text
stringlengths 4
267
|
|---|
በሚያልፍባቸው ስፍራዎች የሚያገኛቸውን ደቀ መዛሙርት በብዙ ቃል እያበረታታ ወደ ግሪክ መጣ።
|
በዚያ ሦስት ወር ቆየ፤ ይሁንና ወደ ሶርያ በመርከብ ለመሄድ ተነስቶ ሳለ አይሁዳውያን ሴራ ስለጠነሰሱበት ሐሳቡን ቀይሮ በመቄዶንያ አድርጎ ለመመለስ ወሰነ።
|
የጳይሮስ ልጅ የቤርያው ሶጳጥሮስ፣ የተሰሎንቄዎቹ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤው ጋይዮስ፣ ጢሞቴዎስ እንዲሁም ከእስያ አውራጃ የመጡት ቲኪቆስና ጢሮፊሞስ አብረውት ነበሩ።
|
እነዚህም ወደ ጥሮአስ ቀድመውን በመሄድ እዚያ ጠበቁን፤
|
እኛ ግን የቂጣ በዓል ካለፈ በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሳን፤ በአምስት ቀን ጊዜ ውስጥም እነሱ ወዳሉበት ወደ ጥሮአስ ደረስን፤ በዚያም ሰባት ቀን ቆየን።
|
በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ምግብ ልንበላ አንድ ላይ ተሰብስበን ሳለን ጳውሎስ በማግስቱ ይሄድ ስለነበር ንግግር ይሰጣቸው ጀመር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አስረዘመ።
|
በመሆኑም ተሰብስበንበት በነበረው ፎቅ ላይ ባለው ክፍል ውስጥ ብዙ መብራት ነበር።
|
ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ መስኮት ላይ ተቀምጦ የነበረ አውጤኪስ የሚባል አንድ ወጣት ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እንቅልፍ ስለጣለውም ከሁለተኛ ፎቅ ላይ ወደቀ፤ ሲያነሱትም ሞቶ ነበር።
|
ጳውሎስም ከፎቅ ላይ ወርዶ በላዩ ላይ ተኝቶ አቀፈውና “በሕይወት ስላለ አትንጫጩ” አላቸው።
|
ከዚያም ወደ ፎቅ ወጥቶ ማዕዱን ካስጀመረ በኋላ በላ። እስከ ንጋትም ድረስ ሲነጋገር ቆየ፤ በኋላም ተነስቶ ሄደ።
|
ሰዎቹም ወጣቱን ወሰዱት፤ ሕያው በመሆኑም እጅግ ተጽናኑ።
|
እኛም ጳውሎስ በሰጠን መመሪያ መሠረት በመርከብ ተሳፍረን በቅድሚያ ወደ አሶስ ተጓዝን፤ ምክንያቱም ጳውሎስ በእግሩ ተጉዞ በዚያ ለመሳፈር አስቦ ነበር።
|
ስለዚህ አሶስ ላይ ከተገናኘን በኋላ አሳፍረነው ወደ ሚጢሊኒ ሄድን።
|
በነጋታውም ጉዟችንን በመቀጠል ከኪዮስ ትይዩ ወዳለው ስፍራ ደረስን፤ በሚቀጥለው ቀን ደግሞ ሳሞስ ላይ አጭር ቆይታ አደረግን፤ በማግስቱም ሚሊጢን ደረስን።
|
ጳውሎስ በእስያ አውራጃ ምንም መቆየት ስላልፈለገ ኤፌሶንን አልፎ ለመሄድ ወሰነ፤ ምክንያቱም ቢችል በጴንጤቆስጤ በዓል ቀን ኢየሩሳሌም ለመድረስ ቸኩሎ ነበር።
|
ይሁን እንጂ ከሚሊጢን ወደ ኤፌሶን መልእክት ልኮ የጉባኤውን ሽማግሌዎች አስጠራ።
|
ወደ እሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “በእስያ አውራጃ እግሬ ከረገጠበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ በመካከላችሁ እንዴት እንደተመላለስኩ ታውቃላችሁ፤
|
በአይሁዳውያን ሴራ ምክንያት ብዙ መከራ ቢደርስብኝም እንኳ በታላቅ ትሕትናና በእንባ ጌታን አገለግል ነበር፤
|
