en
stringlengths
4
1.47k
am
stringlengths
4
1.12k
My plan is to pay off my car early, and then work on the other debts.
እቅዴ አስቀድሞ የመኪናዬን ዕዳ መክፈል ነው፤ ከዚያም ሌሎች ዕዳዎቼን ለመክፈል የምችልበትን ዘዴ ማፈላለግ ነው።
The expected Canadian move has been welcomed by the Bush administration even though Canada has opposed such U.S. actions as the trade embargo against Cuba, the invasion of Grenada and the military support for Nicaragua's Contra guerrillas.
ዩ.ኤስ በኩባ ላይ የንግድ ማዕቀብ መጣሏን፣ ግሪናዳን መውረሯንና ለኒካራጓ ኮንትራ ደፊጣ ተዋጊዎች ወታደራዊ ዕርዳታ መስጠቷን ካናዳ ብትቃወምም እንኳን የተጠበቀው የካናዳ እንቅስቃሴ በቡሽ አስተዳዳር ተቀባይነትን አግኝቷል።
And so we certainly do not want to limit access or will not limit access to the National Park, but we need to design the facilities, design parking areas, design the infrastructure in a way that we can handle these large amounts of people.
ስለሆነም ወደ ብሔራዊ ፖርክ የመግባትን ዕድል በእርግጥ ለመቀነስ አንፈልግም ወይም ውሱን አናደርግም፤ ግን ይህን ሁሉ ሕዝብ ለማስተናገድ በሚያስችለን ሁኔታ ድርጅቶችን፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን፣ መሠረቱ ልማቶችን ለማመቻቸት እንፈልጋለን።
Administration officials traveling with President Bush in Costa Rica interpreted Mr. Ortega's wavering as a sign that he isn't responding to the military attacks so much as he is searching for ways to strengthen his hand prior to the elections.
ከሚስተር ቡሽ ጋር ወደ ኮስታሪካ የሄዱ የአስተዳደር ባለሥለጣናት የሚስተር ኦርቴጋን መዋዠቅ ከምርጫው በፊት ክንዳቸውን የሚያጠነክሩበት መንገድ መፈለግ እንዷ ለተሰነዘረባቸው ወታደራዊ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት እንዳልፈለጉ የሚያሳይ ምልክት ነው ብለውታል።
But Pretoria may instead be creating a climate for more turmoil and uncertainty in this racially divided country.
ግን ፕሪቶሪያ በዚህ ፋንታ በዚች በዘር በተከፋፈለች አገር ውስጥ የከፋ የብጥብጥና ያለመተማመን አየር ትፈጥራለች።
On Monday, U.S. officials received a routine, unclassified message from the military group commander in Panama.
ሰኞ ዕለት የየ.ኤስ ባለሥልጣናት ከፓናማ የወታደራዊ ቡድን አዛዥ አንድ የተለመደ ተራ መልእክት ደረሳቸው።
Small crops are grown in Pakistan, France, Spain, Italy, Belgium and Brazil, but their quality can't compare to that of Indian psyllium.
ትንንሽ ዘሮች ፓኪስታን፣ ፈረንሳይ፣ እስፔን፣ ጣሊያን፣ ቤልጂየምና ብራዚል ያድጋሉ፤ ግን ጥራታቸው ከሕንድ ሳይሊየም ጋር የሚወዳደር አይደለም።
Sandstorms, dangerously long supply lines and a recalcitrant enemy "has led to abroad reassessment by some top generals of US military expectations and timelines," the Post reports.
አሸዋማ ውሽንፍር፣ በአደገኛ ሁኔታ ላይ የሚገኝ የአቅርቦት መስመሮች እና እምቢተኛ ጠላት መገኘት «የዩ.ኤስ ወታደራዊ ጄኔራሎች ቀድመው በወጠኑአቸው የጊዜ ገደብና ግመታ ላይ ሰፋ ያለ ዳግም ግመታ እንዲያደርጉ መርቷቸዋል» ፓስት እንደዘገበው።
Our offices are in one of the patio homes, and I have my own lovely office with a window.
ቢሮዎቻችን ከክፍት /ጣሪያ አልባ/ ቤቶች በአንዱ ውስጥ ናቸው፤ እኔም መስኮት ያለው የግሌ ቆንጆ ቢሮ አለኝ።
The plant has a hairy stem that produces flowers and diminutive seeds.
ተክሉ አበባ የሚያወጣና ጥቃቅን ፍሬዎችን የሚያፈራ ፀጉር ነገር የበዛበት ዛፍ አለው።
The Palestinian Authority also condemned Thursday's early morning missile strikes on Iraq, and warned Israel not to exploit the conflict.
በተጨማሪ የፍልስጤም ባለስልጣን ሐሙስ በማለዳ ጠዋት በኢራቅ ላይ የተወረወረውን ሚሳኤል በማውገዝና እስራኤልም ይህንን ጠብ ተገቢ ላልሆነ አላማ እንዳትጠቀምበት አስጠንቅቋል።
"The government can never put the ANC back into the bottle again," said Cassim Saloojee, a veteran anti-apartheid activist on hand to welcome Mr. Sisulu.
