text stringlengths 4 267 |
|---|
የያዕቆብ ድርሻ ግን እንደነዚህ ነገሮች አይደለም፤እሱ የሁሉ ነገር ሠሪ ነውና፤እስራኤልም የርስቱ በትር ነው። ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው። |
አንቺ የተከበብሽ ሴት፣ጓዝሽን ከመሬት ላይ ሰብስቢ። |
ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፣ በዚህ ጊዜ ነዋሪዎቹን ከምድሪቱ ውጭ እወረውራቸዋለሁ፤ጭንቀት እንዲይዛቸውም አደርጋለሁ።” |
ስብራት ደርሶብኛልና ወዮልኝ! ቁስሌ የማይድን ነው። እኔም እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ ይህ የእኔ ሕመም ነው፤ ልሸከመውም ይገባል። |
ድንኳኔ ፈርሷል፤ የድንኳኔም ገመዶች ሁሉ ተበጥሰዋል። ወንዶች ልጆቼ ጥለውኝ ሄደዋል፤ ከዚህ በኋላ አይኖሩም። ድንኳኔን የሚተክልልኝ ወይም የድንኳኔን ሸራዎች የሚዘረጋልኝ አንድም ሰው የለም። |
እረኞቹ የሞኝነት ድርጊት ፈጽመዋልና፤ይሖዋንም አልጠየቁም። ማስተዋል የጎደለው ድርጊት የፈጸሙት ለዚህ ነው፤መንጎቻቸውም ሁሉ ተበታትነዋል።” |
አዳምጡ! አንድ ወሬ ስሙ! ወደዚህ እየመጣ ነው! የይሁዳን ከተሞች ባድማና የቀበሮዎች ጎሬ ሊያደርግከሰሜን ምድር ድም፣ ድም የሚል ኃይለኛ ድምፅ እየቀረበ ነው። |
ይሖዋ ሆይ፣ የሰው መንገድ በራሱ እጅ እንዳልሆነ በሚገባ አውቃለሁ። አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም። |
ይሖዋ ሆይ፣ አርመኝ፤ሆኖም ፈጽመህ እንዳታጠፋኝ በፍትሕ እንጂ በቁጣህ አይሁን። |
አንተን ችላ በሚሉ ብሔራትእንዲሁም ስምህን በማይጠሩ ነገዶች ላይ ቁጣህን አፍስስ። ያዕቆብን በልተውታልና፤አዎ፣ ሙሉ በሙሉ እስኪጠፋ ድረስ በልተውታል፤የትውልድ አገሩንም አውድመዋል። |
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“በዚህ ስፍራ ሚስት አታግባ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም አትውለድ። |
ይሖዋ በዚህ ስለሚወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲሁም በዚህች ምድር ስለሚወልዷቸው እናቶችና አባቶች እንዲህ ይላልና፦ |
‘በገዳይ በሽታዎች ይሞታሉ፤ ይሁንና ማንም አያለቅስላቸውም ወይም አይቀብራቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ። በሰይፍና በረሃብ ይጠፋሉ፤ አስከሬናቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።’ |
ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦‘ለለቀስተኞች ድግስ ወደተዘጋጀበት ቤት አትግባ፤እዚያም ሄደህ አታልቅስ ወይም አታስተዛዝን።’ ‘ሰላሜን ከዚህ ሕዝብ ወስጄአለሁና’ ይላል ይሖዋ፤‘ታማኝ ፍቅሬና ምሕረቴ ከእነሱ እንዲርቅ አድርጌአለሁ። |
ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች በዚህች ምድር ላይ ይሞታሉ። ደግሞም አይቀበሩም፤ማንም ሰው አያዝንላቸውም፤ለእነሱ ሲል ሰውነቱን የሚተለትልም ሆነ ራሱን የሚላጭ አይኖርም። |
ሰው የሞተባቸውንም ለማጽናናትየእዝን እንጀራ የሚወስድላቸው አይኖርም፤አባት ወይም እናት ለሞተባቸውምየመጽናኛ ጽዋ እንዲጠጡ የሚሰጣቸው አይኖርም። |
ከእነሱ ጋር ተቀምጠህ ለመብላትና ለመጠጣትግብዣ ወደተዘጋጀበት ቤት አትግባ።’ |
“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በዚህ ስፍራ፣ በእናንተ ዘመን ዓይናችሁ እያየ የሐሴትንና የደስታን ድምፅ እንዲሁም የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ አስወግዳለሁ።’ |
