text stringlengths 4 267 |
|---|
ይሖዋን እንድትጠይቁ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ ግን እንዲህ በሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማኸውን ቃል በተመለከተ፣ |
ስለዚህ ቦታና ስለ ነዋሪዎቹ የተናገረውን ቃል ስትሰማ ልብህ ስለተነካና በአምላክ ፊት ራስህን ስላዋረድክ እንዲሁም ራስህን በፊቴ ዝቅ ስላደረግክ፣ ልብስህን ስለቀደድክና በፊቴ ስላለቀስክ እኔም ሰምቼሃለሁ ይላል ይሖዋ። |
ወደ አባቶችህ የምሰበስብህ በዚህ የተነሳ ነው፤ አንተም በሰላም በመቃብርህ ታርፋለህ፤ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ የማመጣውን መከራ ሁሉ ዓይኖችህ አያዩም።’”’” ከዚያም ሰዎቹ መልሱን ለንጉሡ አመጡለት። |
ንጉሡም መልእክት ልኮ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠራ። |
ከዚያ በኋላ ንጉሡ ከይሁዳ ሰዎች፣ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፣ ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑ እንዲሁም ትልቅ ትንሽ ሳይባል ከሕዝቡ ሁሉ ጋር ወደ ይሖዋ ቤት ወጣ። እሱም በይሖዋ ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ የተሰበሰቡት ሰዎች እየሰሙ አነበበላቸው። |
ንጉሡ ባለበት ስፍራ ቆሞ፣ በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈሩትን የቃል ኪዳኑን ቃላት በመፈጸም በሙሉ ልቡና በሙሉ ነፍሱ ይሖዋን ለመከተል እንዲሁም ትእዛዛቱን፣ ማሳሰቢያዎቹንና ሥርዓቶቹን ለመጠበቅ በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ገባ። |
በተጨማሪም በኢየሩሳሌምና በቢንያም ያሉት ሁሉ በቃል ኪዳኑ እንዲስማሙ አደረገ። የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች በአምላክ ይኸውም በአባቶቻቸው አምላክ ቃል ኪዳን መሠረት እርምጃ ወሰዱ። |
ከዚያም ኢዮስያስ ከመላው የእስራኤላውያን ምድር አስጸያፊዎቹን ነገሮች በሙሉ አስወገደ፤ እንዲሁም በእስራኤል ያሉ ሁሉ አምላካቸውን ይሖዋን እንዲያገለግሉ አደረገ። በሕይወት ዘመኑ ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ከመከተል ፈቀቅ አላሉም። |
በዚህ ጊዜ ሰለሞን እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደሚኖር ተናግሯል። |
አሁን እኔ እጅግ ከፍ ያለ ቤት፣ ለዘላለም የምትኖርበት ጸንቶ የተመሠረተ ቦታ ገንብቼልሃለሁ።” |
ከዚያም መላው የእስራኤል ጉባኤ ቆሞ ሳለ ንጉሡ ዞሮ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ መባረክ ጀመረ። |
እንዲህም አለ፦ “ለአባቴ ለዳዊት በገዛ አፉ እንዲህ ብሎ ቃል የገባውና ይህን በራሱ እጆች የፈጸመው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ፦ |
‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ዕለት አንስቶ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ስሜ የሚጠራበት ቤት እንዲሠራበት አንድም ከተማ አልመረጥኩም፤ ደግሞም የሕዝቤ የእስራኤል መሪ እንዲሆን ማንንም አልመረጥኩም። |
