text
stringlengths
4
267
በሚፈራርሱ ከተሞች፣ደግሞም ማንም በማይኖርባቸውናየድንጋይ ክምር በሚሆኑ ቤቶች ውስጥ ይኖራል።
ባለጸጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይከማችም፤ንብረቱም በምድሪቱ ላይ አይበረክትም።
ከጨለማ አያመልጥም፤ነበልባል ቅርንጫፉን ያደርቀዋል፤ከአምላክም አፍ በሚወጣ እስትንፋስ ይጠፋል።
መንገድ መሳትና ከንቱ በሆነ ነገር መታመን የለበትም፤በአጸፋው የሚያገኘው ነገር ዋጋ አይኖረውምና፤
ቀኑ ከመድረሱ በፊት ይፈጸማል፤ቅርንጫፎቹም አይለመልሙም።
ያልበሰሉ ፍሬዎቹን እንደሚጥል የወይን ተክል፣አበቦቹን እንደሚያረግፍ የወይራ ዛፍም ይሆናል።
አምላክ የለሽ የሆኑ ሰዎች ጉባኤ ይመክናልና፤የጉቦ ድንኳኖችም እሳት ይበላቸዋል።
ችግር ይፀንሳሉ፤ ክፉ ነገርም ይወልዳሉ፤ማህፀናቸውም ተንኮል ያፈራል።”
ኢዮብ ጻድቅ ነኝ የሚል ጽኑ እምነት ስለነበረው፣ እነዚህ ሦስት ሰዎች ለእሱ መልስ መስጠታቸውን አቆሙ።
ይሁን እንጂ ከራም ወገን የሆነው የቡዛዊው የባራክኤል ልጅ ኤሊሁ እጅግ ተቆጣ። ከአምላክ ይልቅ ራሱን ጻድቅ ለማድረግ ስለሞከረ በኢዮብ ላይ ቁጣው ነደደ።
በተጨማሪም ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች መልስ መስጠት ባለመቻላቸው፣ ይልቁንም አምላክን ክፉ በማድረጋቸው በእነሱም ላይ እጅግ ተቆጣ።
ኤሊሁ በዕድሜ ይበልጡት ስለነበር፣ ተናግረው እስኪጨርሱ ድረስ ለኢዮብ ምንም መልስ ሳይሰጥ ሲጠብቅ ቆየ።
ኤሊሁ ሦስቱ ሰዎች መልስ መስጠት እንደተሳናቸው ባየ ጊዜ ቁጣው ነደደ።
በመሆኑም የቡዛዊው የባራክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፦ “እኔ በዕድሜ ትንሽ ነኝ፤እናንተ ግን ትላልቆች ናችሁ። ለእናንተ ካለኝ አክብሮት የተነሳ ከመናገር ዝም አልኩ፤ደግሞም የማውቀውን ለመናገር አልደፈርኩም።
እኔም ‘ዕድሜ ይናገር፤ረጅም ዘመንም ጥበብን ያሳውቅ’ ብዬ አስቤ ነበር።
ሆኖም ለሰዎች ማስተዋል የሚሰጠው በውስጣቸው ያለው መንፈስ፣ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ እስትንፋስ ነው።
ዕድሜ በራሱ ሰውን ጥበበኛ አያደርገውም፤ትክክለኛውን ነገር የሚያስተውሉትም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ብቻ አይደሉም።
ስለዚህ ‘እኔን ስማኝ፤እኔም የማውቀውን እነግርሃለሁ’ አልኩ።
እነሆ፣ እናንተ የተናገራችሁትን በትዕግሥት ሳዳምጥ ቆይቻለሁ፤የምትናገሩትን ነገር አውጥታችሁ አውርዳችሁ፣ሐሳባችሁን በምትገልጹበት ጊዜ በትኩረት ስሰማ ነበር።
ልብ ብዬ አዳመጥኳችሁ፤ሆኖም አንዳችሁም ኢዮብ መሳሳቱን ማስረዳት፣ወይም ላቀረበው የመከራከሪያ ሐሳብ መልስ መስጠት አልቻላችሁም።
