text
stringlengths
707
989
### Text: አቡ ባክር አልባግዳዲየአይ ኤስ ቡድን መሪ አቡ ባክር አልባግዳዲ ድምጹን ካጠፋ ከአምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክቱን አስተላልፏል። ቡድኑ ለተነጠቃቸው ይዞታዎችም የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ ዝቷል።በአውሮፓውያኑ 2014 ሞሱል በተባለችው የሶሪያ ከተማ ውስጥ ሆኖ በሶሪያና ኢራቅ ላይ እስላማዊ ካሊፌት መመስረቱን ካወጀ በኋላ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ቀርቶ ነበር።በተንቀሳቃሽ ምስሉ በቅርቡ በባጉዝ ያጋጠማቸውን ሽንፈት ያመነ ሲሆን መልዕክቱ መቼ እንደተቀረጸ ግን እርግጠኛ መሆን አልተቻለም። ቡድኑ በበኩሉ ተንቀሳቃሽ ምስሉ በያዝነው ሚያዚያ ወር ላይ የተቀረጸ እንደሆነ አስታውቋል።አልባግዳዲ በመልዕክቱ ከሁለት ሳምንት በፊት በስሪላንካ የፋሲካ በዓል ዕለት ለደረሰው የቦምብ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን ባጉዝ ላይ ላጋጠማቸው ሽንፈት ምላሽ እንደሆነ አስታውቋል።ከዚህ በተጨማሪም አልባግዳዲ የሚመራው ቡድን በቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ፣ ሱዳንና አልጄሪያ ባሉ የአፍሪካ ሃገራት ስላለው ወታደራዊ ግንኙነትና መታወጅ ስላለበት ኢስላማዊ ጂሃድ መልዕክቱን አስተላልፏል።ቡድኑ ምንም እንኳን በተለያዩ ግዛቶች ሽንፈትን ቢቀምስም የዚህኛው ተንቀሳቃሽ ምስል ዋነኛ ግቡ ሽንፈቶቹን ለመቀበል ሳይሆን አልባግዳዲን ለገደለ 25 ሚሊየን ዶላር ሽልማት ከመኖሩ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ሳይሞት አይቀርም ማለታቸውን ለማስተባበል ይመስላል። ### Response:
### Text: ቃጠሎው የተነሳው ከቅኔ ማህሌቱ ሳይሆን ከመቅደሱ ውስጥ ነው፡፡ ማን አስነሳው እንዴት ተነሳ ሻማ አብርቶ የወጣው ዲያቆኑ ነው ወይስ ቄሰ ገበዙ ለምን ሳያጠፉ ወጡ የሚለው ከፖሊስ ምርመራ በኋላ አብረን የምናየው ይሆናል የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል በቀን 28022012ዓም ጥዋት 11 ሰአት ላይ በኮምቦልቻ መንበረ ሕይወት መድሐኒዓለም ቤተ ክርስትያን በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ከደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል ለሚዲያ አካላት የተሰጠ መግለጫትናንት በ27022012ዓም በመላው ቤተ ክርስያን የሚከበረው የታላቁ በአላችን መድሀኒዓለም የሰው ልጆችን ያዳነበት ነው፡፡ ይህን አስመለክቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተከበሯል፡፡ በተጨማሪም በሀገሪቱ ላይ ባለው አለመረጋጋትና መከራ ስደትና የቤተክርስትያን ቃጠሎ አስመልከቶ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መመርያ መሰረት አጠቃላይ በኢትዮጵያ የሚገኙ ገዳማትና አድባራት አምላካችን የመጣውን መከራ እንዲያስታግስልንና ቀጣይ ደግሞ ምእመናኑ ህወታቸውን እንዲጠብቁ ጸሎተ ምህላ ከጀመርን እነሆ ዛሬ አምስተኛ ቀናችን ነው፡፡የማታው መርሀ ግብር ከንግሱ በአል በላይ የምእመኑ ቁጥር ብዙ ነበር፡፡ በአሉ ፖሊሶችና የፀጥታ አካላት ባሉበት ከቀኑ 11 ሰአት የጀመረው ከምሽቱ 2 ሰአት በሰላም ተጠናቋል፡፡ተረኛ የቤተክርስትያን አገልጋዮች ቁልፉን ለተረኛ ጥበቃ አስረክበው ወጥተዋል፡፡ 11083 ### Response:
### Text: አፍሪካ ሕብረት እንዲገኝ ጥሪ አልደረሰንም ኤባ ካሎንዶአዲሱ የቡድን 20 የበለጸጉ ሀገራት ዓባል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ኅብረት ቡድኑ በሳምንቱ መጨረሻ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ እንዳልተጋበዘ ገልጿል።ነገ ዓርብ እና ቅዳሜ በኒው ደሊ የሚካሄደውን ጉባኤ ያዘጋጀችው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ አፍሪካዊው ድርጅት ቡድኑን እንዲቀላቀል ጥሪ አድርገው ነበር።የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ቃል አቀባይ የሆኑት ኤባ ካሎንዶ፣ ኅብረቱ በጉባኤው ላይ እንዲገኝ ጥሪ እንዳልደረሰው ትናንት ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።19 ሀገራትን እና የአውሮፓ ኅብረትን በዓባልነት ያቀፈው ስብስብ፣ 85 በመቶ የዓለምን የሀገር ውስጥ ምርት እና ከዓለም ሕዝብ ሁለት ሶስተኛውን ይይዛል።ደቡብ አፍሪካ ከአህጉሪቱ ብቸኛዋ የቡድኑ ዓባል ነች፡፡የአፍሪካ ኅብረትን የጋበዝነው ወደፊት ቋሚ ዓባል እንዲሆን ታሳቢ በማድረግ ነው ሲሉ ሞዲ ከ 10 ቀናት በፊት ተናግረው ነበር።የአፍሪካ ኅብረትን በቋሚ ዓባልነት ሞቅ አድርገን ለመቀበል እንጠብቃለን ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ባለፈው ታህሳስ ተናግረው ነበር፡፡የቡድን 20 አባላት እነማን ናቸው 0አርጀንቲና ብራዚል ካናዳ ቻይና ፈረንሳይ ጀርመን ህንድ ኢንዶኔዥያ0ጣልያን ጃፓን ደቡብ ኮሪያ 0ሜክሲኮ0ሩስያ ሱዑዲ አረቢያ0ደቡብ አፍሪካ ቱርክ ዩናይትድ ኪንግደም አሜሪካ አውሮፓ ሕብረት ናቸው። ኤኤፍፒ ቪኦኤ ### Response:
### Text: የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስተዳደር እና የሠራተኛ ማህበር እሰጥ አገባበኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ውስጥ ከሚገኙት የሠራተኛ ማህበራት አንዱ ከአየር መንገዱ አስተዳደር ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቷል።በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ሁለት የሠራተኛ ማህበራት ይገኛሉ። እኚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ይሰኛሉ።ቀዳማዊ የምትለዋን ቃል በውስጡ የያዘው የሠራተኛ ማህበር የተመሰረተው ከ58 ዓመታት በፊት ሲሆን ተቋሙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ተብሎ ሲቋቋም የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ሰራተኞችን ለማካተት እና አዲስ አመራሮችን ወደ ፊት ለማምጣት በአዲሱ ስያሜ ከሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር እውቅና ማግኘቱን የማህበሩ ዋና ጸሃፊ አቶ አብዱ ይመር ተናግረዋል።ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ከአሰሪው ጋር በቅን መንፈስ በመደራደር የሠራተኛውን መብት እና ጥቅም እያስከበረ መሆኑን ከትናንት በስቲያ የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።የዚህ ማህበር ሥራ አስፈጻሚዎች ይህን ይበሉ እንጂ የሌላኛው ማህበር ማለትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር የሆኑት ካፒቴን የሺዋስ ፈንታሁን በዚህ ፈጽሞ አይስማሙም። 1226 ### Response:
### Text: አሁንም በአካባቢው ስጋት በመኖሩ የመከላከያ ኃይል ወደ አካባቢው እንዲላክልን ጠይቀናል አበርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪ ደስታ ለማአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ በኒሯቅ ከተማ ትናንት ታጣቂዎች ጥቃት ከፍተው በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ለማ ጀርመን ድምፅ ሬድዮ አስታውቀዋል።አሁንም በአካባቢው ስጋት በመኖሩ የመከላከያ ኃይል ወደ አካባቢው እንዲላክላቸው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪው ጠይቀዋል፡፡ አቶ ደስታ ለሬድዮ ጣቢያው በዘረዘሩት የጉዳት መጠንም ታጣቂ ሚሊሻ 7 ንፁሀን ዜጎች ወደ 11 አካባቢ ጉዳት ደርሷል። 4 የመንግስት መኪና ተቃጥለዋል። የግለሰብ ሁለት ተቃጥለዋል። ጤና ጣቢያ ተቃጥሏል። መድሃኒት ፣ ወንበር ንብረት፣ ተሰባብሯል ወድሟል።ሰኞ ዕለት ከሌሊቱ 1030 በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ በኒሯቅ ታጣቂዎች በአደረሱት ጥቃት ህይወት ማለፉንና ንብረት መውደሙን አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለጀርመን ድምፅ ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጠረው በአካባቢው ከፍተኛ መዘናጋት ስለነበር አስታውሰው፣ ከአንድ ወር በፊት በዚሁ አስተዳደር ፃታ በተባለ አካባቢ የተፈጠረውን ጥቃት እንደ ማነፃፀሪያ አቅርበዋል።የዋግኽምራ ብሔረሰብ 0የአማራ ክልል ሚሊሺያ ጽቤት ኃላፊ አቶ መኳንንት መልካሙእንደተናገሩት ታጣቂዎች 11 ንፁህ ነዋሪዎችን ገድለዋል፡፡ 0427 ### Response:
### Text: ደቡብ ክልል️በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል የሚነሱ የክልል፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ ጥያቄዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመመለስ የሚያስችል ጥናት ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።ጥናቱ የሚጀመረውም የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ባለፈው መስከረም ወር ባካሄደው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እንዲፈቱ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት መሆኑ ነው የተገለፀው።በዚህ መሰረትም ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችለውን ጥናት ለማካሄድ ከምሁራን፣ከወጣቶች እና ከመንግስት ሰራተኞች የተውጣጡ 20 አባላትን የያዘ ኮሚቴ መቋቋሙን የጥናት ቡድኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶክተር ያኒአ ሰይድ መክይ ተናግረዋል።የጥናት ቡድኑ በዋናነትም እየተነሱ ያሉትን ጥያቄዎች ከክልሉ ህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ዘላቂ ልማት አንፃር በመመርመር ህዝቦቹ በጋራ በኖሩባቸው ጊዜያት ያተረፉትንና ያጡትን አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የሚያጠና መሆኑ ተነግሯል።በሚቀጥለው ሳምንት የሚጀምረው የጥናት ሂደት ከአምስት እስከ ስድስት 0ወራት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ተጠናቆ የክልሉ መንግስት ውሳኔ እንዲሰጥበት ይደረጋል ነው የተባለው ።ጥናቱ እስኪጠናቀቅ እና ጥያቄዎች በሰለጠነ እና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ምላሽ እስኪያገኙ ድረስምየክልሉ ህዝብ ሰላም እና አንድነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል የጥናት ቡድኑ0 የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጠይቀዋል።ምንጭ ፋና ብሮድካስቲንግ ### Response:
### Text: ሳውዲ አረቢያ የፀረሙስና ዘመቻዋን እንዳጠናቀቀች አስታወቀች። ከአመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ጀምራው የነበረውን መጠነ ሰፊ የፀረሙስና ዘመቻ እንዳጠናቀቀች አስታውቃለች፡፡ በፀረሙስና ዘመቻው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር አሊአላሙዲንን ጨምሮ በመቶዎች ሚቆጠሩ የንጉሣዊያን ቤተሰብ አባላት እና ቢሊየነር ነጋዴዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት 100 ቢሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና በቁስ መልክ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መሰብሰቡን አስታውቋል። የባህር ሰላጤዋ ንጉሣዊ ግዛት አስተዳዳሪዎች እንደሚሉት በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት 87 ግለሰቦች የቀረበባቸውን ክስ በማመናቸው ከመግባባት ላይ ተደርሷል። 8ቱ የቀረበባቸውን ክስ ስላላመኑ ጉዳያቸው ለአቃቤ ሕግ ተላልፎ የተሰጠ ሲሆን የ56 ሰዎች ጉዳይ ደግሞ ውሳኔ ያላገኘ የወንጀል ክስ ስላለባቸው ጉዳያቸው አልተጠናቀቀም ተብሏል። የሳዑዲ መንግሥት ያካሄደውን የፀረሙስና ዘመቻን ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊአላሙዲ ከቀናት በፊት ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል። ሳዑዲ ወደ 200 የሚጠጉ ልዑላንን፣ ሚንስትሮችን እና የንግድ ኃላፊዎችን ሪያድ በሚገኘው ባለ 5 ኮከቡ ዘ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ሥር አቆይታ ነበር። የፀረሙስና ዘመቻው የተጀመረው ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው እየጨመረ በመጣው በልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ነው።ምንጭ፡ ቢቢሲ ### Response:
### Text: 553 ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው ተመለሱአምስት መቶ 53 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረብያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡ በሳኡዲ አረብያ ጂዛን ግዛት ኢዋ እና ሲጂንነዓም በተሰኙ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 280 ኢትዮጵያውያን ትናንት ከሌሊቱ በ8፡30 ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።ኢትዮጵያዊያኑ ከ5 ዓመት እስከ 30 ዓመት ድረስ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ጅዳ በሚገኘው የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄነራል ጽቤት በኩል የሳኡዲ መንግስት ምህረት እንዲያደርግላቸው በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።ኢትዮጵያዊያኑ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኮንሱላር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ዮሃንስ ሾዴ እና ሌሎች አካላት በተገኙበተ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።በተመሳሳይ በጅዳ እና ጂዛን ግዛት ያለ ህጋዊ የጉዞ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 273 ኢትዮጵያውን ረቡዕ ማታ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።ከነዚህ ተመላሾች ውስጥ 75ቱ ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወንዶች ናቸው።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተለያዩ ሀገራት በእስር ላይ የሚገኙ ኢትጵያውያንን በማስፈታት በህገወጥ መንገድ የሚኖሩም በፈቃደኝነት ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽቤት የተገኘነው መረጃ ያሳያል። ### Response:
### Text: ፓስፖርት ለማውጣት የልደት ማስረጃ የሚጠየቁት እድሜያቸው ከ18 እስከ 40 አመት ለሆናቸው ዜጎች ብቻ ነው ተባለ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዜጎች ፓስፖርት ለማውጣትና ለማደስ ሲመጡ የሚያቀርቡት የነዋሪነት መታወቂያና የድጋፍ ደብዳቤ ህገወጥ አሰራር እንዲበራከት በማድረጉ ከዚህ በኋላ የልደት ሰርተፊኬትና መታወቂያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ማለቱ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም የልደት የምስክር ወረቀት የትና እንዴት ማግኘት ይቻላል፣ የተወለድንበትን ቀንና አመተ ምህረት በትክክል አናውቅም፣ እና መሰል ጥያቄዎች ከህብረተሰቡ እየተሰሙ ነው፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም የኤጀንሲው ህዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ታሬሳን ስለጉዳዩ ጠይቆ ነበር። የልደት ምስክር ወረቀት በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በወረዳ ወሳኝ ኩነት መቤቶች አማካይነት የሚሰጥ በመሆኑ የተወለዱበትን ቀን የሚገልጽ የሆስፒታል ማስረጃ ይዘው በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ ብለውናል፡፡ ለዚህም ስራ ሲባል ኤጀንሲው የሰርተፊኬት ወረቀቶችን በነጻ ማሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡የተወለድንበትን ቀን አናውቅም እና ሆስፒታል አልተወለድንም ለሚሉ ጥያቄዎች ሲመልሱም ይህን ታሳቢ በማድረግ እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ የሆኑትን አንጠይቅም ብለዋል፡፡ ወደፊትም አዳዲስ ማሻሻያዎች ካሉ እናሳውቃለን ሲሉ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ምንጭ ኢትዮ ኤፍ ኤም ### Response:
### Text: ህገ ወጥ ቤቶቹ መፍረስ ጀምረዋል የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በከተማይቱ አዉሮፕላን ማረፊያ አጠገብና አካባቢ የተገነቡ «ሕገወጥ» ያላቸዉን ቤቶች ማፍረስ ጀመረ። ቤቶቹን የሚያፈርሰዉ ግብረኃይል «ሥራ» እንዳይታወክ የከተማዋ አስተዳደር፣ የፌደራል ፖሊስን እና ባካባቢዉ የሠፈረዉ የሐገር መከላከያ ሠራዊት ፀጥታ እያስከበሩ ነዉ። ይሁንና የቤቶቹን መፍረስ የሚቃወሙ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ቤቶቹን በሚያፈርሱት ላይ ድንጋይ በመወርወር እና ጎማ በማቃጠል እርምጃዉን ተቃዉመዉታል።አንዳንድ ተሽከርካሪዎች በድንጋይ መመታታቸዉን ዘግቧል። የድሬዳዋ መስተዳድር ቤቶቻቸዉ ለሚፈርሱባቸዉ ነዋሪዎች ተለዋጭ ሥፍራም ሆነ ካሳ ሥለመስጠት አለመስጠቱ ግን የተባለ ነገር የለም። ኢትዮጵያ ዉስጥ የአዲስ አበባን ጨምሮ የተለያዩ ከተሞች ባለስልጣናት «ሕገወጥ» የሚሏቸዉ ቤቶች ከመገንባታቸዉ በፊትና ሲገነቡ፣ እንዳይገነቡ ከመከላከል ይልቅ ከተገነቡና ሰዎች በየቤቶቹ መኖር ከጀመሩ በኋላ ማፍረስ የተለመደ ነዉ። እየተገነቡ በኃይል በሚፈርሱ ቤቶች ምክንያት ለሚባክነዉ ሐብት፣ በነዋሪዉ ላይ ለሚደርሰዉ መንገላታትና ኪሳራ ብዙ ትኩረት የሚሰጠዉ ወገን ያለ አይመስልም። የድሬዳዋ መስተዳድር በከተማይቱ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የተሰሩትን «ሕገወጥ» ቤቶች ማፍረስ የጀመረዉ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ቤቶቹ ካልፈረሱ በረራ እንደሚያቋርጥ ካስጠነቀቀ በኋላ ነዉ። ### Response:
### Text: በሱዳን እየተካሔደ በሚገኘው 2ኛው የኢትዮ ሱዳን ድንበር የጋራ ከፍተኛ የፖለቲካ ኮሚቴ ውይይት ላይ ምጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮችን የተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡ከጥቅምት 302013 ዓም ጀምሮ የሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ በተደራጀ መልኩ ጥቃት እየፈጸሙ ስለመሆናቸው አቶ ደመቀ በንግግራቸው አንስተዋል፡፡ ይህም በትግራይ ክልል የተፈጠረው ቀውስ ሳምንት እንኳን ሳይሞላው ነው የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት መፈጸም የጀመረው፡፡አቶ ደመቀ በንግግራቸው ከባድ የጦር መሳሪያዎችን እና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም የሱዳን ጦር የተደራጁ ጥቃቶችን እየፈጸመ መሆኑን እየተመለከትን ነው ብለዋል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የግብርና ምርቶች ተዘርፈዋል ካምፖቻቸው ወድመዋል እንዲሁም የራሳቸውን የእርሻ ምርት እንዳያጭዱ ተደርገዋል ያሉት አቶ ደመቀ በርካታ ንጹሀን ስለመገደላቸው እና ስለመቁሰላቸውም ገልጸዋል፡፡ እናም በድንበር አከባቢዎች የተከሰተው የቅርብ ጊዜ ክስተት የኢትዮጵያን መንግስት ክፉኛ እንዳሳሰበው ነው በንግግራቸው ያካተቱት፡፡ ምጠሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህ ሁኔታ በሰሜን ዳግልሽ ተራራ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ባለበት ለማቆየት የደረስናቸውን ስምምነቶች አደጋ ላይ እየጣለ ነው በማለት ስጋታቸውንም ገልጸዋል፡፡ 1222 ምንጭ አል ዓይን ### Response:
### Text: የባይደን ጉባኤ ላይ ተሳታፊ ሀገራት እነማን ናቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት0ጆ ባይደን0ዴሞክራሲን በተመለከተ በመጪው ታህሳስ ወር ሊያካሂዱ የኦንላይ ጉባኤ ያካሂዳሉ። ለዚሁ ጉባዔ የ110 ሃገራት መሪዎችን ጋብዘዋል።ጉባዔው በዋናነት ዴሞክራሲያዊ እና አምባገነን የሚሉ እሳቤዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በፈረንጆቹ ታህሳስ 9 እና 10 2021 የሚካሄድ ነው፡፡በጉባዔው ሩሲያ እና ቻይና አልተጋበዙም፡፡ሩሲያ ሃገራትን ለመከፋፈል የሚደረግ ነው ስትል የባይደንን የጉባዔ ጥሪ ኮንናዋለች፡፡ ቻይና የግዛቷ አካል አድርጋ የምታያት ታይዋን በጉባዔው እንድትሳተፍ በመጋበዟ ተቆጥታለች።