text
stringlengths
4
267
ሰዎች በጉጉት ያዳምጡኝ፣ምክሬንም ጸጥ ብለው ይጠባበቁ ነበር።
እኔ ከተናገርኩ በኋላ የሚጨምሩት ነገር አልነበረም፤ቃሌም በጆሯቸው ይንቆረቆር ነበር።
ዝናብ እንደሚጠባበቁ ሰዎች እኔን ተጠባበቁ፤ቃሌንም እንደ በልግ ዝናብ ጠጡ።
በፈገግታ ባየኋቸው ጊዜ ማመን አቃታቸው፤የፊቴ ብርሃን ያጽናናቸው ነበር።
እንደ መሪያቸው ሆኜ አመራር ሰጠኋቸው፤በወታደሮቹ መካከል እንዳለ ንጉሥ፣ሐዘንተኞችንም እንደሚያጽናና ሰው ሆኜ ኖርኩ።
ከዚያም ሹሃዊው በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፦
“እንዲህ የምትናገረው እስከ መቼ ነው? ከአፍህ የሚወጣው ቃል ብርቱ ነፋስ ነው!
አምላክ ፍትሕን ያዛባል?ወይስ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ጽድቅን ያጣምማል?
ልጆችህ በእሱ ላይ ኃጢአት ሠርተው ከሆነ፣ለፈጸሙት ዓመፅ እንዲቀጡ አድርጓል፤
አንተ ግን ወደ አምላክ ዞር ብትል፣ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሞገስ እንዲያሳይህ ብትማጸን፣
በእርግጥ ንጹሕና ቅን ብትሆን፣እሱ ትኩረት ይሰጥሃል፤ወደ ትክክለኛ ቦታህም ይመልስሃል።
ጅማሬህ አነስተኛ ቢሆንም፣የወደፊት ሕይወትህ ታላቅ ይሆናል።
እስቲ የቀድሞውን ትውልድ ጠይቅ፤አባቶቻቸው ለተገነዘቧቸው ነገሮችም ትኩረት ስጥ።
እኛ የተወለድነው ገና ትናንት ስለሆነ የምናውቀው ነገር የለም፤ምክንያቱም በምድር ላይ ዘመናችን እንደ ጥላ ነው።
እነሱ አያስተምሩህም?ደግሞስ የሚያውቁትን ነገር አይነግሩህም?
ደንገል ረግረጋማ ባልሆነ ስፍራ ያድጋል? ሸምበቆስ ውኃ በሌለበት ቦታ ያድጋል?
ገና ሳያብብና ሳይቆረጥ፣ከሌላው ተክል ሁሉ በፊት ይደርቃል።
አምላክን የሚረሱ ሰዎች ሁሉ መጨረሻቸው እንደዚህ ነው፤አምላክ የለሽ የሆነ ሰው ተስፋ ይጨልማልና፤
የሚመካበት ነገር ከንቱ ነው፤የሚታመንበትም ነገር ከሸረሪት ድር የማይሻል ነው።
እሱ ቤቱን ይደገፈዋል፤ ሆኖም ቤቱ ጸንቶ አይቆምም፤አጥብቆ ሊይዘው ይሞክራል፤ ሆኖም አይጸናም።
እሱ በፀሐይ ብርሃን እንደሚያድግ እርጥበት ያለው ተክል ነው፤ቅርንጫፎቹም በአትክልት ስፍራው ውስጥ ይንሰራፋሉ።
ሥሩም በድንጋይ ክምር ውስጥ ይጠላለፋል፤በድንጋዮቹ መካከል ቤት ይፈልጋል።
ሆኖም ከስፍራው በሚነቀልበት ጊዜ፣ያ ስፍራ ‘ፈጽሞ አይቼህ አላውቅም’ ብሎ ይክደዋል።
አዎ፣ በዚህ ሁኔታ ይጠፋል፤ከዚያም ሌሎች ከአፈሩ ውስጥ ይበቅላሉ።
በእርግጥም አምላክ ንጹሕ አቋማቸውን የሚጠብቁትን አይጥልም፤ክፉ ሰዎችንም አይረዳም፤
በመጨረሻም አፍህን በሳቅ፣ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላል።
የሚጠሉህ ኀፍረት ይከናነባሉ፤የክፉዎችም ድንኳን ይጠፋል።”
ይሖዋ ጌታዬን “ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስበቀኜ ተቀመጥ” አለው።
ይሖዋ የኃይልህን በትር ከጽዮን ይዘረጋል፤ “በጠላቶችህ መካከል በድል አድራጊነት ግዛ” ይላል።
ወደ ጦርነት በምትዘምትበት ቀን ሕዝብህ በገዛ ፈቃዱ ራሱን ያቀርባል።በቅድስና ተውበህ ሳለ፣ ከንጋት ማህፀን እንደወጣ ጤዛ ያለ የወጣቶች ሠራዊት ከጎንህ ይሰለፋል።
ይሖዋ “እንደ መልከጼዴቅ፣ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ!” ሲል ምሏል፤ደግሞም ሐሳቡን አይለውጥም።
