text
stringlengths
4
267
የሴዴቅያስንም ዓይን አሳወረ፤ ከዚያም ወደ ባቢሎን ለመውሰድ በመዳብ የእግር ብረት አሰረው።
ከለዳውያንም የንጉሡን ቤትና የሕዝቡን ቤቶች አቃጠሉ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች አፈረሱ።
የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን በከተማዋ ውስጥ የቀሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎችና ከድተው ለእሱ እጃቸውን የሰጡትን ሰዎች እንዲሁም የቀሩትን ሁሉ በግዞት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።
ሆኖም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ምንም ነገር ያልነበራቸውን አንዳንድ ያጡ የነጡ ድሆች በይሁዳ ምድር እንዲኖሩ ተዋቸው። ደግሞም በዚያ ቀን የወይን እርሻዎችና የሚያርሱት የእርሻ መሬት ሰጣቸው።
በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ኤርምያስን አስመልክቶ የዘቦች አለቃ ለሆነው ለናቡዛራዳን እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠ፦
“ወስደህ የሚያስፈልገውን እንክብካቤ አድርግለት፤ ክፉ ነገር አታድርግበት፤ የሚጠይቅህንም ነገር ሁሉ አድርግለት።”
በመሆኑም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን፣ ራብሳሪስ የሆነው ናቡሻዝባን፣ ራብማግ የሆነው ኔርጋልሻሬጸር እንዲሁም የባቢሎን ንጉሥ ሹማምንት ሁሉ ልከው
ኤርምያስን ከክብር ዘቦቹ ግቢ አስወጡት፤ ደግሞም ወደ ቤቱ እንዲወስደው ለሳፋን ልጅ፣ ለአኪቃም ልጅ፣ ለጎዶልያስ ሰጡት። በመሆኑም ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ተቀመጠ።
ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ ተዘግቶበት በነበረ ጊዜ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦
“ሂድና ለኢትዮጵያዊው ለኤቤድሜሌክ እንዲህ በለው፦ ‘የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በዚህች ከተማ ላይ ለመልካም ሳይሆን ለጥፋት ቃሌን እፈጽማለሁ፤ በዚያም ቀን ይህ ሲፈጸም ታያለህ።”’
“‘አንተን ግን በዚያ ቀን እታደግሃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለምትፈራቸውም ሰዎች አልፈህ አትሰጥም።’
“‘የምታመልጥበትን መንገድ አዘጋጅልሃለሁ፤ በሰይፍም አትወድቅም። በእኔ ስለታመንክ ሕይወትህ እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች’ ይላል ይሖዋ።”
በይሖዋ ቤት ዋና ሹም የነበረው የኢሜር ልጅ ካህኑ ጳስኮር፣ ኤርምያስ እነዚህን ነገሮች ሲተነብይ ሰማ።
ጳስኮርም ነቢዩ ኤርምያስን መታው፤ ከዚያም በይሖዋ ቤት ባለው በላይኛው የቢንያም በር በእግር ግንድ ጠረቀው።
ይሁንና በማግስቱ ጳስኮር ኤርምያስን ከእግር ግንዱ ውስጥ ፈታው፤ በዚህ ጊዜ ኤርምያስ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ፣ ማጎርሚሳቢብ ብሎ ይጠራሃል እንጂ ጳስኮር አይልህም።
ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘አንተም ሆንክ ወዳጆችህ እንድትሸበሩ አደርጋለሁ፤ እነሱም ዓይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይሁዳንም ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እሱም በግዞት ወደ ባቢሎን ይወስዳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።
የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን ሁሉ፣ ውድ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ እንዲሁም የይሁዳን ነገሥታት ውድ ሀብት ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እነሱም ይበዘብዟቸዋል፤ ወደ ባቢሎንም ያግዟቸዋል።
ጳስኮር ሆይ፣ አንተና በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ በግዞት ትወሰዳላችሁ። ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ፤ በዚያም ትሞታለህ፤ ከወዳጆችህም ሁሉ ጋር በዚያ ትቀበራለህ፤ ምክንያቱም ለእነሱ የሐሰት ትንቢት ተናግረሃል።’”
ይሖዋ ሆይ፣ አሞኘኸኝ፤ እኔም ተሞኘሁ። አንተ በእኔ ላይ በረታህ፤ አሸነፍክም። እኔም ቀኑን ሙሉ መሳለቂያ ሆንኩ፤ሁሉም ያፌዙብኛል።
በተናገርኩ ቁጥር እጮኻለሁና፤“ዓመፅና ጥፋት!” ብዬ አውጃለሁ። የይሖዋ ቃል ቀኑን ሙሉ ስድብና ፌዝ አስከትሎብኛል።
ስለዚህ “እሱን አላነሳም፤ከእንግዲህም በስሙ አልናገርም” አልኩ። ይሁንና ቃሉ በልቤ ውስጥ እንዳለ፣ በአጥንቶቼም ውስጥ እንደገባ የሚነድ እሳት ሆነብኝ፤አፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ከዚህ በላይ መቋቋም አልቻልኩም።
ብዙ መጥፎ ወሬ ሰምቻለሁና፤በዙሪያዬ ያለው ሁኔታ አሸብሮኛል። “አውግዙት፤ እናውግዘው!” ሰላም የሚመኝልኝ ሰው ሁሉ የእኔን ውድቀት ይጠባበቃል፦ “ምናልባት ይታለል ይሆናል፤እኛም እናሸንፈዋለን፤ ደግሞም እንበቀለዋለን።”
ይሖዋ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነበር። ከዚህም የተነሳ የሚያሳድዱኝ ሰዎች ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም። ስለማይሳካላቸውም ለከፍተኛ ኀፍረት ይዳረጋሉ። የሚደርስባቸው ዘላለማዊ ውርደት ፈጽሞ አይረሳም።
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ጻድቁን ትመረምራለህ፤የውስጥ ሐሳብንና ልብን ታያለህ። በእነሱ ላይ የምትወስደውን የበቀል እርምጃ እንዳይ አድርገኝ፤ጉዳዬን ለአንተ አቅርቤአለሁና።
ለይሖዋ ዘምሩ! ይሖዋን አወድሱ! እሱ ድሃውን ከክፉ አድራጊዎች እጅ ታድጓልና።
የተወለድኩበት ቀን የተረገመ ይሁን! እናቴ እኔን የወለደችበት ቀን አይባረክ!
ለአባቴ “ልጅ፣ አዎ ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል!” የሚል ምሥራች አብስሮ እጅግ ደስ ያሰኘው ሰው የተረገመ ይሁን።
ያ ሰው፣ ይሖዋ ያላንዳች ጸጸት እንደገለበጣቸው ከተሞች ይሁን። በማለዳ ዋይታ፣ በቀትርም የጦርነት ሁካታ ይስማ።
እናቴ የመቃብሬ ቦታ እንድትሆን፣ማህፀኗም ዘወትር እርጉዝ እንደሆነ ይኖር ዘንድ፣ገና በማህፀን ሳለሁ ለምን አልገደለኝም?
ችግርንና ሐዘንን እንዳይ፣ዕድሜዬም በኀፍረት እንዲያከትምለምን ከማህፀን ወጣሁ?
ይሖዋ ሆይ፣ አቤቱታዬን ለአንተ ሳቀርብ፣ከፍትሕ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ሳናግርህ እነሆ፣ አንተ ጻድቅ ነህ። ታዲያ የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል?ደግሞስ ከዳተኞች ሳይጨነቁ የሚኖሩት ለምንድን ነው?
