text stringlengths 4 267 |
|---|
ሆኖም በውስጡ ሰላም አይኖረውም፤ያካበተው ሀብት አያድነውም። |
ሊበላው የሚችል የተረፈ ነገር አይኖርም፤ከዚህም የተነሳ ብልጽግናው ዘላቂ አይሆንም። |
ሀብቱ ሲትረፈረፍ በጭንቀት ይዋጣል፤የመከራ ዓይነት ይፈራረቅበታል። |
ሆዱ በሞላ ጊዜ፣አምላክ የሚነድ ቁጣውን በእሱ ላይ በመላክ፣ወደ አንጀቱ እስኪገባ ያዘንብበታል። |
ከብረት የጦር መሣሪያ ሲሸሽ፣ከመዳብ የተሠራ ቀስት ይወጋዋል። |
ቀስት ከጀርባው፣የሚያብረቀርቅ መሣሪያ ከሐሞቱ መዝዞ ያወጣል፤በሽብርም ይዋጣል። |
ውድ ሀብቱ ለድቅድቅ ጨለማ ይዳረጋል፤ማንም ያላርገበገበው እሳት እሱን ይበላዋል፤በድንኳኑ ውስጥ የቀረ ማንኛውም ሰው ጥፋት ይደርስበታል። |
ሰማይ በደሉን ይገልጥበታል፤ምድር በእሱ ላይ ትነሳለች። |
ጎርፍ ቤቱን ጠርጎ ይወስደዋል፤በአምላክ የቁጣ ቀን የውኃ መጥለቅለቅ ይከሰታል። |
ክፉ ሰው ከአምላክ የሚቀበለው ድርሻ፣አምላክም የወሰነለት ርስት ይህ ነው።” |
ከዚያም ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ |
“በእርግጥ አዋቂዎች እናንተ ናችኋ!ጥበብም ከእናንተ ጋር ትሞታለቻ! |
እኔም እኮ ማስተዋል አለኝ። ከእናንተ አላንስም። እነዚህን ነገሮች የማያውቅ ማን ነው? |
ወደ አምላክ ተጣርቼ መልስ የምጠብቅ፣የባልንጀሮቼ መሳለቂያ ሆኛለሁ። ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት ሰው፣ የሰዎች መሳለቂያ ነው። |
የደላው ሰው ‘መከራ የሚደርሰውእግራቸው በሚብረከረክ ሰዎች ላይ ብቻ ነው’ ብሎ በማሰብ መከራን ይንቃል። |
የዘራፊዎች ድንኳን ሰላም አለው፤አምላክን የሚያስቆጡ ሰዎችም፣አምላካቸውን በእጃቸው እንደያዙ ሰዎች የደህንነት ስሜት ይሰማቸዋል። |
ይሁን እንጂ እስቲ እንስሳትን ጠይቅ፤ እነሱም ያስተምሩሃል፤በሰማያት የሚበርሩ ወፎችንም ጠይቅ፤ እነሱም ይነግሩሃል። |
ወይም በምድር ላይ ትኩረትህን አድርግ፤ እሷም ታስተምርሃለች፤የባሕር ዓሣም ያሳውቅሃል። |
የይሖዋ እጅ ይህን ማድረጉን፣ከእነዚህ ሁሉ መካከል የማያውቅ ማን ነው? |
የሕያው ነገር ሁሉ ሕይወት፣የሰውም ሁሉ መንፈስ በእሱ እጅ ነው። |
ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ ሁሉ፣ጆሮስ ቃላትን አያመዛዝንም? |
በዕድሜ በገፉት መካከል ጥበብ፣ከረጅም ዕድሜስ ጋር ማስተዋል አይገኝም? |
በእሱ ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ፤ምክርና ማስተዋልም አለው። |
እሱ ያፈረሰውን ነገር መልሶ መገንባት አይቻልም፤እሱ የዘጋውን ማንም ሰው ሊከፍት አይችልም። |
