text stringlengths 4 267 |
|---|
በብርታትህ ባሕሩን አናወጥክ፤በውኃ ውስጥ ያሉትን ግዙፍ የባሕር ፍጥረታት ራስ ሰባበርክ። |
የሌዋታንን ራሶች አደቀቅክ፤በበረሃ ለሚኖሩት ሰዎች ምግብ አድርገህ ሰጠሃቸው። |
ለምንጮችና ለጅረቶች መውጫ ያበጀኸው አንተ ነህ፤ሳያቋርጡ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅክ። |
ቀኑ የአንተ ነው፤ ሌሊቱም የአንተ ነው። ብርሃንንና ፀሐይን ሠራህ። |
የምድርን ወሰኖች ሁሉ ደነገግክ፤በጋና ክረምት እንዲፈራረቁ አደረግክ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ጠላት እንደተሳለቀ፣ሞኝ ሕዝብ ስምህን እንዴት እንዳቃለለ አስብ። |
የዋኖስህን ሕይወት ለዱር አራዊት አትስጥ። የተጎሳቆለውን ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለም አትርሳ። |
ቃል ኪዳንህን አስብ፤በምድሪቱ ላይ ያሉት ጨለማ ቦታዎች የዓመፅ መናኸሪያ ሆነዋልና። |
የተደቆሰው ሰው አዝኖ አይመለስ፤ችግረኛውና ድሃው ስምህን ያወድስ። |
አምላክ ሆይ፣ ተነስ፤ ደግሞም ለራስህ ተሟገት። ሞኝ ሰው ቀኑን ሙሉ እንዴት እንደሚሳለቅብህ አስብ። |
ጠላቶችህ የሚሉትን አትርሳ። አንተን የሚዳፈሩ ሰዎች የሚያሰሙት ሁካታ ያለማቋረጥ ወደ ላይ እየወጣ ነው። |
አምላክ ለእስራኤል፣ ልባቸው ንጹሕ ለሆነ ሁሉ በእርግጥ ጥሩ ነው። |
እኔ ግን እግሮቼ ከመንገድ ሊወጡ ተቃርበው ነበር፤አዳልጦኝ ልወድቅ ምንም አልቀረኝም። |
ክፉ ሰዎች ያላቸውን ሰላም በተመለከትኩ ጊዜ፣እብሪተኛ በሆኑ ሰዎች ቀንቼ ነበርና። |
ሳይሠቃዩ ይሞታሉና፤ሰውነታቸው ጤናማ ነው። |
እንደ ሌሎች ሰዎች ችግር አያጋጥማቸውም፤እንደ ሌሎች ሰዎችም መከራ አይደርስባቸውም። |
ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ጌጣቸው ነው፤ዓመፅም እንደ ልብስ ይሸፍናቸዋል። |
ከብልጽግናቸው የተነሳ ዓይናቸው ፈጧል፤ልባቸው ካሰበው በላይ አግኝተዋል። |
በሌሎች ላይ ያፌዛሉ፤ ክፉ ነገርም ይናገራሉ፤ ሌሎችን ለመጨቆን በእብሪት ይዝታሉ። |
የሰማይን ያህል ከፍ ያሉ ይመስል በእብሪት ይናገራሉ፤በአንደበታቸው እንዳሻቸው እየተናገሩ በምድር ላይ ይንጎራደዳሉ። |
በመሆኑም ሕዝቡ ወደ እነሱ ይሄዳል፤ከእነሱ የተትረፈረፈ ውኃም ይጠጣል። |
እነሱም “አምላክ እንዴት ያውቃል? ልዑሉ አምላክ በእርግጥ እውቀት አለው?” ይላሉ። |
አዎ፣ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ሁልጊዜ ሳይጨናነቁ ይኖራሉ። የሀብታቸውንም መጠን ያሳድጋሉ። |
በእርግጥም ልቤን ያነጻሁት፣ንጹሕ መሆኔንም ለማሳየት እጄን የታጠብኩት በከንቱ ነው። |
ቀኑን ሙሉም ተጨነቅኩ፤በየማለዳውም ተቀጣሁ። |
እነዚህን ነገሮች ተናግሬ ቢሆን ኖሮ፣ሕዝብህን መክዳት ይሆንብኝ ነበር። |
ይህን ለመረዳት በሞከርኩ ጊዜ፣የሚያስጨንቅ ሆነብኝ፤ |
ይኸውም ወደ ታላቁ የአምላክ መቅደስ እስክገባናየወደፊት ዕጣቸውን እስክረዳ ድረስ ነበር። |
በእርግጥም በሚያዳልጥ መሬት ላይ ታስቀምጣቸዋለህ። ለጥፋት እንዲዳረጉም ትጥላቸዋለህ። |
እንዴት በቅጽበት ጠፉ! በአስደንጋጭ ሁኔታ ተደመሰሱ! የደረሰባቸው ጥፋት ቅጽበታዊ ነው! |
ይሖዋ ሆይ፣ ሰው ከእንቅልፉ ሲነሳ እንደሚረሳው ሕልም፣አንተም በምትነሳበት ጊዜ ምስላቸውን ታስወግዳለህ። |
ሆኖም ልቤ ተመሯል፤ውስጤንም ውጋት ቀስፎ ይዞታል። |
እኔም ማመዛዘን የማልችልና ማስተዋል የጎደለኝ ሆኜ ነበር፤በአንተ ፊት ማሰብ እንደማይችል እንስሳ ሆንኩ። |
