text
stringlengths
4
267
ብሔራትን ሁሉ ሰብስቤወደ ኢዮሳፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ። ለሕዝቤና ርስቴ ለሆነው ለእስራኤል ስልበዚያ ከእነሱ ጋር እፋረዳለሁ፤በብሔራት መካከል በትነዋቸዋልና፤ደግሞም ምድሬን ተከፋፍለዋታል።
በሕዝቤ ላይ ዕጣ ይጣጣላሉና፤ዝሙት አዳሪ ለማግኘት ሲሉ ወንድ ልጅን አሳልፈው ይሰጣሉ፤የወይን ጠጅ ለመጠጣት ሲሉም ሴት ልጅን ይሸጣሉ።
ጢሮስ፣ ሲዶና እና የፍልስጤም ግዛቶች ሁሉ፣ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አላችሁ? ላደረግኩባችሁ ነገር ብድራት ልትመልሱልኝ ነው? ብድራት የምትመልሱልኝ ከሆነብድራታችሁን ወዲያውኑ፣ በፍጥነት በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
ምክንያቱም እናንተ ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፤እጅግ ምርጥ የሆነውን ውድ ንብረቴንም ወደ ቤተ መቅደሶቻችሁ አስገብታችኋል፤
ደግሞም ከምድራቸው ርቀው እንዲሄዱ ለማድረግ ስትሉየይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለግሪኮች ሸጣችሁ፤
እነሆ፣ እነሱን ከሸጣችሁባቸው ቦታዎች እንዲመለሱ አነሳሳቸዋለሁ፤ብድራታችሁንም በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ለይሁዳ ሕዝብ እሸጣለሁ፤እነሱም በሩቅ ላለ ብሔር ይኸውም ለሳባ ሰዎች ይሸጧቸዋል፤ይሖዋ ራሱ ይህን ተናግሯልና።
በብሔራት መካከል ይህን አውጁ፦ ‘ለጦርነት ተዘጋጁ! ኃያላን ሰዎችን አነሳሱ! ወታደሮቹ ሁሉ ቀርበው ጥቃት ይሰንዝሩ!
ማረሻችሁን ሰይፍ፣ ማጭዳችሁንም ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ። ደካማው ሰው “እኔ ብርቱ ነኝ” ይበል።
እናንተ ዙሪያውን ያላችሁ ብሔራት ሁሉ፣ ኑና ተረዳዱ፤ አንድ ላይም ተሰብሰቡ!’” ይሖዋ ሆይ፣ ኃያላንህን ወደዚያ ቦታ አውርድ።
“ብሔራት ይነሱና ወደ ኢዮሳፍጥ ሸለቆ ይምጡ፤ዙሪያውን ባሉት ብሔራት ሁሉ ላይ ለመፍረድ በዚያ እቀመጣለሁና።
መከሩ ስለደረሰ ማጭድ ስደዱ። የወይን መጭመቂያው ስለሞላ ኑ፣ ወርዳችሁ እርገጡ። ማጠራቀሚያዎቹ ሞልተው አፍስሰዋል፤ ክፋታቸው እጅግ በዝቷልና።
ብዙ ሕዝብ፣ በጣም ብዙ ሕዝብ የፍርድ ውሳኔ በሚሰጥበት ሸለቆ ተሰብስቧል፤የፍርድ ውሳኔ በሚሰጥበት ሸለቆ የይሖዋ ቀን ቀርቧልና።
ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ከዋክብትም ብርሃናቸውን አይሰጡም።
ይሖዋም ከጽዮን እንደ አንበሳ ያገሳል፤ከኢየሩሳሌም ድምፁን በኃይል ያሰማል። ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፤ይሖዋ ግን ለሕዝቡ መጠጊያ፣ለእስራኤል ሕዝብ ምሽግ ይሆናል።
እናንተም እኔ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን የምኖር አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። ኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራ ትሆናለች፤እንግዶችም ከእንግዲህ በእሷ አያልፉም።
