text
stringlengths
4
267
አምላክ የሰጣቸው ተስፋዎች የቱንም ያህል ብዙ ቢሆኑም በእሱ አማካኝነት “አዎ” ሆነዋል። ስለዚህ እኛ ለአምላክ ክብር እንድንሰጥ በእሱ አማካኝነት ለአምላክ “አሜን” እንላለን።
ይሁንና እኛም ሆን እናንተ የክርስቶስ ለመሆናችን ዋስትና የሰጠንና የቀባን አምላክ ነው።
በተጨማሪም በማኅተሙ ያተመን ሲሆን ወደፊት ለሚመጣውም ነገር ማረጋገጫ ሰጥቶናል፤ ይህም በልባችን ውስጥ ያለው መንፈስ ነው።
ወደ ቆሮንቶስ እስካሁን ያልመጣሁት ለባሰ ሐዘን እንዳልዳርጋችሁ ብዬ ነው፤ ይህ እውነት ካልሆነ አምላክ በእኔ ላይ ይመሥክርብኝ።
ጸንታችሁ የቆማችሁት በራሳችሁ እምነት ስለሆነ እኛ ለደስታችሁ ከእናንተ ጋር የምንሠራ ነን እንጂ በእምነታችሁ ላይ የምናዝ አይደለንም።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እነዚህ ተስፋዎች ስላሉን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፤ እንዲሁም አምላክን በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርግ።
በልባችሁ ውስጥ ቦታ ስጡን። እኛ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም አላበላሸንም፤ ማንንም መጠቀሚያ አላደረግንም።
ይህን የምለው ልኮንናችሁ አይደለም። ከዚህ በፊት እንደነገርኳችሁ በልባችን ውስጥ ስለሆናችሁ ብንሞትም ሆነ ብንኖር አብረን ነን።
እናንተን በግልጽ ለማናገር ነፃነት ይሰማኛል። በእናንተ በጣም እኮራለሁ። እንዲሁም እጅግ ተጽናንቻለሁ፤ በመከራችንም ሁሉ ደስታዬ ወሰን የለውም።
መቄዶንያ በደረስን ጊዜ በሁሉም አቅጣጫ መከራ ደረሰብን እንጂ ሰውነታችን ምንም እረፍት አላገኘም፤ በውጭ ጠብ፣ በውስጥ ፍርሃት ነበረብን።
ይሁንና ያዘኑትን የሚያጽናናው አምላክ፣ ቲቶ በመካከላችን በመገኘቱ እንድንጽናና አደረገን፤
የተጽናናነውም እሱ በመካከላችን በመገኘቱ ብቻ ሳይሆን እሱ በእናንተ ምክንያት ባገኘው መጽናኛ ጭምር ነው፤ ተመልሶ በመጣ ጊዜ እኔን ስለመናፈቃችሁ፣ ስለተሰማችሁ ጥልቅ ሐዘንና ለእኔ ስላላችሁ ልባዊ አሳቢነት ነግሮናል፤ ስለዚህ ከበፊቱ ይበልጥ ደስ ብሎኛል።
በደብዳቤዬ አሳዝኛችሁ ቢሆን እንኳ በዚህ አልጸጸትም። መጀመሪያ ላይ ብጸጸት እንኳ፣ ደብዳቤው እንድታዝኑ ያደረጋችሁ ለአጭር ጊዜ ብቻ እንደሆነ ስለተረዳሁ
አሁን የምደሰተው እንዲያው በማዘናችሁ ሳይሆን ሐዘናችሁ ለንስሐ ስላበቃችሁ ነው። ያዘናችሁት ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ነውና፤ በመሆኑም በእኛ የተነሳ ምንም ጉዳት አልደረሰባችሁም።
ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ማዘን ለመዳን የሚያበቃ ንስሐ ያስገኛልና፤ ይህ ደግሞ ለጸጸት አይዳርግም፤ የዚህ ዓለም ሐዘን ግን ሞት ያስከትላል።
