text
stringlengths
4
267
ግብፅ ከሌሎቹ መንግሥታት ያነሰች ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ሌሎች ብሔራትን አትጨቁንም፤ ደግሞም በጣም ትንሽ ስለማደርጋቸው ሌሎች ብሔራትን መግዛት አይችሉም።
ግብፅ ለእስራኤል ቤት ዳግመኛ መታመኛ አትሆንም፤ ይልቁንም ከግብፃውያን እርዳታ በመሻት ለሠሩት ስህተት መታሰቢያ ትሆናለች። እነሱም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”
በ27ኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ሠራዊቱ በጢሮስ ላይ ታላቅ ግዳጅ እንዲፈጽም አደረገ። ራስ ሁሉ ተመልጧል፤ ትከሻም ሁሉ ተልጧል። ይሁን እንጂ እሱም ሆነ ሠራዊቱ በጢሮስ ላይ ላፈሰሱት ጉልበት ያገኙት ዋጋ የለም።
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ የግብፅን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር እሰጣለሁ፤ እሱም ሀብቷን ያግዛል፤ በእጅጉ ይበዘብዛል እንዲሁም ይመዘብራል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደሞዝ ይሆናል።’
“‘በእሷ ላይ ላፈሰሰው ጉልበት የግብፅን ምድር ካሳ አድርጌ እሰጠዋለሁ፤ ምክንያቱም ይህን ያደረጉት ለእኔ ነው’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
“በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድ እንዲበቅል አደርጋለሁ፤ ለአንተም በእነሱ መካከል መናገር የምትችልበት አጋጣሚ እከፍትልሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”
በስድስተኛውም ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፣ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ በዚያ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ እጅ ያዘኝ።
እነሆም እሳት የሚመስል ነገር ተመለከትኩ፤ ወገቡ ከሚመስለው ነገር በታች እሳት ነበር፤ ደግሞም ከወገቡ በላይ መልኩ እንደሚያብረቀርቅ ብረት ደማቅ ነበር።
ከዚያም እጅ የሚመስል ነገር ዘርግቶ የራስ ፀጉሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል ይዞ ወሰደኝ፤ አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ቅናት የሚቀሰቅሰው የቅናት ጣዖት ምልክት ወደቆመበት በሰሜን ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው ግቢ በር አመጣኝ።
እነሆም፣ በሸለቋማው ሜዳ አይቼው የነበረውን የሚመስል የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበር።
ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እባክህ ዓይንህን አንስተህ ወደ ሰሜን ተመልከት” አለኝ። ስለዚህ ወደ ሰሜን ተመለከትኩ፤ በዚያም ከመሠዊያው በር በስተ ሰሜን በኩል መግቢያው ላይ ይህ የቅናት ምልክት ነበር።
