text stringlengths 4 267 |
|---|
ክፉዎች በሕይወት የሚኖሩት፣ለእርጅና የሚበቁትና ባለጸጋ የሚሆኑት ለምንድን ነው? |
ልጆቻቸው ሁልጊዜ አብረዋቸው ይኖራሉ፤ዘሮቻቸውንም ያያሉ። |
ቤታቸው ሰላም የሰፈነበት ነው፤ የሚያሰጋቸውም ነገር የለም፤አምላክም በበትሩ አይቀጣቸውም። |
ኮርማዎቻቸው ዘር ያፈራሉ፤ላሞቻቸው ይወልዳሉ፤ ደግሞም አይጨነግፉም። |
ወንዶች ልጆቻቸው እንደ መንጋ በደጅ ይሯሯጣሉ፤ልጆቻቸውም ይቦርቃሉ። |
በአታሞና በበገና ታጅበው ይዘፍናሉ፤በዋሽንትም ድምፅ ደስ ይሰኛሉ። |
ዕድሜያቸውን በደስታ ያሳልፋሉ፤በሰላምም ወደ መቃብር ይወርዳሉ። |
ይሁንና እውነተኛውን አምላክ እንዲህ ይሉታል፦ ‘አትድረስብን! መንገዶችህን ማወቅ አንፈልግም። |
እናገለግለው ዘንድ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው? ከእሱ ጋር መተዋወቃችን ምን ይጠቅመናል?’ |
ሆኖም ብልጽግናቸው በእነሱ ቁጥጥር ሥር እንዳልሆነ አውቃለሁ። የክፉዎች ሐሳብ ከእኔ የራቀች ናት። |
የክፉዎች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው? መዓት የደረሰባቸውስ ስንት ጊዜ ነው? አምላክ ተቆጥቶ ጥፋት የላከባቸው ስንት ጊዜ ነው? |
ለመሆኑ በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ፣አውሎ ነፋስም እንደሚወስደው እብቅ ሆነው ያውቃሉ? |
አምላክ አንድ ሰው የሚደርስበትን ቅጣት ለገዛ ልጆቹ ያከማቻል። ይሁንና ሰውየው ያውቀው ዘንድ አምላክ ብድራቱን ይክፈለው። |
የገዛ ዓይኖቹ የሚደርስበትን ጥፋት ይዩ፤ደግሞም ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ቁጣ ይጠጣ። |
የወራቱ ቁጥር ቢያጥር፣እሱ ከሄደ በኋላ በቤቱ ላይ ስለሚደርሰው ነገር ምን ግድ ይሰጠዋል? |
ከፍ ባሉት ላይ እንኳ የሚፈርደው አምላክ ሆኖ ሳለ፣ለእሱ እውቀት ሊሰጠው የሚችል ይኖራል? |
አንድ ሰው ሙሉ ብርታት እያለው፣ተረጋግቶና ያላንዳች ጭንቀት እየኖረ ሳለ ይሞታል፤ |
ጭኑ በስብ ተሞልቶ፣አጥንቶቹም ጠንካራ ሆነው እያለ በሞት ይለያል። |
ሌላው ሰው ግን አንዳች ጥሩ ነገር ሳይቀምስ፣በጭንቀት እንደተዋጠ ይሞታል። |
ሁለቱም በአንድነት አፈር ውስጥ ይጋደማሉ፤ትሎችም ይሸፍኗቸዋል። |
እነሆ፣ እናንተ የምታስቡትን፣እኔንም ለመጉዳት የጠነሰሳችሁትን ሴራ በሚገባ አውቃለሁ። |
እናንተ ‘የተከበረው ሰው ቤት የት አለ?ክፉው ሰው የኖረበት ድንኳንስ የት አለ?’ ትላላችሁና። |
መንገደኞችን አልጠየቃችሁም? እነሱ የሰጧቸውን አስተያየቶችስ በሚገባ አልመረመራችሁም? |
