text
stringlengths
707
989
### Text: ሜጀር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴሜጀር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴ ገማሪያም የአብዬ ጊዚያዊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጦርሀይልአዛዥ ሆነው መሾማቸውን የተባበሩት መንግስታት ሴክሬታሪ ጄኔራል አንቶኒ ጉቴሬዝ አስታወቁ፡፡ ሜጀር ጄኔራል መሀሪ እንደ እኤአ በሚያዝያ 23 2019 የስራ ጊዚያቸውን የሚያጠናቅቁትን ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሃና ወልደዝጉን ተክተው ይሰራሉ ተብሏል፡፡ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለተሰናባቹ ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሃና ደከመኝ ሳይሉ ላደረጉት አገልግሎትና በተመድ ለነበራቸው...
### Text: የገዛ ባሏን በመርዝ የገደለችው ተከሳሽ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቷን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ አቶ ዋቁማ ጡሪ እንዳስታወቁት በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ ውስጥ በምትኖረው ተከሳሽ ወይዘሮ እልፍነሽ በቀለ ጅራታ ላይውሳኔው የተላለፈው ባሏን አቶ አዳነ አሰፋውን በመርዝ መግደሏ በመረጋገጡ ነው።ሟች ከኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር ከተበደሩት 86ሺህ ብር ውስጥ 10ሺህ ብር እንዲሰጣት ...
### Text: የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ ተጠናቀቀ==================================የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት 10 ቀናት ከሰኔ 28 እስከ ሐምሌ 072011 ዓም በአገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ የፖለቲካና የጸጥታ ሁኔታዎች እንዲሁም አዳዲስ ክልል ሆኖ የመደራጀት ጥያቄዎች ላይ ሲያካሄድ የነበረውን ስብስባው በስኬት አጠናቋል፡፡ ማእከላዊ ኮሚቴው አገራችን አሁን ያለችበትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት...
### Text: ግብፅ️ግብፅ ከ5 ሺህ በላይ ተከታይ ያላቸው እና የሀገርደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ይዘቶችን የሚያሰራጩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲዘጉ የሚያስችል ህግ ይፋ አደረገች፡፡የግብፅ የመገናኛ ብዙሃንን የሚቆጣጠረው አካል ይፋ ያደረገው ይህ አሰራር በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ከፍተኛ የሆነ ገደብ እንዳላው ነው የተነገረው፡፡አዲሱ ህግ የሀገሪቱ ከፍተኛው የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካል ሀሰተኛ ዜናዎችን የሚያሰራጩ አካላትን ለማገድ እንደሚያሰችለውና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከ 14...
### Text: ህይወት ለማዳን ሲሉ ህይወታቸው ያለፈው የሩሲያ ሚኒስትር የሩሲያው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ሚኒስትር የሰውን ህይወት ለማዳን ሲሞክሩ ህይወታቸው አለፈ።የሩስያ አስቿኳይ ጊዜ ሁኔታ ሚኒስትር ህይወታቸው ያለፈው በኖርልስክ አርክቲክ ከተማ አቅራቢያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚደረግበት ጊዜ ሕይወት የማዳን ኃላፊነታቸው ሲወጡ ነው ተብለዋል፡፡ሚኒስትሩ ኢቭጂኒ ዚኒቺቭ ህይወትን ለማዳን በቁፋሮ ስራ ላይ ሳሉ ለሞት የሚዳርግ አደጋ እንዳጋለጠቸውንም ነው የተገለጸው። መስርያ ቤታቸውም ዚኒቺቭ የአንድን...
### Text: ደቡብ ክልልበደቡብ ክልል እየተነሱ ያሉ የአደረጃጀት ጥያቄዎችን በተመለከተ ሳይንሳዊ ጥናት ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ጥናቱን የሚያከናውነው ፎረም አስታወቀ።ላለፉት ሶስት ወራት ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው ፎረሙ በቀጣዮቹ አስር ቀናት መረጃ ሰብሳቢዎች ወደ ስራ ይገባሉ ብሏል።ፎረሙ ጥናቱን ከአራት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለክልሉ መንግስት እንደሚያቀርብም ነው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ያስታወቀው።ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እና የሙያ መስኮች የተውጣጣ 20 አባላት ያለው የጥናት ...
### Text: ሀገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ የተወሰደባቸውን እና እጅ የሰጡ የህወሓት ቡድን አባላት ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል ኮሌኔል የማነ ገብረሚካኤልን ኮሎኔል አለም ገብረመድህን፣ ኮሎኔል ቢንያም ገብረመድህን፣ ኮሎኔል አምባዬ፣ ኮሎኔል ማሾ፣ ኮሎኔል ይርጋ ስዩም፣ ኮሎኔል ሃዱሽ፣ ኮሎኔል አጽብሃ፣ ኮሎኔል ተስፋዬ ገብረመድህን፣ ኮሎኔል ዮሃንስ ካልአዩ፣ ኮሎኔል ተክለእግዚአብሄር፣ ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኔ ቶላ እና ሌሎች በስም ያልተገለጹ 4 ኮሎኔሎች እና...
### Text: ስቴም ፓወር ፣ ቪዛ እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ የተሳተፉ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች የምርቃ መርኃግብር ተካሂዷል።ስልጠናውን ከተከታተሉ 200 ሰልጣኞች ውስጥ በአጠቃላይ 70 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ለመጨረሻው ዙር ከደረሱ 20 ፕሮጀክቶች በአራት ዘርፎች ለአራት አሸናፊዎች የ25000 ብር በድምሩ የ100000 ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።አሸናፊዎቹ በግብርና፣ በጤና፣ በኢንጂነሪንግና በአገልግሎ...
### Text: ቁጥራዊ መረጃከ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሪፖርት ️ በ2021 በመላው ዓለም 591 ሚሊዮን ተፈናቃዮች ተመዝግበዋል ይህ ቁጥር በታሪክ ከፍተኛው ነው። ከ591 ሚሊዮኑ መካከል 532 ሚሊዮን በግጭት እና ሁከት 59 ሚሊዮን በተፈጥሯ አደጋዎች የተፈናቀሉ ናቸው። ኢትዮጵያ ️ በ2021 በኢትዮጵያ ግጭት እና ሁከት ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ይህ ቁጥር ከቀደመው ዓመት በ3 እጥፍ ይበልጣል። ️ በኢትዮጵያ የተመዘገበው የተፈናቃዮች ቁጥር በአንድ አገር ውስጥ ከዚህ ቀደም ከተመዘ...
### Text: የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት ነው የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴርየጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ወደ አፋር ክልል በመግባት ጉዳት አደረሰ በሚል የሚሰራጨው ወሬ ሐሰት ነው ሲል የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ።የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዥር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።በተለያዩ የማሕ...
### Text: አዲስ ለሚገነባው የሀዲስ አለማየው ልዩ አዳሪ ትምህርት ዛሬ ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እየተካሄደ ይገኛልበአንጋፋው ደራሲ ዶር0ሀዲስ ዓለማየሁ ተሰይሞ በትውልድ መንደራቸው በደብረማርቆስ ከተማ በ100000 ካሬ ሜትር ላይ ሊገነባ የታሰበውና 2000 የሚያህሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ለተባለለት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ማስገንቢያ አስመልክቶ ዛሬ በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ዝግጅቱን በንግግር የከፈቱት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒ...
### Text: የአየር ጥቃት ተፈፅሟል ኦነግ️ዕሁድ ጠዋት የሀገር መከላከያ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የኦነግ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰንዝሯል የሚል መረጃ በስፋት ተሰራጭቶ ነበር።የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ገመቺስተመስገን በጉዳዩ ላይ የአማርኛው አገልግሎት አስተያየታቸውን ጠይቆ ይህ መረጃ እስካሁን አልደረሰኝም። በምዕራብ ኦሮሚያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ይንቀሳቀሳል። በተለያዩ አጋጣሚዎችም ከኦነግ ሠራዊት ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል። ዕሁድ ዕለት የአየር ጥቃት...
### Text: ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ በሰው እና በቤቶች ላይ ጉዳት ደረሰ።በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ፑኩሙ ቀበሌ ንፋስ ቀለቀቅሎ በጣለ ዝናብ በርካታ ቤቶችና ሰው ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ፡፡የፑኩሙ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ጆን ኡጁዋቶ እንዳሉት በቀን 042013 ዓም ከምሽቱ 5 አካባቢ ንፋስ ቀላቀሎ በጣለው ዝናብ በቀበሌው ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡በደረሰው ጉዳትም 55 የቆርቆሮና 20 የሳር ቤቶች በድምሩ 75 መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ትምህርት ቤትን ጨምሮ አራት የመንግስት...