ስለሆነም ‘እኛ ጥበብ አለን፤እሱ መሳሳቱን የሚነግረው አምላክ እንጂ ሰው አይደለም’ አትበሉ።
እሱ በእኔ ላይ የተናገረው ነገር የለም፤በመሆኑም እንደ እናንተ አልመልስለትም።
እነሱ ተሸብረዋል፤ መልስ መስጠትም ተስኗቸዋል፤የሚናገሩትም ጠፍቷቸዋል።
እኔ ጠበቅኳቸው፤ እነሱ ግን ንግግራቸውን መቀጠል አልቻሉም፤ከዚህ በላይ መልስ መስጠት አቅቷቸው ዝም ብለው ቆመዋል።
ስለዚህ እኔም መልስ እሰጣለሁ፤የማውቀውንም እናገራለሁ፤
ብዙ የምናገረው ነገር አለኝና፤በውስጤ ያለው መንፈስ ገፋፍቶኛል።
ውስጤ መተንፈሻ እንዳጣ የወይን ጠጅ፣ሊፈነዳ እንደተቃረበ አዲስ አቁማዳ ሆኗል።
እፎይታ እንዳገኝ እስቲ ልናገር! አፌንም ከፍቼ መልስ እሰጣለሁ።
ለማንም ፈጽሞ አላዳላም፤ማንንም ሰው አልሸነግልም፤
ሰውን መሸንገል አላውቅበትምና፤እንደዛ ባደርግ ፈጣሪዬ ወዲያውኑ ባስወገደኝ ነበር።
ከዚያም ቴማናዊው ኤሊፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ፦
“አንድ ሰው ሊያናግርህ ቢሞክር ትዕግሥት ታጣለህ? ደግሞስ ማን ከመናገር ሊቆጠብ ይችላል?
እርግጥ ነው፣ አንተ ብዙዎችን ታርም ነበር፤የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር።
ቃልህ የተሰናከለውን ሁሉ ያነሳ ነበር፤አንተም የሚብረከረኩትን ጉልበቶች ታጸና ነበር።
አሁን ግን በአንተ ላይ ሲደርስ ዛልክ፤በአንተ ላይ ሲመጣ ተደናገጥክ።
ለአምላክ ያለህ አክብሮት መተማመኛህ አይደለም? ንጹሕ አቋምህን ጠብቀህ መመላለስህ ተስፋ አልሰጠህም?
እስቲ ለማስታወስ ሞክር፦ ንጹሕ ከሆኑ ሰዎች መካከል የጠፋ ማን አለ? ቅኖችስ መቼ ተደምስሰው ያውቃሉ?
እኔ እንዳየሁት ክፉ ነገርን የሚያርሱ፣መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ።
በአምላክ እስትንፋስ ይጠፋሉ፤በቁጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ።
አንበሳ ሊያገሳ፣ የአንበሳም ግልገል ሊያጉረመርም ይችላል፤ይሁን እንጂ የብርቱ አንበሶች ጥርስም እንኳ ይሰበራል።
አንበሳ የሚታደን ሲያጣ ይጠፋል፤የአንበሳም ግልገሎች ይበተናሉ።
ቃል በስውር መጣልኝ፤ሹክሹክታውም ወደ ጆሮዬ ደረሰ።
ይህም የሆነው ሌሊት ያየሁት ራእይ ባስጨነቀኝ ወቅት፣ሰዎችም ጭልጥ ያለ እንቅልፍ በወሰዳቸው ጊዜ ነበር፤
በጣም ተንቀጠቀጥኩ፤አጥንቶቼም ሁሉ በፍርሃት ተዋጡ።
መንፈስም በፊቴ አለፈ፤የገላዬም ፀጉር ቆመ።
እሱም ባለበት ቆመ፤ሆኖም መልኩን መለየት አልቻልኩም። አንድ ቅርጽ በዓይኔ ፊት ነበር፤ጸጥታም ሰፍኖ ነበር፤ ከዚያም አንድ ድምፅ ሰማሁ፦
‘ሟች የሆነ ሰው ከአምላክ ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላል? ሰውስ ከገዛ ሠሪው ይበልጥ ንጹሕ ሊሆን ይችላል?’
