text stringlengths 4 267 |
|---|
በሌላ በኩል ግን የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ደግነት፣ ጥሩነት፣ እምነት፣ |
ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው። እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚከለክል ሕግ የለም። |
ከዚህም በተጨማሪ የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከመጥፎ ምኞቱና ፍላጎቱ ጋር በእንጨት ላይ ቸንክረውታል። |
በመንፈስ የምንኖር ከሆነ መንፈስ የሚሰጠንን አመራር በመከተል ምንጊዜም በሥርዓት እንመላለስ። |
በመካከላችን የፉክክር መንፈስ በማነሳሳትና አንዳችን ሌላውን በመመቅኘት በከንቱ አንመካ። |
እንግዲህ ይህን እላለሁ፦ ወራሹ የሁሉም ነገር ጌታ ቢሆንም እንኳ ሕፃን እስከሆነ ድረስ ከባሪያ በምንም አይለይም፤ |
ይልቁንም አባቱ አስቀድሞ የወሰነው ቀን እስኪደርስ ድረስ በሞግዚቶችና በመጋቢዎች ሥር ሆኖ ይቆያል። |
በተመሳሳይ እኛም ልጆች በነበርንበት ጊዜ በዓለም ውስጥ ላሉ ተራ ነገሮች ባሪያ ሆነን ቆይተናል። |
ሆኖም ዘመኑ ሙሉ በሙሉ የሚጠናቀቅበት ጊዜ ሲደርስ አምላክ ከሴት የተወለደውንና በሕግ ሥር የነበረውን ልጁን ላከ፤ |
ይህን ያደረገው እኛን ልጆቹ አድርጎ መውሰድ ይችል ዘንድ በሕግ ሥር ያሉትን ዋጅቶ ነፃ ለማውጣት ነው። |
አሁን እናንተ ልጆች ስለሆናችሁ አምላክ የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ልኳል፤ ይህም መንፈስ “አባ፣ አባት!” እያለ ይጣራል። |
በመሆኑም ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅ ከሆንክ ደግሞ አምላክ ወራሽም አድርጎሃል። |
ይሁንና አምላክን ከማወቃችሁ በፊት በእርግጥ አማልክት ላልሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ትገዙ ነበር። |
አሁን ግን አምላክን አውቃችኋል፤ እንዲያውም አምላክ እናንተን አውቋችኋል፤ ታዲያ ደካማና ከንቱ ወደሆኑ ተራ ነገሮች መመለስና እንደገና ለእነዚህ ነገሮች ባሪያ መሆን ትፈልጋላችሁ? |
ቀናትን፣ ወራትን፣ ወቅቶችንና ዓመታትን በጥንቃቄ እየጠበቃችሁ ታከብራላችሁ። |
የእናንተ ሁኔታ ያሳስበኛል፤ ምክንያቱም ለእናንተ የደከምኩት በከንቱ እንዳይሆን እሰጋለሁ። |
ወንድሞች፣ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ፤ ምክንያቱም እኔም በአንድ ወቅት እንደ እናንተ ነበርኩ። እናንተ ምንም የበደላችሁኝ ነገር የለም። |
በተጨማሪም ለመጀመሪያ ጊዜ ለእናንተ ምሥራቹን ለመስበክ አጋጣሚ ያገኘሁት በመታመሜ የተነሳ እንደነበር ታውቃላችሁ። |
ሕመሜ ፈተና ሆኖባችሁ የነበረ ቢሆንም እንኳ አልናቃችሁኝም ወይም አልተጸየፋችሁኝም፤ ከዚህ ይልቅ እንደ አምላክ መልአክ ወይም እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተቀበላችሁኝ። |
ታዲያ ያ ሁሉ ደስታችሁ የት ጠፋ? የሚቻል ቢሆን ኖሮ ዓይናችሁን እንኳ አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደነበር እርግጠኛ ነኝ። |
ታዲያ እውነቱን ስለምነግራችሁ ጠላት ሆንኩባችሁ ማለት ነው? |