አንተ ተክለሃቸዋል፤ እነሱም ሥር ሰደዋል። አድገዋል፤ ፍሬም አፍርተዋል። ከከንፈራቸው አይለዩህም፤ የውስጥ ሐሳባቸው ግን ከአንተ የራቀ ነው።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን በሚገባ ታውቀኛለህ፤ ታየኛለህም፤ልቤን መረመርክ፤ ከአንተም ጋር የሚስማማ ሆኖ አገኘኸው። ለእርድ እንደተዘጋጁ በጎች ለያቸው፤ለሚገደሉበትም ቀን ለይተህ አቆያቸው።
ምድሪቱ ተራቁታ፣የሜዳውም ተክል ሁሉ ደርቆ የሚቆየው እስከ መቼ ድረስ ነው? በምድሪቱ በሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሳአራዊቱና ወፎቹ ተጠራርገው ጠፉ። እነሱ፣ “ወደፊት ምን እንደሚገጥመን አያውቅም” ብለዋልና።
ከእግረኞች ጋር ሮጠህ ከደከምክ፣ከፈረሶች ጋር እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ? በሰላም ምድር ተማምነህ ብትቀመጥ እንኳጥቅጥቅ ባለው የዮርዳኖስ ጥሻ ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው?
የገዛ ወንድሞችህ፣የገዛ አባትህ ቤተሰቦች እንኳ አታለውሃልና። እነሱ በአንተ ላይ ጮኸዋል። መልካም ነገር ቢናገሩህ እንኳፈጽሞ አትመናቸው።
“ቤቴን ትቻለሁ፤ ርስቴን ጥዬ ሄጃለሁ። እጅግ የምወዳትን በጠላቶቿ እጅ አሳልፌ ሰጥቻታለሁ።
ርስቴ በጫካ ውስጥ እንዳለ አንበሳ ሆነችብኝ። በእኔ ላይ ጮኻብኛለች። በዚህም የተነሳ ጠላኋት።
ርስቴ ለእኔ ብዙ ቀለማት እንዳለው አዳኝ አሞራ ነች፤ሌሎች አዳኝ አሞሮች ይከቧታል፤ ደግሞም ያጠቋታል። እናንተ የዱር አራዊት ሁሉ ኑ፤ በአንድነት ተሰብሰቡ፤ትቀራመቷት ዘንድ ኑ።
ብዙ እረኞች የወይን እርሻዬን አጥፍተውታል፤ይዞታዬንም ረግጠውታል። የተወደደውን ይዞታዬን ጠፍ ምድረ በዳ አድርገውታል።
ባድማ ሆኗል። ደግሞም ተራቁቷል፤በፊቴ ወና ሆኗል። ምድሪቱ በሙሉ ባድማ ሆናለች፤ይሁንና ይህን ልብ ያለ አንድም ሰው የለም።
በምድረ በዳ ባሉት፣ በተበላሹ መንገዶች ሁሉ አጥፊዎች መጥተዋል፤የይሖዋ ሰይፍ ከአንዱ ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ ምድሪቱን ትበላለችና። ማንም ሰው ሰላም የለውም።
ስንዴ ዘሩ፤ ሆኖም እሾህን አጨዱ። እስኪዝሉ ድረስ ሠሩ፤ ነገር ግን ምንም ጥቅም አላገኙም። ከሚነደው የይሖዋ ቁጣ የተነሳበሚያገኙት ምርት ያፍራሉ።”
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እስራኤል እንዲወርሰው ያደረግኩትን ርስት የሚነኩ ክፉ ጎረቤቶቼን ሁሉ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅላለሁ።
ከነቀልኳቸው በኋላ ግን ዳግመኛ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸውን ወደየርስታቸው፣ እያንዳንዳቸውንም ወደየምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።”