ክፉ ሰው በጥፋት ቀን ይተርፍ የለ?በቁጣስ ቀን ይድን የለ? |
ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው?ለሠራውስ ነገር ብድራቱን የሚከፍለው ማን ነው? |
እሱ ወደ መቃብር ቦታ ሲወሰድ፣መቃብሩ ጥበቃ ይደረግለታል። |
የሸለቆ ጓል ይጣፍጠዋል፤ደግሞም ከእሱ በፊት እንደነበሩት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች ሁሉ፣የሰው ዘር በሙሉ ይከተለዋል። |
ታዲያ ትርጉም የለሽ ማጽናኛ የምትሰጡኝ ለምንድን ነው? የምትሰጡት መልስ ሁሉ ማታለያ ነው!” |
ከዚህ በኋላ ኢዮብ መናገርና የተወለደበትን ቀን መርገም ጀመረ። |
ኢዮብም እንዲህ አለ፦ |
“የተወለድኩበት ቀን፣‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ!’ የተባለበትም ሌሊት ይጥፋ። |
ያ ቀን ጨለማ ይሁን። በላይ ያለው አምላክ አያስበው፤ብርሃንም አይፈንጥቅበት። |
ድቅድቅ ጨለማ ይውረሰው። ጥቁር ደመና ይረፍበት። ቀንን የሚያጨልም ነገር ያሸብረው። |
ያን ሌሊት ጨለማ ይውረሰው፤ከዓመቱ ቀኖች መካከል ያ ሌሊት ደስ አይበለው፤ከወራቱም ቁጥር መካከል አይደመር። |
አዎ፣ ያ ሌሊት መሃን ይሁን!እልልታም አይሰማበት። |
ቀንን የሚረግሙ፣ሌዋታንንም መቀስቀስ የሚችሉ ቀኑን ይርገሙት። |
አጥቢያ ኮከቦቹ ይጨልሙ፤የቀን ብርሃንን ቢጠብቅም አያግኝ፤የንጋትንም ጮራ አይመልከት። |
የእናቴን ማህፀን በሮች አልዘጋምና፤ችግርንም ከዓይኔ አልሰወረም። |
ምነው ስወለድ በሞትኩ! ምነው ከማህፀን ስወጣ በተቀጨሁ! |
የሚቀበሉኝ ጉልበቶች፣የሚያጠቡኝም ጡቶች ለምን ተገኙ? |
ይህን ጊዜ ሳልረበሽ በተጋደምኩ ነበርና፤በተኛሁና እረፍት ባገኘሁ ነበር፤ |
በአሁኑ ጊዜ ፈራርሰው ያሉ ቦታዎችን ለራሳቸው ከገነቡየምድር ነገሥታትና አማካሪዎቻቸው ጋር፣ |
ወይም ቤታቸውን በብር ከሞሉወርቅ ካላቸው መኳንንት ጋር ባረፍኩ ነበር። |
እንደተሰወረ ጭንጋፍ፣ፈጽሞ ብርሃን እንዳላዩ ልጆች ለምን አልሆንኩም? |
በዚያ ክፉዎች እንኳ ከሚረብሽ ነገር ተገላግለዋል፤የዛሉ ሰዎች በዚያ አርፈዋል። |
በዚያ እስረኞች በአንድነት ተረጋግተው ይኖራሉ፤አስገድዶ የሚያሠራቸውን ሰው ድምፅ አይሰሙም። |
በዚያ ትንሹም ሆነ ትልቁ አንድ ናቸው፤ባሪያውም ከጌታው ነፃ ወጥቷል። |
እሱ መከራ ላይ ላለ ሰው ብርሃን፣ለተመረሩ ሰዎችስ ሕይወት ለምን ይሰጣል? |
ሞትን ቢመኙም የማያገኙት ለምንድን ነው? ከተሰወረ ሀብት ይበልጥ ይሹታል፤ |
መቃብር ሲያገኙ ሐሴት ያደርጋሉ፤እጅግም ደስ ይላቸዋል። |
መንገዱ ለጠፋበት፣አምላክም ዙሪያውን ላጠረበት ሰው ለምን ብርሃን ይሰጣል? |