አምላካዊ በሆነ መንገድ ማዘናችሁ እንዴት ለተግባር እንዳነሳሳችሁ ተመልከቱ! አዎ፣ አቋማችሁን ለማስተካከል እርምጃ እንድትወስዱ አነሳስቷችኋል፤ ደግሞም እንዴት ያለ ቁጣ፣ እንዴት ያለ ፍርሃት፣ እንዴት ያለ ጉጉት፣ እንዴት ያለ ቅንዓት እንዳስገኘ ተመልከቱ! በእርግጥም ስህተታችሁን ለማረም እርምጃ እንድትወስዱ አድርጓችኋል። በዚህ ጉዳይ ንጹሕ መሆናችሁን በሁሉም ረገድ አስመሥክራችኋል።
ምንም እንኳ ለእናንተ ብጽፍም የጻፍኩት በደል ለሠራው ወይም በደል ለተፈጸመበት ሰው ብዬ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ለመልእክታችን በጎ ምላሽ ለመስጠት የምታደርጉት ጥረት በእናንተ ዘንድና በአምላክ ፊት ግልጽ ሆኖ እንዲታይ ነው።
እኛም የተጽናናነው ለዚህ ነው። ይሁን እንጂ ከመጽናናታችንም በተጨማሪ ሁላችሁም የቲቶ መንፈስ እንዲታደስ ስላደረጋችሁ በእሱ ደስታ እኛም ይበልጥ ተደስተናል።
ምክንያቱም ስለ እናንተ ለእሱ በኩራት ተናግሬ ቢሆን እንኳ አላሳፈራችሁኝም፤ ይሁንና ለእናንተ የተናገርነው ነገር በሙሉ እውነት እንደሆነ ሁሉ ለቲቶ በኩራት የተናገርነውም ነገር እውነት እንደሆነ ተረጋግጧል።
በተጨማሪም ሁላችሁም ያሳያችሁትን ታዛዥነት እንዲሁም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደተቀበላችሁት ሲያስታውስ ለእናንተ ያለው ጥልቅ ፍቅር ጨምሯል።
እኔም በሁሉም መንገድ በእናንተ መተማመን በመቻሌ እጅግ ደስ ብሎኛል።
ወደ እናንተ ለመምጣት ሳስብ ይህ ሦስተኛ ጊዜዬ ነው። “ማንኛውም ጉዳይ የሚጸናው ሁለት ወይም ሦስት ምሥክሮች በሚሰጡት የምሥክርነት ቃል ነው።”
ምንም እንኳ አሁን ከእናንተ ርቄ ያለሁ ቢሆንም ለሁለተኛ ጊዜ አብሬያችሁ እንዳለሁ አድርጋችሁ በማሰብ ቃሌን ተቀበሉ። ደግሞም ዳግመኛ ከመጣሁ ማንንም ሳልገሥጽ እንደማላልፍ ከዚህ በፊት ኃጢአት የሠሩትንም ሆነ የተቀሩትን ሁሉ አስቀድሜ አስጠነቅቃለሁ፤
ይህም የሆነው በእናንተ መካከል በድካም ሳይሆን በኃይል የሚሠራው ክርስቶስ በእኔ አማካኝነት እንደሚናገር የሚያሳይ ማስረጃ ስለፈለጋችሁ ነው።
እርግጥ ነው፣ እሱ በእንጨት ላይ የተሰቀለው በድካም የተነሳ ነው፤ ይሁንና በአምላክ ኃይል የተነሳ ሕያው ሆኗል። እርግጥ እኛም ከእሱ ጋር ደካሞች ነን፤ ሆኖም በእናንተ ላይ እየሠራ ባለው የአምላክ ኃይል ከእሱ ጋር እንኖራለን።
በእምነት ውስጥ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ዘወትር ራሳችሁን ፈትሹ፤ ማንነታችሁን ለማወቅ ዘወትር ራሳችሁን መርምሩ። ተቀባይነት አጥታችሁ ካልሆነ በስተቀር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር አንድነት እንዳለው አትገነዘቡም?