“ሕዝቤን በባአል እንዲምሉ እንዳስተማሩ ሁሉ እነሱም የሕዝቤን መንገድ በእርግጥ ቢማሩና ‘ሕያው ይሖዋን!’ ብለው በስሜ ቢምሉ በሕዝቤ መካከል ጸንተው ይኖራሉ።
ይሁንና ከእነዚህ ብሔራት መካከል የማይታዘዝ ቢኖር ያን ብሔር እነቅለዋለሁ፤ ነቅዬም አጠፋዋለሁ” ይላል ይሖዋ።
የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ሞዓብ እንዲህ ይላል፦ “ወዮ፣ ነቦ ጠፍታለችና! ቂርያታይም ኀፍረት ተከናንባለች፤ ደግሞም ተይዛለች። አስተማማኝ የሆነው መጠጊያ ተዋርዷል፤ ፈራርሷልም።
ከእንግዲህ ሞዓብን አያወድሷትም። ለውድቀት ትዳረግ ዘንድ፣ ‘ኑ ብሔር መሆኗ እንዲያከትም እንደምስሳት’ ብለው በሃሽቦን ይዶልቱባታል። አንቺም ማድመን ሆይ፣ ዝም በይ፤ከኋላሽ ሰይፍ ይከተልሻልና።
ከሆሮናይም የጩኸት ድምፅእንዲሁም የጥፋትና የታላቅ ውድቀት ድምፅ ይሰማል።
ሞዓብ ጠፍታለች። ልጆቿ ይጮኻሉ።
ወደ ሉሂት በሚወስደው አቀበት እያለቀሱ ይወጣሉ። በደረሰው ጥፋት የተነሳ፣ ከሆሮናይም ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ሲወርዱም የጭንቅ ጩኸት ይሰማሉ።
ሽሹ፤ ሕይወታችሁን አትርፉ! በምድረ በዳ እንዳለ የጥድ ዛፍ ሁኑ።
ምክንያቱም አንቺ በሥራሽና ውድ በሆነ ሀብትሽ ትታመኛለሽ፤ደግሞም ትያዣለሽ። ከሞሽ ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋርበአንድነት በግዞት ይወሰዳል።
አጥፊው በእያንዳንዱ ከተማ ላይ ይመጣል፤አንድም ከተማ አያመልጥም። ይሖዋ በተናገረው መሠረትሸለቆው ይጠፋል፤ ደልዳላውም መሬት እንዳልነበረ ይሆናል።
ለሞዓብ ምልክት አቁሙ፤ስትፈራርስ ትሸሻለችና፤ከተሞቿም አስፈሪ ቦታ ይሆናሉ፤የሚቀመጥባቸውም ሰው አይኖርም።
ይሖዋ የሰጠውን ተልእኮ በግድየለሽነት የሚያከናውን የተረገመ ነው! ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚመልስ ሰው የተረገመ ነው!
ሞዓባውያን ከልጅነታቸው ጀምሮበአምቡላው ላይ እንደረጋ ወይን ጠጅ ተረጋግተው ተቀምጠዋል። ከአንዱ ዕቃ ወደ ሌላው ዕቃ አልተገላበጡም፤በግዞትም ተወስደው አያውቁም። በዚህም ምክንያት ቃናቸው እንዳለ ነው፤መዓዛቸውም አልተለወጠም።
“‘ስለዚህ፣ እነሆ እነሱን እንዲገለብጡ ሰዎችን የምልክበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ። ‘እነሱም ይገለብጧቸዋል፤ ዕቃዎቻቸውንም ባዶ ያስቀራሉ፤ ትላልቅ እንስራዎቻቸውንም ይሰባብራሉ።
የእስራኤል ቤት ይተማመንበት በነበረው በቤቴል እንዳፈረ ሁሉ ሞዓባውያንም በከሞሽ ያፍራሉ።
“እኛ ለውጊያ የተዘጋጀን ኃያላን ተዋጊዎች ነን” በማለት እንዴት በድፍረት ትናገራላችሁ?’
