞናሃን የተባለው ይህ ግለሰብ ጊሊስን አንገቷ ላይ በጥይት ከመታት በኋላም ሕይወቷ አልፏል።-የ66 ዓመቱ ግለሰብ በሁለተኛ ደረጃ ...
የፎቶው ባለመብት Ethiopian Federal Police-በእሳት ከተቃጠሉ ንብረቶች አንዱ የሆነው ተሽከርካሪ-በስድስት ወራት ከደረሱት የእሳት ቃጠሎዎች 16 ያህሉ ሆን ተብለው የተፈጸሙ መሆናቸውን እና ከእነዚህም መካከል 15ቱ በአዲስ አበባ መከሰታቸውን የፌደራል ፖሊስ በፎረንሲክ ምርመራ ማረጋገጡን አስታወቀ።-በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በመላው አገሪቱ ከደረሱት የእሳት አደጋዎች መካከል 90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የደረሱት በዋና ከተማዋ ውስጥ እንደሆነ ፖሊስ ተገልጿል።-በ2016 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስ...
-በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው ድሃ አገራትን ለመደጎም አዲስ በጀት ጸድቋል። ነገር ግን ለደረሰው ውድመት የላቀ ድርሻ ማዋጣት ያለበት ማን ነው? በሚለው ዙሪያ ክርክሮች አሉ።-በሌላ በኩል አዲስ በመበልጸግ ላይ የሚገኙ እንደ ቻይና እና ህንድ የመሳሰሉ አገራት ደግሞ ከምዕራባውያን ጋር እኩል ማዋጣት የለብንም የሚል ሃሳብ ያነሳሉ። ለመሆኑ በጀቱ ምንድን ነው? ለማንስ ነው የሚሰጠው?
የፎቶው ባለመብት REUTERS-ባለፉት ሳምንታት በቀይ ባሕር በኩል በመርከቦች ጭነት ማጓጓዝ ፈታኝ ሆኗል። በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማጽያን በሰው አልባ አውሮፕላን እና በሚሳኤል መርከቦች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ነው።-ታጣቂዎቹ በተጨማሪም በጀልባ እና በሄሊኮፕተርም ጥቃት አድርሰዋል።-አብዛኛውን የመን የሚቆጣጠሩት ሁቲዎች “በጋዛ እና በዌስት ባንክ ላሉ ፍልስጤማውያን ወንድሞች” ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል።-ወደ እስራኤል የሚጓዙ የንግድ መርከቦችን ዒላማ እንዳደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።-ቢቢሲ ባጣራው ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጋዛ እስከ ሰኞ ድረስ የተኩስ አቁም እንደሚኖር ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ገለጹ።-አስተያየቱን የሰጡት የእስራኤል እና የሐማስ ባለስልጣናትን አሳትፏል የተባባለ ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ላይ መጠነኛ መሻሻል እንዳለ በተዘገበበት ወቅት ነው።-ይህም እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ እርዳታ እንዲገባ እና መስከረም 26 የተፈጸመውን የሐማስ ጥቃት ተከትሎ የተወሰዱ ታጋቾችን መልቀቅን ያካትታል።-እስራኤል በጉዳዩ ላይ አስተያየት ባትሰጥም...
የፎቶው ባለመብት AFP-በቤት ላሂያ የሚገኘው ካማል አድዋን ሆስፒታል ከምዕራባዊቷ የጋዛ ከተማ አስክሬኖችንና የተጎዱ ሰዎችን መቀበሉን ገልጿል።-በጋዛ እርዳታ ለማግኘት በተሽከርካሪዎች ዙሪያ ተሰባስበው የነበሩ ቢያንስ 112 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ፣ 760 የሚሆኑት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።-ሐሙስ ዕለት በርካቶች የተገደሉበት ክስተት ያጋጠመው በምግብ እጦት የተሰቃዩት ሰዎች በጋዛ በስተደቡብ ምዕራብ በሚገኘው የባህር ዳርቻ መንገድ ላይ በእስራኤል ታንኮች ታጅበው እየተጓዙ ከነበሩ ተሽከርካሪዎች እርዳታ ለማ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ይልቅ የባይደንን ፕሬዚዳንትነት እንደሚመርጡ ተናገሩ።-ባይደን የበለጠ ልምድ ያላቸው እና ሊገመት የሚችል ባህርይ ያላቸው ሰው ናቸው ሲሉም መናገራቸው በርካቶችን አስደንቋል።-ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ከመወዳደራቸው በፊት ፑቲን “ታላቅ እና ጎበዝ” ሲሉም በአውሮፓውያኑ 2016 አሞካሽተዋቸው ነበር።-ባይደን የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ፑቲንን ለዓመታት በሰላ ሁኔታ በመተቸት የሚታወቁ ሲሆን ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-አውሮፓ ሙሉ በሙሉ ራሷን የመከላከል አቅም ለማዳበር አስር ዓመት እንደሚያስፈልጋት ግዙፉ የጀርመን የመከላከያ ኩባንያ የሆነው ርሄይንሜታል ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።-የአህጉሪቱ የጦር መሳሪያ ክምችት “መመናመኑንም” ነው አርሚን ፓፐርገር የተናገሩት።-ኃላፊው ይህንን አስተያየት የሰጡት የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ግዙፍ የተባለውን የጦር መሳሪያ ማምረቻ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ለመጣል ሎወር ሳክሶኒ በተባለችው ግዛት በተገኙበት ወቅት ነው።-በዚህ ዝግጅት ላይ የጀርመን የመከላከ...
ዳረን ፍራንኪሽ ለ17 ዓመታት ያክል ከባድ የራስ ምታት ሲያሰቃየው ኖሯል።-ይህ ራስ ምታት ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ጭንቅላቱን ከግድግዳ እያላተመ እና እየጮኸ ነው ስቃዩን የሚወጣው።-የ53 ዓመቱ እንግሊዛዊ ራስ ምታቱ ሲነሳ አንዳች ቅቤ የጠገበ ዱላ ጭንቅላቱን የመታው ያህል ይሰማዋለ። ይህ አልበቃ ብሎ ዓይኑን በጩቤ የተወጋ ያክል ያመዋል።-በእንግሊዝኛው ክላስተር ሄድኤክ የተሰኘ ስም ያለው ይህ ራስ ምታት እጅግ በጣም ስቃዩ የበዛ ነው።-“በኮቪድ ወቅት ወደ ሆስፒታል ስሄድ ትዝ ይለኛል። አውቶቡስ ሲመታ ዘለህ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የአል-ናስር አጥቂው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ሜዳ ላይ ባሳየው ድርጊት ምክንያት የአንድ ጨዋታ ቅጣት ተላለፈበት።-በሳዑዲ ፕሮ ሊግ የሚጫወተው ሮናልዶ “ደጋፊዎችን በመቀስቀስ” በሚል ነው የተቀጣው።-ሮናልዶ ቡድኑ አል-ናስር ከአል-ሸባብ ጋር ሲጫወት የሸባብ ደጋፊዎችን ለማበሳጨት ባሳየው ምልክት ምክንያት አንድ ጨዋታ ያመልጠዋል።-የአል ሸባብ ደጋፊዎች “ሜሲ፤ ሜሲ” እያሉ የሮናልዶን የረዥም ጊዜ ተፎካካሪ ለማብሸቅ ሞክረዋል።-መዲናዋ ሪያድ የተደረገውን ጨዋታ አል-ናስር 3-2...
የፎቶው ባለመብት Office of the Prime Minister-Ethiopia-የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሊያ ጋር ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን ያሉት ዛሬ ማክሰኞ ጥር 28/2016 ዓ.ም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ውሏቸው ከሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ ጋር ከአንድ ወር በፊት የተፈራረሙት የባሕር በር ለማግኘት የሚያስችል የመ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የስኳር በሽታ ዕድሜ ልክ አበሮ የሚቆይ ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የሚዳርግ ከባድ ህመም ነው።-ህመሙ የሚከሰተው ሰውነት በደምስር ውስጥ ያለን ስኳር (ግሉኮስ) በሙሉ በተገቢው መጠን ማመንጨት ሲያቅተው ነው።-ይህም እንደ የልብ ድካምን፣ ስትሮክን፣ ዐይነ ስውርነትን፣ የኩላሊት ሥራ ማቆምን ሊያስከስት እና ከወገብ በታች ያለን የሰውነት ክፍል ላይ ከባድ ጉዳትን ሊያስከትል ይችላል።-በመላው ዓለም በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየ...