ይሖዋ በቀኝህ ይሆናል፤በቁጣው ቀን ነገሥታትን ያደቃል።
በብሔራት ላይ የፍርድ እርምጃ ይወስዳል፤ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል። ሰፊ የሆነውን አገር የሚገዛውን መሪ ያደቀዋል።
እሱ በመንገድ ዳር ካለው ጅረት ይጠጣል። በመሆኑም ራሱን ቀና ያደርጋል።
ይሖዋን ላወድስ፤ሁለንተናዬ ቅዱስ ስሙን ያወድስ።
ይሖዋን ላወድስ፤ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ ፈጽሞ አልርሳ።
እሱ በደልሽን ሁሉ ይቅር ይላል፤ሕመምሽንም ሁሉ ይፈውሳል፤
ሕይወትሽን ከጉድጓድ ያወጣል፤ታማኝ ፍቅሩንና ምሕረቱን ያጎናጽፍሻል፤
የወጣትነት ዕድሜሽ እንደ ንስር እንዲታደስ፣በሕይወት ዘመንሽ ሁሉ መልካም ነገሮች ያጠግብሻል።
ይሖዋ ለተጨቆኑ ሁሉበጽድቅና በፍትሕ እርምጃ ይወስዳል።
መንገዶቹን ለሙሴ፣ያከናወናቸውንም ነገሮች ለእስራኤል ልጆች አሳወቀ።
ይሖዋ መሐሪና ሩኅሩኅ፣ለቁጣ የዘገየ እንዲሁም ታማኝ ፍቅሩ የበዛ ነው።
እሱ ሁልጊዜ ስህተት አይፈላልግም፤ለዘላለምም ቂም አይዝም።
እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፤ለበደላችን የሚገባውንም ብድራት አልከፈለንም።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣እሱ ለሚፈሩት የሚያሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና።
ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣በደላችንን ከእኛ አራቀ።
አባት ለልጆቹ ምሕረት እንደሚያሳይ፣ይሖዋም ለሚፈሩት ምሕረት አሳይቷል።
እሱ እንዴት እንደተሠራን በሚገባ ያውቃልና፤አፈር መሆናችንን ያስታውሳል።
ሟች የሆነ የሰው ልጅ የሕይወት ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤እንደ ሜዳ አበባ ያብባል።
ይሁንና ነፋስ ሲነፍስበት ደብዛው ይጠፋል፤በዚያ ስፍራ ያልነበረ ያህል ይሆናል።
ይሖዋ ግን እሱን ለሚፈሩትታማኝ ፍቅሩን ከዘላለም እስከ ዘላለም ያሳያል፤ጽድቁንም ለልጅ ልጆቻቸው ይገልጣል፤
ይህን የሚያደርገው ቃል ኪዳኑን ለሚጠብቁ፣መመሪያዎቹን ለመፈጸም ለሚተጉ ነው።
ይሖዋ ዙፋኑን በሰማያት አጽንቶ መሥርቷል፤በሁሉም ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል።
ትእዛዛቱን በማክበር ቃሉን የምትፈጽሙ፣እናንተ ብርቱዎችና ኃያላን መላእክቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ።
ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ፣ሠራዊቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ።
በግዛቱ ሁሉ ያላችሁ፣ፍጥረታቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ። ሁለንተናዬ ይሖዋን ያወድስ።
ይሖዋ ሆይ፣ ከጥልቅ ውስጥ አንተን እጣራለሁ።
ይሖዋ ሆይ፣ ድምፄን ስማ። ጆሮዎችህ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና በትኩረት ያዳምጡ።
ያህ ሆይ፣ አንተ ስህተትን የምትከታተል ቢሆን ኖሮ፣ይሖዋ ሆይ፣ ማን ሊቆም ይችል ነበር?