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ተብሎ የሚጠራው ንጉሥ እንዲህ ይላል፦‘ሞዓብ ጠፍታለች፤ከተሞቿ ተወረዋል፤ ምርጥ የሆኑት ወጣቶቻቸውም ታርደዋል።’
በሞዓባውያን ላይ የሚደርሰው ጥፋት ቀርቧል፤ውድቀታቸውም በፍጥነት እየቀረበ ነው።
በዙሪያቸው ያሉ ሁሉ፣ስማቸውን የሚያውቁ ሁሉ አብረዋቸው ያዝናሉ። ‘ኃያሉ በትር፣ የውበትም ዘንግ እንዴት ተሰበረ!’ በሏቸው።
አንቺ በዲቦን የምትኖሪ ሴት ልጅ ሆይ፣ከክብርሽ ውረጂ፤ ተጠምተሽም ተቀመጪ፤የሞዓብ አጥፊ በአንቺ ላይ መጥቶብሻልና፤የተመሸጉ ቦታዎችሽንም ያፈራርሳል።
አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ፣ መንገዱ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ። የሚሸሸውን ወንድና የምታመልጠውን ሴት ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።
ሞዓብ ኀፍረት ተከናነበች፤ በሽብርም ተውጣለች። ዋይ ዋይ በሉ፤ እንዲሁም ጩኹ። ሞዓብ መጥፋቷን በአርኖን አውጁ።
“ፍርድ ወደ ደልዳላው መሬት መጥቷል፤ በሆሎን፣ በያሃጽና በመፋአት፣
በዲቦን፣ በነቦና በቤትዲብላታይም፣
በቂርያታይም፣ በቤትጋሙልና በቤትምዖን፣
በቀሪዮትና በቦስራ እንዲሁም በሩቅና በቅርብ ባሉ የሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቷል።
‘የሞዓብ ብርታት ተቆርጧል፤ክንዱም ተሰብሯል’ ይላል ይሖዋ።
‘በይሖዋ ላይ ስለ ታበየ አስክሩት። ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለላል፤መሳለቂያም ሆኗል።
እስራኤል የአንተ መሳለቂያ ሆኖ አልነበረም? ራስህን የምትነቀንቀውና እሱን የምትቃወመውእስራኤል ከሌቦች ጋር ተገኝቶ ነው?
እናንተ የሞዓብ ነዋሪዎች፣ ከከተሞቹ ወጥታችሁ በቋጥኝ ላይ ኑሩ፤በገደል አፋፍ ጎጆዋን እንደምትሠራ ርግብም ሁኑ።’”
“ስለ ሞዓብ ኩራት ሰምተናል፤ እሱ በጣም ትዕቢተኛ ነው፤ስለ እብሪቱ፣ ስለ ኩራቱ፣ ስለ ትዕቢቱና ስለ ልቡ ማበጥ ሰምተናል።”
“‘ቁጣውን አውቃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤‘ሆኖም ጉራው ከንቱ ይሆናል። አንዳች ነገር አያደርጉም።
ከዚህ የተነሳ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤ለሞዓብ ምድር ሁሉ እጮኻለሁ፤ለቂርሄረስ ነዋሪዎችም እቃትታለሁ።
የሲብማ ወይን ሆይ፣ ለያዜር ከተለቀሰው በበለጠለአንቺ አለቅሳለሁ። የተንዠረገጉት ቅርንጫፎችሽ ባሕሩን ተሻግረዋል። እስከ ባሕሩ፣ እስከ ያዜርም ደርሰዋል። አጥፊው በበጋ ፍሬሽናለመከር በደረሰው ወይንሽ ላይ መጥቷል።
ከፍራፍሬ እርሻውና ከሞዓብ ምድርሐሴትና ደስታ ጠፍቷል። ከወይን መጭመቂያዎቹ ወይን መፍሰሱን እንዲያቆም አድርጌአለሁ። በእልልታ ወይን የሚረግጥ ሰው አይኖርም። ጩኸቱ ለየት ያለ ጩኸት ይሆናል።’”
“‘በሃሽቦን የሚያስተጋባው ጩኸት እስከ ኤልዓሌ ድረስ ይሰማል። እስከ ያሃጽ ድረስ ድምፃቸውን ያሰማሉ፤በዞአር የሚያስተጋባው ጩኸት እስከ ሆሮናይምና እስከ ኤግላት ሸሊሺያ ድረስ ይሰማል። የኒምሪም ውኃዎች እንኳ ይደርቃሉ።
ከፍ ባለ የማምለኪያ ቦታ ላይ መባ የሚያቀርበውንናለአምላኩ መሥዋዕት የሚያቀርበውን ሰውከሞዓብ አጠፋለሁ’ ይላል ይሖዋ።
‘ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት በሐዘን ያንጎራጉራል፤ለቂርሄረስ ሰዎችም ልቤ እንደ ዋሽንት በሐዘን ያንጎራጉራል። ያከማቸው ሀብት ይጠፋልና።
ራስ ሁሉ ተመልጧል፤ጢምም ሁሉ ተላጭቷል። እጅ ሁሉ ተሸንትሯል፤በወገባቸውም ላይ ማቅ ታጥቀዋል!’”