ከአፍሪካ አንጎላ ፣ ቦትስዋና ፣ ጋና ፣ ሞሪሽዬስ ፣ ናሚቢያ ፣ ሴኔጋል ፣ ሲሼልስ ፣ ዛምቢያ ፣ ዲአር ኮንጎ ፣ ኬንያ ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ ናይጄሪያ እና ኒጀር ተጋብዘዋል። ኢትዮጵያ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መቤት በኩል በወጣው የተጋባዦች ዝርዝር ውስጥ አልተካተተችም፡፡ከመካከለኛው ምስራቅ እስራኤል እና ኢራቅ ብቻ ናቸው የተሳተፉት፡፡ የቀጣናው የአሜሪካ የቅርብ አጋር የሆኑት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ዮርዳኖስ ፣ ኳታር አልተጋበዙም፡፡ከደቡብ አሜሪካ በጃይር ቦልሶናሮ የምትመራውን ብራዚልን ጨምሮ ኡራጓይን የመሳሰሉ የቀጣናው ሃገራት ተጋብዘዋል፡፡ህንድ፣ ፓኪስታን፣ ማልዲቭስ እንዲሁም ኔፓል ከእስያ የጉባዔው ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ምንጭ አል ዓይን ኒውስ ### Response:
### Text: ጋምቤላዩኒቨርሲቲ በጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን ለዞኑ ወጣቶችና ነዋሪዎች ስራ ለመፍጠር እንዲያግዘው የጋምቤላ ዩኒቨርስቲን ጠየቀ። የሳይስንና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በትናትናው ዕለት በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን የሚገኘውን አልዌሮ ሰው ሰራሽ ግድብ ጎብኝተዋል፡፡ፕሮፌሰር አፈወርቅ በከፍተኛ አሳ ምርት የሚታወቀውን ግድብ የጎበኙት ከጋምቤላ ዩኒቨርስቲ አመራሮች ጋር በመሆን ነበር፡፡ የአኙዋክ ዞን አስተዳዳሪ ለዩኒቨርስቲው የድጋፍ ጥያቄያቸውን ያቀረቡትም በጉብኝቱ ላይ በተገኙበት ወቅት ነው፡፡የጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶር ኡጁሉ ኦኮክ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ በጥናት ላይ በመመስረት ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መስራት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው በበኩላቸው ዩኒቨርስቲዎችና ማህበረሰቡ በትስስር በጋራ በመስራት የሚታዩ ችግሮችን ተጋግዘው መቅረፍ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ከሳይስንና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በአልዌሮ ግድብ የመስኖ ቦዮችን በማልማት በአሁኑ ሰዓት በአከባቢው ሩዝ እና ጥጥ እየተመረተ ይገኛል፡፡የመስኖ ቦዮቹ እስከ 10000 ሄክታር መሬት የማልማት አቅምም አላቸው፡፡ ይህ ግድብ 2220 ሄክታር ስፋት እና 13 ሜትር ጥልቀት አለው፡፡ አልዌሮ ሰው ሰራሽ ግድብ በአልዌሮ ወንዝ ላይ የተሰራና በአኙዋክ ዞን አቦቦ ወረዳ የሚገኝ ነው፡፡ ### Response:
### Text: በጉምቢ ቦርደዴ ግጭት የአመራሮች እጅ ነበረበት ተባለ ለ10 ሰዎች ሞትና ለበርካታ ዜጎች ጉዳት መንስኤ በሆነው በምእራብ ሀረርጌ ዞን ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ላይ የአመራሮች እጅ ነበረበት ተባለ፡፡በቦርደዴ ወረዳ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር እና የሰዎች ህይወት ህልፈት ላይ የአመራሮች እጅ እንደነበረበት ተሰምቷል፡፡በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከወረዳው ሊቀመንበር ጀምሮ የተለያዩ አመራሮች፣ የቦርደዴ ወራዳ ወንጀል መከላከል ፖሊሶች ጭምር በድርጊቱ ተሳትፈው ነበር ብለዋል፡፡ በወረዳው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ያደረሱ እንዚህ አካላትን ጨምሮ 7 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተሰምቷል፡፡የሀገር መከላከያ፣ፌደራል ፖሊስ እና የሀገር ሽማግሌዎች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመወያየት ወንጀለኞችን አሳልፈው እንዲሰጡ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ጥቃት አድራሾቹን ህብረተሰቡ አሳልፎ መስጠቱንም አቶ ጀይላን ተናግረዋል፡፡የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ችግሩ የተከሰተበትን አካባቢ የማረጋጋት እና ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረቡን ስራ እያከናወነ ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ሀረርጌ ዞን ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ የታጠቁ ሀይሎች በወረዳዋ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ፈፀመው 10 ሰዎችን መግደላቸው የሚታወስ ነው፡፡ ### Response:
### Text: የምስራቅ ሀረርጌ ፖሊስ መምሪያ️በቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ላይ ለመገኘት የሚመጡ ምዕመናን እና ቱሪስቶችን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡በመምሪያው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዲቪዥን ሀላፊ ኮማደር ስዩም ደገፉ ለኢዜአ እንደገለፁት ነገ የሚከበረውን የንግስ በዓል ለማክበር በብዙ ሽዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ቱሪስቶችና የሀይማኖት አባቶች ወደስፍራው ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በመሆኑም የእንግዶችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የከተማ አስተዳደሩ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግ እንግዶቹን ለማስተናገድ የተለያዩ ዝግጅት አድርጓል፡፡ምዕመናኑ በዓሉን ለማክበር ሲመጡ በተለይ በደብሩ መግቢያና መውጫ በሮችና በሌሎች መጨናነቅ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ንብረቶቻቸውን በጥንቃቄ መያዝ እንደሚገባቸው ኮማንደር ስዩም አሳስበዋል፡፡በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ምዕመናን ማንኛውም አይነት ወንጀል ሲፈጠርና ንብረትም ሆነ ገንዘብ ሲያገኙ ቁልቢ ገብርኤል በጊዜያዊነት በተቀመጠ ፖሊስ ጣቢያ በስልክ ቁጥር 0253390355 ደውለው ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርጉ እንዲሁም ከጨለንቆ እስከ ቀርሳ ባለው መንገድ ማንኛውንም ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ለጊዜው የተከለከለ መሆኑን በማወቅ ህብረተሰቡ ከወዲሁ የሚያስፈልገውን ዝግጅት እንዲያደርግ ኮማንደር ስዩም አሳስበዋል፡፡© ### Response:
### Text: በራስ አምባ ትቤት በኮቪድ19 የተያዙ ተማሪዎች በመገኘታቸው ናሙና እየተወሰደ ነው በራስ አምባ ትምህርት ቤት ከኮቪድ 19 በሽታ የተያዙ ተማሪዎች በመገኘታቸዉ ናሙና ከተማሪዎች እየተወሰደ መሆኑ አሀዱ ራድዮ 943 ዘገበ።በራስ አምባ ትምህርት ቤት በኮቪድ 19 ያለባቸዉ 4 ተማሪዎች በመገኘታቸዉ በየክፍሉ ምርመራ መደረግ መጀመሩን የትምህርት ቤቱ ርእሰ መመህር አቶ ስንታየዉ ገለታ ተናግረዋል፡፡አሁን ናሙና ከተወሰደላቸዉ 22 ተማሪዎች በተጨማሪ በሁለተኛዉ ዙር በነገዉ እለት ማክሰኞ ከ3 ክፍሎች ናሙና እንደሚወሰድ አስታዉቀዋል፡፡አራቱ ተማሪዎች ኮቪድ እንዳለባቸዉ የታወቀዉ ቤተሰቦቻቸዉ ናሙና ሰጥተዉ ነዉ ተብሏል፡፡ተማሪዎቹ ከየክፍሉ አንድ አንድ 4 በመሆናቸዉ ከሁሉም ክፍሎች ናሙና ይወሰዳል ብለዋል፡፡ የመማር ማሰተማር ሂደቱ አሁንም ቀጥሏል ያሉ ሲሆን ለመምህራን ናሙና ለመዉሰድ መታሰቡን በተመከተ ምልክት ከታየ እንደሚወሰድ እና አሁን ላይ ከተማሪዎች ብቻ ለመዉሰድ መታቀዱን አቶ ስንታየዉ ገልፀዋል።በራስ አምባ ትምህርት ቤት መመህር የሆኑ ግለሰብ እንደተናገሩት በትምህርት ቤቱ እስካሁን 6 ተማሪዎች ኮቪድ19 ተገኝቶባቸዋል፡፡ የታወቀዉም በጠና ስለታመሙ ነዉ ብለዋል፡፡ የሚያዙ ተማሪዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል፡፡ በትምህርት ቤቱ አሁን እየተደረገ ያለዉ የምርመራ ቁጥር በቂ አይደለምና ትኩረት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።ምንጭ አሃዱ ሬድዮ 943 ### Response:
### Text: የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ተቋማቱን ለቀው እንዲወጡ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል። ይሁን እንጂ ጦርነትና የፀጥታ ችግር ካለባቸው የትግራይ፣ አማራ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ለመሄድ እንደማይችሉ እና ውጪ ለመቆየት አቅም እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ገልጿል።ፈተና እስከሚጠናቀቅ ተማሪዎቹ የሚቀመጡበት ቦታ እንዲመቻችላቸው ህብረቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን የህብረቱ ፕሬዝዳንት ሚካኤል ያቦነሽ ለቲክቫህ ተናግሯል።ህብረቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ተማሪዎቹ ብሔራዊ አደጋና ስጋት ኮሚሽን ማዕከላት እንዲቆዩ ጥያቄ ቢያቀርቡም ኮሚሽኑ እንደማይችል ገልጿል። በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲዎች የቴሌቪዥን ማሳያ ክፍሎችና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ተማሪዎቹ የሚቆዩበት መመሪያ እንዲሰጥ ህብረቱ ጠይቋል። ተማሪዎቹ ለፈተና አሰጣጡ ስጋት እንዳይሆኑ ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት ከማደሪያቸው እንዳይወጡና ምግብም ከተፈታኞቹ በኋላ እንዲመገቡ በማድረግ ችግር እንዳይፈጠር ህብረቱ እንደሚሰራ የህብረቱ ፕሬዜዳንት ለቲክቫህ ገልጿል።ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 172015 ዓም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል። ### Response:
### Text: ነሃሴ 122012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 437 የላብራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 44 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 515 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።5 ከማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ1 ከህዳሴ ኤርፖርት 1 ሰው ከአሶሳ በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 698 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 49 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።አጠቃላይ በሐረሪ 604 በቫይረሱ የተያዙ15 ሞት107 ያገገሙ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በደቡብ ክልል በተደረገው 1171 የላብራቶሪ ምርመራ 44 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 31 ከጌዴኦ ሁሉም ከዲላ ከተማ 5 ከጉራጌ 2 ከደሶዶ፣ 1ወሊሶ ከመስቃና 1 እዣ 3 ከጋሞ ከምዕራብ አባያ፣ 1 ከአርባ ምንጭ 3 ከጎፋ 2 ከገዜ ጎፋ ወረዳና 1 ከሳውላ ከተማ 1 ከወላይታ ወሶዶ 1 ከስልጤ ወራቤ ከተማ ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 265 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 20 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከማህበረሰቡ በተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው። አጠቃላይ በድሬዳዋ 731 በቫይረሱ የተያዘ 18 ሞት 598 ያገገሙ በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 5274 የላብራቶሪ ምርመራ 67 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 19 ከባህር ዳር 6 ከምዕጎንደር ዞን 5 ከጎንደር ከተማ 5 ሰሸዋ ዞን ይገኙበታል። ### Response:
### Text: አገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናዎችን ከሰኔ 32011 ዓም ጀምሮ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወሮ ጽዮን ተክሉበሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንዳሉት የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናዎቹን ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል።ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ተማሪዎች ተረጋግተው በመፈተን የሚጠበቅባቸውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትና መላው ህብረተሰብ የተማሪዎችን ስነልቦና የሚያጠናክሩ ሥራዎችን በመከወን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርኣያ ገእግዚአብሄር የዘንድሮ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከሰኔ 032011ዓም እስከ ሰኔ 052011 ዓም እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሰኔ 6፣7፣10 እና 112011 ዓም እንደሚሰጥ ገልጸው ለ10ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተመዘገቡ ተማሪዎች 1277533 እና ለ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተመዘገቡ ተማሪዎች 322317 ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡በዚህ ዓመት ከተማሪዎች ምዝገባ ጀምሮ የፈተና ህትመትና ሌሎችን ጨምሮ እስከ ሥርጭት ያሉ ሥራዎች ከዚህ በፊት ከነበሩት ዓመታት በተሻለ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የተከናወኑ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ አክለው መግለጻቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ዘገባ ያመለክታል። ### Response:
### Text: የባህርዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ መመሪያን ተከትለው ያልሰሩ የግል ትምህርት ቤቶችን አስጠነቀቀ።መምሪያው በከተማው ላሉ ትምህርት ቤቶች በፃፈው ደብዳቤ ከዚህ ቀደም በትምህርት ቤት ክፍያ ጉዳይ ተከታታይ ውይይት መደረጉን አስታውሷል።መስከረም 72014 ዓም ትምህርት ቤቶቹ የተማሪ ወላጆችን ሰብስበው በክፍያ ዙሪያ ከወላጅ ጋር ተግባብተው በመመሪያው መሰረት ወላጅ ያመነበትን ክፍያ እንዲያስከፍሉና ወላጆችን ያወያዩበት ቃለጉባኤ የተሳታፊዎችን ፊርማ እና በቪድዮ የተደገፈ ማስረጃ ለትምህርት መምሪያው መረጃ አደራጅተው እንዲያሳውቁ በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት ተቋማቱ ዕድሉን እንዳልተጠቀሙበት ትምህርት መምሪያው በደብዳቤው ላይ ገልጿል።አሁን ላይ ወላጆች የትቤት ክፍያ እንደተጨመረባቸው ይህ የተጨመረው ጭማሪም ወላጆች ያላመኑበት መሆን ለመምሪያው ቅሬታ እያቀረቡ እንደሚኙ ገልጿል።ትምህርት መምሪያው ትምህርት ቤቶች የጨመሩት ክፍያ ከተማሪ ወላጆች ስምምነት ውጭና ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ከመስከረም 2014 ጀምሮ የተከፈለ ክፍያ ለቀጣይ ወራት ታሳቢ ተደርጎ በ2013 ዓም የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ሲያስከፍሉ የነበረውን ክፍያ እንዲያስከፍሉ አሳስቧል።ትቤቶቹ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ የማያደርጉ ከሆነ በቀጣይ የማስተማር ፍቃዳቸው እንደሚነሳ ከ2ኛ ሴሚኒስተር በኃላ ምንም አይነት ተማሪ በተቋማቸው የማይማርና ተቋማቱም እንደሚዘጋ አስጠንቅቋል። ### Response:
### Text: በደቡብ ክልል ከሚገኙት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ውስጥ የ ክላስተር አደረጃጀትን ባለማጽድቅ ብቸኛ የሆነው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ሐሙስ ነሐሴ 52014 እንደሚያካሂድ ተገልጿል።የአስቸኳይ ጉባኤውን መጠራት የዞኑ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አርሽያ አህመድ እንዳረጋገጡ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ አስነብቧል።ድረገፁ አነጋግሬያቸዋለሁ ያላቸው ሶስት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አባላት በነገው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ጥሪ እንደተላለፈላቸው ገልጸዋል። የጉራጌ ዞን ምክር ቤት 97 አባላት ያሉት ሲሆን ከእነርሱ ውስጥ ስድስቱ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ተመራጮች ናቸው። ቀሪዎቹ የምክር ቤት አባላት ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ወክለው የተወዳደሩ እና ምክር ቤቱን የተቀላቀሉ ናቸው።0ከዚህ በፊት በነበረው ልማድ ጉባኤው ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የጉባኤውን አጀንዳዎች በያዘ ደብዳቤ ጥሪ ይደረግላቸው እንደነበር የሚያስታውሱት የም ቤት አባላት የአሁኑ ስብሰባ አጀንዳ ግን እንዳልተገለጸላቸው ተናግረዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የዞኑ ምክር ቤት አባል የነገው አስቸኳይ ጉባኤ ዋና አጀንዳ የአደረጃጀት ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።የነገውን ጉባኤ ዋነኛ አጀንዳ ምን እንደሆነ ጥያቄ የቀረበላቸው የዞኑ ምቤት አፈ ጉባኤ አጀንዳ ለምክር ቤት አባላት ብቻ ነው የሚገለጸው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ### Response:
### Text: በሀዋሳ ከተማና አካባቢው ትናንት ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክለሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወልደሚካኤል ለፋና ብሮድካስት እንደተናገሩት በግጭቱ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ዛሬ ላይ ከተማዋ አንጻራዊ ሰላም ይታይባታል ብለዋል።ግጭቱ ትናንት በታቦር ክፍለ ከተማ መንገድ በመዝጋት መጀመሩን የገለጹት ኮሚሽነሩ በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። እንዲሁም በግጭቱ የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ መሆኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። የፀጥታ ችግሩ ከተማዋን መነሻ አድርጎ ወደ ሲዳማ ዞን ወረዳዎች መዛመቱን ያነሱት ኮሚሽነሩ መንገዶች በመዘጋታቸው የጸጥታው ሀይል በፍጥነት መድረስ አለመቻሉን አስታውሰዋል። በዛሬው እለት አካባቢዎቹን የጸጥታ አካላት እያረጋጉ መሆኑንም ጠቅሰዋል።ማንኛውም ጥያቄ ያለው አካል የህግ የበላይነትን ባከበረ መልኩ ማቅረብ እንደሚኖርበት ጠቅሰው በክልሉ ሌሎች አካባቢዎች ሰላም መሆኑን አስረድተዋል። ነገር ግን ከዚህ ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የዜጎችን ህልውና የሚፈታተኑ በመሆኑ ሊቆም ይገባል ነው ያሉት፡፡ ህብረተሰቡም የሀዋሳ ከተማና አካባቢውን ሰላም እና መረጋጋት ለማስጠበቅ ከጸጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት እንዲሰራና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠይቀዋል።ምንጭ ፋና ብሮድካስቲንግ ### Response:
### Text: ለሊት በዚያው በተኙበት ነው የገደሏቸው በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ቦርደዴ ወረዳ ጉምቢ በተባለ ቦታ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የቦርደዴ ጤና ጣቢያ ባልደረባ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ኮምዩንኬሽን ቢሮ ጥቃቱ መፈጸሙን በፌስቡክ ገጹ ባወጣው አጭር መረጃ አረጋግጧል። የአፋር እና የኦሮሚያ ክልሎች በሚዋሰኑበት አካባቢ በምትገኘው ጉምቢ በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱ ሰዎች መካከል አንዲት እንስት እንደሚገኙበት እና ሌሎች ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን የቦርደዴ ጤና ጣቢያ ባልደረባ የሆኑስት ሲስተር ሐይማኖት ተስፋዬ አስረድተዋል። ሲስተር ሐይማኖት «ለሊት በዚያው በተኙበት ነው የገደሏቸው። ሰባት ሰው ሞቷል። አሁን ሰባት እሬሳ አለ። እየተፈለጉም ያሉ አሉ» ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል የኮምዩንኬሽን ቢሮ ከአንድ ሰዓት ገደማ በፊት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ በቦርደዴ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።ሲስተር ሐይማኖት ከሞቱት ሰባት ሰዎች ባሻገር ሌሎች ሁለት ሴቶች መቁሰላቸውን ተናግረዋል። «ሁለት የቆሰሉ ሴቶች ነበሩ። ወደ አሰቦት ሆስፒታል ልከናቸዋል» ብለዋል።ሲስተር ሐይማኖት እንዳሉት ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የገቡበት ያልታወቀ ሰዎች በመኖራቸው ፍለጋ እየተካሔደ ይገኛል። ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ከአዲስ አበባ ወደ ሐረር እና ድሬዳዋ የሚወስደው መንገድ ለረዥም ሰዓታት ተዘግቷል።ምንጭ የጀርመን ራድዮ ### Response:
### Text: የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢር ታከለ ኡማ ለከተማዋ ምክር ቤት የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ሹመት እንዲፀድቅላቸው አቀረቡ።ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባቀረቡት ሹመት መሰረት፡1 ኢንጅነር እንዳወቅ አብጤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ2 ኢንጅነር ሰናይት ዳምጠው የቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ3 ወይዘሮ ነጂባ አክመል የፋይናስ ቢሮ ሃላፊ4 አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ5 አቶ አብዱልቃድር መሀመድ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ 6 ወይዘሮ ኤፍራህ አሊ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ7 አቶ ሀይሉ ሉሌ የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ8 አቶ ዘላለም ሙለታ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ9 ኢንጅነር ደመላሽ ከበደ የኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ10 አቶ ስጦታው ታከለ የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ11 አቶ ነጋሽ ባጫ የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ ሃላፊ12 አቶ ይመር ከበደ የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንትርፕራይዝ ቢሮ ሃላፊ13 አቶ መኮንን ተፈራ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ14 አቶ አብዱልፈታህ ዩሱፍ የንግድ ቢሮ ሃላፊ15 አቶ አዱኛ ደበላ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ 16 አቶ አብርሃም ታደሰ የወጣቶች በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ17 አቶ ዋቁማ አበበ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር18 አቶ ታምራት ዲላ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር19 አቶ ታዚር ገብረእግዚአብሄር የኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ሆነው በምክትል ከንቲባው በእጩነት ቀርበዋል፡፡ኤፍቢሲ ### Response:
### Text: በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጫካ ያሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በሚፈቱበት አካሄድ ላይ ከተወካዮቻቸው ጋር ውይይት ሊደረግ መሆኑ ታውቋል።የክልሉ መንግስት የተሃድሶ ስልጠና ሃሳቡን ያቀረበው ከጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጉህዴን ታጣቂዎች ጋር ትላንት ቅዳሜ መጋቢት 10 ቀን 2014 በይፋ ዕርቅ መፈጸሙን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።በጉሙዝ ባህል መሰረት የተከናወነው የዕርቅ ስነ ስርዓት የተካሄደው በካማሺ ዞን ካማሺ ከተማ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽና በካማሺ ወንዝ ዳርቻ ነው። በዕርቅ ስነ ስርዓቱ ላይ የምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣ የክልሉ ምቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ እና የጉህዴን ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉደታ ተገኝተው ነበር።በካማሺ ከተማ የስብሰባ አዳራሽ በተከናወነው ዕርቅ ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ነበር።በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት እና በጉህዴን አመራሮች መካከል ዕርቅ መውረድ ተከትሎ በጫካ የነበሩ አማጽያን ከእነ ትጥቃቸው ወደ ካማሺ ከተማ ሲገቡ መመልከታቸውን አንድ የከተማውን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ ድረገፁ አስነብቧል።