text stringlengths 4 267 |
|---|
ብጠራው ይመልስልኛል? እኔ እንደሆነ፣ ስናገር ይሰማኛል የሚል እምነት የለኝም፤ |
በአውሎ ነፋስ ያደቀኛልና፤ያለምክንያትም ቁስሌን ያበዛል። |
ለመተንፈስ እንኳ ፋታ አይሰጠኝም፤መራራ ነገሮችን ያጠግበኛል። |
የኃይል ጉዳይ ከሆነ እሱ ኃያል ነው። የፍትሕ ጉዳይ ከተነሳ ‘ማን ሊጠይቀኝ ይችላል?’ ይላል። |
ትክክል ብሆን እንኳ የገዛ አፌ ይፈርድብኛል፤ንጹሕ አቋሜን ብጠብቅ እንኳ እሱ ጥፋተኛ ነህ ይለኛል። |
ንጹሕ አቋሜን ብጠብቅ እንኳ ስለ ራሴ እርግጠኛ አይደለሁም፤ይህን ሕይወቴን እጠላዋለሁ። |
ምንም ለውጥ የለውም። ‘እሱ ንጹሑንም ሆነ ክፉውን ያጠፋል’የምለው ለዚህ ነው። |
ደራሽ ውኃ በድንገት ሰዎችን ቢያጠፋ፣እሱ ንጹሐን ሰዎች በሚደርስባቸው ሥቃይ ያፌዛል። |
ምድር ለክፉዎች ተሰጥታለች፤እሱ የዳኞቿን ዓይኖች ይሸፍናል። ይህን የሚያደርገው እሱ ካልሆነ ታዲያ ማን ነው? |
ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፤መልካም ነገር ሳያይ ፈጥኖ ይነጉዳል። |
ከደንገል እንደተሠሩ ጀልባዎች፣የሚያድኑትንም ነገር ለመያዝ ወደ ታች እንደሚወረወሩ ንስሮች ይከንፋል። |
‘ብሶቴን እረሳለሁ፤የፊቴን ገጽታ ቀይሬ ደስተኛ እሆናለሁ’ ብል እንኳ፣ |
ከሥቃዬ ሁሉ የተነሳ አሁንም ፍርሃት ይሰማኛል፤ንጹሕ ሆኜ እንደማታገኘኝ አውቃለሁ። |
በደለኛ ሆኜ መገኘቴ አይቀርም። ታዲያ ለምን በከንቱ እደክማለሁ? |
ከቀለጠ በረዶ በተገኘ ውኃ ብታጠብ፣እጆቼንም በእንዶድ ባነጻ፣ |
አንተ አዘቅት ውስጥ ትነክረኛለህ፤ከዚህም የተነሳ የገዛ ልብሶቼ እንኳ ይጸየፉኛል። |
መልስ እሰጠው ዘንድ፣ችሎት ፊትም አብረን እንቀርብ ዘንድ እሱ እንደ እኔ ሰው አይደለምና። |
በመካከላችን የሚበይን፣ሊዳኘንም የሚችል ሰው የለም። |
እኔን መምታቱን ቢያቆም፣ሽብርም ባይለቅብኝ፣ |
ያን ጊዜ ያለፍርሃት አናግረዋለሁ፤በፍርሃት የምናገር ሰው አይደለሁምና። |
ከዚያም ይሖዋ ከአውሎ ነፋስ ውስጥ ለኢዮብ መለሰለት፦ |
“ሐሳቤን የሚሰውርናያለእውቀት የሚናገር ይህ ማን ነው? |
እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም ንገረኝ። |
ምድርን በመሠረትኩ ጊዜ አንተ የት ነበርክ? ማስተዋል አለኝ የምትል ከሆነ ንገረኝ። |
የምታውቅ ከሆነ፣ መለኪያዎቿን የወሰነ፣ወይስ መለኪያ ገመድ በላይዋ ላይ የዘረጋ ማን ነው? |
የምድር ምሰሶዎች የተተከሉት ምን ላይ ነው?የማዕዘኗን ድንጋይ ያኖረስ ማን ነው? |
አጥቢያ ከዋክብት በአንድነት እልል ሲሉ፣የአምላክም ልጆች ሁሉ በደስታ ሲጮኹ አንተ የት ነበርክ? |
ባሕሩ ከማህፀን አፈትልኮ በወጣ ጊዜ፣በር የዘጋበት ማን ነው? |
ደመና ባለበስኩት ጊዜ፣በድቅድቅ ጨለማም በጠቀለልኩት ጊዜ፣ |