### Text: የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫው ወቅት አማራ ክልል ፖሊስ ከሚሽን እንዳስታወቀው በኦፕሬሽን እና በሕዝብ ትብብር 218 የሚሆኑ የብርጋዲዬር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ጥቃት ተባባሪዎች ናቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ 113 ያህሉ በቀላል ደረጃ የተጠረጠሩ በመሆኑ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጣቸው የገለጹት የአማራ ክልል ፖሊስ ...
### Text: ሼር የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች 19 በትኩሳት እና ደረቅ ሳል ይጀምራል። ከሳምንት በኋላ የመተንፈስ ችግር ያጋጥማል። በበሽታው የተያዘ ሰው እስከ 14 ቀናት ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች የበሽታ ምልክት ሳያሳዩ በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ኮሮና ቫይረስ መድሃኒት አለው ቫይረሱን ከሰውነት ውስጥ የሚያስወግድ መድሃኒት የለም። ሃኪሞች በሽተኞችን እያከሙ የሚገኙት የታማሚዎችን የበሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ በማድረግ ነው። ለመተንፈስ የ...
### Text: የየካቲት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 206 ሆኖ ተመዘገበ።የጥር ወር አጠቃላይ ግሽበት 192 ነበረ በየካቲት ወር የ4 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ 206 በመቶ መድረሱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ0ገልጿል።የየካቲት ወር ምግብ ዋጋ ግሽበት0 ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ228 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።በእህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው ወርም የቀጠለ ሲሆን ለምግብ ዋጋ ግሽበት መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ኤጀንሲው ገልጿል። በተጨማሪም አትክልትና...
### Text: የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ ሰኔ 23፣ 24 እና 25 ቀን 2013 ዓም በፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በእስር የሚገኙትን በቃሉ አላምረው፣ ያየሰው ሽመልስ፣ ፋኑኤል ክንፉ፣ አበበ ባዩ፣ መልካም ፍሬ ይማም፣ ፍቅርተ የኑስ፣ ዊንታና በርሄ እና ምህረት ገብረክርስቶስን ጨምሮ 21 የኢትዮፎረም እና የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኞችና ሰራተኞች አያያዝ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በቅርበት ሲከታተል መቆየቱን ገልጿል።ከእነዚህ ታሳሪዎች መካከል ሦስቱን እና አን...
### Text: ጥንቃቄ ለቲክቫህ ቤተስብ አባላት የተለያዩ ገንዘብ የማግኛ ሀብት ማፍሪያ መንገዶች እየተባለ በዲጅታል ሚዲያው በኩል ከቀርብ ጊዜ ወዲህ በርካቶች እጅግ በስፋት እየተከሰቱ ነው።እነዚህ አካላት ፍቃድ ይኑራቸው አይኑራቸው የመስሪያ አድራሻቸው ይታወቅ አይታወቅ ፣ የሚመራቸው የሚያስተባብራቸው ግለሰብ ይኑር አይኑር የሚለውን በግልፅ ለማወቅ አዳጋች ነው።ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከዚህ በፊትም እንዳልናችሁ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችል እንቅስቃሴ ውስጥ ስትገቡ ኢንቨስት ስታደርጉ...
### Text: ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የዜጎች ግድያ፣ የአካል ማጉደል ፣ መፈናቀል ብሎም የሃይማኖት ተቋማት ማውደምና የንብረት ማጋየት ወንጀል ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈጸመበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አመለከተ። ተቋሙ አክሎም በአደባባይ የሕግ የበላይነትን የተገዳደረ ድርጊት መሆኑንም አስታውቋል።ድርጊቱ እጅግ አስደንጋጭ ፣ አሳዛኝና አስቆጭ እንደሆነበት ያመለከተው ኮሚሽኑ አጥፊዎች ገለልተኛ በሆነ መልኩ ጥናት ተደርጎ ለሕግ እንዲቀርቡም ጠይቋል። ይህ እንዲሳካም...
### Text: ቤቲንግ እንዲቆም ተወስኗል በሴቶች ህፃናት ወጣቶች ሚኒስቴር የወጣቶች ስብዕና ልማት ዳይሬክተር አቶ አለሙ ሰኢድ የስፖርት ውድድር ቤቲንግ እንዲቆም ተወስኗል። 26 አባላት ያቀፈ የፌደራል የአሉታዊ መጤ ልማዶችና አደንዛዥ ዕፆች ግብረ ኃይልና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ተሳተፊ የሆኑበት መድረክ በማዘጋጀት የስፖርት ውድድር በዜጎች ስነልቦና፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና አጠቃላይ የሚያደርሰውን ችግር ተፈትሿል። በጥር ወር ውስጥ ለስፖርት ውድድር በሚል ይሰጥ የነበረው ፍቃድ የቆመ ...
### Text: ባለስልጣኑ ስልጣን ሊለቁ የፈለጉበት ምክንያት ምንድነው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጠን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ በፍቃዳቸው ኃላፊነታቸውን እንደሚለቁ ገልፀዋል።ዋና ዳይሬክተሩ ከስልጣን ሊለቁ የፈለጉበት ምክንያት ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጀ ግን ሀሰት መሆኑን ኢብባ አሳውቋል።የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዱአለም በቅርቡ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ የተቋሙን ሰራተኞች ሰብስበው ተቋሙን እንደማይመሩና ኃላፊነታቸውን በፍቃዳቸውን ለመልቀቀ ...
### Text: በበይነመረብ እንዲያስተምሩ የተፈቀደላቸው የግል ተቋማት ቁጥር 5 መድረሱን ኤጀንሲው አሳወቀ።በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ በዋለው በበይነመረብ ትምህርት የእውቅና አሰጣጥ መመሪያ መሰረት ፈቃድ በበይነመረብ እንዲያስተምሩ የተፈቀደላቸው የግል ተቋማት ቁጥር 5 መድረሱን ኤጀንሲው አሳውቋል።ከዚህ ቀደም ኤጀንሲው ለ4 ተቋማት ፈቃድ የሰጠ ሲሆን አሁን ላይ ለሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ ኦፍ አድሚኒስትሬሽን የትምህርት መስክ በድህረምረቃ መርሃግብር በበይነመረብ የትምህርት አሰጣጥ ተማሪ ...
### Text: ሀገር አቀፍ የፆምና የፀሎት ምህላ አዋጅየኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዲሱን አመት በሰላም ለመቀበል ያለመ ለ5 ቀናት የፀሎት መርሐግብር አወጀ።የፀሎት መርሐግብሩ ከጷግሜ 1 እሰከ 5 የሚቆይ መሆኑም ተገልጿል። ጉባኤው አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ የሰላም ጥሪን በሚመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። አገሪቱ ያጋጠማት ወቅታዊ ችግር በይቅርታና በፍቅር እንዲፈታ የተለያዩ እምነት የሚከተሉ ዜጎች በየሐይማኖታቸው የልዩ ፀሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጉባኤው ጥሪ አቅርቧል።በሁለቱም ወገኖች...
### Text: ድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን️ኮማንደር አለሙመግራ የድሬ ዳዋ ከተማ 0አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።ኮማንደር አለሙ መግራ 0ከዚህ በፊት የከተማ አስተዳድሩ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር 0የነበሩትን አቶ ጌታቸው አስረስን በመተካት መሾማቸውን የድሬዳዋ ፖሊስ 0ኮሚሽን አስታውቋል።ኮማንደር አለሙ መግራ ለ26 አመታት በፖሊስ ሙያ በተለያየ ሃላፊነት የሰሩና ያገለገሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በአዳማ ፣ቢሾፍቱ ፣በሻሸመኔ ከተሞችና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች ፖሊስ አ...
### Text: በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ሞጣ ከተማ አስተዳደር ዛሬ አመሻሽ ላይ ከምሽቱ 130 ጀምሮ በከተማዋ በሚገኘው የታላቁ ጀሚዑል ኸይራት መስጂድና ሌሎች ሁለት መስጅዶች ላይ የማቃጠል ተግባር መፈፀሙ ተሰምቷል። ይህ አስደንጋጭ ድርጊት ከመፈፀሙ ቀደም ብሎ ፈፃሚዎቹ እና ምክንያቱ በግልፅ ባይታወቅም በጥንታዊው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ሙከራም ነበር ተብሏል። በአሁን ሰዓት በከተማይቱ ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማም ነው ከአካባቢው እየወጡ የሚገ...