«ከእንግዲህ መንግሥት ኤ.ኤን.ሲን መልሶ ጠርሙስ ውስጥ ማስገባት ፈጽሞ አይችልም» ብለዋል አንጋፋው ፀረ አፖርታይድ ታጋይ ቃሲም ሳሉጂ ሚስተር ሲሱሉን እንኳን ደህና መጡ ለማለት መጥተው እጅ ለእጅ እንደተጨባበጡ።
The flood of claims and counter-claims worried consumers and actually hurt sales of the new cereals.
ለመግዛት በሚጐርፈው ጥያቄና በአጸፋዊ መልሱ ተጠቃሚውቹን አስጨነቃቸው፤ የአዲሱን የጥራጥሬ ምግብ ሽያጭንም በእርግጥ ጐድቶታል።
The U.S. soon found new cause for concern: gun-running.
ዩ.ኤስ ለችግሯ ወዲያው ምክንያት አገኘች፣ መሣሪያን በድብቅ የማስገባት ጉዳይ።
Diplomats and analysts have commented that a joint investigation into the attack may in fact strengthen ties between the world super power and the poor, but strategic Arab state.
ዲኘሎማቶችና ተንታኞች አስተያየት ሲሰጡ የደረሰውን ጥቃት በጋራ መመርመሩ በዓለም ብቸኛዋ ኃያል አገርና በዳሃዋ ግን ስትራቴጂያዊ በሆነች አረብ አገር መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠነክረዋል ብለዋል።
Public protests against him were triggered in June 1987 due to charges by Diaz Herrera, his former chief of staff, that Mr. Noriega had stolen the 1984 election and had ordered the killing of Messrs. Spadafora and Torrijos.
ሚስተር ኖሬጋ የ1984ን ምርጫ በስርቆት በማሸነፉና ሚስተር እስፖዳፎራና ሚስተር ቶሪጆስ እንዲገደሉ በማዘዙ የቀድሞው የእሱ ከፍተኛ መኮንን የነበረው ዲያዝ ሄሬራ በማሳጣቱ ምክንያት በጁን 1987 በእሱ ላይ የተነሣው የሕዝብ አመፅ በዚህ ላይ ያተኮረ ነበር።
Sen. Dole also said he hoped for unanimous support for a resolution he plans to offer tomorrow denouncing the Nicaraguan leader.
ሴኔተር ዶልም እንዲሁ ነገ የኒካራጓን መሪ በማውገዝ ለማውጣት ያቀደው ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ድጋፍ እንደሚያገኘ ተስፋ እንዳለው ተናግሯል።
Iraqi opposition leaders fear the United States is trying to force Ahmed Chalabi, head of the London-based umbrella Iraqi National Congress, on them as leader of a new Iraqi administration.
የኢራቅ ተቃዋሚ ኃይሎች ፍራቻ ዩናይትድ ስቴትስ ሎንደን ያደረገውና በአህመድ ቻላቢ የሚመራው የኢራቅ ብሔራዊ ኮንግሬስን በአዲሱ የኢራቅ አስተዳደር ስም እንዳይሾምባቸው ነው።
I know the special relationship that the Qatari foreign minister has with Abu Mazen," he said, using Abbas's alternative name.
«እኔ የካታሩ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአቡ ማዜን ጋር ያላቸውን ጥብቅ ግንኙነት አውቃለሁ» አሉ የአባሰን ሌላ ስም በመጠቀም።
In Amman, three protestors were hospitalised after some 500 Jordanian lawyers staged a sit-in at the main court house after being forcibly blocked by riot police from marching towards the Iraqi embassy to show their solidarity.
በአማን ሶስት ተቃዋሚዎች ወደ ሆስፒታል ለህክምና የተወሰዱ ሲሆን ይህም የሆነው 500 በሚደርሱ የዮርዳኖስ ጠበቆች ባቀናበሩት ዋናው ፍርድ ቤትን በመያዝ የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰልፈኞቹ ወደ ኢራቅ ኤምባሲ በመሔድ አንድነታቸውን በመግለፅ ላይ እንዳሉ በአድማ በታኝ ፖሊሶች የኃይል ጥቃት ስለደረሰባቸው ነው።
Where non-violent civil disobedience is the centerpiece, rather than a lawful demonstration that may only attract crime, it is difficult to justify.
ወንጀልን ብቻ ሊስብ ከሚችለው ሕጋዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይልቅ አመፅ አልባ ለሕግ አልገዛም ባይነት እንደ ዋና ነገር ከተቆጠረ ለዚህ በቂ ምክንያት ለመስጠት ያስቸግራል።
The agency won't allow mushrooms that were canned or packed in brine at any Chinese plant to enter the U.S. until "satisfactory sanitation-control measures are implemented in China to prevent" bacterial contamination.
የባክቴሪያ ብክለትን ለመከላከል «ተገቢ የሆነ የጽዳት ቁጥጥር እርምጃ ቻይና ውስጥ አስካልተወሰደ ድረስ» እንጉዳይን በጨው እየቀመመ በቆርቆሮ ወይም በካርቶን እያሸገ የሚልክ የቻይና ኢንዱስትሪ ውጤት ወደ ዩ.ኤስ እንደገባ ኤጀንሲው ፈጽሞ አይፈቅድም።
During the Nixon administration, the Drug Enforcement Administration became dismayed at the extent of the G-2's connections to arrested drug traffickers.