የፎቶው ባለመብት WAM-በጥቃቱ የተገደሉ የኤምሬትስ መኮንኖች አስከሬን ወዲያው ወደ አገራቸው ተወስዷል-በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና የባህሬን መኮንኖችን ጨምሮ አምስት የጦር መኮንኖች መገደላቸው ተገለጸ።-ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በተፈጸመው ጥቃት ሦስት የኤምሬትስ፣ አንድ የባሕሬን እና የሶማሊያ የጦር መኮንኖችን ጨምሮ ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።-ቢቢሲ ሶማሊኛ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ካልፈቀዱ ...
የእንዳ አባ ገሪማ ካሕናት የበዓል ልብሰ ተክህኗቸውን ለብሰው፤ ቀሳውስቱ የሚያብረቀርቅ መጎናጸፊያ አጊጠው የዕጣን ማጠኛ ጽንሃቸውን ይዘው፤ ዲያቆናት በመጾር መስቀል በወርቅ ዣንጥላ ተንቆጥቁጠው፤ መሪጌቶች ግራ እና ቀኝ የቤተ ክርስቲያኑ ዐውደ ምህረት መወጣጫ ላይ እዚህም እዚያም እጅብ ብለው ተቀምጠዋል።-በጥንግ ድርብ ልብሳቸው ተውበው እጄታቸው ከብር የተሠሩ መቋሚያቸውን ተደግፈው ለዐውደ ዓመት የሚወጣ ጽናጽላቸውን እንደያዙ ይጠባበቃሉ።-መሬት ላይ ግዙፍ ከበሮዎች ተደግፈው የተቀመጡ ልጅ እግር ሊቃውንት እ...
የፎቶው ባለመብት fana tv-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ-የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከዚህ ቀደም ከመንግሥት ጋር በነበረው ድርድር የተዘጋጀውን “የመጨረሻ ሰነድ” የሚቀበል ከሆነ ሦስተኛ ዙር ድርድር ሊኖር እንደሚችል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሰው እና መንግሥት ‘ሸኔ’ ከሚለው ታጣቂ ቡድን ጋር የሚደረግ ሦስተኛ ድርድር “ወደ ሰላም ለመምጣት ወይም እስከ መጨረሻው ላለመነገጋር” የሚወሰንበት የመጨረሻ ንግግር ሊሆን ...
የፎቶው ባለመብት Merawi Communications-መርዓዊ ከተማ በከፊል-በአማራ ክልል በአዲሱ ሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ሰኞ፣ ጥር 20/2016 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቤተሰቦች፣ ነዋሪዎች አና የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።-ከክልሉ ዋና ከተማ ከባሕር ዳር በ35 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው መርዓዊ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተደረገ ውጊያን ተከትሎ በነዋሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት፣ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኢትዮጵያውያንን በሕገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር የተጠረጠሩ አራት የኬንያ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ።-መርማሪዎች በሕገ ወጥ መንገድ የተዘዋወሩ 37 ኢትዮጵያውያንን ከኬንያ መዲና ናይሮቢ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ በአንድ ቤት ውስጥ አግኝተዋቸዋል ተብሏል።-አራቱ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋሉትም ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲፈፀም በመርዳት ተጠርጥረው ነው ።-ኢትዮጵያውያኑ የተሻለ ሕይወትን ፍለጋ ወደ ደቡብ አፍሪካ እያቀኑ መሆናቸውን ለኬንያ ባለስልጣናት መ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ጥቃቱ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት አላደረሰም-በየመን የሑቲ አማጺያን በአሜሪካ መርከብ ላይ የሚሳኤል ጥቃት ሰነዘሩ። ጥቃቱን ያደረሱት ‘ጂብራልተር ኤግል’ በተሰኘው አቃ ጫኝ ግዙፍ መርከብ ላይ ነው።-የመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ማዘዣ ማዕከል ጥቃቱ በየመን ጠረፍ አካባቢ መፈጸሙን አምኖ ነገር ግን የከፋ ጉዳት እንዳልደረሰ አብራርቷል።-የማርሻል አይላንድ አርማን የያዘው ይህ መርከብ ጉዞውን በኤደን ባሕረ ሰላጤ ቀጥሏል።-በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት ሑቲዎች ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-እስራኤል መስከረም 26 ጥቃት ከተፈጸመባት በኋላ በጋዛ እየፈጸመች ባለችው ወታደራዊ ዘመቻ ቢያንስ ግማሽ የሚሆነው የጋዛ ሕንጻዎችን ማውደሟን የቢቢሲ ምርመራ አመለከተ።-ከጦርነቱ በፊት የተነሱ ምስሎች አሁን ካለው ጋር ሲነጻጸሩ በደቡባዊ እና መካከለኛው ጋዛ የደረሰውን ከፍተኛ ውድመት ያሳያሉ።-የጋዛ ነዋሪዎች የመኖሪያ መንደሮች ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል። ብዙዎች የሚገበያዩባቸው ቦታዎች እንዳልነበሩ ሆነዋል። የዩኒቨርሲቲ ሕንጻዎች ሙሉ በሙሉ ወድመው ጋዛ ከላስቲክ በተሰሩ መ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ባለው የማያባራ ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ከ30 ሺህ በላይ መድረሱን በሃማስ አስተዳደር ስር ያለው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።-ከተገደሉት መካከል አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውንም ከጤና ሚኒስትሩ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።-ከመስከረም መጨረሻ በኋላ የተገደሉት ፍልስጤማውያን ቁጥር ጋዛ ካላት 2.3 ሚሊዮን ያህል ህዝብ 1.3 በመቶው ነው ተብሏል።-የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ጦርነቱ ምን ያህል አስከፊ መሆኑንም አመላካች ነው ተብሏል።-...
የፎቶው ባለመብት AFP-ኬንያ ወደ ግዛቷ ለሚገቡ ተጓዦች ቪዛ መጠየቋን ካቆመች በኋላ ከጀመረችው አዲስ የጉዞ ፈቃድ ማረጋገጫ ጥያቄ እና ክፍያ ኢትዮጵያውያን ነጻ እንዲሆኑ መወሰኗን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አስታወቁ።-አምባሳደር ባጫ ደበሌ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ኢትዮጵያውያን ከአዲሱ አሠራር ነጻ ሆነው ቀደም ሲል እንደነበረው ወደ ኬንያ መግባት እንዲችሉ በመንግሥት የቀረበውን ጥያቄ የኬንያ መንግሥት ተቀብሎታል።-ኬንያ ካለንበት የአውሮፓውያን ዓመት መጀመሪያ አንስቶ የመላው ዓለም ተጓዦች ያለ ቪዛ በበ...
አንድ “ግዙፍ ሚዲያ” ለመፍጠር በሚል ዋልታ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት እንዲሁም ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን፤ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ስር ሊጠቃለሉ ነው። በፋና እና በዋልታ ውስጥ የ25 በመቶ ድርሻ ያለው የትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) በጉዳዩ ላይ አለመሳተፉን ለቢቢሲ ገልጿል።-ከገዢው ፓርቲ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው እነዚህ ተቋማት ከሌሎች በተለየ መንግሥታዊ ዜና እና መረጃዎችን በቀዳሚነት በማግኘት እና በማቅረብ የሚታወቁ ናቸው።-ቀደሞ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታ...
የፎቶው ባለመብት COSMEDACARE-ዶ/ር ኦጉን ኤርሰን ይባላል። ቱርካዊ የሰውነት ክብደት ቅነሳ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ነው።-“ክብደት መቀነሻ” መንገዶች የሚላቸውን በመሸጥ ይታወቃል።-ቢቢሲ ስለ ዶክተሩ የበለጠ ለማወቅ ምርመራ አድርጓል። ጋዜጠኛ መሆኗን ሳትጠቅስ ዶክተሩን ያናገረችው የቢቢሲ ጋዜጠኛ፣ ይህ ዶክተር “ክብደት ጨምሪ” እንዳላት ትናገራለች።-የሰውነት ክብደትና ቁመት መመጣጠን በሚለካበት ቢኤምአይ መሠረት 24.4 ናት። ሆኖም ግን “ምግብ በመብላት” ሰውነቷን እንድትጨምር በዶክተሩ ተነግሯታል።-...
