text stringlengths 4 267 |
|---|
እሱ ገና እየተናገረ ሳለ ሌላው መጥቶ እንዲህ አለ፦ “ከለዳውያን በሦስት ቡድን መጥተው በድንገት ጥቃት በመሰንዘር ግመሎቹን ወሰዱ፤ አገልጋዮቹንም በሰይፍ ገደሉ። እኔም ብቻዬን አምልጬ ልነግርህ መጣሁ።” |
እሱ ገና እየተናገረ ሳለ ሌላው ደግሞ መጥቶ እንዲህ አለ፦ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት እየበሉና የወይን ጠጅ እየጠጡ ነበር። |
በድንገት ከምድረ በዳው ኃይለኛ ነፋስ መጥቶ የቤቱን አራት ማዕዘናት መታ፤ ቤቱም በልጆችህ ላይ ወድቆ ገደላቸው። እኔም ብቻዬን አምልጬ ልነግርህ መጣሁ።” |
በዚህ ጊዜ ኢዮብ ተነስቶ ልብሱን ቀደደ፤ ፀጉሩንም ተላጨ፤ ከዚያም መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ፤ |
እንዲህም አለ፦ “ከእናቴ ማህፀን ራቁቴን ወጣሁ፤ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ። ይሖዋ ሰጠ፤ ይሖዋ ነሳ። የይሖዋ ስም ምንጊዜም ይወደስ።” |
ኢዮብ ይህ ሁሉ ቢደርስበትም ኃጢአት አልሠራም ወይም አምላክን በደል ሠርቷል ብሎ አልወነጀለም። |
ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፦ |
“አምላክን ወክዬ ገና የምናገረው ነገር ስላለጉዳዩን በማብራራበት ጊዜ ትንሽ ታገሠኝ። |
ስለማውቀው ነገር በሰፊው እናገራለሁ፤ፈጣሪዬ ጻድቅ እንደሆነም አስታውቃለሁ። |
በእርግጥ የምናገረው ቃል ውሸት አይደለም፤እውቀቱ ፍጹም የሆነው አምላክ በፊትህ ነው። |
በእርግጥ አምላክ ኃያል ነው፤ ደግሞም ማንንም ገሸሽ አያደርግም፤የማስተዋል ችሎታው ታላቅ ነው። |
የክፉዎችን ሕይወት አይጠብቅም፤ጎስቋላው ግን ፍትሕ እንዲያገኝ ያደርጋል። |
ዓይኖቹን ከጻድቃን ላይ አያነሳም፤ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ እነሱም ለዘላለም ከፍ ከፍ ይላሉ። |
ይሁንና ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣ |
ከመታበያቸው የተነሳ ስለፈጸሙት ድርጊትይኸውም ስለ በደላቸው ይነግራቸዋል። |
እርማት እንዲቀበሉ ጆሯቸውን ይከፍታል፤ከክፋትም እንዲመለሱ ይነግራቸዋል። |
ቢታዘዙትና ቢያገለግሉት፣የሕይወት ዘመናቸውን በብልጽግና ይፈጽማሉ፤ሕይወታቸውም አስደሳች ይሆናል። |
ባይታዘዙ ግን በሰይፍ ይጠፋሉ፤ያለእውቀትም ይሞታሉ። |
በልባቸው አምላክ የለሽ የሆኑ ቂም ይይዛሉ። እሱ በሚያስራቸው ጊዜም እንኳ እርዳታ ለማግኘት አይጮኹም። |
ገና ወጣት እያሉ ይሞታሉ፤በቤተ መቅደስ ቀላጮች መካከል ሕይወታቸውን ያሳልፋሉ። |
ሆኖም አምላክ የተጎሳቆሉ ሰዎችን ከጉስቁልናቸው ይታደጋቸዋል፤ጭቆና በሚደርስባቸው ጊዜ ጆሯቸውን ይከፍታል። |
