text
stringlengths
4
267
ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ፣ የፈራነውን ያህል መጥፎ ነገር ላይደርስ ይችላል።
በተጨማሪም የሚያስጨንቅህን ነገር ሁሉ ልትጥልበት ከምትችለው አምላክ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ምንም ነገር የለም።
አምላክ ታማኞቹን እንደሚባርክ ብሎም ከቀድሞ ሕይወታቸው እንዲሁም አሁን ካሉበትና ወደፊት ሊያጋጥማቸው ከሚችለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሚሰማቸውን ጭንቀት ለመቋቋም እንደሚረዳቸው እርግጠኛ ሁን።
ኢዮሳፍጥ ልክ እንደ አባቱ እንደ አሳ ሕዝቡ ይሖዋን እንዲፈልግ አበረታቷል።
የይሖዋን ሕግ መጽሐፍ የሚያስተምሩ ሰዎችን ወደ ይሁዳ ከተሞች ልኳል።
ከዚህም በላይ ሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት በሚያስተዳድረው ክልል ይኸውም በተራራማው የኤፍሬም ምድር የሚኖረውን ሕዝብ እንኳ ወደ ይሖዋ ለመመለስ እዚያ ድረስ ሄዷል።
በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ታላቅ የማስተማር ዘመቻ እያካሄደ ሲሆን ሁላችንም በዚህ ሥራ መካፈል እንችላለን።
በየወሩ ሌሎችን ስለ አምላክ ቃል በማስተማር ይሖዋን ለማገልገል እንዲነሳሱ የመርዳት ግብ አለህ?
አንተ በምታደርገው ጥረት ላይ የይሖዋ በረከት ታክሎበት ሰዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር ትችል ይሆናል።
እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ ወደ ይሖዋ ትጸልያለህ?
ከራስህ ጊዜ ላይ የተወሰነውን መሥዋዕት አድርገህም እንኳ ቢሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመምራት ፈቃደኛ ነህ?
ኢዮሳፍጥ፣ ሕዝቡን ወደ እውነተኛው አምልኮ ለመመለስ ወደ ኤፍሬም ክልል እንደሄደ ሁሉ እኛም ከጉባኤ የራቁትን ለመርዳት ጥረት ማድረግ እንችላለን።
አምላክ የግለሰቦችን ጤንነት የሚነካ እርምጃ መውሰድ እንደሚችል ጥያቄ የለውም።
እንዲህ የማድረግ ኃይል እንዳለው መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጥልናል።
ለምሳሌ በአብርሃም ዘመን የነበረውን ፈርዖንን እና ከጊዜ በኋላ ደግሞ የሙሴን እህት ሚርያምን እንዲታመሙ በማድረግ ቀጥቷቸዋል።
እስራኤላውያን ታማኝ ካልሆኑ በሽታዎችን ወይም መቅሰፍቶችን ሁሉ በማምጣት እንደሚቀጣቸው አምላክ አስጠንቅቋቸው ነበር።
በሌላ በኩል ደግሞ ይሖዋ በሽታን ማስወገድ ወይም ሕዝቡ እንዳይታመሙ ጥበቃ ማድረግ ይችላል።
በተጨማሪም ሰዎችን መፈወስ ይችላል።
ኢዮብ ሞትን እስኪመኝ ድረስ በጠና ታሞ የነበረ ቢሆንም አምላክ ፈውሶታል! አምላክ የታመመን ሰው የመፈወስ ኃይል እንዳለው ጥርጥር የለውም።
ልጁም ተመሳሳይ ኃይል አለው።
ኢየሱስ የሥጋ ደዌ ወይም የሚጥል በሽታ ያለባቸውን እንዲሁም ዓይነ ስውር አሊያም ሽባ የሆኑ ሰዎችን በተአምራዊ መንገድ እንደፈወሰ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
ኢየሱስ ያከናወናቸው ፈውሶች በአዲሱ ዓለም በላቀ ሁኔታ ለሚያከናውነው ነገር ቅምሻ እንደሆኑ ማወቅ ምንኛ ያበረታታል።
