text
stringlengths
4
267
የአንተ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእውነተኛው ጌታ በይሖዋ ፊት ይቅረቡ።
“የመሥዋዕቴን ደም እርሾ ከገባበት ከማንኛውም ነገር ጋር አብረህ አታቅርብ። በበዓሎቼም ላይ የሚቀርቡት የስብ መሥዋዕቶች እስከ ጠዋት ድረስ ማደር የለባቸውም።
“በምድርህ ላይ የሚገኘውን መጀመሪያ የደረሰውን ምርጥ ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አምጣ። “የፍየል ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።
“በመንገድ ላይ እንዲጠብቅህና ወዳዘጋጀሁት ስፍራ እንዲያመጣህ በፊትህ መልአክ እልካለሁ።
የሚልህን ስማ፤ ቃሉንም ታዘዝ። መተላለፋችሁን ይቅር ስለማይል በእሱ ላይ አታምፁ፤ ምክንያቱም እሱ ስሜን ተሸክሟል።
ይሁን እንጂ ቃሉን በጥንቃቄ ብትታዘዝና የምልህን ሁሉ ብታደርግ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ።
ምክንያቱም መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ እንዲሁም ወደ አሞራውያን፣ ሂታውያን፣ ፈሪዛውያን፣ ከነአናውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን ያመጣሃል፤ እኔም ጠራርጌ አጠፋቸዋለሁ።
ለአማልክታቸው አትስገድ፤ ወይም ተታለህ እነሱን አታገልግል፤ የሚያደርጉትን ነገር አታድርግ። ከዚህ ይልቅ አውድማቸው፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውንም ሰባብር።
አምላካችሁን ይሖዋን አገልግሉ፤ እሱም ምግብህንና ውኃህን ይባርክልሃል። እኔም ከመካከልህ በሽታን አስወግዳለሁ።
በምድርህ ላይ የሚኖሩ ሴቶች አያስወርዳቸውም ወይም መሃን አይሆኑም፤ ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ።
“አንተ ከመድረስህ በፊት ስለ እኔ ሰምተው ይፈራሉ፤ የምታገኛቸውም ሕዝቦች ሁሉ ግራ እንዲጋቡ አደርጋለሁ። ጠላቶችህም ሁሉ ድል ተመተው ከፊትህ እንዲሸሹ አደርጋለሁ።
ከአንተ አስቀድሜ ጭንቀት እልካለሁ፤ ሂዋውያንን፣ ከነአናውያንንና ሂታውያንን ከፊትህ አባሮ ያስወጣቸዋል።
ምድሩ ባድማ እንዳይሆንና የዱር አራዊት በዝተው እንዳያስቸግሩህ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፊትህ አባርሬ አላስወጣቸውም።
ቁጥርህ እስኪበዛና ምድሩን እስክትቆጣጠር ድረስ ጥቂት በጥቂት ከፊትህ አባርሬ አስወጣቸዋለሁ።
“ወሰንህንም ከቀይ ባሕር አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ባሕር እንዲሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ወንዙ ድረስ አደርገዋለሁ። ምክንያቱም የምድሩን ነዋሪዎች በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ አንተም ከፊትህ አባረህ ታስወጣቸዋለህ።
ከእነሱም ሆነ ከአማልክታቸው ጋር ቃል ኪዳን መግባት የለብህም።
በእኔ ላይ ኃጢአት እንድትሠራ እንዳያደርጉህ በምድርህ ላይ መኖር የለባቸውም። አማልክታቸውን ብታገለግል ወጥመድ ይሆንብሃል።”
በኋላም ሙሴ የእስራኤልን ማኅበረሰብ ሁሉ አንድ ላይ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንድትፈጽሟቸው ያዘዛችሁ ነገሮች እነዚህ ናቸው፦
ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእናንተ የተቀደሰ ይሆናል፤ ለይሖዋም ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል። በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራ ማንም ሰው ይገደላል።
በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በሰንበት ቀን እሳት አታቀጣጥሉ።”
ከዚያም ሙሴ ለእስራኤል ማኅበረሰብ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ሲል አዟል፦