የታጣቂዎቹን ወደ ከተማ መግባት የካማሺ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ቦካ አቦሴም አረጋግጠዋል። ታጣቂዎቹ ለጊዜው የካማሺ ዞን ባዘጋጀላቸው ማረፊያ እንደሚቆዩ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊው ገልፀው በየትኛው የከተማው አካባቢ እንደሚቆዩ ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።ያንብቡ 0320 ### Response:
### Text: ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበዋል️በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ በፌዴራሉ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት 34 ሰዎች ለነገ ተቀጠሩ።በጎሃ አጽብሃ መዝገብ የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ናቸው ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ለነገ የተቀጠረው።ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ አቅርቦት የነበረውን አዳምጦ ከቀረቡት 36 ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ በዋስ እንዲወጡ ፈቅዷል።16ቱ ተጠርጣሪዎች መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው የፈቀደው ፍርድ ቤቱ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ለመፍቀድ ለነገ ለነገ ቀጥሯል።ተጠርጣሪዎቹ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የማረሚያ ቤትና የፖሊስ አባልና ሃላፊ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረዋል።ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው ተጠርጣሪዎቹ በሽብር የተፈረጁ ግለሰቦችን በማፈን፣ ስውር እስር ቤት አስገብቶ ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት እንዲፈጸምባቸው ማድረጋቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።በጳጉሜ 2006 ዓም የኢትዮጵያና ናይጄሪያ እግር ኳስ ቡድን ጨዋታ ባደረጉበት ዕለት ቦንብ አፈንድተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በማሰቃየትና የአንድ ሰው ህይወት እንዲያልፍ ማድረግና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል።ምንጭ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ### Response:
### Text: አሳዛኝ ዜና️ከጎንደር ዙሪያ ወረዳ ወደ ምዕራብ በለሳ ሰዎችን አሳፍሮ ይጓጓዝ የነበረ አይሱዚ የደረቅ ጭነት ማመላላሻ ተሸከርካሪ ተገልብጦ የ20 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ የመንገድ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ኮማንደር ውህብነህ አስናቀ እንደተናገሩት ትናንት ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ አደጋውን ያደረሰው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 01254 አዲስ አበባ የሆነ የጭነት ተሸከርካሪ ነው፡፡የጭነት ተሸከርካሪው ከያዘው 25 ኩንታል ጭነት በላይ 40 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ምዕራብ በለሳ ልዩ ስሙ ወራህላ በተባለው ቦታ ሲደርስ መንገድ ስቶ በመገልበጡ አደጋው ደርሷል፡፡በአደጋው ህይወታቸው ካለፈ 20 ሰዎች በተጨማሪም በ20 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ጎንደር ዩንቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ተሳፋሪዎቹ የትንሳኤን በዓል ለማክበር ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ይጓዙ የነበሩ ናቸው ብለዋል፡፡የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ በማጠራት ላይ ሲሆን ÷ ተሰውሮ የነበረው አሽከርካሪው በህዝቡ ጥቆማ ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተገለጸው፡፡ህብረተሰቡ ከዚህ መሰል አሰቃቂ አደጋ እራሱን በመጠበቅ በኩል የጭነት ተሸከርካሪን ከመጠቀም በመቆጠብ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ እንዲጓጓዝ ኮማንደር ውብነህ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ምንጭ፡ ኢ ዜ አ ### Response:
### Text: ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 316 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 31 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።ከሰላሳ አንዱ 31 መካከል 21 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 8 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆኑ 2 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው። በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 241 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው። 2 ሰዎች ከቡራዩ የ 38 እና 30 ዓመት ወንዶች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው ከማህበረሰቡ የተገኙ። 1 ሰው ከአዳማ የ38 ዓመት ወንድ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው ከማህበረሰቡ የተገኘ። በአፋር ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 49 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 66 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። በክልሉ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 33 ደርሰዋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተደር ከተካሄደው 96 የላብራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጧል። በቫይረሱ የተያዙት ሁለቱም ወንዶች ሲሆኑ ግለሰቦቹ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው። በድሬዳዋ አጠቀላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 15 ደርሰዋል 8 ሰዎች አገግመዋል። ### Response:
### Text: መንግስት በአፍሪካ ህብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ ነው አቶ ደመቀ መኮንን የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ይደግፋል ሪታ ላራንጂንሃዛሬ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከሆኑት ሪታ ላራንጂንሃ ውይይት አካሂደው ነበር።በዚህም ወቅት አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። ምትክል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰሜን ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እና የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ስላደረገው የሰላም ግንባታ ጥረት ገለጻ እንዳደረጉ ተገልጿል።አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።ሪታ ላርንጃንሃ በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነቱን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።ዳይሬክተሯ የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ኅብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት እንደሚደግፍ ገልፀው የሰላም ሂደቱን መደገፍ በሚፈለግ ጊዜ ለመርዳት ህብረቱ ፍላጎት እንዳለው አፅንኦት ሰጥተዋል።መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው። ### Response:
### Text: የግብፁ መሪ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብፅን እንዲጎበኙ ግብዣ አደረጉ።ከቀናት በፊት ለሶማሊያው ፕሬዜዳንት ተመሳሳይ መልዕክት መላካቸው ይታወሳል።የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው ነበር። በዚህም ወቅት ከፕሬዜዳንት አልሲሲ የተላከ መልዕክት አድርሰዋል ተብሏል።መልዕክቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ማጠናከር እና የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ አህጉራዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።ሀሙስ ምሽት በአስመራ ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ጋር የተገናኙት የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተለያዩ መልዕክቱን ከማድረስ ባለፈ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋል።ውይይቱ በኤርትራ እና ግብፅ መካከል በወቅታዊ ቀጠናዊና እና ዓለምአቀፋዊ ተግዳሮቶች ላይ መክሯል የተባለ ሲሆን በውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር አጽንኦት መሰጠቱ ተነግሯል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሀገራቸው ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብፅን እንዲጎበኙ የሚል ግብዣ አድርሰዋል።ከቀናት በፊት የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ በነበረበት ወቅት የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ተመሳሳይ ግብፅን ይጎብኙ የሚል መልዕክት ማድረሳቸው አይዘነጋም። ### Response:
### Text: የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ምትክ አቶ ኡመር ሁሴንን የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል አድርጎ መረጠ።የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ ለሶስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባውን በዛሬው እለት አጠናቋል።የኦዲፒ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ ስብሰባውንብ በማስመልከት በሰጡት መግለጫ የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችንና ምትክ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመምረጥ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።በዚህም መሰረት የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ በስራ ምክንያት ከፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት በለቀቁት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ምትክ አቶ ኡመር ሁሴንን የስራ አስፈፃሚ አባል አድርጎ መምረጡን አስታውቀዋል።በዚሁ መሰረት የኦዲፒ ስራ አስፈፃሚ አባላትም1 ዶክተር አብይ አህመድ2 አቶ ለማ መገርሳ3 አቶ ኡመር ሁሴን4 ዶክተር አለሙ ስሜ5 አቶ ሽመልስ አብዲሳ6 አቶ አዲሱ አረጋ7 ወይዘሮ አዳነች አቤቤ8 አቶ ፍቃዱ ተሰማ9 አቶ ፀብርሃኑ ፀጋዬ መሆናቸውን የፅህፈት ቤት ሀላፊው በመግለጫቸው አስታውቀዋል።የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ጸሀፊ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።በዚሁ መሰረት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መቀመጫውን ኬንያ ናይሮቢ ያደረገውን የተመድ ዋና ጽህፈት ቤት የመምራት እና የማስተባበር ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ### Response:
### Text: በጎንደር ከተማ የደረሰ እሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ በጎንደር ከተማ አዘዞ ቀበሌ 19 ትናንት ምሽት በደረሰ የእሳት ቃጠሎ በ3 የእህል ወፍጮ ቤቶችና በአራት ጊዚያዊ የእህል መጋዘኖች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተመልክቷል።የከተማው ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር አበበ አለባቸው እንዳሉት ቃጠሎው የደረሰው 0በከተማው የአውቶብስ መናኸሪያ አጠገብ በሚገኙ ጊዚያዊ የገበያ ስፍራ አጠገብ ነው፡፡ምሽት አራት ሰዓት ተኩል አካባቢ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ሶስት የእህል ወፍጮ ቤቶችና አራት ጊዚያዊ የእህል መጋዘኖች ለጊዜው ግምታቸው ካልታወቁ ንብረቶች ጋር ወድመዋል፡፡ ለአንድ ሰዓት የዘለቀውን የእሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር የአከባቢው ወጣቶችን ሌላም የህብረተሰብ ክፍል ከከተማው እሳት አደጋ መከላከያ ጋር በመሆን 0ርብብር ማድረጋቸውን ምክትል ኮማንደሩ ገልጸዋል፡፡በዚህም ቃጠሎውን መቆጣጠር መቻሉን ጠቁመው እሳቱን ለማጥፋት በተደረገው ርብርብ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሁለት ሰዎች በጭሽ የመታፈን ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ መደረጉን አመልክተዋል። ምክትል ኮማንደሩ እንደተናገሩት ቃጠሎው በሰው ሕይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም፡፡ ፖሊስ ቃጠሎው ያደረሰውን የንብረት ውድመትና የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የምርመራ ስራ መጀመሩንም አብራርተዋል፡፡ ### Response:
### Text: ሀገርን አደጋ ላይ በሚጥሉ ጉዳዮች ላይ በሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የተራድኦ ድርጅቶች ላይ እርምጃዎች ይወሰዳል የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲየኢትዮጵያን ሉዕላዊነት፣ አንድነትና ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥሉ ጉዳዮች እንዲሁም ከተቋቋሙበት አላማ ውጪ በሚንቀሰቀሱ አንዳንድ የተራድኦ ድርጅቶች ላይ በቅርቡ የማስተካከያ እርምጃዎችን እንደሚወስድ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አስታወቀ።የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደገለፁት፣ የሀገሪቱን ህግና ስርዓት ሳያከብሩ ከተቋቋሙበት አላማ ውጪ በሚንቀሰቀሱ አንዳንድ የተራድኦ ድርጅቶች ላይ በቅርቡ እንደጥፋታቸው መጠን ከማስጠንቃቂያ ጀምሮ እስከማገድና ማፍረስ የሚደርሱ የተለያዩ የማስተካከያ እርምጃዎች ይወሰዳሉ።የኢትዮጵን ሉዕላዊነት፣ አንድነትና ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥሉ ጉዳዮች ላይ በሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ ምህረት የለንም። በእንዲህ አይነት ጉዳይ ላይ የምንደረደርበት ሁኔታ በጭራሽ አይኖርም ብለዋል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ።የተወሰኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከሀገር ጥቅም በተፀራሪ በሆነ ጉዳይ ላይ እንደሚንቀሳቀሱ መረጃዎች አሉን ያሉት አቶ ፋሲካው ድርጊቱ የሀገርን ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ በቀላሉ የሚታይ አይደለም የማጣራቱን ስራ እንደጨረስን አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ብለዋል። ### Response:
### Text: ሁላችሁም የውጭ አገራት ጣልቃ እንዳትገቡ ኮሎኔል ሜጀር አማዱበአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት መፈንቅለ መንግሥት ሲደረግ በተደጋጋሚ ተሰምቷል።አሁን ደግሞ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኒጀር ወታደሮች መፈንቅለ መንግሥት አውጀዋል።ወታደሮሹ ሕገመንግሥቱን መበተናቸውን ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ለጊዜው ሥራ ማቆማቸውን እና የሃገሪቱ ድንበሮች መዘጋታቸውን ይፋ አድርገዋል።ከረቡዕ ጀምሮ የኒጀር ፕሬዝደንት ሞሐመድ ባዙም በወታደሮች ቁጥጥር ሥር እንዳሉ ተነግሯል።ተመድ እንዲሁም አሜሪካ ለፕሬዝደንቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል። ረቡዕ ዕለት ዘጠኝ የወታደር መለዮ በለበሱ ሰዎች ተከበው በቴሌቪዥን መስኮት መግለጫ የሰጡት ኮሎኔል ሜጀር አማዱ አብድራማኔ እኛ የመከላከያና የፀጥታ ኃይሎች የምታውቁት መንግሥት ከሥልጣን አውርደናል ብለዋል።የሃገሪቱ ሁሉም ተቋማት ለጊዜ ሥራ እንደሚያቆሙ የገለጹት ኮሎኔሉ ሚኒስትሮች የቀን ተቀን ሥራውን እንደሚመሩ ገልጠዋል። ሁሉም የውጭ አገራት ጣልቃ እንዳይገቡ እንጠይቃለን። ሁኔታዎች እስኪረጋጉ በምድርም ሆነ በአየር ድንበራችንን ዘግተናል ብለዋል።አክለው ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽት 4 ሰዓት እስከ ንጋት 11 የሚቆይ ሰዓት እላፊ መታወጁንም ማሳወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።የኒጀር ጎረቤት የሆኑት ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ በቅርብ ዓመታት በተመሳሳይ በመፈንቅለ መንግሥት ምክንያት ታምሰው እንደነበር አይዘነጋም። ቢቢሲ ### Response:
### Text: ህወሃት️5ኛ ቀኑን የያዘው የህውሃት ድርጅታዊ ጉባዔ በዛሬ ውሎው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።ድርጅታዊ ጉባዔው በዛሬው ውሎው የማእከላዊ ኮሜቴ አባላት ምርጫ ያካሄደ ሲሆን የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ቁጥርም ከ45 ወደ 55 ከፍ እንዲል ወስኗል።በዚህም መሰረት 65 እጩዎች ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የ55 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫተካሂዷል።ለማእከላዊ ኮሚቴ ከተመረጡት 55 ውስጥ 45ቱ ለኢህአዴግ ምክር ቤት አባልነት የሚቀርቡ ይሆናል።ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት የተመረጡት ዝርዝርም በነገው እለት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል። ድርጅታዊ ጉባዔው በዛሬ ውሎው 12 ነባር አመራሮችንም በክብር አሰናብቷል ።በዚህም መሰረት1 አቶ አባይ ወልዱ2 ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ3 አቶ ገብረመስቀል ታረቀኝ4 አቶ ሚካኤል አብረሃ5 አቶ ጎበዛይ ወልደአረጋይ6 አቶ ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ7 አቶ ነጋ በረኸ8 አቶ ተወልደብርሃን ተስፋዓለም9 አቶ ማሞ ገብረእግዚአብሄር10 አቶ ጎይቶም ይብራህ11 አቶ ሀይሌ አሰፈሃ12 አቶ ኪሮስ ቢተው ከድርጅቱ በክብር ተሰናብተዋል።የህወሃት ድርጅታዊ ጉባዔ በነገ ውሎው የድርጅቱን ሊቀ መንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ምርጫን እንዲሁም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን እንደሚያካሄድ ይጠበቃል።በተጨማሪም የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ምርጫ በማካሄድ በነገው እለት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።ምንጭ ፋና ብሮድካስቲንግ ### Response:
### Text: የፈረሰውን በቅርስነት የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ጉዳይ በህግ አግባብ ለመፍታት ጥረት ይደረጋልየአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝምበአዲስ አበባ ትላንት የፈረሰው የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ካሳ መኖሪያ ቤት ጉዳይ በህግ አግባብ ለመፍታት እንሚንቀሳቀስ የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ የሚገኘውና በቅርስነት የተመዘገበው መኖሪያ ቤቱ በትላንትናው ዕለት መፍረሱ ይታወቃል፡፡የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጉዳዩን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ወደ ስፍራው በመሄድ እንደረጋገጠው ከሆነ ከ90 ዓመታት በላይ ያስቆጠረዉ መኖሪያ ቤቱ የፈረሰው በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አማካኝነት ነው፡፡በአዲስ አበበ ከተማ በቅርስነት ከተያዙ ታሪካዊ ግንባታዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ቤት ለምን እንዳፈረሰ የተጠየቀው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በበኩሉ ቤቱ በቅርስነት ስለመመዝገቡ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌለው በተለይ ለኢቲቪ ገልጿል፡፡ኢቲቪ የፈረሰው ታሪካዊ መኖሪያ ቤት በከተማዋ በቅርስነት ከተመዘገቡ ከ400 በላይ ቅርሶች መካከል አንዱ መሆኑን ከአዲስ አበበ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በዛሬው ዕለት ማረጋገጥ ችሏል፡፡በቅርስነት ተመዝግቧል የተባለዉን መኖሪያ ቤት ጉዳይ ወደ ፊት በህግ አግባብ ለመፍታት እንሚንቀሳቀስ ነው የአዲስ አበበ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የገለፀው፡፡ ### Response:
### Text: 19 ህዝብ አሸብሮ የዩትዩብ ገንዘብ መሰብሰብከዩትዩብ ገንዘብ ለማግኘትና እውቅና ለማትረፍ ሲባል ብቻ ያልተፈጠሩ ነገሮችን እንደተፈጥሩ አስመስሎ፣ እንዲሁም ተመልካች ለማግኘት ሲባል የተጋነኑ ርእሶችን በመጠቀም ህዝቡን በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሸብሩ አካላት አንድ ሊባሉ ይገባል። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የጤና ሚኒስቴር በየወቅቱ በቂ መረጃ በዋና ዋና መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ለህዝብ እያደረሱ ነው። የተጠርጣሪዎችን ናሙና የመረመሩ ይመስል እንዲሁም የጠለቀ የህክምና እውቀት ያላቸው ይመስል የተሰሳተ መረጃ የሚያሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ከደርጊታቸው ቢቆጠቡ መልካም ነው።ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ምርመራ አድርገው ለህዝብ ማሳወቅ ያለባቸው አካላት እያሉ ከመሬት እየተነሱ ህዝቡን ማሸበር ተገቢ አይደለም። ኮሮና ቫይረስ ሀገሪቱ ውስጥ ቢገባ እንኳን መናገር ያለባቸው፣ መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ማሳወቅ የሚገባቸው የጤና ባለሞያዎች እያሉ ጭምጭምታዎችን ብቻ እየሰሙ ማራገቡም ተገቢ አይደለም።