እነሆ፣ በአገልጋዮቹ ላይ እምነት የለውም፤በመላእክቱም ላይ ስህተት ያገኛል።
በጭቃ ቤቶች የሚኖሩ፣መሠረታቸው አፈር ውስጥ የሆነ፣እንደ ብል በቀላሉ የሚጨፈለቁማ ሁኔታቸው ምንኛ የከፋ ይሆን!
ከጠዋት እስከ ማታ ባለው ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይደቅቃሉ፤ለዘላለም ይጠፋሉ፤ ደግሞም ማንም ልብ አይላቸውም።
ገመዱ እንደተፈታበት ድንኳን አይደሉም? ያለጥበብ ይሞታሉ።
“የተራራ ፍየሎች የሚወልዱበትን ጊዜ ታውቃለህ? ርኤሞች ግልገሎቻቸውን ሲወልዱ ተመልክተሃል?
የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደሆነ መቁጠር ትችላለህ? የሚወልዱበትን ጊዜስ ታውቃለህ?
ግልገሎቻቸውን ተንበርክከው ይወልዳሉ፤ከምጣቸውም ይገላገላሉ።
ግልገሎቻቸው ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤ይሄዳሉ፤ ወደ እነሱም አይመለሱም።
የዱር አህያውን ነፃ የለቀቀው፣የዱር አህያውን ከእስራቱ የፈታውስ ማን ነው?
በረሃማው ሜዳ ቤቱ፣ጨዋማውም ምድር መኖሪያው እንዲሆን አደረግኩ።
በከተማ ሁካታ ያፌዛል፤የነጂውንም ጩኸት አይሰማም።
መሰማሪያ ለማግኘት በኮረብቶች ላይ ይቅበዘበዛል፤ማንኛውንም አረንጓዴ ተክል ይፈልጋል።
የዱር በሬ አንተን ለማገልገል ፈቃደኛ ነው? በጋጣህ ውስጥ ያድራል?
የዱር በሬ ትልም እንዲያወጣልህ ልትጠምደው ትችላለህ?ወይስ እየተከተለህ ሸለቆውን ያርሳል?
በብርቱ ጉልበቱ ትታመናለህ?ደግሞስ ከባዱን ሥራህን እንዲሠራልህ ታደርጋለህ?
እህልህን እንዲሰበስብልህ፣በአውድማህም ላይ እንዲያከማችልህ በእሱ ትታመናለህ?
የሰጎን ክንፍ በደስታ ይርገበገባል፤ይሁንና የራዛ ዓይነት ክንፍና ላባ አላት?
እንቁላሎቿን መሬት ላይ ትጥላለች፤በአፈርም ውስጥ ታሞቃቸዋለች።
እግር ሊሰብራቸው፣የዱር አውሬም ሊረግጣቸው እንደሚችል አታስብም።
ልጆቿ የራሷ ያልሆኑ ይመስል ትጨክንባቸዋለች፤ድካሜ ሁሉ ከንቱ ይሆናል የሚል ስጋት አያድርባትም።
አምላክ ጥበብ ነስቷታልና፤ማስተዋልንም አልሰጣትም።
ተነስታ ክንፎቿን በምታርገበግብበት ጊዜ ግን፣በፈረሱና በፈረሰኛው ላይ ትስቃለች።
ለፈረስ ጉልበት የምትሰጠው አንተ ነህ? አንገቱንስ የሚርገፈገፍ ጋማ ታለብሰዋለህ?
