text
stringlengths
4
267
የርስቱን ቀሪዎች ኃጢአት ይቅር የሚል፣ በደላቸውንም የሚያልፍእንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? እሱ ለዘላለም አይቆጣም፤ታማኝ ፍቅር በማሳየት ደስ ይሰኛልና።
ዳግመኛ ምሕረት ያሳየናል፤ በደላችንን በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል። ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ ጥልቅ ባሕር ትጥላለህ።
በጥንት ዘመን ለአባቶቻችን በማልክላቸው መሠረትለያዕቆብ ታማኝነትን፣ለአብርሃም ደግሞ ታማኝ ፍቅርን ታሳያለህ።
እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ የያዕቆብ መሪዎችናየእስራኤል ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ስሙ። ትክክል የሆነውን ነገር ማወቅ አይገባችሁም?
ሆኖም እናንተ መልካም የሆነውን ትጠላላችሁ፤ ክፉ የሆነውን ደግሞ ትወዳላችሁ፤የሕዝቤን ቆዳ ትገፍፋላችሁ፤ ሥጋቸውንም ከአጥንቶቻቸው ትለያላችሁ።
የሕዝቤንም ሥጋ ትበላላችሁ፤ቆዳቸውንም ትገፍፋላችሁ፤አጥንቶቻቸውንም ትሰባብራላችሁ፤በድስት ውስጥ እንዳለ አጥንትና በአፍላል ውስጥ እንዳለ ሥጋ ትቆራርጧቸዋላችሁ።
በዚያን ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤እሱ ግን አይመልስላቸውም። ክፉ ድርጊት በመፈጸማቸው፣በዚያን ጊዜ ፊቱን ይሰውርባቸዋል።
ሕዝቤ እንዲባዝን በሚያደርጉ፣በጥርሳቸው ሲነክሱ ‘ሰላም!’ እያሉ በሚያውጁ፣አፋቸው ላይ የሚያደርጉት ነገር በማይሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ግን ጦርነት በሚያውጁ ነቢያት ላይ ይሖዋ እንዲህ ይላል።”
‘ሌሊት ይመጣባችኋል፤ ራእይም አታዩም፤ጨለማ ብቻ ይሆንባችኋል፤ ሟርትም አታሟርቱም። ፀሐይ በነቢያቱ ላይ ትጠልቅባቸዋለች፤ቀኑም ወደ ጨለማ ይለወጥባቸዋል።
ባለ ራእዮች ኀፍረት ይከናነባሉ፤ሟርተኞችም ይዋረዳሉ። ከአምላክ ዘንድ መልስ ስለማይኖርሁሉም አፋቸውን ይሸፍናሉ።’”
እኔ በበኩሌ ለያዕቆብ ዓመፁን፣ ለእስራኤልም ኃጢአቱን እንድነግርበይሖዋ መንፈስ ኃይልን፣ፍትሕንና ብርታትን ተሞልቻለሁ።
ፍትሕን የምትጸየፉና ቀና የሆነውን ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፣እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣የእስራኤልም ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ይህን ስሙ፤
ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ ኢየሩሳሌምንም በዓመፅ የምትገነቡ፣ ስሙ።
መሪዎቿ በጉቦ ይፈርዳሉ፤ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፤ነቢያቷም በገንዘብ ያሟርታሉ። ያም ሆኖ “ይሖዋ ከእኛ ጋር አይደለም? ምንም ዓይነት ጥፋት አይደርስብንም” እያሉ በይሖዋ ይመካሉ።
ስለዚህ በእናንተ የተነሳጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤የቤቱም ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች ይሆናል።
“መጥፎ ነገር ለሚሸርቡናበአልጋቸው ላይ ሆነው ክፉ ነገር ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ጠዋት ሲነጋ ያሰቡትን ይፈጽማሉ፤ምክንያቱም ይህን የሚያደርጉበት ኃይል በእጃቸው ነው።
እርሻን ይመኛሉ፤ ነጥቀውም ይይዙታል፤ቤቶችንም ይመኛሉ፤ ደግሞም ይወስዳሉ፤የሰውን ቤት፣የሰውንም ርስት አታለው ይወስዳሉ።
ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል።” ‘እነሆ፣ በዚህ ወገን ላይ ጥፋት ላመጣ አስቤአለሁ፤ እናንተም ከዚህ ጥፋት አታመልጡም። ከእንግዲህ ወዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤ ይህ የጥፋት ጊዜ ነውና።
በዚያም ቀን ሰዎች እናንተን አስመልክተው ምሳሌ ይናገራሉ፤በእናንተም የተነሳ አምርረው ያለቅሳሉ። እንዲህ ይላሉ፦ “እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል! የሕዝቤን ድርሻ ለሌሎች ሰጥቷል፤ ከእኔም ወስዶታል! እርሻዎቻችንን ለከዳተኛው ይሰጣል።”
ስለዚህ በይሖዋ ጉባኤ ውስጥ፣ምድሪቷን ለማከፋፈል በገመድ የሚለካ ሰው አይኖርህም።
“አትስበኩ!” ብለው ይሰብካሉ፤“እነዚህን ነገሮች መስበክ አይገባቸውም፤ውርደት አይደርስብንም!”
የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ “የይሖዋ መንፈስ አይታገሥም? እነዚህንስ ነገሮች ያደረገው እሱ ነው?” ሲባል ሰምተሃል? ቀና በሆነ መንገድ ለሚሄዱ የገዛ ቃሌ መልካም ነገር አያስገኝም?
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የገዛ ሕዝቤ ጠላት ሆኖ ተነስቷል። ከጦርነት እንደሚመለሱ ሰዎች በልበ ሙሉነት ከሚያልፉት ላይየሚያምረውን ጌጥ ከልብሱ ጋር በይፋ ገፈፋችሁ።
የሕዝቤን ሴቶች ከሚያምረው ቤታቸው አፈናቀላችኋቸው፤ክብሬን ከልጆቻቸው ለዘላለም ወሰዳችሁ።
ተነሱና ከዚህ ሂዱ፤ ይህ የማረፊያ ቦታ አይደለምና። ከርኩሰት የተነሳ ጥፋት ይመጣል፤ ጥፋቱም ከባድ ነው።
አንድ ሰው ነፋስንና ማታለያን ተከትሎ ቢሄድና “ስለ ወይን ጠጅና ስለ መጠጥ እሰብክላችኋለሁ” ብሎ ውሸት ቢናገር ይህ ሰው ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ሰባኪ ይሆናል!
ያዕቆብ ሆይ፣ ሁላችሁንም በእርግጥ እሰበስባለሁ፤ከእስራኤል የቀሩትን ያላንዳች ጥርጥር አንድ ላይ እሰበስባለሁ። በጉረኖ ውስጥ እንዳለ በግ፣በግጦሽ መስክ ላይ እንዳለም መንጋ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤ቦታውም በሕዝብ ሁካታ ይሞላል።’
የሚሰብረውም ከፊታቸው ይሄዳል፤እነሱም ሰብረው በበሩ በኩል ያልፋሉ፤ በዚያም ወጥተው ይሄዳሉ። ንጉሣቸው በፊታቸው ያልፋል፤ይሖዋም ከፊታቸው ይሄዳል።”
“አንቺ ጥቃት የተሰነዘረብሽ ሴት ልጅ ሆይ፣አሁን ሰውነትሽን ትተለትያለሽ፤ዙሪያችንን ተከበናል። የእስራኤልን ፈራጅ ጉንጩን በዱላ ይመቱታል።
ከይሁዳ አእላፋት መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽውቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፣ምንጩ ከጥንት፣ ከረጅም ዘመን በፊት የሆነ፣በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል።
ስለዚህ ልትወልድ የተቃረበችው ሴት እስክትወልድ ድረስአሳልፎ ይሰጣቸዋል። የቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ።
እሱ በይሖዋ ብርታትና በአምላኩ በይሖዋ ስም ታላቅነት ይነሳል፤መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል። እነሱም በዚያ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤በዚያን ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳልና።
እሱም ሰላም ያመጣል። አሦራዊው ምድራችንን ከወረረና የማይደፈሩ ማማዎቻችንን ከረገጠበእሱ ላይ ሰባት እረኞችን፣ አዎ ከሰው ልጆች መካከል ስምንት አለቆችን እናስነሳበታለን።
እነሱ የአሦርን ምድር በሰይፍ ይቀጣሉ፤የናምሩድንም ምድር መግቢያዎች ይቆጣጠራሉ። አሦራዊው ምድራችንን ሲወርና ክልላችንን ሲረግጥእሱ ይታደገናል።
የተረፉት የያዕቆብ ወገኖች በብዙ ሕዝቦች መካከል፣ከይሖዋ ዘንድ እንደሚወርድናሰውን ተስፋ እንደማያደርግወይም የሰው ልጆችን እንደማይጠባበቅ ጠል፣በአትክልትም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ።
በዱር እንስሳት መካከል እንዳለ አንበሳ፣በሚያልፍበት ጊዜ እየረጋገጠና እየሰባበረ እንደሚሄድ፣በበግ መንጎች መካከል እንዳለ ደቦል አንበሳ፣የተረፉት የያዕቆብ ወገኖችም በብሔራት፣በብዙ ሕዝቦችም መካከል እንዲሁ ይሆናሉ፤ሊያስጥል የሚችልም አይኖርም።
እጅህ ከባላጋራዎችህ በላይ ከፍ ከፍ ትላለች፤ጠላቶችህም ሁሉ ይወገዳሉ።”
“በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ፈረሶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ ሠረገሎችህንም አጠፋለሁ።
በምድርህ ላይ የሚገኙትን ከተሞች እደመስሳለሁ፤የተመሸጉ ስፍራዎችህንም ሁሉ አፈራርሳለሁ።
ጥንቆላህን አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም አስማተኛ በመካከልህ አይኖርም።
የተቀረጹ ምስሎችህንና ዓምዶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ወዲህ ለእጆችህ ሥራ አትሰግድም።
የማምለኪያ ግንዶችህንም ከመካከልህ እነቅላለሁ፤ከተሞችህንም እደመስሳለሁ።
ታዛዥ ያልሆኑትን ብሔራት፣በቁጣና በንዴት እበቀላለሁ።”
በዘመኑ መጨረሻየይሖዋ ቤት ተራራከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ወደዚያ ይጎርፋሉ።
ብዙ ብሔራትም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራናወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ። እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
እሱ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤በሩቅ ካሉ ኃያላን ብሔራት ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል። እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ። አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።
እያንዳንዱም ከወይኑና ከበለስ ዛፉ ሥር ይቀመጣል፤የሚያስፈራቸውም አይኖርም፤የሠራዊት ጌታ የይሖዋ አፍ ተናግሯልና።
ሕዝቦች ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው በአምላካቸው ስም ይሄዳሉ፤እኛ ግን በአምላካችን በይሖዋ ስም ለዘላለም እንሄዳለን።
“በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣“የሚያነክሰውን እሰበስባለሁ፤ደግሞም የተበተኑትንናያንገላታኋቸውን ሰዎች አንድ ላይ እሰበስባለሁ።
የሚያነክሰው የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩት አደርጋለሁ፤ወደ ሩቅ ስፍራ የተወሰደውንም ኃያል ብሔር አደርገዋለሁ፤ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምበጽዮን ተራራ በእነሱ ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል።
አንተም የመንጋው ማማ፣የጽዮን ሴት ልጅ ጉብታ ሆይ፣አንተ ወዳለህበት ይመለሳል፤ አዎ፣ የመጀመሪያው ግዛትህ፣የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ይመለሳል።
አሁንስ ድምፅሽን ከፍ አድርገሽ የምትጮኺው ለምንድን ነው? ንጉሥ የለሽም?ወይስ አማካሪሽ ጠፍቷል?ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት የምትሠቃዪው ለዚህ ነው?
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴትተንፈራገጪ፤ አቃስቺም፤አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትሰፍሪያለሽና። እስከ ባቢሎን ድረስ ትሄጃለሽ፤በዚያም ይታደግሻል፤በዚያ ይሖዋ ከጠላቶችሽ እጅ ይዋጅሻል።
አሁንም ብዙ ብሔራት በአንቺ ላይ ይሰበሰባሉ፤እነሱም ‘የረከሰች ትሁን፤ዓይኖቻችንም ይህ በጽዮን ላይ ሲደርስ ይመልከቱ’ ይላሉ።
ይሁንና የይሖዋን ሐሳብ አያውቁም፤ዓላማውንም አይረዱም፤እሱ ገና እንደታጨደ እህል ወደ አውድማ ይሰበስባቸዋልና።
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ተነስተሽ እህሉን ውቂ፤ቀንድሽን ወደ ብረት፣ሰኮናሽንም ወደ መዳብ እለውጣለሁና፤አንቺም ብዙ ሕዝቦችን ታደቂያለሽ። በማጭበርበር ያገኙት ትርፍ ለይሖዋ የተወሰነ እንዲሆን፣ሀብታቸውም ለምድር ሁሉ ጌታ ብቻ እንዲውል ታደርጊያለሽ።”
ይሖዋ የሚለውን እባካችሁ ስሙ። ተነሱ፤ በተራሮች ፊት ሙግታችሁን አቅርቡ፤ኮረብቶችም ቃላችሁን ይስሙ።
ተራሮች ሆይ፣ እናንተ ጽኑ የምድር መሠረቶች፣የይሖዋን ሙግት ስሙ፤ይሖዋ ከሕዝቡ ጋር ሙግት አለውና፤ከእስራኤልም ጋር ይከራከራል፦
“ሕዝቤ ሆይ፣ ምን ያደረግኩህ ነገር አለ? ያደከምኩህስ ምን አድርጌ ነው? እስቲ መሥክርብኝ።
ከግብፅ ምድር አወጣሁህ፤ከባርነትም ቤት ዋጀሁህ፤ሙሴን፣ አሮንንና ሚርያምን በፊትህ ላክሁ።
ሕዝቤ ሆይ፣ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያሴረብህን ነገር፣የቢዖር ልጅ በለዓምም የሰጠውን መልስ እባክህ አስታውስ፤የይሖዋን የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድከሺቲም እስከ ጊልጋል ድረስ የሆነውን ነገር አስታውስ።”
በይሖዋ ፊት ምን ይዤ ልቅረብ? ከፍ ባለ ስፍራ በሚኖረው አምላክ ፊት ምን ይዤ ልስገድ? ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችናየአንድ ዓመት ጥጃዎች ይዤ ልቅረብ?
ይሖዋ በሺህ በሚቆጠሩ አውራ በጎችወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋል? ለሠራሁት በደል የበኩር ወንድ ልጄን፣ለሠራሁትም ኃጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብ?
ሰው ሆይ፣ መልካም የሆነውን ነግሮሃል። ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን እንድታደርግ፣ ታማኝነትን እንድትወድናልክህን አውቀህ ከአምላክህ ጋር እንድትሄድ ብቻ ነው!
የይሖዋ ድምፅ ከተማዋን ይጣራል፤ጥበበኞች ስምህን ይፈራሉ። የበትሩን ድምፅና ቅጣቱን የወሰነውን ስሙ።
ክፉ በሆነ ሰው ቤት፣ በክፋት የተገኘ ሀብትእንዲሁም አስጸያፊ የሆነ ጎዶሎ የኢፍ መስፈሪያ አሁንም አለ?
አባይ ሚዛንና የተዛቡ የድንጋይ መለኪያዎች የያዘ ከረጢት እየተጠቀምኩንጹሕ ሥነ ምግባር ሊኖረኝ ይችላል?
ባለጸጎቿ በግፍ የተሞሉ ናቸው፤ነዋሪዎቿም ውሸት ይናገራሉ፤ምላሳቸው በአፋቸው ውስጥ አታላይ ነው።
“ስለዚህ መትቼ አቆስልሃለሁ፤ከኃጢአትህ የተነሳ አጠፋሃለሁ።
ትበላለህ፤ ግን አትጠግብም፤ሆድህም ባዶ ይሆናል። የምትወስዳቸውን ነገሮች ጠብቀህ ማቆየት አትችልም፤ጠብቀህ ያቆየኸውንም ነገር ሁሉ ለሰይፍ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።
ዘር ትዘራለህ፤ ሆኖም የምታጭደው ነገር አይኖርም። የወይራ ፍሬ ትጨምቃለህ፤ ሆኖም ዘይቱን አትጠቀምበትም፤ደግሞም አዲስ ወይን ትጨምቃለህ፤ ሆኖም የወይን ጠጅ አትጠጣም።
የኦምሪን ደንቦችና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ትከተላላችሁና፤ምክራቸውንም ተከትላችሁ ትሄዳላችሁ። ስለዚህ አንተን መቀጣጫ፣ነዋሪዎቿንም ማፏጫ አደርጋለሁ፤የሰዎችንም ፌዝ ትሸከማላችሁ።”
በነነዌ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው፦
ይሖዋ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግና የሚበቀል አምላክ ነው፤ይሖዋ ይበቀላል፤ ቁጣውንም ለመግለጽ ዝግጁ ነው። ይሖዋ ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ለጠላቶቹም ቁጣ ያከማቻል።
ይሖዋ ለቁጣ የዘገየ ነው፤ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ይሁንና ይሖዋ ተገቢውን ቅጣት ከመስጠት ፈጽሞ ወደኋላ አይልም። መንገዱ በአደገኛ ነፋስና በወጀብ ውስጥ ነው፤ደመናት ከእግሩ በታች እንዳለ አቧራ ናቸው።
ባሕሩን ይገሥጻል፤ ያደርቀዋልም፤ወንዞቹንም በሙሉ ያደርቃቸዋል። ባሳንና ቀርሜሎስ ይጠወልጋሉ፤የሊባኖስ አበባዎችም ይጠወልጋሉ።
ከእሱ የተነሳ ተራሮች ይንቀጠቀጣሉ፤ኮረብቶችም ይቀልጣሉ። ከፊቱም የተነሳ ምድር፣የብስና በላዩ የሚኖሩት ሁሉ ይናወጣሉ።
በቁጣው ፊት ማን ሊቆም ይችላል? የንዴቱን ትኩሳት ሊቋቋም የሚችልስ ማን ነው? ቁጣው እንደ እሳት ይፈስሳል፤ዓለቶችም ከእሱ የተነሳ ይፈረካከሳሉ።
ይሖዋ ጥሩ ነው፤ በጭንቀትም ቀን መሸሸጊያ ነው። እሱን መጠጊያ ማድረግ የሚፈልጉትን ያውቃል።
ጠራርጎ በሚወስድ ጎርፍ ስፍራዋን ፈጽሞ ያጠፋል፤ጠላቶቹንም ጨለማ ያሳድዳቸዋል።
በይሖዋ ላይ የምታሴሩት ምንድን ነው? እሱ ፈጽሞ ያጠፋል። ጭንቀት ዳግመኛ አይመጣም።
እርስ በርሳቸው እንደ እሾህ ተጠላልፈዋልና፤መጠጥ ጠጥተው እንደሰከሩ ሰዎች ናቸው፤ሆኖም እንደደረቀ ገለባ እሳት ይበላቸዋል።
በይሖዋ ላይ ክፉ ነገር የሚያሴር፣ከንቱ ምክርም የሚሰጥ ከመካከልሽ ይወጣል።
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ምንም እንኳ የተሟላ ኃይል ያላቸውና ብዙዎች ቢሆኑምይቆረጣሉ፤ ደግሞም ይጠፋሉ። መከራ አሳይቼሃለሁ፤ ከዚያ በኋላ ግን መከራ አላመጣብህም።
አሁንም ቀንበሩን ከአንተ ላይ እሰብራለሁ፤እስራትህንም እበጥሳለሁ።
ይሖዋ አንተን በተመለከተ እንዲህ ሲል አዟል፦‘ከእንግዲህ ስምህን የሚያስጠራ አይኖርም። የተቀረጹትን ምስሎችና ከብረት የተሠሩትን ሐውልቶች ከአማልክትህ ቤት አስወግዳለሁ። የተናቅክ ስለሆንክ መቃብር አዘጋጅልሃለሁ።’
እነሆ ምሥራች ይዞ የሚመጣ፣ሰላምንም የሚያውጅ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው። ይሁዳ ሆይ፣ በዓሎችሽን አክብሪ፤ ስእለትሽን ፈጽሚ፤ከእንግዲህ ወዲህ የማይረባ ሰው በመካከልሽ አያልፍምና። እንዲህ ያለው ሰው ሙሉ በሙሉ ይወገዳል።”
ለደም አፍሳሿ ከተማ ወዮላት! በማታለልና በዝርፊያ የተሞላች ናት። ከማደን ቦዝና አታውቅም!