ውኃዎችን ሲከለክል ሁሉም ነገር ይደርቃል፤ሲልካቸውም ምድርን ያጥለቀልቃሉ። |
ብርታትና ጥበብ በእሱ ዘንድ ናቸው፤መንገድ የሚስተውም ሆነ የሚያስተው የእሱ ናቸው፤ |
አማካሪዎችን ባዶ እግራቸውን ያስኬዳቸዋል፤ፈራጆችንም ያሞኛቸዋል። |
ነገሥታት ያሰሩትን ይፈታል፤በወገባቸውም ዙሪያ መታጠቂያ ያስራል። |
ካህናትን ባዶ እግራቸውን ያስኬዳቸዋል፤በሥልጣን ላይ ተደላድለው የተቀመጡትንም ይገለብጣል፤ |
የታመኑ አማካሪዎችን የሚሉትን ነገር ያሳጣቸዋል፤ሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይነሳል፤ |
በታላላቅ ሰዎች ላይ የውርደት መዓት ያዘንባል፤ብርቱዎችንም ደካማ ያደርጋል፤ |
ጥልቅ የሆኑ ነገሮችን ከጨለማ ውስጥ ይገልጣል፤በድቅድቅ ጨለማ ላይ ብርሃን ይፈነጥቃል፤ |
ያጠፋቸው ዘንድ ብሔራትን ታላቅ ያደርጋል፤ወደ ግዞት ይወስዳቸውም ዘንድ ብሔራትን እንዲስፋፉ ያደርጋቸዋል። |
የሕዝቡን መሪዎች ማስተዋል ይነሳል፤መንገድ በሌለበት ጠፍ መሬትም እንዲቅበዘበዙ ያደርጋል። |
ብርሃን በሌለበት ጨለማ፣ በዳበሳ ይሄዳሉ፤እንደሰከሩ ሰዎች እንዲዳክሩ ያደርጋቸዋል። |
ሹሃዊው በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ |
“እንዲህ ያለ ንግግር መናገራችሁን የምትቀጥሉት እስከ መቼ ነው? በተወሰነ መጠን ልታስተውሉ ይገባል፤ ያን ጊዜ እኛ እንናገራለን። |
ለምን እንደ እንስሳ እንቆጠራለን?በፊታችሁስ ለምን እንደ ደነዝ እንታያለን? |
አንተ በቁጣ ራስህን ብትቦጫጭቅ፣ለአንተ ሲባል ምድር ባዶ ትቀራለች?ወይስ ዓለት ከስፍራው ተነቅሎ ይወሰዳል? |
አዎ፣ የክፉዎች ብርሃን ይጠፋል፤የእሳቱም ነበልባል አይበራም። |
በድንኳኑ ውስጥ ያለው ብርሃን በእርግጥ ይጨልማል፤በላዩ ያለው መብራትም ይጠፋል። |
ብርታት የተሞላበት እርምጃው ያጥራል፤የገዛ ዕቅዱም ይጥለዋል። |
እግሩ ወደ መረብ ይመራዋልና፤በመረቡም ገመድ ይተበተባል። |
ወጥመድ ተረከዙን ይይዘዋል፤ወስፈንጥርም ያጠምደዋል። |
በመሬት ላይ ሸምቀቆ በስውር ይቀመጥለታል፤ወጥመድም በመንገዱ ላይ ይጠብቀዋል። |
ሽብር ከሁሉም አቅጣጫ ፍርሃት ይለቅበታል፤እግር በእግርም ያሳድደዋል። |
ጉልበቱ ይከዳዋል፤አደጋምያንገዳግደዋል። |
ቆዳው ተበልቷል፤እጅግ ቀሳፊ የሆነ በሽታ እጆቹንና እግሮቹን ይበላል። |
ተማምኖ ከሚኖርበት ድንኳኑ ይወገዳል፤ወደ ሽብር ንጉሥም ይወሰዳል። |
እንግዶች በድንኳኑ ውስጥ ይኖራሉ፤በቤቱም ላይ ድኝ ይበተናል። |
ሥሮቹ ከእሱ በታች ይደርቃሉ፤ቅርንጫፎቹ ደግሞ ከእሱ በላይ ይጠወልጋሉ። |
መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፤በጎዳናም ላይ ስሙ አይታወቅም። |
ከብርሃን ወደ ጨለማ ይወሰዳል፤ፍሬያማ ከሆነችውም ምድር ይባረራል። |