በላዩም ድንበሬን በወሰንኩ ጊዜ፣መቀርቀሪያዎችና በሮች ባደረግኩለት ጊዜ፣ |
ደግሞም ‘እስከዚህ ድረስ መምጣት ትችላለህ፤ ከዚህ ግን አታልፍም፤የኩሩው ማዕበልህም ገደብ ይህ ነው’ ባልኩ ጊዜ አንተ የት ነበርክ? |
ለመሆኑ ንጋትን አዘህ ታውቃለህ?ወይስ ጎህ ስፍራውን እንዲያውቅ አድርገሃል? |
የማለዳ ብርሃን ወደ ምድር ዳርቻዎች እንዲሄድ፣ክፉዎችንም ከላይዋ እንዲያራግፍ ያዘዝከው አንተ ነህ? |
ምድር ከማኅተም በታች እንዳለ የሸክላ ጭቃ ትለወጣለች፤ገጽታዎቿም እንደሚያምር ልብስ ጎልተው ይታያሉ። |
የክፉዎች ብርሃን ግን ከእነሱ ተወስዷል፤ከፍ ያለው ክንዳቸውም ተሰብሯል። |
ወደ ባሕሩ ምንጮች ወርደሃል?ወይስ ጥልቁን ውኃ መርምረሃል? |
የሞት በሮች ተገልጠውልሃል?የድቅድቅ ጨለማንስ በሮች አይተሃል? |
ምድር ምን ያህል ሰፊ እንደሆነች አስተውለሃል? ይህን ሁሉ የምታውቅ ከሆነ ተናገር። |
ብርሃን የሚኖረው በየት አቅጣጫ ነው? የጨለማ ስፍራስ የት ነው? |
ወደ ክልሉ ልትወስደው ትችላለህ?ወደ ቤቱስ የሚወስደውን ጎዳና ታውቃለህ? |
በዚያን ጊዜ ተወልደህ ስለነበር፣ዕድሜህም ትልቅ ስለሆነ ይህን ሳታውቅ አትቀርም! |
አመዳዩ ወደተከማቸበት መጋዘን ገብተሃል?የበረዶውንስ ግምጃ ቤት አይተሃል? |
ይህም ለመከራ ጊዜ፣ለውጊያና ለጦርነት ቀን ያስቀመጥኩት ነው። |
ብርሃን የሚሰራጨው ከየት አቅጣጫ ነው?የምሥራቅስ ነፋስ በምድር ላይ የሚነፍሰው ከየት ነው? |
ለዶፍ መውረጃን፣ነጎድጓድ ለቀላቀለ ጥቁር ደመናም መንገድን ያዘጋጀ ማን ነው? |
አንድም ሰው በሌለበት ቦታ፣ሰውም በማይኖርበት ምድረ በዳ የሚያዘንበው፣ |
የወደመውን ጠፍ መሬት የሚያረካው፣ሣርንም የሚያበቅለው ማን ነው? |
ዝናብ አባት አለው?ጠልንስ የወለደው ማን ነው? |
በረዶ የሚወጣው ከማን ማህፀን ነው?የሰማዩንስ አመዳይ የወለደው ማን ነው? |
ውኃዎች በድንጋይ የተሸፈኑ ያህል እንዲሆኑ፣የጥልቁ ውኃም ገጽ ግግር በረዶ እንዲሆን የሚያደርገው ማን ነው? |
የኪማ ኅብረ ከዋክብትን ገመድ ልታስር፣ወይስ የከሲል ኅብረ ከዋክብትን ገመድ ልትፈታ ትችላለህ? |
ኅብረ ከዋክብትን በወቅቱ ልታወጣ፣ወይስ የአሽ ኅብረ ከዋክብትን ከነልጆቹ ልትመራ ትችላለህ? |
ሰማያት የሚመሩባቸውን ሕጎች ታውቃለህ?ወይስ የሰማያትን ሕጎች በምድር ላይ ተግባራዊ ማድረግ ትችላለህ? |
ጎርፍ ይሸፍንህ ዘንድ፣ድምፅህን ወደ ደመናት ማንሳት ትችላለህ? |
የመብረቅ ብልጭታዎችን መላክ ትችላለህ? እነሱስ አንተ ጋ ቀርበው ‘ይኸው መጥተናል!’ ይሉሃል? |
በደመናት ውስጥ ጥበብ ያኖረው፣በሰማይ ለሚከናወነውስ ክስተት ማስተዋልን የሰጠው ማን ነው? |
ደመናትን ለመቁጠር የሚያስችል ጥበብ ያለው ማን ነው?ወይስ የሰማይን የውኃ ማሰሮዎች ሊደፋ የሚችል ማን ነው? |