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ከመቅደሴ እንድርቅ የሚያደርጉ ነገሮች ይኸውም የሚፈጽሟቸውን አስከፊና አስጸያፊ ነገሮች ትመለከታለህ? ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮችን ገና ታያለህ።”
ከዚያም ወደ ቅጥር ግቢው መግቢያ አመጣኝ፤ እኔም ስመለከት በግድግዳው ላይ አንድ ቀዳዳ አየሁ።
እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እስቲ ግድግዳውን ንደለው” አለኝ። እኔም ግድግዳውን ነደልኩት፤ አንድ መግቢያም ተመለከትኩ።
እሱም “ወደ ውስጥ ግባና በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ተመልከት” አለኝ።
እኔም ገብቼ አየሁ፤ መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታትንና የሚያስጠሉ አራዊትን ሁሉ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ የእስራኤል ቤት ጣዖቶችን ሁሉ ምስል ተመለከትኩ፤ ምስላቸውም በግድግዳው ዙሪያ ተቀርጾ ነበር።
ደግሞም 70 የሚሆኑ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በምስሎቹ ፊት ቆመው ነበር፤ የሳፋን ልጅ ያአዛንያህ በመካከላቸው ቆሞ ነበር። እያንዳንዳቸውም በእጃቸው ጥና የያዙ ሲሆን መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጭስም እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር።
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዳቸው ጣዖቶቻቸው ባሉባቸው እልፍኞች ውስጥ በጨለማ ምን እንደሚያደርጉ ታያለህ? እነሱ ‘ይሖዋ አያየንም። ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል’ ይላሉና።”
ደግሞም “እነሱ የሚሠሯቸውን ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለኝ።
በመሆኑም በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ይሖዋ ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፤ በዚያም ሴቶች ተቀምጠው ታሙዝ ለተባለው አምላክ ሲያለቅሱ አየሁ።
እሱም በመቀጠል “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ? ከእነዚህ የባሰ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለኝ።
በመሆኑም ወደ ይሖዋ ቤት ውስጠኛው ግቢ አመጣኝ። በዚያም በይሖዋ ቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ በበረንዳውና በመሠዊያው መካከል 25 ያህል ወንዶች ነበሩ፤ እነሱም ጀርባቸውን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ ሰጥተው ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ነበር፤ ደግሞም በምሥራቅ አቅጣጫ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ? የይሁዳ ቤት እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች መፈጸማቸው፣ ምድሪቱን በዓመፅ መሙላታቸውና እኔን ማስቆጣታቸው ቀላል ነገር ነው? እነሆ፣ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫዬ አቅርበዋል።
