text
stringlengths
4
267
በመሆኑም በሌላው ሰው ክልል፣ አስቀድሞ በተሠራ ሥራ ከመኩራራት ይልቅ ከእናንተ ወዲያ ባሉት አገሮች ምሥራቹን እንሰብካለን።
“ሆኖም የሚኩራራ በይሖዋ ይኩራራ።”
ተቀባይነት የሚያገኘው ራሱን ብቁ እንደሆነ አድርጎ የሚያቀርብ ሳይሆን ይሖዋ ብቁ ነው የሚለው ሰው ነውና።
ምድራዊ ቤታችን የሆነው ይህ ድንኳን ቢፈርስ በሰው እጅ የተሠራ ቤት ሳይሆን በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ ሕንፃ ከአምላክ እንደምናገኝ እናውቃለን።
ከሰማይ የሆነውን መኖሪያችንን ለመልበስ እየናፈቅን በዚህ ቤት ውስጥ ሆነን እንቃትታለን፤
ስለዚህ ይህን ስንለብስ ራቁታችንን ሆነን አንገኝም።
እንዲያውም በዚህ ድንኳን ውስጥ ያለነው እኛ ከባድ ሸክም ተጭኖን እንቃትታለን፤ ምክንያቱም ዘላለማዊው ሕይወት ሟች የሆነውን አካል እንዲተካ ይህን ድንኳን ማውለቅ ሳይሆን ሰማያዊውን መኖሪያ መልበስ እንፈልጋለን።
ለዚህ ነገር ያዘጋጀን አምላክ ነው፤ ለሚመጣው ነገር ማረጋገጫ አድርጎ መንፈሱን የሰጠን እሱ ነው።
በመሆኑም ስለዚህ ጉዳይ ምንጊዜም እርግጠኞች ነን፤ በተጨማሪም መኖሪያችን በሆነው በዚህ አካል እስካለን ድረስ ከጌታ ጋር አብረን እንዳልሆን እናውቃለን፤
የምንመላለሰው በእምነት እንጂ በማየት አይደለምና።
ሆኖም እኛ እርግጠኞች ነን፤ ደግሞም ከዚህ አካል ተለይተን መኖሪያችንን ከጌታ ጋር ብናደርግ እንመርጣለን።
ስለዚህ ከእሱ ጋር አብረን ብንኖርም ሆነ ባንኖር ዓላማችን በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ነው።
ምክንያቱም እያንዳንዱ በሥጋ እያለ ላደረገው ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር፣ እንደ ሥራው ብድራት እንዲቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ልንቀርብ ይገባል።
እንግዲህ ጌታን መፍራት እንደሚገባን ስለምናውቅ ሰዎች የምንናገረውን እንዲቀበሉ ለማሳመን ምንጊዜም እንጥራለን፤ ሆኖም አምላክ በሚገባ ያውቀናል። የእናንተም ሕሊና እኛን በሚገባ እንድታውቁ እንደረዳችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
እኛ ብቃታችንን ለእናንተ እንደ አዲስ ማቅረባችን አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በልብ ውስጥ ባለው ነገር ሳይሆን በውጫዊ መልክ ለሚኩራሩ መልስ መስጠት ትችሉ ዘንድ በእኛ እንድትኮሩ እያነሳሳናችሁ ነው።
አእምሯችንን ብንስት ለአምላክ ብለን ነውና፤ ጤናማ አእምሮ ቢኖረን ደግሞ ለእናንተ ብለን ነው።
አንድ ሰው ለሁሉም መሞቱን ስለተረዳን ክርስቶስ ያለው ፍቅር ግድ ይለናልና፤ ምክንያቱም ሁሉም ቀድሞውኑ ሞተዋል።
በሕይወት ያሉትም ከእንግዲህ ለራሳቸው ከመኖር ይልቅ ለእነሱ ለሞተውና ለተነሳው እንዲኖሩ እሱ ለሁሉም ሞቷል።
ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ሰዎችን የምናውቀው ከሥጋዊ አመለካከት አንጻር አይደለም። ክርስቶስን በሥጋዊ ሁኔታ እናውቀው የነበረ ቢሆንም ከዚህ በኋላ በዚህ መንገድ አናውቀውም።
በመሆኑም ማንም ከክርስቶስ ጋር አንድ ከሆነ አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌዎቹ ነገሮች አልፈዋል፤ እነሆ፣ አዳዲስ ነገሮች ወደ ሕልውና መጥተዋል!