በኒክሰን አስተዳደር ጊዜ ከታሰሩት አደንዛዥ ዕፅ አስተላላፊዎች ጋር ጂ-2 ግንኙነት እስከመፍጠር ደረጃ በመድረሱ ስለ አደንዛዥ ዕፅ የወጣውን ሕግ ለማስከበር የተቋቋመውን አስተዳደር ተስፋ ከመቁረጥ ደረጃ አድርሶታል።
And the investigators were quickly closing in on Mr. Noriega himself.
እናም መርማሪዎቹም በፍጥነት ወደራሱ ወደ ሚስተር ኖሬጋ ተቃርበዋል።
"Due to health reasons, Lt. Col. Noriega has elected to postpone his visit to Washington," it read.
«በጤና መክንያት ሌተናል ኮሎኔል ኖሬጋ የዋሽንግተን ጉብኝቱን ለሌላ ጊዜ ወስኗል» ይላል መልእክቱ።
"The Storyteller" (Farrar, Straus & Giroux, 246 pages, $17.95), splendidly translated by Helen Lane, first appeared in Spanish in 1987 before the Peruvian economy had reached its present state of virtual collapse.
«ተረት ተናጋሪው» /ፋራር፣ እስትራውስ እና ጊሮውክ 246 ገጽ፣ $17.95/ መጽሐፍ በሄለን ላን በግሩም ሁኔታ ተተርጉሞ ፔሩ አሁን ካለችበት ኢኮኖሚያዊ ውድቀት ከመግባቷ በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ በ1987 በእስፔንኛ ቋንቋ ታትሞ ወጥቷል።
Well, North Korea's attitude has been that if the United States and North Korea are friends and the North Koreans don't feel threatened, they wont object to some US forces remaining in the Korean peninsula in a new role.
ይህም ማለት ሰሜን ኮሪያን ለመውጋትና የደቡብ ኮሪያ አጋር በመሆን ከዚያ የሚቆዩ ከሆነ ሰሜን ኮሪያ ከዚያ እንዲቀመጡ አትፈልግም፤ ዩ.ኤስ ጦሯን እንድታስወጣ ጫናቸውን ይቀጥላሉ።
Saul mysteriously disappears.
ሳውል ባልታወቀ መንገድ ተሰወረ።
Senate Minority Leader Robert Dole (R., Kan.) said yesterday on "Meet the Press": "I would hope after his {Mr. Ortega's} act yesterday or the day before, we'd have unanimous support for quick action on remaining humanitarian aid."
የሴኔት አናሳዎች መሪ ሮበርት ዶል /አር.ካን/ «ከፕሬስ ጋር ተገናኙ» በሚለው ፕሮግራም ሲናገሩ «ትናንት ወይም ከትናንት በፊት እሳቸው /ሚስተር ኦርቴጋ/ ከወሰዱት እርምጃ በኋላ በቀሪው ሰብአዊ ዕርዳታ ላይ አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ሙሉ ድጋፍ እንደምናገኝ ተስፋ ነበረኝ» ብለዋል።
After the Sioux City crash, Lori Michaelson bought a car seat for her daughter for the flight home to Cincinnati.
ከሲውክለ ከተማ የአውሮኘላን አደጋ በኋላ ሎሪ ሚቻኤልሰን ወደ አገሯ ወደ ሲንሲናቴ በምትበርበ ጊዜ ልጇ በመኪና ውስጥ የምትጠቀምበት መቀመጫ ገዛችላት።
The two have already met four times this year.
ሁለቱ በዚህ ዓመት አራት ጊዜ ተገናኝተዋል።
The forty-two prisoners were captured two years ago during clashes with the guerilla group.
42ቱ እስረኞች ከሁለት ዓመት በፊት የተያዙት ከደፈጣ ተዋጊዎች ጋር በተፈጠረው ግጭት ነበር።
And out of necessity: the U.S. can make mistakes and still hope to remove him from power, but a single error on his part could cost him his life.
እናም ከፍላጐት የተነሣ ዩ.ኤስ ስህተት ልትሠራ ትችላለች፤ ሰውየውን ከሥልጣን ለማውረድ አሁንም ተስፋ አላት፤ ግን በእሱ በኩል የሚፈጸም አንድ ስህተት ለሞት ይዳርገዋል።
When Vanessa Merton, an associate dean at Pace University School of Law, decided to take her young son to Europe last spring, she called four carriers to ask about their policies on car seats.
በፔስ ዩኒቨርስቲ የሕግ ት/ቤት ተባባሪ ዲን የነበረችው ቫኔሳ ሜርቶን ባለፈው የፀደይ ወራት ልጇን ወደ አውሮፖ ለመውሰድ በወሰነችበት ጊዜ በእጅ ስለሚያዙ መቀመጫዎች ያላቸውን ፖሊሲ ለማወቅ አራት ሕዝብ አመላላሽ ኩባያዎችን ጠርታ አነጋገረች።
Where truly representative governments are safeguarded by constitutional protections of human rights and an independent judiciary to construe those rights, there is no excuse for breaking the law because some individual or group disagrees with it.