እኛ ግን ተቀባይነት ያለን መሆናችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ አደርጋለሁ።
መጥፎ ነገር እንዳትሠሩ ወደ አምላክ እንጸልያለን፤ ይህን የምናደርገው እኛ ተቀባይነት ያለን ሆነን እንድንታይ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ እኛ ተቀባይነት ያላገኘን መስለን ብንታይም እንኳ እናንተ መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው።
እኛ ለእውነት የቆምን ነን እንጂ እውነትን የሚጻረር ምንም ነገር ማድረግ አንችልምና።
እኛ በደከምንበት ጊዜ ሁሉ እናንተ ብርቱዎች ብትሆኑ ምንጊዜም ደስተኞች ነን። ደግሞም መስተካከላችሁን እንድትቀጥሉ እንጸልያለን።
ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ በመካከላችሁ በምሆንበት ጊዜ ጠበቅ ያለ እርምጃ እንዳልወስድ ነው፤ ጌታ ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።
በተረፈ ወንድሞች፣ መደሰታችሁን፣ መስተካከላችሁን፣ ማጽናኛ መቀበላችሁን፣ በሐሳብ መስማማታችሁንና በሰላም መኖራችሁን ቀጥሉ፤ የፍቅርና የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋር ይሆናል።
እርስ በርስ በመሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ።
ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና የአምላክ ፍቅር እንዲሁም በጋራ የምንቀበለው መንፈስ ቅዱስ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
ብቁ መሆናችንን ለማሳየት ራሳችንን ለእናንተ እንደ አዲስ ማስተዋወቅ ያስፈልገናል? ወይስ እንደ አንዳንድ ሰዎች ለእናንተ ወይም ከእናንተ የምሥክር ወረቀት ያስፈልገን ይሆን?
ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነብቡት በልባችን ላይ የተጻፈ ማስረጃችን እናንተ ራሳችሁ ናችሁ።
ምክንያቱም እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው አምላክ መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላቶች ላይ ሳይሆን በሥጋ ጽላቶች ይኸውም በልብ ላይ፣ አገልጋዮች በሆንነው በእኛ አማካኝነት የተጻፋችሁ የክርስቶስ ደብዳቤ እንደሆናችሁ በግልጽ ታይቷል።
በክርስቶስ በኩል በአምላክ ፊት እንዲህ ያለ እምነት አለን።
ብቃታችንን በገዛ ራሳችን ያገኘነው እንደሆነ አድርገን አናስብም፤ ከዚህ ይልቅ አስፈላጊውን ብቃት ያገኘነው ከአምላክ ነው፤
እሱም የአዲስ ቃል ኪዳን አገልጋዮች ይኸውም የተጻፈ ሕግ ሳይሆን የመንፈስ አገልጋዮች እንድንሆን ብቁዎች አድርጎናል፤ የተጻፈው ሕግ ለሞት ፍርድ ይዳርጋልና፤ መንፈስ ግን ሕያው ያደርጋል።
የእስራኤል ልጆች፣ ከፊቱ ክብር የተነሳ የሙሴን ፊት ትኩር ብለው ማየት እስኪሳናቸው ድረስ የሞት ፍርድ የሚያስከትለውና በድንጋይ ላይ በፊደል የተቀረጸው ሕግ በክብር ይኸውም በሚጠፋ ክብር ከመጣ
የመንፈስ አገልግሎት እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም?
ኩነኔ የሚያስከትለው የሕግ አገልግሎት ክብራማ ከሆነ ጽድቅ የሚያስገኘው አገልግሎትማ እንዴት እጅግ የላቀ ክብር አይኖረውም!
እንዲያውም በአንድ ወቅት ክብራማ የነበረው፣ ከእሱ የላቀ ክብር ያለው በመምጣቱ ምክንያት ክብሩ ተገፏል።
የሚጠፋው በክብር ከመጣ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም!
