text
stringlengths
4
267
ደግሞም ባልንጀሮቹ የሆኑትን ባሪያዎች መደብደብ ቢጀምር እንዲሁም ከሰካራሞች ጋር ቢበላና ቢጠጣ፣
የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቀው ቀንና ባላሰበው ሰዓት ይመጣል፤
ከባድ ቅጣት ይቀጣዋል፤ ዕጣውንም ከግብዞች ጋር ያደርገዋል። በዚያም ያለቅሳል፤ ጥርሱንም ያፋጫል።
በነጋ ጊዜም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች በሙሉ ኢየሱስን ለመግደል አንድ ላይ ተማከሩ።
ካሰሩት በኋላ ወስደው ለአገረ ገዢው ለጲላጦስ አስረከቡት።
አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ኢየሱስ እንደተፈረደበት ባየ ጊዜ ጸጸት ተሰምቶት 30ዎቹን የብር ሳንቲሞች ወደ ካህናት አለቆቹና ወደ ሽማግሌዎቹ ይዞ በመምጣት
“ንጹሕ ሰው አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ” አለ። እነሱም “ታዲያ እኛ ምን አገባን? የራስህ ጉዳይ ነው!” አሉት።
ስለዚህ የብር ሳንቲሞቹን ቤተ መቅደሱ ውስጥ በትኖ ወጣ። ከዚያም ሄደና ታንቆ ሞተ።
የካህናት አለቆቹ ግን የብር ሳንቲሞቹን ወስደው “ይህ ገንዘብ የደም ዋጋ ስለሆነ ግምጃ ቤት ውስጥ መግባት የለበትም” አሉ።
ከተመካከሩም በኋላ ለእንግዶች የመቃብር ቦታ እንዲሆን በገንዘቡ የሸክላ ሠሪውን መሬት ገዙበት።
በመሆኑም ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተብሎ ይጠራል።
በዚህ ጊዜ በነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፦ “ከእስራኤል ልጆች አንዳንዶቹ የገመቱትን፣ ለሰውየው የወጣውን የዋጋ ተመን ይኸውም 30ዎቹን የብር ሳንቲሞች ወሰዱ፤
ይሖዋ ባዘዘኝም መሠረት ሳንቲሞቹን ለሸክላ ሠሪው መሬት ከፈሉ።”
ኢየሱስም አገረ ገዢው ፊት ቀረበ፤ አገረ ገዢውም “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም መልሶ “አንተው ራስህ ተናገርከው” አለው።
የካህናት አለቆቹና ሽማግሌዎቹ በከሰሱት ጊዜ ግን ምንም መልስ አልሰጠም።
በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “በስንት ነገር እየመሠከሩብህ እንዳሉ አትሰማም?” አለው።
እሱ ግን አገረ ገዢው እጅግ እስኪደነቅ ድረስ አንዲት ቃል እንኳ አልመለሰለትም።
አገረ ገዢው ሁልጊዜ በዚህ በዓል ወቅት፣ ሕዝቡ እንዲፈታላቸው የሚፈልጉትን ማንኛውንም እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው።
በዚያን ጊዜ በዓመፀኝነቱ የታወቀ በርባን የተባለ እስረኛ ነበራቸው።
በመሆኑም ሕዝቡ በተሰበሰቡ ጊዜ ጲላጦስ “ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ? በርባንን ወይስ ክርስቶስ የሚባለውን ኢየሱስን?” አላቸው።
ጲላጦስ ይህን ያለው አሳልፈው የሰጡት በቅናት ተነሳስተው እንደሆነ ያውቅ ስለነበር ነው።
በተጨማሪም በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “በእሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ስለተሠቃየሁ በዚያ ጻድቅ ሰው ላይ ምንም ነገር እንዳታደርግ” የሚል መልእክት ላከችበት።
ይሁንና የካህናት አለቆቹና ሽማግሌዎቹ በርባን እንዲፈታላቸው፣ ኢየሱስ ግን እንዲገደል ይጠይቁ ዘንድ ሕዝቡን አግባቡ።
አገረ ገዢውም መልሶ “ከሁለቱ ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። እነሱም “በርባንን” አሉ።
ጲላጦስም “እንግዲያው ክርስቶስ የሚባለውን ኢየሱስን ምን ባደርገው ይሻላል?” አላቸው። ሁሉም “ይሰቀል!” አሉ።
እሱም “ለምን? ምን ያጠፋው ነገር አለ?” አላቸው። እነሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ የባሰ መጮኻቸውን ቀጠሉ።
ጲላጦስ ያደረገው ጥረት ምንም የፈየደው ነገር እንደሌለ ከዚህ ይልቅ ሁከት እያስነሳ መሆኑን በመገንዘብ “ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ። ከዚህ በኋላ ተጠያቂ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ” በማለት ውኃ አምጥቶ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።
በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” አሉ።
ከዚያም በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ካስገረፈው በኋላ በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።
በዚህ ጊዜ የአገረ ገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ አገረ ገዢው መኖሪያ ቤት ወሰዱት፤ ሠራዊቱንም ሁሉ በዙሪያው አሰባሰቡ።
ልብሱንም ገፈው ቀይ መጎናጸፊያ አለበሱት፤
የእሾህ አክሊል ጎንጉነውም በራሱ ላይ ደፉበት፤ በቀኝ እጁም የመቃ ዘንግ አስያዙት። በፊቱ ተንበርክከውም “የአይሁዳውያን ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ አሾፉበት።
ደግሞም ተፉበት፤ መቃውንም ወስደው ራሱን ይመቱት ጀመር።
ሲያፌዙበት ከቆዩ በኋላም መጎናጸፊያውን ገፈው የራሱን መደረቢያዎች አለበሱት፤ ከዚያም በእንጨት ላይ እንዲቸነከር ይዘውት ሄዱ።
እየሄዱም ሳሉ ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው አገኙ። ሰውየውንም ኢየሱስ የሚሰቀልበትን የመከራ እንጨት እንዲሸከም አስገደዱት።
የራስ ቅል ቦታ የሚል ትርጉም ወዳለው ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ በደረሱ ጊዜ
ሐሞት የተቀላቀለበት የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤ እሱ ግን ከቀመሰው በኋላ ሊጠጣው አልፈለገም።
እንጨት ላይ ከቸነከሩት በኋላ ዕጣ ተጣጥለው መደረቢያዎቹን ተከፋፈሉ፤
በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር።
እንዲሁም “ይህ የአይሁዳውያን ንጉሥ ኢየሱስ ነው” የሚል የተከሰሰበትን ጉዳይ የሚገልጽ ጽሑፍ ከራሱ በላይ አንጠልጥለው ነበር።
በዚያን ጊዜ ሁለት ዘራፊዎች ከእሱ ጋር፣ አንዱ በቀኙ ሌላው ደግሞ በግራው በእንጨት ላይ ተሰቅለው ነበር።
በዚያ የሚያልፉም ይሰድቡት ነበር፤ ራሳቸውንም እየነቀነቁ
“ቤተ መቅደሱን አፍርሼ በሦስት ቀን እሠራዋለሁ ባይ፣ እስቲ ራስህን አድን! የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ከተሰቀልክበት እንጨት ላይ ውረድ!” ይሉት ነበር።
የካህናት አለቆችም እንደዚሁ ከጸሐፍትና ከሽማግሌዎች ጋር ሆነው እንዲህ እያሉ ያፌዙበት ጀመር፦
“ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አልቻለም! የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ እስቲ አሁን ከተሰቀለበት እንጨት ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን።
በአምላክ ታምኗል፤ ‘የአምላክ ልጅ ነኝ’ ብሎ የለ፤ አምላክ ከወደደው እስቲ አሁን ያድነው።”
ከእሱ ጋር በእንጨት ላይ የተሰቀሉት ዘራፊዎችም እንኳ ሳይቀሩ ልክ እንደዚሁ ይነቅፉት ነበር።
ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ አገሩ በሙሉ በጨለማ ተሸፈነ።
በዘጠኝ ሰዓት ገደማ ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ “ኤሊ፣ ኤሊ፣ ላማ ሳባቅታኒ?” ብሎ ጮኸ፤ ይህም “አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው።
በዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ይህን ሲሰሙ “ይህ ሰው ኤልያስን እየተጣራ ነው” ይሉ ጀመር።
ወዲያውኑም ከመካከላቸው አንዱ ሮጦ በመሄድ ሰፍነግ ወስዶ የኮመጠጠ የወይን ጠጅ ውስጥ ከነከረ በኋላ በመቃ ላይ አድርጎ እንዲጠጣ ሰጠው።
የቀሩት ግን “ተወው! ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደሆነ እንይ” አሉ።
ኢየሱስ ዳግመኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን ሰጠ።
በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀደደ፤ ምድርም ተናወጠች፤ ዓለቶችም ተሰነጣጠቁ።
