text
stringlengths
4
267
ሕይወቴ በሐዘን፣ዕድሜዬም በመቃተት አልቋል። ከፈጸምኩት ኃጢአት የተነሳ ጉልበቴ ተሟጠጠ፤አጥንቶቼ ደከሙ።
ባላጋራዎቼ ሁሉ፣በተለይ ደግሞ ጎረቤቶቼ ተሳለቁብኝ። የሚያውቁኝ ሰዎችም እጅግ ፈሩኝ፤በአደባባይ ሲያዩኝ ከእኔ ይሸሻሉ።
የሞትኩ ያህል ከልባቸው ወጣሁ፤ ደግሞም ተረሳሁ፤እንደተሰበረ ማሰሮ ነኝ።
ብዙ መጥፎ ወሬ ሰምቻለሁ፤ሽብር ከቦኛል። ግንባር ፈጥረው በእኔ ላይ በተነሱ ጊዜሕይወቴን ለማጥፋት ያሴራሉ።
ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ። “አንተ አምላኬ ነህ” እላለሁ።
የሕይወት ዘመኔ በእጅህ ነው። ከጠላቶቼና ከሚያሳድዱኝ እጅ ታደገኝ።
ፊትህ በአገልጋይህ ላይ እንዲበራ አድርግ። በታማኝ ፍቅርህ አድነኝ።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በጠራሁ ጊዜ አልፈር። ክፉዎች ግን ይፈሩ፤በመቃብር ውስጥ ዝም ይበሉ።
በትዕቢትና በንቀት በጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩሐሰተኛ ከንፈሮች ዱዳ ይሁኑ።
ጥሩነትህ ምንኛ ብዙ ነው! አንተን ለሚፈሩ ጠብቀህ አቆይተኸዋል፤እንዲሁም አንተን መጠጊያ ለሚያደርጉ ስትል በሰዎች ሁሉ ፊት አሳይተኸዋል።
አንተ ባለህበት ሚስጥራዊ ቦታ፣ከሰዎች ሴራ ትሸሽጋቸዋለህ፤በመጠለያህ ውስጥከክፉ ጥቃት ትሰውራቸዋለህ።
በተከበበ ከተማ ውስጥ ታማኝ ፍቅሩን በአስደናቂ ሁኔታ ስላሳየኝይሖዋ የተመሰገነ ይሁን።
እኔ በድንጋጤ ተውጬ “ከፊትህ መጥፋቴ ነው” አልኩ። አንተ ግን እርዳታ ለማግኘት በጮኽኩ ጊዜ ልመናዬን ሰማህ።
እናንተ ለእሱ ታማኝ የሆናችሁ ሁሉ፣ ይሖዋን ውደዱ! ይሖዋ ታማኞችን ይጠብቃል፤ትዕቢተኛ የሆነን ሰው ግን ክፉኛ ይቀጣል።
እናንተ ይሖዋን የምትጠባበቁ ሁሉ፣ደፋር ሁኑ፤ ልባችሁም ይጽና።
መልካም የሆነ ነገር ልቤን አነሳስቶታል። “መዝሙሬ ስለ አንድ ንጉሥ ነው” እላለሁ። አንደበቴ የተዋጣለት ገልባጭ እንደሚጠቀምበት ብዕር ይሁን።
አንተ ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ። ከከንፈሮችህ ጸጋ የተላበሱ ቃላት ይፈስሳሉ። አምላክ ለዘላለም የባረከህ ለዚህ ነው።
ኃያል ሆይ፣ ሰይፍህን በጎንህ ታጠቅ፤ክብርህንና ግርማህንም ተጎናጸፍ።
በግርማህም ድል ለመቀዳጀት ገስግስ፤ፈረስህን እየጋለብክ ለእውነት፣ ለትሕትናና ለጽድቅ ተዋጋ፤ቀኝ እጅህም የሚያስፈሩ ተግባሮችን ያከናውናል።
ፍላጻዎችህ የሾሉ ናቸው፤ ሰዎችን በፊትህ ይረፈርፋሉ፤የንጉሡን ጠላቶች ልብ ይወጋሉ።
አምላክ ለዘላለም ዙፋንህ ነው፤የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትረ መንግሥት ነው።
ጽድቅን ወደድክ፤ ክፋትን ጠላህ። ስለዚህ አምላክ ይኸውም አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይበልጥ በደስታ ዘይት ቀባህ።
ልብሶችህ ሁሉ የከርቤ፣ የእሬትና የብርጉድ መዓዛ አላቸው፤በዝሆን ጥርስ ካጌጠው ታላቅ ቤተ መንግሥት የሚወጣው የባለ አውታር መሣሪያዎች ድምፅ ያስደስትሃል።