“ይህን ሁሉ ቃል ለዚህ ሕዝብ በምትነግርበት ጊዜ እንዲህ ብለው ይጠይቁሃል፦ ‘ይሖዋ ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ የተናገረው ለምንድን ነው? በአምላካችን በይሖዋ ላይ የፈጸምነው በደልና ኃጢአት ምንድን ነው?’ |
አንተም እንዲህ ብለህ ትመልስላቸዋለህ፦ ‘“አባቶቻችሁ እኔን ስለተዉ ነው” ይላል ይሖዋ፤ “ደግሞም ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ስላገለገሉ እንዲሁም ስለሰገዱላቸው ነው። እኔን ግን ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም። |
እናንተ ደግሞ አባቶቻችሁ ከፈጸሙት የባሰ ነገር አድርጋችኋል፤ እያንዳንዳችሁም እኔን ከመታዘዝ ይልቅ ግትር የሆነውን ክፉ ልባችሁን ተከተላችሁ። |
ስለዚህ ከዚህች ምድር አስወጥቼ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቁት ምድር እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ሌሎች አማልክትን ቀን ከሌት ታገለግላላችሁ፤ ምክንያቱም እኔ ምንም ምሕረት አላሳያችሁም።”’ |
“‘ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ “የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ባወጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ” የማይሉበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤ |
‘ከዚህ ይልቅ “እስራኤላውያንን ከሰሜን ምድርና እነሱን ከበተነባቸው አገሮች ሁሉ ሰብስቦ ባመጣቸው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ” ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት፣ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።’ |
‘እነሆ፣ እኔ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰዳለሁ’ ይላል ይሖዋ፤‘እነሱንም ያጠምዷቸዋል። ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እሰዳለሁ፤እነሱም ከየተራራው፣ ከየኮረብታውናከየቋጥኙ ስንጣቂ አድነው ይይዟቸዋል። |
ዓይኖቼ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ ላይ ነውና። ከፊቴ አልተሸሸጉም፤በደላቸውም ከዓይኔ አልተሰወረም። |
በመጀመሪያ፣ ለሠሩት በደልና ኃጢአት የሚገባቸውን ሙሉ ዋጋ እከፍላቸዋለሁ፤ምድሬን አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቻቸው በድን ምስሎች አርክሰዋልና፤ርስቴንም አስነዋሪ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋል።’” |
ብርታቴና መጠጊያዬ፣በጭንቀት ጊዜ መሸሸጊያዬ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣ብሔራት ከምድር ዳርቻዎች ወደ አንተ ይመጣሉ፤እንዲህም ይላሉ፦ “አባቶቻችን ፍጹም ውሸትን፣ከንቱ የሆኑና ምንም ጥቅም የሌላቸውን የማይረቡ ነገሮች ወርሰዋል።” |
ሰው ለራሱ አማልክት ሊሠራ ይችላል?የሚሠራቸው አማልክት እውነተኛ አማልክት አይደሉም። |
“ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤በዚህ ጊዜ ኃይሌንና ብርታቴን እንዲያውቁ አደርጋለሁ፤እነሱም ስሜ ይሖዋ መሆኑን ያውቃሉ።” |
በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ወዲያና ወዲህ ተመላለሱ። ዙሪያውን ተመልከቱ፤ ልብ በሉ። ፍትሕን የሚያደርግ፣ታማኝ መሆን የሚሻ ሰውም ታገኙ እንደሆነበአደባባዮቿ ፈልጉ፤እኔም ይቅር እላታለሁ። |
“ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!” ቢሉም የሚምሉት ሐሰት ለሆነ ነገር ነው። |
ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖችህ የሚመለከቱት ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት አይደለም? አንተ መተሃቸዋል፤ በእነሱ ላይ ግን ያመጣው ለውጥ የለም። አንተ አድቅቀሃቸዋል፤ እነሱ ግን አልታረሙም። ፊታቸውን ከዓለት ይልቅ አጠነከሩ፤ለመመለስም አሻፈረን አሉ። |
እኔ ግን ለራሴ እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ እነዚህ ምስኪኖች ናቸው። የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድ ባለማወቃቸውየሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ። |
ታዋቂ ወደሆኑት ሰዎች ሄጄ አነጋግራቸዋለሁ፤እነሱ የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድአስተውለው መሆን አለበትና። ነገር ግን ሁሉም ቀንበሩን ሰብረዋል፤ማሰሪያውንም በጥሰዋል።” |
ስለዚህ ከጫካ የወጣ አንበሳ ይሰባብራቸዋል፤የበረሃ ተኩላም ይቦጫጭቃቸዋል፤ነብር በከተሞቻቸው አቅራቢያ አድብቶ ይጠብቃል። ከዚያ የሚወጣውንም ሁሉ ይዘነጣጥላል። በደላቸው በዝቷልና፤የክህደት ሥራቸው ተበራክቷል። |
ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ይቅር እልሻለሁ? ወንዶች ልጆችሽ ትተውኛል፤አምላክ ባልሆነውም ይምላሉ። እኔም የሚያስፈልጋቸውን ነገር አሟላሁላቸው፤እነሱ ግን ምንዝር መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤ወደ ዝሙት አዳሪ ቤትም እየተንጋጉ ሄዱ። |
እንደሚቅበጠበጡ፣ ብርቱ ፈረሶች ናቸው፤እያንዳንዱ የሌላውን ሰው ሚስት ተከትሎ ያሽካካል። |
“ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ። “እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል አይገባም?” |
“የወይን እርሻዋን እርከኖች ሄዳችሁ አበላሹ፤ሆኖም ሙሉ በሙሉ አታጥፉት። የተንሰራፉ ቅርንጫፎቿን አስወግዱ፤የይሖዋ አይደሉምና። |
የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤትበእኔ ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽመዋልና” ይላል ይሖዋ። |
“እነሱ ይሖዋን ክደዋል፤‘እሱ ምንም ነገር አያደርግም። በእኛ ላይ ምንም ጥፋት አይመጣም፤ሰይፍም ሆነ ረሃብ አናይም’ ይላሉ። |
ነቢያቱ በነፋስ የተሞሉ ናቸው፤ቃሉም በውስጣቸው የለም። ይህ በእነሱ ላይ ይድረስ!” |
ስለዚህ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነዚህ ሰዎች እንዲህ ስለሚሉ፣ቃሌን በአፋችሁ ውስጥ እሳት አደርጋለሁ፤እንጨቱ ደግሞ ይህ ሕዝብ ነው፤እሳቱም ይበላቸዋል።” |
“የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሩቅ ቦታ ያለን ብሔር አመጣባችኋለሁ” ይላል ይሖዋ። “እሱም ለረጅም ጊዜ የኖረ ብሔር ነው። ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረ፣ቋንቋውን የማታውቀውናንግግሩን የማትረዳው ብሔር ነው። |
የፍላጻ ኮሮጇቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው፤ሁሉም ተዋጊዎች ናቸው። |