ሆኖም ሁሉም ነገሮች የተገኙት በክርስቶስ አማካኝነት ከራሱ ጋር ካስታረቀንና የማስታረቅ አገልግሎት ከሰጠን አምላክ ነው።
ይህም፣ አምላክ በክርስቶስ አማካኝነት ዓለምን ከራሱ ጋር ከማስታረቁም በላይ በደላቸውን አልቆጠረባቸውም ማለት ነው፤ ለእኛ ደግሞ የእርቁን መልእክት በአደራ ሰጥቶናል።
ስለዚህ እኛ ክርስቶስን ተክተን የምንሠራ አምባሳደሮች ነን፤ አምላክ በእኛ አማካኝነት እየተማጸነ ያለ ያህል ነው። ክርስቶስን ተክተን የምንሠራ እንደመሆናችን መጠን “ከአምላክ ጋር ታረቁ” ብለን እንለምናለን።
እኛ በእሱ አማካኝነት በአምላክ ፊት ጻድቅ እንድንሆን ኃጢአት የማያውቀው እሱ ለእኛ የኃጢአት መባ ተደረገ።
ስለዚህ በተደረገልን ምሕረት የተነሳ ይህ አገልግሎት ስላለን ተስፋ አንቆርጥም።
ከዚህ ይልቅ አሳፋሪ የሆኑትን ስውር ነገሮች ትተናል፤ በተንኮል አንመላለስም፤ የአምላክንም ቃል አንበርዝም፤ ነገር ግን እውነትን በመግለጥ በአምላክ ፊት የሰውን ሁሉ ሕሊና በሚማርክ መንገድ ራሳችንን ብቁ አድርገን እናቀርባለን።
እንግዲህ የምናውጀው ምሥራች በእርግጥ የተሸፈነ ከሆነ የተሸፈነው ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ነው፤
የአምላክ አምሳል ስለሆነው ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውና ክብራማ የሆነው ምሥራች የሚፈነጥቀው ብርሃን በእነሱ ላይ እንዳያበራ የዚህ ሥርዓት አምላክ የማያምኑትን ሰዎች አእምሮ አሳውሯል።
እኛ የምንሰብከው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑንና እኛም ስለ ኢየሱስ ስንል የእናንተ ባሪያዎች መሆናችንን እንጂ ስለ ራሳችን አይደለምና።
“በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይብራ” ያለው አምላክ ነውና፤ ስለሆነም በክርስቶስ ፊት አማካኝነት፣ በልባችን ውስጥ ስለ አምላክ አስደናቂ እውቀት ይፈነጥቅ ዘንድ በልባችን ላይ ብርሃን አብርቷል።
ይሁን እንጂ ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነው ኃይል ከእኛ ሳይሆን ከአምላክ የመነጨ መሆኑ ይታወቅ ዘንድ ይህ ውድ ሀብት በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን።
በየአቅጣጫው ብንደቆስም መፈናፈኛ አናጣም፤ ግራ ብንጋባም መውጫ ቀዳዳ አናጣም፤
ስደት ቢደርስብንም አልተተውንም፤ በጭንቀት ብንዋጥም አንጠፋም።
የኢየሱስ ሕይወት በእኛም ሰውነት እንዲገለጥ በኢየሱስ ላይ የደረሰውን ለሞት ሊዳርግ የሚችል መከራ ዘወትር በሰውነታችን እንሸከማለን።
የኢየሱስ ሕይወት ሟች በሆነው ሥጋችንም ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆን ለኢየሱስ ስንል ዘወትር ከሞት ጋር እንፋጠጣለንና።