‘ካላችሁ ነገር ለይሖዋ መዋጮ አምጡ። ልቡ ያነሳሳው ማንኛውም ሰው የሚከተሉትን ነገሮች ለይሖዋ መዋጮ አድርጎ ያምጣ፦ ወርቅ፣ ብር፣ መዳብ፣
ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደማቅ ቀይ ማግ፣ ጥሩ በፍታ፣ የፍየል ፀጉር፣
ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር እንጨት፣
ለመብራት የሚሆን ዘይት፣ ለቅብዓት ዘይትና ጥሩ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆን የበለሳን ዘይት፣
በኤፉዱና በደረት ኪሱ ላይ የሚቀመጡ የኦኒክስ ድንጋዮችና ሌሎች ድንጋዮች።
“‘በመካከላችሁ ያሉ ጥሩ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ሁሉ መጥተው ይሖዋ ያዘዘውን ነገር ሁሉ ይሥሩ፤
እነዚህም የማደሪያ ድንኳኑ ከተለያየ ቁሳቁሱና ከመደረቢያው ጋር፣ ማያያዣዎቹ፣ አራት ማዕዘን ቋሚዎቹ፣ አግዳሚ እንጨቶቹ፣ ዓምዶቹ፣ መሰኪያዎቹ፣
ታቦቱና መሎጊያዎቹ፣ መክደኛው፣ ለመከለያ የሚሆነው መጋረጃ፣
ጠረጴዛው እንዲሁም መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ በሙሉ፣ ገጸ ኅብስቱ፣
የመብራት መቅረዙና ዕቃዎቹ፣ መብራቶቹ፣ ለመብራቱ የሚሆነው ዘይት፣
የዕጣን መሠዊያውና መሎጊያዎቹ፣ የቅብዓት ዘይቱና ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን፣ ለማደሪያ ድንኳኑ መግቢያ የሚሆነው መከለያ፣
የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያ እንዲሁም የመዳብ ፍርግርጉ፣ መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ በሙሉ፣ ገንዳውና ማስቀመጫው፣
የግቢው መጋረጃ እንዲሁም ቋሚዎቹና መሰኪያዎቹ፣ ለግቢው መግቢያ የሚሆነው መከለያ፣
የማደሪያ ድንኳኑ ካስማዎችና የግቢው ካስማዎች እንዲሁም ገመዶቻቸው፣
በመቅደሱ ለማገልገል የሚለበሱት በጥሩ ሁኔታ የተሸመኑት ልብሶች፣ የካህኑ የአሮን ቅዱስ ልብሶች እንዲሁም ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸው ልብሶች ናቸው።’”
ከዚያም የእስራኤል ማኅበረሰብ በሙሉ ከሙሴ ፊት ሄደ።
ከዚያም ልባቸው የገፋፋቸውና መንፈሳቸው ያነሳሳቸው ሁሉ መጥተው ለመገናኛ ድንኳኑ ሥራና በዚያ ለሚከናወነው ማንኛውም አገልግሎት እንዲሁም ለቅዱሶቹ ልብሶች እንዲሆን መዋጮአቸውን ለይሖዋ አመጡ።
ፈቃደኛ ልብ ያላቸው ሁሉ፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የደረት ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ ቀለበትና ሌላ ጌጣጌጥ እንዲሁም ሁሉንም ዓይነት ከወርቅ የተሠራ ጌጣጌጥ ይዘው ይመጡ ነበር። ሁሉም የወርቅ መባዎቻቸውን ለይሖዋ አቀረቡ።
ደግሞም ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደማቅ ቀይ ማግ፣ ጥሩ በፍታ፣ የፍየል ፀጉር፣ ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ እንዲሁም የአቆስጣ ቆዳ ያላቸው ሁሉ እነዚህን አመጡ።
ብርና መዳብ የሚያዋጡ ሁሉ ለይሖዋ የሚሆነውን መዋጮ አመጡ፤ ለመገናኛው ድንኳን ሥራ የሚውል የግራር እንጨት ያላቸውም ሁሉ ይህን አመጡ።
ጥሩ ችሎታ ያላቸው ሴቶችም ሁሉ በእጃቸው ይፈትሉ ነበር፤ እነሱም የሚከተሉትን ነገሮች ፈትለው አመጡ፦ ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም ጥሩ በፍታ።
ጥሩ ችሎታ ያላቸው ልባቸው ያነሳሳቸው ሴቶች ሁሉ የፍየል ፀጉሩን ይፈትሉ ነበር።
አለቆቹም በኤፉዱና በደረት ኪሱ ላይ የሚቀመጡ የኦኒክስ ድንጋዮችንና ሌሎች ድንጋዮችን፣
የበለሳን ዘይቱን እንዲሁም ለመብራት፣ ለቅብዓት ዘይቱና ጥሩ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆነውን ዘይት አመጡ።
ልባቸው ያነሳሳቸው ወንዶችና ሴቶች በሙሉ ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት እንዲከናወን ላዘዘው ሥራ የሚውሉ ነገሮችን አመጡ፤ እስራኤላውያኑ ይህን በፈቃደኝነት የሚቀርብ መባ አድርገው ለይሖዋ አመጡ።
ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፦ “እንደምታዩት ይሖዋ ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሁር ልጅ ዖሪ የወለደውን ባስልኤልን መርጦታል።
ደግሞም በማንኛውም ዓይነት የእጅ ሙያ ማስተዋል፣ ጥበብና እውቀት በመስጠት በአምላክ መንፈስ ሞልቶታል።
ይኸውም የተለያዩ ንድፎችን እንዲያወጣ እንዲሁም በወርቅ፣ በብርና በመዳብ የተለያዩ ነገሮችን እንዲሠራ፣
ፈርጥ የሚሆኑትን ድንጋዮች እንዲቀርጽና በቦታቸው እንዲያስቀምጥ እንዲሁም ድንቅ የሆኑ ልዩ ልዩ የእንጨት ቁሳቁሶችን እንዲሠራ ነው።
አምላክም ለእሱና ከዳን ነገድ ለሆነው ለአሂሳማክ ልጅ ለኤልያብ ሌሎችን የማስተማር ችሎታ ሰጥቷቸዋል።
የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ የጥልፍ ባለሙያ እንዲሁም በሰማያዊ ክር፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ በደማቅ ቀይ ማግና በጥሩ በፍታ የሚሸምን የጥበብ ባለሙያ ብሎም የሽመና ባለሙያ የሚያከናውኗቸውን ሥራዎች በሙሉ እንዲሠሩ ጥሩ ችሎታ ሰጥቷቸዋል። እነዚህ ሰዎች ሁሉንም ዓይነት ሥራዎች የሚሠሩና ሁሉንም ዓይነት ንድፎች የሚያወጡ ነበሩ።
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጥረብ፤ እኔም በጽላቶቹ ላይ አንተ በሰበርካቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ።
አንተም በጠዋት ወደ ሲና ተራራ ወጥተህ በዚያ በተራራው አናት ላይ በፊቴ ስለምትቆም በጠዋት ለመሄድ ተዘጋጅ።
ሆኖም ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይውጣ፤ ደግሞም በተራራው ላይ በየትኛውም ቦታ ሌላ ማንም ሰው አይታይ። ሌላው ቀርቶ በጎችም ሆኑ ከብቶች እንኳ በተራራው ፊት ለፊት አይሰማሩ።”
በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት የመጀመሪያዎቹን የሚመስሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ከጠረበ በኋላ በጠዋት ተነስቶ ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች በእጁ ይዞ ነበር።
ከዚያም ይሖዋ በደመና ውስጥ ወርዶ በዚያ ከእሱ ጋር ሆነ፤ ይሖዋ የተባለውንም ስሙን አወጀ።
ይሖዋም በፊቱ እያለፈ እንዲህ ሲል አወጀ፦ “ይሖዋ፣ ይሖዋ፣ መሐሪና ሩኅሩኅ የሆነ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየ፣ ታማኝ ፍቅሩና እውነቱ እጅግ ብዙ የሆነ፣
ታማኝ ፍቅርን ለሺዎች የሚያሳይ፣ ስህተትን፣ መተላለፍንና ኃጢአትን ይቅር የሚል፣ ጥፋተኛውን ግን በምንም ዓይነት ሳይቀጣ የማያልፍ እንዲሁም አባቶች ለሠሩት ስህተት በልጆች፣ በልጅ ልጆች፣ በሦስተኛና በአራተኛ ትውልድ ላይ ቅጣትን የሚያመጣ።”
ሙሴም ወዲያውኑ መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ።
ከዚያም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ ይሖዋ፣ እኛ ግትር ሕዝብ ብንሆንም በመካከላችን ሆነህ አብረኸን ሂድ፤ ደግሞም ስህተታችንንና ኃጢአታችንን ይቅር በል፤ እንደ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።”
እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኔ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፦ በመላው ምድርም ሆነ በብሔራት ሁሉ መካከል ፈጽሞ ተደርገው የማያውቁ ድንቅ ነገሮችን በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ፤ ለአንተ ስል የማደርገው ነገር የሚያስፈራ ስለሆነ በመካከላቸው የምትኖረው ሕዝቦች ሁሉ የይሖዋን ሥራ ያያሉ።
“እኔ ዛሬ የማዝህን ነገር ልብ በል። እኔም አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ሂታውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ አስወጣቸዋለሁ።