ሆኖም ስሜ እንዲጠራባት ኢየሩሳሌምን፣ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ገዢ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ።’ |
አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ለመሥራት ከልቡ ተመኝቶ ነበር። |
ሆኖም ይሖዋ አባቴን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ ‘ለስሜ ቤት ለመሥራት ከልብህ ተመኝተህ ነበር፤ ይህን በልብህ መመኘትህም መልካም ነው። |
ይሁንና ቤቱን የምትሠራው አንተ አይደለህም፤ ሆኖም ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ የሚወለድልህ የገዛ ልጅህ ይሆናል።’ |
ይሖዋ የገባውን ቃል ፈጽሟል፤ ልክ ይሖዋ ቃል በገባው መሠረት አባቴን ዳዊትን ተክቼ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀምጫለሁና። በተጨማሪም ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ሠርቻለሁ፤ |
በዚያም ይሖዋ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ያለበትን ታቦት አስቀምጫለሁ።” |
ከዚያም ሰለሞን በይሖዋ መሠዊያ ፊት፣ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ለፊት ቆመ፤ እጆቹንም ዘረጋ። |
(ሰለሞን የመዳብ መድረክ ሠርቶ በግቢው መካከል አስቀምጦ ነበር። የመድረኩ ርዝመት አምስት ክንድ፣ ወርዱ አምስት ክንድ፣ ከፍታውም ሦስት ክንድ ነበር፤ እሱም በመድረኩ ላይ ቆሞ ነበር።) በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ተንበርክኮም እጆቹን ወደ ሰማያት ዘረጋ፤ |
እንዲህም አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ በፊቱ በሙሉ ልባቸው ለሚመላለሱ አገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ አምላክ በሰማያትም ሆነ በምድር የለም። |
ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቀሃል። በገዛ አፍህ ቃል ገባህ፤ ዛሬ ደግሞ በራስህ እጅ ፈጸምከው። |
አሁንም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ ‘አንተ በፊቴ እንደተመላለስከው ሁሉ ልጆችህም በጥንቃቄ ሕጌን ጠብቀው ከተመላለሱ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከፊቴ አይታጣም’ በማለት ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቅ። |
አሁንም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ለአገልጋይህ ለዳዊት የገባኸው ቃል ይፈጸም። |
“በእርግጥ አምላክ ከሰው ልጆች ጋር በምድር ላይ ይኖራል? እነሆ ሰማያት፣ አዎ ሰማየ ሰማያት እንኳ ሊይዙህ አይችሉም፤ ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤትማ ምንኛ ያንስ! |
እንግዲህ አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ የአገልጋይህን ጸሎትና ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርበውን ልመና በትኩረት ስማ፤ አገልጋይህ እርዳታ ለማግኘት የሚያሰማውን ጩኸትና በፊትህ የሚያቀርበውን ጸሎት አዳምጥ። |