### Text: የ2005 የ2080 ባለ3 መኝታ ተመዝቢዎች በ14ኛው ዙር የዕጣ አወጣጥ የከተማ አስተዳደሩ ቤቶች በቴክኖሎጂ ሆነ በማኑዋል ዕጣ የማውጣት ሂደቶች በሚፈጠሩ ችግሮች ሊወጣለት ከሚገባው ባለእድለኛ ወጪ ለሌላ ለማይመለከተው አካል እንዳይተላለፉ የሄደበትን ርቀት እናደንቃለን፡፡ ነገር ግን ይህ ቁርጠኝነት በባለ3 መኝታ 2005 ዓም የ2080 ተመዝቢዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲገለጽ እንፈልጋለን፡፡ በቅርቡ የተሰረዘውን የ14ኛው ዙር የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓትን አስመልክቶ በዋዜማውና ከዛ በኋ...
### Text: የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረት የ2012 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእርቅ ሳምንት አውጇል የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረት የ2012 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእርቅ ሳምንት አወጀ። የእርቅ ሳምንቱ ከመስከረም 9 እስከ መስከረም 22 2012 ዓም ድረስ የሚቆይ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።የእርቅ ሳምንቱ የታወጀው በ2012 ዓም መስከረም 24 እና 25 በተከታታይ በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ የሚከበሩ የ...
### Text: የኮቪድ19 ስርጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ ትላንት በዓለም አቀፍ ደረጃ 649149 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 10206 ሰዎች ሞተዋል። ህንድ ውስጥ ትላንት 366499 ሰዎች በኮቪድ19 ሲያዙ 3748 ሰዎች ሞተዋል። ብራዚል ትላንት 34162 ዜጎቿ ለበሽታው ተጋላጭ መሆናቸውን እና 934 ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን ሪፖርት አድርጋለች። ትላንት ከፍተኛ ሞት የተመዘገበባቸው ሀገራት ስንመለከተ ኮሎምቢያ 495 አርጀንቲና 283 ሩሲያ 334 ቱርክ 283 ይገኙበታል። የአፍሪካ አቀፍ የኮሮና ...
### Text: አብይ ነጥቦች ዶር አብይ በህተምቤት ካቀረቡት ንግግር ውስጥ ወቅቱ ከስህተታችን ተምረን ህዝባችንን የምንክስበት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ማህፀነ ለምለም ናት ችግሮቻችን ተለያይተን ቀርቶ ተባብረን ለመፍታት ዘመናትን ይወስዱብናል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ያስተማረን ችግሮቻችንን ወደተሻለ ዕድል መለወጥን ነው፡፡ ማንነታችን እንዳይለያይ ሆኖ የተሰናሰለ እንዳይነጣጠል ሆኖ የተገመደ የተዋደደ እና የተዋሃደ ነዉ፡፡ አንድነት የማይፈታው ችግር የለም አንድነት ማለት ግን አንድ አይነትነት ማለት አይደለም፡፡ ነፃነት...
### Text: የትግራይ ዲያስፖራ ፌስቲቫል2ኛው ዓለምቀፍ የትግራይ ዲያስፓራ ፌስተቫል ለመካሄድ የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል፡፡ፌስቲቫሉ በተለያዩ የዓለም ሃገራት የሚገኙ የትግራይ ዲያስፓራ ማህበረሰብ በክልሉ ብሎም በሃገራቱ እየተከናወኑ ባሉት የሰላም የዴሞክራሲና የልማት ስራዎች ተሳታፊ ለማድረግ ያለው ነው ተብሏል፡፡በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የከተማ ልማትና ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶር አብርሃምተከስተ ዝግጅቱን አስመልክቶ ...
### Text: የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጅማአባጅፋር የእግር ኳስ ክለብን ከማንኛውም ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ማገዱን አስታወቀ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለ እንዳስታወቀው ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ ከየካቲት 29 2011 ጀምሮ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ላይ ታግዷል። እንደ ፌዴሬሽኑ ገለጻ ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ የታገደው አብዱልፈታህ ከማል ለተባለው ተጫዋቹ ተገቢውን ክፍያ ባለመፈፀሙ ነው። አብዱልፈታህ ከማል የተባለው የእግር ኳስ ተጫዋች ከ...
### Text: ትናንት ቅዳሜ ምሽት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ ሁለት ተማሪዎች መሞታቸው ተነገረ። ያነገውራቸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና መምህር የብሄር መልክ በያዘው ግጭት የሁለት ተማሪዎች ህይወት ማለፉን እና በርካቶች መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል።በዩኒቨርሲቲው መምህር የሆኑት የቢቢሲ ምንጭ ትናንት ምሽት በተፈጠረው ግጭት ሁለት ተማሪዎች መሞታቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲው ደውለው መስማታቸውን ተናግረዋል።የሆስፒታል ምንጮች እንደጠቆሙት ደግሞ ወደ ወልዲያ ጄኔራል ሆስ...
### Text: የትምህርት ሚኒስትር ፕር ብርሃኑ ነጋ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ምክክር አደረጉበምክክር መድረኩ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትርፍ ባለፈ ማህበረሰቡን ማገልገል እንዳለባቸው ተገልጿልየትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በትምህርት ዘርፉ ላይ ካሉ የግል ተቋማት ጋር ግልፅ መናበብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።ሚኒስትሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግስት ላይ የሚያነሱትን ቅሬታዎችን እንዲሁም ህብረተሰቡ በተቋማቱ ላይ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች እና ...
### Text: የዋጋ ጭማሪ የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ እንደሆነ ታወቀ፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በምርቶቹ ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርጎ ማከፋፈል መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡በአገሪቱ ውስጥ ቢራ ፋብሪካዎች ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በማከፋፈያ ዋጋቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች የገለጹ ሲሆን፣ ቢጂአይ ግን ይህንን የዋጋ ጭማሪ ከትላንት ጀምሮ ተግባራዊ አድርጓል፡፡በትላንትናው ዕለት ቢጂአይ የዋጋ ለውጡን ተግባራዊ መሆኑን የሚያረጋግጠው፣ በማከፋፈያ ዋጋ የሚረከቡ ሆቴ...
### Text: መንገዱ ተከፍቷል️በጸጥታ ችግር ምክንያት ከሁለት ቀን በላይ ተዘግቶ የበረው ከሐረር ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።የመንገዱ መከፈትን አስመልክቶ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳለው ከባቢሌ ወረዳው ስድስት ቀበሌ ገበሬ ማህበር የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ባስነሱት የጸጥታ ችግር ምክንያት መንገዱ ከሁለት ቀን በላይ ተዘግቶ ቆይቷል።00የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ ቦንሲቱ ኢብራሂም ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት መንገዱ የተከፈተው ያለምን...
### Text: ህጋዊሰነድ እና ማስረጃ ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር 116 ደረሷልህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ሙሉ ለሙሉ ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር 116 መድረሱን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አሳወቀ።እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ ህጋዊ ሰነድ እና ማስረጃዎችን ሙሉ ለሙሉ ያቀረቡ፣ ያላመሟሉ እና ሙሉ ለሙሉ ያቀረቡ በሚል የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ማሳወቁ ይታወሳል ኤጀንሲው አያይዞም የተጠየቁትን ያላቀረቡ ተቋማትን በሚመለከት እስካላቀረ...
### Text: ከወደ ካናዳ የዳቦ ዋጋ ሲጨምር የነበረው ዳቦ አምራች 50 ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በፍርድ ቤት ተቀጣ።ካናዳ ውስጥ ሆን ብሎ የዳቦ ዋጋ የጨመረ እንዲንር ያደረገ የዳቦ አምራች የ50 ሚሊዮን የካናዳ ዶላር ቅጣት መቀጣቱን ቢቢሲ ፅፏል።ድርጅቱ ካናዳ ብሬድ የሚባል ሲሆን ለዓመታት የዳቦ ዋጋ ሲጨምር እንደነበር አምኗል ተብሏል።የካናዳ የገበያ ውድድር ቢሮ ዳቦ ቤቱን ጠርጥሮ ለበርካታ ዓመታት ምርመራ ሲያደርግበት መቆየቱ የተነገር ሲሆን ቢሮው ዳቦ ቤቱ ላይ የተጣለው ቅጣት ሲያንስ ...