እነሱ አዝመራህንና ምግብህን ይበላሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይበላሉ። መንጎችህንና ከብቶችህን ይበላሉ። የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ይበላሉ። የምትታመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችህን በሰይፍ ያወድማሉ።” |
“ይሁንና በእነዚያ ቀናት እንኳ” ይላል ይሖዋ፣ “ሙሉ በሙሉ አላጠፋችሁም። |
‘አምላካችን ይሖዋ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረገብን ለምንድን ነው?’ ብለው ሲጠይቁ ደግሞ ‘በምድራችሁ ላይ ባዕድ አምላክን ለማገልገል ስትሉ እኔን እንደተዋችሁኝ ሁሉ የራሳችሁ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።” |
ይህን በያዕቆብ ቤት ተናገሩ፤በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ አውጁ፦ |
“እናንተ ሞኞችና የማመዛዘን ችሎታ የጎደላችሁ ሰዎች ይህን ስሙ፦ ዓይን አላቸው ግን አያዩም፤ጆሮ አላቸው ግን አይሰሙም። |
‘እኔን አትፈሩም?’ ይላል ይሖዋ፤‘በፊቴስ ልትሸበሩ አይገባም? ውኃው አልፎ እንዳይሄድ፣ በማይሻር ድንጋጌአሸዋውን የባሕሩ ወሰን አድርጌ የሠራሁት እኔ ነኝ። ሞገዶቹ ቢናወጡም ጥሰው መሄድ አይችሉም፤ቢያስገመግሙም ከዚያ አልፈው መሄድ አይችሉም። |
ነገር ግን ይህ ሕዝብ ልቡ ግትርና ዓመፀኛ ነው፤ጀርባቸውን ሰጥተው በራሳቸው መንገድ ሄደዋል። |
እነሱም በልባቸው “እንግዲያው፣ ዝናቡን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብበወቅቱ የሚሰጠንን፣የተወሰኑትን የአዝመራ ሳምንታት የሚጠብቅልንንአምላካችንን ይሖዋን እንፍራ” አላሉም። |
የገዛ ራሳችሁ በደል እነዚህ ነገሮች እንዲቀሩ አድርጓል፤የገዛ ኃጢአታችሁ መልካም የሆነ ነገር አሳጥቷችኋል። |
በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና። አድብተው እንደሚጠብቁ ወፍ አዳኞች፣ በዓይነ ቁራኛ ይመለከታሉ። ገዳይ ወጥመድ ይዘረጋሉ። ሰዎችን ያጠምዳሉ። |
በወፎች እንደተሞላ የወፍ ጎጆ፣ቤቶቻቸው በማታለያ የተሞሉ ናቸው። ኃያላንና ሀብታም የሆኑት ለዚህ ነው። |
ወፍረዋል፤ ቆዳቸውም ለስልሷል፤በክፋት ተሞልተዋል። ለራሳቸው ስኬት ሲያስቡአባት ለሌለው ልጅ አይሟገቱም፤ድሆችንም ፍትሕ ይነፍጋሉ።’” |
“ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ። “እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል አይገባም? |
በምድሪቱ ላይ የሚያስደነግጥና የሚያሰቅቅ ነገር ተከስቷል፦ |
ነቢያቱ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ካህናቱም በራሳቸው ሥልጣን በኃይል ይገዛሉ። የገዛ ሕዝቤም ይህን ወዶታል። ይሁንና መጨረሻው ሲመጣ ምን ታደርጉ ይሆን?” |
ብሔራትን አስመልክቶ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ |
የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውንና የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በካርከሚሽ ድል ያደረገውን የግብፅን ንጉሥ የፈርዖን ኒካዑን ሠራዊት በተመለከተ ለግብፅ የተነገረ መልእክት፦ |
“ትንሹንና ትልቁን ጋሻችሁን አዘጋጁ፤ለውጊያም ውጡ። |
እናንተ ፈረሰኞች፣ ፈረሶችን ጫኑ፤ በላያቸውም ተቀመጡ። ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ የራስ ቁራችሁንም አድርጉ። ጦሩን ወልውሉ፤ ጥሩራችሁንም ልበሱ። |