ደግሞም የሚጠቅማችሁን ማንኛውንም ነገር ከመንገርም ሆነ በአደባባይና ከቤት ወደ ቤት ከማስተማር ወደኋላ ብዬ አላውቅም።
|
ከዚህ ይልቅ አይሁዳውያንም ሆኑ ግሪካውያን ንስሐ እንዲገቡና ወደ አምላክ እንዲመለሱ እንዲሁም በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ በተሟላ ሁኔታ መሥክሬላቸዋለሁ።
|
አሁን ደግሞ እዚያ ምን እንደሚደርስብኝ ባላውቅም መንፈስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው፤
|
እርግጥ ነው፣ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ በደረስኩበት ከተማ ሁሉ በተደጋጋሚ ያሳስበኛል።
|
ይሁንና ሩጫዬን እስካጠናቀቅኩ እንዲሁም ስለ አምላክ ጸጋ የሚገልጸውን ምሥራች በተሟላ ሁኔታ በመመሥከር ከጌታ ኢየሱስ የተቀበልኩትን አገልግሎት እስከፈጸምኩ ድረስ ሕይወቴ ምንም አያሳሳኝም።
|
“አሁንም እነሆ፣ የአምላክን መንግሥት የሰበክሁላችሁ እናንተ ሁላችሁ ዳግመኛ ፊቴን እንደማታዩ አውቃለሁ።
|
ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን ለማሳየት በዚህች ቀን እናንተን ምሥክር አድርጌ መጥራት እችላለሁ፤
|
ምክንያቱም የአምላክን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመንገር ወደኋላ አላልኩም።
|
ለራሳችሁም ሆነ አምላክ በገዛ ልጁ ደም የዋጀውን ጉባኤውን እረኛ ሆናችሁ እንድትጠብቁ መንፈስ ቅዱስ የበላይ ተመልካቾች አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ትኩረት ስጡ።
|
እኔ ከሄድኩ በኋላ ጨካኝ ተኩላዎች በመካከላችሁ እንደሚገቡና መንጋውን በርኅራኄ እንደማይዙ አውቃለሁ፤
|
ከእናንተ መካከል እንኳ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሳቸው ለመሳብ ጠማማ ነገር የሚናገሩ ሰዎች ይነሳሉ።
|
“ስለዚህ ነቅታችሁ ጠብቁ፤ ሦስት ዓመት ሙሉ ሌሊትና ቀን እያንዳንዳችሁን በእንባ ከማሳሰብ ወደኋላ እንዳላልኩ አስታውሱ።
|
አሁንም ለአምላክ እንዲሁም ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው፣ ስለ እሱ ጸጋ ለሚገልጸው ቃል አደራ እሰጣችኋለሁ።
|
የማንንም ብር፣ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም።
|
እነዚህ እጆቼ ለእኔም ሆነ ከእኔ ጋር ለነበሩት የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለማሟላት እንዳገለገሉ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
|
እናንተም እንዲሁ እየሠራችሁ ደካማ የሆኑትን መርዳት እንዳለባችሁ በሁሉም ነገር አሳይቻችኋለሁ፤ እንዲሁም ‘ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል’ በማለት ጌታ ኢየሱስ ራሱ የተናገረውን ቃል ማስታወስ ይኖርባችኋል።”
|
ይህን ተናግሮ ከጨረሰም በኋላ ከሁሉም ጋር ተንበርክኮ ጸለየ።
|
ከዚያም ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም እቅፍ አድርገው ሳሙት፤