### Text: የድሬ ነዋሪዎች ለዶር አብይ ያስተላለፉትይህ መልእክት ለክቡር ለጠቅላይ ሚንስትራችን አብይ አህመድ ነው። እባኮትን ድሬ እያነባች ነው መጥተው ችግራችንን ያዳምጡ። ድሬ ከነልጆችዋ አልቅሳ እየለመነች ነው። እናመሰግናቸዋለን። ጥያቄዎቻችን ድሬድዋችን ብቃትና አቅም ባላቸው ልጆቿ ትመራ ነው ። በልማት ወደ ኋላ የቀረችው ፣ ፕሮጀክቶች በጊዜ ማለቅ ያልቻሉት ፣ በራሳችሁ ሪፖርቶች መሰረት አፈፃፀማችሁ ከ50 ፐርሰንት በታች የሆነው እናንተ አቅም ስለሌላችሁ ነው 40፣ 40፣ 20 ማንንም አልጠቀመም...
### Text: በእነ አቶ ጃዋር ላይ ክስ ሳይመሰረት ቀረአቃቤ ሕግ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ላይ ክስ የሚመሰርትበት ቀን ዛሬ የመጨረሻው የነበረ ቢሆንም በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ ይመሰረታል ተብሎ ሲጠበቅ ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።በዚህም አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ለፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ተናግረዋል።ጠበቃ ቱሊ ባይሳ ለ ከተናገሩት አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በ11 ሰዎች ላይ አቃቤ ሕግ ክስ ለመመ...
### Text: መቐለ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመቐለ ከተማና አካባቢው እንዲሁም ከትግራይ የክልል የተለያዩ ዞኖች ከተውጣጡ ተሳታፊዎች ጋር ተወያዩ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይት መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያን ያለ ትግራይ ትግራይንም ያለ ኢትዮጵያ ማሰብ አይቻልም ብለዋል።የትግራይ ተወላጆች የሃገር መውደድና ፍቅር የቆየ ታሪክ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትግራውያን ኢትዮጵያን ለመውረር የመጡ ሃይሎችን በመመከት ድንበራቸውን ማስጠበቃቸውን ጠቅሰዋል።በየትኛውም ጊዜ ቢሆን ...
### Text: እግር ኳስ ለሰላም እጦት ምክንያት ሊሆን አይገባም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንትእግር ኳስ ለፍቅርና ለአንድነት እንጂ ለሰላም እጦት ምክንያት ሊሆን አይገባም ሲሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን ፕረዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ገለጹ።ከሰባት ወራት በፊት በአዲስ አበባ ስታዲዮም የኢትዮጵያ ቡናና መቀሌ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለቦች ሲጫወቱ ደጋፊዎች በፈጠሩት ችግር ለደረሰው ጥፋት ትላንት በመቀለ ከተማ የይቅርታ ስነስርዓት ተኳሄዷል፡፡በስነስርዓቱ ወቅት የተገኙት አቶ ኢ...
### Text: ቦርደዴ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት 7 ሰው ሞተ ከሀረር ወደ ኢዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ልዩ ስሙ ቦርደዴ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። በአካባቢው በተፈጠረ ግጭት መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ምንም ዓይነት መኪና እንዳያልፍ ተዘግቷል፡፡ከሀረር ወደ አዲስ አበባ ፣አዳማ እንዲሁም ሌሎች አካቢዎች ለመሄድ የተሳፈሩ ተጓዦች ከማለዳው 2 ሰዓት ጀምሮ መንገዱ መዘጋቱን እና በረሀ ላይ መሆናቸውን መንቀሳቀስም እንዳልቻሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡ጥቆማውን የሰጡ ግለሰ...
### Text: የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኤፍ ቢ ሲ የተናገሩትየሀይል መቋረጡ ከጊቤ 2 የሀይል ማመንጫ ከሚነሳው የሀይል ማስተላለፊያ መስመር ጋር የተያያዘ ነው። ከጊቤ 2 የሀይል ማመንጫ የሚነሳው እና ወደ ሰበታ እና ወደ ሶኮሮ የሚሄደው 400 ኪሎ ቮልት ሀይል ተሸካሚ ከፍተኛ መስመር በአካባቢው በነበረ ንፋስ በቀላቀለ ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ችግር ገጥሞት ነበር። በዚህ ምክንያት በዚህ መስመር የሚያልፈው ሀይል ከጊቤ 3 ተነስቶ ከወላይታ ሶ...
### Text: ጳጉሜ 12012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 769 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮቪድ19 መያቸው ተረጋግጧል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 542 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።በቫይረሱ የተያዙት 5 ከአሶሳ ከተማ መናኸሪያ 7 ከጾሬ ስደተኛ መጠለያ 1 ከማኦ ኮሞ ጉራስምቦላ ስደተኛ መጠለያ 6 ከደቡስ ኬላ 3 ከሸርቆሌ ስድተኛ መጠለያ በአማራ ክልል ባለፉ...
### Text: የ4ቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጉዳይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚገኙ አራት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ላይ ሲያካሂድ የነበረውን የወንጀል ምርመራ ማቋረጡን አስታወቀ፡፡ምርመራቸው እንዲቋጥ የተደረጉት የጦር መኮንኖች1 ሜጀ መሀመድ ኢሻ ዘይኑ ትኩእ2 ብጀ ሙሉጌታ በርሄ ይልማ3 ኮል ገእግዚአብሔር ገሚካኤል እና4 ኮል ገዋህድ ኃይሉ መሸሻ ናቸው፡፡በጥቅምት 242013 በሰሜን ዕዝ ላይ በተሰነዘረው ጥቃት ላይ ተሳትፈዋል ተብለው ...
### Text: ቀይ መስቀል አአ ቅርንጫፍ ተለዋጭ ቦታ ተሰጠው።በአዲስ አበባ ከተማ ከ1973 ዓም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽቤት ተለዋጭ ቦታ ማግኘቱንና ከኅዳር 9 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ ወደ አዲሱ ሕንፃ ተዘዋውሮ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊ፣ የዲፕሎማሲና የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሰለሞን ዓሊ ዶር የአዲስ አበባ ከተማ የቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ይገለገልበት የነበረውን ቦታ ለልማት በመፈለጉ ምክንያት የቦታ ይ...
### Text: አዲስአበባ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድርስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት በነባሩክፍያታሪፍ በሙሉ አቅም ሊሰሩ ይገባል ተብሏል።የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም ተቋማት፣ የታክሲና ሀይገር ባለንብረቶች ማህበራትና ግለሰቦች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድረስ በነባሩ የክፍያ ታሪፍ መሰረት አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።ከነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ጋር ተያይዞ አገልግሎቱ...
### Text: አማራ ከፊታችን ያሉት ሃማኖታዊ በዓላት በአደባባይ እንዲከበሩ ተፈቀደ።የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ በአማራ ክልል ለመውሊድ ፣ ደመራ እና መስቀል በዓላት መሰባሰብን ፈቀደ።ዕዙ መስከረም 16 እና 17 2016 የሚከበሩት የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላት በአማራ ክልል የሃይማኖቶቹ ሥርዓት በሚፈቅዱት መንገድ እንዲከበሩ እየሰራሁ ነው ብሏል።ምንም እንኳን የሕዝብ ስብሰባዎች በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ቢከለከሉም መስከረም 16 እና 17 የሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት የአደባባይ...
### Text: የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በሐገሪቱ ዉስጥ ለሚሰሩ የዉጪ ሐገር ባለሙያዎችና ባለወረቶች ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ ሒቃማ ሊሰጥ ነዉ። እስካሁን ድረስ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የሚሰራ የዉጪ ሐገር ባለሙያም ሆነ ባለሐብት መኖሪያ ፍቃድ የሚያገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ዜጋ ከሆነ ቀጣሪዉ ወይም የሐብት ተሻራኪዉ ግለሰብ ወይም ኩባንያ ነዉ። የሳዑዲ አረቢያ ምክር ቤት ሹራ ባለፈዉ ሳምንት ባፀደቀዉ ደንብ መሠረት ለዉጪ ሐገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ የሚሰጠዉ የሐገሪቱ መንግስት ነዉ።ዩናይትድ ስቴትስ «ግሪን...