እነሱ ወደ ራሳቸው ሊስቧችሁ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፤ ይህን የሚያደርጉት ግን ለበጎ ሳይሆን እናንተን ከእኔ በማራቅ እነሱን አጥብቃችሁ እንድትከተሏቸው ለማድረግ ነው። |
ይሁን እንጂ አንድ ሰው ምንጊዜም እናንተን አጥብቆ የሚፈልገው ለበጎ ዓላማ ከሆነ ጥሩ ነው፤ ይህም መሆን ያለበት እኔ ከእናንተ ጋር ስሆን ብቻ አይደለም፤ |
የምወዳችሁ ልጆቼ፣ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ በእናንተ ምክንያት እንደገና ምጥ ይዞኛል። |
በእናንተ ግራ ስለተጋባሁ አሁን በመካከላችሁ ተገኝቼ ለየት ባለ መንገድ ላነጋግራችሁ ብችል ደስ ባለኝ ነበር። |
እናንተ በሕግ ሥር መኖር የምትፈልጉ እስቲ ንገሩኝ፤ ሕጉ የሚለውን አትሰሙም? |
ለምሳሌ ያህል፣ አብርሃም አንዱ ከአገልጋዪቱ፣ ሌላው ደግሞ ከነፃዪቱ ሴት የተወለዱ ሁለት ወንዶች ልጆች እንደነበሩት ተጽፏል፤ |
ሆኖም ከአገልጋዪቱ የተገኘው ልጅ የተወለደው በሥጋዊ መንገድ ሲሆን ከነፃዪቱ ሴት የተገኘው ልጅ ደግሞ የተወለደው በተስፋ ቃል መሠረት ነው። |
እነዚህ ሴቶች ሁለት ቃል ኪዳኖችን ስለሚወክሉ እነዚህ ነገሮች ምሳሌያዊ ትርጉም አላቸው፤ አንደኛው ቃል ኪዳን የተገባው በሲና ተራራ ሲሆን በዚህ ቃል ኪዳን ሥር ያሉት ልጆች ሁሉ ባሪያዎች ናቸው፤ ይህ ቃል ኪዳን ደግሞ አጋርን ያመለክታል። |
አጋር፣ በዓረብ አገር የሚገኘውን የሲና ተራራ የምትወክል ሲሆን ዛሬ ካለችው ኢየሩሳሌም ጋር ትመሳሰላለች፤ ኢየሩሳሌም ከልጆቿ ጋር በባርነት ሥር ናትና። |
ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን ነፃ ናት፤ እሷም እናታችን ናት። |
“አንቺ የማትወልጂ መሃን ሴት፣ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ ምጥ የማታውቂ ሴት፣ እልል በይ፣ ጩኺም፤ ምክንያቱም ባል ካላት ሴት ይልቅ የተተወችው ሴት ልጆች እጅግ በዝተዋል” ተብሎ ተጽፏልና። |
እንግዲህ ወንድሞች፣ እንደ ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ናችሁ። |
ሆኖም ያን ጊዜ በሥጋዊ መንገድ የተወለደው በመንፈስ የተወለደውን ማሳደድ እንደጀመረ ሁሉ አሁንም እንደዚያው ነው። |
ይሁንና ቅዱስ መጽሐፉ ምን ይላል? “የአገልጋዪቱ ልጅ ከነፃዪቱ ልጅ ጋር በምንም ዓይነት አብሮ ስለማይወርስ አገልጋዪቱን ከነልጅዋ አባር።” |
ስለዚህ ወንድሞች፣ እኛ የነፃዪቱ ልጆች እንጂ የአገልጋዪቱ ልጆች አይደለንም። |
ወንድሞች፣ አንድ ሰው ሳያውቅ የተሳሳተ ጎዳና ቢከተል መንፈሳዊ ብቃት ያላችሁ እናንተ እንዲህ ዓይነቱን ሰው በገርነት መንፈስ ለማስተካከል ጥረት አድርጉ። ይሁንና እናንተም ፈተና ላይ እንዳትወድቁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። |
አንዳችሁ የሌላውን ከባድ ሸክም ተሸከሙ፤ በዚህ መንገድ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። |
አንድ ሰው ምንም ሳይሆን ራሱን ከፍ አድርጎ የሚመለከት ከሆነ ራሱን እያታለለ ነው። |
ከዚህ ይልቅ እያንዳንዱ ሰው የራሱን ተግባር ይመርምር፤ ከዚያም ራሱን ከሌላ ሰው ጋር ሳያወዳድር ከራሱ ጋር ብቻ በተያያዘ እጅግ የሚደሰትበት ነገር ያገኛል። |
እያንዳንዱ የራሱን የኃላፊነት ሸክም ይሸከማልና። |
ከዚህም በተጨማሪ ቃሉን በመማር ላይ ያለ ማንኛውም ሰው፣ ይህን ትምህርት ከሚያስተምረው ሰው ጋር መልካም ነገሮችን ሁሉ ይካፈል። |