በአንተ ዘንድ በእርግጥ ይቅርታ አለና፤ይህም ሰዎች አንተን እንዲፈሩ ያደርጋል።
ይሖዋን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ሁለንተናዬ በእሱ ተስፋ ያደርጋል፤ቃሉን በትዕግሥት እጠብቃለሁ።
ንጋትን ከሚጠባበቁ፣አዎ፣ ንጋትን ከሚጠባበቁ ጠባቂዎች ይበልጥይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ።
እስራኤል ይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ፤ይሖዋ በፍቅሩ ታማኝ ነውና፤ሕዝቡንም ለመዋጀት ታላቅ ኃይል አለው።
እስራኤልን ከበደላቸው ሁሉ ይዋጃል።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ። ፈጽሞ ለኀፍረት አልዳረግ።
በጽድቅህ አድነኝ፤ ታደገኝም። ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም።
ምንጊዜም የምገባበትመሸሸጊያ ዓለት ሁንልኝ። አንተ ቋጥኜና ምሽጌ ስለሆንክእኔን ለማዳን ትእዛዝ ስጥ።
አምላኬ ሆይ፣ ከክፉው እጅ፣ግፈኛ ከሆነው ጨቋኝ ሰው መዳፍ ታደገኝ።
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ተስፋዬ ነህ፤ከልጅነቴ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ።
ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ፤ከእናቴ ማህፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ። ሁልጊዜ አወድስሃለሁ።
ለብዙዎች መደነቂያ ሆንኩ፤አንተ ግን ጽኑ መጠጊያዬ ነህ።
አፌ በውዳሴህ ተሞልቷል፤ቀኑን ሙሉ ስለ ግርማህ እናገራለሁ።
በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ጉልበቴ በሚያልቅበት ጊዜም አትተወኝ።
ጠላቶቼ በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይናገራሉ፤ሕይወቴን የሚሹ ሰዎችም በእኔ ላይ ሴራ ይጠነስሳሉ፤
እንዲህም ይላሉ፦ “አምላክ ትቶታል። የሚያድነው ስለሌለ አሳዳችሁ ያዙት።”
አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ። አምላኬ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
የሚቃወሙኝ ሰዎችይፈሩ፤ ይጥፉም። የእኔን ጥፋት የሚሹውርደትና ኀፍረት ይከናነቡ።
እኔ ግን አንተን መጠባበቄን እቀጥላለሁ፤በውዳሴ ላይ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ።
አፌ ስለ ጽድቅህ ያወራል፤ከብዛታቸው የተነሳ ላውቃቸው ባልችልም እንኳአንደበቴ ስለ ማዳን ሥራዎችህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል።
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣መጥቼ ስለ ብርቱ ሥራዎችህ እናገራለሁ፤ስለ አንተ ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ።
አምላክ ሆይ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ አስተምረኸኛል፤እኔም እስካሁን ድረስ ድንቅ ሥራዎችህን አስታውቃለሁ።
አምላክ ሆይ፣ ሳረጅና ስሸብትም እንኳ አትጣለኝ። ለቀጣዩ ትውልድ ስለ ብርታትህ፣ገና ለሚመጡትም ሁሉ ስለ ኃያልነትህ ልናገር።
አምላክ ሆይ፣ ጽድቅህ እጅግ ታላቅ ነው፤ታላላቅ ነገሮችን አከናውነሃል፤አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
ብዙ ጭንቅና መከራ ብታሳየኝም እንኳእንደገና እንዳንሰራራ አድርገኝ፤ጥልቅ ከሆነው ምድር አውጣኝ።
ታላቅነቴ ገናና እንዲሆን አድርግ፤ዙሪያዬንም ከበህ አጽናናኝ።
እኔም አምላኬ ሆይ፣ ከታማኝነትህ የተነሳበባለ አውታር መሣሪያ አወድስሃለሁ። የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፣በበገና የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።
ለአንተ የውዳሴ መዝሙር በምዘምርበት ጊዜ ከንፈሮቼ እልል ይላሉ፤ሕይወቴን አድነሃታልና።
ምላሴ ቀኑን ሙሉ ስለ ጽድቅህ ይናገራል፤የእኔን መጥፋት የሚሹ ሰዎች ያፍራሉና፤ ደግሞም ይዋረዳሉ።
አምላክ ሆይ፣ ለዘላለም የጣልከን ለምንድን ነው? በመስክህ በተሰማራው መንጋ ላይ ቁጣህ የነደደው ለምንድን ነው?
ከረጅም ዘመን በፊት የራስህ ያደረግከውን ሕዝብ፣ርስትህ አድርገህ የዋጀኸውን ነገድ አስታውስ። የኖርክበትን የጽዮን ተራራ አስብ።
ለዘለቄታው ወደፈራረሰው ቦታ አቅና። ጠላት በቅዱሱ ስፍራ ያለውን ነገር ሁሉ አጥፍቷል።
ጠላቶችህ በመሰብሰቢያ ቦታህ ውስጥ በድል አድራጊነት ጮኹ። በዚያም የራሳቸውን ዓርማ ምልክት አድርገው አቆሙ።
መጥረቢያቸውን ይዘው ጥቅጥቅ ያሉ ደኖችን እንደሚጨፈጭፉ ሰዎች ናቸው።
በቅርጻ ቅርጾች ያጌጡትን ግድግዳዎች በጠቅላላ በመጥረቢያና በብረት ዘንግ አፈራረሱ።
መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ። ስምህ የተጠራበትን የማደሪያ ድንኳን መሬት ላይ ጥለው አረከሱት።
እነሱም ሆኑ ዘሮቻቸው በልባቸው “በምድሪቱ ላይ ያሉት የአምላክ መሰብሰቢያ ቦታዎች በሙሉ ይቃጠሉ” ብለዋል።
የምናያቸው ምልክቶች የሉም፤አንድም የቀረ ነቢይ የለም፤ደግሞም ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል ከእኛ መካከል የሚያውቅ የለም።
አምላክ ሆይ፣ ባላጋራ የሚሳለቀው እስከ መቼ ነው? ጠላት ስምህን ለዘላለም እያቃለለ ይኖራል?
እጅህን ይኸውም ቀኝ እጅህን የሰበሰብከው ለምንድን ነው? እጅህን ከጉያህ አውጥተህ አጥፋቸው።
ይሁንና በምድር ላይ ታላቅ የማዳን ሥራ የሚፈጽመው አምላክከጥንት ጀምሮ ንጉሤ ነው።