### Text: አሳዛኝ ዜና️በሕንድ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 19 ተማሪዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ።በትምህርት ቤቱ የተነሳው ቃጠሎ ተፋፍሞ ጥቁር ጭስ በመስኮቶቹ መውጣት እንደጀመረ፣ ተማሪዎች ነፍሳቸውን ለማትረፍ በመስኮት ሲዘሉ መታየታቸው ተዘግቧል።በእሳቱ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎቹ አብዛኛዎቹ ታዳጊዎች ናቸው የተባለ ሲሆን በትምህርት ቤቱ የማጠናከሪያ ትምህርት እየወሰዱ ነበር።እሳቱ የተነሳበት ምክንያት ባይታወቅም ተማሪዎች በብዛት ወደሚገኙበት ክፍል የተዛመ...
### Text: ኢቦላ ኢትዮጵያ የኢቦላ ወረርሽኝን ቀድሞ ለመከላከል የህክምና ባለሙያዎች በመላ ሃገሪቱ መሰማራታቸውን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ለቅድመ መከላከል ስራውም ከ290 በላይ የህክምና ባለሙያዎች በመላ ሃገሪቱ መሰማራታቸውን ነው ኢንስቲቲዩቱ የገለፀው።የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በየነ ሞገስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ወረርሽኙ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የቅድመ መከላከል እና የቁጥጥር ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብ...
### Text: ለታማኙ የፓሊስ አባል የማዕረግ እድገትና የገንዘብ ሽልማት ተበረከተለት በአፋር ክልል ኤሊደአር ወረዳ በህገወጥ መንገድ ወደ መሀል ሀገር ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ሥር ላዋለ የፖሊስ አባል የማእረግ እደገትና የገንዘብ ሽልማት ተበረከተለት። የወረዳው ፖሊስ አባል የሆነው ሲራጅ አብደላ የዋና ሳጅነት ማዕረግና የ50 ሺህ ብር ሽልማት ከክልሉ ርዕሰመስተዳድር አቶ አወል አርባ እጅ ተቀብሏል።ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ የማእረግና የገንዘብ ሽልማቱ የተበረከተለት መስከረም 6 ቀን 20...
### Text: የዘንድሮ የሐጅ አድራጊ ክፍያ 315000 ብር እንዲሆን ተወስኗል።የ14442015 የሁጃጆች ምዝገባ በ16 የምዝገባ ጣቢያዎች እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን የአንድ ሐጅ አድራጊ ክፍያ ብር 315000 ሶስት መቶ አስራ አምስት ሺህ እንደሚሆን ይፋ ተደርጓል።ይህ የተሰማው በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ14442015 ዓል የሐጅ ምዝገባ በተመለከተ እየሰጠ በሚገኘው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።በመግለጫው የሐጅ ተጓዥ ለምዝገባ በአካል መቅረብ ይኖርበታል...
### Text: የባለስልጣኑ እስር የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ ቃል አቀባዩ አቶ ታዬ ዳንዳአ ከመታሰራቸው በፊት በራሳቸው የፌስቡክ ገፅ ላይ ከዚህ በታች ያለውን ፅሁፍ ለጥፈው ነበር። ፅሁፉ ቅዳሜ ሞያሌ ውስጥ በስህተት ነው ስለተባለው የዜጎች ግድያ የሚመለከት ነውየምን ስህተት ሊሆን አይችልም ትላንት ሞያሌ ላይ ከአስር ያላነሱ ንፁሃን ዜጎች ሲገደሉ ከደርዘን በላይ ቆስሏል። ወንጀሉን የፈፀመዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸዉ። ኮማንድ ፖስት ደግሞ ጭፍጨፋዉ የተፈፀመዉ በስህተት ነዉ ይላል። ይህ በንፁሃን ደ...
### Text: ያየነውን እንመሰክራለንባለፉት ዓመታ በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ሜዳዋች ሲፈጠሩ የነበሩትን ክስተቶች ሁላችንም የምናውቀው ነው። በየጊዜው ተስፋ ሲያስቆርጡን፣ በሀዘን ውስጥ ሲከቱን የነበሩ ክስተቶች ነበሩ። እዚህ መዘርዘር አያስፈልግም። ዘንድሮ ግን በእግር ኳስ ሜዳዎቻችን ላይ ያየነው ለውጥ እጅግ ድንቅና ሊበረታታ የሚገባው ነው። ይህ ነው የሚባል ችግር ሳንሰማ ዛሬም በአስደማሚ የሜዳ ላይ ትዕይንቶች እየተገረምን ፣ ተስፋችን እየለመለመ ነው እውነትም እግር ኳስ የፍቅር እና የሰላም ፣ የህዝብ...
### Text: ነገ የሚዘጉ መንገዶች የኢትዮጵያዊነት ቀንነገ ሰኞ ጳጉሜ 1 ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ እዘምራለሁ በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ ዝግጅት ይኖራል።ይህን ዝግጅት አስመልክቶ ከጠዋቱ 1130 ጀምሮ መርሃ ግብሩ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ኡራኤል ቤክ ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኦሎምፒያ ከሸራተን ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ ሀራምቤ ትራፊክ መብራት ከሜክሲኮ ወደ መስቀል ...
### Text: ዛሬ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ አውጥቶ ነበር።በዚህም መግለጫው ላይ ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይቀርብ እንቅፋት ሆኖ መቀጠሉን አስገንዝቧል።የመንግስት ኮሚኒኬሽን እንደ ዓለም ጤና ድርጅት አይነት ለሁሉም ሰው በእኩል ቆመናል የሚሉ አለምአቀፍ ተቋማት ግን አሸባሪው ቡድን የአማራና አፋር ክልሎችን በወረረበት ወቅት ሀስፒታሎችንና የጤና ጣቢያዎችን ሲዘርፍና ሲያወድም ንፁሃንን ሲደፍርና ሲገድል የሽብር ቡድኑን ድርጊት ሲያወግዙ አልተደመጡም ብሏል። ይልቁንም መን...
### Text: የወላይታ ብሄር ተወላጆች ውይይት አደረጉየማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችንን በማዘመን ሚዲያ ለህዝቦች ትስስርና ለሀገር ግንባታ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ከማድረግ ባሻገር በህዝቦች ዘንድ ግጭት የሚቀሰቅሱ መረጃዎችን ባለማሰራጨት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት።የወላይታ ብሔር ተወላጆች ከሌሎች ህዝቦች ጋር ቀድሞ የነበረውን ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነት እና የመቻቻል እሴታቸውን በማጠናከር ለሰላምና ለሀገር ግንባታ የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከት አለባቸው፡፡በወላይታ እና ...
### Text: አረንጓዴአሻራ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በሚኒስቴሩ ስር የሚገኙ 15 ተጠሪ ተቋማት በቦሌ ለሚና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሐምሌ 152011 የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡ከ3800 በላይ ሠራተኞች በተሳተፉበት በዚህ የችግኝ ተከላ ከ22000 በላይ ችግኞችን በቦሌ ለሚና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመትከል ተችሏል፡፡ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በነበረው የቸችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተሳተፉት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረየሱስ እንደገለፁት ይህ የችግኝ ተከ...
### Text: የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመጠገን የሚያስችል ሳይንሳዊ ጥናት ተጀመረአብያተ ክርስቲያናቱ ታሪካዊ ይዘታቸውን እንደጠበቁ ለመጠገን የስነምድርና የአርኪዮሎጂ ጥናት መጀመሩን የኢትዮፈረንሳይ የጥናት ቡድን ገልጿል። የአብያተ ክርስቲያናቱ የሙከራ ጥገና በመውጭው የአውሮፓዊያኑ አዲስ ዓመት ይጀምራል ተብሏል።በ1970 ዓም በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት ቤተክርስቲያናቱ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ከ10 ዓመት በፊት በአምስት ዓመት ጊዜ ይነሳል ተብሎ በ11 ሚሊዮን ዩሮ የተሰራው...
### Text: የኤክሳይዝ ታክሱ በድጋሚ ይታይልኝ ኢትዮ ቴሌኮም ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎቶች ላይ 5 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ መጣሉ ተገቢ ስላልሆነ በድጋሜ ይታይልኝ ብሏል፡፡ የኢንተርኔት ፣ የድምፅ እና የፅሑፍ መልክት ላይ በኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎቶች ላይ 5 በመቶ የኤክሳይስ ታክስ መጣሉ በድጋሜ ቢታይ ጥሩ ነው ብሏል፡፡ኢትዮጵያ ኋላቀር የቴሌኮም አጠቃቀም ያላት ሀገር ናት በመሆኑም መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ፣ አሁን አዲስ የተጣለ...