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ-የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከአማራ ክልል ጋር በይገባኛል እያወዛገቡ ያሉትን አካባቢዎች ጉዳይ በሕዝብ ውሳኔ መፍትሄ ለመስጠት ከስምምነት ተደርሷል መባሉን አስተባበለ።-ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለፈው ሳምንት በመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን በኩል የአከራካሪ ቦታዎችን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታት “ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ከአማራ እና ከትግራይ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ ነበር” ማለቱን በመጥቀስ ነው፤ “ፍጹም የተሳሳተ [ነው]” ሲል አስተባብሏል...
የፎቶው ባለመብት NATASHA KERR-በቀዶ ሕክምና ሰበብ ከሞቱት ሴቶች መካከል የ31 ዓመቷ ሜሊሳ ኬር አንዷ ናት-የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለውበት ሲባል በቱርክ በሚደረግ የቀዶ ሕክምና የሚሞቱ ሴቶች ቁጥር በመጨመሩ ከቱርክ መንግሥት ጋር ሊነጋገር ነው።-ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ዜጎች የመቀመጫ መጠን ከፍ ለማስደረግ በቱርክ ቀዶ ሕክምና ካደረጉ በኋላ ሕይወታቸው አልፏል።-ይህን ተከትሎ የዩኬ ባለሥልጣናት የሕክምና እና የኮስሞቲክስ (ውበት) ቀዶ ሕክምና ቱሪዝም መመሪያዎች...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሶማሊያ የባሕር ጠረፍ ዘራፊዎች እንደ አዲስ መርከቦችን ዒላማ ማድረግ ጀምረዋል።-ይህ ክስተት ከአስርት ዓመታት በፊት የነበረውን ትዝታ አየመለሰ ነው።-በወቅቱ የታጠቁ የሶማሊያ ፓይሬቶች የባሕር ጠረፉን ተቆጣጥረው መርከቦችን በማገት ሚሊዮን ዶላሮች ክፍያ ይጠይቁ ነበር።-ይህ ዓለምን አስጨንቆ የነበረ ዝርፊያ ሀገራት ተደራጅተው የሥፍራውን ደኅንነት ለመጠበቅ ባደረጉት ሙከራ ቀዝቅዞ ነበር።-ነገር ግን ከሰሞኑ ታጣቂዎች መርከቦችን እያገቱ ክፍያ መጠየቅ መጀመራቸው አቅማቸ...
የፎቶው ባለመብት Abdulkadir Mohamed Nur-የሶማሊያ እና የቱርክ የመከላከያ ሚኒስትሮች (አብዲካዲር ሞሐመድ ኑር እና ያሳር ጉለር)-የሶማሊያ እና የቱርክ መንግሥታት በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች ትብብር ለማድረግ ስምምነት መፈራረማቸውን ይፋ አደረጉ።-ይዘቱ በዝርዝር ያልተገለጸው የሁለቱ አገራት ስምምነት የመከላከያ ሚኒስትሮቻቸው በተገኙት መፈረሙን የሶማሊያ የዜና ወኪል እና የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጸዋል።-የሶማሊያ ዜና ወኪል (ሶና) ታሪካዊ ሲል የገለጸው ስምምነት የተፈረመው ሞቃዲሹ ኢትዮጵ...
ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያን ወደ ጂቡቲ የሚያደርጉት የበረሃ ጉዞን ለመመልከት አደገኛ የተባለውን የጂቡቲ-ኦቦክ የጉዞ መስመር ላይ ደርሰናል።-ኦቦክ ትንሽ የባሕር ዳርቻ ከተማ ናት።-በባሕር ዳርቻዋ ላይ ወዲያ ወዲህ ሲሉ የሚታዩት ከነዋሪዎቿ ይልቅ ስደተኞች ናቸው።-ከአገሪቱ ይፋዊ የሥራ ቋንቋ ፈረንሳይኛ እና አረብኛ ይልቅ የባሕር ዳርቻው መግባቢያ ኦሮምኛ ይመስላል።-በከተማዋ የሚገኙ ቤቶች ካስጠለሏቸው ባልተናነሰ የባሕር ዳርቻዎቹ ላይ አሸዋ ተንተርሰው፣ ካርቶን ለብሰው የሚያድሩ ስደተኞች ቁጥር ቀላል ...
የፎቶው ባለመብት social Media-በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በሚካሄደው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ በታንዛንያ የሚገኘው የጦሩ ዋና አዛዥ ኩምሳ ድሪባ “ፖለቲካ አያውቅም” የተባለው ሠራዊታቸው ኃያላን ባሉበት ለድርድር መቀመጡን ተናገረ።-መንግሥት 'ሸኔ' የሚለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ የሆነው ኩምሳ ድሪባ ይህንን የተናገረው ቅዳሜ ኅዳር 08/ 2016 ዓ.ም. በዙም አማካኝነት ከደጋፊዎቹ ጋር ባደረገው ወይይት ላይ ነው።-“ፖለቲካ አያውቁም፤ ልጆች ናቸው፤ አላማ የ...
የፎቶው ባለመብት HoPR/FB-ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ-የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) ወክለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ።-የምክር ቤት አባሉን ረቡዕ ጥር 22/2016 ዓ.ም. በቁጥጥር ስር ያዋሏቸው አራት የታጠቁ የፀጥታ አካላት መሆናቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት የቤተሰብ አባል ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከአራቱ መካከልም ሁለቱ የፌደራል ፖሊስን የደንብ ልብስ መልበሳቸውንም አክለዋል።-የዶክተር ደሳለኝ ጫ...
በደብረ ብርሃን ከተማ ረቡዕ ከንጋት እስከ ቀኑ አጋማሽ የቆየ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን የከተማዋ ከንቲባ እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።-በከተማዋ እንቅስቃሴ መቆሙን ነዋሪዎች የተናገሩ ሲሆን በደብረ ብርሃን በሚገኙ የባለ ሶስት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች ላይም ለሁለት ቀናት የሚቆይ እገዳ ተጥሏል።-ከአዲስ አበባ ከተማ 130 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው ደብረ ብርሃን ከተማ ረቡዕ ታህሳስ 24፤ 2016 ዓ.ም “በተለያዩ አቅጣጫዎች” የተኩስ ልውውጥ መሰማት የጀመረው ከጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ ...
የፎቶው ባለመብት EPA-በስፔን የተገደለው አንድ ግለሰብ ሩሲያን ከድቶ ወደ ዩክሬን ኮብልሏል የተባለው ሩሲያዊ ፓይለት መሆኑ ተገለጸ።-ማስኪም ኩዝሚኖቭ ባለፈው ዓመት ነበር የጦር ሄሊኮፕተሩን እያበረረ ወደ ዩክሬን ግዛት ዘልቆ በመግባት እጁን የሰጠው።-የስፔን ፖሊስ ባለፈው ሳምንት በአሊካንቴ ግዛት አቅራቢያ ስለተገደለው ሰው ማንነት በይፋ አልገለጸም።-ሆኖም የዩክሬን ደኅንነት የተገደለው ግለሰብ ሩሲያዊው ፓይለት ኩዝሚኖቭ መሆኑን ሰኞ እለት አረጋግጧል።-የደኅንነት ቃለ አቀባይ ለዩክሬን ጋዜጣ ዩክሬይንስካ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-ሰሜናዊ ምዕራብ አፍሪካ እና የደቡብ አውሮፓ ግዛቶች በከፋ የሙቀት ማዕበል ተመቱ።-በመጪዎቹ ቀናትም በታሪክ ከፍተኛው የተባለው የሙቀት መጠንም ሊመዘገብ እንደሚችል ተጠብቋል።-በአንዳንድ የስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ክሮሺያ እና ቱርክ የሙቀት መጠኑ ከ40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ከፍ እንደሚልም ተተንብይዋል።-በጣሊያን የሙቀት መጠኑ እስከ 48.8 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደሚደርስ ሲጠበቅ ፍሎረንስ እና ሮምን ጨምሮ በአስር የጣሊያን ከተሞች ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።-ማክሰኞ ዕለት በ...