አፈሩ ቦክቶ እንዲጋገር፣የምድር ጓሎችም እንዲጣበቁ ሊያደርግ የሚችል ማን ነው? |
ለአንበሳ አድነህ ግዳይ ልታመጣለት፣ወይስ የተራቡ የአንበሳ ግልገሎችን ልታጠግብ ትችላለህ? |
እነሱ በዋሻቸው ውስጥ አድፍጠው፣ወይም በጎሬአቸው አድብተው ሳለ ይህን ልታደርግ ትችላለህ? |
ጫጩቶቿ ወደ አምላክ ሲጮኹ፣የሚበሉትም አጥተው ሲቅበዘበዙ፣ለቁራ መብል የሚያዘጋጅ ማን ነው? |
“ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ለምን ጊዜ አልወሰነም? እሱን የሚያውቁትስ ቀኑን ለምን አያዩም? |
ሰዎች የወሰን ምልክቶችን ይገፋሉ፤ነጥቀው የወሰዱትን መንጋ በራሳቸው መስክ ላይ ያሰማራሉ። |
አባት የሌላቸውን ልጆች አህያ እየነዱ ይወስዳሉ፤የመበለቲቱንም በሬ መያዣ አድርገው ይወስዳሉ። |
ድሃውን ከመንገድ ያስወጣሉ፤በዚህ ጊዜ የምድሪቱ ምስኪኖች ከእነሱ ለመሸሸግ ይገደዳሉ። |
ድሆች በምድረ በዳ እንዳሉ የዱር አህዮች፣ ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ፤በበረሃ ለልጆቻቸው ምግብ ይፈልጋሉ። |
ከሌላው ሰው እርሻ እህል ለመሰብሰብ ይገደዳሉ፤ከክፉውም ሰው የወይን እርሻ ይቃርማሉ። |
ያለልብስ ራቁታቸውን ያድራሉ፤ብርድ የሚከላከሉበት ልብስ የላቸውም። |
ከተራሮች በሚወርደው ዝናብ ይበሰብሳሉ፤መጠለያ ስለማያገኙ ዓለት ያቅፋሉ። |
አባት የሌለው ልጅ ከእናቱ ጡት ላይ ተነጥቋል፤የድሃውም ልብስ በመያዣነት ተወስዷል፤ |
ያለልብስ ራቁታቸውን ለመሄድ ይገደዳሉ፤ተርበው እያሉም ነዶ ተሸክመው ይሄዳሉ። |
በቀትር ሐሩር በእርከኖቹ መካከል ይለፋሉ፤የወይን መጭመቂያውን እየረገጡ እነሱ ግን ይጠማሉ። |
በሞት አፋፍ ላይ ያሉት በከተማዋ ውስጥ ያጣጥራሉ፤ክፉኛም የቆሰሉት ሰዎች እርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤አምላክ ግን ይህን በቸልታ ያልፋል። |
በብርሃን ላይ የሚያምፁ አሉ፤የብርሃኑን መንገድ አላወቁም፤ጎዳናውንም አልተከተሉም። |
ነፍሰ ገዳዩ ጎህ ሲቀድ ይነሳል፤ምስኪኑንና ድሃውን ይገድላል፤በሌሊትም ይሰርቃል። |
የአመንዝራ ዓይን ድንግዝግዝታን ይጠባበቃል፤‘ማንም አያየኝም!’ ይላል፤ ፊቱንም ይሸፍናል። |
በጨለማ ቤት ሰብረው ይገባሉ፤ቀን ላይ ተሸሽገው ይውላሉ። ለብርሃን እንግዳ ናቸው። |
ለእነሱ ንጋት እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነውና፤ድቅድቅ ጨለማ የሚያስከትለውን ሽብር ያውቁታል። |
ይሁንና ውኃ በፍጥነት ጠርጎ ይወስዳቸዋል። ርስታቸውም የተረገመ ይሆናል። ወደ ወይን እርሻቸው አይመለሱም። |
ድርቁና ሐሩሩ የቀለጠውን በረዶ እንደሚያስወግደው፣መቃብር ኃጢአተኞችን ይነጥቃል! |
