text stringlengths 4 267 |
|---|
በወይን ጠጅ ግብዣው ላይ ንጉሡ አስቴርን እንዲህ አላት፦ “የምትጠይቂው ምንድን ነው? የጠየቅሽው ይሰጥሻል! የምትፈልጊውስ ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ብትጠይቂ ይሰጥሻል!” |
አስቴርም እንዲህ ስትል መለሰች፦ “የምጠይቀውም ሆነ የምፈልገው ነገር ይህ ነው፦ |
በንጉሡ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ እንዲሁም ንጉሡ የምጠይቀውን ነገር መስጠትና የምፈልገውን መፈጸም ደስ ካሰኘው ነገ ንጉሡና ሃማ ለእነሱ በማዘጋጅላቸው ግብዣ ላይ ይገኙ፤ እኔም በነገው ዕለት ንጉሡ ያለውን አደርጋለሁ።” |
በዚያ ቀን ሃማ ተደስቶ ልቡም ሐሴት አድርጎ ወጣ። ሆኖም ሃማ፣ መርዶክዮስን በንጉሡ በር ላይ ሲያየው እንዲሁም እንዳልተነሳለትና በፊቱ እንዳልተንቀጠቀጠ ሲመለከት በመርዶክዮስ ላይ ቁጣው ነደደ። |
ይሁንና ሃማ ራሱን ተቆጣጥሮ ወደ ቤቱ ሄደ። ከዚያም ጓደኞቹንና ሚስቱን ዜሬሽን አስጠራቸው። |
ሃማም ስለ ሀብቱ ታላቅነትና ስለ ወንዶች ልጆቹ ብዛት እንዲሁም ንጉሡ ላቅ ያለ ሹመት እንደሰጠውና ከመኳንንቱም ሆነ ከንጉሡ አገልጋዮች በላይ ከፍ ከፍ እንዳደረገው በጉራ ይነግራቸው ጀመር። |
ሃማ በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “ምን ይሄ ብቻ፣ ንግሥት አስቴር አዘጋጅታ በነበረው ግብዣ ላይ ከንጉሡ ጋር እንድገኝ የጋበዘችው እኔን ብቻ ነው። በተጨማሪም ነገ ከንጉሡና ከእሷ ጋር እንድገኝ ጋብዛኛለች። |
ይሁን እንጂ አይሁዳዊውን መርዶክዮስን በንጉሡ በር ላይ ተቀምጦ የማየው ከሆነ ይህ ሁሉ ምንም አያስደስተኝም።” |
በዚህ ጊዜ ሚስቱ ዜሬሽና ጓደኞቹ በሙሉ እንዲህ አሉት፦ “ቁመቱ 50 ክንድ የሆነ እንጨት አስተክል። ከዚያም ነገ ጠዋት በላዩ ላይ መርዶክዮስ እንዲሰቀል ለንጉሡ ንገረው። አንተም ከንጉሡ ጋር በግብዣው ላይ ተገኝተህ ሐሴት አድርግ።” ይህ ሐሳብ ሃማን አስደሰተው፤ እንጨቱንም አስተከለ። |
መርዶክዮስ የተደረገውን ነገር ሁሉ ባወቀ ጊዜ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለበሰ፤ በራሱም ላይ አመድ ነሰነሰ። ከዚያም ድምፁን ከፍ አድርጎ እየጮኸና ምርር ብሎ እያለቀሰ ወደ ከተማዋ መሃል ወጣ። |
ማንም ሰው ማቅ ለብሶ በንጉሡ በር እንዲገባ ስለማይፈቀድለት እስከ ንጉሡ በር ድረስ መጣ። |
የንጉሡ ቃልና ድንጋጌ በተሰማባቸው አውራጃዎች በሙሉ በሚገኙ አይሁዳውያን መካከል ታላቅ ሐዘን ሆነ፤ እነሱም ጾሙ፤ አለቀሱ፤ እንዲሁም ዋይታ አሰሙ። ብዙዎቹ ማቅ አንጥፈው፣ አመድ ነስንሰው ተኙ። |