በመሆኑም በቁጣ እርምጃ እወስዳለሁ። ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም። በታላቅ ድምፅ ወደ ጆሮዬ ቢጮኹም አልሰማቸውም።”
“እኔም ሜዶናዊው ዳርዮስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት፣ እሱን ለማበረታታትና ለማጠናከር ቆሜ ነበር።
አሁን የምነግርህ ነገር እውነት ነው፦ “እነሆ፣ ሦስት ተጨማሪ ነገሥታት በፋርስ ምድር ይነሳሉ፤ አራተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይበልጥ ብዙ ሀብት ያከማቻል። በሀብቱም በበረታ ጊዜ፣ ሁሉንም ነገር በግሪክ መንግሥት ላይ ያስነሳል።
“አንድ ኃያል ንጉሥ ይነሳል፤ በታላቅ ኃይልም ይገዛል፤ የፈለገውንም ያደርጋል።
ሆኖም በተነሳ ጊዜ መንግሥቱ ይፈራርሳል፤ ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት አቅጣጫ ይከፋፈላል፤ ለልጆቹ ግን አይተላለፍም፤ ግዛታቸው እንደ እሱ ግዛት አይሆንም፤ መንግሥቱ ይነቀላልና፤ ከእነሱም ለሌሎች ይተላለፋል።
“የደቡቡ ንጉሥ ይኸውም ከገዢዎቹ አንዱ ብርቱ ይሆናል፤ ይሁንና አንዱ በእሱ ላይ ያይላል፤ ከዚያኛው የገዢነት ሥልጣንም በላቀ ኃይል ይገዛል።
“ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ኅብረት ይፈጥራሉ፤ የደቡቡ ንጉሥ ሴት ልጅ ስምምነት ለማድረግ ወደ ሰሜኑ ንጉሥ ትመጣለች። ሆኖም የክንዷ ኃይል አይጸናም፤ ደግሞም እሱም ሆነ ክንዱ አይጸናም፤ እሷም አልፋ ትሰጣለች፤ እሷና ያመጧት ሰዎች፣ የወለዳትና በዚያ ዘመን ብርቱ እንድትሆን ያደረጋት አልፈው ይሰጣሉ።
ከሥሮቿም ከሚበቅለው ቀንበጥ አንዱ በእሱ ቦታ ይነሳል፤ እሱም ወደ ሠራዊቱ ይመጣል፤ በሰሜኑ ንጉሥ ምሽግም ላይ ይዘምታል፤ በእነሱም ላይ እርምጃ ይወስዳል፤ ያሸንፋቸዋልም።
በተጨማሪም አማልክታቸውን፣ ከብረት የተሠሩ ምስሎቻቸውን፣ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ጠቃሚ ዕቃዎቻቸውንና ምርኮኞቹን ይዞ ወደ ግብፅ ይመጣል። ለተወሰኑ ዓመታት ከሰሜኑ ንጉሥ ርቆ ይቆማል፤
የሰሜኑም ንጉሥ የደቡቡን ንጉሥ መንግሥት ይወርራል፤ ሆኖም ወደ ገዛ ምድሩ ይመለሳል።
“ወንዶች ልጆቹም ለጦርነት ይዘጋጃሉ፤ እጅግ ታላቅ ሠራዊትም ያሰባስባሉ። እሱ በእርግጥ ይገሰግሳል፤ እንደ ጎርፍም ምድሪቱን እያጥለቀለቀ ያልፋል። ሆኖም ይመለሳል፤ ወደ ምሽጉም እስከሚደርስ ድረስ ይዋጋል።
“የደቡቡም ንጉሥ በምሬት ተሞልቶ ይወጣል፤ ደግሞም ከእሱ ይኸውም ከሰሜኑ ንጉሥ ጋር ይዋጋል፤ ይሄኛውም ታላቅ ሠራዊት ያሰልፋል፤ ይሁንና ሠራዊቱ ለዚያኛው እጅ አልፎ ይሰጣል።