ዓለም ከተማ የመርሐቤቴ ወረዳ ዋና ከተማ ነች-በአማራ ክልል መርሐቤቴ ወረዳ ከአንድ ትምህርት ቤት አቅራቢያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ቢያንስ አራት ሰዎች እንደቆሰሉ ነዋሪዎች እና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ለቢቢሲ ገለጹ።-በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በምትገኘው መርሐቤቴ ወረዳ ዓለም ከተማ የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት አርብ ጥር 3/2016 ዓ.ም. መሆኑን ሦስት ነዋሪዎች እና የትምህርት ቤቱ አስረድተዋል።-ከቀኑ ሰባት ሰዓት ገደማ የተፈጸመው ጥቃት ያረፈው አርበኞች አጠቃላ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ የአሸናፊነት ግምት የተሰጣቸው አገራት ብዙ ትኩረት ባልተሰጣቸው አገራት መሸነፋቸውን ቀጥለዋል።-ትልቅ የዋንጫ ግምት የተሰጣት ሞሮኮ በደቡብ አፍሪካ 2 ለ 0 ተሸንፋ ከውድድሩ ተሰናብታለች።-በትናንት ምሽቱ ጨዋታ ባፋና ባፋናዎች በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው 2 ጎሎችን ሞሮኮን አሸንፈው ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።-ከዚህ ጨዋታ በፊት ቀድሞ በተካሄደው ጨዋታ ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ ተገኝተው የነበረ ሲሆን ማሊ ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸ...
የፎቶው ባለመብት AFP-የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከወራት በፊት አገራቸው የአፍሪካ አገራት ዜጎች ቪዛ ሳያስፈልጋቸው ኬንያን መጎብኘት ይችላሉ በማለት ይፋ ካደረጉ በኋላ ብዙዎች አወድሰዋቸው ነበር።-የፕሬዝዳንቱ ‘ቪዛ አያስፈልግም’ አዋጅ ግን ‘ለቪዛ ክፍያ አንጠይቅም’ ማለት እንዳልሆነ አፍሪካውያን ተጓዦች የገባቸው ዘግይቶ ነው።-ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ የአፍሪካ አገራት ዜጎች ኬንያ ሲደርሱ ፓስፖርታቸው ላይ ምልክት ተደርጎላቸው ያለ ምንም ክፍያ እና ቪዛ በአገሪቱ እስከ ሦስት ...
የፎቶው ባለመብት AFP-አንድ የ46 ዓመት ጎልማሳ ያለ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት አውሮፕላን ተሳፍሮ ከዴንማርክ ተነስቶ በአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ ከተማ ከደረሰ በኋላ በቁጥጥር ሥር ዋለ።-ሰረጌይ ኦቺጋቫ የተባለው ግለሰብ ያለ ፍቃድ እና በቂ የጉዞ ሰነድ ሳይዝ ድንበር በመሻገሩ በአሜሪካ በቁጥጥር ሥር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል።-ግለሰቡ በሎስ አንጀለስ በቁጥጥር ሥር ሲውል የሩሲያ እና የእስራኤል መታወቂያዎች ይዞ የተገኘ ሲሆን እስካሁን ግን ዜግነቱን መለየት አልታቻለም።-ወንጀል መርማሪዎች ግለሰቡ ከዴንማር...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ቲቢ ጆሽዋ-ዩቲዩብ፤ የጥላቻ ንግግር ደንብ ጥሷል በማለት በቅርቡ ፈጽሞታል በተባለው ከባድ በደል ክስ የቀረበበትን የሟቹ ናይጄሪያዊ ሰባኪ የቲቢ ጆሽዋ ቴሌቪዥን ታዋቂ የዩቲዩብ ቻናልን ዘጋ።-ይህ የዩቲዩብ ውሳኔ ይፋ የሆነው ቢቢሲ እና ኦፕንዴሞክራሲ ሟቹ ሰባኪ ቲቢ ጆሽዋ መጠነ ሰፊ የወሲብ ጥቃቶችን እና አካላዊ ሰቆቃዎችን መፈጸሙን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ያየዘ የምርመራ ዘገባ ካቀረቡ ከሳምንታት በኋላ ነው።-ቲቢ ጆሽዋ ከአካባቢ ፓስተርነት ወደ ዓለም አቀፍ ታዋቂነት እ...
የፎቶው ባለመብት AFP-በአውሮፓውያኑ 2035 ከግማሽ በላይ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ ‘ወፍራም’ ወይም ‘ከልክ ያለፈ ክብደት’ ያለው ተብሎ ሊመደብ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጠ።-የዓለም ኦቢሲቲ ፌዴሬሽን አፋጣኝ እርምጃዎች ካልተወሰዱ ከአንድ አስርት ዓመታት በኋላ አራት ቢሊዮን ሕዝብ ለጤና አስጊ የሆነ ክብደት ይኖረዋል ብሏል።-አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የአፍሪካ እና ኢሲያ አገራት ደግሞ ከልክ ያለፈ ክብደት ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ ጭማሪ የሚታይባቸው አገራት ሊሆኑ እንደሚችሉ ፌዴሬሽኑ ያወጣው ሪፖ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ቢቢሲ በሳዑዲ አረቢያ በስደት የሚኖረውን ያህያን ሲያነጋግረው በእግሩ ላይ ከደረሰበት ጉዳት ገና እያገገመ ነበር።-ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለስደት ከወጣ አምስት ወራቶች ያስቆጠረው ያህያ፣ እግሩን በጥይት የተመታው የሳዑዲን ድንበር ለማቋረጥ ሲሞክር እንደሆነ ይናገራል።-ያህያ ሳዑዲ ከመድረሱ አስቀድሞ ወደ የመን ነው የተሰደደው።-በየመን ደላሎች ይዘው ካቆዩት በኋላ ድንበር ተሻግሮ ወደ ሳዑዲ የሚገባበት ቀን ሲደርስ ከሌሎች ስደተኞች ጋር በመሆን በተከፋይ መንገድ ...
የፎቶው ባለመብት TPLFOFFICIAL/FB-ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር እና ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር)-ከተመሠረተ ግማሽ ምዕተ ዓመት ሊሞላው የተቃረበው ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከአማጺ ቡድንነት ተነስቶ በአገር መሪነት ጉልህ ሚና ይዞ ከቆየ በኋላ፣ ከማዕከላዊ መንግሥት ተገፍቶ ተመልሶ ወደ ትግራይ ክልል ከተመለሰ በኋላ ለሁለት ዓመታት በተካሄደው ጦርነት ወደ ሽምቅ ተዋጊነት ለመመለስ ተገዶ ነበር።-ደም አፋሳሹ የእርስ በርስ ጦርነት ያስቆመውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተከ...
የፎቶው ባለመብት SM-በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወይም 57 ሚሊዮን ሕዝብ አሊያም ከአጠቃላይ ሕዝቡ 51 በመቶ የሚሆነው ምንም አይነት የኤሌክትሪክ አቅርቦት የለውም ይላል - የዓለም ባንክ መረጃ።-በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ባለፉት አስርት ዓመታት ከፍ እያለ ቢሄድም አገሪቱ ከሰሀራ በታች የኤሌክትሪክ እጥረት ካለባቸው አገራት በሦስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።-በአሁኑ ወቅት የሕዳሴ ግድብ ሁለት ዩኒቶችን ጨምሮ ኢትዮጵያ ካላት የኃይል ማመንጫዎች 5250 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ እንደምታመርት የኢትዮጵያ ...
የፎቶው ባለመብት SOPA IMAGES VIA GETTY IMAGES-በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያሉት የዓለማችን ዋነኛው ተጽእኖ ፈጣሪ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ፌስ ቡክ፣ ከተጀመረ 20 ዓመት ሆነው።-ይህ ሲጀመር “ዘ ፌስቡክ” የሚል ስያሜ የነበረው ማኅበራዊ ሚዲያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በምድራችን ላይ በተከሰቱ የተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የራሱ ሚና ነበረው።-ማርክ ዛከርበርግ እና የኮሌጅ ጓደኞቹ ዶርማቸው ውስጥ ሆነው ፌስቡክን ሲፈጥሩት የነበረው ገፅታ ከታች በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ነበር።-በሂ...