አሁን ግን ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነኝ፤አንተም ቀኝ እጄን ይዘሃል። |
በምክርህ ትመራኛለህ፤በኋላም ክብር ታጎናጽፈኛለህ። |
በሰማይ ማን አለኝ? በምድርም ላይ ከአንተ ሌላ የምሻው የለም። |
ሰውነቴም ሆነ ልቤ ሊዝል ይችላል፤አምላክ ግን ለዘላለም የልቤ ዓለትና ድርሻዬ ነው። |
ከአንተ የሚርቁ በእርግጥ ይጠፋሉ። አንተን በመተው ብልሹ ምግባር የሚፈጽሙትን ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ። |
እኔ ግን ወደ አምላክ መቅረብ ይበጀኛል። ሥራዎቹን ሁሉ እንዳውጅሉዓላዊውን ጌታ ይሖዋን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ። |
አምላክ ሆይ፣ ፍረድልኝ፤ከከዳተኛ ብሔር ጋር ያለብኝን ሙግት አንተ ተሟገትልኝ። አታላይና ዓመፀኛ ከሆነ ሰው ታደገኝ። |
አንተ አምላኬና ምሽጌ ነህና። ለምን ተውከኝ? ጠላቴ ከሚያደርስብኝ ጭቆና የተነሳ ለምን አዝኜ ልመላለስ? |
ብርሃንህንና እውነትህን ላክ። እነሱ ይምሩኝ፤ወደተቀደሰው ተራራህና ወደ ታላቁ የማደሪያ ድንኳንህ ይውሰዱኝ። |
ከዚያም ወደ አምላክ መሠዊያ፣እጅግ ሐሴት ወደማደርግበት አምላክ እመጣለሁ። ደግሞም አምላክ ሆይ፣ አምላኬ፣ በበገና አወድስሃለሁ። |
ተስፋ የምቆርጠው ለምንድን ነው? ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው? አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤እሱን እንደ ታላቅ አዳኜና አምላኬ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና። |
ርኤም ጅረቶችን እንደምትናፍቅ፣አምላክ ሆይ፣ አንተን እናፍቃለሁ። |
አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማሁ። ወደ አምላክ የምሄደውና በፊቱ የምቀርበው መቼ ይሆን? |
እንባዬ ቀን ከሌት ምግብ ሆነኝ፤ሰዎች ቀኑን ሙሉ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ይሳለቁብኛል። |
እነዚህን ነገሮች አስታውሳለሁ፤ ነፍሴንም አፈሳለሁ፤በአንድ ወቅት ከብዙ ሰዎች ጋር እጓዝ ነበር፤በእልልታና በምስጋና ድምፅ፣በዓል በሚያከብር ሕዝብ ድምፅ፣ከፊታቸው ሆኜ ወደ አምላክ ቤት በኩራት እሄድ ነበር። |
ተስፋ የምቆርጠው ለምንድን ነው? ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው? አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤እሱን እንደ ታላቅ አዳኜ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና። |
አምላኬ ሆይ፣ ተስፋ ቆርጫለሁ። ከዮርዳኖስ ምድርና ከሄርሞን አናት፣ከሚዛር ተራራየማስብህ ለዚህ ነው። |
በፏፏቴህ ድምፅ አማካኝነትጥልቁ ውኃ፣ ጥልቁን ውኃ ይጣራል። ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ ዋጠኝ። |
ይሖዋ በቀን ታማኝ ፍቅሩን ያሳየኛል፤እኔ ደግሞ በሌሊት ስለ እሱ እዘምራለሁ፤ ሕይወት ለሰጠኝ አምላክ ጸሎት አቀርባለሁ። |
ዓለቴ የሆነውን አምላክ እንዲህ እለዋለሁ፦ “ለምን ረሳኸኝ? ጠላት ከሚያደርስብኝ ግፍ የተነሳ በሐዘን ተውጬ ለምን እሄዳለሁ?” |
ለእኔ ካላቸው ጥላቻ የተነሳ ሊገድሉኝ የሚሹ ጠላቶቼ ይሳለቁብኛል፤ቀኑን ሙሉ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ይሳለቁብኛል። |