በትክክለኛ መንገድ በሕዝብ የተመረጡ መንግሥታት በሰብአዊ መብቶች ሕገ መንግሥታዊ ጥበቃ ከተደገፉና እነዚህን መብቶች የሚተረጉም ነፃ ፍርድ ቤት ካለ አንዳንድ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች አልተስማሙበትም ተብሎ ሕግን መጣስ ይቅርታ የሚደረግለት ጉዳይ አይሆንም።
We don't know who is winning the drug war in Latin America, but we know who's losing it -- the press.
በላቲን አሜሪካ በአደንዛዥ ዕፅ ጦርነት አሸናፊ ማን እንደሆነ አናውቅም፤ ግን ተሸናፊው ማን እንደሆነ እናውቃለን---ጋዜጦች።
Under the guise of "healing the wounds of the nation," President Carter pardoned thousands of draft evaders, thus giving dignity to their allegations of the war's "immorality."
«የሕዝቡ ቁስል እንዲያገግም» በሚል ሽፋን ፕሬዚዳንት ካርተር በብዙ ሺህ የሚቆጠሩትን ለወታደርነት በግዴታ ከመመልመል ያመለጡትን ይቅርታ መጠየቃቸው ጦርነቱን «ከግብረ ገብነት ውጭ የሆነ» ብለው ለተናገሩት ቃል ክብር መስጠት ነው።
In either case, ask yourself whether you have become better informed on the issues under protest by watching the act of civil disobedience.
በየትኛውም ጉዳይ ቢሆን፣ ለሕግ አልገዛም ባይነትን ድርጊት እየተከታተልክ ተቃውሞ የተነሳበት ጉዳይ በደንብ ተረድተኽው ከሆነ እስቲ ራስህን ጠይቅ።
McCarthy currently heads the Office of Gas and Electricity Markets, or Ofgem, which regulates Britain's privatised energy industry.
ማካርቲ በአሁኑ ጊዜ የእንግሊዝን የሃይል ኢንዱስትሪ የሚቆጣጠረውን የጋዝና የኤሌክትሪክ ገበያዎች ጽህፈት ቤትን ወይም ኦ.ኤፍ.ጂ.ኢ.ኤም ን ይመራል።
Over at Conradies, the general store, a black stock boy scurries to help an elderly white woman with her packages.
ከኮንራዲስ ባሻገር ካለው የገበያ አዳራሽ አንድ ጥቁር ልጅ እቃዋን ጠቅልላ የያዘች አንዲት ጠና ያለች ነጭ ሴት ለመርዳት ይሯሯጣል።
The issue has been simmering for years.
ይህ ጉዳይ ለብዙ ዓመታት እየተለሳለሰ ቆይቷል።
After briefing US senators on the war, Rumsfeld told reporters that the number of forces "has been increasing and it will continue to do so until it is finished."
ራምስ ፊልድ ስለጦርነቱ ጉዳይ ለሴናቶሮች ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ የወታደራዊ ኃይሎች ቁጥር «እየጨመረ መሆኑንና ይህም ጦርነቱ እስከሚያበቃ ድረስ ይቀጥላል» ሲሉ ለዘጋቢዎች ገልፀዋል።
And why the political leaders will have such a hard time keeping the streets -- getting the streets calm.
ለምን ብለው ነው የፖለቲካ መሪዎች መንገዶችን ለመጠበቅ -- የመንገዶችን ፀጥታ ለማስከበር ጊዜያቸውን የሚያጠፉት?
Rodrigo Miranda, a local lawyer and human-rights monitor, recalls an intoxicated Noriega visiting prisoners in their cells at the 5th Zone Garrison headquarters in David, where he had his offices.
የአካባቢው ጠበቃ የሰብአዊ መብት ተከላካይ ሮድሪጐ ሚራንዳ አስታውሶ እንደተናገረው የእሱ ቢሮዎች ባሉበት ዳቪድ ውስጥ በ5ኛው ዞን ጋሪሰን ዋና መሥሪያ ቤት በሥካር የነበዘው ኖሬጋ በእሥረኞች ክፍል ገብቶ ጉብኝት ማድረጉን ገልጿል።
"Nothing is too good for our golf course," says Tony George, a mining engineer.
«ለጐልፍ ሜዳችን ምንም ጥሩ ነገር የለም» አለ የማዕድን ማውጣቱ ኤንጂነር ቶኒ ጆርጅ።
"We must either integrate honestly or segregate honestly."
«አንድም ከልብ መዋሐድ አሊያም ከልብ ማግለል ይኖርብናል።»
Mr. Cohen will depart next Tuesday to visit Saudi Arabia, Kuwait, Bahrain, Oman, the United Arab Emirates, Qatar, Israel, Jordan and Egypt.