“‘በሞዓብ ጣሪያዎች ሁሉናበአደባባዮቿ ሁሉ ላይከዋይታ ሌላ የሚሰማ ነገር የለም። ሞዓብን እንደተጣለ እንስራሰባብሬአታለሁና’ ይላል ይሖዋ።
‘እጅግ ተሸብራለች! ዋይ ዋይ በሉ! ሞዓብ ኀፍረት ተከናንቦ ጀርባውን አዙሯል! ሞዓብ መሳለቂያ ሆኗል፤በዙሪያው ያሉት ሁሉ ከእሱ የተነሳ ይደነግጣሉ።’”
“ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ ተወንጭፎ እንደሚወርድ ንስር፣እሱም በሞዓብ ላይ ክንፎቹን ይዘረጋል።
ከተሞቹ ይወረራሉ፤ምሽጎቿም ይያዛሉ። በዚያ ቀን የሞዓብ ተዋጊዎች ልብምጥ እንደያዛት ሴት ልብ ይሆናል።’”
“‘ሞዓብም ሕዝብ መሆኑ ያከትማል፤በይሖዋ ላይ ታብዮአልና።
የሞዓብ ነዋሪ ሆይ፣ሽብር፣ ጉድጓድና ወጥመድ ይጠብቅሃል’ ይላል ይሖዋ።
‘ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ ጉድጓዱ ውስጥ ይወድቃል፤ከጉድጓዱም የሚወጣ ሁሉ በወጥመዱ ይያዛል።’ ‘የሚቀጡበትን ዓመት በሞዓብ ላይ አመጣለሁና’ ይላል ይሖዋ።
‘የሚሸሹት ሰዎች ኃይላቸው ተሟጦ በሃሽቦን ጥላ ሥር ይቆማሉ። ከሃሽቦን እሳት፣ከሲሖን መካከልም ነበልባል ይወጣልና። የሞዓብን ግንባርናየሁከት ልጆችን ራስ ቅል ይበላል።’
‘ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ! የከሞሽ ሰዎች ጠፍተዋል። ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፤ሴቶች ልጆችህም በግዞት ተወስደዋል።
በዘመኑ መጨረሻ ግን፣ ከሞዓብ የተማረኩትን እሰበስባለሁ’ ይላል ይሖዋ። ‘በሞዓብ ላይ የተላለፈው የፍርድ መልእክት እዚህ ላይ ይደመደማል።’”
ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦
“ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፤ እኔም በዚያ ቃሌን አሰማሃለሁ።”
ስለዚህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ወረድኩ፤ እሱም በሸክላ መዘውሮቹ ላይ እየሠራ ነበር።
ሆኖም ሸክላ ሠሪው በጭቃ እየሠራ የነበረው ዕቃ እጁ ላይ ተበላሸ። በመሆኑም ሸክላ ሠሪው ተስማሚ ሆኖ ባገኘው መንገድ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።
ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይህ ሸክላ ሠሪ እንዳደረገው እኔም በእናንተ ላይ ማድረግ አልችልም?’ ይላል ይሖዋ። ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ ጭቃ፣ እናንተም በእኔ እጅ እንዲሁ ናችሁ።