|
ከሁሉ ይበልጥ ያሳዘናቸው ከዚህ በኋላ ፊቱን እንደማያዩ የተናገረው ቃል ነው። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።
|
በዚያን ጊዜ ንጉሡ ሄሮድስ በአንዳንድ የጉባኤው አባላት ላይ ስደት ማድረስ ጀመረ።
|
የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።
|
ይህ ድርጊቱ አይሁዳውያንን እንዳስደሰተ ባየ ጊዜ ጴጥሮስን ደግሞ በቁጥጥር ሥር አዋለው። (ይህም የሆነው በቂጣ በዓል ሰሞን ነበር።)
|
ከያዘውና እስር ቤት ካስገባው በኋላ በአራት ፈረቃ፣ አራት አራት ሆነው እንዲጠብቁት ለተመደቡ ወታደሮች አስረከበው፤ ይህን ያደረገው ከፋሲካ በኋላ ሕዝቡ ፊት ሊያቀርበው አስቦ ነው።
|
ስለዚህ ጴጥሮስ እስር ቤት እንዲቆይ ተደረገ፤ ሆኖም ጉባኤው ስለ እሱ ወደ አምላክ አጥብቆ ይጸልይ ነበር።
|
ሄሮድስ ጴጥሮስን ሕዝቡ ፊት ሊያቀርበው ካሰበበት ቀን በፊት በነበረው ሌሊት፣ ጴጥሮስ በሁለት ወታደሮች መካከል በሁለት ሰንሰለቶች ታስሮ ተኝቶ ነበር፤ በር ላይ ያሉ ጠባቂዎችም እስር ቤቱን እየጠበቁ ነበር።
|
ይሁንና የይሖዋ መልአክ ድንገት መጥቶ ቆመ፤ በክፍሉም ውስጥ ብርሃን በራ። ጴጥሮስን ጎኑን መታ አድርጎ ከእንቅልፉ ቀሰቀሰውና “ቶሎ ብለህ ተነሳ!” አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጆቹ ላይ ወደቁ።
|
መልአኩም “በል ልብስህን ልበስ፤ ጫማህንም አድርግ” አለው። እሱም እንደተባለው አደረገ። ከዚያም “መደረቢያህን ልበስና ተከተለኝ” አለው።
|
እሱም ወጥቶ ይከተለው ጀመር፤ ይሁንና መልአኩ እያደረገ ያለው ነገር በእውን እየተከናወነ ያለ አልመሰለውም። እንዲያውም ራእይ የሚያይ መስሎት ነበር።
|
የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዘብ አልፈው ከእስር ቤቱ ወደ ከተማዋ ወደሚያስወጣው የብረት መዝጊያ ደረሱ፤ መዝጊያውም በራሱ ተከፈተላቸው። ከወጡ በኋላ በአንድ ጎዳና አብረው ተጓዙ፤ ወዲያውም መልአኩ ተለይቶት ሄደ።
|
ጴጥሮስም የሆነውን ነገር ሲረዳ “ይሖዋ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና አይሁዳውያን በእኔ ላይ ይደርሳል ብለው ካሰቡት ነገር ሁሉ እንደታደገኝ አሁን በእርግጥ አወቅኩ” አለ።
|
ይህን ከተገነዘበ በኋላ ማርቆስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት ሄደ፤ በዚያም በርከት ያሉ ሰዎች ተሰብስበው ይጸልዩ ነበር።
|
የውጭውን በር ሲያንኳኳ ሮዳ የተባለች አንዲት አገልጋይ በሩን ለመክፈት መጣች።
|
የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑን ባወቀች ጊዜ በጣም ከመደሰቷ የተነሳ በሩን ሳትከፍት ሮጣ ወደ ውስጥ በመግባት ጴጥሮስ በር ላይ መቆሙን ተናገረች።
|
እነሱም “አብደሻል እንዴ!” አሏት። እሷ ግን ያንኑ አስረግጣ መናገሯን ቀጠለች። እነሱም “ከሆነም የእሱ መልአክ ይሆናል” አሉ።
|
ጴጥሮስ ግን እዚያው ቆሞ ማንኳኳቱን ቀጠለ። በሩን ከከፈቱም በኋላ ሲያዩት በጣም ተገረሙ።
|