የቲክቫህ ቤተሰቦች በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለይም በፌስቡክ እና ዩትዩብ ላይ የሚዘዋወሩትን ያልተረጋገጡ መረጃዎች አይተው የታዘቡትን እያካፈሉ ይገኛሉ። በማህበራዊ ሚዲያ ህዝብን የሚያሸብሩ ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች መበራከታቸው እንዳሳዘናቸው በላኩት የፅሁፍ መልዕክቶች ገልፀዋል። ሀሳብ መቀበያ ### Response:
### Text: የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 100 ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ። ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተከናወነ ስነ ስርዓት የተመረቁት 100 ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ 92 ፖስት ስታፍ እና ስምንት የሁለተኛ ድግሪያቸውን የተከታተሉ ናቸው።ከእነዚህ ውስጥም 21 ተመራቂዎች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ተገልጿል። እነዚህ ተመራቂዎችም ከጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የተውጣጡ መሆናቸው ነው የተመለከተው።የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድም ለተመራቂዎች ዲፕሎማ ከሰጡ በኋላ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። ተመራቂዎች በስነ ምግባር፣ በወታደራዊ ጥበብ፣ በሙያዊ ብቃት እና በላቀ ዝግጅት የሰራዊት አባላትን ለመምራት እና ለድል ለማብቃት የሚያስችላቸውን እውቀት እና ከህሎት ለማግኘት ለአንድ ዓመት ትምህርታቸውን መከታተላቸውን አንስተዋል።በመሆኑም በትምህርት የገበዩትን እውቀት ከዚህ በፊት ካገኙት ልምድ፣ በንባብ ከሚያገኙት እና በተፈጥሮ ከያዙት እውቀት ጋር በማዋሃድ በትጋት ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ነው ያሳሰቡት።ወታደራዊ ተቋማት በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ መሪዎች፣ በስነ ምግባር አርኣያዎች፣ ሀገርን እና ወገንን በመጠበቅ አኩሪዎች፣ ህግና ስርዓትን በማክበር እና በማስከበር ተምሳሌት እንዲሆኑም ያስፈልጋል ብለዋል። ### Response:
### Text: ትላንት ለሊት 6 ሰዓት ገደማ በሚዛን ማረሚያ ተቋማ መዝናኛ ክበብ የተነሳው እሳት አደጋ የከፋ ጉዳት ሳያደረስ መቆጣጠር ተችሏል በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን ማረሚያ ተቋም መዝናኛ ክበብ ላይ ተከስቶ የነበረው ድንገተኛ እሳት አደጋ በፀጥታ ሃይል እና በሚዛን አካባቢ ማኅበረሠብ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በማረሚያ ተቋሙ መዝናኛ ክበብ ላይ ሲሆን ከታራሚዎች መኖሪያ ጋር ግንኙነት እንደሌለውም ተገልጿል።ኮማንደር ዳዊት ጢሞቲዎስ የቤንች ሸኮ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ በስልክ የካቲት 15 ቀን 2013 ዓም ከለሊቱ 6 ሰዓት ገደማ በሚዛን ማረሚያ ተቋም በመዝናኛ ክበብ ላይ የተከሠተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በፀጥታ ኃይሉና በሚዛን አካባቢ ነዋሪዎች ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።የተከሠተው እሳት አደጋ ከታራሚዎች መኖሪያ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ያልነበረውና ብዙ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋል መቻሉን የገለፁት ኮማንደር ዳዊት የሚዛን አካባቢ ማኅበረሠብ የተከሠተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር የፀጥታ አካሉ ጎን በመቆም ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።የተፈጠረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በፀጥታ ኃይሉ እና በህዝቡ ትብብር በቁጥጥር ስር የዋለ በመሆኑ ማኅበረሠቡ ከስጋት ነፃ ሆኖ እንደወትሮው ሁሉ የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ ኃላፊው ማሳሰባቸውን ከቤንች ሸኮ ዞን ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ### Response:
### Text: የጆ ባይደን እና የአል ሲ ሲ የስልክ ውይይት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ትናንት ሰኞ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ዙሪያ መወያየታቸውን ከሁለቱም ወገን የወጣ መግለጫ አመልክቷል።ሁለቱ መሪዎቹ በውይይታቸው ግብጽ ከ ኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት ውስጥ ስለገባችበት ስለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አንስተው መወያየታቸውን ከፕሬዝዳንት ባይደን ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አመልክቷል።ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና አልሲሲ ከሕዳሴው ግድብ ጉዳይ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት ጋዛ ውስጥ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለማስቆም በግብጽ አሸማጋይነት ስለተደረሰው ተኩስ አቁምም ተወያይተዋል ተብሏል።ከዋይት ሐውስ የወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በስልክ በተደረገው ውይይት ላይ ፕሬዝዳንት ባይደን የአባይን ውሃ በተመለከተ ግብጽ ያላትን ስጋት እንደሚረዱ ገልጸዋል ብሏል።በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ባይደን በጉዳዩ ዙሪያ የግብጽን፣ የሱዳንን እና የኢትዮጵያን ሕጋዊ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እንዲገኝ የአሜሪካ ፍላጎት መሆኑን ገልልፀዋል ተብሏል።በሁለቱ መሪዎች መካከል ስለተደረገው ውይይት የግብጽ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ባይደን እና አልሲሲ የሁሉንም ወገኖች የውሃ እና የልማት መብቶችን የሚያስከብር ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚያስችል የተጠናከረ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለማድረግ ተስማምተዋል ብሏል። ### Response:
### Text: የሩሲያ እና የ ፍጣጫ ወዴት ያመራ ይሆን ተጨባጭ የሆነ ወታደራዊ አጸፌታ ጀምሬያለሁ ሩስያ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ጦራቸውን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋታቸው በአካባቢው ላይ ወታደራዊ ፍጥጫ ከምን ጊዜውም በላይ እንዲያይል አድርጓል።ሩስያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር በማንቀሳቀሷ ተጨባጭ የሆነ ወታደራዊ አጸፌታ ጀምሬያለሁ ብሏል። ይህንንም የተሰኘው በጀርመንኛ ቋንቋ የሚታተመው መጽሄት ዘግቧል። አንድ የ ዲፕሎማት ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ የድርጅቱ ተወርዋሪ አጥቂ ጦር ቁጥር በአካባቢው ጨምሯል። የጦር ጫፍ በሚል የሚታወቀው የ አጥቂ ኃይል ከሰኞ ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ በተጠንቀቅ እንዲቆም ትእዛዝ ተሰጥቶታል። ጦሩ የተጠንቀቅ ትእዛዝ የተላለፈለት በእነዚህ 5 ቀናት ውስጥ ወደ ግጭት ቀጠና ሊሰማራ ይችላል በሚል ነው። ይሄው ጦር በአሁኑ ወቅት በሚቀጥሉት 7 ቀናት ለግዳጅ ዝግጁ ሆኖ እንዲቆይም ተነግሮታል። ምዕራቡ ዓለም ሩስያ ዩክሬንን ልትወር እያሴረች ነው ሲል ይከሳል። ሩስያ በበኩሏ አሜሪካ እና በምስራቅ በኩል የሚያደርጉት መስፋፋት ለመገታቱ ዋስትና ሊሰጠኝ ይገባል ትላለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሩስያ እና አሜሪካ መካከል በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የአካባቢው ደህንነትን በሚመለከት ውይይት ሊኖር እንደሚችል ተጠቁሟል።ውይይቱ በአዲስ ዓመት እኤአ 2022 የመጀመሪያ ወር ከ ጋርም ይደረጋል ተብሏል።ምንጭ ዶቼ ቨለ ### Response:
### Text: በጎንደር ከተማ በሸይኽ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር ወቅት ከተፈጠረ ግጭት በኃላ በተፈፀመ ጥቃት እስካሁን ባለው ከ10 ሰዎች በላይ መሞታቸው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን ፣ መስጂዶችም መጠቃታቸው ፣ ከዚህም አልፎ ንብረት መውደሙ ፣ የግለሰብ ቤቶች መጠቃታቸውን የጎንደር ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠምቤት በበኩሉ በጎንደር ሙስሊሙን የማጥቃት፣ መስጂዶችን የመድፈር እና ንብረቶቹን የማውደም የተደራጀ ጥቃት እናወግዛለን ብሏል።ዛሬ የጎንደር ከተማ ፀጥታ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ትላንት በአራዳ ክከተማ የተፈጠረው ሁኔታ በፍፁም የክርስትና እና እስልምና እምነት ተከታዮችን ሊወክል የማይችል ነው ብሎታል።ምክር ቤቱ ጥፋቱ የተፈፀመው በጥቂት ጽንፈኛና አክራሪ ግለሰቦች የተከበሩትን የሁለቱን ዕምነት ተከታዮች ወደ ለየለት ግጭት ለማስገባት ሆን ተብሎ ለግጭት የማያበቃ ምክንያትን በመምዘዝ ጥፋት እንዲፈጠር የተቀነባበረና የተመራ ሴራ ነው ሲል ገልጾታል።በዚህ እኩይ ተግባር ከሁለቱም የዕምነት ተከታዮች የህይዎትና አካል መጉደል እንዲሁም የንብረት መቃጠልና ዘረፋ አጋጥሟል ሲል አሳውቋል።አሁን አካባቢው ሙሉ በሙሉ ከፀጥታ መዋቅርና ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ትብብር በማድረግ የተረጋጋ ሰላም ለመፍጠር በሁሉም አካባቢ ስምሪትና ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ የፀጥታ ምክር ቤቱ አሳውቋል።ሙሉ መግለጫው በዚህ ተያይዟል 0427 ### Response:
### Text: አላማጣ️በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙበት ውይይት በአላማጣ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡በስብሰባው የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮንገብረሚካኤል እና ሌሎች የክልሉ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ውይይቱ በወቅታዊ ጉዮች ላይና በአካባቢው ባለው የልማት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት እንዳደረገም ተገልጿል።በውይይቶቹ ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ለመስጠት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ረዳዒ ኃለፎምን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የዞኑ የስራ ኋላፊዎች በመድረኩ ተገኝተዋል፡፡ብዙ ከመናገር ብዙ መስራት በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ውይይት ላይ ተሳታፊዎቹ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የመሰረተ ልማት ዝርጋታና መልካም አስተዳደርን ጨምሮ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከግምገማ ባለፈ ወደ ተግባር መች ነው የሚገባው የመሰረተ ልማት ጥያቄ እንጂ የማንነት ጥያቄ የለንም የሚሉ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተዋል፡፡የአገልግሎት አሰጣጥን በሚመለከት ቀልጣፋ አለመሆኑን ተናግረዋል ከዚህ በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ዝርጋታ፣ በወጣቶች ተጠቃሚነት፣ የፍትህ አሰጣጥ ስርዓት እና በመሬት አስተዳደር ዙሪያ ያሉትን ችግሮች በስፋት አንስተዋል፡፡ዛሬ በአላማጣ የተጀመረው ውይይት በዞኑ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይቆያል ተብሏል፡፡ምንጭ ### Response:
### Text: አሳዛኝ ዜና️ሰባ ገደማ ኢትዮጵያውያን በቀይ ባህር የጀልባመገልበጥ አደጋ ሞቱ ቀይ ባሕርን አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ እና የመን በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ 70 ገደማ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የመገልበጥ አደጋ ደርሶባቸው ሞቱ። ከሟቾቹ ውስጥ ስድሳዎቹ ከትግራይ ክልል አፅቢ ወንበርታ ወረዳ የተነሱ ነበሩ ተብሏል።ሰባ ገደማ ወጣቶች ይዛ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ የመገልበጥ አደጋ የደረሰባት ቅዳሜ መጋቢት 28 ለሊት መሆኑን ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል። ከጀልባዋ ተሳፋሪዎች መካከል 60ዎቹ ከትግራይ ክልል አፅቢ ወንበርታ ወረዳ የተጓዙ መሆናቸው ከተሰማ በኋላ በወረዳዋ በከባድ የሐዘን እና ድንጋጤ ድባብ እንደምትገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በተገለበጠችው ጀልባ ላይ የነበሩት ቀሪዎቹ ወጣቶች ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ቢነገርም ትክክለኛ ቁጥራቸውን እና ከየት አካባቢ እንደመጡ በተመለከተ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ አብዛኞቹ የሟች ወጣቶች ቤተሰቦች የሞት መርዶውን በአደጋው ማግስት እሁድ እና ትናንት እንደተረዱ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ከ40 በላይ የሟች ቤተሰቦች መርዶው እንደደረሳቸው ገልጿል። የትግራይ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ትናንት ምሽት ባወጣው የሐዘን መግለጫ የአርባዎቹን ወጣቶች መሞት አረጋግጧል። ### Response:
### Text: ሪፖርት በትግራይ ግጭት ሁሉም አካላት ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈፅመው መገኘታቸውን የጋራ ሪፖርቱ አመላክቷል።ተፈፅመዋል የተባሉ ጥሰቶች ከሕግ ውጪ ግድያና ርሸና፣ ማሰቃየት፣ ወሲባዊና ጾታዊ ጥቃቶች፣ በስደተኞች ላይ የተፈጸሙ ግፎች እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን በኃይል ማፈናቀል ይገኙበታል።በጋራ የምርመራ ሪፖርቱ ከቀረቡት ክስተቶች መካካል በጥቂቱ በማይካድራ ሳምረ በተባለ ቡድን የተፈጸመ ጥቃት ይገኝበታል ምንም እንኳን ቁጥሩን እርግጠኛ ለመሆን ባይቻልም ከ200 በላይ ሰዎች በዚህ ጥቃት ተገድለው በጅምላ መቃብሮች መቀበራቸውን ተመላክቷል።የመከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ልዩ ኃይል ከተማውን በተቆጣጠሩባቸው ቀጣይ ቀናት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ላይ የበቀል ግድያዎች መፈጸማቸውን እና የፋኖ ሚሊሺያዎችም በግድያው መሳተፋቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል።በአክሱም ከተማ የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከ100 በላይ ሲቪሎችን መግደላቸውን በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ግድያዎቹ ሲፈጸሙ ጣልቃ ሳይገቡ መቅረታቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።በቦራ አምደውሃ ፣ በቦራ ጫማላ እና ማኢ ሊሃም ከተሞች ከ70 በላይ ሲቪሎች በመከላከያ ሠራዊት መገደላቸውን የጋራ ሪፖርቱ ገልጿል።እነዚህን እና ሌሎች የግድያ ማስረጃዎችን በመያዝ የሕግ ትንታኔ የሰጠው የምርመራ ቡድኑ በዚህ ጦርነት ውስጥ የጦር ወንጀሎች ተፈጽመው ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል። ### Response:
### Text: ቀናት በፊት በቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስረኞች ማቆያ እንዲገቡ የተደረጉት ረፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ።የሲዳማ ክልል መንግስት ምቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት ረፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ 3 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ማቶ ማሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል ያሏቸውን ረፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ፣ አቶ አበራ አሬራ አቶ ተሰማ ደንጉሼ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ማብራሪያ መሰረት ም ቤቱ ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ በህግ እንዲጠየቁ ውሳኔ አሳልፏል።ረፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከቀናት በፊት ወደ ሀገር ሲገቡ ቦሌ ኤርፖርት ላይ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በሀዋሳ በሚገኝ የእስረኞች ማቆያ ውስጥ እንደሆኑ የክልሉ ፖሊስ ማሳወቁ አይዘነጋም።በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በክልሉ አራት ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች እንዲቋቋሙ በቀረበለት ሞሽን ላይ ተወያይቶ አፅድቋል። የፍቤቶቹ መቀመጫም በአለታወንዶ፣ በበንሳ፣ ይርጋለምና ሀዋሳ ከተሞች ላይ እንዲሆን ወስኗል።ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ የቀረበለትን የተለያየ ሹመት አፅድቋል። አቶ ጎሳዬ ጎዳና የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ወሰንየለህ ሰለሞን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ፣ ወይዘሮ ሰላማዊት መኩሪያ የንግድ ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል። ### Response:
### Text: መስከረም 22013 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 114 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በኮቪድ19 የተያዘ ሰው አልተገኘም። በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 51 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 682 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 80 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1408 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 17 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል ከመኮድ ህክምና ማዕከልበቫይረሱ የተያዙት 6 ከባህር ዳር ከተማ 3 ከአዊ ብሰብ ዞን 2 ከምዕጎጃም ዞን 4 ከጎንደር ከተማ 2 ከሰወሎ ዞን በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 148 የላብራቶሪ 15 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1178 የላብራቶሪ ምርመራ 47 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።በቫይረሱ የተያዙት ከቤንች ሸኮ ዞን 16 8 ከሚዛን አማን፣ 6 ከሸኮ እና 2 ከደቡብ ቤንች ከወላይታ ዞን 12 11 ከቦሎሶ ቦምቤ እና 1 ከሶዶ ከተማ ከጌዴኦ ዞን 8 4 ከኮቾሬ እና 4 ከይርጋጨፌ ከደቡብ ኦሞ ዞን 6 5 ከጂንካ ከተማ እና 1 ከሳላማጎ ከጉራጌ ዞን 3 3ቱም ከቸሀ፣ ከጋሞ ዞን 2 2ቱም ከአርባምንጭ ከተማ ናቸው በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 123 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 6 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ### Response:
### Text: የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። 62 50 እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ 80 ፐርሰንታይል ያገኙ በሚፈልጉበት ተቋም ገብተው መማር ይችላሉ የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና የመቁረጫ ነጥብ አሳውቋል።በዚህም መሠረት አጠቃላይ ከተፈተኑት ጥያቄዎች ውስጥ 62 50 እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል 80 ያገኙ ተፈታኞች ብቻ ለመማር በሚፈልጉበት ተቋም አመልክተው መማር የሚችሉ እንደሆነ ተገልጿል።የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመልካቾች ለማመልከት ሲመጡ ውጤታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት እና የተማሪውን የመግቢያ ስም እና የይለፍ ቃል በመጠቀም ማረጋገጥ ይቻላሉ ተብሏል።በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት በሁሉም የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾች በሙሉ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ተፈትነው ያለፉ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡ ይታወሳል።ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓም በትምህርት ሚኒስትሩ ፕር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደብዳቤውን ትክክለኝነት ከትምህርት ሚኒስቴር አመራር ማረጋገጡን በዚሁ አጋጣሚ ያሳውቃል። ### Response:
### Text: ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ 1 ነጥብ 75 ግራም የጆሮ ጌጥ ወርቅ የዋጠው ዶሮ ለሽያጭ ገበያ የወጣው ዶሮ 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ወርቅ ይውጣል። ነገሩ የተከሰተው ጳጉሜ 03 ቀን 2011 ዓም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ነው፡፡ ባለቤትነቱ የአቶ ደነቀ ሸለመ የሆነው ዶሮ ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ ገዢዎችን በመጠባበቅ ላይ እንዳለ የወይዘሮ ሃጫልቱ በድሩን 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ላይ አነጣጥሮ ከጆሮዋ ላይ በጥሶ ይውጣል።ነገሩ ከተከሰተ በኋላ የዶሮው ባለቤትና የወርቋ ባለቤት ሰጣ ገባ ውስጥ ይገባሉ፡፡ የወርቋ ባለቤት ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው ወዲያው ታርዶ ወርቃቸው እንዲሰጣቸው ቢሹም የዶሮው ባለቤት ደግሞ በጉዳዩ አልተስማሙም።ነገሩ መክረሩን ያዩት ገቢያተኞች ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄድ በማድረግ በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኝ የወሊሶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ያመራሉ፡፡ ጉዳዩ እንግዳ የሆነበት የወሊሶ ከተማ አስተዳዳር ፖሊስ ጣቢያም ጉዳያቸውን በመስማማት እንዲፈቱ ትዕዛዝ ይሰጣቸዋል።