የአስቴር ሴት አገልጋዮችና ጃንደረቦችም ወደ እሷ ገብተው በነገሯት ጊዜ ንግሥቲቱ እጅግ ተጨነቀች። ከዚያም መርዶክዮስ ማቁን አውልቆ የሚለብሰው ልብስ ላከችለት፤ እሱ ግን አልተቀበለም። |
በዚህ ጊዜ አስቴር ከንጉሡ ጃንደረቦች አንዱ የሆነውንና ንጉሡ እሷን እንዲያገለግል የመደበውን ሃታክን ጠርታ ወደ መርዶክዮስ ሄዶ ምን ችግር እንደተፈጠረና ምን እንደተከሰተ እንዲያጣራ አዘዘችው። |
ስለዚህ ሃታክ በንጉሡ በር ፊት ለፊት ባለው የከተማዋ አደባባይ ወደሚገኘው ወደ መርዶክዮስ ወጣ። |
መርዶክዮስም ያጋጠመውን ነገር ሁሉ ነገረው፤ እንዲሁም ሃማ አይሁዳውያንን ለማጥፋት ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ለማስገባት ቃል ስለገባው ገንዘብ መጠን ነገረው። |
በተጨማሪም እነሱን ለማጥፋት በሹሻን በጽሑፍ የወጣውን ድንጋጌ ቅጂ ሰጠው። ቅጂውን ለአስቴር እንዲያሳያትና እንዲያስረዳት እንዲሁም ወደ ንጉሡ ገብታ ሞገስ እንዲያሳያት እንድትለምነውና ስለ ሕዝቧ በግንባር ቀርባ እንድትማጸነው ይነግራት ዘንድ አሳሰበው። |
ሃታክ ተመልሶ መርዶክዮስ ያለውን ለአስቴር ነገራት። |
አስቴርም ለመርዶክዮስ እንዲህ ብሎ እንዲነግረው ሃታክን አዘዘችው፦ |
“የንጉሡ አገልጋዮች ሁሉና በንጉሡ አውራጃዎች ውስጥ የሚኖሩት ሕዝቦች፣ ሳይጠራ ወደ ንጉሡ ውስጠኛ ግቢ የሚገባን ማንኛውንም ወንድ ወይም ሴት በተመለከተ ንጉሡ አንድ ሕግ እንዳለው ያውቃሉ፦ እንዲህ ያደረገ ሰው ይገደላል፤ ሰውየው በሕይወት ሊተርፍ የሚችለው ንጉሡ የወርቅ በትረ መንግሥቱን ከዘረጋለት ብቻ ነው። እኔ ደግሞ ላለፉት 30 ቀናት ወደ ንጉሡ እንድገባ አልተጠራሁም።” |
መርዶክዮስ፣ የአስቴር ቃል በተነገረው ጊዜ |
ለአስቴር ይህን መልስ ላከ፦ “በንጉሡ ቤት ስላለሽ ብቻ ከሌሎቹ አይሁዳውያን ተለይቼ እኔ እተርፋለሁ ብለሽ እንዳታስቢ። |
በዚህ ጊዜ አንቺ ዝም ብትዪ አይሁዳውያን እፎይታና መዳን ከሌላ ቦታ ያገኛሉ፤ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ። ደግሞስ ንግሥት ለመሆን የበቃሽው እንዲህ ላለው ጊዜ እንደሆነ ማን ያውቃል?” |
ከዚያም አስቴር በምላሹ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ መርዶክዮስ ላከች፦ |
“ሂድ፤ በሹሻን ያሉትን አይሁዳውያን ሁሉ ሰብስብ፤ ስለ እኔም ጹሙ። ቀንም ሆነ ሌሊት ለሦስት ቀን እንዳትበሉ እንዲሁም እንዳትጠጡ። እኔም ከሴት አገልጋዮቼ ጋር እጾማለሁ። ከዚያም ሕጉ ባይፈቅድም እንኳ ወደ ንጉሡ እገባለሁ፤ ከጠፋሁም ልጥፋ።” |
በመሆኑም መርዶክዮስ ሄደ፤ አስቴር ያዘዘችውንም ነገር ሁሉ አደረገ። |
