text stringlengths 4 267 |
|---|
ዮፍታሔም በእስራኤል ውስጥ ለስድስት ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ፤ ከዚያም ጊልያዳዊው ዮፍታሔ ሞተ፤ በጊልያድ በምትገኘው ከተማውም ተቀበረ። |
ከእሱም በኋላ የቤተልሔሙ ኢብጻን በእስራኤል ውስጥ ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። |
ኢብጻን 30 ወንዶችና 30 ሴቶች ልጆች ነበሩት። እሱም ሴቶች ልጆቹን ከጎሳው ውጭ የሆኑ ሰዎችን እንዲያገቡ ላካቸው፤ እንዲሁም ከወንዶች ልጆቹ ጋር እንዲጋቡ ከጎሳው ውጭ የሆኑ 30 ሴቶችን አስመጣ። በእስራኤልም ውስጥ ለሰባት ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። |
ከዚያም ኢብጻን ሞተ፤ በቤተልሔምም ተቀበረ። |
ከእሱም በኋላ ዛብሎናዊው ኤሎን በእስራኤል ውስጥ ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። እሱም በእስራኤል ውስጥ ለአሥር ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። |
ከዚያም ዛብሎናዊው ኤሎን ሞተ፤ በዛብሎን ምድር በአይሎንም ተቀበረ። |
ከእሱም በኋላ የጲራቶናዊው የሂሌል ልጅ አብዶን በእስራኤል ውስጥ ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። |
እሱም በ70 አህዮች የሚጋልቡ 40 ወንዶች ልጆችና 30 የልጅ ልጆች ነበሩት። በእስራኤልም ውስጥ ለስምንት ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። |
ከዚያም የጲራቶናዊው የሂሌል ልጅ አብዶን ሞተ፤ በአማሌቃውያን ተራራ በኤፍሬም ምድር በምትገኘው በጲራቶንም ተቀበረ። |
በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም። በዚያ ጊዜ የዳናውያን ነገድ የሚሰፍርበት ርስት እየፈለገ ነበር፤ ምክንያቱም ዳናውያን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልተሰጣቸውም ነበር። |
ዳናውያን ከቤተሰባቸው መካከል ብቃት ያላቸውን አምስት ወንዶች መርጠው ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲቃኙ ከጾራና ከኤሽታዖል ላኳቸው። እነሱንም “ሂዱ፣ ምድሪቱን ቃኙ” አሏቸው። እነሱም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ሚክያስ ቤት ሲደርሱ እዚያ አደሩ። |
ወደ ሚክያስ ቤት በቀረቡም ጊዜ የወጣቱን ሌዋዊ ድምፅ ለዩት፤ በመሆኑም ወደ እሱ ገብተው “ለመሆኑ እዚህ ማን አመጣህ? ደግሞስ እዚህ ምን ትሠራለህ? እዚህ እንድትቆይ ያደረገህስ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። |
እሱም መልሶ “ሚክያስ ይህን ይህን አደረገልኝ፤ ካህን ሆኜ እንዳገለግለውም ቀጠረኝ” አላቸው። |
ከዚያም እነሱ “መንገዳችን የተቃና መሆን አለመሆኑን እባክህ አምላክን ጠይቅልን” አሉት። |