የዶሮው ባላቤትም ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው የሚያወጣውን ዋጋ ከፍለው ዶሮውን ይረከቡኝ ሲሉ ይስማማሉ። አቶ ደነቅም የወርቁ ባለቤት 250 ብር እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም ባለ ወርቋ የተጠየቀውን ብር የለኝም በማለታቸው 150 ብር ሰጥተዋቸው ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን ነው የወሊሶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ሃላፊ ኮማንደር ከበደ በዳዳ የተናገሩት። ### Response:
### Text: አልፈልግም ማለት አልፈልግም ነው አቁም ማለት አልፈልግም ነው መሸሽ ማለት አልፈልግም ነው እምቢ ማለት አልፈልግም ነው መግፋትመገፍተር ማለት አልፈልግም ነው ዝግጁ አይደለሁም ማለት አልፈልግም ነው ተወኝ ማለት አልፈልግም ነው ዞር በል ማለት አልፈልግም ነው መጮህ ማለት አልፈልግም ነው እረፍ ማለት አልፈልግም ነው ማልቀስ ማለት አልፈልግም ነውየሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያንቺ ንቅናቄ ለሶስት ቀን በሚቆየው የሴት ልጅ ጥቃትን በመቃወም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡ ዝግጅቱ ትላንት የተጀመረ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ16 ቀን ንቅናቄ አንድ አካል እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸውልናል፡፡ በዚህ ንቅናቄ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ሌሎች ክበባትም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡በሌላ በኩል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው መራሂት ክበብ አትኩሮቱን ሴት ተማሪዎችን በማብቃት ላይ አድርጎ እየሰራ ሲሆን ለሴት ተማሪዎች የፅዳት መጠበቂያ የሚሆን 88 ካርቶን ሞዴስ በመግዛት ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሴቶች ህፃናት ወጣቶች እና ኤችአይቪ ኤድስ ዳይሬክትቶሬት አስረክበዋል። የመጀመሪያውን ድጋፋቸውንም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ በሆነው በአዋዳ ካምፓስ አድርገዋል። በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም እየሰራችሁት ላለው መልካም ስራና ለሌሎች ወጣቶች ትምህርት የሚሰጥ ተግባር ላይ በመሳተፋችሁ ያለንን አክብሮት እና ምስጋና እናቀርባለን በርቱልን ### Response:
### Text: ለስድስት ወራት የተዘጋው በመተማ ጋላባት በኩል ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው መንገድ ነገ ክፍት ይሆናል ተብሏል።ዛሬ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች እና የሁለቱ ሀገራት አጎራባቸው አስተዳደሮች ማለትም የምዕራብ ጎንደርና በሱዳን በኩል ደግሞ የጋላባት አካባቢ አስተዳደር ተወካዮች በመተማ ተወያይተዋል፡፡ይህን በተመለከተ የመተማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብቴ አዲሱ ለአል ዐይን አማርኛ ክፍል በሰጡት ቃል ሐምሌ17 ቀን 2013 ዓም የመተማጋላባት መንገድ በሱዳን በኩል ተዘግቶ ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።የሱዳን መንግስት መንገዱን የዘጋው አንድ ወታደራዊ አመራር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ተገድሎብኛል ብሎ በማሰቡ መሆኑን አቶ ሀብቴ ተናግረዋል፡፡ከንቲባው እንዳሉት መንገዱ አለምአቀፍ መስመር ስለሆነ እንዲከፈት በአካባቢው አስተዳደር እና በሀገር ሽማግሌዎች ለማስከፈት ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡በስብሰባው ላይ መንገዱ ተክፍቶ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንዲቀጥል መግባባት ላይ መደረሱን የገለጹት አቶ ሀብቴ ከዚህ በተጨማሪም ለሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችም ተነስተዋል ብለዋል፡፡በሱዳን ግዛት ውስጥ ሚንቀሳቀሱ የህወሓት ኃይሎች መኖራቸውንና ያሉበትን ቦታ ጭምር በመጥቀስ እና ትክክል እንዳልሆነ ለሱዳን ወታደራዊ አመራር እንደተነገራቸው ከንቲባው ተናግረዋል፡፡ምንጭ አል ዓይን ኒውስ ፎቶ የምዕራብ ጎንደር ዞን ### Response:
### Text: ከወጣት አምባሳደር ፕሮግራም ፀግሽ እንዴት ነክ ባሳልፍነው ሳምንት በደቡብ ክልል ከተሞች በተነሳው ግጭት ብዙ ወጣት ወገኖቻችን አልቀዋል ይህም በጣም ያሳዝናል፡፡ በዚህ ጉዳይ በማህበራዊ ገጾች ላይ በጣም ብዙ ምስሎች እና ቪድዮዎች የተለቀቁ ሲሆን፣ ወጣቱ በስሜታዊነት የተለያዩ የብሔር ስሞችን በመጥቀስ ስድብ እና መሰል ፅሁፎችን በማህበራዊ ገጾች ላይ እየተጠቀመ አይቻለሁኝ፡፡ይህ ተግባር እርስ በርስ አለመተማመንን፣ ቂምና ቁርሾን የሚያመጣ ሲሆን፣ በተቀረው አለም ያለንን ስምም የሚያጎድፍ ነው፡፡ በአንድ ላይ እየኖርን አንዱ በአንዱ ላይ እንዲ አይነት አፀያፊ ተግባር እና ንግግር ማድረጉ ለነገ አብሮነታችን ትልቅ ጠባሳ ይጥላል፡፡ስለዚህ እኛ ወጣቶች በሁለ ስራችን ምክንያታዊ ሆነን እነደዚህ አይነት ግጭቶች ለወደፊቱ እናዳይከሰት ወገኖቻችንን ማስተማር እና አለመግባባትን በውይይት ብቻ መፍታት የሚችል ትውልድ እንዲፈጠር መትጋት አለብን፡፡ ኢትዮጵያ የሁላችንም ሀገር ስትሆን እኛም ልጆችዋ ከዚህ ውጭ ሀገር የለንም፡፡ፀግሽ እጅ ለእጅ ካልተያያዝን ሰላም እድገት ብልፅግና ሚባለው ከየትም አይመጣም ስለዚህ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ያለፈውን ይቅር ብለን መልካምነትን ሰንቀን ወደፊት መጔዝ ይኖርብናል፡፡ ይሄን መልዕክቴ ነው፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ልጆችዋን ይባርክ፡፡ ሳምሶን ነኝ ከኢትዮጵያ ወጣት አምባሳደር ፕሮግራም ### Response:
### Text: የኢቦላ ወረርሽኝ️በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በቅርቡ ያገረሸው ኢቦላ ወረርሽኝ በአገሪቷ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና አሰከፊ ነው ሲል የአገሪቷ ጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታውቀዋል።ከባለፉት አራት ወራት ጀምሮ ቢያንስ 200 ሰዎች በወረርሽኙ ሕይወታቸው ሲያልፍ ወደ 300 የሚሆኑ የተጠረጠሩ ህመምተኞች ተገኝተዋል።ወረርሽኙን ለመግታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረገ ሲሆን እስካሁን 25 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች ክትባት ተሰጥቷል።ይሁን እንጂ የአገሪቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና የጤና ባለሙያዎች ላይ በተለያየ ጊዜ ጥቃት በመድረሱ ለዓመታት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ተፈታትኖታል።የጤና ጥበቃው ሚንስትር ኦሊ ኢሉንጋ በዚህ ሰዓት 319 በበሽታው የተያዙና 198 ሞት መመዝገቡን ገልፀዋል።ቤተሰቦቻቸውን ላጡ፣ ያለ አሳዳጊ ለቀሩ ሕፃናትና ለተበተኑ የቤተሰብ አባላት የተሰማኝን ሀዘን እገልፃለሁ መፅናናትን እመኛለሁ በፀሎትም አስባቸዋለሁ ሲሉ ተናግረዋል።ባለስልጣኑ እንደተናገሩት ግማሽ ያህሉ ተጎጂዎች 800 ሺህ ህዝብ ከሚኖርባት የሰሜናዊ ኪቩ ግዛት ቤኒ ነዋሪዎች ናቸው።አገሪቱ በአውሮፓውያኑ 1976 ካጋጠማት ስሙ በውል ካልታወቀው ወረርሽኝ በኋላ የአሁኑ በጣም አሰቃቂውና አስፈሪው ነው።ኢቦላ ከሰውነት ከሚወጣ ፈሻሽ እና ሌሎች ኢንፌክሽኖች አማካኝነት ይተላለፋል ምልክቱም ጉንፋን መሳይ ህመም፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ፣ ውስጣዊና ውጫዊ መድማት ናቸው።ምንጭ ### Response:
### Text: የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር 14 እጩ የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረጉየሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ 14 የካቢኔ እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።በእጩ ካቢኔ አባላት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሹመት ቀርበዋል የዓለም ባንክ0የቀድሞው0የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ደግሞ ለገንዘብ ሚኒስትርነት ቀርበዋል።አስማ አብደላህ የመጀመሪያዋ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እጩ ሲሆኑ ኢብራሂም ኤልባዳዊ ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትርነቱን እንዲመሩ በነጻነትና የለውጥ ኃይሎች ለሹመት ተጠቁመዋል።የገንዘብ ሚኒስትርነቱን የሚረከቡት ኢብራሂም ኤልባዳዊ በቀውስ ላይ የሚገኘውን የሱዳን ምጣኔ ሀብት እንዲያገግም የማድረግ ኃላፊነት ይጣልባቸዋል ተብሏል።ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈም ለሌሎች 12 መስሪያ ቤቶች ሚኒስትር ለመሾም እጩዎች ይፋ መሆናቸው ነው የተነገረው።እንደ መረጃ ምንጮች ከሆነ አደል ኢብራሂም የኢነርጅና የማዕድን ሚኒስትር፣ ጀኔራል ጀማል አለዲን ኦማር የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀርበዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ ሙሉ የካቢኔ አባላትን በ48 ሰዓታት ውስጥ ይፋ የሚያደርጉ ሲሆን ካቢኔው የሱዳንን ሦስት የሽግግር ዓመታት የመንግሥት ስራዎችን ያስፈፅማል።ሃምዶክ የካቢኔ አባላቱ ከመላው ሱዳን የተውጣጡ እና የሴት ተሿሚዎች ቁጥርም ተመጣጣኝ እንዲሆን ማቀዳቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው አል ጄዚራ ነው። ### Response:
### Text: የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስራ አመራር ቦርድ አባላት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን እየጎበኙ ነው በአምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስራ አመራር ቦርድ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የመስክ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡ በጉብኝቱ ወቅት አምባሰደር ግርማ እንደተናገሩት ጉብኝቱ ፕሮጀክቱን ከሰነድ ሪፖርት ባለፈ በአካል የማየት እና የመገምገም ዓላማ አለው።ጉብኝቱ ከፕሮጀክቱ የስራ ተቋራጮች ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በመወያየት ያጋጠሙ ችግሮችና ደካማ አፈፃፀሞች ካሉ በግልፅ በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ለመስቀመጥ እንዲሁም ፕሮጀክቱ በቀጣይ በተሻለ አፈፃፀም ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በመስክ ምልከታውም የስራ አመራር ቦርድ አባላቱ የፕሮጀክቱን የተለያዩ የሲቪልና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ በዶር አብርሃም በላይ እና በፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ሰፋ ያለ ገለጻና ማብራሪያ ተሠጥቷቸዋል፡፡ ከጉብኝቱ በኋላም ከፕሮጀክቱ የስራ ተቋራቱጮች ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በተለይ በቅድሚያ ኃይል ያመነጫሉ ተብሎ በሚጠበቁት ሁለቱ ዩኒቶች ማለትም ዩኒት 9 እና 10 የስራ አፈጻጸም ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ማካሄዳቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡ኢቢሲ ### Response:
### Text: አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ሀደራየኤርትራ ልዑክ ጥምቀትን በጎንደር እየታደመ ይገኛል። በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ሀደራ የተመራ የኤርትራ ልዑክ ዛሬ ጠዋት ነው የጥምቀት በዓልን ለመታደም ጎንደር የገባው። የከተማዋ ነዋሪዎችና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከአቀባበል ጀምሮ ላሳዩት አክብሮት አምባሳደሩ ምስጋና አቅርበዋል። አምባሳደሩ ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ተብሎ ይጠራ በነበረው በዛሬው ፋሲለደስ የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሆነው ይሰሩ እንደነበርም አስታውሰዋል።በወጣትነት እድሜያቸው ጥምቀትን ከጎንደር ሕዝብ ጋር ያከብሩ እንደነበር አስታውሰው ከበርካታ ዓመታት በኋላ የዘንድሮውን ጥምቀት በመታደማቸው ደስተኛ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።በከተማዋ ይኖሩ የነበሩ፣ልዩ ትዝታ ያላቸው ኤርትራውያን ታሪካዊቷን ጎንደር ከተማን የመመልከት እድል ሰፊ ሊሆን እንደሚገባም ነው አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ሀደራ ሀሳብ የሰጡት። ሁለቱ ሀገራት ወደ ሰላማዊ ስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ አዎንታዊ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም በተለይ ለአብመድ ተናግረዋል።ወደፊት የጦርነት ድምፅ የማይሰማበት ጊዜ እንዲመጣ፣ በሁለቱ ሀገራት መሪዎችና ባለስልጣናት የተጀመረው ግንኙነት ወደ ሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት ማደግ እንዳለበትም ነው የተናገሩት። ### Response:
### Text: ሱዳን ሱዳን ሰነድ የላቸውም ያለቻቸውን የሀገራችንን ዜጎች እያፈሰች እያሰረችና እየቀጣች ነው።ጎረቤት ሀገር ሱዳን በሀገሯ የሚገኙትን ዜጎቻችንን እያፈሰች እያሰረች ሲሆን በዛው ያሉ ዜጎቻችን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን የያዘበትን መንገድ እየወቀሱ ይገኛሉ።ዜጎቻችን ከፍተኛ ቅጣት እየተጣለባቸው እስከ ድብደብዳ የደረሰ እንግልትም እየደረሰባቸው ኤምባሲው ዝምታን እየመረጠ ነው ሲሉ ተችተዋል።ኤምባሲው በበኩሉ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ፓስፖርት የሌላቸው በሱዳን የሚገኙ ዜጎቻችን ፓስፖርት እንዲያገኙ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰነድ አልባ ዜጎቻችን የሞሉትን ሰነድ አልባ ፎርም በማጣራት ውሳኔ በመስጠት ፓስፖርት እያዲያገኙ እየተሰራ ነው ብሏል። ነገር ግን ብዙ ዜጎቻችን ፓስፖርት እያላቸው የመኖሪያ ፍቃድ ኢቃማ ባለማውጣታቸው ምክንያት እየታሰሩና ገንዘብ እየተቀጡ እንደሚገኙም አመልክቷል።ኤምባሲው ፓስፖርት መያዝ ብቻ ከቅጣትና ከመታሠር አያድንም ብሏል።ፓስፖርት አውጥተው 5 ዓመት ሙሉ መኖሪያ ፍቃድኢቃማ ሳያሰሩ ፓስፖርት የሚያሳድሱ ዜጎቻችን ብዙ ናቸው ያለድ ኤምባሲድ የመኖሪያ ፍቃድ ካላወጡ ፓስፖርት ብቻ መያዝ ህጋዊ አያደርግም ብሏል።የመኖሪያ ፍቃድ ባላወጡ ዜጎች ላይ አሁንም አፈሳውሊቀጥል ይችላል ያለው ኤምባሲው ፓስፖርት ያላችሁ የመኖርያ ፍቃድ ኢቃማ እንድታወጡና ህጋዊ ሆናችሁ እንድትኖሩ እንመክራለን ብሏል።ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል ### Response:
### Text: መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል። 200 0000 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ0 ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል።መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ዶር 0 በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ0 እንደገለጹት0መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ0 ወር ለሁሉም0ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች0 በአንድ ጊዜ0ይሰጣል።የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ0 ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ0የመውጫ ፈተና0ከ6 ወራት0 በኋላ0እንደሚሰጥም0ዶር ኤባ0 አስረድተዋል።የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት0ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን0ለ200 0000የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።ፈተናው ለሁሉም ተማሪዎች0በኦንላይን እንደሚሰጥ የጠቀሱት0አቶ ሰይድ ይህ የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ0 በመሆኑ ነው ብለዋል።የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ0 ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ከወዲሁዝግጅት እንዲያደርጉ አቶ ሰይድ አሳስበዋል።በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።ትምህርት ሚኒስቴር ### Response:
### Text: ፍትህ ለብላቴናው መሀመድ የዛኔው ለጋ ህፃን የአሁኑ ታዳጊ መሀመድ ከዛሬ 12 አመት በፊት የ4 አመት ጨቅላ ህፃን ሳለ ነበር አፍንጫው ላይ የወጣችን አነስተኛ ስጋ ለማስነሳት ቤተሰቡ ጋር በሳኡዲ አረቢያ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል የገባው በወቅቱም እናቱ በገባበት የህክምና ክፍል አጠገብ ሁና የልጇን መውጣት ብትጠብቅም ሳይመጣ ቀረባት ከሰአታት ቡሃላም ፈፅሞ ያልጠበቀችው ያልገመተችው ዱብ እዳ ተነገራት ።ልጇ መሀመድ በጣም ደክሞ ህይወቱ አደጋ ላይ መሆኑን ሰማች እንዴ በምን ምክንያት ልጄ እኮ ጤነኛ ነበር ምን አደረጋችሁብኝ እያለች ጠየቀች አለቀሰች ግን ሰሚ አላገኘችም እነሆ ላለፉት 12 አመታት ወይዘሮ ሀሊማ በሞትና በህይወት መካከል የሚገኘውን ልጇን አይን አይኑን እያየች አጠገቡ ኩርምት ብላ እያለቀሰች ትገኛለች ለመሆኑ ህፃን መሀመድን ምን ቢያደርጉባት ይሆን 12 አመት ሙሉ ከገባበት ሰመመን ሳይነቃ የአልጋ ቁራኛ ያደረጉባት ይሄን ወንጀል የፈፀሙትስ አካላቶች ተጠይቀው ይሆን የኢትዮጲያ ኤምባሲ በሳኡዲ ለመሆኑ የመሀመድን ጉዳይ ምነው ዝም አለውቢቢኤን ከወላጅ እናቱ ከወይዘሮ ሀሊማ ባደረገው አጠር ያለ ቆይታ የህፃን መሀመድ እናት ወይዘሮ ሀሊማ ይህን ብላለችወገኖቼ ሆይ ፍረዱኝ ልጄን ተቀማሁ ሀዘን ጠበሰኝ ሀሊማ ሁላችንም ከጎኗ ሁነን ለፍትህ እንጮህላት ዘንድ በየእምነታችን በዱአ እና ፆለት እናግዛት ዘንድ ትማፀናለች። ፍትህ ለብላቴናው መሀመድ© ### Response:
### Text: ለጋሾች ርዳታ ለማድረስ በእግር መጓዝ ጀምረዋል በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ እና ሊተነበይ የማይችል መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ጽቤት ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።በአፋር በኩል በመጋሌ፣ ኢረብቲ፣ በራህሌ፣ ዳሎል እና አባላ ግጭት መኖሩን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በኩል፣ በዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ከትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት መኖሩን ሪፖርት አድርጓል።በተቀረው የአማራ ክልል ሁኔታው 200200የተረጋጋ እና ለሰብአዊ ምላሽ ተደራሽ መሆኑን ገልጿል። በትግራይ ክልል ባለው የነዳጅ እጥረት ሳቢያ የውጭ ሃገራት ርዳታ ድርጅቶች በምግብ እጦት የተጎዱ ሴቶች እና ህጻናትን ለመርዳት በእግራቸው መጓዝ ጀምረዋል ሲል አሳውቋል። የሰሜን ኢትዮጵያ የሰብአዊ አቅርቦት ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት ባወጣው ሪፖርቱ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የርዳታ ድርጅቶች በአጠቃላይ ካለፉት አራት ቀናት አንስቶ ነዳጃቸው መሟጠጡን ገልጿል።ያም ቢሆን ግን ድርጅቶቹ ሠራተኞቻቸው የቀሯቸውን ጥቂት የርዳታ አቅርቦቶች ለማዳረስ እስከ ቻሉት ድረስ በእግር መጓዝ ጀምረዋል ብሏል። ትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሀገር በቀል የርዳታ ድርጅቶችም ቢሆኑ በነዳጅ እጥረት ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴያቸውን የማቆም ስጋት ተጋርጦባቸዋል ብሏል።ከነዳጁ በተጨማሪ የገንዘብ እጥረት መከሰቱም ተገልጿል።ሙሉ ሪፖርት ### Response:
### Text: የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሀገራዊ ሰላም በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ በማስተላለፍ ውሳኔውን የሚያስፈጽሙ አባቶችን ሰይሟል።የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 23 የመወያያ አጀንዳዎችን አጽድቆ በመወያየት ልዩልዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ ጀምሯል።ዓመታዊው የግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓም በጸሎት ከተጀመረ በኋላ በትላንትናው ዕለት በጠዋቱ መርሐ ግብር የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ መልዕክት አዳምጧል። በመቀጠልም ሰባት አባቶችን የያዘ የአጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ አባላትን በመሰየም አጀንዳዎችን አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ ካደረገ በኋላ በኮሚቴው ተዘጋጅተው የቀረቡለትን አጀንዳዎች መርምሮ ማስተካከያ ካደረገባቸው በኋላ አጽድቋቸዋል።በመቀጠልም በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል መሰረት የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ መልዕክት ያጸደቀ ሲሆን ሀገራዊ ሰላም በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ በማስተላለፍ ውሳኔውን የሚያስፈጽሙ አባቶችን ሰይሟል።የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ ጠዋት የጉባኤ ውሎው ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍ የሚጠበቅ ሲሆን ከሰዓት በኋላን ጨምሮ እስከ እሁድ ድረስ በበዓላት ምክንያት ጉባኤው እንደማይካሔድ ታውቋል። ምልዐተ ጉባኤው ከሰኞ ጠዋት ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን በማከናወን ቀሪ አጀንዳዎችን መሰረት ያደረጉ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።ምንጭ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ### Response:
### Text: ስፖኪዮ የተሰረቀባችሁ ማስረጃ በማቅረብ ንብረታችሁን መውሰድ ትችላላችሁ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ ከ200 በላይ የተሽከርካሪ ስፖኪዮ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን አስታውቋቃ።ስፖኪዮዎቹን እየተቀበሉ በማከማቸት የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛልም ብሏል።ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ አሜሪካን ግቢ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።ተጠርጣሪዎቹ በአካባቢው በላስቲክ ተወጥሮ በተሰራ መኖሪያ ቤት ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ በርካታ የመኪና ስፖኪዮዎችን አከማችተው የተገኙ ናቸው። ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማና ፖሊስ ባደረገው ክትትል 2 ግለሰቦችን ከነኤግዚቢቶቹ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ የገለፀው ፖሊስ በተከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የተሰረቁ ተጨማሪ ስፖኪዮዎች በልደታ ክከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ጎላ ሚካኤል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ እንደተመለሱ እና በአጠቃላይ 202 ስፖኪዮዎች ከነመፍቻዎቹ እንደተያዙ አሳውቋል።