በዚያ ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ እንቢ አለው። በመሆኑም በዘመኑ የነበረውን የታሪክ መጽሐፍ እንዲያመጡለት አዘዘ። መጽሐፉም በንጉሡ ፊት ተነበበ። |
በዚህ ጊዜ ንጉሥ አሐሽዌሮስን ለመግደል አሲረው የነበሩትን የንጉሡን ሁለት የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ማለትም በር ጠባቂዎቹን ቢግታናን እና ቴሬሽን አስመልክቶ መርዶክዮስ የተናገረው ነገር ተጽፎ ተገኘ። |
ንጉሡም “ታዲያ መርዶክዮስ ይህን በማድረጉ ምን ክብርና እውቅና አገኘ?” ሲል ጠየቀ። በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ አገልጋዮች “ምንም አልተደረገለትም” አሉ። |
ንጉሡም “በግቢው ውስጥ ያለው ማን ነው?” አለ። ሃማም ባዘጋጀው እንጨት ላይ መርዶክዮስ እንዲሰቀል ለንጉሡ ለመናገር ወደ ንጉሡ ቤት ውጨኛ ግቢ ገብቶ ነበር። |
የንጉሡ አገልጋዮችም “ሃማ ግቢው ውስጥ ቆሟል” አሉት። ንጉሡም “ግባ በሉት” አለ። |
ንጉሡም ሃማ በገባ ጊዜ “ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው ምን ሊደረግለት ይገባል?” አለው። ሃማም በልቡ “ንጉሡ ከእኔ በላይ ሊያከብረው የሚወደው ሰው ማን አለ?” ሲል አሰበ። |
በመሆኑም ሃማ ንጉሡን እንዲህ አለው፦ “ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው፣ |
ንጉሡ የሚጎናጸፈውን ልብሰ መንግሥት እንዲሁም ንጉሡ የሚቀመጥበትንና በራሱ ላይ አክሊል የተደረገለትን ፈረስ ያምጡለት። |
ከዚያም ልብሱና ፈረሱ ከንጉሡ ታላላቅ መኳንንት መካከል ለአንዱ በኃላፊነት ይሰጥ፤ እነሱም ንጉሡ ሊያከብረው የወደደውን ሰው ያልብሱት፤ እንዲሁም በፈረሱ ላይ አስቀምጠው በከተማው አደባባይ እንዲያልፍ ያድርጉ። በፊቱም ‘ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው እንዲህ ይደረግለታል!’ ይበሉ።” |
ንጉሡም ወዲያውኑ ሃማን እንዲህ አለው፦ “ፈጠን በል! ልብሱንና ፈረሱን ውሰድ፤ በንጉሡ በር ላይ ለሚቀመጠው ለአይሁዳዊው ለመርዶክዮስም ልክ እንዳልከው አድርግለት። ከተናገርከው ውስጥ አንዱም ሳይፈጸም እንዳይቀር።” |
ስለዚህ ሃማ ልብሱንና ፈረሱን ወሰደ፤ መርዶክዮስንም አለበሰው፤ በፈረሱም ላይ አስቀምጦ በከተማው አደባባይ እንዲያልፍ አደረገ፤ “ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው እንዲህ ይደረግለታል!” እያለ በፊቱ ያውጅ ነበር። |
ከዚያም መርዶክዮስ ወደ ንጉሡ በር ተመለሰ፤ ሃማ ግን ራሱን ተከናንቦ እያዘነ በጥድፊያ ወደ ቤቱ ሄደ። |
ሃማ ያጋጠመውን ነገር ሁሉ ለሚስቱ ለዜሬሽና ለጓደኞቹ በሙሉ ሲነግራቸው ጥበበኛ አማካሪዎቹና ሚስቱ ዜሬሽ “በፊቱ መውደቅ የጀመርክለት መርዶክዮስ የአይሁዳውያን ዘር ከሆነ ልታሸንፈው አትችልም፤ ያለምንም ጥርጥር በፊቱ ትወድቃለህ” አሉት። |
እነሱም ገና ከእሱ ጋር እየተነጋገሩ ሳሉ የንጉሡ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ደርሰው ሃማን አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ እያጣደፉ ወሰዱት። |
በዚያው ቀን ንጉሥ አሐሽዌሮስ የአይሁዳውያን ጠላት የነበረውን የሃማን ቤት ለንግሥት አስቴር ሰጣት፤ አስቴር ከመርዶክዮስ ጋር ምን ዝምድና እንዳላቸው ለንጉሡ ነግራው ስለነበር መርዶክዮስ ንጉሡ ፊት ቀረበ። |
ከዚያም ንጉሡ ከሃማ ላይ የወሰደውን የማኅተም ቀለበቱን አውልቆ ለመርዶክዮስ ሰጠው። አስቴርም መርዶክዮስን በሃማ ቤት ላይ ሾመችው። |
በተጨማሪም አስቴር ንጉሡን እንደገና አናገረችው። እግሩ ላይ ወድቃ እያለቀሰች አጋጋዊው ሃማ ያደረሰውን ጉዳትና በአይሁዳውያን ላይ የጠነሰሰውን ሴራ እንዲያስወግድ ለመነችው። |
ንጉሡም የወርቅ በትረ መንግሥቱን ለአስቴር ዘረጋላት፤ አስቴርም ተነስታ በንጉሡ ፊት ቆመች። |
እሷም እንዲህ አለች፦ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ከሆነና እኔም በፊቱ ሞገስ ካገኘሁ፣ ነገሩም በንጉሡ ፊት ተገቢ ሆኖ ከተገኘና በእኔ ደስ ከተሰኘ፣ ያ ሴረኛ አጋጋዊው የሃመዳታ ልጅ ሃማ በመላው የንጉሡ አውራጃዎች የሚገኙትን አይሁዳውያን ለማጥፋት ያዘጋጀውን ሰነድ የሚሽር ትእዛዝ ይጻፍ። |
በሕዝቤ ላይ መዓት ሲወርድ ዓይኔ እያየ እንዴት አስችሎኝ ዝም እላለሁ? ዘመዶቼ ሲጠፉስ እያየሁ እንዴት አስችሎኝ ዝም እላለሁ?” |
በመሆኑም ንጉሥ አሐሽዌሮስ ንግሥት አስቴርንና አይሁዳዊውን መርዶክዮስን እንዲህ አላቸው፦ “የሃማን ቤት ለአስቴር ሰጥቻለሁ፤ አይሁዳውያንን ለማጥቃት በጠነሰሰው ሴራ የተነሳም በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አድርጌአለሁ። |
በንጉሡ ስም የተጻፈንና በንጉሡ የማኅተም ቀለበት የታተመን ድንጋጌ መሻር ስለማይቻል አይሁዳውያንን በተመለከተ ተገቢ መስሎ የታያችሁን ማንኛውንም ነገር በንጉሡ ስም ጻፉ፤ በንጉሡም የማኅተም ቀለበት አትሙት።” |
ስለሆነም ሲዋን በተባለው በሦስተኛው ወር፣ በ23ኛው ቀን የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠሩ፤ እነሱም መርዶክዮስ ያዘዘውን ሁሉ ለአይሁዳውያኑ፣ ለአስተዳዳሪዎቹ፣ ለገዢዎቹና ከሕንድ አንስቶ እስከ ኢትዮጵያ ላሉት 127 አውራጃዎች መኳንንት ጻፉ፤ ለእያንዳንዱ አውራጃ በራሱ ጽሑፍ፣ ለእያንዳንዱም ሕዝብ በራሱ ቋንቋ ተጻፈለት፤ ለአይሁዳውያኑም በራሳቸው ጽሑፍና በራሳቸው ቋንቋ ተጻፈላቸው። |