በሕዝቡ መካከል ልጆችም ሆኑ ዘሮች አይኖሩትም፤በሚኖርበት ስፍራም የሚተርፍ ሰው አይኖረውም። |
የሚጠፋበት ቀን ሲደርስ በምዕራብ ያሉ ሰዎች ይደነግጣሉ፤በምሥራቅ ያሉ ሰዎችም በፍርሃት ይዋጣሉ። |
የክፉ አድራጊ ድንኳኖች፣አምላክን የማያውቁ ሰዎች ስፍራም እንዲህ ያለ ነገር ይደርስባቸዋል።” |
ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ |
“ዛሬም እንኳ ብሶት ማሰማቴን አላቆምም፤ከመቃተቴ የተነሳ ኃይሌ ተሟጠጠ። |
አምላክን የት እንደማገኘው ባወቅኩ! ወደሚኖርበት ስፍራ እሄድ ነበር። |
ጉዳዬን በፊቱ አቀርብ፣አፌንም በሙግት እሞላ ነበር፤ |
እሱ እንዴት እንደሚመልስልኝ ባወቅኩ፣የሚለኝንም ባስተዋልኩ ነበር። |
ታላቅ ኃይሉን ተጠቅሞ ከእኔ ጋር ይሟገት ይሆን? በፍጹም! ይልቁንም ያዳምጠኛል። |
ያን ጊዜ ቅን የሆነው ሰው ከአምላክ ጋር ስምምነት መፍጠር ይችላል፤ፈራጄም እኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በነፃ ይለቀኛል። |
ይሁንና ወደ ምሥራቅ ብሄድ እሱ በዚያ የለም፤ተመልሼ ብመጣም ላገኘው አልችልም። |
በስተ ግራ ሆኖ ሲሠራ ላየው አልችልም፤ከዚያም ወደ ቀኝ ይዞራል፤ በዚህ ጊዜም ቢሆን አላየውም። |
እሱ ግን የሄድኩበትን መንገድ ያውቃል። ከፈተነኝ በኋላ እንደጠራ ወርቅ እሆናለሁ። |
እግሬ የእሱን ዱካ በጥብቅ ተከትሏል፤ምንም ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ። |
ከከንፈሩ ትእዛዝ አልራቅኩም። የተናገረውን ቃል ከሚጠበቅብኝ በላይ ከፍ አድርጌ ተመልክቻለሁ። |
ቆርጦ ከተነሳ ማን ሊቃወመው ይችላል? እሱ አንድ ነገር ማድረግ ከፈለገ ከማድረግ ወደኋላ አይልም። |
በእኔ ላይ የተወሰነውን ሙሉ በሙሉ ይፈጽማልና፤እንደዚህ ያሉ ብዙ ነገሮችም በእሱ ዘንድ አሉ። |
በእሱ የተነሳ የተጨነቅኩት ለዚህ ነው፤ስለ እሱ ሳስብ ይበልጥ ፍርሃት ያድርብኛል። |
አምላክ ራሱ ፈሪ አድርጎኛል፤ሁሉን ቻይ የሆነውም አምላክ አስደንግጦኛል። |
ይሁን እንጂ ጨለማውም ሆነፊቴን የሸፈነው ድቅድቅ ጨለማ ዝም አላሰኘኝም። |
ኤሊሁ እንዲህ ሲል መልስ መስጠቱን ቀጠለ፦ |
“ትክክል እንደሆንክ በጣም እርግጠኛ ከመሆንህ የተነሳ‘እኔ ከአምላክ ይበልጥ ጻድቅ ነኝ’ ትላለህ? |
ደግሞም ‘ይህ ለአንተ ምን ለውጥ ያመጣል? ኃጢአት ብሠራ ኖሮ ከዚህ የከፋ ነገር ይደርስብኝ ነበር?’ ብለሃልና። |
ለአንተና አብረውህ ላሉት ወዳጆችህ፣መልስ እሰጣለሁ። |
ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤ከአንተ ከፍ ያሉትን ደመናት በጥሞና ተመልከት። |
ኃጢአት ብትሠራ እሱን ምን ትጎዳዋለህ? በደልህ ቢበዛ እሱን ምን ታደርገዋለህ? |
