text
stringlengths
4
267
የአባቶቻቸው ቤት መሪዎችም እነዚህ ናቸው፦ የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች ሃኖክ፣ ፓሉ፣ ኤስሮን እና ካርሚ ነበሩ። እነዚህ የሮቤል ቤተሰቦች ናቸው።
የስምዖን ወንዶች ልጆች የሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሃር እና ከአንዲት ከነአናዊት የወለደው ሻኡል ነበሩ። እነዚህ የስምዖን ቤተሰቦች ናቸው።
የሌዊ ወንዶች ልጆች በየቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው ስማቸው ይህ ነው፦ ጌድሶን፣ ቀአት እና ሜራሪ። ሌዊ 137 ዓመት ኖረ።
የጌድሶን ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸው ሊብኒ እና ሺምአይ ነበሩ።
የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣ ኬብሮን እና ዑዚኤል ነበሩ። ቀአት 133 ዓመት ኖረ።
የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ። የሌዋውያን ቤተሰቦች በየቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው እነዚህ ነበሩ።
አምራም የአባቱን እህት ዮካቤድን አገባ። እሷም አሮንንና ሙሴን ወለደችለት። አምራም 137 ዓመት ኖረ።
የይጽሃር ወንዶች ልጆች ቆሬ፣ ኔፌግ እና ዚክሪ ነበሩ።
የዑዚኤል ወንዶች ልጆች ሚሳኤል፣ ኤሊጻፋን እና ሲትሪ ነበሩ።
አሮን የነአሶን እህት የሆነችውን የአሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ። እሷም ናዳብን፣ አቢሁን፣ አልዓዛርን እና ኢታምርን ወለደችለት።
የቆሬ ወንዶች ልጆች አሲር፣ ሕልቃና እና አቢያሳፍ ነበሩ። የቆሬያውያን ቤተሰቦች እነዚህ ናቸው።
የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፑቲኤል ልጆች መካከል አንዷን አገባ። እሷም ፊንሃስን ወለደችለት። የሌዋውያን የአባቶች ቤት መሪዎች በየቤተሰባቸው እነዚህ ናቸው።
ይሖዋ “የእስራኤልን ሕዝብ በቡድን በቡድን በማድረግ ከግብፅ ምድር ይዛችሁ ውጡ” ብሎ የነገራቸው አሮንና ሙሴ እነዚህ ናቸው።
የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ለማውጣት የግብፁን ንጉሥ ፈርዖንን ያነጋገሩት ሙሴና አሮን ነበሩ።
ይሖዋ በግብፅ ምድር ሙሴን ባነጋገረበት በዚያ ዕለት
ይሖዋ ሙሴን “እኔ ይሖዋ ነኝ። የምነግርህን ሁሉ ለግብፁ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው” አለው።
ከዚያም ሙሴ ይሖዋን “እኔ እንደሆነ የመናገር ችግር አለብኝ፤ ታዲያ ፈርዖን እንዴት ብሎ ይሰማኛል?” አለው።
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦
“በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የማደሪያ ድንኳኑን ይኸውም የመገናኛ ድንኳኑን ትከል።
የምሥክሩን ታቦት በውስጡ ካስቀመጥክ በኋላ ታቦቱን በመጋረጃው ከልለው።
ጠረጴዛውንም ካስገባህ በኋላ በላዩ ላይ የሚቀመጡትን ነገሮች አስተካክለህ አስቀምጥ፤ መቅረዙንም አስገብተህ መብራቶቹን አብራቸው።
ከዚያም ለዕጣን የሚሆነውን የወርቅ መሠዊያ ከምሥክሩ ታቦት በፊት አስቀምጠው፤ ለማደሪያ ድንኳኑ መግቢያ የሚሆነውን መከለያም በቦታው አድርገው።
“የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያም በማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ፊት አድርገው፤
ገንዳውንም በመገናኛ ድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አድርገህ ውኃ ጨምርበት።
በመገናኛ ድንኳኑም ዙሪያ ግቢ ከልልለት፤ ለግቢውም መግቢያ መከለያ አድርግለት።
የማደሪያ ድንኳኑም የተቀደሰ እንዲሆን የቅብዓት ዘይቱን ወስደህ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች በሙሉ ትቀባቸዋለህ፤ ድንኳኑንም ሆነ ዕቃዎቹን በሙሉ ትቀድሳለህ።
የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትም መሠዊያ እጅግ ቅዱስ እንዲሆን መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ ትቀባቸዋለህ፤ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ።
ገንዳውንና ማስቀመጫውንም ቀባ፤ ቀድሰውም።
“ከዚያም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ አቅርባቸው፤ በውኃም እጠባቸው።
አሮንንም ቅዱስ የሆኑትን ልብሶች ካለበስከው በኋላ ቀባው፤ እንዲሁም ቀድሰው፤ እሱም ካህን ሆኖ ያገለግለኛል።
ከዚያም ወንዶች ልጆቹን አቅርበህ ረጃጅሞቹን ቀሚሶች አልብሳቸው።