እሱ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ምልክት ከሰጣቸው በኋላ ይሖዋ ከእስር ቤት እንዴት እንዳወጣው በዝርዝር ነገራቸው፤ ከዚያም “ይህን ነገር ለያዕቆብና ለወንድሞች ንገሯቸው” አላቸው። ይህን ካለም በኋላ ወጥቶ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ።
|
በነጋም ጊዜ ወታደሮቹ ጴጥሮስ የት እንደደረሰ ግራ ስለተጋቡ በመካከላቸው ከፍተኛ ትርምስ ተፈጠረ።
|
ሄሮድስም ፈልጎ አፈላልጎ ባጣው ጊዜ ጠባቂዎቹን ከመረመረ በኋላ እርምጃ እንዲወሰድባቸው አዘዘ፤ ከዚያም ከይሁዳ ወደ ቂሳርያ ወርዶ በዚያ የተወሰነ ጊዜ ተቀመጠ።
|
ሄሮድስ በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ በጣም ተቆጥቶ ነበር። እነሱም በአንድ ልብ ሆነው ወደ እሱ በመምጣት የንጉሡ ባለሟል የሆነውን ብላስጦስን ካግባቡ በኋላ ንጉሡን እርቅ ጠየቁ፤ ይህን ያደረጉት አገራቸው ምግብ የምታገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለነበረ ነው።
|
አንድ ልዩ ዝግጅት በተደረገበት ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ፤ ከዚያም ለሕዝቡ ንግግር መስጠት ጀመረ።
|
የተሰበሰበውም ሕዝብ “ይህ የአምላክ ድምፅ ነው እንጂ የሰው አይደለም!” እያለ ይጮኽ ጀመር።
|
በዚህ ጊዜ፣ ለአምላክ ክብር ባለመስጠቱ ወዲያውኑ የይሖዋ መልአክ ቀሰፈው፤ በትል ተበልቶም ሞተ።
|
የይሖዋ ቃል ግን እየተስፋፋ ሄደ፤ ብዙ ሰዎችም አማኞች ሆኑ።
|
በርናባስና ሳኦልም በኢየሩሳሌም እርዳታ ከሰጡ በኋላ ተመለሱ፤ ማርቆስ ተብሎ የሚጠራውን ዮሐንስንም ይዘውት መጡ።
|
ከዚህ በኋላ ከአቴንስ ተነስቶ ወደ ቆሮንቶስ መጣ።
|
በዚያም የጳንጦስ ተወላጅ የሆነ አቂላ የተባለ አይሁዳዊ አገኘ፤ ይህ ሰው ቀላውዴዎስ አይሁዳውያን ሁሉ ከሮም እንዲወጡ ባዘዘው መሠረት ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር በቅርቡ ከጣሊያን የመጣ ነበር። ጳውሎስም ወደ እነሱ ሄደ፤
|
ሙያቸው አንድ ዓይነት በመሆኑ እነሱ ቤት ተቀምጦ አብሯቸው ይሠራ ነበር፤ ሙያቸውም ድንኳን መሥራት ነበር።
|
በየሰንበቱ በምኩራብ ንግግር እየሰጠ አይሁዳውያንንና ግሪካውያንን ያሳምን ነበር።
|
ሲላስና ጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ በወረዱ ጊዜ፣ ጳውሎስ ቃሉን በመስበኩ ሥራ በእጅጉ ተጠመደ፤ ኢየሱስ በእርግጥ ክርስቶስ መሆኑን እያስረዳ ለአይሁዳውያን ይመሠክር ነበር።
|
አይሁዳውያኑ እሱን መቃወማቸውንና መሳደባቸውን በቀጠሉ ጊዜ ግን ልብሱን አራግፎ “ደማችሁ በራሳችሁ ላይ ይሁን። እኔ ንጹሕ ነኝ። ከአሁን ጀምሮ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ” አላቸው።
|
ከዚያም ተነስቶ ቲቶስ ኢዮስጦስ ወደሚባል አምላክን ወደሚያመልክ ሰው ቤት ሄደ፤ የዚህ ሰው ቤት ምኩራቡ አጠገብ ነበር።
|
የምኩራብ አለቃው ቀርስጶስ ከቤተሰቡ ሁሉ ጋር በጌታ አመነ። መልእክቱን የሰሙ በርካታ የቆሮንቶስ ሰዎችም አምነው ይጠመቁ ጀመር።
|
ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን እንዲህ አለው፦ “አትፍራ፣ መናገርህን ቀጥል፤ ደግሞም ተስፋ አትቁረጥ፤
|
እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ ማንም አንተን ሊያጠቃና ሊጎዳህ አይችልም፤ በዚህች ከተማ ብዙ ሰዎች አሉኝና።”
|
ስለዚህ በመካከላቸው የአምላክን ቃል እያስተማረ ለአንድ ዓመት ተኩል እዚያ ቆየ።
|
የሮም አገረ ገዢ የሆነው ጋልዮስ አካይያን ያስተዳድር በነበረበት ጊዜ አይሁዳውያን ግንባር ፈጥረው በጳውሎስ ላይ ተነሱበት፤ በፍርድ ወንበር ፊት አቅርበውትም
|
እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ሕጉን በሚጻረር መንገድ ሰዎች አምላክን እንዲያመልኩ እያሳመነ ነው።”
|
ይሁንና ጳውሎስ ሊናገር ሲል ጋልዮስ አይሁዳውያንን እንዲህ አላቸው፦ “አይሁዳውያን ሆይ፣ አንድ ዓይነት በደል ወይም ከባድ ወንጀል ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ በትዕግሥት ላዳምጣችሁ በተገባኝ ነበር።
|
ነገር ግን ክርክራችሁ ስለ ቃላትና ስለ ስሞች እንዲሁም ስለ ሕጋችሁ ከሆነ እናንተው ጨርሱት። እኔ እንዲህ ላለ ነገር ፈራጅ መሆን አልፈልግም።”
|
ከዚያም ከፍርድ ወንበሩ ፊት አስወጣቸው።
|
በዚህ ጊዜ የምኩራብ አለቃ የሆነውን ሶስቴንስን ይዘው በፍርድ ወንበሩ ፊት ይደበድቡት ጀመር። ጋልዮስ ግን እንዲህ ባሉ ጉዳዮች እጁን አያስገባም ነበር።
|
ይሁንና ጳውሎስ በዚያ ለተወሰኑ ቀናት ከቆየ በኋላ ወንድሞችን ተሰናብቶ ከጵርስቅላና ከአቂላ ጋር በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ። ስእለት ስለነበረበትም ክንክራኦስ በተባለ ቦታ ፀጉሩን በአጭሩ ተቆረጠ።
|
ኤፌሶን በደረሱም ጊዜ እነሱን እዚያው ተዋቸው፤ እሱ ግን ወደ ምኩራብ ገብቶ ከአይሁዳውያን ጋር ይወያይ ነበር።
|
ምንም እንኳ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲሰነብት አጥብቀው ቢለምኑትም ፈቃደኛ አልሆነም፤
|
ከዚህ ይልቅ “ይሖዋ ከፈቀደ ተመልሼ እመጣለሁ” ብሎ ተሰናበታቸው። ከዚያም ከኤፌሶን መርከብ ተሳፍሮ
|
ወደ ቂሳርያ ወረደ። ወጥቶም ለጉባኤው ሰላምታ ካቀረበ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወረደ።
|
በዚያም የተወሰነ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ከዚያ ወጥቶ በገላትያና በፍርግያ አገሮች ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ አበረታታ።
|
በዚህ ጊዜ የእስክንድርያ ተወላጅ የሆነ አጵሎስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እሱም ጥሩ የመናገር ተሰጥኦ ያለውና ቅዱሳን መጻሕፍትን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ነበር።
|
ይህ ሰው የይሖዋን መንገድ የተማረ ሲሆን በመንፈስ እየተቃጠለ ኢየሱስን ስለሚመለከቱ ጉዳዮች በትክክል ይናገርና ያስተምር ነበር፤ ይሁን እንጂ እሱ የሚያውቀው ዮሐንስ ይሰብከው ስለነበረው ጥምቀት ብቻ ነበር።