እሱ ከመከራ መንጋጋ አስጥሎየሚያጨናንቅ ነገር ወደሌለበት ሰፊ ስፍራ ያመጣሃል፤ማዕድህ ምርጥ በሆነ ምግብ የተሞላ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ ያጽናናሃል። |
ፍርድ ሲበየንና ፍትሕ ሲሰፍን፣በክፉዎች ላይ በሚፈጸመው ፍርድ ትረካለህ። |
ይሁንና ቁጣ ወደ ክፋት እንዳይመራህ ተጠንቀቅ፤ጠቀም ያለ ጉቦም አያስትህ። |
እርዳታ ለማግኘት መጮኽህ፣ወይም የምታደርገው ማንኛውም ብርቱ ጥረት ከጭንቀት ነፃ ያደርግሃል? |
ሰዎች ካሉበት ስፍራ የሚጠፉበትንየሌሊቱን ጊዜ አትናፍቅ። |
ከጉስቁልና ይልቅ ይህን መርጠህ፣ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ። |
እነሆ፣ አምላክ በኃይሉ ከፍ ከፍ ብሏል፤እንደ እሱ ያለ አስተማሪ ማን ነው? |
እሱን መንገድ የመራው፣ወይም ‘የሠራኸው ነገር ትክክል አይደለም’ ያለው ማን ነው? |
ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣የእሱን ሥራ ከፍ ከፍ ማድረግ አትዘንጋ። |
የሰው ልጆች ሁሉ አይተውታል፤ሟች የሆነ ሰው ከሩቅ ያያል። |
አዎ፣ አምላክ እኛ ልናውቀው ከምንችለው በላይ ታላቅ ነው፤የዘመኑም ቁጥር ከመረዳት ችሎታ በላይ ነው። |
እሱ የውኃ ጠብታዎችን ወደ ላይ ይስባል፤ጭጋጉም ወደ ዝናብነት ይለወጣል፤ |
ከዚያም ደመናት ያዘንባሉ፤በሰው ልጆችም ላይ ዶፍ ያወርዳሉ። |
የደመናትን ንብርብር፣ከድንኳኑም የሚሰማውን ነጎድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል? |
መብረቁን በላዩ ላይ እንዴት እንደሚዘረጋ፣የባሕሩንም ወለል እንዴት እንደሚሸፍን ተመልከት። |
በእነዚህም ሕዝቦችን ያኖራልምግብ አትረፍርፎ ይሰጣቸዋል። |
በእጆቹ መብረቁን ይሸፍናል፤ወደ ዒላማውም ይሰደዋል። |
ነጎድጓዱ ስለ እሱ ይናገራል፤ከብቶች እንኳ ሳይቀሩ ማን እየመጣ እንዳለ ይጠቁማሉ። |
“በምድር ላይ ያለ ሟች የሆነ ሰው ሕይወት፣ እንደ ግዳጅ አገልግሎት አይደለም?የሕይወት ዘመኑስ እንደ ቅጥር ሠራተኛ ዘመን አይደለም? |
እንደ ባሪያ፣ ጥላ ለማግኘት ይመኛል፤እንደ ቅጥር ሠራተኛም ደሞዙን ለመቀበል በጉጉት ይጠባበቃል። |
እኔም ከንቱ የሆኑ ወራት ተመድበውልኛል፤በሥቃይ የተሞሉ ሌሊቶችም ተወስነውልኛል። |
በተኛሁ ጊዜ ‘የምነሳው መቼ ነው?’ እላለሁ። ሌሊቱም ሲረዝም ጎህ እስኪቀድ ድረስ ያለእረፍት እገላበጣለሁ። |
ሥጋዬ ትልና የአፈር ጓል ለብሷል፤ቆዳዬ በሙሉ አፈክፍኳል፤ ደግሞም መግል ይዟል። |
ዘመኔ ከሸማኔ መወርወሪያ ይበልጥ በፍጥነት ያልፋል፤ያላንዳች ተስፋም ወደ ፍጻሜ ይደርሳል። |
ሕይወቴ ነፋስ እንደሆነ፣ዓይኔም ዳግመኛ ደስታ እንደማያይ አስታውስ። |