የፎቶው ባለመብት UN-በፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ሲያካሂድ (ፎቶ ፋይል)-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ ማምሻውን በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ጉዳይ ላይ ሊመክር መሆኑ ተሰምቷል።-ይህ በሁለቱ አገራት መካከል ውዝግብን በፈጠረው ጉዳይ ላይ የሚካሄደው ውይይት በዝግ የሚከናወን ሲሆን ስብሰባ “የአፍሪካ ሠላም እና ፀጥታ” በሚል ርዕስ እንደሚካሄድ ታውቋል።-በዚህ ስብሰባ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ሀና ስርዌ ቴተ ቀርበው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ልክ የዛሬ 10 ዓመት፣ በዕለተ ሐሙስ እኤአ ጥቅምት 03 ቀን 2013፣ 368 ኤርትራውያን ስደተኞች በላምፔዱዛ የባሕር ዳርቻ በጀልባ አደጋ ሞቱ።-ሟቾቹ ከቀናት በፊት ጉዞ መጀመራቸውን በስልክ የነገሯቸው ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው “በሰላም ገብተናል” የሚል ምሥራች እየጠበቁ ሳለ ነበር በመላው ዓለም የመገናኛ ብዙኃን ይህ አስደንጋጭ ዜና ተሰማው።-ከላምፔዱዛ የባሕር ዳርቻ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የደረሰው አደጋ፣ በካሜራ እና በሕዝቡ ዐይን በመታየቱ ቢቢሲን ጨምሮ ...
ጥንታዊቷ የስቶን ታውን ከተማ-በዛንዚባሯ ደሴት መዲና ታሪካዊቷ ስቶን ታውን ኮፍያቸውን ያጠለቁ ሙስሊም ሽማግሌዎች የሚያፈሉት ቡና መዓዛ በሩቅ ይጣራል።-ቡናቸውን በቀረፋ፣ ቅርንፉድ እና ዝንጅብል ቅመሞች በመቀመምም ካፈሉ በኋላ ከባልዲያቸው ሲኒ እያወጡ ቡናውን በአገሬው አጠራር 'ካሃዋ' ያድላሉ።-ሲኒዎቹ በሚያስገርም ሁኔታ ከኢትዮጵያ ጋርም ተመሳሳይ ናቸው። ሲኒው ብቻ ሳይሆን ዛንዚባራውያን “ሰውን ሰው ያደረገው ዕቁብ ነው” ይላሉ።-በስቶን ታውን ‘ጆስ ኮርነር’ በምትገኘው ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሙስሊም ወን...
ባለፉት አስርተ ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጸምበት ስለነበረው ማዕከላዊ እስር ቤት ብዙ ሰምተናል።-‘ጄል ኦጋዴን’ ተብሎ ከሚጠራው የጂግጅጋ ከተማ ማረሚያ ቤት የወጡ የሰቆቃ ድምጾችንም እንዲሁ።-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚፈራረቅባት ኢትዮጵያ በርካቶች ስለሚታሰሩበት የአዋሽ ወታደራዊ ካምፕ ግን ብዙ የተባለለት ነገር የለም።-አዋሽ አርባ ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በተለይ በሕዝባዊ ተቃውሞ እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት እስረኞችን በጅምላ ለመቅጣት ሁነኛ ምርጫ ሲሆን ተ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ጥቅምት 2016 ዓ.ም፤ የላስታዋ ላሊበላ ውጥረት ላይ ነበረች።-ወጣቶቿ “ፋኖን ትደግፋላችሁ” በሚል በገፍ ተይዘው በኮምቦልቻ እየታሰሩ ነው። የከተማውን ጥግ ጥግ የከበበ ታጣቂ ኃይል አለ። በሌላ ጎን ደግሞ ከባድ መሳሪያ ተክሎ ጆሮውን ከፍቶ መከላከያ ሰራዊት በተጠንቀቅ ይጠባበቃል።-ከቅዳሜ ጥቅምት 24 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ወሎዋ ላሊበላ ዙሪያ በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ ተደርጓል።-በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በአገራቸው የተሠራ ቅንጡ መኪና በስጦታ ማበርከታቸውን ደቡብ ኮሪያ ተቃወመች።-የሰሜን ኮሪያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት የፑቲን ስጦታ የሆነው ሊሞዚን፣ ፒዮንግ ያንግ ውስጥ ለፕሬዝዳንቱ ከፍተኛ ረዳቶች የተሰጠው እሁድ ዕለት ነው።-የፑቲን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ስጦታው መበርከቱን አረጋግጠው፣ አውረስ ከተባለ ቭላድሚር ፑቲን ከሚጠቀሙት ጋር ተመሳሳይ ቅንጡ መኪና መሆኑን ተናግረዋል...
የፎቶው ባለመብት PA Media-አንድ ታዳጊ ወሲባዊ ይዘት ያለው ፎቶግራፍ እንዲልኩ ገንዘብ ከፍሏል በሚል ከሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ የነበረው ጋዜጠኛ ማንነት ይፋ ሆኗል።-በዚህ የተወነጀለው ለአራት አስርት ዓመታት በቢሲ በጋዜጠኝነትና አቅራቢነት እያገለገለ ያለው ሂው ኤድዋርድስ መሆኑን የተናገረችው ባለቤቱ ናት።-ባለቤቱ ጋዜጠኛው ሂው ኤድዋርድስ “በከባድ የአዕምሮ ጤና ጉዳዮች” ምክንያት ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኝ በተናገረችበት መግለጫዋ ነው ከዚህ ውዝግብ ጀርባ ያለው ባለቤቷ መሆኑን የጠቀሰችው።-ዘ ሰን የ...
ከትናንት በስትያ ታኅሣሥ 24/ 2016 ዓ. ም. በአማራ ክልል፣ ደብረ ብርሃን ከተማ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ አምስት ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ እና የሆስፒታል ባልደረባን ጨምሮ አራት ሰዎች እንደቆሰሉ የደብረ ብርሃን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምንጭ ለቢቢሲ ተናገሩ።-ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው ከትናንት በስትያ ከሰዓት እና ትናንት ቢያንስ የሰባት ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት መከናወኑን ገልጸዋል።-በደብረ ብርሃን ከተማ ባሳለፍነው ረቡዕ እስከ ቀኑ አጋማሽ የ...
የፎቶው ባለመብት EPA-የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፓል ካጋሜ የአፍሪካ አገራት ዜጎች ወደ ሩዋንዳ ያለ ቪዛ እንዲገቡ የሚፈቅድ አሠራር ይፋ አደረጉ።-ያለ ቪዛ አፍሪካውያን ወደ ግዛቷ እንዲገቡ በመፍቀድ ሩዋንዳ አራተኛዋ አፍሪካዊ አገር ናት።-“ማንኛውም አፍሪካዊ አውሮፕላን ተሳፍሮ ወደ ሩዋንዳ መምጣት እንደሚችል ለመግለጽ እወዳለሁ። አንዳችም ገንዘብ መክፈል አይጠበቅበትም” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።-ፕሬዝዳንቱ ይህ ውሳኔ የተላለፈው በአህጉሪቱ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ እያደገ ካለው ...
የፎቶው ባለመብት ANADOLU-"ስለቤተሰቡ ሲጠይቀኝ መልስ መስጠት አልችልም። በረዥሙ እተነፍስና ርዕሰ ጉዳዩን በመቀየር ጥያቄውን ለማረሳሳት እሞክራለሁ።”-የአራት ዓመቱ ኦማር በሕይወት የተረፈው ብቸኛ ዘመዱ የሆነው አጎቱ ሞኢን አቡ ሬዝክ ነው። ኦማርም ቢሆን በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ በዲር አል-ባላ በሚገኘው አል-አቅሳ ሆስፒታል ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ላይ ነው።-ኦማር ግራ እጁን መቆረጥ ነበረበት። በቀኝ እግሩ ላይ ትልቅ ቁስል አለ። ደረቱ እና ፊቱ ላይ ትናንሽ ቁስሎች አሉት። መንጋጋውም ጉዳት ደርሶበታል።...
