text stringlengths 4 267 |
|---|
የግንባታውን ሥራ የሚሠራ እያንዳንዱ ሰው ግንባታውን የሚያከናውነው ሰይፉን በወገቡ ታጥቆ ነበር፤ ቀንደ መለከት የሚነፋውም ሰው አጠገቤ ይቆም ነበር። |
ከዚያም የተከበሩትን ሰዎች፣ የበታች ገዢዎቹንና የቀረውን ሕዝብ እንዲህ አልኳቸው፦ “ሥራው እንደምታዩት ብዙና ሰፊ ነው፤ ቅጥሩንም የምንገነባው አንዳችን ከሌላው ተራርቀን ነው። |
በመሆኑም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ እኛ ወዳለንበት ቦታ ተሰብሰቡ። አምላካችን ራሱ ይዋጋልናል።” |
ስለዚህ ግማሾቻችን ሥራውን ስናከናውን ግማሾቹ ደግሞ ጎህ ከሚቀድበት አንስቶ ከዋክብት እስከሚወጡበት ጊዜ ድረስ ጦር ይዘው ይቆሙ ነበር። |
በዚህ ጊዜ ሕዝቡን እንዲህ አልኳቸው፦ “እያንዳንዱ ሰው ከአገልጋዩ ጋር ሆኖ ሌሊቱን በኢየሩሳሌም ውስጥ ያሳልፍ፤ እነሱም ሌሊቱን ይጠብቁናል፤ ቀን ላይ ደግሞ ይሠራሉ።” |
እኔም ሆንኩ ወንድሞቼና አገልጋዮቼ እንዲሁም ይከተሉኝ የነበሩት ጠባቂዎች ፈጽሞ ልብሳችንን አናወልቅም ነበር፤ የጦር መሣሪያችንም ከቀኝ እጃችን አይለይም ነበር። |
ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከየሆሹዋ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን የሚከተሉት ነበሩ፦ ሰራያህ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣ |
አማርያህ፣ ማሉክ፣ ሃጡሽ፣ |
ሸካንያህ፣ ረሁም፣ መሬሞት፣ |
ኢዶ፣ ጊነቶአይ፣ አቢያህ፣ |
ሚያሚን፣ ማአድያህ፣ ቢልጋ፣ |
ሸማያህ፣ ዮያሪብ፣ የዳያህ፣ |
ሳሉ፣ አሞቅ፣ ኬልቅያስ እና የዳያህ። እነዚህ በየሆሹዋ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው መሪዎች ነበሩ። |
ሌዋውያኑ ደግሞ የሹዋ፣ ቢኑይ፣ ቃድሚኤል፣ ሸረበያህ፣ ይሁዳ እና ከወንድሞቹ ጋር ሆኖ የምስጋና መዝሙሮቹን የሚመራው ማታንያህ ነበሩ። |
ወንድሞቻቸው ባቅቡቅያ እና ዑኒ ከእነሱ ትይዩ ለጥበቃ ቆመው ነበር። |
የሹዋ ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂምም ኤልያሺብን ወለደ፤ ኤልያሺብም ዮያዳን ወለደ። |
ዮያዳም ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታንም ያዱአን ወለደ። |
በዮአቂም ዘመን የአባቶች ቤት መሪዎች የሆኑት ካህናት የሚከተሉት ነበሩ፦ ከሰራያህ መራያህ፣ ከኤርምያስ ሃናንያህ፣ |
ከዕዝራ መሹላም፣ ከአማርያህ የሆሃናን፣ |
ከማሉኪ ዮናታን፣ ከሸባንያህ ዮሴፍ፣ |
ከሃሪም አድና፣ ከመራዮት ሄልቃይ፣ |
ከኢዶ ዘካርያስ፣ ከጊነቶን መሹላም፣ |
ከአቢያህ ዚክሪ፣ ከሚንያሚን . . . ፣ ከሞአድያህ ፒልጣይ፣ |
ከቢልጋ ሻሙአ፣ ከሸማያህ የሆናታን፣ |
ከዮያሪብ ማቴናይ፣ ከየዳያህ ዑዚ፣ |
ከሳላይ ቃላይ፣ ከአሞቅ ኤቤር፣ |
ከኬልቅያስ ሃሻብያህ፣ ከየዳያህ ናትናኤል ተወክለው ነበር። |