ከተከበሩት እመቤቶችህ መካከል የነገሥታት ልጆች ይገኛሉ። እቴጌይቱ በኦፊር ወርቅ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።
ልጄ ሆይ፣ አዳምጪ፣ ልብ በዪ፣ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።
ንጉሡም በውበትሽ ተማርኳል፤እሱ ጌታሽ ነውና፣እጅ ንሺው።
የጢሮስ ሴት ልጅ ስጦታ ይዛ ትመጣለች፤እጅግ ባለጸጋ የሆኑትም በአንቺ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ።
የንጉሡ ሴት ልጅ እጅግ ተውባ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ተቀምጣለች፤ልብሷ በወርቅ ያጌጠ ነው።
ያጌጠ ልብሷን ለብሳ ወደ ንጉሡ ትወሰዳለች። ወዳጆቿ የሆኑ ደናግል አጃቢዎቿን ወደ ፊትህ ያቀርቧቸዋል።
በደስታና በሐሴት ይመሯቸዋል፤ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት ይገባሉ።
በአባቶችህ ፋንታ ወንዶች ልጆችህ ይተካሉ። በምድር ሁሉ ላይ መኳንንት አድርገህ ትሾማቸዋለህ።
ለሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ስምህን አሳውቃለሁ። በመሆኑም ሕዝቦች ለዘላለም ያወድሱሃል።
ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ አምላክ ሆይ፣ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ስምህ ከእኛ ጋር ነው፤ሰዎችም ድንቅ ሥራዎችህን ያውጃሉ።
አንተ እንዲህ ትላለህ፦ “ጊዜ ስወስንበትክክል እፈርዳለሁ።
ምድርና በላይዋ የሚኖሩ ሁሉ ሲቀልጡ፣ምሰሶዎቿን አጽንቼ ያቆምኩት እኔ ነኝ።” (ሴላ)
ጉራቸውን ለሚነዙት “ጉራ አትንዙ” እላለሁ፤ ክፉዎቹንም እንዲህ እላለሁ፦ “ኃይላችሁን ከፍ ከፍ አታድርጉ።
ኃይላችሁን ወደ ላይ ከፍ አታድርጉ፤ወይም በትዕቢት አትናገሩ።
ክብር ከምሥራቅም ሆነ ከምዕራብወይም ከደቡብ አይመጣምና።
አምላክ ፈራጅ ነውና። አንዱን ያዋርዳል፤ ሌላውን ደግሞ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
በይሖዋ እጅ ጽዋ አለና፤ወይኑ አረፋ ያወጣል፤ ደግሞም ሙሉ በሙሉ የተደባለቀ ነው። እሱ በእርግጥ ያፈሰዋል፤በምድርም ላይ ያሉ ክፉዎች ሁሉ ከነአተላው ይጨልጡታል።”
እኔ ግን ይህን ለዘላለም አውጃለሁ፤ለያዕቆብ አምላክ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።
እሱ እንዲህ ይላልና፦ “የክፉዎችን ኃይል በሙሉ እቆርጣለሁ፤የጻድቅ ሰው ኃይል ግን ከፍ ከፍ ይላል።”
ሰማያት የአምላክን ክብር ይናገራሉ፤ጠፈርም የእጆቹን ሥራ ያውጃል።
በየዕለቱ ንግግራቸው ይሰማል፤በእያንዳንዱም ሌሊት እውቀትን ይገልጣሉ።
ንግግር የለም፤ ቃልም የለም፤ድምፃቸው አይሰማም።
ይሁንና ጩኸታቸው ወደ መላው ምድር ወጣ፤መልእክታቸውም እስከ ዓለም ዳርቻዎች ተሰማ። እሱ በሰማያት ለፀሐይ ድንኳን ተክሏል፤
ፀሐይም ከጫጉላ ቤት እንደሚወጣ ሙሽራ ነው፤በጎዳናው ላይ እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል።