ሚስተር ኮኸን ሳውዲ አረቢያን፣ ኩዌትን፣ ባሕሬንን፣ ኦማንን፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን፣ እስራኤልን፣ ዮርዳኖስንና ግብፅን ለመጐብኘት በሚቀጥለው ማክሰኞ ይነሣሉ።
We just got new computers a week and half ago, and she's griping about XP (her old OS was Windows 98--mine was 95, so I'm thrilled with the new stuff).
ከአንድ ሣምንት ተኩል በፊት አዳዲስ ኮምፒውተሮች አግኝተናል፤ እሷ ግን ስለኤክስ ፒ /XP/ አቤቱታ እያቀረበች ነው /የሷ አሮጌ ኦ ኤስ /OS/ ዊንዶው 98--- የኔ ደግሞ 95 ስለሆነ እኔ በአደዲሶቹ ኮምፒውተሮች ጥልቅ የደስታ ስሜት ተሰምቶኛል።
Mr. Noriega's proposal was turned down.
ሚስተር ኖሬጋ ያቀረበው ሐሳብ ውድቅ ሆኗል።
The meeting concluded with the delegates voting by show of hands to meet again in 10 days.
ስብሰባው የተጠናቀቀው ተወካዮች ከ10 ቀናት በኋላ እንደገና ለመገናኘት እጃቸውን አውጥተው ድምፅ በመስጠት ነበር።
G got me a nice office stereo for my birthday and it does have an aux jack, so I could listen to it here.
ጂ ለልደቴ የምታምር የቢሮ ሲዲ ማጫወቻ ሸለመችኝ ረዳት ማዳመጫ ስላላት ከዚህ ሆኜ መስማት እችላለሁ።
U.S. officials hope more Iraqis join the process and stressed that this was just the first of many such meetings in Iraq.
ሒደቱን ከዚህ የበለጡ ኢራቃውያን ተካፋይ እንደሚሆኑ ተስፋ እንዳላቸውና ይህ በኢራቅ ውስጥ በተመሳሳይ አይነት ከሚካሄዱ ብዙ ስብሰባዎች ውስጥ ገና የመጀመሪያው እንደሆነ የዮኤስ ባለስልጣናት አስምረውበታል።
Russia accuses the former US naval intelligence officer of illegally obtaining secrets about a high-tech Russian torpedo.
ከሰርጓጅ መርከብ ስለሚወረወርና በከፍተኛ ቴክኖሎጂ ስለተሰራ የሩሲያ ፈንጂ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሚስጥር ለማግኘት ሞክሯል ስትል ሩሲያ የቀድሞውን የዩ.ኤስ ባሕር ኃይል የደህንነት መኮንን ከሰሰች።
He was superb.
ሰውየው በጣም የሚደነቅ ነበር።
The spy network would serve two clients: the Panamanian government, by monitoring political opponents in the region, and the U.S., by tracking the growing Communist influence in the unions organized at United Fruit Co.'s banana plantations in Bocas del Toros and Puerto Armuelles.
የስለላው መዋቅር ሁለት ደንበኞችን ያስተናግዳል፤ የፖናማ መንግሥት በክልሉ ውስጥ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን ይቆጣጠራል፤ ዩ.ኤስ ደግሞ ባካስ፣ ዴል ቶሮስና ፑኤርቶ አርሙኤልስ ውስጥ በተባበሩት የፍራፍሬ ኮርፖሬሽን የሙዝ ተክል ሥር በተደራጁት ማኀበራት ውስጥ የኮሚኒስትን ተጽእኖ ፈለግ ትከታተላለች።
So then as North Korea opens up more and more, what are the possible repercussions down the road for the nearly 40,000 American troops who remain in South Korea?
ደህና፣ የሰሜን ኮሪያ ዝንባሌ እንግዲህ ሰሜን ኮሪያና ዩ.ኤስ ወዳጅነት ከመሠረቱና ሰሜን ኮሪያ የሥጋት ስሜት የማይፈጥርባት ከሆነ ጥቂት የዩ.ኤስ ወታደሮች ለአዲስ ሚና በኮሪያ ባሕረ ገብ መሬት ቢቀሩ ተቃውሞ አይኖራትም።
Mr. Ingersoll later recalled that Gen. Torrijos seemed afraid to act on the concerns of the U.S.
ሚስተር ኢንገርሶል በኋላ እንዳስታወሱት ጄኔራል ቶሪጆንስ ዩ.ኤስን ስላሳሰባት ጉዳይ ለመናገር የፈሩ ይመስላል።
While infections among adults are decreasing, infections among children are increasing.
በበሽታው የመያዝ ሁኔታ በአዋቂዎች ላይ እየቀነሰ ሲሄድ በልጆች ላይ እየጨመረ ሄዷል።
She was looking for a Development Assistant at the retirement community where she works.
በምትሠራበት መስሪያ ቤት ለጡረተኞች ማህበረሰብ ረዳት የዕድገት ሠራተኛ ትፈልግ ነበር።
As a result, they often speak one language at home, another at school.
በዚህም የተነሣ በቤታቸው በአንድ ቋንቋ ት/ቤት ደግሞ በሌላ ቋንቋ ይናገራሉ።
Others worry that the FAA might write a rule forcing airlines to pick up part of the tab for increased infant safety.