አትታለሉ፤ አምላክ አይዘበትበትም። አንድ ሰው ምንም ዘራ ምን ያንኑ መልሶ ያጭዳል፤ |
ምክንያቱም ለሥጋው ብሎ የሚዘራ ከሥጋው መበስበስን ያጭዳል፤ ለመንፈስ ብሎ የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለም ሕይወት ያጭዳል። |
ካልታከትን ጊዜው ሲደርስ ስለምናጭድ ተስፋ ቆርጠን መልካም ሥራ መሥራታችንን አንተው። |
እንግዲያው ይህን ለማድረግ የሚያስችል አጋጣሚ እስካገኘን ድረስ ለሁሉም፣ በተለይ ደግሞ በእምነት ለሚዛመዱን ሰዎች መልካም እናድርግ። |
በራሴ እጅ እንዴት ባሉ ትላልቅ ፊደላት እንደጻፍኩላችሁ ተመልከቱ። |
በሥጋ ተቀባይነት ለማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ እንድትገረዙ ሊያስገድዷችሁ ይሞክራሉ፤ ይህን የሚያደርጉት ግን በክርስቶስ የመከራ እንጨት ሳቢያ ስደት እንዳይደርስባቸው ነው። |
እነሱ እንድትገረዙ የሚፈልጉት በእናንተ ሥጋ ለመኩራራት ብለው ነው እንጂ የተገረዙት ራሳቸውም እንኳ ሕጉን አይጠብቁም። |
ይሁንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የመከራ እንጨት ካልሆነ በስተቀር በሌላ ነገር ፈጽሞ መኩራራት አልፈልግም፤ በእሱ የተነሳ፣ በእኔ አመለካከት ዓለም ሞቷል፤ በዓለም አመለካከት ደግሞ እኔ ሞቻለሁ። |
መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም አይጠቅምም፤ ከዚህ ይልቅ የሚጠቅመው አዲስ ፍጥረት መሆን ነው። |
ይህን የሥነ ምግባር ደንብ በመከተል በሥርዓት በሚመላለሱ ሁሉ ይኸውም በአምላክ እስራኤል ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን። |
የኢየሱስ ባሪያ መሆኔን የሚያሳይ መለያ ምልክት በሰውነቴ ላይ ስላለ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አያስቸግረኝ። |
ወንድሞች፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከምታሳዩት መንፈስ ጋር ይሁን። አሜን። |
በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ በኤፌሶን ላሉ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ላላቸው ታማኝ የሆኑ ቅዱሳን፦ |
አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። |
ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ስለባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይወደስ፤ |
በእሱ ፊት ፍቅር እንድናሳይ እንዲሁም ቅዱሳንና እንከን የለሽ ሆነን እንድንገኝ ዓለም ከመመሥረቱ በፊት ከክርስቶስ ጋር አንድ እንድንሆን መርጦናልና። |
ደግሞም እሱ እንደወደደና እንደ በጎ ፈቃዱ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የገዛ ራሱ ልጆች አድርጎ ሊወስደን አስቀድሞ ወስኗል፤ |
ይኸውም በተወደደው ልጁ አማካኝነት በደግነት ለእኛ በሰጠው ክቡር በሆነው ጸጋው የተነሳ እንዲወደስ ነው። |
በተትረፈረፈ ጸጋው መሠረት በልጁ ደም አማካኝነት ቤዛውን በመክፈሉ ነፃ ወጥተናል፤ አዎ፣ ለበደላችን ይቅርታ አግኝተናል። |
ጸጋውንም ከጥበብና ከማስተዋል ሁሉ ጋር አትረፍርፎ ሰጥቶናል፤ |
ይህን ያደረገው የፈቃዱን ቅዱስ ሚስጥር ለእኛ በማሳወቅ ነው። ይህ ሚስጥር ደግሞ እሱ ራሱ ካሰበው ዓላማው ጋር የሚስማማ ነው፤ |