ከአንደኛው የሰማያት ዳርቻ ይወጣል፤ዞሮም ወደ ሌላኛው ዳርቻ ይሄዳል፤ከሙቀቱም የሚሰወር አንዳች ነገር የለም።
የይሖዋ ሕግ ፍጹም ነው፤ ኃይልን ያድሳል። የይሖዋ ማሳሰቢያ አስተማማኝ ነው፤ ተሞክሮ የሌለውን ጥበበኛ ያደርጋል።
የይሖዋ መመሪያዎች ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ፤የይሖዋ ትእዛዝ ንጹሕ ነው፤ ዓይንን ያበራል።
ይሖዋን መፍራት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል። የይሖዋ ፍርዶች እውነት ናቸው፤ ሙሉ በሙሉ ትክክል ናቸው።
ከወርቅ እንዲያውም ብዛት ካለው ምርጥ ወርቅየበለጠ የሚወደዱ ናቸው፤ደግሞም ከማርና ከማር እንጀራ ከሚንጠባጠብ ወለላ ይበልጥ ይጣፍጣሉ።
ለአገልጋይህ ማስጠንቀቂያ ሆነውለታል፤እነሱን መጠበቅ ትልቅ ወሮታ አለው።
የራሱን ስህተት ማን ሊያስተውል ይችላል? ሳላውቅ የሠራኋቸውን ኃጢአቶች አትቁጠርብኝ።
አገልጋይህንም ከእብሪት ድርጊቶች ጠብቀው፤እንዲቆጣጠሩኝም አትፍቀድ። ያን ጊዜ እንከን የሌለብኝ እሆናለሁ፤ዓይን ካወጣ ኃጢአትም ነፃ እሆናለሁ።
ዓለቴና አዳኜ ይሖዋ ሆይ፣ የአፌ ቃልና በልቤ የማሰላስለው ነገርአንተን ደስ የሚያሰኝ ይሁን።
እናንተ ጻድቃን ሆይ፣ ይሖዋ ባደረጋቸው ነገሮች የተነሳ እልል በሉ። ቅኖች እሱን ማወደሳቸው የተገባ ነው።
ይሖዋን በበገና አመስግኑት፤አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩለት።
አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤በባለ አውታር መሣሪያ ጥሩ አድርጋችሁ ተጫወቱ፤ እልልም በሉ።
የይሖዋ ቃል ትክክል ነውና፤ሥራውም ሁሉ እምነት የሚጣልበት ነው።
ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል። ምድር በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ተሞልታለች።
ሰማያት በይሖዋ ቃል፣በውስጣቸው ያሉትም ሁሉ ከአፉ በሚወጣው መንፈስ ተሠሩ።
የባሕርን ውኃዎች እንደ ግድብ ያከማቻል፤የሚናወጠውንም ውኃ በማከማቻ ቦታ ይሰበስባል።
መላዋ ምድር ይሖዋን ትፍራ። የምድር ነዋሪዎች እሱን ይፍሩ።
እሱ ተናግሯልና፣ ሆኗል፤እሱ አዟል፤ ደግሞም ተፈጽሟል።
ይሖዋ የብሔራትን ሴራ አክሽፏል፤የሕዝቦችን ዕቅድ አጨናግፏል።
ይሁንና የይሖዋ ውሳኔዎች ለዘላለም ይጸናሉ፤የልቡ ሐሳብ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።
ይሖዋ አምላኩ የሆነ ብሔር፣የራሱ ንብረት አድርጎ የመረጠው ሕዝብ ደስተኛ ነው።
ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ይመለከታል፤የሰው ልጆችን ሁሉ ያያል።
ከመኖሪያ ቦታው ሆኖበምድር የሚኖሩትን በትኩረት ይመለከታል።
የሁሉንም ልብ የሚሠራው እሱ ነው፤ሥራቸውን ሁሉ ይመረምራል።
በሠራዊት ብዛት የዳነ ንጉሥ የለም፤ኃያል ሰው በታላቅ ኃይሉ አይድንም።
ፈረስ ያድነኛል ብሎ መታመን ከንቱ ተስፋ ነው፤ታላቅ ኃይሉ ለመዳን ዋስትና አይሆንም።
እነሆ፣ የይሖዋ ዓይን የሚፈሩትን፣ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን የሚጠባበቁትን በትኩረት ይመለከታል፤