አሁን የሚያየኝ ዓይን ከእንግዲህ አያየኝም፤ዓይኖችህ እኔን ይፈልጋሉ፤ እኔ ግን አልኖርም። |
እንደሚበተንና እንደሚጠፋ ደመና፣ወደ መቃብር የሚወርድም ተመልሶ አይወጣም። |
ዳግመኛ ወደ ቤቱ አይመለስም፤ስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ አያውቀውም። |
ስለዚህ እኔ ከመናገር ወደኋላ አልልም። ከመንፈሴ ጭንቀት የተነሳ እናገራለሁ፤በከባድ ምሬት እሮሮ አሰማለሁ! |
በእኔ ላይ ጠባቂ የምታቆመው፣እኔ ባሕር ነኝ ወይስ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት? |
‘መኝታዬ ያጽናናኛል፣አልጋዬ ሥቃዬን ያቀልልኛል’ ባልኩ ጊዜ፣ |
አንተ በሕልም ታሸብረኛለህ፤በራእይም ታስፈራራኛለህ፤ |
ስለዚህ እኔ መታፈንን፣አዎ፣ ከሰውነቴም ይልቅ ሞትን መረጥኩ። |
ሕይወቴን ተጸየፍኳት፤ በሕይወት መቀጠል አልፈልግም። ዘመኔ እንደ እስትንፋስ ስለሆነ ተወት አድርገኝ። |
ታስበው ዘንድ፣ትኩረት ትሰጠውም ዘንድ ሟች የሆነ ሰው ምንድን ነው? |
በየማለዳው የምትመረምረው፣በየጊዜውም የምትፈትነው ለምንድን ነው? |
ዓይንህን ከእኔ ላይ አታነሳም?ምራቄን እስክውጥስ ድረስ ፋታ አትሰጠኝም? |
የሰውን ልጅ የምትከታተል ሆይ፣ ኃጢአት ብሠራ እንኳ አንተን እንዴት ልጎዳህ እችላለሁ? ዒላማህ ያደረግከኝ ለምንድን ነው? ሸክም ሆኜብሃለሁ? |
መተላለፌን ይቅር የማትለው፣በደሌንም በምሕረት የማታልፈው ለምንድን ነው? ከጥቂት ጊዜ በኋላ አፈር ውስጥ እጋደማለሁና፤አንተም ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን አልገኝም።” |
ሹሃዊው በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ |
“የመግዛት ሥልጣንና አስፈሪ ኃይል የእሱ ነው፤በሰማይ ሰላምን ያሰፍናል። |
የሠራዊቱ ብዛት ሊቆጠር ይችላል? የእሱ ብርሃን የማያበራበት ማን አለ? |
ታዲያ ሟች የሆነ ሰው በአምላክ ፊት እንዴት ጻድቅ ሊሆን ይችላል?ወይስ ከሴት የተወለደ ሰው እንዴት ንጹሕ ሊሆን ይችላል? |
ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለችም፤ከዋክብትም በእሱ ፊት ንጹሕ አይደሉም፤ |
እጭ የሆነው ሟች የሰው ልጅ፣ትል የሆነው ሰውማ ምንኛ የባሰ ይሆን!” |
“አዎ፣ ዓይኔ ይህን ሁሉ አይታለች፤ጆሮዬም ሰምታ አስተውላለች። |
እናንተ የምታውቁትን እኔም አውቃለሁ፤ከእናንተ አላንስም። |
እኔ በበኩሌ ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራሱን ባነጋግር እመርጣለሁ፤ከአምላክ ጋር መሟገት እፈልጋለሁ። |
እናንተ ግን በውሸት ስሜን እያጠፋችሁ ነው፤ሁላችሁም የማትረቡ ሐኪሞች ናችሁ። |