ካህናት ሆነውም እንዲያገለግሉኝ አባታቸውን እንደቀባኸው ሁሉ እነሱንም ቀባቸው፤ መቀባታቸውም ክህነታቸው ለትውልዶቻቸው ሁሉ በዘላቂነት እንዲቀጥል ያስችላል።”
ሙሴም ይሖዋ ባዘዘው መሠረት አደረገ። ልክ እንደዚሁ አደረገ።
በሁለተኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የማደሪያ ድንኳኑ ተተከለ።
ሙሴም የማደሪያ ድንኳኑን ሲተክል መሰኪያዎቹን ከሥር በማስቀመጥ አራት ማዕዘን ቋሚዎቹን አደረገባቸው፤ አግዳሚ እንጨቶቹንም አስገባቸው፤ ዓምዶቹንም አቆማቸው።
ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የማደሪያ ድንኳኑን በድንኳኑ ጨርቅ አለበሰው፤ በላዩም ላይ የድንኳኑን መደረቢያ ደረበበት።
ቀጥሎም የምሥክሩን ጽላቶች ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጣቸው፤ የታቦቱንም መሎጊያዎች አስገባቸው፤ መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አደረገው።
ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ታቦቱን ወደ ማደሪያ ድንኳኑ አስገባው፤ የመግቢያው መከለያ የሆነውን መጋረጃ በቦታው በማድረግ የምሥክሩን ታቦት ከለለው።
በመቀጠልም ጠረጴዛውን በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በስተ ሰሜን በኩል ባለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ከመጋረጃው ውጭ አደረገው፤
በላዩም ላይ ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የተነባበረውን ኅብስት በይሖዋ ፊት አስቀመጠ።
መቅረዙንም በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ከጠረጴዛው ትይዩ፣ በስተ ደቡብ በኩል ባለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን አስቀመጠው።
ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት መብራቶቹን በይሖዋ ፊት አበራቸው።
የወርቅ መሠዊያውንም በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ከመጋረጃው በፊት አስቀመጠው፤
ይህን ያደረገውም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን እንዲጨስበት ነው።
ቀጥሎም የማደሪያ ድንኳኑን መግቢያ መከለያ በቦታው አደረገው።
ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የሚቃጠለውን መባና የእህሉን መባ በላዩ ላይ እንዲያቀርብበት የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ በማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ አደረገው።
በመቀጠልም ገንዳውን በመገናኛ ድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አደረገው፤ ለመታጠቢያ የሚሆን ውኃም ጨመረበት።
ሙሴ እንዲሁም አሮንና ወንዶች ልጆቹ እጃቸውንና እግራቸውን ታጠቡበት።
ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገቡበትና ወደ መሠዊያው በሚቀርቡበት ጊዜ ሁሉ ይታጠቡ ነበር።
በመጨረሻም በማደሪያ ድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ግቢውን ከለለ፤ ለግቢውም መግቢያ መከለያ አደረገለት። በዚህ መንገድ ሙሴ ሥራውን አጠናቀቀ።
ደመናውም የመገናኛ ድንኳኑን ሸፈነው፤ የይሖዋም ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ሞላው።
ደመናው በመገናኛ ድንኳኑ ላይ አርፎ ስለነበርና የይሖዋም ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ስለሞላው ሙሴ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግባት አልቻለም ነበር።
እስራኤላውያንም በጉዟቸው ወቅት ሁሉ ደመናው ከማደሪያ ድንኳኑ ላይ በሚነሳበት ጊዜ ድንኳናቸውን ነቅለው ይንቀሳቀሱ ነበር።
ሆኖም ደመናው ካልተነሳ፣ ደመናው እስከሚነሳበት ቀን ድረስ ድንኳናቸውን ነቅለው አይንቀሳቀሱም ነበር።
መላው የእስራኤል ቤት በሚጓዝበት ወቅት ሁሉ ቀን ቀን የይሖዋ ደመና፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ እሳት በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ሆኖ ያይ ነበር።
“ለእኔ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነሱን ለመቀደስ የምታደርገው ነገር ይህ ነው፦ እንከን የሌለበትን አንድ ወይፈንና እንከን የሌለባቸውን ሁለት አውራ በጎች ውሰድ፤