የአዲስ አበባ ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት ስፖኪዮ የተሰረቀባቸው ባለንብረቶች ማስረጃዎቻቸውን በማቅረብና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል እየቀረቡ ንብረታቸው ስለመኖሩ አረጋግጠው እንዲረከቡ መልዕክቱን አስተላልፏል።አዲስ አበባ ፖሊስ ### Response:
### Text: ቤንሻንጉል ጉምዝ️ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉ የገጠር መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበረ ግለሰብ በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል በአምስት ዓመት ከስድስት ወር እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጠ።ፍርድ ቤቱ ዛሬ ባዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበረው አቶ መልካሙ ታደሰ ላይ ነው።ግለሰቡ ለመንገድ ሥራ የሚውሉ መሳሪያዎች ግዢ ለመፈፀም በወጣ ጨረታ የግዢ ስርዓቱን ባለመከተል ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብና የመንግስት ሃብት እንዲባክን በማድረጉ ውሳኔው እንደተላለፈበት በችሎቱ ተመልከቷል።የተሰጠውን የመንግስት ኃላፊነት አለአግባብ በመጠቀም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ2008 እስከ 2009 ዓም የተለያዩ መስሪያዎችን ግዢ ለመፈፀም ባወጣው ጨረታ አሸናፊው ድርጅት ላሸነፈበት የውል ማስከበሪያ ሳያቀርብ ውል እንዲገባ በማድረግ የውሉን 30 በመቶ ቅድመክፍያ እንዲፈፀም ትዕዛዝ መስጠቱ ተጠቅሷል።በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ቅድመ ክፍያ ተቀብሎ በገባው ውል መሰረት መሳሪያዎቹን ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሳያቀርብ መቅረቱም በችሎቱ ተመልክቷል፡፡ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ከዋለበት ጊዜ አንስቶ በአምስት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል።ምንጭ ኢዜአ ### Response:
### Text: ምዕራብ ጉጂ ዞን️በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን በፀጥታ ችግር ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች ማስተማር ጀምረዋል። በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር ተሻሽሎ 0አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ዋና አስተዳዳሪው አቶ አበራ ቡኖ ተናግረዋል። በዞኑ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ እንደነበርም ገልጸዋል። በአባገዳዎች ሰብሳቢነት አስተዳደሩ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ አባላት ጋር በመወያየት በአሁኑ ወቅት በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ጠቁመዋል። በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎችና በሁለት ከተሞች የተካሄደውን የሰላም ውይይት ተከትሎ ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ማስተማር መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።በፀጥታ ችግር አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የመሰረተ ልማት ተቋማትም በአብዛኛው ሥራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል። በዱግዳ ዳዋና ቡሌ ሆራ ዙሪያ ወረዳ ያልተከፈቱ አንዳንድ ትምህርት ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር በአሁኑ ወቅት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ መሆኑንም አቶ አበራ አመልክተዋል፡፡ በጉጂ ዞን በአሁኑ ወቅት 592 ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ተግባራቸውን በአግባቡ እየተወጡ ይገኛሉ። በትምህርት ቤቶቹ ከ300 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችም መደበኛ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።ምንጭኢዜአ ### Response:
### Text: ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ የሰው ኃይል ይፈልጋል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ለማስፈጸም 140 ሺህ በላይ አስፈጻሚ ለመሆን የሚችሉ ሰዎቸን ምልመላ የሚያከናውንበት ሂደት በማጠናቀቅ የአስፈጻሚዎችን ፍቃደኝነትን፣ ገለልተኝነትን እና ብቃትን በማረጋገጥ ስራ ላይ ነው።ምርጫ አስፈጻሚዎች የምርጫ ሂደቱ ዋና አካል መሆናቸውን በመረዳት እና ስራውም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ በመሆኑ እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የሰው ሃይል እጥረት እነዳይፈጠር በማሰብ ተጨማሪ የሰው ሃይል ምልመላ ማከናወን እንዳለበት አምኗል። በዚህም መሰረት ለምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት አገራችሁን ለማገልገል የምትፈልጉ ምንም አይነት ፓርቲ አባልነት፣ የዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች ላይ ሰርታችሁ የማታውቁ ከሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጪ በሌሎች የቀድሞ ምርጫ የማስፈጻም ተግባራት ላይ ተሳትፋችሁ የማታውቁ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ረጅም አመት የስራ ልምድ ያላችሁ በዚህ ፎርም በመጠቀም በሚቀጥሉት አራት ቀናት እስከ የካቲት 27 ድረስ ብቻ ማመልከት ትችላላችሁ። የስራው ቆይታ ለ4 ወራት ሲሆን ፣ የቀን አበል ፣ አስፈላጊ የሆኑ ቦታዎች ሁኔታዎች ላይ ጥበቃ ፣ እንዲሁም ስራውን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ነገሮች ቦርዱ ያሟላል። የስራ ልምድ ሰርተፍኬት፣ የድጋፍ ደብዳቤ ቦርዱ እንደሚሰጥ ገልጿል። ለሌሎችምእንዲደርስሼርያድርጉ ### Response:
### Text: ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በ25 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተገልብጦ በ25 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።የጽህፈት ቤቱ የወንጀል መከላከል የስራ ሂደት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር አንዳርጌ በላይ እንደገለፁት አደጋው የተከሰተው ዛሬ ጠዋት 60 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት 00830 አውቶብስ ኤፍራታና ግድም ወረዳ ሆራ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ሲደርስ በመገልበጡ ነው።በአደጋው በአራት ሰዎች ላይ ከባድ በ21 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ረዳት ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል። ጉዳት ከደረሰባቸው መንገደኞች መካከልም የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሰዎች ይገኙበታል ተብሏል።የአውቶቡሱ አሽከርካሪ ከአደጋው በኋላ እጁን ለፖሊስ ሰጠቶ ጉዳዩ እየተጣራ እንደሚገኝ ከረዳት ኢንስፔክተር አንዳርጌ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል። በአደጋው የተጎዱት ሰዎች በደሴ ሪፈራል ሆስፒታልና በአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ ነው የተባለው ።እንደ ረዳት ኢንስፔክተሩ ገለጻ የአደጋዉ መንስኤ እየተጣራ ቢሆንም ከፊት የነበረውን 0ተሽከርካሪ ለመቅደም ሲሞክር ጭቃ አዳልጦት ሊወድቅ እንደቻለ በአካባቢው ከነበሩ የአይን እማኞች መገንዘባቸውን ተናግረዋል። ኢዜአ ### Response:
### Text: የአዲስ አበባና ዙሩያዋ ሰላም እና ፀጥታ ካለፈው ሳምንት ወዲህ አጠያያቂ ሆኖ ቀጥሏል ካሳለፍነው ሳምንት ወዲህ በለቡ፣ ጀሞ፣ አስኮ፣ በአቃቂ ክከተማ የተለያዩ አካባዎች፣ ኮየ ፈጬ እና በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ በተደራጁ ወጣቶች ምክንያት ሰላም ደፍርሷል ህብረተሰቡም ስጋት ውስጥ ወድቋል፡፡የተደራጁ ወጣቶቹ ከየት መጡ ሳይባል መንገድ ይዘጋሉ፣ የጥላቻ ንግግሮችን በአደባባይ ያስተላልፋሉ፣ የተለያዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ዜጎችን ያስፈራራሉ ንብረትም ያወደሙ እንዳልጠፉ ለማወቅ ችለናል፡፡በማህበራዊ ድህረገፆች ደግሞ መንገድ በድንጋይ ከመዝጋት ጀምሮ የተለያዩ የድርጅቶች ማስታወቂያዎችን እና አርማዎችን ሲያወርዱ፣መንገድ ዘግተው በርካታ ህገወጥ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ ተመልክተናል፡፡ የደንብ ልብስ የለበሱ የፀጥታ አካላት ህግ ከማስከበር ይልቅ ቆመው ሲታዘቡ ለማየትም ችለናል፡፡ጉዳዩ በጊዜ ካልተቀረፈ ስጋቱ ወደ መሀል ከተማ የማይመጣበት ምክንያት የለም እና ቆሞ ከመታዘብ ውጪ የፀጥታ ሀይሎች ህግ እንዲያስከብሩ የየአካባቢው ነዋሪዎች ሀሳባቸውን አካፍለውናል፡፡ በአዲስ አበባ የተፈጠረው የሰላም እጦት አሁንም ቀጥሏል ይህ ሁሉ ሲፈጠር ለመሆኑ ፖሊስ ቆሞ መታዘቡን ይቀጥላል፣ ወይስ ሰላም ያስከብራል በሚለው ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም፡፡ ጋዜጠኛ ትግስት ዘላለም ### Response:
### Text: ከየትኛዉም ጊዜ በላይ ወንድማዊ ትስስራችሁን አጥብቃችሁ ተረጋግታችሁ የትምህርታችሁን ጊዜ በአግባቡ እንድትጠቀሙ ቤተሰባዊ ምክራችንን እንለግሳለን ጅማ ዩኒቨርሲቲመላዉ የጅማ የኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተዉ ግጭት ህይወታቸዉን ላጡና የአካል እና መንፈስ ጉዳት ለደረሰበቸዉ ተማሪዎች የተሰማዉን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ በእነዚህ በምንሳሳላቸዉ ልጆቻችን ላይ የደረሰዉ ጉዳት በዬትኛዉም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለዉና ሰብአዊነትን ያልተላበሰ በመሆኑ በከፍተኛ ደረጃ እናወግዛለን፡፡ከዚህ በተጨማሪ የሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ሁሉ የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ በሙሉ ሃይላቸዉ ተንቀሳቅሰዉ በዚህ አስነዋሪ ድርጊት ዉስጥ የተሳተፉ አካላት ላይ በአፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎችም ከዬትኛዉም ጊዜ በላይ ወንድማዊ ትስስራችሁን አጥብቃችሁ ተረጋግታችሁ የትምህርታችሁን ጊዜ በአግባቡ እንድትጠቀሙ ቤተሰባዊ ምክራችንን እየለገስን የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብና የበላይ አስተዳደር አካላት ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ ከጎናችሁ መሆናችንና እያነሳችሁ የምትገኙትን ጥያቄ ለሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት በማቅረብ ተገቢዉን ምላሽ እንድታገኙ የበኩላችንን ጥረት ሁሉ እንደምናደርግ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን፡፡ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን ### Response:
### Text: የሚዲያዎቹ ተፅእኖከሰሞኑን ቢቢሲ ትግርኛ፣ ቢቢሲ አማርኛ፣ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎክ እና አውሎ ሚዲያ በነጀነራል ሰዓረ ጉዳይ ባለቤታቸውን ኮሎኔል ፅጌ አለማየሁን አነጋግረው ያለውን ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው አድርገዋል።የኢትዮጵያ ህዝብ ስለተፈጠረው ሁኔታ፣ ስለ ፍርድ ሂደቱ ፣ የጀነራል ሰዓረ ቤተሰቦች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ በግልፅ ሳያውቅ ከአንድ ዓመት በላይ ተቆጥሯል።ኮሎኔል ፅጌ አለማየሁ ትላትን ምሽት በ በተሰራጨ ልዩ ዝግጅት ላይ ስለጉዳዩ ልክ እንደሌላው ሰው በፌስቡክ እና ዩትዩብ እንደሚከታተሉ ይፋ አድርገዋል ይህ ብዙዎችን አስደንግጧል አሳዝኗልም።ኮሎኔል ፅጌ የባለቤታቸው ደም በከንቱ መፍሰሱ፣ ያለፍትህ ከዓመት በላይ መቆየታቸው፣ ስለ ሀገር መሪው ስለጀግናው ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ሲል ስለተሰዋው ባለቤታቸው ጠያቂ ማጣታቸው ፣ ለጉዳዩ ትኩረት መነፈጉ አሁንም ድረስ እንደሚያንገበግባቸው እያለቀሱ ተናግረዋል።ከላይ የተጠቀሱት ሚዲያዎች ኮሎኔል ፅጌን በማነጋገር ከሰሩት ስራ በኃላ ዛሬ ጥዋት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጀነራል ሰዓረ እና የሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ግድያ ወንጀል ሲካሄድ የነበረው የክርክር ሂደት እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጻል። የችሎት ክርክሩ ከሰኔ 232012 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት የተጎጂ ቤተሰቦች ጉዳዩን መከታተል የሚፈልጉ ውስን ሚዲያዎች ወይም ግለሰቦች ባሉበት ይቀጥላል ተብሏል። ### Response:
### Text: በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በተለይም በወላድ እናቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት መሆኑን ሁሉም አካል ሊያውቀው ይገባል ቀይ መስቀልየኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የምዕራብ ወለጋ ዞን ሀሩ ወረዳ ቅርንጫፍ ጽቤት ንብረት የሆነ ማኅበሩ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚጠቀምበት ታርጋ ቁጥሩ 0501939 አምቡላንስ ተሽከርካሪ በዛሬው ዕለት ማለትም ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት በሀሩ ወረዳ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ በቆመበት በታጣቂ ኃይሎች ተቃጥሏል፡፡ ማኅበሩ መሰል ድርጊቶች ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ሥምምነቶች የሚጥሱና በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ የሚያስጠይቁ መሆናቸውን ገልጿል።በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎቹ ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶች በሰብዓዊ አገልግሎቱ ላይ እንቅፋት እየፈጠሩበት እንደሚገኙ ማህበሩ አመልክቷል።በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በተለይም በወላድ እናቶች ላይ የሚፀም ጥቃት መሆኑን ሁሉም አካል ሊያውቀው ይገባል ሲል አስገዝቧል።ማህበሩ አሁንም በድጋሚ በመላው አገራችን በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ሠራተኞችና በጎፈቃደኞች እንዲሁም አምቡላንሶችና ሌሎች ተሽከርካሪዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ መሰል ድርጊቶችን የሚፈፅሙ አካላት ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን ብሏል። ### Response:
### Text: በተከሰተው ድርቅ ህብረተሰቡ ለሞት እና ረሐብ ተጋልጧል ጃን አሞራ ወረዳ በሰሜን ጎንደር ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ሰዎች እና እንስሳት እየሞቱ ነው ተባለ። በሰሜን ጎንደር ዞን በምትገኘው ጃን አሞራ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ 13 ቀበሌዎች በክረምት ወራት ምንም አይነት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ ህብረተሰቡ ለሞት እና ረሐብ መጋለጣቸውን የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸጋው ተሰማ ገልፀዋል ። አስተዳዳሪው አክለውም በድርቁ ምክንያት እስካሁን 16 ሰዎች ፣6500 የጋማ ከብቶች እና 400 ዶሮዎች መሞታቸውን ገልጸው 1400 ሰዎች በድርቁ ምክንያት አካባቢውን ጥለው መሰደዳቸውን እና አሁንም ከ 58 ሺ በላይ ሰዎች የከፋ ረሃብ ላይ መውደቃቸውን አክለዋል። ጃን አሞራ ወረዳ ውስጥ 38 ቀበሌዎች የሚገኙ ሲሆን በውስጡ ከ 230ሺ በላይ ህዝብ የሚኖር ሲሆን ከ 38 ቀበሌዎች ውስጥ በ13 ቀበሌዎች ውስጥ በክረምቱ ምንም አይነት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት ረሐብ እና ድርቅ መከሰቱ ነው የተገለጸው። በዚህም ምክንያት ድርቁን ተከትሎ የተለያዩ ወረርሽኞች መከሰታቸውን እና በአተት ምክንያት ብቻ 6 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቀዋል። ላለፉት ዓመታትም በወረዳው ድርቅ መከሰቱን የገለፁት አስተዳዳሪው የአሁኑ ግን ከዚህ በፊቱ የከፋ መሆኑን እና መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ0አሳስበዋል። ዘገባው የሸገር ራድዮ ነው። ### Response:
### Text: ዶክተር አብይ አህመድ ማናቸው ዶክተር አብይ አህመድ በአጋሮ ከተማ የተወለዱ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ አግኝተዋል። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ሰርተዋል። በግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ እና በሊደርሺፕ ተቋም ደግሞየሥራ አመራር ሳይንስ አጥንተዋል። እንዲሁም አሽላንድ ዩኒቨርሲቲ በንግድ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሰላም እና ደህንነት ጥናት ፒኤችዲ አላቸው። በመጀመሪያ 40ዎቹ የሚገኙት ዶክተር አብይ ኦህዴድን የተቀላቀሉት በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው። ከፖለቲካ ተሳትፏቸው በተጨማሪ በወታደራዊ ጉዳዮች ሰፊ ተሳትፎየነበራቸው ሲሆን የሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ አላቸው። በተባበሩት መንግሥታት የስላም ማስከበር ተልዕኮን ለማስፈጸም ሩዋንዳ ዘምተዋል። ከ2000 እሰከ 2003 የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር በመሆነ አገልግለዋል። ከዚያም የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር በመሆን ሰርተዋል። ከ2002 ጀምሮ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩሲሆን ከ2007 ጀምሮ ደግሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ ላለፉት ሦስት ዓመታት የኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። የኦህዴድ ሊቀመንበር ሆነው በቅርቡ የተመረጡት ዶክተር አብይ በአሁኑ ጊዜ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትአባል ናቸው።ምንጭ ### Response:
### Text: የእሳት አደጋአዲስ አበባ️በዛሬው ዕለት በመዲናዋ ሶስት ቦታዎች የእሳትአደጋ መከሰቱን የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን ገለጸ፡፡የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ30 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ቁስቋም ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚገኝ ንብረትነቱ የንግድ ባንክ በሆነ የቤት እቃዎች መጋዘን ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።ባለስልጣኑም ሁለት ከባድ ተሽከርካሪ፣ 5 ሺህ ሊትር ውሃና 7 የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞችን በማሰማራት 3 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን ገልጸዋል፡፡በተመሳሳይ መልኩ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ቅርንጫፍ ጀርባ በሚገኝ አንድ የመኪና ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አንድ ተሽከርካሪና 10 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም ግምቱ ከ300 ሺህ ብር በላይ የሆነ ንብረት ማዳን ተችሏል።ከዚህም ሌላ ዛሬ ከሰዓት በአንዋር መስኪድ የሴቶች መግቢያ በር ላይ በሚገኝ አንድ የንግድ ሱቅ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ 30 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።ከአደጋው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡ምንጭ ### Response:
### Text: የኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 406 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። 3 ከመተከል ዞን ጉባ ወረዳ 2 ከአሶሳ ዞን አሶሳ ወረዳ 1 ከአሶሳ ህዳሴ ኤርፖት በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 587 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 66 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል የሁለት ሰዎችም ህይወት አልፏል። አጠቃላይ በሀረሪ 432 በቫይረሱ የተያዙ 14 ሞት 80 ያገገሙ በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 552 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 109 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ከነዚህ መካከል 27 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው።አጠቃላይ በትግራይ 1361 በቫይረሱ የተያዙ 10 ሞት 710 ያገገሙ በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 332 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 26 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከማህበረሰቡ በተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው። በተጨማሪ ትላንት የአንድ ሰው ህይወት አልፏል። በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4340 የላብራቶሪ ምርመራ 72 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።ከነዚህ መካከል 15 ከባህር ዳር 14 ከሰሜን ሸዋ ዞን 7 ከደጎንዳር ዞን 13 ከሰወሎ ዞን 9 ከምስጎጃም ዞን 6 ከደሴ ከተማ 4 ከማዕጎንድር 5 ደወሎ ዞን 3 አዊ ብሰብ ዞን 2 ከምዕራብ ጎጃም ዞን 1 ከደቡብ ጎንደር ዞን በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 68 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮቪድ19 ተይዘዋል።