ተስፋ የምቆርጠው ለምንድን ነው? ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው? አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤እሱን እንደ ታላቅ አዳኜና አምላኬ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና። |
ለተቸገረ ሰው የሚያስብ ደስተኛ ነው፤በመከራ ቀን ይሖዋ ይታደገዋል። |
ይሖዋ ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል። በምድር ላይ ደስተኛ ይባላል፤ለጠላቶቹ ምኞት አሳልፈህ አትሰጠውም። |
ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ይሖዋ ይደግፈዋል፤በታመመበት ወቅት መኝታውን ሙሉ በሙሉ ትቀይርለታለህ። |
እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ። በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና ፈውሰኝ” አልኩ። |
ጠላቶቼ ግን “የሚሞተውና ስሙ ከናካቴው የሚረሳው መቼ ነው?” እያሉ ስለ እኔ ክፉ ወሬ ያወራሉ። |
ከእነሱ አንዱ እኔን ለማየት ቢመጣ ልቡ ውሸት ይናገራል። እኔን የሚጎዳ ወሬ ይቃርማል፤ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ በየቦታው ያወራዋል። |
የሚጠሉኝ ሁሉ እርስ በርስ ይንሾካሾካሉ፤በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይሸርባሉ፤ |
“ክፉ ነገር ደርሶበታል፤ከእንግዲህ ከወደቀበት አይነሳም” ይላሉ። |
ሌላው ቀርቶ ከእኔ ጋር ሰላም የነበረው፣ እምነት የጣልኩበትናከማዕዴ ይበላ የነበረ ሰው ተረከዙን በእኔ ላይ አነሳ። |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ብድራታቸውን እከፍል ዘንድሞገስ አሳየኝ፤ ደግሞም አንሳኝ። |
ጠላቴ በእኔ ላይ በድል አድራጊነት እልል ሳይል ሲቀር፣ አንተ በእኔ ደስ እንደተሰኘህ በዚህ አውቃለሁ። |
እኔ በበኩሌ ንጹሕ አቋሜን በመጠበቄ ትደግፈኛለህ፤በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ። |
የእስራኤል አምላክ ይሖዋከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ። አሜን፣ አሜን። |
ይሖዋ ሆይ፣ ፍትሕ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ፤እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት በጥሞና አዳምጥ፤ያለምንም ማታለል ያቀረብኩትን ጸሎት ስማ። |
ለእኔ ስትል ፍትሐዊ ውሳኔ አድርግ፤ዓይኖችህ ትክክለኛ የሆነውን ነገር ይዩ። |
ልቤን መረመርክ፤ በሌሊት በሚገባ አጤንከኝ፤ደግሞም አጠራኸኝ፤አንዳች መጥፎ ነገር እንዳላሰብኩ ታውቃለህ፤አንደበቴም አልበደለም። |
የሰዎችን ሥራ በተመለከተ ደግሞ፣የከንፈርህን ቃል በማክበር ከዘራፊዎች መንገድ ርቄአለሁ። |
እግሮቼ እንዳይደነቃቀፉ፣አረማመዴ በመንገድህ ላይ ይጽና። |
አምላክ ሆይ፣ መልስ ስለምትሰጠኝ አንተን እጣራለሁ። ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል። ቃሌን ስማ። |
በቀኝ እጅህ እንድትጠብቃቸው የሚሹትን፣በአንተ ላይ ከሚያምፁ ሰዎች የምታድን ሆይ፣ታማኝ ፍቅርህን ድንቅ በሆነ መንገድ አሳይ። |
እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ። |
ጥቃት ከሚሰነዝሩብኝ ክፉዎች፣ከሚከቡኝና ሊገድሉኝ ከሚፈልጉ ጠላቶቼ ጠብቀኝ። |