|
እሱም በምኩራብ ውስጥ በድፍረት መናገር ጀመረ፤ ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ ይዘውት በመሄድ የአምላክን መንገድ ይበልጥ በትክክል አብራሩለት።
|
በተጨማሪም ወደ አካይያ መሄድ ፈልጎ ስለነበር ወንድሞች በዚያ የሚገኙት ደቀ መዛሙርት ጥሩ አቀባበል እንዲያደርጉለት የሚያሳስብ ደብዳቤ ጻፉለት። እዚያ በደረሰ ጊዜም በአምላክ ጸጋ አማኞች የሆኑትን ሰዎች በእጅጉ ረዳቸው፤
|
ከአይሁዳውያን ጋር በይፋ በመወያየት ከቅዱሳን መጻሕፍት ላይ እያሳያቸው ኢየሱስ እሱ ክርስቶስ እንደሆነ በመግለጽ ትክክል እንዳልሆኑ በጋለ ስሜት ያስረዳቸው ነበር።
|
ጳውሎስ የሳንሄድሪንን ሸንጎ ትኩር ብሎ እየተመለከተ “ወንድሞች፣ እኔ እስከዚህ ቀን ድረስ በአምላክ ፊት ሙሉ በሙሉ ንጹሕ ሕሊና ይዤ ተመላልሻለሁ” አለ።
|
በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ፣ ጳውሎስ አጠገብ የቆሙት ሰዎች አፉን እንዲመቱት አዘዘ።
|
ጳውሎስም “አንተ በኖራ የተለሰንክ ግድግዳ! አምላክ አንተን ይመታሃል። በሕጉ መሠረት በእኔ ላይ ለመፍረድ ተቀምጠህ ሳለ አንተ ራስህ ሕጉን በመጣስ እንድመታ ታዛለህ?” አለው።
|
አጠገቡ የቆሙትም “የአምላክን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህ?” አሉት።
|
ጳውሎስም “ወንድሞች፣ እኔ እኮ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላወቅኩም። ምክንያቱም ‘በሕዝብህ ገዢ ላይ ክፉ ቃል አትናገር’ ተብሎ ተጽፏል” አላቸው።
|
ጳውሎስ ግማሾቹ ሰዱቃውያን ግማሾቹ ደግሞ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ስላወቀ በሳንሄድሪን ሸንጎ ውስጥ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ወንድሞች፣ እኔ ከፈሪሳውያን የተወለድኩ ፈሪሳዊ ነኝ። ለፍርድ የቀረብኩት በሙታን ትንሣኤ ተስፋ በማመኔ ነው” ሲል ተናገረ።
|
ይህን በመናገሩ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ግጭት ተፈጥሮ ጉባኤው ለሁለት ተከፈለ።
|
ምክንያቱም ሰዱቃውያን ትንሣኤም፣ መልአክም፣ መንፈሳዊ ፍጥረታትም የሉም ይሉ የነበረ ሲሆን ፈሪሳውያን ግን በእነዚህ ነገሮች ያምኑ ነበር።
|
ስለዚህ ከፍተኛ ሁከት ተፈጠረ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ ጸሐፍት ተነስተው እንዲህ ሲሉ አጥብቀው ተከራከሩ፦ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘንም፤ መንፈስ ወይም መልአክ አናግሮት ከሆነ ግን . . . ።”
|
በመካከላቸው የተፈጠረው ግጭት እየከረረ ሲሄድ የሠራዊቱ ሻለቃ ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ወታደሮቹ ወርደው ከመካከላቸው ነጥቀው እንዲያመጡትና ወደ ጦር ሰፈሩ እንዲያስገቡት አዘዘ።
|
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.