ፓስተር ቲቢ ጆሽዋ-የዓለማችን ትልቅ ቤተ እምነቶች መካከል አንዱ የሆነው ቤተ-ክርስቲያን መሥራች እና መሪ ፓስተር ቲቢ ጆሽዋ ምዕመናን አስገድዶ መድፈሩን እና ማሰቃየቱን የቢቢሲ ምርመራ አጋለጠ።-የሲኖግ ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽን የቀድሞ አባላት የሆኑ አምስት እንግሊዛውያን በናይጄሪያዊው ፓስተር ቲቢ ጆሽዋ አስገድዶ መድፈር እና በግዳጅ ጽንስ ማቋረጥን የሚጨምር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል።-መስል ጥቃቶቹ ምሥጢራዊ ተብሎ በተለየና በሌጎስ ከተማ በሚገኝ አንድ ግቢ ውስጥ ለ20 ዓመታት ሲፈጸም ቆይቷል።-እ...
በአየር ንብረት ለውጥ እና በግጭት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለችግር በመጋለጣቸው እርዳታን እንደሚሹ እየተነገረ ነው።-በዚህም ሳቢያ በአገሪቱ ውስጥ ከ20 ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) ገልጿል።-የአገር ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ እና የግለሰቦች ስብስብም ለችግር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለመርዳት የተለያዩ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ። ካጋጠመው ችግር አንጻር አሃዞች ምን ያሳያሉ?
የፎቶው ባለመብት THIS IS LEBANON/FB PAGE-መጋቢት 02/2015 ሥልጠና ተጀምሯል። ሥልጠናው የሚሰጠው በነጻ ነው። የዕድሜ ገደብም አልተቀመጠለትም።-ለዚህም የሚሆኑ ከ70 በላይ የሥልጠና ማዕከላት ተዘጋጅተዋል።-ቅድሚያ የሚሰጠው ከዚህ በፊት ወደ ተለያዩ አረብ አገራት ደርሰው ለተመለሱት ነው።-ይህ በውጭ አገራት የሥራ ዕድል ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ሥልጠና ነው።-ማንኛውም ሠርቶ መለወጥ የሚፈልግ ሰው ሥልጠናውን ወስዶ ወደ ውጭ አገር ሄዶ መሥራትም ይችላል ተብሏል።-ሥልጠናው ቋንቋን ጨምሮ በመዳረሻ አ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል-አምስት አስርት ዓመታት ለሚሆን ጊዜ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ ጉልህ ሚና የነበረው ህወሓት ለሁለት ዓመታት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ጦርነት ውስጥ ቆይቷል። ጦርነቱ በአጠቃላይ በአገሪቱ ላይ በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል ላይ ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመትን አስከትሏል።-በጦርነቱ ወቅት በትግራይ በኩል ዋነኛ ተዋናይ የነበረው ህወሓት በሽብር ቡድንነት ተፈርጆ ሕገወጥ ሆኖ ቢቆይም፣ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በተደረሰው የ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኢትዮጵያ አራተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ ሙሌትን አከናውኛለሁ ማለቷን ተከትሎ ግብጽ ከናይል ወንዝ የማገኘው የውሃ መጠን አቅርቦት ላይ አደጋ የጋረጠ ነው ስትል ከሳለች።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቀናት በፊት የታላቁ የህዳሴ ግድብ አራተኛ እና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።-በግድቡ የውሃ ሙሌት እና ከግድቡ በሚለቀቀው የውሃ መጠን ላይ ህጋዊ እና አስገዳጅ ሶስትዮሽ ስምምነት ካልተፈረመ ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌቱን ማከናወን እንደሌለባትም ግብጽ ስ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የቀድሞው የፌስቡክ የይዘት ተቆጣጣሪ (content moderator) ሥራው የአእምሮ ጤንነቱ ላይ ስላመጣው ጫና ለቢቢሲ ይናገራል።-ሰዎችን ራሳቸውን ሲያጠፉ ከሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ጀምሮ በጣም አሰቃቂ የሚባሉ ይዘቶችን ይቆጣጠራ። እኒህ ይዘቶች የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ጋር እንዳይደርሱ ይጥራል።-ግለሰቡ ኬንያ መዲና ናይሮቢ መቀመጫውን ባደረገ አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ውስጥ የሚሠራ ነው።-ፌስቡክ አፍሪካ ውስጥ በጣም አስከፊ እና አሰቃቂ የሚባሉ ይዘቶችን እየተቆጣጠረ አይደለም የሚ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኢትዮ-ሶማሊ ጦርነት-ከሰሞኑ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን በአንድ በተመሳሳይ አጀንዳ ተይዘዋል።-መገናኛ ብዙሃኑ ኢትዮጵያን እንደ ታሪካዊ ጠላት አድርጎ የሚገልጸውን እና ጦርነት የሚጎስመውን ሙዚቃ ደጋግመው እያጫወቱ ይገኛሉ።-አንዳንዶች በሶማሊያ መንግሥታዊ ሚዲያዎች እየተከፈተ ያለው ይህ የሶማሊያ ፖሊስ ባንድ ሙዚቃ “ስሜት ቀስቃሽ” ነው ይሉታል።-ከሳምንታት በፊት ኢትዮጵያ እና ነጻ አገርነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ የባሕር ጠረፍ ያስገኛል የተባለውን የመግባቢያ ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-ምንም እንኳን የአሜሪካ መንግሥት ባይፋ ባይገልጸውም ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዜጋዋ አብረሃም ተክሉ ለማ የመከላከያ እና የደኅንነት ምስጢራዊ መረጃዎችን ወደ ኢትዮጵያ ያስተላልፍ ነበር መባሉ መነጋገሪያ ሆኗል።-ከዚህ ቀደም የአሜሪካ መንግሥትን የስደነገጡ ምስጢራዊ መረጃዎች ሾልከው ሲወጡ የነበሩት ወደ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ወደ ተቀናቃኞቿ ኃያላን አገራት መሆኑ የአሁኑን ክስተት የተለየ አድርጎታል።-በተለያዩ ጊዜያት ከአሜሪካ የመከላከያ፣ የደኅንነት፣ የቴክኖሎጂ ምስጢራዊ መረጃዎ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኤርትራ ውስጥ የተቃውሞ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እና ሠላማዊ ሰልፎች እምብዛም ናቸው።-በተለያዩ አገራት የሚኖሩ በርካታ ኤርትራውያን ደግሞ የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አገዛዝን በመቃወም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እና ሰላማዊ ሰልፎች ሲያካሂዱ ቆይተዋል።-በአገሪቱ የተረቀቀው ሕገ መንግሥት ተግባራዊ እንዲደረግ፣ ምርጫ እንዲካሄድ፣ የፖለቲካው ምህዳር እንዲሰፋ፣ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት የታሰሩ እንዲፈቱ እና ለብዙ ወጣቶች ፍልሰት ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለት ገደብ የለሽ...
የፎቶው ባለመብት EOTC-ባለፈው ሳምንት የቤተክርስቲያኗ ምዕመናን በአብያተ ክርስቲያናት በመገኘት የጸሎት ሥነ ሥርዓቶች ተካሂደዋል--ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ክስተት ጋር በተያያዘ የእምነቱ ተከታዮች መታሰራቸውን እና አብዛኞቹም ወደ አዋሽ ሰባት የጦር ካምፕ መወሰዳቸውን የቤተ ክርስቲያኗ ጠበቆች ለቢቢሲ ገለጹ።-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አያሌው ቢታኔ እስካሁን ባላቸው መረጃ ከ200 በላይ ምዕመ...
የፎቶው ባለመብት Gettyimage-በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት ከሦስት ወራት በላይ ሆኖታል።-ክልሉ ካለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያን በተለያዩ ጊዜያት እያስተናገደ ይገኛል።-በዚህም ምክንያት በበርካታ የክልሉ አካባቢዎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ተስተጓጉለዋል። በዚህም ሳቢያ ነዋሪዎች ከመደበኛ የሥራ እንቅስቃሴ ውጪ ሆነው ሕይወታቸውን ለመምራት ተቸግረዋል።-ከክልሉ ወደ አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ወደ ክልሉ የተለያዩ ከተሞች የሚደረጉ ጉዞዎች ...