ደንታ ቢሶች ሆነዋል፤በአፋቸው በእብሪት ይናገራሉ፤ |
መፈናፈኛ አሳጡን፤እኛን መጣል የሚችሉበትን አጋጣሚ ነቅተው ይጠባበቃሉ። |
እያንዳንዳቸው ያደነውን ለመዘነጣጠል እንደሚጓጓ አንበሳ፣በስውር እንደሚያደባ ደቦል አንበሳ ናቸው። |
ይሖዋ ሆይ፣ ተነስተህ ፊት ለፊት ግጠመው፤ ደግሞም ጣለው፤በሰይፍህ ከክፉው ሰው ታደገኝ፤ |
ይሖዋ ሆይ፣ ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ ታደገኝ፤እነዚህ ሰዎች ድርሻቸው አሁን ያለው ሕይወት ነው፤አንተ በሰጠሃቸው መልካም ነገሮች አጥግበሃቸዋል፤ደግሞም ለብዙ ወንዶች ልጆቻቸው ርስት ያስተላልፋሉ። |
እኔ ግን ፊትህን በጽድቅ አያለሁ፤በምነቃበት ጊዜ አንተን በማየት እደሰታለሁ። |
በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ። በሌሎች አማልክት ፊትየውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ። |
ከታማኝ ፍቅርህና ከታማኝነትህ የተነሳወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ስምህንም አወድሳለሁ። ቃልህና ስምህ ከሁሉም ነገር በላይ ጎልቶ እንዲታይ አድርገሃልና። |
በተጣራሁ ቀን መለስክልኝ፤ደፋርና ብርቱ አደረግከኝ። |
ይሖዋ ሆይ፣ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያወድሱሃል፤የተናገርካቸውን የተስፋ ቃሎች ይሰማሉና። |
ስለ ይሖዋ መንገዶች ይዘምራሉ፤የይሖዋ ክብር ታላቅ ነውና። |
ይሖዋ ከፍ ያለ ቢሆንም ትሑት የሆነውን ሰው ይመለከታል፤ትዕቢተኛውን ግን ወደ እሱ እንዲቀርብ አይፈቅድም። |
አደገኛ በሆነ አካባቢ ባልፍም እንኳ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃለህ። በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤ቀኝ እጅህ ያድነኛል። |
ይሖዋ ለእኔ ሲል ሁሉንም ነገር ይፈጽማል። ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤የእጅህን ሥራ ቸል አትበል። |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ። ፈጽሞ አልፈር። ከጽድቅህ የተነሳ ታደገኝ። |
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል። ፈጥነህ ታደገኝ። እኔን ለማዳን በተራራ ላይ ያለ ምሽግ፣የተመሸገ ስፍራም ሁንልኝ። |
አንተ ቋጥኜና ምሽጌ ነህና፤ለስምህ ስትል ትመራኛለህ፤ የምሄድበትንም መንገድ ታሳየኛለህ። |
አንተ መሸሸጊያዬ ስለሆንክ፣እነሱ በስውር ከዘረጉብኝ ወጥመድ ታስጥለኛለህ። |
መንፈሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። የእውነት አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣ ዋጅተኸኛል። |
የማይረቡና ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችን የሚያመልኩ ሰዎችን እጠላለሁ፤እኔ ግን በይሖዋ እታመናለሁ። |
በታማኝ ፍቅርህ እጅግ ሐሴት አደርጋለሁ፤ጉስቁልናዬን አይተሃልና፤በጭንቀት መዋጤን ታውቃለህ። |
ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ይልቁንም ደህንነት በማገኝበት ስፍራ አቆምከኝ። |
ይሖዋ ሆይ፣ በጭንቀት ስለተዋጥኩ ሞገስ አሳየኝ። መከራ ዓይኔንም ሆነ መላ ሰውነቴን አድክሞታል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.