እሱም ደብዳቤውን በንጉሥ አሐሽዌሮስ ስም ጽፎ በንጉሡ የማኅተም ቀለበት አተመው፤ ደብዳቤውንም ፈረስ በሚጋልቡ መልእክተኞች እጅ ላከው፤ እነዚህ መልእክተኞች ለንጉሡ አገልግሎት የሚያሳድጓቸውን፣ ደብዳቤ ለማድረስ የሚያገለግሉ ፈጣን ፈረሶች የሚጋልቡ ነበሩ። |
በእነዚህም ደብዳቤዎች ላይ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ አይሁዳውያን በሙሉ ተሰብስበው ሕይወታቸውን ከጥቃት እንዲከላከሉ እንዲሁም ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ በእነሱ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩትን የየትኛውም ሕዝብ ወይም አውራጃ ኃይሎች በሙሉ እንዲያጠፉ፣ እንዲገድሉና እንዲደመስሱ ብሎም ንብረታቸውን እንዲዘርፉ ንጉሡ መፍቀዱን የሚገልጽ ሐሳብ ሰፍሮ ነበር። |
ይህም በመላው የንጉሥ አሐሽዌሮስ አውራጃዎች በተመሳሳይ ቀን ይኸውም አዳር በተባለው በ12ኛው ወር 13ኛ ቀን ላይ እንዲፈጸም ተወሰነ። |
በደብዳቤው ላይ የሰፈረው ጽሑፍ በሁሉም አውራጃዎች ውስጥ ሕግ ሆኖ እንዲወጣ ተወስኖ ነበር። በተጨማሪም አይሁዳውያኑ በዚያ ቀን ጠላቶቻቸውን ለመበቀል ዝግጁ እንዲሆኑ ለማድረግ ሲባል ለሕዝቦቹ ሁሉ እንዲታወጅ ተደንግጎ ነበር። |
ለንጉሡ አገልግሎት የተመደቡትን ደብዳቤ ለማድረስ የሚያገለግሉ ፈረሶች የሚጋልቡት መልእክተኞች በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት እየተቻኮሉና እየተጣደፉ ወጡ። ሕጉ በሹሻን ግንብም ታውጆ ነበር። |
መርዶክዮስም ሰማያዊና ነጭ ልብሰ መንግሥት ለብሶ፣ ትልቅ የወርቅ አክሊል ደፍቶ እንዲሁም ከፍተኛ ጥራት ካለው ክርና ከሐምራዊ ሱፍ የተሠራ መጎናጸፊያ ደርቦ ከንጉሡ ፊት ወጣ። የሹሻን ከተማም እልል አለች። |
ለአይሁዳውያኑም እፎይታ፣ ደስታ፣ ሐሴትና ክብር ሆነላቸው። |
የንጉሡ ድንጋጌና ሕግ በተሰማባቸው በሁሉም አውራጃዎችና ከተሞች የሚኖሩ አይሁዳውያን ተደሰቱ፤ ሐሴትም አደረጉ፤ የግብዣና የፈንጠዝያ ቀን ሆነ። ብዙዎቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች አይሁዳውያንን ከመፍራታቸው የተነሳ አይሁዳዊ ሆኑ። |
ከዚያም ኢዮብ ለይሖዋ እንዲህ ሲል መለሰ፦ |
“አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል፣ደግሞም ያሰብከውን ነገር ሁሉ ማድረግ እንደማይሳንህ አሁን አወቅኩ። |
አንተ ‘ያለእውቀት ሐሳቤን የሚሰውር ይህ ማን ነው?’ አልክ። በመሆኑም ስለማላውቃቸው እጅግ ድንቅ የሆኑ ነገሮችማስተዋል በጎደለው መንገድ ተናግሬአለሁ። |
‘እባክህ ስማኝ፤ እኔም እናገራለሁ። እጠይቅሃለሁ፤ አንተም ትነግረኛለህ’ አልከኝ። |
ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤አሁን ግን በገዛ ዓይኔ አየሁህ። |
ስለዚህ በተናገርኩት ነገር እጸጸታለሁ፤በአፈርና በአመድ ላይ ተቀምጬም ንስሐ እገባለሁ።” |
ይሖዋ ከኢዮብ ጋር ተነጋግሮ ካበቃ በኋላ፣ ቴማናዊውን ኤሊፋዝን ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ እውነቱን ስላልተናገራችሁ በአንተና በሁለቱ ጓደኞችህ ላይ ቁጣዬ ነዷል። |
አሁን ሰባት ኮርማዎችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ ለራሳችሁም የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ። አገልጋዬ ኢዮብም ለእናንተ ይጸልያል። እንደ ሞኝነታችሁ እንዳላደርግባችሁ የእሱን ልመና እቀበላለሁ፤ አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ እውነቱን አልተናገራችሁምና።” |
በመሆኑም ቴማናዊው ኤሊፋዝ፣ ሹሃዊው በልዳዶስና ናአማታዊው ሶፋር ሄደው ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ። ይሖዋም የኢዮብን ጸሎት ሰማ። |
ኢዮብ ለጓደኞቹ ከጸለየ በኋላ ይሖዋ በኢዮብ ላይ የደረሰው መከራ እንዲያበቃ አደረገ፤ ደግሞም ብልጽግናውን መለሰለት። ይሖዋ ለኢዮብ ቀድሞ የነበረውን እጥፍ አድርጎ ሰጠው። |
ወንድሞቹና እህቶቹ ሁሉ እንዲሁም የቀድሞ ወዳጆቹ ሁሉ ወደ እሱ መጡ፤ በቤቱም ከእሱ ጋር ምግብ በሉ። ሐዘናቸውን ገለጹለት፤ እንዲሁም ይሖዋ በእሱ ላይ እንዲደርስበት ከፈቀደው መከራ ሁሉ አጽናኑት። እያንዳንዳቸውም የገንዘብ ስጦታና የወርቅ ጌጥ ሰጡት። |
በመሆኑም ይሖዋ ከፊተኛው የኢዮብ ሕይወት ይልቅ የኋለኛውን አብዝቶ ባረከ፤ ኢዮብም 14,000 በጎች፣ 6,000 ግመሎች፣ 1,000 ጥማድ ከብቶችና 1,000 እንስት አህዮች አገኘ። |
ደግሞም ሌሎች ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ወለደ። |
የመጀመሪያዋን ሴት ልጁን ይሚማ፣ ሁለተኛዋን ቃስያ፣ ሦስተኛዋን ደግሞ ቄሬንሃጱክ ብሎ ስም አወጣላቸው። |
በምድሪቱ ሁሉ የኢዮብን ሴቶች ልጆች ያህል የተዋቡ ሴቶች አልነበሩም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት ሰጣቸው። |
ከዚህ በኋላ ኢዮብ 140 ዓመት ኖረ፤ እስከ አራት ትውልድም ድረስ ልጆችንና የልጅ ልጆችን አየ። |