ሌሎች ደግሞ የፌደራሉ አየር ማመላለሻ አስተዳደር የሕፃናትን ደኀንነት ለመጨመር ሲል ገሚሱን የህግ ረቂቅ እንዲያወጣ አየር መንገዱን በሕግ ያስገድደዋል ብለው ይጨነቃሉ።
Five countries announced they would not honor what one Zimbabwean delegate wryly called the "made in Switzerland" solution.
አንድ የዝምባብዌ ልኡክ ፊቱን ኮሶ አስመስሎ «ስዊዘርላንድ የተሠራ» መፍትሔ ነው ብሎ ለተናገረው ክብር እንደማይሰጡት አምስት አገሮች ገልጸዋል።
"We emphasize discipline because we know that the government is very, very sensitive," said Andrew Mlangeni, another early Umkhonto leader who is now 63.
«ስለዲሲፒሊን አጽንኦት እናደርጋለን፤ ምክንያቱም መንግሥት በጣም፣ በጣም የሚሰማው መሆኑን እናውቃለን» ብሏል አሁን 63 ዓመት የሆነው የኡምክሪሆንቶ ሌላው የድሮ መሪ አንድሪው ምላንገኒ።
When President Corazon Aquino, whose command of Filipino is spotty, announced last year that the language would be used in official communications, there was an uproar from many legislators, who continue to conduct debates mostly in English.
የፊሊፒኖ ችሎታቸው ተለዋዋጭ የሆነው ፕሬዚዳንት ኮራዞን አኩኢኖ ይህ ቋንቋ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ባለፈው ዓመት ሲገልጹ ክርክራቸውን በአብዛኛው በእንግሊዘኛ የቀጠሉት አብዛኛዎቹ ሕግ አውጪዎች ሁካታውን አቀለጡት።
The head of the DEA at the time, John Ingersoll, scotched the assassination plan.
በወቅቱ የአደንዛዥ ዕፅ ሕግ አስከባሪ አስተዳደር ኃላፊ የነበሩት ጆን ኢንገርሶል የግድያዉን ዕቅድ እንዲቋረጥ አደረጉ።
In one way, the psyllium middlemen -- the buyers and exporters -- are glad to keep news of the boom to themselves.
በአንድ መንገድ የሳይሊየም መካከለኛ ሰዎች -- ገዥዎችና ኤክስፐርቶች -- የገበያውን መድራት ዜና ለብቻቸው አፍነው በመያዛቸው ይደሰታሉ።
It is difficult, however, to justify civil disobedience, non-violent or not, where citizens have full recourse to the ballot box to effect change.
የሆነ ሆኖ ዜጐች በምርጫ ሳጥን ለውጥ ለማምጣት ቀና መንገድ ካገኙ በአመፅም ሆነ ያለአመፅ ለሕግ አልገዛም ባይነትን ተገቢ አስመስሎ ለማቅረብ በጣም ይከብዳል።
The Greens from the First World wanted a morality play, not a negotiation.
ከአንደኛው ዓለም የመጡትና ዘግሪንስ የተባሉት በስምምነት ሳይሆን ከሞራል አንፃር እንዲወሰን ፈልገው ነበር።
In the Egyptian capital, 10 demonstrators and at least four policeman were injured in clashes after several thousand demonstrators took to the streets near the US and British embassies.
በግብፅ መዲና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች በአሜሪካና በእንግሊዝ ኤምባሲዎች አካባቢ አደባባይ የወጡ ሲሆን 10 ሰላማዊ ሰልፈኞችና ቢያንስ አራት ፖሊሶች ቆስለዋል።
The report charged that Panama's Manuel Noriega is not only in league with the drug traffickers but also is bullying the press as never before.
የፖናማው ማኑኤል ኖሪዬጋ ከአደንዛዥ ዕፅ ሕገ ወጥ ንግድ አስተላላፊዎች ጋር አባሪ ተባባሪ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ፕሬሱን ለመጉዳት ጥረት በማድረጉ ነበር ሪፖርቱ የወነጀለው።
Mr. Barco has refused U.S. troops or advisers but has accepted U.S. military aid.
ባርኮ የዩ.ኤስ ወታደሮችንና አማካሪዎችን አልተቀበለም፤ ነገር ግን የዩ.ኤስ ወታደራዊ ዕርዳታን ተቀብሏል።
"It was believed Naotia was a practicing sorcerer and through his black magic he had cast evil spells on villagers, prompting a group within the village to eliminate them," the spokesman said.
«ናኦቲያ አስማተኛ ነበር፣ እናም በጥቁር አስማቱ መንደርተኞቹን በመተት በማሰር ከዚያው መንደር አንድ ቡድን ተነስቶ እንዲያጠፋቸው አድርጓል» ሲል ይኽው ቃል አቀባይ ገልጿል።
Accounts of previous such meetings with media and other groups have been printed, sometimes after a delay of several days.
ከዜና ማሠራጫ አውታሮች እና ከሌሎች ቡድኖች ጋር ቀደም ሲል የተካሄዱት የዚህ ዓይነት ስብሰባዎች ዘገባዎች ለጥቂት ቀናት ከተጓተቱ በኋላ ታትመው ወጥተዋል።
But U.S. intelligence, rather than rein in or cut loose its new spy, merely filed the report away.