ቅዱስ ለሆነው አምላካችን፣ ለመንፈሳዊ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም በክልላችን ላሉ ሰዎች ያለን አክብሮት ለምንሰብከው መልእክትም ሆነ ለይሖዋ ክብር የሚያመጣ አለባበስ እንዲኖረን ያነሳሳናል።
በተለይ ደግሞ በክርስቲያናዊ እንቅስቃሴዎች ስንካፈል ለምሳሌ፣ ስብሰባዎች ላይ ስንገኝ ወይም ምሥራቹን ስንሰብክ ለአለባበሳችን ትኩረት መስጠት ይኖርብናል።
አለባበሳችን ለአምላክ ያደርን ነን ለሚሉ ሰዎች የሚገባ መሆን ይኖርበታል።
እርግጥ ነው፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ተገቢ የሚባለው አለባበስ በሌሎች አካባቢዎች ተገቢ ላይሆን ይችላል።
በመሆኑም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የአምላክ ሕዝቦች ሌሎችን ቅር ላለማሰኘት ሲሉ የአካባቢውን ባሕል ግምት ውስጥ ያስገባሉ።
በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ ስንገኝ አለባበሳችን በዓለም ላይ የተለመደውን ወጣ ያለ ፋሽን የሚያንጸባርቅ ሳይሆን ተገቢና ልከኛ ሊሆን ይገባል።
እንዲህ ካደረግን የይሖዋ ምሥክሮች መሆናችንን ለመናገር አንሸማቀቅም።
ለመመሥከር የሚያስችል አጋጣሚ ካገኘንም ነፃነት ተሰምቶን እንመሠክራለን።
ጳውሎስ የእምነት ምሳሌ የሚሆኑ የተለያዩ ወንዶችንና ሴቶችን ከዘረዘረ በኋላ ከሁሉ የላቀ አርዓያ ስለሆነው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተናግሯል።
ከፊቱ ለሚጠብቀው ደስታ ሲል፣ የሚደርስበትን ውርደት ከምንም ሳይቆጥር በመከራ እንጨት ላይ እስከ መሞት ድረስ ጸንቷል፤ እንዲሁም በአምላክ ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ይላል።
በእርግጥም፣ ኢየሱስ በጣም ከባድ ፈተናዎችን በመቋቋም የተወውን የእምነት ምሳሌ በጥሞና ማሰብ ይኖርብናል።
እንደ አንቲጳስ ያሉ በጥንት ዘመን የነበሩና ሰማዕት የሆኑ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል በንጹሕ አቋማቸው ጸንተዋል።
በመሆኑም እነዚህ የአምላክ አገልጋዮች የላቀ ትንሣኤ ያገኛሉ፤ ይኸውም ከሞት ተነስተው በሰማይ ይኖራሉ፤ ይህ ደግሞ የጥንቶቹ የእምነት ሰዎች ተስፋ ያደርጉት ከነበረው የተሻለ ትንሣኤ እንኳ የበለጠ ነው።
በሞት አንቀላፍተው የነበሩት ታማኝ ቅቡዓን በሙሉ፣ የአምላክ መንግሥት በ1914 ከተወለደ ብዙም ሳይቆይ ከሞት ተነስተው መንፈሳዊ ሕይወት ተቀብለዋል፤ እነዚህ ቅቡዓን ከኢየሱስ ጋር ሆነው በሰው ልጆች ላይ ይገዛሉ።
ኢየሱስ ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ደቀ መዛሙርቱን የዚህ ዓለም ገዢ ስለሆነው ስለ ዲያብሎስ ሦስት ጊዜ አስጠንቅቋቸዋል።
ኢየሱስ፣ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢቶች እንዳያስተውሉና መጨረሻው መቅረቡን እንዳይገነዘቡ በማድረግ ዲያብሎስ አእምሯቸውን እንደሚያጨልም ያውቅ ነበር።
ሰይጣን በዓለም ላይ ያሉ የሐሰት ሃይማኖቶችን ተጠቅሞ የሰዎችን አእምሮ እያሳወረ ነው።
ሰዎችን ስታነጋግሩ ምን ምላሽ እንደሚሰጡ አስተውላችኋል?