በኤልያሺብ፣ በዮያዳ፣ በዮሃናን እና በያዱአ ዘመን የነበሩት የሌዋውያኑ የአባቶች ቤት መሪዎች ልክ እንደ ካህናቱ ሁሉ እስከ ፋርሳዊው ዳርዮስ የንግሥና ዘመን ድረስ ተመዘገቡ። |
የአባቶች ቤት መሪዎች የነበሩት ሌዋውያን የኤልያሺብ ልጅ እስከሆነው እስከ ዮሃናን ዘመን ድረስ በዘመኑ በነበረው የታሪክ መጽሐፍ ላይ ተመዝግበው ነበር። |
የሌዋውያኑ መሪዎች ሃሻብያህ፣ ሸረበያህና የቃድሚኤል ልጅ የሹዋ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ከእነሱ ትይዩ ቆመው ይኸውም አንዱ የጥበቃ ቡድን ከሌላው የጥበቃ ቡድን ጎን ለጎን ሆኖ የእውነተኛው አምላክ ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት ለአምላክ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር። |
ማታንያህ፣ ባቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ መሹላም፣ ታልሞን እና አቁብ እንደ በር ጠባቂዎች ዘብ በመቆም በበሮቹ አጠገብ ያሉትን ግምጃ ቤቶች ይጠብቁ ነበር። |
እነዚህም በዮጻዴቅ ልጅ፣ በየሆሹዋ ልጅ በዮአቂም ዘመን እንዲሁም በገዢው በነህምያና የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ በሆነው በካህኑ ዕዝራ ዘመን አገለገሉ። |
የኢየሩሳሌም ቅጥሮች በሚመረቁበት ጊዜ የምረቃውን በዓል በምስጋና መዝሙር፣ በሲምባል፣ በባለ አውታር መሣሪያዎችና በበገና በደስታ እንዲያከብሩ ሌዋውያኑን ከሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም አመጧቸው። |
የዘማሪዎቹ ወንዶች ልጆችም ከአውራጃው፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉት ቦታዎች ሁሉና ነጦፋውያን ከሰፈሩባቸው መንደሮች ተሰበሰቡ፤ |
እንዲሁም ከቤትጊልጋል፣ ከጌባ የእርሻ ቦታዎችና ከአዝማዌት ተሰበሰቡ፤ ምክንያቱም ዘማሪዎቹ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ለራሳቸው የሰፈራ መንደሮችን መሥርተው ነበር። |
ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡን፣ በሮቹንና ቅጥሩንም አነጹ። |
ከዚያም የይሁዳን መኳንንት አምጥቼ በቅጥሩ አናት ላይ እንዲቆሙ አደረግኩ። በተጨማሪም ምስጋና የሚያቀርቡ ሁለት ትላልቅ የዘማሪ ቡድኖችን እንዲሁም እነሱን የሚያጅቡ ቡድኖችን መደብኩ፤ አንደኛው ቡድን በስተ ቀኝ በኩል በቅጥሩ አናት ላይ ወደ አመድ ቁልል በር ሄደ። |
ሆሻያህ እና ከይሁዳ መኳንንት ግማሾቹ ከኋላ ተከተሏቸው፤ |
ከእነሱም ጋር አዛርያስ፣ ዕዝራ፣ መሹላም፣ |
ይሁዳ፣ ቢንያም፣ ሸማያህ እና ኤርምያስ ነበሩ። |
መለከት ከሚነፉት ካህናት ወንዶች ልጆች መካከል የተወሰኑት አብረዋቸው ነበሩ፤ እነሱም የአሳፍ ልጅ፣ የዛኩር ልጅ፣ የሚካያህ ልጅ፣ የማታንያህ ልጅ፣ የሸማያህ ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ |
እንዲሁም ወንድሞቹ ሸማያህ፣ አዛርዔል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ ማአይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳ እና ሃናኒ ናቸው፤ እነሱም የእውነተኛውን አምላክ ሰው የዳዊትን የሙዚቃ መሣሪያዎች ይዘው ነበር፤ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ የሆነው ዕዝራም ከፊታቸው ይሄድ ነበር። |
ከዚያም፣ ምንጭ በር ጋ ሲደርሱ ሽቅብ የሚወጣውን ቅጥር ይዘው ፊት ለፊት ቀጥ ብለው በመሄድ በዳዊት ከተማ ደረጃ ላይ አልፈው ከዳዊት ቤት በላይ ወዳለው ስፍራና በስተ ምሥራቅ ወዳለው ወደ ውኃ በር አቀኑ። |
ምስጋና የሚያቀርበው ሌላኛው የዘማሪዎች ቡድን ደግሞ በተቃራኒ አቅጣጫ ሄደ፤ እኔም ከግማሹ ሕዝብ ጋር በመሆን ቡድኑን ተከትዬ በቅጥሩ አናት ላይ በመሄድ የመጋገሪያ ምድጃ ማማን አልፌ ወደ ሰፊ ቅጥር ተጓዝኩ፤ |
ከዚያም በኤፍሬም በርና በአሮጌው ከተማ በር አድርጌ ወደ ዓሣ በር፣ ወደ ሃናንኤል ማማና ወደ መአህ ማማ፣ በኋላም ወደ በግ በር ሄድኩ፤ እነሱም የጠባቂው በር ጋ ሲደርሱ ቆሙ። |
በመጨረሻም ምስጋና የሚያቀርቡት ሁለቱም የዘማሪ ቡድኖች በእውነተኛው አምላክ ቤት ፊት ለፊት ቆሙ፤ እኔም እንዲሁ አደረግኩ፤ በተጨማሪም ከእኔ ጋር የነበሩት ግማሾቹ የበታች ገዢዎች፣ |
ካህናት የሆኑት ኤልያቄም፣ ማአሴያህ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያህ፣ ኤሊዮዔናይ፣ ዘካርያስና ሃናንያህ ከነመለከታቸው |
እንዲሁም ማአሴያህ፣ ሸማያህ፣ አልዓዛር፣ ዑዚ፣ የሆሃናን፣ ማልኪያህ፣ ኤላም እና ኤጼር አብረውኝ ቆሙ። ዘማሪዎቹም በይዝራህያህ መሪነት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ዘመሩ። |
እውነተኛው አምላክ እጅግ እንዲደሰቱ ስላደረጋቸው በዚያን ቀን ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሐሴትም አደረጉ። ሴቶችና ልጆችም ጭምር በጣም ተደሰቱ፤ ስለዚህ የኢየሩሳሌም ደስታ ከሩቅ ይሰማ ነበር። |
በዚያን ቀን መዋጮዎች፣ የእህል በኩራትና አሥራት በሚቀመጡባቸው ግምጃ ቤቶች ላይ ሰዎች ተሾሙ። እነሱም በሕጉ ላይ በታዘዘው መሠረት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሚሰጠውን ድርሻ ከየከተሞቹ እርሻዎች እየሰበሰቡ ወደዚያ ማስገባት ነበረባቸው፤ ምክንያቱም በሚያገለግሉት ካህናትና ሌዋውያን የተነሳ በይሁዳ ውስጥ ታላቅ ደስታ ነበር። |
ዘማሪዎቹና በር ጠባቂዎቹ እንዳደረጉት ሁሉ ካህናቱና ሌዋውያኑም አምላካቸው የሚጠብቅባቸውን ግዴታም ሆነ ከመንጻት ጋር በተያያዘ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ዳዊትና ልጁ ሰለሞን በሰጡት መመሪያ መሠረት መወጣት ጀመሩ። |
ጥንት በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ዘማሪዎቹን እንዲሁም ለአምላክ የሚቀርቡትን የውዳሴና የምስጋና መዝሙሮች የሚመሩ ሰዎች ነበሩ። |