እንዲህ ዓይነት ተስፋ ስላለን ታላቅ የመናገር ነፃነት አለን፤
ደግሞም የእስራኤል ልጆች የዚያን የሚሻረውን ነገር መጨረሻ እንዳይመለከቱ ሙሴ ፊቱን በመሸፈኛ ይሸፍን በነበረበት ጊዜ ያደርግ እንደነበረው አናደርግም።
ሆኖም እነሱ አእምሯቸው ደንዝዟል። እስከ ዛሬ ድረስ፣ አሮጌው ቃል ኪዳን ሲነበብ ያው መሸፈኛ እንደጋረዳቸው ነውና፤ ምክንያቱም መሸፈኛው የሚወገደው በክርስቶስ አማካኝነት ብቻ ነው።
እንዲያውም እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቁጥር ልባቸው በመሸፈኛ እንደተሸፈነ ነው።
ሆኖም አንድ ሰው ወደ ይሖዋ ሲመለስ መሸፈኛው ይወገዳል።
ይሖዋ መንፈስ ነው፤ የይሖዋ መንፈስ ባለበት ደግሞ ነፃነት አለ።
እኛ ሁላችንም ባልተሸፈነ ፊት የይሖዋን ክብር እንደ መስተዋት ስናንጸባርቅ ያንኑ መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፤ በዚህ መንገድ መንፈስ የሆነው ይሖዋ ራሱ እንደሚያደርገን እንሆናለን።
ለቅዱሳን የሚደረገውን አገልግሎት በተመለከተ ልጽፍላችሁ አያስፈልግም፤
እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆናችሁን አውቃለሁና፤ በመሆኑም “የአካይያ ወንድሞች ሌሎችን ለመርዳት ለአንድ ዓመት ያህል ዝግጁ ሆነው ሲጠባበቁ ቆይተዋል” ብዬ ለመቄዶንያ ወንድሞች በኩራት ተናግሬአለሁ፤ የእናንተ ቅንዓት ደግሞ አብዛኞቹን አነሳስቷል።
ይሁንና በዚህ ረገድ በእናንተ ላይ ያለን ትምክህት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር አስቀድሞ ስለ እናንተ እንደተናገርኩት ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁ ወንድሞችን እልካለሁ።
አለዚያ የመቄዶንያ ወንድሞች ከእኔ ጋር መጥተው ዝግጁ ሳትሆኑ ቢያገኟችሁ፣ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ እኛም በእናንተ በመተማመናችን እናፍራለን።
ስለዚህ ቀደም ሲል ልትሰጡ ቃል የገባችሁትን የልግስና ስጦታ አስቀድመው ያዘጋጁ ዘንድ ወንድሞች ቀደም ብለው ወደ እናንተ እንዲመጡ ማበረታታት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እንዲህ ከሆነ ስጦታው ተዘጋጅቶ ይጠብቀናል፤ ይህ ደግሞ ስጦታ የሰጣችሁት አስገድደናችሁ ሳይሆን በልግስና እንደሆነ ያሳያል።
ይሁንና ጥቂት የሚዘራ ሁሉ ጥቂት ያጭዳል፤ በብዛት የሚዘራ ሁሉ ደግሞ በብዛት ያጭዳል።
አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ እያንዳንዱ ሰው ቅር እያለው ወይም ተገዶ ሳይሆን በልቡ ያሰበውን ይስጥ።
በተጨማሪም ምንጊዜም የሚያስፈልጋችሁ ነገር በበቂ ሁኔታ እንዲኖራችሁ እንዲሁም መልካም ሥራን ሁሉ ለመሥራት የሚያስችላችሁን ነገር በብዛት እንድታገኙ አምላክ ጸጋውን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
(ይህም “በብዛት አከፋፈለ፤ ለድሆችም ሰጠ። ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
እንግዲህ ለዘሪ ዘርን፣ ለመብል እህልን አትረፍርፎ የሚሰጠው እሱ የምትዘሩትን ዘር አትረፍርፎ ይሰጣችኋል፤ እንዲሁም የጽድቃችሁን ፍሬ ያበዛላችኋል።)
በሁሉም መንገድ በልግስና መስጠት እንድትችሉ አምላክ አትረፍርፎ ይባርካችኋል፤ እኛ በምናከናውነው ሥራ የተነሳ እንዲህ ያለው ልግስና ሰዎች ለአምላክ ምስጋና እንዲያቀርቡ ያነሳሳቸዋል፤
ምክንያቱም ይህ የምታከናውኑት ሕዝባዊ አገልግሎት ቅዱሳን የሚያስፈልጓቸው ነገሮች በሚገባ እንዲሟሉላቸው ከማድረጉም በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ለአምላክ ብዙ ምስጋና እንዲያቀርቡ ያደርጋል።
በዚህ የእርዳታ አገልግሎት አማካኝነት የሚያዩት ማስረጃ አምላክን እንዲያከብሩ ያደርጋቸዋል፤ ምክንያቱም እናንተ በይፋ ለምታውጁት ስለ ክርስቶስ ለሚገልጸው ምሥራች ተገዢዎች ናችሁ፤ እንዲሁም ለእነሱም ሆነ ለሁሉም በምታደርጉት መዋጮ ለጋሶች ናችሁ።
ደግሞም አምላክ ከሰጣችሁ የላቀ ጸጋ የተነሳ ስለ እናንተ ምልጃ እያቀረቡ ለእናንተ ያላቸውን ፍቅር ይገልጻሉ።
በቃላት ሊገለጽ ለማይችለው ነፃ ስጦታው አምላክ የተመሰገነ ይሁን።
እንደገና በምመጣበት ጊዜ ለሐዘን ምክንያት የሚሆን ነገር እንዳይፈጠር ወስኛለሁ።
ምክንያቱም የደስታዬ ምንጭ የሆናችሁትን እናንተን ካሳዘንኳችሁ እንግዲህ እኔን ማን ሊያስደስተኝ ነው?