ስለሆነም በእኛ ላይ ሞት፣ በእናንተ ላይ ግን ሕይወት እየሠራ ነው።
“አመንኩ፤ ስለዚህም ተናገርኩ” ተብሎ ተጽፏል። እኛም እንዲህ ዓይነት የእምነት መንፈስ ስላለን እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን፤
ኢየሱስን ያስነሳው እሱ፣ እኛንም ከኢየሱስ ጋር እንደሚያስነሳንና ከእናንተ ጋር አንድ ላይ በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን።
ይህ ሁሉ የሆነው ለእናንተ ሲባል ነውና፤ ይኸውም ብዙ ሰዎች ለአምላክ ክብር ምስጋና እያቀረቡ ስለሆነ የተትረፈረፈው ጸጋ ይበልጥ እንዲበዛ ነው።
ስለዚህ ተስፋ አንቆርጥም፤ ምንም እንኳ ውጫዊው ሰውነታችን እየመነመነ ቢሄድም ውስጣዊው ሰውነታችን ከቀን ወደ ቀን እየታደሰ እንደሚሄድ ምንም ጥርጥር የለውም።
የሚደርስብን መከራ ጊዜያዊና ቀላል ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድና ዘላለማዊ የሆነ ክብር ያስገኝልናል፤
ስለዚህ ዓይናችን እንዲያተኩር የምናደርገው በሚታዩት ነገሮች ላይ ሳይሆን በማይታዩት ነገሮች ላይ ነው። የሚታዩት ጊዜያዊ ናቸውና፤ የማይታዩት ግን ዘላለማዊ ናቸው።
ልኩራራ ይገባኛል። ምንም ጥቅም ባይኖረውም እንኳ ከጌታ የተቀበልኳቸውን ተአምራዊ ራእዮችና ጌታ የገለጠልኝን መልእክቶች እናገራለሁ።
የክርስቶስ ደቀ መዝሙር የሆነ አንድ ሰው አውቃለሁ፤ ይህ ሰው ከ14 ዓመት በፊት ወደ ሦስተኛው ሰማይ ተነጠቀ፤ የተነጠቀው በሥጋ ይሁን ከሥጋ ውጭ አላውቅም፤ አምላክ ግን ያውቃል።
አዎ፣ እንዲህ ያለ ሰው አውቃለሁ፤ በሥጋ ይሁን ከሥጋ ውጭ አላውቅም፤ አምላክ ግን ያውቃል፤
ይህ ሰው ወደ ገነት ተነጥቆ በአንደበት ሊገለጹ የማይችሉና ሰው እንዲናገራቸው ያልተፈቀዱ ቃላት ሰማ።
እንዲህ ባለው ሰው እኩራራለሁ፤ ሆኖም በድክመቶቼ ካልሆነ በስተቀር በራሴ አልኩራራም።
ልኮራ ብፈልግ እንኳ የምናገረው እውነት ስለሆነ ምክንያታዊነት እንደሚጎድለኝ ሆኜ ልቆጠር አይገባም። ይሁንና ማንም በእኔ ላይ ከሚያየውና ከእኔ ከሚሰማው በላይ እንደሆንኩ አድርጎ እንዳይገምተኝ ይህን ከማድረግ እቆጠባለሁ፤
እንዲህ ያሉ አስደናቂ ነገሮች ስለተገለጡልኝ ብቻ ማንም ሰው ለእኔ ከፍ ያለ ግምት ሊኖረው አይገባም። እንዳልታበይ ሥጋዬን የሚወጋ እሾህ ተሰጠኝ፤ ይህም እንዳልታበይ ዘወትር የሚያሠቃየኝ የሰይጣን መልአክ ነው።
ይህ ነገር ከእኔ እንዲርቅ ጌታን ሦስት ጊዜ ለመንኩት።
እሱ ግን “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ምክንያቱም ኃይሌ ፍጹም የሚሆነው በምትደክምበት ጊዜ ነው” አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል በእኔ ላይ እንደ ድንኳን እንዲኖር እጅግ ደስ እያለኝ በድክመቴ እኩራራለሁ።