በዚያ ቀን ተራሮቹ ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤ኮረብቶቹ ወተት ያፈሳሉ፤የይሁዳ ጅረቶችም ሁሉ በውኃ ይሞላሉ። ከይሖዋም ቤት ምንጭ ይፈልቃል፤የሺቲምንም ሸለቆ ያጠጣል።
ግብፅ ግን ባድማ ትሆናለች፤ኤዶምም በምድራቸው ንጹሕ ደም በማፍሰስበይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ስለፈጸመችጠፍ ምድረ በዳ ትሆናለች።
ይሁንና ይሁዳ ምንጊዜም፣ኢየሩሳሌምም ከትውልድ እስከ ትውልድ የሰው መኖሪያ ትሆናለች።
ንጹሕ አድርጌ ያልቆጠርኩትን ደማቸውን ንጹሕ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፤ይሖዋም በጽዮን ይኖራል።”
“በጽዮን ቀንደ መለከት ንፉ! በቅዱሱ ተራራዬ ላይ ቀረርቶ አሰሙ። የአገሪቱ ነዋሪዎች በሙሉ ይንቀጥቀጡ፤የይሖዋ ቀን ቀርቧልና! ቀኑ ደፍ ላይ ነው!
የጨለማና የጭጋግ ቀን፣የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤በተራሮች ላይ እንደፈነጠቀ የማለዳ ወጋገን ነው። ስፍር ቁጥር የሌለውና ኃያል የሆነ ሕዝብ ይመጣል፤ከዚህ በፊት እንደ እሱ ያለ ፈጽሞ ታይቶ አያውቅም፤ወደፊትም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስእንደ እሱ ያለ አይኖርም።
ከፊቱ ያለውን እሳት ይበላዋል፤ከኋላው ያለውንም ነበልባል ያቃጥለዋል። ከፊቱ ያለው ምድር እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ ነው፤ከኋላው ያለው ግን ወና ምድረ በዳ ነው፤ከእሱም የሚያመልጥ አይኖርም።
መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፤እንደ ጦር ፈረሶችም ይጋልባሉ።
በተራሮች አናት ላይ ሲዘሉ የሚሰማው ድምፅ እንደ ሠረገሎች ድምፅ፣ገለባንም እንደሚበላ የሚንጣጣ የእሳት ነበልባል ድምፅ ነው። ለጦርነት እንደተሰለፈ ኃያል ሕዝብ ናቸው።
ከእነሱም የተነሳ ሕዝቦች ይጨነቃሉ። የሰውም ፊት ሁሉ ይቀላል።
እንደ ተዋጊዎች በፍጥነት ጥቃት ይሰነዝራሉ፤እንደ ወታደሮች ቅጥር ላይ ይወጣሉ፤እያንዳንዱም የራሱን መንገድ ይዞ ይሄዳል፤አቅጣጫቸውንም አይቀይሩም።
እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤እያንዳንዱ ሰው መንገዱን ይዞ ይገሰግሳል። አንዳንዶቹ በመሣሪያ ተመተው ቢወድቁ እንኳሌሎቹ አይፍረከረኩም።
ወደ ከተማዋ እየተጣደፉ ይገባሉ፤ በቅጥርም ላይ ይሮጣሉ። ቤቶችም ላይ ይወጣሉ፤ እንደ ሌባ በመስኮት ይገባሉ።
ምድሪቱ በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፤ ሰማያትም ይናወጣሉ። ፀሐይና ጨረቃ ጨልመዋል፤ከዋክብትም ብርሃናቸውን መስጠት አቁመዋል።
ይሖዋ በሠራዊቱ ፊት ድምፁን በኃይል ያሰማል፤ ሠራዊቱ ስፍር ቁጥር የለውም። ቃሉን የሚፈጽመው ኃያል ነውና፤የይሖዋ ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነው። ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?”