ዓላማውም በተወሰኑት ዘመናት ማብቂያ ላይ አንድ አስተዳደር ለማቋቋም ይኸውም ሁሉንም ነገሮች ማለትም በሰማያት የሚሆኑ ነገሮችንና በምድር የሚሆኑ ነገሮችን በክርስቶስ አንድ ላይ ለመሰብሰብ ነው። አዎ፣ በእሱ አማካኝነት ሁሉም ነገሮች ይሰበሰባሉ፤ |
እኛም ከእሱ ጋር አንድነት ያለን ሲሆን ወራሾች እንድንሆንም ተመርጠናል፤ ምክንያቱም ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ሁሉንም ነገር በወሰነው መንገድ የሚያከናውነው እሱ ከዓላማው ጋር በሚስማማ ሁኔታ አስቀድሞ መርጦናል፤ |
ይህም የሆነው በክርስቶስ ተስፋ በማድረግ የመጀመሪያ የሆንነው እኛ አምላክን ከፍ ከፍ እንድናደርግና እንድናወድስ ነው። |
ይሁንና እናንተም የእውነትን ቃል ማለትም ስለ መዳናችሁ የሚገልጸውን ምሥራች ከሰማችሁ በኋላ በእሱ ተስፋ አድርጋችኋል። ካመናችሁ በኋላ በእሱ አማካኝነት፣ ቃል በተገባው መንፈስ ቅዱስ ታትማችኋል፤ |
ይህም ለአምላክ ታላቅ ምስጋና ያስገኝ ዘንድ የራሱ ንብረት የሆኑትን በቤዛ አማካኝነት ነፃ ለማውጣት ለውርሻችን አስቀድሞ የተሰጠ ማረጋገጫ ነው። |
ስለዚህ በጌታ ኢየሱስ ላይ ስላላችሁ እምነት እንዲሁም ለቅዱሳን ሁሉ ስለምታሳዩት ፍቅር ከሰማሁበት ጊዜ አንስቶ |
ስለ እናንተ ምስጋና ማቅረቤን አላቋረጥኩም። ወደፊትም ስለ እናንተ መጸለዬን እቀጥላለሁ፤ |
የክብር አባት የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ስለ እሱ ትክክለኛ እውቀት ስትቀስሙ የጥበብ መንፈስ እንዲሰጣችሁና እሱ የሚገልጣቸውን ነገሮች መረዳት እንድትችሉ እጸልያለሁ። |
የልባችሁ ዓይኖች እንዲበሩ አድርጓል፤ ይህን ያደረገው ለምን ዓይነት ተስፋ እንደጠራችሁ እንድታውቁ፣ ለቅዱሳን ውርሻ አድርጎ የሚሰጠው ታላቅ ብልጽግና ምን እንደሆነ እንድትረዱ |
እንዲሁም ታላቅ ኃይሉ ለእኛ ለምናምነው ምን ያህል የላቀ እንደሆነ እንድታውቁ ነው። የዚህ ኃይል ታላቅነት፣ እጅግ ከፍተኛ የሆነው ብርታቱ በሚያከናውነው ሥራ ታይቷል፤ |
ክርስቶስን ከሞት ባስነሳውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ባስቀመጠው ጊዜ ይህን ኃይሉን ተጠቅሟል፤ |
በዚህ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ጭምር ከየትኛውም መስተዳድር፣ ሥልጣን፣ ኃይልና ጌትነት እንዲሁም ከተሰየመው ከየትኛውም ስም በላይ እጅግ የላቀ ቦታ ሰጥቶታል። |
በተጨማሪም ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ ከጉባኤው ጋር በተያያዘም በሁሉ ነገር ላይ ራስ አደረገው፤ |
ጉባኤው የእሱ አካል ከመሆኑም በላይ በእሱ የተሞላ ነው፤ እሱ ደግሞ ሁሉንም ነገር በሁሉ የሚሞላ ነው። |
በዚህ ምክንያት እኔ ጳውሎስ ከአሕዛብ ወገን ለሆናችሁት ለእናንተ ስል የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ሆኛለሁ። |
ለእናንተ ጥቅም ሲባል ስለተሰጠኝ የአምላክ ጸጋ መጋቢነት በእርግጥ ሰምታችኋል፤ |
ቀደም ሲል በአጭሩ እንደጻፍኩት ቅዱሱ ሚስጥር ተገልጦልኛል። |
በመሆኑም ይህን ስታነቡ ስለ ክርስቶስ ቅዱስ ሚስጥር ያለኝን ግንዛቤ መረዳት ትችላላችሁ። |
ይህ ሚስጥር አሁን ለቅዱሳን ሐዋርያትና ነቢያት በመንፈስ እንደተገለጠው ባለፉት ትውልዶች ለነበሩ የሰው ልጆች አልተገለጠም ነበር። |