ስለሆነም ስለ ክርስቶስ ስል በድክመት፣ በስድብ፣ በእጦት፣ በስደትና በችግር ደስ እሰኛለሁ። ስደክም ያን ጊዜ ብርቱ ነኝና።
ምክንያታዊነት የሚጎድለኝ ሆኛለሁ። እንዲህ እንድሆን ያስገደዳችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ እናንተ ስለ እኔ ብቃት መመሥከር መቻል ነበረባችሁና። ምንም እንኳ እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆንም ከእናንተ የተራቀቁ ሐዋርያት በአንዲት ነገር እንኳ አላንስም።
ደግሞም የሐዋርያነቴን ማስረጃዎች በታላቅ ጽናት እንዲሁም ምልክቶችን፣ ድንቅ ነገሮችንና ተአምራትን በመፈጸም አሳይቻችኋለሁ።
እናንተ ከሌሎች ጉባኤዎች ያነሳችሁት በምንድን ነው? ምናልባት እኔ በእናንተ ላይ ሸክም ሳልሆን በመቅረቴ ሊሆን ይችላል፤ እንዲህ ከሆነ ይህን ጥፋቴን በደግነት ይቅር በሉኝ።
እነሆ ወደ እናንተ ለመምጣት ስዘጋጅ ይህ ሦስተኛ ጊዜዬ ነው፤ በእናንተ ላይ ሸክም አልሆንም። እኔ የምፈልገው እናንተን እንጂ ንብረታችሁን አይደለምና፤ ደግሞም ለልጆቻቸው ሀብት ማከማቸት የሚጠበቅባቸው ወላጆች ናቸው እንጂ ልጆች ለወላጆቻቸው አያከማቹም።
በእኔ በኩል ስለ እናንተ ያለኝን ሁሉ፣ ራሴንም ጭምር ብሰጥ እጅግ ደስ ይለኛል። እኔ ይህን ያህል አጥብቄ ከወደድኳችሁ እናንተ ለእኔ ያላችሁ ፍቅር ከዚህ ያነሰ ሊሆን ይገባል?
የሆነ ሆኖ ሸክም አልሆንኩባችሁም። ነገር ግን እናንተ “መሠሪ” እንደሆንኩና “አታልዬ” እንዳጠመድኳችሁ ትናገራላችሁ።
ለመሆኑ ወደ እናንተ ከላክኋቸው ሰዎች መካከል በአንዱ እንኳ ተጠቅሜ ከእናንተ አላግባብ ጥቅም ለማግኘት ሞክሬአለሁ?
ቲቶ ወደ እናንተ እንዲመጣ ገፋፋሁት፤ ከእሱም ጋር ወንድምን ላክሁት። ለመሆኑ ቲቶ ከእናንተ አላግባብ ጥቅም ለማግኘት ሞክሮ ነበር? ከእሱ ጋር በአንድ መንፈስ አልተመላለስንም? አካሄዳችንስ አንድ አልነበረም?
እስካሁን ድረስ የምታስቡት እኛ ለእናንተ የመከላከያ መልስ እየሰጠን እንዳለን አድርጋችሁ ነው? እኛ የክርስቶስ ተከታዮች ሆነን የምንናገረው በአምላክ ፊት ነው። ይሁንና የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ሁሉንም ነገር የምናደርገው እናንተን ለማነጽ ነው።
እኔ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ምናልባት እኔ እንደምፈልገው ሳትሆኑ እንዳላገኛችሁ፣ እናንተም እኔን እንደምትፈልጉት ሆኜ ሳታገኙኝ እንዳትቀሩ እሰጋለሁ፤ እንዲያውም ጠብ፣ ቅናት፣ ኃይለኛ ቁጣ፣ ንትርክ፣ ስም ማጥፋት፣ ሐሜትና ብጥብጥ እንዲሁም በኩራት የተወጠሩ ሰዎች እንዳይኖሩ እሰጋለሁ።