3 ጅግጅጋ1 ሞያሌ ### Response:
### Text: ጥንቃቄ በድሬደዋ ከተማ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን መስተዋሉን ተከትሎ የከተማው ጤና ቢሮ ለነዋሪዎች የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፏል።በተለይም አረጋውያን እና የተለያዩ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው ከፍተኛ ደም ግፊት፣ የስኳር ህመም፣ የልብ ህመም፣ የኩላሊት ህመምና ሌሎችም፣ እራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ የአእምሮ ህሙማን እና ህፃናት በተለየ መልኩ ከታች የተዘረዘሩትን የጥንቃቄ መልእክቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።1 ወቅታዊው ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስኪያልፍ መኖሪያ ቤትዎን በተለያዩ መንገዶች ማቀዝቀዝ2 ቤትዎ በሚሆኑበት ግዜና በእንቅልፍ ወቅት የቤትዎን መስኮትና በር ክፍት ማድረግ3 በቤትዎ የአየር መታፈን እና ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ወቅት ከቤትዎ ውጪበረንዳዎ ላይ መቆየት4 ጥም ባይኖርቦትም በቂ ፈሳሽውሃ መውሰድ5 አመጋገብዎን ማስተካከልስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ6 ቀለል ይሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ጥላማ በሆኑ ቦታዎች ላይ መስራት7 የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀምመቀነስ8 ህፃናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን በተዘጉአየር በሌላቸው ክፍሎች ለብቻ አለመተው9 የተለያየ ህመም0 ማለትም እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመም ካለብዎ የህክምና ክትትልዎን በሚገባ ማድረግ፣ የታዘዘውን መድኃኒት በትዕዛዙ መሰረት በመውሰድ ጤናዎን እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል። 6 ### Response:
### Text: ሰላም ሚኒስቴር የአገር ግንባታ መሠረታዊያን በሚል ርዕስ ለሚዲያ አካላት ከቅን ልቦች በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ትላንት በአዳማ ከተማ የአንድ ቀን የምክክር መድረክ አካሂዶ ነበር።በመርሀ ግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደኣ፣ መሰል የውይይት መድረክ በኢትዮጵያ ለሚስተዋለው ግጭትና አለመግባባት መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል ጠቁመዋል።በኢትዮጵያ ብዙ የሚያለያዩ ጉዳዮች ቢኖሩም ብዙ የጋራ ትስስር የሚፈጥሩ ነገሮች እንዳሉ፣ ይሁን እንጅ ልዩነት ላይ በማተኮር ግጭቶችና አለመግባባቶች እየተፈጠሩ ከዚህ መደረሱን ገልጸዋል።በመርሀ ግብሩ የተገኙት የቅን ልቦች በጎ ሥራ ድርጅት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ስንሻው፣ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ በሌለበት ማኅበራዊ ሚዲያ ሰላምን መገንባት እንዴት እንደሚቻል በገለጹበት አውድ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስበዋል።አክለውም፣ ሰፊ ውይይት በማድረግ አገራችን ከድጡ ወደ ማጡ የምትሄድበትን ሁኔታ መቀልበስ እንደሚገባ አስረድተዋል።በውይይት መድረኩ ላይ አገር፣ አገረ መንግሥት፣ አገረ ብሔርአገራዊ ማንነት፣ ምንነት፣ የአገራት ተሞክሮአገራዊ እሴት፣ ምንነት፣ የአገራት ተሞክሮአገራዊ ጥቅም፣ ምንነት፣ የአገራት ተሞክሮየሚዲያ ሚና ሰላምን ከመገንባት ረገድ0በሚሉት ነጥቦች ላይ ውይይት ተደርጓል።መረጃው በአአ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋግቶ የተላከ ነው።0 ### Response:
### Text: 2022 የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ35ተኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና በ40ኛዉ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ናቸው።እስካሁን የገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች 0ፍሬድሪክ ሻቫ ዝምባብዌ ኤዲቴ ራሞስ ቴንዡዋ የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ ሌዡን ቤላ ቤላ ካሜሩን ማህማት ዜኑ ሸሪፍ ቻድ ካንዲያ ካሚስኮ ካማራ ኮትዲቯር አብዲሳድ ሙሴ አሊ ሶማሊያ ዢያን ክላውዴ ጋኮሶ የሪፐብሊክ ኮንጎ ሀሱሚ ማሹዱ ኒጀር ምክትል ጠሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ናለዲ ፓንዶር ደቡብ አፍሪካ አሲታ ቶል ሳል ሴኔጋል እስማኤል ኡልድ ሼክ አህመድ ሞሪታኒያ ሙሀሙድ አሊ የሱፍ ጂቡቲ ናጅላ አልማንጉሽ ሊቢያ ጃፍሬ ኦኖማ ናይጄሪያ ቲቴአን ቶኒያ አንጎላ ኦሪም ሄነሪ ኦክሎ ዩጋንዳ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ናይሲ ቴምቦ ማላዊ አምባሳደር ራምታን ላማምራ አልጀሪያ ሙበሌት ቡቤያ ጋቦን ቦሪታ ናስር ሞሮኮ ኦተማን ጃርዲ ቱኒዚያ ፖትሪክ ራአጆልንት ማዳጋስካር ማሪያና ዳጃምላ ኬፕ ቨርዲ አልበርት ሻንግሮ ቡሩንዲ ሲሞኔ ኦዮኖ ኢሶኔ ኢኳቶሪያል ጊኒ ዶህር ዶል ከማል ኮሞሮስ ቱሊሲሌ ድላድላ ስዋህቲኒ ረይሼል ኦማሞ ኬኒያ ቬሮኒካ ማካሞ ንዶቮ ሞዛምቢክ ኮምላን ኢዱ ሮበርት ቶጎ ስታንሌይ ካኩቦ ዛምቢያ ሌሞሀንግ ኪዌፔ ቦትስዋና ሳፊ ሳንካሬ ጋምቢያ ኔቱምቦ ናንዲ ንዳይትዋህ ናሚቢያ ም ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ኤርትራ ### Response:
### Text: መቀለ️ በፖለቲካዊ ምክንያት ለዓመታት ተለያይተው የቆዩት የህወሓት ነባር አመራሮች ትላንት በመቐለ ተገናኝተው 44ኛውን0የካቲት 11 በዓል በጋራ አክብረዋል፡፡0በመድረኩ ለሁሉም የህወሓት ታጋዮችና የቀድሞ አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል፡፡0በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 1993 ዓም ህወሓት ካጋጠመው ክፍፍል በኋላ ነባር የሚባሉት የድርጅቱ አመራሮች ፖርቲው ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል፡፡ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ በአንድ መድረክ ተገናኝተው ትግል የጀመሩበት 44ኛውን ዓመት የካቲት 11 አክብረዋል፡፡0አስተያየታቸውን የሰጡት የቀድሞ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር እንዲሁም ከክፍፍሉ በኋላ ዓረና ትግራይ የተባለ ፖርቲ መስርተው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ ገብሩአስራት የካቲት 11 የአንድ ድርጅት በዓል ተደርጎ እየተከበረ መቆየቱ ተገቢ አልነበረም ብለዋል፡፡0የቀድሞ ታጋይ፣ ከትግል በኋላ የመከላከያ ሚኒስተር የነበሩት እንዲሁም ከክፍፍሉ በኋላ ለዓመታት ታስረው የተፈቱት አቶ ስየ አብረሃ በበኩላቸው ብዙ መቆሳሰል ቢያልፍም የጋራ ታሪክ አለን በማለት በአሉ ከቀድሞ ጓዶቻቸው ጋር ማክበራቸው ጥሩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡0በስነ ስርዓቱ የወቅቱ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡ የመድረኩ አዘጋጅ የትግራይ ክልል ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክርቤት መሆኑ ተገልጿል፡፡ምንጭ የጀርመን ራድዮ ### Response:
### Text: ዳኞች በክረምት ወራት በእረፍት ሰአታቸው ከአመቱ የተጠራቀሙ መዝገቦችን እልባት ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንደጨረሱ ተነገረ፡፡ የተሻሻለው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዳኞች ስነምግባርና የዲሲፕሊን ደንብም ተመርቋል፡፡ዳኞች ለበርካታ አመታት መፍትሄ ያልሰጡባቸውን ውዝፍ የክስ መዝገቦች በእረፍት ሰአታቸው እልባት ለማሰጠት የመግባቢያ ሰነድ በተፈረመበት ወቅት የበጀስቲስ ፎር ኦል ፌሎው ሽፕ ኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ እንዳሉት ዳኞች በመጪው የክረምት ወራት የተጠራቀሙ መዝገቦችን እልባት ለመስጠትና በተለያዩ ክልሎች ዳኞች ሲያጠፉ የሚቀጡበትን የስነስርአት ደንብ ለማሳተም እየሰሩ ነው፡፡ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ከ20 እስከ 30 ሺህ መዝገቦች ይቀንሳሉ ብለው እንደሚያስቡ የጠቀሱት ፓስተር ዳንኤል ባለፈው አመት 23 ሺህ መዝገብ በመሰራቱ 23 ሺህ ዜጎች ፍትህ አግኝተዋልም ብለዋል፡፡እንደ ፓሰተር ዳንኤል ድርጅታቸው ከክልሎች ጋር በመስራት ላይ ሲሆን በአራቱ ክልሎች ማለትም የአማራ፣ የትግራይ፣የደቡብ እና የኦሮሚያ ክልሎች ጋር እየሰራ ነው በዛሬው እለትም የተሻሻለው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዳኞች ስነምግባርና የዲሲፕሊን ደንብም ተመርቋል፡፡ የመግባቢያ ሰነዱ የተፈረመው በበጀስቲስ ፎር ኦል ፌሎው ሽፕ ኢትዮጲያ እና በፌዴራልና ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች መካከል ነው። ቀን ሰኔ 262011 ዓም ### Response:
### Text: በህገወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ በህገወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ወሮ ፈትለወርቅ ገእግዚአብሄር አስታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ በሚገኙ ትልልቅ ከተሞች በአገልግሎትና በመሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት በአቅርቦት ችግር ሳይሆን የህገወጥ ደላሎች ጣላቃ ግብነት መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ የዋጋ ንረቱ በተለይም በደሃው ማህበረሰብ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና እያሰደረ ነው ብለዋል፡፡ጥቂቶች አላስፈላጊ ንዋይ በመሰብሰብ ኢፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል እንዲፈጠር አድርጓልም ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በህገ ወጥ ደላሎች አማካኝነት አየር በአየር በመኪና ላይ ህገወጥ ግብይት ሲያካሂዱ የተገኙ 59 መኪኖች አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም 52 መኪኖች ጤፍና ሌሎች እህሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ወሮ ፈትለወርቅ ጠቁማዋል፡፡የቁጥጥርና እርምጃ የመውሰድ ስራ በሁሉም የሀገሪቷ ክልሎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት፡፡ ደላሎችን ከግብይት ሰንሰለት ውጪ በማድረግና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር አምራቾችና ተጠቃሚዎች በቀጥታ የሚገናኙበትን አግባብ ለመፍጠር ሚኒስቴር መቤቱ የረጅም ጊዜ እቅድ አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡ምንጭ፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ### Response:
### Text: የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እየተጠገኑ ነው።ከገረገራ እስከ ጋሸና ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ ይገኛል።ከህዳር 23 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ በተካሄደ የፍተሻ ሥራ ሠላሳ አራት በሚሆኑ በታወሮች መካከል በሚገኙ ቦታዎች ላይ 50 የመስመሮች መበጣጠስ፣ 7 የድምፅና ዳታ ማስተላለፊያ የኦፕቲካል ፋይበር መቆረጥ እና 13 ቦታዎች ላይ መስመር ሳይበጠስ ጉዳት መድረሱን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ሥር በምትገኘው የአርቢት ቀበሌ ባለ 3 ፌዝ መሥመሮችና የኦፕቲካል ፋይበር ላይ ከፍተኛ በመጣጠስ ደርሷል፡፡ ጉዳት በደረሰባቸው መስመሮች ላይ ጥገና የተጀመረ ሲሆን ጥገናውን በፍጥነት በማጠናቀቅ አካባቢዎቹ ኃይል ማግኘት እንዲችሉ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡በሌላ በኩል በሸዋሮቢት፣ በጀውሀ፣ በሰንበቴ፣ በአጣዬና ካራቆሬ ከተሞች የሚያልፈውን የከፍተኛ መስመር በመጠገን ለስርጭት መስመሮች ኃይል መስጠት እንዲችሉ ዝግጁ የማድረግ ሥራ ተጠናቋል።በቀጣዮቹ ቀናት ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው መስመር የመጠገን ሥራ እንደሚሰራ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያሳያል። የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ ትላንት በሰጡት ቃል የመብራት አገልግሎት ሸዋሮቢት ፣ ደብረሲና ፣ መሀልሜዳ ፣ ዘመሮ ፣ ሞላሌ ድረስ መጀመሩን ገልፀዋል። ### Response:
### Text: መንግስትቶሎ ወደ ስራ ያስገባን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሞተርብስክሌት አሽከርካሪዎችና ባለቤቶች አስተዳደሩ ያወጣውን የአፈፃፀም መመሪያ ማስተካከያ አድርጎ ቶሎ ወደ ስራ እንዲያስገባቸው ጠየቁ። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት የማሽከርከር ስልጣን ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ላይ እያወያያቸው ነው፡፡መመሪያው ሞተር ብስክሌቶች የፍጥነት መቆጣጠሪያ ማስገጠም እንዳለባቸው እንዲሁም የንግድ ስራ የሚሰሩ ሰሌዳቸውን ወደ 3 ቁጥር መለወጥ እንደሚኖርባቸው፣ በከተማዋ መንቀሳቀስ የሚችሉ ሞተሮች ሰሌዳቸው አዲስ አበባ የሆነ ብቻ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ይህም በቢሮው ሀላፊ በዶር ሰለሞን ኪዳኔ በዝርዝር ለውይይት ቀርቧል፡፡ተወያዮቹ የሞተር ብስክሌቶችን በህግ ሥርዓት ውስጥ ማስገባቱ ላይ ቢስማሙም መመሪያው ግን እንዲስተካከል ተሰማምተዋል፡፡ ከተነሱት ሀሳቦች መካከል የሚገጠሙ ጂፒኤሶች ገንዘባቸው ውድ የመሆኑ ጉዳይ፣ የተማረ የሰው ሀይል ማስፈለጉ፣ የክልል ሰሌዳዎች ያሉን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስላለን መመሪያው ሊካተት ይገባል የሚሉት ናቸው፡፡ የቢሮው ሀላፊዎች በተነሱት ሀሳቦች ላይ በድጋሚ በቢሮ ደረጃ እንደሚነጋገሩባቸው ተናግረዋል፡፡ የሞተር ብስክሌት ባለቤቶች ግን መመሪያው ከወጣ ጀምሮ የከፋ ችግር ውስጥ ስለወደቅን ቢሮው ለጥያቄያችን አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠን ይገባሉ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ምንጭ ሸገር ራድዮ ### Response:
### Text: የአፍጋኒስታን ሴቶች ተቋውሞ ታሊባን በአፍጋኒስታን ካቡል ከተማ ስለመብታቸው ለመጠየቅ ተቃውሞ የወጡ ሴቶች መበተነ ታውቋል።ሰልኞቹ ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ላይ እያሉ ታሊባን አስለቃሽ ጭስና አይን የሚያቃጥል ሌላ ፈሳሽ ጭምር በመጠቀም ሰልፉን ለመበተን ጥረት አድርጓል።አንዳንድ የአፍጋኒስታን ሚዲያዎች እንዳሉት ከሆነ ታሊባን ተቃውሞውን ሙሉ በሙሉ መበተን አቅቶት እንደነበርና ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ሆነው እንደነበር ዘግበዋል።ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች የካቡል ሴቶች ተቃውሟቸውን አደባባይ ወጥተው ሲገልጹ ነበር።ሰልፈኞቹ ሴቶች ስራ የመስራት እንዲሁም በመንግስት መዋቅር ውስጥ የመካተት መብታቸውን በመጠየቅ ነው የተቃወሙት። በተጨማሪ የሴቶች መብት እንዲከበር ፣ ሴቶች በፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ሳይረጋገጥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለታሊባን እውቅና እንዳይሰጥ ጠይቀዋል። ታሊባን አፍጋኒስታንን የሚያስተዳድረውን መንግስት በቅርብ ቀን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ምንም እንኳን ታሊባን ሴቶች በመንግስት መዋቅር ውስጥ እንደሚካተቱ የገለጸ ቢሆንም በሚኒስትር ደረጃ ግን ማገልገል አይችሉም ብሏል።ይህን ተከትሎም በርካታ ሴቶች ታሊባን በአውሮፓውያኑ ከ1996 እስከ 2001 ስልጣን ላይ በነበረበት ይከተለው የነበረውን ሴቶች ላይ ያለው አቋም መልሶ እንዳኣመጣ ስጋታቸው እየገለጹ መሆናቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል። ### Response:
### Text: ድሬ በድሬዳዋ ከተማ ትላንት በደረሰ የእሳት አደጋ የዋጋ ግምቱ 46 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ። ለጊዜው0 ምክንያቱ ባልታወቀ0 ሁኔታ0 በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት 46 ሚሊዬን ብር የሚገመት ንብረት ውድሟል ሲል የድሬድዋ ፖሊስ አሳውቋል።ፖሊስ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ትላንት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓም ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ንብረትነቱ የሮያል ፎም ፍራሽ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ ላይ ነው፡፡ከቀኑ 5 ሰአት ገደማ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ የፋብሪካው ንብረት የሆኑ አንድ ትልቅ የምርት ማከማቻ መጋዘን አንድ0 ቦንድድ ማሽን በርካታ የተጠናቀቁ የስፖንጅ ፍራሽ ምርቶች እንዲሁም ሁለት ሆዝ የእሳት ማጥፊያ በአጠቃላይ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት 46 ሚሊዬን ብር ንብረት ወድሟል።አደጋው እንደደረሰ የድሬዳዋ ፖሊስ የእሳት እና ድንገተኛ ዲቪዥን እና የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የእሳት አደጋ ተከላካይ ቡድን በቦታው ላይ በመድረስ እሳቱ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። አደጋውን ለመከላከል አርባ ስምንት ሺ ሊትር ውሃ እና አንድ መቶ ሊትር ፎም መጠቀማቸው ተገልጿል።በደረሰው የእሳት አደጋ ከንብረት ጉዳት ውጪ በሰው ላይ ምንም አይነት አደጋ ያልደረሰ መሆኑን የገለፀው የድሬዳዋ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።ምንጭ፡ ድሬፖሊስ ### Response:
### Text: የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብን ይፋ አደረገ።የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቁት የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብ1 የሶሻል ሳይንስ ሴቶች መግቢያ ውጤት 164 እና በላይ2 የሶሻል ሳይንስ ወንዶች መውጤት ውጤት 174 እና በላይ3 የናቹራል ሳይንስ ወንዶች መግቢያ ውጤት 176 እና በላይ4 የናቹራል ሳይንስ ሴቶሽ መግቢያ ውጤት 166 እና በላይ5 ለግል ተፈታኞች ለወንዶች 190 እና ከዚያ በላይ6 ለግል ተፈታኞች ሴቶች 185 እና ከዚያ በላይ7 ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ናቹራል ወንዶች 1668 ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ናቹራል ሴቶች 156 እና ከዚያ በላይ9 ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ማህበራዊ ሳይንስ ወንዶች 164 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 154 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል።በተጨማሪም መስማት ለተሳናቸው በተፈጥሮ ሳይንስ ወንዶች 120 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 115 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ማየት ለተሳናቸው ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ወንዶች 110 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 105 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም በመንግስት እና በግል ተቋማት በግላቸው ከፍለው ለሚማሩ ተፈታኞች በሁለቱም መስክና ጾታ 140 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተፈታኞች መማር ይችላሉ ተብሏል። በአጠቃላይ በዘንድሮው ዓመት 142 ሺህ 821 ተማሪዎች ወደ መንግስት ዩንቨርሲቲዎች ይገባሉ ተብሏል። ### Response:
### Text: በኦሮሚያ ክልል አባ ቶርቤ የሚባልና ጽሑፍ ያለው ወረቀት እየበተነ 0አስጠንቅቆ 0ሲያበቃ ቀጠሮ ሰጥቶ የሚገድል የተባለ አካል የክልሉን ሰላም እያወከ መሆኑን የክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።አቶ ጌታቸው ባልቻ ለዶቼ ቬለ የተናገሩትትናንት በአምቦ ከተማ ለመንግሥት ድጋፍ የወጡ ሰዎችን እንቅስቃሴ ለማስቆም 0ያሰበ ግን ያልተሳካ ያሉት የቦንብ ጥቃት ተሰንዝሮ 29 ሰዎች ተጎድተዋል። ከተጎጂዎቹ 0አንዱ ብቻ አሁንም በህክምና ላይ እንደሚገኝ ቀሪዎቹ ግን ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። በጉዳዩ በአካል ተሳትፈዋል በሚል እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች እጅ ከፈንጅ የተያዙ ሲሆን ክትትሉ ቀጥሏል። ራሱን በድርጅትም ይሁን በቡድን ደረጃ እንዲህ ነኝ ብሎ የሚጠራ አካል ባይኖርም ግድያ እየፈጸመ ፣ ዜጎችን እያፈናቀለ ፣ ጉዳት እያደረሰ ያለው «አባ ቶርቤ» የሚባል አካል ነው። ባለፈው ዓርብ የተገደሉትን የቡራዩ ከተማ ፓሊስ አዛዥ በተመለከተም ክትትሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሕዝቡን የማረጋጋት እና አጥፊዎቹን ወደ ሕግ የማቅረብ ሥራ በተጠናከረ 0ሁኔታ 0እየተከናወነ ነው። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም 18 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል። መከላከያ ሠራዊት በተለይም በምዕራብ የክልሉ ክፍል ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጸጥታ የማስከበር ሥራ እየሠራ ነው። በሞያሌ ተመሳሳይ ጥቃት በጸጥታ አካላት ላይ ተፈጽሟል ስለሚባለው እስካሁን የጠራ መረጃ የለኝም። ### Response:
### Text: የካንሰር ቀን️በኢትዮጵያ ያለው የካንሰር ህክምና ደካማነት የተነሳ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ዜጎች በበሽታው ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ፡፡ከቲቢ እና ወባ በሽታዎች ይልቅም በካንሰር ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡የበሽታው ስርጭትና የሚያደርሰው ጉዳት ከሌሎች ዓለማት ይልቅ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሀ አገራት ላይ ይበረታል ተብሏል፡፡ህሙማኑ የካንሰር ተጠቂ እንደሆኑ የሚያውቁት እጅግ ዘግይተው በመሆኑና ለህክምና አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ወደ ህክምና ተቋም መምጣታቸው ካንሰርን የመከላከል ስራ ፈታኝ እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል፡፡ዛሬ የጤና ሚኒስቴር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን የአለም የካንሰር ቀንን ምክንያት በማድረግ ባሰናዱት ምክክር ላይ ነው ይሄን የሰማነው፡፡በኢትዮጵያ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ሰዎች በካንሰር ይያዛሉ፡፡ በተመሳሳይ ሌሎች 65 ሺ ያህል ሰዎችም ይሞታሉ፡፡ለህክምና የሚሆኑ ግብአቶች አለመሟላት እና የህክምና ተቋማቱ አነስተኛ መሆን ካንሰርን ለመከላል የሚሰራውን ስራ ፈታኝ እንዲሆን እንዳደረገው የጤና ሚኒስትር ድኤታዋ ዶር ሊያታደሰ ተናግረዋል፡፡የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላትን ማስፋፋት ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ በ3 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላት ግንባታቸው እየተጠናቀቀ እንደሆነና የህክምና ግብአቶች እየተሟሉላቸው ነው መባሉን ተሰምቷል፡፡ምንጭ ሸገር 1021 ### Response:
### Text: የሰላም ዋጋ በሞቃዲሾ የሱማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ስታዲየም ለዓመታት ስፖርታዊየእግር ኳስ ጨዋታዎችን አያስተናግድም ነበር።