የዚህ ሥርዓት መጨረሻ መቅረቡንም ሆነ ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ እየገዛ መሆኑን ማስተዋል እንዳይችሉ ዲያብሎስ የማያምኑትን ሰዎች አእምሮ እንዳሳወረ እየተመለከትን አይደለም?
አብዛኞቹ ሰዎች ይህ ዓለም ወዴት እያመራ እንደሆነ ልንነግራቸው ስንሞክር ይህ ጉዳይ ብዙም ግድ እንደማይሰጣቸው እንመለከታለን።
የሰዎች ግድየለሽነት ተስፋ እንዲያስቆርጣችሁ ወይም ነቅታችሁ ከመጠበቅ እንዲያዘናጋችሁ አትፍቀዱ።
ነቅተን መጠበቅ ያለብን ለምን እንደሆነ እናውቃለን።
ይሖዋ፣ ማበረታቻ ሊሰጡን የሚችሉ አሳቢ የሆኑ ወንድሞች የሚገኙበት ዓለም አቀፋዊ የወንድማማች ማኅበር ሰጥቶናል።
በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ በርካታ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለ መንፈሳዊ ማበረታቻ አግኝተዋል።
በዛሬው ጊዜም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው።
ታዲያ እኛ ምን ማድረግ እንችላለን?
አሮን እና ሁር በውጊያው ወቅት ቃል በቃል የሙሴን እጅ ደግፈውለት እንደነበር አስታውሱ።
እኛም ሌሎችን መደገፍና መርዳት የምንችልባቸውን መንገዶች መፈለግ እንችላለን።
ማንን መርዳት እንችላለን?
የዕድሜ መግፋት፣ የጤና እክል፣ የቤተሰብ ተቃውሞ፣ ብቸኝነት ወይም የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት ከሚያስከትለው ተፈታታኝ ሁኔታ ጋር እየታገሉ ያሉ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን መርዳት እንችላለን።
በተጨማሪም መጥፎ ነገር እንዲሠሩ ወይም በዚህ ሥርዓት በትምህርትም ይሁን በሙያቸው ጥሩ ደረጃ የሚባለው ቦታ ላይ እንዲደርሱ አሊያም ሀብት እንዲያሳድዱ ከፍተኛ ጫና የሚደርስባቸውን ወጣቶች ማበረታታት እንችላለን።
ከወንድሞችና ከእህቶች ጋር በመንግሥት አዳራሽ ውስጥም ሆነ በአገልግሎት ላይ ስትሆኑ አሊያም አብራችሁ ስትመገቡ ወይም በስልክ ስታወሩ ልባዊ አሳቢነት ልታሳዩ የምትችሉባቸውን መንገዶች ለማሰብ ሞክሩ።
በወቅቱ ጢሞቴዎስ ተሞክሮ ያለው የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪ ነበር።
ሆኖም በአገልግሎቱ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ለሚያስተምረው ትምህርት ምንጊዜም ትኩረት ከሰጠ ብቻ ነው።
አዘውትሮ በሚጠቀምበት መንገድ መስበኩን ቢቀጥል፣ ሰዎች ሁልጊዜ ጥሩ ምላሽ እንደሚሰጡት መጠበቅ አይችልም።
የሰዎችን ልብ መንካት እንዲችል የማስተማር ዘዴዎቹን እንደ ሰዎቹ ሁኔታ መቀያየር ነበረበት።
እኛም የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች እንደመሆናችን መጠን ተመሳሳይ ነገር ማድረግ አለብን።
ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል ብዙ ጊዜ ሰዎችን ቤታቸው አናገኛቸውም።
ወደ አፓርታማዎች ወይም ወደ አንዳንድ የታጠሩ መኖሪያ ሰፈሮች መግባት አስቸጋሪ የሚሆንባቸው አካባቢዎች አሉ።
አንተም በክልልህ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ የሚያጋጥምህ ከሆነ ምሥራቹን ለመስበክ ለምን የተለያዩ ዘዴዎችን አትሞክርም?