ሠራዊቱም ተጠራርጎ ይወሰዳል። ልቡም ይታበያል፤ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጠፋል፤ ሆኖም ያገኘውን ጥሩ አጋጣሚ አይጠቀምበትም።
“የሰሜኑም ንጉሥ ይመለሳል፤ ከመጀመሪያውም የሚበልጥ ሠራዊት ያሰባስባል፤ ከተወሰነ ጊዜ ይኸውም ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ በሚገባ የታጠቀ ታላቅ ሠራዊት ይዞ ይመጣል።
በዚያ ዘመን ብዙዎች በደቡቡ ንጉሥ ላይ ይነሳሉ። “በሕዝብህ መካከል ያሉ ዓመፀኛ ሰዎች ይነሳሉ፤ ደግሞም ራእይን ለመፈጸም ይጥራሉ፤ ሆኖም አይሳካላቸውም።
“የሰሜኑም ንጉሥ ይመጣል፤ የአፈር ቁልልም ይደለድላል፤ የተመሸገችንም ከተማ ይይዛል። የደቡቡ ክንዶችም ሆኑ የተመረጡት ተዋጊዎቹ አይቋቋሙትም፤ ለመቋቋም የሚያስችል ኃይልም አይኖራቸውም።
በእሱ ላይ የሚመጣው እንደፈለገው ያደርጋል፤ በፊቱም የሚቆም አይኖርም። ውብ በሆነችው ምድር ላይ ይቆማል፤ የማጥፋትም ኃይል ይኖረዋል።
የመንግሥቱን ወታደራዊ ኃይል በሙሉ አሰባስቦ ለመምጣት ፊቱን ያቀናል፤ ከእሱም ጋር ስምምነት ያደርጋል፤ እርምጃም ይወስዳል። የሴቶችንም ሴት ልጅ እንዲያጠፋ ይፈቀድለታል። እሷም አትጸናም፤ የእሱም ሆና አትቀጥልም።
እሱም ፊቱን ወደ ባሕር ዳርቻዎች በመመለስ ብዙ ቦታዎችን ይይዛል። አንድ አዛዥ ከእሱ የደረሰበትን ነቀፋ ያስቀራል፤ ከዚያ በኋላ የሚሰነዘርበት ነቀፋ ይቆማል። ነቀፋውንም በራሱ ላይ ይመልስበታል።
ከዚያም ፊቱን በገዛ ምድሩ ወደሚገኙት ምሽጎች ይመልሳል፤ ተሰናክሎም ይወድቃል፤ ደግሞም አይገኝም።
“በእሱም ቦታ የሚነሳው ዕፁብ ድንቅ በሆነው ግዛቱ የሚያልፍ አስገባሪ ይልካል፤ ይሁንና በቁጣ ወይም በጦርነት ባይሆንም እንኳ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይሰበራል።
“በእሱም ቦታ የተናቀ ሰው ይነሳል፤ እነሱም ንጉሣዊ ክብር አይሰጡትም፤ እሱም ሰዎች ተረጋግተው በሚኖሩበት ጊዜ ይመጣል፤ መንግሥቱንም በብልጠት ይይዛል።
የጎርፉም ክንዶች በእሱ የተነሳ ተጠራርገው ይወሰዳሉ፤ ደግሞም ይሰበራሉ፤ የቃል ኪዳኑም መሪ ይሰበራል።
እነሱም ከእሱ ጋር በማበራቸው ማታለሉን ይቀጥላል፤ ደግሞም ይነሳል፤ በጥቂት ሕዝብ አማካኝነትም ኃያል ይሆናል።
ሰዎች ተረጋግተው በሚኖሩበት ጊዜ ወደበለጸገው የአውራጃው ክፍል ይገባል፤ አባቶቹና የአባቶቹ አባቶች ያላደረጉትን ነገር ያደርጋል። ብዝበዛን፣ ምርኮንና ንብረትን በሕዝቡ መካከል ያከፋፍላል፤ በተመሸጉት ቦታዎችም ላይ ሴራ ይጠነስሳል፤ ይህን የሚያደርገው ግን ለጊዜው ብቻ ነው።
“እሱም ታላቅ ሠራዊት አሰባስቦ ኃይሉንና ልቡን በደቡቡ ንጉሥ ላይ ያነሳሳል፤ የደቡቡም ንጉሥ እጅግ ታላቅና ኃያል የሆነ ሠራዊት አሰባስቦ ለጦርነቱ ይዘጋጃል። ሴራ ስለሚጠነስሱበትም መቋቋም አይችልም።
የእሱን ምርጥ ምግብ የሚበሉም ለውድቀት ይዳርጉታል። “ሠራዊቱ ተጠራርጎ ይወሰዳል፤ ብዙዎችም ተገድለው ይወድቃሉ።
“እነዚህ ሁለት ነገሥታት ልባቸው መጥፎ ነገር ለመሥራት ይነሳሳል፤ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው እርስ በርስ ውሸት ይነጋገራሉ። ሆኖም ፍጻሜው እስከተወሰነው ጊዜ ድረስ ስለሚቆይ ምንም ነገር አይሳካላቸውም።