ምነው ዝም ብትሉ!ጥበበኛ መሆናችሁ በዚህ ይታወቅ ነበር። |
እስቲ የመከራከሪያ ሐሳቤን ስሙ፤የከንፈሬንም አቤቱታ አዳምጡ። |
ከአምላክ ጎን ቆማችሁ አግባብ ያልሆነ ነገር ታወራላችሁ?ለእሱ ብላችሁስ የማታለያ ቃል ትናገራላችሁ? |
ከእሱ ጎን ትቆማላችሁ?ወይስ ለእውነተኛው አምላክ ትሟገታላችሁ? |
እሱ ቢመረምራችሁ መልካም ይሆንላችኋል? ሟች የሆነውን ሰው እንደምታሞኙ እሱን ታሞኛላችሁ? |
በስውር አድልዎ ለማድረግ ብትሞክሩ፣እሱ በእርግጥ ይገሥጻችኋል። |
ክብሩ ሽብር አይለቅባችሁም?የእሱ ፍርሃትስ አይወድቅባችሁም? |
ጥበብ የተንጸባረቀባቸው አባባሎቻችሁ ከንቱ ምሳሌዎች ናቸው፤መከላከያዎቻችሁ ከሸክላ እንደተሠሩ ጋሻዎች ተሰባሪ ናቸው። |
እኔ እንድናገር በፊቴ ዝም በሉ። ከዚያ በኋላ የመጣው ይምጣብኝ! |
ራሴን ለምን ለአደጋ አጋልጣለሁ?ሕይወቴንስ ለምን በእጄ እይዛለሁ? |
ቢገድለኝ እንኳ እሱን በተስፋ እጠባበቃለሁ፤በፊቱ ጉዳዬን አቅርቤ እከራከራለሁ። |
በዚህ ጊዜ እሱ አዳኜ ይሆናል፤አምላክ የለሽ ሰው ፈጽሞ ፊቱ አይቀርብምና። |
ቃሌን በጥሞና ስሙ፤የምናገረውንም ነገር ልብ ብላችሁ አድምጡ። |
እንግዲህ ሙግቴን አዘጋጅቻለሁ፤ትክክል እንደሆንኩ አውቃለሁ። |
ከእኔ ጋር የሚሟገት ማን ነው? ዝም ብል እሞታለሁ! |
አምላክ ሆይ፣ ከአንተ ሁለት ነገሮች ብቻ እሻለሁ፤በዚያን ጊዜ ራሴን ከፊትህ አልሰውርም፦ |
ከባዱን እጅህን ከእኔ አርቅ፤አስፈሪነትህም አያስደንግጠኝ። |
ጥራኝና ልመልስልህ፤አለዚያ እኔ ልናገር፤ አንተም መልስ ስጠኝ። |
የሠራሁት በደልና ኃጢአት ምንድን ነው? መተላለፌንና ኃጢአቴን አሳውቀኝ። |
ፊትህን የምትሰውረውናእንደ ጠላትህ የምትቆጥረኝ ለምንድን ነው? |
ነፋስ የወሰደውን ቅጠል ለማስፈራራት ትሞክራለህ?ወይስ የደረቀውን ገለባ ታሳድዳለህ? |
ከባድ ክሶችን ትመዘግብብኛለህ፤በወጣትነቴ ለሠራኋቸው ኃጢአቶች መልስ እንድሰጥ ታደርገኛለህ። |
እግሮቼን በእግር ግንድ አስረሃል፤መንገዴን ሁሉ ትመረምራለህ፤ዱካዬንም ሁሉ በዓይነ ቁራኛ ትከታተላለህ። |
በመሆኑም ሰው እንደበሰበሰ ነገር፣ብልም እንደበላው ልብስ እያለቀ ይሄዳል። |
ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ |
“የምናገረውን በጥሞና አዳምጡ፤የምታጽናኑኝ በዚህ ይሁን። |
በምናገርበት ጊዜ በትዕግሥት አዳምጡኝ፤ከተናገርኩ በኋላ ልትሳለቁብኝ ትችላላችሁ። |
ቅሬታዬ በሰው ላይ ነው? ቢሆንማ ኖሮ የእኔ ትዕግሥት አያልቅም ነበር? |
እዩኝ፤ በመገረምም ተመልከቱኝ፤እጃችሁን በአፋችሁ ላይ አድርጉ። |
ስለዚህ ነገር ሳስብ እረበሻለሁ፤መላ ሰውነቴም ይንቀጠቀጣል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.