ምሥራቹን ከምናዳርስባቸው ግሩም መንገዶች አንዱ የአደባባይ ምሥክርነት ነው።
ብዙ አስፋፊዎች ይህን የአገልግሎት ዘዴ ውጤታማና አስደሳች ሆኖ አግኝተውታል።
በባቡርና በአውቶቡስ ፌርማታዎች፣ በገበያ ቦታዎች፣ በመናፈሻዎችና ሰዎች በሚገኙባቸው ሌሎች ቦታዎች ምሥራቹን ለመስበክ ጥረት ያደርጋሉ።
አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን የማያደንቁት፣ የራሳቸው ወላጆች ምንም ዓይነት ማበረታቻ ሰጥተዋቸው ስለማያውቁ ነው።
በሥራው ዓለም ያሉ በርካታ ሰዎችም በሥራ ቦታቸው ጨርሶ ማበረታቻ እንደማያገኙ በምሬት ይናገራሉ።
ማበረታቻ መስጠት አንድ ሰው ላደረገው መልካም ነገር ማመስገንን ይጨምራል።
በተጨማሪም ሰዎች ያሏቸውን ጥሩ ባሕርያት በማድነቅ ወይም ተስፋ የቆረጡትን የሚያጽናና ነገር በመናገር ሌሎችን ማበረታታት ይቻላል።
ግርጌ አብዛኛውን ጊዜ ማበረታቻ ተብሎ የሚተረጎመው የግሪክኛ ቃል ቀጥተኛ ፍቺ ከጎኔ ሁን የሚል ነው።
ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር ስናገለግል እነሱን የሚያበረታታ ነገር ለመናገር አጋጣሚዎች ማግኘታችን አይቀርም።
ታዲያ አመቺ አጋጣሚዎችን ተጠቅመን፣ ሌሎችን እንድንወዳቸውና እንድናደንቃቸው የሚያደርጉንን ምክንያቶች እንነግራቸዋለን?
ለዚህ ጥያቄ መልስ ከመስጠታችን በፊት በትክክለኛው ጊዜ የተነገረ ቃል ምንኛ መልካም ነው! በሚለው ጥቅስ ላይ ማሰላሰላችን ጠቃሚ ነው።
ባለንበት ሁኔታ የተነሳ፣ የመንግሥቱን ሥራ ለመደገፍ ማከናወን የምንችለው ነገርና የምናደርገው መዋጮ ውስን ሊሆን ይችላል፤ ያም ቢሆን ይሖዋና ኢየሱስ ሁላችንም በዚህ ረገድ የምናደርገውን ጥረት በጣም ያደንቃሉ።
በዕድሜ ከገፉ ውድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መካከል አንዳንዶቹ በስብሰባዎች ላይ ለመገኘትና ተሳትፎ ለማድረግ እንዲሁም በአገልግሎት አዘውትረው ለመካፈል ብርቱ ጥረት ያደርጋሉ።
ታዲያ እነዚህን ክርስቲያኖች እንደምናደንቃቸው ልንገልጽላቸውና ልናበረታታቸው አይገባም?
አዎ፣ ሌሎችን ለማበረታታት የሚያስችሏችሁን አጋጣሚዎች ፈልጉ።
ወንድሞቻችንን እንድናደንቅ የሚያደርግ ነገር ካስተዋልን ይህን ከማድረግ ወደኋላ የምንልበት ምን ምክንያት አለ?
ጳውሎስና በርናባስ፣ በጵስድያ በምትገኘው አንጾኪያ በነበሩበት ጊዜ ያጋጠማቸውን ነገር እንመልከት።
በዚያ የነበረው ምኩራብ አለቆች ወንድሞች ሆይ፣ ሕዝቡን የሚያበረታታ የምትናገሩት ቃል ካላችሁ ተናገሩ አሏቸው።
በምላሹም ጳውሎስ ግሩም ንግግር ሰጣቸው።
እኛም ሌሎችን የሚያበረታታ ነገር መናገር የምንችል ከሆነ ለምን ዝም እንላለን?