በምግቤ ፋንታ ሲቃ ተናንቆኛልና፤የሥቃይ ጩኸቴ እንደ ውኃ ይፈስሳል። |
የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፤ያሸበረኝም ነገር ደርሶብኛል። |
ሰላምም ሆነ እርጋታ አላገኘሁም፤ እረፍትም አልነበረኝም፤ይልቁንም መከራ አልተለየኝም።” |
“አሁን ግን ከእኔ በዕድሜ የሚያንሱ፣በእኔ ላይ ይስቃሉ፤አባቶቻቸው መንጋዬን ከሚጠብቁ ውሾች ጋር እንዲሆኑፈቃደኛ አልነበርኩም። |
የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምን ይፈይድልኝ ነበር? እነሱ ጉልበት ከድቷቸዋል። |
ከችጋርና ከረሃብ የተነሳ ዝለዋል፤በወደመ እና ወና በሆነ ደረቅ ምድርያገኟትን ነገር ያላምጣሉ። |
በቁጥቋጦዎች አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚል ተክል ይሰበስባሉ፤ምግባቸው የክትክታ ዛፍ ሥር ነው። |
ከማኅበረሰቡ ተባረዋል፤ሰዎችም ሌባ ላይ እንደሚጮኹ ይጮኹባቸዋል። |
በሸለቆዎች ተዳፋት ላይ፣መሬት ላይ ባሉ ጉድጓዶች ውስጥና በዓለቶች መካከል ይኖራሉ። |
ከቁጥቋጦዎች ውስጥ ይጮኻሉ፤በሳማዎችም መካከል ይከማቻሉ። |
ማመዛዘን የጎደላቸውና የአልባሌ ሰዎች ልጆች ናቸው፤ከምድሪቱ ላይ ተባረዋል። |
አሁን ግን በዘፈኖቻቸው ሳይቀር ይሳለቁብኛል፤የእነሱ መሳለቂያ ሆኛለሁ። |
ይጸየፉኛል፤ ከእኔም ርቀዋል፤በፊቴ ከመትፋት ወደኋላ አይሉም። |
ምክንያቱም አምላክ ትጥቅ አስፈትቶኛል፤ ደግሞም አዋርዶኛል፤እነሱ በፊቴ እንዳሻቸው ይሆናሉ። |
በቀኜ በኩል እንደ አድመኛ ተነስተውብኛል፤እንድሸሽ አድርገውኛል፤በመንገዴም ላይ ለጥፋት የሚዳርግ መሰናክል አስቀምጠዋል። |
መንገዶቼን ያፈርሳሉ፤መከራዬንም ያባብሳሉ፤የሚገታቸውም የለም። |
ሰፊ ክፍተት ባለው ቅጥር እንደሚመጣ ሰው መጡ፤በፍርስራሹ መካከል እየገሰገሱ ገቡ። |
በሽብር ተዋጥኩ፤ክብሬ በነፋስ እንደሚወሰድ ተወስዷል፤የመዳን ተስፋዬም እንደ ደመና እልም ብሎ ጠፍቷል። |
አሁን ሕይወቴ ከውስጤ ተሟጠጠች፤የጉስቁልና ዘመን ያዘኝ። |
ከባድ ሕመም በሌሊት አጥንቶቼን ይበሳል፤የሚመዘምዘኝ ሥቃይ እረፍት አይሰጠኝም። |
ልብሴ በታላቅ ኃይል ተበላሸ፤እንደ ልብሴ አንገትጌ አንቆ ያዘኝ። |
አምላክ ጭቃ ውስጥ ጥሎኛል፤አፈርና አመድ ሆንኩ። |
እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትመልስልኝም፤በፊትህ ቆምኩ፤ አንተ ግን ዝም ብለህ ታየኛለህ። |
በጭካኔ በእኔ ላይ ተነሳህ፤በእጅህ ብርታት አጠቃኸኝ። |
ወደ ላይ አንስተህ በነፋስ ወሰድከኝ፤ከዚያም በአውሎ ነፋስ አንገላታኸኝ። |