እንዲሁም ቂጣ፣ በዘይት ከተለወሰ ሊጥ የተጋገረ የቀለበት ቅርጽ ያለው እርሾ ያልገባበት ዳቦና ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ውሰድ። እነዚህንም ከላመ የስንዴ ዱቄት ጋግረህ
በቅርጫት ውስጥ ታደርጋቸዋለህ፤ በቅርጫት ውስጥ አድርገህም ከወይፈኑና ከሁለቱ አውራ በጎች ጋር ታቀርባቸዋለህ።
“አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ታቀርባቸዋለህ፤ በውኃም ታጥባቸዋለህ።
ከዚያም ልብሶቹን ወስደህ ረጅሙን ቀሚስ፣ እጅጌ የሌለውን የኤፉዱን ቀሚስ፣ ኤፉዱንና የደረት ኪሱን አሮንን አልብሰው፤ በሽመና የተሠራውን የኤፉዱን መቀነትም ወገቡ ላይ ጠበቅ አድርገህ ታስርለታለህ።
ጥምጥሙንም በራሱ ላይ ታደርግለታለህ፤ በጥምጥሙም ላይ ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየውን ቅዱስ ምልክት ታደርጋለህ፤
የቅብዓት ዘይቱንም ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ትቀባዋለህ።
“ከዚያም ወንዶች ልጆቹን አምጥተህ ረጃጅሞቹን ቀሚሶች አልብሳቸው፤
አሮንንና ወንዶች ልጆቹን መቀነቱን አስታጥቃቸው፤ የራስ ቆባቸውንም አድርግላቸው፤ ክህነቱም ዘላለማዊ ደንብ ሆኖ የእነሱ ይሆናል። በዚህም መንገድ አሮንና ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ ትሾማቸዋለህ።
“ከዚያም ወይፈኑን በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ታቀርበዋለህ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በወይፈኑ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጭናሉ።
ወይፈኑንም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በይሖዋ ፊት እረደው።
ከወይፈኑም ደም ላይ የተወሰነውን ወስደህ በጣትህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ አድርግ፤ የቀረውንም ደም በሙሉ መሠዊያው ሥር አፍስሰው።
ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣ በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ ውሰድ፤ በመሠዊያውም ላይ እንዲጨሱ አቃጥላቸው።
የወይፈኑን ሥጋ፣ ቆዳውንና ፈርሱን ግን ከሰፈሩ ውጭ አውጥተህ በእሳት ታቃጥለዋለህ። ይህ የኃጢአት መባ ነው።
“ከዚያም አንዱን አውራ በግ ውሰድ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ።
አንተም አውራውን በግ እረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ እርጨው።
አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራርጠው፤ ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም እጠባቸው፤ ከዚያም የተቆራረጡትን ብልቶች ከጭንቅላቱ ጋር አሰናድተህ አስቀምጣቸው።
አውራውንም በግ ሙሉ በሙሉ በማቃጠል በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አድርገው። ይህም ለይሖዋ የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ነው። ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው።
“ከዚያም ሌላኛውን አውራ በግ ትወስዳለህ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጭኑበታል።
አንተም አውራውን በግ እረደው፤ ከደሙም ወስደህ የአሮንን የቀኝ ጆሮ ጫፍና የወንዶች ልጆቹን የቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጃቸውን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ቀባ፤ ደሙንም በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ እርጨው።
በመሠዊያው ላይ ካለው ደምና ከቅብዓት ዘይቱ ውሰድ፤ ከዚያም አሮንና ልብሶቹ እንዲሁም ወንዶች ልጆቹና ልብሶቻቸው ቅዱስ እንዲሆኑ በአሮንና በልብሶቹ እንዲሁም በወንዶች ልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ እርጨው።
“አውራው በግ የክህነት ሹመት ሥርዓት በሚካሄድበት ጊዜ የሚቀርብ ስለሆነ ከአውራው በግ ላይ ስቡን፣ ላቱን፣ አንጀቱን የሚሸፍነውን ስብ፣ የጉበቱን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ እንዲሁም ቀኝ እግሩን ውሰድ።
በተጨማሪም በይሖዋ ፊት ካለው ቂጣ ከተቀመጠበት ቅርጫት ውስጥ ቂጣውን፣ በዘይት ከተለወሰ ሊጥ የተጋገረውን የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦና ስሱን ቂጣ ውሰድ።