እንደ አንበጣ እንዲዘል ልታደርገው ትችላለህ? የፉርፉርታው ግርማ አስፈሪ ነው።
የሸለቆውን መሬት ይጎደፍራል፤ ደግሞም በኃይል ይዘላል፤ወደ ውጊያ ይገሰግሳል።
በፍርሃት ላይ ይስቃል፤ የሚያስፈራውም ነገር የለም። ሰይፍ አይቶም ወደኋላ አይልም።
ኮሮጆው በጎኑ ይንኳኳል፤ጭሬውና ጦሩ ያብረቀርቃል።
በደስታ እየተርገፈገፈ ወደ ፊት ይሸመጥጣል፤የቀንደ መለከት ድምፅ ሲሰማ ያቅበጠብጠዋል።
ቀንደ መለከቱ ሲነፋ ‘እሰይ!’ ይላል፤ ጦርነቱን ከሩቅ ያሸታል፤ደግሞም የጦር አዛዦችን ጩኸትና ቀረርቶውን ይሰማል።
ሲላ ክንፎቹን ወደ ደቡብ ዘርግቶወደ ላይ የሚወነጨፈው በአንተ ማስተዋል ነው?
ወይስ ንስር ወደ ላይ የሚመጥቀው፣ጎጆውንም ከፍ ባለ ቦታ ላይ የሚሠራው አንተ አዘኸው ነው?
በገደል ላይ ያድራል፤በገደሉ አፋፍ ላይ በሚገኝ ዓለታማ ምሽግ ውስጥ ይኖራል።
በዚያም ሆኖ የሚበላውን ነገር ይፈልጋል፤ዓይኖቹም እጅግ ሩቅ ወደሆነ ቦታ ይመለከታሉ።
ጫጩቶቹም ደም ይጠጣሉ፤በድን ባለበት ስፍራም ሁሉ ይገኛል።”
ናአማታዊው ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፦
“ስሜቴ ስለታወከ፣የሚረብሸኝ ሐሳብ መልስ እንድሰጥ ይገፋፋኛል።
እኔን የሚዘልፍ ወቀሳ ሰምቻለሁ፤ያለኝ ማስተዋል መልስ እንድሰጥ ይገፋፋኛል።
ከድሮ ጀምሮ ይህን ታውቅ ነበር ማለት ነው፤ሰው በምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እንዲህ ነበርና፤
የክፉዎች እልልታ ለአጭር ጊዜ፣አምላክ የለሽ የሆነ ሰው ደስታም ለቅጽበት ነው።
ታላቅነቱ ወደ ሰማይ ከፍ ቢል፣ራሱም እስከ ደመናት ቢደርስ፣
እንደ ራሱ እዳሪ ለዘላለም ይጠፋል፤ያዩት የነበሩ ሰዎችም ‘የት ገባ?’ ይላሉ።
እንደ ሕልም በሮ ይጠፋል፤ እነሱም አያገኙትም፤እንደ ሌሊት ራእይ ይሰደዳል።
ቀድሞ ያየው ዓይን ዳግመኛ አያየውም፤የነበረበት ስፍራም ከእንግዲህ አይመለከተውም።
የገዛ ልጆቹ የድሆችን ሞገስ ለማግኘት ይሻሉ፤የገዛ እጆቹም ሀብቱን መልሰው ይሰጣሉ።
አጥንቶቹ በወጣትነት ጉልበት የተሞሉ ነበሩ፤ሆኖም ጉልበቱ ከእሱ ጋር አፈር ውስጥ ይተኛል።
መጥፎ የሆነ ነገር በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፣ከምላሱም በታች ቢደብቀው፣
እንዳያልቅበት ሳስቶ ቢያላምጠው፣በአፉም ውስጥ ቢያቆየው፣
ምግቡ በውስጡ ይጎመዝዛል፤በውስጡም እንደ ጉበና መርዝ ይሆናል።
የዋጠውን ሀብት መልሶ ይተፋዋል፤አምላክ ከሆዱ ውስጥ ያወጣዋል።
የጉበናዎችን መርዝ ይጠባል፤የእፉኝት ጥርስ ይገድለዋል።
የውኃ ፈሳሾችን፣የማርና የቅቤ ጅረቶችን ፈጽሞ አያይም።
ንብረቱን ሳይጠቀምበት ይመልሳል፤ነግዶ ባገኘው ሀብት አይደሰትም።
ድሆችን አድቅቋልና፤ ደግሞም ትቷቸዋል፤ያልገነባውን ቤት ቀምቷል።