ሚስጥሩ ይህ ነው፦ ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሰዎች ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ በመሆን በምሥራቹ አማካኝነት አብረው ወራሾች፣ የአንድ አካል ክፍሎችና ከእኛ ጋር የተስፋው ተካፋዮች ይሆናሉ። |
አምላክ የኃይሉ መግለጫ አድርጎ በሰጠኝ ነፃ ስጦታ ይኸውም በጸጋው አማካኝነት የዚህ ሚስጥር አገልጋይ ሆኛለሁ። |
ከቅዱሳን ሁሉ ለማንስ ለእኔ ይህ ጸጋ ተሰጠኝ፤ ይህም ሊደረስበት ስለማይችለው የክርስቶስ ብልጽግና የሚገልጸውን ምሥራች ለአሕዛብ እንዳውጅ |
እንዲሁም ሁሉን ነገር የፈጠረው አምላክ ለብዙ ዘመናት ሰውሮት የቆየው ቅዱሱ ሚስጥር ሥራ ላይ የዋለበትን መንገድ ሰዎች ሁሉ እንዲያስተውሉ እረዳቸው ዘንድ ነው። |
ይህ የሆነው በርካታ ገጽታዎች ያሉት የአምላክ ጥበብ በሰማያዊ ስፍራ ላሉት መስተዳድሮችና ባለሥልጣናት አሁን በጉባኤው አማካኝነት ግልጽ ይሆን ዘንድ ነው። |
ይህም አምላክ ከጌታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ ባዘጋጀው ዘላለማዊ ዓላማ መሠረት ነው፤ |
በእሱም አማካኝነት ይህ የመናገር ነፃነት አለን፤ በክርስቶስ ላይ ባለን እምነት አማካኝነትም በልበ ሙሉነት ወደ አምላክ በነፃነት መቅረብ እንችላለን። |
ስለዚህ ለእናንተ ስል እየደረሰብኝ ባለው መከራ የተነሳ ተስፋ እንዳትቆርጡ አደራ እላችኋለሁ፤ ይህ ለእናንተ ክብር ነውና። |
በዚህም ምክንያት በአብ ፊት ለመጸለይ እንበረከካለሁ፤ |
በሰማይና በምድር ያለ እያንዳንዱ ቤተሰብ ስያሜውን ያገኘው ከእሱ ነው። |
እሱ ታላቅ ክብር ያለው እንደመሆኑ መጠን ውስጣዊውን ሰውነታችሁን የሚያጠነክር ኃይል በመንፈሱ አማካኝነት እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤ |
ደግሞም በእምነታችሁ አማካኝነት ክርስቶስ ከፍቅር ጋር በልባችሁ ውስጥ እንዲያድር እጸልያለሁ። ሥር እንድትሰዱና በመሠረቱ ላይ እንድትታነጹ ያስችላችሁ ዘንድ እለምናለሁ፤ |
ይህም ስፋቱ፣ ርዝመቱ፣ ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደሆነ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር በሚገባ መረዳት እንድትችሉ |
እንዲሁም አምላክ በሚሰጠው ሙላት ሁሉ ትሞሉ ዘንድ ከእውቀት በላይ የሆነውን የክርስቶስ ፍቅር እንድታውቁ ነው። |
እንግዲህ በእኛ ውስጥ ከሚሠራው ኃይሉ ጋር በሚስማማ ሁኔታ፣ ከምንጠይቀው ወይም ከምናስበው ሁሉ በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚችለው |
ለእሱ በጉባኤው አማካኝነትና በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት በትውልዶች ሁሉ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። |
በተጨማሪም፣ እናንተ በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ምክንያት ሙታን የነበራችሁ ቢሆንም አምላክ ሕያው አድርጓችኋል፤ |
በዚያን ጊዜ የዚህን ዓለም ሥርዓት ተከትላችሁ፣ የአየሩ ሥልጣን ገዢ በሚፈልገው መንገድ ትመላለሱ ነበር፤ ይህም አየር በማይታዘዙት ልጆች ላይ አሁን ተጽዕኖ እያሳደረ ያለ መንፈስ ነው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.