text
stringlengths
4
267
ከእሱ በኋላ የተረፉት ወገኖቹ በመቅሰፍት ይቀበራሉ፤መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።
ብርን እንደ አፈር ቢቆልል፣ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች እንኳ፣
እሱ የሰበሰበውንጻድቁ ሰው ይለብሰዋል፤ብሩንም ንጹሐን ይከፋፈሉታል።
የሚሠራው ቤት ብል እንደሠራው ሽፋን፣ጠባቂም እንደቀለሰው መጠለያ በቀላሉ የሚፈርስ ነው።
ባለጸጋ ሆኖ ይተኛል፤ ሆኖም ምንም የሚሰበስበው ነገር የለም፤ዓይኑን ሲገልጥ በዚያ ምንም ነገር አይኖርም።
ሽብር እንደ ጎርፍ ድንገት ያጥለቀልቀዋል፤አውሎ ነፋስ በሌሊት ይዞት ይሄዳል።
የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፤ እሱም አይገኝም፤ከቦታው ጠርጎ ይወስደዋል።
ከነፋሱ ኃይል ለማምለጥ ሲፍጨረጨር፣ያለርኅራኄ ተወርውሮ ይመጣበታል።
እጁን ያጨበጭብበታል፤ደግሞም ካለበት ቦታ ሆኖ ያፏጭበታል።
የእውነተኛው አምላክ ልጆች፣ በይሖዋ ፊት ለመቆም የሚገቡበት ቀን በደረሰ ጊዜ ሰይጣንም በይሖዋ ፊት ለመቆም እነሱ መካከል ገባ።
ከዚያም ይሖዋ ሰይጣንን “ከየት መጣህ?” አለው። ሰይጣንም “በምድር ሁሉ ላይ ስዞርና በእሷ ላይ ስመላለስ ቆይቼ መጣሁ” ሲል ለይሖዋ መለሰ።
ይሖዋም ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትከው? በምድር ላይ እንደ እሱ ያለ ሰው የለም። በንጹሕ አቋም የሚመላለስ ቅን ሰው እንዲሁም አምላክን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ነው። ያለምንም ምክንያት እንዳጠፋው እኔን ለማነሳሳት ብትሞክርም እንኳ አሁንም በንጹሕ አቋሙ እንደጸና ነው።”
ሆኖም ሰይጣን እንዲህ ሲል ለይሖዋ መለሰ፦ “ቁርበት ስለ ቁርበት ነው። ሰውም ለሕይወቱ ሲል ያለውን ነገር ሁሉ ይሰጣል።
ሆኖም እጅህን ዘርግተህ በአጥንቱና በሥጋው ላይ ጉዳት አድርስበት፤ በእርግጥ ፊት ለፊት ይረግምሃል።”
ከዚያም ይሖዋ ሰይጣንን “እነሆ፣ እሱ በእጅህ ነው! ብቻ ሕይወቱን እንዳታጠፋ!” አለው።
ሰይጣንም ከይሖዋ ፊት ወጥቶ በመሄድ ኢዮብን ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ ድረስ ክፉኛ በሚያሠቃይ እባጭ መታው።
ኢዮብም ገላውን የሚያክበት ገል ወሰደ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ።
በመጨረሻም ሚስቱ “አሁንም በንጹሕ አቋምህ እንደጸናህ ነው? አምላክን እርገምና ሙት!” አለችው።
እሱ ግን እንዲህ አላት፦ “የምትናገሪው ማመዛዘን እንደጎደላት ሴት ነው። ከእውነተኛው አምላክ መቀበል ያለብን መልካም ነገር ብቻ ነው? ክፉውንስ መቀበል የለብንም?” ኢዮብ ይህ ሁሉ ቢደርስበትም በከንፈሩ አልበደለም።
የኢዮብ ሦስት ጓደኞች በእሱ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ ሰምተው እያንዳንዳቸው ከሚኖሩበት ቦታ መጡ፤ ጓደኞቹም ቴማናዊው ኤሊፋዝ፣ ሹሃዊው በልዳዶስ እና ናአማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነሱም አንድ ላይ ተገናኝተው ወደ ኢዮብ በመሄድ እሱን ለማስተዛዘንና ለማጽናናት ተስማሙ።
ከሩቅ ሲመለከቱት እሱ መሆኑን መለየት አቃታቸው። እነሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ማልቀስ ጀመሩ፤ ልብሳቸውንም ቀደዱ፤ እንዲሁም አቧራ ወደ ላይ በተኑ፤ ራሳቸውም ላይ ነሰነሱ።
ከዚያም ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት መሬት ላይ ከእሱ ጋር ተቀመጡ። ሥቃዩ በጣም ከባድ መሆኑን ስለተረዱ ከመካከላቸው አንድም ቃል የተናገረው አልነበረም።
“ሕይወቴን ተጸየፍኳት። አንዳች ሳላስቀር ብሶቴን አሰማለሁ። በታላቅ ምሬት እናገራለሁ!