ካህኑም “በሰላም ሂዱ። በመንገዳችሁ ሁሉ ይሖዋ ከእናንተ ጋር ነው” አላቸው። |
ስለሆነም አምስቱ ሰዎች ጉዟቸውን በመቀጠል ወደ ላይሽ መጡ። የከተማዋም ሰዎች ልክ እንደ ሲዶናውያን ራሳቸውን ችለው እንደሚኖሩ ተመለከቱ። እነዚህ ሰዎች ያለምንም ስጋት ተረጋግተው የተቀመጡ ከመሆናቸውም ሌላ በምድሪቱ ላይ እነሱን የሚያውክ ጨቋኝ ቅኝ ገዢ አልነበረም። በተጨማሪም የሚኖሩት ከሲዶናውያን ርቀው ነበር፤ ከማንም ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አልነበራቸውም። |
እነሱም በጾራና በኤሽታዖል ወደሚገኙት ወንድሞቻቸው በተመለሱ ጊዜ ወንድሞቻቸው “የሄዳችሁበት ጉዳይ እንዴት ሆነ?” በማለት ጠየቋቸው። |
እነሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ምድሪቱ በጣም ጥሩ ምድር መሆኗን ስላየን ተነሱ፣ እንዝመትባቸው። ለምን ታመነታላችሁ? ገብታችሁ ምድሪቱን ለመውረስ አትዘግዩ። |
እዚያ ስትደርሱ ያለምንም ስጋት የተቀመጠ ሕዝብ ታገኛላችሁ፤ ምድሪቱም በጣም ሰፊ ነች። አምላክም በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ነገር የማይታጣበትን ስፍራ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷችኋል።” |
ከዚያም ከዳናውያን ቤተሰብ የሆኑና ለጦርነት የታጠቁ 600 ሰዎች ከጾርና ከኤሽታዖል ተንቀሳቀሱ። |
እነሱም ወጥተው በይሁዳ በምትገኘው በቂርያትየአሪም ሰፈሩ። ከቂርያትየአሪም በስተ ምዕራብ የሚገኘው ያ ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ ማሃነህዳን ተብሎ የሚጠራው በዚህ የተነሳ ነው። |
ከዚያም ተነስተው ወደ ኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ተጓዙ፤ ወደ ሚክያስም ቤት መጡ። |
በኋላም ላይሽን ለመሰለል ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ወንድሞቻቸውን “እነዚህ ቤቶች ውስጥ ኤፉድ፣ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾች፣ የተቀረጸ ምስልና ከብረት የተሠራ ሐውልት እንዳለ ታውቃላችሁ? እንግዲህ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ አስቡ” አሏቸው። |
እነሱም በሚክያስ ቤት ወደሚገኘው ወደ ወጣቱ ሌዋዊ ቤት ጎራ ብለው ስለ ደህንነቱ ጠየቁት። |
በዚህ ጊዜ ሁሉ ለጦርነት የታጠቁት 600ዎቹ የዳን ሰዎች መግቢያው በር ላይ ቆመው ነበር። |
ምድሪቱን ለመሰለል ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎችም የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹንና ከብረት የተሠራውን ምስል ለመውሰድ ወደ ውስጥ ገቡ። (ካህኑም ለጦርነት ከታጠቁት 600 ሰዎች ጋር መግቢያው በር ላይ ቆሞ ነበር።) |
እነሱም ወደ ሚክያስ ቤት ገብተው የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹንና ከብረት የተሠራውን ምስል ወሰዱ። ካህኑም “ምን እያደረጋችሁ ነው?” አላቸው። |