በምትሄድበት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳትጋባ ተጠንቀቅ፤ አለዚያ ወጥመድ ይሆንብሃል።
ከዚህ ይልቅ መሠዊያዎቻቸውን ታፈራርሳላችሁ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ትሰባብራላችሁ፤ እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶቻቸውን ትቆራርጣላችሁ።
ይሖዋ፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ በመሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ ለሌላ አምላክ አትስገድ። አዎ፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው።
ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳትጋባ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም እነሱ አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር በሚፈጽሙበትና ለአማልክታቸው በሚሠዉበት ጊዜ ከመካከላቸው አንዱ አንተን መጋበዙ አይቀርም፣ አንተም ካቀረበው መሥዋዕት ትበላለህ።
ከዚያም ሴቶች ልጆቻቸውን ከወንዶች ልጆችህ ጋር ታጋባለህ፤ ሴቶች ልጆቻቸውም አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር መፈጸማቸው እንዲሁም ወንዶች ልጆችህ የእነሱን አማልክት በማምለክ ምንዝር እንዲፈጽሙ ማድረጋቸው አይቀርም።
“ከቀለጠ ብረት አማልክት አትሥራ።
“የቂጣን በዓል ታከብራለህ። ልክ ባዘዝኩህ መሠረት ቂጣ ትበላለህ፤ ከግብፅ የወጣኸው በአቢብ ወር ስለሆነ በአቢብ ወር በተወሰነው ጊዜ ላይ ለሰባት ቀን ይህን ታደርጋለህ።
“በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ የእኔ ነው፤ ደግሞም የመንጋህ በኩር ሁሉ፣ በኩር የሆነ በሬም ሆነ ተባዕት በግ የእኔ ነው።
የአህያን በኩር በበግ ዋጀው። የማትዋጀው ከሆነ ግን አንገቱን ስበረው። ከወንዶች ልጆችህ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ ትዋጀዋለህ። ማንም ባዶ እጁን ፊቴ አይቅረብ።
“ስድስት ቀን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋለህ። በሚታረስበትም ሆነ አዝመራ በሚሰበሰብበት ወቅትም እንኳ ታርፋለህ።
“የሳምንታት በዓልህን መጀመሪያ በደረሰው የስንዴ በኩር አክብር፤ የአዝመራ መክተቻን በዓልም በዓመቱ ማብቂያ ላይ አክብር።
“የአንተ የሆነ ሰው ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ የእስራኤል አምላክ በሆነው በእውነተኛው ጌታ በይሖዋ ፊት ይቅረብ።
ብሔራትን ከፊትህ አስወጣለሁና፤ ክልልህንም ሰፊ አደርገዋለሁ፤ የአምላክህን የይሖዋን ፊት ለማየት በዓመት ሦስቴ በምትወጣበት ጊዜ ማንም ምድርህን አይመኝም።
“የመሥዋዕቴን ደም እርሾ ከገባበት ከማንኛውም ነገር ጋር አድርገህ አታቅርብ። የፋሲካ በዓል መሥዋዕት እስከ ጠዋት ድረስ መቆየት የለበትም።
“መጀመሪያ የደረሰውን የአፈርህን ምርጥ ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አምጣ። “የፍየልን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።”
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ከአንተም ሆነ ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን የምገባው በእነዚህ ቃላት መሠረት ስለሆነ እነዚህን ቃላት ጻፍ” አለው።
እሱም በዚያ ከይሖዋ ጋር 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆየ። እህል አልቀመሰም፤ ውኃም አልጠጣም። እሱም በጽላቶቹ ላይ የቃል ኪዳኑን ቃላት ይኸውም አሥርቱን ትእዛዛት ጻፈ።