ሌሎችን የማበረታታት ልማድ ካለን እነሱም በምላሹ ያበረታቱናል።
ጊዜያችን የተጣበበ ቢሆንም ሁላችንም ለግል ጥናትና ለቤተሰብ አምልኮ ጊዜ መመደብ ይኖርብናል።
ይሁንና ግባችን በጥናቱ ወቅት የተወሰኑ ገጾችን መሸፈን ወይም በስብሰባዎች ላይ የምንሰጠውን ሐሳብ መዘጋጀት ብቻ መሆን የለበትም።
የአምላክ ቃል ልባችንን እንዲነካውና እምነታችንን እንዲያጠናክረው ማድረግ እንፈልጋለን።
በመሆኑም በምናጠናበት ጊዜ ሌሎች ስለሚያስፈልጓቸው ነገሮች ብቻ ሳይሆን እኛ ራሳችን ስለሚያስፈልገን ነገር ማሰብ አለብን።
ለአገልግሎት፣ ለስብሰባዎች ወይም ንግግር ለማቅረብ ስንዘጋጅ ትምህርቱን እኛ ራሳችን እንዴት ተግባራዊ እንደምናደርገው ላናስብ እንችላለን።
ነጥቡን በምሳሌ ለማስረዳት፦ የምግብ ዝግጅት ባለሙያ የሆነ ሰው ምግቡን ለሌሎች ከማቅረቡ በፊት መቅመስ ቢኖርበትም በዚህ ብቻ መኖር አይችልም።
ጤናማ መሆን ከፈለገ ለራሱም ገንቢ ምግብ ማዘጋጀት ይኖርበታል።
በተመሳሳይ እኛም መንፈሳዊ ፍላጎታችንን የሚያረካ ምግብ ለመመገብ ጥረት ማድረግ አለብን።
በትዳር ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች መንስኤው የትዳር ጓደኛሞች ከእውነታው የራቁ ነገሮችን መጠበቃቸው ሊሆን ይችላል።
አንድ ሰው ትዳሩ አስደሳች እንደሚሆን ተስፋ አድርጎ ይህ እውን ሳይሆን ሲቀር እርካታ ሊያጣ፣ እንደተታለለ ሊሰማው አልፎ ተርፎም በምሬት ሊዋጥ ይችላል።
ባልና ሚስት ስሜታቸውን የሚገልጹበት መንገድ ተመሳሳይ አለመሆኑ ወይም በመካከላቸው የአስተዳደግ ልዩነት መኖሩ ችግሮች እንዲከሰቱ ሊያደርግ ይችላል፤ አሊያም ደግሞ ከገንዘብ፣ ከአማቶች ወይም ከልጅ አስተዳደግ ጋር በተያያዘ አለመግባባት ሊፈጠር ይችላል።
ይሁንና አብዛኞቹ ክርስቲያን ባለትዳሮች የአምላክን መመሪያ ስለሚከተሉ፣ ለእነዚህ ችግሮች ሁለቱንም ወገኖች የሚያስማሙ መፍትሔዎችን ማግኘት ችለዋል፤ ይህም የሚያስመሰግናቸው ነው።
በትዳራቸው ውስጥ ከባድ ችግር ያጋጠማቸው ባለትዳሮች፣ ሽማግሌዎች እንዲረዷቸው መጠየቅ አለባቸው።
ተሞክሮ ያላቸው እነዚህ ወንድሞች፣ ባለትዳሮች በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ምክር ተግባራዊ እንዲያደርጉ ሊረዷቸው ይችላሉ።
በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ስንጥር፣ ይሖዋ መንፈሱን እንዲሰጠን እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በተግባር ለማዋልና የመንፈስ ፍሬ ለማፍራት እንዲረዳን መጸለይም ይኖርብናል።
ኢየሱስ አገልግሎቱን ለማከናወን ያለው ጊዜ ውስን ነበር።
ሆኖም ለምሥራቹ ጥሩ ምላሽ የሰጡ ሰዎችን ፍላጎት ለማሳደግ ጊዜ መድቧል።