“እሱም በጣም ብዙ ንብረት ሰብስቦ ወደ አገሩ ይመለሳል፤ ልቡም በቅዱሱ ቃል ኪዳን ላይ ይነሳል። እርምጃ ይወስዳል፤ ወደ አገሩም ይመለሳል።
“በተወሰነው ጊዜ ይመለሳል፤ በደቡቡ ላይም ይነሳል። በዚህ ጊዜ ግን ቀድሞ እንደነበረው አይሆንም፤
የኪቲም መርከቦች በእሱ ላይ ይመጡበታልና፤ ይዋረዳልም። “ወደ ኋላ ይመለሳል፤ በቅዱሱ ቃል ኪዳንም ላይ የውግዘት ቃል ይሰነዝራል፤ እርምጃም ይወስዳል፤ ተመልሶም ትኩረቱን ቅዱስ ቃል ኪዳኑን በተዉት ላይ ያደርጋል።
ከእሱ የሚወጡ ክንዶች ይቆማሉ፤ እነሱም ምሽጉን ይኸውም መቅደሱን ያረክሳሉ፤ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ። “ጥፋት የሚያመጣውንም ርኩስ ነገር በዚያ ያኖራሉ።
“ክፋት የሚሠሩትንና ቃል ኪዳኑን የሚያፈርሱትን በማታለል ወደ ክህደት ጎዳና ይመራቸዋል። አምላካቸውን የሚያውቁት ሰዎች ግን ይበረታሉ፤ እርምጃም ይወስዳሉ።
በሕዝቡም መካከል ያሉ ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች ብዙዎች ማስተዋል እንዲኖራቸው ያደርጋሉ። እነሱም ለተወሰነ ጊዜ የሰይፍ፣ የእሳት፣ የምርኮና የብዝበዛ ሰለባ በመሆን ይወድቃሉ።
ሆኖም በሚወድቁበት ጊዜ መጠነኛ እርዳታ ያገኛሉ፤ ብዙዎችም አታላይ በሆነ አንደበት ከእነሱ ጋር ይተባበራሉ።
እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ በእነሱ የተነሳ የማጥራት፣ የማጽዳትና የማንጻት ሥራ ይከናወን ዘንድ ጥልቅ ማስተዋል ካላቸው ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እንዲወድቁ ይደረጋል፤ ምክንያቱም ይህ እስከተወሰነው ጊዜ ድረስ ይቆያል።
“ንጉሡ እንደፈለገው ያደርጋል፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ እጅግም ይኩራራል፤ በአማልክትም አምላክ ላይ አስደንጋጭ ነገር ይናገራል። ቁጣው እስኪፈጸም ድረስ ይሳካለታል፤ ምክንያቱም የተወሰነው ነገር መፈጸም አለበት።
ለአባቶቹ አምላክ ምንም ቦታ አይሰጥም፤ ደግሞም ለሴቶች ፍላጎትም ሆነ ለሌላ ለማንኛውም አምላክ ምንም ቦታ አይሰጥም፤ ራሱን ግን በሁሉም ላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ይልቁንም ለምሽጎች አምላክ ክብር ይሰጣል፤ አባቶቹም ለማያውቁት አምላክ በወርቅ፣ በብር፣ በከበሩ ድንጋዮችና ተፈላጊ በሆኑ ነገሮች ክብር ይሰጣል።
ከባዕድ አምላክ ጋር ሆኖ እጅግ ጠንካራ በሆኑት ምሽጎች ላይ እርምጃ ይወስዳል። ለእሱ እውቅና የሚሰጡትን ሁሉ ከፍተኛ ክብር ያጎናጽፋቸዋል፤ በብዙዎችም መካከል እንዲገዙ ያደርጋል፤ ምድሩንም በዋጋ ያከፋፍላል።
“በፍጻሜው ዘመን የደቡቡ ንጉሥ ከእሱ ጋር ይጋፋል፤ የሰሜኑም ንጉሥ ከሠረገሎች፣ ከፈረሰኞችና ከብዙ መርከቦች ጋር እንደ አውሎ ነፋስ ይመጣበታል፤ ወደ ብዙ አገሮችም ይገባል፤ እንደ ጎርፍም እያጥለቀለቀ ያልፋል።
ውብ ወደሆነችውም ምድር ይገባል፤ ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ። ሆኖም ኤዶም፣ ሞዓብና የአሞናውያን ዋነኛ ክፍል ከእጁ ያመልጣሉ።
እጁንም በብዙ አገሮች ላይ ይዘረጋል፤ የግብፅም ምድር አታመልጥም።