አምላክን እንዲህ እለዋለሁ፦ ‘በደለኛ ነህ አትበለኝ። ከእኔ ጋር የምትሟገተው ለምን እንደሆነ ንገረኝ።
በክፉዎች ዕቅድ ደስ እየተሰኘህ፣የእጆችህን ሥራ መጨቆንህና መናቅህምን ይጠቅምሃል?
ዓይንህ የሥጋ ለባሽ ዓይን ነው?ወይስ የምታየው ሟች የሆነ ሰው በሚያይበት መንገድ ነው?
ዘመንህ እንደ ሟች ሰዎች ዘመን ነው?ወይስ ዕድሜህ እንደ ሰው ዘመን ነው?
ታዲያ በደልን የምትፈላልግብኝ፣ኃጢአቴንስ የምትከታተለው ለምንድን ነው?
በደለኛ እንዳልሆንኩ ታውቃለህ፤ደግሞም ማንም ከእጅህ ሊያስጥለኝ አይችልም።
የገዛ እጆችህ ቀረጹኝ፤ ደግሞም ሠሩኝ፤አሁን ግን ሙሉ በሙሉ ልታጠፋኝ ነው።
ከሸክላ እንደሠራኸኝ እባክህ አስታውስ፤አሁን ግን ወደ አፈር ትመልሰኛለህ።
እንደ ወተት አላፈሰስከኝም?እንደ እርጎስ አላረጋኸኝም?
ቆዳና ሥጋ አለበስከኝ፤በአጥንትና በጅማት አያይዘህ ሠራኸኝ።
ሕይወት ሰጠኸኝ፤ ታማኝ ፍቅርም አሳየኸኝ፤መንፈሴን በእንክብካቤ ጠበቅክ።
ሆኖም እነዚህን ነገሮች በስውር ለማድረግ አሰብክ። እነዚህ ነገሮች ከአንተ እንደመጡ አውቃለሁ።
ኃጢአት ብሠራ ትመለከተኛለህ፤ከበደሌም ነፃ አታደርገኝም።
በደለኛ ከሆንኩ ወዮልኝ! ንጹሕ ብሆንም እንኳ ራሴን ቀና ማድረግ አልችልም፤ውርደትና ጉስቁልና በዝቶብኛልና።
ራሴን ቀና ባደርግ እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፤ዳግመኛም በእኔ ላይ ኃይልህን ታሳያለህ።
አዳዲስ ምሥክሮችን በእኔ ላይ ታቆማለህ፤ቁጣህንም በእኔ ላይ ታበዛለህ፤በመከራ ላይ መከራ ተደራርቦብኛል።
ታዲያ ከማህፀን ለምን አወጣኸኝ? ምነው የሰው ዓይን ሳያየኝ በሞትኩ ኖሮ!
እንዳልተፈጠርኩ በሆንኩ ነበር!በቀጥታ ከማህፀን ወደ መቃብር በተወሰድኩ ነበር!’
የሕይወት ዘመኔ ጥቂት አይደለም? እስቲ ተወት ያድርገኝ፤ትንሽ ፋታ እንዳገኝ ዓይኑን ከእኔ ላይ ያንሳ፤
ወደማልመለስበት ስፍራ፣ወደ ድቅድቅ ጨለማ ምድር በቅርቡ እሄዳለሁ፤
በጨለማ ወደተዋጠ፣ ፅልማሞት ወዳጠላበትናዝብርቅ ወደሰፈነበት፣ብርሃኑ እንኳ እንደ ጨለማ ወደሆነበት ምድር እሄዳለሁ።”
ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦
“ከዚህ በፊት እንዲህ ያሉ ብዙ ነገሮች ሰምቻለሁ። ሁላችሁም የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ!