መቃብሮችም ተከፈቱ፤ በሞት ካንቀላፉት ቅዱሳን ሰዎች መካከልም የብዙዎቹ አስከሬኖች ወጡ፤
ብዙ ሰዎችም አዩአቸው። (ኢየሱስ ከተነሳ በኋላ ሰዎች ከመቃብር ስፍራው ወጥተው ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ገቡ።)
ሆኖም መኮንኑና አብረውት ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች የምድር ነውጡንና የተከሰቱትን ነገሮች ሲመለከቱ እጅግ ፈርተው “ይህ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነበር” አሉ።
ኢየሱስን ለማገልገል ከገሊላ ጀምሮ አብረውት የነበሩ ብዙ ሴቶችም እዚያ ሆነው ከሩቅ ይመለከቱ ነበር፤
ከእነሱም መካከል መግደላዊቷ ማርያም፣ የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም እንዲሁም የዘብዴዎስ ልጆች እናት ይገኙ ነበር።
ቀኑ በመገባደድ ላይ ሳለ የአርማትያስ ሰው የሆነ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሀብታም መጣ፤ እሱም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር።
ይህ ሰው ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጠየቀ። ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ።
ከዚያም ዮሴፍ አስከሬኑን ወስዶ በንጹሕ በፍታ ገነዘው፤
ከዓለት ፈልፍሎ በሠራው በራሱ አዲስ መቃብር ውስጥም አኖረው። ከዚያም አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ የመቃብሩን ደጃፍ ዘጋውና ሄደ።
በዚህ ጊዜ መግደላዊቷ ማርያምና ሌላዋ ማርያም ከመቃብሩ ፊት ለፊት እዚያው ተቀምጠው ነበር።
እነዚህ ነገሮች የተከናወኑት ለሰንበት ዝግጅት በሚደረግበት ቀን ነበር። በማግስቱም የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን አንድ ላይ ተሰብስበው ጲላጦስ ፊት ቀረቡና
እንዲህ አሉ፦ “ክቡር ሆይ፣ ያ አስመሳይ በሕይወት ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሳለሁ’ ብሎ የተናገረው ትዝ አለን።
ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው እንዳይሰርቁትና ለሕዝቡ ‘ከሞት ተነስቷል!’ እንዳይሉ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ መቃብሩ እንዲጠበቅ ትእዛዝ ስጥልን። አለዚያ ይህ የኋለኛው ማታለያ ከፊተኛው የከፋ ይሆናል።”
ጲላጦስም “ጠባቂዎች መውሰድ ትችላላችሁ። ሄዳችሁ በምታውቁት መንገድ አስጠብቁ” አላቸው።
ስለዚህ ሄደው ድንጋዩ ላይ ማኅተም በማድረግ መቃብሩን አሸጉ፤ ጠባቂም አቆሙ።
በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ኢየሱስ በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም ከተወለደ በኋላ ኮከብ ቆጣሪዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፣
“የተወለደው የአይሁዳውያን ንጉሥ የሚገኘው የት ነው? በምሥራቅ ሳለን ኮከቡን በማየታችን ልንሰግድለት መጥተናል” አሉ።
ንጉሥ ሄሮድስና መላው የኢየሩሳሌም ሕዝብ ይህን ሲሰሙ ተሸበሩ።
ንጉሡም የሕዝቡን የካህናት አለቆችና ጸሐፍት በሙሉ ሰብስቦ ክርስቶስ የት እንደሚወለድ ጠየቃቸው።
እነሱም እንዲህ አሉት፦ “በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም ነው፤ ምክንያቱም ነቢዩ እንዲህ ብሎ ጽፏል፦
‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተልሔም ሆይ፣ ለሕዝቤ ለእስራኤል እረኛ የሚሆን ገዢ ከአንቺ ስለሚወጣ በይሁዳ ገዢዎች ዘንድ ከሁሉ የተናቅሽ ከተማ አትሆኚም።’”
ከዚያም ሄሮድስ ኮከብ ቆጣሪዎቹን በድብቅ ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ጊዜ በትክክል አረጋገጠ።
ኮከብ ቆጣሪዎቹንም “ሄዳችሁ ሕፃኑን በደንብ ፈልጉ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔም ሄጄ እንድሰግድለት መጥታችሁ ንገሩኝ” ብሎ ወደ ቤተልሔም ላካቸው።
እነሱም ንጉሡ የነገራቸውን ከሰሙ በኋላ ጉዟቸውን ቀጠሉ፤ እነሆም፣ በምሥራቅ ሳሉ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ቦታ እስከቆመበት ጊዜ ድረስ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር።
ኮከቡ መቆሙን ሲያዩ በጣም ተደሰቱ።
ወደ ቤት ሲገቡም ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። ዕቃ መያዣቸውንም ከፍተው ወርቅ፣ ነጭ ዕጣንና ከርቤ በስጦታ መልክ አቀረቡለት።
ይሁንና ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ በሕልም መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ስለተሰጣቸው በሌላ መንገድ አድርገው ወደ አገራቸው ሄዱ።
እነሱ ከሄዱ በኋላ የይሖዋ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ “ሄሮድስ ሕፃኑን አፈላልጎ ሊገድለው ስላሰበ ተነስ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፤ እኔ እስካሳውቅህም ድረስ እዚያው ቆይ” አለው።
ስለዚህ ዮሴፍ ተነሳ፤ ሕፃኑንና የሕፃኑን እናት ይዞ በሌሊት ወደ ግብፅ ሄደ።
ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ እዚያው ቆየ። በመሆኑም ይሖዋ “ልጄን ከግብፅ ጠራሁት” ብሎ በነቢዩ አማካኝነት የተናገረው ቃል ተፈጸመ።
ከዚያም ሄሮድስ ኮከብ ቆጣሪዎቹ እንዳታለሉት ሲያውቅ በጣም ተናደደ፤ ኮከቡ የታየበትን ጊዜ በተመለከተ ከኮከብ ቆጣሪዎቹ ባገኘው መረጃ መሠረት ሰዎች ልኮ በቤተልሔምና በአካባቢዋ ሁሉ የሚገኙትን ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑትን ወንዶች ልጆች በሙሉ አስገደለ።
በዚህ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው የሚከተለው ቃል ተፈጸመ፦
“የለቅሶና የዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ። ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፤ ልጆቿ ስለሌሉ ልትጽናና አልቻለችም።”
ሄሮድስ ከሞተ በኋላ የይሖዋ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ
“ተነስ፣ የሕፃኑን ሕይወት ለማጥፋት የሚፈልጉት ሰዎች ስለሞቱ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ምድር ተመለስ” አለው።
ዮሴፍም ተነሳ፤ ሕፃኑንና የሕፃኑን እናት ይዞ ወደ እስራኤል ምድር ተመለሰ።
ሆኖም አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ፋንታ ይሁዳን እየገዛ እንዳለ በመስማቱ ወደዚያ መሄድ ፈራ። በተጨማሪም በሕልም መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ስለተሰጠው ወደ ገሊላ ምድር ሄደ።
ደግሞም “የናዝሬት ሰው ይባላል” ተብሎ በነቢያት የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ መኖር ጀመረ።
ከዚያም ኢየሱስ 12ቱን ደቀ መዛሙርት ጠርቶ ርኩሳን መናፍስትን እንዲያዝዙ ሥልጣን ሰጣቸው፤ ይህን ያደረገውም ርኩሳን መናፍስትን እንዲያስወጡ እንዲሁም ማንኛውንም ዓይነት በሽታና ማንኛውንም ዓይነት ሕመም እንዲፈውሱ ነው።
የ12ቱ ሐዋርያት ስም የሚከተለው ነው፦ በመጀመሪያ፣ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፣ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፣
ፊልጶስና በርቶሎሜዎስ፣ ቶማስና ቀረጥ ሰብሳቢው ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ታዴዎስ፣
ቀነናዊው ስምዖንና በኋላ ኢየሱስን የከዳው የአስቆሮቱ ይሁዳ።
ኢየሱስ እነዚህን 12ቱን የሚከተለውን መመሪያ በመስጠት ላካቸው፦ “ወደ አሕዛብ አትሂዱ፤ ወደ ማንኛውም የሳምራውያን ከተማም አትግቡ፤
ከዚህ ይልቅ ከእስራኤል ቤት ወደጠፉት በጎች ብቻ ሂዱ።
በምትሄዱበት ጊዜም ‘መንግሥተ ሰማያት ቀርቧል’ ብላችሁ ስበኩ።
የታመሙትን ፈውሱ፤ የሞቱትን አስነሱ፤ የሥጋ ደዌ ያለባቸውን አንጹ፤ አጋንንትንም አስወጡ። በነፃ እንደተቀበላችሁ በነፃ ስጡ።