እናቱ ትረሳዋለች፤ ትልም ትመጠምጠዋለች። ዳግመኛ አይታወስም። ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል። |
በመሃኒቱ ላይ ያደባል፤መበለቲቱንም ይበድላል። |
አምላክ ኃይሉን ተጠቅሞ ብርቱ ሰዎችን ያጠፋል፤ከፍ ከፍ ቢሉም ሕይወታቸው ዋስትና የለውም። |
አምላክ የመተማመን ስሜት እንዲያድርባቸውና ደህንነት እንዲሰማቸው ይፈቅዳል፤ይሁንና ዓይኑ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ ላይ ነው። |
ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ከዚያም ደብዛቸው ይጠፋል። ዝቅ ዝቅ ይደረጋሉ፤ ደግሞም እንደ ማንኛውም ሰው ይሰበሰባሉ፤እንደ እህል ዛላ ይቆረጣሉ። |
እንግዲህ አሁን እኔን ውሸታም ሊያደርገኝ፣ወይም ቃሌን ሊያስተባብል የሚችል ማን ነው?” |
ኢዮብ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ |
“ፍትሕ በነፈገኝ ሕያው በሆነው አምላክ፣እንድመረር ባደረገኝ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ እምላለሁ፤ |
እስትንፋሴ በውስጤ፣ከአምላክ ያገኘሁትም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ እስካለ ድረስ፣ |
ከንፈሮቼ ክፋት አይናገሩም፤ምላሴም ፈጽሞ የማታለያ ቃል አይወጣውም! |
በእኔ በኩል እናንተን ጻድቅ አድርጎ መቁጠር የማይታሰብ ነገር ነው! እስክሞት ድረስ ንጹሕ አቋሜን አላጎድፍም! |
ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ፤ ደግሞም ፈጽሞ አለቀውም፤በሕይወት ዘመኔም ሁሉ ልቤ አይኮንነኝም። |
ጠላቴ እንደ ክፉ ሰው ይሁን፤እኔን የሚያጠቁኝ ሰዎች እንደ ዓመፀኛ ይሁኑ። |
አምላክ የለሽ የሆነ ሰው ሲጠፋ፣አምላክ ሕይወቱን ሲቀጨው ምን ተስፋ ይኖረዋል? |
መከራ ሲደርስበትአምላክ ጩኸቱን ይሰማዋል? |
ወይስ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ደስ ይሰኛል? ሁልጊዜስ ወደ አምላክ ይጣራል? |
እኔ ስለ አምላክ ኃይል አስተምራችኋለሁ፤ሁሉን ቻይ ስለሆነው አምላክ ምንም የምደብቀው ነገር የለም። |
ሁላችሁም ራእይ ካያችሁ፣ንግግራችሁ ጨርሶ ባዶ የሆነው ለምንድን ነው? |
ክፉ ሰው ከአምላክ የሚያገኘው ድርሻ፣ጨቋኞችም ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ የሚወርሱት ውርሻ ይህ ነው። |
ልጆቹ ቢበዙ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ዘሮቹም በቂ ምግብ አያገኙም። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.