እንደገና በምመጣበት ጊዜ ምናልባት አምላኬ በፊታችሁ ያሳፍረኝ ይሆናል፤ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ኃጢአት ፈጽመው ከሠሩት ርኩሰት፣ የፆታ ብልግናና ዓይን ያወጣ ምግባር ንስሐ ባልገቡት በርካታ ሰዎች አዝን ይሆናል ብዬ እፈራለሁ።
ደግሞም ከእሱ ጋር አብረን የምንሠራ እንደመሆናችን መጠን የአምላክን ጸጋ ከተቀበላችሁ በኋላ ዓላማውን እንዳትስቱ እናሳስባችኋለን።
እሱ “ሞገስ በማሳይበት ጊዜ ሰምቼሃለሁ፤ በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ” ይላልና። እነሆ፣ አምላክ ሞገስ የሚያሳይበት ልዩ ጊዜ አሁን ነው። እነሆ፣ የመዳን ቀን አሁን ነው።
አገልግሎታችን እንከን እንዳይገኝበት በምንም መንገድ ማሰናከያ እንዲኖር አናደርግም፤
ከዚህ ይልቅ በሁሉም ነገር ራሳችንን ብቁ የአምላክ አገልጋዮች አድርገን እናቀርባለን፤ ይህን የምናደርገው በብዙ ነገር በመጽናት፣ በመከራ፣ በእጦት፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች፣
በድብደባ፣ በእስር፣ በሁከት፣ በከባድ ሥራ፣ እንቅልፍ አጥቶ በማደርና ጾም በመዋል ነው።
የአምላክ አገልጋዮች መሆናችንን በንጽሕና፣ በእውቀት፣ በትዕግሥት፣ በደግነት፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፣
እውነት የሆነውን በመናገርና በአምላክ ኃይል እናሳያለን። እንዲሁም በቀኝ እጅና በግራ እጅ የጽድቅ መሣሪያዎችን በመያዝ፣
ክብርንም ሆነ ውርደትን እንዲሁም ነቀፋንም ሆነ ምስጋናን በመቀበል የአምላክ አገልጋዮች መሆናችንን እናስመሠክራለን። እውነተኞች ሆነን ሳለን እንደ አታላዮች ተቆጥረናል፤
በሚገባ የታወቅን ሆነን ሳለን እንደማንታወቅ ተቆጥረናል፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ፣ ሕያዋን ነን፤ ብንቀጣም ለሞት አልተዳረግንም፤
ሐዘንተኞች ተደርገን ብንታይም ምንጊዜም ደስተኞች ነን፤ እንደ ድሆች ብንቆጠርም ብዙዎችን ባለጸጋ እያደረግን ነው፤ ምንም የሌለን ብንመስልም ሁሉ ነገር አለን።
የቆሮንቶስ ወንድሞች ሆይ፣ በግልጽ ነግረናችኋል፤ ልባችንም ወለል ብሎ ተከፍቶላችኋል።
እኛ ፍቅራችንን አልነፈግናችሁም፤ እናንተ ግን ጥልቅ ፍቅራችሁን ነፍጋችሁናል።
ስለዚህ ልጆቼን እንደማናግር ሆኜ አናግራችኋለሁ፤ እናንተም በአጸፋው ልባችሁን ወለል አድርጋችሁ ክፈቱ።
ከማያምኑ ጋር አቻ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ። ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ኅብረት አለው? ወይስ ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ያገናኘዋል?
በተጨማሪም በክርስቶስና በቤልሆር መካከል ምን ስምምነት አለ? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ድርሻ አለው?