እሱም በተደበቁ ውድ ሀብቶች፣ በወርቅና በብር እንዲሁም በግብፅ የከበሩ ነገሮች ሁሉ ላይ ይሠለጥናል። ሊቢያውያንና ኢትዮጵያውያንም ይከተሉታል።
“ሆኖም ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣ ወሬ ይረብሸዋል፤ እሱም ለማጥፋትና ብዙዎችን ለመደምሰስ በታላቅ ቁጣ ይወጣል።
ንጉሣዊ ድንኳኖቹንም በታላቁ ባሕርና ቅዱስ በሆነው ውብ ተራራ መካከል ይተክላል፤ እሱም ወደ ፍጻሜው ይመጣል፤ የሚረዳውም አይኖርም።
የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት።
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይሖዋ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮዓቄምንና በእውነተኛው አምላክ ቤት ውስጥ ካሉት ዕቃዎች መካከል የተወሰኑትን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በሰናኦር ምድር ወደሚገኘው ወደ አምላኩ ቤት አመጣቸው። ዕቃዎቹን በአምላኩ ግምጃ ቤት ውስጥ አስቀመጣቸው።
ከዚያም ንጉሡ የቤተ መንግሥቱ ዋና ባለሥልጣን የሆነውን አሽፈኔዝን ከንጉሡና ከመሳፍንቱ ዘር የሆኑትን ጨምሮ አንዳንድ እስራኤላውያንን እንዲያመጣ አዘዘው።
እነሱም ምንም እንከን የሌለባቸው፣ መልከ መልካሞች፣ ጥበብ፣ እውቀትና ማስተዋል ያላቸው እንዲሁም በንጉሡ ቤተ መንግሥት ውስጥ ማገልገል የሚችሉ ወጣቶች መሆን ነበረባቸው። የከለዳውያንን ጽሑፍና ቋንቋም እንዲያስተምራቸው አዘዘው።
በተጨማሪም ንጉሡ ለእሱ ከሚቀርበው ምርጥ ምግብና ከሚጠጣው የወይን ጠጅ ላይ የዕለት ቀለብ እንዲሰጣቸው አደረገ። እነዚህ ወጣቶች ለሦስት ዓመት ከሠለጠኑ በኋላ ንጉሡን ለማገልገል የሚሰማሩ ናቸው።
ከእነሱ መካከል ከይሁዳ ነገድ የሆኑት ዳንኤል፣ ሃናንያህ፣ ሚሳኤልና አዛርያስ ይገኙበታል።
ዋናው ባለሥልጣንም ስም አወጣላቸው፤ ዳንኤልን ብልጣሶር፣ ሃናንያህን ሲድራቅ፣ ሚሳኤልን ሚሳቅ፣ አዛርያስን ደግሞ አብደናጎ ብሎ ጠራቸው።
ዳንኤል ግን በንጉሡ ምርጥ ምግብ ወይም በሚጠጣው የወይን ጠጅ ላለመርከስ በልቡ ቁርጥ ውሳኔ አደረገ። በመሆኑም በዚህ መንገድ ራሱን እንዳያረክስ ዋናውን ባለሥልጣን ፈቃድ ጠየቀው።
እውነተኛው አምላክም ዋናው ባለሥልጣን ለዳንኤል ሞገስና ምሕረት እንዲያሳየው አደረገ።
ሆኖም ዋናው ባለሥልጣን ዳንኤልን እንዲህ አለው፦ “የምትበሉትንና የምትጠጡትን የመደበላችሁን ጌታዬን ንጉሡን እፈራለሁ። እኩዮቻችሁ ከሆኑት ከሌሎቹ ወጣቶች ይልቅ ፊታችሁ ተጎሳቁሎ ቢያይስ? እኔን በንጉሡ ፊት በደለኛ ታደርጉኛላችሁ።”
ዳንኤል ግን ዋናው ባለሥልጣን በዳንኤል፣ በሃናንያህ፣ በሚሳኤልና በአዛርያስ ላይ ጠባቂ አድርጎ የሾመውን ሰው እንዲህ አለው፦
“እባክህ አገልጋዮችህን ለአሥር ቀን ያህል ፈትነን፤ የምንበላው አትክልትና የምንጠጣው ውኃ ይሰጠን፤
ከዚያም የእኛን ቁመና የንጉሡን ምርጥ ምግብ ከሚበሉት ወጣቶች ቁመና ጋር አወዳድር፤ በኋላም ባየኸው መሠረት በአገልጋዮችህ ላይ የፈለግከውን ነገር አድርግ።”
እሱም በሐሳባቸው ተስማማ፤ ለአሥር ቀንም ፈተናቸው።
