text
stringlengths
4
267
ኢየሱስ አንድ ጀልባ ላይ ሆኖ ተሰብስበው የነበሩ ሰዎችን ያስተማረበትን ወቅት እንደ ምሳሌ እንውሰድ።
በዚያ ወቅት ጴጥሮስን በተአምራዊ መንገድ ብዙ ዓሣ እንዲያጠምድ ከረዳው በኋላ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ ነግሮታል።
ኢየሱስ የተናገረው ነገርና ድርጊቱ ምን ውጤት አስገኘ?
ጴጥሮስና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉን ነገር ትተው ኢየሱስን ተከተሉት።
የሳንሄድሪን ሸንጎ አባል የነበረው ኒቆዲሞስ ኢየሱስ የሚያስተምረው ትምህርት ትኩረቱን ስቦት ነበር።
ተጨማሪ እውቀት ማግኘት ቢፈልግም በአደባባይ ከኢየሱስ ጋር ሲነጋገር ቢታይ ሰዎች ምን እንደሚሉት በማሰብ ፈርቶ ነበር።
ኢየሱስ፣ ሰዎችን በሚመቻቸው ጊዜ ለማነጋገርና ጊዜውን ሳይሰስት ለመስጠት ፈቃደኛ ስለነበር ማታ ላይ ሰው በሌለበት ኒቆዲሞስን አነጋገረው።
የአምላክ ልጅ የሰዎችን እምነት ለመገንባት ጊዜ መድቧል።
የሰው ልጆች በሙሉ የኃጢአትንና የሞትን እርግማን የወረሱት እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ሰው በአዳም በደል የተነሳ ሞት በአዳም ዘሮች ላይ እንደነገሠ ይናገራል።
ደስ የሚለው ግን የኃጢአት ተገዢዎች ወይም ባሪያዎች ላለመሆን መምረጥ እንችላለን።
በክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት በማመን፣ የይሖዋ ጸጋ በእኛ ላይ እንዲነግሥ እንደምንፈልግ እናሳያለን።
ኃጢአተኞች ብንሆንም እንኳ ኃጢአት ሕይወታችንን እንዲቆጣጠረው ከመፍቀድ ሌላ አማራጭ እንደሌለን አድርገን ልናስብ አይገባም።
ኃጢአት ስንሠራ ይሖዋ ይቅር እንዲለን መለመን እንችላለን።
በመሆኑም በእኛ ላይ የሚገዛው የአምላክ ጸጋ ነው።
ይህ ምን ውጤት ያስገኛል?
ጳውሎስ እንደሚከተለው በማለት አብራርቶታል፦ የአምላክ ጸጋ ፈሪሃ አምላክ በጎደለው መንገድ መኖርና ዓለማዊ ምኞቶችን መከተል ትተን አሁን ባለው በዚህ ሥርዓት ውስጥ ጤናማ አስተሳሰብ በመያዝ፣ በጽድቅና ለአምላክ በማደር እንድንኖር ያሠለጥነናል።
የወንድማማች ፍቅር ከአሁኑ ማዳበራችን አስፈላጊ ነው፤ እንዲህ ማድረጋችን ወደፊት የሚያጋጥመንን ማንኛውንም ፈተናና መከራ ለመቋቋም ያስችለናል።
ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት አሁንም እንኳ ጠንካራ የወንድማማች ፍቅር ማዳበር ያስፈልገናል።
በርካታ ወንድሞቻችን በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በኃይለኛ አውሎ ነፋስ፣ በሱናሚ ወይም በሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች የተነሳ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አንዳንድ ወንድሞች ደግሞ ተቃውሞና ስደት እያጋጠማቸው ነው።
ይህም እንዳይበቃ፣ ምግባረ ብልሹነት በተንሰራፋበት በዚህ ሥርዓት ውስጥ ስለምንኖር በየዕለቱ ኢኮኖሚያዊ ጫና ያታግለናል።
እንዲህ ያሉት ችግሮች እየጨመሩ ሲሄዱ የወንድማማች ፍቅራችንን ጥልቀት ለማሳየት የሚያስችሉን አጋጣሚዎችም ይጨምራሉ።
የብዙዎች ፍቅር ቢቀዘቅዝም እኛ ግን የወንድማማች ፍቅራችን ምንጊዜም እንዲቀጥል ማድረግ አለብን።
በጉባኤ፣ በወረዳና በክልል ስብሰባዎች ላይ ንግግር ሲሰጥ ማስታወሻ ትይዛለህ?