እንዲሁም የአምላክ ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ የሕያው አምላክ ቤተ መቅደስ ነንና፤ አምላክ “በመካከላቸው እኖራለሁ፤ ከእነሱም ጋር እሄዳለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፣ እነሱ ደግሞ ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደተናገረው ነው።
“‘ስለዚህ ከመካከላቸው ውጡና ራሳችሁን ለዩ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ርኩስ የሆነውንም ነገር አትንኩ’”፤ “‘እኔም እቀበላችኋለሁ።’”
“‘እኔ አባት እሆናችኋለሁ፤ እናንተ ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትሆኑኛላችሁ’ ይላል ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ።”
ወንድሞች፣ በመቄዶንያ ላሉት ጉባኤዎች ስለተሰጠው የአምላክ ጸጋ እንድታውቁ እንፈልጋለን።
ከባድ ፈተና ደርሶባቸው በመከራ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ታላቅ ደስታ የነበራቸው ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ልግስና አሳይተዋል፤ ይህን ያደረጉት በጣም ድሆች ሆነው ሳለ ነው።
እንደ አቅማቸው እንዲያውም ከአቅማቸው በላይ እንደሰጡ እመሠክርላቸዋለሁና፤
ምክንያቱም እነዚህ ወንድሞች ለቅዱሳን በልግስና በመስጠት፣ በእርዳታ አገልግሎቱ ለመካፈል መብት እንዲሰጣቸው በራሳቸው ፍላጎት ተነሳስተው ይለምኑን እንዲያውም ይማጸኑን ነበር።
ደግሞም ከጠበቅነው በላይ አድርገዋል፤ ምክንያቱም ራሳቸውን በመጀመሪያ ለጌታ ከዚያም በአምላክ ፈቃድ ለእኛ ሰጥተዋል።
ስለዚህ ቲቶ ቀደም ሲል በእናንተ መካከል የልግስና ስጦታችሁን የማሰባሰቡን ሥራ እንዳስጀመረ ሁሉ ይህንኑ ሥራ ወደ ፍጻሜ እንዲያደርስ አበረታታነው።
ስለዚህ በሁሉም ነገር ይኸውም በእምነት፣ በቃል፣ በእውቀት፣ በትጋት ሁሉና እኛ ለእናንተ ባለን ፍቅር ባለጸጋ እንደሆናችሁ ሁሉ በልግስና በመስጠት ረገድም ባለጸጋ ሁኑ።
ይህን የምላችሁ እናንተን ለማዘዝ ሳይሆን ሌሎች የሚያሳዩትን ትጋት እንድታውቁ ለማድረግና የፍቅራችሁን እውነተኝነት ለመፈተን ነው።
የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና፤ በእሱ ድህነት እናንተ ባለጸጋ ትሆኑ ዘንድ እሱ ባለጸጋ ሆኖ ሳለ ለእናንተ ሲል ድሃ ሆኗል።
በዚህ ረገድ የምሰጠው ሐሳብ አለ፦ ይህን ሥራ መሥራታችሁ ይጠቅማችኋል፤ ምክንያቱም ከአንድ ዓመት በፊት ሥራውን መጀመር ብቻ ሳይሆን ዳር ለማድረስም ፍላጎት እንዳላችሁ አሳይታችኋል።
ስለዚህ የጀመራችሁትን ሥራ ዳር አድርሱት፤ ሥራውን ለመጀመር ጓጉታችሁ እንደነበር ሁሉ፣ አሁንም እንደ አቅማችሁ በመስጠት ከፍጻሜ እንዲደርስ አድርጉ።
ለመስጠት ፈቃደኝነቱ ካለ ስጦታው ይበልጥ ተቀባይነት የሚኖረው አንድ ሰው ባለው መጠን ሲሰጥ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለምና።
ይህን የምለውም ሌሎች እንዲቀላቸው አድርጌ እናንተ እንዲከብዳችሁ ለማድረግ አይደለም፤
ከዚህ ይልቅ በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነሱን ጉድለት እንዲሸፍን ነው፤ የእነሱ ትርፍ ደግሞ የእናንተን ጉድለት ይሸፍናል፤ ይህም ሸክሙን እኩል እንድትጋሩ ያስችላል።
ይህ ደግሞ “ብዙ የሰበሰበ ብዙ አላተረፈም፤ ጥቂት የሰበሰበም ምንም አልጎደለበትም” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
እኛ ለእናንተ ያለንን ዓይነት ልባዊ አሳቢነት በቲቶ ልብ ውስጥ ያሳደረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤
ምክንያቱም ቲቶ ወደ እናንተ የሚመጣው የእኛን ማበረታቻ በመቀበል ብቻ ሳይሆን በታላቅ ጉጉት፣ በራሱ ፈቃድ ተነሳስቶ ነው።
ይሁንና ከምሥራቹ ጋር በተያያዘ እያከናወነ ባለው ሥራ በጉባኤዎች ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ከእሱ ጋር እንልከዋለን።
ከዚህም በላይ ጌታን ለማስከበርና ሌሎችን ለመርዳት ዝግጁ መሆናችንን ለማሳየት ይህን የልግስና ስጦታ በምናከፋፍልበት ጊዜ ይህ ወንድም የጉዞ አጋራችን እንዲሆን በጉባኤዎች ተሹሟል።