እንዲሁም በዘሩባቤል ዘመንና በነህምያ ዘመን እስራኤላውያን በሙሉ ለዘማሪዎቹና ለበር ጠባቂዎቹ በየዕለቱ የሚያስፈልጋቸውን ያህል ድርሻ ይሰጧቸው ነበር። በተጨማሪም ለሌዋውያኑ የሚገባውን ድርሻ ለይተው ያስቀምጡ የነበረ ሲሆን ሌዋውያኑ ደግሞ ለአሮን ዘሮች የሚገባውን ድርሻ ለይተው ያስቀምጡ ነበር። |
ሳንባላጥ፣ ጦብያ፣ የዓረብ ተወላጅ የሆነው ጌሼምና የቀሩት ጠላቶቻችን ቅጥሩን መልሼ እንደገነባሁና ክፍተቶቹ ሁሉ እንደተደፈኑ ሲነገራቸው (ምንም እንኳ ገና መዝጊያዎቹን በበሮቹ ላይ ባልገጥማቸውም)፣ |
ሳንባላጥና ጌሼም “እስቲ መጥተህ በኦኖ ሸለቋማ ሜዳ ከሚገኙት መንደሮች በአንዱ ለመገናኘት ቀጠሮ እንያዝ” የሚል መልእክት ወዲያውኑ ላኩብኝ። ሆኖም እኔን ለመጉዳት አሲረው ነበር። |
በመሆኑም “ትልቅ ሥራ እየሠራሁ ስለሆነ ወደዚያ መውረድ አልችልም። ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ምክንያት ለምን ሥራው ይስተጓጎል?” ብለው እንዲነግሯቸው መልእክተኞችን ላክሁባቸው። |
እነሱም ያንኑ መልእክት አራት ጊዜ ላኩብኝ፤ እኔም በላኩብኝ ቁጥር ይህንኑ መልስ መለስኩላቸው። |
ከዚያም ሳንባላጥ አገልጋዩን ያልታሸገ ደብዳቤ በእጁ አስይዞ ለአምስተኛ ጊዜ ያንኑ መልእክት ላከብኝ። |
ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፦ “አንተም ሆንክ አይሁዳውያኑ ለማመፅ እያሴራችሁ መሆኑን ብሔራት ሁሉ ሰምተዋል፤ ጌሼምም ይህንኑ እየተናገረ ነው። ቅጥሩንም እየገነባህ ያለኸው ለዚሁ ነው፤ እንደተባለው ከሆነ ደግሞ ንጉሣቸው ልትሆን ነው። |
በተጨማሪም በመላው ኢየሩሳሌም ‘በይሁዳ ንጉሥ አለ!’ ብለው ስለ አንተ እንዲያውጁ ነቢያትን ሾመሃል። እነዚህ ነገሮች ደግሞ ንጉሡ ጆሮ መድረሳቸው አይቀርም። ስለሆነም መጥተህ በጉዳዩ ላይ ብንነጋገር ይሻላል።” |
እኔ ግን እንዲህ ስል መለስኩለት፦ “ከተናገርከው ነገር መካከል አንዱም አልተፈጸመም፤ ሁሉም ነገር አንተ ራስህ በአእምሮህ የፈጠርከው ነው።” |
ምክንያቱም ሁሉም “እጃቸው ስለሚዝል ሥራው እንደሆነ አይጠናቀቅም” በማለት ሊያስፈራሩን ይሞክሩ ነበር። በዚህ ጊዜ እጆቼን አበርታልኝ ብዬ ጸለይኩ። |
ከዚያም የመሄጣቤል ልጅ ወደሆነው ወደ ደላያህ ልጅ ወደ ሸማያህ ቤት ሄድኩ፤ እሱም ቤቱ ውስጥ ነበር። እንዲህም አለኝ፦ “ሊገድሉህ ስለሚመጡ በእውነተኛው አምላክ ቤት ይኸውም ቤተ መቅደሱ ውስጥ መቼ እንደምንገናኝ እንቀጣጠር፤ የቤተ መቅደሱንም በሮች እንዝጋ። አንተን ለመግደል በሌሊት ይመጣሉ።” |
እኔ ግን “እንደ እኔ ያለ ሰው መሸሽ ይገባዋል? ደግሞስ እንደ እኔ ያለ ሰው ቤተ መቅደሱ ውስጥ ገብቶ በሕይወት ሊኖር ይችላል? በፍጹም አልገባም!” አልኩት። |
ከዚያም ይህን ሰው አምላክ እንዳላከው ከዚህ ይልቅ ጦብያና ሳንባላጥ በእኔ ላይ ይህን ትንቢት እንዲናገር እንደቀጠሩት ተገነዘብኩ። |
ይህን ሰው የቀጠሩት አስፈራርቶ ኃጢአት እንድሠራ እንዲያደርገኝና በዚህም የተነሳ ስሜን የሚያጠፉበት ምክንያት በማግኘት ሊሳለቁብኝ ፈልገው ነው። |
አምላኬ ሆይ፣ ጦብያና ሳንባላጥ የሚያደርጉትን ይህን ነገር እንዲሁም እኔን ለማስፈራራት ተደጋጋሚ ሙከራ የሚያደርጉትን ነቢዪቱ ኖአድያህንና ሌሎቹን ነቢያት አስብ። |