ባለፈው ጊዜ የጻፍኩላችሁ በምመጣበት ጊዜ ልደሰትባቸው በሚገባ ሰዎች እንዳላዝን ነው፤ ምክንያቱም የእኔ ደስታ የእናንተ የሁላችሁም ደስታ እንደሚሆን እተማመናለሁ።
ልቤ በብዙ መከራና ጭንቀት ተውጦ በብዙ እንባ የጻፍኩላችሁ እንድታዝኑ ሳይሆን ለእናንተ ያለኝን ጥልቅ ፍቅር እንድታውቁ ነው።
ለሐዘን የሚዳርግ ነገር ያደረገ ማንም ቢኖር ያሳዘነው እኔን ሳይሆን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሁላችሁንም ነው፤ እንዲህ ያልኩት ግን ነገሩን ለማክበድ ብዬ አይደለም።
እንዲህ ዓይነቱ ሰው ከእናንተ አብዛኞቻችሁ የሰጣችሁት ተግሣጽ ይበቃዋል፤
አሁን ይህ ሰው ከልክ በላይ በሐዘን እንዳይዋጥ በደግነት ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባል።
ስለዚህ ለእሱ ያላችሁን ፍቅር እንድታረጋግጡለት አሳስባችኋለሁ።
የጻፍኩላችሁም በሁሉም ነገር ታዛዥ መሆናችሁን ታሳዩ እንደሆነ ለማረጋገጥ ነው።
በደሉ ምንም ይሁን ምን እናንተ ይቅር ያላችሁትን ማንኛውንም ሰው እኔም ይቅር እለዋለሁ። እንዲያውም ሁሉንም ነገር በክርስቶስ ፊት ይቅር ያልኩት (ይቅር ያልኩት ነገር ካለ) ለእናንተ ስል ነው፤
ይህም ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ ነው፤ እሱ የሚሸርበውን ተንኮል እናውቃለንና።
ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች ለማወጅ ጥሮአስ በደረስኩ ጊዜ የጌታን ሥራ ለማከናወን በር ተከፍቶልኝ ነበር፤
ይሁንና ወንድሜን ቲቶን ስላላገኘሁት መንፈሴ ተረብሾ ነበር። በመሆኑም በዚያ ያሉትን ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ሄድኩ።
በድል ሰልፍ ከክርስቶስ ጋር አብረን እንድንጓዝ በማድረግ ዘወትር ለሚመራንና የእውቀቱ መዓዛ በእኛ አማካኝነት በሁሉም ቦታ እንዲናኝ ለሚያደርገው አምላክ ምስጋና ይድረሰው!
እኛ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ባሉት መካከልና ወደ ጥፋት እያመሩ ባሉት መካከል ለአምላክ የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤
ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ለሞት የሚዳርግ የሞት ሽታ፣ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ላሉት ደግሞ ወደ ሕይወት የሚመራ የሕይወት መዓዛ ነን። እንዲህ ላለው አገልግሎት ብቃት ያለው ማን ነው?