### Text: በጊዜ ገደቡ ምላሽ ካልሰጠ ወደ ክሥ እናመራለን የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ቤቶቻቸው ለፈረሱባቸው ሰዎች አቤቱታዎች፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥ መጠየቁን ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።ተቋሙ፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር የቤቶች ፈረሳ ጋራ ተያይዞ፣ ከ100 ሺሕ በላይ አቤቱታዎችን እንደተቀበለ፣ ከዚኽ ቀደም ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽቤት የምርመራ ዲሬክተር አቶ ቶሌራ በላይ፣ የከተማ አስተዳደሩ ለአቤቱታዎ...
### Text: የመብራት መቆራረጥ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሃይል ስርጭት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተትአቶ ምስክር ነጋሽ ለ እንዳሉት በጊቤ 3 የሃይል ማመንጫ ጣቢያ የሚገኘውብሬከር በመከፈቱ ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች የሃይል መቋረጥ ተከስቷል።አቶ ምስክር ከምሽቱ ጋር ባደረጉት ቆይታ በብሬከሩ መከፈት ሳቢያ ወደ ሌሎች የሃይል ማሰራጫ ጣቢያዎች የሚሄዱ መስመሮች ጠፍተዋል። በዚህ ሳቢያም በ...
### Text: ደቡብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚታዩ የክልል እንሁን ጥያቄዎችን በጥናት ለመፍታት የክልሉ ገዥ ፓርቲ ደኢህዴን ሲያስጠና ቆየው ጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ ሆነ።የጥናት ቡድኑ ምክትል ሰብሳቢ ዶር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት 20 አባላት ያሉት የጥናት ቡድን ተዋቅሮ ላለፉት ሰባት ወራት ሰፊ ጥናት ሲያካሂድ ቆየቷል። በዚህም መሰረት ሶስት አማራጮችን አስቀምጧል ብለዋል ምክትል ሰብሳቢዋ።በጥናቱ የተለየው የመጀመሪያው አማራጭ አብዛኛው የክልሉ ህዝብ አሁን ያለ...
### Text: ተጨማሪ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ለህክምና 98 ተማሪዎች የመጡ ሲሆን ምርመራ ከተደረገላቸዉ ሴት 47 እና 51 ወንድ በአጠቃላይ 98 ተማሪዎች የመደንገጥና ከመጠነኛ ማስታወክ ስሜት ዉጭ የከፋ ኬዝ አለመኖሩን ነገር ግን ሁለት ተማሪዎች ብቻ መጠነኛ ህመም እንዳጋጠማቸው ሆስፒታሉ አሳውቋል።ሆስፒታሉ ይህን ያሳወቀው ለኢትዮ ኤፍ ኤም 1078 ሬድዮ ነው።የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶክተር ሳምሶን ጉታ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል የዛሬው ክስተት ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ አለመሆኑን ...
### Text: በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ትላንት በተፈፀመው የሽብር ጥቃት በትንሹ 100 ሰዎች ሲሞቱ 300 ሰዎች ተጎድተዋል።በሁለት መኪና በተፈፀመውን የቦንብ ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገድለዋል።የሶማሊያ ፕት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ የትላንቱን የሽብር ጥቃት ጭካኔ የተሞላበት እና የፈሪዎች ጥቃት ሲሉ ገልፀው ድርጊቱን የፈፀመው ሽብርተኛው አልሸባብ መሆኑን አመልክተዋል።በጥቃቱ ሲቪሎች መሞታቸውን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ድርጊት ተስፋ ሊያስቆርጠን አይች...
### Text: ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝምን ለማጠናከርና በህዝቦች መካከል አንድነትና እኩልነት እንዲኖር ይሰራል ጋድሰ ሆገንሰ ኦሮሞበጋድሰ ሆገንሰ ኦሮሞ ስር የተደራጁ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝምን ለማጠናከርና በህዝቦች መካከል አንድነት፣ እኩልነትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲኖር ይሰራሉ፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች አሁን የምንወስዳቸው እርምጃዎች ለቀጣይ የኦሮሞና የአገሪቱ ህዝቦች ዕጣ ፋንታ ወሳኝ ናቸው ብለዋል፡፡ ...
### Text: ጳጉሜ 32012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 2 በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1528 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ አንድ 61 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል የአንድ ሰው ህይወት አልፏል ከቤንች ሸኮ ዞን የ32 ዓመት ወንድበቫይረሱ የተያዙት፡ ከከምባታ ጠምባሮ ዞን 17 9 ከሺንሺቾ፣ 3 ከዱራሜ ከተማ፣ 2 ከደምቦያ፣ 1 ከቃጫቢራ፣ 1 ከጠምባሮ እና 1 ከዶዮ ገና ከጌዴኦ ዞን 12 8 ከዲላ ከተማ፣ 2 ከረጲ፣ 1 ከዲላ ዙሪያ እና 1 ከይርጋጨፌ፣ ከወላይታ ...
### Text: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የበረራ ቁጥር ኢቲ 3905 አውሮፕላን ናይጄሪያ ሌጎስ ደርሶ ካረፈ በኋላ ወደ መቆሚያ ስፍራው እየሄደ ሳለ ከመንገዱ ወጥቶ እንደነበር ተገለጸ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳደረጋገጠው ወደ ካርጎ የተቀየረው የመንገደኞች ቦይንግ 777300 ግዙፍ አውሮፕላን ካጋጠመው ከስተት በኋላ ወደ ሥራ ተመልሷል።አውሮፕላኑ ከአዲስ አበባ ወደ ናይጄሪያ ሌጎስ ከተማ ጭነት ይዞ ከበረረ በኋላ በሌጎስ ኤርፖርት አርፎ ወደ መቆሚያው እየሄደ ሳለ የአውሮፕላኑ በስተግራ በኩል...
### Text: የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግተከሳሽ መሀዲ መሀመድ ሳድቅ የወንጀል ህግ አንቀጽ 6271 ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ቦታው ዳትሰን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አስር አመት በሆናት ህጻን ላይ በፈጸመው የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ማድረስ ወንጀል ተከሶ ፍቤት ቀርቧል፡፡ተከሳሹ በ2010ዓም መጋቢት ወር መጀመሪያ ሳምንት ባሉት ቀናት በግምት ከቀኑ 5፡00 ስዓት ሲሆን ታዳጊ የሆነችዋን ህ...
### Text: አሜሪካ ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እያበረከተች ያለውን በጎ ሚና አደነቀች የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በዋሽንግተን ዲሲ የተወያዩ ሲሆን፣ በውይይቱ ላይ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ኃላፊዎች ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም የሚታበረክተው በጎ ሚና እና በመከላከያ ዘርፍ የምታካሄደውን ማሻሻያ አድንቀዋል፡፡ የሁለቱ አገራት 9ኛው የሁለትዮሽ የመከላከያ ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባ በዋሽንግተን ከተማ ተካሂዷል።በስብሰባው ሁለ...
### Text: ህዳር 24 ቀን 2013 ሮይተርስ ዜና ወኪል በትግራይ ክልል 4 ለውጭ ድርጅቶች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን ገልፆ እንደ ነበር የምታስታውሱት ነው።በወቅቱ ሮይተርስ ሰራተኞቹ ስለሚሰሩበት ድርጅቶቹ እንዲሁም በማን እና እንዴት እንደተገደሉ ምንም ያለው ነገር አልነበረም። በዛሬው ዕለት ባወጣው መረጃ ሰራተኞቻቸው የተገደሉባቸው ድርጅቶች ዳኒሽ ሪፊውጂ ካውንስል እና ኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ መሆናቸው ታውቋል።ዳኒሽ ሪፊውጂ ካውንስል ባሳለፍነው ወር 3 የሰብዓዊ እርዳታ...
### Text: አጫጭር የምርጫ 2013 መረጃዎች ነገ መጋቢት 162013 ዓም የ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ይጀምራል። የመራጮች ምዝገባ ነገ ጀምሮ የሚጠናቀቀው ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓም ነው። እንደምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ከትላንት ጀምሮ ለምርጫ ክልሎች ማሰራጨት ጀምሯል፡፡ ቦርዱ ለአንድ ወር ለሚቆየው የመራጮች ምዝገባ ለ673 የምርጫ ክልሎችና 50 ሺህ የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች የሚሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶችን ነው ማጓጓዝ የጀ...