የፎቶው ባለመብት KOREA SUMMIT PRESS POOL-የኪም መርሰዲስ ልዩ መጸዳጃ ቤት ተገጥሞለታል-የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ወደ ሩሲያዋ ቭላዲቮስቶክ የወደብ ከተማ ፑቲንን ለማግኘት እየተጓዙ ነው።-እርሳቸው የተሳፈሩበት ‘የጦር ባቡር’ ከ20 በላይ ጥይት የማይበሳቸው መኪናዎች ተጭነውበት ጉዞው አዝጋሚ ሆኗል።-ይህ ኪም የተሳፈሩበት ባቡር ራሱ ጥይት አይበሳውም። ልዩ ልዩ ዘመናዊ የቅኝት መሣሪያዎችም ተገጥመውለታል።-የሰሜን ኮሪያ መሪዎች ለጉዞ ለምን ባቡር እንደሚመርጡ ግልጽ አይደለም። ምናልባት ከ...
የፎቶው ባለመብት DOREEN MORAA MORACHA-የፀረ ኤችአይቪ ሕክምና መድኃኒቶች የበሽታውን መስፋፋት በመግታት በኩል ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አላቸው-አዲስ የወጣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት እንደሚለው መሠረታዊ የጤና ፕሮግራሞችን በገንዘብ መደገፍ ከተቻለ ኤድስን በአውሮፓውያኑ 2030 ከዓለም ማጥፋት ይቻላል።-በዓለማችን ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ከሚገኝ ጠቅላላ ሕዝብ 65 በመቶ የሚሆኑት ባሉባቸው ከሰሃራ በታች አገራት እንኳ ይህንን ዕቅድ የማሳካት ዕድላቸው ሰፊ ነው ብሏል።-እንደ የተባበሩት መ...
የፎቶው ባለመብት PA Media-ወሲባዊ ይዘት ላላቸው ፎቶዎች ለታዳጊ ከፍለዋል በሚል በታገዱት የቢቢሲ ጋዜጠኛ ዙሪያ የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር ጥያቄ ሊቀርብላቸው እንደሚችል ተጠቆመ።-ዋና ዳይሬክተሩ ቲም ዴቪ ዛሬ ሐምሌ 4፣ 2015 ዓ.ም የቢቢሲ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘዋል።-ዋና ዳይሬክተሩ ከጋዜጠኞች ጋር በሚኖራቸውም ቆይታ አብዛኛዎቹ ጥያቄዎች ከሰሞኑ መወዛገቢያ የሆነው የቢቢሲ አቅራቢ ቅሌት ዙሪያ ሊሆን እንደሚችልም ተገምቷል።-ቢቢሲ የግል የመረጃ መብ...
የፎቶው ባለመብት AFP-ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ አጥብቃ ከመቃወሟ በተጨማሪ በአገሪቱ ፍልስጤማውያንን የሚደግፉ በርካታ ሰልፎች ተካሂደዋል-እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄድ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ላይ ጠንካራ ተቃውሞዋን እያሰማች ባለችው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አምባሳደሯን መጥራቷን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።-እስራኤል የየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አምባሳደሩ የተጠሩት “ለምክክር ነው” ብሏል።-የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ሊዮር ሃይታ በኤክስ ገጻቸው ላይ አምባሳደሩ ወ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-አንቶኒ ብሊንከን-ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጠብ ከሚያጭሩ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ጥሪ አቀረቡ።-ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት ሲካሄድ የነበረውን የእርስ በርስ ጦርነት ያስቆመው ስምምነት አንደኛ ዓመትን በማስመልከት ባወጡት መግለጫ ላይ ሁለቱ አገራት “ጠብ ከሚያጭሩ ድርጊቶች በመቆጠብ የአካባቢውን አገራት ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማክበር አለባቸው” ብለዋል።-የውጭ ጉዳይ ኃላፊው ይህ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-ከፍርስራሾች መካከል ዳቦ የምትጋግር ፍልስጤማዊት-ጋዛ ላይ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ ያለው የእስራኤል ጦር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፊቱን ወደ ደቡብ ጋዛ በማዞር ኻን ዩኒስ የተሰኘችውን ከተማ ዒላማ ማድረግ ጀምሯል።-2.3 ሚሊዮን ፍልስጤማዊያን ሰሜናዊ ጋዛ ጥቃት ሲደርስበት ወደ ደቡባ አቅጣጫ ነው ያመሩት። መዳረሻቸው ደግሞ ኻን ዩኒስ።-ከተማዋ በአዲስ መጥ ተፈናቃዮች ተጨናንቃለች። ምግብ፣ ውሃ እና መጠለያ ማግኘት ከባድ ሆኗል።-ከሰርጡ ቢያንስ 1.9 ሚሊዮን ያክል ሰዎች እንደተፈ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የሶማሊላንድ መዲና ሐርጌሳ-ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት እንደ ሀገር የሚያስቆጥራትን እውቅና ለማግኘት ስትባዝን የቆየችው ራስ ገዟ ሶማሊላንድ፤ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ሠነድ የመጀመሪያውን እውቅና እንደሚያስገኝላት ይፋ አድርጋለች።-በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የአዲስ አበባ እና ሐርጌሳ መንግሥታት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ የባሕር በር ሰጥተው በምላሹ ከአዲስ አበባ እውቅና ለመቀበል መ...
የፎቶው ባለመብት HRW-ስደተኞች በተጨናነቀ የሳዑዲ እስር ቤት ውስጥ-በሳዑዲ አረቢያ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ናቸው የተባሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ስደተኞች በተጨናነቁ እስር ቤቶች በሰቆቃ ውስጥ እንደሚገኙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።-ዓለም አቀፉ ሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ ያሉበትን ሁኔታ እና እየገጠማቸው ያለውን አሳሳቢ ሁኔታን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ቁጥራቸው ከ30 ሺህ እንደሚልቅ አመልክቷል።-...
የፎቶው ባለመብት tigray tv/fb-በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በትግራይ ፖለቲካ ውስጥ ጎልተው ከሚታዩ ፖለቲከኞች አንዱ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉን አስፈጻሚ አካል በማዋቀር የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መሾማቸው ተገልጿል።-በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል ውስጥ በኃላፊነት በቆዩባቸው ዓመታት በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ላይ በመቅረብ ሃሳባቸውን በመግለጽ እና በመከራከር በተደጋጋሚ ከሚታወቁ ጥቂት ባለሥልጣናት መካከል አን...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ኢትዮጵያ አራተኛው እና የመጨረሻው ዙር የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሙሌት መጠናቀቁን ገለፀች-ኢትዮጵያ የመጨረሻውን የሕዳሴ ግድብ ሙሌት “በተሰካ ሁኔታ” ማካሄዷን ገለፀች።-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በይፋዊ የኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ “አራተኛውንን እና የመጨረሻውን ሙሌት በተሳካ ሁኔታ” ማካሄዷን ይፋ አድርገዋል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድቡን ለመገደብ በገንዘብ በዕውቀት፣ በጉልበት እና በጸሎት የተሳተፉትን ሁሉ በዚሁ መልዕክታቸው ላይ አመስግ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ከጥቂት ወራት በፊት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የተቀረጸና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተሰራጨ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል በርካቶችን አስደንግጧል።-ምስሉ ላይ አንድ በሕይወት ያለ ግለሰብ በዙሪያው ሰዎች በተሰበሰቡበት ከሚነድ እሳት ውስጥ ሲጨመርና ይህንን የሚያበራታቱ ንግግሮች ተሰምተዋል።-ይህ ቪዲዮ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በስፋት ከተዘዋወረ በኋላ በርካቶች ድርጊቱን ሲያወግዙና መንግሥት በፈጻሚዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ሲጠይቁ ነበር።-ከዚህ በ...