ከዚያም ሙሴ ከሲና ተራራ ወረደ፤ ሁለቱንም የምሥክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ነበር። ከአምላክ ጋር ሲነጋገር ስለቆየ ከተራራው በወረደበት ጊዜ ፊቱ እንደሚያንጸባርቅ አላወቀም ነበር።
አሮንና እስራኤላውያን ሁሉ ሙሴን ሲያዩት ፊቱ እንደሚያንጸባርቅ አስተዋሉ፤ ወደ እሱ ለመቅረብም ፈሩ።
ሙሴ ግን ጠራቸው፤ በመሆኑም አሮንና የማኅበረሰቡ አለቆች በሙሉ ወደ እሱ መጡ፤ ሙሴም አነጋገራቸው።
ከዚያም እስራኤላውያን በሙሉ ወደ እሱ ቀረቡ፤ እሱም ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ የሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ ሰጣቸው።
ሙሴም ከእነሱ ጋር ተነጋግሮ ሲጨርስ ፊቱን በመሸፈኛ ይሸፍን ነበር።
ሙሴ፣ ይሖዋ ፊት ቀርቦ ከእሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ግን ከዚያ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን ያነሳ ነበር። ከዚያም ወጥቶ የተቀበለውን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን ይነግራቸው ነበር።
እስራኤላውያንም የሙሴ ፊት እንደሚያንጸባርቅ ተመለከቱ፤ ከዚያም ሙሴ አምላክን ለማነጋገር ወደ ውስጥ እስከሚገባበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን መልሶ ፊቱ ላይ አደረገው።
በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን “አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ። በኃያል ክንድ ተገዶ ይለቃቸዋል፤ በኃያል ክንድ ተገዶም ከምድሩ እንዲወጡ ያደርጋቸዋል” አለው።
ከዚያም አምላክ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ ይሖዋ ነኝ።
ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሁሉን ቻይ አምላክ ሆኜ እገለጥላቸው ነበር፤ ይሖዋ የሚለውን ስሜን በተመለከተ ግን ራሴን ሙሉ በሙሉ አልገለጥኩላቸውም።
በተጨማሪም የከነአንን ምድር ማለትም የባዕድ አገር ሰው ሆነው የኖሩባትን ምድር ልሰጣቸው ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።
እንግዲህ አሁን ግብፃውያን በባርነት እየገዟቸው ያሉት የእስራኤል ሰዎች እያሰሙት ያለውን የሥቃይ ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም አስባለሁ።
“ስለዚህ እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከግብፃውያን ከባድ ሸክም ነፃ አወጣችኋለሁ፤ ከጫኑባችሁም የባርነት ቀንበር አላቅቃችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድና በታላቅ ፍርድ እታደጋችኋለሁ።
የራሴ ሕዝብ አድርጌ እወስዳችኋለሁ፤ አምላካችሁም እሆናለሁ፤ እናንተም ከግብፃውያን ከባድ ሸክም ነፃ የማወጣችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ታውቃላችሁ።
ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት እጄን አንስቼ ወደማልኩላቸው ምድር አስገባችኋለሁ፤ ርስት አድርጌም እሰጣችኋለሁ። እኔ ይሖዋ ነኝ።’”
ከዚያም ሙሴ ለእስራኤላውያን ይህን መልእክት ነገራቸው፤ እነሱ ግን ተስፋ ከመቁረጣቸውና አስከፊ ከሆነው የባርነት ሕይወታቸው የተነሳ ሊሰሙት ፈቃደኞች አልሆኑም።
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦
“ወደ ግብፁ ንጉሥ ወደ ፈርዖን ገብተህ እስራኤላውያንን ከምድሩ እንዲያሰናብታቸው ንገረው።”
ሆኖም ሙሴ “እንግዲህ እስራኤላውያን ሊሰሙኝ ፈቃደኛ አልሆኑም፤ ታዲያ የመናገር ችግር ያለብኝን እኔን፣ ፈርዖን እንዴት ብሎ ሊሰማኝ ይችላል?” በማለት ለይሖዋ መለሰ።
ይሖዋ ግን እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ለማውጣት ለእነሱና ለግብፁ ንጉሥ ለፈርዖን ማስተላለፍ ያለባቸውን ትእዛዝ ለሙሴና ለአሮን በድጋሚ ነገራቸው።