በሕይወት ያለ ሁሉ ወደሚሰበሰብበት ቤት፣ወደ ሞት እንደምታወርደኝ አውቃለሁና። |
ይሁንና የተሰበረ ሰው አደጋ ደርሶበት ለእርዳታ ሲጮኽ፣እጁን የሚያነሳበት ሰው አይኖርም። |
መከራ ላይ ለወደቁ ሰዎች አላለቀስኩም? ለድሃውስ አላዘንኩም? |
መልካም ነገር በተስፋ ብጠባበቅም ክፉ ነገር ደረሰ፤ብርሃን ብጠባበቅም ጨለማ መጣ። |
ውስጤ ያለማቋረጥ ተናወጠ፤የጉስቁልናም ዘመን መጣብኝ። |
በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ፤ የፀሐይ ብርሃንም የለም። በጉባኤ መካከል ቆሜ እርዳታ ለማግኘት እጮኻለሁ። |
የቀበሮዎች ወንድም፣የሰጎንም ሴቶች ልጆች ባልንጀራ ሆንኩ። |
ቆዳዬ ጠቁሮ ተቀረፈ፤ከሙቀቱ የተነሳ አጥንቶቼ ነደዱ። |
በገናዬ ለሐዘን ብቻ ዋለ፤ዋሽንቴም ለለቅሶ ሆነ። |
ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ |
“እርግጥ ነገሩ እንዲህ መሆኑን አውቃለሁ። ሆኖም ሟች የሆነ ሰው ከአምላክ ጋር ተሟግቶ እንዴት ትክክል ሊሆን ይችላል? |
ሰው ከእሱ ጋር መሟገት ቢፈልግ፣አምላክ ከሚያቀርብለት አንድ ሺህ ጥያቄዎች መካከል ለአንዱ እንኳ መልስ መስጠት አይችልም። |
እሱ ጥበበኛ ልብ አለው፤ ኃይሉም ታላቅ ነው። እሱን ተገዳድሮ ከጉዳት ማምለጥ የሚችል ማን ነው? |
ማንም ሳያውቅ ተራሮችን ከስፍራቸው ይወስዳል፤በቁጣውም ይገለብጣቸዋል። |
ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፤በመሆኑም ምሰሶዎቿ ይንቀጠቀጣሉ። |
ብርሃን እንዳትፈነጥቅ ፀሐይን ያዛታል፤የከዋክብትን ብርሃን ያሽጋል፤ |
ሰማያትንም ብቻውን ይዘረጋል፤ከፍ ባለው የባሕር ማዕበልም ላይ ይራመዳል። |
የአሽ፣ የከሲልና የኪማ ኅብረ ከዋክብትንእንዲሁም የደቡቡን ሰማይ ኅብረ ከዋክብት ሠርቷል፤ |
ታላላቅና የማይመረመሩ ነገሮችን፣ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ድንቅ ነገሮች ያደርጋል። |
በአጠገቤ ያልፋል፤ እኔ ግን ላየው አልችልም፤አልፎኝ ይሄዳል፤ እኔ ግን አለየውም። |
አንዳች ነገር ነጥቆ ሲወስድ ማን ሊከለክለው ይችላል? ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ሊለው የሚችልስ ማን ነው? |
አምላክ ቁጣውን አይገታም፤የረዓብ ረዳቶች እንኳ እግሩ ሥር ይወድቃሉ። |
በመሆኑም ለእሱ መልስ ስሰጥ፣ይልቁንም ከእሱ ጋር ስከራከር አስቤ መናገር ይጠበቅብኛል። |
ትክክል ብሆን እንኳ መልስ አልሰጠውም። ዳኛዬን ምሕረት ከመለመን ሌላ ምንም ማድረግ አልችልም። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.