ቅጥሩም በኤሉል ወር በ25ኛው ቀን በ52 ቀናት ውስጥ ተሠርቶ ተጠናቀቀ። |
ጠላቶቻችን በሙሉ ይህን ሲሰሙና በዙሪያችን ያሉት ብሔራትም ይህን ሲያዩ በኀፍረት ተዋጡ፤ ይህ ሥራ የተከናወነው በአምላካችን እርዳታ እንደሆነም ተገነዘቡ። |
በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ የተከበሩ ሰዎች ለጦብያ ብዙ ደብዳቤዎችን ይልኩለት የነበረ ሲሆን እሱም መልስ ይጽፍላቸው ነበር። |
ጦብያ የኤራ ልጅ የሸካንያህ አማች ስለነበርና ልጁ የሆሃናን ደግሞ የቤራክያህን ልጅ የመሹላምን ሴት ልጅ ስላገባ በይሁዳ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በታማኝነት ከጎኑ እንደሚቆሙ ምለውለት ነበር። |
በተጨማሪም ዘወትር ስለ እሱ መልካም ነገሮችን ይነግሩኝ የነበረ ከመሆኑም ሌላ እኔ የምለውንም ለእሱ ያወሩለት ነበር። ጦብያም እኔን ለማስፈራራት ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር። |
ሕዝቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ከውኃ በር ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ተሰበሰቡ፤ ከዚያም የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ የሆነው ዕዝራ ይሖዋ ለእስራኤል የሰጠውን ትእዛዝ የያዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣላቸው ጠየቁት። |
በመሆኑም ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ ወንዶችን፣ ሴቶችንና የሚነገረውን ነገር ሰምተው ማስተዋል የሚችሉትን ሁሉ ወዳቀፈው ጉባኤ ሕጉን አመጣ። |
እሱም ከውኃ በር ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ በተሰበሰቡት ወንዶች፣ ሴቶችና ሰምተው ማስተዋል በሚችሉ ሁሉ ፊት ድምፁን ከፍ አድርጎ ከማለዳ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ሕጉን አነበበ፤ ሕዝቡም የሕጉ መጽሐፍ ሲነበብ በትኩረት አዳመጡ። |
የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ የሆነው ዕዝራ ለዝግጅቱ ተብሎ በተሠራው የእንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ ከጎኑም በስተ ቀኝ በኩል ማቲትያህ፣ ሼማ፣ አናያ፣ ኦርዮ፣ ኬልቅያስ እና ማአሴያህ ቆመው ነበር፤ በስተ ግራው ደግሞ ፐዳያህ፣ ሚሳኤል፣ ማልኪያህ፣ ሃሹም፣ ሃሽባዳናህ፣ ዘካርያስ እና መሹላም ቆመው ነበር። |
ዕዝራ ከሕዝቡ ሁሉ ከፍ ብሎ ቆሞ ስለነበር ሁሉም እያዩት በፊታቸው መጽሐፉን ከፈተ። መጽሐፉንም ሲከፍት ሕዝቡ ሁሉ ተነስቶ ቆመ። |
ከዚያም ዕዝራ ታላቁንና እውነተኛውን አምላክ ይሖዋን አመሰገነ፤ በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “አሜን! አሜን!” በማለት መለሰ፤ ሁሉም እጃቸውን ወደ ላይ ዘረጉ፤ መሬት ላይ በግንባራቸው ተደፍተውም ለይሖዋ ሰገዱ። |