የያዝከውን ማስታወሻ መከለስህ ከአምላክ ቃልም ሆነ ከድርጅቱ በተማርካቸው ነገሮች ላይ ለማሰላሰል ግሩም አጋጣሚ ይከፍትልሃል።
በተጨማሪም በየወሩ የሚወጡት የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት እትሞች እንዲሁም በክልል ስብሰባ ላይ የሚወጡ አዳዲስ ጽሑፎች የምናነባቸውና የምናሰላስልባቸው መረጃዎች ይዘዋል።
የዓመት መጽሐፍ በምታነብበት ጊዜ ቆም ብለህ ማሰብህ እንዲሁም ባነበብካቸው ተሞክሮዎች ላይ ማሰላሰልህና ልብህ እንዲነካ ማድረግህ ጠቃሚ ነው።
ተመላልሶ መጠየቅ ወይም የእረኝነት ጉብኝት ለማድረግ አሊያም ንግግር ለመስጠት በምትዘጋጅበት ጊዜ ቁልፍ በሆኑ ሐሳቦች ላይ ማስመርህ ወይም በኅዳጉ ላይ ማስታወሻ መያዝህ ይጠቅምሃል።
ከሁሉ በላይ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎችን ስታነብ አልፎ አልፎ ቆም እያልክ ማሰላሰልህ ትምህርቱ ወደ ልብህ ዘልቆ እንዲገባና ለተማርከው መልካም ነገር ይሖዋን በጸሎት እንድታመሰግን አጋጣሚ ይሰጥሃል።
በመስክ አገልግሎት ስንካፈል ሌሎች እምነት እንዲያዳብሩ ከመርዳታችን በተጨማሪ የራሳችንም እምነት እያደገ ይሄዳል።
እንደ ጥንቶቹ ክርስቲያኖች ሁሉ በይሖዋ ላይ ጠንካራ እምነት እናዳብራለን፤ እንዲሁም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ በድፍረት መናገር እንችላለን።
ይሖዋ በሕይወታችን ውስጥ እንዴት እንደሚረዳንና ለጸሎታችን እንዴት መልስ እንደሚሰጥ ስንመለከት እምነታችን ያድጋል።
የካሌብና የኢያሱ ሁኔታ ይህን ያሳያል።
ተስፋይቱን ምድር በሰለሉበት ወቅት በይሖዋ ላይ እምነት እንዳላቸው አሳይተዋል።
ይሁንና ከዚያ በኋላ በእያንዳንዱ የሕይወታቸው ክፍል የይሖዋን አመራር ሲመለከቱ እምነታቸው ይበልጥ እያደገ ሄዷል።
ኢያሱ አምላካችሁ ይሖዋ ከገባላችሁ መልካም ቃል ሁሉ አንዲቷም እንኳ ሳትፈጸም አልቀረችም በማለት ለእስራኤላውያን በእርግጠኝነት መናገሩ የሚያስገርም አይደለም።
ከጊዜ በኋላም ስለዚህ ይሖዋን ፍሩ፤ በንጹሕ አቋምና በታማኝነትም አገልግሉት ብሏቸዋል።
እኛም የይሖዋን ጥሩነት ስንቀምስ እንዲህ ዓይነት የጸና እምነት ማዳበር እንችላለን።
እንዲሁም እሱን በሙሉ ልባችን፣ በሙሉ ነፍሳችን፣ በሙሉ አእምሯችንና በሙሉ ኃይላችን በመውደድ ለእሱ ያለን ፍቅር ምንጊዜም እየጨመረ ይሂድ!—⁠፤
የአምላክ ስምና የስሙ መቀደስ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ የሚያሳዩ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አሉ።
የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት የሆነው ይሖዋ አምላክ፣ ጸሐፊዎቹ ስሙን በተደጋጋሚ ጊዜያት እንዲጠቀሙበት በመንፈሱ መርቷቸዋል።
በጥንታዊ የቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂዎች ውስጥ በሺዎች በሚቆጠሩ ጊዜያት የሚገኘውን ስም ማውጣት ለመጽሐፉ ባለቤት አክብሮት ማጣት ነው።