እነሱ ግን እንዲህ አሉት፦ “ዝም በል። ምንም ቃል አትናገር፤ ይልቅስ ከእኛ ጋር ሄደህ አባትና ካህን ሁነን። ለአንድ ሰው ቤት ካህን ብትሆን ይሻልሃል ወይስ በእስራኤል ለሚገኝ አንድ ነገድና ቤተሰብ ካህን ብትሆን?” |
በዚህ ጊዜ የካህኑ ልብ ደስ ተሰኘ፤ እሱም ኤፉዱን፣ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹንና የተቀረጸውን ምስል ይዞ ከሕዝቡ ጋር ሄደ። |
ከዚያም ልጆቹን፣ ከብቶቹንና ውድ የሆኑትን ነገሮች ከፊት አስቀድመው ጉዟቸውን ለመቀጠል ተነሱ። |
ከሚክያስ ቤት የተወሰነ መንገድ ርቀው ከሄዱም በኋላ በሚክያስ ቤት አቅራቢያ በሚገኙ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች አንድ ላይ ተሰበሰቡ፤ ዳናውያንንም ተከታትለው ደረሱባቸው። |
ከዚያም ጮኸው ሲጠሯቸው ዳናውያኑ ዞር በማለት ሚክያስን “ምን ሆነሃል? ተሰባስባችሁ የመጣችሁትስ ለምንድን ነው?” አሉት። |
እሱም “የሠራኋቸውን አማልክቴን ወሰዳችሁ፤ ካህኑንም ይዛችሁ ሄዳችሁ። እንግዲህ ምን ቀረኝ? ታዲያ እንዴት ‘ምን ሆነሃል?’ ትሉኛላችሁ?” አላቸው። |
በዚህ ጊዜ ዳናውያኑ “አትጩኽብን፤ አለዚያ የተቆጡ ሰዎች ጉዳት ያደርሱባችኋል፤ ይህም የገዛ ሕይወትህንና የቤተሰብህን ሕይወት ሊያሳጣህ ይችላል” አሉት። |
ዳናውያኑም ጉዟቸውን ቀጠሉ፤ ሚክያስም እነሱ ከእሱ ይልቅ ብርቱዎች እንደሆኑ ስለተረዳ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ። |
እነሱም ሚክያስ የሠራቸውን ነገሮችና የእሱን ካህን ከወሰዱ በኋላ ወደ ላይሽ ይኸውም ያለምንም ስጋት ተረጋግተው ይኖሩ ወደነበሩት ሰዎች ሄዱ። እነሱንም በሰይፍ መቷቸው፤ ከተማዋንም በእሳት አቃጠሉ። |
ከተማዋ የምትገኘው ከሲዶና ርቃ ስለነበርና ነዋሪዎቿም ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ስላልነበራቸው ማንም የሚያድናት አልነበረም፤ ላይሽ የምትገኘው በቤትሬሆብ ባለው ሸለቋማ ሜዳ ላይ ነበር። እነሱም ከተማዋን ዳግመኛ ገንብተው በዚያ መኖር ጀመሩ። |
በተጨማሪም ከተማዋን ለእስራኤል በተወለደለት በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት። የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ላይሽ ነበር። |
ከዚያም ዳናውያን የተቀረጸውን ምስል ለራሳቸው አቆሙት፤ የሙሴ ልጅ የሆነው የጌርሳም ልጅ ዮናታንና ወንዶች ልጆቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች በግዞት እስከተወሰዱበት ጊዜ ድረስ የዳናውያን ነገድ ካህናት ሆኑ። |
ሚክያስ የሠራውንም የተቀረጸ ምስል አቆሙት፤ ምስሉም የእውነተኛው አምላክ ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ በዚያ ነበር። |