ጻድቅ ብትሆን ለእሱ ምን ትጨምርለታለህ?ከአንተ እጅ ምን ይቀበላል? |
ክፋት ብትሠራ የምትጎዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጅ ነው። |
ሰዎች ከባድ ጭቆና ሲደርስባቸው ይጮኻሉ፤ከኃያል ሰው የሥልጣን ቀንበር ለመገላገል ይጮኻሉ። |
ይሁንና ‘በሌሊት መዝሙር እንዲዘመር የሚያደርገው፣ታላቅ ፈጣሪዬ የሆነው አምላክ የት አለ?’ የሚል የለም። |
ከምድር እንስሳት ይበልጥ እኛን ያስተምረናል፤በሰማይ ከሚበርሩ ወፎችም በላይ ጥበበኞች አድርጎናል። |
በክፉዎች ኩራት የተነሳ ሰዎች ይጮኻሉ፤ሆኖም እሱ አይመልስላቸውም። |
በእርግጥ አምላክ ከንቱ ጩኸት አይሰማም፤ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ትኩረት አይሰጠውም። |
አላየሁትም ብለህ ቅሬታ እያሰማህ፣ አንተንማ እንዴት ይስማህ! ጉዳይህ በእሱ ፊት ነው፤ ስለዚህ እሱን በትዕግሥት ተጠባበቅ። |
ተቆጥቶ ተጠያቂ አላደረገህምና፤በችኮላ ያደረግከውንም አልያዘብህም። |
ኢዮብ አፉን የሚከፍተው በከንቱ ነው፤እውቀት ሳይኖረው ብዙ ይናገራል።” |
ኤሊሁም መልስ መስጠቱን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ |
“እናንተ ጥበበኞች፣ ቃሌን አዳምጡ፤እናንተ ብዙ እውቀት ያላችሁ ስሙኝ። |
ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ ሁሉ፣ጆሮም ቃላትን ያመዛዝናል። |
ትክክለኛ የሆነውን ነገር እናመዛዝን፤መልካም የሆነውን ነገር በመካከላችን እንወስን። |
ኢዮብ እንዲህ ብሏልና፦ ‘እኔ ትክክል ነኝ፤አምላክ ግን ፍትሕ ነፍጎኛል። |
ሊበየንብኝ የሚገባውን ፍርድ በተመለከተ እዋሻለሁ? በደል ባልሠራም እንኳ በላዬ ላይ ያለው ቁስል የማይሽር ነው።’ |
ፌዝን እንደ ውኃ የሚጠጣ፣እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው? |
ክፉ ድርጊት ከሚፈጽሙ ጋር ተወዳጅቷል፤ከክፉዎችም ጋር ገጥሟል። |
ኢዮብ ‘ሰው አምላክን ለማስደሰት መሞከሩምንም ፋይዳ የለውም’ ብሏልና። |
ስለዚህ እናንተ አስተዋዮች ስሙኝ፦ ‘እውነተኛው አምላክ ክፉ ነገር ያደርጋል፤ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በደል ይፈጽማል’ ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር ነው! |
ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋልና፤መንገዱም ያስከተለበትን መዘዝ እንዲቀበል ያደርገዋል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.