ሌዋውያን የሆኑት የሹዋ፣ ባኒ፣ ሸረበያህ፣ ያሚን፣ አቁብ፣ ሻበታይ፣ ሆዲያህ፣ ማአሴያህ፣ ቀሊጣ፣ አዛርያስ፣ ዮዛባድ፣ ሃናን እና ፐላያህ ደግሞ ሕዝቡ እዚያው ቆሞ ሳለ ሕጉን ለሕዝቡ ያብራሩ ነበር። |
እነሱም ከመጽሐፉ ይኸውም ከእውነተኛው አምላክ ሕግ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በማንበብ ሕጉን በግልጽ ያብራሩና ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይናገሩ ነበር፤ በዚህ መንገድ የተነበበውን ነገር ማስተዋል እንዲችል ሕዝቡን ይረዱት ነበር። |
በወቅቱ ገዢ የነበረው ነህምያ፣ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ የሆነው ካህኑ ዕዝራና ሕዝቡን ያስተምሩ የነበሩት ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ “ይህ ቀን ለአምላካችሁ ለይሖዋ ቅዱስ ቀን ነው። አትዘኑ ወይም አታልቅሱ” አሉ። ይህን ያሉት ሕዝቡ ሁሉ የሕጉ ቃል ሲነበብ በሚሰማበት ጊዜ ያለቅስ ስለነበር ነው። |
እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሂዱ፤ ምርጥ የሆኑትን ነገሮች ብሉ፤ ጣፋጩንም ጠጡ፤ ምንም የተዘጋጀ ነገር ለሌላቸውም ምግብ ላኩላቸው፤ ይህ ቀን ለጌታችን ቅዱስ ነውና፤ የይሖዋ ደስታ ምሽጋችሁ ስለሆነ አትዘኑ።” |
ሌዋውያኑም “ይህ ቀን ቅዱስ ስለሆነ ዝም በሉ! አትዘኑ” በማለት ሕዝቡን ያረጋጉ ነበር። |
በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ ሊበላ፣ ሊጠጣ፣ ምግቡን ለሌሎች ሊያካፍልና ሊደሰት ሄደ፤ ምክንያቱም የተነገራቸውን ቃል ተረድተውት ነበር። |
በሁለተኛውም ቀን የሕዝቡ ሁሉ የአባቶች ቤት መሪዎች፣ ካህናቱና ሌዋውያኑ የሕጉን ቃል ይበልጥ በጥልቀት ለማስተዋል የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ በሆነው በዕዝራ ዙሪያ ተሰበሰቡ። |
ከዚያም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት ባዘዘው ሕግ ውስጥ እስራኤላውያን በሰባተኛው ወር በሚከበረው በዓል ወቅት ዳስ ውስጥ መቀመጥ እንዳለባቸው የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ አገኙ፤ |
እንዲሁም “ወደ ተራራማው አካባቢ ውጡና በተጻፈው መሠረት ዳሶችን ለመሥራት ከወይራ ዛፍ፣ ከዘይት ዛፍ፣ ከአደስ ዛፍ፣ ከዘንባባና ከሌሎች ዛፎች ቅጠል ያላቸውን ቅርንጫፎች አምጡ” የሚል አዋጅ በከተሞቻቸው በሙሉና በመላው ኢየሩሳሌም ማወጅ እንዳለባቸው የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ አገኙ። |
ስለዚህ ሕዝቡ ወጥቶ እነዚህን ቅጠሎች በማምጣት እያንዳንዱ ሰው በቤቱ ጣሪያ ላይ እንዲሁም በግቢውና በእውነተኛው አምላክ ቤት ግቢ ውስጥ፣ በውኃ በር አደባባይና በኤፍሬም በር አደባባይ ለራሱ ዳሶች ሠራ። |