እስራኤላውያን ግን እንደገና በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤ በመሆኑም ይሖዋ ለሰባት ዓመት ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው። |
የምድያማውያን እጅ በእስራኤል ላይ በረታ። እስራኤላውያን በምድያማውያን የተነሳ በተራሮች ላይ፣ በዋሻዎች ውስጥና በቀላሉ በማይደረስባቸው ስፍራዎች ለመደበቂያ የሚሆኑ ቦታዎችን ለራሳቸው አዘጋጁ። |
እነሱም ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ሁሉ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች ጥቃት ይሰነዝሩባቸው ነበር። |
እንዲሁም በዙሪያቸው በመስፈር እስከ ጋዛ ድረስ ያለውን የምድሩን ሰብል ያጠፉ ነበር፤ ለእስራኤላውያን የሚበሉት ምንም ነገር አያስተርፉላቸውም፤ በግም ሆነ ከብት ወይም አህያ አያስቀሩላቸውም ነበር። |
ምክንያቱም ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው እንደ አንበጣ መንጋ ብዙ ሆነው ይመጡ ነበር፤ እነሱም ሆኑ ግመሎቻቸው ለቁጥር የሚያታክቱ ነበሩ፤ ወደዚያም የሚመጡት ምድሪቱን ለማጥፋት ነበር። |
በመሆኑም እስራኤላውያን በምድያማውያን የተነሳ ለከፍተኛ ድህነት ተዳረጉ፤ እነሱም ይሖዋ እንዲረዳቸው መጮኽ ጀመሩ። |
እስራኤላውያን በምድያማውያን የተነሳ ለእርዳታ ወደ ይሖዋ በጮኹ ጊዜ |
ይሖዋ ነቢይ ላከላቸው፤ እሱም እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከግብፅ አወጣኋችሁ፤ በዚህ መንገድ ከባርነት ቤት አላቀኳችሁ። |
ከግብፅ እጅና ከሚጨቁኗችሁ ሁሉ ታደግኳችሁ፤ እነሱንም ከፊታችሁ በማባረር ምድራቸውን ሰጠኋችሁ። |
እንዲሁም “እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። በምድራቸው ላይ የምትኖሩባቸው አሞራውያን የሚያመልኳቸውን አማልክት አትፍሩ” አልኳችሁ። እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም።’” |
በኋላም የይሖዋ መልአክ መጥቶ በኦፍራ በሚገኘው በአቢዔዜራዊው በዮአስ ትልቅ ዛፍ ሥር ተቀመጠ። የዮአስም ልጅ ጌድዮን ከምድያማውያን ተደብቆ በወይን መጭመቂያው ስፍራ ስንዴ እየወቃ ነበር። |
ከዚያም የይሖዋ መልአክ ተገለጠለትና “አንተ ኃያል ተዋጊ፣ ይሖዋ ከአንተ ጋር ነው” አለው። |
ጌድዮንም እንዲህ አለው፦ “ይቅርታ ጌታዬ፤ ታዲያ ይሖዋ ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ሁሉ የሚደርስብን ለምንድን ነው? አባቶቻችን ‘ይሖዋ ከግብፅ ምድር አላወጣንም?’ እያሉ ይነግሩን የነበረው ድንቅ ሥራው ሁሉ የት አለ? አሁን ይሖዋ ትቶናል፤ ለምድያማውያንም እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል።” |
ይሖዋም ፊት ለፊቱ ቆመና እንዲህ አለው፦ “በል ባለህ ኃይል ሂድ፤ እስራኤልንም ከምድያማውያን እጅ ታድናለህ። የምልክህ እኔ አይደለሁም?” |
ጌድዮንም መልሶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ይቅርታ አድርግልኝ፤ እኔ እንዴት እስራኤልን ላድን እችላለሁ? የእኔ ጎሳ እንደሆነ ከምናሴ ነገድ የመጨረሻው ነው፤ እኔም ብሆን በአባቴ ቤት ውስጥ እዚህ ግባ የምባል አይደለሁም።” |
ሆኖም ይሖዋ “እኔ ከአንተ ጋር ስለምሆን ምድያማውያንን ልክ እንደ አንድ ሰው ትመታቸዋለህ” አለው። |
ከዚያም ጌድዮን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ ከእኔ ጋር እየተነጋገርክ ያለኸው አንተ ስለመሆንህ አንድ ምልክት አሳየኝ። |
ደግሞም ተመልሼ መጥቼ ስጦታዬን በፊትህ እስካቀርብ ድረስ እባክህ ከዚህ አትሂድ” አለው። እሱም “እስክትመለስ ድረስ እዚሁ እጠብቅሃለሁ” አለው። |
ጌድዮንም ገብቶ አንድ የፍየል ጠቦትና ከአንድ ኢፍ ዱቄት ቂጣ አዘጋጀ። ሥጋውን በቅርጫት፣ መረቁን ደግሞ በድስት አድርጎ ወደ እሱ ይዞ በመምጣት በትልቁ ዛፍ ሥር አቀረበለት። |
የእውነተኛው አምላክ መልአክም “ሥጋውንና ቂጣውን ወስደህ እዚያ ባለው ዓለት ላይ አስቀምጣቸው፤ መረቁንም አፍስሰው” አለው። እሱም እንዲሁ አደረገ። |
ከዚያም የይሖዋ መልአክ በእጁ ይዞት የነበረውን በትር ዘርግቶ በጫፉ ሥጋውንና ቂጣውን ነካ፤ በዚህ ጊዜ እሳት ከዓለቱ ወጥቶ ሥጋውንና ቂጣውን በላ። ከዚያም የይሖዋ መልአክ ከእይታው ተሰወረ። |
በዚህ ጊዜ ጌድዮን የይሖዋ መልአክ እንደነበር አስተዋለ። ወዲያውኑም “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ የይሖዋን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና ወዮልኝ!” አለ። |
ሆኖም ይሖዋ “ሰላም ለአንተ ይሁን። አትፍራ፤ አትሞትም” አለው። |
ጌድዮንም በዚያ ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ፤ መሠዊያውም እስከ ዛሬ ድረስ ‘ይሖዋ ሻሎም’ ተብሎ ይጠራል። አሁንም ድረስ የአቢዔዜራውያን በሆነችው በኦፍራ ይገኛል። |
በዚያ ምሽት ይሖዋ ጌድዮንን እንዲህ አለው፦ “የአባትህ ንብረት የሆነውን ሰባት ዓመት የሞላውን ሁለተኛውን ወይፈን ውሰድ፤ የአባትህ የሆነውን የባአልን መሠዊያም አፈራርስ፤ አጠገቡም የሚገኘውን የማምለኪያ ግንድ ሰባብር። |
በዚህ ምሽግ አናት ላይ ድንጋይ ደርድረህ ለአምላክህ ለይሖዋ መሠዊያ ከሠራህ በኋላ ሁለተኛውን ወይፈን ወስደህ በምትሰባብረው የማምለኪያ ግንድ እንጨት ላይ የሚቃጠል መባ አድርገህ አቅርበው።” |
ስለዚህ ጌድዮን ከአገልጋዮቹ መካከል አሥር ሰዎችን ወስዶ ልክ ይሖዋ እንዳለው አደረገ። ይሁንና የአባቱን ቤትና የከተማዋን ሰዎች በጣም ስለፈራ ይህን ያደረገው በቀን ሳይሆን በሌሊት ነበር። |
የከተማዋ ሰዎች በማግስቱ በማለዳ ሲነሱ የባአል መሠዊያ ፈራርሶ፣ አጠገቡ የነበረው የማምለኪያ ግንድም ተሰባብሮ እንዲሁም ሁለተኛው ወይፈን በተሠራው መሠዊያ ላይ ተሠውቶ ተመለከቱ። |
እነሱም እርስ በርሳቸው “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ተባባሉ። ሁኔታውንም ካጣሩ በኋላ “ይህን ያደረገው የዮአስ ልጅ ጌድዮን ነው” አሉ። |