### Text: ጊዳሚ ከተማ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው ተገደሉ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ከተማ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ይህን መሰሉ ግድያ ነዋሪ የዕለት ተዕለት ሰቆቃ ከሆነ ሰነባብቷል።ቅዳሜ ምሽት ተኩስ ነበር። በዚያ ተኩስ ሳቢያ ነው ሁለቱ ነዋሪዎች የተገደሉት። እነሱን የገደለው አካል የቱ እንደሆነ ደግሞ መለየት አልቻልንም በማለት ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንጠቅስ አንድ የ...
### Text: የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በፓስፖርት አቅርቦት ዕጥረት እየተስተዋለ ያለበትን የኪራይ ሰብሳቢነት ድርጊት ለመታገል የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አውጥቶ በጥብቅ ዲስፕሊን እንዲተገብር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።የኤጀንሲውን የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓም በገመገመበት ወቅት ኤጀንሲው በበቂ መጠን ፓስፖርት ባለማሳተሙ በተፈጠረበት የፓስፖርት ዕጥረት አስቸኳይ ጉዳዮችን ከማስተናገድ ባለፈ አብዛኛ...
### Text: 19 ከአዲስ አበባ ከተማ ቀጥሎ ከፍተኛው የ24 ሰዓት ኬዝ የተመዘገበው በሐረሪ ነው። 100 የላብራቶሪ ምርመራ 7 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። 6 ወንዶች እና 1 ሴት ሲሆኑ ሁለቱ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ አምስቱ ለህክምና ወደ ሐረር መጥተው ናሙና የተወሰደላቸውና ነዋሪነታቸው 1 ሰው ሱማሌ ክልልና 6 ሰዎች ምስራቅ ሐረርጌ ዞን የሆኑ ናቸው። 19 በትግራይ ክልል ከኮሮና ቫይረስ ኮቪድ19 ያገገሙ ሰዎች 96 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 19 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል...
### Text: በሊባኖስ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉየኢትዮጵያ ቆንስላ ጄፅቤት ቤይሩት ሊባኖስበቤይሩት ወደብ ዛሬ የተከሰተው ፍንዳታ ጋር ተያይዞ እስከ አሁን ወደ 10 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸው የተዘገበ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ደግሞ እንደቆሰሉ ሪፖርት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ፍንዳታው በተከሰተበት አካባቢ መንገዶች እና ህንጻዎች የፈራረሱ ሲሆን ከፍንዳታው እስከ በ10 ኪሎሜትር ርቀት ደግሞ ብዙ ህንጻዎች መስኮቶች ተሰባብረዋል፡፡ በመሆኑም ሁኔታዎች እስኪረጋጉ ዜጎች በተቻለ መጠን በቤታችሁ እ...
### Text: አጠቃላይ የምርጫ ውጤት ፓርላማ 1 አዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና 22 መቀመጫዎችን አሸንፏል አንዷን መቀመጫ አንድ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ አሸንፈዋል2 አፋር ክልል 8 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው 6 መቀመጫዎችን በሙሉ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል 3 አማራ ክልል ምርጫ ከተካሄደባቸው 125 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና በ114ቱ አሸንፏል አብን 5 መቀመጫዎችን አሸንፏል4 ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 9 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት በሶስት የፓርላማ መቀመጫዎች ሰኔ ...
### Text: ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የሚያገናኟትን መንገዶች ግንባታ እና ጥገና ማጠናቀቋን አስታወቀች ኢትዮ ኤፍ ኤም 1078የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 1078 እንዳስታወቀዉ ኢትዮጵያን እና ኤርትራን የሚያገናኙት መንገዶች ጥገናቸዉ ተጠናቋል ብሏል፡፡ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ቡሬ አሰብ ራማ መረብ እና አዲግራት ዛላምበሳ መንገዶች ጥገናቸዉ በመጠናቀቁ የትራንስፖርቱ አገልግሎቱ ካለ መንገዶቹ ዝግጁ ናቸዉ ባለስልጣኑም የሚጠበቅበትን ሃ...
### Text: ነሃሴ 202012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 555 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 14 ሰዎች በኮቪድ19 መያቸው ተረጋግጧል። በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3869 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 383 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል።በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 39 ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ 38 ከምስራቅ ሸዋ 34 ከቢሾፍቱ ከተማ 33 ከምዕራብ አርሲ 28 ከምዕራብ ወለጋ 24 ከሻሸመኔ ከተማ 23 ከ...
### Text: ጎረቤት ሀገር ኬንያ እንደአዲስ የተቀሰቀሰውን የኮቪድ 19 ስርጭት ለመቆጣጠር በ5 ግዛቶች ናይሮቢ ፣ ካጂያዶ ፣ ኪያምቡ፣ ማቻኮስ እና ናኩሩ ጥብቅ ክልከላዎችን ጣለች። ጥብቅ ክልከለዎቹ ምንድናቸው በግዛቶቹ እና ከግዛቶቹ ውጪ የሚደረጉ ማናቸው አይነት ጉዞዎች ታግደዋል። ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ተወስኗል። በምግብ ቤቶች ውስጥ ተቀምጦ መመገብ ተከልክሏል። መጠጥ ቤቶች አልኮል መሸጥ አይችሉም ተብሏል። ከዚህ ቀደም ከምሽቱ አራት ሰዓት ይጀምር የነ...
### Text: ከ ልብ የሚነካ መልዕክትበፀሎታችሁ አትርሱን እያሉ ነው ተማሪዎቹእንዴት አደርክ ጸግሽ እኔ የ ተማሪ ነኝ ግን የ አአ ልጅ ነኝ ወደ ቤት እንዳንመለስ መኪናም ተከልክለናል። ትላንት ሙሉ ቀን ከቁርስ በስተቀር በረሀብ ተገርፈን ነው የዋልነው እቺንም ሽሮ ከለከሉን ወላሂ ነው ምልህ በታም ተስፋ እየቆረጥን ነው ያለነው ለሊት ግማሹ መስጊድ ግማሹ ቤተ ክርስቲያን የቀረው ደሞ ጎረቤት ምናምን ለምነው እያደሩ ነው ዛሬ ደሞ ከ ቁርስ ጀምሮ እንደሚቀጡን ነው ሚወራው።21ኛው ክዘመን ላይ ...
### Text: አጫጭር መረጃዎች በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ45000 በልጧል። በአንድ ቀን ብቻ ከ2700 በላይ ሰው ሞቷል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ824000 በልጧል። በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 759 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተድርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 18100 ደርሷል። በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 1194 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 94 ሰዎች ሞተዋል። በስፔን የሟቾች ቁጥር መጨመር እያሳየ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 435 ሰዎች ሞተዋል። አጠቃላይ የሟቾች ...
### Text: ሴት ሰራተኞች አርፋችሁ ቤት ተቀመጡ የካቡል ከንቲባየታሊባን አዲሱ የካቡል ከንቲባ ስማቸው ሐምዱላህ ኖማኒ በካቡል የሚገኙ የማዘጋጃ ቤት ሴት ሠራተኞችን አርፋችሁ ቤት ተቀመጡ ሲሉ ተናገሩ።ከንቲባው ይህን ያሉት ታሊባን ለጊዜው ሴቶች ሥራ እንዳይሠሩ ማዘዙን በመጥቀስ ነው።ክፍት የሥራ መደቦች በወንዶች የማይሞሉ ከሆነ ብቻ ለሥራ ልትመጡ ትችላላችሁ አለበለዚያ ግን አርፋችሁ ቤት ተቀመጡ ብለዋል ከንቲባው።የካቡል አዲሱ ከንቲባ እንዳሉት በከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ሠራተኞች ውስጥ አንድ ሦስተኛው...
### Text: ይቅርታ ባቀድነው ልክ ውጤታማ ባለመሆናችን የ ኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁንየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአፍሪካ ዋንጫው ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠየቀ።ዛሬ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን የኢትዮጵያን የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ቆይታ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን...
### Text: ዕድሜ አጭበርብረዋል የተባሉት አትሌቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።ከጥር 23 282015 ዓም በአሰላ አረንጓዴው ስቴድዮም ከ ሃያ 20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል።በዚሁ ውድድር ላይ ከእድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መነጋገሪያ ጉዳዮች ተፈጥረዋል በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወሩ የነበሩ ፎቶዎችም በርካቶችን እንዴት እኚህን የሚያክሉ አትሌቶች ከ20 ዓመት በታች ይወዳደራሉ በሚል አስገርመዋል።ይህን በተመለከተ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ...