ግን የዩ.ኤስ ደኀንነት ከዚህ ሰላይዋ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጥ ወይም ከእጇ እንዳይወጣ ከማድረግ ይልቅ እንዲሁ ሪፖርቱን መዝግቦ አስቀመጠ።
For the first time, the U.S. considered cutting Mr. Noriega from its intelligence payroll -- and the deliberations were intense, Mr. Turner says.
ለመጀመሪያ ጊዜ ዩ.ኤስ ሚስተር ኖሬጋን ከደኀንነት ደመወዝ መክፈያ ዝርዝር ውስጥ ለመሠረዝ አሰበች-- እናም ጥንቃቄው በጣም የጠነከረ እንደነበር ሚስተር ተርነር ተናግረዋል።
Officials say the trouble began when striking dock workers tried to storm the port authority offices and police fired to disperse them.
ችግሩ የተከሰተው ሥራ ያቆሙ የመርከብ መቆሚያ ሠራተኞች የወደቡን ባለሥልጣናት ቢሮዎች ለመውረር ሲሞክሩ ፖሊሶች እነሱን ለመበተን በተኮሱበት ጊዜ ነበር።
At the same time, six ANC colleagues, five of whom were arrested with him in 1963 and sentenced to life imprisonment, were reunited with their families at various places around the country.
በዚያው ወቅት ስድስት የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ የሥራ ጓደኞች፣ ከእነሱም ውስጥ አምስቱ በ1963 ከእሳቸው ጋር የታሰሩና የዕድሜ ልክ እሥራት የተፈረደባቸው ነበሩ፣ በአገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላሉ።
Last year, when the rising Orange River threatened to swamp the course, the same engineers who are pushing back the Atlantic rushed to build a wall to hold back the flood.
ባለፈው ዓመት እየሞላ የሚሄደው የብርቱካናማው ወንዝ ሜዳውን ያጥለቀልቃል የሚል ሥጋት በማስከተሉ አትላንቲክን ወደ ኋላው እንዲመለስ ያደረገው ኤንጂነር ጐርፉን የሚያግድ ግንብ ለመሥራት ተጣደፈ።
Among them, dioxins and other chemicals, which are known as "the dirty dozen."
ክእነዚህም መካከል ዳዬክሲንስ እና ሌሎች ኬሚካሎች ሲሆኑ «ስድስቱ ቆሻሻዎች» በመባል የሚታወቁ ናቸው።
After 26 years in prison, Mr. Sisulu, the 77-year-old former secretary-general of the liberation movement, was dropped off at his house by a prison services' van just as the sun was coming up.
ከ26 ዓመት እስራት በኋላ የነፃነት ንቅናቄው የቀድሞው ዋና ፀሐፊ የ77 ዓመቱ አዛውንት ሚስተር ሲሱሉ ፀሐይ ስትወጣ በቫን ጀስት የእስር ቤቱ ሰርቪስ ከቤታቸው ደረሱ።
Generally, airlines say they welcome the use of a government-approved safety seat and will even allow the restraint to take up a regular seat for free if the flight isn't crowded.
በአጠቃላይ አየር መንገዶች በመንግሥት ተቀባይነትን ያገኙ የደኀንነት መቀመጫዎችን መጠቀም እንደሚቻልና አውሮኘላኑ በመንገደኞች እስካልሞላ ድረስም ቁጥጥሩ ተነስቶ መደበኛ መቀመጫዎችን በነፃ ቢጠቀሙ እንደሚፈቅዱላቸው ይናገራሉ።
Without claiming responsibility, Hamas and another hardline group, Islamic Jihad, said the blast was revenge for a string of bloody Israeli army raids into the Gaza Strip in recent weeks.
ሀላፊነቱን ባይወስዱም ሀማስ እና ኢስላሚክ ጂሀድ የተባለ የአክራሪ ቡድን ፍንዳታው እስራኤሎች በቅርብ ሳምንታት በጋዛ ሰርጥ ላይ በተከታታይ ያደረጉትን ወታደራዊ ጥቃት ለመበቀል የተደረገ ነው ብሏል።
But he admits that the agency is in "a very uncomfortable position."
ነገር ግን ድርጅቱ «በማይመች ቦታላይ መሆኑን» እኒህ ሰው አምነው ይቀበላሉ።
Farmers in loose turbans and fancy earrings spend their afternoons laughing and gossiping at the markets.
ገበሬዎች ጥምጥማቸውን ላላ አድርገው ወደር በሌለው ገቢያቸው የሰዓት በኋላ ጊዜያቸውን በገበያ ላይ በመሣሣቅና በመጫወት ያሳልፋሉ።
And Zion National Park in Utah has just established a new shuttle bus system.
ኡታህ ውስጥ ያለው ዚኦን ብሔራዊ ፖርክም ተመላላሽ የአዉቶቡስ ሥርዓት ዘርግቷል።
It might not be a bad idea to do that sooner, rather than later.