የፎቶው ባለመብት @TheVillaSomalia-የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ማህሙድ-ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት እስካላነሳች እና ለሶማሊያ የግዛት አንድነት ማረጋገጫ እስካልሰጠች ድረስ ከአዲስ አበባ ጋር ለሚደረግ ሽምግልና “ቦታ እንደሌላት” ሶማሊያ አስታወቀች።-ሶማሊያ ይህንን አቋሟን ያሳወቀችው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ትላንት ረቡዕ ካደረገው ስብሰባ በኋላ ሁለቱ አገራት “ትርጉም ያለው ንግግር” በማድረግ ችግራቸውን እንዲፈቱ መጠየቁን ተከትሎ...
የፎቶው ባለመብት FACEBOOK-ምሥጢራዊ ሰነዶችን ይፋ በማድረግ የተከሰሰው ጃክ ቴሼራ አሁንም የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ነው ሲል የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ተናገረ።-ከ100 በላይ ገጾች ያሉትን ምሥጢራዊ ሰነዶች አደባባይ ያወጣው ወጣት አሁንም ቁልፍ የሚባሉ ሰነዶች በእጁ ሊኖሩ ይችላሉ ሲል ዐቃቤ ሕግ ስጋቱን ገልጿል።-በአሜሪካ አየር ኃይል ብሔራዊ ዘብ የዝቅተኛ እርከን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆነው የ21 ዓመት ወጣት ከሳምንታት በፊት ምሥጢራዊ ሰነዶችን በማውጣቱ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወሳል...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-በጀርመኗ ጊሰን ከተማ በኤርትራውያን የባሕል ፌስቲቫል ላይ በተከሰተ ግጭት 26 የጀርመን ፖሊስ አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።-የአገሪቱ ፖሊስ በጊሰን ከተማ የተዘጋጀውን የባሕል ፌስቲቫል ለማወክ የወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያንን ለመበተን ዱላ እና ዐይን የሚያቃጥል ፈሳሽ ረጭቷል፤ ሄሊኮተፕር ጭምር በአካባቢው አሰማርቶ ነበር።-ፖሊስ በግጭቱ ተሳታፊ ናቸው ያላቸውን ከ100 የማያንሱ ኤርትራውያንን እና ትውልደ ኤርትራውያንን በቁጥጥር...
የፎቶው ባለመብት EOTC-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሪዎች ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት የቤተክርስቲያኗ አቋም ተቀባይነት በማግኘቱ ለእሁድ ታቅዶ የነበረው ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገለጸ።-በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ ውጥረት በነገሰበት ጊዜ በቤተክርስቲያኗ እና በመንግሥት መሪዎች መካከል አርብ ከሰዓት በኋላ በተደረገው ውይይት፣ መንግሥት ቤተክርስቲያኗ ያቀረበችውን ቅድመ ሁኔታ መቀበሉ ተገልጿል።-ዛሬ ቅዳሜ የካቲት...
የፎቶው ባለመብት Debremarkos City Communication-በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት ምክንያት በትራንስፖርት እና በመድኃኒት እጥረት ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸውን ተናገሩ።-በላሊባላ ደብረ ማርቆስ እና ሸዋሮቢት የሚገኙ ነዋሪዎች በቀጠለው ግጭት ምክንያት የትራንስፖርት ችግር፣ የመድኃኒት እጥረት እና መሰረታዊ ፍጆታዎች እጥረት እንዲሁም ዋጋቸውም መናሩን ለቢቢሲ አስረድተዋል።-በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎችም በመድኃኒት እጥረት ህ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ አውሮፕላናቸው የቴክኒክ ብልሽት ገጥሞት ያለዕቅዳቸው ሕንድ ለመቆየት ተገደዋል።-የካናዳ ጦር ሠራዊት ትሩዶን በፍጥነት ወደ ቤታቸው ሊያመጣቸው እየተሯሯጠ ቢሆንም ከማክሰኞ ከሰዓት በፊት ካናዳ እንደማይገቡ ቢሯቸው ገልጧል።-በቡድን 20 ሃገራት ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ ሕንድ ያቀኑት ትሩዶ ከሕንዱ አቻቸው ናሬንድራ ሞዲ ጋር ጠጠር ያለ ውይይት ካደረጉ በኋላ ዕለተ ሰንበት ነበር ሊመለሱ ያቀዱት።-ቢሯቸው እንደገለጠው በረራቸው “ይ...
የፎቶው ባለመብት Getty Images-ከአውሮፓውያኑ ከ1980ዎቹ ጀምሮ በደሙ ውስጥ ኤችአይቪ ቫይረስ የነበረበት ግለሰብ ከበሽታው ነጻ መሆኑን ዶክተሮች ገለጹ።-በዚህም እስካሁን ከኤችአይቪ ቫይረስ ነጻ መሆናቸው ከተነገረላቸው ሰዎች አራተኛው ሆኗል።-ግለሰቡ የነበረበትን የደም ካንሰር ለማከም በተፈጥሮ ቫይረሱን ለመቋቋም ከሚችል አንድ ግለሰብ የአጥንት መቅኔ ዝውውር ሕክምና ተደርጎለታል።-ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ የተነገረለት ግለሰብ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የ66 ዓመት ሰው ሲሆን፣ አሁን የፀረ ኤችአይቪ መድኃ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የቭጌኒ ፕሪጎዢን የሩሲያዋን ከተማ ሮስቶቭን ለቆ ሲወጣ-ከሁለት ሳምንት በፊት የቫግነር ቅጥረኛ ቡድን ከአመጹ በኋላ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቡድኑ መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን ጋር ተገናኝተው እንደነበር ክሬሚሊን አስታወቀች።-የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንዳሉት የቫግነር ቅጥረኛ ቡድንን የሚመራው ፕሪጎዢን፣ በሞስኮ በተካሄደው ስብስባ ላይ እንዲገኙ ከተጋበዙ 35 ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበር።-ከአስራ አንድ ቀናት በፊት በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ወቅትም ፕሬዝ...
የፎቶው ባለመብት Reuters-የአፍሪካ መሪዎች የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሐማስ በሰነዘረው ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት የተቀሰቀሰውን ግጭት እንዲያቆሙ ሁሉንም ተፋላሚ ወገኖች ጠይቀዋል።-የአገራቱ አቋም ግን ሙሉ ለሙሉ ተመሳሳይ አልነበረም።-ዛምቢያ፣ ኬንያ እና ጋና ሐማስን በግልጽ አውግዘዋል። እስራኤልን እንደሚደግፉም አስታውቀዋል። ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ደቡብ አፍሪካ ለፍልስጥኤማውያን ያላቸውን ድጋፍ በይፋ ገልጸዋል።-እስራኤል ባለፉት አስር ዓመታት በአህጉሪቱ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ አሳድጋለች። በርካታ የ...
የፎቶው ባለመብት pm office-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ-የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አገራቸው በኃይል እና በወረራ ማሳካት የምትፈልገው ነገር እንደሌለ በመግለጽ በአጎራባች አገራት ላይ ወረራ የመፈጸም ፍላጎት እንደሌላት ተናገሩ።-ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያ የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት ለአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ያደረጉት ንግግር በአካባቢው ውጥረትን እና ግጭትን ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሮ ቆይቷል።-ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ116ኛው የኢትዮጵያ ሠራዊት ቀን ዛሬ ጥቅምት...
የፎቶው ባለመብት GETTY IMAGES-መስከረም 26/2016 ዓ.ም ሐማስ እስራኤል ላይ ሊያደርስ ያቀደውን ጥቃት የአክስዮን ድርሻ ነጋዴዎች ቀድመው ያውቁ ነበር መባሉን በተመለከተ እስራኤል ምርመራ እንደምታካሂድ አስታውቃለች።-አንድ አካዳሚያዊ ጥናት የአክስዮን ድርሻ ነጋዴዎች በጥቃቱ ምክንያት የእስራኤል ኢኮኖሚ ሊያጋጥመው የሚችለው ሁኔታ ላይ “በመቆመር” ትልቅ ትርፍ አግኝተዋል ሲል አመልክቷል።-አጥኚዎቹ በጥቃቱ ጊዜ የአክስዮን ድርሻ ነጋዴዎች ‘ፈጣን ሽያጮችን’ ሲያከናውኑ እንደነበር ጠቅሰዋል።-‘ፈጣን ...