“አሁንም ቢሆን” ይላል ይሖዋ፣“በጾም፣ በለቅሶና በዋይታ በሙሉ ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ።
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋም ተመለሱ፤እሱ ሩኅሩኅና መሐሪ፣ ለቁጣ የዘገየና ታማኝ ፍቅሩ የበዛ ነውና፤ሊያመጣ ያሰበውንም ጥፋት መለስ ብሎ ያጤናል።
ደግሞም ተመልሶ ጉዳዩን እንደገና በማጤን፣ለአምላካችሁ ለይሖዋ የእህል መባና የመጠጥ መባ ማቅረብ ትችሉ ዘንድበረከት ያስቀርላችሁ እንደሆነ ማን ያውቃል?
በጽዮን ቀንደ መለከት ንፉ! ጾም አውጁ፤ የተቀደሰ ጉባኤ ጥሩ።
ሕዝቡን ሰብስቡ፤ ጉባኤውን ቀድሱ። ሽማግሌዎቹን ሰብስቡ፤ ልጆቹንና ጡት የሚጠቡትን ሕፃናት ሰብስቡ። ሙሽራው ከውስጠኛው ክፍል፣ ሙሽሪትም ከጫጉላ ቤት ይውጡ።
የይሖዋ አገልጋዮች የሆኑት ካህናቱበበረንዳውና በመሠዊያው መካከል ሆነው ያልቅሱ፤ እንዲህም ይበሉ፦ ‘ይሖዋ ሆይ፣ ለሕዝብህ እዘን፤ርስትህ መሳለቂያ እንዲሆን አታድርግ፤ብሔራትም አይግዟቸው። ሕዝቦች “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?’
ያን ጊዜ ይሖዋ ለምድሩ ይቀናል፤ለሕዝቡም ይራራል።
ይሖዋ ለሕዝቡ መልስ ይሰጣል፦ ‘እነሆ እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት እልክላችኋለሁ፤እናንተም በሚገባ ትጠግባላችሁ፤ከእንግዲህ በብሔራት መካከል ለነቀፋ አልዳርጋችሁም።
የሰሜኑን ሠራዊት ከእናንተ አርቃለሁ፤ደረቅና ወና ወደሆነ ጠፍ መሬት እበትነዋለሁ፤ፊቱ ወደ ምሥራቁ ባሕር፣ኋላውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይሆናል። ግማቱ ወደ ላይ ይወጣል፤ክርፋቱም ወደ ላይ መውጣቱን ይቀጥላል፤አምላክ ታላላቅ ነገሮች ያደርጋልና።’
ምድር ሆይ፣ አትፍሪ። ደስ ይበልሽ፤ ሐሴትም አድርጊ፤ ይሖዋ ታላላቅ ነገሮች ያደርጋልና።
እናንተ የዱር እንስሳት፣ አትፍሩ፤በምድረ በዳ ያሉት መሰማሪያዎች ይለመልማሉና፤ዛፎችም ፍሬ ያፈራሉ፤የበለስ ዛፉና የወይን ተክሉ ጥሩ ምርት ይሰጣሉ።
እናንተ የጽዮን ልጆች ሆይ፣ በአምላካችሁ በይሖዋ ተደሰቱ፤ ሐሴትም አድርጉ፤እሱ የፊተኛውን ዝናብ በተገቢው መጠን ይሰጣችኋልና፤በእናንተም ላይ ዝናቡን ያዘንባል፤እንደቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ ይሰጣችኋል።
አውድማዎቹ በእህል ይሞላሉ፤መጭመቂያዎቹም በአዲስ የወይን ጠጅና በዘይት ተሞልተው ያፈሳሉ።
ደግሞም በመካከላችሁ የሰደድኩት ታላቁ ሠራዊቴይኸውም የአንበጣ መንጋው፣ ኩብኩባው፣ የማይጠግበው አንበጣና አውዳሚው አንበጣሰብላችሁን ለበሉባቸው ዓመታት ማካካሻ እሰጣችኋለሁ።
እስክትጠግቡ ድረስ ትበላላችሁ፤ደግሞም ድንቅ ነገሮችን ያደረገላችሁንየአምላካችሁን የይሖዋን ስም ታወድሳላችሁ፤ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ አያፍርም።
እናንተም እኔ በእስራኤል መካከል እንደሆንኩእንዲሁም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ፣ ከእኔም በቀር ሌላ እንደሌለ ታውቃላችሁ! ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ አያፍርም።
ከዚያ በኋላ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁ፤ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፤ወጣቶቻችሁም ራእዮችን ያያሉ።
በዚያ ቀን በወንዶች ባሪያዎቼና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ሳይቀርመንፈሴን አፈሳለሁ።
በሰማያትና በምድር ድንቅ ነገሮች አሳያለሁ፤ደም፣ እሳትና የጭስ ዓምድ ይታያል።
ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን ከመምጣቱ በፊትፀሐይ ወደ ጨለማ፣ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።
የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ይሖዋ እንደተናገረው በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚድኑ ይኸውምይሖዋ የሚጠራቸው ከጥፋት የሚተርፉ ሰዎች ይኖራሉ።”
በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያና በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፣ የመሬት መንቀጥቀጡ ከመከሰቱ ከሁለት ዓመት በፊት በተቆአ ከነበሩት በግ አርቢዎች መካከል አንዱ ለሆነው ለአሞጽ ስለ እስራኤል በራእይ የተገለጠለት ቃል።
እሱ እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ ከጽዮን እንደ አንበሳ ያገሳል፤ከኢየሩሳሌምም ድምፁን በኃይል ያሰማል። የእረኞቹ ማሰማሪያዎች ያለቅሳሉ፤የቀርሜሎስም አናት ይደርቃል።”
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘“ስለ ሦስቱ የደማስቆ ዓመፅ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም በብረት ማሄጃ ጊልያድን ወቅተዋል።
በመሆኑም በሃዛኤል ቤት ላይ እሳት እሰዳለሁ፤የቤንሃዳድንም የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።
የደማስቆን በሮች መቀርቀሪያ እሰብራለሁ፤የቢቃትአዌን ነዋሪዎችን አጠፋለሁ፤በቤትኤደን ተቀምጦ የሚገዛውን አስወግዳለሁ፤የሶርያ ሰዎችም ወደ ቂር በግዞት ይሄዳሉ” ይላል ይሖዋ።’
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘“ስለ ሦስቱ የጋዛ ዓመፅ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም ሕዝቡን ሁሉ ማርከው ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል።
በመሆኑም በጋዛ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል።
የአሽዶድን ነዋሪዎች አጠፋለሁ፤በአስቀሎን ተቀምጦ የሚገዛውንም አስወግዳለሁ፤እጄን በኤቅሮን ላይ እዘረጋለሁ፤የተረፉት ፍልስጤማውያንም ይጠፋሉ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የጢሮስ ዓመፅ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም ሕዝቡን ሁሉ ማርከው ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤ደግሞም የወንድማማቾችን ቃል ኪዳን አላስታወሱም።
በመሆኑም በጢሮስ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል።’
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የኤዶም ዓመፅ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም የገዛ ወንድሙን በሰይፍ አሳዷል፤ምሕረት ለማሳየትም እንቢተኛ ሆኗል፤በቁጣው ያላንዳች ፋታ ይዘነጣጥላቸዋል፤አሁንም ቢሆን በእነሱ ላይ ቁጣው አልበረደም።
በመሆኑም በቴማን ላይ እሳት እሰዳለሁ፤የቦስራንም የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።’
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘“ስለ ሦስቱ የአሞናውያን ዓመፅ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም ግዛታቸውን ለማስፋት ሲሉ የጊልያድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀደዋል።
በመሆኑም በራባ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል፤በውጊያው ቀን ቀረርቶ ይሰማል፤አውሎ ነፋስ በሚነሳበትም ቀን ነውጥ ይኖራል።
ንጉሣቸውም ከመኳንንቱ ጋር በግዞት ይወሰዳል” ይላል ይሖዋ።’
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ በኋለኛው ወቅት የተዘራው እህል መብቀል በጀመረበት ጊዜ እሱ የአንበጣ መንጋ ሰደደ። ይህም የንጉሡ ድርሻ የሆነው ሣር ታጭዶ ሲያበቃ በኋለኛው ወቅት የበቀለ እህል ነበር።
የአንበጣው መንጋ በምድሪቱ ላይ የበቀለውን ተክል ሁሉ በልቶ በጨረሰ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ይቅር በል! ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋም ይችላል? እሱ አቅመ ቢስ ነውና!”