‘እንዲህ ተሸብረው ያየኋቸው ለምንድን ነው? እያፈገፈጉ ነው፤ ተዋጊዎቻቸው ተፍረክርከዋል። በድንጋጤ እግሬ አውጪኝ ብለዋል፤ ተዋጊዎቻቸው ወደ ኋላ አልተመለከቱም። በየቦታው ሽብር ነግሦአል’ ይላል ይሖዋ። |
‘ፈጣን የሆኑት መሸሽ አይችሉም፤ ተዋጊዎቹም ማምለጥ አይችሉም። በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ ዳርቻተሰናክለው ወድቀዋል።’ |
እንደ አባይ ወንዝ፣እንደሚናወጥም የወንዝ ውኃ ሆኖ የሚመጣው ይህ ማን ነው? |
ግብፅ እንደ አባይ ወንዝናእንደሚናወጥ የወንዝ ውኃ ሆኖ ይመጣል፤ደግሞም ‘እወጣለሁ፤ ምድርንም እሸፍናለሁ። ከተማዋንና ነዋሪዎቿን አጠፋለሁ’ ይላል። |
እናንተ ፈረሶች፣ ወደ ላይ ውጡ! እናንተ ሠረገሎች፣ በፍጥነት ገስግሱ! ተዋጊዎቹ ይውጡ፤ጋሻ የሚያነግቡት የኢትዮጵያ እና የፑጥ ሰዎችእንዲሁም ደጋን የመወጠርና በጥበብ የመጠቀም ችሎታ ያላቸው የሉድ ሰዎች ይውጡ። |
“ያ ቀን የሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን ነው። ሰይፉ ይበላል፤ ይጠግባልም፤ ደማቸውንም እስኪረካ ድረስ ይጠጣል፤ ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ በሚገኘው የሰሜን ምድር መሥዋዕት አዘጋጅቷልና። |
ድንግሊቱ የግብፅ ሴት ልጅ ሆይ፣ወደ ጊልያድ ወጥተሽ በለሳን አምጪ። መድኃኒት የምታበዢው እንዲያው በከንቱ ነው፤ፈውስ አታገኚምና። |
ብሔራት በአንቺ ላይ የደረሰውን ውርደት ሰምተዋል፤ጩኸትሽም አገር ምድሩን አናውጧል። ተዋጊ በተዋጊው ይሰናከላልና፤ሁለቱም በአንድነት ተያይዘው ወድቀዋል።” |
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር የግብፅን ምድር ለመምታት ስለመምጣቱ ይሖዋ ለነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ |
“ይህን በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶል አውጁት። በኖፍ እና በጣፍነስ አውጁት። እንዲህም በሉ፦ ‘ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ተዘጋጁም፤ሰይፍ በዙሪያችሁ ያለውን ሁሉ ይበላልና። |
ኃያላኖቻችሁ ተጠራርገው የጠፉት ለምንድን ነው? ጸንተው መቆም አልቻሉም፤ይሖዋ ገፍትሮ ጥሏቸዋልና። |
ብዙዎቹ ይሰናከላሉ፤ ደግሞም ይወድቃሉ። እርስ በርሳቸውም “ተነሱ! ከጨካኙ ሰይፍ የተነሳወደ ሕዝባችንና ወደ ትውልድ አገራችን እንመለስ” ይባባላሉ።’ |
በዚያም ‘ያገኘውን አጋጣሚ ያልተጠቀመበትየግብፅ ንጉሥ ፈርዖንጉራውን የሚነዛው በከንቱ ነው’ ብለዋል። |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ተብሎ የተጠራው ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤እሱ በተራሮች መካከል እንዳለው እንደ ታቦርናበባሕር አጠገብ እንዳለው እንደ ቀርሜሎስ ሆኖ ይመጣል። |
አንቺ በግብፅ የምትኖሪ ሴት ልጅ ሆይ፣በግዞት ለመሄድ ጓዝሽን አሰናጂ። ኖፍ አስፈሪ ቦታ ትሆናለችና፤በእሳት ትጋያለች፤ ማንም ሰው የማይኖርባትም ምድር ትሆናለች። |
ግብፅ እንደምታምር ጊደር ናት፤ሆኖም ከሰሜን ተናዳፊ ዝንቦች ይመጡባታል። |
በመካከሏ ያሉት ቅጥረኛ ወታደሮችም እንኳ እንደሰቡ ጥጆች ናቸው፤ይሁንና እነሱም ጭምር ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ሸሽተዋል። ጸንተው መቆም አልቻሉም፤የሚጠፉበት ቀን፣የሚመረመሩበትም ጊዜ ደርሶባቸዋልና።’ |
‘ድምፅዋ እየተጥመዘመዘ እንደሚሄድ እባብ ድምፅ ነው፤ዛፍ እንደሚቆርጡ ሰዎችመጥረቢያ ይዘው በኃይል ይመጡባታልና። |