ይህን ጉዳይ ከማጓተቱ ይልቅ በፍጥነት ማድረጉ መጥፎ ላይሆን ይችላል።
I'm still doing my TV announcing and my weekend radio stuff, so that money will help.
እስካሁን ድረስ በቴሌቪዥን ማስተዋወቄንና ቅዳሜና ዕሁድ በሬድዮ ማስተማሬን እየሠራሁ ነኝ፤ ስለዚህ ያ ገንዘብ ይጠቅማል።
It was as easy as collecting sea shells at Malibu.
ማሊቡ ላይ ዛጐል የመሰብሰብ ያህል ቀላል ሥራ ነበር።
Israeli police were not immediately available for comment, but Palestinian sources in Hebron said Mahmoud Qawasmi was a 21-year-old student with links to the Islamic radical group Hamas.
የእስራኤል ፖሊሶች አስተያየት ለመስጠት በወቅቱ አልነበሩም ነገር ግን በሂብሮን የሚገኙ ምንጮች እንደገለፁት የ21 ዓመቱ መሀመድ ኩዋስሚ አክራሪ እስላማዊ ድርጅት ከሆነው ከሀማስ ጋር ግንኙነት እንደነበረው ገልፀዋል።
At least 54 soldiers and 50 guerillas have died in clashes around the northwestern cities of Bagado and Dabeiba.
በሰሜን ምዕራብ በሚገኙ የባጋዶና ዳቤባ ከተሞች አካባቢ በተፈጠረው ውጊያ ቢያንስ 54 ወታደሮችና 50 ደፈጣ ተዋጊዎች ሞተዋል።
For most of the book, there is no direct connection between its urban and its Amazonian modes.
በአብዛኛው በመጽሐፉ ውስጥ በከተማውና በአማዞኒያውያን ባህል መካከል ምንም ቀጥተኛ ግንኙነት የለም።
Participants included Kurds, Sunnis and Shiites from inside the country and others who spent years in exile.
ተሳታፊዎቹ ከአገር ውስጥ ሱኒዎችና ሺአይቶች ሲሆኑ በውጪ አገር ስደት የቆዩ ሌሎችንም የካትታል።
She held him down tightly, trying to protect him.
እንዳይጋጭ ለመጠበቅ በእጇ ተጭና ያዘችው።
Yosemite is not alone in seeking new management strategies to preserve natural areas.
የተፈጥሮ ቦታዎችን ለመጠበቅ የአስተዳደር እስትራቴጂዎችን የምትፈልገው ዩሴሚቲ ብቻ አይደለችም።
Thus, farmer Johan Fischer, his T-shirt and jeans covered in grease, crawls around under his planter, tightening bolts and fixing dents.
ስለሆነም ቲ-ሸርቱና ጂንሱ በግሪስ የተበከለው ገበሬው ጆሃን ፊሸር በገዛ መሬቱ ላይ እየተንከባለለ መኪናውን ይጠግናል፣ ቡሎኑን ያጠብቃል።
The U.S. discovered the young Tony Noriega in late 1959, when he was in his second year at the Chorrillos Military Academy in Lima, according to former U.S. intelligence officials.
ዩ.ኤስ ወጣቱን ቶኒ ኖሬጋን ያገኘችው ሊማ ውስጥ ኮሪሎስ ሚሊታሪ አካዳሚ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ በነበረበት ወቅት በ1959 መገባደጃ ላይ እንደሆነ የዱሮው የዩ.ኤስ ደኀንነት ባለሥልጣን ተናግረዋል።
So far two little known Islamic groups have claimed responsibility for the attack.
እስካሁን በትንሹ የታወቁ ሁለት እስላማዊ ቡድኖች ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን ወስደዋል።
Several hours later, dozens of Israeli tanks advanced into the northern Gaza Strip backed by helicopters which fired at least three rockets in the Jabaliya area, Palestinian security sources said.
ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በፒካታ የእስራኤል ታንኮች ወደ ሰሜናዊ የጋዛ ሰርጥ ክፍል በማቅናት በሚታገዙአቸው ሔሊኮኘተሮች ሳቢያ ቢያንስ ሶስት ሮኬቶችን ጀባሊያ በተባለው አካባቢ መተኮሳቸውን የፍልስጤም የደህንነት ምንጭ አስታውቆአል።
Periodically, there are threats that the program will fold.
በየወቅቱ ፕሮግራሙ ይታጠፋል የሚል ሥጋት አለ።
That is because Sidhpur has a near-monopoly on the world's supply of flea seed, also known as flea wort or, in Western parlance, psyllium: a tiny, tasteless, obscure seed that, according to early research, may reduce cholesterol levels in the blood.
ይህም የሆነበት ምክንያት ሲድህፑር ለዓለም ፍሊፍሬ ለማቅረብ በሞኖፖል የተያዘ ነው ማለት ይቻላል፤ ይህ ፍሊ ፍሬ ፍሊ ተክል በመባልም ይታወቃል፤ በምዕራባውያን አጠራርም ሳይሊየም ይባላል። ይህ ፍሬ በጣም ደቃቅና ጣዕም አልባ ነው፤ ቀደም ብሎ በተደረገው ምርምር መሠረት በደም ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል ደረጃ ይቀንሳል።