በመሆኑም ይሖዋ ጉዳዩን በድጋሚ አጤነ። ይሖዋም “ይህ አይፈጸምም” አለ።
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእሳት እንደሚቀጣ ተናገረ። እሳቱም የተንጣለለውን ጥልቅ ውኃ በላ፤ ደግሞም የተወሰነውን የምድሪቱን ክፍል በላ።
በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ይህ ነገር እንዲደርስ አታድርግ። ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋም ይችላል? እሱ አቅመ ቢስ ነውና!”
በመሆኑም ይሖዋ ጉዳዩን በድጋሚ አጤነ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋም “ይህም ቢሆን አይፈጸምም” አለ።
እሱም ይህን አሳየኝ፦ እነሆ ይሖዋ በቱምቢ በተሠራ ቅጥር ላይ ቆሞ ነበር፤ በእጁም ቱምቢ ይዞ ነበር።
ከዚያም ይሖዋ “አሞጽ፣ ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “ቱምቢ” አልኩ። ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ፣ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱምቢ እዘረጋለሁ። ከእንግዲህ ወዲህ ይቅርታ አላደርግላቸውም።
የይስሐቅ ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ይወድማሉ፤ የእስራኤልም መቅደሶች ይፈራርሳሉ፤ ደግሞም በኢዮርብዓም ቤት ላይ ሰይፍ ይዤ እመጣለሁ።”
የቤቴል ካህን የሆነው አሜስያስ ለእስራኤል ንጉሥ ለኢዮርብዓም ይህን መልእክት ላከ፦ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሴረ ነው። ምድሪቱ የእሱን ቃል ሁሉ መታገሥ አትችልም።
አሞጽ እንዲህ ይላልና፦ ‘ኢዮርብዓም በሰይፍ ይገደላል፤ እስራኤልም ያላንዳች ጥርጥር ከምድሩ ተፈናቅሎ በግዞት ይወሰዳል።’”
ከዚያም አሜስያስ አሞጽን እንዲህ አለው፦ “አንተ ባለ ራእይ፣ ሂድ፤ ወደ ይሁዳም ምድር ሽሽ፤ ቀለብህን ከዚያ አግኝ፤ በዚያም ትንቢት ተናገር።
ከእንግዲህ ወዲያ ግን በቤቴል ትንቢት አትናገር፤ ቤቴል የንጉሥ መቅደስና የመንግሥት መኖሪያ ናትና።”
በዚህ ጊዜ አሞጽ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤ ከዚህ ይልቅ እረኛና የሾላ ዛፎች የምንከባከብ ሰው ነኝ።
ይሖዋ ግን ከመንጋ ጠባቂነት ወሰደኝ፤ ይሖዋም ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ።
እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ፦ ‘አንተ “በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤ በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ” እያልክ ነው።
በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሚስትህ በከተማዋ ውስጥ ዝሙት አዳሪ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ደግሞ በሰይፍ ይወድቃሉ። ምድርህም በገመድ እየተለካ ይከፋፈላል፤ አንተ ራስህም በረከሰ ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ያላንዳች ጥርጥር ከምድሩ ተፈናቅሎ በግዞት ይወሰዳል።”’”
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ይሖዋ ስለ እናንተ ይኸውም ከግብፅ ምድር ስላወጣሁት ስለ መላው ብሔር የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፦
‘በምድር ላይ ካሉ ብሔራት ሁሉ እኔ የማውቀው እናንተን ብቻ ነው። ስለዚህ ለፈጸማችሁት በደል ሁሉ ተጠያቂ አደርጋችኋለሁ።
ሁለት ሰዎች ለመገናኘት ሳይስማሙ አብረው ይጓዛሉ?
አንበሳ አድኖ ሳይዝ በጫካ ውስጥ ያገሳል? ደቦል አንበሳስ ምንም ነገር ሳይዝ በዋሻው ውስጥ ሆኖ ያጉረመርማል?
ወጥመድ ሳይዘጋጅ ወፍ መሬት ላይ ይጠመዳል? ወጥመድስ ምንም ነገር ሳይዝ ይፈነጠራል?
በከተማ ውስጥ ቀንደ መለከት ቢነፋ ሕዝቡ አይሸበርም? በከተማው ውስጥ ጥፋት ቢከሰት ይህን ያደረገው ይሖዋ አይደለም?
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ሚስጥሩን ሳይገልጥምንም ነገር አያደርግምና።
አንበሳ አገሳ! የማይፈራ ማን ነው? ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ተናገረ! ትንቢት የማይናገር ማን ነው?’
‘በአሽዶድ በሚገኙ የማይደፈሩ ማማዎችደግሞም በግብፅ ምድር በሚገኙ የማይደፈሩ ማማዎች ላይ አውጁት። እንዲህ በሉ፦ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤በመካከሏ ያለውን ሁከትናበውስጧ የሚፈጸመውን ግፍ ተመልከቱ።
በማይደፈሩ ማማዎቻቸው ውስጥ ዓመፅንና ጥፋትን የሚያከማቹ ሰዎችትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ አያውቁምና” ይላል ይሖዋ።’
ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ጠላት ምድሪቱን ይከባል፤ብርታትሽን ያሟጥጣል፤የማይደፈሩ ማማዎችሽም ይበዘበዛሉ።’
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት ቅልጥም ወይም የጆሮ ቁራጭ ነጥቆ እንደሚወስድ ሁሉበሰማርያ ባማረ አልጋና ምርጥ በሆነ ድንክ አልጋ የሚቀመጡየእስራኤል ሰዎችም ተነጥቀው ይወሰዳሉ።’
‘ስሙ፤ የያዕቆብንም ቤት አስጠንቅቁ’ ይላል የሠራዊት አምላክ የሆነው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
‘እስራኤልን ለፈጸመው የዓመፅ ድርጊት ሁሉ ተጠያቂ በማደርገው ቀንየቤቴልንም መሠዊያዎች ተጠያቂ አደርጋለሁና፤የመሠዊያው ቀንዶች ተቆርጠው ወደ ምድር ይወድቃሉ።
የክረምቱን ቤትና የበጋውን ቤት አፈርሳለሁ።’ ‘በዝሆን ጥርስ የተሠሩት ቤቶች ይወድማሉ፤ትላልቅ ቤቶችም ይደመሰሳሉ’ ይላል ይሖዋ።”
ይሖዋን ከመሠዊያው በላይ ቆሞ አየሁት፤ እሱም እንዲህ አለ፦ “የዓምዱን አናት ምታ፤ መሠረቶቹም ይናወጣሉ። አናታቸውን ቁረጥ፤ የቀሩትንም በሰይፍ እገድላቸዋለሁ። የሚሸሽ ሁሉ አያመልጥም፤ ለማምለጥ የሚሞክርም ሁሉ አይሳካለትም።