ይህም እነሱን ከሞት ለመታደግ፣በረሃብ ወቅትም እነሱን በሕይወት ለማኖር ነው።
ይሖዋን በተስፋ እንጠባበቃለን። እሱ ረዳታችንና ጋሻችን ነው።
ልባችን በእሱ ሐሴት ያደርጋል፤በቅዱስ ስሙ እንታመናለንና።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተን ስንጠባበቅ፣ታማኝ ፍቅርህ በእኛ ላይ ይሁን።
ኑ፣ ለይሖዋ እልል እንበል! አዳኛችን ለሆነው ዓለት በድል አድራጊነት ስሜት እልል እንበል።
ምስጋና ይዘን በፊቱ እንቅረብ፤በድል አድራጊነት ስሜት ለእሱ እንዘምር፤ ደግሞም እልል እንበል።
ይሖዋ ታላቅ አምላክ ነውና፤በሌሎች አማልክት ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።
ጥልቅ የሆኑት የምድር ክፍሎች በእጁ ናቸው፤የተራሮችም ጫፍ የእሱ ነው።
እሱ የሠራው ባሕር የራሱ ነው፤የብሱንም የሠሩት እጆቹ ናቸው።
ኑ፣ እናምልክ፤ እንስገድም፤ሠሪያችን በሆነው በይሖዋ ፊት እንንበርከክ።
እሱ አምላካችን ነውና፤እኛ ደግሞ በመስኩ የተሰማራን ሕዝቦች፣በእሱ እንክብካቤ ሥር ያለን በጎች ነን። ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ፣
አባቶቻችሁ በምድረ በዳ ሳሉ በመሪባ፣በማሳህ ቀን እንዳደረጉት ልባችሁን አታደንድኑ፤
በዚያን ጊዜ እነሱ ፈተኑኝ፤ሥራዬን ቢያዩም ተገዳደሩኝ።
ያን ትውልድ ለ40 ዓመት ተጸየፍኩት፤እኔም “ይህ ሕዝብ ሁልጊዜ ልቡ ይስታል፤መንገዴን ሊያውቅ አልቻለም” አልኩ።
በመሆኑም “ወደ እረፍቴ አይገቡም” ብዬ በቁጣዬ ማልኩ።
ለይሖዋ ምስጋና ማቅረብ ጥሩ ነው፤ልዑሉ አምላክ ሆይ፣ ለስምህም የውዳሴ መዝሙር መዘመር መልካም ነው፤
ታማኝ ፍቅርህን በማለዳ፣ታማኝነትህንም በሌሊት ማሳወቅ መልካም ነው፤
አሥር አውታር ባለው መሣሪያና በክራር፣ደስ በሚል የበገና ድምፅ ታጅቦ ማሳወቅ ጥሩ ነው።
ይሖዋ ሆይ፣ ባከናወንካቸው ነገሮች እንድደሰት አድርገኸኛልና፤ከእጅህ ሥራዎች የተነሳ እልል እላለሁ።
ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ምንኛ ታላቅ ነው! ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው!
ማመዛዘን የጎደለው ሰው ይህን ሊያውቅ አይችልም፤ሞኝ የሆነም ሰው ይህን ሊረዳ አይችልም፦
ክፉዎች እንደ አረም ቢበቅሉ፣ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ቢያብቡ እንኳ፣ለዘላለም መጥፋታቸው የማይቀር ነው።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም ከሁሉ በላይ ነህ።
ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶችህን በድል አድራጊነት ስሜት ተመልከት፤ጠላቶችህ እንዴት እንደሚጠፉ እይ፤ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ይበተናሉ።
አንተ ግን ኃይሌን እንደ ዱር በሬ ኃይል ታደርጋለህ፤እኔም ገላዬን ጥሩ ዘይት እቀባለሁ።
ዓይኔ ጠላቶቼን በድል አድራጊነት ስሜት ያያል፤ጆሮዬም የሚያጠቁኝን ክፉ ሰዎች ውድቀት ይሰማል።