### Text: ባህር ዳርበኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ላይነር በባሕር ዳር ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ላይነር በባሕር ዳር ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡አምባሳደሩ ከባሕር ዳር ከንቲባ ከሙሉቀን አየሁ ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይታቸውም ሶስት አበይት ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ፣በጣና ላይ የተጋረጠው እንቦጭ እና በግንባታው ዘርፍ ባለሀብቶች ወደ ከተማዋ እንዲመጡ ምን መደረግ እንዳለበት ተወያይተዋል፡፡አምባሳደር ማይክል የወጣቶች...
### Text: ልዩ 2 ሎተሪ ወጣ ሼር በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የልዩ ሎተሪ ግንቦት 192011 ዓም በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል1ኛ 7000000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 00562402ኛ 3000000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር07443953ኛ 1000000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 10596644ኛ 400000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 07...
### Text: አስቸኳይ ግዜ አዋጅ️ቡርኪናፋሶ አስቸኳይ የግዜ አዋጅ አወጀች። ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ቡርኪናፋሶ ከማሊ በሚያዋስናት ሰሜናዊ ግዛቷ ነው አስቸኳይ ግዜ አዋጅ ያወጀችው፡፡አገሪቱ በአካባቢው አስቸኳይ ግዜ አዋጅ ያወጀችው እስላማዊ ቡድኑ የሚሰነዝራቸው ጥቃቶች አጠናክሮ በመቀጠሉ እንደሆነ የአገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡የምዕራብ አፍሪካ አገራት ጄ ኒም የተሰኘ ጅሃዲስት ቡድን በሚያደርስባቸው ጥቃት ደህንነታቸው ከግዜ ወደ ግዜ አደጋ ላይ እየወደቀ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡የቡርኪና...
### Text: ካዎ ኮይሻ ወረዳ በደረሰ ድንገተኛ አደጋ የ1 ሰው ህይወት አለፈ በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት በተፈጠረ የመኖሪያ ቤት የመደርመስ አደጋ የአባወራው ህይወት ማለፉንና በልጃቸው ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።አደጋው የደረሰው ትናንት እኩለ ቀን አካባቢ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲጥል የቆየው ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት የአንድ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት በመደርመሱ ነው፡፡ በወረዳው ኦፋ ሂራ የገጠር ቀበሌ እኩለ ቀ...
### Text: 5 በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸው ገፆች ️ ቴሌግራም 1 አማርኛ ይህ የቴሌግራም ቻናል የቢቢሲ አይደለም። ቢቢሲ አማርኛ በፌስቡክና በትዊተር ላይ ካለው የመገናኛ አማራጭ ውጪ በቴሌግራም ምንም አይነት ገፅ የለውም2 የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ምንም አይነት ይፋዊ የሆነ የቴሌግራም ገፅ የለውም። 3 የ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ በቴልግራም መልዕክት የሚያሰራጭበት ምንም ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል የለውም። እንዲሁም በፌስቡክ ላይ ያለው የግል ገፁ በ የተ...
### Text: በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር እና ኧሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓም ደግም ያገረሸው ግጭት በመኃል ለቀናት ጋብ እያለ የመጣ ቢሆንም ከመጋቢት 15 ወዲህ ግን ለተከታታይ 4 ቀናት ያለመቋረጥ በቀጠለ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን የቲክቫህ ቤተሰቦች ገልጸዋል።በኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር በኩል ዲማያ የሚባል አካባቢ ወደ 6 ሰው እንደሞተና በርካታ መኖሪያ ቤቶች እንደተቃጠሉ እንዲሁም በኧለ ልዩ ወረዳ በኩል ዳታኔ...
### Text: የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ አዲስ አበባ ይገኛሉ።የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ይገኛሉ።አምባሳደር ሐመር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ የመከሩ ሲሆን ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋርም ተገናኘተው መምክራቸው ታውቋል።የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ከአምባሳደር ምስጋኑ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያና የአሜሪካ የሁለትዮሽ ጉዳዮች እንዲሁም ቀጣናዊ፣ አኅጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉ...
### Text: በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪኤድስ ወረርሽኝ ሊባል በሚችል ደረጃእየተስፋፋ መምጣቱ ተገለፀ።በዓመት ከ27 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ይይዛሉ የተባለ ሲሆን ከ19 ሺህ በላይ የሰዎች ደግሞ በቫይረሱ አማካኝነት ይሞታሉ ነው የተባለው።በዚህ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና በፌዴራል የኤች አይ ቪኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።በመድረኩ እንደተገለፀው ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የስርጭት ምጣኔው ከ2 ነጥብ 5 እ...
### Text: ሆሳዕናየሆሳዕና ከተማ የመብራት ጉዳይ አሰልቺ ደረጃ ላይ ደርሷል። የመብራት ሀይል ዝርክርክ አሰራሮች ህዝብን ምሬት ውስጥ ከቶታል የሆሳዕና ከተማ የመብራት ጉዳይ አሁንስ ቅጥ አጣ። ሀይ የሚላቸው አካል የለም ወይ 3 እና አራት ቀን እያጠፉ በስለት ብልጭ ቢል ለደቂቃ እንኳ ሳይቆይ ህልም እያለ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። እንዲህ አይነት ዝርክርክ አሰራር በጣም ያበሽቃል። ሆቴሎችንና የተለያዩ ፍሪጅ የሚጠቀሙ ጁስ ቤቶችና ወተት ቤቶች ለኪሳራ እየተዳረጉ ነው ያሉት። ከምንም በላይ ሆስፒታሎች እ...
### Text: ትምህርት ሚኒስቴር በ2012 ዓም የትምህርት ዘመን ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነበ2011ዓም የአጠቃላይ ትምህርት 10ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ መሆኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት፡ 08 የመደበኛ፣የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ለወንድ 200 እና በላይ ለሴት 186 እና በላይ ሆኖ የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች በማታው ፕሮግራም ይ...
### Text: ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በዓለም ተፅዕኖ ከፈጠሩ 50 ግለሰቦች አንዱ ሆኑጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዓቢይ አህመድ በፋይናንሺያል ታይምስ ጋዜጣ ከፈረንጆቹ 20102019 በነበሩት 10 ዓመታት በዓለም ላይ ለውጥ በማምጣት ከተጠቀሱት 50 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ዝርዝር ተካትተዋል። 1ኛ በፖለቲካው መስክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ቱኒዚያዊው ሞሃመድ ቡአዚዝ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜሪከል የ...
### Text: ሀርጌሳ ሀገራችንን አልሸጥንም ሙሴ ባሂ አብዲባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል።ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።አደባባይ ወጥቶ ለተቀበላቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ከጠሚ ዶር ዐቢይ አህመድ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑ ገልጸዋል።ፕሬዜዳንቱ ሀገራችንን አልሸጥንም ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ጦር ሰፈር በ...
### Text: ጊፋታ2013 የዘንድሮው የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በተለያዩ ፕሮግራሞች ይከበራ ተብሎ ይጠበቃል።በዓሉን በዩነስኮ ለማስመዝገብ የሚያደርገውን ጥረት የዞኑ አስተዳደር መላ የዞኑን ህዝብና አጋር አካላትን በማስተባበር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።ኮቪድ19 በፈጠረው ችግር ምክንያት የዘንድሮውን የወላይታ ህዝብ ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል ከዚህ በፊት በተለመደው ሁኔታ ህዝቡ በብዛት በተሰበሰበት ቦታ ለማክበር የማይቻል ቢሆንም ህዝቡ ቫይረሱን እየተከላከለ በተለያዩ ሁነቶች ማ...
### Text: 350 ሺ ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል ሮይተርስ ተመልከቱት ያለው የተመድ የውስጥ ሪፖርት ኢትዮጵያ ውስጥ ረሃብ ተከስቷል ለማለት የተቀመጡ መስፈርቶች አሉ አሁን በትግራይ ባለው ሁኔታ ከ90 በላይ የክልሉ ነዋሪ ሰብዓዊ ድጋፍ አግኝቷል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርበሮይተርስ የተመለከትኩኝ ባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውስጥ ሰነድ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ወደ 350000 ያህል ሰዎች በረሃብ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ተገምቷል።በሰነዱ ላይ ትንታኔ የሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት...