text
stringlengths
4
267
ብረትን እንደ ገለባ፣መዳብንም እንደበሰበሰ እንጨት ይቆጥራል።
ፍላጻ አያባርረውም፤የወንጭፍ ድንጋይም ለእሱ እንደ ገለባ ነው።
ቆመጥን እንደ ገለባ ይቆጥረዋል፤ጦር ሲሰበቅም ይስቃል።
ሆዱ እንደሾሉ የሸክላ ስብርባሪዎች ነው፤እንደ ማሄጃ በጭቃ ላይ ምልክት ትቶ ያልፋል።
ጥልቁን ውኃ እንደ ድስት ያፈላዋል፤ባሕሩንም እንደ ቅባት መያዣ ይበጠብጠዋል።
በመንገዱ ላይ የሚያብረቀርቅ ፈለግ እየተወ ያልፋል። ተመልካችም ጥልቁ ውኃ ሽበት ያለው ይመስለዋል።
በምድር ላይ ያለፍርሃት የተፈጠረ፣እንደ እሱ ያለ ፍጡር የለም።
ትዕቢተኛ በሆነው ሁሉ ላይ በቁጣ ያፈጣል። ግርማ በተላበሱ የዱር እንስሳት ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።”
“መንፈሴ ተሰብሯል፤ ዘመኔ አብቅቷል፤መቃብር ይጠብቀኛል።
ፌዘኞች ከበውኛል፤ዓይኔም የዓመፅ ተግባራቸውን በትኩረት ትመለከታለች።
እባክህ፣ መያዣዬን ተቀብለህ አንተ ዘንድ አስቀምጥልኝ። እጄን የሚመታና ተያዥ የሚሆነኝ ሌላ ማን ይኖራል?
ማስተዋልን ከልባቸው ሰውረሃልና፤ከዚህም የተነሳ ከፍ ከፍ አታደርጋቸውም።
የልጆቹ ዓይን ደክሞ እያለ፣ያለውን ለወዳጆቹ ሊያካፍል ይችላል።
አምላክ የሰዎች መቀለጃ አደረገኝ፤በመሆኑም ፊቱ ላይ እንደሚተፉበት ሰው ሆንኩ።
ከሐዘን የተነሳ ዓይኔ ፈዘዘ፤እጆቼና እግሮቼም እንደ ጥላ ሆኑ።
ቅን የሆኑ ሰዎች በዚህ ነገር በመገረም ትኩር ብለው ይመለከታሉ፤ንጹሕ የሆነውም፣ አምላክ የለሽ በሆነው ሰው ይረበሻል።
ጻድቅ መንገዱን በጥብቅ ይከተላል፤እጁ ንጹሕ የሆነ ሰውም እየበረታ ይሄዳል።
ይሁን እንጂ ሁላችሁም ተመልሳችሁ መከራከራችሁን መቀጠል ትችላላችሁ፤ከእናንተ መካከል አንድም ጥበበኛ አላገኘሁምና።
የሕይወት ዘመኔ አበቃ፤ዕቅዴና የልቤ ምኞት ተንኮታኮተ።
ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤‘ጨለማ ስለሆነ ብርሃን የሚፈነጥቅበት ጊዜ ቀርቧል’ ይላሉ።
ዝም ብዬ ብጠብቅ ያን ጊዜ መቃብር፣ ቤቴ ይሆናል፤በጨለማ መኝታዬን እዘረጋለሁ።
ጉድጓዱን ‘አንተ አባቴ ነህ!’ እለዋለሁ፤ ትሏን ‘አንቺ እናቴና እህቴ ነሽ!’ እላታለሁ።
እንግዲህ የእኔ ተስፋ የት አለ? ተስፋ እንዳለኝ አድርጎ የሚያስብስ ማን ነው?
ሁላችንም ተያይዘን ወደ አፈር ስንገባ፣ተስፋዬ ወደተቀረቀሩ የመቃብር በሮች ይወርዳል።”
“ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ። ታዲያ ለድንግሊቱ ተገቢ ያልሆነ ትኩረት እንዴት እሰጣለሁ?
ለመሆኑ ከላይ ከአምላክ የማገኘው ድርሻ ምንድን ነው?ከፍ ባለ ስፍራ ከሚኖረው ሁሉን ቻይ አምላክ የማገኘውስ ውርሻ ምንድን ነው?
በደለኛ ሰው ጥፋት፣ክፉ ነገር የሚያደርጉስ መቅሰፍት አይደርስባቸውም?
እሱ መንገዴን ሁሉ አያይም?እርምጃዬንስ ሁሉ አይቆጥርም?
በውሸት ጎዳና ተመላልሼ አውቃለሁ? እግሬ ለማታለል ተጣድፎ ያውቃል?
አምላክ በትክክለኛ ሚዛን ይመዝነኝ፤ያን ጊዜ ንጹሕ አቋም እንዳለኝ ይገነዘባል።
እርምጃዬ ከመንገዱ ወጣ ብሎ፣ወይም ልቤ ዓይኔን ተከትሎ፣አሊያም እጄ ረክሶ ከሆነ፣
የዘራሁትን ዘር ሌላ ይብላው፤የተከልኩትም ይነቀል።
ልቤ ሌላ ሴት ከጅሎ፣በባልንጀራዬም ደጃፍ ላይ አድብቼ ከሆነ፣
ሚስቴ ለሌላ ሰው እህል ትፍጭ፤ሌሎች ወንዶችም ከእሷ ጋር ይተኙ።
ይህ አሳፋሪ ምግባር፣ደግሞም በዳኞች ሊያስቀጣ የሚገባ በደል በሆነ ነበርና።
ይህ የሚያጠፋና የሚደመስስ፣የፍሬዬንም ሥር ሁሉ የሚፈጅ እሳት በሆነ ነበር።
ወንድ ባሪያዬ ወይም ሴት ባሪያዬ በእኔ ላይ አቤቱታ ባቀረቡ ጊዜፍትሕ ነፍጌ ከሆነ፣
አምላክ ሲከራከረኝ ምን ማድረግ እችላለሁ? ሲጠይቀኝስ ምን መልስ እሰጣለሁ?
እኔን በማህፀን ውስጥ የሠራኝ እነሱንስ አልሠራም? ከመወለዳችን በፊት የሠራን እሱ ራሱ አይደለም?
ድሃ የሆኑ ሰዎች የፈለጉትን ነገር ነፍጌ፣ወይም የመበለቲቱ ዓይን እንዲያዝን አድርጌ ከሆነ፣
ወላጅ አልባ ለሆኑ ልጆች ሳላካፍል፣የራሴን ምግብ ብቻዬን በልቼ ከሆነ፣
(ወላጅ አልባ የሆነውን ልጅ ከወጣትነቴ ጀምሮ እንደ አባት ሆኜ አሳድጌዋለሁና፤ከልጅነቴም አንስቶ መበለቲቱን ስመራት ቆይቻለሁ።)
ሰው የሚለብሰው አጥቶ በብርድ ሲያልቅ፣ወይም ድሃው ሲታረዝ አይቼ ከሆነ፣
ከጠቦቶቼ የተሸለተውን ፀጉር ለብሶ በሞቀው ጊዜ፣ሳይባርከኝ ቀርቶ ከሆነ፣
በከተማዋ በር ላይ የእኔን እርዳታ በሚፈልግ ወላጅ አልባ ልጅ ላይእጄን በዛቻ አወዛውዤ ከሆነ፣
ክንዴ ከትከሻዬ ይውለቅ፤ክንዴም ከክርኔ ይሰበር።
ከአምላክ የሚመጣ ጥፋት ያስፈራኛልና፤በግርማውም ፊት መቆም አልችልም።
ወርቅን መታመኛዬ አድርጌ፣ወይም ምርጥ የሆነውን ወርቅ ‘አንተ መመኪያዬ ነህ!’ ብዬ ከሆነ፣
ታላቅ ሀብት በማፍራቴ፣እንዲሁም ብዙ ንብረት በማግኘቴ ደስ ብሎኝ ከሆነ፣
ፀሐይ ስትፈነጥቅ፣ወይም ጨረቃ ግርማ ተላብሳ ስትሄድ አይቼ ከሆነ፣
ልቤ በስውር ተታሎ፣አፌም ለእነሱ አምልኮ ለማቅረብ እጄን ስሞ ከሆነ፣
ይህ በዳኞች ሊያስቀጣ የሚገባ በደል በሆነ ነበር፤በላይ ያለውን እውነተኛውን አምላክ መካድ ይሆንብኝ ነበርና።
ጠላቴ በደረሰበት ጥፋት ደስ ብሎኝ ያውቃል?ወይስ ክፉ ነገር ስለደረሰበት ሐሴት አድርጌ አውቃለሁ?