እኛ ነን፤ ምክንያቱም እኛ እንደ ብዙዎቹ ሰዎች የአምላክን ቃል አንሸቃቅጥም፤ ከዚህ ይልቅ በአምላክ የተላክን እንደመሆናችን መጠን በቅንነት እንናገራለን፤ ይህን የምናደርገው በአምላክ ፊት ሆነን እንዲሁም ከክርስቶስ ጋር በመተባበር ነው።
በመካከላችሁ ሆኜ ፊት ለፊት ስታይ እንደ ደካማ የምቆጠረውና ከእናንተ ስርቅ እንደ ደፋር የምታየው እኔ ጳውሎስ በክርስቶስ ገርነትና ደግነት እለምናችኋለሁ።
በመካከላችሁ በምገኝበት ጊዜ በሥጋዊ አስተሳሰብ እንደምንመላለስ አድርገው በሚቆጥሩን አንዳንድ ሰዎች ላይ በድፍረት ከባድ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስገድድ ሁኔታ እንደማይፈጠር ተስፋ አደርጋለሁ።
ምንም እንኳ በሥጋ የምንኖር ቢሆንም የምንዋጋው በሥጋዊ መንገድ አይደለም።
የምንዋጋባቸው የጦር መሣሪያዎቻችን ሥጋዊ አይደሉምና፤ ይሁን እንጂ ምሽግን ለመደርመስ የሚያስችል መለኮታዊ ኃይል ያላቸው ናቸው።
ስለ አምላክ የሚገልጸውን እውቀት የሚጻረሩ የተሳሳቱ ሐሳቦችንና ይህን እውቀት የሚያግድን ማንኛውንም ከፍ ያለ ነገር እናፈርሳለን፤ እንዲሁም ማንኛውንም ሐሳብ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን፤
ሙሉ በሙሉ ታዛዦች መሆናችሁን ካሳያችሁ በኋላ በማንኛውም መንገድ ታዛዥ በማይሆን ግለሰብ ላይ የቅጣት እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተናል።
እናንተ የምትመለከቱት ውጫዊውን ነገር ብቻ ነው። ማንም ሰው የክርስቶስ ነኝ ብሎ በራሱ የሚተማመን ከሆነ እሱ የክርስቶስ እንደሆነ ሁሉ እኛም የክርስቶስ እንደሆን በድጋሚ ሊያጤን ይገባዋል።
ጌታ እናንተን ለማፍረስ ሳይሆን ለማነጽ በሰጠን ሥልጣን እጅግ ብኮራም እንኳ ለኀፍረት አልዳረግምና።
እናንተን በደብዳቤዎቼ ለማስፈራራት እየሞከርኩ ያለሁ ሆኖ እንዲሰማችሁ አልፈልግም።
አንዳንዶች “ደብዳቤዎቹ ከባድና ኃይለኛ ናቸው፤ በመካከላችን በአካል ሲገኝ ግን ደካማ ከመሆኑም በላይ ንግግሩ የተናቀ ነው” ይላሉና።
እንዲህ ያለው ሰው፣ በአካል ሳንኖር በደብዳቤዎቻችን የምንናገረው ቃልና በአካል ስንገኝ የምናደርገው ነገር ምንም ልዩነት እንደሌለው መገንዘብ ይገባዋል።
እኛ ራሳቸውን ብቁ አድርገው ከሚያቀርቡ ሰዎች ጋር ራሳችንን ለመመደብ ወይም ለማነጻጸር አንደፍርምና። ይሁንና እነሱ ራሳቸውን በራሳቸው ሲመዝኑና ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያነጻጽሩ ማስተዋል እንደሌላቸው ያሳያሉ።
እኛ ግን ከተሰጠን ወሰን ውጭ ባለው ነገር አንኩራራም፤ ከዚህ ይልቅ የምንኮራው አምላክ ለክቶ በሰጠን ክልል ውስጥ ባለው ነገር ብቻ ነው፤ ይህ ክልል ደግሞ እናንተንም ያጠቃልላል።
እናንተ ከክልላችን ውጭ ያላችሁ ይመስል እናንተ ጋር ለመድረስ ከክልላችን ውጭ መሄድ አላስፈለገንም፤ ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች በመጀመሪያ እናንተ እስካላችሁበት ድረስ ይዘን የመጣነው እኛ ነንና።
ከተመደበልን ወሰን ውጭ ሌላ ሰው በደከመበት ነገር እየተኩራራን አይደለም፤ ሆኖም እምነታችሁ እያደገ ሲሄድ በክልላችን ውስጥ ያከናወንነውን ሥራ በሚገባ እንደምትገነዘቡ ተስፋ እናደርጋለን። ይህም ይበልጥ እንድንሠራ ያደርገናል፤