ከንቱ ቃላት ማብቂያ የላቸውም? እንዲህ ብለህ እንድትመልስ ያነሳሳህ ምንድን ነው?
እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር። እናንተ በእኔ ቦታ ብትሆኑ ኖሮ፣አሳማኝ በሆነ መንገድ ልናገራችሁ እችል ነበር፤በእናንተም ላይ ራሴን መነቅነቅ እችል ነበር።
እንዲህ ከማድረግ ይልቅ በአፌ ቃል አበረታችሁ ነበር፤የከንፈሮቼም ማጽናኛ ባሳረፋችሁ ነበር።
ብናገር ከሥቃዬ አልገላገልም፤ዝም ብልስ ሥቃዬ ምን ያህል ይቀንስልኛል?
አሁን ግን አምላክ እንድዝል አድርጎኛል፤መላ ቤተሰቤን አጥፍቷል።
ደግሞም ያዝከኝ፤ ይህም ምሥክር ሆኖብኛል፤በመሆኑም ክሳቴ ተነስቶ በፊቴ ይመሠክራል።
ቁጣው ቦጫጨቀኝ፤ በጥላቻ ተመለከተኝ። ጥርሱን አፋጨብኝ። ባላጋራዬ በዓይኑ ወጋኝ።
እነሱ አፋቸውን በሰፊው ከፈቱብኝ፤በንቀትም ጉንጬን አጮሉኝ፤ብዙ ሆነው በእኔ ላይ ተሰበሰቡ።
አምላክ ለልጆች አሳልፎ ሰጠኝ፤በክፉዎችም እጅ ላይ ገፍትሮ ጣለኝ።
ያለምንም ችግር እኖር ነበር፤ እሱ ግን ሰባበረኝ፤ማጅራቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ከዚያም ዒላማው አደረገኝ።
ቀስተኞቹ ከበቡኝ፤ኩላሊቴን ወጋ፤ ምንም ርኅራኄ አላሳየኝም፤ሐሞቴን መሬት ላይ አፈሰሰ።
እንደ ግንብ ሰንጥቆ ሰነጣጥቆ አፈራረሰኝ፤እንደ ተዋጊ ተንደርድሮ መጣብኝ።
ቆዳዬን ለመሸፈን ማቅ ሰፍቻለሁ፤ክብሬንም አፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ።
ከለቅሶ የተነሳ ፊቴ ቀልቷል፤ድቅድቅ ጨለማም በዓይኖቼ ቆብ ላይ አጥልቷል፤
ይሁንና እጆቼ ምንም ዓመፅ አልሠሩም፤ጸሎቴም ንጹሕ ነው።
ምድር ሆይ፣ ደሜን አትሸፍኚ! ጩኸቴም ማረፊያ ስፍራ አያግኝ!
አሁንም እንኳ ምሥክሬ በሰማያት አለ፤ስለ እኔ መመሥከር የሚችል በከፍታ ቦታዎች ላይ ይገኛል።
ጓደኞቼ በእኔ ላይ ያፌዛሉ፤ዓይኔም ወደ አምላክ ያነባል።
በሰውና በባልንጀራው መካከል የሚዳኝ እንደሚኖር፣በሰውና በአምላክ መካከልም የሚዳኝ ይኑር።
የሚቀሩት ዓመታት ጥቂት ናቸውና፤እኔም በማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ።
“እስቲ ተጣራ! የሚመልስልህ ይኖራል? ከቅዱሳንስ መካከል ወደ የትኛው ዞር ትላለህ?