የአምላክ ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የሚጠቁሙት ማስረጃዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መጥተዋል እንጂ አልቀነሱም።
በ2013 ተሻሽሎ በወጣው የእንግሊዝኛ አዲስ ዓለም ትርጉም ላይ የአምላክ ስም 7,216 ጊዜ የሚገኝ ሲሆን ይህ ቁጥር በ1984 በተዘጋጀው እትም ላይ ካለው በ6 ይበልጣል።
የአምላክ ስም የገባባቸው አምስት ተጨማሪ ቦታዎች ናቸው።
በእነዚህ ጥቅሶች ላይ የአምላክ ስም ቀድሞ በነበረበት ቦታ እንዲገባ የተደረገበት ዋነኛ ምክንያት፣ ማሶሬቶች ከገለበጡት የዕብራይስጥ ቅጂ 1,000 ዓመት በፊት በተዘጋጁት የሙት ባሕር ጥቅልሎች ላይ ስሙ ስለሚገኝ ነው።
ከዚህም ሌላ በጥንታዊ የቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂዎች ላይ በተደረገ ተጨማሪ ጥናት ምክንያት ላይ የአምላክ ስም እንዲገባ ተደርጓል።
በብዙ አገሮች የመጽሐፍ ቅዱስ ዋጋ ውድ ከመሆኑም በላይ በቀላሉ አይገኝም፤ ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስን ማግኘት በራሱ በረከት ነው።
ከሩዋንዳ የተላከ አንድ ሪፖርት እንዲህ ይላል፦ ወንድሞች መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስጠኗቸው ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ስለሌላቸው ለረጅም ጊዜ እድገት ሳያደርጉ ቆይተዋል።
በአካባቢያቸው የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን የሚያዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስ ውድ ስለሆነ ለመግዛት አቅማቸው አይፈቅድላቸውም።
በዚያ ላይ ደግሞ ብዙውን ጊዜ የአንዳንድ ጥቅሶችን ትርጉም መረዳት ይከብዳቸዋል፤ ይህም ለእድገታቸው እንቅፋት ሆኗል።
አዲስ ዓለም ትርጉም በአካባቢያቸው በሚነገረው ቋንቋ ሲዘጋጅ ግን ሁኔታዎች ይለወጣሉ።
በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ አራት ልጆች ያሏቸው በሩዋንዳ የሚኖሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት እንዲህ ብለዋል፦ ይህን መጽሐፍ ቅዱስ ስለሰጡን ይሖዋን እንዲሁም ታማኝና ልባም ባሪያን በእጅጉ እናመሰግናቸዋለን።
በጣም ድሆች ስለሆንን ለእያንዳንዱ የቤተሰባችን አባል መጽሐፍ ቅዱስ ለመግዛት ገንዘብ የለንም።
አሁን ግን ሁላችንም የየራሳችን መጽሐፍ ቅዱስ አለን።
አመስጋኝነታችንን ለይሖዋ ለመግለጽ መጽሐፍ ቅዱስን በቤተሰብ ሆነን በየዕለቱ እናነባለን።
ሐዋርያው ዮሐንስ፣ መጀመሪያ ከአምላክ ጋር የነበረውን አካል ቃል እንዲሁም የአምላክ ፍጥረት መጀመሪያ ሲል ጠርቶታል።
ይሖዋ አምላክ ሐሳቡንና ስሜቱን ለዚህ የበኩር ልጁ አካፍሎታል።
ሐዋርያው ጳውሎስ ደግሞ ስለ መላእክት ልሳን ተናግሯል፤ ይህም ከሰው ልጆች ቋንቋ እጅግ የሚልቅና በሰማይ ያሉ አካላት የሚግባቡበት ልሳን ነው።
ይሖዋ በምድርም ሆነ በሰማይ ስላሉት በቢሊዮን የሚቆጠሩ የማሰብ ችሎታ ያላቸው ፍጥረታት በሚገባ ያውቃል።
ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች በተመሳሳይ ጊዜ ላይ በበርካታ ቋንቋዎች ወደ እሱ ይጸልዩ ይሆናል።
ይሖዋ እነዚህን ሁሉ ጸሎቶች የሚሰማ ከመሆኑም ሌላ በዚያው ቅጽበት ለመላእክት መመሪያ ይሰጣል እንዲሁም ከእነሱ ጋር ይነጋገራል።
ይህን ሁሉ ለማከናወን እንዲችል ሐሳቡ፣ ቋንቋውና ከሌሎች ጋር የሚግባባበት መንገድ ከሰው ልጆች በእጅጉ የላቀ ሊሆን ይገባል።
በግልጽ ማየት እንደምንችለው ይሖዋ ለሰው ልጆች ሐሳቡን የሚያስተላልፈው እነሱ ሊረዱት በሚችሉ ቀለል ያለ መንገድ ነው።
አምላክ መሲሐዊውን መንግሥት ማቋቋሙ የሰው ልጆችን እንደሚወድ ያረጋግጣል።
ይሖዋ ይህን መንግሥት ለልጁ ሰጥቶታል፤ ኢየሱስ የሰው ልጆችን የሚወድ ከመሆኑም ሌላ እነሱን ለመግዛት የላቀ ብቃት አለው።
ከኢየሱስ ጋር ሰማያዊ ውርሻ የሚያገኙት 144,000ዎች ከሞት ከተነሱ በኋላ፣ ሰው ሆነው ሲኖሩ ያካበቱትን ልምድ ይጠቀሙበታል።
የኢየሱስ ስብከት ዋና ጭብጥ የአምላክ መንግሥት ሲሆን ደቀ መዛሙርቱንም ስለ መንግሥቱም ሆነ ስለሚያመጣቸው በረከቶች እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት እንደሚያሳየው በ1914 ክርስቶስ በሥልጣኑ ሲገኝ የአምላክ መንግሥት በሰማይ መግዛት ጀምሯል።
ከዚያ ጊዜ ወዲህ፣ ከኢየሱስ ጋር በሰማይ የሚገዙት ቅቡዓን ቀሪዎችና ከዚህ ሥርዓት ጥፋት ተርፈው ወደ አዲሱ ዓለም የሚገቡት እጅግ ብዙ ሕዝብ እየተሰበሰቡ ነው።
ክርስቲያን ወላጆች፣ ልጆቻቸው ሲጠመቁ ማየት በጣም እንደሚያስደስታቸው የታወቀ ነው።
አራቱም ልጆቿ 14 ዓመት ሳይሞላቸው የተጠመቁላት ቤረኒሲ እንዲህ ብላለች፦ የተደበላለቀ ስሜት ተሰምቶን ነበር።
ልጆቻችን ይሖዋን ለማገልገል መፈለጋቸው እንዳስደሰተን ጥያቄ የለውም።
ይሁንና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ በመሆናቸው ብዙ ተፈታታኝ ነገሮች እንደሚያጋጥሟቸው ተገንዝበን ነበር።
ስለ ልጆች ሥነ ልቦና የሚያጠኑ አንድ ባለሙያ፣ ወላጆች በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻቸው እንዳበዱ ወይም ብስለት እንደጎደላቸው አድርገው ሊያስቡ እንደማይገባ ተናግረዋል።
ከዚህ ይልቅ በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻቸው፣ በዚህ ጊዜ የፈጠራ ችሎታቸው እንደሚዳብር፣ ከጓደኞቻቸው ጋር ጊዜ ለማሳለፍ እንደሚፈልጉ እንዲሁም ለነገሮች ጠንካራ ስሜት እንደሚኖራቸውና ስሜታቸውን መግለጽ እንደሚፈልጉ መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
ልጆቻችሁ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያሉ ከይሖዋ ጋር ይበልጥ ትርጉም ያለው ወዳጅነት መመሥረት፣ ለአገልግሎታቸው ግብ ማውጣትና እዚያ ላይ ለመድረስ መሥራት እንዲሁም ራሳቸውን መወሰን ብሎም ከውሳኔያቸው ጋር ተስማምተው ለመኖር ጥረት ማድረግ ይችላሉ።
ልክ እንደ ኢየሱስ ሁሉ ለእነሱም ይህ ዕድሜ በመንፈሳዊ እድገት የሚያደርጉበት አስደሳች ጊዜ ሊሆንላቸው ይችላል።