አገልጋይህ ወደዚህ ስፍራ የሚያቀርበውን ጸሎት ለመስማት ስምህ እንደሚጠራበት ወደተናገርከው ወደዚህ ቤት ዓይኖችህ ሌሊትና ቀን ይመልከቱ። |
አገልጋይህ እርዳታ ለማግኘት የሚያቀርበውን ልመናና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ በሚጸልይበት ጊዜ የሚያቀርበውን ልመና አዳምጥ፤ በማደሪያህም በሰማያት ሆነህ ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል። |
“አንድ ሰው ባልንጀራውን በድሎ እንዲምል ቢደረግ፣ በመሐላውም ተጠያቂ ቢሆን፣ በዳዩም በዚህ መሐላ ሥር ሆኖ እዚህ ቤት ውስጥ ባለው መሠዊያህ ፊት ቢቀርብ፣ |
አንተ በሰማያት ሆነህ ስማ፤ ለክፉው እንደ ሥራው በመመለስና የእጁን እንዲያገኝ በማድረግ፣ ጻድቁንም ንጹሕ መሆኑን በማሳወቅና እንደ ጽድቁ ወሮታውን በመክፈል እርምጃ ውሰድ፤ አገልጋዮችህንም ዳኝ። |
“ሕዝብህ እስራኤላውያን አንተን ከመበደላቸው የተነሳ በጠላት ድል ቢነሱና ተመልሰው ስምህን ቢያወድሱ እንዲሁም በዚህ ቤት በፊትህ ቢጸልዩና ሞገስ ለማግኘት ልመና ቢያቀርቡ |
ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የሕዝብህንም የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ለእነሱና ለአባቶቻቸው ወደሰጠኸው ምድርም መልሳቸው። |
“ሕዝቡ አንተን በመበደሉ የተነሳ ሰማያት ተዘግተው ዝናብ ቢጠፋ፣ እነሱም አንተ ስላዋረድካቸው ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩና ስምህን ቢያወድሱ እንዲሁም ከኃጢአታቸው ቢመለሱ |
ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የአገልጋዮችህን፣ የሕዝብህን የእስራኤላውያንን ኃጢአት ይቅር በል፤ ስለሚሄዱበት ቀና መንገድ ታስተምራቸዋለህና፤ ለሕዝብህ ርስት አድርገህ ባወረስከው ምድርህም ላይ ዝናብ አዝንብ። |
“በምድሪቱ ላይ ረሃብ ወይም ቸነፈር፣ የሚለበልብና የሚያደርቅ ነፋስ ወይም ዋግ ቢከሰት፣ የአንበጣ መንጋ ወይም የማይጠግብ አንበጣ ቢመጣ አሊያም ጠላቶቻቸው በምድሪቱ ላይ ባለ በየትኛውም ከተማ ውስጥ ሳሉ ቢከቧቸው ወይም ደግሞ ማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት አሊያም ማንኛውም ዓይነት በሽታ ቢከሰትና |
ማንኛውም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል በሙሉ (እያንዳንዱ የገዛ ጭንቀቱንና ሥቃዩን ያውቃልና) ወደ አንተ ለመጸለይ ወይም ሞገስ እንድታሳየው ልመና ለማቅረብ እጁን ወደዚህ ቤት ቢዘረጋ |
አንተ ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ ደግሞም ይቅር በል፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው ብድራቱን ክፈለው፤ ምክንያቱም አንተ ልቡን ታውቃለህ (የሰውን ልብ በሚገባ የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ)፤ |
ይህም ለአባቶቻችን በሰጠኸው ምድር ላይ በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ በመንገዶችህ በመመላለስ አንተን እንዲፈሩ ነው። |
“በተጨማሪም ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ የባዕድ አገር ሰው ከታላቁ ስምህ፣ ከኃያሉ እጅህና ከተዘረጋው ክንድህ የተነሳ ከሩቅ አገር ቢመጣ፣ ወደዚህም ቤት መጥቶ ቢጸልይ፣ |
ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና እንዲፈሩህ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ ያ የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት። |
“ሕዝብህ ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ በምትልካቸው መንገድ ለጦርነት ቢወጡና አንተ ወደመረጥከው ወደዚህ ከተማ እንዲሁም ለስምህ ወደሠራሁት ቤት አቅጣጫ ቢጸልዩ |
ከሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውንና ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርቡትን ልመና ስማ፤ ፍረድላቸውም። |
“በአንተ ላይ ኃጢአት ቢሠሩ (መቼም ኃጢአት የማይሠራ ሰው የለም)፣ አንተም በእነሱ እጅግ ተቆጥተህ ለጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው፣ ጠላቶቻቸውም ራቅ ወዳለ ወይም ቅርብ ወደሆነ ምድር ምርኮኛ አድርገው ቢወስዷቸው፣ |
እነሱም በምርኮ በተወሰዱበት ምድር ወደ ልቦናቸው ቢመለሱና ወደ አንተ ዞር በማለት ‘ኃጢአት ሠርተናል፤ አጥፍተናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል’ በማለት በተማረኩበት ምድር ሆነው ሞገስ ለማግኘት ወደ አንተ ልመና ቢያቀርቡ፣ |
ደግሞም ተማርከው በተወሰዱበት፣ ምርኮኛ ሆነው በሚኖሩበት ምድር፣ በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው ወደ አንተ ቢመለሱ እንዲሁም ለአባቶቻቸው በሰጠሃቸው ምድር፣ አንተ በመረጥካት ከተማና ለስምህ በሠራሁት ቤት አቅጣጫ ቢጸልዩ፣ |
ጸሎታቸውንና ሞገስ ለማግኘት ያቀረቡትን ልመና ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ ፍረድላቸውም፤ በአንተ ላይ ኃጢአት የሠራውን ሕዝብህን ይቅር በል። |
“አሁንም አምላኬ ሆይ፣ እባክህ በዚህ ቦታ ወደቀረበው ጸሎት ዓይኖችህ ይመልከቱ፤ ጆሮዎችህም በትኩረት ያዳምጡ። |
አሁንም ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ከብርታትህ ታቦት ጋር ወደ ማረፊያ ቦታህ ውጣ። ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ካህናትህ መዳንን ይልበሱ፤ ታማኞችህም በጥሩነትህ ሐሴት ያድርጉ። |
ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ የቀባኸውን ሰው ገሸሽ አታድርግ። ለአገልጋይህ ለዳዊት ያሳየኸውን ታማኝ ፍቅር አስብ።” |
ሕዝቅያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ29 ዓመት ገዛ። እናቱ አቢያህ ትባል ነበር፤ እሷም የዘካርያስ ልጅ ነበረች። |
አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ። |
መግዛት በጀመረ በመጀመሪያው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር የይሖዋን ቤት በሮች ከፈተ፤ አደሳቸውም። |
ከዚያም ካህናቱንና ሌዋውያኑን አስጠርቶ በምሥራቅ በኩል በሚገኘው አደባባይ ሰበሰባቸው። |
እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ሌዋውያን፣ ስሙኝ። ራሳችሁንም ሆነ የአባቶቻችሁን አምላክ የይሖዋን ቤት ቀድሱ፤ ርኩስ የሆነውንም ነገር ከቅዱሱ ስፍራ አስወግዱ። |
አባቶቻችን ታማኞች አልነበሩም፤ በአምላካችን በይሖዋም ፊት ክፉ ነገር አድርገዋል። እሱን የተዉት ከመሆኑም ሌላ ከይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊታቸውን መልሰዋል፤ ጀርባቸውንም ሰጥተውታል። |
በተጨማሪም የበረንዳውን በሮች ዘጉ፤ መብራቶቹንም አጠፉ። ዕጣን ማጠንና በተቀደሰው ስፍራ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ አቆሙ። |
ስለዚህ የይሖዋ ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ነደደ፤ በመሆኑም በገዛ ዓይናችሁ እንደምታዩት መቀጣጫ፣ የሰዎች መደነቂያና ማፏጫ አደረጋቸው። |
በዚህም የተነሳ አባቶቻችን በሰይፍ ወደቁ፤ እንዲሁም ወንዶች ልጆቻችን፣ ሴቶች ልጆቻችንና ሚስቶቻችን ተማርከው ተወሰዱ። |
አሁንም የሚነድ ቁጣው ከእኛ እንዲመለስ ከእስራኤል አምላክ ከይሖዋ ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ከልቤ ተመኝቻለሁ። |
እንግዲህ ልጆቼ በፊቱ እንድትቆሙ፣ እንድታገለግሉትና የሚጨስ መሥዋዕቱን እንድታቀርቡ ይሖዋ የመረጠው እናንተን ስለሆነ አሁን ቸልተኛ የምትሆኑበት ጊዜ አይደለም።” |
በዚህ ጊዜ ሌዋውያኑ ለሥራ ተነሱ፤ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦ ከቀአታውያን መካከል የአማሳይ ልጅ ማሃት እና የአዛርያስ ልጅ ኢዩኤል፤ ከሜራራውያን መካከል የአብዲ ልጅ ቂስ እና የይሃሌልዔል ልጅ አዛርያስ፤ ከጌድሶናውያን መካከል የዚማ ልጅ ዮአህ እና የዮአህ ልጅ ኤደን፤ |
ከኤሊጻፋን ልጆች መካከል ሺምሪ እና የኡዔል፤ ከአሳፍ ልጆች መካከል ዘካርያስ እና ማታንያህ፤ |
ከሄማን ልጆች መካከል የሂኤል እና ሺምአይ እንዲሁም ከየዱቱን ልጆች መካከል ሸማያህ እና ዑዚኤል። |
እነሱም ወንድሞቻቸውን ከሰበሰቡና ራሳቸውን ከቀደሱ በኋላ ንጉሡ በይሖዋ ቃል ባዘዛቸው መሠረት የይሖዋን ቤት ለማንጻት መጡ። |
ከዚያም ካህናቱ የይሖዋን ቤት ለማንጻት ወደ ውስጥ ገቡ፤ በይሖዋ ቤተ መቅደስ ውስጥ ያገኙትን ርኩስ የሆነ ነገር ሁሉ አውጥተው ወደ ይሖዋ ቤት ግቢ ወሰዱት። ሌዋውያኑ ደግሞ ከዚያ አውጥተው በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ ጣሉት። |
እነሱም በዚህ መንገድ በመጀመሪያው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን የማንጻት ሥራውን ጀመሩ፤ በወሩም በስምንተኛ ቀን ወደ ይሖዋ ቤት በረንዳ ደረሱ። የይሖዋንም ቤት ለስምንት ቀን ቀደሱ፤ በመጀመሪያውም ወር በ16ኛው ቀን ሥራውን አጠናቀቁ። |
ከዚያም ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ገብተው እንዲህ አሉት፦ “የይሖዋን ቤት በሙሉ፣ የሚቃጠለው መባ የሚቀርብበትን መሠዊያና ዕቃዎቹን በሙሉ እንዲሁም የሚነባበረው ዳቦ የሚቀመጥበትን ጠረጴዛና ዕቃዎቹን በሙሉ አንጽተናል። |
ንጉሥ አካዝ በንግሥና ዘመኑ ታማኝነቱን ባጎደለ ጊዜ ከቦታቸው ያስወገዳቸውን ዕቃዎች ሁሉ አዘጋጅተን ቀድሰናቸዋል፤ ዕቃዎቹም በይሖዋ መሠዊያ ፊት ይገኛሉ።” |
ንጉሥ ሕዝቅያስም በማለዳ ተነስቶ የከተማዋን መኳንንት ሰበሰበ፤ ከዚያም ወደ ይሖዋ ቤት ወጡ። |
እነሱም ለመንግሥቱ፣ ለመቅደሱና ለይሁዳ የኃጢአት መባ ሆነው የሚቀርቡ ሰባት በሬዎች፣ ሰባት አውራ በጎች፣ ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና ሰባት ተባዕት ፍየሎች አመጡ። እሱም በይሖዋ መሠዊያ ላይ እንዲያቀርቧቸው የአሮን ዘሮች ለሆኑት ካህናት ነገራቸው። |
ከዚያም ከብቶቹን አረዱ፤ ካህናቱም ደሙን ወስደው በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ ቀጥሎም አውራ በጎቹን አርደው ደሙን መሠዊያው ላይ ረጩ፤ ተባዕት የበግ ጠቦቶቹንም አርደው ደሙን በመሠዊያው ላይ ረጩ። |
ከዚያ በኋላ ለኃጢአት መባ የሚሆኑትን ተባዕት ፍየሎች በንጉሡና በጉባኤው ፊት አቀረቧቸው፤ እጆቻቸውንም ጫኑባቸው። |
ካህናቱም ፍየሎቹን አርደው ለእስራኤል ሁሉ ማስተሰረያ እንዲሆን ደማቸውን በመሠዊያው ላይ የኃጢአት መባ አድርገው አቀረቡ፤ ምክንያቱም ንጉሡ የሚቃጠለው መባና ለኃጢአት የሚሆነው መባ ለመላው እስራኤል እንዲቀርብ አዝዞ ነበር። |
እሱም በዳዊት፣ የንጉሡ ባለ ራእይ በሆነው በጋድና በነቢዩ ናታን በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሌዋውያኑን ሲምባል፣ ባለ አውታር መሣሪያዎችና በገና አስይዞ በይሖዋ ቤት እንዲቆሙ አደረገ፤ ይህም ይሖዋ በነቢያቱ አማካኝነት የሰጠው ትእዛዝ ነበር። |
በመሆኑም ሌዋውያኑ የዳዊትን የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ ካህናቱ ደግሞ መለከቶችን ይዘው ቆሙ። |
ከዚያም ሕዝቅያስ የሚቃጠለው መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ እንዲቀርብ አዘዘ። የሚቃጠለው መባ መቅረብ በጀመረበት ጊዜ የይሖዋ መዝሙር ተሰማ፤ ደግሞም የእስራኤልን ንጉሥ የዳዊትን የሙዚቃ መሣሪያዎች ተከትለው መለከቶቹ ተነፉ። |
መዝሙሩ በሚዘመርበትና መለከቶቹ በሚነፉበት ጊዜም መላው ጉባኤ ተደፍቶ ሰገደ፤ የሚቃጠለው መባ እስኪጠናቀቅ ድረስ ይህ ሁሉ መከናወኑን ቀጠለ። |
መባውን አቅርበው እንደጨረሱም ንጉሡና አብረውት ያሉት ሁሉ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ። |
ንጉሥ ሕዝቅያስና መኳንንቱ በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ መዝሙራት ይሖዋን እንዲያወድሱ ሌዋውያኑን አዘዙ። እነሱም በታላቅ ደስታ ውዳሴ አቀረቡ፤ ተደፍተውም ሰገዱ። |
ከዚያም ሕዝቅያስ እንዲህ አለ፦ “አሁን እናንተ ለይሖዋ ስለተለያችሁ ቅረቡ፤ ለይሖዋም ቤት መሥዋዕቶችና የምስጋና መባዎች አምጡ።” በመሆኑም ጉባኤው መሥዋዕቶችንና የምስጋና መባዎችን ማምጣት ጀመረ፤ ልቡ ያነሳሳውም ሁሉ የሚቃጠል መባ አመጣ። |
ጉባኤው ያመጣቸው የሚቃጠሉ መባዎች ብዛት 70 ከብቶች፣ 100 አውራ በጎችና 200 ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ ሆነው የሚቀርቡ ነበሩ፤ |
ሌሎቹ ቅዱስ መባዎች ደግሞ 600 ከብቶችና 3,000 በጎች ነበሩ። |
ይሁንና የሚቃጠል መባ ሆነው የሚቀርቡትን እንስሳት ሁሉ ለመግፈፍ በቂ ካህናት ስላልነበሩ ሥራው እስኪጠናቀቅና ካህናቱ ራሳቸውን እስኪቀድሱ ድረስ ወንድሞቻቸው የሆኑት ሌዋውያን ረዷቸው፤ ሌዋውያኑ ራሳቸውን በመቀደስ ረገድ ከካህናቱ ይበልጥ ጠንቃቆች ነበሩና። |