ከአሥር ቀን በኋላም የንጉሡን ምርጥ ምግብ ከሚበሉት ወጣቶች ሁሉ ይበልጥ ቁመናቸው የተሻለና ጤናማ ሆነው ተገኙ።
ስለዚህ ጠባቂው ምርጥ በሆነው ምግባቸውና በወይን ጠጃቸው ምትክ አትክልት ይሰጣቸው ነበር።
እውነተኛው አምላክም ለእነዚህ አራት ወጣቶች በሁሉም ዓይነት የጽሑፍና የጥበብ መስክ እውቀትና ጥልቅ ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤልም ሁሉንም ዓይነት ራእዮችና ሕልሞች የመረዳት ችሎታ ተሰጠው።
ንጉሡ በፊቱ እንዲያቀርቧቸው የቀጠረው ጊዜ ሲደርስ ዋናው ባለሥልጣን ናቡከደነጾር ፊት አቀረባቸው።
ንጉሡ ሲያነጋግራቸው ከወጣቶቹ መካከል እንደ ዳንኤል፣ ሃናንያህ፣ ሚሳኤልና አዛርያስ ያለ አልተገኘም፤ እነሱም በንጉሡ ፊት ማገልገላቸውን ቀጠሉ።
ንጉሡ ጥበብና ማስተዋል የሚጠይቁ ጉዳዮችን ሁሉ አንስቶ በጠየቃቸው ጊዜ በመላ ግዛቱ ካሉት አስማተኛ ካህናትና ጠንቋዮች ሁሉ አሥር እጅ በልጠው አገኛቸው።
ዳንኤልም እስከ ንጉሥ ቂሮስ የመጀመሪያ ዓመት ድረስ በዚያ ቆየ።
የባቢሎን ንጉሥ ቤልሻዛር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልምና ራእዮች አየ። ከዚያም ያየውን ሕልም ጻፈ፤ ጉዳዩንም በዝርዝር አሰፈረ።
ዳንኤልም እንዲህ ሲል ገለጸ፦ “በሌሊት ባየኋቸው ራእዮች ላይ አራቱ የሰማያት ነፋሳት የተንጣለለውን ባሕር ሲያናውጡት ተመለከትኩ።
አራት ግዙፍ አራዊትም ከባሕር ውስጥ ወጡ፤ እያንዳንዳቸውም አንዱ ከሌላው የተለዩ ነበሩ።
“የመጀመሪያው አንበሳ ይመስል ነበር፤ የንስር ክንፎችም ነበሩት። እኔም እየተመለከትኩ ሳለ ክንፎቹ ተነቃቀሉ፤ ከምድር እንዲነሳና ልክ እንደ ሰው በሁለት እግሩ እንዲቆም ተደረገ፤ የሰውም ልብ ተሰጠው።
“እነሆ፣ ሁለተኛው አውሬ ድብ ይመስል ነበር። በአንድ ጎኑም ተነስቶ ነበር፤ በአፉም ውስጥ በጥርሶቹ መካከል ሦስት የጎድን አጥንቶች ይዞ ነበር፤ ‘ተነስተህ ብዙ ሥጋ ብላ’ ተባለ።
“ከዚህም በኋላ አየሁ፤ እነሆ ነብር የሚመስል ሌላ አውሬ ነበር፤ ሆኖም ጀርባው ላይ አራት የወፍ ክንፎች ነበሩት። አውሬውም አራት ራሶች ነበሩት፤ የመግዛት ሥልጣንም ተሰጠው።
“ከዚህ በኋላ በሌሊት ባየኋቸው ራእዮች ላይ የሚያስፈራ፣ የሚያስደነግጥና ለየት ያለ ጥንካሬ ያለው አራተኛ አውሬ ተመለከትኩ፤ ትላልቅ የብረት ጥርሶችም ነበሩት። ይበላና ያደቅ እንዲሁም የቀረውን በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከእሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን አሥር ቀንዶች ነበሩት።
ቀንዶቹን እየተመለከትኩ ሳለ፣ እነሆ ሌላ ትንሽ ቀንድ በመካከላቸው ወጣ፤ ከመጀመሪያዎቹ ቀንዶች መካከል ሦስቱ በፊቱ ተነቃቀሉ። እነሆ፣ በዚህ ቀንድ ላይ የሰው ዓይኖች የሚመስሉ ዓይኖች ነበሩ፤ በእብሪት የሚናገርም አፍ ነበረው።
“እኔም እየተመለከትኩ ሳለ ዙፋኖች ተዘጋጁ፤ ከዘመናት በፊት የነበረውም ተቀመጠ። ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ፣ የራሱም ፀጉር እንደጠራ ሱፍ ነበር። ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣ መንኮራኩሮቹም የሚነድ እሳት ነበሩ።