ሁሉንም በአሮን እጅና በወንዶች ልጆቹ እጅ ላይ አስቀምጣቸው፤ ከዚያም በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባ ወዲያና ወዲህ ወዝውዛቸው።
በይሖዋም ፊት ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሆን ከእጃቸው ላይ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይ ታቃጥላቸዋለህ። ይህ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው።
“ከዚያም ለአሮን የክህነት ሹመት ሥርዓት የሚቀርበውን አውራ በግ ፍርምባ ወስደህ በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባ ወዲያና ወዲህ ወዝውዘው፤ እሱም የአንተ ድርሻ ይሆናል።
ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የክህነት ሹመት ሥርዓት ከቀረበው አውራ በግ ተወስዶ ለሚወዘወዝ መባ የቀረበውን ፍርምባና የተቀደሰ ድርሻ እንዲሆን የተወዘወዘውን እግር ትቀድሳቸዋለህ።
ይህም የተቀደሰ ድርሻ ስለሆነ የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል፤ ይህም እስራኤላውያን የሚፈጽሙት ዘላለማዊ ሥርዓት ነው፤ ይህ ድርሻ እስራኤላውያን የሚያቀርቡት የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል። ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ ለይሖዋ የሚሰጥ የተቀደሰ ድርሻቸው ነው።
“የአሮን ቅዱስ ልብሶችም ከእሱ በኋላ የሚመጡት ወንዶች ልጆቹ በሚቀቡበትና ካህናት ሆነው በሚሾሙበት ጊዜ ይገለገሉባቸዋል።
ከወንዶች ልጆቹ መካከል እሱን የሚተካውና በቅዱሱ ስፍራ ለማገልገል ወደ መገናኛ ድንኳኑ የሚገባው ካህን ለሰባት ቀን ይለብሳቸዋል።
“ለክህነት ሹመት ሥርዓት የሚቀርበውን አውራ በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ትቀቅለዋለህ።
አሮንና ወንዶች ልጆቹ የአውራውን በግ ሥጋና በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ቂጣ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ይበሉታል።
እነሱን ካህናት አድርጎ ለመሾምና ለመቀደስ ማስተሰረያ ሆነው የቀረቡትን ነገሮች ይበላሉ። ሆኖም እነዚህ ነገሮች የተቀደሱ ስለሆኑ ያልተፈቀደለት ሰው ሊበላቸው አይችልም።
ለክህነት ሹመት ሥርዓቱ መሥዋዕት ሆኖ ከቀረበው ሥጋና ቂጣ ተርፎ ያደረ ካለ የተረፈውን በእሳት አቃጥለው። የተቀደሰ ስለሆነ መበላት የለበትም።
“እኔ ባዘዝኩህ ሁሉ መሠረት ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ በዚሁ መንገድ ታደርግላቸዋለህ። እነሱን ካህናት አድርገህ ለመሾም ሰባት ቀን ይፈጅብሃል።
ለማስተሰረያ እንዲሆን የኃጢአት መባ የሚሆነውን በሬ በየዕለቱ ታቀርባለህ፤ ለመሠዊያውም ማስተሰረያ በማቅረብ መሠዊያውን ከኃጢአት ታነጻዋለህ፤ መሠዊያውን ለመቀደስም ቀባው።
መሠዊያውን ለማስተሰረይ ሰባት ቀን ይፈጅብሃል፤ እጅግ ቅዱስ መሠዊያ እንዲሆንም ቀድሰው። መሠዊያውን የሚነካ ማንኛውም ሰው ቅዱስ መሆን አለበት።
“በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው እነዚህን ይሆናል፦ አንድ ዓመት የሆናቸው ሁለት የበግ ጠቦቶችን በየቀኑ ሳታቋርጥ ታቀርባለህ።
አንደኛውን የበግ ጠቦት ጠዋት ላይ ታቀርበዋለህ፤ ሌላኛውን የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ ታቀርበዋለህ።
ተጨቅጭቆ በተጠለለ አንድ አራተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ የላመ ዱቄትና ለመጠጥ መባ የሚሆን አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋር ይቅረብ።
ሁለተኛውንም የበግ ጠቦት ልክ ማለዳ ላይ ከምታቀርባቸው ጋር ተመሳሳይ ከሆኑ የእህልና የመጠጥ መባዎች ጋር አመሻሹ ላይ ታቀርበዋለህ። ይህን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርገህ ታቀርበዋለህ።
ይህም እኔ እናንተን ለማነጋገር ራሴን በምገልጥበት በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ በይሖዋ ፊት ዘወትር የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ይሆናል።
“እኔም በዚያ ራሴን ለእስራኤላውያን እገልጣለሁ፤ ያም ስፍራ በክብሬ የተቀደሰ ይሆናል።
መገናኛ ድንኳኑንና መሠዊያውን እቀድሰዋለሁ፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እቀድሳቸዋለሁ።
እኔም በእስራኤል ሕዝብ መካከል እኖራለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።