በዚህም መንገድ ከምርኮ የተመለሱትን ሰዎች ያቀፈው መላው ጉባኤ ዳሶችን ሠራ፤ በዳሶቹም ውስጥ ተቀመጠ፤ እስራኤላውያን ከነዌ ልጅ ከኢያሱ ዘመን ጀምሮ እስከዚያ ቀን ድረስ በዓሉን በዚህ መንገድ አክብረው አያውቁም ነበር፤ ስለሆነም ደስታቸው ታላቅ ሆነ። |
የእውነተኛው አምላክ ሕግ መጽሐፍም ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ በየዕለቱ ይነበብ ነበር። እነሱም በዓሉን ለሰባት ቀን አከበሩ፤ በደንቡ መሠረትም በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ተደረገ። |
ከሕንድ አንስቶ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ባሉ 127 አውራጃዎች ይገዛ በነበረው በአሐሽዌሮስ ዘመን |
ይኸውም ንጉሥ አሐሽዌሮስ በሹሻን ግንብ በሚገኘው ንጉሣዊ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛ በነበረበት ጊዜ፣ |
በግዛት ዘመኑ ሦስተኛ ዓመት ላይ ለመኳንንቱና ለአገልጋዮቹ በሙሉ ግብዣ አደረገ። የፋርስና የሜዶን ሠራዊት፣ ታላላቆቹ ሰዎችና የየአውራጃዎቹ መኳንንት በፊቱ ነበሩ፤ |
እሱም የክብራማ መንግሥቱን ብልጽግና እንዲሁም የግርማውን ታላቅነትና ውበት ለብዙ ቀናት ይኸውም ለ180 ቀናት ሲያሳያቸው ቆየ። |
እነዚህ ቀናት ሲያበቁ ንጉሡ ትልቅ ትንሽ ሳይባል በሹሻን ግንብ ለተገኘው ሕዝብ ሁሉ በንጉሡ ቤተ መንግሥት የአትክልት ስፍራ ባለው ግቢ ለሰባት ቀን ታላቅ ግብዣ አደረገ። |
በዚያም ከበፍታ፣ ከጥሩ ጥጥና ከሰማያዊ ጨርቅ የተሠሩ መጋረጃዎች፣ ከፍተኛ ጥራት ካለው ክርና ከሐምራዊ ሱፍ በተሠሩ ገመዶች፣ በእብነ በረድ ዓምዶቹ ላይ በነበሩት የብር ቀለበቶች ላይ ታስረው ነበር፤ ነጭ ነጠብጣብ ያለው ቀይ ድንጋይ፣ ነጭ እብነ በረድ፣ ዕንቁና ጥቁር እብነ በረድ በተነጠፈበት መሬት ላይ ደግሞ ከወርቅና ከብር የተሠሩ ድንክ አልጋዎች ነበሩ። |
የወይን ጠጅ በወርቅ ጽዋዎች ቀርቦ ነበር፤ ጽዋዎቹም አንዳቸው ከሌላው የተለዩ ናቸው፤ ከንጉሡም ብልጽግና የተነሳ የቤተ መንግሥቱ የወይን ጠጅ በገፍ ቀርቦ ነበር። |
የመጠጡ ዝግጅት የተደረገው ማንም ጫና እንዳይደረግበት ከሚያዘው ደንብ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ነበር፤ ንጉሡ እያንዳንዱ ሰው ደስ ያሰኘውን ማድረግ እንዲችል ለቤተ መንግሥቱ ባለሥልጣናት መመሪያ አስተላልፎ ነበርና። |
ንግሥት አስጢንም በንጉሥ አሐሽዌሮስ ንጉሣዊ ቤት ውስጥ ለሴቶቹ ታላቅ ግብዣ አድርጋ ነበር። |
በሰባተኛው ቀን ንጉሥ አሐሽዌሮስ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ደስ በተሰኘ ጊዜ የቅርብ አገልጋዮቹ ለነበሩት ሰባት የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ማለትም ለሜሁማን፣ ለቢዝታ፣ ለሃርቦና፣ ለቢግታ፣ ለአባግታ፣ ለዜታር እና ለካርካስ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.