በመሆኑም የከተማዋ ሰዎች ዮአስን “ልጅህ የባአልን መሠዊያ ስላፈራረሰና አጠገቡ የነበረውን የማምለኪያ ግንድ ስለሰባበረ ወደዚህ አውጣው፤ መሞት አለበት” አሉት። |
ከዚያም ዮአስ እሱን የሚቃወሙትን ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “ለባአል መሟገት ይኖርባችኋል? እሱን ለማዳን መሞከርስ ይገባችኋል? ለእሱ የሚሟገት ማንኛውም ሰው በዚህ ጠዋት መሞት ይገባዋል። እሱ አምላክ ከሆነ አንድ ሰው መሠዊያውን ስላፈረሰበት ለራሱ ይሟገት።” |
እሱም “ባአል አንድ ሰው መሠዊያውን ስላፈረሰበት ለራሱ ይሟገት” በማለት ጌድዮንን በዚያ ቀን የሩባአል ብሎ ጠራው። |
ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች በሙሉ ግንባር ፈጥረው ወደ ኢይዝራኤል ሸለቆ በመሻገር በዚያ ሰፈሩ። |
የይሖዋም መንፈስ በጌድዮን ላይ ወረደ፤ እሱም ቀንደ መለከት ነፋ፤ አቢዔዜራውያንም እሱን በመደገፍ ተከትለውት ወጡ። |
ከዚያም በመላው ምናሴ መልእክተኞችን ላከ፤ እነሱም እሱን በመደገፍ ተከትለውት ወጡ። በተጨማሪም ወደ አሴር፣ ወደ ዛብሎንና ወደ ንፍታሌም መልእክተኞችን ላከ፤ እነሱም ከእሱ ጋር ለመገናኘት ወጡ። |
ከዚያም ጌድዮን እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለው፦ “ቃል በገባኸው መሠረት በእኔ አማካኝነት እስራኤልን የምታድን ከሆነ |
ይኸው አውድማው ላይ የተባዘተ የበግ ፀጉር አስቀምጣለሁ። በዙሪያው ያለው ምድር በሙሉ ደረቅ ሆኖ የበግ ፀጉሩ ላይ ብቻ ጤዛ ከተገኘ ቃል በገባኸው መሠረት በእኔ አማካኝነት እስራኤልን እንደምታድን አውቃለሁ።” |
ልክ እንደዚሁም ሆነ። በማግስቱ በማለዳ ተነስቶ የበግ ፀጉሩን ሲጨምቀው ከበግ ፀጉሩ ላይ የወጣው ውኃ በትልቅ ጎድጓዳ ሳህን ሙሉ ሆነ። |
ሆኖም ጌድዮን እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለው፦ “እባክህ ቁጣህ በእኔ ላይ አይንደድ፤ አንድ ጊዜ ብቻ እንድናገር ፍቀድልኝ። ከበግ ፀጉሩ ጋር በተያያዘ አንድ ሌላ ሙከራ ብቻ ላድርግ። እባክህ የበግ ፀጉሩ ብቻ ደረቅ ሆኖ ምድሩ በሙሉ ጤዛ እንዲሆን አድርግ።” |
በመሆኑም አምላክ በዚያ ሌሊት እንደዚሁ አደረገ፤ የበግ ፀጉሩ ብቻ ደረቅ ሆኖ ምድሩ በሙሉ ጤዛ ሆነ። |
ከዚያም የኤፍሬም ሰዎች ጌድዮንን “እንዴት እንዲህ ያለ ነገር ታደርግብናለህ? ከምድያማውያን ጋር ለመዋጋት ስትወጣ ያልጠራኸን ለምንድን ነው?” አሉት። የመረረ ጥልም ተጣሉት። |
እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ካደረጋችሁት ጋር ሲነጻጸር እኔ ምን አደረግኩ? የኤፍሬም ቃርሚያ ከአቢዔዜር የወይን መከር አይሻልም? |
አምላክ የምድያማውያንን መኳንንት ኦሬብን እና ዜብን አሳልፎ የሰጠው ለእናንተ ነው፤ ታዲያ እናንተ ካደረጋችሁት ጋር ሲነጻጸር እኔ ምን አደረግኩ?” እነሱም በዚህ መንገድ ሲያነጋግራቸው ቁጣቸው በረደ። |
ከዚያም ጌድዮን ወደ ዮርዳኖስ መጥቶ ወንዙን ተሻገረ። እሱም ሆነ ከእሱ ጋር የነበሩት 300 ሰዎች ደክሟቸው የነበረ ቢሆንም ጠላቶቻቸውን ከማሳደድ ወደኋላ አላሉም ነበር። |