ሞኝን ሰው ብስጭት ይገድለዋልና፤ማስተዋል የጎደለውንም ቅናት ይገድለዋል።
ሞኝ ሰው ሥር ሰዶ አየሁት፤ይሁንና የመኖሪያ ስፍራው በድንገት ተረገመ።
ወንዶች ልጆቹ ደህንነት ርቋቸዋል፤በከተማው በር ተረግጠዋል፤ የሚያድናቸውም የለም።
እሱ የሰበሰበውን፣ የራበው ሰው ይበላዋል፤ከእሾህም መካከል ይወስድበታል፤ደግሞም ንብረታቸው በወጥመድ ተይዟል።
ጎጂ የሆነ ነገር ከአፈር አይበቅልምና፤ችግርም ከመሬት አይፈልቅም።
የእሳት ፍንጣሪ ወደ ላይ እንደሚወረወር፣ሰው የሚወለደው ለችግር ነው።
እኔ ብሆን ኖሮ አምላክን እለምን ነበር፤ጉዳዬንም ለአምላክ አቀርብ ነበር፤
እሱ ታላላቅና የማይመረመሩ ነገሮችን ያደርጋል፤ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ድንቅ ነገሮች ይሠራል።
በምድር ላይ ዝናብ ያዘንባል፤በሜዳዎችም ላይ ውኃ ይልካል።
ችግረኞችን ከፍ ያደርጋል፤እንዲሁም ያዘነውን ሰው መዳን እንዲያገኝ ከፍ ከፍ ያደርገዋል።
የብልጣ ብልጦችን ዕቅድ ያከሽፋል፤ስለዚህ የእጃቸው ሥራ አይሰምርም።
ጥበበኞችን በራሳቸው ተንኮል ይይዛቸዋል፤ስለሆነም የጮሌዎች ዕቅድ ይከሽፋል።
ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ሌሊት የሆነ ይመስል እኩለ ቀን ላይ በዳበሳ ይሄዳሉ።
ከአፋቸው ሰይፍ ያድናል፤ድሃውንም ከብርቱው እጅ ይታደጋል፤
በመሆኑም ችግረኛው ተስፋ ይኖረዋል፤የክፋት አፍ ግን ይዘጋል።
እነሆ፣ አምላክ የሚወቅሰው ሰው ደስተኛ ነው፤ስለዚህ ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ተግሣጽ አትናቅ!
እሱ ሥቃይ ያመጣልና፤ ሆኖም ቁስሉን ይጠግናል፤እሱ ይሰብራል፤ ይሁንና በገዛ እጆቹ ይፈውሳል።
ከስድስት መቅሰፍቶች ያድንሃል፤ሰባተኛውም አይጎዳህም።
በረሃብ ወቅት ከሞት ይዋጅሃል፤በጦርነትም ጊዜ ከሰይፍ ኃይል ይታደግሃል።
ከምላስ ጅራፍ ትጠበቃለህ፤ጥፋት ሲመጣም አትፈራም።
በጥፋትና በረሃብ ላይ ትስቃለህ፤የምድርንም አራዊት አትፈራም።
በሜዳ ያሉ ድንጋዮች አይጎዱህም፤የዱር አራዊትም ከአንተ ጋር ሰላም ይኖራቸዋል።
በድንኳንህ ውስጥ አስተማማኝ ሁኔታ እንደሚሰፍን ታውቃለህ፤የግጦሽ መሬትህን ስትቃኝም አንዳች ነገር አይጎድልብህም።
ብዙ ልጆች ይኖሩሃል፤ዘሮችህም በምድር ላይ እንደሚበቅል ሣር ይበዛሉ።
በወቅቱ እንደተሰበሰበ የእህል ነዶ፣ብርቱ እንደሆንክ ወደ መቃብር ትወርዳለህ።
እነሆ፣ ይህን መርምረናል፤ እውነት መሆኑንም አረጋግጠናል። ይህን ስማ፤ ደግሞም ተቀበል።”
“ከሴት የተወለደ ሰው፣የሕይወት ዘመኑ አጭርና በመከራ የተሞላ ነው።
እንደ አበባ ይፈካል፤ ከዚያም ይጠወልጋል፤እንደ ጥላም ወዲያው ያልፋል፤ ደብዛውም ይጠፋል።
አዎ፣ ዓይንህን በዚህ ሰው ላይ አሳርፈሃል፤እሱንም ከአንተ ጋር ፍርድ ፊት ታቀርበዋለህ።
ንጹሕ ካልሆነ ሰው፣ ንጹሕ የሆነ ሰው መውለድ የሚችል ማን ነው? ማንም የለም!
የሰው የሕይወት ዘመን አጭር እንዲሆን የተወሰነ ከሆነ፣የወራቱ ቁጥር በአንተ ቁጥጥር ሥር ነው፤ከዚያ እንዳያልፍ ገደብ አበጅተህለታል።
እንደ ቅጥር ሠራተኛ ጊዜውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ፣እረፍት ያገኝ ዘንድ ዓይንህን ከእሱ ላይ መልስ።
ዛፍ እንኳ ተስፋ አለውና። ቢቆረጥ መልሶ ያቆጠቁጣል፤ቅርንጫፎቹም ማደጋቸውን ይቀጥላሉ።