በእርግማን ሕይወቱን በመሻት፣አንደበቴ ኃጢአት እንዲሠራ አልፈቀድኩም።
በድንኳኔ የሚኖሩ ሰዎች‘እሱ ካቀረበው ምግብ በልቶ ያልጠገበ ሰው ማግኘት የሚችል ማን አለ?’ አላሉም?
አንድም እንግዳ ደጅ አያድርም ነበር፤ቤቴን ለመንገደኛ እከፍት ነበር።
በደሌን በልብሴ ኪስ በመሸሸግ፣እንደ ሌሎች ሰዎች ጥፋቴን ለመሸፋፈን ሞክሬ አውቃለሁ?
የብዙ ሰዎችን ምላሽ በመፍራት፣ወይም በሌሎች ቤተሰቦች ንቀት በመሸበር፣ዝም ብያለሁ? ደግሞስ ወደ ውጭ መውጣት ፈርቻለሁ?
ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ! በተናገርኩት ነገር ላይ ስሜን አሰፍር ነበር። ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ መልስ ይስጠኝ! ምነው ከሳሼ ክሱን በሰነድ ላይ ባሰፈረ ኖሮ!
በትከሻዬ እሸከመው ነበር፤እንደ አክሊልም በራሴ ላይ አስረው ነበር።
የወሰድኩትን እያንዳንዱን እርምጃ ባሳወቅኩት ነበር፤እንደ አለቃ በልበ ሙሉነት ወደ እሱ እቀርብ ነበር።
እርሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ፣ትልሞቿም በአንድ ላይ አልቅሰው ከሆነ፣
ፍሬዋን ያለዋጋ በልቼ፣ባለቤቶቿንም አሳዝኜ ከሆነ፣
በስንዴ ፋንታ እሾህ፣በገብስም ምትክ የሚገማ አረም ይብቀልብኝ።” የኢዮብ ቃል እዚህ ላይ ተፈጸመ።
ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦
“እናንተ ሰዎች ነፍሴን የምታበሳጯት፣በቃላት የምትደቁሱኝስ እስከ መቼ ነው?