ስለዚህ ጌድዮን የሱኮትን ሰዎች “የምድያማውያን ነገሥታት የሆኑትን ዘባህን እና ጻልሙናን በማሳደድ ላይ ስለሆንኩና የሚከተሉኝም ሰዎች ስለደከማቸው እባካችሁ ዳቦ ስጧቸው” አላቸው። |
የሱኮት መኳንንት ግን “ለሠራዊትህ ዳቦ የምንሰጠው ለመሆኑ የዘባህ እና የጻልሙና መዳፍ እጅህ ገብቷል?” አሉት። |
በዚህ ጊዜ ጌድዮን “እንግዲያው ይሖዋ ዘባህን እና ጻልሙናን በእጄ አሳልፎ ሲሰጠኝ በምድረ በዳ እሾህና አሜኬላ ሥጋችሁን እተለትላለሁ” አላቸው። |
ከዚያም ወደ ጰኑኤል ወጣ፤ ለእነሱም ተመሳሳይ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ የጰኑኤል ሰዎችም የሱኮት ሰዎች የሰጡትን ዓይነት መልስ ሰጡት። |
ስለዚህ የጰኑኤልንም ሰዎች “በሰላም በምመለስበት ጊዜ ይህን ግንብ አፈርሰዋለሁ” አላቸው። |
በዚህ ጊዜ ዘባህ እና ጻልሙና ከሠራዊታቸው ጋር በቃርቆር ሰፍረው ነበር፤ የሠራዊቱም ቁጥር ወደ 15,000 ገደማ ነበር። ቀደም ሲል 120,000 የሚያህሉ ሰይፍ የታጠቁ ወንዶች ተገድለው ስለነበር ከመላው የምሥራቅ ሰዎች ሠራዊት የቀሩት እነዚህ ብቻ ነበሩ። |
ጌድዮንም ከኖባህ እና ከዮግበሃ በስተ ምሥራቅ የሚኖሩ ዘላኖች የሚሄዱበትን መንገድ ተከትሎ ወጣ፤ የጠላት ሠራዊት ተዘናግቶ ባለበትም ወቅት በሰፈሩ ላይ ጥቃት ሰነዘረ። |
ሁለቱ ምድያማውያን ነገሥታት ማለትም ዘባህ እና ጻልሙና በሸሹም ጊዜ አሳዶ ያዛቸው፤ መላውን ሠራዊትም አሸበረው። |
ከዚያም የዮአስ ልጅ ጌድዮን ወደ ሄሬስ ሽቅብ በሚያስወጣው መንገድ በኩል አድርጎ ከውጊያው ተመለሰ። |
እሱም በመንገድ ላይ የሱኮት ሰው የሆነ አንድ ወጣት ያዘ፤ እሱንም መረመረው። በመሆኑም ወጣቱ የሱኮት መኳንንትና ሽማግሌዎች የሆኑ የ77 ሰዎችን ስም ጻፈለት። |
ጌድዮንም ወደ ሱኮት ሰዎች ሄዶ “‘ለደከሙት ሰዎችህ ዳቦ የምንሰጠው ለመሆኑ የዘባህ እና የጻልሙና መዳፍ እጅህ ገብቷል?’ በማለት የተሳለቃችሁብኝ ዘባህ እና ጻልሙና እነዚሁላችሁ” አላቸው። |
ከዚያም የከተማዋን ሽማግሌዎች ወሰደ፤ በምድረ በዳ እሾህና አሜኬላም ለሱኮት ሰዎች ትምህርት ሰጣቸው። |
እንዲሁም የጰኑኤልን ግንብ አፈረሰ፤ የከተማዋንም ሰዎች ገደለ። |
ጌድዮንም ዘባህን እና ጻልሙናን “ለመሆኑ በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች ምን ዓይነት ነበሩ?” አላቸው። እነሱም መልሰው “እንደ አንተ ዓይነት ነበሩ፤ እያንዳንዳቸውም የንጉሥ ልጅ ይመስሉ ነበር” አሉት። |
በዚህ ጊዜ “እነሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ነበሩ። ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ በሕይወት ትታችኋቸው ቢሆን ኖሮ አልገድላችሁም ነበር” አላቸው። |
ከዚያም የበኩር ልጁን የቴርን “ተነስ፤ ግደላቸው” አለው። ወጣቱ ግን ሰይፉን አልመዘዘም፤ ምክንያቱም ገና ወጣት ስለሆነ ፈርቶ ነበር። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.