ከአምላክ እንዲህ ያለ ልዩ ጥሪ ያገኙ ግለሰቦች ይህን የሚያረጋግጥላቸው ሌላ ምሥክር አይፈልጉም።
ለመቀባታቸው ማስተማመኛ የሚሰጣቸው ሌላ አካል አያስፈልጋቸውም።
ይሖዋ ስለዚህ ጉዳይ በልባቸው ውስጥ አንዳች ጥርጣሬ እንዳያድር ያደርጋል።
ሐዋርያው ዮሐንስ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን እናንተ ግን ቅዱስ ከሆነው ከእሱ የመንፈስ ቅብዓት አግኝታችኋል፤ ደግሞም ሁላችሁም እውቀት አላችሁ ብሏቸዋል።
አክሎም እንዲህ ብሏል፦ እናንተ ግን ከእሱ የተቀበላችሁት የመንፈስ ቅብዓት በውስጣችሁ ይኖራል፤ በመሆኑም ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ ከእሱ ያገኛችሁት ይህ ቅብዓት ስለ ሁሉም ነገር እያስተማራችሁ ነው፤ ደግሞም እውነት እንጂ ውሸት አይደለም።
ይህ ቅብዓት ባስተማራችሁ መሠረት ከእሱ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ኑሩ።
እነዚህ ቅቡዓን እንደ ማንኛውም ሰው መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት አለባቸው።
ይሁንና መቀባታቸውን ሌላ አካል እንዲያጸድቅላቸው አያስፈልግም።
ዳዊት ይህን የጻፈው እሱ በታመመበትና ሁኔታዎችን መቆጣጠር ባልቻለበት ወቅት አቤሴሎም ዙፋኑን ለመቀማት የተነሳበትን ጊዜ በማሰብ ሊሆን ይችላል።
ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ለፈጸመው ኃጢአት አምላክ ይቅር ቢለውም እሱ ግን በደሉንና ያስከተላቸውን መዘዞች አልረሳም።
ያም ቢሆን ንጉሡ ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ አምላክ እንደሚደግፈው እርግጠኛ ነበር።
ዳዊት የጸለየው ይሖዋ በተአምራዊ መንገድ እንዲፈውሰው አይደለም።
በጥቅሱ ዙሪያ ካለው ሐሳብ መረዳት እንደምንችለው ዳዊት ይሖዋን የጠየቀው፣ ለተቸገረ ሰው አሳቢነት ለሚያሳይ ግለሰብ የሚያደርገውን ነገር ለእሱም እንዲያደርግለት ነው።
ይህም ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ አምላክ የሚሰጠውን ድጋፍ ይጨምራል።
ዳዊት ኃጢአቱ ይቅር ስለተባለለት፣ አምላክ እንዲያጽናናውና እንዲደግፈው እንዲሁም ሰውነቱ በሽታውን ተቋቁሞ እንዲያገግም መጠየቅ ይችላል።
እኛም እንዲህ ዓይነት ጸሎት ማቅረብ እንችላለን።
ይሖዋ፣ እሱን ለማገልገል የምናደርገውን ማንኛውንም ጥረት ከፍ አድርጎ እንደሚመለከት እርግጠኞች መሆን እንችላለን።
በራስ ያለመተማመን ስሜት ሊያድርብን እንደሚችል ያውቃል።
ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ቢያስጨንቁን አሊያም የጤና ወይም የስሜት መቃወስ ቅዱስ አገልግሎታችንን ቢገድቡብን ይሖዋ ይራራልናል።
ይሖዋ፣ አገልጋዮቹ ለእሱ ታማኝ ለመሆን ሲሉ የሚያደርጓቸውን ነገሮች ከፍ አድርጎ እንደሚመለከት ሙሉ በሙሉ መተማመን እንችላለን።
በተጨማሪም ጸሎት ሰሚ የሆነው አምላክ የሚያሳስቡንን ነገሮች ስንነግረው እንደሚሰማን በመተማመን ወደ እሱ መቅረብ እንችላለን።