text
stringlengths
4
267
ዮሐንስ ከግመል ፀጉር የተሠራ ልብስ ይለብስ፣ ወገቡም ላይ የቆዳ ቀበቶ ይታጠቅ ነበር። ምግቡ አንበጣና የዱር ማር ነበር።
በኢየሩሳሌምና በመላዋ ይሁዳ እንዲሁም በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ክልል ሁሉ የሚኖሩ ሰዎች ወደ እሱ ይመጡ ነበር፤
ደግሞም ኃጢአታቸውን በግልጽ እየተናዘዙ ዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ በእሱ ይጠመቁ ነበር።
ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደሚያጠምቅበት ቦታ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእፉኝት ልጆች፣ ከሚመጣው ቁጣ እንድትሸሹ ያስጠነቀቃችሁ ማን ነው?
እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ።
‘እኛ እኮ አባታችን አብርሃም ነው’ ብላችሁ አታስቡ። አምላክ ለአብርሃም ከእነዚህ ድንጋዮች ልጆች ሊያስነሳለት እንደሚችል ልነግራችሁ እወዳለሁ።
መጥረቢያው ዛፎቹ ሥር ተቀምጧል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ እሳት ውስጥ ይጣላል።
እኔ በበኩሌ ንስሐ በመግባታችሁ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይበረታል፤ እኔ ጫማውን ለማውለቅ እንኳ ብቁ አይደለሁም። እሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።
ላይዳውን በእጁ ይዟል፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጸዳል፤ ስንዴውንም ወደ ጎተራ ያስገባል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።
ዮሐንስ ግን “በአንተ መጠመቅ የሚያስፈልገኝ እኔ ሆኜ ሳለ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህ?” ብሎ ሊከለክለው ሞከረ።
ኢየሱስም መልሶ “ግድ የለም እሺ በለኝ፤ በዚህ መንገድ ጽድቅ የሆነውን ሁሉ መፈጸማችን ተገቢ ነው” አለው። በዚህ ጊዜ ዮሐንስ ፈቀደለት።
ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃው ወጣ፤ እነሆ፣ ሰማያት ተከፈቱ፤ የአምላክም መንፈስ በእሱ ላይ እንደ ርግብ ሲወርድ አየ።
ደግሞም “በጣም የምደሰትበት የምወደው ልጄ ይህ ነው” የሚል ድምፅ ከሰማያት ተሰማ።
ከዚህ በኋላ ጀልባ በመሳፈር ባሕሩን ተሻግሮ ወደ ራሱ ከተማ መጣ።
በዚያም ሰዎች ቃሬዛ ላይ የተኛ አንድ ሽባ ሰው ወደ እሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ፣ ሽባውን “ልጄ ሆይ አይዞህ! ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው።
በዚህ ጊዜ አንዳንድ ጸሐፍት በልባቸው “ይህ ሰው እኮ አምላክን እየተዳፈረ ነው” አሉ።
ኢየሱስ ሐሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ “በልባችሁ ክፉ ነገር የምታስቡት ለምንድን ነው?
ለመሆኑ ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሏል’ ከማለትና ‘ተነስተህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀላል?
ይሁን እንጂ የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ . . .” አላቸውና ሽባውን “ተነስ፣ ቃሬዛህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።
እሱም ተነስቶ ወደ ቤቱ ሄደ።
ሕዝቡም ይህን ሲያዩ በፍርሃት ተዋጡ፤ እንዲህ ያለ ሥልጣን ለሰው የሰጠውንም አምላክ አከበሩ።
ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ እየሄደ ሳለ ማቴዎስ የሚባል ሰው በቀረጥ መሰብሰቢያው ቦታ ተቀምጦ አየና “ተከታዬ ሁን” አለው። በዚህ ጊዜ ተነስቶ ተከተለው።
በኋላም በማቴዎስ ቤት እየበላ ሳለ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ኃጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይበሉ ጀመር።
ፈሪሳውያን ግን ይህን ባዩ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላው ለምንድን ነው?” አሏቸው።
ኢየሱስም የተናገሩትን ሰምቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።
እንግዲያው ሄዳችሁ ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን እንጂ መሥዋዕትን አይደለም’ የሚለውን ቃል ትርጉም አስተውሉ። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ልጠራ ነውና።”
ከዚያም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እሱ መጥተው “እኛና ፈሪሳውያን ዘወትር ስንጾም የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት።
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የሙሽራው ጓደኞች ሙሽራው ከእነሱ ጋር እስካለ ድረስ የሚያዝኑበት ምን ምክንያት አለ? ሆኖም ሙሽራው ከእነሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ።
በአሮጌ ልብስ ላይ ውኃ ያልነካው አዲስ ጨርቅ የሚጥፍ ሰው የለም፤ አዲሱ ጨርቅ ሲሸበሸብ ልብሱን ስለሚስበው ቀዳዳው የባሰ ይሰፋልና።
ደግሞም ሰዎች ባረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ አያስቀምጡም። እንዲህ ቢያደርጉ አቁማዳው ይፈነዳል፤ ወይኑ ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል። ነገር ግን ሰዎች አዲስ የወይን ጠጅ የሚያስቀምጡት በአዲስ አቁማዳ ነው፤ በመሆኑም ሁለቱም ሳይበላሹ ይቆያሉ።”
ይህን እየነገራቸው ሳለ አንድ የምኩራብ አለቃ ወደ እሱ መጥቶ በመስገድ “እስካሁን ልጄ ሳትሞት አትቀርም፤ ቢሆንም መጥተህ እጅህን ጫንባት፤ ዳግመኛም ሕያው ትሆናለች” አለው።
ኢየሱስም ተነስቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው።
እነሆም፣ ለ12 ዓመት ደም ይፈሳት የነበረች አንዲት ሴት ከኋላ መጥታ የልብሱን ዘርፍ ነካች፤
“ልብሱን ብቻ እንኳ ብነካ እድናለሁ” ብላ ታስብ ነበርና።
ኢየሱስ ወደ ኋላ ዞር ብሎ አያትና “ልጄ ሆይ አይዞሽ! እምነትሽ አድኖሻል” አላት። ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ሴትየዋ ዳነች።
ኢየሱስ ወደ ምኩራብ አለቃው ቤት ሲደርስ ዋሽንት ነፊዎቹን እንዲሁም የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ
“እስቲ አንዴ ውጡ፤ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አለ። በዚህ ጊዜ በማፌዝ ይስቁበት ጀመር።
ሕዝቡ ከወጣ በኋላ ወደ ውስጥ ገብቶ እጇን ያዛት፤ ልጅቷም ተነሳች።
ይህም ነገር በዚያ አገር ሁሉ በሰፊው ተወራ።
ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ ሁለት ዓይነ ስውሮች “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልን” ብለው እየጮኹ ተከተሉት።
ወደ ቤት ከገባ በኋላ ዓይነ ስውሮቹ ወደ እሱ መጡ፤ ኢየሱስም “ዓይናችሁን ላበራላችሁ እንደምችል ታምናላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እነሱም “አዎ ጌታ ሆይ” ብለው መለሱለት።
ከዚያም ዓይናቸውን ዳስሶ “እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ” አላቸው።
ዓይናቸውም በራ። ኢየሱስም “ማንም ሰው ስለዚህ ጉዳይ እንዳያውቅ ተጠንቀቁ” ሲል አጥብቆ አሳሰባቸው።
እነሱ ግን ከወጡ በኋላ በዚያ አካባቢ ሁሉ ስለ እሱ በይፋ አወሩ።
እነሱም ሲወጡ፣ ሰዎች ጋኔን ያደረበት ዱዳ ሰው ወደ እሱ አመጡ፤
ጋኔኑን ካስወጣለት በኋላ ዱዳው ተናገረ። ሕዝቡም እጅግ ተደንቀው “በእስራኤል ምድር እንዲህ ያለ ነገር ታይቶ አያውቅም” አሉ።
ፈሪሳውያን ግን “አጋንንትን የሚያስወጣው በአጋንንት አለቃ ነው” ይሉ ነበር።
ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፣ የመንግሥቱን ምሥራች እየሰበከ እንዲሁም ማንኛውንም ዓይነት በሽታና ማንኛውንም ዓይነት ሕመም እየፈወሰ በየከተማውና በየመንደሩ ይዞር ጀመር።
ሕዝቡንም ባየ ጊዜ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተገፈውና ተጥለው ስለነበር እጅግ አዘነላቸው።
ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “አዎ፣ አዝመራው ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂት ናቸው።
ስለዚህ የመከሩ ሥራ ኃላፊ ወደ መከሩ፣ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።”
ኢየሱስ ከቤተ መቅደሱ ወጥቶ እየሄደ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ የቤተ መቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ወደ እሱ ቀረቡ።
እሱም መልሶ “ይህን ሁሉ ታያላችሁ? እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ ሁሉ ሳይፈርስ እንዲህ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደተነባበረ ከቶ አይኖርም” አላቸው።
በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እሱ መጥተው “እስቲ ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው? የመገኘትህና የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ምልክትስ ምንድን ነው?” አሉት።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ማንም እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ፤
ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ።
ጦርነትና የጦርነት ወሬ ትሰማላችሁ። በዚህ ጊዜ እንዳትደናገጡ ተጠንቀቁ፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸው የግድ ነው፤ ሆኖም ፍጻሜው ገና ነው።
“ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳልና፤ በተለያየ ስፍራ የምግብ እጥረትና የምድር ነውጥ ይከሰታል።
እነዚህ ነገሮች ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
“በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፣ ይገድሏችኋል እንዲሁም በስሜ ምክንያት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።
በተጨማሪም ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ እርስ በርሳቸውም ይጠላላሉ።
ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ፤
ክፋት እየበዛ ስለሚሄድ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል።
እስከ መጨረሻው የጸና ግን ይድናል።
ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።
“ስለዚህ ነቢዩ ዳንኤል በተናገረው መሠረት ጥፋት የሚያመጣው ‘ርኩስ ነገር’ በተቀደሰ ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል፤
በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ።
በጣሪያ ላይ ያለ ሰው ዕቃውን ከቤቱ ለመውሰድ አይውረድ፤
በእርሻም ያለ መደረቢያውን ለመውሰድ አይመለስ።
በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው!
ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት ቀን እንዳይሆን ዘወትር ጸልዩ፤
ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሆኖ የማያውቅ ዳግመኛም የማይሆን ታላቅ መከራ ይከሰታል።
እንዲያውም ቀኖቹ ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ ሁሉ ባልዳነ ነበር፤ ሆኖም ለተመረጡት ሲባል ቀኖቹ ያጥራሉ።
“በዚያን ጊዜ ማንም ‘እነሆ፣ ክርስቶስ ይኸውላችሁ’ ወይም ‘ያውላችሁ’ ቢላችሁ አትመኑ።
ምክንያቱም ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችና አስደናቂ ነገሮች ያደርጋሉ።
እንግዲህ አስቀድሜ አስጠንቅቄያችኋለሁ።
ስለዚህ ሰዎች ‘እነሆ፣ በምድረ በዳ ነው’ ቢሏችሁ ወደዚያ አትውጡ፤ ‘እነሆ፣ ቤት ውስጥ በውስጠኛው ክፍል ይገኛል’ ቢሏችሁ አትመኑ።
መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚያበራ ሁሉ የሰው ልጅ መገኘትም እንዲሁ ይሆናል።
በድን ባለበት ሁሉ ንስሮች ይሰበሰባሉ።
“በእነዚያ ቀናት ከሚኖረው መከራ በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይላትም ይናወጣሉ።
ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ የምድር ወገኖችም ሁሉ በሐዘን ደረታቸውን ይደቃሉ፤ የሰው ልጅም በኃይልና በታላቅ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል።
እሱም መላእክቱን በታላቅ የመለከት ድምፅ ይልካል፤ እነሱም ከአራቱ ነፋሳት፣ ከአንዱ የሰማይ ዳርቻ እስከ ሌላው የሰማይ ዳርቻ ለእሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።
“እንግዲያው ይህን ምሳሌ ከበለስ ዛፍ ተማሩ፦ ቅርንጫፎቿ ሲለመልሙና ቅጠሎቿ ሲያቆጠቁጡ በጋ እንደቀረበ ታውቃላችሁ።
በተመሳሳይ እናንተም እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስታዩ የሰው ልጅ ደጃፍ ላይ እንደደረሰ እርግጠኞች ሁኑ።
እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ ፈጽሞ አያልፍም።
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።
“ስለዚያ ቀንና ሰዓት ከአብ ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ሆኑ ወልድ፣ ማንም አያውቅም።
በኖኅ ዘመን እንደነበረው ሁሉ የሰው ልጅ መገኘትም እንደዚሁ ይሆናል።
ከጥፋት ውኃ በፊት በነበረው ዘመን ኖኅ ወደ መርከቡ እስከገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ወንዶች ያገቡ፣ ሴቶችም ይዳሩ ነበር፤
የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉንም ጠራርጎ እስከወሰዳቸው ጊዜ ድረስ ምንም አላስተዋሉም፤ የሰው ልጅ መገኘትም እንደዚሁ ይሆናል።
በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ቦታ ይሠራሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው እዚያው ይተዋል።
ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላዋ እዚያው ትተዋለች።
ስለዚህ ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ ስለማታውቁ ምንጊዜም ነቅታችሁ ጠብቁ።
“ነገር ግን ይህን እወቁ፦ አንድ ሰው ሌባ በየትኛው ክፍለ ሌሊት እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ ነቅቶ በጠበቀና ቤቱ እንዳይደፈር በተከላከለ ነበር።
ስለዚህ እናንተም የሰው ልጅ ባላሰባችሁት ሰዓት ስለሚመጣ ዝግጁ ሁኑ።
“በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንዲሰጣቸው ጌታው በቤተሰቦቹ ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ በእርግጥ ማን ነው?
ጌታው በሚመጣበት ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ ካገኘው ያ ባሪያ ደስተኛ ነው!
እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታው በንብረቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
“ነገር ግን ያ ክፉ ባሪያ በልቡ ‘ጌታዬ ይዘገያል’ ብሎ ቢያስብ