የአለንጋ ድምፅና የመንኮራኩር ኳኳቴ ይሰማል፤ፈረሶች ሲጋልቡና ሠረገሎች ሲፈተለኩ ይታያል።
ፈረስ ጋላቢው ይጋልባል፤ ሰይፉ ያንጸባርቃል፤ ጦሩ ያብረቀርቃል፤የተገደሉት በጣም ብዙ ናቸው፤ የአስከሬን ክምር ይታያል፤ሬሳው ስፍር ቁጥር የለውም። አስከሬኖቹም ያደናቅፏቸዋል።
ይህ የሆነው ዝሙት አዳሪዋ በምትፈጽመው በርካታ የአመንዝራነት ተግባር የተነሳ ነው፤እሷ ብሔራትን በምንዝሯ፣ ወገኖችንም በጥንቆላዋ የምታጠምድ፣የምታምርና የምትማርክ እንዲሁም በጥንቆላ የተካነች ናት።
“እነሆ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤“ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ ድረስ እገልበዋለሁ፤ብሔራትም እርቃንሽን፣መንግሥታትም ነውርሽን እንዲያዩ አደርጋለሁ።
ቆሻሻ እደፋብሻለሁ፤የተናቅሽ አደርግሻለሁ፤ማላገጫም እንድትሆኚ አደርጋለሁ።
አንቺን የሚያይ ሁሉ ከአንቺ ይሸሻል፤ደግሞም ‘ነነዌ ወድማለች! የሚያዝንላት ማን ነው?’ ይላል። አንቺን የሚያጽናና ከየት ማግኘት እችላለሁ?
አንቺ በአባይ የመስኖ ቦዮች አጠገብ ከነበረችው ከኖአሞን ትሻያለሽ? እሷ በውኃ የተከበበች ነበረች፤ባሕሩም ሀብት ያስገኝላት፣ እንደ ቅጥርም ሆኖ ያገለግላት ነበር።
ኢትዮጵያና ግብፅ ገደብ የለሽ የኃይል ምንጮቿ ነበሩ። ፑጥና ሊቢያውያን ረዳቶቿ ነበሩ።
ይሁንና እሷም እንኳ በግዞት ተወሰደች፤ተማርካም ሄደች። ልጆቿም በየመንገዱ ማዕዘን ተፈጠፈጡ። በተከበሩ ሰዎቿ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ታላላቅ ሰዎቿም ሁሉ በእግር ብረት ታሰሩ።
አንቺም ትሰክሪያለሽ፤ደግሞም ትሰወሪያለሽ። ከጠላት የምትሸሸጊበት ቦታ ትፈልጊያለሽ።
ምሽጎችሽ ሁሉ የመጀመሪያዎቹን የበሰሉ ፍሬዎች እንደያዙ የበለስ ዛፎች ናቸው፤ዛፎቹ ከተነቀነቁ ፍሬዎቹ ረግፈው በበላተኛ አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።
እነሆ፣ ወታደሮችሽ በመካከልሽ እንዳሉ ሴቶች ናቸው። የምድርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ይከፈታሉ። የበሮችሽን መቀርቀሪያዎች እሳት ይበላቸዋል።