በመጨረሻም ኢዮብ ሸምግሎና ዕድሜ ጠግቦ ሞተ። |
“ሌዋታንን በመንጠቆ ልትይዘው፣ወይስ ምላሱን በገመድ ልታስረው ትችላለህ? |
በአፍንጫው ገመድ ልታስገባ፣ወይስ መንጋጋዎቹን በሜንጦ ልትበሳ ትችላለህ? |
እሱ እንድትምረው ይለማመጥሃል?ወይስ በለሰለሰ አንደበት ያናግርሃል? |
ዕድሜ ልኩን ባሪያህ ታደርገው ዘንድ፣ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን ይገባል? |
ከወፍ ጋር እንደምትጫወተው ከእሱ ጋር ትጫወታለህ?ወይስ ለትናንሽ ሴት ልጆችህ መጫወቻ እንዲሆን በውሻ ማሰሪያ ታስረዋለህ? |
ነጋዴዎች ይገበያዩበታል? ለቸርቻሪዎችስ ያከፋፍሉታል? |
ቆዳውን ለአደን በሚያገለግል ጦር፣ራሱንስ በዓሣ መውጊያ ጭሬ ልትጠቀጥቅ ትችላለህ? |
እስቲ እጅህን አሳርፍበት፤ግብግቡን መቼም አትረሳውም፤ ዳግመኛም እንዲህ ለማድረግ አይቃጣህም! |
እሱን በቁጥጥር ሥር አውላለሁ ማለት ከንቱ ልፋት ነው። እሱን በማየትህ ብቻ እንኳ ብርክ ይይዝሃል። |
እሱን ለመተንኮስ የሚደፍር የለም። ታዲያ እኔን ሊቋቋም የሚችል ማን ነው? |
ብድራት እመልስለት ዘንድ በመጀመሪያ አንዳች ነገር የሰጠኝ ማን ነው? ከሰማያት በታች ያለው ሁሉ የእኔ ነው። |
ስለ እግሮቹ፣ ደግሞም ስለ ኃይሉናግሩም በሆነ መንገድ ስለተሠራው አካሉ ከመናገር አልቆጠብም። |
የላይኛውን ሽፋኑን የገፈፈ ማን ነው? ወደተከፈቱ መንጋጋዎቹስ ማን ይገባል? |
የአፉን በሮች በኃይል ሊከፍት የሚችል ማን ነው? በዙሪያው ያሉት ጥርሶቹ አስፈሪ ናቸው። |
ጀርባው ላይ እርስ በርስ የተጣበቁ፣በረድፍ የተቀመጡ ቅርፊቶች አሉ። |
ቅርፊቶቹ ግጥግጥ ያሉ ከመሆናቸው የተነሳ፣በመካከላቸው አየር እንኳ ሊገባ አይችልም። |
አንዳቸው ከሌላው ጋር የተጣበቁ ናቸው፤እርስ በርስ የተያያዙ ናቸው፤ ሊለያዩም አይችሉም። |
ፉርፉርታው የብርሃን ብልጭታ ያወጣል፤ዓይኖቹም እንደ ማለዳ ጨረር ናቸው። |
ከአፉ የመብረቅ ብልጭታዎች ይወጣሉ፤የእሳት ፍንጣሪዎችም ይረጫሉ። |
በእንግጫ እንደተቀጣጠለ ምድጃ፣ከአፍንጫው ጭስ ይወጣል። |
እስትንፋሱ ከሰል ያቀጣጥላል፤ከአፉም ነበልባል ይወረወራል። |
በአንገቱ ውስጥ ታላቅ ብርታት አለ፤ሽብርም በፊቱ ይሮጣል። |
የሥጋው ንብርብር እርስ በርስ የተጣበቀ ነው፤ከቦታው እንደማይነቃነቅ ብረት ጠንካራ ነው። |
ልቡ እንደ ድንጋይ የጠጠረ፣አዎ፣ እንደ ወፍጮ ድንጋይ የጠነከረ ነው። |
በሚነሳበት ጊዜ ኃያላን እንኳ ይርዳሉ፤ውኃውን እየመታ ሲሄድ ያስደነብራል። |
ሰይፍ፣ ጦር፣ መውጊያም ሆነ ፍላጻ ቢያገኙትሊያሸንፉት አይችሉም። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.