በሀገሪቱ በነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት ፣ የሽብር ጥቃት የሱማሊያ የስፖርት እንቅስቃሴ ተደክሞ ነበር ታድክሞ ብቻ ሳይሆን ሞቶም ጭምር ነበር።ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን ሀገሪቱ በአንፃራዊነት እየተረጋጋች ፣ ሰላሟም እየተመለሰ ከእርስ በእስር ጦርነቱ እያገገመች ስትመጣ የስፖርት እንቅስቃሴው መነቃቃት ጀምሯል።የአሚሶም ወታደሮች መቀመጫ የነበረው የሞቃዲሾ ስታዲየም አሁን ላይ እድሳት ተደርጎለት ጨዋታዎችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል።ትላንት 65 ሺህ ህዝብ የታደመበት ታሪካዊ ጨዋታ ሞቃዲሾ ስታዲየም አስተናግዳል።ጨዋታው በሶማሊያ ፕሪሚየር ሪግ የሆርሴድ ክለብ እና የሞቃዲሾ ከተማ ክለብ መካከል የተደረገ ሲሆን ያለ ግብ በአቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።በሀገሪቱ ፕሪምየር ሊግ ግርጌ ላይ የሚገኙ ሁለቱ ክለቦች በሶማሊያ በርካታ ደጋፊዎች ያላቸው ናቸው።በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ ሞቃዲሾ ስታድዮም በመግባት ጨዋታውን የታደመው እንደአስታን ስፖርት መረጃ።ለጦርነት እና ለሽብር ጥቃት ከማንም ቀድመው የሚደርሱ፣ የሚዘግቡ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ይህን በጎ ዜና ለዓለም ህዝብ አልማድረሳቸው እንዳሳዘናቸው አንዳንድ የሱማሊያ ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲፅፉ ተመልክተናል። ### Response:
### Text: አሶሳ መናናቅ አያዋጣም ልክ እንደ በቆሎው ምሳሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐቢይ አህመድመናናቅ መጠላላት ትክክል የማይሆነው የሚናቅ ሰው የሚናቅ ማህበረሰብ ስለሌለም ጭምር ነው፡፡አሶሳ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ድንበር ጠብቋል፡፡ ድንበሩ ክፍት ከሆነ ወለጋ የለም ማለት ነው፡፡ሸዋ የለም ማለት ነው፡፡ መናቅ አይቻልም፡፡ኦሮምያ ተማምኖ የሚተኛው ወንድሞቼ ቤኒሻንጉል ህዝቦች ድንበር ይጠብቃሉ ብሎ ነው፡፡ቤኒሻንጉልም ወደመሃል ሃገር ሲያስብ ወንድሞቼ አሉ ብሎ ማሰብ አለበት፡፡በቆሎ በመጠንዋ ከጤፍ ከፍ ትላለች፡፡ከፍ ስለምትል ጤፍን ትንቅና አሁን ሰው በከንቱ ይለፋል እንጂ ጤፍ ምን ዱቄት ከማህፀኑ ይወጣል ተብሎ ነው ወፍጮ ቤት የሚላከው ትላለች፡፡በቆሎ መጠንዋ ተለቅ ተለቅ ስለሚል እስዋ ስትፈጭ ዱቄት ስለሚገኝ ጤፍ ሲፈጭ ዱቄት የማይገኝ ነው የሚመስላት ግን አንድ ኩንታል በቆሎና አንድ ኩንታል ጤፍ ወፍጮ ቤት ከሄዱም በኋላ የተሸለ ዱቄት የሚገኘው ከጤፍ ነው፡፡መናናቅ አያዋጣም በሆነ በሆነ ነገር ማለት ነው፡፡ በከለር በሃይማኖት በሳይዝ አንዱ አንዱን ቢንቅ ኪሳራ ነው፡፡ ለዚህ ነው እንደመር እያልን ያለነው፡፡ስንደመር እንጠነክራለን ስንደመር እንበዛለን ስንደመር ሃይል ይኖረናል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት በአሶሳ ከህብረተሰቡ ጋር በተወያዪበት ወቅት የመደመርን አስፈላጊነት የገለፁበት ምሳሌ፡፡ሚያዚያ 232010 ዓም ### Response:
### Text: ለፋሲል ግቢ የተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈፃሚ አመራር በሙሉ ጉዳዩ ከቤንሻንጉል ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የገንዘብ ድጋፍ እንድናደርግ ስለመጠየቅ ይመለከታልከላይ በርእሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በያዝነው አመት ከቤንሻንጉልጉሙዝ ክልል የአማራ ብሄር ተወላጆችን ማእከል ባደረገ መልኩ ዜጎች ለዘመናት ሀብታቸውን ካካበቱበት ቀዬአቸው ተፈናቅለው በባህርዳር ቅዱስጊዬርጊስ ቤተክርስቲያን በጊዜያዊነት ተጠለው ይገኛሉ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የግቢያችን መምህራኖች በቅርቡ ገንዘብ አሰባስበው ከ50 ሺህ ብር በላይ መለገሳቸው ይታወቃል። ይህንን የተቀደሰ ስራ ወደ ተማሪው በማውረድ ለወገናችን አጋርነታችንን በተግባር ለማሳየት ያመቸን ዘንድ ጊዜያዊ ኮሚቴ በግቢያችን ከተቻለም በአምስቱም የጎንደር ዩኒቨርስቲ ግቢዎች በማዋቀር ገንዘብ የሚሰበሰብበትን መንገድ በመንደፍ ወደ ስራ ለመግባት ያስችለን ዘንድ የተማሪዎች ህብረት እውቅናውን በመስጠትና ኮሚቴውን በማዋቀር አስፈላጊውን ትብብር ያደርግልን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው ከሰላምታ ጋር የፋሲል ግሩፕ አድሚን ግልባጭ️ለተማሪ አንዷለም ሙሉ የፋሲል ግቢ ተማሪ ህብረት ፕሬዝዳንት️ለተማሪ ተመስገን ስመኝ የፋሲል ግቢ ተማሪ ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት️ለተማሪ አቤኔዘር ተፈሪ የፋሲል ግቢ ተማሪ ህብረት ህዝብ ግንኙነት 222 ጎንደር ዩኒቨርሲቲኢትዮጵያ ### Response:
### Text: የፅዳት ዘመቻበኢትዮጵያ የፊታችን እሁድ በሁሉም ከተሞች፣ መንገዶች እና ሰፈሮች የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል፡፡የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በትናትናው እለት ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ሚያዚያ 6 ቀን 2011 በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል፡፡ይህ የፅዳት ዘመቻ በመላ ሀገሪቱ እሁድ ጠዋት 1፡ 30 ጀምሮ እስከ ሶስት እንደሚካሄደ የወጣው መርሃ ግብ ያመለክታል፡፡የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ባስተላለፈው ጥሪ የምናጸዳው በክብርና በንጹሕ አከባቢ መኖር መብታችን እንደሆነ ስለምናምን ነው ብሏል፡፡ፅህፈት ቤት የምናጸዳው ለጤናችን ነውማጽዳትም ኃላፊነታችን ስለሆነ ሲል ጥሪ አቀርቧል፡፡ለኢትዮጵያ ጽዳት በአንድነት እንነሳ በማለት ጥሪ ይስተላለፈው ፅህፈት ቤቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለአካባቢ ፅዳት በአንድነት መነሳት እንዳለባቸው ጠቁሟል፡፡በትናትናው ዕለት መልካም አስተሳሰብን ለመስበክ የሚያግዝ የጽዳት ዘመቻ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚካሄድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሀገሪቱ በሚከሰተው የጸጥታና ተያያዥ ችግር ሣምንትን ያለ ክፉ ዜና ማለፍ እየከበደ መጥቷል ብለዋል፡፡በመሆኑም ችግሮችን ባሉበት ለማቆምና እንዳይዛመቱ ለማስቻል ቀና ማሰብ ስለሚያስፈልግ በመጪው እሁድ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የጽዳት ዘመቻ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡ ### Response:
### Text: 37 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ️ባለፈው ቅዳሜ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል ሊካሄድ በነበረው ጨዋታ ላይ ግጭት እንዲፈጠር በማነሳሳት የተጠረጠሩ 37 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ደስታ ዳንጊሶ ጉዳዩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።ሃላፊው በመግለጫቸው የራሳቸውን ፖለቲካዊ አጀንዳ የሚያራምዱ አካላት በሸረቡት ሴራ በዕለቱ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።በተፈጠረው ግጭትም በአንዲት ሴት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ሆስፒታል እንደምትገኝና 17 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።ከዚህ ባለፈም የ10 መኪናዎች መስታወት ሙሉ በሙሉ የተሰባበረ ሲሆን አንድ ግሮሰሪ ላይም ዘረፋ ተፈጽሟል ነው ያሉት።ግጭቱ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት በመቀናጀት ባደረጉት ርብርብ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉንም አንስተዋል።ስለሆነም መገናኛ ብዙሃን የተከሰተውን ችግር ከማጋነንና የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል የሚደረገውን ጨዋታ ጨምሮ ሀዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ታውቋል። ### Response:
### Text: ለከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በተጋነነ ዋጋ የሚገዛው ሞባይልና ላፕቶፕ ኮምፒውተር ህገወጥ ነው ለአንድ ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ እስከ መቶ ሺህ ብር ግዢ ተፈጽሟልለከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተጋነነ ዋጋ ተንቀሳቃሽ ስልክና ላፕቶፕ ኮምፒውተር የሚገዙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የግዥን መመሪያና ህግ እየጣሱ በመሆኑ ህገ ወጥ መሆናቸውን የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ለአንድ ባለስልጣን አንድ ስልክ እስከ መቶ ሺ ብር ግዥ መፈጸሙንም ገልጿል።የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት ለተቀላጠፈ ሥራ በሚል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተመላሽ የማይሆን ተንቀሳቃሽ ስልክና የላፕቶፕ ኮምፒውተር ግዥዎችን ፈቅዷል፡፡ይሁን እንጂ መመሪያውን ተፈፃሚ ለማድረግ የእቃዎች ደረጃ፣ የገንዘብ ጣሪያና በጥቅል ተገዝተው ይከፋፈሉ ወይስ በየመስሪያ ቤቱ ይገዙ የሚሉና ተጨማሪ ዝርዝር መመሪያዎች ስላልተወሰኑ ምንም አይነት ግዥ እንዳይካሄድ ለሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤትና ለተጠሪ ተቋማት ኤጀንሲው በደብዳቤ ማሳወቁን ገልፀዋል፡፡ነገር ግን ለአንድ ባለስልጣን አንድ ስልክ እስከ መቶ ሺ ብር በማውጣት ግዥዎች እንደተፈፀሙ መስማታቸውን ገልፀው ይህ አይነት እንቅስቃሴ ለግል ጥቅም ሲባል የሚደረግ በመሆኑ ህገ ወጥ ነው ብለዋል፡፡ ### Response:
### Text: ኢህአዴግ የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባውን በሚቀጥለው ሳምንት ያካሄዳል። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሶስት ብሄራዊ ድርጅቶችን የግምገማ ሪፖርትን በዝርዝር መመልከቱን ገለፀ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በታህሳስ ወር ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች አፈፃፀም ላይ በዝርዝር የሚያደርገውን ግምገማ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለኢቢሲ እንዳስታወቁት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በታህሣስ ባካሄደው የ17 ቀናት ስብሰባ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ብሄራዊ ድርጅቶች በስራ አስፈፃሚና በማዕከላዊ ኮሚቴ ደረጃ ባካሄዱት ግምገማ ሪፖርትና የተሃድሶ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ በዝርዝር እየፈተሸ ነው፡፡በእስካሁን ቆይታ የሶስት ብሄራዊ ድርጅቶችን የግምገማ ሪፖርት በዝርዝር አይቶ እንደተቀበለው ገልፀዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ደግሞ በቀሪው ብሄራዊ ድርጅት ሪፖርት ላይ የሚያደርገውን ውይይት እንደሚያጠናቅቅ ተናግረዋል፡፡ይህን ጨምሮ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በተለያየ ደረጃ ያቋቋማቸው ኮሚቴዎች የስራ እንቅስቃሴን በመገምገም ለኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትም ይመለከታል ነው ያሉት፡፡ ይህን ተከትሎም በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባውን በማድረግ ሪፖርቱን ከገመገመ በኋላ የተፈጠረውን የአመራር ክፍተት እንደሚያሟላም አስታውቀዋል፡፡ምንጭ ### Response:
### Text: አዲስ አበባ️በአዲስ አበባ በካርቶን የታሸገ 3 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና 61400 የአሜሪካ ዶላር በነሐሴ ወር 2010 ዓም መያዙን የከተማይቱ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የቻይና ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች ከቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን በየቀኑ ማታ ማታ በካርቶን የታሸጉ ብሮች ያወጡ እንደነበር ከአስራ አምስት ቀን በላይ ከፈጀ ጥብቅ ክትትል በኋላ ፖሊስ ደርሶበታል፡፡ነሀሴ 28 ቀን 2010 ዓም ምሽት ላይ መነሻዋን ከቦሌ ሻላ ያደረገች ፕራዶ መኪና ወደ ቦሌ ሩዋንዳ ታመራለች፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የክትትልና ኦፕሬሽን ክፍል አባላትም መኪናዋን በቅርብ ርቀት መከታተል ይጀምራሉ፡፡ፕራዶዋ ቦሌ ሩዋንዳ ከአንድ ሰዋራ ቦታ ትደርስና ከአንዲት ነጭ ዶልፊን መኪና አጠገብ ትቆማለች፡፡ከዚያም ከፕራዶዋ ውስጥ የነበሩት ተጠርጣሪዎች በካርቶን የታሸጉት የገንዘብ ኖቶችን ወደ ዶልፊነኗ ሲያዛውሩ በክትትል ቡድኑ በቁጥጥር ስር ይውላሉ፡፡በዕለቱ በቁጥጥር ስር የዋሉት ቀደም ሲል የተጠቀሱትና የቻይና ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦችና አንድ ኢትዮጵያዊ ግብረአበራቸው በድምሩ 3 ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡ተጠርጣሪዎቹ በወቅቱ ለክትትል ፖሊስ አባላቱ 2 ሁለት ሚሊየን ብር እንስጣችሁነና ልቀቁን ሲሉ ተማፅነዋቸዉ የነበረ ቢሆንም የፖሊስ አባላቱ ግን ቀጥታ ጉዳዩን ለኃላፊዎቻቸው በመንገር ከእነ ኤግዚቢቱ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተነግሯል፡፡© ### Response:
### Text: ወንጀል ነክ መረጃ️የስራ ባልደረባውን የገደለው የፖሊስ አባል በጽኑእስራት ተቀጣ፡፡ በጋምቤላ ክልል ልዩ ቦታው ደንቦስኮ በተባለው አካባቢ ከምሽቱ 3፡00 በስናይፐር ጠመንጃ ተኩሶ የስራ ባልደረባውን የገደለው የፌዴራል ፖሊስ አባል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው 3 ክስ በእስራት ተቀጣ፡፡ተከሳሽ ወንጀል ህግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ በ1ኛ እና በ2ኛ ክስ ተከሳሹ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሲሆን ከሌሎች አስራ ሁለት አባላት ጋር ለግዳጂ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ሙኒ ከተባለ ቦታ የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ ለማደር ተገኝው ባሉበት ወቅት ሰው ለመግደል አስቦ በስናይፐር ጠመንጃ ተኩሶ ሁለት የስራ ባልደረቦችን አንደኛውን ሆዱ እና ሁለተኛውን ጭንቅላቱ ላይ በመምታት ደም ፈሷቸው ህይወታቸው እንዲያልፍ በማድረጉ እና በ3ኛ ክስ ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት በሌላ ሰው አካል ወይም ጤና ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ 3ኛውን የስራ ባልደረባውን ተኩሶ ግራ ታፋውን በመምታት እንዲቆስልና የህመም ስሜት እንዲሰማው በማድረጉ በፈጸመው አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሷል፡፡ዐቃቤ ህግም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎትም ጥር 7 ቀን 2011 ዓም በዋለው ችሎት በ19 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በማለት ወስኗል፡፡ምንጭ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ### Response:
### Text: ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ በድርጊቱ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸውበባህርዳርና አዲስ አበባ ከአማራ ክልል አመራሮችና ከእነ ጀነራል ሰዓረ መኮንን ግድያ ጋር በተያያዘ በወንጀል ድርጊቱ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው። የጀነራል ሰዓረ ጥበቃ የነበረው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡን ጨምሮ 13ቱም ተከሳሾች ዛሬ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ እየተነበበላቸው ነው።ተጠርጣሪ ተከሳሽ አስር አለቃ መሳፍንት ችሎቱ የሚጠይቀውን ምላሽ መስጠት እንዳልቻለና እሺ እና አዎ የሚሉ ምላሾችን ብቻ እንደሚሰጥ ኢቢሲ ከችሎቱ ቦታ ዘግቧል።ችሎቱ መናገር ካልቻልክ ሀሳብህን በፅሁፍ ግለፅ ቢለውም ተከሳሹ ይህንንም አለመቻሉ ተመልክቷል።ከሰኔ 15ቱ ወንጀል ጋር በተያያዘ ባህርዳር ላይ የአማራ ክልል አመራሮች አቶ አምባቸው መኮንን፣ አቶ ምግባሩ ከበደና አቶ እዘዝ ዋሴ ሲገደሉ እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ደግሞ የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጀነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ መገደላቸው ይታወሳል።ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ከተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች መካከል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ይገኙበታል። ዓቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ ህገ መንግስትን በኃይል ለመናድ በሚል ነው ክሱ የመሰረተባቸው። ### Response:
### Text: በአሜሪካ ኒውዮርክ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰርና ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ከሰሞኑን የኮሮና ቫይረስ ይዟቸው እንዳገገሙ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ከሰሞኑን ዶክተር ፅዮን ፍሬውን በተለያዩ ጉዳዮች አነጋግሮ ነበር። ዶክተር ፅዮን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፈዋል በሽታው ስር ሳይሰድ በፊት መንግሥት እና የሚመለከታቸው ተቋሞች ጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚያወጧቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች መከተል ይገባል።ሰው አላግባብ መደንገጥ ሳይሆን የሚነገረውን ማድረግ አለበት በማኅበራዊም ይሁን በማንኛውም ጉዳይ አትሰብሰቡ እየተባለ ሰው መሰብሰብ ካላቆመ በሽታው ይስፋፋል።በተለይም በአሁን ወቅት መዘናጋት ትክክል አይደለም። የምናውቀው ሰው እስኪሞት መጠበቅ የለብንም ቁጥሩ 40 ሺህ ወይም 60 ሺህ እስኪደርስ መጠበቅ የለብንም። በጣም የምወደው ሰው ከዚህ በሽታ ሊሞት ይችላል ብለን እናስብ።መዘናጋት በበሽታው የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ከፍ ከማድረጉም ባሻገር ቫይረሱ ስጋት የሚሆንበትን ጊዜም እንደሚያራዝመው ያስረዳሉ።በተጨማሪም ቤት መቀመጥና እጅ መታጠብን የመሰሉ ተግባሮች ቀላል ቢመስሉም የበርካቶችን ሕይወት ይታደጋሉ። ### Response:
### Text: ችሎትበፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ0 ከአራተኛ እስከ 14ኛ0 የተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች የኮቪድ19 ምርመራ ተደርጎላቸው ነፃ መሆናቸውን የሚገልፅ ውጤት ለፍርድ ቤቱ ቀርቧል።ከዚህ በፊት አቶ ጃዋር መሀመድና አቶ በቀለ ገርባ ከጓደኞቻቸው ጋር መገናኘት አልቻልንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ፍርድ ቤቱ በጓደኛ የመጠየቅ0 መብት ቢኖራቸውም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚከለክል በመሆኑ አልተቀበለም።አንደኛ ተጠርጣሪ የሆኑት አቶ ጃዋር መሃመድ ከልጄ እና ከባለቤቴ ጋር በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንድገናኝ ይፈቀድልኝ0 ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ በሳምንት ሁለት ጊዜ በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንዲገናኙ አዟል።12ኛ ተጠርጣሪ የሆኑት አቶ ሸምሰዲን ጣሃ ጆሮዬን ታምሚያለሁ የተሻለ ሆስፒታል ልታከም0 ብለው አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤት በመረጡት ሆስፒታል እንዲታከሙ እንዲመቻችላቸው አዟል።ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ ቀሪ ምስክሮችን ለማድመጥ ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ኤፍ ቢ ሲ ### Response:
### Text: ፍርድ ቤቱ ሀያት ቲቺንግ ሆስፒታልን በነፃ አሰናበተ የሸማቶች ጥበቃ እና የንግድ ውድድር ባለሥልጣን አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የሀያት ቲቺንግ ሆስፒታል የቀድሞ ባለቤቶች የአክሲዮን ድርሻቸውን ለሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት ድንቁ በያሳ እና ወላጅ እናታቸው ዳንሳ ጉርሙ መሸጣቸው ሕገወጥ ውሕደት ነው በሚል ከቀረበባቸው ክስ ኅዳር 282011 በነፃ አሰናበታቸው።ግንቦት 262011 የተመሰረተው ክስ እንደሚያስረዳው ዳንሳ ጉርሙ ከፍተኛውን አክሲዮን በመያዝ ድርጅቱን የገዙ ሲሆን ይህ ውል እንደ ውህደት ይቆጠራል በሚል የባለሥጣኑ ነገረ ፈጆች አቤቱታቸውን አሰምተው ነበር።ሀያት ሆስፒታል ኅዳር 282011 ዓም ከባለአክስዮኖቹ ጋር ባካሔደው ጠቅላላ ጉባዬ ላይ ባለአክሲዮኖቹ ኢብራሂም ናኦድ እና ልጃቸው አሕመድ ኢብራሂም ድርሻቸውን ለመሸጥ ውሳኔ አሳልፈዋል። በዚህም መሰረት ባላአክስዮኖቹ ያደረጉትን የአክስዮን ግብይት ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ ነበረባቸው ሲሉ የባለሥልጣኑ ነገረ ፈጆች ክሳቸውን መመስረታቸው ይታወቃል።ነገረ ፈጆቹ በባለሥልጣኑ ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት ማንኛውም ዓመታዊ ሽያጩ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የንግድ ድርጅት ውህደት ከመፈፀሙ በፊት ለባለሥልጣኑ በማሳወቅ ባለሥልጣኑ በሸማቾች መብት እንዲሁም በፍትሐዊ ገበያ ውድድር ላይ ያለውን ጫና በማጥናት ፈቃድ ባልሰጠበት ሁኔታ መዋሐድ ሕገወጥ ነው በማለት ተከራክረዋል።ተጨማሪያ ንብቡ 09092 ### Response: