text stringlengths 4 267 |
|---|
ኢየሱስም ከጀልባዋ ሲወርድ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተመለከተ፤ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለነበሩም በጣም አዘነላቸው። ብዙ ነገርም ያስተምራቸው ጀመር። |
ሰዓቱ እየገፋ በመሄዱ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ ቀርበው እንዲህ አሉት፦ “ይህ ቦታ ራቅ ያለ ነው፤ ሰዓቱ ደግሞ ገፍቷል። |
በአካባቢው ወዳሉት ገጠሮችና መንደሮች ሄደው ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ አሰናብታቸው።” |
እሱም መልሶ “እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው። እነሱም “ሄደን በ200 ዲናር ዳቦ ገዝተን እንዲበሉ እንስጣቸው?” አሉት። |
እሱም “ስንት ዳቦ አላችሁ? እስቲ ሄዳችሁ እዩ!” አላቸው። ሄደው ካዩ በኋላ “አምስት ዳቦና ሁለት ዓሣ” አሉት። |
ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ በቡድን በቡድን ሆኖ በለመለመው መስክ ላይ እንዲቀመጥ አዘዘ። |
በመሆኑም ሕዝቡ መቶ መቶና ሃምሳ ሃምሳ እየሆነ በቡድን ተቀመጠ። |
እሱም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ። ከዚያም ዳቦውን ቆርሶ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ሁለቱን ዓሣም ለሁሉም አከፋፈለ። |
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ |
ከዚያም ቁርስራሹን ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ዓሣውን ሳይጨምር 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ። |
ዳቦውን የበሉትም 5,000 ወንዶች ነበሩ። |
ወዲያውም፣ እሱ ሕዝቡን እያሰናበተ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ጀልባ ተሳፍረው በቤተሳይዳ አቅጣጫ ወዳለው የባሕር ዳርቻ ቀድመውት እንዲሻገሩ አደረገ። |
ከተሰናበታቸው በኋላ ግን ለመጸለይ ወደ አንድ ተራራ ወጣ። |
በመሸም ጊዜ ጀልባዋ በባሕሩ መካከል ነበረች፤ እሱ ግን ብቻውን የብስ ላይ ነበር። |
ነፋሱ ከፊት ለፊታቸው ይነፍስ ስለነበር ለመቅዘፍ ሲታገሉ ባያቸው ጊዜ በአራተኛው ክፍለ ሌሊት ገደማ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነሱ መጣ፤ ይሁንና አልፏቸው ሊሄድ ነበር። |
እነሱም በባሕሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ “ምትሃት ነው!” ብለው ስላሰቡ በኃይል ጮኹ። |
ሁሉም እሱን ባዩት ጊዜ ተረበሹ። ሆኖም ወዲያውኑ አነጋገራቸው፤ ደግሞም “አይዟችሁ! እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው። |
ከዚያም ጀልባዋ ላይ ወጥቶ አብሯቸው ሆነ፤ ነፋሱም ቆመ። በዚህ ጊዜ በከፍተኛ የአድናቆት ስሜት ተዋጡ፤ |
ይህም የሆነው የዳቦውን ተአምር ትርጉም ባለማስተዋላቸው ነው፤ ልባቸው አሁንም መረዳት ተስኖት ነበር። |
ወደ የብስ በተሻገሩ ጊዜ ጌንሴሬጥ ደረሱ፤ በአቅራቢያውም ጀልባዋን አቆሙ። |
ሆኖም ከጀልባዋ እንደወረዱ ሰዎች አወቁት። |
ወደ አካባቢው ሁሉ በመሮጥ ሕመምተኞችን በቃሬዛ እየተሸከሙ እሱ ይገኝበታል ወደተባለው ቦታ ያመጡ ጀመር። |
በገባበት መንደር ወይም ከተማ ወይም ገጠር ሁሉ ሕመምተኞቹን በገበያ ስፍራ ያስቀምጡ ነበር፤ የልብሱንም ዘርፍ እንኳ ለመንካት ይማጸኑት ነበር። የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ። |
በዚያን ወቅት፣ እንደገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ የሚበሉትም አልነበራቸውም። ስለዚህ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ |
“እነዚህ ሰዎች ሦስት ቀን ሙሉ ከእኔ ጋር ስለቆዩና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ። |
እንዲሁ ጦማቸውን ወደ ቤታቸው ብሰዳቸው መንገድ ላይ ዝለው ይወድቃሉ፤ ደግሞም አንዳንዶቹ የመጡት ከሩቅ ነው።” |
ደቀ መዛሙርቱ ግን “በዚህ ገለልተኛ ስፍራ እነዚህን ሰዎች የሚያጠግብ በቂ ዳቦ ከየት ማግኘት ይቻላል?” ሲሉ መለሱለት። |
በዚህ ጊዜ “ስንት ዳቦ አላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እነሱም “ሰባት” አሉት። |
እሱም ሕዝቡ መሬት ላይ እንዲቀመጥ አዘዘ። ከዚያም ሰባቱን ዳቦ ይዞ አምላክን አመሰገነ፤ ቆርሶም እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነሱም ለሕዝቡ አደሉ። |
ጥቂት ትናንሽ ዓሣዎችም ነበሯቸው፤ እነዚህንም ከባረከ በኋላ እንዲያድሉ ነገራቸው። |
ሕዝቡም በልቶ ጠገበ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ሰባት ትላልቅ ቅርጫት ሙሉ ሆነ። |
በዚያም 4,000 ገደማ ወንዶች ነበሩ። በመጨረሻም አሰናበታቸው። |
ወዲያውኑ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በጀልባ ተሳፍሮ ዳልማኑታ ወደተባለ ክልል መጣ። |
እዚያም ፈሪሳውያን መጥተው እሱን ለመፈተን ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው በመጠየቅ ይከራከሩት ጀመር። |
እሱም እጅግ አዝኖ በረጅሙ ከተነፈሰ በኋላ “ይህ ትውልድ ምልክት የሚፈልገው ለምንድን ነው? እውነት እላችኋለሁ፣ ለዚህ ትውልድ ምንም ምልክት አይሰጠውም” አለ። |
ከዚያም ትቷቸው ሄደ፤ እንደገና ጀልባ ተሳፍሮም ወደ ባሕሩ ማዶ ተሻገረ። |
ይሁንና ዳቦ መያዝ ረስተው ስለነበር በጀልባው ውስጥ ከአንድ ዳቦ በስተቀር ምንም አልነበራቸውም። |
ኢየሱስም “ተጠንቀቁ፣ ከፈሪሳውያን እርሾና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ” ሲል በግልጽ አስጠነቀቃቸው። |
እነሱም ዳቦ ባለመያዛቸው እርስ በርሳቸው ይከራከሩ ጀመር። |
ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ዳቦ ባለመያዛችሁ ለምን ትከራከራላችሁ? አሁንም አልገባችሁም? ደግሞስ አላስተዋላችሁም? ልባችሁ መረዳት እንደተሳነው ነው? |
‘ዓይን እያላችሁ አታዩም? ጆሮ እያላችሁ አትሰሙም?’ ደግሞስ አታስታውሱም? |
አምስቱን ዳቦ ለ5,000ዎቹ ወንዶች በቆረስኩ ጊዜ ስንት ቅርጫት ሙሉ ትርፍራፊ ሰበሰባችሁ?” እነሱም “አሥራ ሁለት” አሉት። |
“ሰባቱን ዳቦ ለ4,000ዎቹ ወንዶች በቆረስኩ ጊዜ ስንት ትላልቅ ቅርጫት ሙሉ ትርፍራፊ አነሳችሁ?” እነሱም “ሰባት” አሉት። |
እሱም “ታዲያ አሁንም አልገባችሁም?” አላቸው። |
ከዚያም ወደ ቤተሳይዳ መጡ። በዚያም ሰዎች አንድ ዓይነ ስውር ወደ ኢየሱስ አምጥተው እንዲዳስሰው ተማጸኑት። |
እሱም ዓይነ ስውሩን፣ እጁን ይዞ ከመንደሩ ውጭ ወሰደው። በዓይኖቹ ላይ እንትፍ ካለ በኋላ እጆቹን ጫነበትና “የሚታይህ ነገር አለ?” ሲል ጠየቀው። |
ሰውየውም ቀና ብሎ በማየት “ሰዎች ይታዩኛል፤ ሆኖም የሚራመዱ ዛፎች ይመስላሉ” አለ። |
ኢየሱስ እንደገና እጆቹን ሰውየው ዓይኖች ላይ ጫነ፤ በዚህ ጊዜ ሰውየው አጥርቶ አየ። ዓይኖቹም በሩ፤ ሁሉንም ነገር በደንብ ለይቶ ማየት ቻለ። |
በመጨረሻም “ወደ መንደሩ አትግባ” ብሎ ወደ ቤቱ ሰደደው። |
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቂሳርያ ፊልጵስዩስ መንደሮች አመሩ፤ በመንገድም ላይ ሳሉ ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል?” ሲል ጠየቃቸው። |
እነሱም “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል” አሉት። |
ከዚያም እነሱን “እናንተስ ስለ እኔ ማንነት ምን ትላላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ ነህ” ብሎ መለሰለት። |
በዚህ ጊዜ ስለ እሱ ለማንም እንዳይናገሩ አጥብቆ አዘዛቸው። |
በተጨማሪም የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበሉ እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት ተቀባይነት ማጣቱ ብሎም መገደሉና ከሦስት ቀን በኋላ መነሳቱ እንደማይቀር ያስተምራቸው ጀመር። |
ደግሞም ይህን በግልጽ ነገራቸው። ጴጥሮስ ግን ኢየሱስን ለብቻው በመውሰድ ይገሥጸው ጀመር። |
በዚህ ጊዜ ዞር ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ተመለከተና ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፣ ሰይጣን! የሰውን እንጂ የአምላክን ሐሳብ አታስብም” ሲል ገሠጸው። |
ከዚህ በኋላ ሕዝቡን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ እሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ፤ የራሱን የመከራ እንጨት ይሸከም፤ ያለማቋረጥም ይከተለኝ። |
ሕይወቱን ማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታልና፤ ለእኔና ለምሥራቹ ሲል ሕይወቱን የሚያጣ ሁሉ ግን ያድናታል። |
ደግሞስ አንድ ሰው ዓለምን ሁሉ የራሱ ቢያደርግና ሕይወቱን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? |
ሰው ለሕይወቱ ምትክ የሚሆን ምን ነገር ሊሰጥ ይችላል? |
በዚህ አመንዝራና ኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ የሰው ልጅም ከቅዱሳን መላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ሲመጣ ያፍርበታል።” |
ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ሰዎችን የሚያሰናክሉ ነገሮች መከሰታቸው የማይቀር ነው። ሆኖም ለመሰናክሉ ምክንያት ለሚሆነው ለዚያ ሰው ወዮለት! |
ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል። |
ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤ ከተጸጸተም ይቅር በለው። |
በቀን ሰባት ጊዜ ቢበድልህ እንኳ ‘ተጸጽቻለሁ’ እያለ ሰባት ጊዜ ወደ አንተ ከመጣ ይቅር ልትለው ይገባል።” |
በዚህ ጊዜ ሐዋርያቱ ጌታን “እምነት ጨምርልን” አሉት። |
ጌታም እንዲህ አለ፦ “የሰናፍጭ ዘር የሚያህል እምነት ካላችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ ባሕሩ ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዛችኋል። |
“ከእናንተ መካከል አራሽ ወይም እረኛ የሆነ ባሪያ ያለው ሰው ቢኖር፣ ባሪያው ከእርሻ ሲመለስ ‘ቶሎ ናና ወደ ማዕድ ቅረብ’ ይለዋል? |
ከዚህ ይልቅ ‘ራቴን አዘጋጅልኝ፤ በልቼና ጠጥቼ እስክጨርስም ድረስ አሸርጠህ አገልግለኝ፤ ከዚያ በኋላ መብላትና መጠጣት ትችላለህ’ አይለውም? |
ባሪያው የተሰጠውን ሥራ በማከናወኑ ጌታው የሚያመሰግነው ይመስላችኋል? |
በተመሳሳይ እናንተም የተሰጣችሁን ሥራ ሁሉ ባከናወናችሁ ጊዜ ‘ምንም የማንጠቅም ባሪያዎች ነን። ያደረግነው ልናደርገው የሚገባንን ነገር ነው’ በሉ።” |
ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየሄደ ሳለ በሰማርያና በገሊላ መካከል አለፈ። |
ወደ አንድ መንደር እየገባም ሳለ የሥጋ ደዌ የያዛቸው አሥር ሰዎች አዩት፤ እነሱም በርቀት ቆሙ። |
ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ “ኢየሱስ፣ መምህር፣ ምሕረት አድርግልን!” አሉ። |
እሱም ባያቸው ጊዜ “ሄዳችሁ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ” አላቸው። ከዚያም እየሄዱ ሳሉ ነጹ። |
ከእነሱ አንዱ እንደተፈወሰ ባየ ጊዜ አምላክን በታላቅ ድምፅ እያመሰገነ ተመለሰ። |
ኢየሱስ እግር ላይ ተደፍቶም አመሰገነው። ሰውየውም ሳምራዊ ነበር። |
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “የነጹት አሥሩም አይደሉም እንዴ? ታዲያ ዘጠኙ የት አሉ? |
ከዚህ ከባዕድ አገር ሰው በስተቀር አምላክን ለማመስገን የተመለሰ ሌላ አንድም ሰው የለም?” |
ከዚያም ሰውየውን “ተነስና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው። |
ፈሪሳውያን የአምላክ መንግሥት መቼ እንደሚመጣ ሲጠይቁት እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “የአምላክ መንግሥት በግልጽ በሚታይ ሁኔታ አይመጣም፤ |
ሰዎችም ‘እነሆ እዚህ ነው!’ ወይም ‘እዚያ ነው!’ አይሉም። እነሆ፣ የአምላክ መንግሥት በመካከላችሁ ነውና።” |
ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ለማየት የምትመኙበት ጊዜ ይመጣል፤ ግን አታዩትም። |
ሰዎችም ‘እዚያ ነው!’ ወይም ‘እዚህ ነው!’ ይሏችኋል። ነገር ግን አትሂዱ ወይም አትከተሏቸው። |
ምክንያቱም መብረቅ ከአንዱ የሰማይ ክፍል እስከ ሌላኛው የሰማይ ክፍል እንደሚያበራ ሁሉ የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን እንዲሁ ይሆናል። |
በመጀመሪያ ግን ብዙ መከራ መቀበሉና በዚህ ትውልድ ተቀባይነት ማጣቱ የግድ ነው። |
በተጨማሪም በኖኅ ዘመን እንደተከሰተው ሁሉ በሰው ልጅ ዘመንም እንዲሁ ይሆናል፦ |
ኖኅ ወደ መርከቡ እስከገባበትና የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉንም እስካጠፋበት ቀን ድረስ ሰዎች ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ወንዶች ያገቡ፣ ሴቶችም ይዳሩ ነበር። |
በተመሳሳይም በሎጥ ዘመን እንደተከሰተው ሁሉ እንዲሁ ይሆናል፦ ሰዎች ይበሉ፣ ይጠጡ፣ ይገዙ፣ ይሸጡ፣ ይተክሉና ቤቶችን ይገነቡ ነበር። |
ሆኖም ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ከሰማይ እሳትና ድኝ ዘንቦ ሁሉንም አጠፋቸው። |
የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን እንዲሁ ይሆናል። |
“በዚያን ቀን በጣሪያ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ ለመውሰድ አይውረድ፤ እርሻም ላይ ያለ ሰው በኋላው ያለውን ነገር ለመውሰድ አይመለስ። |
የሎጥን ሚስት አስታውሱ። |
ሕይወቱን ጠብቆ ለማቆየት የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ሕይወቱን የሚያጣት ሁሉ ግን በሕይወት ጠብቆ ያቆያታል። |
እላችኋለሁ፣ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ላይ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላኛው ግን ይተዋል። |
ሁለት ሴቶች በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላኛዋ ግን ትተዋለች።” |
እነሱም መልሰው “ጌታ ሆይ፣ የት?” አሉት። እሱም “በድን ባለበት ንስሮች ይሰበሰባሉ” አላቸው። |
ከዚያም ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ገብቶ በዚያ እያለፈ ነበር። |
በዚያም ዘኬዎስ የተባለ አንድ ሀብታም ሰው የነበረ ሲሆን ይህ ሰው የቀረጥ ሰብሳቢዎች አለቃ ነበር። |
እሱም ኢየሱስ የሚባለው ማን እንደሆነ ለማየት ይፈልግ ነበር፤ ሆኖም አጭር በመሆኑ ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ማየት አልቻለም። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.