በውስጡ ማለፍ የማይቻል ቢመስልም ጫካዋን ይመነጥራሉ’ ይላል ይሖዋ። ‘ቁጥራቸው ከአንበጣ ይበልጥ ይበዛልና፤ ስፍር ቁጥርም የላቸውም። |
የግብፅ ሴት ልጅ ለኀፍረት ትዳረጋለች። ለሰሜን ሰዎች ትሰጣለች።’ |
“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አሁን ትኩረቴን በኖእ ከተማ ወደሚገኘው ወደ አምዖን፣ ወደ ፈርዖን፣ ወደ ግብፅ፣ ወደ አማልክቷና ወደ ነገሥታቷ፣ አዎ በፈርዖንና በእሱ ወደሚታመኑት ሰዎች ሁሉ አደርጋለሁ።’ |
“‘ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ ሰዎች፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾርና ለአገልጋዮቹ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ከዚያ በኋላ ግን እንደቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች’ ይላል ይሖዋ። |
‘አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፤እስራኤልም ሆይ፣ አትሸበር። አንተን ከሩቅ ቦታ፣ዘሮችህንም ተማርከው ከተወሰዱበት ምድር አድናለሁና። ያዕቆብ ይመለሳል፤ የሚያስፈራውም ሳይኖርተረጋግቶና ሰላም አግኝቶ ይቀመጣል። |
ስለዚህ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘እኔ ከአንተ ጋር ነኝና። አንተን የበተንኩባቸውን ብሔራት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም። በተገቢው መጠን እገሥጽሃለሁ እንጂበምንም ዓይነት ሳልቀጣ አልተውህም።’” |
ድርቅን አስመልክቶ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ |
ይሁዳ ታለቅሳለች፤ በሮቿም ወላልቀዋል። በሐዘን ተውጠው መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ከኢየሩሳሌምም ጩኸት ይሰማል። |
ጌቶቻቸውም አገልጋዮቻቸውን ውኃ እንዲፈልጉ ላኳቸው። እነሱም ወደ ውኃ ጉድጓዶቹ ሄዱ፤ ውኃ ግን አላገኙም። ባዶ ዕቃ ይዘው ተመለሱ። በኀፍረት ተዋጡ፤ ተስፋም ቆረጡ፤ራሳቸውንም ተከናነቡ። |
በምድሪቱ ላይ ዝናብ ባለመዝነቡ የተነሳመሬቱ ስለተሰነጣጠቀገበሬዎቹ እጅግ አዘኑ፤ ራሳቸውንም ተከናነቡ። |
በሜዳ ያለች እንስት ርኤም እንኳምንም ሣር ባለመኖሩ እንደወለደች ግልገሏን ጥላ ትሄዳለች። |
የዱር አህዮች በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ይቆማሉ። እንደ ቀበሮ አየር አጥሯቸው ያለከልካሉ፤ምንም ዓይነት ተክል ባለመኖሩ ዓይኖቻቸው ፈዘዙ። |
ይሖዋ ሆይ፣ የገዛ ራሳችን በደል በእኛ ላይ የሚመሠክርብን ቢሆንምለስምህ ስትል እርምጃ ውሰድ። የክህደት ሥራችን በዝቷልና፤ኃጢአት የሠራነውም በአንተ ላይ ነው። |
አንተ የእስራኤል ተስፋ፣ በጭንቀትም ጊዜ አዳኙ የሆንክ ሆይ፣በምድሪቱ እንደ እንግዳ፣ሌሊቱን ለማሳለፍ ሲል ብቻ ጎራ እንዳለ መንገደኛ የሆንከው ለምንድን ነው? |
ክው ብሎ እንደቀረ ሰው፣ማዳን እንደማይችል ኃያል ሰው የሆንከው ለምንድን ነው? ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በመካከላችን ነህና፤እኛም በስምህ ተጠርተናል። እባክህ አትተወን። |
ይሖዋ ይህን ሕዝብ አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦ “መቅበዝበዝ ይወዳሉ፤ እግራቸውን አልሰበሰቡም። ስለዚህ ይሖዋ በእነሱ ደስ አይሰኝም። አሁን በደላቸውን ያስባል፤ በኃጢአታቸውም የተነሳ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።” |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.