ይኸው አሥር ጊዜ ገሠጻችሁኝ፤ከባድ በደል ስትፈጽሙብኝ አላፈራችሁም።
ስህተት ብፈጽምም እንኳ፣የሠራሁት ስህተት ከእኔ ጋር ይኖራል።
በእኔ ላይ የደረሰው ነቀፋ ተገቢ እንደሆነ አድርጋችሁ በመከራከር፣በእኔ ላይ ራሳችሁን ከፍ ከፍ ብታደርጉ፣
ያሳተኝ አምላክ እንደሆነ እወቁ፤በማጥመጃ መረቡም ይዞኛል።
እነሆ ‘ግፍ ተፈጸመብኝ!’ ብዬ ብጮኽም መልስ አላገኘሁም፤እርዳታ ለማግኘት ብጣራም ፍትሕ የለም።
መንገዴን በድንጋይ ግንብ ዘጋ፤ እኔም ማለፍ አልቻልኩም፤ጎዳናዬንም በጨለማ ጋረደ።
ክብሬን ገፎኛል፤አክሊሉንም ከራሴ ላይ አንስቷል።
እስክጠፋ ድረስ በሁሉም አቅጣጫ አፈራረሰኝ፤ተስፋዬን እንደ ዛፍ ነቀለው።
ቁጣው በእኔ ላይ ነደደ፤እንደ ጠላቱም ቆጠረኝ።
ሠራዊቱ በአንድነት መጥተው ከበቡኝ፤በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ።
የገዛ ወንድሞቼን ከእኔ አራቀ፤የሚያውቁኝም ሰዎች ጥለውኝ ሄዱ።
የቅርብ ወዳጆቼ ትተውኛል፤በደንብ የማውቃቸውም ሰዎች ረሱኝ።
በቤቴ ያሉ እንግዶችና ሴቶች ባሪያዎቼ እንደ መጤ ቆጠሩኝ፤እንደ ባዕድ አገር ሰው ተመለከቱኝ።
አገልጋዬን ጠራሁት፤ እሱ ግን አልመለሰልኝም፤እንዲራራልኝ በአንደበቴ ለመንኩት።
ሚስቴ ትንፋሼን እንኳ ተጸየፈችው፤ለገዛ ወንድሞቼም መጥፎ ጠረን ሆንኩባቸው።
ትናንሽ ልጆች እንኳ ናቁኝ፤ስነሳ በእኔ ላይ ያላግጣሉ።
የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤የምወዳቸውም ሰዎች በእኔ ላይ ተነሱ።
አጥንቶቼ ከቆዳዬና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቁ፤ከሞት ለጥቂት ተረፍኩ።
ወዳጆቼ ሆይ፣ ማሩኝ፤ እባካችሁ ማሩኝ፤የአምላክ እጅ መታኛለችና።
አምላክ እንዳሳደደኝ የምታሳድዱኝ ለምንድን ነው?ያለፋታ የምታጠቁኝስ ለምንድን ነው?
ምነው ቃሌ በተጻፈ!ምነው በመጽሐፍ ላይ በሰፈረ!
ምነው በብረት ብዕርና በእርሳስ፣በዓለቱ ላይ ለዘላለም በተቀረጸ!
የሚዋጀኝ ሕያው እንደሆነ በሚገባ አውቃለሁና፤ከጊዜ በኋላ መጥቶ በምድር ላይ ይቆማል።
ቆዳዬ በዚህ መንገድ ቢጠፋም፣ገና በሥጋ እያለሁ አምላክን አየዋለሁ፤
እኔ ራሴ እሱን እመለከተዋለሁ፤የሌላ ሰው ዓይን ሳይሆን የገዛ ዓይኖቼ ያዩታል። ይሁንና በውስጤ እንደዛልኩ ይሰማኛል!
የችግሩ መንስኤ እኔ ጋ እያለ፣ ‘የምናሳድደው እንዴት ነው?’ ትላላችሁና።
እናንተ ራሳችሁ ሰይፉን ፍሩ፤ሰይፉ በበደል ላይ ቅጣት ያመጣልና፤ፈራጅ መኖሩን ልታውቁ ይገባል።”
“አሁን ግን ኢዮብ፣ እባክህ ቃሌን ስማ፤የምናገረውንም ሁሉ አዳምጥ።
እባክህ ልብ በል! አፌን እከፍታለሁ፤አንደበቴም ይናገራል።
ቃሌ የልቤን ቅንነት ይገልጻል፤ከንፈሮቼም የማውቀውን ነገር በቅንነት ይናገራሉ።
የአምላክ መንፈስ ሠራኝ፤ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ እስትንፋስም ሕይወት ሰጠኝ።
የምትችል ከሆነ መልስልኝ፤የመከራከሪያ ሐሳብህን በፊቴ አቅርብ፤ ቦታህንም ያዝ።
እነሆ፣ በእውነተኛው አምላክ ፊት እኔም እንደ አንተው ነኝ፤እኔም የተሠራሁት ከሸክላ ነው።
ስለዚህ እኔን ፈርተህ ልትሸበር አይገባም፤የማሳድርብህ ጫናም ሊደቁስህ አይገባም።