በተጨማሪም የሚቃጠሉት መባዎችና የኅብረት መሥዋዕቶቹ ስብ እንዲሁም ከሚቃጠሉት መባዎች ጋር የሚቀርቡት የመጠጥ መባዎች ብዙ ነበሩ። በዚህ መንገድ የይሖዋ ቤት አገልግሎት እንደገና ተደራጀ። |
ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ እውነተኛው አምላክ ለሕዝቡ ይህን በማቋቋሙና ይህ ሁሉ ነገር በአጭር ጊዜ ውስጥ በመከናወኑ እጅግ ተደሰቱ። |
ሰለሞን የይሖዋን ቤትና የራሱን ቤት ገንብቶ በጨረሰበት በ20ኛው ዓመት ማብቂያ ላይ |
ኪራም የሰጠውን ከተሞች መልሶ ገነባቸው፤ እስራኤላውያንንም በዚያ አሰፈረ። |
በተጨማሪም ሰለሞን በሃማትጾባ ላይ ዘምቶ ያዛት። |
ከዚያም በምድረ በዳ የምትገኘውን ታድሞርንና በሃማት የሠራቸውን የማከማቻ ከተሞች ሁሉ ገነባ። |
ደግሞም ቅጥሮች፣ በሮችና መቀርቀሪያዎች ያሏቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ይኸውም ላይኛውን ቤትሆሮንንና ታችኛውን ቤትሆሮንን ገነባ፤ |
በተጨማሪም ባዓላትን፣ የሰለሞንን የእህልና የዕቃ ማከማቻ ከተሞች በሙሉ፣ የሠረገላ ከተሞቹን በሙሉ፣ የፈረሰኞቹን ከተሞች እንዲሁም ሰለሞን በኢየሩሳሌም፣ በሊባኖስና በእሱ ግዛት ውስጥ ባለው ምድር ሁሉ መገንባት የፈለጋቸውን ነገሮች በሙሉ ሠራ። |
ከእስራኤል ወገን ያልሆኑትን ከሂታውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፈሪዛውያን፣ ከሂዋውያንና ከኢያቡሳውያን የተረፉትን ሕዝቦች በሙሉ፣ |
ይኸውም እስራኤላውያን ፈጽመው ያላጠፏቸውን በምድሪቱ ላይ የቀሩትን ዘሮቻቸውን ሰለሞን የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ መለመላቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ ይሠራሉ። |
ሆኖም ሰለሞን ለሚያከናውነው ሥራ ከእስራኤላውያን መካከል አንዳቸውንም ባሪያ አላደረገም፤ ምክንያቱም እነሱ ተዋጊዎቹ፣ የጦር መኮንኖቹ፣ የሠረገለኞቹና የፈረሰኞቹ አለቆች ነበሩ። |
በሠራተኞቹ ላይ የተሾሙት ይኸውም የንጉሥ ሰለሞን የበታች ተቆጣጣሪዎቹ አለቆች 250 ነበሩ። |
በተጨማሪም ሰለሞን የፈርዖንን ሴት ልጅ ከዳዊት ከተማ አውጥቶ ወደሠራላት ቤት አመጣት፤ ይህን ያደረገው “እሷ ሚስቴ ብትሆንም የይሖዋ ታቦት የገባባቸው ቦታዎች ቅዱስ ስለሆኑ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት ልትኖር አይገባም” በማለት ነበር። |
ከዚያም ሰለሞን ከበረንዳው ፊት ለፊት በሠራው የይሖዋ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለይሖዋ አቀረበ። |
ለሙሴ ከተሰጠው ትእዛዝ ጋር በሚስማማ ሁኔታ በሥርዓቱ መሠረት በየዕለቱ ሊቀርቡ የሚገባቸውን መባዎች ማለትም የየሰንበቱን፣ የየወሩን መባቻና በዓመት ሦስት ጊዜ የሚደረጉትን የተወሰኑትን በዓላት ይኸውም የቂጣን በዓል፣ የሳምንታትን በዓልና የዳስን በዓል መባዎች አቀረበ። |
በተጨማሪም አባቱ ዳዊት ባወጣው ደንብ መሠረት ካህናቱን በየአገልግሎት ምድባቸው፣ ሌዋውያኑንም በየዕለቱ ሊከናወን በሚገባው ሥርዓት መሠረት ካህናቱ ባሉበት አምላክን እንዲያወድሱና እንዲያገለግሉ በተመደቡበት ስፍራ ላይ ሾማቸው፤ በር ጠባቂዎቹንም በተለያዩ በሮች ላይ በየቡድናቸው መደባቸው፤ የእውነተኛው አምላክ ሰው ዳዊት ይህን ትእዛዝ አስተላልፎ ነበርና። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.